Saturday, February 11, 2012

ለመምህር ምህረተአብ አሰፋ “አልተሳሳትንም” የቪሲዲ ስብከት በዲያቆን አግዛቸው ተፈራ “አልተሳሳትንምን?” ተብሎ ምላሽ ከተሰጠበት መጽሐፍ ገጽ 53 ላይ የተወሰደ - ስለ ታቦት መባዛት

ስለ ታቦት መባዛት
እግዚአብሔር ለሙሴ አንድ የቃል ኪዳን ታቦት ከሰጠው አሁን በየገዳማቱና በየአድባራቱ ያሉ በርካታ ታቦታት ከየት መጡ?

ይህን ጥያቄ ለመጽሐፍ ቅዱስ ማቅረብ ቢቻል፥ ደግሞ የምን የታቦት መባዛት አመጣችሁብኝ? በሚል ጥያቄውን በጥያቄ እንደሚመልሰው ጥርጥር የለውም፤ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ የሚያውቀው አንድ የቃል ኪዳን ታቦትን ብቻ ነው፡፡ ከመምህር ምሕረተ አብ እየቀደሙ ጥያቄውን የሚያቀርቡት ሰው ግን፥ እግዚአብሔር አንድ [ታቦት] ሰጥቶ እናንተ ብዙ ይዛችሁ በመገኘታችሁ ተሳስታችኋል ይሉናል፡፡ እኛ ግን አልተሳሳትንም እንላለን፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የሚነግረንን እውነት መሠረት አድርገናልና በማለት፥ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ታቦት መባዛት እንደሚናገር በድፍረት ይጠቅሳሉ፡፡ መምህር ምሕረተ አብም፥ ለዚህም መልሳችን መጽሐፍ ቅዱስ ነው ሲሉ ሐሳቡን ያጸድቁታል፡፡

ለዚህ የጠቀሱት ሙሴ በሕዝበ እስራኤል ኀጢአት ተቈጥቶ በሰበራቸው ሁለት ጽላት ምትክ፥ እንደ ፊተኞቹ አድርጎ ሁለት ጽላት ጠርቦ እንዲያመጣ እግዚአብሔር የተናገረውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ነው (ዘፀ. 32፥1-20፤ 34፥1)፡፡ በተለይም ዘፀአት 34፥1 ላይ ያለውን ቃል አንብበው በራሳቸው መንገድ ሲገልጹት፥ ይህ ነገር ተሰብሮ መቅረት የለበትም፡፡ እንደበፊተኛው አድርገህ እንድታዘጋጅ ና ፎርሙላውን ልስጥህ፤ መመሪያውን እንዴት አድርገህ እንደምትሠራ ልስጥህ አለውና ይላል» በማለት ያላነበቡትን እየተረጐሙ ነው፡፡ ይገርማል! ዘፀአት 34፥1 እንዲህ የሚል ንባብ፣ መልእክትም ሆነ ሐሳብ ፈጽሞ የለውም፡፡

ይህ ሁሉ የፈጠራ ሐሳብ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የሌላቸውን የኢትዮጵያን ታቦታት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ለማስመሰል ነው፡፡ ስሕተትን በመጽሐፍ ቅዱስ ማስተካከል ሲገባ፥ መጽሐፍ ቅዱስን ለስሕተት መሸፈኛ አድርጎ ማቅረብ ሰውን እንጂ እግዚአብሔርን ደስ አያሰኝም፡፡ መምህር፥ ሰውን ወይስ እግዚአብሔርን አሁን እሺ አሰኛለሁን? ወይም ሰውን ደስ ላሰኝ እፈልጋለሁን? አሁን ሰውን ደስ ባሰኝ የክርስቶስ ባሪያ ባልሆንሁም፡፡ (ገላ. 1፥10) በሚለው የታማኝ አገልጋይ ዐቋም እስኪ ራስዎን ይፈትሹ!

