Monday, January 9, 2012

ነጋዴው ማህበረ ቅዱሳን የቲን (Tin) ቊጥር ለማውጣት እንቅስቃሴ መጀመሩ ተሰማ

በሃይማኖት ካባ ተሸፍኖ በቤተክርስቲያናችን ስም ሲነግድና ስንጥቅ ሲያተርፍ የኖረውና አሁንም በተመሳሳይ መንገድ የንግድ ተቋማቱን በማስፋፋት ላይ የሚገኘው ነጋዴው ማህበረ ቅዱሳን ለጠቅላይ ቤተ ክህነት በጻፈው ደብዳቤ ጉዳዩ ለሚመለከተው የመንግስት አካል የቲን ቁጥር ይሰጠው ዘንድ እንዲጻፍለት መጠየቁን ምንጮቻችን ገለጹ፡፡ አባ ሰረቀ ከሀላፊነት ከተነሱ በኋላና የግንቦቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ስበሰባ ከመድረሱ በፊት፣ የንግዱን አለም በይፋ ለመቀላቀል እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የሚናሩት ምንጮቻችን፣ በአባ ሰረቀ ምትክ አዲስ የተሾሙት አዲሱ የመምሪያ ሃላፊን አባ ህሩይን በጥቅማጥቅም እንደያዘ የሚናገሩ አልጠፉም፡፡ ለዚህም እንደማስረጃ የሚያነሱት አባ ህሩይ ከዚህ ቀደም ያልታየና ጳጳሳት የሚያደርጉትን አይነት ትልቅ የአንገት መስቀል አድርገው መታየታቸውን ነው፡፡ እንደእነዚህ ሰዎች ጥርጣሬ ማህበረ ቅዱሳን ለአዲሱ የመምሪያ ሃላፊ መስቀሉን በስጦታ መልክ “የገቢ” ብሏቸዋል ነው የሚባለው፡፡ በማህበሩ ሰጥቶ የመቀበል ስልትም እርሳቸው የገቢ እንደተባሉ ሁሉ፣ ማህበሩ የሚፈልገውን ነገር የማድረግ የውዴታ ግዴታ ውስጥ እንደገቡ ይታሰባል፡፡ ምናልባትም ያስገባው ማመልከቻ ተቀባይነት አግኝቶ ደብዳቤው ከተጻፈለት ያው “የወጪ” ተባለ ማለት ነው፡፡ ብዙዎችም በዚሁ ቤተ ክርስቲያናችንን ለቆ ቢወጣልን ጥሩ ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ይሰጣሉ፡፡
ማህበረ ቅዱሳን ከዚህ ቀደም አባ ሠረቀ አላሠራ ስላሉኝ ነው ቀደጠቅላይ ቤተ ክህነት ለመጻፍ የተገደድሁት ሲል በተደጋጋሚ መናገሩ የሚታወስ ሲሆን፣ አባ ሠረቀ ከተነሱም በኋላ በዚያው በለመደው መንገድ አስተዳደራዊ ሰንሰለትን ጠብቆ መስራት አለመፈለጉ፣ ማህበሩ የደረሰበትን የትዕቢት ደረጃ የሚያሳይ ሆኗል፡፡ ከዚህ በኋላም ራሱን እንደአንድ በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ስር እንዳለ ማህበር ሳይሆን፣ ከዚያ በላይ እንዳለ አካል መመልከቱ እንደማይቀርና ራሱን ሲኖዶሱን የሚተካ አካል አድርጎ ወደመሰየም መሸጋገሩ የማይቀርና የማህበሩ መዳረሻ እርሱ መሆኑን ማህበሩን በቅርብ የሚያውቁትና አካሄዱን በንቃት እየተከታተሉ የሚገኙ ወገኖች ይናገራሉ፡፡
ማህበሩ ከአባ ሠረቀ መነሳት በኋላም ከጠቅላይ ቤተክህነት ጋር በቀጥታ መጻጻፉን መቀጠሉ፣ ቀድሞም ቢሆን ችግር እየፈጠረ የነበረው ራሱ ማህበሩ እንጂ፣ በሕግና በስርዐትን ተከትለህ ስራ ያሉት አባ ሠረቀ አለመሆናቸውን በዚህ ለጠቅላይ ቤተክህነት ጽ/ቤት በጻፈው ደብዳቤም አረጋግጧል፡፡ ከማህበሩ ይልቅ የሚገርመው የማህበሩን ደብዳቤ ተመልክቶ፣ ይህንማ ለሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ነው ማስገባት ያለብህ በማለትና በመመለስ ፈንታ፣ ለሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ “አስተያየት ይሰጥበት” ሲል የመራው የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ነው፡፡ ማህበሩ በቤተክርስቲያን ላይ የባሰ ጥፋትና አልታዘዝ ባይነትን እንዲያሳይ ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ ድጋፍ እየሰጡ የሚገኙትና ለማህበሩ የልብ ልብ የሰጡት የጠቅላይ ቤተ ክህነት ስራ አስኪያጅ አባ ፊልጶስ በዚህ ውስጥ ትልቅ ተጠያቂነት እንዳለባቸው ብዙዎች ይናራሉ፡፡
ማህበረ ቅዱሳን በአሁኑ ጊዜ የቲን ቁጥር ለማውጣት መንቀሳቀሱና ወደ ህጋዊ መንገድ መምጣቱ መልካም ቢሆንም፣ ዋና አላማው ግን እስካሁን ኦዲት ሳይደረግና በተለያዩ ግለሰቦች ስም በየባንኩ ተበትኖ የሚገኘውንና የግለሰቦች መጠቀሚያ የሆነውን በቤተክርስቲያን ስም የተሰበሰበውን ሀብት ለማሸሽ የታሰበ ነገር ቢኖር ነው ሲሉ ጥርጣሬያቸውን ይገልጻሉ፡፡ ማህበረ ቅዱሳን ቤተክርስቲያንን የሚፈልጋት በስሟ ለመነገድና ህጋዊ ሽፋን እንድትሰጠው ብቻ መሆኑን የሚናገሩት ምንጮቻችን፣ ቤተክርስቲያን ይህን የማህበሩን አደገኛ አካሄድ የማታስቆመው እስከመቼ ነው ሲሉም ይጠይቃሉ፡፡  

