Sunday, February 26, 2012

ማህበረ ቅዱሳን በምዕራብ ኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል ተሰሚነት ማጣቱ ተገለጸ፤ በጥር ወር ብቻ 14 ጉባኤዎችን ለመሰረዝ ተገዷል - - - Read PDF

ከውጪ አገር በሚመጣ የአገልግሎት ግብዣ “እኔ ልሂድ፣ እኔ ልሂድ” በሚል የማህበሩ አገልጋዮች እርስ በርስ እየተወዛገቡ ነው

እግዚአብሔር በዘመናችን ለቤተክርስቲያናችን ያስነሳቸውን ወንጌል ሰባኪዎች “ተሐድሶ” በሚል ፍረጃው፣ እንደ አባ ፊልጶስ ያሉ አንዳንድ ሊቃነ ጳጳሳቱን ተገን በማድረግና በቀጠራቸው ወሮበሎች በአዲስ አበባ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ሁከት በማስነሳት ከዐውደ ምሕረት እንዲርቁና ከሕዝቡ ልብ እንዲወጡ ለማድረግ ከፍተኛ ትግል ሲያደርግ የቆየውና በእነርሱ እግር ራሱን ለመተካት በመውተርተር ላይ ያለው ማህበረ ቅዱሳን በምዕራብ ኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል ተሰሚነቱ እየቀነሰ መምጣቱን ከስፍራው የደረሰን ዜና አመለከተ፡፡

ለተሰሚነቱ መቀነስ ምክንያቱ ማህበሩ የሚያዘጋጃቸው ጉባኤዎች የሚቀርበው ስብከትም ሆነ ዝማሬዎች የሰውን ትኩረት መሳብ የማይችሉ መሆናቸው ሲሆን አገልጋይ በማጣትም ጭምር መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡ በነዚህና በሌሎቹም ምክንያቶች ከህዝበ ክርስቲያኑ በኩል ተባባሪነት እየቀነሰ መምጣቱን ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡ ጉባኤ በሚያዘጋጅበት ጊዜ የሚወጣለት ሰው እጅግ አነስተኛ ሲሆን፣ በጥር ወር 2004 ዓ.ም ብቻ እንኳን 14 ጉባኤዎች የታጠፉ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል መቱ ላይ 2፣ ወለጋ ውስጥ ደግሞ 3 የታጠፉትን ጉባኤዎቹ መጥቀስ ይቻላል ብለዋል ምንጮቻችን፡፡

ለአገር ውስጥ አገልግሎት ሲሆን የአገልጋይ እጥረት አለብኝ የሚለው ማህበሩ በአሜሪካና በአውሮፓ የሚገኙ ደጋፊዎቹና አባላቱ በሚያዘጋጇቸው ጉባኤዎች ላይ ለማገልገል ግን “እኔ ካልሄድኩ፣ እኔ ካልሄድኩ” እያሉ አገልጋዮቹ እርስ በርሳቸው እየተቀናቀኑ መሆናቸውን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ይናገራሉ፡፡ በዚህም የማህበሩ አገልጋዮች ለግል ጥቅማቸውና ከማህበሩ ክበብ ለማይወጣ ዝናቸው የቆሙ እንጂ ለቤተክርስቲያን ግድ የሌላቸው መሆናቸውን አስመስክረዋል ሲሉ እነዚሁ ምንጮች አክለው ይናገራሉ፡፡

