Wednesday, February 29, 2012

የየካቲት 16ቱ የአዶላ ወዩ ቅዱስ ሚካኤልና ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የማኅበረ ቅዱሳን የአመጽ ድራማ አርባ አባላቱን ወኅኒ በማውረድ ተጠናቀቀ - - - Read PDF

በአመጹ ሳቢያ በአለ ንግሱ ሳይከበር ተስተጓጉሏል
በጉጂ ቦረና ሀገረ ስብከት አንዳንድ የማህበረ ቅዱሳን አባላትና በግል ጥቅም የተሳሰሩ ጀሌዎቻቸው በህገ ወጥ መንገድ በያዙት የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ለመቆየት ሲሉ የቤተ ክርስቲያንን ሰላም በማደፍረስ በቀሰቀሱት አመጽ የየካቲት ኪዳነ ምህረት በኣል ሳይከበር መቅረቱንና አመጹን ያስነሱት 40 ያህል ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ከስፍራው የደረሰን ዜና አመለከተ፡፡
በእለቱ የካቲት 16/2004 ዓ.ም የጉጂ ቦረና ሀገረ ስብከት ቆሞስ አባ ወልደ ጊዮርጊስ፣ የጉጂ ቦረና ሊበን ዋና ስራ አስኪያጅ ሊቀ ትጉሀን ተሾመ ሀይለማርያም እና የአዶላ ወዩ ቅዱስ ሚካኤልና ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪና ሌሎችም የቤተክርስቲያን አገልጋዮች በህዝበ ክርስቲያኑ ታጅበው ከሌሊቱ 11 ሰዓት ስርአተ ቅዳሴ ወደ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ግቢ ሊገቡ ሲሉ፡- ከበቡሽ፣ በቀለ ቀሬሳ፣ ፋንቱ አራጋው፣ ሐይማኖት ጥላሁን፣ ምርትነሽ ቀሬሳ እና ሌሎችም ግብረ አበሮቻቸው በስልጣነ ክህነትም ሆነ በሰበካው አስተዳደር ምንም አይነት ውክልና የሌላቸው ተራ የማህበረ ቅዱሳን አባላት አትገቡም ብለው ውዝግብ ይፈጥራሉ፡፡ ሌሊቱ እየነጋ የሕዝቡም ቁጥር እየበረከተ ሲመጣ አመጹና አመጸኞቹ ገሀድ ወጡ፡፡ በዚህ ጊዜ አቶ ዘውዴ የተባለ ሰው ላለፉት የሰበካ ጉባኤ አባል ነኝ በማለት ቅኔ ማህሌቱን አስቁሞ በድምጽ ማጉ‹‹ሁከት ለመፍጠር የመጣችሁ አካለት ወደ ግቢ እንዳትገቡብን እንቢ ካላችሁ ግን በዓለ ንግሱን የማናደርግ መሆኑን እንድታውቁ›› በማለት የበኣሉ መከበርና አለመከበር በእርሱ እጅ ያለ ጉዳይ መሆኑን በትእቢት በመናገር ህዝቡን ለውዝግብ፣ ለብጥብጥና ለሁከት አነሳስቷል፡፡
ከግቢ ውጭ ላለው ምእመን ቆሞስ አባ ውልደ ጊዮርጊስ ‹‹ሕገ ወጥና ፎርጅድ ደብዳቤ ነው ይዘው የመጡት›› በማለት የማህበረ ቅዱሳን አባላት ለነዙባቸው አሉባልታ፣ ከቅዱስ ፓትርያርኩና ከጠቅላይ ቤተክህነት በሕጋዊ መንገድ ተመድበው የመጡበትን ደብዳቤና እንዲሁም የማህበሩ ቀንደኛ ደጋፊ የሆነው አቶ ሲያምር ተክለማርያም ከስራው የተባረረበትን ደብዳቤና በምትኩ ተሹመው የመጡትን ሊቀ ትጉሃን ተሾመ ሀይለማርያምንና ጊዜያዊ ጽሕፈት ቤት በአዶላ ወዮ ከተማ የተፈቀደላቸውን ማስረጃ ለህዝቡ አቅርበው ህዝቡን አረጋግተውታል፡፡
አንድ የሰበካ ጉባኤ አባል ለ3 ዓመት እና በድጋሚ ከተመረጠ ለሌላ 3 ዓመት በድምሩ ለ6 ዓመት ብቻ እንዲያገለግል በቃለ አዋዲ የተደነገገውን ህገ ቤተክርስቲያን በመጣስ የሰበካ ጉባኤ አባልነትን በርስትነት ለ32 አመታት ይዞ የቆየው አቶ ዘውዴ፣ በሌለው ስልጣን በኣሉ እንዳይከበር እንደሚያደርግ መዛቱ ሳያንስ፣ ‹‹ክርስቲያኖችን አልከለከልንም ክርስቲያኖች ግቡ ሌላ አካለት ግን በይፋ መግባት አትችሉም፡፡›› በማለቱ ከፍተኛ ብጥብጥ እንዲጀመር ምክንያት ሆኗል፡፡ መረጃው የደረሳቸውና ጸጥታና ሰላምን የማስፈን ሀላፊነትና ግዴታ ያለባቸው የመንግስት አካለትና አድማ በታኝ የወረዳው ፓሊስ መጥተው አካባቢውን ለማረጋጋት የቻሉ ሲሆን፣ የችግሩ ፈጣሪ የሆኑትን ወደ አርባ የሚደርሱ የማህበረ ቅዱሳን አባላትንም በቁጥጥር ስር አውለዋል፡፡ በነጋታውም ፍርድ ቤት ቀርበው ሁከት በማነሳሳት ተከሰው ወደ ወህኒ ወርደዋል፡፡
