Thursday, January 26, 2012

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እውነትና እውነተኞች የሚገፉባት፤ ሐሰትና ሐሰተኞች የሚነግሱባት እስከ መቼ ይሆን? - - ክፍል 2 - - PDF

ዘሪሁን ሙላቱ ኦርቶዶክሳዊ ነውን?
የዛሬው ጽሑፍ ትኩረት ዘሪሁን ከዕንቁ መጽሔት ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስ ነው፡፡ ይህን ቃለ ምልልስ ዕንቁ መጽሔት በነሐሴ 2003 ዓ.ም. እትሙ ላይ ነው ያወጣው፡፡ የማህበረ ቅዱሳን ድረገጽ ደጀሰላምም ለአንባብያኑ ፖስት አድርጎት ነበር (http://www.dejeselam.org/2011/08/blog-post_41.html)፡፡

ደጀሰላም እንዲህ በማድረጉ ከዘሪሁን ኑፋቄዎች ጋር ያለውን ስምምነት አሳይቷል፤ ወይም ኑፋቄን ከእውነተኛው አስተምህሮ የሚለይበት ብቃት የለውም፤ አሊያ ኑፋቄም ቢናገር እንኳን፣ ተሀድሶ እየተባለ የሚብጠለጠለውን የነበጋሻውን ቡድን ደህና አድርጎ ከሰደበ ኑፋቄው እንደ ኑፋቄ አይቆጠርበትም፡፡

በእኔ እይታ ቃለ መጠይቅ ያደረገለት ጋዜጠኛ ዘሪሁን ሲናገራቸው የነበሩትን ኑፋቄዎች በተቻለው መጠን ለመመከት ጥረት አድርጓል ባይ ነኝ፡፡ ለምሳሌ “ድንግል ማርያም እግዚአብሔርን ወልዳለች ሲባል ሶስቱ አካላት ሥላሴ ስጋ ለበሱ አያሰኝም?” ሲል ተሟግቶታል፡፡ ዘሪሁን ጥያቄውን አልቆስቁሶ ሲመልስለትም “እንዴት?” ሲል አጥጋቢ ምላሽ አለማግኘቱን በድጋሚ አንጸባርቋል፡፡ በተደጋጋሚም ዘሪሁን የሰጠውን ግላዊ ማብራሪያ ማስረዳት የሚችል ማስረጃ ከመጽሐፍ ቅዱስ ወይም ከቤተ ክርስቲያን መጻህፍት ይገኛል ወይ? ሲልም አፋጦታል፡፡ እርሱ የሆነ ያልሆነውን ቢዘላብድም፡፡

ደጀ ሰላም ግን ገና ለገና ተሀድሶን አውግዞልኛል፤ እነበጋሻውን አዋርዶልኛል፤ አቡነ ጳውሎስን ጎንጦልኛል ብሎ ስላመነ ብቻ፣ “ማርያም ስላሴን ወልዳለች፣ ሀዋርያት በኢየሱስ ስም ነው ያጠመቁት፣” ወዘተ እያለ ኑፋቄዎቹን ሲዘራ ከምንም አልቆጠረውም፡፡ ይህም የሚያሳየው የማህበረ ቅዱሳን ልሳን ደጀ ሰላም የቆመው ለሃይማኖት ሳይሆን ለግል ጥቅሙ መሆኑን ነው፡፡ እስኪ ዘሪሁን ያለ ከልካይ እንደ ዘበት የተናገራቸውን ኑፋቄዎች ልጥቀስ፤

ኑፋቄ አንድ
“ማርያም ሥላሴን ወልዳለች”

በቃለ ምልልሱ ውስጥ ሊቀ ትጉሃን ዘሪሁን ይህን ከዚህ ቀደም ታስቦም ተሰምቶም የማያውቅ ኑፋቄ መዝራት የጀመረው፣ በማዳን ሥራ ውስጥ አብ ወልድና መንፈስ ቅዱስ አሉ በማለት ተንደርድሮ ነው፡፡ ይህ ትክክል ነው፡፡ ነገር ግን “ይህ ማለት ሥላሴ ዓለምን ሲያድኑ ድንግል ማርያም ለሥላሴ ማደሪያ” ናት ማለት ነው ሲል ፍጹም ኑፋቄ ተናግሯል፡፡ የሰዎች መዳን በአብ የታቀደ፣ በወልድ የተከናወነ እና በመንፈስ ቅዱስ ገላጭነት ለሰዎች የሚገለጥና ሰዎች አምነው የሚድኑበት ምስጢር ነው ማለት ነው፡፡ ጴጥሮስም በመልእክቱ በአብ አስቀድሞ እንደታወቅን፣ በወልድ ደም እንደ ተረጨን፣ በመንፈስ ቅዱስ እንደ ተቀደስን የሚናገረው ክፍል የሚያስረዳው ይህንኑ እውነት ነው፤ (1ጴጥ. 1፡1-2)፡፡

በምክረ ሥላሴ የተከናወነው የአድኅኖት ሥራ ሥላሴ በድንግል ማሕፀን በማደር ያከናወኑት ግን አይደለም፡፡ ቃል ሥጋ ሲሆን መንፈስ ቅዱስ በድንግል ማርያም ላይ መጥቷል፤ የልዑል ኃይልም ጸልሏታል፤ (ሉቃ. 1፡35)፡፡ ይህም ከእርስዋ የሚወለደው ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ይባል ዘንድ ነው፤ ስለዚህ በእርሷ ማሕፀን ያደረው ወልድ ብቻ ነው፡፡ ይህን ትምህርት ሊቃውንት ተጠንቅቀው ሲገልጹ ወልድ በድንግል ማሕጸን ያደረው በተለየ አካሉ ነው ይላሉ፡፡ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስም በአካል በግብር ሦስት ናቸው፤ ወልድ ሥጋ የለበሰውም ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ልዩ በሆነው አካሉ ነው እንጂ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ በሆነበት ባሕርዩ ወይም በመለኮቱ አይደለም፡፡

ዮሐንስ ዘእስክንድርያ፡- “በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ህልውና እንዳለ የምናውቀው መለኮት ሁለንተናው ሰው እንደሆነ፤ ሰው የሆነው ከሶስቱ አካላት አንዱ አካል እንዳይደለ በመናገራቸው ሶስቱ አካላት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሰው እንደሆኑ የሚያስቡትን … እናወግዛለን፡፡” (ሃይማኖተ አበው ገጽ 392)

ሌላውም አባት “ይቤ ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር ኢይቤ ወልድየ ዘከመ ትስብእት አላ ዘከመ መለኮት፡፡ አኮ ወልደ ማርያም በመለኮት፤ አላ ዘከመ ሥርዐተ ትስብእት፡፡”
ትርጓሜ፡- “ይህ የምወደው ልጄ ነው አለ፤ ልጄ ያለው የትስብእት በሆነው ስርአት ሳይሆን የመለኮት በሆነው ስርአት ነው፡፡ እርሱ የማርያም ልጅ የተሰኘው የትስብእት በሆነው ስርአት ነው እንጂ በመለኮት የማርያም ልጅ አይደለም፡፡” (ሃይማኖተ አበው)

ዮሐንስ አፈወርቅም የዕብራውያንን መልእክት በተረጎመበት ድርሳን ባሕርየ መለኮቱ ሥጋ አልሆነም ወይም መለኮት ሥጋ አለበሰም ብሏል (ድርሳን 1 ቁጥር 185)፡፡ ብንያሚ ዘእስክንድርያም “ቃል ዘኮነ ሥጋ በአካሉ ባሕቲቱ” ማለትም ቃል ሥጋ የሆነው በአካሉ ብቻ ነው (በመለኮቱ አይደለም) (ሃይማኖተ አበው ገጽ 382) ብሏል፡፡ እነዚህ የአበው ምስክርነቶች የሚያሳዩት ወልድ በተለየ አካሉ ሰው መሆኑንና መለኮት ስጋ አለመልበሱን ነው፡፡ መለኮት ነው ስጋ የለበሰው ከተባለ ግን ሥላሴ ሥጋ ለብሰዋል ወደሚል የስህተት ትምህርት ውስጥ እንገባለን፡፡ መለኮት ግን አይከፈልም፤ ሶስቱ አካላተ ሥላሴ፣ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ የተወሐዱበትና በመገናዘብ አንድ አምላክ የሆኑበት ነውና፡፡ “ይሤለሱ በአካላት ወይትወሐዱ በመለኮት” (በአካል ሶስት በመለኮት አንድ ናቸው) እንዲል፡፡