በአጠቃላይ ማህበረ ቅዱሳን የህዝቡን መንፈሳዊ ሕይወት እያነቃቁና የእግዚአብሔር ቃል ጥማቱን እያረኩ ያሉትን አገልጋዮች ስም በማጥፋት በየአቅጣጫው ከህዝቡ ልብ እንዲወጡ ለማድረግ በመሞከርና በእነርሱ እግር ራሱን ለመተካት የጀመረው መፍጨርጨር ብዙም እንዳላዋጣው የሚናገሩት ምንጮቻችን፣ ጉዳዩ በዚሁ ከቀጠለ በአንዳንድ ቦታዎች ህዝቡ በትምህርት ወንጌል ረሃብ ሊሰቃይ እንደሚችል እየተናገሩ ነው፡፡ ምክንያቱም ማህበሩ ጉባኤ አዘጋጀሁ ቢልም እንደ ጸሐፍት ፈሪሳውያን ወግና ስርአትን ከመጠረቅ ውጪ የሰውን የውስጥ ጥያቄ ሊመልስና ሰውን ከድካሙ ሊያሳርፍ የሚችለውን ትምህርተ ወንጌል ሲያስተምሩ እንዳልታየ አገር ያወቀው ጸሀይ የሞቀው ሀቅ ነው፡፡ በዚህ መንገድ ህዝቡን መያዝና ከቤተክርስቲያኑ ወደሌላ እንዳይፈልስ ማድረግ ስለማይቻል ማህበረ ቅዱሳን በምቀኝነት ተነሳስቶ እኔ ካልያዝኩት ከሚለው የስብከተ ወንጌል አገልግሎት እጁን መሰብሰብ አለበት የሚሉ በርካቶች ናቸው፡፡ “ተሀድሶ” ሲል የፈረጃቸው የቤተክርስቲያን ልጆች ገጠር ድረስ እየገቡ በስብከተ ወንጌል፣ ልብን በሚነኩና ለአምልኮተ እግዚአብሔር በሚያነሳሱ ዝማሬዎቻቸው ወደ ቤተክርስቲያን የሰበሰቡትን ትውልድ፣ እህል ውሃ በማይል ጣእመ ቢስ አገልግሎቱ እየበተነ መሆኑ ከየአቅጣጫው እየተደመጠ ነው፡፡ ማህበሩ በወንጌል ካልታደሰና ይህንኑ ፈሪሳዊ መንገዱን ካልለወጠ ለራሱም ለቤተክርስቲያናችንም ጠንቅ መሆኑ እንደሚቀጥል ጥርጥር የለውም፡፡
        

12 comments:

 1. ሃይማኖትና ቤተ ክርስቲያንን ሳትነኩ እነዚህንስ የማይረቡ ነገሮች ሌላም ሌላ በሏቸው ፡፡ እናንተ ስለ እነሱ ይህን ያህል ስትሉ አንድ ቀን እንኳን መልስ ሲሰጡ አላየሁዋቸውም ፡፡
  ሃይማኖት ሲተች ፣ ቤተ ክርስቲያንም በሆነ ባልሆነው ስሟ ሲነሳ አንድም ሰዓት ላይ አልቆሙላትም ፡፡ ምናልባት ሃሳባቸውን ሳንሱር አላደረጋችሁ እንደሁ ማለቴ ነው ፡፡
  እናም ታድያ የሚያባላችሁ የእኔ እበላ እኔ እበላ ፣ የእኔ እበልጥ እኔ እበልጥ ጉዳይ መሆኑን ቀስ በቀስ እየወጣ ሊመጣ ይመስላልና ጨምሩበት ፡፡ ይኸው ሁሉንም መድረክ እኔ ልያዘው አለ የሚለው እሮሮ ይጠቁማልና ፣ እርስ በርሳችሁስ ራቅ ብላችሁ ተባባሉ ፤ እኛም ተንፈስ እንላለን ፡፡ ሰላምም ይኖረናል ፡፡ የናንተ የግል ቅራኔ ነው ቤተ ክርስቲያንና ሃይማኖታችን ላይ እያነጣጠረ ያስቸገረን ፡፡
  በርቱ ፣ ሌላም ምክንያት ካላችሁ ቀስ በቀስ ንገሩን

  ReplyDelete
 2. 100% true. mk is purely the son of devil.

