Monday, January 30, 2012

ከአንባብያችን የተላከ መልዕክት - በመጋቤ ሐዲስ መምህር በጋሻው ላይ እየተካሄደ ያለውን የስም ማጥፋት ዘመቻ አስመልክቶ

ውድ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ብናስተውል መልካም ነው፡፡ አይሁድ የአለምን መድኃኒት ለመስቀል አሳልፈው የሰጡት ባለማስተዋል ነው፡፡

እኔ መጋቤ ሐዲስ መምህር በጋሻውን የማውቀው በስራዎቹ ቤተክርስቲያን አውደ ምህረት ላይ ነው፡፡ አሉ የሚባሉትን የቤተክርስቲን መምህራን ጠንቅቄ አውቃለሁ፡፡ የማውቀውን ልናገር፣ልመሰክር ሀይማኖቴ ያስገድደኛልና ይኸው እናገራለሁ፡፡
መልእክቴ ትድረስልኝ በተለይ በተለይ ማህበረቅዱሳን”/ሰይጣን አሰልጥኖ በየስርቻው የቤተክርስቲያን ሰዎችን ለመዋጋት የሰይጣን ሰይፍ አስይዞ አስታጥቆ ላሰማራችሁ፣ለላካችሁ የማህበረ ሰይጣን ሰራዊቶች በሙሉ፡፡ በአንድ ግለሰብ ላይ እንዲህ የመስቀል ጦርነት ይመስል እንድትዘምቱ ያደረጋችሁ ነገር ምንድን ነው? ዛሬ በየቤተክርስቲያኑ ያለውን ወጣት ማን የሰበሰበው መሰለህ? እናንተማ ውጣ እነጂ ግባ ብላችሁ አታውቁም፡፡ ይህ ግብራችሁ ነው፡፡

በእውነቱ ከሆነ እንደ ምናከብራቸው ቅዱሳን፣ ሐዋርት፣ ሰማእታት በዘመናችን ትልቅ ተጋድሎ እየፈጸመ ያለ እግዚዘብሔር የመረጠው እንደ ቅዱስ ጳውሎስ በአጭር ጊዜ ውስጥ አለምን ማለት ይቻላል በወንጌል ዳር እስከዳር ያናወጠ ትክክለኛ የወንጌል መምህር ማለት መጋቤ ሐዲስ / በጋሻው ነው፡፡ ሐዋርያት 72 ቋንቋ ተገልጾላቸው ዓለምን ያስተማሩት ዩኒቨርስቲ ገብተው 72 ቋንቋ ተምረው አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ስለገለጸላቸው ነው፡፡ በመማር ብቻ ሰው ሊቅ መሆን አይችልም፡፡ እንደ ሰሎሞን ከእግዚአብሔር ሲሰጥ እንጂ፡፡ የመጋቤ ሐዲስ በጋሻው ጉዳይ ከእግዚአብሔር የተሰጠ ትክክለኛ ጸጋ መሆኑ ምንም የማይካድ ጉዳይ ነው፡፡ አሉ እኮ ስንት የሐዲስ፣የብሉይ እና የሌሎችም መምህራን የቤተክርስቲን አባቶች፡፡ ነገር ግን እነርሱ ብዙ ዘመናትን ወጥተው ወርደው ተምረው ነው ያገኙት፡፡ ሆኖም ቢማሩም በጋሻው በቆመበት አውደ ምህረት ላይ ቆመው የትኛውን ምእመን ነው በወንጌል ያረሰረሱት፡፡ በኦርቶዶክሳውያን ብቻ ሳይሆን በሌሎችም ኢአማንያን ዘንድ ልዩ ቦታ ያገኘ የዘመኑ ተጋዳይ የወንጌል መምህር ማለት መጋቤ ሐዲስ በጋሻው ብቻ ነው፡፡ እኔ እንጃ በህይወት ዘመኔ እንዲህ ገኖ የወጣ ብዙ የወንጌል እንቅፋት የሆነበት የወንጌል መምህር አላየሁም አልሰማሁም፡፡ በሀገራችን ታሪክ የተማረን፣ተቀባይነት ያለውን፣ህዝብ የሚወደውን፣ጥሩ ስራ የሰራን፣ቅን ሰውን በህይወት ሳለ አንድም ቀን አዘክራው አታውቅም፡፡ሱማ ብዙም አይገርመኝም፡፡ ከክርስቶስ ጀምሮ፣ሐዋርያት፣ሊቃውንት እንዲሁ እንደ መጋቤ ሐዲስ በጋሻው ተሳደዋል፣ተገርፈዋል፣ስማቸው ጠፍቷል፣ተገለዋል፡፡ መልአኩ ቅዱስ ጊዮርጊስን ጽና እንዳለው እኔ መጋቤ ሐዲስ በጋሻውጽና ነው የምልህ፡፡ እኒህ የሚያሳድዱህ ሁሉ አንድ ቀን ዋጋቸውን ያገኛሉ፡፡ ማንም የወንጌል መምሀር የመጋቤ ሐዲስ በጋሻውን ያህል ጸጋ የለህም፡፡ ይህ በቃላት ሳይሆን በተግባር ታይቷል፡፡ ህዝበ ክርስቲያኑ ጠጠር መጣያ እስኪታጣ ድረስ መንገድ ዘግቶ ወንጌልን ሲሰማ ከመጋቤ ሐዲስ በጋሻው ደሳለኝ አውደ ምህረት የበለጠ በቤተክርስቲያናችን ታሪክ ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም፡፡ ሰይጣን ቀና ጠላት አስነሳ፤ እንደ ሐዋርያት ሊያስወግር፡፡ በጋሻው ቢያልፍም የሰራው ስራ ግን አያልፍም፡፡ ብዙወች በጋሻው እኮ አልተማረም ሲሉ እሰማለሁ፡፡ አቋርጦ ነው የወጣው ይላሉ፡፡ ማድነቅም ያለብህ ይህንን ነው፡፡ ሳይማር እንዴት ወንድሜ አንተን በለጠህ? እንዴት ከአንተ ብዙ ከተማርከው የበለጠ ታሪክ ሰራ? ምን ታደርገዋለህ፣ከእግዚአብሔር ሲሰጥ እንጂ በመማር ብቻ አይደለም፡፡ ስንት የተማሩ የሚባሉ ግን ያልተማሩ ብዙ ሰዎች እንዳሉ አታውቅም? በአለማችን ድንቅ ድንቅ የተባሉ የፈጠራ ውጤቶች የተገኙት ባልተማሩ ሰነፍ ተብለው በሚጠሩ ሰዎች እንደ ሆነ ታውቃለህ? ወንድሜ እኔ ተምሬ፣ድግሪ ይዤ፣አቋቋም አውቄ እያልክ ስትኮራ ያልተማረ ነገር ግን ከእግዚአብሔር የተሰጠው መጣና አለምን አስደነቀ፡፡ ታሪክ ሰራ!  