ሥላሴ በድንግል ማሕጸን አድረዋል የሚል ቃልም ሆነ ትምህርት በመጽሐፍ ቅዱስም ሆነ መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት ባደረገው የአበው ትምህርት ውስጥም ፈጽሞ አልተሰማም፡፡ ዘሪሁን ግን ማርያምን ወላዲተ ስላሴ ይላታል፡፡ ስላሴ በማርያም ላይ ማደራቸውን “አበው ሊቃውንት ይህንን ብሥራት አስተርእዮ ማርያም ይሉታል በድንግል ማርያም ላይ የተገለጸ የሥላሴ ሦስትነት ለማለት፡፡ የመለኮት ማደሪያም እንላታለን፡፡” ሲል በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ከዚህ ቀደም ተሰምቶ የማያውቅ ትምህርት አምጥቷል፡፡ አስተርእዮ/አስተርእዮት የሚለው ቃል ጥቅም ላይ የዋለው በጌታችን ጥምቀት የሥላሴ ምስጢር መገለጡን ለማሳየት ነው፡፡ በአንዳንዶች ዘንድ ግን አስተርእዮ የሚለው ቃል ከማርያም ጋር ተያይዞ የተነሳው ከጊዜ በኋላ ከካቶሊካውያን ወደ ቤተ ክርስቲያናችን ሠርጎ የገባውን ማርያም ተነስታለች አርጋለች የሚለውን ትምህርት ለመግለጽ
 ነው፡፡ “አስተርእዮ በሰማይ ኮነ” እንዳለ ደራሲ፡፡

ወደሌላው ነጥብ ስናልፍ የዕንቁ ጋዜጠኛ፡- “የመለኮት ማደሪያ ማለት እንዴት ይቻላል?” ሲል ላቀረበው ጥያቄ ዘሪሁን ሲመልስ
“መለኮት አንድ ነው እግዚአብሔርነት አይከፈልም፡፡ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ድንግል ማርያም የአብ፣ የወልድ፣ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ናት ማለት ነው፡፡ በዚህን ጊዜ ታዲያ አብ መረጣት፣ ወልድ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሳ መንፈስ ቅዱስ አጸናት ማለት መሆኑን ልብ ማለት ይገባል፡፡” ብሏል፡፡

እዚህም ላይ ቃል ሥጋ የሆነው በተለየ አካሉ ነው የሚለውን የሊቃውንት ማብራሪያ መሰረት ያላደረገና ሥላሴ ስጋ ለብሰዋል የሚያሰኝ ገለጻ ነው ያደረገው፡፡ ይህም ጥያቄ ሊያስነሳብኝ ይችላል በሚል ማርያም የሥላሴ ማደሪያ ናት ማለትም “አብ መረጣት፣ ወልድ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሳ መንፈስ ቅዱስ አጸናት ማለት” ነው ሲል በመጀመሪያ የተናገረውን ኑፋቄ በማይገናኝ ማብራሪያ ሊሸፍነውና በስልት ሊያፈገፍግ ሞክሯል፡፡ ማርያም የመለኮት (የሥላሴ) ማደሪያ ናት የሚለው ንባብ እንዴት ሆኖ ነው አብ መረጣት፣ ወልድ ሥጋዋን ለበሰ፣ መንፈስ ቅዱስ አጸናት የሚል ትርጉም ሊያሰጥ የሚችለው? ይህን አስተዋይ አንባቢ ይፍረደው፡፡