ዘፀ. 34፥1 የሚለውስ እንዲህ ነው፤ እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፤ ሁለት የድንጋይ ጽላቶች እንደ ፊተኞች አድርገህ ጥረብ፤ በሰበርኻቸው በፊተኞቹ ጽላቶች የነበሩትን ቃሎች እጽፍባቸዋለሁ፡፡ በዚህ ቃል ውስጥ በግልጽ እንደሚነበበው ሙሴ የድንጋዮቹን ጽላቶች ጠርቦ አመጣ፤ እግዚአብሔር ደግሞ ቃሎቹን ጻፈባቸው፡፡ ከዚህ ውጪ በዚህ ክፍል እግዚአብሔር ስለ ጽላት አሠራር ለሙሴ የሰጠው ቀመርም (ፎርሙላም) ሆነ መመሪያ የለም፡፡ መጀመሪያውኑ ና ላሳይህ በማለት ፈንታ ጥረብ ነው ያለው፡፡ ሙሴም በታዘዘው መሠረት ጽላቱን ጠርቦታል፡፡ የጻፈበት ግን እግዚአብሔር ነው፡፡ የተከናወነው ይህ ብቻ ከሆነ፥ መምህሩ እንደበፊተኛው አድርገህ እንድታዘጋጅ ና ፎርሙላውን ልስጥህ ... አለው ያሉት ምን ትርጕም ሊኖረው ነው? ምክንያቱም ሙሴ ወደ እግዚአብሔር የሄደው የጠረበውን ጽላት ይዞ እንጂ የጽላት አጠራረብን ጥበብ ለመማር አይደለም፡፡ ወይም የእግዚአብሔርን ድርሻ ወስዶ በጽላቱ ላይ ቃሎቹን እንዴት እንደሚጽፍ ለማየት አልነበረም፡፡ ስለዚህ መምህር፥ ስለ ኢትዮጵያ ታቦታት ብዜት ጕዳይ ደጋፊ የሚሆን ጥቅስ ከመጽሐፍ ቅዱስ ስለማያገኙ፥ ቅዱስ ቃሉን ባያጣምሙና ታቦት የሚባዛበትን ምክንያት ከእነዚያው ከአዋልድ መጻሕፍት ቢፈልጉ ይሻላል፡፡

ማስረጃ ይሆነኛል ብለው የጠቀሱት ቃል የሚናገረው፥ ሙሴ በሰበራቸው ሁለት ጽላቶች ምትክ እንደ ፊተኞቹ ያሉ ሌሎች ሁለት ጽላቶች መተካታቸውን ነው፤ በአገራችን እንደሚደረገው ጽላቶች እንዲባዙ መፈቀዱን ፈጽሞ አያመለክትም፡፡[1] እርስዎ እንዳሉት ቢሆን ኖሮ እነሙሴ በእስራኤል አውራጃዎች ሁሉ ብዙ አብያተ መቅደስን ባነጹ፥ በርካታ ጽላቶችንም በቀረጹ ነበር፡፡ በእስራኤል ታሪክ ግን እንዲህ አልተደረገም፡፡ የነበራቸው አንድ ቤተ መቅደስና በአንድ ታቦት ውስጥ የተቀመጡ ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ብቻ ናቸው፡፡

መምህር፥ ርግጥ ያልተጻፈውን አብራርተው ሙሴ ፎርሙላና መመሪያ ተሰጠው በሚለው የሐሰት ማብራሪያ የተንደረደሩት፥  የኢትዮጵያን ታቦታት የሚቀርጹትን ሰዎች በሙሴ እግር የተተኩ ናቸው ለማለት እንደ ሆነ ግልጽ አድርገዋል፤ እንዲህ በማለት፥ ስለዚህ [በ]ቤተ ክርስቲያናችንም በሙሴ እግር የተተኩ ብፁዓን አባቶች፥ እግዚአብሔር በእንዲህ ዐይነት መንገድ ሥሩ ባላቸው መሠረት፥ ጽላት እየቀረጹ፥ እግዚአብሔር ባዘዘው መመሪያ መሠረት ይህን እየሠሩ፥ በቤተ ክርስቲያን፣ በመቅደሱ፣ በመንበሩ ማስቀመጣቸው ስሕተት ሳይሆን ትክክል ነው፡፡ የሚገርም ሌላ ውሸት ነው!!

