Tuesday, January 3, 2012

የለውጥ ያለህ! ንስሐ ለኢትዮጵያውያን - - - Read PDF

ኢትዮጵያ ሀገራችን በአሁኑ ጊዜ ዓለምን እያስጨነቀች ያለች አገር ናት። ዓለም በየጊዜው ስለችግር የሚያወጣው ሪፖርት ኢትዮጵያን በተራ ቁጥር አንድ በመጥቀስ ነው። ስለ ጦርነት፣ ስለ ድርቅ፣ ሰለ ረሃብ፣ ስለ ወባ፣ ስለ ኤች አይ ኤድስ፣ ስለ ሳንባ ነቀርሳ፣ ስለ አየር መዛባት፣ ስለ ሙስና፣ ስለ ኑሮ ውድነት ሰለስደት ወዘተ ኢትዮጵያ ግንባር ቀደም ናት።
  ዓለም የሚያውቀውን የላይ የላዩን ሪፖርት ያቀርባል እኛ ባለቤቶቹ ግን ውስጣችንን ዓለም ከሚያወቀው በላይ እናውቀዋለን። ጥንቆላዎችና አስማቶች፣ መንፈሳዊ ድንዛዜዎች፣ የሐሰት ሥራዎች፣ እግዚአብሔር የሚጠላቸው ነውሮችና ርኩሰቶች ሁሉ በሕዝባችን ኑሮና ሕወይት ላይ ወድቀው እንደሚገኙ የማንክደው ሐቅ ነው። እኛ እውነቱን ክደን ራሳችንን ትምክህተኞች አድርገን ብንመጻደቅም እንኳ የእግዚአብሔር ቃል ነውሮኞች መሆናችንን አይደብቅልንም። በመጸሐፍ ቅዱስ ላይ የምናነባቸው እርግማኖች ሁሉ ኢትዮጵያ ላይ ተደራርበው እናያቸዋለን። ሃይማኖተኞች መስለን ለመታየት ግን የሚወዳደረን የለም እንዲያውም ከኛ ውጭ ሃይማኖት ያለው ሕዝብ ያለ እስከማይመስለን ድረስ ግብዞች ሆነናል።
  እንደዚህ በግብዝነት አማኞች መስለን እንታይ እንጂ በችግር የተከበብን ንስሐ የሚያስፈልገን ኃጢአተኞች መሆናችንን እውነት የሆነው የጌታ ቃል ያረጋግጥልናል። በኛ ላይ እየሆነ ያለው እያንዳዱ ችግር በምን ምክንያት እንደመጣ ለማወቅ የሚከተለውን የእግዚአብሔር ቃል እንከታተል።

ዘዳግም 28 ቁ 15 ጀምሮ ያለውን ቃል መሠረት አድርገን ኢትዮጵያ ምን እንደምትመስል እንመልከት
«ነገር ግን የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል ባትሰማ፥ ዛሬም ያዘዝሁህን ሥርዓቱንና ትእዛዙን ሁሉ ባትጠብቅ ባታደርግም፥ እነዚህ መርገሞች ሁሉ ይመጡብሃል ያገኙህማል» 15
 በረከት ስለማጣት
«በከተማ ርጉም ትሆናለህ በእርሻም ርጉም ትሆናለህ እንቅብህና ቡሃቃህ ርጉም ይሆናል፣ እጅግ ዘር ወደ እርሻ ታወጣለህ፤ አንበጣም ይበላዋልና ጥቂት ትሰበስባለህ» ዘዳ 2818 38
   ዛሬ በማዳበሪያ ኃይል የሚሰበሰበው እህል ለገበሬውም ሆነ ለከተሜው አልበቃም። የአሜሪካና የካናዳ ስንዴ ባይኖር ቀስ በቀስ ባለቅን ነበር። ይህም እርግማኑ የደረሰባቸው ኃጢአተኞች እጣ ፋንታ ነው። በእውነት እኛ እግዚአብሔርን በእውነትና በመንፈስ የምናመልክ ሆነን ቢሆን እንዲህ የሚለው ቃል ያገኘን ነበር?   
«ጐለመስሁ አረጀሁም፤ ጻድቅ ሲጣል፥ ዘሩም እህል ሲለምን አላየሁም።  ሁልጊዜ ይራራል ያበድርማል፥ ዘሩም በበረከት ይኖራል» መዝ 3625-26 ታዲያ እኛ እውነተኞች ከሆንን ለምን ስንለምን እንኖራለን?

