Monday, January 23, 2012

ተጠንቀቁ ክፍል ሦስት - - - Read PDF

ፈሪሳውያን በመንፈሳዊነት እውሮች ናቸው::

ጌታ እንደዚህ አለ "ተዉአቸው፤ ዕውሮችን የሚመሩ ዕውሮች ናቸው፤ ዕውርም ዕውርን ቢመራው ሁለቱም ወደ ጉድጓድ ይወድቃሉ አለ" (ማቴ 1514) ፈሪሳውያን መጽሐፍ ቅዱስን ያወቁ ናቸው፤ በመንፈሳዊነት ግን እውሮች ናቸው። ስለዚህ በመንፈሳዊ ነገር ላይ ምንም መገለጥ አይኖራቸውም። እንደዚህ ያሉ መሪዎች ደግሞ ሌሎችን ሲመሩ አይቶ ጌታ "ተዋቸው ሁለቱም ተያይዘው ገደል ይገባሉ" አለ። (15:14)በምንም ምክንያት እውርን መከተል የለብንም። የምንከተለው ሰው መንፈሳዊ ብርሃን የበራለት ሰው መሆን አለበት። ፍቅር ማጣት ነው የመንፈሳዊነት እውርነትን የሚያመጣው። ጌታን የሚወድ ሰው እግዚአብሔርን በግልጽ ያየዋል። መከተል ያለብን እንደዚህ ያለውን መሪ ነው።

ፈሪሳውያን ግብዞች ናቸው

በዚያን ጊዜ የሕዝብ አእላፍ እርስ በርሳቸው እስኪረጋገጡ ድረስ ተሰብስበው ሳሉ፥ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ይል ጀመር። አስቀድማችሁ ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠበቁ፥ እርሱም ግብዝነት ነው። (ሉቃ 12:1) ግብዝ የሚለው ቃል የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "አክተር" ውይም "ተዋናይ" ማለት ነው። አንድ ሰው በቲያትር ወይም በፊልም ስራ ላይ እንደ መጥምቁ ዮሐንስ ሆኖ መስራት ይችልና በግል ሕይወቱ ደግሞ በጣም ጠጪ እና ዝሙት አዳሪ ሊሆን ይችላል። ዛሬም ብዙ ክርስቲያኖች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሲሆኑ ብቻ ጥሩ ለመሆን አስመስለው ይቆዩና በሌላው ጊዜ ግን በቤታቸው ሄዳችሁ ብታዩአቸው እውነተኛ ማንነታቸውን ትረዳላችሁ። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሲሆኑ አስመሳዮች ብቻ እንደሆኑ ትረዳላችሁ። በቤታቸው ሲሆኑ አምላክን የማያመሰግኑ የሚአጉረመርሙ ሐሜተኞች አኩራፊዎች ሆነው ይገኛሉ። እኛስ እንደዚህ አይነት ክርስቲያኖች ነን??

