Thursday, January 12, 2012

አባ ሳሙኤል በወ/ሮ መሰረት ላይ የመሰረተቱት ክስ በዝግ ችሎት እየታየ መሆኑ ተነገረ - - - Read PDF

የብፁዕ አቡነ ሚካኤል ባለቤት ወ/ሮ መሠረት ታደሰ የወራሽነት መብታቸውን ለማስከበር እየተንቀሳቀሱ ባለበት ሁኔታ፣ እንቅፋት ሆነውብኛል በሚል ቅዱስ ሲኖዶስና በግልባጭ ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትም ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው በአባ ሳሙኤል ላይ ማመልከቻ ማስገባታቸውን ተከትሎ፣ አባ ሳሙኤል ጉዳዩ በሲኖዶስ እንዳይታይ ጓደኞቻቸውን በማሳደም ታፍኖ እንዲቀር ከፍተኛ ጥረት ያደረጉት አባ ሳሙኤል፣ “ስሜ ጠፍቷል” በሚል የመሰረቱት ክስ በዝግ ችሎት እየታየ መሆኑን ያገኘነው መረጃ ያስረዳል፡፡ ከዚህ ቀደም እንደዘገብነው በቀጠሮው ዕለት ያልተገኙትና በፖሊስ ተይዘው እንዲቀርቡ ትእዛዝ የወጣባቸው አባ ሳሙኤል በ10/4/2004 ዓ.ም. ከቀረቡ በኋላ በቀነ ቀጠሮው ያልተገኙት አስቸኳይ ሥራ ስለነበረባቸው መሆኑን በማስረዳትና ከተመደቡበት የልማት ኮምሽን ደብዳቤ አጽፈው በማቅረብ የክሱ ሂደት እንዲቀጥል ተደርጓል፡፡ በዚህም መሰረት አባ ሳሙኤል ክሱን ማሻሻል እፈልጋለሁ ሲሉ ወደ “ከፍተኛ የስም ማጥፋት ወንጀል” ለውጠዉታል፡፡ አክለውም ጉዳዩ መሰናዘሪያ በተባለ ጋዜጣ ላይ መዘገቡ ቅሬታ እንዳሳደረባቸው በመግለጽና ከሃይማኖት ጋር ስለሚያያዝ በዝግ ችሎት እንዲታይላቸው ጠይቀዋል፡፡

የተከሳሿ ጠበቃ ግን ጉዳዩ የሃይማኖት አይደለም፤ እንደ ሃይማኖቱ ትምህርት ቢሆን ግራህን ለሚመታህ ቀኝህን ስጥ ነው የሚለው፡፡ ይህን በተግባር ማሳየትም ከጳጳሱ የሚጠበቅ ነበር፤ ወ/ሮ መሰረት መብታቸውን ለማስከበር ያደረጉትን እንቅስቃሴ “የስም ማጥፋት ወንጀል” ሲሉ የከሰሱት ደግሞ አባ ሳሙኤል ናቸው፡፡ ጉዳዩ ሃይማኖታዊ ቢሆን ኖሮ ወደ ፍርድ ቤት ከመምጣት በዚያው በእምነት ተቋሙ ውስጥ መፍታት ይቻል ነበር፤ ስለዚህ ጉዳዩ ሃይማኖታዊ አለመሆኑ ታውቆ አሁን እየታየ ባለበት መንገድ ነው ሊታይ የሚገባው ሲሉ ተቃውመዋል፡፡ ሆኖም ዳኛው ጉዳዩ በዝግ ችሎት መታየቱ ምንም የሚያመጣው ለውጥ ስለሌለ በዝግ ችሎት እንዲታይ ወስነው በዝግ ችሎት በመታየት ላይ ይገኛል፡፡

በዕለቱ ከችሎት መልስ አባ ሳሙኤልን ለማነጋገር የቁምነገር ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ታምራት ወደ ጳጳሱ ሲቀርብ አጃቢዎቻቸው ገፈታትረው እንዳያናግራቸው እንዳደረጉት ለማወቅ ተችሏል፡፡