  ReplyDelete
 3. በጣም ይገርማል? እናንተ ተሃድሶ አለ ለቤተ ክርስቲያን ይጠቅማል ትላላችሁ::
  በሌላ በኩል ደግሞ ተሃድሶን የፈጠሩ ማህበሩ ነው የሚሉ እና እንደሌላችሁ የሚመሰክሩ አሉ:: 2 ተቃራኒ እውነት መቼም የለ ስለዚህ ተሃድሶ ና አስተምህሮቱ አለ ማለት ነው::
  ህይ ብሎጋችሁ ብዙ ተቃራኒ ሃሳብ /መልዕክት/ ያስተላልፋል:: አንዳንዴ ደግሞ ውሸት እንደዜና ያቀርባል:: ስለዚህም ያንባቢን የማገናዘብ ችሎታ የናቀ ይመስላል:: እንዲህ አይነት ሚዲያ የሚያዘጋጅ ሰው ቆም ብሎ የቱ ጋር የሚጋጭ ሃሳብ አቀረብኩ በሎ እራሱን ሊመረምር ይገባዋል እላለሁ::
  በውሸት መንግስተሰማያት አይወረስምና::
  እግዚአብሄር ወደትክክለኛው መንገድ ይምራችሁ::

  ReplyDelete
 4. ለመሆኑ ማኅበረ ቅዱሳን(ፈሪሳውያን)የተሰኘው ዱልዱም መሣሪያ እስከ መቼ ድረስ ሰዎችን የውስጥ ድማት ሲያደማ
  ይኖራል፤ሰዎችን በነገር ማድማት ተገቢ እንዳልሆነ ፤ራሱም ያርጋጅ አናጓጆቹም ግጥም አድርገው ያውቃሉ ይኸውም
  (ለቀደሙ ሰዎች ነፍስ አትግደል የተባለውን ሰምታችኋል እኔ ግን የተፈጥሮ ወንድሙን የሚያበሳጭና ውሳጣዊ አካሉን
  የሚያደማ በፍርድ ቀን ከፍርጃ አያመልጥም እላችኋለሁ) ማቴ ፭ ፳፩

  ReplyDelete
 5. ato yargal abgaz (koromiya)February 27, 2012 at 2:20 PM

  mahiberu bdingizgiz silale ywangel brihan ybralachewn lmayet edlu yelewim silzhim chlmaw brihan new yilal ende ato yargal ena masalochu

  ReplyDelete
 6. what is the use of this news for us to read be constructive for the churches mission for such news the world is enough to tell us about the failure.

  ReplyDelete
 7. Most of us already identified which is true and which one is false. Jesus is the only way to heaven. But we are not denying the role/place of St. Marry.

  ReplyDelete
 8. plz look forward to the people everything u and others wrote is driving us to nowhere.. i believe there is a problem but the solution is not this.. we are in 21 ch. we can talk and sort it so try to solve urs problem by discussion but don't write bad things about any one this is not our religion aim!!!

  ReplyDelete
 9. mechem behon cheru egzihabher agelgayochon yemertal bealefut zemenat yetemeretu neberu zarem mahebere kidusa ye jerba atint hono eyagelegel new edme yestew

  ReplyDelete
 10. Enante tehadeso honachehu manen tehadeso telalachu gebrachehu enanten geletse endet betelugn tamere mariamn techachu mechershachu yeh hone aydel wegen neka

  ReplyDelete
 11. Mechem approval belachehu ende matawetut awkalhu mannenetachun enawkalen. meche tekekelegna yebetekrstian abatochen sem beteru ansetachehu tawkalachu. enante yaba sereke, yebegashaw, ena mesel tehadeso sewech degafi mehonachehun asmesekerachu.

