Friday, February 24, 2012

ሰባ ስምንት ነፍስ የገደለው ሰው [በላኤ ሰብእ]በጥርኝ ውሃና በማርያም ጥላ ዳነ [ታምረ ማርያም 12፥89-120]።

እኔ መንገድ እውነት ሕይወትም ነኝ በኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም [መጽሐፍ ቅዱስ ዮሐ 146]
ታምረ ማርያም የተባለው ጉደኛ መጽሐፍ ድንግል ማርያምን ያከበረ የሚመስል ነገር ግን ስድብ እና ክህደት የሞላበት መጽሐፍ መሆኑን ደጋግመን ለማሳየት ሞክረናል። መጽሐፍ ቅዱስ ከተጻፈ 1400 ዓመት በኋላ በኢትዮጵያ ንጉሥ በዘርዓ ያዕቆብ የተደረሰ ሲሆን በወቅቱ የነበሩ የቤተ ክርስቲያናችን ሊቃውንት እና ምእመናን ይህ ልዩ ወንጌል ከሐዋርያት ትምህርት የወጣ ስለሆነ አንቀበለውም በማለታቸው፣ እስከ አንገታቸው በጉድጓድ ተቀብረው በጭንቅላታቸው ላይ የፈረስና የከብት መንጋ እንደተነዳባቸው ምላሳቸውንና አፍንጫቸውን እንደተቆረጡ እራሱ ታምረ ማርያም ይመሰክራል። [ታምር 24 እና 25 ገጽ 112- 121]

ታምረ ማርያምን ቁጭ ብለን በማስተዋል ብንመረምረው መጽሐፍ ቅዱስን ለመቃወም የክርስትናን ትምህርት ለመበረዝ በጠላት ሆን ተብሎ የተቀመመ ይመስላል። አጼ ዘርዓ ያዕቆብ እስራኤላዊ ነኝ ስለሚል ምን አልባት አይሁዶች መሲሐዊ እምነታችንን ለማጠፋት የፈጸሙት ሴራ ይሆን? ብለን እንድንጠይቅ ያደርገናል። ዘራ ያዕቆብ አይሁዳዊ ነኝ እያለ ይመካ ነበር፤ ከዚያም አልፎ የይሁዳ ነገድ ነኝ ይል ነበር። አባ እስጢፋኖስ ግን ኢትዮጵያዊ ነህ አትዋሽ ከአይሁዳዊነት ይልቅ ክርስቲያን መሆን ይበልጣልና በዚህ አትመካ በማለት እንደተከራከረው ገድለ እስጢፋኖስ ይናገራል [በሕግ አምላክ በፕሮፌሰር ጌታቸው]


መጽሐፉን ዛሬ መመርመር ለምን አስፈለገ? የሚል ጠያቂ ሊኖር ይችላል፣ መልሳችን አብዛኛው የዋሕ ምእመን እምነቱን የመሠረተው በታምረ ማርያም ላይ ነው የሚል ሥጋት ስላለን ነው። ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲሄድ ታምሯን ሰምቼ ልምጣ እንጂ ወንጌል ሰምቼ ልምጣ ብሎ አያስብም፣ እሑድ እሑድ ታምር የሚያነብ እንጂ ወንጌል ለማስተማር የሚያስብ ቄስም የለንም። 400 000 ካህናት እንዳላት የሚነገርላት ቤተ ክርስቲያናችን ታምረ ማርያም አንብቦ ከማሳለም ያላፈ አገልግሎት የሚሰጥ አይደለም። በተለይም ታምሯን ሰምቶ የሄደ ሥጋውና ደሙን እንደተቀበለ ይቆጠርለታል የሚለው ባዕድ ወንጌል ብዙ ሕዝብ ወደ ስጋውና ደሙ እንዳይደርስ ስላደረገው ይህም የስሕተት ትምህርቶች ውጤት ሆኖ ስላገኘነው፣ ሲኖዶሱ ከተኛበት እስኪነቃ ድረስ ጩኸታችንን አናቆምም። ወደ ተነሳንበት እርስ እንመለስ፥

መጽሐፉቅምርበሚባል አገር አንድ ሰው ነበር በማለት ታሪኩን ይጀምራል

ወኢየበልዕ እክለ ወኢ ሥጋ ላሕም ወኢ ካልአ እንሥሣ አላ ይበልዕ ሥጋ ሰብእ

ትርጉም እህል፥ የላም፥ ሥጋ የሌሎችንም እንሥሳ ሥጋ አይበላም ነበር የሰው ሥጋ ይበላ ነበር እንጂ 68

«ወዘበልዖሙሰ ሰብእ የአክሉ ፸ወ፰ተ ነፍሳተ ወኀልቁ ወተወድኡ ዓርካኒሁ ወፍቁራኒሁ ወአዝማዲሁ ወመገብቱ» ትርጉም «የበላቸውም ሰዎች 78 ነፍሳት ያህላሉ ባልንጀሮቹ ወዳጆቹም ዘመዶቹም ቤተ ሰቦቹም አለቁ ተጨረሱ» 69

ሰውየው ልጆቹን ከበላ በኋላ ከቤት ወጥቶ ሄደ በማለት ታሪኩ ይቀጥላል። ሲዞርም ሁለንተናው በደዌ ሥጋ የታመመ ሰው አገኘ።( 92) ሊበላው አስቦ ነበር ነገር ግን በደዌው ምክንያት ሰለጠላው ሊበላው አልወደደም። በደዌ የተያዘው ሰው ግን ፈጽሞ የተጠማ ስለነበረ በላዔ ሰብን ስለ እግዚአብሔር ብለህ ውሃ አጠጣኝ አለው፣ በላዔ ሰብእ ግን ተቆጣ፣ ለሁለተኛ ጊዜ ስለ ጻድቃን እና ስለ ሰማዕታት አጠጣኝ አለው፤ አሁንም በላዔ ሰብእ ፈጽሞ ተቆጣው ሊያጠጣው አልፈለገም። የተጠማው ሰው ሦስተኛ ፈጣሪን ስለወለደች ስለማርያም አጠጣኝ አለው። በዚህ ጊዜ በላዔ ሰብእ እስኪ ቃልህን ድገመው አለ፤ አምላክን ስለወለደች ስለማርያም ብለህ አጠጣኝ አለው በዚህ ጊዜ በላዔ ሰብእ «ስለዚህች ስም ከሲኦል እንደምታድን ሰምቻለሁ» አለ አሁንም እኔ በሷ ተማጽኛለሁ በማርያም ስም እንካ ጠጣ አለው። ውሃው ትንሽ ስለነበር እጁ ላይ ፈሶ ቀረ ጉሮሮውንም አንጣጣው እንጂ ጥሙን አልቆረጠለትም በማለት ያጭውተናል። ነገሩን ስናስተውለው በላዔ ሰብእ ስለ እግዚአብሔር ተብሎ በእግዚአብሔር ስም ሲለመን፣ እግዚአብሔርን አላውቅም ብሏል። እንዲያውም ስሙ ሲጠራ ተቆጥቷል። በማርያም ተብሎ ሲለመን ግን ውሃውን ሰጠ። የእግዚአብሔርን ይቅርታ ተጠራጥሮ በማርያም ስም በሰጠው ውሃ እንደሚድን ነው ያመነው። የክህደቱ ምሥጢር እዚህ ላይ ነው። ይህ ትምህርት ህዝባችንን በሚቀቀለው ንፍሮ፣ በሚጠመቀው ጠላ፣ በሚዘከረው ዝክር እድናለሁ የሚል አጉል ተስፋ እንዲይዝ አድርጎታል። ዝክርሽን የዘከረ፣ ስምሽን የጠራ ይድናል የሚለው ባዕድ ወንጌል ተቀባይነት እንዲያገኝ የበላዔ ሰብን ልብ ወለድ ታሪክ እንደማስረጃ አድርጎ ለማሳመን ለሕዝብ የቀረበ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ግን እንዲህ ይላል፦

«እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፥ የምንስት፥ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባሪያዎች የምንገዛ፥ በክፋትና በምቀኝነት የንንኖር፥ የምንጠላ፥ እርስ በእርሳችን የመንጠላላ ነበርን። ነገር ግን የመድኃኒታችን የእግዚአብሔር ቸርነትና ሰውን መውደዱ በተገለጠ ጊዜ፥ እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥ እና ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም፤ ያን መንፈስም በጸጋው ጸeቀን በዘላለም ሕይወት ተስፋ ወራሾች እንድንሆን፥ በመኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ ላይ አትርፎ አፈሰሰው»። ቲቶ 3፥3-7
እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለነበረው ሥራ አይደለም የሚለውን እውነተኛ ወንጌል ለመሸፈን ጠላት በጥርኝ ውሃ ጽድቅ አለ ብሎ አታለለን። ይገርማል!
ታሪኩ ይቀጥልና የምድሩን ጨርሶ በላይ በሰማይ በእግዚአብሐር የፍርድ ዙፋን የተከናወነውን በታዛቢነት ተቀምጦ ያየ ይመስል ሊነግረን ይሞክራል። በላዔ ሰብእ አንድ ዋሻ ውስጥ ገብቶ ሞተ «ወመጽኡ መላእክተ ጽልመት በአፍርሆ ወበ አደንግጾ ወከበብዎ ወአውጽኡ ነፍሶ በጕጸት ወበግዱድ» ትርጉም «በማስፈራትና በማስደንገጥ የጨለማ አበጋዞች አጋንንት መጥተው ከበቡት በመቀማትና በግድ ነፍሱን ከሥጋው ለዩ» ይላል ደራሲው ይህ ሁሉ ሲሆን ቁጭ ብሎ የሚመለከት ይመስላልይህ በእንዲህ እንዳለ መላእክት ይህን ጉዳይ ለማርያም ነገሯት ድንግል ማርያም ግን በስሟ ያጠጣውን ቀዝቃዛ ጽዋ ውሃ በጎኑ ተሸክሞ ስላየችቅው ደስ አላት

«ወርእየት እግዝእትነ ቅድስት ድንግል ወላዲተ አምላክ በገቦሁ ማየ ምልአ ሕፍን ዘአስተየ ለነዳይ ምጽዋተ ቤእንተ ስማ ወተፈስሐት ሶቤሃ»
ትርጉም «እመቤታችን ስለ ስሟ ለድሀ ምጽዋት አድርጎ ያጠጣውን ጥርኝ ውሃ በጎኑ አይታ ያን ጊዜ ደስ አላት» ማለት ነው።

ነፍሳት በምድር ላይ እንደፈለጋቸው ሲቀላውጡ ኖረው አንድ ቀን የሰጡትን ውሃ ወደ ሰማይ ሲሄዱ ተሸክመው እንደሚገኙ የሚያስተምር የክርስትና ትምህርት የለም። የዚህ ነፍሰ ገዳይ ነፍስ ግን በጎኗ ጥርኝ ውሃ ተሸክማ ስትሄድ ማርያም አየችና ደስ አላት ይለናል። ነፍሳት ወደ ማርያም ሳይደርሱ ወደ እግዚአብሔር እንደማይቀርቡ 111 ላይ ይናገራል ድንግል ማርያም የበላዔ ሰብእን ነፍስ ውሃ ተሸክማ ያየቻት በዚህ ምክንያት ነው።

በመጨረሻ መላእክት የባላዔ ሰብእን ነፍስ ወደ እግዚአብሔር ፊት አደረሷትና ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት ጣሏት የሚል ትእዛዝ ከዙፋኑ ወጣ ይላል። በዚህ ጊዜ ድንግል ማርያም ማርልኝ እያለች ለመነች በስሜ ቀዝቃዛ ጽዋ ውሃ ያጠጣውን ልትምርልኝ ቃል ገብተህልኝ አልነበረምን? አለች። እግዚአብሔርም ፍርዱን ገልብጦ ሚካኤልን ጥርኝ ውሃንና 78ቱን ነፍሳት መዝንልኝ አለው። ሚካኤልም ውሃንና 78ቱን ነፍሳት ሲመዝን ውሃ ቀለለ ነፍሳት ግን ክብደት አሳዩ ይላል። ድንግል ማርያም ግን ፈጠን ብላ በውሃው ላይ ጥላዋን ጣለችበት በዚህ ጊዜ ውሃው ክብደት አሳየ ነፍሳት ግን ቀለሉ፤ በላዔ ሰብም በማርያም ጥላ ምክንያት ለትንሽ ከሲኦል አመለጠ በማለት አስቂኝ ልቦለድ ያስነብበናል። ይህም ታሪክ እውነት ነው ተብሎ አመታዊ በአል ሆኖ እንዲከበር፣ ዜማ ተዘጋጅቶለት መልክ ተድርሶለት እንዲነገር ተብሎ በየካቲት 16 ቀን ታስቦ ይውላል። የየካቲት አስራ ስድስት የኪዳነ ምሕረት በዓል ይህን ቃል ኪዳን የተመለከተ ነው።

ታሪኩን በጌታና በሐዋርያቱ ቃል ስንገመግመው

የኃጢአት ደሞዝ ሞት ነው። ሮሜ 623 ኃጢአት እና መልካም ሥራ በሚካኤል እንደሚመዘኑ መጽሐፍ ቅዱስ አይናገርም። ኃጢአት በመልካም ሥራ መልካም ሥራ ከኃጢአት ጋር የሚመዘኑ እና ሰውም በዚህ መሠረት የሚድን ከሆነ ክፉ እየሠሩ መልካም መሥራት ይችላል ወደሚል የስሕተት ትምሕርት ይወስዳል።

ታምረ ማርያም የሚያስነብበን ግን ሥራንና ኃጢአትን ከመመዘን ያለፈ ነው በእግዚአብሔር መልክ የተፈጠሩ ክቡራን ነፍሳትን እና ትንሽ ውሃን ነው በአንድ ሚዛን ተመዘኑ ያለው። በእውነቱ 78 ነፍሳትን ከትንሽ ውሃ ጋር ማወዳደሩ እግዚአብሔር ለሰው የሰጠውን ክብር የሚያንጸባርቅ አይደለም። ሰው በእግዚአብሔር ፊት ክቡር ነው ይህም እውነት ኢየሱስ ክርስቶስን እስከሞት አድርሶታል። ሰው ከትንሽ ውሃ ጋር ሊመዘን አይችልም።

የእግዚአብሔር መንግሥት የፍርድ አሠራር እንደ ደብረ ብርሃን ሸንጎ የተዛባ አይደለም። ነፍሳትም በስማይ እንደ ሽንኩርት እየተመዘኑ የሚገመገሙበት ሁኔታም የለም። ፍርድ የሚጠናቀቀው በዚሁ በምድር መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ሲል ያስረዳል "በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም በእርሱ የማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታልዮሐ 317 ፍርድ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እና ባለማመን የሚፈጸም ነው። ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጠው ተብሎ ተጽፋል። በሚካኤል መዛኝነት ሌላ ፍርድ የሚሰጥ መሆኑን ከጌታም ሆነ ከሐዋርያት አልተማርንም። ይህ ባዕድ ወንጌል ነው።

እመቤታችን ድንግል ማርያም ሚዛኑ የሚፈርደውን በመጠበቅ ፋንታ ሚዛን እንዲያጋድል ለማድረግ ጥላዋን ጣለች እያሉ ያላደርገችውን አደረገች በማለት እናታችንን ተሳድበዋል። እጅግ ያስዝናል። እመቤታችን የእግዚአብሔርን ፍርድ የምትጠብቅ ፈሪሃ እግዚአብሔር ያላት በእግዚአብሔር መለኮታዊ ክብር የከበረች ናት። ሚዛን እንዲያጋድል በጥላዋ የፈጸመችው የፍርድ ማዛባት ሥራ የለም። ድንግል ማርያም ቅድስት ናት ቅድስናዋም እግዚአብሔርን በመታዘዝ ቃሉን በመፈጸም እንደቃሉ በመኖር ነው። እግዚአብሔርን አላውቅም ያለ ነፍሰ ገዳይ ለማዳን ስትል ከእግዚአብሔር ይልቅ ለራሷ ስም ክብር በመስጠት ያደረገችው የፍርድ ማዛባት የለም። በናታችን በድንግል ማርያም ላይ የሚነገረው ውሸት ሁሉ ይቁም! ጠላት እርሷን እያከበርሁ ነው እያለ ክብሯን ይንዳል

በእውነቱ ፍርድ በሰማይም እንዲህ የሚዛባ ከሆነ ምን ዋስትና ይኖራል? በዚህ ዓለም ያሉ ዘመድ እና ገንዘብ ያላቸው ሁሉ ፍርድ ሲያዛቡ እናያለን። ብዙዎቻችን እውነተኛ ፍርድ አጥተን እያለቀስን እንኖራለን። የዚህ ዓለም መንግሥት ፍርድ ቤቶች በአድልዎ በጉቦ የተበላሹ ናቸው። በሰማይም ግን እንዲህ ዓይነት የፍርድ የለም። መጽሐፍ ቅዱስ የሚነግረን ሁሉ የሥራውን እንደሚያገኝ እንጂ በመሽሎክሎክ ወደ መንግሥተ ሰማያት ፈጽሞ መግባት እንደማይቻል ነው።

«ዓመፀኛው ወደ ፊት ያምፅ ርኩሱም ወደ ፊት ይርከስ ፤ጻድቁም ወደ ፊት ጽድቅ ያድርግ ቅዱሱም ወደ ፊት ይቀደስ ለእያንዳዱ እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከኔ ጋር አለ» ራእ 2211 እንዲል።

በላኤ ሰብእ በሥራው ሳይሆን በተዛባ ሚዛን ነው ወደ መንግሥተ ሰማያት እንደገባ ተደርጎ የሚቆጠረው። ሚዛን አዛብተው ወደ መንግሥተ ሰማያት ለማስገባት ከማስተማር ይልቅ በክርስቶስ ቤዛነት የእግዚአብሔር ምህረት ተድርጎለት ዳነ ቢል ወንጌል ስለሆነ እውነት ነው እንቀበለዋለን። የኃጢአት ዋጋው የክርስቶ ሞት ሆኖለታልና እኛም በዚህ ነው የዳነው። ሚዛን ተዛብቶ ዳነ የሚለው ትምህርት ግን ክህደት ስለሆነ አንቀበለውም አናስተምረውምም።

የእግዚአብሔር መንግሥት እንዲህ የሚጭበረበር መንግሥት ነውን? አይደለም! ድንግል ማርያምም ይህን ታሪክ አታውቀውም። እንግዲህ ድንግል ንጽሕት፣ ቅድስት፣ ክብርት፣ ብጽዕት እናታችንን እናክብራት፣ ያላደረገችውን አደርገች ያልሰራችውን ሠራች እየተባለ በስሟ ውሸት ሲነገር ዝም አንበል። በረከቷ ይደርብን አሜን!

ዲያቆን ሉሌ ነኝ

44 comments:

 1. እግዚአብሔር ይባርክህ! መንፈስ ቅዱስ እንጂ ሥጋና ደም አልገለጸልህም። በዚህ ተረት ላይ ብዙ ጽሁፍ ያነበብኩ ቢሆንም እንደዚህ ግን ከልቤ የገባ አላገኘሁም። እግዚአብሔር የበለጠ ይግለጽልህ!!