ጋዜጠኛው ሥላሴ በማርያም አድረዋል ለሚለው ትምህርት መረጃ ከየትኞቹ መጻሕፍት ማግኘት ይቻላል? ሲል ላቀረበለት ሌላ ጥያቄ ዘሪሁን ሲመልስ እንዲህ ብሏል፤ “ሊቁ አባ ሕርያቆስ ሐይመቱ ለአብርሃም ይላታል፤ የአብርሃም ድንኳን ማለት ነው፡፡ በዘፍጥረት ምዕራፍ 18 እንደተገለጸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ በአብርሃም ድንኳን የገቡት ሦስቱ ሥላሴ ናቸው የሚል ነው፡፡ ሥላሴ በአብርሃም ድንኳን እንደተስተናገዱት ሁሉ በድንግል ማርያምም ማህፀን ተስተናግደዋል ማለት ነው፡፡ የአብርሃም ድንኳን የምንላት በዚህ መልኩ ነው፡፡” በዚህ ገለጻ ውስጥም ዘሪሁን በዙሪያ ጥምጥም ማስረጃው ለማጠናከር የፈለገው ማርያም ሥላሴን ጸንሳለች ወልዳለች የሚለውን ኑፋቄውን ነው፡፡

በቅድሚያ የአብሃም ድንኳን እና ድንግል ማርያምን የሚያገናኛቸው አንድም ነገር የለም፡፡ አብርሃም በእንግድነት የተቀበለው እግዚአብሔርንና ሁለት መላእክትን ነው፡፡ ይህን ለመረዳት “ሰዎቹም ከዚያ ፊታቸውን አቀኑ፥ ወደ ሰዶምም ሄዱ አብርሃም ግን በእግዚአብሔር ፊት ገና ቆሞ ነበር።” (ዘፍጥረት 18፡22) የሚለውን መመልከት ያስፈልጋል፡፡ እግዚአብሔርና ሁለቱ ሰዎች ሲደመሩ ሶስት ይሆናሉ፡፡ በምዕራፍ 18 ላይ ሁለት ሰዎች ያላቸውን በቀጣዩ ምዕራፍ “ሁለቱም መላእክት በመሸ ጊዜ ወደ ሰዶም ገቡ” (19:1) ይላል፡፡ በዕብራውያን መልእክት ውስጥም “የወንድማማች መዋደድ ይኑር። እንግዶችን መቀበል አትርሱ፤ በዚህ አንዳንዶች ሳያውቁ መላእክትን እንግድነት ተቀብለዋልና።” (ዕብ. 13፡1-2) የሚለው የሚመራን ወደ አብርሃም ታሪክ ነው፡፡ ከዚህ ሁሉ የምንረዳው አብርሃም እግዚአብሔርንና ሁለት መላእክትን በእንግድነት መቀበሉን ነው፡፡ በዚህ ክፍል እግዚአብሔር በሦስትነት አልተገለጸም ማለት በዚህ ምዕራፍ ስለ ሥላሴ አልተጻፈም ማለት ነው እንጂ ትምህርተ ሥላሴን መካድ አይደለም፡፡ ከተጻፈው አትለፍ እንደተባለውም (1ቆሮ. 4፡6) ከተጻፈው ላለማለፍ ነው፡፡ ቃሉ የማይለውን አባ ሕርያቆስ ብሎ ቢገኝ እንኳ ያ የእርሱ ሀሳብ እንጂ የእግዚአብሔር ሀሳብ አለመሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ደግሞም የእርሱ ምስክርነት ከመጽሐፍ ቅዱስ ምስክርነት ጋር ካልተስማማ ተቀባይነት የለውም፡፡ ስለዚህ ዘሪሁን መጽሐፍ ቅዱስ የማይለውን አባ ሕርያቆስ ድንግል ማርያም የአብርሃም ድንኳን ናት አለ በሚል በዙሪያ ጥምጥም ምሰክር የራስህን ማብራሪያ አክለህ ሥላሴ በማርያም ማሕጸን አደሩ ብትል ትልቅ ኑፋቄ ነው፡፡ ማርያምንም ወላዲተ ሥላሴ ያሰኝብሃል፡፡

ይቀጥላል

19 comments:

 1. libona yistachihu,

  ReplyDelete
 2. እንዲህ አይነት የመናፍቃን አስተሳሰብና አባባል አታስነብቡን እነርሱ እንደሆነ አንዴ ማንነታቸውን አውቀነዋል