24 comments:

 1. Aye mk blese blese merkato gebase yisalesal. anchi yenebsat leba

  ReplyDelete
 2. Mahibere Kidusan min Aderegachihu smonun Dege Selam yetebalew bilog yesewn sim mansat aref sil temesgen bilen nebere ahun degimo enante basachihu Aba Hiruy sira Kjemeru gena 2 wer honachew wedefit yitayalu bemeseretu Aba Hiruy menkuse mehonachew wedefit yigeletsal hulunim neger Kemanim Befit Mahibere Kidusan yawkal gin Ahun metayet yalebachew besrachew new Aba Selamawoch yesewn sim ansitachihu atasadu bedel new egiziabher yeshefenewn yesew neger enante min agebachihu Mahibere Kidusan degimo melkam siraw yibeltsal ene abal balhonim degafi neg Ahun Aba Hiruyn mesdebachihu hatsiat newna nisiha gibu

  ReplyDelete
 3. Tada lezhi lemen yahulu merkato yikenahe. I say congradulation to all eotc followers fot Negadew out from our chirch. Mk is the floop side of simon mesreye. Inaddition , aba hiruye or Heyeru he was stealing half mellion dollars from wolkite and left overnite. So, that not business as usual.

  ReplyDelete
 4. ከመቅናት መስራት፤፡ አሁንስ አሮጊት ሆናችሁ። ወሬ ከምትለቃቅሙ ለምን ሰርታችሁ አታሳዩንም።

  ReplyDelete
 5. የማኅበረ ቅዱሳን የተንኰል ዓላማ አሁን ግልጽ እየሆነ መጥቷል። ይኸውም፣
  1/ ወደንግዱ ዓለም ከተቀላቀለ ከቤተክርስቲያን ቁጥጥር ውጪ ሆነ ማለት ነው።
  2/ የንግድ ምዝገባ ካከናወነ ቤተክርስቲያን ኦዲት አደርግሃለሁ ልትለው አትችልም።
  3/ነጋዴ ሆኖ የኖረበት የ20 ዓመት የገፈፋ ገንዘብ ጉዳይ ተከድኖ እንደአዲስ «ሀ» ብሎ ስለሚጀምር እዳ በደሉን ሁሉ ከደነው ማለት ነው።
  4/መንግሥት ይህን ሁሉ ካፒታል ስታፈራ የሚጠበቅብህን ግብርና ታክስ አልከፈልክም ብሎ እንዳይጠይቀው ወይም እንዲጠየቅ የሚፈልግ ካለ በዚህ ምዝገባ ወደሕጋዊ ከለላ በዘዴ ተቀላቀለ ማለት ነው።
  4/በመጨረሻም ቤተክርስቲያን ገፋችኝ፣ ወረወረችኝ ብሎ ራሱን የቻለ «ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር» ሆኖ ክርስቲያናዊ ድርጅት ወደመሆን ዞረ ማለት ነው።
  ብዙዎቻችን የዚህን ማኅበር ዓላማ ስለምናውቅ ይህ የአሁኑ ጉዳይ ይጠበቅ የነበረው መሆኑን እንረዳለን። በአደንዛዥ አዚሙ አስክሮ የመንግሥተ ሰማያት ብቸኛ መንገድ እንደሆነ ለሚያምኑ ደጋፊዎቹ ይህ አሳፋሪ ነው። Shame on you!!በማለት ከአዚሙ አገዛዝ የሚላቀቁበት ጊዜ ቢኖር አሁን ነበር። ግን ምን ያደርጋል፣ ይህንን የተነገረው ቃል ደርሶባቸዋልና አይችሉም።
  « ገላትያ3፥1 የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ፥ በዓይናችሁ ፊት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተሰቀለ ሆኖ ተሥሎ ነበር፤ ለእውነት እንዳትታዘዙ አዚም ያደረገባችሁ ማን ነው?» ብሎ ጳውሎስ የገላትያ ሰዎችን እንደጠየቀው እነዚህን የኛዎቹን ገላትያዎች አዚም ያደረገባችሁ ማነው?» ብለን ብንጠይቃቸው «የፈለገውን ብታወሩ MK ነፍሳችን ነው እንደሚሉ እናውቃለን። አንዴ በአዚሙ መንፈስ ተነክተዋልና።

  ReplyDelete
 6. ይህች ብሎግ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቤተ ክርስቲያን እየተባባሱ የመጡ አማጻዎችን፣ ክህደቶችና የስሐተት ትምህርቶችን፣ በማጋለጥ ማስጠንቀቂያዎችንና ትምህርቶችን ለመስጠት የተዘጋጀች ናት።
  እንዲሁም በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ የተነሡ ሁለት ኃያላን እነርሱም ማህበረ ቅዱሳን እና ቤተ ክርስቲያናችን ተሃድሶ[መሻሻል] ያስፈልጋታል የሚሉ ወገኖች የሚወያዩባት ነጻ መድረክ ናት። በዚህች መድረግ የሰውን ስም ከማጥፋት እና ከስድብ ነጻ በሆነ ሥነ ጽሑፋዊ ጨዋነት መሳተፍ እና አስተያየት መስጠት ይቻላል። የግለሰብን ስም ያለ እውነተኛ መረጃ በመጥፎ የሚያነሱ ሥነ ጽሑፍም ሆነ አስተያየት ብሎጓ ፈጽሞ አትቀበልም።
  ብሎጓ የሁለቱን ሐሳቦች እና አመለካከቶች ከመጽሔቶቻቸው፤ ከመጻሕፍቶቻቸው እና ከስብከቶቻቸው ታቀርባለች። እንዲሁም ወቅታዊ እና ትኩስ የሆኑ የቤተ ክርስቲያናችን ዜናዎችንም ትዘግባለች።
  ይህን የውይይት መድረክ የከፍትንበት ምክንያት የቤተ ክርስቲያናችን ምእመን በተባራሪ ወሬዎች ግራ ሳይጋባ ሁሉንም በውል ተረድቶ የሚጠቅመውን እንዲይዝ ራሱንም ከወንበዴዎች እንዲጠብቅ ለመርዳት ነው። kkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkk
  bewinet keledachihubat yihichin betekiristiyan
  any ways "" BUY THE TRUTH DON"T SELL IT ""

