Wednesday, January 4, 2012

አስቸኳዩ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ውሳኔና የደጀ ሰላም ድረ ገጽ ዘገባ አራምባና ቆቦ መሆናቸው ተገለጸ - - - Read PDF

የወሬ ጠኔ ይዞት የሰነበተውና ከውሸት በቀር አንድም እውነት ተናግሮ የማያውቀው ደጀ ሰላም እንደ ለመደው ታኅሣሥ 23 ቀን 2004 . የተደረገውን አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ውሳኔዎችን እርሱ በሚፈለገው መንገድ ዘግቦ አንባብያኑን እያሳሳተና በባዶ ተስፋ እየሞላ መሆኑን ምንጮቻችን ገለጹ፡፡

የወሬ ድረ ገጹ ከዚህ ቀደም በጥቅምቱ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ሲዘግብ የነበረው ሁሉ ማኅበረ ቅዱሳን የሚመኘውን እንጂ ሲኖዶስ የወሰነውን እንዳልሆነ የሚናገሩት ምንጮቻችን፣ በምሳሌነት የሚያነሱት በአባ ሠረቀ እና በማኅበረ ቅዱሳን መካከል ባለው ጉዳይ ላይ ሲኖዶስ የወሰነው ውሳኔና ደጀ ሰላምና ግብረ አበሮቹ ብሎጎች የዘገቡት ፈጽሞ የማይገናኝ መሆኑን ነው፡፡ ሲኖዶሱ የወሰነው በአባ ሠረቀ እና በማኅበረ ቅዱሳን መካከል ያለውን ችግር በተመለከተ አጣሪ ኮሚቴው ያቀረበውን አስተያየት የሊቃውንት ጉባኤ መርምሮ ለግንቦቱ የሲኖዶስ ስበሰባ እንዲያቀርብ ነው እንጂ አባ ሠረቀ የሃይማኖት ችግር አለባቸው የሚል ነጥብ ፈጽሞ አላሰፈረም፡፡ እርሳቸውን የሃይማኖት ችግር አለባቸው ሲል የከሰሰው ማኅበረ ቅዱሳን ለዚያውም በአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አመራር ተብዬዎች ስም መሆኑን በስማቸው የቀረበው የክስ ዶሴ ያስረዳል፡፡ እርግጥ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ ብቻ ሳይሆኑ የማኅበረ ቅዱሳን ግብረበላ የሆኑት አባ ፊልጶስ አባ ሠረቀን የሃይማኖት ችግር አለባቸው ሲሉ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሆነው እንዳይመደቡ ማኅበሩ የሰጣቸውን ተልእኮ መወጣታቸው አይዘነጋም፡፡
ከላይ የተጠቀሰው ዶሴ በአባ ሠረቀ ላይ ያቀረባቸው አራት የክስ ጭብጦች ከሃይማኖት ጋር ፈጽሞ የማይገናኙና ችግሮች ናቸው ከተባሉ እንኳን የሚያያዙት ከአስተዳደራዊ ነገሮች ጋር ነው፡፡ ከሁሉም የሚገርመው ውሸት በ4ኛ ተራ ቁጥር ላይ የተጠቀሰውና መምህር አባ ኀይለሚካኤል ወልደተክለሃይማኖት የተባሉትን አባት በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ውስጥ ሥራ ሰጥተዋቸዋል የሚለው ክስ ነው፡፡ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ውስጥ ሥራ መመደብ የሚችለው አንድ መመሪያ ሳይሆን የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ነው፡፡ አባ ኃይለሚካኤልም የተመደቡት በጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እንጂ በአባ ሠረቀ ሊሆን ፈጽሞ አይችልም፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ግን አባ ሠረቀን የሚከስበት ነጥብ ሲያጣ ይህን መሠረተ ቢስ ነጥብ መክሰሻ አድርጎ አቅርቦታል፤ ለዚያውም የሃይማኖት ችግር ሲል፡፡ እንደ ተባለው እርሳቸው ቅጥር ፈጽመው ቢሆን እንኳ ጉዳዩ አስተዳደራዊ እንጂ ሃይማኖታዊ ሊሆን እንደማይችል መገመት አያዳግትም፡፡ ደግሞም አባ ሠረቀ የሃይማኖት ችግር አለባቸው የሚለው የሲኖዶስ ውሳኔ ቢሆን ኖሮ፣ ውሳኔው በማኅበሩ እጅ መግባቱ ይታወቃልና በጋዜጣውም ሆነ በድረ ገጾቹ ያወጣው ነበር፡፡ ነገር ግን ውሳኔው አስቀድሞ ማኅበሩ ሲያስወራው ከነበረው ጉዳይ ጋር አብሮ ስለማይሄድ ሳያወጣው እንደ ቀረ ለማኅበሩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልጸዋል፡፡