  ReplyDelete
 2. Tiru Milketa new
  Gedle Estifanosenes man new yetsafew
  Lib woled endayhon bemen yitawekal

  ReplyDelete
 3. The Son of God Jesus Christ is the High priest upon us so, no body enter to heaven except through Him( john 14:6.Dear brothers and sisters be careful from false teaching that is out of Holy Bible.Tamire Mariam one of the worst book in our Church.Do not Kidd on your life.If you want get eternal life Jesus is enough for it. Why you guys spend your precious time for reading and listening this life killer book , tamire mariam remove from your house, and from your heart read only holy bible.
  Great Job luele
  God has shined his light upon you Keep it up!

  ReplyDelete
 4. ይህ የጸረ ማርያሞች ወሬ ነው። ፀሐፊው ጸረ ማርያም መሆንዎን በደንብ ያስረዳል። በጭራሽ ትምህርታዊ አይደለም። ቁልጭ ያለች የተሃድሶ ሴራና ጴንጤነት ነው። በላዔ ሰብእ የፈራትን የጌታን እናት የደፈርክ አንተ የመቅደሱ ሰይጣን ነህ። ውጣ ከኢንተርኔት። ኮምፒዩተሬን በአማላጅቱ ምስል አሽቸብሃለሁ። ፀሐይ መንፈሰ እርኩስ ከአባ ሰላማ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. My friend @Brhanu are not you ready to learn from this TERTERET? Yhe yemedafer guday adelem it is a matter of reality and facts.It is over you can not rule and deceive generation like before .Enough is enough . ABA SELAMA EGZIABHER ENANTEN YASNESA AMLAK YETEBEREKE YIHUN.

   Delete
  2. yes yes yes very good comment .

   Delete
  3. @BERHANU "A'AB KALGELETSELET BEKER WELDIN YEMIAWK YELEM"በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም በእርሱ የማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል‚ ዮሐ 3፥17።YEMILEW KAL EKO YEHIYAW EGZIABHER KAL NEW.KEZIH YILIK TAMRE MARIAMN MERETK?"ENDAYASTEWULU YEZIH ALEM GEZHI HASABACHEWN ASAWERE"SILEMIL KALU ALGEREMIM.YIH KAL BERTOLIH ASTEWAY ENDIADERGIH ETSELYALEHU.COZ"YEKALIH FICHI YABERAL HITSANATINIM ASTEWAY YADERGAL"YILAL BIBLE.EGZIABHER YIRDAH.HULACHINIM BERSU REDATNET ENJI BERASACHIN EWKET WENGEL SILALBERALIN.BETEREFE ABA SELAMAWOCH BERTU."BENESU(BE'ALEM) KALEW YILIK BANANTE YALEW SILMIBELT ATIFRU EGZIABHER KENANTE GAR KEHONE MAN YIKAWEMACHIHUAL?WUGIAW KEGETA GAR YIHONAL,BESU SELF DEGMO MESHENEF YELEM.TEBAREKU.(E.B)SON OF JESUS.

   Delete
  4. Dear my bro, Birhanu you should have welling to learn the truth, the bible says there is no salivation without be leaving Jesus, don’t forget we are on new testament no one will go to heaven if you nkill ad eat people, the book called TA AMIRE MARIYAM is the false book which is preaching hiding people from bible truth,
   Let me tell you what is saying this book, ADAM WE HIWAN TEGEBRU BE INTE IGIZI ITNE MARIYAM (mikidm 1 verses 7), meaning Adam and Eve was created because of merry.

   Delete
 5. በጣም ይገርማል !!!!!!!!!!!! ምንድነው የናንተ እምነት?

  ReplyDelete
  Replies
  1. IT IS NOT ALL ABOUT RELIGION IT IS A FACT,TRUTH THE WRITER TO PORTRAY HOW OUR PEOPLE HAD BEEN DECEIVED.ANY LAIMAN CAN JUDGE HOW IT HAS BEEN PRESENTED IN REFERNCE TO THE BIBLE . BLESS YOU ABA SELAMA.I UNDERSTAND THE LITRETURE IS HELPING MANY TO OPEN OUR EYES

   Delete
 6. Why read Matthew chapter 10 no 40-42 ?

  ReplyDelete
 7. አልደረሳችሁ እንደሁ በማለት

  ዲያቆን ሉሌ ይህን በሩቅ ሆኘ የምሰማውን ትምህርት ክፍል ስላስነበብከኝ አመሰግናለሁ ፤ ቆንጆ ትንተና አድርገሃል ፤ ድንቅ ሥራ ነው፡፡ የኔዋ ምልከታና ግንዛቤ የተመረኮዘችው ከተጻፈው በመነሳት እንጅ የተጠቀሰውን መጽሐፍ አንብቤና ተረድቼ ወይም እንደሚባለው ገምግሜ አይደለም፡፡

  ቅዱሳት መጽሐፍት በማን ተጻፉ ?
  1. ቅዱሳኑ (በእምነታቸውና በምግባራቸው መልካምነት የታወቁ ሰዎች) ከመሞታቸው በፊት በህይወት ዘመናቸው እግዚአብሔር የፈጸመላቸውን ገድል ለመመስከር በማለት ራሳቸው ይጽፉታል
  2. ቅዱሳኑ ከሞቱ በኋላ ታሪኩን በሰሙ ተማሪዎቻቸው (ተከታዮቻቸው) ገድልና ተአምሩ ተሰውሮ እንዳይቀር በማሰብ ፣ የሰሙትንና ያዩትን ሳያዛቡ ይጽፋሉ (ወንጌል እንደተጻፈው ዓይነት ማለት ነው)
  3. ቅዱሳኑ ራሳቸው በራዕይ መልክ ሲገለጥላቸው ፣ ያንን ተመርኩዘው ለህዝባቸው (ሙሴ ስለ ዓለም መፈጠር እንደተረከው ወይም ሐዋርያው ዮሐንስ የከተበልንን ዓይነት ማለት) ይጽፋሉ
  የቤተ ክርስቲያን አባቶችም ይህንኑ በመከተል ትክክለኛነቱን መርምረውና አጣርተው ፣ ማስተማሪያነቱንም ፈትሸው መጽሐፍቱን ለቤተ ክርስቲያን ሃይማኖትና እምነት ማስተማሪያነት ይቀበላሉ እንጅ ግለሰብ ባቃዠው ቁጥር እየጻፈ ያመጣውን ሁሉ ወደ ሃይማኖት ማስተማሪያነት አላስገቡም ፡፡

  የቅዱሳት መጽሐፍት የሚጻፉበት ተቀዳሚ ዓላማ ምንድር ነው ?
  1.“በአብ ወልድና መንፈስ ቅዱስ እንዲያምን ምእመናንን ለማስተማርና ለማትጋት” /በሙሉ ይሰመርበት/
  2.በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጹትን ትምህርቶች በኑሮውና በህይወቱ እንዲተገብር ፣ እምነቱን በተቻለው እንዲኖረው ማስተማር ፣ ሃይማኖቱ ያስቸግረኛል ብሎ እንዳይሰንፍም ሌሎች አማኞች የፈጸሙትን እንደ ምሳሌ በማቅረብ ለማጽናት፡፡ (ከዚሁ ትምህርት የተነሳ ዛሬ ዛሬ ተረት እየሆነ ሄደ እንጅ እንደ አብርሃም እንግዳን የሚቀበልና የመጽሐፍ ቅዱሱን ቃል የሚተገብር ወገን እንደነበረ እኛ ሳንሆን ገጠመኙን የታዘቡ ፈረንጆች - የመጽሐፍ ቅዱስን ታሪክ ለማጥናት እሥራኤል ፣ መጽሐፍ ቅዱሱን በተግባር ለማየት ደግሞ ኢትዮጵያ በማለት መስክረዋል)

  ከተጠቀሰው ታሪክ ምን ተማርክበት ብባል ፡-
  1. በምድራዊ ዘመናችን የሰራነው በሙሉ የኃጢአትና የክፋት ምግባር ቢሆንም ትንሽ የቅድስና ፍሬ እንኳን ቢገኝብን መልካም እንደሆነና ዋጋ እንዳለው ተምሬአለሁ፡፡

  2. የኢትዮጵያ የክርስትና እምነት የየዋሃትና የቅዱሶች እንደነበረ ፣ በምርምርና በአእምሮ ብልሃት ያልተፈጠረ መሆኑን ገልጾልኛል ፡፡ ትንሽ እንደ ተማሩት ሰዎች የጥበብ ውጤት ቢሆን ኖሮ እንኳንስ ሌላው ንዋየ ቅዱሳት ፣ መጽሐፍ ቅዱሱም ቢሆን እስከዚህ ዘመን ባልደረሰልን ነበር ፤ ስህተት የመሰለንን ሁሉ እየቆነጣጠርን ስናወጣና ስንጥል ማለቴ ነው ፡፡ ስለዚህም በየዋህነት እንዲያመልኩ ትልቅ በረከት የተሰጣቸው መሆኑን ተምሬአለሁ ፤ የሃይማኖት ትርጉምም ሊሆንና ሊታመን የማይችለውን ሁሉ ነው ብሎ መቀበል ነውና ነው ፡፡

  3. የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ያሏትን ቅዱሳት መጽሐፍት ፣ በአእምሮ ጥበብ ተመርታ ለማረምና ለማስተካከል አለመሞከሯን ፣ ሳትነካካና ሳታበላሽ ማቆየቷን አስተምሮኛል ፡፡ መጽሐፍ ቅዱሱ ውስጥ ተከብሮ እንደተጠበቀው የዮፍታሔ ዓይነትና ልጅ ቀቅለን በላን ታሪክ ማለቴ ነው ፡፡ ይህም በእምነቷና በሃይማኖቷ ተአማኒነቷን ያረጋግጣል ፡፡

  4. የገድለ እስጢፋኖስ መጽሐፍ ለዚህ ትውልድ መድረሱ ፣ ለደቂቀ እስጢፋኖስም መታሰቢያ እንዲኖር መደረጉ ቤተ ክርስቲያናችን በሚቃወሟት እንኳን ተጽእኖ ሳታደርግ ፍጹም ሃይማኖትን በመጠበቅ በኩል ታማኝነቷን በድጋሚ ያሳያል ፡፡ እንደምትሉት የንጉሡ ፈቃድና ምኞት በሃይማኖት ውስጥ ቢታከልበት ኑሮ የተጠቀሰው የገድል መጽሐፍና መታሰቢያው ለተረት እንኳን አይተርፍም ነበር ፡፡

  5. ሌላው የዚህ ምሳሌ ትምህርትና መልእክት ከማቴዎስ ወንጌል ኃይለ ቃል ጋር መያያዙን ተረድቼአለሁ ፡፡ ማቴ 1ዐ፡4ዐ - 42 "እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል። ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል። ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋው አይጠፋበትም።" ማለትም ከእምነት በተጨማሪ ትንሽ የቅድስና ሥራ ብሰራ ቶማስ እንደ ስልቻ ተገፎ ፣ ጳውሎስም አንገቱን ተቀልቶ የሚያገኘውን በረከትና ዋጋ እኔም እንደማገኘው ተስፋ አደርጋለሁ ፡፡

  ይኸኛው ትውልድ ለሁሉም ነገር አቋራጩን ይፈልግለታል ፤ ወንዝ ካለ ድልድይ ይሠራል እንጅ ፣ መሻገሪያ ፍለጋ አይንከራተትም ፤ ድኀነትንም ለመላቀቅ ወንጀል ይሠራል እንደሆን እንጅ ፣ ጥሮ ለፍቶ ግሮ ፣ ቀስ በቀስ ለማደግ ትዕግሥት አያደርግም ፤ ጽድቅንም ለመፈለግ በሚያደርገውም የሃይማኖት ትምህርትና ጥናትም አቋራጭን ሊያበጅ ብዙ ይታገላል ፤ ብዙ ይመረምራል ፡፡ ሌሎች ወገኖች በየዋህነታቸውና በራሳቸው ብቁነት ባለመተማመን በጻድቃንና በቅዱሳን በኩል እያሉ ደጅ ሲጠኑ ፣ በእምነት ጀግና የሆነው ችኩል ደግሞ አይ በደረት በማለት በቀጥታ ለመቅረብ ይደክማል ፡፡ የሁሉንም የሚመለከተው ግን አንድ አምላክ ነው ፡፡ ለጽድቅ በጽናት ብዙ የሚደክም ፣ ብዙ የሚንገላታ ፣ ብዙ የሚጐዳ ያለውን ያህል ፣ ሃይማኖትንና እምነትን አልጋ በአልጋ አድርጐ የሚንደላቀቅበትና የሚዝናናባትም አለ ፡፡ መንገዱን ለመያዝ ምርጫው የየግላችን ነው ፡፡

  በተረፈ መጽሐፍትን አትመርምሩ አልልም ፤ የምችለውን ያህል እኔም ለመረዳት እየዳከርኩ ነው ፡፡ መንፈሳዊ መልዕክትን ያስተላልፋል አያስተላልፍም የሚለው መመዘኛችን ቢሆን ግን መልካም ነው ፡፡ ወንጌልን እጅግ የተማሩና የሰለጠኑበት ሰዎች ከምርምር ብዛት ፣ ዛሬ እምነት የለሽ ሆነዋልና እግዚአብሔር ከእንደዛ ዓይነቱ የምርምር አደጋ ይጠብቀን ፡፡

  ሌሎች ያነበቡ ሰዎች ደግሞ ቢሳተፉበት መድረኩ ጥሩ የመማማሪያ ይሆን ነበር ፤ ባህሉ ስላልዳበረ ግን ጉዳዩን ከሥረ መሠረቱ የማናውቀው ሞከርን ፡፡

  እግዚአብሔር ሁላችንንም በእምነታችን እንድንሰነብት ይርዳን ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Amen! Wondime betam asteway endehonk ayalehu! Yetemark endehonkim endihu! Tihitinah kirstiyaninetihinim yigeltsal silezih bertalin!

   Delete
 8. ከዚያም አልፎ የይሁዳ ነገድ ነኝ ይል ነበር። አባ እስጢፋኖስ ግን ኢትዮጵያዊ ነህ አትዋሽ ከአይሁዳዊነት ይልቅ ክርስቲያን መሆን ይበልጣልና በዚህ አትመካ በማለት እንደተከራከረው ገድለ እስጢፋኖስ ይናገራል

  How do you believe in ገድለ እስጢፋኖስ an you don't believe ታምረ ማርያም?
  You are a dus.... As usual don't post my comments

  ReplyDelete
 9. ሁለት ጊዜ ሞክሬአለሁ ይኸ የመጨረሻ ሙከራዬ ይሆናል -

  ዲያቆን ሉሌ ይህን በሩቅ ሆኘ የምሰማውን ትምህርት ክፍል ስላስነበብከኝ አመሰግናለሁ ፤ ቆንጆ ትንተና አድርገሃል ፤ ድንቅ ሥራ ነው፡፡ የኔዋ ምልከታና ግንዛቤ የተመረኮዘችው ከተጻፈው በመነሳት እንጅ የተጠቀሰውን መጽሐፍ አንብቤና ተረድቼ ወይም እንደሚባለው ገምግሜ አይደለም፡፡

  ቅዱሳት መጽሐፍት በማን ተጻፉ ?
  1. ቅዱሳኑ (በእምነታቸውና በምግባራቸው መልካምነት የታወቁ ሰዎች) ከመሞታቸው በፊት በህይወት ዘመናቸው እግዚአብሔር የፈጸመላቸውን ገድል ለመመስከር በማለት ራሳቸው ይጽፉታል
  2. ቅዱሳኑ ከሞቱ በኋላ ታሪኩን የሰሙና ያዩ ተማሪዎቻቸው (ተከታዮቻቸው) ገድልና ተአምሩ ተሰውሮ እንዳይቀር በማሰብ ፣ የሰሙትንና ያዩትን ሳያዛቡ ይጽፋሉ (ወንጌል እንደተጻፈው ዓይነት ማለት ነው)
  3. ቅዱሳኑ ራሳቸው በራዕይ መልክ ሲገለጥላቸው ፣ ያንን ተመርኩዘው ለህዝባቸው ይጽፋሉ (ሙሴ ስለ ዓለም መፈጠር እንደተረከው ወይም ሐዋርያው ዮሐንስ የከተበልንን ዓይነት ማለት) ፡፡
  የቤተ ክርስቲያን አባቶችም ይህንኑ በመከተል ትክክለኛነቱን መርምረውና አጣርተው ፣ ማስተማሪያነቱንም ፈትሸውና መዝነው መጽሐፍቱን ለቤተ ክርስቲያን ሃይማኖትና እምነት ማስተማሪያነት ይቀበላሉ እንጅ ግለሰብ ባቃዠው ቁጥር እየጻፈ ያመጣውን ሁሉ ወደ ሃይማኖት ማስተማሪያነት አላስገቡም ፤ ጊዜ የሰጠው ባለሥልጣንም በጫና ብዛት አስገድዷቸው የፈጸሙበት ሁኔታና ታሪክ የለም ፡፡

  የቅዱሳት መጽሐፍት የሚጻፉበት ተቀዳሚ ዓላማ ምንድር ነው ?
  1.“በአብ ወልድና መንፈስ ቅዱስ እንዲያምን ምእመናንን ለማስተማርና ለማትጋት” /በሙሉ ይሰመርበት/
  2.በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጹትን ትምህርቶች በኑሮውና በህይወቱ እንዲተገብር ፣ እምነቱን በተቻለው እንዲኖረው ማስተማር ፣ ሃይማኖቱ ያስቸግረኛል ብሎ እንዳይሰንፍም ሌሎች አማኞች የፈጸሙትን እንደ ምሳሌ በማቅረብ ለማጽናት፡፡ (ከዚሁ ትምህርት የተነሳ ዛሬ ዛሬ ተረት እየሆነ ሄደ እንጅ እንደ አብርሃም እንግዳን የሚቀበልና የመጽሐፍ ቅዱሱን ቃል የሚተገብር ወገን እንደነበረ እኛ ሳንሆን ገጠመኙን የታዘቡ ፈረንጆች - የመጽሐፍ ቅዱስን ታሪክ ለማጥናት እሥራኤል ፣ መጽሐፍ ቅዱሱን በተግባር ለማየት ደግሞ ኢትዮጵያ መጐብኘት በማለት መስክረዋል)

  ከተጠቀሰው ታሪክ ምን ተማርክበት ብባል ፡-
  1. በምድራዊ ዘመናችን የሰራነው በሙሉ የኃጢአት ፣ የክፋትና የግፍ ምግባር ቢሆንም ትንሽ የቅድስና ፍሬ እንኳን ሠርተን ቢገኝብን መልካም እንደሆነና ዋጋ እንዳለው ተምሬአለሁ፡፡

  2. የኢትዮጵያ የክርስትና እምነት የየዋሃትና የቅዱሶች እንደነበረ ፣ በምርምርና በአእምሮ ብልሃት ያልተፈጠረ መሆኑን ገልጾልኛል ፡፡ ትንሽ እንደ ተማሩት ዘመነኛ ሰዎች የጥበብ ውጤት ቢሆን ኖሮ እንኳንስ ሌላው ንዋየ ቅዱሳት ፣ መጽሐፍ ቅዱሱም ቢሆን እስከዚህ ዘመን ባልደረሰልን ነበር ፤ ስህተት የመሰለንን ሁሉ እየቆነጣጠርን ስናወጣና ስንጥል ማለቴ ነው ፡፡ ስለዚህም በየዋህነት እንዲያመልኩ ትልቅ በረከት የተሰጣቸው መሆኑን ተገንዝቤአለሁ ፤ የሃይማኖት ትርጉምም ሊሆንና ሊታመን የማይችለውን ሁሉ ነው ብሎ መቀበል ነውና ነው ፡፡