ፈሪሳውያን ሌሎችን በተናገሩበት ቃል ማጥመድ ይወዳሉ

ፈሪሳውያንም ወደ እርሱ ቀረቡና ሲፈትኑት። ሰው በሆነው ምክንያት ሁሉ ሚስቱን ሊፈታ ተፈቅዶለታልን? አሉት። (ማቴ 19:3) ፈሪሳውያን ሰዎችን በንግግራቸው ማጥመድ እና ከዛም መክሰስ ይወዳሉ። ጥያቄም ጠይቀው ሰዎችን በሚመልሱት መልስ ሊያጠምዱዋቸው ይሞክራሉ። ማቴ 22:15 ላይ ስናነብ እንዲህ ይላል "ስለዚህ ፈሪሳውያን ሄዱና እንዴት አድርገው በነገር እንዲያጠምዱት ተማከሩ" (በተጨማሪም ሉቃ 11:54 ተመልክቱ)
በአሁኑ ጊዜም አንዳንድ ሰዎች አሉ ሰባኪዎችን ጥያቄ ጠይቀው በሚመልሱት መልስ ወጥመድ ውስጥ ሊያስገቧቸው ይፈልጋሉ። እነዚህ ሰዎች የመዳን ፍላጎት ሳይሆን ያላቸው፣ ሰባኪዎችን የማሳደድ ጉጉት ብቻ ነው ያላቸው ፈሪሳውያንም እንደዚህ ነበሩ። ጌታ የተናገረውን ቃል ይዘው ያለአግባብ ይተረጉሙትና ሊከሱት ይሞክራሉ። የማህበረ ቅዱሳን ዋና አገልግሎት ዛሬ ይኸው ነው። ሰዎችን በንግግራቸው ማጥመድና መክሰስ የየቀኑ ተግባር ሆኗል። ሰዎችን የምንወድ ከሆነ ምንም ነገር ቢናገሩ እንሸፍንላቸዋለን እንጂ የተናገሩትን አጣመን አንከሳቸውም። ተሳስተውም እንኳ ቢሆን ምክንያት ፈጥረን ስህተታቸውን እንሸፍንላቸዋለን። ስለ ጌታ እንዲህ ተብሎ ተጽፎአል "እግዚአብሔርን በመፍራት ደስታውን ያያል። ዓይኑም እንደምታይ አይፈርድም፥ ጆሮውም እንደምትሰማ አይበይንም" (ኢሳ 11:3) ይህ ለማንኛውም ክርስቲያን ምሳሌ መሆን አለበት።

ፈሪሳውያን ልበ ደንዳኖች ናቸው

ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፥ ልቡ ግን ከእኔ በጣም የራቀ ነው፤(ማቴ 15:8) የፈሪሳውያን ልብ ደንዳና ነው ምክንያቱም ከእግዚአብሔር የራቀ ስለሆነ ነው። ለምሳሌ ቅቤ እሳት ዳር ቢደረግ ይቀልጣል ፍሪጅ ውስጥ ቢደረግ ግን ይጠነክራል። የፈሪሳውያንም ልብ እንደዚሁ ነው። እግዚአብሔር እንደ እሳት ነው። እሱ አጠገብ ካለን ልባችን ለስላሳ ይሆናል።ድንጋይ እንኳ በእግዚአብሔር ፊት ይቀልጣል። ልባችን ለሌሎች ሰዎች ጠንካራ ከሆነ ከእግዚአብሔር ርቀን እየኖርን እንደሆነ መረዳት አለብን። የፈሪሳውያንም ልብ ለሌሎች ሰዎች ጠንካራ ነበር ምክንያቱም ከእግዚአብሔር በጣም ርቀው ስለሚኖሩ ነው። እግዚአብሔርን የሚያመልኩት በከንፈራቸው ብቻ ነበር።

ፈሪሳውያን ከፍ ባለ ድምጽ ለእግዚአብሔር የሚቀርበውን ምስጋና አይወዱም

ነገር ግን የካህናት አለቆችና ጻፎች ያደረገውን ድንቃ ድንቅ በመቅደስም ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ እያሉ የሚጮኹትን ልጆች ባዩ ጊዜ፥ ተቈጥተው። (ማቴ 21:15) ፈሪሳውያን ሰዎች ከፍ ባለ ድምጽ ለእግዚአብሔር በሚያቀርቡት ምስጋና ይረበሻሉ። ምስጋና ለእግዚአብሔር ሲቀርብ በጸጥታ ወይም ለዘብ ባለ ድምጽ ነው ብለው ያምናሉ። የማህበሩ ክርክርም ይኸው ነው፤ የነትዝታውን መዝሙር የሚቃወመው ለጌታ የሚሰጠውን ክብር ስለማይቀበል ነው ከጌታ ይልቅ የማህበሩ ባሕል ይበልጣል። ኢየሱስ ግን ልጆቹ እየጮሁ ሲያመሰግኑ በሰማ ጊዜ በጣም ተደሰተ ምክንያቱም ሁኔታው መንግሥተ ሰማይን አስታወሰው። በመንግሥተ ሰማይ የሚቀርበው ምስጋና በማይቋረጥ እና ከፍታ ባለው ድምጽ አንዳንድ ጊዜ እንደውም ከመብረቅ እንኳ በበለጠ ድምጽ (ራዕይ 19:6) የሚቀርብ ነው። ፈሪሳውያን ሰዎች አሜን ወይም ደግሞ ሃሌ ሉያ ሲሉ እንኳ ይረበሻሉ። እንደነዚህ ያሉ ቃላቶች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መባል የለባቸውም ብለው ያምናሉ። ሰዎችም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በስብከት ጊዜ ልክ ለቅሶ ቤት ያሉ ይመስል በጸጥታ መቀመጥ አለባቸው ብለው ነው የሚያምኑት። መዝሙር ሲዘምሩ ለሚያያቸውማ፣ ኢየሱስ ከሞት መነሣቱን ገና ያልሰሙ ነው የሚመስሉት።

