Tuesday, February 14, 2012

የጥር 20 2004 ዓ.ም. ጉባኤ የተስተጓጎለው በማህበረ ቅዱሳን ሴራና በሳሙኤል ሮቶ አስፈጻሚነት መሆኑ ታወቀ - - - Read PDF

ጉባኤው የተዘጋጀው በከፍተኛ የልብ ሕመም እየተሰቃየ የሚገኘው እንዳለ ገብሬ የተባለው ወንድም ሕክምናውን በአገር ውስጥ ማግኘት ስላልቻለ በጥቂት ጊዜ ውስጥ ወደ ውጭ አገር ሄዶ ካልታከመ ለህይወቱ አስጊ መሆኑ በሀኪሞች ስለተነገረው ለእርሱ ገንዘብ ለማሰባበስ ነው፡፡ በዚሁ መሠረት የ20፣ የ50 እና የ100 ብር ቲኬቶች እየተሸጡ የነበረ ሲሆን፣ በSMS 8512 ላይ ባዶ መልእክት በመላክም ከየስልኩ ላይ ብር 1.50 (አንድ ብር ከሃምሳ ሣንቲም) የሚዋጣበት መንገድም ተመቻችቷል፡፡ በሪፖርተር እና በአዲስ አድማስ ጋዜጣ  በኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ላይና በሸገር ኤፍ ላይም ማስታወቂያ ተሰርቶለታል፡፡ ጉባኤው ህይወት አድን እንጂ ሌላ አልነበረም፡፡
እነመምህር አሰግድ ህይወት ለማዳን መንፈሳዊ ጉባኤ ሲያዘጋጁ፣ ማህበረ ቅዱሳንና ጀሌዎቹ ደግሞ የሰው ሕይወት እንዲጠፋ መራወጣቸው ብዙዎችን አሳዝኗል፡፡ ማን ምን መሆኑን፣ ማን ከማን ወገን እንደሆነም አሳይቷል፡፡ በወንጌል እንደተጻፈው ጉባኤውን ያስተጓጎሉት የሌባው የአራጁና የነፍሰ ገዳዩ (ዮሐንስ 10፡10) ተከታዮች መሆናቸውን ስራቸው መስክሯል፡፡

ሕይወትን ለማዳን በበጎ ስራ ላይ በተሰማሩት የቤተክርስቲያን ልጆች ጉባኤውን ለማስተዋወቅ ፖስተር ተዘጋጅቶ የነበረ ሲሆን፣ ጉባኤውን ለማዘጋጀት የተንቀሳቀሱት ደግሞ መምህር አሰግድን ጨምሮ በማህበረ ቅዱሳን ተሐድሶ መናፍቃን ናቸው ተብለው የተፈረጁና የማህበረ ቅዱሳን እጅ እንዲሰበሰብ በተደረገባቸው የቤተክርስቲያን አውደ ምህረቶች ላይ እስካሁንም እያገለገሉ በሚገኙ የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ነው፡፡

ይሁን እንጂ በዚህ ደስ ያልተሰኙት ማህበረ ቅዱሳንና የእነ ምህረተ አብ (ፍልፍሉ) ቡድን የስብከተ ወንጌል መምሪያ ምክትል ሀላፊ የሆነውን ሳሙኤልን (ሳሚ ሮቶን) በመጠቀም በመጨረሻው ሰአት ጉባኤው እንዲስተጓጎል አድርገዋል፡፡ በዚህም ማህበረ ቅዱሳንና ግብረ አበሮቹ ለሰው ህይወት ግድ የሌላቸው መሆናቸውን በተግባር አሳይተዋል፡፡ ጉባኤው እንዲስተጓጎል በድረገጽ ሲቀሰቀሱ የነበሩት እነ አንድ አድርገንና ደጀሰላም ስራቸውን ከሰሩና በልብ ህመም እየተሰቃየ ያለውን ወንድም ድጋፍ እንዲያጣ ካደረጉ በኋላ አዛኝ ለመምሰል “አሁንም ደግመን መናገር የምንፈልገው ነገር የልብ ህመም የደረሰበት ወንድማችን የሚያስፈልገውን ገንዘብ ያህል ለማሰባሰብ ይረዳው ዘንድ ቤተክርስትያኗ ፍቃድ ከሰጠቻቸው መምህራን ጋር ጉባኤ ቢያዘጋጁ መልካም ነው እንላለን፡፡ እኛም ብዙ ሰዎች በጉባኤው እለት እንዲገኙ የቻሉትን ያህል እንዲረዱ የአቅማችንን ያህል በመስራት ከጎኑ ለመቆም ቃል እንገባለን፡፡” ቢሉም ከወሬ ባለፈ ምንም ያደረጉለት ነገር እንደሌለ ለእንዳለ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ተናግረዋል፡፡

