Wednesday, February 29, 2012

የየካቲት 16ቱ የአዶላ ወዩ ቅዱስ ሚካኤልና ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የማኅበረ ቅዱሳን የአመጽ ድራማ አርባ አባላቱን ወኅኒ በማውረድ ተጠናቀቀ - - - Read PDF

በአመጹ ሳቢያ በአለ ንግሱ ሳይከበር ተስተጓጉሏል
በጉጂ ቦረና ሀገረ ስብከት አንዳንድ የማህበረ ቅዱሳን አባላትና በግል ጥቅም የተሳሰሩ ጀሌዎቻቸው በህገ ወጥ መንገድ በያዙት የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ለመቆየት ሲሉ የቤተ ክርስቲያንን ሰላም በማደፍረስ በቀሰቀሱት አመጽ የየካቲት ኪዳነ ምህረት በኣል ሳይከበር መቅረቱንና አመጹን ያስነሱት 40 ያህል ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ከስፍራው የደረሰን ዜና አመለከተ፡፡

Monday, February 27, 2012

መርጌታ ሙሴ ከአጋንንት በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነጻ መውጣቱንና ተሐድሶዎች ባላቸው ሰዎች ጴንጤ ነህ ተብሎ መባረሩን ገለጠ።

 የመርጌታ ሙሴ ቃለ ምልልስ ክፍል ሁለት
መርጌታ ሙሴ ቀደም ሲል ባደረገው ቃለ ምልልስ እንዴት ወደ ጥንቆላ እንደገባ ከሰይጣንም ጋር ስለነበረው ቁርኝት፣ስለፈጸማቸው የኃጢአት ሥራዎች አጫውቶን ነበር። ዛሬ ደግሞ ከተወዳጀው ሰይጣን ጋር እንዴት እንደተለያየና ለመጨረሻ ጊዜ ነጻነቱን ማወጁን እና አሁን ያለውን ህይወቱን ያጫውተናል።
መርጌታ ሙሴ እንደገለጸው ከፍተኛ የአስማት ሥራ ለመማር ወደ ሱዳን በሚጓዝበት ወቅት ንብረቱንና የአስማት መጽሐፉን መዘረፉን፣ በዚያው በተዘረፈበት አካባቢ ጴንጤዎች እንግድነት ተቀብለውት ስለ እግዚአብሔር ቃል ሲነጋገርና ስለ ሃይማኖቱ ሲከራከር ማደሩን፤ ነገር ግን አንድ ወንጌላዊ የመሰከረለት ቃል እንቅልፍ ነሥቶት እንደቆየ ይናገራል።ቀጥሎ መጽሐፍ ቅዱስን በቃሉ ለማጥናት ቢሞክርም የተቆራኘው ሰይጣን ይሰውርበት እንደነበር በኋላ ግን በጸሎት ኃይል አጋንቱ ከርሱ መውጣታቸውን ተናግሯል። ሆኖም አጋንንቱ በተኛበት ሊሊት ሊገሉት መጥተው ሲይዙት ሌሊቱን ሙሉ መልካ ሚካኤል እየደገመ ሲታገል ማደሩን ነገር ግን ከአቅሙ በላይ እንደሆኑበት አውቆ፤ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሲገስጻቸው አጋንንቱ ከርሱ ሸሽተው መበታናቸውንና ከዚያንጊዜ ጀምሮ ኢየሱስን መውደዱን ይናገራል።

Sunday, February 26, 2012

ማህበረ ቅዱሳን በምዕራብ ኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል ተሰሚነት ማጣቱ ተገለጸ፤ በጥር ወር ብቻ 14 ጉባኤዎችን ለመሰረዝ ተገዷል - - - Read PDF