አሁን ሙስሊሙም፣መናፍቁም፣ኦርቶዶክሱም፣ሚዲያውም ሁሉም ነገር የሚያወራው ስለአንድ ሰው ብቻ ነው፡፡ አረ እናንት ይህ ሰው ምን አይነት ሰው ቢሆን ነው ይህ ሁሉ የሚነገርለት? ወንጌሉም፣መዝሙሩም፣ተግሳጹም ለአንድ ሰው ብቻ የተሰጠ እስኪመስል ድረስ አለም ስለሱ ብቻ ታወራለች፡፡ ዓለም ድሮም እንደዚህ ናት፡፡ ደግሞ እኮ የሚገርመው ነገር ከየትኛውም ወገን የሚሰማው ተስተካክሎ ያገልግል አይደለም፡፡ ከኦርቶደክስ ይለይ ነው፡፡ አስገራሚ ነው፡፡ እኔ እማውቀው ከውጭ ያሉትን ማምጣት እነጂ በግድ አንተ ውጣ እኛ ብቻ ኦርቶዶክስ እንባል፡፡ አስገራሚ ነገር ነው፡፡ ምን ይደረግ የተማሩት ተዋጡ ያልተማረውን እግዚአብሔር አገነነው፡፡ እንደ ይሁዳ ታናሽ ሳለ መረጠው፡፡ አለምና መላው በእርሱ የወንጌል ትምህርት ስትናወጥ ሰይጣን አየና እንዴት አድርገን ይህን ደቀ መዝሙር ከቤተክርስቲያን እንለየው ብሎ ክፉ ሀሳብ አሰበ፡፡ እስቲ ማን ይሙት የየትኛው ደቀ መዝሙር የስብከት ካሴት ነው እንደ መጋቤ ሐዲስ መምህር በጋሻው በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት አግኝቶ በመላው አለም እንደ ወረርሽኝ የተበተነው? እንዲያው የእርሱ ስብከት በሞባይሉ፣በኮምፒዩተሩ አድርጎ አንዴ አይደለም 1000 ጊዚ ደጋግሞ የላደመጠ፣የማያደምጥ እርሱ ማን ነው? በእውነት ከሰይጣን በስተቀር አርሱን የሚያሳድዱት ሁሉ እቤቱ ገዝቶ ያላዳመጠ፣ያላስደመጠ ማን ነው፡፡ ይህ ሁሉ ህዝብ መጋቤ ሐዲስ መምህር በጋሻውን የተከተለው ሌላ ምኑንም ብሎ ሳይሆን እንደ ኢሱስ ክርስቶስ ንጹህ የወንጌል ትምህርት በማስተማሩ ብቻ ነው፡፡ ዛሬማ በየመድረኩ የምንሰማው እነርሱን አትስሟቸው፡፡ እኛን ብቻ ስሙ፡፡ እናንተ በየቤተክርስቲን አውደምህረቱ የእግዚአብሔርን ቃል ሳይሆን የተጫናችሁትን ይዛችሁ እየመጣችሁ እነ መምህር በጋሻው እንዲህ አድርገው ህዝቡን ወደ ራሳቸው ወስደውት እኛን ደብቀውን ነበር፡፡ አሁን ይኸው መጣን፡፡ ተእንግዲህ አታስገቧቸው፡፡ የኛን መዝሙር፣ስብከት ብቻ ግዙ ትሉናላችሁ፡፡ የመምህር በጋሻው ስራዎች ግን ማንም በየአውደምህረቱ አንደናንተ ሳይጮህ ህዝቡ ባለበት ቦታ ድረስ ሄዶ አሁን አሳተመ ወይስ አላሳተመም እያለ ገና ከማተሚያ ቤት ነው የሚያልከው፡፡ እናንተን ያስቀናችሁ ሌላ ምንም አይደለም ይህ ነው፡፡ ገንዘብ ገንዘብ ያለ ያውቃል ተብሎ የል፡፡ እርሱ ግን ክርስቲያንና ሚስማር ሲመቱት ይጠብቃል እንደተባለው የበለጠ ነው ያገነናችሁት እንጂ ምንም አታደርጉትም፡፡ እዚህ ቦታ በዚህ ተመርቄ እያልክ አትደስኩርብን ወንድሜ፤ ዲግሪ አይደለም መጋቤ ሐዲስ መምህር በጋሻው ደሳለኝን ታላቅ ገድል እንዲፈጽም ያደረገው፡፡ ክርስትና በመማር ሳይሆን በማመን ነው። ወንድሜ ዝም ብለህ አትድከም፡፡ እንደ መጋቤ ሐዲስ መምህር በጋሻው እኔ ምንም አላውቅም በመማርማ ስንት አመት የሚበልጡኝ አሉ በል ዝም ብለህ፡፡ ነገሩ  አይፈረድባችሁም ክርስትና ይኸው ነው፡፡ አልጋ በአልጋ ነው መንገዱ መንግስተ ሰማት ሴሄዱ የሚል ጥቅስ የለም፡፡ እንኳን በወንጌል መምህሩ በእኛ በሰሚዎችም ላይ ያለውን ፈተና እኛ ነው የምናውቀው፡፡
በመጨረሻም መጋቤ ሐዲስ መምህር በጋሻው እየሆነ ያለው ነገር በሐዋርያት ላይ የደረሰው ግፍና መካራ ነውና እግዚአብሔር በተጋድሎ ያጽናህ ነው የምለው፡፡
ወስብሀት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር
አሜን፡፡
ሰይፉ ነኝ
አዲስ አበባ,ልደታ