ፈሪሳውያን በድሆች ይጠቀማሉ

እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ በጸሎት ርዝመት እያመካኛችሁ የመበለቶችን ቤት ስለምትበሉ፥ ወዮላችሁ፤ ስለዚህ የባሰ ፍርድ ትቀበላላችሁ።(ማቴ 23:14) ፈሪሳውያን እንዴት አድርገው እነዚህን ድሀ መበለቶች እንደሚጠቀሙባቸው አናውቅም። ምናልባት እነዚህን ሴቶች እግዚአብሔር እንዲመርቃቸው ያላቸውን እንዲሰጡ በማሳመን እና የሚሰጠውን ከተቀበሉ በኋላ ለራሳቸው ጥቅም ያውሉት ይሆናል። በእግዚአብሔር ስም እያሉ የድሐውን ቤት እና ጉልበት የሚበዘብዙ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ዛሬም በዓለም ላይ በብዛት ይገኛሉ። ጳውሎስ (2 ቆሮ 72) ላይ እንዳለው "በልባችሁ ስፍራ አስፉልን፤ ማንንም አልበደልንም፥ ማንንም አላጠፋንም፥ ማንንም አላታለልንም።" ይህ ቃል የማንኛውም የእግዚአብሔር አገልጋይ ምስክርነት መሆን አለበት።

ፈሪሳውያን መጽሐፍ ቅዱስን የሚተረጉሙት ምንም ከእግዚአብሔር መገለጥ ሳይኖራቸው በራሳቸው መንገድ ነው

"እናንተ ማንም በቤተ መቅደስ የሚምል ምንም የለበትም፤ ማንም በቤተ መቅደስ ወርቅ የሚምል ግን በመሐላው ይያዛል የምትሉ፥ ዕውሮች መሪዎች፥ ወዮላችሁ። እናንተ ደንቆሮዎችና ዕውሮች፥ ማናቸው ይበልጣል? ወርቁ ነውን? ወይስ ወርቁን የቀደሰው ቤተ መቅደስ? ደግማችሁም። ማንም በመሠዊያው የሚምል ምንም የለበትም፤ ማንም በላዩ ባለው መባ የሚምል ግን በመሐላው ይያዛል ትላላችሁ። እናንተ ደንቆሮዎችና ዕውሮች፥ ማናቸው ይበልጣል? መባው ነውን? ወይስ መባውን የሚቀድሰው መሠዊያው? እንግዲህ በመሠዊያው የሚምለው በእርሱና በእርሱ ላይ ባለው ሁሉ ይምላል፤በቤተ መቅደስም የሚምለው በእርሱና በእርሱ በሚኖረው ይምላል፤ በሰማይም የሚምለው በእግዚአብሔር ዙፋንና በእርሱ ላይ በተቀመጠው ይምላል»  ፈሪሳውያን መጽሐፍ ቅዱስን የሚተረጉሙት በራሳቸው አእምሮ በመመራት ምንም የእግዚአብሔር መገለጥ ሳይኖራቸው ነው። የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል በፈለጉት መንገድ አስተካክለው የእግዚአብሔር ቃል ነው በማለት ለሕዝብ ያስተምራሉ። እንደነዚህ ዓይነት አስተማሪዎች ዛሬም ይገኛሉ። ከእግዚአብሔር ቃል በስተጀርባ ያለውን መንፈስ ሳይረዱት ፊደሉን ብቻ ይሰብካሉ። ፊደል ደግሞ ይገላል። "እርሱም ደግሞ በመንፈስ እንጂ በፊደል ለማይሆን ለአዲስ ኪዳን አገልጋዮች እንሆን ዘንድ አበቃን፤ ፊደል ይገድላልና መንፈስ ግን ሕይወትን ይሰጣል" (2 ቆሮ 3:6)