  ReplyDelete
 7. ሠይፈ ገብርኤልJanuary 9, 2012 at 11:45 PM

  አውቆ የሚያጠፋን መምከር አዳጋች እንደሆነ እያየን ነው ፤ አሁንም ያላችሁበትን ጐጥ ብታዩት በማለት ከሰሞኑ ከቃኘሁዋቸው ድኀረ ገጾች ሥራ ቆራርጨ አቅርቤላችኋለሁ
  - ደጀ ሰላም፡- በድኀረ ገጹ ላይ ቤዘ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ የሚል በፎቶ ላይ የተጻፈ ጽሁፍ ከማሳየቱ በስተቀር ስለ ልደት በዓል ምንም አልዘገበም ፤ እንደ ባህላችንም ምንም መልእክት አላስተላለፈም ፡፡ ለዚህ ድህረ ገጽ ጠቃሚው የመ/ር ዘመድኩን ጉዳይ ነው
  - አባ ሰላማ፡- የልደት በዓል መኖሩም ትዝ ያለው አይመስልም ፣ ለልደት ያቀረበው የተለመደውን ስለ ማኀበረ ቅዱሳን አሉባልታ ነው ፡፡ በዓሉን አስመልክቶ ምንም መንፈሳዊ ትምህርት ወይም መልእክት አላቀረበም
  - ማኀበረ ቅዱሳን፡- የሉቃስ ወንጌልን ተከትሎ የጌታን መወለድ ከለፈፈ በኋላ ልደቱ ክብርና ድንቅ መሆኑን በመግለጽ ፤ ከቀደምት አባቶች ትምህርትም በአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ከተጻፈው የልደት ምንባብ ቀንጭቦ አስመልክቷል
  - ቤተ ጳውሎስ፡- ስለ ጌታ መወለድ ከሉቃስ ወንጌል በመጥቀስ የምሥራቹን ካበሠረ በኋላ ባህላዊ ግድፈታችንን እንድናርም ጠቆም አድርጐ ትምህርት የሚሆን መልዕክት አስተላልፏል
  - መልአኩ አዘዘው፡- የእንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ ምኞቱን ከገለጸ በኋላ ነገረ ልደቱ ለክርስቶስ በሚል አርዕስት ስለ አምላክ ሰው መሆን ምስጢር በውብ አገላለጽ አቅርቧል
  - ቤተ ደጀኔ፡- በዓሉን አስታኮ ያሰፈረው “እውነተኛው የበጎች በር እኔ ነኝ” የሚል ሰፊ ትምህርት ነው
  - ደጀ ብርሃን፡- “እኔ ማነኝ” በሚል ርዕስ ስለ ክርስቶስ ውለታ ረጅም ግጥም አቅርበዋል
  - የብስራት እይታ ከከረመው የተለየ አዲስ አቅርቦት የለውም
  - አሐቲ ተዋህዶ፡- ዕለቱን አስመልክቶ በአሜሪካ የሚገኙትን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያናትን የጓዳ ችግር ገሃድ አውጥቷል
  - አንድ አድርገን፡- የሚባለው ከቶውንም ወቅታዊ ዘገባ የለውም ፤ የሰነበተ የቤተ ክርስቲያን ቃጠሎ ሙከራ ታሪክ ነው የቀረበው
  - አደባባይ፡- በዓሉን አንተርሶ ስለበዓሉ አንዳች ሳይጽፍ ፣ የአዲስ ጉዳይ መጽሔትን ልደት ነው በዓሉ ያደረገው
  - አቤላዊነት፡- የመሲህ መወለድ በማለት የጌታችንን ልደት ትምህርት በሁለት ቋንቋ እያዳቀለ ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ በማለት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክቱን አስተላልፏል
  - ገብረሔር፡- ለበዓሉ ምንም ምርቃት ሳይጨምር እንደባዳ ፈረንጅ እንኳን ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት በሰላም አደረሳችሁ በማለት ዘግቶታል
  - ዳንኤል ክብረት፡- በዓሉን አንተርሶ ያወጣው ምክር አዘል ነገር አገራችንን ለማሳደግ ራሳችንን መለወጥ እንደሚገባንና እራሳችንን እንድንቃኝ የሚያሳስብ ነው
  - እውነተኛ ሕይወት፡- ከተለመደ የወንጌል ትምህርቱ ለየት ያለ አዲስ ነገር አላሳየም
  - ጮራ፡- ልደትን አስታኮ እኔ ጐስቋላ ሰው ነኝ …ማን ያድነኛል በሚል ርዕስ ተከታታይ ትምህርት አቅርቦ በማሳረፊያቸው ያመለከቱት ጥቅር እንዲህ ይላል “ከርኩስ ነገር ንጹሕን ሊያወጣ ማን ይችላል? አንድ እንኳ የሚችል የለም” (ኢዮ. 14፥4)፡፡


  አባት ሆናችሁ ብትዘነጉትም በበኩሌ እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም በጤና አደረሳችሁ እላችኋለሁና ገንዘባችሁ አድርጓትና ተማሩ ፡፡

  ReplyDelete
 8. እኛ ከተናገርን ቆይተናል፡፡ አሁንም የማ/ቅን ነጋዴነትና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የቀጠለውን ብዝበዛ ምእመናን እንዲረዱት ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ የአባ ፓውሎስ ቤተዘመዶች እንኳን፤ የማ/ቅን ያህል አልበዘበዙም፡፡

  ReplyDelete
 9. mak'n drom enawkewalen miyasaznew eyawekin meshewedachin new .eski komblen ahunm jerbachewn eniy!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 10. mak mak mak ay mak!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 11. Maferiyawoc nachihu,America bezu amet yenoru abat mesqel megzat selemayichilu Mk gezto settachew?hafret yilugnita ke enante teftewal malet new

  ReplyDelete
 12. I like the comment of Seife Gabriel God bless you.

