Wednesday, January 18, 2012

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እውነትና እውነተኞች የሚገፉባት፤ ሐሰትና ሐሰተኞች የሚነግሱባት እስከ መቼ ይሆን? - - - Read PDF

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እያየንና እየታዘብን ያለው ነገር እጅግ ይገርማል፡፡ በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሀብትን ለማካበት፣ ዝናን ለማትረፍና የበላይ ለመሆን በሚደረገው ትግል አንዱ ሌላውን እየደፈጠጠ ለማለፍ በሚያደርገው ሩጫ፣ በዕውቀት ሳይሆን በአፍ ብቻ ለመንገስ በሚደረገው ግስጋሴ፣ አንዱን ዝነኛ በህብረት አውርዶ በእርሱ እግር ለመተካት ዝነኛውን ከመድረክ ማውረድና ከህዝብ ልብ ማስወጣት የሚለው አላማ የተሳካ ሲመስል፣ በአድማው ካበሩት መካከል አንዱ ተነጥሎ ስፍራውን ለመሙላት የሚያደርገው ጥድፊያ ለተመለከተው ያስገርማል፡፡ ጋኖች አልቀው ምንቸቶች ጋን በሆኑበት ዘመን ላይ መገኘታችንም በእጅጉ ያሳዝናል፡፡


በዚህ ዘመን ቤተ ክርስቲያኒቱ ለአፈኞች እንጂ ለአዋቂዎች ግድ የሌላት መስላ ትታያለች፡፡ እውነት በአደባባይ ሲወገዝና ሐሰት በአደባባይ ሲነግስ እያየችም ዝምታን መርጣለች፡፡ ብዙው ህዝብም የሚያሳርፈውንና የሚያድነውን እውነት ካለማወቁ የተነሳ የሰባኪ ፋሽን ተከታይ ሆኗል፡፡ ነቢዩ እንዳለው ሕዝቡ ዕውቀት ከማጣት የተነሳ ጠፍቷል፡፡

አንድ ሰሞን በጋሻው በጋሻው ሲል የነበረው ሰው፣ ዛሬ ተከፋፍሎ ግማሹ ከበጋሻው ወዲያ ማንንም አልሰማም ሲል፣ ግማሹ ደግሞ በበጋሻውና ጓደኞቹ ላይ መፈንቅለ ዝና ያካሄዱ ሰዎችን በልቡ ይሁን በእግሩ ለጊዜው ባይታወቅም መከተል የጀመረ ይመስላል፡፡ ሌላው ተረኛ ነገ ሲመጣ ደግሞ ወደዚያው መገልበጡ አይቀርም፡፡

ሰው ሰውን ከመከተል ነጻ የሚወጣው አምላኩን በትክክል መከተል የጀመረ ዕለት ነው፡፡ ታዲያ ይህን ህዝብ ከአምላኩ ጋር ማን ያስተዋውቀው? ሁሉም ባለጊዜ እያደረገ ያለው ህዝቡን ከራሱ ጋር ማስተዋወቅ ነው፡፡ የእውነተኛ ሰባኪ ተልእኮ በስብከቱ ለሰው መድኃኔዓለም ክርስቶስን ማሳየት ነው፡፡ ብዙ ሰባኪዎች ግን በተቃራኒው ስብከትን ራሳቸውን ለማስተዋወቅ እየተጠቀሙበት ነው፡፡ ይህ ህዝብ ወደመድኃኒቱ ክርስቶስ ማየት ከጀመረ እኛን ይተወናል የሚል ስጋት ሀብትና ዝናን በሚናፍቁ ሰባኪዎች ዘንድ አለ፡፡

በእነበጋሻው ላይ ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ ከተከፈተ ጊዜ ጀምሮ እነርሱ የለቀቁትን ክፍት የዝና አውደ ምህረት ለመቆጣጠር ሁሉም እየተሯሯጠ ይገኛል፡፡ ማህበረ ቅዱሳን የሰጠውን የስም ማጥፋት ተልእኮ በሚገባ ለመወጣት በሙሉ ፈቃደኝነት ራሱን የሰጠውና ዋናው ተዋናይ የነበረው ዘመድኩን በሀብትና በዝና ትግሉ ወቅት የዘራውን በማጨድ ላይ ስለሆነ ለጊዜው መከሩን በመሰብሰብ ስራ ተጠምዷል፡፡ ይህም አጋጣሚ በነዘመድኩን የስም ማጥፋት ትግል ውስጥ እምብዛም ስሙ ያልተነሳውና የድል አጥቢያ ጀግና ሆኖ ብቅ ያለው ዘሪሁን ሙላቱ ከሰሞኑ ራሱን ለማስተዋወቅና ዝነኛ ሆኖ ህዝቡ ውስጥ ለመግባት እየተጣደፈ ነው፡፡ በየሳምንቱ ረቡዕ በአዲሱ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በሰርክ የጥያቄና መልስ መርሀግብር፣ በግብር ወንድሙ በምህረተአብ አሰፋ በኩል ተመቻችቶለት አስፓልት እስኪዘጋ ድረስ ብዙ ህዝብ እየተሰበሰበ ነው፡፡