ለዚህ ሁሉ ችግር ዋናው ምንጭ ከጠቅላይ ቤተክህነት ተባርሮ በፍርድ ቤት በህግ የታገደውና የቤተክህነቱን ንብረትና ማህተም በማን አለብኝነት በእጁ ይዞ አላስረክብም እያለ የሚገኘው አቶ ሲያምር ተክለማርያምና ግብረ አበሩ መሪጌታ ልሳነውርቅ ሁንዴ ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች አላማቸው የቤተክርስቲያንን ጥቅም ማስጠበቅ ሣይሆን የማህበሩን አላማ ማስፈፀም በመሆኑ የጉጂ ቦረና ሀገረ ስብከትን በሁከት ሲያምሷት ከርመዋል፡፡ ማህበረ ቅዱሳን ጊዜያዊ ጥቅሙን እንጂ የቤተ ክርስቲያንን ጥቅምና ደህንነት የህዝቡን ሰላምና መረጋጋት ከግምት ውስጥ የማያስገባ ማህበር በመሆኑ በዕለቱ ሊከበር የነበረውን በዓል አስተጓጉሎታል፡፡
አቶ ሲያምር “ማቅን እንጂ ቤተክህነትን አላውቅም፤ ካለሁበትም ቦታ ቤተክህነቱ ሊያስነሳኝ አይችልም” በሚል ዕብሪተኛነት የማህበሩ አባላት የሆኑ ግብረ አበሮቹን አስተባብሮ “የቆሞስ ኣባ ወልደጊዮርጊስንና የሊቀ ትጉሀን ተሾመ ሀይለ ማርያምን ሹመት አልቀበልም፤ ጽህፈት ቤቱንም አላስረክብም፤” በማለት በአመጻ በቦታው ላይ ለመቆየት በመሞከሩ በነገሌ ቦረና ሀገረስብከት ቆሞስ አባ ወልደ ጊዮርጊስ ስራ ለመጀመር ስላልቻሉ ለጠቅላይ ቤተክህነቱ ያለውን ችግር አስረድተው በአዶላ ወዮ ከተማ ጊዜያዊ ጽህፈት ቤት ለማቋቋም ፈቃድ ጠይቀው ጊዜያዊ ጽ/ቤቱን  በአዶላ ወዩ ከተማ አቋቁመዋል፡፡ ከዚያ በኋለም የዞኑን ጽ/ቤት ለማስለቀቅ በሁከት ይወገድልኝ በፍርድ ቤት ጉዳዩን እየተከታተሉት መሆኑ ለአቶ ሲያምር በተለይም ደግሞ እሱን እንዳበደ ውሻ ንከስ የምልህን ንከስ እያለ እንደፈለገ የሚመራውን ማህበሩን እንቅልፍ ስለነሳ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ቆሞሱ ከህዝብ እንዳይገናኙ ለማድረግ በማሰባቸው ይህ ችግር መከሰቱ ታውቋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ገልብጦ ማንበብ ተቃርኖ መዘገብ ልማዱ የሆነው አንድ አድርገን ድረ ገጽ ጉዳዩን ገልብጦ በማቅርብ የራሱን ማህበር የማህበረ ቅዱሳንን አባለት ‹‹እውነተኛ ክርስቲያኖች ተያዙ፤ ወህኒ ወረዱ›› በሚል ሐሰተኛ ዘገባ ማቅረቡን በቦታው የነበሩና ጉዳዩን ከመነሻው ሲከታተሉ የነበሩ ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡
መቼም አንድ አድርገን የእውነት አገሩ የት ነው? ተብሎ ቢጠየቅ ማህበረ ቅዱሳን ጓሮ ብሎ እንደሚመልስ ጥርጥር የለውም፡፡ ማህበረ ቅዱሳን ጋ ምን እንደሚገኝ ግን ህዝቡ ጠንቅቆ አውቋል፡፡ በየቦታው እየገጠመው ያለው ቅሌትና ሽንፈት፣ እየተገለጠ ያለው ገመናና በውስጡ እየተፈጠረ ያለው ሽኩቻ ለማህበሩ ትልቅ ራስ ምታት መሆኑን ለማህበሩ ቅርበት ያላቸው ምንጮቻችን ይናገራሉ፡፡ ለቤተ ክርስቲያን የሚያስፈልገው አስተዳደራዊ ተሀድሶ ነው እያለ በአደባባይ መናገር የጀመረውና ውስጥ ውስጡን ራሱን በእጩነት እያቀረበ ያለው ማህበሩ ለቤተ ክርስቲያን እየተመኘላት ያለው አመራር እንዴት ያለ መሆኑን ከጉጂ ሀገረ ስብከት ተሞክሮ መውሰድ እንደሚቻል ግልጽ ነው፡፡      
9 comments:

 1. እንግዲህ የሸከናው ሁሴን በሥርዓት እየሰሩ ነው ማለት ነው ልበል ወይስ ምን? ትናንት ቤተ ክርስቲያን በየሥፍራው ባልታወቁ ወገኖች ስትቃጠል ነበረች ፡፡ ዛሬ ደግሞ ክርስቲያን የሆነው ወገን እርስ በእርሱ በተቀደሰው ሥፍራ ሲባላ ሌላ መግለጫ አላገኝለትማ ፡፡ ማጤን ያለብን አሁንም የግጭቱ መንስዔ ግን የእምነትና የዶግማ ልዩነት ሳይሆን የሥልጣን ሽኩቻ ነው ፡፡ የሆድ ነገር ለሆዳሞች ትልቅ አጀንዳ ነውና ፡፡ ይኸ በእንደዚሁ በያለበት ቢቀጥል ማን ይጠቀማል? ለጊዜው በመሃከል የተጐዳው ግን ምንም ምን የማይመለከተው የምእመኑ እምነት ይመስለናል ፡፡ መጨረሻው ግን ቤተ ክርስቲያን ራሷ በሆነ ባልሆነው ልጆቿን በማጣት መጐዳቷ አይቀርም ፡፡ ግርግር ለሌባ ያመቻል የሚለውንም ማሰብ ጥሩ ነው ፡፡ በዚህ ቅራኔ ውስጥ የሚያተርፉ ወገኖች ሊኖሩ ይችላሉ ፡፡

  ስለሆነው አዝናለሁ ፡፡
  እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያናችንን ይመልከት !!!

  ReplyDelete
 2. lemangnawm ewenetawn esu yawekal enantem endih atenadedu negeru kewedeku bewala meferaget le melelat new

  ReplyDelete
 3. ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ የጽርፈትና የጥፋት ዘመቻ የሚያካሂዱት በዋናነት የራሳቸው ማንነት የጠፋባቸው ምዕራባውያን(ሉተራውያን) ናቸው፡፡ እነዚህ አካላት ከመቶ ዓመታት በላይ በራሳቸው ጥረትና ስልት የወጡትን ያህል ወርደዋል፤ የወረዱትንም ያህል ወጥተዋል፤ ነገር ግን የተመኙትንና የፈለጉት በእጃቸው ማድረግ አልቻሉምና ሌላ ስልት ሌላ ስትራቴጂ መቀየስ ግድ ነው፡፡ ይህ ስትራቴጂ ደግሞ ከዘመኑ ሥልጣኔ ጋር ሻማና ክር ሆኖ በመመሳሰል እንዲቀረጽ የተደረገ በመሆኑ ብዙዎቻችን የተሃድሶአውያን ተላላኪነት በፍጹም ሊገባን አልቻለም፡፡

  ተሃድሶ የፕሮቴስታንቱ ዓለም ተላላኪ መሆኑ ግልጥ ያለ ነገር ነው፡፡ ማስረገጫው ደግሞ በዚሁ አዚም የተማረኩ ወገኖች ይኸው ቡድን በሚያደረግው የጸሎትና የዝማሬ ዝግጅት ላይ ሲገኙ የገጠማቸው ፕሮቴስታንታዊ ሥርዓት ነው፡፡

