Monday, January 30, 2012

ከአንባብያችን የተላከ መልዕክት - በመጋቤ ሐዲስ መምህር በጋሻው ላይ እየተካሄደ ያለውን የስም ማጥፋት ዘመቻ አስመልክቶ

ውድ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ብናስተውል መልካም ነው፡፡ አይሁድ የአለምን መድኃኒት ለመስቀል አሳልፈው የሰጡት ባለማስተዋል ነው፡፡

እኔ መጋቤ ሐዲስ መምህር በጋሻውን የማውቀው በስራዎቹ ቤተክርስቲያን አውደ ምህረት ላይ ነው፡፡ አሉ የሚባሉትን የቤተክርስቲን መምህራን ጠንቅቄ አውቃለሁ፡፡ የማውቀውን ልናገር፣ልመሰክር ሀይማኖቴ ያስገድደኛልና ይኸው እናገራለሁ፡፡
መልእክቴ ትድረስልኝ በተለይ በተለይ ማህበረቅዱሳን”/ሰይጣን አሰልጥኖ በየስርቻው የቤተክርስቲያን ሰዎችን ለመዋጋት የሰይጣን ሰይፍ አስይዞ አስታጥቆ ላሰማራችሁ፣ለላካችሁ የማህበረ ሰይጣን ሰራዊቶች በሙሉ፡፡ በአንድ ግለሰብ ላይ እንዲህ የመስቀል ጦርነት ይመስል እንድትዘምቱ ያደረጋችሁ ነገር ምንድን ነው? ዛሬ በየቤተክርስቲያኑ ያለውን ወጣት ማን የሰበሰበው መሰለህ? እናንተማ ውጣ እነጂ ግባ ብላችሁ አታውቁም፡፡ ይህ ግብራችሁ ነው፡፡

Saturday, January 28, 2012

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የአባ ሠረቀ ብርሃን “እውነትና ንጋት” መጽሐፍ ተመረቀ - - - Read PDF

የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሃላፊ የነበሩትና ማህበረ ቅዱሳንን በህገ ቤተክርስቲያን እንዲመራ ለማድረግ ከፍተኛ ተጋድሎ ያደረጉት አባ ሠረቀ ብርሃን “እውነትና ንጋት” በሚል ርእስ ያዘጋጁት መጽሐፍ በ17/5/2004 ዓ.ም. በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ ብፁኣን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የጠቅላይ ቤተክህነት የመምሪያ ሃላፊዎች የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ካህናት፣ ዲያቆናት፣ የሰንበት ተማሪዎችና በርካታ ምእመናን በተገኙበት እጅግ በደመቀ መርሀግብር ተመረቀ፡፡ ይህ በአይነቱ ለየት ያለና በበርካታ ሰነዶች የተሞላው፣ 222 ገጽ ያለው መጽሐፍ የተዘጋጀው በሶስት አበይት ምክንያቶች እንደሆነ መግቢያው ላይ ተጠቅሷል፡፡ ምክንያቶቹም፡-

Friday, January 27, 2012

በደቂቀ እስጢፋኖስ የነገረ መለኮት ኮሌጅ ደቀ መዛሙርትና በማኅበረ ቀናዕያን አመራሮች መካከል የተደረገ ክርክር (2)

ቅዳሜ ኅዳር 16 2004
ክፍል ሁለት

“ሌላው የነመምህር በቃሉ የማደናገሪያ ስልት ከአባቶች ትምህርት የሚስማማቸውን ብቻ ከፍሎ በመጥቀስና ሌላውን በመተው የእኛ ትምህርት የአባቶች ነው ለማለትና ኦርቶዶክሳዊውን ትምህርት ወደ ፕሮቴስታንታዊ ትምህርት ለማንሸራተት መሞከራቸው ነው። እኛ እያልን ያለነው አንዱን ጠቅሶ ሌላውን መተው ትክክለኛ አያሰኝምና ከአባቶች ከጠቀሳችሁ ሁሉንም መጥቀስና ስለ ኢየሱስ ብቻ ሳይሆን ስለ እመቤታችን፣ ስለ መላእክት፣ ስለ ቅዱሳን አስተምሩ፤ ትክክለኛውን አስተምህሮአችንን ወደ ፕሮቴስታንቶች አስተምህሮ አታንሸራቱ ነው። ይህ ደግሞ ወንጌል እንጂ ከወንጌል የሚቃረን አይደለም” አለና ንግግሩን አጠናቀቀ።