ፈሪሳውያን የህግን ፈደል ያጠብቃሉ

"እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ ከአዝሙድና ከእንስላል ከከሙንም አሥራት ስለምታወጡ፥ ፍርድንና ምሕረትን ታማኝነትንም፥ በሕግ ያለውን ዋና ነገር ስለምትተዉ፥ ወዮላችሁ፤ ሌላውን ሳትተዉ ይህን
ልታደርጉ ይገባችሁ ነበር" (ማቴ 23:23) ፈሪሳውያን ትንንሹን ነገር ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ወስደው የበለጠ ዋጋ ይሰጡታል። ትንሹን ነገር ትልቅ ያደርጉታል። ዛሬም ብዙ ይሄን የመሰለ ትምህርት አለ። እንደዚህ ዓይነት ትምህርት በትናንሽ ነገሮች ላይ ታዛዥ በመሆናቸው የሚኮሩ ነገር ግን ዋናውን ከአፋቸው የሚወጣውን ቃል የማያስተውሉ ብዙ ሰዎችን ያፈራል። ጌታ ከከሙንና ከእንስላል አስራት እንዳያወጡ ማለቱ አልነበረም። ጌታ ያለው ዋና ነገሮች በእግዚአብሔር ሕግ ውስጥ ከአስራት የበለጠ መታሰብ እና ትኩረት መሰጠት ይገባቸዋል። ጌታ ከሰበካቸው ነገሮች ምካከል በመንፈስ ድህነት፤ ቅድስና፤ ስለኃጢአት ማዘን፤ መክፈል ያለብንን ታክስ ባግባቡ መክፈል፤ ዳግም መወለድ፤ እግዚአብሔርን በመንፈስ ማምለክ፤ ፍቅር፤ ትሕትና፤ ጋብቻ ውስጥ ታማኝነትን፤ የሰውን ሥርዓት ማፍረስ የመሳሰሉትን ነው።

ፈሪሳውያን ምንም ፍርድ: ምህረት ወይም ታማኝነት የላቸውም

"እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ ከአዝሙድና ከእንስላል ከከሙንም አሥራት ስለምታወጡ፥ ፍርድንና ምሕረትን ታማኝነትንም፥ በሕግ ያለውን ዋና ነገር ስለምትተዉ፥ ወዮላችሁ፤ ሌላውን ሳትተዉ ይህን ልታደርጉ ይገባችሁ ነበር(ማቴ 23:23) ፈሪሳውያን ትክክለኛ ፍርድ የማያውቁና በአግባቡ የማይፈርዱ ናቸው። ለሚሳሳቱ ሰዎች ምንም ምሕረት የሌላቸው እና በራሳቸው ሕይወት ውስጥ ደግሞ ታማኝነት የሌላቸው ሰዎች ናቸው። ይሄ ሁሉ ነገር በሕይወታቸው ውስጥ ጎድሎአቸው እንኳ ቅዱሳን ነን ብለው ያስባሉ። ይህንንም የሚሉት ስለሚጾሙ ስለሚጸልዩ እና የሕግ እውቀት ስላላቸው ነው።በሕይወታችን ውስጥ እራስን ወዳድነት፣ ኩራት፣ ይቅርታን አለማድረግ እምነተ ቢስነት፣ የመሳሰሉት ባሕሪዎች ውስጥ እያሉ። የሃየማኖት ስርዓትን ተከትለናል ብለን
የምንኩራራ ከሆነ እራሳችንን ነው የምናታልለው። መጀመሪያ በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ ከፍተኛ ቦታ ሊሰጣቸው የሚገባቸውን ነገሮች መገንዘብ ትኩረት መስጠት አለብን።

ፈሪሳውያን ትንኝን አጥርተው ግመልን ይውጣሉ

"እናንተ ዕውሮች መሪዎች፥ ትንኝን የምታጠሩ ግመልንም የምትውጡ።" (ማቴ 23:24) ፈሪሳውያን ጥቃቅን ነገሮች ላይ በጣም ይጠነቀቃሉ ነገር ግን ትኩረት መሰጠት የሚገባውን ነገር ደግሞ ችላ ይላሉ። የሚጠነቀቁበት ነገር ለምሳሌ: ቤተ ክርስቲያን ሲሄድ ንጹሕ ልብስ መልበስን ወይም ቤታቸውን በንጽሕና መጠበቅ ነው። እነዚህ ጥሩ ልምድ ናቸው። ነገር ግን ትኩረት መሰጠት የሚገባቸውን ነገሮች ደግሞ ለምሳሌ ሴሰኝነተን እና ቁጠኝነትን ለመቋቋም የእግዚአብሔርን እርዳታ መጠየቅ፤ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ጠቃሚ የሆኑ ሥራዎች ላይ ተሳትፎ ማድረግን፣ ሰዎችን ወደ ክርስቶስ ማምጣትን በእንደዚህ ያሉ ነገሮች ደግሞ ትጋት እና ጥንካሬ የላቸውም። ምክንያቱም እንደዚህ ያሉ ነገሮች ጊዜንና የገንዘብ አቅምን ስለሚጠይቁ ፈሪሳውያን ደግሞ በዚህ ተስማሚ አይሆኑም።

ፈሪሳውያን ጥሩ ምስክርነት እንዲኖራቸው የሚተጉት በውጪ ብቻ ነው

«እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ በውስጡ ቅሚያና ስስት ሞልቶ ሳለ የጽዋውንና የወጭቱን ውጭ ስለምታጠሩ፥ ወዮላችሁ። አንተ ዕውር ፈሪሳዊ፥ ውጭው ደግሞ ጥሩ እንዲሆን አስቀድመህ የጽዋውንና የወጭቱን ውስጡን አጥራ» (ማቴ 23:25-26) ፈሪሳውያን ሕይወታቸውን ከውጪ ብቻ አጽድተው በልባቸው ውስጥ ስላሉ ነገሮች : ስስትን እና ማግበስበስን ለመሳሰሉ ነገሮች ግን ምንም አይጨነቁም። ኑሮአቸው የተመሰረተው በራስ ወዳድነት ገንዘብን ሀብትን በማግበስበስ እና የራሳቸውንና የቤተሰባቸውን ኩራትና ምቾት በመጠበቅ ነው። በውጪው ግን ጿሚዎች ሃይማኖተኞች እና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ባሉ ሥራዎች ላይም ተሳታፊ ስለሆኑ በሰው ዘንድ ክብርን አድናቆትንና ተቀባይነትን ያገኛሉ። እግዚአብሔር ደግሞ የሱን ወይስ የሰውን ተቀባይነት እንደምንፈልግ ያየናል የልባችንን ያያል "....ሰው ፊትን ያያል፥ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል አለው" (1ሳሙ 16:7)። ለእግዚአብሔር ሰው የመጀመሪያ ምልክቱ መሆን ያለበት በእግዚአሔር ፊት ንጹህ ልብ እንዲኖረው ማድረግ ነው።