ለአስቸኳዩ የሲኖዶስ ስብሰባ መነሻ የሆነው በደቡብ ክልል በማኅበረ ቅዱሳን አባላትና በኦርቶዶክሳውያን መካከል የተፈጠረውንና መቋጫ ያልተበጀለትን ውዝግብ ተከትሎ ከ15 ሺህ በላይ ካህናትና ምእመናን ፊርማ አሰባስበው ለቤተ ክርስቲያን ሳይሆን ለማኅበረ ቅዱሳን አላማ የቆሙት አባ ገብርኤል ከሀገረ ስብከቱ ይነሡልን ሲሉ ጥያቄ ማቅረባቸውን ተከትሎ ነው፡፡ አባ ገብርኤልም በስብሰባው ላይ “ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር ነው የምሠራው ለማንም ዱርዬ ተሐድሶ ቦታ አልሰጥም” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ ቋሚ ሲኖዶስ ተወያይቶ ለግንቦቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ጉዳዩን አጣርቶና አጥንቶ የሚያቀርብ ኮሚቴ በመሠየም ተጠናቋል፡፡ ይሁን እንጂ ደጀ ሰላም በግማሽ ቀኑ ስብሰባ ይሆናል ተብሎ የማይታስብና ፍጹም ልቦለድ የሆነ ዘገባ አስነብቧል፡፡ እርስ በርሱ የሚጋጭም ሐሳብ አንስቷል፡፡ ለምሳሌ “‹በአስቸኳይ መነጋገር ካለብን መነጋገር ያለብን እርስዎን በተመለከተ ነው፤ ያቀረቡት አጀንዳ ሆነ ተብሎ ግጭት ለመፍጠር የታሰበበት ነው፤ ይህንንም የሚያደርጉት እርስዎ ነዎት፤ ከጀርባውም የተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ አለበት፤ ቤቱም ድጋፍ እየሰጠበት ነው፤ ስለ ወንጌል አገልግሎት፣ ገዳማት ልማት፣ ሰላም እና መልካም አስተዳደር መነጋገር ሲገባን ሁልጊዜ በዚህ መቸገር አለብን? ጥለን ወደ ገዳም እንሂድ እንዴ? ቤተ ክርስቲያን ሁልጊዜ መበጥበጥ ሁልጊዜ መናጥ አይገባትም፤ ነገሩ የሃይማኖትም ጉዳይ ስላለበት ከቤቱ ጀምሮ ተጣርቶ፣ ተለይቶ መወገዝ ያለበት ይወገዝ!!› በማለት በፓትርያርኩ የማያባራ እልክ እና ተንኮል መማረራቸውን በመግለጽ ቁርጥ ማሳሰቢያቸውን አስታውቀዋቸዋል፡፡” ሲል በሲኖዶሱና በአቡነ ጳውሎስ መካከል ጠብ እንደ ነበረ አድርጎ ያቀረበ ሲሆን፣ አስከትሎ ግን በቀረበው አጀንዳ ላይ ቋሚ ሲኖዶሱ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፉን ጽፏል፡፡ ለሚያስተውል አንባቢ ይህ በራሱ ሐሰተኛ ዘገባ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ አባላቱ በአጀንዳው ላይ ደጀሰላም ያሟረተው ሟርት ቢኖር፣ አባላቱ እንዲያ ያለ ጥርጣሬ ካላቸውና እስከ መማረር ከደረሱ ጉዳዩ እንዴት በግማሽ ቀን ተቋጨ? የሚል ጥያቄን ያስነሳል፡፡

ሌላው ውሸትና በአስቸኳዩ የሲኖዶስ ስብሰባ ስም የተላለፈው የማኅበረ ቅዱሳን ሐሣብ እንዲህ ይላል፤ “… የሲዳሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል እንዲነሡ ቀርቧል የተባለው 15,000 ሕዝብ የፊርማ አቤቱታ ከጀርባው የተሐድሶ መናፍቃኑ ቅስቀሳና ሤራ እንዳለበት አስረግጦ የተናገረው ቅዱስ ሲኖዶስ÷ የሚቋቋመው ኮሚቴ ፈርመዋል የተባሉ ግለሰቦችን ሃይማኖታዊ ማንነት ጭምር በሚገባ እንዲያጣራ ነው ያዘዘው፡፡” ሲል ያተተው ደጀ ሰላም ራሱን ትልቅ ትዝብት ላይና ሲኖዶስ የእርሱ ተላላኪ እንደሆነ አስመስሎ ነው ልቦለዱን የተረተው፡፡ ምንም ቢሆን ሁለት የተጣሉ ወገኖችን ጉዳይ የሚመለከት አካል፣ እንዲህ ይላል ተብሎ አይታሰብም፡፡ በማኅበረ ቅዱሳን ወገን ተፈርሞ ገብቷል ባለው የ20,000 ሰው ፊርማ (ልብ በሉ በ5 ሺህ እንበልጣለን ነው ነገሩ) ግን መጣራት የማያስፈልገው የንጹሓን ፊርማ እንደ ሆነ አድርጎ ነው ያቀረበው፡፡ ማኅበሩና ድረ ገጾቹ ዘወትር በደቡብ፣ በምሥራቅና ቤሎችም የአገራችን ክፍሎች ያሉትንና ማኅበሩን በጽኑ እየተቃወሙ ኅብረታቸውን እያጠናከሩ የመጡትን ኦርቶዶክሳውያን አሳንሶ ማየቱና “ተሐድሶ መናፍቃን” እያለ መጥራቱ የተለመደ ቢሆንም፣ ይህ በራሱ እነዚህ ወገኖች ለማኅበሩ የጎን ውጋት ሆነው እንዳስቸገሩት የሚያሳይ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በየጊዜው በተለይ ከደቡብ ክልል ሕዝቡን ወክለውና ብዙ ዋጋ ከፍለው በበርካታ አውቶቡሶች የሚመጡትን የቤተ ክርስቲያን ልጆች ለተመለከተ ሰው ቁጥራቸው ማኅበረ ቅዱሳን ጥቂቶች እያለ እንደሚያሳንሰው አይደለም፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከደቡብ ክልል የማኅበሩ ወኪሎች ነን እያሉ የሚቀርቡት ብዙዎቹ በገንዘብ በተገዙ፣ በተለያየ ኢክርስቲያናዊ ተግባር ላይ በተሰማሩና የቤተ ክርስቲያንን ሀብትና ንብረት በመዘበሩ አንዳንድ የማኅበሩ አባላት አቀነባባሪነት የተደራጁ ክፍሎች መሆናቸውን ከስፍራው ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡ የጠቡ መነሻም የቀድሞው የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል “በስራ ላይ ያሉት የሰበካ ጉባኤ አባላት ከሰባት ዓመት በላይ ያስቆጠሩና በሙስና የተዘፈቁ ስለሆኑ መውረድና ምርጫ መካሄድ አለበት፤ ሂሳቡም ኦዲት መደረግ አለበት” የሚል አቋም መያዛቸውን ተከትሎ፣ በዚህ ጥቅማቸው የተነካ የሰበካ ጉባኤ አባላት የነበሩ የማኅበሩ አባላት አባ ፋኑኤል “ተሐድሶ መናፍቅ” ናቸው ሲሉ ዘመቻ ከከፈቱባቸው በኋላ እንደ ሆነ ይነገራል፡፡ እንደ ምንጮቻችን ከሆነ ብዙዎቹ የሀዋሳ ገብርኤል የሰበካ ጉባኤ አባላት ባለሀብት የሆኑት ከቤተ ክርስቲያን አለአግባብ በዘረፉት ገንዘብ መሆኑ ይነገራል፡፡ ከእነዚህም መካከል፡- ብንያም አድማሱ የብሎኬት ማምረቻ ያለው፣ አዳነ ለማ፣ ግርማ ሞገስ እና ክብረ ወርቁ  የሕንጻ መሣሪያ ያላቸው ሲሆኑ፣ በቤተክርስቲያን ውስጥ ግንባታ የሚካሄድና ዕቃም የሚገዛ ከሆነ እነዚህ ግለሰቦች ያለ ጨረታ ሁሉንም ሥራ እንዲሰሩና ዕቃም እንዲያቀርቡ እንደሚደረግ ብዙዎች ይናገራሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያን የሀብታቸው ምንጭ ስለሆነችም ከእርሷ መራቅ ፈጽሞ አይፈልጉም፡፡ በመሆኑም ሙስናዊ አሰራራቸውን ለመግታት እንቅስቃሴ ሲጀመር፣ ሙስናዊና ኪራይ ሰብሳቢ አሰራራቸውን የተቃወሙትን ሁሉ “ተሐድሶ መናፍቃን” ናቸው በሚል ለጉዳዩ ሃይማኖታዊ ሽፋን ሰጥተው በቤተ ክርስቲያን ገቢ ላይ የተመሰረተው ቢዝነሳቸው እንዳይቋረጥ የሞት ሽረት ትግል እያደረጉ ይገኛል፡፡ ከመካከላቸውም አቶ በጋሻው የተባለው ሰው ከቃለ አዋዲው ደንብ ውጪ የሀዋሳ ገብርኤልና የይርጋለም መድኃኔዓለም በድምሩ የሁለት ሰበካ ጉባኤ አባል መሆኑ ታውቋል፡፡   