Thursday, January 26, 2012

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እውነትና እውነተኞች የሚገፉባት፤ ሐሰትና ሐሰተኞች የሚነግሱባት እስከ መቼ ይሆን? - - ክፍል 2 - - PDF

ዘሪሁን ሙላቱ ኦርቶዶክሳዊ ነውን?
የዛሬው ጽሑፍ ትኩረት ዘሪሁን ከዕንቁ መጽሔት ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስ ነው፡፡ ይህን ቃለ ምልልስ ዕንቁ መጽሔት በነሐሴ 2003 ዓ.ም. እትሙ ላይ ነው ያወጣው፡፡ የማህበረ ቅዱሳን ድረገጽ ደጀሰላምም ለአንባብያኑ ፖስት አድርጎት ነበር (http://www.dejeselam.org/2011/08/blog-post_41.html)፡፡

ደጀሰላም እንዲህ በማድረጉ ከዘሪሁን ኑፋቄዎች ጋር ያለውን ስምምነት አሳይቷል፤ ወይም ኑፋቄን ከእውነተኛው አስተምህሮ የሚለይበት ብቃት የለውም፤ አሊያ ኑፋቄም ቢናገር እንኳን፣ ተሀድሶ እየተባለ የሚብጠለጠለውን የነበጋሻውን ቡድን ደህና አድርጎ ከሰደበ ኑፋቄው እንደ ኑፋቄ አይቆጠርበትም፡፡

በእኔ እይታ ቃለ መጠይቅ ያደረገለት ጋዜጠኛ ዘሪሁን ሲናገራቸው የነበሩትን ኑፋቄዎች በተቻለው መጠን ለመመከት ጥረት አድርጓል ባይ ነኝ፡፡ ለምሳሌ “ድንግል ማርያም እግዚአብሔርን ወልዳለች ሲባል ሶስቱ አካላት ሥላሴ ስጋ ለበሱ አያሰኝም?” ሲል ተሟግቶታል፡፡ ዘሪሁን ጥያቄውን አልቆስቁሶ ሲመልስለትም “እንዴት?” ሲል አጥጋቢ ምላሽ አለማግኘቱን በድጋሚ አንጸባርቋል፡፡ በተደጋጋሚም ዘሪሁን የሰጠውን ግላዊ ማብራሪያ ማስረዳት የሚችል ማስረጃ ከመጽሐፍ ቅዱስ ወይም ከቤተ ክርስቲያን መጻህፍት ይገኛል ወይ? ሲልም አፋጦታል፡፡ እርሱ የሆነ ያልሆነውን ቢዘላብድም፡፡

Monday, January 23, 2012

ተጠንቀቁ ክፍል ሦስት - - - Read PDF

ፈሪሳውያን በመንፈሳዊነት እውሮች ናቸው::

ጌታ እንደዚህ አለ "ተዉአቸው፤ ዕውሮችን የሚመሩ ዕውሮች ናቸው፤ ዕውርም ዕውርን ቢመራው ሁለቱም ወደ ጉድጓድ ይወድቃሉ አለ" (ማቴ 1514) ፈሪሳውያን መጽሐፍ ቅዱስን ያወቁ ናቸው፤ በመንፈሳዊነት ግን እውሮች ናቸው። ስለዚህ በመንፈሳዊ ነገር ላይ ምንም መገለጥ አይኖራቸውም። እንደዚህ ያሉ መሪዎች ደግሞ ሌሎችን ሲመሩ አይቶ ጌታ "ተዋቸው ሁለቱም ተያይዘው ገደል ይገባሉ" አለ። (15:14)በምንም ምክንያት እውርን መከተል የለብንም። የምንከተለው ሰው መንፈሳዊ ብርሃን የበራለት ሰው መሆን አለበት። ፍቅር ማጣት ነው የመንፈሳዊነት እውርነትን የሚያመጣው። ጌታን የሚወድ ሰው እግዚአብሔርን በግልጽ ያየዋል። መከተል ያለብን እንደዚህ ያለውን መሪ ነው።