43 comments:

 1. You an ignorant writer? I know Begashaw is one of the fruits of our church who can be encouraged;but why didn't you say "knowledge,... is not only acquired via learning but also through the grace of God" instead of swaying here and there?

  And also, if your target is to be offensive against Begashaw's foes, why do you go ups and downs? Or is your plan to buy extra-enemies?

  Indeed your thoughts are totally irrational though I am not interested to spend time for defending you.
  Yet, for sample-:
  if you don't believe in learning,
  Why Jesus did teach His disciples for many years?
  Why St. Paul studied philosophies under Greek scholars and OT under Gemalial?
  Why our church trains deacons, priests, monks, bishops and approves them by certificate? If you are a lay man, can you have an opportunity to celebrate a Mass?
  why secular institutions certify persons by status? if you work under private or government institutions, are u appointed without license?

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሰውዬው! ትምህርት አያስፈልግም የተባለ ይመስል ለምን የሌለ ነገር ለመቆፈር ትሞክራለህ? የማቅ ፍልፍሎች ምንጊዜም ዋናውን ነጥብ ጠምዝዘው ወደልባቸው መሻት ነገሮችን ሁሉ ለማጦዝ ይፈልጋሉ። ማን መሆናቸውም በዚህ ይታወቃል። ጸሀፊው ትምህርት አያስፈልግም አላለም፣አልወጣውም። እውቀት በትምህርት እንደሚገኝ ሁሉ በተለይም መንፈሳዊ እውቀት በእግዚአብሔር ስጦታ ሊገኝ እንደሚችል ነው እየተናገረ ያለው። አንተ ይህንን ትጠራጠራለህ? የትኛውም ት/ቤት ሳይገቡ ከእግዚአብሔር እውቀት ሊሰጥ እንደሚችል አታምንም? ገማልያል ምሁረ ኦሪት አንጂ መምህረ አዲስ ኪዳን እንዳልነበረ እስከዛሬ አታውቅም? ጳውሎስ ከገማልያል የተማረው ኦሪትን እንጂ የአዲስ ኪዳን የሕይወት ትምህርትን አይደለም። ኢየሱስን ያወቀው ወደ ደማስቆ ክርስቲያኖችን ለማሳደድና ለመደብደብ የይለፍ ወረቀት ይዞ ሲሄድ ነው። ወደሕይወት የመጣው ተሰብኮ ወይም ተምሮት አይደለም። ይህ እውቀት በትምህርት ነው? ወይስ በመገለጥ?ሐዋርያት ከአሳ ማጥመድ እና ከቀራጭነት የተናቀ ስራ ወደወንጌል የተጠሩት በመመረጥ እንጂ ከኦሪት ኮሌጅ አጠናቀው ወደአዲስ ኪዳን አዲሱ ት/ቤት ተዛውረው አይደለም። ይህ ሲባል መደበኛ መንፈሳዊ ትምህርት አያስፈልግም ማለት እንዳልሆነ ከግንዛቤ ይግባ። ሊሰመርበት የሚገባው ነገር እግዚአብሔር ለስራው ሲፈልግ ከውዳቂ ቦታ አንስቶ ሊቅ ሊያደርግ እንደሚችልም መዘንጋት እንደሌለበት ነው። ኢትዮጵያዊ የዜማ አባት ቅዱስ ያሬድን ልብ ይሏል? ከሚያውቁ ሰዎች ጠይቅና እውነቱን እወቅ!!!
   ስለሆነም በጋሻው ሊቅ ይሁን- አይሁን ያንን ለሰሚ ለአድማጩ ሚዛን ትተን፤ ነገር ግን በጋሻውን ለመቃወምና ለማጣጣል ሲባል ብቻ እግዚአብሔር በራሱ ምርጫ ሰዎችን በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ከየትኛውም የሰዎች ኮሌጅ በተሻለ እውቀትን በመስጠት ለአገልግሎት መላክ እንደሚችል መካድና አለመቀበል አደገኛ ስህተት መሆኑን አስረግጬ እነግርሃለሁ።
   እውቀት በመማር ይገኛል፣ ያ ማለት ግን እግዚአብሔር በራሱ ምርጫ ያለምንም ትምህርት እውቀትን አይሰጥም ማለት አይደለም። ተግባባን?
   በጋሻውን ማጣጣል ሌላ፣ የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ መካድ ደግሞ ሌላ ሆኖብህ በሁለት ወገን አትጎዳ ምክራችን ነው!!!

   Delete
  2. Am am smn on the street

   Absolutely shameful I will repeat the same shameful I don;t even know who u r but I will tell u wht u r a loser ok and don't tell us grammar we want smn who is devoted to his God n knows-well how to take care of his sheep not rather anything else. please stay away from him for God sake he is doing well his Job like his father day and night without hesitating.

   Moreover, don't raise about educational qualification and all this is useless in-front of God I know that it's required but am sure u r in on the wrong track (ths is being ostentatious, showy which is the summed up balance is zero).

   Here last point I would like to advice u one more point, when smn gets out shined please appreciate and try the same to be the same, do not rather make him fail by putting many hurdles on the track pleaseeeeeeeee u know holy book more than anybody use it for good tooooooooooooo!!!!!!!!!!!

   Delete
  3. በጣም አሳዛኝ ዘመን ልይ ደርሰናል ቀደም ሲባል የምሰማው መናፍቃን ቤተክርስቲያናችንን ሊያጠፉ ውንድም እህቶቻችንን ሊወስዱ እየሱስ ስየሱስ ይላሉ ነበር። ዛሬ ላይ ሆነን ስንመለከት ግን የመናፍቃኑን ሥራ እኝው እየሰራነው ነው። በወንድሞች ላይ በዘማሪ እህቶች ላይ ምነው ምን ነካን ከአስተያየት የሳበኝ ቢኖር በጋሻውን ለመቃወምና ለማጣጣል ሲባል ብቻ እግዚአብሄር በራሱ ምርቻ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በተሻለ እውቀት በመስጠት ላገልግሎት መላክ ይችላል፡፤ የሚለው ነው የግዚአብሄር መንፈስ እኮ እንደኛ እርስ ብርሱ የሚጣረስ አይደለም። የእግዚአብሄር መንፈስ ደግሞ አሰላም መንፈስ መሆኑንስ እናውቃለን። እርስ ብርሳችን ለምን እንባላለን በጋሻውን እንተወው እኔ ሰባኪ ከሆንኩ እግዚአቤርን የማገለግልበትን ሓዋርያ ትለእኮ ልወጣ ቅረ ለመሆኑ በጋሻውን የሚቃውም መናፍቅ ጠአ እንዴ? እርሱ ብቻ ሳይሆን ዛሬ ዛሬ የመናፍቃኑን ሥራ ጳጳሳቱም እየሰሩልን ነው ቤትክርስቲያናችንን በረት እስከማለት ደፋሮች ሆነዋል። እግዚአብሄር አምላካችን ከማያልቀው ፍቅርሩ ያድለን።

   Delete
  4. endayferedibachihu atiferdu EGZIABHERE yikir yibleachu be ewnetu MAHIBEREKIDUSAN malet ye ethiopia orthodox misesonew lielaw ende enesu bisera ybietekiristianachin yet bederesech

   Delete
 2. This comment was for Deje selam blog, but may be if they didn,t post it, people will read it on this blog. How ever Tesfu, I am very happy about this article. God Bless you more.


  በእውነት ይህንን መልዕክት ወይም ክርስቲያናዊ ተግሳፅ አስተናግዱልኝ እባካችሁ ስለ ጉዳዩ በደንብ ጠንቅቄ የማውቅ ሰለሆነ ነው።
  በቅድሚያ ግን አመሰግናለሁ፣

