Saturday, January 28, 2012

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የአባ ሠረቀ ብርሃን “እውነትና ንጋት” መጽሐፍ ተመረቀ - - - Read PDF

የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሃላፊ የነበሩትና ማህበረ ቅዱሳንን በህገ ቤተክርስቲያን እንዲመራ ለማድረግ ከፍተኛ ተጋድሎ ያደረጉት አባ ሠረቀ ብርሃን “እውነትና ንጋት” በሚል ርእስ ያዘጋጁት መጽሐፍ በ17/5/2004 ዓ.ም. በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ ብፁኣን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የጠቅላይ ቤተክህነት የመምሪያ ሃላፊዎች የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ካህናት፣ ዲያቆናት፣ የሰንበት ተማሪዎችና በርካታ ምእመናን በተገኙበት እጅግ በደመቀ መርሀግብር ተመረቀ፡፡ ይህ በአይነቱ ለየት ያለና በበርካታ ሰነዶች የተሞላው፣ 222 ገጽ ያለው መጽሐፍ የተዘጋጀው በሶስት አበይት ምክንያቶች እንደሆነ መግቢያው ላይ ተጠቅሷል፡፡ ምክንያቶቹም፡-
1.      በሃይማኖት የወለድኳቸውና በስነ ምግባር ያሳደግኋቸው የመንፈስ ቅዱስ ልጆቼ በእኔ ላይ የደረሰው የስም ማጥፋት ዘመቻ ፍጹም ሐሰትና አሉባልታ እንደሆነ በሚገባ ለማስረዳትና በተማሩትና በተረዱት እውነት እንዲበረቱና ብሎም በእኔ ላይ እየደረሰ ያለው የስም ማጥፋት በደል በእኔ ብቻ የተጀመረ ሳይሆን ከጥንት ጀምሮ ከአምላካችንና ከመድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብሎም በደቀመዛሙርቱ ሀዋርያት የተማርነውና በውርስ የተረከብነው እንደሆነ በውል እንዲረዱት ለማድረግ፤
2.     የዲያብሎስ የግብር ልጆች ከሆኑት አካላት በእኔም ሆነ እንደእኔ በመሳሰሉት የቤተክርስቲያኒቱ ልጆች እየደረሰ ያለው የስም ማጥፋት ዘመቻ ሁሉም ወገኖች ፍጹም ሐሰት እንደሆነ ተገንዝበው እንደእነዚህ ከመሳሰሉት አካላት እንዲርቁና እስካሁን እውነት መስሏቸው የነበሩትን ወገኖች ከዚህ የተሳሳተ አካሄድ ተመልሰው የሰውን ሀጢአት ከመመልከት ይልቅ የራሳቸውን ማንነት እንዲገነዘቡ ለማድረግ፣
3.     በእኔ ላይ የተፈጸመውና እየተፈጸመ ያለው የስም ማጥፋት ዘመቻ በማን? ለምን? እንደሆነ ማንም ሰው እንዲገነዘበው ለማድረግ ነው፡፡ በመሆኑም የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ሃላፊ ሆኜ ቤተክርስቲያኔን እንዳገለግል ስመደብ የተጣለብኝን ሃላፊነት በአግባቡ ለመወጣትና በተለይ የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብርና ሉዓላዊነት ለመጠበቅ ብሎም ለማስጠበቅ ሲባል የቤተ ክርስቲያኑቱን ሀብትና ንብረት የግል ንብረታቸው በማድረግ እንደፈለጉት ያደርጓት የነበሩት ስርአት እንዲይዙና ከአድራጎታቸው እንዲቆጠቡ በቆራጥነት ፊት ለፊት በመጋፈጤ ብቻ ነው፡፡ ይላል፡፡
መጽሐፉ አባ ሠረቀ በማህበረ ቅዱሳን የተከፈተባቸው የስም ማጥፋት ዘመቻ ሀሰት መሆኑን ከመነሻው እስከ አሁን ድረስ ያለውን ሁኔታ በበርካታ ሰነዶች አስደግፎ ያቀረበ ሲሆን፣ ማህበረ ቅዱሳንን ትልቅ ኪሳራ ውስጥ እንደሚከተው ተገምቷል፡፡ ማህበሩ በማያውቀው ገብቶና በሃይማኖት ጉዳይ ከእኔ በላይ ለአሳር በሚል ባዶ ትምክህት ተወጥሮ ማርያም ሰው በመሆኗ የውርስ ኀጢአት አለባት የሚለውን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንደ ኑፋቄ በመቁጠር አባ ሠረቀ መናፍቅ ናቸው ሲል በሰፊው ማስወራቱና በሲኖዶስ ስብሰባ ላይ በምንደኛ ጳጳሳቱ አቧራ ለማስነሳት መሞከሩ የሚታወስ ሲሆን፣ አባ ሰረቀ በመጽሐፋቸው የዚህን ትምህርት ትክክለኛነት በመጽሐፋቸው በበርካታ ሊቃውንት ምስክርነትና የሰነድ ማስረጃ አሳይተዋል፡፡ ከሰነዶቹ መካከል ዛሬ የማህበረ ቅዱሳን ፊታውራሪ ነኝ የሚሉት ብፁዕ አቡነ ገብርኤል የሰጡት አስተያየትም ተካቷል፡፡ በሌሎቹም ማህበሩ እርሳቸውን በከሰሳበቸው ጉዳዮች ሁሉ ተጨባጭ ማስረጃ በማቅረብ የማህበሩን እኩይ ግብር ገልጠዋል፡፡
በምረቃው ስነስርዓት ላይ መጽሐፉን አስመልክቶ ዶ/ር ሀዲስ የሻነው፣ ጋዜጠኛ ካህሳይ ገብረ እግዚአብሔርና መምህር ተመስገን ዮሐንስ የተለያዩ አስተያየቶችን ሰጥተዋል፡፡
“ዛቲ እለት በዓልነ ነያ
ሠረቀ ብርሃን ዘተመነያ …”
ብለው አስተያየታቸውን የጀመሩት ዶ/ር ሀዲስ መጽሐፉ የሰነዶች ጥንቅር ስለሆነ ድርሰት ነው ማለት ስለማይቻል ደራሲ የለውም፤ ስለዚህ እኔም ሀያሲ አይደለሁም ብለዋል፡፡ ውሃን የሚያናግር ድንጋይ እንደሆነ ሁሉ፣ ይህም መጽሐፍ ተናግሮ አናጋሪ ነው ሲሉ ንግግራቸውን በአዳራሹ ውስጥ የተሰበሰበው ምእመን በጭብጨባ አጅቦታል፡፡ አክለውም አባ ሠረቀ መዝገብ ቤት ውጦ ሊያስቀራቸው የነበሩትን እነዚህን ጠቃሚ ሰነዶች ለታሪክ ተመራማሪዎች ፍጆታ እንዲውሉ ማሳተማቸው ታላቅ ጀግንነት ነው ሲሉ አድናቆታቸውን ችረዋቸዋል፡፡ መጽሐፉ አላማ ያደረገው በውይይት መቀራረብን መመስረት ሲሆን በተለይ ወጣቱን ትውልድ ለውይይት ይጋብዛል፤ በነገረ ድኅነት ላይ ለሚደረግ ጥናትም ምንጭ በመሆን ከማገልገሉም በላይ ለቤተ ክርስቲያን የአቅም ግንባታ ሆኖ ሊያገለግል እንደሚችልም ተናግረዋል፡፡ በመጨረሻም “ንቃህ መዋቲ ዘትነውም (አንተ የምትተኛ ንቃ)” የሚል መልእክት ይዞ የመጣና በተለይ ለኮሌጆች የተበረከተ ስጦታ ነው ብለዋል፡፡ ምናልባትም በመጨረሻው ሐሳባቸው ማርያም የውርስ ሀጢአት ነበረባት የሚለው ጉዳይ በመንፈሳዊ ኮሌጆቻችን ውስጥ መነጋገሪያ ሊሆን እንደሚገባ ጠቁመዋል የሚል ግምት አለ፡፡