ቀደም ሲል የጉባኤው አስተባባሪዎች ወደ አቡነ ፊልጶስ በመሄድ ለማስፈቀድ የቻሉ ቢሆንም፣ የማህበረ ቅዱሳን ሰዎች እየተመላለሱ ጉባኤውን እንዳይፈቅዱ በማግባባትና በሐሰት “የዲያቆን ትዝታው ወንድም ነው አይፍቀዱለት” በማለት ጳጳሱን ስለጠመዘዟቸው ወጥ አቋም መያዝ አቅቷቸው “ፈቅጃለሁ - ከልክያለሁ” በሚል አቋማቸው ሲለዋወጥ ተስተውሏል፡፡ አቡኑ የማህበረ ቅዱሳንን አጀንዳ ለማስፈጸም እንጂ ቤተክርስቲያንን በተገቢው መንገድና በቤተክርስቲያን ልጆች መካከል ያለአድልዎ ሁሉንም በእኩል ለማስተናገድ እንዳልቻሉ ከዚህ ቀደም በፈጸሟቸው ግድፈቶችም ተረጋግጧል፡፡ በቅርቡ እንኳ የአባ ሠረቀ መጽሐፍ በተመረቀ ዕለት በጉባኤው መክፈቻ ላይ ተገኝተው የነበረ ቢሆንም፣ ዘማሪት ምርትነሽ መዝሙር ስታቀርብ ጉባኤውን ረግጠው ለመውጣት ተገደዋል፡፡ ይህም በዚያ ሰዓት ሌላ ጉዳይ ኖሯቸው ሳይሆን ምርትነሽ ስትዘምር እዚያ ብገኝ ማህበረ ቅዱሳን ይከፋል ብለው ያደረጉት እንደሆነ በብዙዎች ዘንድ ግምት ተወስዷል፡፡ ይሁን እንጂ አባ ሠረቀ ብፁዕ አባታችን ሌላ ስራ ስላለባቸው ነው በሚል ጉባኤውን ይቅርታ ጠይቀውላቸዋል፡፡

አባ ፊልጶስ ለአቶ እንዳለ የገቢ ማሰባሰቢያ ተብሎ የተዘጋጀውን ጉባኤ እያመነቱም ቢሆን የፈቀዱ ሲሆን፣ ለስብከተ ወንጌል መምሪያም ጽፈዋል፡፡ ስብከተ ወንጌሉም በማህበረ ቅዱሳን በኩል ብጥብጥ እናነሳለን የሚለው ነገር መወራቱን ከግምት በማስገባት ህይወት አድን ጉባኤው እንዳይስተጓጎል በራሱ በኩል መምህራን እንዲመደቡ አድርጎ እንደነበር ታውቋል፡፡ የስብከተ ወንጌል ሃላፊ የሆኑት መምህር አእመረ ከአዲስ አበባ ውጪ መሆናቸውን እንደ መልካም አጋጣሚ የቆጠረው ምክትላቸው ሳሚ ሮቶ ግን፣ አርብ አመሻሹ ላይ ብጥብጥ ሊከሰት ይችላል በሚል ለመንግስት አካላት ጽፎ ጉባኤውን  አግዶታል፡፡ ከዚያ ቀደም ብሎም ለአቶ እንዳለ “ማህበረ ቅዱሳን እንዲያሳክምህ ለምን አታነጋግራቸውም” በማለት እርሱን ከእነ በጋሻው ለመነጠል ሲያግባባው እንደነበር ውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ፡፡