ከሁሉም የሚገርመው ደግሞ በሀዋሳ ከተማ ለማኅበሩ ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገ ያለውና አቤቱታ ሲኖር በራሱ ወጪ በገንዘብ የተገዙና በዙሪያው ያሉ ሰዎችን የቤተ ክርስቲያን ልጆች አስመስሎ ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሚልከው ብርሃን ተድላ የተባለው የማኅበረ ቅዱሳን አባል “ዩጎቪያ” የተባለ የራቁት ዳንስ ቤት ከፍቶ ለብዙ ወጣቶች ሕይወት መበላሸት ምክንያት ሆኗል፡፡ ወደ ሀዋሳ ለሚሄድ ሰው ዩጎቪያ ጭፈራ ቤት እንዳትሄድ ተብሎ ምክር እንደሚሰጥ ምንጮቻን የገለጹ ሲሆን፣ ይህም የጭፈራና የራቁት ዳንስ ቤትን አደገኛነት የሚያሳይ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡ ይህ ሰው ከማኅበረ ቅዱሳን ጎን የተሰለፈውና ማኅበረ ቅዱሳን የሚቃወማቸውን የቤተ ክርስቲያን ልጆች የሚያሳድደው፣ በኀጢአት ሥራ የሚሰበስበው ትርፍ እንዳይቀርበት በመስጋት እንደ ሆነ ምንጮቻችን ጥርጣሬያቸውን ይገልጻሉ፡፡ ማኅበሩም ቦታ የሌለው ወንጌል ለሚሰብኩ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች እንጂ በተለያየ የአመጽ ስራ ላይ ለተሰማሩ ክፍሎች ግን መሸሸጊያ መሆኑን ከዚህ መረዳት ይቻላል፡፡ ሰውዬው ከማኅበሩ ጎን ተሰልፎ የቤተ ክርስቲያንን ልጆች የሚቃወመው እነዚህ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ወንጌል ይሰበክ የሚል አቋም ስላላቸው ወንጌል ከተሰበከ ሰውዬው መተዳደሪያ የሚያጣ መስሎ ስለሚሰማው ነው ይላሉ ምንጮቻችን፡፡ ከወንጌል ጋር መጣላቱና በተረት መተብተቡ፣ በሃይማኖት ሽፋን ፖለቲካና ንግድ ማጧጧፉ፣ ሌሎችንም ምድራዊ አጀንዳዎችን ለመፈጸም መሯሯጡ ማኅበረ ቅዱሳን በጨለማ ስራ እንዲወረስ ከማድረግ ውጪ ምንም እንዳልጠቀመው ብዙዎች ይናገራሉ፡፡
    
ሌላው በአስቸኳዩ የሲኖዶስ ስብሰባ ላይ የተነሳውና ማኅበሩ ሌላ መልክ የሰጠው ጉዳይ፣ በአሁኑ ጊዜ የአክሱም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ሰላማ ራሳቸውን “ሊቀጳጳስ ዘአክሱም” እያሉ መጥራታቸውንና በሶስት የተለያዩ ማህተሞችና ቲተሮች መጠቀማቸውን በመቃወም የአክሱም ጽዮን ገዳም ካህናትና ምእመናን ያቀረቡት አቤቱታ ነው፡፡ በአቤቱታው የገዳሙ ካህናትና ምእመናን እንዳመለከቱት በትውፊቱ መሰረት የርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ማርያም ሊቀ ጳጳስ ፓትርያርኩ እንጂ ሌላ ጳጳስ ሊሆን አይችልም የሚል ነው፡፡ አባ ሰላማም የአክሱም ሀገረ ስብከት እንጂ የርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ሊቀ ጳጳስ አይደሉም ነው ሙግቱ፡፡