 ስለ ስደት
«ስለ ሥራህ ሁሉ ክፋት እስክትጠፋ ፈጥነህም እስክታልቅ ድረስ በምትሠራው ሥራ ሁሉ እግዚአብሔር መርገምን ሽሽትን ተግሳጽን ይሰድብሃል» 20
በአሁኑ ዘመን ኢትዮጵያውያን ያልተሰደዱበት አገር አይገኝም፣ በየበርሃው እየተገደሉ የቀሩት፣ በረሃብ መንገድ ላይ የወደቁት ወደ የመን እና ወደ ጣሊያን ሲሰደዱ በባህር ሰጥመው የቀሩት ኢትዮጵያውያን ናቸው።
ስለወባ ስለድርቅ ስለ ዋግ ስለ ክሳት
«እግዚአብሔር በክሳት በንዳድ በጥብሳት በትኩሳትም በድርቅም በዋግም በአረማሞም ይመታሃል» 22 እህሉ አፍርቶ ሊታጨድ ጥቂት ሲቀረው ዋግ ይመታዋልበኢትዮጵያ ያለጊዜው እየዘነመ ያለው ዝናም እህሉን እያራገፈ ዋግም እየመታው መሆኑን ልብ ይበሉ። በጊዜው ሲፈለግ ያልመጣው ዝናም በሰብል ጊዜ የተገኘችውን ፍሬ ለማራገፍ እየዘነመ ነው። ለእግዚአብሔር ብንታዘዝ ሁሉም በሥርዓት ይታዘዝልን ነበር።

  ቃሉ «በሥርዓቴ ብትሄዱ፥ ትእዛዛቴንም ብትጠብቁ ብታደርጉትም፥ ዝናባችሁን በወቅቱ አዘንባለሁ፥ ምድሪቱም እህልዋን ትሰጣለች፥ የሜዳው ዛፎችም ፍሬአቸውን ይሰጣሉ።  የእህሉም ማበራየት በእናንተ ዘንድ እስከ ወይኑ መቍረጥ ይደርሳል፥ የወይኑም መቍረጥ እስከ እህሉ መዝራት ይደርሳል፤ እስክትጠግቡም ድረስ እንጀራችሁን ትበላላችሁ፥ በምድራችሁም ላይ በጸጥታ ትኖራላችሁ።  በምድራችሁም ላይ ሰላምን እሰጣለሁ፥ ማንም ሳያስፈራችሁ ትተኛላችሁ፤ ክፉዎችንም አራዊት ከምድራችሁ አጠፋለሁ፥ ሰይፍም በምድራችሁ ላይ አያልፍም» ይላል ዘሌ 264-6