  ReplyDelete
 12. ቀደም ያስተላለፍኩላችሁ ስላልወጣ ይህ በተሻለ ያብራራሁትን እስቲ ሞክሩት
  1. ለአስተያየት ሰጭ መልሶቼ ፡- የግለሰቡ መልዕክት ስለአነሳሳኝ ነው እንጅ ፣ እኔ ስለተሰጠው አስተያየት የተዛባ አመለካከት እንዲኖረኝ ፈልጌ አይደለም ፡፡ ነገር ግን የናንተ አገልጋይ የነበረው ያስተላለፈውን ታሪክ ለማመን የሚያስችለኝ በስሌት /በሎጂክ/ ምንም የጭብጥ ነገር አላገኘሁበትም ፤ እንዲሁም አካባቢውን ስለኖርኩበትና ስለማውቀው ከነባራዊው ሁኔታም አንጻርም ፣ ለማረጋገጥ ብሞክር እንኳን መንገድ አጣሁለት ፡፡ በአጭሩ ብዙ ታሪክና ማጣፈጫ ሳይገባለት ቀደም ደብተራና ጠንቋይ ነበርኩ ማለት ይችል ነበር ፤ አሁን ደግሞ እግዚአብሔር ስለፈቀደና ድክመቴ ስለገባኝ ከችግሬ ተፈወስኩ ፤ የኢየሱስ ተከታይም ሆኛለሁና ጌታ ይመስገን ቢለን ተደራቢ ብዙ ደባደቦ መልዕክት ስለሌለው በቀላሉ ይገባን ነበር ፡፡ ከዚህ ውጭ ለማሳመን በማለት የሆኑ ያልሆኑ ቅባቶችና ወቀሳዎች ስለታከሉበት ሆዴን ጐረባበጡኝ ፡፡ ያልተማረውን ወገን የሚያጭበረብሩ እንደ እርሱ ዓይነት የሰይጣን መልዕክተኞች ይኖራሉ ፤ እግዚአብሔር ሲያዘጋጃቸው ደግሞ በምክንያት ነጻ ይወጣሉ ፡፡

  አሁን ባለቤትና ፊትአውራሪ ለመሆን ብትፍጨረጨሩም ፣ የሙሴ መለወጥ የመጣው በናንተ ጥረት ለመሆኑ የትም ቦታ አልተገለጸም ፤ ከዜና ያለፈ አስተዋጽዖ የላችሁም ፡፡ እግዚአብሔር ስለፈቀደለት ብቻ ኘሮቴስታንት በሆነ ወንድም ምክንያት ከዛ የክፋት መንገድ መገላገል ችሏል ፡፡ እዚህ ከመድረሱ በፊት ተሰራ የተባለው መግለጫ ቲያትር ግን ላምነው የምችል ቅንብር አይደለም ፡፡ ስለሆነ ነገር በማለም የተፈጠረ ታሪክ ይመስለኛል ፤ ስለዚህም አብጠርጥሬ ፣ ጥርጣሬ ሊፈጥሩ የሚችሉትን ነጥቦች አውጥቼአለሁ ፡፡ የተነካ ካለ ከሙሴ በላይ መጐዳት ይችላል ፡፡

  ለእኔ ታሪኩ አሁንም የሆነ ዓላማና ግብ ያለው ድራማ ነው ፡፡ በቀላሉ የሚታዩ ሁለት ነገሮችን ለመግለጽ - አንድም ተሃድሶ ጴንጤ አይደለም የሚለውን ትምህርትና መልዕክት በማራገብ ፣ እናንት ነን ለምትሉት ክርስቲያኖች የሹምባሽ ሹመት ለማስገኘት ፡፡ ሁለትም ተሃድሶ ማለት እንደ እነዚህ ዓይነት ሰዎችን ለማስወገድ የሚታገል /ህቡዕና ግልጥ/ ክርስቲያናዊ ድርጅት ነው እንዲባልም ሊሆን ይችላል ፡፡ ነገር ግን በሙሴ መለወጥ ላይ እናንተ የጨመራችሁት ቅንጣት ነገር የላችሁም ፡፡ ከፊት የሞተው ተዋጊ እያለ ፣ ከኋላ እንደሚፎክረው የጦር ሜዳ አጫፋሪ ሥራ ሆኖ ነው የማየው ፡፡ ሙሴን ለዋጭ ሌላ አካል ቁጭ ብሎ ሳለ ፣ አሁን እንደ ዋና ሆናችሁ ወሬ የምታቀናብሩና የምትከራከሩ ፣ ራሳችሁን የቤተ ክርስቲያን ሞግዚት አድርጋችሁ የምትነግሩን አስመሳዮች ፣ ነገር ግን የምታሰድቧትና የምትወቅሷት ጠላቶቿ ናችሁ፡፡