በርግጥም የመጀመሪያው ጳጳስ አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን መንበረ ጵጵስናውን የተከለው በአክሱም በመሆኑ፣ አክሱም ጽዮን ማርያም በኢትዮጵያ የክርስትና መዲና ናት፡፡ ከክርስትና አንጻርም ርእሰ ሀገር ተደርጋ ነው የምትወሰደው፡፡ የመጀመሪያው የግብጽ ፓትርያርክ ማርቆስ መንበረ ጵጵስናውን በእስክንድርያ ስለ ተከለ ለግብጾች ርእሰ ሀገር እስክንድርያ እንደ ሆነች ሁሉ፣ ለእኛም አክሱም ናት፡፡ በቅዳሴ ላይ “ወዲበ ርእሰ ሀገረ አበዊነ” የሚለው የሚጠቁመውም አክሱምን ነው (የኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት ገጽ 219)፡፡ ርእሰ ሀገር የተባለችው አክሱም፣ ርእሰ አድባራት ወገዳማት መባሏም በኢትዮጵያ ላሉ አድባራትና ገዳማት ርእስ ወይም እናት ተደርጋ ስለምትወሰድ ነው፡፡ ስለዚህ “ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም” የሚለው ማዕርግ የፓትርያርኩ ነው፤ እንዲሁም የርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ሊቀጳጳስም ፓርያርኩ ናቸው፡፡

“ሊቀጳጳስ ዘአክሱም” እና “ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት” የሚሉትን ማዕርጋት በትውፊት ላይ ተመስርቶ ለፓትርያርኩ የሰጠው ቅዱስ ሲኖዶስ መሆኑ ሲታወቅ፣ የማኅበረ ቅዱሳን ልሳን የሆነው ደጀሰላም ግን ይህን እውነት በማስተባበል፣ የኖረውን ትውፊታዊ አሰራር ለጊዜያዊና በውሸት ላይ ለተመሰረተ የወሬ ፍጆታው ሲል ሽምጥጥ አድርጎ ክዷል፡፡ እስከ ዛሬ የወሸት ወሬ ሲቀልባቸው የኖሩ አንባቢዎቹንም አሳስቷል፡፡

ደጀ ሰላም፣ አቤቱታውን ያቀረቡት የርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ማርያም ካህናትና ምእመናን መሆናቸውን ፈጽሞ ካለመጥቀሱም በላይ፣ አባ ሰላማ በሶስት ማህተም መጠቀማቸውንና ራሳቸውን ከሕግ ውጪ “ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም” እያሉ መጥራታቸውን ቅዱስ ሲኖዶስ እንዲያስተካከል፣ ካልሆነ ግን ጉዳዩን ወደ መንግሥት ለመውሰድ እንደሚገደዱ ማመልከታቸውንም ፈጽሞ አላወሳም፡፡ ይህም ዘገባ ደጀሰላም አንድን ጉዳይ ገልብጦና ዘቅዝቆ ከማንበብና ከመረዳት ልምዱ የሚከተለው የአዘጋገብ ስልቱ መሆኑን የሚጠቁም ነው፡፡ የአክሱምን ጉዳይ እንዳይቀበልና ያደረገውና አንባቢዎቹን ያሳሳተውም ፖለቲካዊ ማንነቱ ስለማይፈቅድለት መሆኑን አንዳንዶች ይናገራሉ፡፡

የአሁኑ የአክሱም ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ አባ ሰላማ ራሳቸውን ከሕገ ቤተክርስቲያን ውጪ “ሊቀጳጳስ ዘአክሱም” ብለው ለመጥራት የደፈሩት፣ ምናልባት የተሰጣቸው ስመ ጵጵስና ከመጀመሪያው የኢትዮጵያ ጳጳስ ከአባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ጋር ሞክሼ ስለሆነ፣ ያን ተተግነው የፓትርያርኩን ማዕርግ ለራሳቸው ለመውሰድ በማሰብ ይሆናል የሚል ግምት በብዙዎች ዘንድ አሳድሯል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ በዚህ አጀንዳ ላይ ከተነጋገረ በኋላ አባ ሰላማ በሶስት ማህተም መጠቀማቸውንና ራሳቸውን ከሕገ ቤተ ክርስቲያን ውጪ “ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም” ብለው መጥራታቸውን በተመለከተ ጉዳዩን የሚያጣራ ኮሚቴ መሠየሙን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ደጀ ሰላም ግን አሁንም ስለዚህ ጉዳይ ያለው አንዳችም ነገር የለም፡፡ የስብሰባው ትክክለኛ ገጽታ ይህ ሆኖ ሳለ፣ ድረገጹ ግን አጀንዳውን የአባ ሰላማና የፓትርያርኩ ጠብ አስመስሎ ማቅረቡና በደጋሚነት የታወቁትንና የኖረውን ትውፊት በመጣስ የተከሰሱትን አባ ሰላማን “በጸሎታቸውና ፍጹም መንፈሳዊነታቸው የሚታወቁት” ሲል ማሞካሸቱ፣ ለእርሱ መንፈሳዊነት ማለት ምን ማለት መሆኑን ያሳየበት አጋጣሚ ሆኖ አልፏል፡፡

26 comments:

 1. Aba Selam Betsam lamesegnachihu ewedalehu Zewtir Deje Selam ( Mahibere Kidusan )sewn behaset siyasadidi-siyaward-yehset sim eyesetse -sikesi zemariwn- sebakiwin-kahinun Papasun melkam yehonewin hulu siyasadidi nore Ahun gin ewinetun ewnet hasetun haset yemil Aba Selam tenesa temesgen
  bertu Ahunim Yede jeselamin yehaset wer beyegizew teketatelu yihinn asteyayeten be amarga nibab giletsulachew

  ReplyDelete
 2. we need concise and clear information just like this. Great job abaslama!