ሰማይ ዝናብን ምድር እህልን ስለመከልከሏ
«በራስህም ላይ ሰማይ ናስ ይሆንብሃል ከእግርህም በታች ምድሪቱ ብረት ትሆንብሃለች እግዚአብሔር የምድርህን ዝናብ ትቢያና አፈር ያደርጋል እስክትጠፋ ድረስ ከሰማይ ይወርድብሃል» 23
ድርቅ የኢትዮጵያ ዋና መታወቂያ ሆኗል። በደቡብና በሰሜን በድርቅ ተመተናል፤ ሰማይ ናስ ሆኖብናል፣ ድሮ በትንሽ ቁፋሮ ብዙ ምርት የሚያስገኘው መሬት ብረት ሆኖብናል፤ ያለ ማዳበሪያ ከመሬት ብቅ የሚል ቡቃያ ጠፍቷል። መሬቱን ምን ነካው? ጎርፍ ያልበላው መሬት እንኳ ያለማዳበሪያ አላበቅልም ብሏል። እናስ እርግማኑ በኛ ላይ እየተፈጸመ አይደለምን?
ስለ ጦርነትና ለዓለም ነገሥታት ጭንቀት ስለመሆን
«ለምድርም መንግሥታት ሁሉ ድንጋጤ ትሆናለህ፣ ሬሳህ ለሰማይ ወፎች ሁሉ ለምድርም አራዊት መብል ይሆናል» 26
የኢትዮጵያ ታሪክ የጦርነትና የደም መፋሰስ ነው። ይህን ለታሪክ ምሑራን እተወዋለሁ። ዓለም በዲፕሎማሲ እያመነ ሰላምን ባሰፈነበት ዘመን እንኳ እኛ ገና ከጦርነት አላረፍንም ከአሥራ ሰባት ዓመቱ ጦርነት በኋላ በኤርትራና በኢትዮጵያ መካከል በተደረገው ጦርነት ብዙ ትውልዶች ሞተዋል። በዙሪያችን ለጦርነት የሚዘጋጁ በርካታ ግንባሮች አሉ። የጎረቤት ሀገሮችም ጣታቸውን ገና በኢትዮጵያ ላይ እንደቀሰሩ ናቸው። ዓለም ምሥራቅ አፍሪካ የሥጋት ቀጠና እንደሆነ ሁልጊዜ ይናገራል።
ሴቶቻችን ለዓረብ ሕዝብ ስለመሸጣቸው
«ወንዶች ልጆችህና ሴቶች ልጆችህ ለሌላ ሕዝብ ይሰጣሉ ዓይኖችህም ያያሉ ሁልጊዜም ስለነርሱ ሲባክኑ ያልቃሉ» 32
    ሴቶች እሕቶቻችን ስማቸውን አንዳዶች ሃይማኖታቸውን እየቀየሩ ተሽጠዋል። ይህን ሽያጭ የሚያካሂዱት ደግሞ ኢትዮጵያውያን ናቸው። የባሪያ ንግድ ከቆመ ከስንት አመታት በኋላ በኢትዮጵያ ግን አሁንም ንግዱ ትጧጡፏል። መብታቸውን፣ ሃይማኖታቸውን፣ ሕይወታቸውን አጥተው ገንዘብ ለማግኘት እሄዱ ነው። ሄደውም በሕይወት የሚቆዩት እድለኞች ብቻ ናቸው፤ ይህ የኃጢአታችን ፍሬ አይደለምን?
 የዓለም መቀለጃ ምሳሌ እና መተረቻ ስለመሆናችን
«አንተና ባቶችህ ወደ አላወቃችኋቸው ሕዝብ ይወስድሃል በዚያም ሌሎችን የእንጨትና የድንጋይ አማላክት ታመልካለህ እግዚአብሔር በሚያገባህ በአሕዛብ መካከል ሁሉ ድንጋጤ ምሳሌም ተረትም ትሆናለህ» 36-37
የዓለም የእርዳታ ድርጅቶች ሁሉ ልመና የሚያካሂዱት ኢትዮጵያን እንደምሳሌ በመጥቀስ ነው። በተለያዩ ዘርፎች የተቋቋሙ ድርጅቶች ለምሳሌ በረሃብ፣ የኤድስ፣ የሳንባ፣ የወባ፣ ወዘተ ኢትዮጵያን ሳይጠቅሱ አያልፉም። ረሃብ ሲነሳ ለማይገባቸው ለማስረዳት ሲባል የኢትዮጵያውያንን ፎቶ በስክሪን ማሳየት የተለመደ ነው። ይህስ የኃጢአታችን ፍሬ አይደለምን?
 ነጻነትን ስለ ማጣትና ስለ ጠቅላላው የቀንበር አገዛዝ ስለ ድህነት
«ሁሉን አብዝቶ ስለ ሰጠህ አምላክህን እግዚአብሔርን በፍሥሐና በሐሤት አላመለክህምና በራብና በጥማት በዕራቁትነትም ሁሉንም በማጣት እግዚአብሔር ለሚልክብህ ለጠላቶችህ ትገዛለህ፤ እስኪያጠፋህም ድረስ በአንገትህ ላይ የብረት ቀንበር ይጭናል።  እግዚአብሔር ቋንቋቸውን የማታውቀውን፥ ፊታቸው የደነደነውን፥ ሽማግሌውንም የማያፍሩትን፥ ሕፃኑንም የማይምሩትን ሕዝብ ንስር እንደሚበርር ከሩቅ አገር ከምድር ዳር ያመጣብሃል። እስክትጠፋ ድረስ የከብትህን ፍሬ የምድርህንም ፍሬ ይበላሉ፤ እስኪያጠፉህም ድረስ እህልን የወይንም ጠጅ ዘይትንም የላምህንና የበግህን ርቢ አይተዉልህም።  በአገርህ ሁሉ ያሉ፥ ትታመንባቸው የነበሩ፥ የረዘሙ የጸኑም ቅጥሮች እስኪፈርሱ ድረስ፥ በከተሞችህ ደጆች ሁሉ ከብበው ያስጭንቁሃል፤ አምላክህም እግዚአብሔር በሰጠህ ምድር ሁሉ በደጆች ሁሉ ከብበው ያስጨንቁሃል» 47-52