ሁለተኛው ተናጋሪ የሆኑት ካህሳይ ገብረ እግዚአብሔር አስተያየታቸው የተመሰረተው በሽፋኑና በመግቢያ ጽሁፉ ላይ መሆኑን በመጠቆም ከተራሮች በስተጀርባ የሚታየውን የጎሕ መቅደድ ሁኔታ በራሳቸው እይታ ለማብራራት የሞከሩ ሲሆን፣ መጽሐፉ አንድን ተራራ ነጻ እንደሚያወጣ ይጠቁማል፤ የትኛውን ተራራ ነጻ ለማውጣት ይሆን? ሲሉ ምስጢሩ የገባው በአዳራሹ የተሰበሰበው ታዳሚ የጋለ ጭብጨባ አጨብጭቧል፡፡ መጽሀፉ ቤተክርስቲያናችንን ከማህበረ ቅዱሳን ተጽእኖ ነጻ የሚያወጣ ነው የሚል አንድምታ እንደሰጡትም ተገምቷል፡፡ በመግቢያው ላይ በሰጡት አስተያየትም ከሀዋርያት ጀምሮ በክርስቶስ ተከታዮች ላይ በርካታ መከራና የስም ማጥፋት ዘመቻ ተከፍቶ የነበረ መሆኑንና በአገራችንም ብዙዎች በዚህ መንገድ ማለፋቸውን አውስተው አባ ሠረቀ በደቂቀ እስጢፋኖስ ላይ የደረሰውን ተመሳሳይ ስደት መጥቀስ ነበረባቸው ሲሉ አዳራሾ ሞቅ ባለ ጭብጨባ ተናግቷል፡፡ በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ ስለ ደቂቀ እስጢፋኖስ እውነተኛነት መነገሩና በውስጠ ታዋቂነት  የአጼ ዘርአ ያዕቆብ ክፉ ስራ መገለጡ በእርግጥም በቤተክርስቲያናችን ጎህ ሊቀድ ዘመን መድረሱን የሚያሳይ ነው፡፡ ካህሳይ ገብረ እግዚአብሔር ምንኩስና በኢትዮጵያ በተሰኘው መጽሐፋቸው ስለደቂቀ እስጢፋኖስ ትክክለኛነት በመጻፋቸው ማህበረ ቅዱሳን እንዲወገዙ ክስ ከመሰረተባቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ ሊቃውንት መካከል አንዱ መሆናቸው ይታወሳል፡፡
በመጨረሻ አስተያየቱን የሰጠው መምህር ተመስገን አባ ሠረቀ ከአሜሪካ ተመልሰው ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ እንደሚያውቃቸው ጠቅሶ፣ ገና እንደመጡ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በር ላይ ወድቆ ሲያቃስት የነበረ አንድ የታመመ ድሃን ተመልከተው፣ እንዴት ዝም ብለን እናየዋለን ብለው  ላዳ ታክሲ ተኮናትረው ወደህክምና ስፍራ ወስደው ማሳከማቸውንና በሌላም ቀን ተመሳሳይ ምግባረ ሰናይ መፈጸማቸውን አስታውሶ፣ ቤተ ክርስቲያን እንደእዚህ በደጇ ወድቀው ያሉትን ችግረኞች ሁሉ መርዳት አለባት የሚል አቋማቸውን በፍቅር ማንጸባረቃቸውን ገልጿል፡፡ አባ ሠረቀ ማህበረ ቅዱሳን በህግና በስርአት መሰረት ይመራ ማለት ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ ከማህበሩ ጋር ግጭት ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ ጉዳዩ በግል ጋዜጦችና መጽሔቶች ላይ ሲዘገብ መምህር ተመስገን በጊዜው ዋና አዘጋጅ በነበረበትና በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስር በሚዘጋጀው ኆኅተ ጥበብ ጋዜጣ ላይ አባ ሠረቀንና የማህበረ ቅዱሳንን አመራሮች አነጋግሮ በጋዜጣው ለማውጣት ተንቀሳቅሶ የነበረ ሲሆን ከአባ ሠረቀ በኩል ፈቃደኛነቱ የነበረ ሲሆን በማኅበረ በኩል ግን ፈቃደኛ የሆነ ሰው ባለመገኘቱ የእርሳቸው አስተያየት ተጽፎ ወደማተሚያ ቤት ከገባ በኋላ፣ የማህበረ ቅዱሳንን ጉዳይ ስለያዘ መታተም የለበትም ተብሎ እንደገና የአባ ሠረቀ ቃለ መጠይቅ እንዳይወጣ መደረጉን ጠቅሷል፡፡ ይህን ያደረገው ማን እንደሆነ መምህር ተመስገን ባይጠቅስም በጊዜው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ የነበሩት አባ ሳሙኤል መሆናቸውን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ያም ወቅት ጳጳሱ ፓትርያሪኩን ለመገልበጥና ፓትርያርክ ለመሆን ከማህበረ ቅዱሳን ጋር ውስጥ ውስጡን ስራ የጀመሩበት ጊዜ መሆኑን እነዚሁ ምንጮች ይናገራሉ፡፡
መምህር ተመስገን አስተያየት እንዲሰጥበት የተሰጠው ክፍል ከገጽ 81-221 ድረስ መሆኑን ጠቅሶ በዚህ ክፍል አባ ሠረቀ የሠሩትን ታላላቅ ሥራ የጠቃቀሰ ሲሆን፣ በዚህም መሰረት አባ ሠረቀ ቤተ ክርስቲያኒቱ ወደፊት ልታከናውነው በሚገባ አንድ ትልቅ ጉዳይ ላይ መሠረት ጥለዋል፤ ከእርሳቸው በፊት አይደፈሬ የነበረውን አጀንዳ በመድፈር ለመነቅነቅ ሞክረዋል ብሏል፡፡ የማህበረ ቅዱሳን አመራሮች አባ ሰረቀ ማህበረ ቅዱሳንን ብቻ ለመጉዳት እንደተነሡና በእነርሱ ላይ ብቻ እንደተነሡ አድርጎ ቢያቀርብም፣ አባ ሠረቀ ግን በቤተክህነቱ ላይ የሚመለከቱትን ችግርም በመግለጽ እንዲስተካከል የተሟገቱ መሆናቸውን አክሎ ገልጿል፡፡ በመጨረሻም በማህበረ ቅዱሳን አካሄድ ላይ ብዙዎች ትችት እያቀረቡና ማህበሩን እየከሰሱት ስለሚገኝ ለምን ማህበሩ አንድ ፎረም ፈጥሮ ውይይት የሚደረግበትን ሁኔታ አያመቻችም ሲልም ለማህበረ ቅዱሳን ሰዎች አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡
በመጨረሻ ንግግር ያደረጉት ብፁዕ አቡነ አረጋዊ ስለአባ ሠረቀ ከሊቃውንቶቻችን አንዱ ነው ሲሉ ምስክርነታቸውን የሰጡ ሲሆን፣ ማህበረ ቅዱሳንን በተመለከተም የቤተ ክርስቲያን ትምህርት የላቸውም እንጂ በዘመናዊ እውቀት ጎበዞች ናቸው ሲሉ ሳቅና ጭብጨባ የተደባለቀበት ምላሽ ከታዳሚው ተችሯቸዋል፡፡ ከዚያም ብፁዕነታቸው ጭብጨባ ባይበዛ ጥሩ ነው ሲሉ አሁንም ታዳሚው በመሳቅ ስሜቱን ገልጿል፡፡ ብፁእነታቸው አክለው የማህበሩ አባላት የቤተክርስቲያን ትምህርት ባይኖራቸውም ባላቸው ዘመናዊ እውቀት ብዙ ሊሰሩ እንደሚችሉ ጠቅሰው ሁላችንም እንደየእውቀታችንና እንደየደረጃችን ብንሰራ ለአገርም ለቤተክርስቲያንም እንደሚጠቅም ተናግረዋል፡፡ የቤተ ክርስቲያንን ጉዳይ በቤተክርስቲያን ብንጨርስ ይሻላል እንጂ በየጋዜጣው መተቻቸቱ መልካም አለመሆኑን ጠቅሰው፣ ይህ በእኛ ቤተክርስቲያን እንጂ በሌሎች ዘንድ ብዙ የማይታይ ነውና ሊታረም ይገባል ብለዋል፡፡                            