  ReplyDelete
 3. በዚህ ጽሁፍ ላይ ለመሆኑ

  ተብሎ መጻፉ የትኛው ፓትርያርክ ነው ከአራቱ ውስጥ ይህን ቅጥልጥል የተጠቀመው። ደግሞስ አቡነ ሰላማን ለመተቸት መድፈራችሁ የሚገርም ነው። እስከአሁን ማህበረቅዱሳንን ስትተቹ እንደው ምክንያት ይኖራችኃል ብዮ ነበረ። አሁን ግን የአቡነ ፋኑኤልን የጥፋት ተልዕኮ ስተደግፉ በአባትነታቸው በሄዱበት ቦታ ሁሉ የሚወደዱትን አባት አቡነ ሰላማን ለመተቸት መነሳታችሁ ሥራችሁ ግብራችሁን ይናገራል። ለቦና ይሰጣችሁ።

  ReplyDelete
 4. ሠይፈ ገብርኤልJanuary 4, 2012 at 4:29 PM

  “አስቀድመን የራሳችንን ሥራ እንመርምር”

  የክርስትና ሃይማኖትን ከሌሎች የእምነት ዓይነቶች የምንለይበት ትልቅ መመዘኛ ፣ አስተምህሮው በነጻነትና በፈቃድ ላይ ብቻ የተመሠረተ እምነት መሆኑ ነው ፡፡ ክርስትናን በስሜት ተነድተን በማስገደድ በሌሎች ላይ በግድ የምንጭነው ፣ በአእምሮአቸውም የምንደፈድፈው ወይም ጀሃድ አውጀን በመማረክ ሰዎችን በኃይል የምናሳምንና የምንለውጥበት ሃይማኖት አይደለም ፡፡

  ኢየሱስም ክርስትና የነጻ ፈቃድ እምነት እንጅ የጦርነት አለመሆኑን በተግባር ሲያስረዳን ፣ በመጨረሻው ሰዓት ሊይዙት የመጡትን ተቀናቃኞች ፣ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ በያዘው ሰይፍ የሊቀ ካህናቱን ባሪያ ጆሮ ሲበጥስ የተናገረው ፣ ሰይፍ የሚያነሡ ሁሉ በሰይፍ ይጠፋሉና ሰይፍህን ወደ ስፍራው መልስ ፤ አባቴን ብለምነው አሁን ከአሥራ ሁለት ጭፍሮች የሚበዙ መላእክት እንዲሰድልኝ የማይቻል ይመስልሃልን? በማለት ነው /ማቴ 27 ፡ 51– 53/ ፡፡

  አሁን አሁን የድኀነታችን መለያ የኤኮኖሚው ብቻ መሆኑ ቀርቶ በሃይማኖታችንም ምናምንቴዎች ሊያደርጉን እየተጋፉንና እየታገሉን የመጡ ይመስላል ፡፡ እንደ ባህልና ወጋችን ታላቅ ታናሹን የማይሰማበት ፣ መሃይሙ ሊቁን ፣ እንደ ክርስቲያንም በሥርዓት ልጅ አባቱን ማድመጥና ሃሳብን ከሃሳብ እያስማማ መመካከር ቀርቶ በዘለፋና በነቀፋ ለመማማር የተነሳን ይመስል ፣ በአግባቡ ከማስረዳትና ጭብጥን ከመግለጽ ይልቅ አጓጉል ለአእምሮ የሚከብዱ ቃላትን መጠቀሙ ይቀለናል ፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ስድብ ውጉዝ እንደሆነ ፣ ለፍርድና ቅጣትም እንደሚዳርግ ሲያስተምር “እኔ ግን እላችኋለሁ ካለ በኋላ የሚደርሱትን የፍርድ ዓይነቶች ሲዘረዝራቸው
  - በወንድሙ ሊይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል ፤
  - ወንድሙንም ጨርቃም የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል ፤
  - ደንቆሮ የሚለውም ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይገባዋል /ማቴ 5 ፡ 22/ ይላልና እርስ በርሳችን ከመነቃቀፍ እንታቀብ ። አንተ ምን እያደረግህ ነው እንዳትሉኝ ብቻ


  መጽሐፍ ቅዱስ እጅግ በጣም ጥልቅና ሰፊ ስለሆነ ለመረዳት አስቀድሞ እምነትን ፣ በመቀጠልም ትዕግስትንና ጠለቅ ያለ በዕውቀት መመርመርን የሚሻ በመሆኑ ፣ እግዚአብሔር ካልገለጸልን ፣ በመጀመሪያዎቹ ሐዋርያትም የተገለጸውንና ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውን ትምህርት ተመርኩዘን ካልተረጐምነው በስተቀር ፣ ልንሳሳትበትና ወዳልጠበቅነው ትምህርት ልናመራበት ፤ የተለያየ ትርጉም በመስጠትም ወደ ተለየ እምነት ልንገባበት የምንችል መጽሐፍ ነው ፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ አተረጓጐም ላይ ልዩነትን ፈጥረው የሚከራከሩት ደግሞ አማኝ ክርስቲያኖች /ኦርቶዶክስ ፣ ካቶሊክና ኘሮቴስታንት/ ብቻ ሳይሆኑ የእስልምና እምነትም የሚስማማውን ኃይለ ቃል በመውሰድ ከትግሉ ሜዳ ለመዳበል ይሞክራል ፡፡ ዲያቢሎስም እንኳን ለራሱ አተረጓጐም የሚመቸውንና የሚያሳስትበትን እየመረጠ ባይገባውም /ሥልጣኑ ባይሆንም ማለት/ ከኢየሱስ ጋር እንደተገዳደረበት እናስተውል ፡፡

  “ክርስቶስ አይደለም ብሎ ኢየሱስን ከሚክድ በቀር ውሸተኛ ማን ነው ? አብንና ወልድን የሚክድ ይህ የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው ፡፡ ወልድን የሚክድ ሁሉ አብ እንኳ የለውም ፤ በወልድ የሚታመን አብ ደግሞ አለው” /1 ዮሐ 2 ፡ 22 - 23/ ስለሚል ክርክራችን ከማን መሆን እንዳለበት መጽሐፍ ይነግረናልና ሥራችንን በጥሞናና በዕርጋታ እንመርምረው ፡፡