Sunday, January 22, 2012

የዳንኤል ክብረት “የወግ” መጻሕፍት የወግን መስፈርት አያሟሉም ተብለው በባለሙያ ተተቹ - - - Read PDF

ከማህበረ ቅዱሳን መሥራቾች አንዱ የሆነውና በአሁኑ ጊዜ ራሱን በራሱ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ተመራማሪ ብሎ በመሰየም በየሚዲያው ገጽታውን በመገንባት ላይ የሚገኘው ዳንኤል ክብረት፣ ማህበረ ቅዱሳን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እጁን ባስገባባቸው የግል መጽሔቶችና ጋዜጦች ላይ በየጊዜው የጫጫራቸውንና በእርሱ አጠራር “ወጎች” የሚላቸውን፣ በወግ አጻጻፍ ቴክኒክ ረገድ ግን ወግ ለመባል ብዙ የሚቀራቸውን ጽሑፎቹን በአንድ ላይ አሳትሞ በሁለት ጥራዝ ማሳተሙ የሚታወስ ሲሆን፣ እነዚህ ስብስቦቹ የወግን መስፈርት የማያሟሉ መሆናቸውን ሐያሲ ዓለማየሁ ገላጋይ በሰጠው ሂስ አመለከተ፡፡በአዲስ አድማስ ጋዜጣ የታህሳስ 7 እና 14 እትም ላይ “ወግ ሲባል ከሁለቱ ሐውልቶች … እስከ ጠጠሮቹ” በሚል ርእስ በቀረበው ሂስ ላይ፣ ሃያሲው የዳንኤልን ጽሁፎች ብርቱና ደካማ ጎን በሄሰበት ጽሑፉ ዳንኤል ወጎቹን የጻፋቸው “በሰማይ እየበረረ በምድር እየተሽከረከረ በምናብ እየተፈተለከ” መሆኑን ገልጾ፣ “አብዛኞቹ አንዴ ተነበው የሚቀሩ ሳይሆኑ፣ ለእድሜ ልኩ ጉዟችን ስንቅ ለመሆን የሚዳዳቸው” መሆናቸውን አመልክቷል፡፡ “ዳንኤል የርእሰ ጉዳይ ደሃ አይደለም፤ ባለጸጋ ነው” ያለው ሀያሲ ዓለማየሁ፣ “ለእያንዳንዱ ርእሰ ጉዳይ የተረት ወይም የገጠመኝ አዲስ መለበጫ ስለሚያዘጋጅለት ወደ ታሪኩ የምንገባው ተሟልጨን ሳናውቀው ነው፡፡ ትረካው እንደ ቄራ በሬ ግራና ቀኝ እንዳናይ፣ ቀጥ ብለን እንድንጓዝ የሚያደርግ ጠባብ ፍርግርግ ነውና ዳንኤል ያሰበበት ሳንደርስ መለስ-ቀለስ የለም፡፡” በማለት ከወጎቹ ምሳሌ በመጥቀስ ሄሷል፡፡     