  ድንቄም የተዋህዶ ልጅ\ በቤተክርስቲያን ሥም የሚነግደው ዘመድኩን\ጠላት ሁን\ ፣ ዳንኤል ክስረትና፣ የማቅ የማፍያ ቡድን ሥራ
  በእግዚአብሔር ሃይልና ሥልጣን ከሸፈ። ክርስቶስ ተመረመረ ዲያቢሎስ አፈረ\ከሰረ አሜን። መጋቢ ሐዲስ መምህር በጋሻው ፤ እግዚአብሔርን
  ጋሻ አድርጎ አላፈረም ተነሳ። ወደፊትም እግዚአብሔርን የያዘ አያፍርምና ተመስገን። ማቅ ከስህተቱ ተምሮ ንስሃ ካልገባ በቀር፤ ከነሠራዊቱ
  በምድርም ሆነ በሰማይ እንደተቃጠለ ይኖራል። ሰርቃችሁ፣ አጭበርብራችሁ፣ ዘርፋችሁና ከምስኪኑ ከኢትዮጵያ ህዝበ ክርስቲያን በቤተክርስቲያን ሥም በዘረፋችሁት ገንዘብ ተመክታችሁ በምታደርጉት በደል ሁሉ እግዚአብሔር ቢታገስ የምታደርጉትን አሳጣችሁ፣ እምነት የላችሁም
  እንጂ ቢኖራችሁማ ከገንዘብ ይልቅ ከሃሰት ይልቅ የእግዚአብሔር መንግሥትና እውነት እንደሚያሸንፍ ከትንሳኤው ትረዱ ነበር። ለነገሩ ለጥፋት
  የታዘዘ ከተማ ነጋሪት ቢጎሰም አይሰማ አደል የተባለው፤ ዳንኤል ክስረትና ዘመድኩን\ጠላትሁን\ የማቅ ደንቆሮዎች፤ የሃሰት አባታችሁ
  ዲያቢሎስ ያስተማራችሁ፤ ሃሰት፣ ቅናት፣ ምቀኝነት፣ ሙግት፣ ክርክርና አሉባልታ ወዘተ\\\\ ሲሆኑ መጋቢ ሐዲስ መምህር በጋሻውን
  ግን ጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ያስተማረውና ታላቅ ፀጋውን የሰጠው በመሆኑ እንደ ሰለስቱ ደቂቅ የፀና አድርጎታል። ሰለስቱ
  ደቂቅ እንደተናገሩት አምላካችን ፈቃዱ ባይሆንና ከነደደው እሳት ባያወጣን እንኩአን አንተ ላቆምከው ምስል አንሰግድም እንዳሉት፤ ወንድማችን በጋሻውና በክርስቶስ የምንመስለው ወንድሞቹና እህቶቹ እውነተኛ የተዋህዶ ልጆች፤ ሐይማኖት የለሹ የማቅ ድርጅት ጋር በፍፁም ሊተባበርና
  የገንዘብም ሆነ የሰይጣን ተባባሪ እንደማንሆን በእርግጠኛነት በራሴና በክርስቲያኖች ወገኖቼ ሥም ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ። በተረፈ አባ
  ሰላማንና ደጀ ብርሃን እንዲሁም ሌሎች እውነተኛ ብሎጎችን ተመልከቱ። ይህንን መልዕክቴን ለማውጣት እግዚአብሔር ይርዳችሁ።
  ወስብሐት ለእግዚአብሔር።

  ReplyDelete
 3. Ewnet new endante endh yemilu bizwoch nachew. Ewntna ngat kas blo yigeletal.

  ReplyDelete
  Replies
  1. betam yemigermew neger ene seytan negn sil, kirebegn sil, merak kerto lerasih kerbe lelelan masasat endet yale kunene yihon ? ewnet yih blog ewnetegna new , ,? eski yesew degafi mehon titen ewnetun enimermir ? huala endaykochen ?
   yemisadeb blog ye cristian bolog newn ? ye orthodox blog newn ? ok be e/her mamen titachu be begashaw litamnu tinish yekerachu sintochachu nachu ? ere please erasachin eniwek ewnetun rasachin enifeligew besew animera , !!! bagashawun madnek , yikirna memkers min endaylen new ?wesibhat le e/here weleweladitu dingl welemeskelu kibur amen...!!! e/her orthodoxsn yitebikat !!!!!!!

   Delete
 4. ዲግሪ ተሸክሞ ከአገሬ ገበሬ የማይሻል ብዙ ሰው አጋጥሞኛል። ዶክተር እየተባለ በትምህርት ቤት በር ያላለፈ ያህል የሚያሳፍር የአእምሮ ጥበት ያለውም አጋጥሞኛል። በአንጻሩ ደግሞ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት እንኩዋ ሳያጠናቅቁ የሚያስደንቅ ጥበብ እና የአእምሮ ስፋት ያላቸውም ሰዎች አጋጥመውኛል። ትምህርት ቤት የሰውን እውቀት እንደሚያሻሽል ግልጽ ነው ነገር ግን ትምህርት ቤት የገባው እና ዲግሪ ያለው ሁሉ ተምሮአል ለማለት ግን ያስቸግራል። በመንፈሳዊው ዓለምም እንደዚሁ ነው። ብዙ ተማረ የሚባል፤ መምህር፣ ሊቀ ሊቃውንት ወዘተ እየተባለ የክርስናው ሐሳብ ዳብዛው የጠፋበትም ብዙ ነው። የተማረ ሁሉ ገብቶታል ማለት አይቻልም። በአንጻሩ መንፈሳዊ ኮሌጅ ሳይገቡ በራሳቸው ጥረት እን በእግዚአብሔር እርዳታ አንቱ ከሚባሉት መምህራን የላቀ ክርስትና እና የማስተማር ጸጋ ያላቸውም ብዙ ናቸው። እግዚአብሔር ባለ እውቀቶችንም፤ ማህይማንም፤ እንዴት መጠቀም እንዳለበት ያውቅበታል። ሁሉን ቻይ ነው እና። ልቡን ከፍቶ ስላስረከበው በበጋሻው ህይወት ላይ እግዚአብሔር ብዙ ነገር እየሰራ ነው። ሁሉን ቻይ የሆነው ጌታ ይክበር ይመስገን።

  ReplyDelete
 5. erasachu tsehafiwoch melisachu asteyayet sechiwoch!!!kkkkkkkkki

  ReplyDelete
  Replies
  1. Perfect you are! I sent good comments to 'aba selama' but they couldn't post mine. They post only this kinds of articles and write comment following the article.

   Delete
 6. ለእኔ እውነት ማለት እውነት ለሌላቸው እውነትን መመስከር ነው።ተመልከቱ ወገኖቸ!እወነት የሌለው ኢየሱስ ፍጡር ብለው ከሚያመልኩ ጋር ወይስ ማርያም ምስጋና ይገባታል የጌታ እናት ስለሆነች ከሚሉ ጋር?እንዴ እስኪ እውነት ወንጌልን ለመስበክ ከሆነ ሩጫችን መጀመርያ አህዛብን እንጎብኝቸው።እነሱ እኮ ምንም እውነት የሚባል ነገር የላቸውም። ሰውን ገለን ጀነት እንገባለን ብለው የሚያመኑ ሰዎች ናቸው እንድረስላቸው።
  እውነት የሆነውን ክርስቶስን መመስከር እንፈልጋለን? እንግዲያውስ በሥርዓትና በማይጠቅም ነገር ጊዜያችንን ከምናጠፋ እውነትን ላላዩ እውነት እናሳይ።ስንቱ ሕዝብ እኮ ኢየሱስ ማን ነው ተብሎ ቢጠየቅ ነቢይ አልያም ፍጡር ወይንም ደግሞ አማላጅ ሲከፋም ደግሞ ኢየሱስ የሚባል አላውቅም ነው የሚለው። ታዲያ ይህ ሁሉ እያለ ምነው ኦርቶዶክስ አረጀች እናድሳት ማለቱ አስፈለገ? እሽ ማደስም ካስፈለገ በጥላቻና በመካሰስ ነው ወይ? የሚቀድመውስ የትኛው ነው?ለአህዛብ መድረስ ወይንስ ማደስ? እረ ወዳጆቸ እውነት ከሰው ራቅች።ምነው ልባችን እያውቀው?!እንዴ እውነት የራቀው ለግብረ ሰዶማውያን ወይንስ ጻድቃን ሰማእታት ክብር ይገባቸዋል ለሚለው? ለማን ነው ወንጌል መሰበክ ያለበት?እረ እባካችሁ! ለምን በየቦታው ለሚታረዱት ክርስቲያኖች አንደርስላቸውም? በክርስቲያኖች ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍና መከራ እንመልከት እንጂ። ምነው ከተማ ውስጥ ቁጭ ብለን ለስልጣን መፋተጋችንን ብንተው። በወንጌል ስም አለማዊነትን መስበካችንን እናቁም። የትኛው ወንጌል ነው የግለሰብ ስም እየጠራችሁ ተሳደቡ ያለው? አቤት አቤት ጊዜውስ እውነትም አልቋል።

  ReplyDelete
 7. MK is anti christian, God bless Begashwe! I hope he will be strong. Bible! Bible! Bible!