  ምዕራባውያን ክርስትናውን የተቀበሉት ከእኛ እጅግ ዘግይተው ቢሆንም ፣ አሁኑ ባሉበት ደረጃና ይዘት ግን ክርስትናን በማስተማር ሥልታቸው ብዙ ልንቀስመው የሚገባ ልምድ አዳብረዋል ፡፡ በየምኩራባቸው ሲሰባሰቡ ሊያስረዱና ሊያስተላልፉ የሚፍጨረጨሩት ፣ ለማስተማር የተዘጋጁበትን የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ነው እንጅ ፣ በሰይጣናዊ አምልኮ ራሳቸውን የተደራጁትን ስብስቦች እንኳን ስለሚሰጡት አምልኮና ትምህርት ጣልቃ አይገቡባቸውም ፡፡ ወደ በረታቸው የገባው መንጋ ተመልሶ እንዳይወጣና እንዳይጠፋባቸው ማስተላለፍ በሚገባቸው ላይ ብቻ ይተጋሉ ፤ እኛ ግን ከአስተዳደግ ጉድለት ይሁን ከሌላ አይታወቅም ፣ በንጽህና የምናምንበትን የራሳችንን ትምህርት ከማስተማር ይልቅ ስለሌላው ስህተትና ጐደሎነት በመጨነቅ መተንተኑ ይቀለናል ፡፡ በራሳችን ቤት ስለተጋገረው ዳቦ ከመናገር ይልቅ ጐረቤት ስለታረደው በግና ዶሮ የመቸገር ልማድ ያለን ይመስላልና ራሳችንን እንታዘበው ፡፡
  ይቀጥላል

  ReplyDelete
 5. ሠይፈ ገብርኤልJanuary 4, 2012 at 4:30 PM

  ስለኦርቶዶክስ ሃይማኖት ሊቃውንቱ የራሳቸውን ትምህርት እየተረጐሙና ከመጽሐፍ እየጠቀሱ በስፋት ቢያስተምሩ ፣ ኘሮቴስታንቱም የሚከተለውን ቢያስረዳ ፣ ካቶሊኩም እንዲሁ ቢያደርግ ፣ ሁሉንም በጥሞና የሚያነብና የሚያዳምጥ ምእመን ፣ የእምነት ልዩነታቸውን በመረዳት የማነጻጸርና የመረዳት አቅም ያዳብራል ፡፡ አንደኛው ከሌላው በእምነት የሚለይበትን መሠረታዊ ልዩነት በአግባቡ ግልጽ እያደረግን ሌሎችን ማስተማርና ማስረዳት ካልቻልን ፣ ግብራችን መግለጽ ሳይሆን ማደናቆር ፣ መንጋውንም በሆነ ባልሆነው በማሳሳት መረበሽ ነው የሚሆነው ፡፡ በእስከ አሁን አካሄዳችን ለክርስትናው እምነት መጐልበትና ማደግ እያደረግን ያለውን አስተዋጽዖ ብንመለከተው መልካም ይሆናል ፤ ጊዜው ገና አልሞተምና ራሳችንን ለማረምና ለማስተካከል እናስተውል ፡፡

  በተረፈ በአገራችን ከኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ትምህርት በተቃራኒ እግዚአብሔር አይወልድም ፣ አይወለድም ፤ ኢየሱስ አምላክ አይደለም ፣ አልሞተም ፣ አልተነሳም በማለት በአደባባይ በሚያስተምረው ትምህርተ ሃይማኖት ሳንረበሽ ፣ ከድንግል ማርያም ያለ አባት ተወለደ ፣ ያለ ኃጢአቱ ለኛ ሲል በመስቀል ላይ ሞተ ፣ በሶስተኛው ቀንም ከሙታን መሃል ተነሳ ፣ አረገ ፣ በአባቱ ቀኝም ተቀመጠ ፣ በመጨረሻም በሁሉም ስለሁሉም ሊፈርድ ዳግም ይመጣል ብላ የምታስተምረዋን የሚዘመትባትና የጦር አውድማ ታሪክ የሚነገርባት ስለምን ምክንያት እንደሆነ ቢታወቅ ለሁላችንም መልካም ዕውቀት ይሆናልና የሚያስረዳ አዋቂ ከተገኘ መልሱን ወዲህ ይበል ፡፡ ለዚህኛው በቂ ምክንያት የማናገኝና የምንቃወመውን የማናውቅ ከሆነ ግን ፣ ችግሩ ሃይማኖትን ሽፋን ያደረገ የጥቅም ግጭት ፣ የስግብግብነትና የሆዳምነት ፣ የእኔ እበልጥ ችግር ስለሚባል ከመሰዳደብ ፣ ከመተቻቸትና ከመወቃቀስ ይልቅ አንድነታችንንና ልዩነታችንን አጥርተን የምናምንበትን በእርጋታ እናስተምር ፡፡ አሉባልታውንም ከምታስተላልፉልን እስቲ በየሰንበቱ እንደ ስማችሁ የሰላም አባት እንድትባሉ ዕርቅ የሚፈጥረውን ከወንጌል አንዳንድ ምዕራፍ እንኳን እየተከፋፈላችሁ አስተምሩና ለውጥ በማምጣት ምሳሌ ለመሆን ሞክሩ ፡፡ የሁላችሁም ሥራ ሥጋዊ እየመሰለ መጥቷልና ፡፡

  “እንግዲህ
  - ክፋትን ሁሉ
  - ተንኰልንም ሁሉ
  - ግብዝነትንም
  - ቅንዓትንም
  - ሐሜትንም ሁሉ አስወግዳችሁ ፣ ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እንደ ሆነ ፣ ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ ተንኰል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ” ፡፡ 1 ጴጥ 2 ፡ 1
  “ሁላችሁ
  - በአንድ ልብ ሁኑ ፣
  - የሌላው መከራ ለእናንተ እንደሚሆን አድርጉ ፣
  - እንደ ወንድሞች ተዋደዱ ፣
  - ርኀሩኆችና ትሑታን ሁኑ” 1 ጴጥ 3 ፡ 8

  በመነቃቀፍ ፈንታ ሃሳባችንንና ችሎታችንን ሁሉ ኢየሱስን ለማወቅ ፣ ለማመስገን ፣ ለማወደስና ለመቀደስ ብናውለው ሌሎችንም ወደ ፍቅሩ ማዕበል ልናስገባ እንችላለንና ድክመትን እንድንፈጽም የሚገፋፋንን ክፉ መንፈስ እየጐሰምን እንስተካከል ፡፡
  “መልካሙን ሥራችሁን አይተው ፣ በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ፣ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ”። ማቴ 5 ፡ 16