36 comments:

 1. great Article Aba selamas, I was at the ceremony that day and was expecting some one to blog about it and see who really writes the truth about current church affairs, I have been following your blogs however, I was not sure if you tell the truth sometimes or if you put spice in your stories, to make things short I now see that you do post real stories, And I thank you for that. Keep up the good job the book opening was amazing I didn't think people would really show up like that in great numbers, I liked Dr hadis and kasayes speech. Thx again

  ReplyDelete
  Replies
  1. አባ ሰረቀ ምን አይነት ቀጣፊ ባለጌ መናፍቅ ተሃድሶ እምነት ተከታይ እንደሆኑ በዚህ በአቶ ሰረቀ መጽሃፍ መረዳት ይቻላል።ድንግል ማርያምን በጥንተ ተሃብሶ ሓጥያት ነዉ ብሎ መጻፍ ከዚህ በላይ ዉሽታምነት እና ምንፍውና አለ ወይ።ስለድንግል ማርያም ማወቅ እና መጽሃፍትን ማገላበጥ ካስፈለገ banned bibles or chronological bibles ዉስጥ የሃዋርያዉ ቶማስ ወንጌልን ወይንምመጽሃፍ ሢራክን ለምን አይመለከት አቶ ሰረቀ ወይንም የኒቆዲሞስን መጽሃፍቶችን ለምን አታገላብጥም።ሃሰተኛ እንደስምክ ሰርቀ ሌባ ነህ።

   Delete
 2. You did good My dear father Abba sereke Birhan. God be with you all the time. yours faithful.
  Abba K.M.