በዚህ ገለጻዎ ውስጥ አንድም እውነት የለም፡፡ ነገር ግን ቢያንስ ሦስት ውሸቶችን ነቅሶ ማውጣት ይቻላል፡፡
1.  ሙሴንና የቤተ ክርስቲያናችንን ጳጳሳት የሚያገናኛቸውና የሚያተካካቸው ምንም ምክንያት የለም፡፡ ሙሴ በብሉይ ኪዳን የእስራኤል መሪ፥ ብፁዓን አባቶች ደግሞ በሐዲስ ኪዳን የቤተ ክርስቲያናችን መሪዎች ናቸው፡፡ በሙሴ እግር የተተኩት ከኢያሱ ጀምሮ ያሉ በእስራኤል ላይ የተሾሙ መሳፍንት፣ ነቢያትና ነገሥት ናቸው እንጂ በኢኦተቤክ ላይ የተሾሙ ጳጳሳት አይደሉም፡፡ ብፁዓን አባቶችም ቢሆኑ ራሳቸውን በሐዋርያት እግር እንደ ተተኩ እንጂ የሙሴ ምትክ እንደ ሆኑ አይቈጥሩም፡፡ ስለዚህ በሙሴ እግር ተተኩ የሚለው አያስኬድም፡፡

2. ብፁዓን አባቶች ጽላት እንዲቀርጹ እግዚአብሔር አዘዛቸው የሚለውም ምንጭ አልባ የሐሰት ምስክርነት ነው፡፡ ሙሴ በሰበራቸው ሁለት ጽላቶች ምትክ እንደ ፊተኞቹ አድርጎ ሁለት ጽላቶችን ብቻ እንዲቀርጽ እግዚአብሔር ለአንዴም ለመጨረሻ ጊዜም ያዘዘው ሙሴን ብቻ ነው፡፡ ከእርሱ በኋላ ጽላት የሚጠረብበት ምክንያት ስለሌለም ጽላት እንዲጠርብ የታዘዘ፥ እንኳ ኢትዮጵያዊ እስራኤላዊም የለም፡፡ ስለዚህ የኢትዮጵያ ታቦታት/ጽላት እንዲቀረጹ እግዚአብሔር አዘዘ ብሎ ያልተጻፈ ከማንበብና ሕዝብን ከማሳሳት ይልቅ፥ የቤተ ክርስቲያናችን አባቶች አዘዙ፤ በፍትሐ ነገሥት ጽላት እንዲቀረጽ ደነገጉ[2] ቢባል ሊያስኬድ ይችላል፡፡

3. ጽላት የሚቀርጹት ብፁዓን አባቶች ናቸው መባሉም ፍጹም ሐሰት ነው፡፡ ፍትሐ ነገሥት ከቦታ ወደ ቦታ ለማንቀሳቀስ በሚቻል መልኩ ጽላት እንዲቀረጽ ደንግጓል፡፡ ከዚህ ውጪ ስለሚቀርጹት ሰዎች ማንነት ያለው ነገር የለም፡፡ ርግጥ ሲቀርጹ አልሰማንም፥ አላየንም እንጂ፥ የቅርጻ ቅርጽ ሙያ ያላቸው ጳጳሳት ካሉ ጽላት ሊቀርጹ ይችላሉ፡፡ በመሆኑም የኢትዮጵያ ታቦታት/ጽላት የሚቀረጹት የቤተ ክህነት ትምህርትና የቅርጻ ቅርጽ ሙያ ባላቸው የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ነው፡፡ ከዚህ በቀር ጽላትን ለመቅረጽ የሚያስችል ሌላ መስፈርት ያለ አይመስልም፡፡ እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ጽላት የሚቀረጸው በጳጳሳት ነው ማለት ለምን አስፈለገ? ያው እንደ ተለመደው ሕዝቡ ታቦታቱን አቃልሎ እንዳይመለከታቸውና የተለየ ክብርና አምልኮ እንዲሰጣቸው ለማድረግ አይደለምን? ለነገሩ ጳጳስም ይቅረጸው ሌላ እግዚአብሔር ያላዘዘው በመሆኑ የሚያመጣው ለውጥ አይኖርም፡፡