ተመሳሳይ መርሀግብር በልደታ ቤተክርስቲያን ጀምሮ የነበረ ቢሆንም የደብሩ አስተዳዳሪ እንዲቆም አድርገዋል፡፡ እዚያ እንዲቆም የተደረገው መርሀ ግብር አዲሱ ሚካኤል እንዲቀጥል ለምን ተደረገ? የሚለው ገና መመለስ አለበት፡፡ እንዲያውም መርሀግብሩን ወደ አራዳ ጊዮርጊስና ወደ ስድስት ኪሎ ማርቆስ ለማስፋፋት እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን እየሰማን ነው።

አዲሱ ሚካኤል የምህረተአብ (በቅጽል ስሙ ፍልፍሉ) ቤተኮሜዲ፣ የዳንኤል ክብረትም ተረት መተረቻ ወግ መሰለቂያ፣ (ለነገሩ ዳንኤል ክብረት ወግ ጸሀፊ አድርጎ ራሱን ቢቆልልም ወግ ጸሀፊ አለመሆኑን ሐያሲ አለማየሁ ገላጋይ በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ ነግሮናል) የማህበረ ቅዱሳን አንዱ ስትራቴጂካዊ ቦታ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ይህ ሳያንስ የእምነት የለሹ፣ የዘዳቬንቺ ኮድ ክህደት ዋና አቀንቃኝ፣ የኦንሊ ጂሰሱ፣ የሰባልዮሱ፣ በምግባረ ብልሹነት ከቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በተደጋጋሚ በመታገድ የዲሲፕሊን እርምጃ የተወሰደበትና የግለሰቦችን ስም ለማጠፋት በጻፋቸው መጻሕፍቱ ተከሶ 1 ዓመት ከ8 ወር የተፈረደበትና በገደብ የተለቀቀው ዘሪሁን መፈንጫ መሆኑ ደግሞ በጣም ያሳዝናል፡፡ እርግጥ ጅማሮው የማይዘልቅ ማኅበር አይነት በመሆኑ የትም እንደማይደርስ ይታወቃል፡፡ እስከዚያው ግን ሕዝቡ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አውደ ምህረት ላይ እየተላለፈ ያለውን የኑፋቄና የሐሰት ትምህርት እንዲመረምርና እንደዘሪሁን ካሉ ከሃድያንና መናፍቃን ትምህርት ራሱን እንዲጠብቅ ማሳሰብ አስፈልጓል፡፡

በዚህ ጽሑፍ በተከታታይ ዘሪሁን በአዲሱ ሚካኤል ቤተክርስቲያን እየዘራ ያለውን ክህደትና ኑፋቄ እንዲሁም በጋሻውን እየኮነነ ራሱን እውነተኛና ሊቅ እያስመሰለ ያቀረበበትንና ከእንቁ መጽሄት ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ውስጥ የዘራቸውን ኦርቶዶክሳዊ ያልሆኑ ትምህርቶችና በጌታችንና በመደኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የጻፈውን ከዳቬንቺ ኮድ የከፋና በእጁ የተጻፈ ጽርፈትና ሌሎችንም የእርሱን ማንነት የሚያመለክቱ ዘገባዎችን በመረጃ ላይ በማስደገፍ እዳስሳለሁ፡፡