  3. የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ያሏትን ቅዱሳት መጽሐፍት ፣ በአእምሮ ጥበብ ተመርታ ለማረምና ለማስተካከል አለመሞከሯን ፣ ሳትነካካና ሳታበላሽ ማቆየቷን አስረድቶኛል ፡፡ መጽሐፍ ቅዱሱ ውስጥ ተከብሮ እንደተጠበቀው የዮፍታሔ ዓይነትና ልጅ ቀቅለን በላን ታሪክ ማለቴ ነው ፡፡ ይህም በእምነቷና በሃይማኖቷ ተአማኒነቷን ያሰጣታል ፡፡

  4. የገድለ እስጢፋኖስ መጽሐፍ ለዚህ ትውልድ መድረሱ ፣ ለደቂቀ እስጢፋኖስም መታሰቢያ እንዲኖር መደረጉ ቤተ ክርስቲያናችን በሚቃወሟት እንኳን ተጽእኖ ሳታደርግ ፍጹም ሃይማኖትን ብቻ እንደምትመዝን እምነቷንም በመጠበቅ በኩል ታማኝነቷን በድጋሚ ማየት ችያለሁ ፡፡ እንደምትሉት የንጉሡ ፈቃድና ምኞት በሃይማኖት ውስጥ ቢታከልበት ኑሮ የተጠቀሰው የገድል መጽሐፍና መታሰቢያው ለተረት እንኳን አይተርፍም ነበር እንኳንስ ዛሬ እንዲህ ብሎ ነበር እንዲያ ብሎ የምትሉበት ማስረጃ ለታገኙ ቀርቶ፡፡

  5. ሌላው የዚህ ምሳሌ ትምህርትና መልእክት ከማቴዎስ ወንጌል ኃይለ ቃል ጋር መያያዙን ተረድቼአለሁ ፡፡ ማቴ 1ዐ፡4ዐ - 42 "እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል። ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል። ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋው አይጠፋበትም።" ማለትም ከእምነት በተጨማሪ ትንሽ የቅድስና ሥራ ብሰራ ቶማስ እንደ ስልቻ ተገፎ ፣ ጳውሎስም አንገቱን ተቀልቶ የሚያገኘውን በረከትና ዋጋ እኔም እንደማገኘው ተስፋ አደርጋለሁ ፡፡

  ይኸኛው ትውልድ ለሁሉም ነገር አቋራጩን ይፈልግለታል ፤ ወንዝ ካለ ድልድይ ይሠራል እንጅ ፣ መሻገሪያ ፍለጋ አይንከራተትም ፤ ድኀነትንም ለመላቀቅ ወንጀል ይሠራ እንደሆን እንጅ ፣ ጥሮ ለፍቶ ግሮ ፣ ቀስ በቀስ ለማደግ ትዕግሥት አያደርግም ፤ ጽድቅንም ለመፈለግ በሚያደርገውም የሃይማኖት ትምህርትና ጥናትም አቋራጭን ሊያበጅ ብዙ ይታገላል ፤ ብዙ ይመረምራል ፡፡ ሌሎች ወገኖች በየዋህነታቸውና በራሳቸው ብቁነት ባለመተማመን ፣ በጻድቃንና በቅዱሳን በኩል እያሉ ደጅ ሲጠኑ ፣ በእምነት ጀግና የሆነው ችኩል ደግሞ አይ በደረት በማለት በቀጥታ ለመቅረብ ይደክማል ፤ ይህንኑ ዓላማ ያነገበው ቡድን ዛሬ በቀጥታ በድንግል ማርያም ስም ብሎ ተቃውሞ ቢያሰማ ፣ ተቀባይ ስለማያገኝ የዙሪያ ጥምጥም ሄዶ የሰው በላ ታሪክ በማውሳት ቀዳዳ ይፈለጋል ፡፡ ዋና አጀንዳና ዓላማ ድንግል ማርያም አታማልድም የሚለው ትምህርታቸው ነው ፡፡የሁሉንም የሚመለከተው ግን አንድ አምላክ ነውና እሱ ይፍረድ ፡፡ ለጽድቅ በጽናት ብዙ የሚደክም ፣ ብዙ የሚንገላታ ፣ ብዙ የሚጐዳ ያለውን ያህል ፣ ሃይማኖትንና እምነትን አልጋ በአልጋ አድርጐ የሚንደላቀቅበትና የሚዝናናባት ፣ የማጠቀምባትም ወገን አለ ፡፡ መንገዱን ለመያዝ ምርጫው የየግላችን ነው ፡፡

  በተረፈ መጽሐፍትን አትመርምሩ አልልም ፤ የምችለውን ያህል እኔም ለመረዳት እየዳከርኩ ነው ፡፡ መንፈሳዊ መልዕክትን ያስተላልፋል አያስተላልፍም የሚለው መመዘኛችን ቢሆን ግን መልካም ነው ፡፡ ወንጌልን እጅግ የተማሩና የሰለጠኑበት ሰዎች ከምርምር ብዛት ፣ ዛሬ እምነት የለሽ ሆነዋልና እግዚአብሔር ከእንደዛ ዓይነቱ የምርምር አደጋ ይጠብቀን ፡፡

  ሌሎች ያነበቡ ሰዎች ደግሞ ቢሳተፉበት መድረኩ ጥሩ የመማማሪያ ይሆን ነበር ፤ ባህሉ ስላልዳበረ ግን ጉዳዩን ከሥረ መሠረቱ የማናውቀው ሞከርን ፡፡

  እግዚአብሔር ሁላችንንም በእምነታችን እንድንሰነብት ይርዳን ፡፡

  ReplyDelete
 10. endihnew ye enante telatFebruary 26, 2012 at 3:02 AM

  yasaznal betam yasafral nege eko mot aykerm endi bezelabdkbet milash tteyekbetalh sewun bewashut amlakinh mewashet aychal kifuwech defaroch yekir ybelachu enkuan alilachum

  ReplyDelete
 11. To Berhanu Gabriel: you are so funny! The truth is our church is in the wrong direction. most of us do not have a doubt that our mother kidste Mariam can help us in out prayer, the case is Satan never like our mother, therefor satan use debetara to write a fictions like the one we read, this fictions wrote by debetara have been using a weapon to disgrace our mother. I personally do not accept gedele and other books which are contrary to the bible. I read only bible and I have Jesus and his mother. I love him first and then his mother loving me and helping me in my prayer. fiends! her his my advise, if you do not have Jesus in your life, his mother will not help in your prayer. Thanks to the Holy trinity!

  ReplyDelete
 12. ሰላምን አጥብቀው ስለፈለጓትና ስለተመኟት ብቻ አትገኝም ፡፡ በቀደመው ጽሁፍ ግለ ሰዎችን ላለማስቀየም ተጠንቅቄ ፣ የተማሩትም ሊቃውንት ለመጋበዝ በማለት ከብዙው ዝርዝር ተገትቼ አጠቃላይ አመለካከቴ ላይ አተኩሬ ነበር ፡፡ ነገር ግን ያም ተደርጐ በአስተያየት ሰጭ ምእመን ላይ የሚሰነዘሩት ውግዘቶችና እርግማኖች የተዛቡ በመሆናቸው ፣ የጽሁፉን ደካማነት ለማስጨበጥና አንባቢ የግሉን ሚዛናዊ አመለካከት እንዲፈጥር ስለ ዲያቆን ሉሌ ጽሁፍ የሚከተለውንም አክላለሁ ፡፡

  - መጀመሪያ መጽሐፍን በሥርዓቱ ለተማሩት ጸሃፊዎቻችን ማሳሰቢያ ይሆን ዘንድ አስቀድሜ ይህን እላለሁ ፡- ሃይማኖትን የተመለከተ ማጣቀሻ ለመጥቀስ መጀመሪያ የጸሃፊውን እምነትና አመለካከትን /ቢያንስ ያልተዛባ መሆኑን/ መመዘን ያስፈልጋል ፡፡ ከስማቸው በፊት በተለጠፈላቸው ማዕረግ ብቻ እየተመራን ፣ ሥራቸው ከሰው አእምሮ ጸባይ ውጭ የሆነ እንዳይመስለንና እንዳንታለል ዛሬም ደግሜ ለማስገንዘብ እወዳለሁ ፡፡ ኢየሱስን ሚካኤል ነው የሚል መደምደሚያ ላይ የደረሰው ግለሰብ ፣ በማዕረጉና በዓለም ጥበብ ዕውቀቱ እጅግ የተካነና አንቱ የተባለ ፤ የሃይማኖት መጽሃፍትንም እጅግ የሚያውቃት ነበር ፤ ይኸው የረቀቀ ምድራዊ ጥበቡ ግን በመጨረሻ ወደ ክህደት ትምህርት አስገባው ፡፡ ስለዚህ ከማጣቀሳችን በፊት ስህተቱን መልሰን እንዳናስተጋባ የጸሃፊውን አምልኮና ዓላማ በውል ማወቅ በእጅጉ ይጠቅመናል እላለሁ፡፡

  ጽሁፉን በሥርዓቱ ስመለከተው ፡-
  - የኢኦተቤ በሰማይ በፈጣሪ ከተበተኑት ከዋክብት መሃል ፣ አንደኛው ኮከብ እንደ እጅ ባትሪ ያህል ሰብአ ሰገልን እየመራ ጌታ ከተወለደበት ሥፍራ ላይ ሲደርስ ቆመ ፤ ጠቢባኖቹም ህጻኑን ከእናቱ ጋር አገኙት ብላ ስታስተምር (ፍጹም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል ነው - ማቴዎስ 2 ይመልከቱ) የተቀበልናት ሌላውን ትምህርቷን ስለምን ጉዳይ ቢባል አናምነውም? በአእምሮ ፍተሻ ከሆነ ይኸም የሚታመን ፣ የተለመደ ክስተት ፣ ምሳሌ የሚጠቅሱለት አይደለም ፡፡ በሃይማኖት ሚዛን ፣ በመንፈስ ስለቃኘነው ብቻ በሙሉ ልብ እውነት ነው ብለን አምነናል ፡፡ ሌሎች ትምህርቶቿም ቢሆኑ በዚሁ ስልት መፈተሽ ይገባቸዋል እንጅ በተለያየ ምልከታ አንጓዝባቸው እላለሁ ፡፡ ወደ ሌላ ባዕድና ጣዖት አምልኮ እስካልመሩን ፣ ከመጽሐፍ ቅዱሱም ቃል እስካልተፋጩ ወይም እስካልተጣረሱ ድረስ ትክክል ነው ብሎ መቀበሉ አግባብና የጨዋ ነው ፡፡

  - ታምረ ማርያምን ለምስክርነት እንደ አስረጅ የሚጠቅስ አንድ ጸሃፊ ፣ በምን ዘዴና የቋንቋ ብልሃት ፣ መልሶ የክህደት መጽሐፍ ብሎ ይኰንነዋል ፡፡ ቃሉ “ይህ ልዩ ወንጌል ከሐዋርያት ትምህርት የወጣ ስለሆነ አንቀበለውም በማለታቸው፣ እስከ አንገታቸው በጉድጓድ ተቀብረው በጭንቅላታቸው ላይ የፈረስና የከብት መንጋ እንደተነዳባቸው ምላሳቸውንና አፍንጫቸውን እንደተቆረጡ እራሱ ታምረ ማርያም ይመሰክራል።” የዞረበት ሰው በእኛም ሊያዞርብን እየሞከረ ካልሆነ በስተቀር ይኸን የተናገረ መልሶ ሲክድ ምን ይሉታል ፡፡ ይህን እውነት ካልክ ለምን የበላኤ ሰብን ታሪክ አልቀበለውም ትለናለህ ? ይህቺን ፍትፍትና ገንፎ በቅቤ ለጉረሮ መረጣ እላታለሁ እንጅ ጥሩ ፍርድ አይደለችም ፤ ሰለዚህም የተሰጡ አስተያየቶችህ በተአምረ መጽሐፍ ላይ መጀመሪያውኑ አንድ ወጥ አይደሉም ፡፡ የተቀበልከው ክፍል እንደ አለህ ሁሉ የኰነንከውም አለና እንደ ወንድም አስተካክለው ማለትን እመርጣለሁ ፡፡

  - የአባ እስጢፋኖስ ታሪክስ ከወዴት ተገኘና ቅዱስነቱ ሊጠቀስ ቻለ ? የዘርዓ ያዕቆብንስ ታሪክ ከምን ጉድጓድ አውጥተው ይተርኩታል ፡፡ ፈረንጆች የፈጠሩልን ድርሰት ወይስ ከቤተ መንግሥት ተገኘ ወይስ በቁፋሮ ከከርሰ ምድር ? መልሱ ከቤተ ክርስቲያን ከሆነ ፣ ይህንንም ታሪክ እውነት ለማለትና ለመከራከር ቤተ ክርስቲያን የምትለውንና የምታስተምረውንም በሙሉ ተቀብሎ ማመንና መተግባር ይጠይቃል ፡፡ ሃይማኖት የገበታ ምግብ አይደለም ፣ እየመረጡ ለሰው ባህርይና ጠባይ የተስማማውን የሚወስዱበት ፣ የሚጨንቀውንና የሚከብደውን የሚያንጓልሉበት አይደለም ፡፡ ምንጫችሁ የኢኦተቤ ከሆነች መላ ትምህርቷን ቢመራችሁም አዋህዱት ፤ ሃይማኖት ማለት እንደዚህ ናትና፡፡ ለህሊናችን የማይመቸውን ፣ የማይመስለንን እንንቀስ ካልን እኮ የማይነቀስለት የሃይማኖት መጽሐፍ ዝርያ አይኖርም ፤ ሥልጣኑና ችሎታው ስለሌለን ግን ሁሉም በያለበት ይቀጥላል ፡፡

  - ሌላው የጽሁፉ የውግዘት ቃል “…. የክህደቱ ምሥጢር እዚህ ላይ ነው። ይህ ትምህርት ህዝባችንን በሚቀቀለው ንፍሮ፣ በሚጠመቀው ጠላ፣ በሚዘከረው ዝክር እድናለሁ የሚል አጉል ተስፋ እንዲይዝ አድርጎታል። ዝክርሽን የዘከረ፣ ስምሽን የጠራ ይድናል የሚለው ባዕድ ወንጌል ተቀባይነት እንዲያገኝ …” ፤ “… ነፍሳት በምድር ላይ እንደፈለጋቸው ሲቀላውጡ ኖረው አንድ ቀን የሰጡትን ውሃ ወደ ሰማይ ሲሄዱ ተሸክመው እንደሚገኙ የሚያስተምር የክርስትና ትምህርት የለም። ….” ይላል፡፡ ይህ ዲያቆን ተብዬ / ስልጣኑን ስለተጠራጠርኩ የተጠቀምኩት ቃል ነውና ይቅርታ/ ብሎ ብሎ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃልን ጭምር ለመሻር የተነሳ ይመስላል እንጅ በተአምረ ማርያም ውግዘት ብቻ የሚያበቃ አይደለም ፡፡ ወንድም ህዝብ የሚጠቀምበትን ትክክለኛ መጽሐፍ ቅዱስ አውጣና ማቴዎስ በምዕራፍ 1ዐ ፡ 4ዐ - 42 የጻፈውን አንብበህ ለራስህ እርምት አድርግ ፡፡ በቀደመው ጽሁፌ ስለገለጽኩት እዚህ እንደገና አልደግመውም ፡፡ አሁንም አላማህ ከሆነ ይኸም እንኳን ትክክል አይደለምና ይቃና ወይም ይታደስ ማለት ትችላለህ ፤ መብትህ ነው፡፡

  - “ኃጢአት እና መልካም ሥራ በሚካኤል እንደሚመዘኑ መጽሐፍ ቅዱስ አይናገርም።” ፡--- ዳንኤል 1ዐ፡13 ፣ 1ዐ፡21 ፤ ይሁዳ 9 ፤ ራዕይ 12፡7 እነዚህ ሁሉ ስለ ሚካኤል ማንነት የሚገልጹ ፣ አለቅኑቱን ፣ ስለጻድቃን ተከራካሪነቱን ፣ ለአማንያን ወጋኝነቱን ፣ ተራዳኢነቱን ፣ ተዋጊነቱን ሁሉ የሚገልጹ ናቸውና የምታነበው መጽሐፍ የሚካኤል ነገር ከሌለው አሁንም መጀመሪያ መጽሐፍ ቅዱስህን አስተካክል ፡፡ ለመሆኑ ስታስበው ከዘንዶው ጋር ለመዋጋት መሪ ከመሆን ፣ የድል አድራጊነትንም ክብር ከመረከብና ከመመዘን ሥራ የትኛው የበለጠ ክብር ያስገኝ ይመስልሃል? ሰዎች ወደ ሌላ እምነት የሄዱት ይህንኑ ታላቅ ክብር ለሚካኤል አይገባውም ከማለት ተነስተው ነውና ዓይነትህ ከየት እንደሆነ በውል ለይልን እንጅ ቀላሉን የሥራ ድርሻ አታክብደው ፡፡ ሌላ ቀርቶ እኔና አንተም እንኳን የአምላክ ፈቃድ ከሆነ እንደ ንግሥት አዜብና ደቀ መዛሙርቱ ወንበር ተሰጥቶን መመዘን ሳይሆን መፍረድ እንችላለንና በንጹህ ልብ ሆነህ ፈጣሪህን ሳታወላውል እመን ብቻ ፡፡

  የመጨረሻው ክፍል 2 ይቀጥላል

  ReplyDelete
  Replies
  1. POSITIVE YEHONE MIND ALEH TIRU NEW.GIN YEMIABREKERIK HULU GIN WERK AYDELEM.YE'EZIABHER FIRD BESEW TALKA GEBNET YEMIKEYER KEHONE GOD BERASU MULU AYDELEM MALET NEW.YIH DEGMO TILIK MENAFIKNET NEW."MENAFIK"MALET MIN MALET NEW?LEMILEW DEGMO KEMETSHAF KIDUS GAR YEMIKAREN TIMIHIRT MALET NEW>SILEZIH TAMRE MARIAM "GEDIL" SAYHON "TILIK GEDEL"NEW COZ HASABU KE BIBLE GA5R FETSIMO YETERARAKE SILEHONE>GETA YEWUSTUN LIBACHIN YABRA,MASTEWAL YISTEN,KETIFAT MENGED WEDE HIWOT MENGED YIMELSEN ERSUM EYESUS KIRISTOS NEW.BEMECHERESHAM JOHN14:6 LITKES."EGNAM AREMAMEDACHIN KERSU GAR YIHUN WANAW CHIGIR KEGNA GAR SILEHONE.ERSUMA ESKEZELALEM KENANTE GAR EHONALEHU SILALE LEKALU TAMAGN NEW.(E.B)SON OF JESUS