ፈሪሳውያን ሰዎች የሚሰሩትን መጥፎ ስራ ሰርተን አናውቅም ይላሉ

"እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ የነቢያትን መቃብር ስለምትሠሩ የጻድቃንንም መቃብር ስለምታስጌጡና። በአባቶቻችን ዘመን ኖረን በሆነስ በነቢያት ደም ባልተባበርናቸውም ነበር ስለምትሉ፥ ወዮላችሁ" (ማቴ 23:29-30)
ፈሪሳውያን ሌሎች በኃጢአት ውስጥ ሲወድቁ በመመልከት "እኛ እንደዚህ አድርገን አናውቅም እንደዚህ ተናግረን አናውቅም.." ማለት ይወዳሉ:: መገንዘብ ያለብን ነገር ምንም ጥሩ ክርስቲያን ብንሆን እንኳ ከአዳም የወረስነውን ኃጢአተኛ ሥጋ መርሳት የለብንም። ፈሪሳውያን የሚዘነጉት ይሄንን በኃጢአት የተወለዱበትን ሥጋ ነው። ክርስቲያን የሆነ የእግዚአብሔር ሰው ግን ኃጢአተኛ ሥጋውን ባለመርሳት ሌሎች ሰዎች የሚሰሩትን ኃጢአት እሱም ሊሠራው እንደሚችል በመገንዘብ እና በእግዚአብሔር ቸርነት እና ጥበቃ ደግሞ ከብዙ ኃጢአቶች በመቆጠቡ አምላኩን ያመሰግናል።

ፈሪሳውያን የእግዚአብሔርን መልእክተኛ ያሳድዳሉ

"ስለዚህ፥ እነሆ፥ ነቢያትንና ጥበበኞችን ጻፎችንም ወደ እናንተ እልካለሁ፤ ከእነርሱም ትገድላላችሁ ትሰቅሉማላችሁ፥ ከእነርሱም በምኵራባችሁ ትገርፋላችሁ ከከተማም ወደ ከተማ ታሳድዳላችሁ፤ ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በቤተ መቅደስና በመሠዊያው መካከል እስከ ገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ የፈሰሰው የጻድቅ ደም ሁሉ ይደርስባችሁ ዘንድ" (ማቴ 23:34-35) ፈሪሳውያን እውነትን ከነቢያት ሲሰሙ ይናደዳሉ። በዚህም ምክንያት ሰባኪውችን ያሳደዳሉ። እነሱን የሚያሞግሱትን ሰባኪዎች ግን ይወዳሉ ነገር ግን የሚነቅፉዋቸውን እና የሚያርሟቸውን ያሳድዳሉ። የብሉይ ኪዳን ነቢያት ለእስራኤላውያን ስለኃጢአታቸው በፊትለፊት ይነግሩዋቸው ነበር። እነዚያም ነቢያት ብዙዎቹ ተገደሉ ብዙዎቹም ተሰደዱ። እኛም እውነተኛ ክርስቲያኖች ሲያርሙን እና ሲገስጹን የምንናደድ ከሆነ እንደ ፈሪሳውያን ነን ማለት ነው። ዛሬም የማህበሩ አባላት እግዚአብሔር ለኦርቶዶክሳውያን የላካቸውን ቀና ሐሳብ ያላቸውን ሰባኪዎች ማሳደዳቸውን እንዲያቆሙና እራሳቸውን ቆም ብለው እንዲመረምሩ እንመክራለን
ከፈሪሳዊነት ተጠንቀቁ
ከፍቅርተ ኢየሱስ

9 comments:

 1. I like this post,bless you Guys,that's so true...keep going !

  ReplyDelete
 2. yihen sihuf menfes kidus kalgelet beker manm lisefew aychilm .. kale hiwoten yasemalen lewondmochachen mahbere kidusanm amlak ye ferisawiyanin leb sayhon ye hawariyaten lib yistilen masadedachewon dem mafsesachewn yaskumeln maleyayet kedabilos enji kelela aydelem.