  ReplyDelete
 3. I am so happy for this news. Aba Selama Thank you for your information, you stand olways with the truth. God Bless you all.

  If you need any help, please let me know, a lot of pepele are standing with your true post all the time.

  Thank you, God Blesse.

  ReplyDelete
 4. Eotc now in the critical time has needed those wel educated fathers such as aba serke, aba fanuel, megabe hadis begashaw ,and all others currentely attacked by mk (mafya killer). Patriarc pawlos made big progress that he cleaned debtrra in the church so those elememts plus mk killed and attack for non reasonable point. They created false information to hated by others. The solution is clrar just look at jesus life they accused him baselesly. So truth is powerful.

  ReplyDelete
 5. አሁን ገና በምድራችን ላይ ሊነጋ እያቅላላ እንደሆነ ተሰማኝ:: ደግሞስ ጌታ 'እሳትን ልጥል መጣሁ ከነደደስ ምንን እፈልጋለሁ' አይደል ያለው:: አቤቱ የእስራኤ ዛሬም ደግሞ በክርስቶስ በኩል የእኛ አምላክ አንተን ፍለጋ በባዶ እግሩ ጽድቅን ፍለጋ ከደብር ወደ ደብር ለሚንከራተተውና በድህነት ጎኑ ለሙታን በመደገስ የበለጠ ለተራቆተው ሕዝባችን የምህረት እጆችህ ይዘርጉለት:: ክፉውም ይደንግጥ እንደ ፈረስ አድርጎ የሚጠቀምባቸው ወገኖቻችንም ማስተዋል አግኝተው ማንን እያገለገሉ እንደሆነ ተገልጦላቸው በንስሃ በዙፋንህ ስር ይውደቁ:: አሜን::

  በእውነት ቤተ ክርስቲያናችንን ጌታ ያስባት!!!!

  ከእንግዲህ እርፍ ይዞ ወደኋላ ማየት አይቻልምና የእውነት ልጆች በእንባ ሁሉን ወደሚችለው አምላካችን እግር ስር አብዝተን እንቅረብ:: በፍቅር እንበርታ::

  ሰላም ሁኑልኝ

  የምድሬን ትንሳኤ ናፋቂ እህታችሁ

  ሰላም ነኝ

  ReplyDelete
 6. Aba Sereke gobez sew nachew Alamachewn yalsatu menekuse mehon yechalu menfesawiwn ewket tsenkikew yemiyawku Mahibere Kidusan yehone hulu kesachew zend memar alebachew beteley Aba Sereke sira asikiyaj honew biseru bizu neger yistekakel neber Mahibere Kidusan sewn bemasaded metsekem yelem gebenachihu wetsa gena Abalatu hulu gudachihu yiwetsal

  ReplyDelete
 7. Aba Sereke,

  I am proud of you, Your are the one and the only one real Orthodox. If there is a true gadje in our church. Aba Sereke have to take over Abune Pawlos place. I start to know the truth since I read your book. Keep it up, I promise I am beside you. God bless you.

  ReplyDelete
 8. wechew gud ayemetsahaf aya?

  ReplyDelete
 9. maryam tinite abiso norebat alnorebat kedihinet gar yemiagenagnew minidin new?yihie ke amalaginetua gar yemiagenagnew mindin new????????????

  ReplyDelete
 10. GOOD JOB ABA WONDERFUL
  KEEP IT UP

  ReplyDelete
 11. በርግጥ አባ ሰረቀ በሁለተኛ ክፍል ያሳውቁን እንደሆነ አላውቅም እንጅ ስለ ወጣቶች በአንድነት ቤተ ክርስቲያንን ማገልገል የከፈሉት መስዋዕትነት ከዚህ በላይ ነው፡፡ በማኅበር ስም እና ማህበርን አርአያ በማድረግ በአሁኑ ጊዜ ስንት ማህበር ተፈልፍሏል፣ በቤተ ክርስቲያን ስም እሷ የማታውቀው ስንት ኳየር ተመስርቷል፣ በቤተ ክርስቲያን ስም እሷ የማታውቀው ስንት የግል ባንክ ተከፍቷል፣ በቤተ ክርስቲያን ስም እሷ የማታውቀው ስንት አክሲዮን ተፈጥሯል፣ ስንት የፖለቲካ ፓርቲ ተደራጅቷል፣ ይህን ሁሉ በአንድነት በአንድ መምሪያ ስር በማደራጀት የወደፊቷን ቤተቨ ክርስቲያን አንድ ማኅበር ሆና ሳትከፋፈል እንድትቆይ ለማድረግ እስከ መባረር መስዋዕት ሆነዋል፡፡ ለቅዱስ አቡነ ጳውሎስና ለቅዱስ ሲኖዶስ እባካችሁ የሄ ማኅር ሚባል ነገር ይቁም ቅዱስ አቡነ ጳውሎስና ቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ አይስጡ አያስተናግዱ የቤተ ክርስቲያኗ አንድነት አደጋ ላይ ነው እያሉ ተንብየዋል ነቢይ ናቸው፡፡ የተወሰኑት አባቶች የገባቸው ደግፈዋቸዋል አሀንም ይደግፏዋል፡፡ የማህበራት ተጠቃሚ የሆኑት ተቃውመው ከቦታቸው አንስተዋቸዋል ያሳዝናል፡፡ ማነው ተጠያቂ ማነው የቤተ ክርስቲያኗን ሕግ የሚያውቅና የሚያስጠብቀው፡፡