 ደርግ እና ኢሐፓ በኢትዮጵያ የፈጸሙት ጥፋት ዋጋ እያስከፈለን ነው። የገደሉት ሰው ብዛት፣ ያጠፉት የተማረ ኃይል፣ ያስተማሩት የጥላቻ አመለካከት ዛሬ ትውልዱን ችግር ውስጥ ከቶት ይገኛል። ከዚህ የከፋው ኃጢአታቸው ግን እግዚአብሔር የለም በማለት ያወጁት አዋጅ ነው። ከድጡ ወደ ማጡ ማለት እንዲህ ነው። ድሮም ከባዕድ አምልኮ ያልጸዳው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሃይማኖት ወደ ባሰ ችግር ተዘፈቀ። በዚያን ወቅት እግዚአብሔርን መካድ ሥልጣኔ ወይም ሊቅነት እንደነበር እናስታውሳለን። በግብጽ አሥራ ሁለት የመቅሰፍት ዓይነቶች የተላኩት ፈርዖን እግዚአብሔርን አላውቅም በማለቱ እንደነበር የሚረሳ አይደለም።

   ኢሐፓ ሥልጣን ለማግኘት፤ ደርግ ስልጣን ላለመልቀቅ ሲተናነቁ ሁለቱንም እስከ ወዲያኛው አስወግዶ ወያኔን ጣለባቸው። «እስኪያጠፋህም ድረስ የብረት ቀንበር ባንገትህ ላይ ይጭናል» 58 የሚለው የርግማን ቃል ዛሬ ባኛ ላይ ሆኖ እናየዋለን። እግዚአብሔር አሁንም አለ፤ የለም ብለው የካዱት ግን የሉም ካሉም ለምልክት ብቻ ይመስለኛል። ሆኖም የኢትዮጵያን ትውልድ ዋጋ እያስከፈሉት ነው። እስራኤላውያን ወደ ተስፋይቱ ምድር ሳይገቡ አርባ ዓመት ሁሉ በበርሃ የተንከራተቱበት ምክንያት እግዚአብሔርን የካዱ ሰዎች እስኪሞቱ ድረስ እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ይመሰክራል  ዘኍ 3213 እነዚህም ከሐዲዎች ንስሐ እስኪገቡ ወይም እስኪ ሞቱ ድረስ ኢትዮጵያን  ሊያዩ አይችሉም። ንስሐ ቢገቡ ግን ሕያው ሊሆኑ ይችላሉ። ኢሕዴግም እግዚአብሔርን የሚያምን አይመስለኝም። አያመልክምም ሆኖም የሚያምኑትንና የሚያመልኩትን እንደ ደርግና ኢሐፓ ባለመከልከሉ ትንሽ እድሜው ሊረዝም ችሏል። እርሱም ንስሐ ካልገባ አወዳደቁ ከነዚያ ይልቅ እጅግ የከፋ እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለውም።

ስለ ኤድስና በመጽሐፍ ቅዱስ ስላልተገለጠው ወደ ፊት ስለሚመጣ መቅሰፍት

«አምላክህ እግዚአብሔር» የተባለውን የተመሰገነውንና የተፈራውን ስም ባትፈራ፥ እግዚአብሔር መቅሠፍትህን፥ የዘርህንም መቅሠፍት፥ ብዙ ዘመንም የሚኖረውን ታላቅ መቅሠፍት፥ ብዙ ዘመን የሚኖረውንም ክፉ ደዌ ያደርግብሃል። የፈራኸውንም የግብፅ ደዌ ሁሉ እንደ ገና ያመጣብሃል፥ ይጣበቅብህማል። ደግሞም ይህ ሕግ ባለበት መጽሐፍ ውስጥ ያልተጻፈውን ደዌ ሁሉ መቅሠፍትም ሁሉ እስክትጠፋ ድረስ እግዚአብሔር ያመጣብሃል 58-61
 