ወገኑን ረድቶ ወንጌልን ለመስማት ቋምጦ የነበረውና የጉባኤውን መታገድ ያልሰማው ምእመን እሁድ በ8 ሰአት ይደረጋል ለተባለው ጉባኤ ከጠዋቱ 5 ሰአት ጀምሮ ወደ ጠቅላይ ቤተክህነት መጉረፉን ጀምሮ ነበር፡፡ ህዝቡ እንዳይንገላታ ጉባኤው መቅረቱን ለመግለጽ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በር ላይ የተለጠፈውን ማስታወቂያ ምህረተ አብ በርቀት ቆሞ እየቃኘ ወንድወሰን የተባለ የቡድኑ አባል ሲገነጥል ታይቷል፡፡ ይህም ጉባኤው አልቀረም ብሎ ሰው ግራ እንዲጋባና ማህበረ ቅዱሳን አቀዶት የነበረው ብጥብጥ እንዲነሳ ጽኑ ፍላጎት የነበራቸው መሆኑን አመላክቷል፡፡
ሳሙኤል ሮቶ ስብሰባው እሑድ እንዲካሄድ ከተፈቀደና መምህራን በስብከተ ወንጌል መምሪያ ከተመደቡ በኋላ፣ በቆረጣ ገብቶ አርብ አመሻሹ ላይ አግጃለሁ ማለቱ እነመምህር አሰግድን ለመቃወም ያደረገው ብቻ ሳይሆን በልብ ህመም እየተሰቃየና ለህክምናው ጥቂት ቀናት ብቻ የቀሩትን እንዳለን ለከፋ አደጋ እንዲጋለጥ በመፈለግም ጭምር እንዳደረገው ከፍተኛ ግምት ተወስዷል፡፡ የተፈቀደው ጉባኤ በሳሙኤል ሮቶ “ሥልጣን” መታገዱን ከሰማ በኋላ እንዳለ ራሱን ስቶ እንደ ነበረ ምንጮቻችን ጠቅሰው አሁንም የቀሩት ጥቂት ቀናት በመሆናቸው በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወገኖች ድጋፋቸውን እንዲለግሱትና ህይወቱን እንዲትርፉለት ተማጽኗል፡፡ ለመርዳት ለምትፈልጉ አዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ የወጣውን ማስታወቂያ እንዳለ እናቀርባለን፡፡
እንዳለ ገብሬ ሀይሌ
ከፍተኛ የሆነ የልብ ቧንቧ ጥበት ሕመም ያለበት ሲሆን የጥቁር አንበሳ የሕክምና ቦርድ በአገር ውስጥ የሕክምና እርዳታ ማግኘት ስለማይችል በአስቸኳይ በውጭ ሀገር ህክምና እንዲያገኝ ደብዳቤ ጽፎለታል፡፡
እርዳታ ለመስጠት
በ8512 ቁጥር ላይ  sms(የጽሁፍ መልዕክት)  ባዶ መልዕክት በመላክ 1.50(አንድ ብር ከሃምሳ) በአንድ መልዕክት መርዳት የሚቻል ሲሆን
እንዲሁም በባንክ ሂሳብ ቁጥር
ዳሽን ባንክ ፒያሳ አካባቢ ቅርንጫፍ
የሂሳብ ቁጥር 5026903144004
መጠቀም ይቻላል 
በዚህ አጋጣሚ ይህንን መልዕክት የምታነቡ ወገኖች ሁሉ ለወንድማችን አቅማችሁ የፈቀደውን እንድትረዱ በእግዚአብሔር ርህራሄ እንለምናችኋለን፡፡

28 comments:

 1. egeziabehere yimare. egam endegefehalen. mk motehen bemegem geta gin yifewesehal.

  ReplyDelete
 2. አህያን አስታኮ ጅብን መውጋት ይሏል ይሄ ነው። ተሃድሶዎች ለዛሬ አልተሳካም። ሌላ ዘዴ ቀይሱ።

  ReplyDelete
 3. ማህበረ ቅዱሳን ሰዎች በስጋም በነፍስም ተጠቃሚ እንዳይሆኑ የሚሰራ የነፍሰ በላ ወንበዴዎች ጥርቅም መሆኑ በግልጽ እየታየ ነው:: ይህ ቡድን አሁን አሁን ነፍስ የሚያጠፉ ተደባዳቢዎችን በገንዘብ በመመደብ የትም ያልታየ ሰይጣናዊ ስራ በመከወን ላ ይገኛል;:

  የሚገርመው ግን ለገንዘብ ያደረው ሳሚ ሮቶ እና ከኮሜዲ በቀር የበሰለ ነገር ማስተማር የማይችለው ምረተአብ (ፍልፍሉ) ከነፍሰ በላው ቡድን ጋር መሰለፋቸው ነው::
  ለማንኛውም የወንድማችን ጤነኛ ሆኖ ለማየት ያብቃን;:

  ReplyDelete
 4. Aba Selam, Thank you. We will help our Brother in Christ.