ምስጢራችን ለምን ተገለጠ በሚል አንድ ጳጳስ አንዲትን ምእመን በፍርድ ቤት ሲከስ አባ ሳሙኤል የመጀመሪያው መሆናቸው የተገመተ ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም ሌሎችን ከሰውና በሌሎችም ተከሰው ፍርድ ቤት በመመላለስ ሰፊ ልምድ ያላቸው አባ ሳሙኤል፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በነበሩበት ጊዜ በብዙዎች ላይ በፈጸሙት የሰብአዊ መብት ጥሰት ሲከሰሱ ያመልጡበት የነበረውንና “ጉዳዩ ሃይማኖታዊ ነው” የሚለውን ሰበባቸውን፣ ራሳቸውም ለመሰረቱት ክስ ደግመው ማቅረባቸው አስገራሚ ሆኗል፡፡ እውነታው ግን የአንዳንድ ጳጳሳት ገመና በዚህ መልክ አደባባይ ላይ መዋሉ ደስ ስላላሰኛቸው እንደ ሆነ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ሰዎች ይናገራሉ፡፡ ቀደም ሲል ጉዳዩን ሲኖዶስ ተመልከቶ ተገቢውን ብይን ቢሰጥና አባ ሳሙኤልም ለክስ ባይሮጡ ኖሮ እዚህ ሁሉ ነገር ውስጥ ባልተገባ ነበር የሚሉት ምንጮቻችን፣ ዳዊት በኦርዮ ሚስት ላይ የፈጸመውን ኀጢአት ለመሸፈን የወሰደው የራሱ እርምጃ ወደ በለጠ ኃጢአት እንዳሸጋገረው ሁሉ፣ ገመናችን መውጣት የለበትም በሚል በዚህ ጉዳይ ላይ ንክኪ ያላቸው አንዳንድ ጳጳሳት “ነግ በእኔ” ብለው ባሳደሩት ግፊት ጉዳዩ ታፍኖ እንዲቀር ለማድረግ መሞከራቸውና የወ/ሮ መሰረትን መብት አለማስከበራቸው፣ በአባ ሳሙኤል ከሳሽነት ጉዳዩ ወደአደባባይ ለመውጣት በቅቷል፡፡  በዝግ ችሎት እየታየ ያለው የክሱ ሂደት ከምን ደረጃ ላይ እንደ ደረሰ ለጊዜው ለማወቅ ባይቻልም ወደፊት ተከታትለን ለመዘገብ እንሞክራለን፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ አባ ሚካኤል ከወ/ሮ መሰረት በፊት ከትዳር ውጪ ከሌላ ሴት የወለዱት ልጃቸው ዮሐንስ ሚካኤል ወራሽነቱን በፍርድ ቤት ማስወኑን ከደረሰን መረጃ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይሁን እንጂ በወ/ሮ መሰረት ላይ ክስ የመሰረቱት አባ ሳሙኤል “እርሳቸው ድንግል ናቸው፤ እንኳን ልጅ ሊወልዱ ሚስትም አላገቡም” በሚል ምክንያት የአባ ሚካኤል ልጅ ዮሐንስ እንዳይወርስ እያከላለኩ ሲሆን፤ የሚወርሱት ዘመዶቻቸው ናቸው ሲሉም ሁለት ጠበቆች አቁመው እየተከራከሩ ይገኛሉ፡፡ ዮሐንስም ክብራቸውን ጠብቀው ካልተቀመጡ ልጅነቴን በዲ ኤን ኤ ምርመራ ለማረጋገጥ እገደዳለሁ ሲሉ መናገሩን ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ የያዘ ሁለት ገጽ ደብዳቤ ደርሶናል፡፡ ለማንበብ ይህን ይጫኑ፡፡

18 comments:

 1. Hi Aba Selamawoch negeru Asazag & Asafari Lihon yichilal kesash papas tekesash miemen mehonachewm lemenafikan yetemeche neger honelachew Abune Samueil berkata kum neger sertewal Addis Abeba Hagere Sibketin yashashalu yelewetsu Abat nachew Simachewn Lemansat - Lematsifat - Lemasaded yetenesa birtu tselat Alebachew lezihim enante timeslalachihu Fird betu bezig chilot lemayet yasebewin ye church Guday enante le Adebabay abekachihut Minew Lemehonu Enante menafikan tihonu weyis ye Deje Selam bilog ayinet yesewn melkam Sim Lematsifat bicha yeteselefachihu nachihu
  Aba Selama - Deje Selam _ Ahat Tewahrdo-Gebir Her-Qedamaw - yemesaselachihut ye Ethiopia Ortodox Tewahedo Churchn Papasat Menekosat -Kesawsit - Diyakonat -Sebakyan - mezemiran bemasadedi lamatsifat yetenesachihu mehonachihun yemnayew sewn sedibo lesedab mestset tazewetralachihu
  Aba Selamawoch wengail mezigibu - sewn astemiru yesewn bedel atasibu egiziabher yayal beterefe bertu

  ReplyDelete
 2. አየ አባስላማዎች አሁን በዚህ ዘመን ስንት የሚታፍ እያለ ተራ ተራ ወሬ ያዉም የመደር ወሬ አረ ባካችሁ ከቴከኖሎጂዉ ጋር ሂዱ እናም እኛ የተዋህዶ ልጆች እንዲህ ያለ የወንደምን ሀጢያት ከማዉራት አሰትማሪ ነገር ታፉ እባካችሁ እባካችሁ እባካችሁ እባካችሁ እባካችሁ............