በሽታዎች ዛሬም እያስጨነቁን ነው
በሽታ የተግሳጽ ምልክት ነው። ኃጢአት እንደ ጽድቅ እየታየ ሲመጣ እግዚአሔር ማዘኑን የሚገልጥበት መንገድ ነው። ቸነፈር የነፋስና የበረዶ የድርቅ፣ የልዩ ልዩ ተፈጥሯዊ ቁጣ መከሰት እግዚአብሔርን እንድናስታውስ የሚያደርግ ነው። ፍጥረትን ተመራምረናል የሚሉ ሰዎች ግን ከእግዚአብሔር ጋር እንዳንታረቅ ልዩ ልዩ ምክንያት እየሰጡ ያዘናጉናል ችግሩ ግን እየባሰ እንጂ እየቀለለ አልመጣም።
 ንስሐ ያስፈልገናል ሁላችንም ለለውጥ እንነሳ። እኛ ለውጥ የምንለው ፓርቲን በፓርቲ መቀየር አይደለም። ወይም ትላልቅ ፎቆችን ድልድዮችንና መንገዶችን እንስራ ማለታችን አይደለም። ወይም የኛን ባሕል በሌላ አዲስ ባሕል፣ የክርስትና ሃይማኖትን በሌላ ሃይማኖት፣ ሥርዓተ አምልኮን በሌላ ሥርዓተ አምልኮ እንለውጥ ማለታችን አይደለም። በጠቅላላው የሰው ወይም የማሽን ለውጥ አልፈለግንም። እነዚህ ሁሉ ከእውነተኛው ለውጥ በኋላ የሚመጡ ቁሳቁስ ናቸው። በአግባቡ ሊጠቅሙን የሚችሉትም ከተለወጥን በኋላ ነው። የሊብያ ረጃጅም ፎቆች ድልድዮችና ልዩ ልዩ ግንባታዎች እንዴት እንደፈረሱ አይታችኋል፤ ከለውጡ በፊት ስለተሰሩ ያልተለወጡ ሰዎች አፈረሷቸው። ፓትርያርክን በፓትርያርክ ለመለወጥ ስንታገል ምን አልባት ሌላ ችግር ጎትተን እንዳናመጣ እፈራለሁ።
  በጌታ ቃል ላይ የተመሠረተ የሕይወት ለውጥ እናምጣ። በስሜት፣ በጫጫታ፣ በጅ ብልጫ፣ በጠብ መንጃ፣ በጩኸት የሚመጣ ለውጥ ለረጅም ጊዜ ሲያከራክረን ሊኖር ይችላል። በአላማ፣ በእውቀት፣ ባማስተዋል የሚመጣ ለውጥ ግን በረከትን፣ ንጽሕናን፣ ፍቅርን፣ አንድነትን፣ ሰላምን፣ ብልጽግናን ያመጣል። በመደማመጥና በማስተዋል ለውጥ እናምጣ፣ ይህን ማስተዋል የሚሰጠን የጌታ ቃል ነው። ንስሐ እንግባ እንደ እግዚአብሔር ቃል፣ እንደ ክርስትና ሐዋርያዊ ሃይማኖት ያለሆኑ ባዕድ አምልኮዎችን እናስወግድ። ያመለካከት ለውጥ እናምጣ፣ እግዚአብሔርን መፍራት፣ ስሙን መቀደስ፣ ይገባናል። በእውነትና በመንፈስ እናምልክው፤ በእርሱ ላይ ተደርቦ ሌላ የሚመሰገንና የሚሰገድለት ሊኖር አይገባም። ወደ ጥንታዊው የሐዋርያት እምነት እንመለስ። እኛ ለውጥ የምንለው ይህንን ነው።

 የፖለቲካ መሪዎችም ምንም እንኳ ብትሰለጥኑም እግዚአብሔርን ንቃችሁ ለውጥ አታመጡም። በጥላቻ እየሄዳችሁ ምን ዓይነት ለውጥ ልታመጡ ነው? ክፉውን አስወግዳችሁ ክፉውን ለመተካት ካልሆነ በስተቀር ምን ልታመጡ ነው? እግዚአብሔርን ሳትፈሩ ኢትዮጵያውያን ልታከብሩ አትችሉም። እግዚአብሔርን የማያምን ሰው ሊታመን አይችልም። የአሜሪካ አባቶች ከዚህ ትልቅ እድገት የደረሱት በመጽሐፍ ቅዱስ እየተመሩ እንደሆነ ታሪክ አንብቢያለሁ፣ የኛ የፖለቲካ መሪዎችም ንስሐ ሊገቡ ይገባል። በጌታ ቃል የተመሠረተ ያስተሳሰብ ለውጥ ለኢትዮጵያ ይበጃል ብለን እናምናለን።    
 የለውጥ ያለህ !!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
 ተስፋ ነኝ

19 comments:

 1. Hi Tesfa we don't need only Neseha but also hard work. Hardwork Pays. Work is one of God's order. Don't expect miracle for the development of Ethiopia. We need to work in a good way. Actually good government for development not Miracle. I know God makes blessings but God Blesses those who work whether they follow him or not as far as they work.

  ReplyDelete
 2. who is more sinner USA or Ethiopia?