Friday, January 20, 2012

እንኳን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

የጥምቀት ቀን የጌታ የመገለጥ ቀን ነው፤ አብ ስለ ልጁ የመሰከረበትና ሰማይ የተከፈተበት ቀን ነው። ይህን ቀን ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን በታላቅ ምስጋና አስባው ትውላለች።
ዛሬም ላልተገለጠላቸው ወገኖች ሁሉ ጌታ እንዲገለጥላቸውና አብ ስለ ልጁ የመሰከረውን ምሥክርነት በማመን የሚገኘውን ሕይወት እንዲቀበሉ መልካም ምኞታችን ነው።
 በዚሁ አጋጣሚ ለአባ ሰላማ ብሎግ አንደኛ ዓመትም እንኳን አደረሳችሁ እንላለን። አባ ሰላማ ብሎግ ባጭር ጊዜ ውስጥ ይህን ያህል እውቅና ታገኛለች ተብሎ አልተጠበቀም። ይሁን እንጂ በአንድ ዓመት ውስጥ ከሚጠበቀው በላይ ዓለም አቀፍ እውቅናን በማግኝት የመጀመሪያዋ ብሎግ ለመሆን በቅታለች። ወደ ፊት ብሎጓ በኢትዮጵያ እና በመላው ዓለም እየተካሄደ ላለው ወደ እውነት የሽግግር እንቅሥቃሴ ከፍተኛ እገዛ ታደርጋለች ብለን እናምናለን። በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ዓይናችን ተገልጧል እያሉ የሚሰጡት አስተያየት ለኛ እንደ ክፍያ ስለሆነን በርትተን ለመሥራት በዝግጅት ላይ ነን። ጸልዩልን!

Wednesday, January 18, 2012

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እውነትና እውነተኞች የሚገፉባት፤ ሐሰትና ሐሰተኞች የሚነግሱባት እስከ መቼ ይሆን? - - - Read PDF

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እያየንና እየታዘብን ያለው ነገር እጅግ ይገርማል፡፡ በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሀብትን ለማካበት፣ ዝናን ለማትረፍና የበላይ ለመሆን በሚደረገው ትግል አንዱ ሌላውን እየደፈጠጠ ለማለፍ በሚያደርገው ሩጫ፣ በዕውቀት ሳይሆን በአፍ ብቻ ለመንገስ በሚደረገው ግስጋሴ፣ አንዱን ዝነኛ በህብረት አውርዶ በእርሱ እግር ለመተካት ዝነኛውን ከመድረክ ማውረድና ከህዝብ ልብ ማስወጣት የሚለው አላማ የተሳካ ሲመስል፣ በአድማው ካበሩት መካከል አንዱ ተነጥሎ ስፍራውን ለመሙላት የሚያደርገው ጥድፊያ ለተመለከተው ያስገርማል፡፡ ጋኖች አልቀው ምንቸቶች ጋን በሆኑበት ዘመን ላይ መገኘታችንም በእጅጉ ያሳዝናል፡፡

Monday, January 16, 2012

ራዕይ ያለው ትውልድ መጽሐፍ አጭር ዳሰሳ
በዲ/ን ክንፈ ገብርኤል

‹‹ራዕይ ያለው ትውልድ››[1] በሚል ርዕስ በዲ/ን አሸናፊ መኮንን የተጻፈውን መጽሐፍ በራሴና በትውልዴ በርካታ ጥያቄዎችና እንቆቅልሽ ውስጥ ሆኜ ነበር ያነበብኩት፣ የዚህን መጽሐፍ እያንዳንዱን ገጽ ስገልጽም ለተወሰኑ ደቂቃዎች ከራሴ ጋር የተከራከርኩባቸው፣ ልቤን ከእጆቼ ጋር ወደ አርያም ወዳለው የአባቶቼ አምላክ ያነሳሁባቸውን የእኔን እና የትውልዴን በርካታ እንቆቅልሾችን በመጠየቅ ብቻ ሳይወሰን ሰፊና የተብራራ የእግዚአብሔርን ህያው ቃል መሰረት በማድረግ ምላሽ በመስጠት ወደራሴ እንዳይ፣ የራዕይን ሰፊና ጥልቅ የሆነ ትምህርትና ትረጓሜ ዳግም በማስተዋል፣ በእግዚአብሔር ቃል መስታወትነት እንዳይ የረዳኝ መጽሐፍ ሆኖ ስላገኘሁት በመጽሐፉ ዙሪያ ጥቂት ነገሮችን ለማለት ወደድሁ፡፡

የትውልድ እሪታለትውልዳችን ጩኽት ቤተክርስቲያን ምን ምላሽ፣ ምንስ መፍትኄ ይኖራት ይሆን...???