ከውጪ አገር በሚመጣ የአገልግሎት ግብዣ “እኔ ልሂድ፣ እኔ ልሂድ” በሚል የማህበሩ አገልጋዮች እርስ በርስ እየተወዛገቡ ነው

እግዚአብሔር በዘመናችን ለቤተክርስቲያናችን ያስነሳቸውን ወንጌል ሰባኪዎች “ተሐድሶ” በሚል ፍረጃው፣ እንደ አባ ፊልጶስ ያሉ አንዳንድ ሊቃነ ጳጳሳቱን ተገን በማድረግና በቀጠራቸው ወሮበሎች በአዲስ አበባ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ሁከት በማስነሳት ከዐውደ ምሕረት እንዲርቁና ከሕዝቡ ልብ እንዲወጡ ለማድረግ ከፍተኛ ትግል ሲያደርግ የቆየውና በእነርሱ እግር ራሱን ለመተካት በመውተርተር ላይ ያለው ማህበረ ቅዱሳን በምዕራብ ኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል ተሰሚነቱ እየቀነሰ መምጣቱን ከስፍራው የደረሰን ዜና አመለከተ፡፡

ለተሰሚነቱ መቀነስ ምክንያቱ ማህበሩ የሚያዘጋጃቸው ጉባኤዎች የሚቀርበው ስብከትም ሆነ ዝማሬዎች የሰውን ትኩረት መሳብ የማይችሉ መሆናቸው ሲሆን አገልጋይ በማጣትም ጭምር መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡ በነዚህና በሌሎቹም ምክንያቶች ከህዝበ ክርስቲያኑ በኩል ተባባሪነት እየቀነሰ መምጣቱን ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡ ጉባኤ በሚያዘጋጅበት ጊዜ የሚወጣለት ሰው እጅግ አነስተኛ ሲሆን፣ በጥር ወር 2004 ዓ.ም ብቻ እንኳን 14 ጉባኤዎች የታጠፉ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል መቱ ላይ 2፣ ወለጋ ውስጥ ደግሞ 3 የታጠፉትን ጉባኤዎቹ መጥቀስ ይቻላል ብለዋል ምንጮቻችን፡፡

Friday, February 24, 2012

ሰባ ስምንት ነፍስ የገደለው ሰው [በላኤ ሰብእ]በጥርኝ ውሃና በማርያም ጥላ ዳነ [ታምረ ማርያም 12፥89-120]።

እኔ መንገድ እውነት ሕይወትም ነኝ በኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም [መጽሐፍ ቅዱስ ዮሐ 146]
ታምረ ማርያም የተባለው ጉደኛ መጽሐፍ ድንግል ማርያምን ያከበረ የሚመስል ነገር ግን ስድብ እና ክህደት የሞላበት መጽሐፍ መሆኑን ደጋግመን ለማሳየት ሞክረናል። መጽሐፍ ቅዱስ ከተጻፈ 1400 ዓመት በኋላ በኢትዮጵያ ንጉሥ በዘርዓ ያዕቆብ የተደረሰ ሲሆን በወቅቱ የነበሩ የቤተ ክርስቲያናችን ሊቃውንት እና ምእመናን ይህ ልዩ ወንጌል ከሐዋርያት ትምህርት የወጣ ስለሆነ አንቀበለውም በማለታቸው፣ እስከ አንገታቸው በጉድጓድ ተቀብረው በጭንቅላታቸው ላይ የፈረስና የከብት መንጋ እንደተነዳባቸው ምላሳቸውንና አፍንጫቸውን እንደተቆረጡ እራሱ ታምረ ማርያም ይመሰክራል። [ታምር 24 እና 25 ገጽ 112- 121]

ታምረ ማርያምን ቁጭ ብለን በማስተዋል ብንመረምረው መጽሐፍ ቅዱስን ለመቃወም የክርስትናን ትምህርት ለመበረዝ በጠላት ሆን ተብሎ የተቀመመ ይመስላል። አጼ ዘርዓ ያዕቆብ እስራኤላዊ ነኝ ስለሚል ምን አልባት አይሁዶች መሲሐዊ እምነታችንን ለማጠፋት የፈጸሙት ሴራ ይሆን? ብለን እንድንጠይቅ ያደርገናል። ዘራ ያዕቆብ አይሁዳዊ ነኝ እያለ ይመካ ነበር፤ ከዚያም አልፎ የይሁዳ ነገድ ነኝ ይል ነበር። አባ እስጢፋኖስ ግን ኢትዮጵያዊ ነህ አትዋሽ ከአይሁዳዊነት ይልቅ ክርስቲያን መሆን ይበልጣልና በዚህ አትመካ በማለት እንደተከራከረው ገድለ እስጢፋኖስ ይናገራል [በሕግ አምላክ በፕሮፌሰር ጌታቸው]