  ReplyDelete
 12. እንደተከታተልነው የምረቃው ሥነ ሥርዓት እጅግ ማራኪ አዳራሹ ሞልቶ የሚመለከታቸው ባለ ሥልጣኖች ተገኘተው፣ በጥሩ መስተንግዶ የታጀበ ነበር፡፡ አባ ሰረቀ ብርሃን እንኳን ደስ ያለዎት የሚያስብል ነበር፡፡

  አሁንም አባ ሰረቀ እንኳን ደስ ያለዎት

  በመሠረቱ መጽሐፉ በጣም ዲሲፕሊን የተሞላ፣ እንደ ጎጠኛ ማኅበርተኞች በስድብ ያልታጀበ እውነቱን የሚያሳይ አንባቢ ይፍረድ የሚል ነው፣ ከሀሜትና ከቧልት የጸዳ ነው፡፡

  የዶክተር ሀዲስን ንግግር በጣም ወድጀዋለሁ እሳቸውም ከሚሳደዱት ሊቃውንት አንዱ በመሆናቸው የሆዳቸውን በሆዳቸው አድረገው የተሰማቸውን ደስታ ተናግረዋል፡፡

  የመ/ር ካህሳይ ንግግር በርግጥ ጥሩ ቢሆንም ስለ ደቂቀ እስጢፋኖስ ማንሳቱ ቦታው አይደለም፡፡ በደቂቀ እስጢፋኖስ ላይ የደረሰው ግፍና የንጉሡ ጉዳይ ለብቻው መታየት ያለበት፡፡ ትውልዱንም ሆነ ቤተ ክርስቲያኗን ከታሪክ ተጠያቂነት ነጻ በሚያወጣ መንገድ ቅዱሳኑንን በአግባቡ ቅድስናቸውን ሰማዕትነታቸው በሚገባ ለትውልዱ ማስረዳት የሚቻልበት ሁኔታ መሰናዳት አለበት፡፡ ተቆጥሮ የማያልቀ መጻሕፍትና የዕውነት ምስክር ባለበት ሁኔታ ታሪክን ለማጥፋት የሚጥሩት ክፉዋች ማሳፈር በሚችል መንገድ ፖለቲከኛም ቢሆኑም ዶ/ር ጌታቸው ኃይሌ አንዳደረጉት ያለ ደፈር ያለ ጥረት ያስፈልጋል፡፡ የንጉሡን ጭካኔና የሰማዕታቱን እልቂት በእንደዚህ ያለ ሁኔታ ማቅረብ ያፈልጋል ብየ አላምንም ስለዚህ መ/ር ካህሳይ አስተያየታቸው ጥሩ ነው ግን ይህን ለብቻው ቢጠቅሱት፡፡ በርግጥ እሳቸው በመጽሐፋቸው ትንሽ ተናግረዋል፡፡

  መ/ር ተመስገን በርግጥ በቅርብ አላውቃቸውም ነገር ግን ንግግቸው አባ ሰረቀን በግል ከማወቅ ጀምሮ ሥራቸውንም ጠቅሰዋል፡፡ አስተያየታቸው ራሳቸውንም ለማስተዋወቅ ይመስላል፡፡ ስለ ራሳቸው በጣም አውርተዋል እሳቸው እንደ አባ ሰረቀ መስዋዕት የሆኑ እንደሆነ አድርገው አቅርበዋል በእውነቱ ምን ያህል እውነት እንደሆነ በትክክል አናውቅም፡፡ ምክንያተም እንደ አባ ሰረቀ ለቤተ ክርስቲያን አንድነትና ሥርዓት መከበር የተፋለመ እስከ አሁን የለም፡፡ ወደ ፊት ግን አንዳንድ ከጥም ትስስር የወጡና ዕነተኛ አባቶች የበለጠ ይሠራሉ የሚል እምነት አለን፡፡ መ/ር ተመስገን በጣም ገርሟቸው የተናገሩት ማቆች ለማህበራዊ ቡድነኛ ህልውናቸው ቤተ ክርስቲያኗ መከፋፈል እንደሚፈልጉ፣ የተጣሉት እንደተጣሉ ቢቀጥሉ እነሱ በመሐል ተጠቃሚዎች እንደሚሆኑ፣ ገበያ ግርግር ለሌባ ይመቻል እንዲሉ በተጣሉት አባቶች መካከል ገብተው ልዩነቱን በማስፋት የሲኖዶስን ውሳኔ አስፈጻሚ በመምሰል የሚያደርጉትን ዝርፊያ በጣም ብዙ ሰዎች በተደጋጋሚ በግልጽ ቢናገሩትም ያንን የሚነካውን ክፍል አባ ሰረቀም አስምረውበታል፡፡ በግልጽ ይታወቃል፡፡

  ግልጹ ነገር በአባቶች መለያያት ተጠቃሚ ከሚሆኖት አካላት ውስጥ ማቆችና ሌሎች ቡድኖች ናቸው በርግጥ በትክክል በመገለጹ አባ ሰረቀ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስላለው መከፋፈል ያላቸውን አቋም ይናገራል፡፡

  ያልተፈጸሙ ሲኖዶስ ውሳኔዎችን

  የመንግሥት ባለ ሥልጣናት ሳይቀሩ ምስክር የሆነበትን ስብሰባ ውሳኔ ያለተፈጸመ ለመሆኑ ታሪካዊ ምስክር የሆነ

  አባ ሰረቀ ማኅበርን ለማፍረስና ወጣቶችን ለመበተን ሳይሆን ወጣቶች ቤተ ክርስቲያን በሠራችላቸው መዋቅር እንዲያገለግሉ እንጅ ለየቡድኑ ወይም ለየድርጅቱ ሀብታቸውን፣ ዕውቀታቸውን፣ እና ጉልበታቸውን እንዳያጠፉ የሚጥሩ በጣም ጥሩና ቅን አባታ፣ እሩህሩህ መነኩሴ መሆናቸውን የሚመሠክር ነው