  ReplyDelete
 3. ዮሐንስ አፈወርቅም የዕብራውያንን መልእክት በተረጎመበት ድርሳን ባሕርየ መለኮቱ ሥጋ አልሆነም ወይም መለኮት ሥጋ አለበሰም ብሏል (ድርሳን 1 ቁጥር 185)፡፡ ብንያሚ ዘእስክንድርያም “ቃል ዘኮነ ሥጋ በአካሉ ባሕቲቱ” ማለትም ቃል ሥጋ የሆነው በአካሉ ብቻ ነው (በመለኮቱ አይደለም) (ሃይማኖተ አበው ገጽ 382) ብሏል፡፡ እነዚህ የአበው ምስክርነቶች የሚያሳዩት ወልድ በተለየ አካሉ ሰው መሆኑንና መለኮት ስጋ አለመልበሱን ነው፡፡
  Do you know that these fathers are saying that the behavior of God have not converted to be flesh?
  What does it mean by "TEWAHIDO" with out "MELEKOT" and "SIGA"?
  If you are saying that MELEKOT has not become Man by TEWAHIDO are you saying that we are not saved till now? because with out MELEKOT no one can save ADAM and his generation. If so go to hell your self. As I am an ORTHDOX TEWAHIDO CHRISTIAN I believe that our Lord Jesus Christ is One God from the two behaviors that are MELEKOT and SIGA which become one behavior from the two and one body from the two bodies by tewahido So Jesus Christ Our Savior is the true God.
  The above article you wrote shows that when you are trying to oppose Memhir Zerihun in one side,You are trying to teach us your heresy. Even though you tried to make our fore fathers as witnesses you have not got and understand what they are saying OR you are converting their teachings to your sides of protestantism. If your teachings say that "NO MELEKOT in Jesus Christ" as your post says, understand that you are saying that you are not saved till now and God has not become Flesh till now.

  ReplyDelete
 4. ማኅበረ ቅዱሳንን ሳትጠቅሱ መጻፍ የማትችሁ ጉዶች ናችሁ። ማኅበሩ ደጀሰላም የኔት አላለም። ደጀሰላምም የማኅበሩ ነኝ አልላላችም።እናንተ ጽሑፋችሁ የፕሮቴስታንት ይመስላል እና የፕሮቴስታንት ብሎግ እንበላችሁ? ደጀሰላም ራሱን ችሎ ጠንካራ እና ደካማ ዜናዎችን ለዓመታት እያስነበበችን ናት። ለምን ደጀሰላምን ተጠያቂ አድርጋችሁ መጻፍ አቃታችሁ? ለምን ዘላችሁ ማኅበሩ ጋር ትሄዳላችሁ? እናንተ ደጀሰላም ማቅን ይደግፋል እንደምትሉት የነበጋሻውን ቡድን እና ሆዳሞቹን አባቶች ላለመደገፋችሁ እርግጠኛ ናችሁ?

  ወደተነሳው ነጥብ ስመለስ፡ በጋሻውና ዘሪሁን ሁለቱም አንድ ናቸው። ከዝንጀሮ ቆንጆ ምን ይመረጥለታል ነው።

  ReplyDelete
 5. i think in this explanation there are contradictions that require clarification.

  ReplyDelete
 6. If any thing happen to abune fanuel Ergetekale and mesfin will be take 100% responsibilty. They had paid money for adis demite radio to attack aba fanuel with out any fact by hiring agent. You can read by dejselam whats wrong for that if he support government bc current gov beter than before fewodal and miletary killer.

  ReplyDelete
 7. For centuries these people, their fathers and their for-fathers kept arguing about God - theology. Unlike the apostles and those who truly follow them they never bother to read and understand the Gospel of Jesus Christ and his salivation message.
  In staid of spreading the Good News of the Gospel to all people they were and still are a stumbling block.
  They never reialize that if one wants to be a good preacher one has to be a good student of the Word, The Gospel.
  1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ ምዕራፍ 6

  3 ማንም ልዩ ትምህርት የሚያስተምር ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ በሆነው ጤናማ ቃልና እግዚአብሔርን ለመምሰል በሚስማማ ትምህርት የማይጠጋ ቢሆን፥

  4-5 በትዕቢት ተነፍቶአል አንዳችም አያውቅም፥ ነገር ግን ምርመራን በቃልም መዋጋትን እንደ በሽተኛ ይናፍቃል፤ ከእነዚህም ቅንዓትና ክርክር ስድብም ክፉ አሳብም እርስ በርስ መናደድም ይወጣሉ፥ አእምሮአቸውም በጠፋባቸው እውነትንም በተቀሙ፥ እግዚአብሔርን መምሰል ማትረፊያ የሚሆን በመሰላቸው ሰዎች ይገኛሉ። እንደነዚህ ካሉት ራቅ።

  ReplyDelete
 8. 1) “በምክረ ሥላሴ የተከናወነው የአድኅኖት…” what do u mean?