"አቤቱ እባክህ የሆነብንን አስብ፣ ዘመናችንን እንደ ቀድሞ አድስ..." ሰቆ ኤር. ፭፥ ፩ _ ፳፪


ለብዙ ዘመናት አንገታችንን የደፋን ህዝቦች ነን። ሺ ዘመናትን በሚያስከነዳው ዥንጉርጉር ታሪካችን ከምንኮራበት ስልጣኔያችንና ጀግንነታችን ይልቅ የምናፍርበት ጉስቁልናችን፣ ስብራታችንና ኃፍረታችን አይሎብን በእጅጉ ተሸማቀናል፡፡ በሀገራችን ትናት በሆነው ዛሬም እየሆነ ባለው፣ በምናየውና በምንሰማው ነገር ሁሉ አንገተ ሰባራ ሆነናል። መቼ ነው ይህ ታሪካችን ተለውጦ ቀና ብለን የምንሄደው ብለን በብዙ ተስፋ አድርገናል፡፡ የብዙዎች ወገኖቻችን ደምም ለለውጥ፣ ለአዲስና ብሩህ ተስፋ በሀገራችን ተራሮችና ሸንተረሮች እንደ ውኃ ፈሷል፣ ብዙዎቻችንም ነፍሳችን እስክትዝል ለሀገራችን ለውጥ በብዙ አንብተናል፣ ወጥተናል ወርደናል፡፡ የለውጥ ያለህ በሚል ከልብ በሆነ ናፍቆትም ተቃጥለናል። ዛሬም በናፍቆት እንደተቃጠልን ዛሬም በናፍቆት ነፍሳችን እንደዛለች መሽቶ ይነጋል

Thursday, January 12, 2012

አባ ሳሙኤል በወ/ሮ መሰረት ላይ የመሰረተቱት ክስ በዝግ ችሎት እየታየ መሆኑ ተነገረ - - - Read PDF

የብፁዕ አቡነ ሚካኤል ባለቤት ወ/ሮ መሠረት ታደሰ የወራሽነት መብታቸውን ለማስከበር እየተንቀሳቀሱ ባለበት ሁኔታ፣ እንቅፋት ሆነውብኛል በሚል ቅዱስ ሲኖዶስና በግልባጭ ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትም ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው በአባ ሳሙኤል ላይ ማመልከቻ ማስገባታቸውን ተከትሎ፣ አባ ሳሙኤል ጉዳዩ በሲኖዶስ እንዳይታይ ጓደኞቻቸውን በማሳደም ታፍኖ እንዲቀር ከፍተኛ ጥረት ያደረጉት አባ ሳሙኤል፣ “ስሜ ጠፍቷል” በሚል የመሰረቱት ክስ በዝግ ችሎት እየታየ መሆኑን ያገኘነው መረጃ ያስረዳል፡፡ ከዚህ ቀደም እንደዘገብነው በቀጠሮው ዕለት ያልተገኙትና በፖሊስ ተይዘው እንዲቀርቡ ትእዛዝ የወጣባቸው አባ ሳሙኤል በ10/4/2004 ዓ.ም. ከቀረቡ በኋላ በቀነ ቀጠሮው ያልተገኙት አስቸኳይ ሥራ ስለነበረባቸው መሆኑን በማስረዳትና ከተመደቡበት የልማት ኮምሽን ደብዳቤ አጽፈው በማቅረብ የክሱ ሂደት እንዲቀጥል ተደርጓል፡፡ በዚህም መሰረት አባ ሳሙኤል ክሱን ማሻሻል እፈልጋለሁ ሲሉ ወደ “ከፍተኛ የስም ማጥፋት ወንጀል” ለውጠዉታል፡፡ አክለውም ጉዳዩ መሰናዘሪያ በተባለ ጋዜጣ ላይ መዘገቡ ቅሬታ እንዳሳደረባቸው በመግለጽና ከሃይማኖት ጋር ስለሚያያዝ በዝግ ችሎት እንዲታይላቸው ጠይቀዋል፡፡