  በመሠረቱ ማንም ሃሳቡን ማራመድ ይችላል፤ የፈለገውን ማመንም እንዲሁ፤ ዓለማመንም የራሱ መብት ነው፡፡ በእኛ ቅኝት ዝፈኑ ማለት ግን በእኔ ሳንባ ተንፍሱ፣ በእኔም አፍ ተናገሩ ማለትን ግን የትኛውም የሰው ልጅ ሊቀበለው የማይችል ጉዳይ ነው፡፡

  ልጅ የቤተሰቡ ነገር ካልተመቸው ወጥቶ በራሱ መንገድ ራሱን መምራት የሚጠበቅ ነው፤ የቤተክርስቲያን ነገር በልበ ደንዳናነቱ አልዋጥለት ያለውም እንዲሁ፡፡ ልጅ ነውና ይመከራል፣ ይዘከራል፣ የሚጠቅመው ይነገረዋል፣ እኔ ነኝ የማውቀው ካለ መንገዱ ሰፊ ነው መጓዝ ይችላል፡፡

  የተሃድሶአውያን መሠረታዊ ችግር ሁለት ነው፥ በእኔ እምነት፥

  አንደኛ
  ግብዝነት፥ እንደ ፈሪሳዊ፡፡ በእውቀት የደረጀን፣ ለወንጌል አገልግሎት ቀሚስ የታጠቅን፣ የበሰበሰ የአስተዳደር ሥርዓትን መቀየር የምንችል ምሩቃን፣ ልሂቃን ብሎ መኮፈስ፡፡ በመሠረቱ ክርስትና በእውቀት ሳይሆን በልጅነት፣ በጸጋ፣ በሰማዕትነት፣በየዋህነት የሚወረስ መንግሥት ነው፡፡ ሊቀ ሐዋርያ ቅዳስ ጴጥሮስ በሮም አደባባይ የቁልቁሊት ተሰቅሎ ያገኘው መንግሥት ነው፣ የሐዋርያት መሪ የነበረውም በትምህርቱም ልሂቅነት አይደለም፡፡ አስተውሉ!!!

  ሁለተኛ፥
  ከፍጹማዊው ሕግ ይልቅ ለሰው ሠራሹ ሕግ ቅሩብ መሆናቸው ነው፡፡ በዚህ ጽሑፍ ከላይ የተገለጹት በሕግ ውስጥ በስውር የተቀመጡ ኢክርስቲያናዊ አሠራሮችን በመተግበር ለመፈጸም መሞከር፡፡ ተኩላ በበግ ለምድ እንዲሉ በሕግ ማዕቀፍ ስም በሰው ልጆች ላይ የተቀመጡትን አሳሪ ሕግጋትን ከዲያብሎሳዊ መንገድ ከሚከለክሉ የእግዚአብሔር ትዕዛዛት ይልቅ ሙጭጭ ብሎ መያዝ፡፡ አካሄዱ ሥጋዊነትን ያጋለጥ እንደሆነ እንጂ መንፈሳዊነትን የሚያውጅ አንዳች ኃይል የለውም