  ReplyDelete
 3. አፍቃሬ ዘርዓያዕቆብ እንደሆነ የሚታወቀው ደጀሰላም ብሎግ አባ ጳውሎስን ለማጥፋት ይሁን ለደብረ ብርሃን የዘርዓያዕቆብ ሸንጎ አደባባይ በመቆርቆር ለጊዜው ባላብራራው ምክንያት ደብረብርሃን ላይ የመዓት ንፋስ ወረደ እያለ ሽብር ይነዛ ገብቷል። ታሪክ እንደነገረንና ተአምረ ማርያም እንደመሰከረው ደብረ ብርሃን የሸንጎ አደባባይ ላይ ዘርዓያዕቆብ ያደረገው እነ አባ እስጢፋኖስንና ደቀመዛሙርቱን አፍንጫና ጆሮ እየቆረጡ፣ አንገታቸውን ብቻ አስቀርተው ከጉድጓድ ቀብረው ከብት እንደነዱባቸውና እንደገደሏቸው ነው። አርዮስ፣ መቅደንዮስና ሰባልዮስ እንኳን ሲክዱ ተወግዘው ተለዩ እንጂ እንዲህ ዓይነት ግፍ አልወረደባቸውም ነበር። አባ እስጢፋኖስ እንኳን ያልካደውና ክዶ እንኳን ቢሆን ተወግዞ ከመለየት በላይ አረመኔዎች(እምነት የለሾች) ከሚያደርጉት የባሰ የግፍ አገዳደል የፈጸመባቸው ክርስቶስን ይከተላል እየተባለ የሚነገርለት ዘርዓያዕቆብ አደባባይ ላይ አውሎ ነፋስ ተነሳ ብሎ የደጀሰላም መጻፍ ምን ለማለት ተፈልጎ ነው? ከሰማይ ዘርዓያቆብ ንፋስ ልኮ ደጁን እንደተለመደው በደም ሊያስከብር ወይስ ደጁ የደም መሬት መሆኑን ሊጠቁም? ሀፍረት የሌላችሁ ሆናችሁ እንጂ ታሪክን እስከዛሬ በማጣመም ስታሳስቱ አትኖሩም ነበር። ዘርዓያእቆብ ለሀገሪቱ ብዙ ጠቃሚ ነገር ሰርተዋል እንደዚሁ ሁሉ ብዙ ሰው ፈጅተዋል። እውነታው ይሄ ነው። ነፋስ መጣ፣ አቧራ ቦነነ እያላችሁ የሌለ ነገር በሰው ኅሊና ውስጥ ለማስቀመጥ አትድከሙ!!

  ReplyDelete
 4. In the first place, I am sending my great pleasure and appreciation to all collagues of aba selama including to all followers of eotc that except mk(mafeya killer). I urge to all eotc followers to be unite to eradicate from the earth surface those mk currentely attack church fathers, followers and even the church. God bless aba selama.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Don't be hater. Hate is from Devil, God is love.

   Delete
 5. alawaki sami ...malet endeanch new. Mikniyatum mengste semay tiz alewna blesh tsafsh. Lemehonu Kirstos yiresal lemalet new? Ebakish yene eht mkn lemekawom blesh kihdet atfetsmi. Endematawotut bawkim tsifelahu yikr yibelachihu.

  ReplyDelete
 6. Priest with out formal church education such like ergetekale , zemawie like tebate and zelebsnose blind feresaw just read abaselama and out from this darkeness and go to heaven.all those priest lier and they suck the blood of eotc follower similar to mk.

  ReplyDelete
 7. Kirsos nawu yemaseratewu MK enante betechristiyanin lemafres ganzab tisebesibalachu MK Betechristiyanin be ewukat beganzab yiredal, menafikan endalibachewu endayfanechu yitebikal, yetazegu abinet timhirt betochin yaskefital,gedamatin yidogmal bizu matkes yichalal ay aba diyabilos MK alalawus alachu aydal? Bicha yihin astayayet post endamatadergut awukale bicha gin anbibachu tawut !!!E/R LEHULACHINIM LIBONA ASTEWAY AYMIRO YADILEN AMEN!!!

  ReplyDelete
 8. Well said. There are a lot of people who are preaching God. But in the reality they are against GOD.Some of them are even preaching in the electronic media. It seems that they are preaching to get approval from some one in the world, not from God. Aba Selama is one of the electronic medias who says a lot to get approval from the Ethiopian government and some church leaders and finally to demolish the church for his own benefit. You are perfectly writing about you. God bless Ethiopia and Ethiopian Church.

  ReplyDelete