Monday, January 9, 2012

ነጋዴው ማህበረ ቅዱሳን የቲን (Tin) ቊጥር ለማውጣት እንቅስቃሴ መጀመሩ ተሰማ

በሃይማኖት ካባ ተሸፍኖ በቤተክርስቲያናችን ስም ሲነግድና ስንጥቅ ሲያተርፍ የኖረውና አሁንም በተመሳሳይ መንገድ የንግድ ተቋማቱን በማስፋፋት ላይ የሚገኘው ነጋዴው ማህበረ ቅዱሳን ለጠቅላይ ቤተ ክህነት በጻፈው ደብዳቤ ጉዳዩ ለሚመለከተው የመንግስት አካል የቲን ቁጥር ይሰጠው ዘንድ እንዲጻፍለት መጠየቁን ምንጮቻችን ገለጹ፡፡ አባ ሰረቀ ከሀላፊነት ከተነሱ በኋላና የግንቦቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ስበሰባ ከመድረሱ በፊት፣ የንግዱን አለም በይፋ ለመቀላቀል እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የሚናሩት ምንጮቻችን፣ በአባ ሰረቀ ምትክ አዲስ የተሾሙት አዲሱ የመምሪያ ሃላፊን አባ ህሩይን በጥቅማጥቅም እንደያዘ የሚናገሩ አልጠፉም፡፡ ለዚህም እንደማስረጃ የሚያነሱት አባ ህሩይ ከዚህ ቀደም ያልታየና ጳጳሳት የሚያደርጉትን አይነት ትልቅ የአንገት መስቀል አድርገው መታየታቸውን ነው፡፡ እንደእነዚህ ሰዎች ጥርጣሬ ማህበረ ቅዱሳን ለአዲሱ የመምሪያ ሃላፊ መስቀሉን በስጦታ መልክ “የገቢ” ብሏቸዋል ነው የሚባለው፡፡ በማህበሩ ሰጥቶ የመቀበል ስልትም እርሳቸው የገቢ እንደተባሉ ሁሉ፣ ማህበሩ የሚፈልገውን ነገር የማድረግ የውዴታ ግዴታ ውስጥ እንደገቡ ይታሰባል፡፡ ምናልባትም ያስገባው ማመልከቻ ተቀባይነት አግኝቶ ደብዳቤው ከተጻፈለት ያው “የወጪ” ተባለ ማለት ነው፡፡ ብዙዎችም በዚሁ ቤተ ክርስቲያናችንን ለቆ ቢወጣልን ጥሩ ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ይሰጣሉ፡፡

Wednesday, January 4, 2012

አስቸኳዩ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ውሳኔና የደጀ ሰላም ድረ ገጽ ዘገባ አራምባና ቆቦ መሆናቸው ተገለጸ - - - Read PDF

የወሬ ጠኔ ይዞት የሰነበተውና ከውሸት በቀር አንድም እውነት ተናግሮ የማያውቀው ደጀ ሰላም እንደ ለመደው ታኅሣሥ 23 ቀን 2004 . የተደረገውን አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ውሳኔዎችን እርሱ በሚፈለገው መንገድ ዘግቦ አንባብያኑን እያሳሳተና በባዶ ተስፋ እየሞላ መሆኑን ምንጮቻችን ገለጹ፡፡