  ወገኖች እስከአሁን አላወቃችሁም ነበር እንዴ\ ማቅ እኮ ሥራው ይህ ነው። በክፉ ሃሳብ
  ታስቦ፣ በቅናት ተፀንሶ፣ በተንኮል የተረገዘና ለጥፋት የተወለደ ነው እኮ። እንዳንድ ጊዜ
  ዝም ብየ ነገራቸውንና ክፉ ሥራቸውን ስመለከት እንደ ይሁዳ ትንቢት የተነገረላቸው
  በመጨረሻው ዘመን የሚመጡ የአምልኮት መልክ አላቸው ኅይሉን ግን ክደዋል፣ አይን
  እያላቸው አያዩም፣ ጆሮ እያላቸው አይሰሙም፣ አያስተውሉም፣ ፍቅር የሌላቸውና ሌላም
  ሌላም እያለ መፅሐፍ ቅዱስ የሚነግረን እነዚህኑ አስመሳይ የቤተክርስቲያን ሰዎች ነን
  ለሚሉት ለማቅ ድርጅት ሥራ ለሚሮጡት የተነገረ ነው ብየ አምናለሁ።

  ማቅ ደግሞ ዝግጅቱን ለማዘጋጀት ምንም እቅድና ሃሳብ ስላልነበረው፣ እነዚህ ትጉሃን
  የቤተክርስቲያን ልጆች በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ሲሰማ ፤ 1\ኛ፣ እነሱን ስለቀደማቸው፣
  2ተኛ፣ ምን ጊዜም ቢሆን ለምቀኝነት የማያንቀላፋው ማቅ እራሱ ስላላዘጋጀው ከፍተኛ
  ሠይጣናዊ ቅናት ዘወትር በነሱ ላይ ስላለው፣ 3ተኛ፣ ደግሞ ማህበሩ ግብዝ በመሆኑ የተነሳ
  ለሥምና ለገንዘብ እንዲሁም ለሰይጣን የሚገዛ ማህበር እንጂ ለቤተክርስቲያንና ለክርስቲያኖች
  ደንታ የሌለው በመሆኑ እሱ ጥቅም የማያገኝበት በመሆኑ ነው ፣ ለጊዜው ሰይጣን አላማው
  የተሳካ ቢመስለውም እግዚአብሔር የራሱ መንገድ ስላለው በከንቱ ይደክማሉ።
  ሌላው ፀረ ወንጌሎችና ፀረ ክርስቶስ ስለሆኑ ወንጌል እንዲሰበክና ክርስቲያን እንዲበዛም
  አይፈልጉም። ማቅ የሚፈልገው ቤተክርስቲያኒቱን ያለ ክርስቲያን ለራሱ ብቻ መጠቀሚያና
  መነገጃ ለማድረግ ነው፣ በአጠቃላይ ማቅ በቤተክርስቲያን ላይ የመጣ ፈተና 666 ነው።
  እንጃ ትንሽ ቆይቶ እኔ ክርስቶስ ነኝ፣ በእኔ እመኑ ብሎ ሳያስገድድ ይቀራል ብላችሁ ነው \
  ስለዚህ ክርስቲያኖች ፈተናውን ለማለፍ በፅሞና ከእግዚአብሔር ጋር እንጣበቅ። እስከ
  መጨረሻው የፀና እርሱ ይድናል ነውና ከሃሰተኛ ከደም አፍሳሽ፣ ከወንበዴዎች ተጠንቀቁ፣
  ንቁ፣ ከዘላለም ባርነት የአንድ ቀን ነፃነት እንደሚባለው በክርስቶስ ነፃ የዘላለም ህይወት
  እንድንኖር እግዚአብሔር ይርዳን። መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ የገዛን ከፍተኛ
  ዋጋ ከፍሎ የወደደን ውድ ልጆቹ በመሆናችን የሞተውም ለሰው ለጆች ሁሉ ስለሆነ ማቆችን
  ይህንን የሚያዩበት የልብ አይናቸውን አምላክ ይክፈትላቸው።

  የእግዚአብሔር ሰላምና ፀጋ ይብዛላችሁ፣ አሜን።

  ReplyDelete
 5. yihenen neger yaderegew mk kehone betam teseminet alew malet new.Ende endet yihenen abune paulos enkua mazez akatachew? min ayinet hailegna mahiber new ebakachihu?yihen yakil eko kehone lewodefitum ayaserachihum malet new? ende! lelochu endefelegut eko endayihiedu aderegachew. min ayinet Tenkara mahiber new Ebakachihu?