   Delete
 13. - ጸሃፊው የጥናት ውጤት በእጁ ያስገባ ይመስል እንደሆነ እኔ አላውቅም ፤ እናቶቻችንና አባቶቻችንን ፣ ቀሳውስቱን ሁሉ ሲወቅሰ “ታምሯን ሰምቼ ልምጣ ይላል እንጅ ወንጌል ሰምቼ ልምጣ ብሎ አያስብም ፣ እሑድ እሑድ ታምር የሚያነብ እንጅ ወንጌል ለማስተማር የሚያስብ ቄስም የለንም፡፡” ወረድ ብሎ ደግሞ “ይህም ታሪክ እውነት ነው ተብሎ አመታዊ በአል ሆኖ እንዲከበር፣ ዜማ ተዘጋጅቶለት መልክ ተድርሶለት እንዲነገር ተብሎ በየካቲት 16 ቀን ታስቦ ይውላል።” -----ከነዚህ ቃሎች በመነሳት ደግሞ የሚከተሉትን ወንድሜ መግለጫ ካለህ አጠይቃለሁ

  o በአብዛኛው ወላጆቻችን እንደ እኛ መጽሐፍ መርማሪዎች እንዳልሆኑ እገምታለሁ ፤ ነገር ግን ኑሮ ካስቸገራቸውና በጣም ከቸኮሉ ፣ የተለመደው ቃላቸው ባላስቀድስ እንኳን ተሳልሜ ልምጣ እንጅ ተአምር ልስማን አኔ ባደግሁበት ቤተሰብና አካባቢ ሰምቼ አላውቅም ፤ እናትህን በማያውቁትና በሌሉበት ጉዳይ አታስወቅሳቸው ፡፡ ይህንን የሚመሰክሩት አጉል መንፈስ ጆሮአቸውን የሚያስታቸው ፣ አይናቸውንም እንዳያዩ ሸፍኖ የሚያደናብራቸው ሰዎች ናቸው እላለሁ ፡፡ በኛው ዘመን ይህን አስተያየት እንደ ህዝበ ክርስቲያን ቃል ለመመስከር ካስፈለገ ቢያንስ አንድ ሰባት ቤተ ክርስቲያናት ተሄዶ ፣ ምእመኑን ለምን ለምን ጉዳይ ሲሉ እንደመጡ ቃለ መጠይቅ አቅርቦ መልስ ይያዝና ፣ በናሙና ከተገኘው የመልስ ውጤት ፣ አጠቃላዩን ባይወክልም ፣ ያን ተጠግተህ ወይም አንተርሰህ የግል ግምትህን መናገር ትችላለህ ፡፡ ሳይንሳዊ ግኝትህና የሃይማኖት ምልከታህ እንዲደጋገፉልህ መምራቴ ነው ፡፡ ከዛ ውጭ በዘልማድ የማይባለውን አንፍጠር ፤ ለጆሮ አዲስ ስለሚሆን ሚዛን አይመታልህም፡፡

  o ከመጀመሪያው እሑድ እሑድ ያልከውን የተአምር ስብከት እልፍ ብለህ ደግሞ በየዓመቱ የካቲት 16 እነደሚታሰብ ታትታለህ ፡፡ ወንድሜ ስትጽፍ አስቀድመህ ከልብህ ሁን ፡፡ እሁድ እሁድ የሚደገም ከሆነ አንድም - ህዝቡ ሁሉ እንደ አቡነ ዘበሰማያት ስለሚለምደው በቃሉ በያለበት ያነበንበው ነበር እንጅ ናፍቆት ለመወጣት ሳምንትን አይጠብቅም ፤ ይኸነ ያህል ዘገምተኛ ወገን የለንምና ፤ ሁለትም ትምህርቱ ሲደጋገምበት ይሰለችና ቤተ ክርስቲያን ማዘውተሩን ይቀንሳል እንጅ በፍላጐቱ በጉጉት አይከታተለውም ፡፡ በዓመት የሚታሰብ የሚለውን ከመረጥህ የሰጠኸው የእሁድ ፣ እሁድ ምልከታ መታረም ይገባዋል ፤ ተጨማሪ የሌለ ሪፖርት አንፍጠርላቸው ፡፡ እየዋሸህም ለማስተማር አትሞክር ፤ ዝም ብሎ የተነገረውንና የሚያነበውን ሁሉ የሚያምን ሞኝና የዋህ ህዝብ ፣ የወስላታ ዘመን ስለሆነ ዛሬ ዛሬ የለም ፤ በተቻለው እንዳቅሙ ይመረምራል ፡፡ ያ የነበረበት ዘመን ፣ የእነ ክንዴ ክበደው ታሪክ የተወራበት ጊዜ ከኛ እጅግ በጣም ርቋል ፡፡

  o አሁንም ዲያቆን የሚለው ተቀጥላ ትክክለኛ ሹመትህ ከሆነ የአንዱ ቀን የቤተ ክርስቲያናችን ግልጋሎት ምን ምንን ያካትታል ? ከቻልክ መልስህን በመቶኛ ስሌት ብታደርግ ጥሩ ነው ፡፡ ከዚህስ የግልጋሎት ጊዜ ውስጥ ደግሞ ምን ያህሉ የትምህርት ጊዜ የሰው በላው ስብከት ታሪክ ጊዜ ይሆናል ፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን አብዛኛውን ሰዓት በሌላ ሃይማኖታዊ ግልጋሎትና ትምህርት ላይ የምታሳልፍ ከሆነ ፣ ይኸኛው እንደ ዋና ርዕስ ተደርጐ የሚከራከሩበት ጉዳይ አይሆንምና አቤቱታህን በግልህ ዝጋው ፡፡ ከኋላ ሌሎች የተሰወሩ አጀንዶች ካሉህ ፣ ስላልታዩኝ ነውና ግልጽ አድርገህ እንደ ሉተር ዘጠና አምስቱንም በዝርዝር አስነብበ ፡፡

  o እንደተረዳሁት የዚህ ሁሉ ምንባብ ትልቁ ሥውር ቅዝምዝም ፣ በድንግል ማርያም አማላጅነት ላይ ያነጣጠረ ነው ፤ ምክንያቱም በዚህ ታሪክ ውስጥ አብዛኛው አደረገችና ሆነ የተባለው የሷው ተአምር ነውና ፡፡ በጅምላ አማላጅ አያስፈልጉንም ሲሉን ከርመው ፣ በዛ ሲያዳግታቸው ፣ ውስጠ አዋቂ ይዘው ፣ ግዕዝ ተናጋሪ ሸምተው አሁን በተናጠል ለመምታት መሞከራቸው እንዳይሆን እጠረጥራለሁ ፡፡ እመቤታችንና እናታችን ፣ ለአምላክ ማደሪያነትና እናትነት የተመረጠች ብፅዕት ፣ ቅድስትና ድንግል ማርያም (ሹመትና ስልጣኗን ዘርዝሬ አልጨርሰውም) ከየትኛውም መልአክና ቅዱሳን በላይ ሆና ልጇ ከሆነው ፈጣሪዋ ጋር ታማልደናለች ፤ ቀጥለውም መላአክት ከዛም ቅዱሳኑን ሁሉ ያማልዱናል እንላለን ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስን ደግሞ ፈጣሪያችን ፣ አምላካችን ፣ መድኃኒታችን /አዳኛችን/ ነው ብለን በአምልኮ እንሰግድለታለን እንጅ ፣ እንደ ጥፋት ልጆች ያማልደናል አንልም ፡፡ በመስቀል ላይ ሆኖ ፣ ኃጢአታችንን ሽሮ ፣ እኛን ከራሱ ጋር አስታርቆናል ብለንም ስለፈጸመው ውለታው ሳናፍር እንመሰክራለን ፣ ስለዚህም ደግሞ እናመሰግነዋለን ፡፡

  - “በእግዚአብሔር መልክ የተፈጠሩ ክቡራን ነፍሳትን እና ትንሽ ውሃን ነው በአንድ ሚዛን ተመዘኑ ያለው።” ፡--- ይህም አባባል የቋንቋ ችግርና የንባቡን ጠቅላላ መልዕክት የመገንዘብ ድክመት ሆኖ ስለተሰማኝ ፤ እንዲገባህ ያህል የሚከተለውን አስነብባለሁ -- የጻፍከው ቃል የሚያወዳድረው ወይም ሊያነጻጽር የፈለገው በበላኤ ሰብ ላይ የተደፈደፈውን የኃጢአትን ክምርና የፈጸማትን ትንሽ የቅድስና ተግባር እንጅ ፣ የእግዚአብሔር እስትንፋስን /ነፍሳትን/ በየትኛውም መንገድ ለማወዳደር ፈልጐ አይደለም ፤ በላኤ ሰብ ያጠፋቸውን ነፍሳት ቁጥር እንደፈጠማቸው የራሱ ኃጢአት አድርጐ መዝኗቸዋል ማለቴ ነው፡፡ ይኸ ክፉ መንፈስ ወንድሜን ሊያሳስትህ የፈጠረብህ ግንዛቤ ነውና ሁላችንንም እግዚአብሔር በየምክንያቱ ከታሠርንበት አጓጉል መንፈስ ነጻ እንዲያወጣን ከልብ ሆነን እንጸልይ ፡፡

  ስለ ማታምኑበት በጾም ወራት እንደምንም ብላችሁ አነካካችሁኝ ፤ እስቲ እርግማናችሁ ተሰርዞ በጸሎታችሁ የምተርፍ ከሆነ ይህቺን ደግሞ በሉልኝ ፡፡
  ኃጢአተኛ ባሪያህንና ልጅህን በቸርነትህና በምህረትህ ባርከው ፤
  ይህን መንገድ ባይመርጠውም ፣ ኃጢአትን ፈጽሞበታልና ይቅር በለው ፤
  የአንተን ፍጹም ቅድስናና ክብር እንዲረዳ ፣ ብሩህ አእምሮን ስጠው ፤
  በሃይማኖቱና እምነቱም እስከ መጨረሻው እነዲጸና አግዘው ፡፡ አሜን !!!

  እናንተንም እግዚአብሔር ይባርክ ፡፡ አሜን !!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. "ኢየሱስ ክርስቶስን ደግሞ ፈጣሪያችን ፣ አምላካችን ፣ መድኃኒታችን /አዳኛችን/ ነው ብለን በአምልኮ እንሰግድለታለን እንጅ ፣ እንደ ጥፋት ልጆች ያማልደናል አንልም ፡፡ በመስቀል ላይ ሆኖ ፣ ኃጢአታችንን ሽሮ ፣ እኛን ከራሱ ጋር አስታርቆናል ብለንም"


   "እንደ ጥፋት ልጆች ያማልደናል አንልም" contradicts with "በመስቀል ላይ ሆኖ ፣ ኃጢአታችንን ሽሮ ፣ እኛን ከራሱ ጋር አስታርቆናል ብለንም"

   "አስታርቆናል" = ያማልደናል

   the difference is he did it once "በመስቀል ላይ ሆኖ" AND IT WORKS FOREVER,EVEN WHILE I AM WRITING THIS. Let me remind you what he said "Jesus said, "Father, forgive them, for they do not know what they are doing.", luke 23:34

   you tried to hide the open truth, you intentionally omitted by saying "እኛን ከራሱ ጋር አስታርቆናል ብለንም" ignoring "Father, forgive them" while he was soaked by his holy blood.
   "the law requires that nearly everything be cleansed with blood, and without the shedding of blood there is no forgiveness" Hebrews 9:22

   "And to Jesus the mediator of the new covenant, and to the blood of sprinkling, that speaketh better things than that of Abel" Hebrew 12:24

   "that speaketh better things" is interpreted as forgive them, forgive them, forgive them ...

   Betewahdo BESIGA አስታርቆናል BEMELEKOT ታርቆናል. Keeping in mind that when we say ኢየሱስ ክርስቶስ, FROM 2 AKALAT one AKAL and from 2 BAHRIAT 1 BAHRIY. We should always proudly say ያማልደናል and አስታርቆናል. That is why our church gives his body and blood every day.

   Regarding "በጾም ወራት እንደምንም ብላችሁ አነካካችሁኝ" I always believe that being a witness for your believe during በጾም ወራት is good. What is not good is being a false witness during በጾም ወራት. To just remind you that for good christian everyday is የጾም ወራት.

   Delete
 14. ከሐዋርያት ትምህርት የወጣ ስለሆነ አንቀበለውም በማለታቸው፣ እስከ አንገታቸው በጉድጓድ ተቀብረው በጭንቅላታቸው ላይ የፈረስና የከብት መንጋ እንደተነዳባቸው ምላሳቸውንና አፍንጫቸውን እንደተቆረጡ እራሱ ታምረ ማርያም ይመሰክራል። [ታምር 24 እና 25 ገጽ 112- 121።] የሚገርም ነው፡፡
  እንዴት ክርስቲያን በመግደል ያምናል፡፡ ያውም በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክነት የሚያምኑትን ክርስቲያኖች እንዲህ አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ መግደል ትክክል ነው የሚል ካለ ክርስትናውን መመርመር አለበት፡፡ የታምረ ማርያምን ምንነት ለማረጋገጥ በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል (በእግዚአብሔር ቃል) መመዘን ነው፡፡

  - ታምረ ማርያምን ለምስክርነት እንደ አስረጅ የሚጠቅስ አንድ ጸሃፊ ፣ በምን ዘዴና የቋንቋ ብልሃት ፣ መልሶ የክህደት መጽሐፍ ብሎ ይኰንነዋል ፡፡ ቃሉ “ይህ ልዩ ወንጌል ከሐዋርያት ትምህርት የወጣ ስለሆነ አንቀበለውም በማለታቸው፣ እስከ አንገታቸው በጉድጓድ ተቀብረው በጭንቅላታቸው ላይ የፈረስና የከብት መንጋ እንደተነዳባቸው ምላሳቸውንና አፍንጫቸውን እንደተቆረጡ እራሱ ታምረ ማርያም ይመሰክራል።” የዞረበት ሰው በእኛም ሊያዞርብን እየሞከረ ካልሆነ በስተቀር ይኸን የተናገረ መልሶ ሲክድ ምን ይሉታል ፡፡ ይህን እውነት ካልክ ለምን የበላኤ ሰብን ታሪክ አልቀበለውም ትለናለህ ? ይህቺን ፍትፍትና ገንፎ በቅቤ ለጉረሮ መረጣ እላታለሁ እንጅ ጥሩ ፍርድ አይደለችም ፤ ሰለዚህም የተሰጡ አስተያየቶችህ በተአምረ መጽሐፍ ላይ መጀመሪያውኑ አንድ ወጥ አይደሉም ፡፡ የተቀበልከው ክፍል እንደ አለህ ሁሉ የኰነንከውም አለና እንደ ወንድም አስተካክለው ማለትን እመርጣለሁ ፡፡
  -
  - ምንም የሚስተካከል ነገር የለም፡፡ እግዚአብሔር የሚቀጣው ኃጢአትን በገዛ አንደበታቸው እያስመሰከረ ነውና ያለቁትን ሰማዕታት እንዴት አድርጎም እንደገደላቸው አጼ ዘርዐ ያዕቆብ እራሱ ጽፎልናል፡፡
  ‹‹አጼ ዘርዐ ያዕቆብ 10 ሺህ የሚያህሉ መናፍቃንን በሬሳ በሚባል ወንዝ አረዳቸው፡፡ ይህ ደብረ ብርሃን መግቢያ ላይ ያለው በሬሳ ወንዝ ሬሳ በሬሳ ለማለት በሬሳ ተባለ እያለች ቤተክርስቲያን ትተርክልናለች፡፡ ›› እነዚህ ሰዎች በተገደሉ ዕለት ብርሃን በመውረዱ ከተማይቱ ደብረ ብርሃን ተብላለች ይባላል፡፡ የዐጼ ዘርዐ ያዕቆብም ግብር የሚበሉ ደብተሮች ብርሃኑ የወረደው ለእርስዎ ነው እግዚአብሔር በሥራዎ ረክተEል አላEቸው፡፡ ግን ያውም በአዲስ ኪዳን ዘመን ሰው ሲታረድ እግዚአብሔር ብርሃን ያወርዳል ማለት እርሱን የበደላችን ተባባሪ ማድረግ ነው፡፡ ማንም ሰው እንደሚረዳው ግን ብርሃኑ የሰማዕትነት ዋጋ ነው፡፡
  አባ እስጢፋኖስ ለዘመናት ታሪኩን ተጋድሎው በክፉዎች ተቀብሮ ሲኖር አሁን ግን ከንጋት ይልቅ እየጠራ የሰማዕትነቱ ዜና እየወጣ ነው፡፡ ሸዋ ላይ አባ እስጢፋኖስ መናፍቅ ተብሎ ይወገዛል፡፡ ተአምረ ማርያምም የመገደሉን ዜና ያበስራል፡፡ ትግራይ ላይ ደግሞ ጉንዳጉንዲ በተባለው ገዳም ሰማዕትነቱ ይታወጃል፡፡ ገድሉ ይነበባል፡፡ የወንድሞች ገድል ‹‹ ገድለ አኀው›› የተባለውም የደቀ መዛሙርቱ የሰማዕትነት ዜና በግልጥ ይገኛል፡፡ በአንድ ራስ ሁለት ምላስ እንደሚባል በአንድ ቤተክርስቲያን መናፍቅና ቅዱስ እየተባለ መጠራቱ ይደንቃል፡፡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህም ገድለ አባ እስጢፋኖስ በገዳሙ ታትሞ በየስፍራው ይሸጣል፡፡ የእውነተኞች ዜና ተቀብሮ አይቀርምና፡፡

  ReplyDelete
 15. ከሐዋርያት ትምህርት የወጣ ስለሆነ አንቀበለውም በማለታቸው፣ እስከ አንገታቸው በጉድጓድ ተቀብረው በጭንቅላታቸው ላይ የፈረስና የከብት መንጋ እንደተነዳባቸው ምላሳቸውንና አፍንጫቸውን እንደተቆረጡ እራሱ ታምረ ማርያም ይመሰክራል። [ታምር 24 እና 25 ገጽ 112- 121።] የሚገርም ነው፡፡
  እንዴት ክርስቲያን በመግደል ያምናል፡፡ ያውም በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክነት የሚያምኑትን ክርስቲያኖች እንዲህ አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ መግደል ትክክል ነው የሚል ካለ ክርስትናውን መመርመር አለበት፡፡ የታምረ ማርያምን ምንነት ለማረጋገጥ በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል (በእግዚአብሔር ቃል) መመዘን ነው፡፡