  መንፈሳዊ ሰላምን ለሁላችሁም እመኛለሁ

  ReplyDelete
 6. እግዚአብሔር ቃለ ሕይወት ያሰመማችሁ !!! ይህን ሐሰተኛ ነፍሰ ገዳይ ከንቱ ማኅበር ራቁቱን አውጡት ማንነቱ እነዲህ ይታወቅ እንጂ የተለያዩ መረጃዎች ስላሉ ለመላክ እሞክራለሁ በነገር ሁሉ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን ወንድማችሁ ሰይፉ ከአሜሪካ

  ReplyDelete
 7. እውቱን ስለገለጣችሁልን እግዚአብሔር ጥበቡን ይግለጽላችሁ ማኅበረ ሰይጣን (ማቅ) ዐዓላማውና ምኞቱ እውቱን በውሸት ለውጦ መናገር ልማዱነውና በዚህ አትገረሙ!

  ReplyDelete
 8. It is well known that MK has its own adgenda on this church as well as nation. What is important here will be to reveal their satanic mission.

  ReplyDelete
 9. sorry for those the so called '' aba selam'' why you always mislead people. we are from dilla. was the former sebeka leading 7 year at sebeka gubae? any body can come and check when that sebeka gubae was selected. please readers you can check how the new sebeka selected by kids when the matured people angrly leave the church. why you lie. if you want to check, check the present secretary of the sebeka where abouts. which was not known. you wrote about bishop of axum about you donot know. I can give my witness about his pray. I saw how the devil shout when this father come before he become bishop. I know him closly because he was where my relatives live. so I got the chance to see him before. SORRY ABA SELAM DUE TO THIS FACTS I AM IN DOUBT TO ACCEPT WHAT YOU WROTE.

  ReplyDelete
 10. So your political identity accept st Mary today?

  ReplyDelete
 11. Mk never wrote truth only alegation,attack and plan to kill. Your poltical agenda will be explode in southern Ethiopia by using of aba Geberiel or gebril to start arab style uprising, but Ethiopian now never say yes for GOjame that was enough in the past aba Paulos is the best leader he is fare for all not GOJAME.

  ReplyDelete
 12. "የሰነበተውና ከውሸት በቀር አንድም እውነት ተናግሮ የማያውቀው ደጀ ሰላም"

  አንድን ሰው ወይም ጽሁፍ እንዲህ በደፈናው መኮነን
  የኢትዮጵያውያን ባህል ነው ወይስ አለመማር

  ውሸት ተናግረሃል ማለትና ውነት ተናግረህ አታውቅም ማለት
  እንደ ሰማይና መሬት የተራራቁ ናቸው

  እረ እንማር
  ጥላቻ የተሞላበት ሂስ ትምህርት አይገኝበትም

  ReplyDelete
 13. aba selamawech min new lekonjo metsyet mels mestet tesanachu esa

  ReplyDelete
 14. WAS THE ASCHEQUAY SIBSBA SUCCESSFUL AND GONE AS NEEDED BY THE PATRIARCH?
  Tell me why the meeting was called and perished with out strong decision?

  ReplyDelete
 15. Aba abraham and aba gebril are floop side of coin. They are hunger in power using mk to take patriarc position from aba pulos. On the contary, those elemdnts aba abrha and aba gebril have children with out marrige. As this result the church boss will be fire them from any eotc service.

  ReplyDelete
 16. Kesis Teshome Yohans wndime hoy tsekam mikir lemestset efelgalehu Addis Abeba Lay simihi sinesa semche Azenku Abune Fanueiln Tekawam Abune Abirhamin Degaf hono Adima kesekese tebilo
  wondime Aznalehu hager bet eyalehi Abune Abirhamin Bemimeleket Yenegerkegina yawerahilg kefelekew kasitu aleg lemehonu Abune Fanueil& Abune Abirham min And Aderegachew Abune Abirham Zerga -Gosega -Adimega-Genzeb Bekag Yemayilu Beteley Yenegerkeg kebadi Mistsir yalebachew Zare America Sitders telewtsew -bektew Agegehachew Yasazinal Abune Fanueil yemtawekut diha tebedele -fird tegadele -sewn yale masrega atfiredubet bemalet new Abune Pawlos sinodosun sibetsebtsu Balcha Hosptal Gebtew Ke anget Belay yimermeru yalu tsekara Abat nachew tarkachewin -dignetachewin -kinnetachewn lemawek kefelk Addis Abeba teweldew yadegubet sefer Gotera Akababi metseyek tichilali
  Kesis Teshome Yohans Diredew- Gola-Amanueil-Kara Kore Megenaga-yeserahiwin medhane alem Sebaki honeh betekerayehew bet yaderkewn kebad neger lelochinim hulu tawkaleh ahun rasin sayayu Kidus Sinodos Yemedebewin Papas Mekawemina Adima Mekeskes yigebal sew Amerca Gebto temiro yilewetal- nurowin yashasilal- fimiyun yiredal
  Kesis Teshome Yohans gidihin Awtsana Gudif lemayet tezegag ya kealhone berkata neger timezalehi negeroch yibelashubhal Abune Abirhamn Mewded lela neger new Abune Fanueiln Mekawemim degimo lala neger new
  Kesis ene Yesemahut Mahibere kidusan offis legubae hej new Mahibere Kidusan Balhonim Degafi sew neg Mahibere Kidusan Melkam yehone sira alew Masadedi- Sim Matsifat-yalhonewin hone malet yabezal- bichal Abalatu Kezihi aynet sedibo lesedabi kemestset Endikotsebu memiker Kaltechale rasin madan bilhinet new
  Ahun Abune Pawlos Yeserutn hulu tawkalehi bekefetut kolj lememar gebtehal beye churchu yalewn meshashal tawkalehi Kidus Kidus Kidus bemalet yenork sew neh Gin Ahun yematawkachew lememsel mokrehal tew Dr Mesifi- Birhanu Gobena- Ergete Kal -Efirem Eshet Hulum yemahiberu Abalat nachew betsam yemgermew D Erget Kal meche new yetemezegebewna Kahin yehonew yihininim semahu yigermal
  hulunim neger zerzire -kasetunim Negrochin hulu endilikileh kefelk Addrsha
  Kenu Derese
  Pox 8645
  Addis Abeba Ethiopia new tsiyake kealehi Mulu Addshahin lakilig be aschekay elkilhalehu engidih yemayigeba neger tenagire askeficheh kehone yikirta Adirgilg memekaker sile Alebin new Abiren norenal- Abiren sertenal Abiren Atsiftenal-Ahun sitgoda zim malet yelebgim besefiw yetenesaw ye ante sim new Amerca yegebahew bekirb ken new le berkata Amtetat yekoyut Abatoch benegeroch yelum Minew?
  Aba Selamawoch Yihinin Asteyayetenina Mikiren be ethiopia fidel ( Amarga ) Enditlewtulig Bedingil Maryam sim eleminalehu mechem yemtaminu atimesilum sayachihu Amesegnalehu