  ReplyDelete
 6. He was x members of mk.

  ReplyDelete
 7. ምነው ጉዳችሁ ስለወጣ ነው አስተያየቴን ያላወጣችሁት!!!!!! አይደንቀኝም

  ReplyDelete
 8. በጌታ ወንድሞቼ ለሆናችሁ የአባቴ ልጆች እና
  እንዲሁም በሥጋ ወንድሞቼ ለሆናችሁ በሙሉ!

  የክርስትና ትክክለኛ ትርጉሙ ይህ ስለሆነ ማንነቱን በትክክል ባላውቀውም ጌታን የምትወዱ ሁሉ በጎ የሆነውን ሁሉ ለማድረግ ስላልተከለከልን ጌታ ባስቻለን ሁሉ ለዚህ የእግዚአብሔር እጅ ሥራ ለሆነው ወንድማችን እንረባረብ:: ከሌሎች የእፉኝት ልጆች እንዴት መልካም ነገር ትጠብቃላችሁ? አመጸኛውም እስከ መጨረሻው ያምጽ ጻድቁም ይጽደቅ ነውና ሁሉም ያባቱን ሥራ ይሥራ ተውት:: ያ ቀን ብቻ ሳይሆን በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ሆኖ በክርስትና ስምና በሕዝቡ ዝቅተኛ መንፈሳዊ መረዳት ተጠቅሞ በማስመሰል ወገናችንን ለሞት ፍርድ ለማዘጋጀት ደፋ ቀና በሚሉትና በሚያምሱት አስመሳዮች ላይ የአምላካችን ክንድ ለዚህ ግራና ቀኙን ለማያውቅ የዋህ ሕዝብ ሲል በቅርቡ እንደሚገለጥ አምናለሁ:: አንተ ግን እንደ ሎጥ አምልጥ የሎጥ ሚስትና መሰሎቿ የጨው ኃውልት ሲሆኑ ታያለህ ነው መልእክቱ:: የወገኖቻችንን ጥፋት እንኳን እግዚአብሔር እኛም ሰዎች አንሻምና ተመለሱ እንላለን ለአፋኝ ቡድኑ አባላት::

  ማስተዋል በክፉው ተጠልፈው በወገናቸው ላይ ለከፉት ይብዛላቸው!!

  ለታመመው ወንድማችን የፈውስ እንጀራ ትምጣለት!!
  ተግባራዊ እርዳታውም ይቀጥል እንበርታ!!

  ሰላም ሁኑልኝ

  እህታችሁ

  ሰላም ነኝ

  ReplyDelete
 9. do you think "praying is not necessary for such type of brothers who is there in dangers?"
  God bless him and also really you terrorists!

  Zegebre-AA

  ReplyDelete
 10. This is, on Feb. 14,2012 03:01 PM. Comment.

  ባንተ ቤት የማህበሩን ጠንካራነት ለመግለፅ በማሾፍ የሰጠከው አስተያየት ነው።
  ድሮስ ከነእንዳንተ ያለው የእፉኝት ልጆች የሰይጣን መሳሪያዎች ምን ይጠበቃል፣
  ያም ሆነ ይህ ምንም አላችሁ ምንም ጌታችን በልበ ንፁሃን ላይ እያደረ ሥራውን
  ይሰራል። ይልቁንስ ሳይመሽብህና\ባችሁ\ አይናችሁን ለሰይጣን ማህበር ሳይሆን
  ሁሉን ወደሚችል አምላክ አድርጉ። እርሱ መሐሪ ነውና፣ ቤተመቅደስን የጠበቁ
  መስሎአቸው የወጉትን፣ የናቁትን፣ የተፉበትን፣ የቀለዱበትን፣ ያሾፉበትን፣ ብሎም
  የሰቀሉትን ሁሉ ምህረቱ ብዙና ፍቅሩ ብዙ ሰለሆነ አቤቱ የሚያደርጉትን አያውቁምና
  ይቅር በላቸው ወዳለው አምላክ ተመለሱ። ጊዜ ስለሰጣችሁና ስለታገሳችሁ ትክክለኛ
  ነን ብላችሁ ታበያችሁ ነገር ግን እራሳችሁ ጠፍታችሁ ሌላውን ሁሉ ይዛችሁ
  ለመጥፋት የከንቱ ሩጫ ከምትሮጡ እስቲ ቢያንስ እራሳችሁን ለማዳን ሞክሩ።
  አውቆ የተደበቀን ቢጠሩት አይሰማም አትሁኑ። ክርስትና ማለት የገባቸው፣ክርስቲያኖችን
  ለማሰናከል አትሩጡ፣ እስኪገባችሁ ድረስ ይጠብቃችሁአል። አሜን።