  በጣም አስጊው ሁኔታ ደግሞ የጥንተ አብሶን ክርክር እንደገና እንዲያገረሽ የሚገፋፋ መሆኑ ነው፡፡ አሁንም ቤተ ክርስቲያኗ እንደ እህቶቿ ኦርቶዶክሳያን ቤተ ክርስቲያኖች አንድ ወጥ ውሳኔ ወስና ሊቃውንቷን ማረጋጋት እንዳለባት፡፡ የተማሩት ሊቃውንት ምንም በማያውቁ በሠፈር አጭበርባሪዎችና አስመሳይ ነጋዴዎች እየተጠቁ እንዳይሸሹ ማረጋጋት እንዳለባት ጠቋሚ ነው፡፡

  ReplyDelete
 13. SEREKE BIRHAN, JEMERE ENJI GENA ALICHERESEM. EGZIABHETRE BEZIH ZEMEN LEZIH TIWULID YASNESAW MENEKUSIE NEW. KERIBE LALEFUT AMETAT AYICHEWALEHU. MENIFESAWI ABAT RUHRUH, RAEYYYYY YALEM EOTC KENEZIH WORO BELA MAHIBERAT NETSA LEMAWUTAT YETAGELE. HULACHINIM YETEMARINIBET ABBBBBAAAAATTTTT NEW! YEMAHIBER SAYTAN GUDAY AYIZUACHIHU ALIKUAL. MAHIBERUN YETALEW EGZIABHER NEW YEBIZU AGELIGAYOUCH LIKISU BE'ARIYAM TESEMITO NEW ENDE RAHEL ENIBA. BETELEY DANIEL KIBIRET ENA MULUGETA H/MARIAM YADEREGUT NEGER BEKI NEW. BE' BABILONAWIYAN MEKAKEL KONKOCHEW TEDEBELALEK.ሰረቀ Talak Abat ena Semaet new. Ketay METSAHIFIT Yitezegaju alu Bekirb Milekeku Beleloch Ageligayouch Teketatelu

  1. Zimot Ena Kihenet Be'Mahibere Kidusasn Mekakel
  2. Menefasawi Mahiberat Be' Politicaw Alem
  3. Yale Dikuna Kisina be' MK Sefer
  4. Liwogez Yemigebaw Tehadisu Manew (MK or Leloch)
  5. Lelochimmmmm Alu

  ReplyDelete
 14. congra Aba sereke b. u did great job,I 'm glad to hre this good news. this book is good message to all young genration mostly mk u must turn ur heart to the turth way and that is orthodox tewahedo not mk campany our age is new erea we have to work to our church unity not giving falls name.
  I thing the name of the book is the same with aba Sereke's name sereke and nigat is sun rise that means darknnes is gone and the light is coming up this is big hope to our church thank u Aba keep going may God bless u.

  ReplyDelete
 15. Aba Sereke,

  I know you for long time when you were here in US. I always admire your stand for truth and your dedication and regular visit of patient at Alexandria Hospital, in Virginia. When you went to Ethiopia I noticed that you were trying to give a closer attention to your sick MENFESAWI LIJOCH,(MK) who have been sick for so long that their soul is soaked with HATE AND REVANGE AND VINGENCE (total opposite of LOVE, the foundation of the true church TEWAHDO). It is an open secret that there is no "LOVE" in MK dictionary. It is obvious from where they leaned their guidance,like "accuse, kill, betray, hate, disrespect, chase good people from church, etc). You should never give up on the TRUTH AND THE LORD. Stand by them no matter what happens to you and your name. The Lord is watching. He always defend people who are ready to sacrifice foe the truth. Please keep up the fight against our MENFESAWI enemy. BY THE HELP OF OUR LORD, WE SHALL OVERCOME.
  CONGRAT FOR YOUR BOOK
  Your MENFESAWI STUDENT

  ReplyDelete
 16. እኔ በጣም ያስቸገረኝ ነገር ይህ ሁሉ በአንድ ሰው ላይ ያነጣጠረ ከፍተኛ የስም ማጥፋትና ሰውን የማባረር ሥራ ለምን ተሠራ? ለሠሪውስ ማን እንዲህ እንዲሆን ፈቀደ? የወሳኙ አካል አባላትስ ነገሮችን የመረዳትና ውሳኔ የማስተላለፍ ሂደታቸው በምን ላይ የተመሠረተ ነው? ይህን ሁሉ የሠሩ በጣም ቅንና ጥሩ አባት ለምን እንዲህ ያለ በደል ሊደርስባቸው ቻለ? ስለ ሰማዕትነት አውርታችኋል ለመሆኑ የቀድሞዎቹ ሰማዕታት የተቀበሉት መከራ እኮ ከቤተ ክርስቲያን ባዕድ በሆኑ ጨካኞች፣ ከሃዲዎችና፣ መናፍቃን ነበር አሁኖቹ ሰማዕታት ደግሞ በእነዚህ አምሳል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በተደበቁ በቲን የግብር ከፋይ የተመዘገቡ ነጋዴ ድርጅቶችና፣ ያለ ደንባቸው ቲን ቁጥር እናውጣ እያሉ በደንባቸው የሌለውን ሲኖዶስ ያልፈቀደውን ደሥራ አስኪያጅ የሚያስፈቅዱ፣ ….. ነው ማለት ነው፡፡ ሃ ሃ ሃ ሃ ሃ አሁን ለአንዱ ይፈቀዳል ከዚያ አዳሜ በየማህበሩ ቲን ይሰጠን ከዚያ ህጋዊ ነን እያሉ ይችን ቤተ ክርስቲያን ለማጥፋት ጥላቷ መብዛቱ፡፡ ታሪክ ነው ታሪክ ነው ታሪክ ነው ታሪክ ነው ዝም ብሎ ማየት ነው፡፡ ታሪክ ደጉ ሁሉንም በኋላ እንደ አባ ሰረቀ ያስነብበናል፡፡