ህዝቡ ያሻውን ጥያቄ በቀጥታ ይጠይቅ፤ ሊቀ ጠበብት ዘሪሁን በቀጥታ ምላሽ ይሰጣል ተብሎ የተጀመረው ይህ መርሀግብር ትክክለኛውን ሰው አላገኘም እንጂ ጥሩ ነበር፡፡ በህዝቡ ውስጥ ለሚጉላሉ ጥያቄዎች እውነተኛና የሚያሳርፍ ምላሽ አይሰጥበትም እንጂ መልካም ነበር፡፡ ከዚህ ቀደም ያልተሰሙና ከመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮት ውጪ የሆኑና በአውቃለሁ ባይነት ብቻ በቃላት ኳኳታና በኩሸት የተሞሉ የሐሰት ትምህርቶች የሚዘሩበት መስክ ሆነ እንጂ መልካም ነበር። በአጠቃላይ መድረኩ ራስን አዋቂ ለማሰኘትና ዝናን ለማትረፍ ያለመ ሆነ እንጂ መድረኩ መመቻቱ ጥሩ መሆኑን መግለጽ እፈልጋለሁ፡፡

በእስካሁኑ ሂደት ዘሪሁን ከሰጣቸው ምላሾችና በምላሾቹ ውስጥ ከዘራቸው የሐሰት ትምህርቶችና ኑፋቄዎች መካከል ሦስቱን እጠቅሳለሁ፡፡ የመጀመሪያው ሰይጣን ንስሀ ገብቷል የሚለው ነው፡፡ ይህን መሰል ቧልት ከዚህ በፊት የሰማነው ከክርስቶስ ሰምራ የገድል መጽሐፍ ነበር፡፡ ክርስቶስ ሰምራ ሰይጣንን ከእግዚአብሔር ጋር ለማስታረቅ ሞክራ እንደነበረና በሰይጣን እንቢተኝነት እርቁ ሳይሳካ መቅረቱ ተጽፏል፡፡ ክርስቶስ ሰምራ ሰይጣን ከእግዚአብሄር ጋር ቢታረቅ ሰው ሀጢአት መስራት ያቆማል የሚል ሐሳብ አለው፡፡ ነገር ግን ሰይጣን ከእግዚአብሔር አይታረቅም እንጂ ቢታረቅ እንኳ ሰው ውስጡ በሀጢአት የተበከለ፣ ክፉና ተንኮለኛ ልብ ያለው ሀጢአተኛና ከፍጥረቱ የቁጣ ልጅ ስለሆነ ሀጢአት መስራቱን ይቀጥል ነበር፡፡ ተክልዬም ሰይጣኑን እንዳመነኮሱት ገድላቸው ይናገራል፡፡ ይህም ተመሳሳይና ሊሆን የማይችል ነገር ነው፡፡

ዘሪሁን ግን ክርስቶስ ሰምራ ለማስታረቅ ከመሞከሯ በፊት፣ ተክልዬም ሳያመነኩሱት ሰይጣን ንስሀ ገብቷል የሚል የሐሰት ትምህርት ዘርቷል፡፡ የትና መቼ ነው? ይህ የሆነው ለሚለው ጥያቄ ሲመልስ፣ ጌታችንን ለመፈተን በመጣ ጊዜ ሰይጣን ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ተጠራጥሮ ‹‹የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንክ›› አለ:: ከዚያ በኋላ ግን ‹‹ማን እንደሆንክ አውቄሃለሁ የእግዚአብሔር ቅዱስ›› ብሎ መሰከረ፤ ይህም ንስሀ መግባቱን ያሳያል፡፡ እውን ይህ ንስሀ መግባት ነውን? በእርሱ ቤት አዲስ ምስጢር ማመስጠሩ ነው፡፡ ወንጌሎች ግን እነዚህን ታሪኮች ያሰፈሩ ቢሆንም ሰይጣን ንስሀ ገብቷል የሚል ሀሳብ በታሪኮቹ ውስጥ አላስተላለፉም፡፡