  ReplyDelete
 8. if by chance Begashawe read this writing I want to say one thing.
  Brother you are history maker who every accuse you don't give up, just keep doing what you are doing "woragna mahibere kidusanene atesema".And I am sure, you will win.God is good.

  ReplyDelete
 9. Tg mk is not a part of eotc any more?

  ReplyDelete
 10. God Bless Begashaw......ahunim kezih yebelete tsegawin yabizalet........egna be were sayhon betegbar new....enji....Ahunim God Bless Megabi hadis Begashw Desalegn..the true orthodox preacher.....he is not asmesay!!!!

  ReplyDelete
 11. God Bless Megabi Hadis Begashaw Desalegn!!

  ReplyDelete
 12. Mk is killer, hater, attacker , chatkami, smoker, zemawi, pretender , defaer, ferisawe, kodalebash for gojam debtera, there for those elemnts which now swim in sin not part of eotc. All eotc do every thing in any where and place to clean up our church from enemy of Jesus. What ever worth do it. For informations the key church enemy Ergetkale, mesfin abraham aba, daniel gojam debtera and others.

  ReplyDelete
 13. ወገኖቼ!!!!

  ክርስትና ሲጠሉት የሚወድ ሲረግሙት የሚመርቅ ገድለው ሲቀብሩት መቃብር ፈንቅሎ የሚነሳ ሕይወት እንጂ ጦርነት አይደለምና እናስተውል!!!! ለሁሉም እንደሥራው የሚከፍል የጌታ ክንድ በኃይልና በስልጣን እንድትገለጥ ለምን የጾምና የጸሎት አዋጅ ለ 7 ቀናት በልቅሶ እንዲደረግ እናንተ የዚህ መድረክ አስተናጋጆች አታመቻቹም??? እባካችሁ ግብ ግቡን ለሥራው ባለቤት እንስጠው:: ይህን ስል በማስተዋልና በፍቅር መደረግ ወይም መፈተሽ የሚገባውን ሥራ ተትቶ ማለቴ አይደለም:: የክፉውን ሃሳብ አንስተውምና::

  ስለዚህ እውነትን በፍቅር እየተነጋገርን (ስድቡን ትተን - በእርግጥ ማን እንደሚሳደብ ቢገባኝም) እባካችሁ ለዚች በመንፈስ ጀምራ በስጋ እያጨደች ላለች ቤተ ክርስቲያናችን ትንሳኤ እጅ ለእጅ ተያይዘንና የመንፈስ አንድነትን ጠብቀን እንሥራ:: እናንተም ሳታውቁት የሕይወትን ጌታ እለት እለት እየሰቀላችሁት ያላችሁ ወገኖቻችን ልብ ገዘታችሁ ለሕዝባችን ጥቅም አብረን ብንሠራ ይሻላልና አስተውሉ አስተውሉ ጌታም ሳውል ሳውል ለምን ታሳድደኛለህ?? የሚለው ጥያቄ ዛሬም ለእናንተ ነውና አስተውሉ:: ጌታ ቕን ልብ ይስጣችሁ:: አሜን!!!

  የጾሙን አዋጅ በይፋ እባካችሁ ቀን ወስናቹህ አውጁት????

  የሰላም ዝናብ ለቤተ ክርስቲያናችን ለምድራችንና ለሕዝባችን ይዝነብ!!!

  እህታችሁ

  ሰላም ነኝ

  ReplyDelete
 14. ለዘመናት የወንድሞች ጠላት የሆነው ዲያብሎስ መልኩን በመቀያየር ዛሬም መንፈሳዊ መስለው ሰውን ከአባቱ ቤት የሚያባርሩ የግብር አባታቸውን ውክልና በያዙ ግልሰቦች ልብ ማደሩን ልብ ልንል ይግባል::
  ማህበረ ቅዱሳን አመራሩ የዘቀጠ ነፍስ ልማጥፋት በሚያድቡ: ነግዶ ለማትረፍ የሚሮጡ: አጠገቡ ያለውን ወንድም ውድቀት ቢቻ ለማየት የሚፈልጉ ግልሰቦች የተጠራቀሙበት ነው::

  ስለዚህም ኦርቶዶክሳውያን በያላችሁበት በንቃት በመሆን ጥላቻን የሚዘሩ ግለሰቦች ከጥፋት እንዲመለሱ በጸሎት እና በመምከር እንድትርዱአቸው አደራ እላለሁ::

  የማህበሩን አመራር አባላት የዘቀጠ ማንነት የሚያጋልጥጽሁፍ በዚህ ብሎግ እና በተለያዩ ሚዲያዎች ለማሰማት ዝግጅቱ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ለማሳወቅ እወዳለሁ በተለይም ስለ ግብረሰዶማውያን የማህበሩ ቁልፍ ሰዎች ምእመኑ ማወቅ ያለበትን ከሙሉ መረጃ ጋር ለማሳወቅ ተዘጋጅቼአለሁ::

  ReplyDelete
 15. most of us know megabi adis begashaw is ye tewahido lij and he will be always we hope..ayizoh amlak yabertah fetena yalena yeminor new, mesnat degmo keewonetgna chrstnan yitebkal ena menfes kidus yasnah.dont worry about mks and ye 4kilo sirafet dreft gelbachoch enesu sidoltu ante lehzboch yemihon wengel sibken. tebarke kidist arsema tabrtah.

  ReplyDelete
 16. That is true just take action to cleam up our church from enemy mk. Talk no more work action …

  ReplyDelete
 17. It is real time to uncover realities. Those that hate Megabi Hadis Begashw are the one who targeted to bury the bible. They do not realized that God is working in one way or another round. It is not time for "Teret- Teret". It is time for recon essence of our church, in both spiritual and development works.Therefore, together with our holy fathers, Begashw is a person selected to perform this duty.

  MK- Though we know your hidden target, it is time for you to confess

  ReplyDelete
 18. dear mr. begashaw, btslot tsina asadajochi alamabisoch silahonu yibatanalu!

  ReplyDelete
 19. ወነንገጌል በ ጸገጋና በ እምነት ነዉ እንጂ በሀይል አይደለም፡፡ወንጌል ደግሞ ራሱ ክርስቶስ ብቻ ነዉ፡፡ከተሰበከልን የክርስቶስ ወንጌል ዉጪ የሚሰብክ ደግሞ የተረገመ ይሁን መልአክም ቢሆን ተብሎ እንደተጻፈ እኛ ክርስቲያኖች ያልተሸቀጠን ቅዱሱን ወንጌል በጸጋ የመሚያስተምርነን ሰዉ በ ሀይማኖት ሳይሆን በእምት ባገኘነዉ ጸጋ እየመረመረርን መማር ተገቢ ነዉ፡፡የሚሰበክ ሁሉ ደግሞ ወንጌል አይደለምና ጠነንቀቀቅ!!