  2) የሰዎች መዳን በአብ የታቀደ፣ በወልድ የተከናወነ እና በመንፈስ ቅዱስ ገላጭነት ለሰዎች የሚገለጥና ሰዎች አምነው የሚድኑበት ምስጢር ነው ማለት ነው፡ what do u mean?

  3) The difference between ቃል of divine & አካል of divine becomes difficult for me

  ReplyDelete
 9. Whenever I am opening this blog, I am ready read 'sidib'. Abaselamas, anyone who doesn't support you is MK, right? Can you do something yourself instead of criticizing those people who are already doing something.

  Egziabhere Libona Yistachihu.

  ReplyDelete
 10. ሠይፈ ገብርኤልJanuary 27, 2012 at 7:41 PM

  ይኸኛው ወጋችሁ ደስ ብሎኝ ነበር ፡፡ ጨዋታውን በሥርዓቱ አለማወቄ ግን እጅግ በደለኝ ፡፡ ቋንቋየ የክፋት አይደለም ፣ የዚህ ወገን ነኝ የምለውም የለኝም ፣ ነገር ግን ነገረ መለኮት ረቂቅ ምስጢር ስለሆነ ፣ የእምነታችንም መሠረት በመሆኑና የምለው በማጣቴ እጅግ አፈርኩ ፣ በራሴ አዘንኩ ፡፡
  - በተለምዶ እመቤታችን ድንግል ማርያምን ወላዲተ አምላክ እንላታለን እንጂ ወላዲተ ሥላሴ አንልም ፡፡ ይህንንም ለማለት የምንደፍረው በባህርዩ ከእርሷ መወለድ የሚችለው ወልድ ፣ አምላክ ስለሆነ ብቻ ነው ፡፡ አምላክነት ደግሞ ያለ መለኮት የሚሆን አይመስለኝም ፤ ለሶስቱም ያለቸው መለኮት ደግሞ አንድ ብቻ ነው ፡፡ ከገለጻችሁ እንደተረዳሁት መለኮት የሌለበት ልዩ አካል ሥጋን ተዋሃደው ስለሚል ፣ አምላክ ሰው አልሆነም ያሰኛልና ጥንቃቄ ማድረግ የሚያስፈልግ መሰለኝ ፡፡
  - ተወህዶ ሲባልም እንደሚገባኝ የትስብዕትና የመለኮት አንድ መሆን ፣ መዋሃድ ማለት ነው ፡፡ ጽሁፋችሁ “ወልድ ሥጋ የለበሰውም ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ልዩ በሆነው አካሉ ነው እንጂ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ በሆነበት ባሕርዩ ወይም በመለኮቱ አይደለም” ይላል ፡፡ ይህኛውን አባባል መለኮት የሌለበት አካል ሥጋን ተዋሃደ ካልን መለኮት እንደ ኮት የሚወልቅና የሚጠለቅ ማለት ያህል ይመስላልና ትክክል ከሆነ ከንስጥሮስ አመለካከት በምን ተለየ ፡፡ ብዙ እንዳልጽፍ ፣ ጠልቄ በማላውቀው እንዳልሳሳት እፈራለሁ ፡፡
  ለአንባቢዎች “ሃይማኖተ አበው” የተባለው መጽሐፍ ከገጽ 381 ጀምሮ በምዕራፍ 89 ክፍል አንድ ስለዚሁ ስለተዋህዶውና ባህርዩ በሰፊው ስለሚገልጽ ቢያነቡና የግል ግንዛቤ ቢወስዱ በማለት ይህን አድራሻ አግኝቼአለሁ
  http://ethiopianorthodox.org/amharic/holybooks/haimanote/05haimanoteabewupage%20300.pdf