ነገር ግን እርስዎ ያሉት ሁሉ ይሁንና፥ ብፁዓን አበው እንደ ሙሴ ጽላቱን ጠረቡ እንበል፤ ግን በእነዚህ ሁሉ ጽላቶች ላይ ማን ጻፈባቸው? ስለ ቃል ኪዳኑ ታቦት የተነገረውን ሁሉ ለኢትዮጵያ ታቦታት ሰጥተው እንዳስተማሩት፥ እግዚአብሔር ነው የጻፈው ማለት እንኳ ሊነገር የማይታሰብ ነው፡፡ ዛሬ የሰማዎ ሁሉ የተቀበለዎ እንዳይመስልዎ፤ ያጨበጨበልዎ ምእመን ነገ እያነበበና እየተረዳ ሲመጣ፥ እርስዎንም ኢመጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርትዎንም መተዉ አይቀርም፡፡ የባሰው ግን ሕዝብን ከእግዚአብሔር መንገድ ማስወጣት በእግዚአብሔር ፊት የሚያመጣው ጽኑ ፍርድ ነው፡፡   

መምህር፥ ከፍ ብሎ የተጠቀሰውና በተጨባጩ እውነት የፈረሰውን የሐሰት ምስክርነትዎን ብርድ እንዳይመታው ሠግተው ነው መሰል፥ መምህር ዘበነ የተናገሩት ብለው በጠቀሱት ማስረጃ ለመሸፈን ሞክረዋል፡፡ የጠቀሱትና ውስጤ አለ እስካሁን ያሉት የመምህር ዘበነ ምሳሌ በእርስዎ አገላለጽ እንዲህ የሚል ነው፤

በመጀመሪያ ስንት መጽሐፍ ቅዱስ ነበር? ... አንድ አይደል! ... አስፈላጊ ስለ ሆነ በክርስቲያኖች ሁሉ እጅ እንዲገኝ፥ ተባዝቶ እንዲገኝ ተደረገ፡፡ እንደዚሁም አንዱ የቃል ኪዳን ታቦት፥ ታቦተ ሕጉ አስፈላጊ ስለ ሆነ፥ ካህናት፣ ምእመናን፣ አባቶች፣ አማንያን ባሉበት ቦታ፥ በገዳማትና በአድባራት ሁሉ እየተቀረጸ እንዲቀመጥ በመደረጉ ትክክል ነው፡፡

እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ሁሉ ታቦታትም እየተባዙ በየግለ ሰቡ ቤት ሁሉ ሊቀመጡ ይገባል አለ ማለትዎ መልካም ነው፡፡