  ReplyDelete
 17. Good to hear such a positive narration about Aba Sereke from this blog. I didn't expect you would hail the father so positively after he named this blog a "devil" in one of his articles previously.
  see the link below to refresh your memory.
  http://www.eotcssd.org/message/35-message/184-blogs-for-gospel-or-crime-in-eotc.html

  ReplyDelete
 18. 'ማርያም ሰው በመሆኗ የውርስ ኀጢአት አለባት የሚለውን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንደ ኑፋቄ በመቁጠር'
  የትኛው የኦርቶዶክስ መጻፍ ነው የሚናገረው ይህንን ቃል??? ይህ ምንፍቅና አይደለም አላችሁ? አዎ እዉነት ነው ለመናፍቃን ይህ ምንፍቅና አይደለም። ለኛ ለኦርቶዶክሶች ግን እጅግ ምንፍቅና ነው። "የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ፥ እንደ ሰዶም በሆንነ እንደ ገሞራም በመሰልነ ነበር።" ኢሳ 1፡9

  ReplyDelete
 19. Orthodox Christians have usually understood Roman Catholicism as professing St. Augustine's teaching that everyone bears not only the consequence, but also the guilt, of Adam's sin. This teaching appears to have been confirmed by multiple councils, the first of them being the Council of Orange in 529. This difference between the two Churches in their understanding of the original sin was one of the doctrinal reasons underlying the Catholic Church's declaration of its dogma of the Immaculate Conception in the 19th century, a dogma that is rejected by the Orthodox Church.

  http://orthodoxwiki.org/Original_sin

  ReplyDelete
 20. I know most of us have the habit of accepting other than our fellow country men. That is why I cut and paste this from coptic dogma than your own church dogma or Aba Serek's boo


  Doctrine, Practice and Spirituality The Coptic Orthodox Church is a deeply spiritual and conservative church that does not want to change any of the doctrines or rites as handed down to her by the founding Fathers of the Church in the early centuries of Christianity. The following are the seven basic corners of the Coptic Orthodox Church doctrine and practice: (a) The Bible: The Holy Bible is the basic foundation of Coptic Orthodox faith and life. It is used frequently during communal prayers, Bible Study Groups are conducted in all churches, and every family and individual is encouraged to study it at home. (b) The Creed: In her liturgies sacraments, prayers and all other ministries, the Coptic Orthodox Church uses the Nicean Constantinoplean Creed. It best summarises her doctrine. (c) The Sacraments: A sacrament is an invisible grace given under a visible (material) sign. It should be administrated by a canonical priest. The Coptic Orthodox Church believes in seven sacraments and these are: Baptism, Chrismation (Confirmation), Repentance and Confession, Eucharist, Unction of the Sick, Matrimony and Priesthood. (d) The Virgin Mary: Saint Mary is called, ‘‘Theotokos’’ meaning Mother of God. The Coptic Orthodox Church believes in the perpetual virginity of Saint Mary, before, during, and after the birth of the Lord Jesus Christ. Like all other human beings, Saint Mary was born with the original sin (Ps. 51; Rom 5:12-19; 1 Cor. 15:22); but sanctified by the descent of the Holy Spirit since the incarnation of the Son of God. (e) Intercession: The church asks, not only for the intercession of Saint Mary, but also for that of the angels, apostles, saints and martyrs. (f) Fasting: Fasting for the Coptic Orthodox Church is a spiritual practice for the whole congregation, and it is not merely fasting from animal protein, but fasting helps one to conquer his bad habits and to express his love of God by trying to come closer to him. Fasting lasts for more than half of the year on different occasions, such as lent and advent. (g)

  http://oakleighcopts.org/copticorthodox.html

  ReplyDelete
 21. ማህበረ ቅዱሳን እንደ ጣዖት የሚቆጥሯውና ለመክካም አስተዳደር ምሳሌ ለሃይማኖት ጠበቃ አድርገው የሚቆጥሯቸው ግብጻውያን የኦርቶዶክስ አባቶች የሚያምኑት

  d) The Virgin Mary: Saint Mary is called, ‘‘Theotokos’’ meaning Mother of God. The Coptic Orthodox Church believes in the perpetual virginity of Saint Mary, before, during, and after the birth of the Lord Jesus Christ. Like all other human beings, Saint Mary was born with the original sin (Ps. 51; Rom 5:12-19; 1 Cor. 15:22); but sanctified by the descent of the Holy Spirit since the incarnation of the Son of God.