ወደ ሁለተኛው ተጠቃሽ የዘሪሁን ሐሰተኛ ትምህርት እናምራ፡፡ የዘላለምን ህይወት ለመውረስ ምን ላድርግ ሲል ለጠየቀው ሰው፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲመልስ ትእዛዛትን ጠብቅ ብሎ ዝርዝራቸውን ይነግረዋል፡፡ ያም ሰው እነዚህንማ ከልጅነቴ ጀምሬ ጠብቄያለሁ ይለዋል፡፡ ከዚያም ኢየሱስ ፍጹም ልትሆን ብትወድ ያለህን ሁሉ ሸጠህ ለድሆች ስጥ መጥተህም ተከተለኝ አለው፡፡ ሊቁ ዘሪሁን ይህን ታሪክ ከኦርቶዶክስ አማኞች ጋር በማዛመድ ጌታ አሁን ወደ እኛ ቢመጣ ፍጹም ልትሆን ብትወድ አይለንም፡፡ እኛ ሁሉንም ስለ ያዝን፣ ማለትም ማርያምን፣ ገብርኤልን፣ ሚካኤልን፣ ጊዮርጊስን በአጠቃላይ ጻድቃንን ሰማዕታትን ስለያዝን ይህን ጥያቄ ከቶም አያነሳብንም፡፡ እናንተ ፍጹማን ስለሆናችሁ ሰተት ብላችሁ ግቡ ነው የሚለን ሲል፣ ህዝቡ እውነትን እንዳያውቅ፣ እግዚአብሔርን በትክክል እንዳያመልክና በክርስቶስ ጸንቶ በጎ ምግባርን እንዳያፈራ በባዶ ተስፋ በመሙላት በዚሁ ሕይወቱ እንዲገፋና የእርሱ ተከታይ ሆኖ እንዲቀር በማሳት ላይ ይገኛል፡፡

ሌላው ዘሪሁን የዘራው ኑፋቄ ካህኑ ዘካርያስና ሚስቱ ኤልሳቤጥ ጻድቃን የተባሉት የሙሴን አስሩን ሕግጋት መቶ በመቶ ስለጠበቁ ነው የሚል ነው። ይህ ትልቅ ስሕተት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ጻድቅ የለም አንድስ እንኳ (ሮሜ 3፡11) ሲል ህገ እግዚአብሔርን መቶ በመቶ የጠበቀ አንድም ሰው እንደሌለ ይመሰክራል። መጽሐፍ ቅዱስ በሌላ ስፍራ ላይ እገሌ ጻድቅ ነው ሲልም፥ ህግን መቶ በመቶ ጠብቋል ማለት እንዳልሆነ ግልጽ ነው። ምክንያቱም ሰው ከስጋው ደካማነት የተነሳ ሕግን መፈጸም እንደተሳነው ተጽፏልና (ሮሜ 8፡3-4)፡፡ እገሌ ጻድቅ ነው ሲባልም ዘሪሁን እንዳለው መቶ በመቶ ህግን ጠብቋል ማለት ሳይሆን፥ ያ ሰው ከሌላው ሰው ጋር ሲነጻጸር የተሻለ ሰው ነው የሚል አንድምታ ያለው አነጋገር ነው። በመሆኑም ስጋን የለበሰ ሁሉ የህግን ስራ በመስራት እንደማይጸድቅ ታውቋል፤ ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሏልና ማንም በእግዚአብሔር ፊት በህግ እንዳይጸድቅ ግልጥ ነው (ገላ. 3፡11)። ስለዚህ ዘሪሁን ሰውን ከጸጋ ለማሸሽና ከህግ ቀንበር በታች ለማኖር የጀመርከው የስህተት ትምህርት እነሐዋርያው ጳውሎስ ያወገዙት የጥንት ኑፋቄ ነው (ገላ. 1፡6-9)። ስለዚህ ዛሬም ቃሉ በህግ ልትጸድቁ የምትፈልጉ ከክርስቶስ ተለይታችሁ ከጸጋው ወድቃችኋል (ገላ. 5፡4) ይልብሃል።  

ይህ ሁሉ ሲሆን ዘሪሁን ተሳስቷል ያለ፣ ትምህርቱ ሊመረመር ይገባል ብሎ የተናገረ የለም፡፡ ይህን ጊዜ አንዱ ተነስቶ ወንጌልን ቢሰብክና እውነተኛው አዳኝ መድሀኔ አለም ክርስቶስን ቢያስተምር ተሐድሶ ሆኗልና ይወገዝ ባዩ ይበዛ ነበር፡፡ ለዚህ ነው ቤተክርስቲያን እውነትና እውነተኞች የሚገፉባት ሐሰትና ሐሰተኞች ደግሞ እየነገሱባት ነው ያልኩት፡፡ እውነት የሚወገዘው፣ ሐሰት ያለ ተቃውሞ የሚነግሰው ግን ከቶ ለምን ይሆን?

በቀጣይ ዘሪሁን ከዕንቁ መጽሔት ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ውስጥ፣ ማርያም ሥላሴን ወልዳለች ማለቱን፣ ትምህርተ ሥላሴን በማያውቀው ገብቶ ማደፈራረሱን፣ ሐዋርያት ያጠመቁት በኢየሱስ ስም ነው ማለቱንና ሌሎችንም ኑፋቄዎችና ክህደቶች ይዤ እመለሳለሁ፡፡ 

ይቀጥላል

ጸጋ ታደለ

13 comments:

 1. God may help u!!!

  ReplyDelete
 2. bravo abaselama, keep informing us please.