  ምስጋና ይሁን አንድ አምላክ ለሚሆን
  ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሜን።

  ReplyDelete
 11. yemiasazen new MK yemibal mahebere new weyes anti christ yemiasbel new. betam betam yasasenal kesem matfat wede yetecheger sew endayereda hiwot matfat teshageru malet new. enezihen sewoche bekachehu yemil yebelay akal alemenoru betam yasazenal.

  ReplyDelete
 12. Take action instead of crying to stop taliban mk invassion from our anncient church. Mk is hate Jesus that is the reason they work 7/24 to reduce the credibilty of our famouse preacher such like megabe hadis begashaow by using rummor and alegation. The solution is one take very bad action to clean up the church all eotc if necezsary paying life as like as jesus.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Hulunim tawuqalaachu Tehodisom hone M/ kidusan maan min endemisera gilitsi new,gin yesewun hiwot yemyadin Amlak'nji Mk/ Tehadisowochu aydelem.Gudayu gubaa'ewun maan yimra/yakahid new inji yetaamemaw aytakem yimil maanim fitur yelam ebaakachihu sile feterachihu bezise'at zim bilen yegnan hasab bicha anawura mastawaalin genzab enadrig

   Delete
  2. Seyfin yemiyanesa beseif yigedel min ale zim bilachihu kemitawaru inantem berasachihu church bitadergu gudayu legizew yetagedut wendmoch indysebku new yetebalew himamtegnew ayireda aydelam shek alamudi liyasakmu yichilalu gin guba'e lazegaj bilu mk no bil ayasweksewum yihin sil bemisale lemglets inji wandimoch Muslimoch nachew lemalet aydelem

   Delete
 13. Why do you not write in a christian manner? It is difficult for me to think the way you write(report) is a spiritual way?

  ReplyDelete
 14. How every body makes mistakes that the menbers of Mk are doing bad things? As an Ethiopian it is not fair to say publicly an association of thausends menbers who do have their owen income do for such things? by the way is there any person who is blamed by MK as Tehadso and who is not? Why you use the sick person as a cover to your Tehadso objective? As a "spritual"person publikly use the words "Roto" "Filflu" in public media? Is it Christianity? Who teachs you such communication? Of course it is not a surprising for a person who donot respect the Gods Saints to respect the one ... Let us at least use FACTS and Facts only! Let God Give Us the paitence .

  ReplyDelete
  Replies
  1. No one had officially proclaimed who is Tehadiso & who is not!! And No one of others have had an authority to justify on the matter of Tehadiso except the Holy Synod!!!
   ተሐድሶ እነዚህ ናቸው ብሎ በስም ዝርዝር ሲኖዶስ የወሰነበት ሰው አለ? አንድም የለም!! ማኅበረ ሰይጣኑ ጭምር የሲኖዶስ የተሀድሶ ዝርዝር በእጁ የለም። አለ ካለ እስኪ ያሳየና!! እራሱ ማኅበረ ሰይጣኑ ነው እያገደ ያለው!! የሰይጣን ማኅበር በየብሎጎቹ ይጮሃል። ተከታዮቹም ይጮሃሉ። ሰይጣን ከራሱ አመንጭቶ ስለሚዋሽ ማኅበሩ ሰይጣን ነው፤ ተከታዮቹም ሰይጣናት ናችሁ!!
   እስኪ በጋሻው ሆነ ትዝታው ተሃድሶ መሆናቸው በሲኖዶስ የተወሰነባቸው መሆኑን ማስረጃ አሳዩን!!
   ምድረ ሰይጣን-ውሸታም ሁላ!!!!!!11

   Delete
  2. I don't believe begashaw or tizitaw is tehadiso but I can dare to say that they are not spiritual becuase they are preaching themselves.