  ReplyDelete
 20. Mk be dejeselam blog lay leMindinew asteYayet yemaikebelew mahberun yemIbarkutin bicha new . Wushetam blog silehone new aydel?

  ReplyDelete
 21. አባ ሰላማዎች?
  በጣም የገረመኝ የናንተ ብሎግ ከጀመራችሁበት ቀን ጀምሮ እስከ ቅርብ ወራት የነበረው ግስጋሴያችሁ ለወንጌል የቀናችሁ መስሎኝ ነበረ ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ መልኩን በመለወጥ የደጀ ሰላም ብሎግ ወንድም እየሆነ መምጣቱና ለብቀላ’ንጂ ለትክክለኛው ወንጌል አገልግሎት አለመሆኑን በተለያየ መንገድ ጥናት በማካሄድ ተረድቻለሁ። ታዲያ የንግድ ድርጅትና የስም ማጥፋት ታፔላ ከሆነው ማቅ አንድ ከሆናችሁ ውጤቱ ምንድር ነው? ሁለታችሁ ቤተ ክርስቲያንን ለማንቀዝ የተሰለፋችሁ ሰራዊት መሰላችሁኝ።
  “ሥረይ ሎሙ እስመ በዘኢይአምሩ ይገብሩ!”
  በቁጥር 1 አስተያየት የሰጠሁ ነኝ

  ReplyDelete
  Replies
  1. endet aynet defret newe egizibher lebonawen yesteh keman gare newe yemetawerawe selamnewe yemtawerawe

   Mehertun Yelakeleh

   Delete
 22. we know deeply you. so you can write what ever what you want.

  May God give strength for our church!!!

  ReplyDelete
 23. Ebakachu ende ayente kal atetekemu "የማህበረ ሰይጣን ሰራዊቶች በሙሉ"

  ReplyDelete
 24. Menew mahbere seytan neh ende?

  ReplyDelete
 25. megabi hadis begashaw ahunm amlak segawn yabezalik dengil be milgewa titebkik

  ReplyDelete
 26. megabi hadis begashaw amlak yebleata segawen yabezalik dengil be milgewa titabkik

  ReplyDelete
 27. ክርስቶስ ያስተማረን ጸሎት "ወደ ፈተናም አታግባን" የሚል ነው። መጽሓፍ ቀዱሳችን ደግሞ ክርስትና ማለት በፈተና የተከበበ ደሴት አድርጎ ነው የሚያሳየን። አረ እናስተውል ነው ያሉት ጸሃፊው አዎ ስናስተውል እኮ እነ እስጢፋኖስን ነው የምንመለከተው፣ ታዲያ ዲያቆን በጋሻው ምን ሆነ ነው የምንለው? በምናውቃቸው ዲያብሎስ በሚገባ በሚጋልባቸው የጌታን ቃል መጥቀስ ከማይችሉ ነገር ግን ከኛ በላይ አውቂ ለአሳር ከሚሉ ጨዋዎች በደረሰበት የስድብ ናዳ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ይነቃነቃል ብዬ ቅንጣት ታህል አልጠራጠርም እልቅስ መሃበረ ሰይጣን ምን አይነት የለየለት የዘመናችን ሰይጣን መሆኑን እያሳወቀ ስለሆነ በጌታችን ቢየሱስ ክርስቶስ ስም እየገሰጽን እነርሱን ማሰር ነው አለበለዚያ ብዙ ያጠፋሉ። የናንተን አላውቅም እንጂ የኔ መጽሃፍ ቅዱስ ማንንም "መምህር አትበሉ" ስለሚል ዲያቆን በጋሻው ውንድማችን በርታ ጌታን ስታገለግል ገና ገና ብዙ ይገጥምሃል እግዚአብሄር አምላካችንም ይህን ሁሉ መከራ በስሙ እንድታሸንፍ ሃያሉን መንፈስ ቀዱስ ይልክልሃል በርትተህ ጸልይ። እኛ የክርስቶስ የሆነው እኮ ለዚህ ሁሉ አገልግሎት ስንገባ "ኃይልን በሚሰጠን በክርስቶስ ሁሉን እንችላለን።" ብለን ነውና እንኳን የነኚህ የውሪዎችን ውጊያ ቀርቶ ከዚህም የሚበልጠውን ውንድማችን በድል እንዲወጣ ክርስቲያኖች ሁሉ መጸለይ ይገባናል። ለወንድማችችን ብቻ ሳይሆን እነኚህ በቤተክርስትያናችን የበቀሉ ሙጃዎች ናቸውና እግዚአብሄር ለቤተክርስቲያናችን ሰላሙን ያምጣልን። ለነርሱም ልቦና ይስጥልን። አሜን። በቸር ይግጠመን።

  ReplyDelete
 28. Mimenu gira tegabital tiwlidus minieyetemare new teb kirikr new fikir
  bichal abtoch mstarek ena begara lebietecistianachin begara enisira ltiwldum melikam negerin(fikirin) selamin enastemirew

  ReplyDelete
 29. menigaw tebetinual ebacachihu anide enihun meleyayet yitfa Begashawm hone mehabere kidusan hulachihum mitserut letewhido bitecrisitian new slehonem bemecacelachiu fikir yinur lemenigawm true misalie hunu yalebelezia gin benanite meleyayet mekineyat menigawn tekulaw belaw ebacachihu anidhunu!!!

  ReplyDelete
 30. yemiyiastariku ena mekirew tiwlidun anid yemiyderig abatochin EGIZHABIHIER YISTEN ELALEHU

  ReplyDelete
 31. as mine this comment(text ) not write by real orthodox tewahido church believer rather than other believer our enemy wants to us to conflict one another so we should take care and stand to work together for the security orthodocs tewahido church