  ReplyDelete
 13. Please Please Please Please Please Please Please
  write the article that change the human life and enter The Heaven .........

  ReplyDelete
 14. if mk gets money works for the church. you get money from your family- menafiqan to disturb our church

  ReplyDelete
 15. I like and share your comments,ሠይፈ ገብርኤል. Thank you.Please continue to do so. Most bloggers are not teaching themselves or others at least recently.What surprizes me most that every blogger claims to be a standard for our EOTC dogma, canon and related principles.We EOTC me'ameanan can survive without blogers to inherit the kingdom of God as long as we belive and practice the teachings of Christ per our church books.Belive in one God(Trinity),respect the mother of Jesus(St. Mary) and respect other Saints and Martyrs.

  ReplyDelete
 16. ሠይፈ ገብርኤል in your next review please include other websites such as sundayschool department where it's contents reads like a blog content unless and other wise it has been modified recently.Good job!

  ReplyDelete
 17. Lemen legnas kerebin new aydel.kemawrat serto masayet...

  ReplyDelete
 18. እናንተ የእውነት ወገኖች እባካችሁ በተናጠል ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ በሆነ የጠበቀ አንድነት የአባቱ ልጅ (የዲያብሎስ) የሆነውን 'ማኅበረ ቅዱሳንን' ሃይ በሉት:: ሕዝባችንን በአገር ፍቅር ስም ነጠላውን ለብሶና ተሸፋፍኖ ወደ ገደል ለመክተት ሌት ከቀን እይሠራ ነውና:: ለነገሩ ሰውን የሚወድ ጌታ ይህን እሱን የሚፈልግ ልብ ያለውንና መንፈሳዊ መሪ ያጣውን ወገናችንን ዝም ብሎ ለአውሬ እንደማይሰጠው አምነዋለሁ:: ሆኖም ግን እናንተ በዚች ቤተ ክርስቲያን ተወልዳችሁ ያደጋችሁና ብዙ ሚስጢር ለማወቅ እድሉን ያገኛችሁና በቃሉ ብርሃን በፍቅሩ ያገኛችሁ ወገኖቼ/በጌታ ወንድሞቼ እባካችሁ ለመልካም ነገር እንቅልፍ/ጥቅም/ሥጋ አያሸናፋችሁ/አያሸንፈን በርቱ በርቱ በአንዳንድ ሥራዎቻችሁ ረክቻለሁና እኔም በመንፈስ ለዚህ ሳይማር ላስተማረን በልቶ ሳይጠግብ እያበላ ለቁምነገር ላደረሰንና ግራና ቀኙን ሳያውቅ በፈሪሃ እግዚአብሔር ለተሞላ የዋህ ወገናችን ከእናንተ ጋር አብሬ ልቃትት ቃል እገባላችኋለሁና በርቱ!! ለምድራችን ፈውስ ከፓለቲከኞች ሳይሆን በዚች ቤ/ክ በኩል ከሚመጣ መመልስና ንስሃ መግባት ምክንያት ከላይ ከሰማይ እንጂ ከሌላ አንጠብቅ እንበርታ

  ሕዝባችንን የምህረት አምላክ ይጎብኛት!! አሜን::

  የጌታ ሰላም ይብዛላችሁ

  እህታችሁ

  ሰላም ነኝ

  ReplyDelete
 19. THIS IS ALL RUBISH,WHY DO NOT ALL THE GROUPS TALK ABOUT SOMETHING ESSENTIAL THAN NONSENSE!!!!

  ReplyDelete
 20. Ebachachihu mahibere kidusanoch papasatin bemawared tamagninetachihun atasatun bergit sew fitsum aydelem lisasatu yichilalu. yerasachin gemena mawtat lemin asfelege.yatiat yelelebet yiwgerat yetebalewin enasib.lehulum neger egziabher melkamun neger yadilen amen!

  ReplyDelete
 21. ebachachihu sile waldiba andand neger belun

  ReplyDelete
 22. eyateratere yeminor dabilos new.mikniatumt andm ewnet masrega alanebebkum ;yilkunm tsihufu tertirenal bemalet new yalekew . sigemer tsehafiw yesew sim enkuan astekaklo metsaf yemaychil new kelay ABA SEREKE yemilew sim yemgemeriawa fidel esatu se kehonech leba yemil tirgum alat. silezih sew lemnkef kemerot yerasin ewket ena melkam migbar masadeg bikedm melkam new.

  ReplyDelete