  ReplyDelete
 3. ለመሆኑ የችግሩ ፈጣሪ ማን ሆነና ነው? ለመሆኑ አለማችን በአሁኑ ሰዓት በአንድ ሃያል መንግስት ሥር መሆናን ታውቃለህ? የአለማችን ዕድል የሚወሰነው ከጥቂት እራሳቸውን ከቻሉ አገሮች በስተቀር በአብዛኛው እንደኢትዮጵያ ያሉ አገሮች እድል የሚወሰነው በሕዝቦቻቸው ሳይሆን በዚሁ ሃያል መንግስት ነውና "አህያውን ፈርቶ ዳውላውን" ወይንም " አህያ ለበላበት ይጮህል" እንደሚባለው የአባቶች ምሳሌ እንዳይሆንብህ ህዝባችንንም ይሁን አገራችንን አታውግዝ::

  ReplyDelete
 4. Free masons are lucifer worshipers and they are the richest people on earth!! How do you justify it with what you ahve writen here. Try to have broader view

  ReplyDelete
 5. is that your white masters brain wash you? thay teach you good. you belive them alot. poor man.

  ReplyDelete
 6. If you blasphemers have not entered to ethiopia none of the above bad things have arised on this country of saints. You are right in saying the above artice about yourself and your members not about others since you know your sins and bad doings well than any one. You are the one who insult saints and saying the Lord intercessor whuich is out of the bible teachings. You are bringing the beleives of death from abroad and killing our chritians by your false preachings. This all shows that you are responsible foer the out comes of your sins. You write such articles with out considering your share is the lions share of these things.

  ReplyDelete
 7. The only killer in Ethiopia is mk. Preaching bible with out foundation of geta. Mk has served three masters such as poltics, money and zemoot.

  ReplyDelete
 8. በዚህ ጽሑፍህ ተሀድሶ ማለት በተ ክርስቲያን ማደስ ሳይሆን ራስን በንስሐ ማደስ መሆኑን ተናገርክ፤ጥሩ ቆይተህ ካላፈረስከው።ከራስ ነው የሚጀመር ተሀድሶው ተስፋ ልብ ካለህ።ማቅን ከመስደብ ራስን መስደብ ነው ተሀድሶ ንስሐ ማለት።ግን ግን አማሪካ እንዲህ ህብታም የሆነችው የዓለም ፖሊስ እስከ መሆን የደረሰችው በዉኑ ከላይ የዘረዘርካቸው መቅሰፍቶች ያልደረሱባት ከኢትዮጵያዉያን የተሻለ መንፈሳዊ ሕይወት አገልግሎት ስላላት ነው እያልከን ነው?

  ReplyDelete
 9. Tikitim bithonu eko enanite alachihu. Sile Enante bilo lemin Hageritun bebereket almolatim? sile enante silis lemin yikir alalatim? Sile Andi tsadik sil minew almaren??? metsihafu yilal mesilogn new yikirta?

  ReplyDelete
 10. ሠይፈ ገብርኤልJanuary 4, 2012 at 7:59 AM

  ንስሓ በሙሉ ልብ መለወጥና ከጥፋት መመለስ ፣ ባለፈ የተፈጸመውን ስህተት ሙሉ በሙሉ መናዘዝና ማውገዝ ፣ ሁለተኛም ወደ ቀደመው ስህተት ላለመመለስ ለፈጣሪ ቃል መግባት ነው ፡፡ ንስሓ በሥርዓቱ ከልብ ከተፈጸመ ለመዳናችን አስፈላጊ የሆነ የክርስትና እምነታችን የመጀመሪያ እርምጃ ነው ፡፡

  ሁሉም ንስሓ እንዲገባ መንገድ ጠራጊው ዮሐንስ የጀመረውን የቅስቀሳ ትምህርት ፣ ጌታችንና መድኃኒታችን የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስም አጽንቶታል ፡፡ የፈጣሪአችን ትዕዛዝ በመሆኑ ንስሓ አያስፈልግም የሚል አንድም በክርስትና ሃይማኖት እምነቱን ያደረገ ወገን አይኖርም ፡፡