   Delete
 15. he is biger than roto ..and he know it also. lehodu yader ..mk enet ayent tenkara letbalew asteyayet pilatosm eko getan asalfo eskemestet siltanun tetekmobetal..but geta selfekedle bicha new ..kaltemelsu ena if they dont repent they will go to the hell.felflu tert tertu eyeteselch and semiw eykenese selhone he dont have any thing better to do .meheret ke geta selhone yetamaewon teameru yemayalkwo amlak yedasew.

  ReplyDelete
 16. The above two anonymous...It is good to advise others to act in a christian manner. but first you have to advise your MK friends writing on the Dejeselam and Andeadrgen blogs who are insulting our holly fathers,brothers and sisters day in day out. MK is teaching ppl to insult others including preachers, singers and pops on these blogs. I hope you have red the bad news, comments and insults written by these blogs on Aba paulos, Aba Fanuel, etc Everybody knows that THESE BLOGS are the mouth of MK. If you really are worrying for ' christian behavior' first try to advice your bloggers out there. Then you might have enough moral background to advise others.

  ReplyDelete
 17. One very critical question for the blog admin.
  What is your evidence that MK did this and that? Any single evidence?

  On a side note, I tired to follow MK's website and publications for the past several months. They are simply preaching the gospel and supporting their church. It all sound so spiritual and so comfortable to be on their websites and publications. There is peace there. I have never read an article similar to yours. They are so spiritual and so much like a christian.

  ReplyDelete
 18. To the above to anonymous to whom said about MK. God created us in his image and give us mouth to warship but not to accuses one others without any evidence. please bother or sister do you know we will be judged beside on our action? so don't be hate others instead pray if you really care about church. i didn't see any major mistake about MK. as human we all make a mistake but don't judge them if you see any manner mistakes because some one who always work can make mistakes. and learn from their mistake but those don't do anything they always sit and make criticize other so don't be like those people do your part and God will bless you more

  ReplyDelete
 19. oh woshet i never read any thing in there mks blog that yemiyans ke woshet beker ,, thats all out there. evry body know dejeselam is mks blog they use this one to say some thing bad about others and mahber kidusan blog to cover up .sewochen legizwo matalel yichal yihonal but not amlaken

  ReplyDelete
 20. i dont think begashawo is priching about him self ..by the way tizitaw is not a pricher he is zemari as long as i know''ye kinategnch were new kekenah ask god to give you there kind of gift ,, if u ask god with pure heart he will grant you,but u cant be megabi hadis begashaw or decon zemari tizitaw.sim matfat kinat mekgnenet tenkol hamet kirker meleyayet beker sira yelelew ppl.

  ReplyDelete
 21. betam yasazinal ,begashawn ,mirtneshn,tizitawn,zerfen,na lelochinem........ iski minew mahbere "kidusan " lemin tasadidachewalachihu. kidusan woym bekidusan sim yetesebasebe yezih aynet sira yiseral? betam yazenkut lenesu yalhone sim mestetachihu. aree asibubet .beyehageru hulum awkwachuhal.minale batbetebituna bewshet rasachihun batisekilu. cher yaseman..

  ReplyDelete
 22. WeYmahbere kidusan! Leka ye menafikan ras mitat new!!

  ReplyDelete
 23. ለመሆኑ አቡነ ጰውሎስ የፈቀዱትን ጉበኤ ም/ ሀለፊ በሆኑት ቄስ ሳሙኤል ምክንየት ከተከለከለ እውነትም ጉባኤው ህገወጥ ነበር አያስብልም? ምክንያቱም ጠቅላይ ስራ አስኪያክጁ ፈቅደው ቢሆን ኖሮ ቀሲስ ሳሙኤል ብቸውን መዝጋት አይችልም ። ደግሞስ ህገወጡ ግሩፕ ማንም አያዘኝም እያለ በየ መጽሄቱ ሲቀባጥሩ ኖረው ዛሬም መማር አለመቻላቸው ያስገርማል

  ReplyDelete
 24. ሣናዉቅ አታለላቹህን አይበቃቹህም፧እፈሩ እንጂ የምን መጠጋጋት ነው።በዲ\ን ሉልሰገድ ስም የሠበሠባቹህት አይበቃቹህም እንዴ።

  ReplyDelete