  በተረፈ አባባሉን ሲቋጨው "እሱ ክርስቶስ በሥጋ በታመመ ጊዜ የታመመው እርሱ ራሱ የእግዚአብሔር ቃል ነው ፤ እንደኛ ያለ ሰው ስንኳ በሞተ ጊዜ ነፍስ በባሕርይዋ እንዳትሞት ሰውም በሞተ ጊዜ ሞት ለነፍስም ለሥጋም በአንድነት እንዲነገር ሞተም እንዲባል ፤ እንዲሁም በሕማም በስቅለት በሞት ፤ በመቀበር ጊዜ እግዚአብሔር ቃል ከተዋሐዳቸው ከነፍስም ከሥጋም እንዳልተለየ ፤ ሰው ከመሆንም እንዳልተለወጠ እናምናለን" ይላልና የገባ ይግባው ፡፡

  መቸም የሰው ነገር ባትሰሙም ለእናንተ ደግሞ የማሳስበው ፣ እንዲህ ዓይነቱን ረቂቅ ምስጢር መረዳትና መፍታት የሚችለው ተራው መንጋ /ምእመኑ/ ሳይሆን ሲኖዶሱ ስለሆነ ፣ ግድፈት የምትሉትን ሁሉ በአካለ ባትቀርቡም ከነማስረጃችሁ አያይዛችሁ ቢያንስ በአድራሻ ብትልኩላቸው የዜግነትና የክርስቲያንነት ግዴታችሁን እንደተወጣችሁ እንደሚቆጠርላችሁ ነው ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Egziabhere yibarkih. it is better to learn before writing this kind of teaching. Abaselamas, sewochin lemasatat yemitadergut neger kewanaw negere-himanot eyawotachihu yimeslegnal.

   Welete-Amanuel

   Delete
 11. "....የአብሃም ድንኳን እና ድንግል ማርያምን የሚያገናኛቸው አንድም ነገር የለም"

  ድንግል ማርያምን is called የአብሃም ድንኳን because she become the host for Jesus Christ just የአብሃም ድንኳን host Sillassie. What is your religion? Do you Believe in Ab, Wold, and Menfes Qidus? Your preaching doesn't look like Orthodox Tewahido. It is Protestants preaching. So, why just go on your own belief??

  ReplyDelete
 12. U comment come from little knowlge.

  ReplyDelete
 13. የማከብራችሁ የዚህ መድረክ ተሳታፊ ወግኖቼ በሙሉ !!!

  በእንደዚህ ያለ ብዙ ሕዝብ በሚያነበው መድረክ ላይ ጽሑፍም ሆነ አስተያየት ስናቀርብና ለማስተማር ወይም ለመምከር ሳይሆን ሆነ ብለን በማንወደው ሰው ወይም ቡድን ላይ ጥላቻችንን ስንገልጽ የሌላውን በርካታ የዋህ ሕዝብ አእምሮ እያቆሸሽን መሆኑን የዘነጋን ይመስለኛል:: አዎ እውነት ነው የለየለት የእውነትና የጽድቅ ጠላት የሆነው የክፉው መጠቀሚያ የሆኑ አንዳንድ ግለሰቦች/ቡድኖች እንደዚህ ባለው የዘለፋና የስድብ ሥራ ላይ መሳተፋቸው ወደው ሳይሆን ተገደው ወይም ቃሉ እንደሚለው የዚህ ዓለም አምላክ እንዳያዩና እንዳያስተውሉ ዓይኖቻቸውን አሳውሮዋቸው ሊሆን ይችላልና እንደዚህ ላሉ ወገኖቻችን ደግሞ እንደ ቃሉ በመኖር ጌታን የምንታዘዝ ከሆነ ልናዝንላቸውና ልንጸልይላቸው ይገባል::