የወሬ ድረ ገጹ ከዚህ ቀደም በጥቅምቱ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ሲዘግብ የነበረው ሁሉ ማኅበረ ቅዱሳን የሚመኘውን እንጂ ሲኖዶስ የወሰነውን እንዳልሆነ የሚናገሩት ምንጮቻችን፣ በምሳሌነት የሚያነሱት በአባ ሠረቀ እና በማኅበረ ቅዱሳን መካከል ባለው ጉዳይ ላይ ሲኖዶስ የወሰነው ውሳኔና ደጀ ሰላምና ግብረ አበሮቹ ብሎጎች የዘገቡት ፈጽሞ የማይገናኝ መሆኑን ነው፡፡ ሲኖዶሱ የወሰነው በአባ ሠረቀ እና በማኅበረ ቅዱሳን መካከል ያለውን ችግር በተመለከተ አጣሪ ኮሚቴው ያቀረበውን አስተያየት የሊቃውንት ጉባኤ መርምሮ ለግንቦቱ የሲኖዶስ ስበሰባ እንዲያቀርብ ነው እንጂ አባ ሠረቀ የሃይማኖት ችግር አለባቸው የሚል ነጥብ ፈጽሞ አላሰፈረም፡፡ እርሳቸውን የሃይማኖት ችግር አለባቸው ሲል የከሰሰው ማኅበረ ቅዱሳን ለዚያውም በአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አመራር ተብዬዎች ስም መሆኑን በስማቸው የቀረበው የክስ ዶሴ ያስረዳል፡፡ እርግጥ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ ብቻ ሳይሆኑ የማኅበረ ቅዱሳን ግብረበላ የሆኑት አባ ፊልጶስ አባ ሠረቀን የሃይማኖት ችግር አለባቸው ሲሉ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሆነው እንዳይመደቡ ማኅበሩ የሰጣቸውን ተልእኮ መወጣታቸው አይዘነጋም፡፡

Tuesday, January 3, 2012

የለውጥ ያለህ! ንስሐ ለኢትዮጵያውያን - - - Read PDF

ኢትዮጵያ ሀገራችን በአሁኑ ጊዜ ዓለምን እያስጨነቀች ያለች አገር ናት። ዓለም በየጊዜው ስለችግር የሚያወጣው ሪፖርት ኢትዮጵያን በተራ ቁጥር አንድ በመጥቀስ ነው። ስለ ጦርነት፣ ስለ ድርቅ፣ ሰለ ረሃብ፣ ስለ ወባ፣ ስለ ኤች አይ ኤድስ፣ ስለ ሳንባ ነቀርሳ፣ ስለ አየር መዛባት፣ ስለ ሙስና፣ ስለ ኑሮ ውድነት ሰለስደት ወዘተ ኢትዮጵያ ግንባር ቀደም ናት።
  ዓለም የሚያውቀውን የላይ የላዩን ሪፖርት ያቀርባል እኛ ባለቤቶቹ ግን ውስጣችንን ዓለም ከሚያወቀው በላይ እናውቀዋለን። ጥንቆላዎችና አስማቶች፣ መንፈሳዊ ድንዛዜዎች፣ የሐሰት ሥራዎች፣ እግዚአብሔር የሚጠላቸው ነውሮችና ርኩሰቶች ሁሉ በሕዝባችን ኑሮና ሕወይት ላይ ወድቀው እንደሚገኙ የማንክደው ሐቅ ነው። እኛ እውነቱን ክደን ራሳችንን ትምክህተኞች አድርገን ብንመጻደቅም እንኳ የእግዚአብሔር ቃል ነውሮኞች መሆናችንን አይደብቅልንም። በመጸሐፍ ቅዱስ ላይ የምናነባቸው እርግማኖች ሁሉ ኢትዮጵያ ላይ ተደራርበው እናያቸዋለን። ሃይማኖተኞች መስለን ለመታየት ግን የሚወዳደረን የለም እንዲያውም ከኛ ውጭ ሃይማኖት ያለው ሕዝብ ያለ እስከማይመስለን ድረስ ግብዞች ሆነናል።
  እንደዚህ በግብዝነት አማኞች መስለን እንታይ እንጂ በችግር የተከበብን ንስሐ የሚያስፈልገን ኃጢአተኞች መሆናችንን እውነት የሆነው የጌታ ቃል ያረጋግጥልናል። በኛ ላይ እየሆነ ያለው እያንዳዱ ችግር በምን ምክንያት እንደመጣ ለማወቅ የሚከተለውን የእግዚአብሔር ቃል እንከታተል።