  ReplyDelete
 32. በትረ ክህነት ያለው ሰው አይደለም መናገር ማርመሙ እራሱ የሚያስፈራ ነው፡፡ ምርመሙ እራሱ እራስን የሚያስት ነው፡፡ ቅዱስ አብርሃም ቅዱስ መልከ ጸዲቅን የእግዚያብሔር ሰው ሆይ፣ የእግዚያብሔር ሰው ሆይ፣ የእግዚያብሔር ሰው ሆይ፣ ብሎ ጠራው፡፡ ከዚያ በኋላ ጸጓር ሰው ወጣ፡፡ እንደ ቅዱስ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሰውነቱ በጸጉር የተመላ ሰው ወጣ፡፡ የዚህ ግዜ ደነገጠ፡፡ እሚሆነውን አጣ፡፡ እንደ ሞተም ሰው ሆነ፡፡ ክህነት በሐዋሪያትም ዘመን እንደዛ ነበረች፡፡ ቅዱስ መልከ ጸዲቅ በታየበትም ግዜ እንደዛ ነበረች፡፡ ክርስቶስም እራሱ ማንን ልትፈልጉ መታችኋል ብሎ በጠየቀ ግዜ ዧ ብለው ወድቀዋል፡፡ ወደ ገደል አፋፍ ላይ ወስደው ለመወርወር ሞክረው ነበር፡፡ ከዛ በኋላ እነሱ የሆኑትን አላወቁትም ክረስቶስ ግን በመካከላቸው ተመልሶ ወደ ነበረበት ሄደ፡፡
  ከዚህ የተነሳ ክህነት አካሄዷና አሰራሯ እንዲህ ነው፡፡ ጉልበተኛ ናት፡፡ ባለስልጣን ናት፡፡ ጸጉርንም ጥፍርንም ሁለንተናን ጨምዳ የምትገዛ ናት፡፡ ስንብቷም አንዴ ለዘላለም ወደ ገነት ወደ ጽድቅ ፡፡ አንዴ ወደ ሲኦል ወደ ዘላለም ሃሳር ነው፡፡ ወደ ክብር ወደ ገነት ወደ ገነት ወደ ክብር፡፡ ወደ ሲኦል ወደ ሃሳር ነው፡፡
  ከዚህ የተነሳ ክህነት የምትፈራ ናት፡፡ በዙፋኑ ላይ ያለ ንጉስ ቢሆን በካህን ፊት ከመመርመር የሚያመልጥበት የሚሸሽበት ምንም ነገር የለም፡፡ ሰራዊትም ሊያድነው አይችልም፡፡ የጦር መሳሪያም ሊያድነው አይችልም፡፡ በቅዱስ ኤልያስ ፊት የነበሩ ነገስታት የደረሰባቸው ይታወቃል፡፡ ቅዱስ ሙሴም ቢሆን ያደረገው ይታወቃል፡፡ የእግዚያብሔር ስልጣኑ አርፎባቸው የነበሩ ሰዎች ያደረጉት ይታወቃል፡፡
  ከዚህ የተነሳ ዛሬም እግዚያብሔር አለ፡፡ ዛሬም ስርአቱ የሚፈራ ነው፡፡ የሚደፈር አይደለም፡፡ የተደፋፈረ ሰው ይሄኔ ነው መፍራት ያለበት፡፡ ተደፋፍሮ እያለ በሰውነቱ ላይ የድፍረት መዝገብ እያለ ፡፡ በሰውነቱ ሰሌዳ ላይ የበደል መጽሃፉ እንዳለ ተሞልቶ እያለ፣ ጨርቅ በመልበሱ ምክንያት በደሌ ተሸፍኖልኛል ማለት አይችልም፡፡ እንዲ ያላችሁ ሰዎች ብትኖሩ በሞኝነታችሁ በመታለላችሁ ልታለቅሱና ልታዝኑ ይገባል ማለት ነው፡፡
  ሃይማኖት ተዋህዶ መሆኗ ይታወቃል፡፡ ክህነትም ምእመናን የሚታገዱባት በትር ናት፡፡ ነብስንም ስጋንም የምትገዛ በትር በሆኗ የታወቀ ነው፡፡ ነብስን ለመግዛቷ ስጋ የሰራውን ስራ መርምራ በማስወጣቷ መሆኑን አባቶቻችን በጎላ በተረዳ አስተምረውናል፡፡ አሳይተውንማል፡፡ ክህነት ነብስን መግዛቷን የምትገልጸው ደግሞ በማሳረር በማቃጠል ነው፡፡
  ልኡል እግዚያብሔር ለካህናት የእሳት ልሳንን የሰጠ ነው፡፡ ዛሬ የሳት ልሳን ያለው ካህን አይደለም የሞቀ ትንፋሽ ያለው ካህን አይገኝም፡፡ ከዚህ የተነሳ ህዝበ ክርስትያን ከስርአት ወቶ ነው ያለ፡፡ ዛሬ በቤተ ክርስጥያን በውስጡ ስርአት የለ በውጪ ስርአት የለ፡፡ ስርአት እንዳልተሰራለት ፈርሃ እግዚያብሔር ተለይቶት ነው ያለው፡፡ አንድ ነገር ያልተለየው ቢኖር መመጻደቁ ነው፡፡ ቤተ ክርስትያን ሄጃለው ይላል መረምረቡን አያውቅም፡፡ ስጋውን ደሙን ተቀብያለው ይላል ማርከሱን አያውቅም፡፡ ሃይማኖት አለኝ ይላል ሃይማኖቱን እየረመረመና እያጎሰቆለ መሆኑን አያውቅም፡፡ አክሊሉ እንደተለየው አጋንንት እየተዋረደ መሆኑን አልተረዳም፡፡ ለዚህ መምህራን እኮ አያስፈልጉም ፡፡ እራሱ ምእመኑ እኮ ሰውነቱ ያውቃል ይረዳል ፡፡ ከዚ የተነሳ እግዚያብሔር መፈራት አለበት፡፡ የቤተክርስትያን ስርአት መከበር አለበት፡፡
  ምእመኑም ያልታየ ቢመስለው አይታለል፡፡ በመንግስቱ ሃይለማሪያም ግዜ ንጉሴ በመንግስቱ ሃይለማሪያም ነው፡፡ ጳጳሴም ተ/ሃይማኖት/መርቆርዮስ ነው፡፡ ማን ምን ያደርገኛል አለ፡፡ የእጅጌው ልብስ ቆረጠ፡፡ ቆብ አጠለቀ፡፡ እግዚያብሔር የለም አለ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ የተናገረውን ነገር፡፡ ቅዱስ ህስቄል የተናገረውን ትንቢት በላዩ ላይ ፈጸመ፡፡ የደላው ነገር የለም ፡፡ ግንባሩ ተገመሰ፡፡ ደሙ ፈሰሰ፡፡ አጥንቱ ተከሰከሰ፡፡ የሰው ስውነት እንደ ዘንጋዳ በጉድጓድ ተከማቸ፡፡ ሌላ ትርፍ የለም፡፡ የመጣ በረከት፡፡ የወረዳ ሰላም የለም፡፡
  ዛሬም ቢሆን ያው ነው፡፡ ማን ምን ያደርገኛል ነው፡፡ ማን ይጠይቀኛል ነው፡፡ መጠየቅ አለ፡፡ እንኳን በምድር በሰማይ ማን ይጠይቀኛል ነው፡፡ እወቀው እንኳን በሰማይ በምድር ጥያቄ አለ፡፡ እወቀው በምድርም ተጠያቂ ነህ፡፡
  ቤተክርስቲያን ማለት የስላሴ መንግስት ዙፋን የተዘረጋባት ቦታ ናት፡፡ ከዚ የተነሳ እዛ ቦታ ላይ ዳኝነትም ይካሄዳል፡፡ ጽድቅም ኩነኔም አለ፡፡ እርግማንም በረከትም አለ፡፡ ቤተክርስቲያን የሚሄደው ሰው ለበረከት መሆን አለበት እንጂ ለርግማን መሆን የለበትም፡፡ እዛ ቦታ ላይ ይሉ የቤተክርስቲያን አገልጋዮች የእግዚያብሄር የክህነት ቁልፍ ሊኖራቸው ያስፈልጋል፡፡ አለበለዛ ግን ጽላቱን መዳሰስ፣ ስጋውን ደሙም መፈተት፣ ይህ በምን ጣት እንደሚቻል በልኡል እግዚያብሔር ሲመረመሩ ያስረዳሉ፡፡
  ምእመኑም ሙአግደ ህሊናው በመመራመር በመጠራጠር አይዋዥቅ፡፡ ቀጥ ይበል፡፡ አይለያይ፡፡ ታማኝነቱ ለክርስቶስ ይሁን፡፡ የቤተክርስቲያን እራሷ ክርስቶስ ነው፡፡ ምእመኑ አንድ ክርስቶስን የሚያይ ከሆነ ቤተክርስቲያን በምትሰይምለት ሞግዚት ምክንያት አንዴ ካቦ እንቶኔ ጋረ፣ አንዴ ከዲያቆን እንቶኔ ጋር አንዴ ከማህበር እንቶኔ ጋር በመሆን እራሱን አይለያይ፡፡ ወደ ቤተክርስቲያን የሄደው ለመለያየት አይደለም፡፡ ክርስቶስን ፍለጋ ነው፡፡ ይህን ያስተውል፡፡ እዚ ቦታ ላይ አባ እንቶኔ ፣ ዲያቆን እንቶኔ ፣ ማህበር እንቶኔ ጥቅም ኖሮት ያችን ጥቅም ለማስከበር ዘጥ ዘጥ ሲል በዚያ ጋር ደግሞ አባ እንቶኔ ፣ ዲያቆን እንቶኔ ፣ ማህበር እንቶኔ ደግሞ ጥቅም ኖሮት ያችን ጥቅም ለማስከበር ዘጥ ዘጥ ሲል ግማሹ ማመልከቻ ጸሃፊ ግማሹ ተፈራራሚ ሆኖ ግማሹም አጨብጫቢ ሆኖ ቤተክርስቲያንን አያውክ፡፡
  ቤተክርስትያን የምትመራበት ወንጌል ዶግማና ቀኖና አላት፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት፣ ቅዱሳን አባቶች ሰልስቱ ምእልት ያስቀመጡት የ ቤተክርስትያን መተዳደርያ ቀኖና ፍትሃ ነገስት አለ፡፡ ለጳጳሱም ሆነ ለቄሱ ለዲያቆኑም ብሎም ለምእመኑም ለሁሉም ፍትሃ ነገስቱ መመሪያ ነው፡፡ ከዛ ውጪ ከሆነ አንዲትን ቤተ ክርስትያን አባ እንቶኔም ፣ ዲያቆን እንቶኔም ፣ ማህበር እንቶኔም ምእመን እንቶኔም ጥቅም ኖሮት ያችን ጥቅም ለማስከበር ዘጥ ዘጥ ሲል ያንን መከተል ዋጋ የሌለው ሃጥያት ነው ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ክቡራን ኦርቶዶክሳውያን ሆይ ኢትዮጵያንና ዕዝቦቿን አምላክ ይጠብቅልን:: ሲያስፈራ ዘመኑ ! ከጥቂት አመታት በኋላ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የምትመራው በማን ይመስላችኋል ? ማርያምን የጠራ ኦርቶዶክሳዊ ኢየሱስን የጠራ ተሃድሶ ማን ነው ያረገው ? አባቶች ዝም አሉ ! ቤተ ክርስቲያንም ርብቃን ሆነች ! ማነው የዚህን ዘመን የቤተክርስቲያንን ታላቅ ችግር የሚፈታው ?