  ከተጻፈው የማልስማማበት መልዕክት የአገራችንን ችግር ከንስሓ ጉድለት ጋር ማቆራኘቱን ነው ፡፡ “እግዚአብሔርንም የሚፈልግ እንዳለ ያይ ዘንድ ፣ እግዚአብሔር ከሰማይ የሰው ልጆችን ተመለከተ ፤ ሁሉ ዐመፁ ፣ በአንድነትም ረከሱ ፣ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም ፣ አንድም ስንኳ የለም” /መዝ 14 ፡ 2 – 3/ ስለሚል ንስሓ የሚያስፈልገው በአጠቃላይ የዚህ ዓለም ዜጋ ለሆነው ሁሉ እንጅ ከዓለም አንድ ከመቶ /1%/ለሆነው ህዝብ ብቻ ተለይቶ አይደለም ፡፡ አምላክም መርጦና ለይቶ ይህን በየዋህነት የሚያመልከውን ወገን እየቀጣና እያሰቃየ ማለት ፣ በእግዚአብሔር ላይ እንዲያኮርፍ ፣ እንዲቀየም ምእመንን የመቀስቀስ ያህል እንደሆነ ነው የምቆጥረው ፡፡ እንዲያውም የሚገርመው በዓለም ዕድገት ውስጥ በቀዳሚነት እየገሰገሱ ፣ በሃብት ላይ ሃብት ፣ በበረከት ላይ በረከትን በመያዝ የተደላደለ ህይወትን ለህዝባቸው እያቋደሱና እየመሩ ያሉትን አገሮች /ቻይና ፣ ህንድ ፣ ሳዑዲ አረቢያ ፣ ኢራቅ ፣ ኩዌት …./ ከተመለከትን የአብ ወልድ መንፈስ ቅዱስን መኖር እንደ እኛ የማያምኑ ሆነው እናገኛቸዋለን ፡፡ ከዚህ በመነሳት ጸሃፊውን የምጠይቀው በእውነት እግዚአብሔር ለይቶ እየቀጣን ይሆን ወይስ ፓለቲከኞች ህዝባቸውን ለማደንዘዝ የሚነዙት አዲስ ቀመር ይሆን ?

  ሠይፈ ገብርኤል

  ReplyDelete
  Replies
  1. እግዚአብሔርን የማያምን/ከላይ የዘረዘርካቸዉ አገሮች/ እና የሚያምን በእግዚአብሔር አይን እኩል አይደለም። እግዚአብሔር የራሱ የሆኑትን፣ ያመኑቱን ግን እንደትእዛዙ የማይገዙትን ብሎም በእኛ ሀገር ትልቁ ችግር በባእድ አምልኮ የተተበተቡትን ይገስጻል ይቀጣል። ካልቀጣ ካልገሰጸ ምኑን አባት ሆነን? ሕዝቡስ ካልተቀጣ የያዘዉ የስህተት ጉዞ ልክ እንደመሰለዉ ወደ ንስህ ሳይመለስ አስቀድሞ ያመለከዉን ጌታዉን እንደካደ ማለፉ አይደለምን? እግዚአብሔር ግን የሚወደዉን የሚቀጣ መልካም እና የፍቅር አባት ነው።

   ተስፋ የጻፈዉን መልእክት በቅንነት ለሚያነበው እና ለተገበረው በእዉነት ዉጤት እንደሚያመጣ ጥርጥር የለዉም። ምክንያቱም እኔ እስከተረዳሁት ድረስ በመጀመሪያ እግዚአብሔርን በይቅርታ/በንስህ/ ታረቁ፣ በእዉነት እሱን ብቻ አምልኩ፣ በፍቅር እና በቅንነት ኑሩ ከዚያ በኋላ በትጋት ስሩ የያዝነዉ ሁሉ ይባረካል ለሌላም እንተርፋለን ነዉ።

   ነገር ግን እንዲሁ ከእዉነት አንጻር ሳይሆን ከራሳችን ሁኔታ፣ ስሜት እና ቡድን ዙሪያ እንደመሰለን ሰንጫጫ ብንኖር ያዉ ያለንበት ሂወት ስለሆነ ለዉጥ አናመጣም። ይልቁንስ እዉነትን በቅንነት እንፈልግ ከላይ የተነገሩንን በንስህ ሆነን በእዉነት እግዚአብሄርን ማምለክ እንለማመድ። በቅዱስ መንፈስ በሆን መለወጥ እንታደስ።

   የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ! ይህ ከስም ሁሉ በላይ የሆነው ስም የተመሰገነ ይሁን!
   እግዚአብሔር የቀደመችዉን የኦርቶዶክስ ተዋህዶን ቤተ ክርስትያን አንድነት ይጠብቅልን!!! አሜን!

   Delete
 11. The Arabs have oil and they r getting richer and richer, is that because they are the Christians you want?

  ReplyDelete
 12. Aye Tehadiso Zare Belestegu Yemitilachew Hageroch Hayimanot Yelelebet Egizabiherin Kidew Seyitan Amilke New Bilew Yemiyaminu Kehige Tefetiro Wuch Wond Ke Wond Set Keset Gar Yerekese Hatiat Yemifestemibet Tininishe Histanat Sayiker Eyetedefru Ende Ensisa Yemitalubet Hager New Yiminayew Seletenu Belöestegu Yemibalut Hagerat Yemitayew Ante Yekoyewun Yetewehedo Eminet Kemitberiz Yet New Yalhut Bileh Temelikt "Nestir Erisike"