  ስለዚህ እባካችሁ የቃሉ እውነት የገባችሁ በመንፈስ ቅዱስ እየተመራችሁ ዝባዝንኬ ወይም ተረት ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱስ እየጠቀሳችሁ የሕይወት ቃል የሆነውን ብቻ አስተምሩን ንጹሕና እውነት የሆነውን ለይቶና አበጥሮ የመብላት መብቱ የእኛ ያንባቢዎች/የተመጋቢዎች ድርሻ ነውና ለእኛ ተውት:: ከስድብ በቀር ቃሉ የሌላችሁ ወገኖቻችንም ከማስተማር መማርን እንደ እኔ ብታስቀድሙ መልካምና ለሕይወት ይሆንላችኋልና ቆም ብላችሁ አስተውሉ:: ምናልባት በዚህ ዓለም እውቀት ተሞልታችሁ ይሆናል ሆኖም ግን ይህ ዓይንቱ እውቀት ለሥጋ ብቻ እንጂ ለመንፈሳዊ ሕይወት እንደ ወረደ አይጠቅምምና ከላይ በመንፈሱ እንደማርያም እግሩ ስር ቁጭ ብላችሁ ብትማሩ ይጠቅማችኋልና ቅድሚያ ለዚህ ስጡት:: 'ልጆችሽ ከእግዚአብሔር የተማሩ ይሆናሉ'እንዲሁም 'ያስተምራቸው ዘንድ መንፈሱን ሰጣቸው' ይል የለ ቃሉ? ይህን ብታደርጉ ጥሩ መንፈሳዊ አስተማሪዎች ይወጣችኋል:: ቤተ ክርስቲያናችንም ያለባትን የእውነተኛ አስተማሪዎች እጥረት ችግር ታቃልላለችና በእውነት ከልቤ ነውና በዚህ ጉዳይ ላይ በርቱ ማለት እወዳለሁ::

  ከዚህ በተረፈ ዛሬ እንደ ትናንቱ ሕዝብን በሃይማኖትህ ጠፋ! ፕሮቴስታንት ነው! መናፍቅ ነው! የነጭ ቅጥረኛ ነው! በአጠቃላይ እንዲህ ነው! እንደዚያ ነው! በሚል በሬ ወለደ አሉባልታ ሕዝብን ለድብቅ ዓላማ መሳሪያ ለማድረግና ሕዝብን ከሕዝብ ጋር ለማጋጨት የሚደረገው ሙከራና ከንቱና ትዝብት ላይ የሚጥል መሆኑን ኢትዮጵያውያን ወገኖቼና በተለይ የዚች ቤተ ክርስቲያን አማኞች የሆን በሙሉ ከተመክሮ የተማርነው ስለሆነ ይህን የተለመደ ስልት ለመጠቀም የምትሞክሩ አሉባልተኞች ወገኖቻችን 'የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ባንተ ይብስብሃል' የሚለውን መልእክት ብታስተውሉት ይጠቅማችኋል እላለሁ::

  ለማጠቃለል ማ? ማነው? የትምህርቱ መልእክት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ንውን? ለሚሉት ጥያቄዎች 'ሁሉን ፈትኑ የሚጠቅማችሁን ያዙ' በሚለው የአምላካችን ቃል መመሪያነት መዝነንና አጣርተን ቃሉን ስለምንበላ ምግብ የሌላችሁ ካላቸው አበረን እንብላ እያልኩ ለተሳዳቢዎች ግን ጌታ ማስተዋል ይስጣችሁ አሜን::

  ቸሩ አምላካችን እግዚአብሔር አገራችንንና ቤተ ክርስቲያናችንን ይባርክ!!!

  ሁላችሁንም (ተሳዳቢው ተሳዳቢ በማድረግ የሚጠቀምባችሁንና የሃሰት አስተማሪ ያደረጋችሁን ጭምር) ፍቅር በሆነው ጌታ እወዳችኋለሁ::

  ሰላም ሁኑልኝ

  እህታችሁ

  ሰላም ነኝ

  ReplyDelete
 14. "መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ'
  "ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ፤"

  ReplyDelete
 15. TESBEL ALELACHIHU MEGEMEREA 3..7 ABATOCH YATMEKOACHIHU!!!!!

  ReplyDelete
 16. Egzeabher Lebona yestachewu!!! Abetu ante Astagslegn.Egnas behawreyatena benebeyat dem betansech emnet tebekehanalena hulem lzelalem enamsegnehalen!!!

  ReplyDelete