  - ታምረ ማርያምን ለምስክርነት እንደ አስረጅ የሚጠቅስ አንድ ጸሃፊ ፣ በምን ዘዴና የቋንቋ ብልሃት ፣ መልሶ የክህደት መጽሐፍ ብሎ ይኰንነዋል ፡፡ ቃሉ “ይህ ልዩ ወንጌል ከሐዋርያት ትምህርት የወጣ ስለሆነ አንቀበለውም በማለታቸው፣ እስከ አንገታቸው በጉድጓድ ተቀብረው በጭንቅላታቸው ላይ የፈረስና የከብት መንጋ እንደተነዳባቸው ምላሳቸውንና አፍንጫቸውን እንደተቆረጡ እራሱ ታምረ ማርያም ይመሰክራል።” የዞረበት ሰው በእኛም ሊያዞርብን እየሞከረ ካልሆነ በስተቀር ይኸን የተናገረ መልሶ ሲክድ ምን ይሉታል ፡፡ ይህን እውነት ካልክ ለምን የበላኤ ሰብን ታሪክ አልቀበለውም ትለናለህ ? ይህቺን ፍትፍትና ገንፎ በቅቤ ለጉረሮ መረጣ እላታለሁ እንጅ ጥሩ ፍርድ አይደለችም ፤ ሰለዚህም የተሰጡ አስተያየቶችህ በተአምረ መጽሐፍ ላይ መጀመሪያውኑ አንድ ወጥ አይደሉም ፡፡ የተቀበልከው ክፍል እንደ አለህ ሁሉ የኰነንከውም አለና እንደ ወንድም አስተካክለው ማለትን እመርጣለሁ ፡፡
  -
  - ምንም የሚስተካከል ነገር የለም፡፡ እግዚአብሔር የሚቀጣው ኃጢአትን በገዛ አንደበታቸው እያስመሰከረ ነውና ያለቁትን ሰማዕታት እንዴት አድርጎም እንደገደላቸው አጼ ዘርዐ ያዕቆብ እራሱ ጽፎልናል፡፡
  ‹‹አጼ ዘርዐ ያዕቆብ 10 ሺህ የሚያህሉ መናፍቃንን በሬሳ በሚባል ወንዝ አረዳቸው፡፡ ይህ ደብረ ብርሃን መግቢያ ላይ ያለው በሬሳ ወንዝ ሬሳ በሬሳ ለማለት በሬሳ ተባለ እያለች ቤተክርስቲያን ትተርክልናለች፡፡ ›› እነዚህ ሰዎች በተገደሉ ዕለት ብርሃን በመውረዱ ከተማይቱ ደብረ ብርሃን ተብላለች ይባላል፡፡ የዐጼ ዘርዐ ያዕቆብም ግብር የሚበሉ ደብተሮች ብርሃኑ የወረደው ለእርስዎ ነው እግዚአብሔር በሥራዎ ረክተEል አላEቸው፡፡ ግን ያውም በአዲስ ኪዳን ዘመን ሰው ሲታረድ እግዚአብሔር ብርሃን ያወርዳል ማለት እርሱን የበደላችን ተባባሪ ማድረግ ነው፡፡ ማንም ሰው እንደሚረዳው ግን ብርሃኑ የሰማዕትነት ዋጋ ነው፡፡
  አባ እስጢፋኖስ ለዘመናት ታሪኩን ተጋድሎው በክፉዎች ተቀብሮ ሲኖር አሁን ግን ከንጋት ይልቅ እየጠራ የሰማዕትነቱ ዜና እየወጣ ነው፡፡ ሸዋ ላይ አባ እስጢፋኖስ መናፍቅ ተብሎ ይወገዛል፡፡ ተአምረ ማርያምም የመገደሉን ዜና ያበስራል፡፡ ትግራይ ላይ ደግሞ ጉንዳጉንዲ በተባለው ገዳም ሰማዕትነቱ ይታወጃል፡፡ ገድሉ ይነበባል፡፡ የወንድሞች ገድል ‹‹ ገድለ አኀው›› የተባለውም የደቀ መዛሙርቱ የሰማዕትነት ዜና በግልጥ ይገኛል፡፡ በአንድ ራስ ሁለት ምላስ እንደሚባል በአንድ ቤተክርስቲያን መናፍቅና ቅዱስ እየተባለ መጠራቱ ይደንቃል፡፡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህም ገድለ አባ እስጢፋኖስ በገዳሙ ታትሞ በየስፍራው ይሸጣል፡፡ የእውነተኞች ዜና ተቀብሮ አይቀርምና፡፡

  ReplyDelete
 16. በአማርኛ ብጽፈውም ሃሳቤን ያልተረዳ ወገን ስላለ መግባባት ላይ ብንደርስ በማለት አባባሌን ለማብራራት እሞክራለሁ ፡፡
  ኢየሱስ በስጋ የተገለጠ /በተዋኀዶ/ አምላካችንና ፈጣሪያችን ነው ፡፡ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ ነው ፡፡ በዚህ አገላለጽ ላይ ከተስማማን የተቀረው ቀላል ይመስለኛልና እስቲ እንመልከት ፡፡ የሰውን ሥጋ በመዋሃዱ ከመንበሩ የተነሳ ቢመስለንም ፣ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ /ሥላሴ/ ዓለምን በሦስትነት እያስተዳደሯት ከሥፍራቸው ዝንፍ ሳይሉ ፣ እየተቆጣጠሯት በአንድነት ይገኛሉ ፤ ይኸ ሶስትነታቸው ለቅጽበት ያህል እንኳን አንተሻረም ፡፡ የአምላክነት ሥልጣኑን ስላልተገፈፈ ወይም ስላልተወረሰ ምክንያት ፣ ኢየሱስን ደሙን አፍስሶ በመስቀል ላይ በመታገስ ከራሱ ጋር አስታረቀ እንላለን እንጅ ፣ ከሶስቱ አካላት ተነጥሎ ለሌላ ወገን እንደ አማለደን አንልም ፡፡ እሱ ራሱ ሰው ቢሆንም አምላክ ስለሆነ ያስታረቀን ከራሱ ጋር ነው ብዬም አምናለሁ ፡፡

  በቋንቋችን ማማለድ ወይም ማስታረቅ ሶስት አካላት ያስፈልጉታል አማላጅ ፣ ተማላጅና የሚማለድለት አካል ፡፡ በዚህ በመለኮታዊ ጥበብና ፈቃድ ላይ አማላጁና ተማላጁ እሱ ራሱ ስለሆነ ከራሱ ጋር አስታረቀን እንላለን ፡፡ ይኸም እርቅ /በአዳም በኩል የተዋረስነውን ኃጢአት የመደምሰስ ሥራ በሌሎች ቅዱሳንና ነቢያት ሊፈጸም ስላልተቻለ/ በመስቀል ላይ አንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የተፈጸመ በመሆኑ ዘላለማዊውን እርቅ አስገኘልን እንላለን እንጅ ፣ በየዕለቱ ለምንፈጽመው የስጋ ድካምና የክህደት ሥራ ሁሉ ዛሬም አማለደ ፣ ነገም አማለደ እንደ ከሃዲዎቹ ስንል አንኖርም ፡፡ ለሌላ አካል አማለደን የምትሉ ካላችሁ ፣ የኢየሱስን አምላክነት አለመቀበል መሆኑን እንድታጤኑት አሳስባለሁ ፡፡ ሌባው ስለሌብነቱ ፣ ዘማዊውም ስለ ሴሰኛነቱ ዕለት ተዕለት ያማልደኛል የሚል ሥርዓት ስላለ ልዩነቴን ለማሳወቅ የተጠቀምኩበት ቃል ነው ፡፡ በዚህ አገላለጼ ከተግባባን ልዩ ቋንቋ የለንም ፡፡

  ከዚህ በተረፈ ኢየሱስ እኛን ለማስተማር ምሳሌ ፣ እውነተኛ መምህርም በመሆኑ የተናገራቸውን በመከተል ከአምላክነት ሥልጣኑ ፈቀቅ ያለ የሚመስለን ካለን በነገሩ ዕውቀት ያላቸውን ሊቃውንትን እናማክር ፡፡ ለኔ ወደ ምድር ቢመጣም ከነሥልጣኑ ነው ፡፡ አባቴ ፣ አምላኬ የሚሉ አገላለጾቹ እኛ ማለት ያለብንን ሲያስተምረን እንጅ አምላክ የሆነው ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሱም አምላክ አለው ማለት አይደለም ፡፡ ይህን አሌ ለማለት የምንሞክር ካለን ወደ ስህተት መንገድ ይመራናልና እንደ ወንድም ተጠንቀቁ እላለሁ ፡፡

  ለሁለተኛው አመልካች እኔ በጽሁፌ መግቢያ ላይ ገልጫለሁ ፡፡ የዐፄ ዘርአ ያዕቆብንም ሆነ የአባ እስጢፋኖስ ገድል ወይም ተአምረ ማርያም የሚባለውን መጽሐፍ አንብቤው አላውቅም ፡፡ መጽሃፉ ከዚህ ቀደም ያጋጠመኝ በግዕዝ የተጻፈ ስለነበረ ምን እንደሚል የማወቅ ዕድሉ አልተፈጠረልኝም ፡፡ ከተጻፈው ግን በመነሳት ያልተዛባ ወይም ያልተጋነነ ትክክለኛ መግለጫዬን ሰጥቻለሁ ፡፡ እግዜር ደግሞ ዕድሜና ዕድሉን ካመቻችልኝ ይኸን እናንተ ያነበባችሁና የተረዳችሁትን መጽሃፍ ለማንበብ እቅዱ አለኝ ፡፡ በስማ በለው ግን ለመሥራት ዘመኑ ተቀያይሯል ፡፡ አያስኬድም ፤ በተመሳሳይ የመስራት ጥበብ /ፎርጀሪ/ እጅግ አድጓልና እጠነቀቃለሁ ፡፡

  ስለ ደብረ ብርሃን ስያሜ የተባለው እውነት ከሆነ ድንቅ መገለጥ ነው ፡፡ ትግራይ ሳንገባ /ይኸ የሃይማኖት ቋንቋ የጐሳ ተጽዕኖ ተሸክሞ እንዳይሆን እሰጋለሁ/ ጣና ሃይቅ ከሚገኙት ደሴቶች ደቅ እስጢፋኖስ ማለት የማንኛቸው መታሰቢያ ነው ፡፡ የተደበቀና የተገፋ ታሪክ ከሆነ ፣ የዚህ አባት መታሰቢያ እስከ ዛሬ አይኖርም ነበርና አሠራራቸውን መመርመሩ የተሻለ ይመስለኛል ፤ እየገደሉ መታሰቢያና ማስታወሻ ማስቀመጡ ስላልተጣጣመልኝ ነው ፡፡ የሌላ እስጢፋኖስ ማስታወሻ ከሆነ ግን መጽሃፉን እስከማነበው ድረስ ታገሱኝ እላለሁ ፡፡

  እኔ ለራሴ ለመማማር በሚል መንፈስ ሁሉንም የግል አስተያየቶች እጽፋለሁ ፡፡ ሃሳቤ የሚስማማው ካለ እሰየው ፤ የማይስማማው ሰው ደግሞ ቁልጭ እያደረገ ከነምክንያቱ ወዲህ ቢልልኝ ደስ ብሎኝ የምማርበት ከሆነ ለመቀበል ፤ የማይዋሃደኝ ከሆነ ደግሞ ምክንያቴን ለማስረዳት እሞክራለሁና ፣ ይኸን መንፈስ ብትከተሉት ለሁላችንም መልካም ነው ፡፡ እኔ ስለጻፍኩ ማንንም አላጠምቅም ፤ ወይም ክርስትና አላነሳም ፤ ሌላውም ስለጻፈና ስላስነበበኝ ከእምነቴ ፍንክች አያደርገኝም ፤ አመለካከትን በመለዋወጥ ግን ብዙ እንማማርበታለን ፡፡ ከእኛ ውጭ የሚሽከረከሩትን አመለካከቶችና አካሄድ እንቃኝበታለንና በርቱ ፡፡

  ስለ አስተያየቶቻችሁ ሁሉ አመሰግናለሁ

  ReplyDelete
  Replies
  1. you said "የሰውን ሥጋ በመዋሃዱ ከመንበሩ የተነሳ ቢመስለንም ፣ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ /ሥላሴ/ ዓለምን በሦስትነት እያስተዳደሯት ከሥፍራቸው ዝንፍ ሳይሉ ፣ እየተቆጣጠሯት በአንድነት ይገኛሉ ፤ ይኸ ሶስትነታቸው ለቅጽበት ያህል እንኳን አንተሻረም" and "ለኔ ወደ ምድር ቢመጣም ከነሥልጣኑ ነው"


   you said "የአምላክነት ሥልጣኑን ስላልተገፈፈ ወይም ስላልተወረሰ ምክንያት ፣ ኢየሱስን ደሙን አፍስሶ በመስቀል ላይ በመታገስ ከራሱ ጋር አስታረቀ እንላለን እንጅ ፣ ከሶስቱ አካላት ተነጥሎ ለሌላ ወገን እንደ አማለደን አንልም ፡፡ እሱ ራሱ ሰው ቢሆንም አምላክ ስለሆነ ያስታረቀን ከራሱ ጋር ነው ብዬም አምናለሁ "


   "ይኸ ሶስትነታቸው ለቅጽበት ያህል እንኳን አንተሻረም" contradict with "እሱ ራሱ ሰው ቢሆንም አምላክ ስለሆነ ያስታረቀን ከራሱ ጋር ነው ብዬም አምናለሁ "


   at least you should have said ያስታረቀን ከራሱ ጋር,and ከአብ እና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር because per your word ይኸ ሶስትነታቸው ለቅጽበት ያህል እንኳን አንተሻረም"

   "ኢየሱስን ደሙን አፍስሶ በመስቀል ላይ በመታገስ ከራሱ ጋር አስታረቀ እንላለን እንጅ ፣ ከሶስቱ አካላት ተነጥሎ ለሌላ ወገን እንደ አማለደን አንልም "

   If you meant "ለሌላ ወገን" = ከአብ እና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር, you are totally wrong, because ኢየሱስን ደሙን አፍስሶ በመስቀል ላይ በመታገስ ከራሱ ጋር,ከአብ እና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አስታረቀ እንላለንና.

   you said "ለሌላ አካል አማለደን የምትሉ ካላችሁ"
   If you are saying only "ከራሱ ጋር" again that leads us to only JESUS which I don't want to get into it now.

   To make it easier for you
   "ከራሱ ጋር ከአብ እና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አስታረቀ" = "KEMELEKOT" ጋር

   you said በቋንቋችን ማማለድ ወይም ማስታረቅ ሶስት አካላት ያስፈልጉታል አማላጅ ፣ ተማላጅና የሚማለድለት አካል "true, however, you failed to tell us the ሶስት አካላት, i.e. አማላጅ ፣ ተማላጅና የሚማለድለት አካል
   Let me try
   አማላጅ = ኢየሱስ (በተዋኀዶ)
   ተማላጅ = አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ /ሥላሴ/ (MELEKOT)
   ተማላጅና የሚማለድለት አካል = አዳም and his children

   You said ይኸም እርቅ /በአዳም በኩል የተዋረስነውን ኃጢአት የመደምሰስ ሥራ በሌሎች ቅዱሳንና ነቢያት ሊፈጸም ስላልተቻለ/ በመስቀል ላይ አንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የተፈጸመ በመሆኑ ዘላለማዊውን እርቅ አስገኘልን እንላለን እንጅ" is true

   but you and I were not present when our lord DIED and we didn't exist 50 years ago(am assuming that you are less than 50 years old) We don't get automatic salvation just because we were born humans, however, when our parents took us to church while we are 40 or 80 days old and baptized and got his body and blood we are saved and born again, who is አማላጅ for us "ኢየሱስ (በተዋኀዶ)". This will continue until he comes back. So he is አማላጅ yesterday, now and forever. Even በየዕለቱ ለምንፈጽመው የስጋ ድካምና የክህደት ሥራ ሁሉ ዛሬም አማለደ ፣ ነገም አማለደ እንላለን. The difference is HOW. I don't believe he prays for me now as he did when he was on earth (BESGA), but by his blood. If you go to kiddase, that is what is given to you and and all others በየዕለቱ ለምንፈጽመው የስጋ ድካምና የክህደት ሥራ ሁሉ, his blood is the only way out as you said "በሌሎች ቅዱሳንና ነቢያት ሊፈጸም ስላልተቻለ". If it was enough በሌሎች ቅዱሳንና ነቢያት ሊፈጸም, we did not need to have his blood.

   Delete
  2. "አባቴ ፣ አምላኬ የሚሉ አገላለጾቹ እኛ ማለት ያለብንን ሲያስተምረን" half true, what about this
   "And a voice from heaven said, "This is my Son, whom I love; with him I am well pleased" Matthew 3:17

   ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ ነው will answer አባቴ ፣ አምላኬ የሚሉ አገላለጾቹን

   ፍጹም ሰው can say አምላኬ. HOW? it needs some explanation and I won't try it now since i wrote too much already. But i can write if you insist.
   just to remind you please do not deny his ፍጹም ሰውነት and say "እኛ ማለት ያለብንን ሲያስተምረን ነው " what about this

   In old days "usually the prisoner had to carry his own cross and "to crucify a man is terrible. The prisoner had painful injuries. The sun burned him and insects crawled over him. Most of all, the weight of the body was so heavy that the man had to struggle for every breath"

   our lord's suffering for our sins is beyond imaginable. Are you saying he was acting?

   "Carrying the cross by himself, he went to the place called Place of the Skull (in Hebrew, [Golgotha])There they nailed him to the cross. Two others were crucified with him, one on either side, with Jesus between them...Jesus knew that his mission was now finished, and to fulfill Scripture he said, I am thirsty. A jar of sour wine was sitting there, so they soaked a sponge in it, put it on a hyssop branch, and held it up to his lips. When Jesus had tasted it, he said, "It is finished!" Then he bowed his head and released his spirit. John 19

   Please note the words below and many others

   "Carrying the cross by himself"

   "I am thirsty"

   "he bowed his head" Was he acting and እኛ ማለት ያለብንን ሲያስተምረን ነው?