  ReplyDelete
 17. ዬሄ ደጀ ሰላም የሚባለው ብሎግ፣ ለመሆኑ ጤናና ዕውቀት አለው? አሁን አሁንስ ከልብ እየገረመኝ መጥቷል። አረ እንዲያው በእውነቱ ምን እንበለው? ዘመድኩንን አይዞህ እያሉ ቆይተው እንዴት ዕርቃነ ስጋውንና ነፍሱን እንዳስወጡት እስኪ ከብሎጋቸው ተመልከቱት።ወይግርምምምምምምምምምምም!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 18. who is LEKE (TELEKE) TEBOT HARGEWOIN?

  ReplyDelete
 19. አባ ሰላማ ጸሎተኛ ናቸው የሚል መንፈሳዊ አይኑ ያልበራለት የማቅ ወገን ነው፡፡ እርሳቸው አጥማቂ መሆናቸውን አውቃለሁ፡፡ ለሰዎች እንደሚጠነቁሉም ግልጽ ነው፤ ለአንዳንድ በሽተኛዎች ይህን እንጨት ይዘሽ ይህን መፅሐፍ ድገሚ ብለው ተረታተረቱን ያስደግማሉ ታዲያ እሳቸው ደጋሚ ናቸው መባሉ ምን ስህተት አለው፡፡ እኔ ግን ደጋሚ ብቻ ሳይሆኑ ጠንቋይም ናቸው ቢባል ያስኬዳል፡፡ ስለዚህ ማቆች ሰውን ከማምለክ ውጡ፡፡

  ReplyDelete
 20. Amlak bemdr lalu wogenochih aynelibonachewn abralachew, mastewalinm adlachew!

  ReplyDelete
 21. simplyyyyyyyyyyyyyyyyy"tasaznalachihu"! binegruachu atisemu.bekirstos sim linegrachihu yemfelgew neger yehone and nigs lay hulum neger alko bemecheresha yehageresibketachin likepapas betselot lizegu simokru yetewosenu wegenoch mezmure iyezemeru neber .akumu sibalu liakomu alfelegum .papasu binagerum alakom alu.yih yehonew be2004 meskel lay chimr mehonun astaweshe "min aynet sewoch?" nachew biye siteyk "tehadiso" nachew alugn.yasaznal lepapas alemetazez yemeskel beal lay "man kere kemeda",yalante geta"......iyalu hizbu gar abrew yemayzemru sewoch yetedebeke alama indalachew seamahu.bizu teyekhu .kewebsiteachew wust andu aba selama mehonun sisema azenhu.lebalefut 2 months abaselama yemibal site alkefetum neber.zare sikefit yihen agegnehu.ahunm tasaznalachiu!!!!!!

  ReplyDelete
 22. የወሬ ጠኔ ይዞት የሰነበተውና ከውሸት በቀር አንድም እውነት ተናግሮ የማያውቀው ደጀ ሰላም እንደ ለመደው
  hey If you are Christians you won't start your news by this kind of Devilish word anyways you all are CURSED and YESEYTAM ALEKOCH NACHIHU FETARI MENGEDUN YASAYACHIHU

  ReplyDelete
 23. U just cry your dirty sin instead to blame others aba selama web it is best for this generation to learn bible rather than the teret game of gojam debetera that hide him self in mk.

  ReplyDelete
 24. አይ ኢትዮጵያ የቀደሙት ልጆችሽ ወዴት ሄዱ(አጽማቸው እንኳ -----------------
  ኦ አምላከ አበዊነ አምላከ አብርሃም ወይስሐቅ ---እቀባ ወአድኅና ለሀገሪትነ ኢትዮጵያ እምኩሉ መንሱት ዘመጽአ ባቲ እምነ ውሉዳ
  እምትካት ሀገሪትነ ሀገረ +++ ናሁሰ ሀገረ ---
  ዘቦ እዝን ሰሚዐ ለይስማዕ

  ReplyDelete
 25. hulacenm yehawassa ezboch endmenawokew abune fanuel ejig betam tikit sewoch tekawemugn belwo bota lekewal ato gadafi gin behayil kalhone mulu yehawassa hizb teseyifoachewo enkwan yemutegn belwal..aba gibrel we dont need u .. once u were saying emebetachen yewors hatiyat alebat ..u are tehadiso u and mks .so pls go were ever u belong

  ReplyDelete
 26. የብርሃን ተድላን ነገርማ እግዚአብሔር ያሳየን፡፡ የሰውን ልጆች እራቁታቸውን እያስጨፈረ እንደሚያሳድር ሁሉ እርሱም በቤተክርስቲያን ላይ በገንዘቡ በገዛቸው ወረበሎችና ግብረአበሮቹ ጋር በአደደባባ አእምሮውን ስቶ(አብዶ) እራቁቱን እንደሚወጣ እርግጠኛ ነኝ

  ReplyDelete