  ትርጉም፣ ድንግል ማርያም፣ ቅድሰት ማርያም ወላዲተ አምላች ትባላለች፣ የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እመቤታችን ዘላለማዊ ድንግል መሆኗን ጌታችንን ከመውለዷ በፊት፣ በወለደች ጊዜ ከወለደችም በኋላ ድንግል መሆኗን እናምናለን፡፡ እንደማንኛውም ሰው በጥንተ አብሶ (ከአዳም በተወረሰ ኃጢአት) መወለዷን እናምናለን፡፡ (መዝ 51፣ ሮሜ 5:12-19; 1 ቆሮ. 15:22) ነገር ግን ጌታችንን በጸነሰች ጊዜ በጀንፈስ ቅዱስ አማካኘነት ንጽት እንደሆነች እናምናለን፡፡ ትርጉም፣ ድንግል ማርያም፣ ቅድሰት ማርያም ወላዲተ አምላች ትባላለች፣ የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እመቤታችን ዘላለማዊ ድንግል መሆኗን ጌታችንን ከመውለዷ በፊት፣ በወለደች ጊዜ ከወለደችም በኋላ ድንግል መሆኗን እናምናለን፡፡ እንደማንኛውም ሰው በጥንተ አብሶ (ከአዳም በተወረሰ ኃጢአት) መወለዷን እናምናለን፡፡ (መዝ 51፣ ሮሜ 5:12-19; 1 ቆሮ. 15:22) ነገር ግን ጌታችንን በጸነሰች ጊዜ በጀንፈስ ቅዱስ አማካኘነት ንጽሐት እንደሆነች እናምናለን፡፡  ችግሩ ግን ለማኅበራቱ የዶግማ ጉዳይ ነው አጀንዳቸው የሚለው ነው፡፡
  ችግሩ ግን ለማኅበራቱ የዶግማ ጉዳይ ነው አጀንዳቸው የሚለው ነው፡፡
  ችግሩ ግን ለማኅበራቱ የዶግማ ጉዳይ ነው አጀንዳቸው የሚለው ነው፡፡
  ችግሩ ግን ለማኅበራቱ የዶግማ ጉዳይ ነው አጀንዳቸው የሚለው ነው፡፡ ...........................................................................

  ReplyDelete
  Replies
  1. talak merdo leewnetegna orthodoxawyan
   bezemenachin be betekrstian shifan betarik yemnawkew"gubae kelebat" tekahede be nitsiht emebetachnm lay yesdbn nada awerede.
   yesua chernet ena amalajinet ayleyen

   Delete
  2. becareful on what you are saying, when you insult the true teaching of the church as if it is the teaching of "gubae kelebat" you are accusing all good saints who believed in the same teaching. If you don't understand it, please open your heart and ask God he will give you wisdom. The holy spirit will guide you to the absolute truth. You need to ask for pure heart also. Please do not be emotional and do not think as if you are the only true tewahdo left. Ask God, he will show you where you stand. May God bless your heart.

   Delete
 22. Thank you for interpreting this, i thought most MK members are highly educated that they can read and understand it, isn't their leader a doctor and most of them are higher education graduates?

  ReplyDelete
 23. ችግሩ ምን መሰለህ እነሱ ማንበበ የሚችሉት ማህበራቸው ያላቸውን ብቻ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያንን እምነትና ሥርዓት ቢያነቡማ በማህበር ባልተመሩ ነበር

  ReplyDelete
 24. MK MEMBERS ARE HIGHLY EDUCATED BEZI ALEM ENJI BEMENFESAWI AYDELEM THAT IS THE PROBLEM

  ReplyDelete
 25. U wrong most of them amaharic graduate such like daniel kisret.

  ReplyDelete
 26. Guys don't rush to judge anyone. God is just, you will be judged for what you misjudge.
  I believe Virgin Mary was not free of the original sin, like what our Coptic brethren do. But Christ is God the Son Incarnate.

  But all this doesn't make Aba Sereke and Begashaw free from mistakes. It is a very irritating theological fallacy to say about our Lord "እግዚአብሔር አትበሉ ኢየሱስ በሉ". The tone of this heresy is very very dangerous, even the Devil might not have thought about it.

  The LORD, God of Abraham guide us to His way.

  ReplyDelete
 27. whoever wrote this "The tone of this heresy is very very dangerous, even the Devil might not have thought about it".

  May be you don't understand the church teaching or your are blinded by hate and you called this "እግዚአብሔር አትበሉ ኢየሱስ በሉ" as you found some kind of Heresy. Your spritual fathers, the Pharisees, should jump for joy from their graves, to know that a son/daughter (MK) like you exists in this civilized world. Please tell me, what is wrong with this "እግዚአብሔር አትበሉ ኢየሱስ በሉ".
  As I try to understand it in pure mind. When you say "እግዚአብሔር" you invoking The Father, the Son and the Holy Spirit. It true the in trinity one lives in the other. But when we talk about context, we stick to the contextual meaning. If I am asked about who turned water to wine I would say Lord Jesus Christ. I know that the Son is "እግዚአብሔር" BETELYE AKALU. However, answered "እግዚአብሔር" and some one says እግዚአብሔር አትበሉ ኢየሱስ በሉ, how can that be heresy. For example, if someone asked "who died for us" I would first say Lord Jesus Christ, before I say እግዚአብሔር. Then the next question would be is he እግዚአብሔር. The answer would be absolutely YES. What if I answered እግዚአብሔር first, I probably invoke trinity and we don't say that in our church. Even when we say it እግዚአብሔር died we have to mention BESEGA. I don't think there is heresy, it is just misunderstanding and hate or jealousy.
  So picking one sentence and running to accuse a devoted brother is not a behavior of good christian. Even if we found out that there is heresy, I always believe in second chance. If you agree you and me have been given thousand chances so far. Because God of Israel is a forgiving God.

  peace

  ReplyDelete
 28. mahberekidusan kidusan sayhonu mahbere hatian nachew !!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 29. God bless maheberekidusan but i will for aba sereke(leba hone, being tiff)our mother, mother of God vergin mary never has and/or had original sin but the diabilos said this one
  Getachew chane from Addis Ababa university (Memhir).

  ReplyDelete
 30. please stop and destroying our holy orthodox church by Pickering one another. The Holy Synod is the ultimate decision maker on such an issue not Mahebere Kidusan or Abba selama.why do not yoy pass it to The Holy Synod for decision?

  ReplyDelete
 31. ስለ ማህበረ ቅዱሳን ክፋ ተጽፎ ስለ ደቂቀ እስቲፋኖስ መልካም የተጻፈበት እንዲሁም ስለ እመቤታችን የውርስ ሃጢያት እንደ ኦርቶዶክሳዊ ትምሕርት የቀረበበት መጽሃፍ ከተዋህዶ ኣባት ቀረበ ብሎ ለማመን ያስቸግራል ይቅር ይበለን!!!!!

  ReplyDelete