  ReplyDelete
 13. ሠይፈ ገብርኤልJanuary 4, 2012 at 10:13 AM

  መደምደምያ
  - በእርግጥ የአምላካችንን በረከት በመፈለግ ሁልጊዜም እንዳይለየን የምንጸልይና ፣ የምንለገሰውም ጸጋና ረድዔት መልካም እንደሆነ ባምንም የዚህን ዓለም ደስታ ፣ ተድላና ብልጽግና ግን የጽድቅና የኩነኔ መለኪያ ፣ የቅዱስነትና የኀጥዕነት መሥፈርት አድርጐ ማየቱ ትልቅ ስህተትና መዘናጋት ይመስለኛል
  - ለአምላክ ባህርይ የተለያየ መልክ ቢሰጠውም ፣ ክርስቲያኖች የምንቀበለው እንደ ጥፋታችን መጠን ባለመቅጣቱ ፣ ቸርና መሃሪ ፣ በፈቃዱም ብቻ የሚያፈቅረን አምላክ መሆኑን ነው ፡፡ በሰቆቃ የሚቀጣ ፣ የሁለትና ሶስት ዓመት ህጻናትንም በረሃብ እየገረፈ የሚገድል አምላክ ለኢትዮጵያውያኖች ብቻ ተመደበ በማለት እንደ ሰነፍም አላምንም ፤ ለሌላው ዓለም ማስተማሪያ ትሆን ዘንድም አገራችን ለፈጣሪ ላቦራቶርነት ተመርጣ ይሆናል በማለት ራሴን አልሸንግለውም ፡፡ ከሃይማኖት ይልቅ ምክንያቶቹ ብዙና ምድራዊ ናቸው ፡፡ ቀደም አንድ ትልቅ የሃይማኖት ጠበብት /ፓስተር/ አገራችንን ጠፍራ ወደ ኋላ ያስቀረቻት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ናት በማለት የተሳሳተ አመለካከታቸውን ለተከታዮቻቸው ሲያስተምሩ አድምጫለሁ ፤ ከዓመታት በኋላ ዛሬም እንደገና ለሃይማኖታችንና ለህዝባችን ተቆርቋሪ ነን በሚሉ ወገኖች በአዙሪት ደግመው ሊነግሩን የፈለጉት ከዚህ በፊት የተባለውን ይዛመዳልና እንጠንቀቅ ፡፡

  ReplyDelete
 14. On top of all pro blames Ethiopians faced in Ethiopia there is always God"s blessing.Although they looks very poor and malnourished,they don't have shoes,good clothes,sponge mattress etc etc they always say TEMESGEN AMLAKE.As the developed and rich countries they don't need any sleeping pills ,drug etc etc to get the basic human need SLEEP.
  Have you ever noticed those kids born in USA go back home for vacation and they want stay longer there.Do you think it is because of he material confer t ?????wrong. It is because GOd sprite is in our beloved country who give as a peace of mind.
  YERASACHENEN BEMANANAK MENEM ANAGEGNEM.FERENGEM MEHON ANCHELEM.SELETANE TERU BEHONEM KELIKE ALFO SEYTAN YEMIMELEKEBETNA GEBRESEDOM BEHEG YETSEDEKEBET ALEM WOUST NEW YALENEW.
  Kehabtena hatiat deheneten sidek yeshalal.

  Just for your INFO when the Italian invaded EThiopia their reason was to free the savage people.Do you really believe this???
  After a century you sound like them.Pray hard.Let God be with you.

  ReplyDelete
 15. All mk elements about 99% from Gojam rural area.

  ReplyDelete
 16. All Mahibere kidusan Gojam & shewa new Bet yemiseraw melkam sira mehonun mawek alebin yesewn sim Matfat yazewetral Ahun Ahun degimo Meshashal alew Aba Selamawochim temesasay tsebay alachihu yesew neger tabezalachihu Menafikinetim tasayalachu Mahibere Kidusan Behayimanot Ayitseretserm dina hunu

  ReplyDelete
 17. ende yehe sewuye min hono naw ere Hay! belut 1 neger lingereh Keristos beberet yewoledal bilo man gemete? beZih mider diha kehonech keDingel MARIAM yewoledal yales man naw? keDihoch gar erat yibelal bilos man gemete?...bicha bizi mider lay simelales keDihoch gar yalwalebet ken yelem...Awo beZih alem statistics Ethiopia diha nat ...esu gin ahunim dihochin yewodal ayizoh diha mehonihen atitelaw esu kedihoch gar naw yalew "Iyesus kirstos tilantinam zarem yaw naw"

  ReplyDelete
 18. እናንተ እንዲህ ብትሉ ምን ይገርማል። ክርስትና ከናንተ በላይ አሳዳጆች አሉባት።

  ReplyDelete