   I thank you for this discussion, i am ready to learn as well, i might have wrote some mistakes as well if so let me know

   peace

   Delete
 17. ከተአምረ ማርያም ወደ ነገረ መለኮት ትንተና ሽግግር ፤ ይኸ ሁሉ የአምላክ ጥበብ እንደሆነ ማን ያስተውላል ፡፡

  ወንድሜ ያደረከው ጥሩ ምልከታ ነው ፡፡
  1. ኢየሱስ ደሙን አፍስሶ ከራሱ ጋር አስታረቀን ማለት ከአብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ጋር ነው ፡፡ የእኔም አባባል ይህንኑ ለመግለጽ ነው ፡፡ ማጠንከር የፈለግሁት ኢየሱስን ከሥፍራው ገለል አድርገው ከአባቱ ጋር እንዳስታረቀ ዓይነት ከሚሉት ራሴን ለመለየትና ትኩረትን ለመስጠት ነው እንጅ ፣ የራሴን አባባል ለመቃረን አይደለም ፡፡ በመንበር ካሉት ሦስት አካላት አለመለየቱን መግለጼም ለዚሁ ሲባል ነው ፡፡ at least you should have said ያስታረቀን ከራሱ ጋር, and ከአብ እና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር because per your word ይኸ ሶስትነታቸው ለቅጽበት ያህል እንኳን አልተሻረም" ያልከውን እርምት ተቀብያለሁ ፡፡

  2. አማለደን ማለት የሚገባን ከአዳም የውርስ ኃጢአት ነጻ ስላወጣን ነው እንጅ ፣ የሥጋ ድክመታችንንማ ንስሐ ስንገባ በይቅርታው ፣ በምህረቱ ነው የሚያልፈን ፤ ስንፍናችንን ሁሉ እያየ እንዳላየ ይተወዋልና ፡፡ የሰው ልጅ በእናቱ ማህጸን ከተፀነሰ አንስቶ የአዳምን የኃጢአት ፍርድ ይወርሳል ፡፡ ይህ የአዳም ኃጢአት ያመጣውን የፍርድ ውሳኔ የሚሽር ሌላ ብልሃትና ኃይል ስለሌለ /ሰው ራሱን በማንጻትም መስዋዕት ለመሆን ብቁም ስላልሆነ/ አምላክ እኛን ለማዳን ሲል ሰው መሆንን ፈቀደ ፡፡ ያ በሰው ዘር ላይ ሁሉ ይተላለፍ የነበረውን ፍርድ አንዴ በሞቱ በመሻር ለዘለዓለም እንዲሆነን አጸናው ፡፡ እኔም ስወለድ አስታረቀኝ እላለሁ ፤ የኔ የልጅ ፣ ልጅ ልጆችም ወደፊት አማለደን ብለው ይመሰክራሉ /በክርስትናው ከገፉበት ማለቴ ነው/፡፡ የዕለት ተዕለት ኃጢአታችንን ግን በእምነት ቀርበን ኃጢአተኛነታችንን /በማወቅና ባለማወቅ የምንፈጽመውን ስህተት/ ማረን ብለን ስንጸልይ ይቅር ይለናል ፣ ጥፋታችንን ሁሉ ይሽርልናል ብዬ አምናለሁ ፡፡ በዚህ አረዳድ ላይ ልዩነት ያለን ስለመሰለኝ ፣ የምትለኝን እጠብቃለሁ ፡፡

  3. “"አባቴ ፣ አምላኬ የሚሉ አገላለጾቹ እኛ ማለት ያለብንን ሲያስተምረን" half true, what about this "And a voice from heaven said, "This is my Son, whom I love; with him I am well pleased" Matthew 3:17” ልጅ የሚለውን ቃል ለትስብዕት በምንጠቀመው ዘይቤ እንዳንመለከተው ፡፡ እንደ እኛ ቋንቋ ከተረዳነው በመሃላቸው መቀዳደመን ይፈጥራልና ነው ፡፡ በዚህ አገላለጽ የስላሴን ምስጢር ለማስረዳት ፣ አምላክነቱንም ለማብሰር የተጠቀመበት አገላለጽ እንደሆነ እንማራለን ፡፡

  4. “ፍጹም ሰው can say አምላኬ.” የፍጹም ሰው መሆንን አገላለጽ እኔ የምረዳው ሰዎች የምትሃት ሃይል ፣ መንፈሳዊ ነገር ብለው እንዳይጠራጠሩት ፣ የሚዳሰስ አካል ፣ የሚበላ ፣ የሚጠጣ ፣ የሚያድግ ፣ የሚተኛ ፣ የሚነሳ ፣ የሚያዝን ፣ የሚያነባ ሰውነት /ገላ/ መኖሩን እንዲመለከቱ የተገለጸበት ነው ፡፡ ምክንያቱም በሰው ብልሃት የማይቻሉ በቃሉ ብዙ ተአምራትን ፈጽሟል ፣ በባህር ላይ በእግሩ ተጉዟልና ያን የመናፍስት ሥራ አድርገው የመገንዘብ ልማድ በአይሁድ ዘንድ ስለነበረ የተጠቀመበት ቃል ነው፡፡ ከትንሣዔ በኋላ ሁሉ እንኳን ፣ በተዘጋ ቤት ሲገባ ፣ ትንሣዔውን እንዳይሰናከሉበት አካሉን እንዲዳስሱት ያደረገ ጥርጣሬን ከአእምሮአቸው ለማስወገድ ነው ፡፡ “ፍጹም ሰው ሲሆን አምላኬ አለ ፤ ፍጹም አምላክ ሲሆን ደግሞ ሙት አስነሳ ካልን ተዋህዶውን እናፋልሳለን” እላለሁ ፤ ወደ ሌላ የእምነት ዓይነትም ይወስደናል ፡፡ ይኸም ሁለተኛው የግንዛቤአችን ልዩነት ይመስለኛልና መግለጫ ካለህ ደስ ይለኛል ፡፡

  5. Our lord's suffering for our sins is beyond imaginable. Are you saying he was acting? - ሮማዊ ላልሆነ ዜጋ የሮማውያን አቀጣጥ ዘዴ እጅግ ከባድና የሰቆቃ ነው ፡፡ ቶሎ ያልሞተ ሰው እኮ ተንጠልጥሎ ይከርማል ፣ ወይም ከበዛበት ጭኑን ሰብረው ሞቱን ያፋጥኑለታል ፡፡ የጌታ በአጭር ሰዓት ውስጥ ነፍሱን መስጠቱን /መሞቱን/ እንኳን ተጠራጥረው ነበር ፤ የጐኑ መወጋትም እርግጥ መሞቱን ለማረጋገጥ ነበር /ዮሐ 19፡32-34/፡፡ ጌታችንና መድኃኒታችን በተዋሃደው አካሉ እኛን ለማዳን ሲል በመስቀል ላይ ሞቷል ፡፡ ነገር ግን እዚህም በፍጹም ሰውነቱ ብቻ አንልም ፡፡ ይህን ስቃይ በስጋው ብቻ ካልን አምላካችን ሞተልን ማለት ያስቸግረናልና ፡፡ ወደ ሌላ መሄድ ካልፈለግን በዚህም መግለጫዬ የምንስማማ ይመስለኛል ፡፡

  ዛሬም ወዳጄና ወንድሜን አመሰግንሃለሁ ፡፡ ብዙ የማላውቀው ትምህርት አለና ከማስተማር አትስነፍ ፡፡

  ReplyDelete
 18. I thank for taking your time to respond,

  "የዕለት ተዕለት ኃጢአታችንን ግን በእምነት ቀርበን ኃጢአተኛነታችንን /በማወቅና ባለማወቅ የምንፈጽመውን ስህተት/ ማረን ብለን ስንጸልይ ይቅር ይለናል ፣ ጥፋታችንን ሁሉ ይሽርልናል ብዬ አምናለሁ ፡፡ በዚህ አረዳድ ላይ ልዩነት ያለን ስለመሰለኝ ፣ የምትለኝን እጠብቃለሁ" It is perfectly true but is not the only way,

  I believe in the power of prayer,
  1. በእምነት ቀርበን ኃጢአተኛነታችንን /በማወቅና ባለማወቅ የምንፈጽመውን ስህተት/ ማረን ብለን ስንጸልይ
  2. If you pray for me
  3. If other respected Christians pray for me
  4. If i confess to or others
  5. Holy Kurban
  6. If angels pray for me (especially my Guardian angel, since he is always with me and has to report everyday to my holy father)
  7. If God just want to forgive me

  "Then he took a cup, gave thanks, and gave it to them, saying, "Drink from it, all of you This is my blood of the covenant, which is poured out for many for the forgiveness of sins" Mathew 26:27 I was just trying to stay in the topic and I was not trying to exclude the power of prayer

  ReplyDelete
 19. YOU SAID "አባቴ ፣ አምላኬ የሚሉ አገላለጾቹ እኛ ማለት ያለብንን ሲያስተምረን" half true, what about this "And a voice from heaven said, "This is my Son, whom I love; with him I am well pleased" Matthew 3:17” ልጅ የሚለውን ቃል ለትስብዕት በምንጠቀመው ዘይቤ እንዳንመለከተው ፡፡ እንደ እኛ ቋንቋ ከተረዳነው በመሃላቸው መቀዳደመን ይፈጥራልና ነው ፡፡ በዚህ አገላለጽ የስላሴን ምስጢር ለማስረዳት ፣ አምላክነቱንም ለማብሰር የተጠቀመበት አገላለጽ እንደሆነ እንማራለን"

  I don't think I expressed myself very well,
  If Our Lord said አባቴ ፣ አምላኬ who are we to correct him, to even question him or interpret it in other way. It will be wise if we take the word አምላኬ as is and ask his grace to understand it or ask holy fathers who are still alive and good enough to care about tewahdo willing to teach us.
  This is how I am going to put it
  If you agree we humans are made of soul and body.

  When king David once prayed he said

  "Praise the LORD, my soul;
  all my inmost being, praise his holy name.
  Praise the LORD, my soul,
  and forget not all his benefits" Psalm 102/103

  please note the word "my soul" is he really talking to his soul? what about his body? The truth is the same David, (only one David), speaking BESEGA MEDEB. Same analogy works for "አምላኬ" "አምላኬ" Our Lord was speaking BESEGA MEDEB because ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ ነውና.
  you said "ፍጹም ሰው ሲሆን አምላኬ አለ ፤ ፍጹም አምላክ ሲሆን ደግሞ ሙት አስነሳ ካልን ተዋህዶውን እናፋልሳለን"

  ተዋህዶውን እናፋልሳለን not true

  let me change it for you
  ፍጹም ሰው ስለሆነ አምላኬ አለ ፤ ፍጹም አምላክ ስለሆነ ደግሞ ሙት አስነሳ or ፍጹም አምላክ ስለሆነ ተነሳ this is the beauty of tewahdo

  "ነገር ግን እዚህም በፍጹም ሰውነቱ ብቻ አንልም ፡፡ ይህን ስቃይ በስጋው ብቻ ካልን አምላካችን ሞተልን ማለት ያስቸግረናልና"

  I did not say "በስጋው ብቻ or በፍጹም ሰውነቱ ብቻ" I would say አምላክ በስጋ ሞተ
  we don't say አምላካችን ሞተልን again we will say አምላካችን በስጋ ሞተልን

  You need to be careful for this sentence "ይህን ስቃይ በስጋው ብቻ ካልን". DEATH AND SUFFERING ለአምላክ BAHIRY AYSMAMAM. WE ALWAYS HAVE TO SAY

  TEWELEDE በስጋ

  ADEGE በስጋ

  TELAKE በስጋ

  ALKESE በስጋ

  DEKEME በስጋ

  TERABE በስጋ

  TEYAZE በስጋ

  asked "where did you put alazar's body" በስጋ

  TEGNA በስጋ

  TETEMA በስጋ

  MOTE በስጋ

  TENESA በስጋ AND SO ON

  ReplyDelete
 20. እግዚአብሔር ጸጋውን ያብዛልህ ፡፡
  - አስቀድመህ በሰባት ዝርዝር የተነተንካቸውን ትክክል ናቸው ፡፡ እኔ ለመግለጽ የሞከርኩት የነበረ በአጭሩ ስለ ሃጢአት ሥርየት /በውርስና በየቀኑ ድክመት/ በኢየሱስ በኩል ስለሚገኘው ምህረት ላይ ብቻ በማተኮር ነበረ ፡፡ ጠቅላላ ዝርዝሮችህን እኔም የምጋራቸው ናቸው ፡፡

  - ኢየሱስ አባቴና አምላኬ ያለበትን ምስጢር ለማረም ወይም ለመተርጐም ችሎታው የለኝም ፡፡ እንኳን እኔ እጃቸውን እየጐተተ ያስተማራቸው ሐዋርያቱ ፣ እራሱ መልሶ ካልተረጐመና በቀጥታ ካልነገራቸው በስተቀር የነገራቸውን ትምህርት አይገነዘቡትም ነበር ፡፡ ምን አለፋህ አንዳንዴ በቀጥታ ተነግረውም እንኳን አይገባቸውም ነበር ፡፡ እኔ ደግሞ ከእነሱ ሳይሆን በዘመናችን ከሚገኙት መሃይም የማልለይ ሰው ነኝ ፤ ያልተማሩትን የምበልጣቸው አንብቤ በመረዳቴ ብቻ ነው ፡፡ አምላኬ ስለሚለው አባባል ለመግለጽ የታገልኩት በጽሁፌ የአምላክነቱን ሥልጣን እንዳልዳፈር ለመጠንቀቅ በማሰብ ነበረ ፡፡ ስለዚህም ያልካቸውን ነጥቦች የምከራከርባቸው አይደሉም ፡፡ የምትለውን ተረድቻለሁ ፡፡ የምፍጨረጨረው ትንሽ ብረዳና ራሴን ከሚያጭበረብሩ ግለሰቦች ብታደግ በማለት ነው እንጅ የሃይማኖት ሊቅ ነኝ ብዬ አይደለም ፡፡

  - ይኸ "we don't say አምላካችን ሞተልን again we will say አምላካችን በስጋ ሞተልን" ከዚህ ቀደም በዚህ ዓይነት መልኩ አልተገነዘብኩትም ነበር ፡፡ አሁን ስለጻፍከው ግን ብዙ ጥያቄዎችን እንደሚመልስልኝ ይሰማኛል ፡፡ እኔ በግርድፍ የገለጽኩትን ፣ እያስተካከልክልኝ ስለሆነ አመሰገንኩ ፡፡

  በሃይማኖተ አበው መጽሐፍ ይመስለኛል /ቆይቷል ካነበብኩት/ ስለ መለኮትና ሥጋ ተዋህዶ ምሳሌዎች ሲሰጥ በጋመ ብረት /ቀጥቃጮች እንዳዘጋጁት የጋለ ብረት/ ይመስለውና ፡፡ ብረቱ ሲቀጠቀጥ ግመቱም ከብረቱ ጋር አብሮ እንደሚሰፋ ሁሉ ፣ ሥጋ በሞተበትም ሰዓት ፣ መለኮት ሞተ ማለት ሰለማንችል አብሮት ነበረ እንላለን ይላል ፡፡ መለኮት ባይሞትም በተዋህዶው ጸንቶ የሥጋ ሞትን አብሮ በመሆን ተጋርቷል ፡፡ ሌላ ቦታም አንድ ሰው በሚሞትበት ጊዜ ስጋው ሲሞት ነፍስ ባትሞትም ሰውየው ሞተ እንደሚባለው /ሥጋና ነፍስን በአንድነት አድርጐ እንደ ሞቱ ያህል እንደሚገልጸው/ ዓይነት ማለት ነው ፡፡ የኔ መግለጫ እነዚህን ምሳሌዎች የተከተለ ነበረ ፡፡ መለኮት ሞተ ባንልም ስጋን ተነጥሎ ስላልሄደ አምላካችን ሞተልን የሚለውን ግንዛቤ ያዝኩኝ ፡፡

  የየትኛው የእምነት ድርጅት እንደሆነ በትክክል አላስታውስም መለኮትና ሥጋ መስቀል ላይ ተለያይተዋል ብሎ ይደመድማል ፡፡ ለዚህም እንደ ማስረጃ የሚያደርጉት መለኮት ሥጋን ትቶት ሲሄድ "አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ " ብሏልና ብለው ይከራከራሉ ፡፡ ይኸ ቤተ ክርስቲያን ምስጢር ብላ የምታስተምራቸው በሙሉ በሥርዓት ተብራርተው እምንማርበት መንገድ ስለሌለ ግድፈቶችን ማድረጋችን አይቀርም ፡፡ በበኩሌ የምፈልገው እንደዚህ ያለውን የምስጢር ግድፈት የሚያርመኝ ሰው ነበርና ስለማንኛውም "እግዚአብሔር ይመስገን" እላለሁ ፡፡

  አንዳንድ ቦታዎች ላይ ብቅ እያልክ ሃሳብክን ብታካፍለን በግሌ ብዙ እጠቀማለሁ ፡፡
  አመሰግናለሁ ፡፡

  ReplyDelete
 21. ትንሽ ለመጨመር ያክል፡፡
  ኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ጊዜ ‹‹አባት ሆይ›› ሌላ ጊዜ ደግሞ ‹‹አምላኬ አምላኬ›› ሲል እናገኘዋለን፡፡ እርሱ ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው ነው፡፡ በመለኮትነቱ የአብ የመንፈስ ቅዱስ እኩያ፣ የባሕርይ አምላክ፣ የምስጋና ተካፋይ፣ ስግደት ተቀባይ፣ ዘመን የማይቆጠርለት፣ ኃይሉ የማይለካ፣ ፍጻሜ የሌለው አምላክ ነው፡፡ በሰውነቱ የሰው ልጆች የሥጋ ዘምደ፣ ታላቅ ወንድም፣ በኩረ ምዕመናን፣ የቤተክርስቲያን መሪ ፣ነቢይ ፣ካህን ንጉስ መሥዋዕት ነው፡፡ እርሱ አባት ሆይ በማለቱ ፍጹም አምላክነቱን የሚክዱትን አርዮሳውያንን ያሳፍራል፡፡ አምላኬ አምላኬ በማለቱ አምላክነቱን አጉልተው ሰውነቱን የሚክዱትን ቤተ አውጣኪን ይገስጻል፡፡
  አባቴ ሆይ የሚለው ቃሉ አምላክነቱን ይገልጻል፡፡ ምክንያቱም አብ አባቱ ከሆነ ፈጣሪው ሊሆን አይችልምና፡፡ ማንም ሰው የሚወልደውን አይፈጥረውም፡፡ የሚፈጥረውንም አይወልደውምና፡፡ ቃሉ፡- ‹‹እንግዲህ ሰንበትን ስለ ሻረ ብቻ አይደለም፡፡ ነገር ግን ደግሞ ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር አስተካክሎ እግዚአብሔር አባቴ ነው ስላለ ስለዚህ አይሁድ ሊገድሉት አብዝተው ይፈልጉት ነበር፡፡›› (ዮሐ 5፡18) ይላል፡፡ ማንኛውም አይሁዳዊ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ እያለ ይናገራል፡፡ ታዲያ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ስላለ ለምን ተቃወሙት; ስንል እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ያለበት አገላለጽ እኩያነትን የሚገልጥ ስለነበረ ነው፡፡ በሌላ ስፍራም ‹‹እኔና አብ አንድ ነን›› (ዮሐ. 10፡30) ብላEልና፡፡ ፡፡
  ‹‹አምላኬ አምላኬ›› የሚለው ቃሉ ደግሞ ፍጹም ሰውነቱን ይገልጻል፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስን ፍጹም ሰውነት የማይቀበሉ ቤተ አውጣኪያውያን ነቢይነቱን፣ ካህንነቱን፣ ማስታረቁን፣ አይቀበሉም፡፡ እርሱ አምላክ ነው እንዴት አስታራቂ ይባላል ይላሉ፡፡ ነገር ግን እርሱ ፍጹም ሰውም ነው፡፡ በሰውነቱ አምላኬ አምላኬ ብላል፡፡