አንዱ መጽሐፍ ቅዱስ እየተባዛ በሰዎች እጅ ውስጥ እንዲገባ መደረጉ አስፈላጊና ተገቢ የሆነ ቅዱስ ተግባር ነው፡፡ ቃሉ ለሰው የተሰጠበት ዐቢይ ምክንያት፥ ሰው አንብቦት እውነትን እንዲያውቅና ወደ ዘላለም ሕይወት ለመግባት እንዲዘጋጅ ለማድረግ ነውና፡፡ የቃል ኪዳኑ ታቦት ግን መጀመሪያውኑ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ያለ ተግባር ለመፈጸም የተሰጠ አይደለም፡፡ ስለዚህ እንዲባዛም ሆነ በኢየሩሳሌም ባለው ቤተ መቅደስ ቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ ካልሆነ በቀር፥ በተለያዩ ስፍራዎች እንዲቀመጥ አልታዘዘም፡፡ የኢትዮጵያው ዝርግ ሰሌዳ ግን ከመጽሐፍ ቅዱስ መባዛት ጋር መነጻጸር ሳያስፈልገው፥ ለሥጋ ወደሙ መክበሪያ በሆነው አገልግሎቱ ብቻ በየቤተ ክርስቲያኑ መገኘቱ በራሱ ስሕተት የለውም፡፡ ታቦት ተብሎ መጠራቱና እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ሊባዛ ይችላል መባሉ ነው ስሕተት የሚሆነው፡፡ ታዲያስ መምህር፥ አሁንም አልተሳሳትሁም እያሉ ነው?[1] ስለዚህ ጕዳይ ይበልጥ ለመገንዘብ «የተቀበረ መክሊት» የተሰኘውን መጽሐፍ ገጽ 106 ላይ ያለውን ይመልከቱ፡፡
[2] ፍትሐ ነገሥት (1990 21)፡፡

39 comments:

 1. ooooooooooohhhhhhhhhhhhhoooooooooo endihe new ende!!!! aye mihereteab sew meselehene nebre. aferkubehe.

  ReplyDelete
  Replies
  1. አትሳሳቱ በትሞና አስተዉሉ የኣሪቱ ታሪክ ለአዲስ ኪዳ ን ምሳሌ ነዉ ባችሩ እሰራኤላዉያን ለአዲስኪዳን አማኞች ምሳሌ ናቸዉ ስለዚህ ለእነሱ የታዘዙትሁሉ ለአዲስኪዳን ለድህነት ምሳሌ ዉን በአማናዊነት እንተቀምበታለን እስራኤላዉያን ለአዲስኪዳን አማኞችምሳሌ እንደሆኑ ሁሉ ያለጥርትር(ያለመናፍቃን ሀሳብ) የ ፖለቲካ መሪ ሳይኖራቸዉ ሙሴ መንፈሳዊ መሪ አባታቸዉ ነበር ሰለዚህ መ ንፈሳዊ መሪ ብጹአን አባቶች የሙሴ ምሳሌ ናቸዉ አሁንም ያለ ትቢት(ያለመናፍቅን ልብ)

   Delete
 2. አግዛቸው ጎበዝ ጸሀፊ ነው፡፡ ብዙዎቹ መጽሀፍት እጅግ ጠቃሚ ናቸው፡፡ በተለይ የተቀበረ መክሊት የእውነትን መንገድ ያሳወቀን ነው፡፡ ይህንን መጽሀፉን እንዴት ማግኘት ይቻላል፡፡ መሸጫ ቦታውን ብትጠቁሙን ጥሩ ነው፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. you can download the book from good-amharic-books.com

   Delete
 3. aye filfilu seygbahe bhezebu lay tekeldaleh

  ReplyDelete
 4. mihereteab defar mehayem new. yesew dinkurena bemin yeleka teblo biteyeke bemihereteab yiml melse yigegal. defar mehayem new. yemayawekewn new yimizelabedew.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Christian bithon noro ke mesadeb titselylet neber.yezih tsuf akerarebim bedenb bitastewulew ena tikikilegna astesaseb bityiz noro (biased bathon noro) sihitet alneberewum endeyewum ye mihireteabin hasb yidegfal.bemenekakef mengiste semay agigebam befikr enji!!!

   Delete
 5. ይድረስ በቅንነት እግዚአብሔርን ፍለጋ ለምትንከራተተው የዋህ ወገኔ በሙሉ!!!