  2. እርግማንና ጸሎት የተደባለቁት ስለሁለት ነገሮች ነው ፡፡ ማንበብ ስለሚቻል በድጋሚ ይቃኝ እንጅ እኔም እንደ አንዳንዶቹ ዞሮብኝ ሳላስተውል እንደ መጣልኝ ያስቀመጥኩት አይደለም ፡፡
  - እርግማኑ የመጣው በአገራችን ገዳማት በጾምና በጸሎት ተንበርክከው የሚኖሩትን አባቶች ለመውቀስ ምላሱን ስላንቀሳቀሰ ነው ፡፡ እኒህ ያበቁ ሰዎች እንዴት እንደሚኖሩ ለመረዳት የግድ ገዳም መግባት አያስፈልግም ፡፡ በኢንተርኔት መዳሰስ ይቻላል ፡፡ ለዛ ወግ የታደለ ዘመድ ያለው ደግሞ ስለኑሮአቸው በመጠየቅ መማር ይቻላል ፡፡ ደብተራ ሙሴ እንዳለው እንደ ተስካር ፣ ድግስ የሚደገስበት ሥፍራ ግን አይደለም ፡፡ አምልኮአቸውም ቢሆን ጥርት ያለ ወደ አንድ አምላክ ነው እንጅ ተራራና ወንዝ ፣ ዛፍና ሸንተረር አይደለም ፡፡ እንደዚህ ያለውን ልቅ ያ ብዙ የሚያበሳጫችሁ ሰው ቢኖር ኖሮ እርግማን ብቻ ሳይሆን ፣ ዛሬም ፈረስ ይነዳበት ነበር ፡፡ የተፈጸመው እጅግ ክፉ ብልግና ነው ፤ ቤተ ክርስቲያንን መጽረፍ ፤ የደከሙ አባቶችን ያልሆነ የአምልኮ ስም መስጠት እጅግ ከሰይጣን ነው ፡፡ ለቀቀኝ ቢልም ገና አልወጣለትም ፣ ጠበል ያልሽው /አትጠራጠሪ ፊደሉን በሙሉ ካነበብሽ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል ነው/ ነገር ሳይፈውሰው አይቀርምና ወደ እዛ ተወስዶ ግድየለም ይሞከር ፡፡

  - ጸልዩ ማለት የመጣው እናንተ ወንድሞቼንና እህቶቼን ገድሎ የማዳን ዓይነት ሥራ ስለ ሠራና ጴንጤ አይደላችሁም ብሎ ምስክርነቱን ስለሰጠ ነው ፡፡ ቃሌም የሚለው እንጸልይለት አይደለም ፡፡ ትእዛዝ ነውና ስለ ሙሴ ጸልዩ ይላል ፡፡ ጸሎቱ ቢያንስ እኔን አይጨምርም ፡፡ የኔ የሚሆነው እርግማኑ ነው ፤ ምክንያቱም ባለፈ በአስማት ያደነዘዝኳትን ሴት እንደ ሙክት አስከትዬ ቤተ ክርስቲያን ወሰድኳት ፣ ዛሬ ደግሞ በገዳም ህይወታቸውን በሙሉ በጾምና በጸሎት የሚኖሩትን ፣ ዓለምን የናቁ ሰዎች ላይ እምነትና አምልኮአቸውን ጨምሮ ስለኰነነ ነው ፡፡ ግልጽ ካደረግሁ የተሰጠው አስተያየት ይታረምልኝ ፡፡

  ለኔም ሰላም ሁኑልኝ

  ReplyDelete