  ትንሽ ስለ ዘለዓለማዊ ተዋህዶ ልጨምር፡፡
  አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ በመባል በዋሕድና መለኮት ራሳቸውን ከገለጹት ሦስት ህላዌያት (አካላት) አንዱ ‹‹ቃል›› (ወልድ) ትስብእትን በመወሐድ አንድ ህላዌ፣ አንድ ክርስቶስ ፣ አንድ ዐማኑኤል፣ ኾኖአልና በዚሁ በአንዱ ህላዌ አምላክም ሰውም ይባላል፡፡ በዚሁ በአንዱ ህላዌ ግብረ መለኮትንም ግብረ ትስብዕትንም ፈጽሞአል፡፡ ይህንን ውሕደቱን ቅዱስ ቄርሎስ በኮሬብ ለሙሴ በታየው ቁጥቀጦና እሳት መስሎታል፡፡ በኮሬብ የታየው የቁጥቀጦና የእሳት ውሕደት የመለኮትንና የትስብእትን ተዋሕዶ ያመለክታል፡፡ በውሕደቱ ታሪክ የቁጥቀEጦው አካልና ባሕርይ ሳይጣፉ እንዳሉ ነበሩ፡፡ እንደዚሁም የእሳቱ አካልና ባሕርይ ሳይጣፉ እንዳሉ ኾነው ታይተዋል፡፡ ያልተጣፉ አካላትና ባሕርያት በተገኙበት ተዋሕዶ ሁለቱም በተዓቅቦ ነበሩ፡፡ በተጨማሪም በሃ.አ. ዘቄርሎስ እንደሚያስረዳው ብረት በእሳት ውስጥ ሲጨመር የእሳቱን ሙቀት ይወስድና የብረትና የእሳት ውሕደት ይፈጠራል፡፡ የትኛውም ሌላውን ወደ መኾን አይለወጥም፡፡ የጋለውም ብረት በመዶሻ ሲመታ ከተወሐደው እሳት ጋር በአንድነት ይመታል፡፡ ነገር ግን የሚጎዳው ብረቱ እንጂ ከብረቱ ጋር አብሮ የተመታው እሳት ከቶ አይጎዳም፡፡ ከትስብዕት ጋር የተወሐደው መለኮትም በትስብእቱ መከራን ተቀብላEል፡፡ ነገር ግን መለኮቱ በመከራው አልተጎዳም፡፡ ይህም ምሳሌ የእሳቱና የብረቱ አካልና ባሕርይ ያለ መጠፋፋት በተዓቅቦ መወሐዳቸውን ያስረዳል፡፡

  ኃጢያት ሁለት ታላላቅ ውጤቶች አሉት፡፡ አንደኛው ሞት ሲሆን ሁለተኛው ብቸኝነት ነው፡፡ በብሉይ ዘመን የሕዝቡን ኃጢአት እንዲሸከሙ የተመረጡት ፍየሎች የኃጢአት ውጤት የሆነውን ሞትና ብቸኝነት እንዲቀበሉ ይፈረድባቸው ነበር፡፡ ኃጢአት ከእግዚአብሔርና ከጸጋው ይለያል፡፡ ያ ፍየል ኃጢአት የሚያስከትለውን የመጣልና የብቸኝነት በረሃ ስለ ሕዝቡ ሊቀበል ወደ ምድረ በዳ ይለቀቃል፡፡ አይሞትም ግን ተቅበዝባዥ ነው፡፡ አይጠፋም ግን ብቸኛ ነው፡፡ ሊቀ ካህኑ የሕዝቡን ኃጢአት በመናዘዝ በራሱ ላይ ያሸክመዋል፡፡ ፍየሉም ንጹሕ ሳለ ስለ ሕዝቡ በደለኛ ይሆናል፡፡ በደለኛ ከሆነ በደል ወደሚያስከትለው የተራቆተ ዓለም ይወሰዳል፡፡ እንዳይመለስ ያባርሩታል፡፡ ጭው ባለ በረሃ ይባዝናል፡፡ መቅበዝበዝ ከሰው ተለይቶ በተፈረደ ሕሊና መኖር ዕጣው ይሆናል፡፡ አሳዛኝ እንስሳ! ያለ ኃጢአቱ የሚደክም ምትክ! በዚያ በማስተሰሪያ ቀን ይቀርቡ የነበሩት ሁለት መስዋዕቶች ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚያሳዩ ቀስቶች ነበሩ፡፡ እርሱም በመስቀል ላይ የሕዝቡን ኃጢአት ተሸክሞ ሞትንና ብቸኝነትን (መተውን) ተቀብላEል፡፡ (ዘሌ.16'ዕብ.10፡1-4)
  ኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበለው መከራ በሥጋው'በነፍሱና በመንፈሱ ነው፡፡ ሁለመናው ስለ እኛ ታማEል፡፡ በሥጋው ግርፋት'ችንካር'የእሾህ አክሊል'በጦር መወጋት' ሞት ደርሶበታል፡፡ በነፍሱ ወዳጆች ከድተውታል፣ ጌታ ሲሆን በባሪያ ዋጋ ተስጣEል፣ ፍርድ ተዛብቶበታል ስድብና ውርደት ተቀብላEል፡፡ በመንፈሱ የደረሰበት መከራ ግን በእግዚአብሔር መተው ነበር፡፡ ማቴዎስ ይህን ሲገልጥ፡- ‹‹ ከስድስት ሰዓትም ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በምድር ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ፡፡ በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስ፡- ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ ብሎ በታላቅ ድምጽ ጮኸ፡፡ ይህም፡- አምላኬ አምላኬ ስለምን ተውኸኝ ማለት ነው፡፡ ልብን የሚሰነጥቅ ብርቱ ጩኸት ነው፡፡ ስድብን የፍርድ መዛባትን የእሾህ አክሊልን በተቀበለ ጊዜ አልጮኸም፡፡ አሁን ግን ጮኸ፡፡ የሕዝቡን ኃጢአት ተሸክሞ ወደ ብቸኝነት በረሃ የተለቀቀ ሕያው ፍየል ሆናEልና፡፡
  የኃጢአት ዋጋ የተከፈለው በሥጋው ወይም በነፍሱ በተቀበለው መከራ አይደለም፡፡ የኃጢአት ዋጋ የተከፈለው በመንፈሱ በደረሰበት ሕማም ነው፡፡ የመንፈስ ሕማም ከእግዚአብሔር መለየት ነው፡፡ አንድ ኃጢአተኛ ኃጢአት ሲሠራ እግዚአብሔር ይተወዋል፡፡ የብቸኝነት ሥቃይም ይደርስበታል፡፡ ክርስቶስም የሕዝቡን ኃጢአት የተሸከመ ቅዱስ በግ ነበርና (ዮሐ1፡29) ስለ ኃጢአተኞች በብቸኝነትና በመተው በረሃ ተንከራተተ፡፡ እግዚአብሔር የሰውን ዘር ለማዳን ቆርጦአልና፡፡ በሚወደው ልጁ ጨከነ፡፡ ልጁን ሊተው፣ በብቸኝነት በረሃ እንዲንከራተት ፈቀደ፡፡ እስከ መቼ; የኃጢአት ዋጋ እስኪከፈል፡፡ ጳውሎስ ‹‹ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለሁላችን አሳልፎ የሰጠው…›› (ሮሜ 8፡32) ይላል፡፡

  ReplyDelete
 22. ይድረስ ለ'ዲያቆን'ሉሌ

  ይህን ጽሁፍ ሳነብ የኤማሁሱ መንገደኞ ናቸዉ ትዝ ያሉኝ ጌታን ለማወቅ አይነ ልቦናቸዉ ሊበራላቸዉ ያስፈልግ ነበር:: ዛሬም የአንተ ገለጻ መሃመዳዊያን ጌታ አይወልድም አይወለድም ብለዉ እንደሚያስቡት ነዉ ምክንያቱም የጌታን መወለድ በሰዉ ባህሪ ስለመዘኑት ነዉ ያም ማለት አብርሃም ይሳቅን እንደወለደ በዚህ አሳብ ከታሰበ እንዴት ሊሆን እደሚችል አስበዉ ያንተም ጽሁፍ ሊያስረዳን የሞከረዉ ይህንኑ ነዉ :: መጽሓፍ ቅዱስ ላይ ባይጻፍ ኖሮ የበላዐም አህያ በሰዉ ልሳን ተናገረች ሲባል በአንተ ሃሳብ ከተሄደ እንዴት ሊገለጽ ይቻላል? ወይስ ሊሆን አይችልም ተብሎ ዉሽት ነዉ ልትል ነዉ::
  መቼም ቆም ብሎ ለማሰብና ምን እያደረጋችሁ እንደሆነ ለመገንዘብ እግዚአብሔር ይሁናችሁ ከማለት ዉጭ ምን ይባላል፥ አይነ ልቦናህም ሊበራልህ ያስፈልጋል ምክንያቱም በእግዚአብሔር ዘንድ አንድ + አንድ = አንድ እንጂ ሁለት ሊሆን አይችልም ለምሳሌ በጋብቻ አንድ መሆንን ይህን ለማወቅ በሎጂክ ሳይሆን ፥ ያልታወረና ጠንካራ እምነት ያለዉ ልቦና ያስፈልጋል። ይህ ደግሞ ከእግዚአብሔር ካልተሰጠ ለሚታበይ ልቦና አይታደልም፥ እመብርሃን ትዘንላችሁ....

  ReplyDelete
 23. Enante manafikan yebtekirstiyan telatoch bebetkirstyan sim eskemech tingidalachu behizibu tekebayinet sitatu ahun degmo bezi metachihu.Egziabiher libona yistachihu.

  ReplyDelete
 24. The two Anonymous's Geta yibarkachihu,

  True Orthodoxawiyan, chiwa menfesawi chiwuwut,

  Ahunim yibarkachihu elalehu,

  ReplyDelete
 25. ኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ጊዜ ‹‹አባት ሆይ›› ሌላ ጊዜ ደግሞ ‹‹አምላኬ አምላኬ›› ሲል እናገኘዋለን፡፡ እርሱ ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው ነው፡፡ በመለኮትነቱ የአብ የመንፈስ ቅዱስ እኩያ' የባሕርይ አምላክ' የምስጋና ተካፋይ' ስግደት ተቀባይ' ዘመን የማይቆጠርለት' ኃይሉ የማይለካ' ፍጻሜ የሌለው አምላክ ነው፡፡ በሰውነቱ የሰው ልጆች የሥጋ ዘምደ' ታላቅ ወንድም በኩረ ምዕመናን የቤተክርስቲያን መሪ ነቢይ ካህን ንጉስ መሥዋዕት ነው፡፡ እርሱ አባት ሆይ በማለቱ ፍጹም አምላክነቱን የሚክዱትን አርዮሳውያንን ያሳፍራል፡፡ አምላኬ አምላኬ በማለቱ አምላክነቱን አጉልተው ሰውነቱን የሚክዱትን ቤተ አውጣኪን ይገስጻል፡፡
  አባቴ ሆይ የሚለው ቃሉ አምላክነቱን ይገልጻል፡፡ ምክንያቱም አብ አባቱ ከሆነ ፈጣሪው ሊሆን አይችልምና፡፡ ማንም ሰው የሚወልደውን አይፈጥረውም፡፡ የሚፈጥረውንም አይወልደውምና፡፡ ቃሉ፡- ‹‹እንግዲህ ሰንበትን ስለ ሻረ ብቻ አይደለም፡፡ ነገር ግን ደግሞ ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር አስተካክሎ እግዚአብሔር አባቴ ነው ስላለ ስለዚህ አይሁድ ሊገድሉት አብዝተው ይፈልጉት ነበር፡፡›› (ዮሐ 5፡18) ይላል፡፡ ማንኛውም አይሁዳዊ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ እያለ ይናገራል፡፡ ታዲያ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ስላለ ለምን ተቃወሙት; ስንል እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ያለበት አገላለጽ እኩያነትን የሚገልጥ ስለነበረ ነው፡፡ በሌላ ስፍራም ‹‹እኔና አብ አንድ ነን›› (ዮሐ. 10፡30) ብላEል፡፡
  ‹‹አምላኬ አምላኬ›› የሚለው ቃሉ ደግሞ ፍጹም ሰውነቱን ይገልጻል፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስን ፍጹም ሰውነት የማይቀበሉ ቤተ አውጣኪያውያን ነቢይነቱን፣ ካህንነቱን፣ ማስታረቁን፣ አይቀበሉም፡፡ እርሱ አምላክ ነው እንዴት አስታራቂ ይባላል ይላሉ፡፡ ነገር ግን እርሱ ፍጹም ሰውም ነው፡፡ በሰውነቱ አምላኬ አምላኬ ብላEልና፡፡

  ትንሽ ስለ ዘለዓለማዊ ተዋህዶ ልጨምር፡፡
  አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ በመባል በዋሕድና መለኮት ራሳቸውን ከገለጹት ሦስት ህላዌያት (አካላት) አንዱ ‹‹ቃል›› (ወልድ) ትስብእትን በመወሐድ አንድ ህላዌ' አንድ ክርስቶስ ' አንድ ዐማኑኤል ኾኖአልና በዚሁ በአንዱ ህላዌ አምላክም ሰውም ይባላል፡፡ በዚሁ በአንዱ ህላዌ ግብረ መለኮትንም ግብረ ትስብዕትንም ፈጽሞአል፡፡ ይህንን ውሕደቱን ቅዱስ ቄርሎስ በኮሬብ ለሙሴ በታየው ቁጥቀEጦና እሳት መስሎታል፡፡ በኮሬብ የታየው የቁጥቀEጦና የእሳት ውሕደት የመለኮትንና የትስብእትን ተዋሕዶ ያመለክታል፡፡ በውሕደቱ ታሪክ የቁጥቀEጦው አካልና ባሕርይ ሳይጣፉ እንዳሉ ነበሩ፡፡ እንደዚሁም የእሳቱ አካልና ባሕርይ ሳይጣፉ እንዳሉ ኾነው ታይተዋል፡፡ ያልተጣፉ አካላትና ባሕርያት በተገኙበት ተዋሕዶ ሁለቱም በተዓቅቦ ነበሩ፡፡ በተጨማሪም በሃ.አ. ዘቄርሎስ እንደሚያስረዳው ብረት በእሳት ውስጥ ሲጨመር የእሳቱን ሙቀት ይወስድና የብረትና የእሳት ውሕደት ይፈጠራል፡፡ የትኛውም ሌላውን ወደ መኾን አይለወጥም፡፡ የጋለውም ብረት በመዶሻ ሲመታ ከተወሐደው እሳት ጋር በአንድነት ይመታል፡፡ ነገር ግን የሚጎዳው ብረቱ እንጂ ከብረቱ ጋር አብሮ የተመታው እሳት ከቶ አይጎዳም፡፡ ከትስብዕት ጋር የተወሐደው መለኮትም በትስብእቱ መከራን ተቀብላEል፡፡ ነገር ግን መለኮቱ በመከራው አልተጎዳም፡፡ ይህም ምሳሌ የእሳቱና የብረቱ አካልና ባሕርይ ያለ መጠፋፋት በተዓቅቦ መወሐዳቸውን ያስረዳል፡፡

  ኃጢያት ሁለት ታላላቅ ውጤቶች አሉት፡፡ አንደኛው ሞት ሲሆን ሁለተኛው ብቸኝነት ነው፡፡ በብሉይ ዘመን የሕዝቡን ኃጢአት እንዲሸከሙ የተመረጡት ፍየሎች የኃጢአት ውጤት የሆነውን ሞትና ብቸኝነት እንዲቀበሉ ይፈረድባቸው ነበር፡፡ ኃጢአት ከእግዚአብሔርና ከጸጋው ይለያል፡፡ ያ ፍየል ኃጢአት የሚያስከትለውን የመጣልና የብቸኝነት በረሃ ስለ ሕዝቡ ሊቀበል ወደ ምድረ በዳ ይለቀቃል፡፡ አይሞትም ግን ተቅበዝባዥ ነው፡፡ አይጠፋም ግን ብቸኛ ነው፡፡ ሊቀ ካህኑ የሕዝቡን ኃጢአት በመናዘዝ በራሱ ላይ ያሸክመዋል፡፡ ፍየሉም ንጹሕ ሳለ ስለ ሕዝቡ በደለኛ ይሆናል፡፡ በደለኛ ከሆነ በደል ወደሚያስከትለው የተራቆተ ዓለም ይወሰዳል፡፡ እንዳይመለስ ያባርሩታል፡፡ ጭው ባለ በረሃ ይባዝናል፡፡ መቅበዝበዝ ከሰው ተለይቶ በተፈረደ ሕሊና መኖር ዕጣው ይሆናል፡፡ አሳዛኝ እንስሳ! ያለ ኃጢአቱ የሚደክም ምትክ! በዚያ በማስተሰሪያ ቀን ይቀርቡ የነበሩት ሁለት መስዋዕቶች ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚያሳዩ ቀስቶች ነበሩ፡፡ እርሱም በመስቀል ላይ የሕዝቡን ኃጢአት ተሸክሞ ሞትንና ብቸኝነትን (መተውን) ተቀብላEል፡፡ (ዘሌ.16'ዕብ.10፡1-4)
  ኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበለው መከራ በሥጋው'በነፍሱና በመንፈሱ ነው፡፡ ሁለመናው ስለ እኛ ታማEል፡፡ በሥጋው ግርፋት'ችንካር'የእሾህ አክሊል'በጦር መወጋት' ሞት ደርሶበታል፡፡ በነፍሱ ወዳጆች ከድተውታል' ጌታ ሲሆን በባሪያ ዋጋ ተሽጣEል' ፍርድ ተዛብቶበታል ስድብና ውርደት ተቀብላEል፡፡ በመንፈሱ የደረሰበት መከራ ግን በእግዚአብሔር መተው ነበር፡፡ ማቴዎስ ይህን ሲገልጥ፡- ‹‹ ከስድስት ሰዓትም ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በምድር ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ፡፡ በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስ፡- ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ ብሎ በታላቅ ድምጽ ጮኸ፡፡ ይህም፡- አምላኬ አምላኬ ስለምን ተውኸኝ ማለት ነው፡፡ ልብን የሚሰነጥቅ ብርቱ ጩኸት ነው፡፡ ስድብን የፍርድ መዛባትን የእሾህ አክሊልን በተቀበለ ጊዜ አልጮኸም፡፡ አሁን ግን ጮኸ፡፡ የሕዝቡን ኃጢአት ተሸክሞ ወደ ብቸኝነት በረሃ የተለቀቀ ሕያው ፍየል ሆናEልና፡፡
  የኃጢአት ዋጋ የተከፈለው በሥጋው ወይም በነፍሱ በተቀበለው መከራ አይደለም፡፡ የኃጢአት ዋጋ የተከፈለው በመንፈሱ በደረሰበት ሕማም ነው፡፡ የመንፈስ ሕማም ከእግዚአብሔር መለየት ነው፡፡ አንድ ኃጢአተኛ ኃጢአት ሲሠራ እግዚአብሔር ይተወዋል፡፡ የብቸኝነት ሥቃይም ይደርስበታል፡፡ ክርስቶስም የሕዝቡን ኃጢአት የተሸከመ ቅዱስ በግ ነበርና (ዮሐ1፡29) ስለ ኃጢአተኞች በብቸኝነትና በመተው በረሃ ተንከራተተ፡፡ እግዚአብሔር የሰውን ዘር ለማዳን ቆርጣEልና በሚወደው ልጁ ጨከነ፡፡ ልጁን ሊተው' በብቸኝነት በረሃ እንዲንከራተት ፈቀደ፡፡ እስከ መቼ; የኃጢአት ዋጋ እስኪከፈል፡፡ ጳውሎስ ‹‹ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለሁላችን አሳልፎ የሰጠው…›› (ሮሜ 8፡32) ይላል፡፡

  ReplyDelete
 26. ፍቅረ ማርያምMarch 8, 2012 at 10:45 AM

  የተጻፈውን ሳነበው እራሴን ማመን አቃተኝ ፤ ሰዎች ምኑን ያህል ዕውቀት ደብቀውታል ፣ ምን የሚያህለውን ጥበብስ ለሰዎች አሸክሟቸዋል ፡፡ የእግዚአብሔር ችሎታው ፣ ፈቃዱና ችሮታው ሁሉ ድንቅ ፣ ድንቅ ፣ ድንቅ ነው ፡፡