  ReplyDelete
 3. menafik malet eko yesewun melkamun neger yemikawom malet new, woyew le enanite.

  ReplyDelete
  Replies
  1. yetekawemut eko hasetun new.yeminagerut eko ewnet new.bible kefet adirgna endaltesasatu tayaleh.lenegeru"endayastewulu yezih alem gezhi aynachewun asawurotal enezih degmo letifat ken yetemedebu nachew"yilalna bible balkew neger algeremim.aba selama GOD tsegawun yabzalachihu,liyu yehone yekalun megelet begeta be'EYESUS sim yistachihu.stay blessed.

   Delete
 4. Dear Abaselama,

  I appreciate your throuth information. You will see what will happen in a very near future. For those who adore MK is the best way to judge who they are. When I knew that Zeryehun is the member of MK I hate them. It is easy to know who they are when you know their friends. I am know hundered percent sure about MK. I used to support them. But now NO MORE!!!!!!!

  ReplyDelete
 5. Yes that is good idea. Mehretab(feleflu) ha ha ha ha good name for him B/s he is not sebaki but he is sebaqi. Zerihun also spritualy cerizy he is not beliver. Keep it up aba selamas.

  ReplyDelete
 6. Ende enanet ewentegnoch endteluachewen eysusen new ymisbekut belachu endtadenkuachew SILASE ATEBELU EYESUS BELU malet alebachew you haven't a moral to criticize those people MAHIBER KIDUSANENEM HONE ENZIHN SEBAKIWOCH ENANET EKO CHEWAWOCH NACHU DO YOU KNOW THE MEANING OF CHEWA? YEHINM LEMAWEK ENKUAN EWENTEGNA ORTHODOXAWI MEHONEN YETEYIKAL HAMETEGNOCH, FERAJOCH, SIRA FETOCH NACHU ESHI

  ReplyDelete
 7. WE NEED SOME ONE LIKE U TO TELL THE TRUTH TO THE WORLD THOS PPL MKS ARE DESRTOYING OOUR CURCH AND YE ABATOCHEN KIBER.. I DONT KNOW WHY THE PAPASAT R AFREAID OF THEM I KNOW THEY DONT SUPOR THEM FROM THERE HEAR BUT OUT OF AFREAID OF SOME THING... BUT YEWONET AMLAK EYAGALETACHEW NEW .. PLS TELL TO ZEMARIOCHACHEN D TIZITAW Z MIRTENSH..Z ZERFE D EZIRA D HAWAZ ..Z KIDIST..ETC..AMLAK YABERTAHCU BEGFACHU KUTER YEBELET WED KIBER EYASTEGWACHU ENDHON TERDU ESEMAETAT YESADKAN BERKET AYILEYACHU ..

  ReplyDelete
 8. Mehretab pls first of all do you remember the money you steal.
  First of all, pay the money of those who still crying because of you. Then try to speach in front of the pulpit. You are all liers. Your best friend Zeryehun he is not a beliver, he knows what he wrote about Jesus Christ and........ Any way if he don't stop cheating the Christians All Christanis will read in the near future his own handrightin.

  Aba Selama I wish you all the best in the world and Happy Birthday!!!!!

  ReplyDelete
 9. begahsawo selase atbelu eyesus kirstos bilu yalew silasen lemekad endalhone ke kehadiwo zemedkun armagedo vcd lay lemeredat aemroachen ena lebachen kaltedefene beker lemen yihin kal endetekeme gilse new.. if i know my bibel and some one ask me 'alazaren kkemot yasnesawo manew?' i will say eyesus kirstos,, cos that is what the bibel says. begashaw did not say besilase atmenu .. but do no be afreaid ye kirstosen sim lemetrat simun lemtrat kafern ersum yafrbnalina.. ebakachu ene zemedkun en 4 kiloch tebeleten blachu tornet akumo bewhala tafralachu yafrbachwal.

  ReplyDelete
 10. that is true Alazaren kemot yasnesaw is jesus . yemayikad hak new. yebabilonen kwankwa yedeblalekut degmo selasewoch abrhamn yegobgnut selasewoch. that is true.

  ReplyDelete
 11. mhreteab and pastor dawit temekakerw biznes endseruben yeterdan min yahiloch nen ??

  ReplyDelete