   Delete
 33. ማህበረ ቅዱሳን
  በአገር አቀፍ ደረጃ የከፍተኛ ት/ት ተቋም ተማሪወችን አሰባስቦ ስላስተማረ ፡ ብዛት ያላቸውን በግእዝ የተፃፉ መፃህፍትን ተርጉሞ ፡ ለወጣቱ የሚጠቅሙና የሚያንፁ መፃህፍትን አሳትሞ ስላቀረበ ፡ እጅግ የበዙ ገዳማትን አድባራትን ስለረዳ ፡ የአብነት ተማሪወችና አስተማሪወች ራሳቸውን እንዲችሉ እጅግ ብዙ ፕሮጄክቶችን ቀርፆ በተግባር ስላዋለ ፡ የፈረሱ አብያተ ክርስቲያናትን ስላሳነፀ ፡ ብዙ ሺህ ኢአማንያንን በፈቃዳቸው አስተምሮ እንዲጠመቁ ስላስተባበረ ፡ የካህናት ማሰልጠኛወች በየቦታው እንዲቋቋሙ ስላስተባበረ ፡ አፅራረ ቤተክርስቲያንን ነቅቶ ስለጠበቀ ፡ የመናፍቃንን ክፉ አላማ ለሁሉ ዘወትር ግልፅ ስላደረገ ፡ ቤተክርስቲያንን ከተሃድሶወች ስለተከላከለ ፡ የክርስቶስን ወንጌል በየገጠሪቷ ክፍል እየዞረ ስላስተላለፈ ፡ ወጣቶች በነፃ ያለምንም ክፍያ ቤተክርስቲያንን እንዲያገለግሉ አርአያ ስለሆነና ስላስቻለ ፡ በጣም ርቀው የነበሩ ክርስቲያኖችን አቅርቦ ለቤተክርስቲያን በሙያቸው እንዲያገለግሉ ስላስተባበረ ፦አክራሪ ከተባለ እንግዲህ እኔም አክራሪ ልባል እወዳለሁ!!!

  ከሙስና መራቅ ፡ ሃገርን መውደድ ፡ ቤተክርስቲያንን ማወቅ ፡ ክርስቶስን ማምለክ አክራሪ ካስባለ እኔም አክራሪ ተብየ እንድከሰስ እወዳለሁ!!!

  ቦንብ ሳልወረውር ቦንብ የሚወረዉሩትን አስቀድሜ አይቼ ወገኖቼን እንዳያጠፉ ማሳሰቢያ መስጠቴ አክራሪ ካስባለኝ ፡ እንዲህ ያለ አክራሪነቴን እወደዋለሁ!!!

  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ትክክል ናት ፡ ክርስቶስም መሰረቷ ነው ፡ ድንግል ማርያምም ክብሯ ናት ማለት አክራሪ ካስባለ ፡ አክራሪ ተብሎ መሞት ክብር ነው!!!

  ክርስቶስን በካደ ትውልድ መካከል ፡ በዲያቢሎስ በምትደምቅ አለም ለመዋብ በሚቋምጥ ሰው መካከል እውነት እውሽት መስላ መወቀሷ ፡ ውሽትና ክፋትም ከሚሰሯት ጋር መከበሯ የሚጠበቅ ነው፡፡

  ዲያቢሎስ የተጣባት ክርስቶስ የራቃት ህሊና ፦ የገደላትን እየሾመች የሞተላትን መጥላቷ የሚጠበቅ ነው፡፡

  ነገር ግን ፦ እኛ ከዚህ ህብረት አለመሆናችን ይታወቅ ዘንድ : አንድም እውነት ስለሆነው ስለጌታችን ስለክርስቶስ ምስክርነት ከእውነት ጎን እንቆማለን፡፡

  ማቴ 5፡11 “ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ።”

  ReplyDelete