  ብርሃነ አምላክ አሁንም የበለጠውን ያድልህ
  እመ ብርሃንም በመከራህ ሁሉ ትታደግህ
  ቃለ ህይወትን ያሰማልኝ

  አንድ ነገር ብቻ ላስጠንቅቅህ ፡-
  እንዲህ ዓይነቱን ዕውቀት ተሸክመህ ፣ ለዕውራኖቹ ሳታስተላልፈው ብታልፍ ከአምላክ ዘንድ ትጠየቅበታለህ ፤ ሰዎችን ከጥፋት ለመመለስ ማስተማር ስትችል ፣ አንድም ሳትሰራ ብትቀር እኔም እንኳን ዕድሉን ካገኘሁ አቤቱታ አቀርብብሃለሁ ፣ ያወቅከው ልታስተምርበት እንጅ ፣ ራስክን ሸሽገህ ፣ በግልህ ልትጸድቅበት አይደለም ፡፡ ራስክን ፈትሸው የሚለው ያደራ ቃሌ ነው ፡፡

  እኔ እስከ ዛሬ በቁጭትና በመገፋፋት ብቻ ያለዕውቀትና ጥበቤ ፣ በከበሮው ምትክ ታምቡር ይዤ ወደ አደባባይ ወጣሁ ፤ ባደረግሁት አልጸጸትም ፤ ቢያንስ አንዱ ዓላማዬ ጥበበኞቹን ማስቆጣትና ማስወጣት ስለነበረ ይኸው እግዚአብሔር ይመስገን ፣ በደከምኩበትና ተስፋ በቆረጥኩበት ሰዓት ችቦው የበራልኝ መስሎኛል ፡፡ በተረፈ የምትጽፍበትን ድኀረ ገጽ ባውቅ እጅግ ደስ ይለኛል ፡፡

  "የኃጢአት ዋጋ የተከፈለው በሥጋው ወይም በነፍሱ በተቀበለው መከራ አይደለም፡፡ የኃጢአት ዋጋ የተከፈለው በመንፈሱ በደረሰበት ሕማም ነው፡፡ የመንፈስ ሕማም ከእግዚአብሔር መለየት ነው፡፡ ይኸኛውን ጨመር አድርገህ ብታብራራልኝ በማለት መልሼ ጽፌዋለሁ ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ያነበብኩት ገለጻ ስለሆነብኝ ትንሽ ግር ስላለኝ ነው ፡፡

  የቀድሞው ሠይፈ ገብርኤል የቅርብ ጊዜው አኖኒመስና የአሁኑ ፍቅረ ማርያም ነኝ
  እግዚአብሔር ይስጥህ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሰው ሥጋና ደማዊት ነፍስ፣ እንደዚሁም ሕያዊት ለባዊትና ነባቢት የምትባለው ነፍስ ወይም መንፈስ ያሉት ፍጡር ነው፡፡ በሥጋና በደማዊት ነፍሱ ሰው ከእንስሳት ጋር ይመሳሰላል ቢባል ስለሚርበው፣ ስለሚጠማው ስለሚበርደው ስለሚዋለድ ወዘተ…. እንደዚሁም የሥጋው የእንቅስቃሴ ኃይል በደሙ ብቻ ሆኖ የደሙ እንቅስቃሴ ሲያቀEርጥ ሞተ ስለሚባል ነው፡፡ ነገር ግን በሰው ዘንድ ከዚህ በላይ የሆነች በእንስሳት ዘንድ የሌለ ባሕርይ ያላት ሕያዊት ለባዊትና ነባቢት ነፍስ (መንፈስ) አለች፡፡ በእርሳE ለሰው ዘለዓለማዊ ሕያውነት ተሰጥቶታል፡፡
   ሰው በበደለ ጊዜ በእንስሳዊ ባሕርዩ (በደማዊት ነፍሱ) ብቻ አልበደለም፡፡ ከተከለከለው ዛፍ ለመብላት የወሰነው ስለ ተራበ አልነበረም፡፡ እንደ አምላክ ለመሆን ከማሰብ የተነሳ ነበረ እንጂ፡፡ እንደ አምላክ ለመሆን ፍላጎት ከእንስሳዊ ባህርይ አይነሳም፣ ከሕያዊት፣ ለባዊትና ነባቢት ነፍስ (መንፈስ) ነው፡፡ ስለሆነም በደማዊት ነፍስና ሥጋ መሣሪያነት የሰው መንፈስ ውሳኔውን ተግባራዊ በማድረግ በድላEል፡፡
   እግዚአብሔር ሲናገር ‹‹ በበላህ ቀን ትሞታለህ›› ብሎ በሳለፈው ውሳኔ መሰረት አዳምና ሔዋን ከተከለከለው ዛፍ በበሉበት ቀን ወዲያው ሞቱ፡፡ ሞቱ ሲባልም መንፈሳዊ ሞትን መሞት፣ ከኃጢአት ጋር ህብረት ከሌለው አምላክ ግንኙነትን ማቀEረጥና መለየት ነው፡፡ የሕይወታቸው ምንጭ ከሆነው ቅዱስ እግዚአብሔር መለየት መንፈሳዊ ሞትን መሞት ነውና፡፡
   ሰው በሁለንተናው የሰራውን የኀጢአት እዳ ለመክፈልና የሰውን ሁለንተና ነጻ ለማውጣት ቃለ እግዚአብሔር ወልድ ከቅድስት ድንግል የነሳው የሰውን ሁለንተና ማለት ሥጋን፣ ደማዊት ነፍስንና፣ ሕያዊት ነፍስን (መንፈስን) ነው፡፡ ‹‹በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ….የአብርሃምን ዘር ይዞአል፣ …..በነገር ሁሉ ወንድሞተቹን ሊመስል ተገባው›› (ዕብ 2፡14-18) የሚለው ይህን ሁሉ አጠቃሎ ይገልጻል፡፡ ‹‹ሰው ሆነ›› ሲባልም ለሰው ሁለንተና ቤዛ ሆኖ ለመስጥ ስለሆነ ሙሉ (ፍጹም) ሰው መሆኑ ግድ ነበረ፡፡
   ስለሆነም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደማንኛውም ሰው ተርባል፣ ተጠምተል፣ ደክማል፣ አዝናል፣ ታማል፣ በፈቃዱም ስለእኛ ኃጢያትን በተሸከመ ጊዜም በመንፈሱ ኃጢአት የሚያስከትለውን ከእግዚአብሔር መለየት ደርሶበታል፡፡ ስለ ኃጢአት የተከፈለው ዋጋም መራራ መሆኑን ሊገልጥ ‹‹አምላኬ አምላኬ›› ሲል በታላቅ ድምጽ ጮኸ፡፡

   Delete
  2. ፍቅረ ማርያምMarch 12, 2012 at 9:23 AM

   አክብረህ ጥያቄዬን ስለመለስክልኝ እግዚአብሔር ለክብር ያብቃህ ፡፡ ድንቅ ግንዛቤ ፣ ድንቅ ዕውቀት ነው ፡፡ አሁን ስለአባባሉ በአግባቡ ተረድቼአለሁ ፤
   ከአለፉት ገለጻዎቼ የጐደለና የምታርመኝ ጉዳይ ካለ ርዕስ ሰጥተህ ብትጽፍ እጅግ ደስ እሰኝበታለሁ ፤ ለወደፊቱም እማርበታለሁ ፤ ለሌሎች ወገኖቼም በየአጋጣሚው አስተላልፈዋለሁ ፡፡ ሶስት ስም የመጥቀሴ ጉዳይም ከተከራከርኩባቸው ወይም ግንዛቤዬን ካስተላለፍኩባቸው ነጥቦች ስህተት የመሰለህን ቃኝተህ ብታርመኝ በማለት ነው እንጅ ፣ ዝናን ለማትረፍ ወይም ሰዎች እንደተጓዙበት በተሣሣተ አመለካከት እንዲተረጉሙት አልነበረም ፡፡ እስከ አሁን ሃይማኖት ነክ ሆነው ብዙ ያከራከሩን ስለ ታቦት ፣ ስለ ጾም በሥርዓት መደንገግ እና ሌሎችም ብዙ አሉ ፤ በሙሉ ዝርዝራቸውን ስላልያዝኩ ሁሉን መደርደር አልችልም ፡፡ ጊዜ ካለህ ወደ ኋላ ያለፍናቸውን ርዕሶች እርማት የሚገባቸውን ብትዳስስና ግንዛቤህን ብትጽፍ በጣም ደስ ይለኛል ፡፡

   ስለአደረግህልን ሁሉ እግዚአብሔር ይስጥልኝ

   Delete
 27. ሠይፈ ገብርኤል/አኖኒመስ/ፍቅረ ማርያም.....

  ምነው እንደ ሌባ እና ወንበዴ ስም መለዋወጥ አስፈለገ? እውነትን በፍቅር የሚናገሩና የሚኖሩት አይፈሩምና ይህ ዓይነቱ አካሄድ ለእውነተኛ ክርስቲያን አያዋጣምና ቢያስቡበት?? እዚህ ላይ ደግሞ እንደ እንጂ ያልኩት ሌላ አይደለምና ያበሻው ወኔ ተቀስቅሶዎበት ወደ ስህተት እንዳያመሩ በቅድሚያ አሳስባለሁ::

  ለሁሉም ከእንደዚህ ያለው የስም መለዋወጥና ፍርሃት ይልቅ ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ(ከክፉ ሥራና ውሸት በስተቀር በጎ የሆነውን ብቻ ለመድረግ)በማለት መንፈሳዊ ፉከራን ይፎክሩ (ያበሻውን ቅም ቅም አለኝ የሰው ጠመንጃ...ለመቀማት ዓይነት ፉከራ ሳይሆን እስቲ ፊልጵሲዩስ (4:8-9) በመንፈስ በመሆን ያሰላስሉትና በሕይወትዎ ይተርጉሙት:: 'ልጆችሽ ከእግዚአብሔር የተማሩ ይሆናሉ' ተብሎ እነደተጻፈው ሁላችንም ያባቶችን ወኔ ትተን በዚህ መልኩ ከመንፈስ ቅዱስ ብቻ ብንማር ለአገራችን/ለሕዝባችንና ለቤተ ክርስቲያናችን መልካም ነገር አብረን ሆነን በጋራ በመሥራት በጎ የጽድቅ ተጽእኖ ማምጣት ይቻለን ነበር:: እግዚአብሔር በቃሉና በመንፈሱ ይርዳን:: አሜን::

  የጌታ ሰላም በነገር ሁሉ ይብዛልዎት!!!

  አክባሪ እህትዎ

  ሰላም ነኝ

  ReplyDelete
 28. ፍቅረ ማርያምMarch 11, 2012 at 8:26 AM

  ይድረስ ለወለተ ሉተር
  በመጀመሪያ ይኸን እንጉርጉሮ ያስጀመረሽ በክርስቲያን ወንድምሽ መደነቅ ቀንተሽ ነው ፡፡ ትምህርቱም ኦርቶዶክሳዊና የተዋህዶ ስለሆነብሽ ነው ፡፡ ሠይፈ ገብርኤል የሚለውን ስሜን የቀየርኩት አንቺው ለስምና ለዝና ፣ ሰዎች እንዲያደንቁህ ነው የምትጽፈው ብለሽ ስለወቀስሽኝ ነው ፡፡ በአኖኒመስ ስጠቀም ደግሞ ፍቅረ ማርያም የሚለውን ስምም የለጠፍሽልኝ አንቺው ታማሚዋ እህቴ ነሽ ፡፡ አንድም በራሴ የፈጠርኩት ስም ፣ ራሴንም ለመሸሸግ የፈቀድኩበት ነገርም የለም ፡፡ አንቺ እህቴ ትድኝ እንደሁ ፣ ትታደሽ ቢሆን ብዬ በተደሰትሽበት ሁሉ ሞከርኩሽ ፡፡ ለማንኛውም ይህንን አንቢው ፡፡ ይናገራል ፤ የስም ማጭበርበሩ ንስሓ ነውና ይመሰክራል ፡፡

  ሠይፈ ገብርኤል ብዬ ራሴን ሰይሜ
  ጥንትም በማደጌ ታቦት ተሳልሜ
  ሲወቅሱና ሲያሙን ፣ ባገኛቸው ድንገት
  ገባሁ ለማስረዳት በቀና አንደበት
  እግዜርን የፈራ ፣ ለጌታም ያደረ
  ወገን ያለ መስሎኝ ያልተደፋፈረ
  አልኳቸው በድፍረት ፣ ታቦትን አክብሩ ፣ ወገን አትውቀሱ
  ከሄዳችሁበት ፣ ስህተት ተመለሱ

  የመጣፍ ቅዱስ ጥቅስ ፣ እየጠቃቀሱ
  ቀርቷል ጠፍቷል አሉኝ የጥንት ቅዱሱ
  በቤተክሲያናችን የታቦታት ጥቅም
  ለመፈተት እንደሁ ደግሜ ባስረዳም
  ከከሃዲዎቹ አንድ አልተቀበለም

  ክርክሩ ሲግም ፣ የእሰጥ አገባው
  ለዝናዬ አረጉት ሁሉን የምጽፈው
  ሙገሳና አድናቆት ለእኔስ ምኔም አይደል
  አኖኒመስ በሉኝ መስማማት ብንችል
  ሰላምም ካገኘን ልሁን ስም የለሽ
  ክህደትን አጥፉ ፣ ለኔም በሉኝ እሽ

  የመከራከሪያው ርዕሱ ሲቀየር
  ፍቅረ ማርያም አሉኝ ፣ መስሏቸው የማፍር
  ክብርና ሞገሴን ለኔስ ሽልማቴን
  ላምላክ ከመላላክ ታቀፍኩኝ እናቴን
  ታሪኩ ይኸ ነው የስም መዘዋወር
  ሰላም ለማግኘት ስል ፣ ቢጠፋ ክርክር
  ደስ ይበላችሁ ፣ ስም የለህም በሉኝ ፣ መለያየት ይቅር
  ወንጌልን እንማር ፣ በእምነት እንበርታ ፣ አንድነት እንፍጠር

  እናም ወለተ ሉተር ስህተቱ ሁሉ ያለው ከአንቺ ቤት ነው ፤ መንፈስሽ ከመንፈሴ ሁሌም ትግል ላይ ነው ፡፡አንቺው ራስሽ ፍቅረ ማርያም ብለሽኝ ስታበቂ ፣ በሁለተኛው ቀን መለስ አድርገሽ ፣ አደራ በግል የተቀበልሽ ይመስል ፣ በአምላክ እናት ብለሽ ቲያትር ለመስራት ሞከርሽ ፡፡ እኔ ሁሉን የማደርገው እግዚአብሔር ይመስገን ከልቦናዬ ሆኝ ነው ፡፡ እምነቴም ከልብ ነው ፡፡ አንቺ እንደምትፎክሪበት የቃላት አይደለም ፡፡ ክርስቲያን ፍቅርን አንድነትን ይሰብካል ፣ ያስተምራል ፣ ለማያውቁት ብርሃንን ፣ ዕውቀትን ይሰጣል ፡፡ ያንቺ ጽሁፍ ግን ወቀሳን ፣ ክስን ፣ አቤቱታን ፣ ጥላቻን ፣ ንቀትን ፣ ውግዘትን ስድብን ብቻ ነው እያስተላለፈልኝ ያለው ፡፡ እስቲ እንድንማርበት አንድ ርዕስ አብራርተሽ ለማናውቀው ግለሰቦች ጽፈሽ እንደሁ ወዲህ በይና ይታይልሽ ፡፡ እኔ አሁንም የምትሄጅበትን መንገድ ለመጠቆም ነው እንጅ በትምክህት ተወጥሬ አይደለም ፡፡ የሚያስተምሩኝንማ እንዴት እንደማደንቅ ከምስክርነቴ አይተሻል ፡፡ ለሚወቅሱና ለሚያወግዙ ግን ፣ በተዋህዶ እምነቴ የሚሸከም ትከሻ የለኝም ፤ አግባብ ያለው መጽሐፍ ቅዱሳዊ መልስ ዛሬም ፣ ወደፊትም በህይወት እስካለሁ ድረስ እሰጣለሁ ፡፡ ምክንያቱም ሃይማኖታችን ከሌሎቹ ሁሉ እውነትንና ሃቅን የተመረኮዘ ፣ መጽሐፍ ቅዱስን በተግባር ጭምር እያሳየ የመጣና የሚሄድ ስለሆነ ነው ፡፡ አንቺ የምትሰክሪበት ግን በሰዎች ምርምርና ፣ ብልሃት የመጣ ፣ አእምሮአቸው የፈቀደውን እውነት ያሉበት ፣ አንድ ሺህ ዓመት እንኳን የማይቆጠርለት ዘመናዊ እምነት ነው ፡፡

  እግዚአብሔር ምህረቱን ያውርድ

  ReplyDelete
 29. ፍቅረ ማርያምMarch 11, 2012 at 9:03 AM

  የኤግዚቢት ማስረጃዎቼ፡-
  የውይይቱ ርዕስ “እግዚአብሔር ለሙሴ አንድ የቃል ኪዳን ታቦት ከሰጠው አሁን በየገዳማቱና በየአድባራቱ ያሉ በርካታ ታቦታት ከየት መጡ?” ለመምህር ምህረተአብ አሰፋ “አልተሳሳትንም” የቪሲዲ ስብከት በዲያቆን አግዛቸው ተፈራ “አልተሳሳትንምን?” ተብሎ ምላሽ ከተሰጠበት መጽሐፍ ገጽ 53 ላይ የተወሰደ - ስለ ታቦት መባዛት

  በተጠቀሰው ርዕስ ውስጥ ከሰጠሽው አስተያየት መሃል እንዲህ የሚል ይነበባል
  ….ከዚህ በተረፈ ወገኖቼ ማንኛችንም በተናገርነው /በጻፍነው ጉዳይ ላይ የሚጠይቅ ጻድቅ ጌታ መኖሩን ባንዘነጋ መልካም ይመስለኛል እንዲያው እከሌ እንዲህ አለ ለመባልና ከበሬታን ከሰዎች እሱማ / እሷማ ለሃይማኖቱ /ቷ በሚል ምድራዊ ብድራትን / መደነቅን ለማግኘት ባይሆንና እውነትን / ቃሉን ብቻ በፍቅር እየተነጋገርን ብንማማር ሁላችንም እጅግ እንጠቀማለን:: እባካችሁ ለመማር ጭምር እንጂ ለማስተማር ብቻ አንጻፍ???? አንደበት ከስድብ ሳይጠራ እንዴት አድርጌ ነው የምማረው???

  ጥንቆላንና አስማትን አስመልክቶ ስለ ወንድማችሁ ሙሴ ስትከራከሪ የሚከተለውን ስምም ሰጥተሽኛል ፡፡
  ለተከበርከው ወገኔ ፍቀረማርያም!!!
  እንዳንተ ደካማ ሥጋን የለበስኩትን ሴት ከምጠይቅ ይልቅ ሁሉን ቻይ የሆነውና ጸሎትን ሰምቶ የሚመልሰውን ቸር አምላክ በንጹህ ልብህ ብትጠይቀው እጅግ እጅግ እጅግ የተሻለ መልስ ይሰጥሃልና ይህንኑ ብታደርግ ያዋጣሃል::

  ታድያ ስህተት የፈጸምኩት እኔ እሆን

  ReplyDelete