  ReplyDelete
  Replies
  1. ይሄኔ አባ ፋኑኤል ሆነው ቢሆን ኖሮ አገር ይያዝልኝ አስተያየት ትሰጥ ነበር። የማኅበረ ቅዱሳን ቡችሎች!!!!

   Delete
  2. ማህበሩ እኮ የቃየል ማህበር ስለሆነ ነው። ይህንን መልእክት የሰጠህ ወንድም ወይም እህት ጥሩ አስተውለሃል\ሻል። አቡነ ፋኑኤልን ከቃየል
   ማህበር በቀር እኛ የቤተክርስቲያን ልጆች እናከብራቸዋለን፣ እንወዳቸዋለን። ጎበዝ የልማትና የሥራ ሰው ናቸው። አባ ሳሙኤልማ የቃየል
   ማህበር ተጠቃሚ ናቸው ለጊዜው። ይቆየን

   Delete
  3. True! Aba Samuel is not papas. He must leave the Church and lead his own life with his wives.

   Delete
 3. bewushet tetsensachihu, bewushet teweldachihu, bewushet adigachihu, bewushet litmotu new? Egzio fetari yikr yibelachihu.

  ReplyDelete
 4. ሰው ብቻውን ይኖር ዘንድ መልካም አይደለም ያለው እግዚአብሔር ነው። ጋብቻም ክቡር ነው ያለው እግዚአብሔር ነው። በምኞት ከመቃጠል መጋባት ይሻላል ያለውም እግዚአብሔር ነው። ስለድንግልናው ያፈረም ያግባ ያለም እግዚአብሔር ነው። እነዚህኞቹ ግን ከወደየትኛው ናቸው?ጳጳስ ማለት ቄስ ማለት ነው።ግሪኩ(παπάς) በማለት ያስቀምጠዋል። ቄስ ማለት ደግሞ ህጋዊ ጋብቻ ያለው ሰው ነው። እነዚህ ጳጳስ የሚለውን ቃል ከየት አመጡት? ኤጲስ መሆን የፈለገ የአንዲት ሴት ባል የሆነ ይሁን ይላል፣ እነዚህ የየት ሀገር ኤጲስ ቆጶሶች ናቸው? እውነተኛው ነገር «የእግዚአብሔርን ጽድቅ ሳያውቁ የራሳቸውንም ጽድቅ ሊያቆሙ ሲፈልጉ፥ ለእግዚአብሔር ጽድቅ አልተገዙም» ሮሜ10፣3 የተባለው የሚሆንባቸው ናቸው።

  ReplyDelete
 5. Ahun Manin tsekemachihu ? Menafikann new noh rakutun bekere gize yesakew liju teregeme ye abatin gebena meshefen Ye church Gebena meshefen new mezerzeru lemanew ?

  ReplyDelete
 6. Aba selama nurulen balegana shirmuta papas ena leba mk agaltu. Kastemaru ayker end abaselama.

  ReplyDelete
 7. Mafeeeeeeeeeeeeriy wonbedewoch shame "aba selam" yenebegashawu blog nawu sibal alamenkum naber ahun maninetachu siletawoke simachun tolo blachu kayiru menafikan hulu!

  ReplyDelete
 8. 99.5% eotc follower like begashaow.

  ReplyDelete
 9. Absolutliy!!!!!! He is a very good Teacher.

  ReplyDelete
 10. Hate begashaw means not ready to learn the truth and reality of God word. I always apperciated this wonderful preacher. Why mk againest him because of his support of mass of eotc followers. that enough gojam teret tenqwola.

  ReplyDelete
 11. Lemin yanen astayayet post atadergutim

  ReplyDelete
 12. oh my god i think the pops have wifes and kiddes; and mk knows all about it and mk used it to use all the pops who do some thing worng ..i have miker abatoch amlak mehari selhone just repent yemhabere aganint metekemiya athunu.. i think mk is a bad bad girl mahiber set nat wond???mahiberwa

  ReplyDelete
 13. Because nothing to teach. This is a web for God word.

  ReplyDelete
 14. i heard most of the orthodox pops have echogna or yetedbeku lijjoch..what is going on ????kobun eko meshekem kalchalwo awlikw wed alem hiwot megbat ichlalu kobu lemichilut bicha new ..some times i admier behatwi g meskel he did not dinay any thing hew is marreid ..bec0s we cant hide frome god beswo ejji kemwodek degmo beamlak ejji mewodek yishalal..asafari zemen new lebetchrstianachen.

  ReplyDelete