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሃሳብህ ከጽሁፉ ርእስ ጋር የሚሄድ አይደለም። ይልቁንም ጽሁፉ ያሳረፈብህን በትር ለመከላከል እንደጋሻ ለመከላከል የሰነዘርከው መመከቻ ወደመሆን ያዘነብላል። በዚህም የተነሳ የጽሁፉ መንስኤ ነው ብለህ ወዳመንከው ክፍል ላይ የተለመደውን ትችትና ነቀፋ ወደመሰንዘር ወረድክ። ባጭሩ ከጽሁፍህ ከዚህ ውጭ የተለየ ነገር አላየንም። በዓለም ላይ ያለው የመጽሐፍ ቅዱሳዊ እምነት አንድ ብቻ መሆኑ አይካድም። ችግሩ ያለው ሁሉም እኔ ዘንድ ያለው እምነት ነው ትክክል እያለ ብዙ እምነቶችን በየሄድንበት ማግኘታችን ነው የከበደው የሚሆነው!
   ግማሹ እድሜውን ይቆጥራል፣ እድሜ ግን እውነት እንጂ እምነት ሊሆን አይችልም። ገሚሱ ደግሞ ልምምዱን ምስክር አድርጎ ያቀርባል። ልምምዶች ሁሉ የእምነት ምስክሮች ሊሆኑ ያለመቻል፣ አለማወቃቸውን አያውቁም። በእድሜ ረጅምነት አይሁዳዊነት በእርግጥም እውነት ነው። ግን በእድሜው ረጅም መሆን የተነሳ የመዳን እምነት ሊሆን አይችልም። ልምምዶቻቸውን የመንፈስ ቅዱስ መገለጥ አድርገው የሚያቀርቡ «በስሜ ይመጣሉ»የሚለውን በቁጥር ከሚያታክት ብዛታቸው ጋር ትክክለኛ እምነት እንዳንላቸው ብንገደድም መኖራቸው ግን እውነት ነው።
   ስለዚህ በላይኛው ጸሀፊ ላይ ሃሳቤን ሳጠቃልል ስለቀደመ ወይም ስለተከተለ የሚመዘን እምነት የለም።እምነት አለን የምንለው ሃይማኖትን ስለተከተልን ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱስን ስላመንንና ትእዛዛቱን ስለፈጸምን ብቻ ነው። ተሃድሶአዊ ይሁን ፈሪሳዊ፣ አይሁዳዊ ይሁን ኦርቶዶክሳዊ፣ ካቶሊካዊ ይሁን ፕሮቴስታንታዊ የሚመዘኑትና መመዘን ያለባቸው ምንም ስህተት በሌለበት በመጽሐፍ ቅዱስ ነው። እነዚህ ሁሉ የኔ የተሻለ ነው ስላሉ የነሱ የተሻለ ሃይማኖት ነው ማለት አይደለም። መጽሐፍ ቅዱሳዊውን እውነት ሃይማኖቶች ይጠቀሙበታል እንጂ አያምኑም። ማስረጃችን «አንዲት እምነት» እንጂ ብዙ ሃይማኖት እንዳለ አልተነገረንም። ስለዚህ የበግ ለምድ ምናምን የሚለውን አባባልህ «ሃይማኖቶች ሁሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ይመርመሩ» እና ያንን የሚከተል ይሁን!!!!!!!!!!!!

   Delete
 4. tienaniet yekatit kidane miehieretien (kal kidanuwan)sietietechu neber zarea demo yekaliekidanuwa beal endayiekeber eniekiefat honu alachiehu ......alamachiehu mien endehone begieliest eyetawekebachiehu new beyetiem beyetiem beate kieriestiyanien mebetiebet.....aykeriem anied ken yebeate kieriestiyan amielak yieferdal

  ReplyDelete
  Replies
  1. አንተ ቀጣፊ ነህ፤ ማነብነብ እንጂ ማንበብ የምታውቅ አልመሰለኝም፤ በዚህ ዜና ውስጥ ያንተን ኪዳነ ምህረት ደግፎ ማን ጻፈና ነው ኪዳነ ምህረትን ትናንት ስትነቅፉ ነበር ዛሬ ግን ደገፋችሁ ምናምን ... የምትለው? ዛሬ የቀረበው እኮ ዜና እንጂ ኪዳነ ምህረትህን የተመለከተ ነገር አይደለም፡፡ ስለዚህ እባክህን አስተውል! መዳን በሌላ በማንም የለም፤ የእኛ ኪዳነ ምህረት ኢየሡስ ብቻ ነው፡፡

   Delete
  2. አንተ በለምድ የተሸፈንክ ማህበረ ቅዱሳን፣
   ወይም ልበልህ ‘አሳሳች ማህበረ ሰይጣን’ ፣
   በገዛ እጃችን ከማብዛት መከራን ፣
   ሞትን እናስተግድ ድምጻችንን ቀብረን፣
   የንስሀን ጊዜም አሟጠን ጨርሰን፣
   እሄው ቁጭ ብለናል ፍርድን እየጠበቅን፣
   አንተ በሄድክበት እኛም አልተከተልን፣
   ምክንያት በመፈለግ እየተጠቃቀስን፣
   እየተረዳዳን ጉድጔድ እየቆፈርን፣
   እርቀን ሄደናል መመለሻም የለን፣
   እዛው በፍርድ ቀን እንናገኛለን፣
   በጻድቃኖቻችን እየተስተናገድን፣
   ከናሺቭል ቴንሲ ፓስፖርታችን ይዘን፣
   አንተ ወዲህ ስትቀር እኛም እንገባለን፣
   መንገዱ እንዳይጠፋን በድንግል ታጅበን።

   Delete
 5. Looks little knowldge.

  ReplyDelete