  1)እግዚአብሔር መንፈስ ነው የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል(የሐ4:24)
  2)የተቀረጸውን ምስል የሚሠሩ ሁሉ ከንቱዎች ናቸው (ኢሳ44:9)
  3)አምላክን የሠራ ወይስ ለምንም የማይረባ ምስልን የቀረጸ ማነው (ኢሳ44:10)
  4)የተቀረጸውን የምስላቸውን እንጨት የሚሸከሙና ያድን ዘንድ ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ እውቀት
  የላቸውም (ኢሳ45:20)
  5)እግዚአብሔር ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ በልባቸውም እጽፈዋለሁ(ኤርሚ31:33)
  6)እናንተም በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በቀለም አይደለም ሥጋ በሆነ በልብ ጽላት እንጂ
  በድንጋይ ጽላት ያልተጻፈ---(2ቆሮ3:3)

  በማለት እግዚአብሔር በማይሻር ቃሉ ስለተናገረን ለቁራሽ እንጀራ ብለው ስተው ከሚያስቱን አስመሳይ አገልጋዮች እንጠንቀቅ:: ደግሞም የሚወደን አምላካችን:

  ልጆችሽ ሁሉ ከእግዚአብሔር የተማሩ ይሆናሉ የልጆችሽም ሰላም ብዙ ይሆናል (ኢሳ54:13)ስለሚል
  በእግዚአብሔር መንፈስ የተላኩትንና እንደቃሉ ብቻ የሚያስተምሩትን አስተማሪዎች ካልሆነ በስተቀር በስሜታችን አስታከው (ጌታ እንደራበው አውቆ ይህን ድንጋይ ዳቦ አድረገው በማለት ቃሉን እንደጠቀሰው ሰይጣን) በእግዚአብሔር ቃል አስታከው መርዝ የሚረጩትን በሥራቸውና በሕይወት ፍሬያቸው እየመዘን ለሕይወታችን የሚጠቅመንን እንያዝ እንጂ ሁሉን አናግበስብስ????

  ከዚህ በተረፈ ለክብሩ የፈጠረንና ከሃጢአታችን በልጁ ደም አጥቦ በማንጻት ከራሱ ጋር ያስታረቀን ርህሩህ አምላካችን ለተኩላ አሳልፎ ስለማይሰጠን አጥብቀን በጸሎት እንድንማጸነው በጌታ ፍቅር ለምወዳችሁ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ወገኖቼ አጥብቄ እያሳሰብኩ:

  ሀ) ጽላት በብሉይ ኪዳን ዘመን 10ቱ ትእዛዛት በራሱ በእግዚአብሔር ጣት ብቻ የተጻፉባቸው ሁለት ድንጋዮች እንጂ በሰው (በሙሴ) ያልተጻፉ መሆናቸውን (ዘጽ31:18)

  ለ) እነዚህን ድንጋዮች ልይ ድንጋይ ያደረጋቸው የአምላካችን ቃሎች እንጂ ሌላ አለመሆኑን

  ሐ) ጽላት በአዲስ ኪዳን ግን ልባችን እንደሆነ (2ቆሮ3:3)
  በአፍህ በልብህም ሆኖ ቃሉ ቀርቦልሃል (ሮሜ10:8; ዘዳ30:12-14)
  የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ይኑርባችሁ (ቆላ3:16)
  በመዝሙርና በዝማሬ በመንፋሳዊም ቅኔ እርስ በእርሳችሁ
  ተነጋገሩ ለጌታ በልባችሁ ተቀኙና ዘምሩ (ኤፌ5:19)
  ወዘተ....

  በሚለው የእግዚአብሔር ቃል እየመዘንና ስንዴውን ከገለባ በመለየት ንጹህ ቃሉን በፍጹም ትህትና በመንፈስ ቅዱስ መልካም መጋቢነት እንብላ እንጂ አሰስ ገሰሱ እንኳን መንግሥተ ሰማይ ሊያደርስ ይቅርና ወንዝ የማያሻግር የእነ እለት እንጀራቸው ሰባኪዎችን/አስተማሪዎችን ቅጥ ያጣ ውጥንቅት ለይተን እናስወግድ እላለሁ::

  በመጨረሻም ይህን ከዚህ በታች ያለውን የጌታ ቃል በጥሞና እናጥናው:

  ዳሩ ግን የእስራኤል ልጆች ስለዚያ ስለ ተሻረው ስለ ፊቱ ክብር የሙሴን ፊት ትኩር ብለው መመልከት እስኪሳናቸው ድረስ ያ በፊደላት በድንጋዮች ላይ የተጻፈ የሞት አገልግሎት በክብር ከሆነ የመንፈስ አገልግሎት እንዴት ይልቅ በክብር አይሆንም? የኩነኔ አገልግሎት ክብር ከሆነ ይልቅ የጽድቅ አገልግሎት በክብር አብዝቶ ይበልጣልና:: ያ የከበረ እንኳ እጅግ በሚበልጠው ክብር ምክንያት በዚህ ነገር ክብሩን አጥቶአልና:: ያ ይሻር የነበረው በክብር ከሆነ ጸንቶ የሚኖረውማ እጅግ ይልቅ በክብር ሆኖአልና(2ቆሮ3:7-11)

  ጌታ በእውነትና በመንፈሱ ለመንግሥቱ ያብቃን

  ሰላም ሁኑልኝ

  በጌታ እህታችሁ

  ሰላም ነኝ

  ReplyDelete
 6. TIGERS ARE COMING. PLEASE GO AHEAD AND CHANGE THIS ROTTEN SYSTEM OF DEBTERAS .I AM PROUD OF U PEOPLE .

  ReplyDelete
 7. ሠይፈ ገብርኤልFebruary 12, 2012 at 12:27 PM

  ስለ መጽሐፉ ፡- ጉዳያችሁን ከቀለም አዋቂዎች ልታቆላልፉት የፈለጋችሁት ይመስለኛል ፤ ቢሆንም አንድ ነገር ልበል፤
  አንድ ብዙ ገጽ የያዘን ትልቅ መጽሐፍ በአንድ ገጽ ገለጻው ለመኰነንም ሆነ ጠቅላላ መልዕክት ለመረዳት ያስቸግረኛል ፡፡ ይኸ ችግር በመጽሐፍ ቅዱስ አጠቃቀም ላይ የለመድነው ይመስላል ፡፡ ከአንድ ምዕራፍ አንድ ኃይለ ቃል መዝዘን እሱን ተርጉመን ድምዳሜ ላይ የመድረስ አባዜ እንደ ሆነ ሁሉ ፤ እኔ በግል ስላጠቃላዩ ምንም ማለት አልችልም ፡፡ ከቀረበልን እንደተረዳሁት ግን ልዩነት እንዳለን አውቄአለሁ ፡፡ ነገር ግን ይህን የልዩነት ጥያቄ መጠቆምና ማሳወቅ ፣ እንዲሻሻልም መጠየቅ የሚገባው ፣ እንደ አሠራር ቤተ ክርስቲያናችንን የሚመሩትን ሲኖዶሱንና ፓትሪያርኩን ነው እንጅ ምእመኑን አይደለም ፡፡ ከዚህ ሥርዓት ውጭ ፣ ደንብን ያልተከተለ አካሄድ ግን የገንዘብ መለቃቀሚያ ስልት ፣ አለበለዚያም በቤተ ክርስቲያን ላይ ሽምቅ ውጊያ መክፈት ይመስለኛል ፡፡ ይኸ ጐርዶ የማውጣት ችግር ሊፈጥር የሚችለውን እንድትረዱና ለወደፊት ብታስተካክሉ የሚከተለውን አገላለጽ ተመልከቱ ፡፡
  “ሮሜ 16 ፡ 22 ይህን መልእክት የጻፍሁ እኔ ጤርጥዮስ በጌታ ሰላምታ አቀርብላችኋለሁ።” እንደ እናንተ አሠራር የዚህን የሮሜ መልዕክት ባለቤት ማን ነው እንላለን ?

  ዘፀዓት 25
  8፤ በመካከላቸውም አድር ዘንድ መቅደስ ይሥሩልኝ።
  9፤ እኔ እንደማሳይህ ሁሉ፥ እንደ ማደሪያው ምሳሌ እንደ ዕቃውም ሁሉ ምሳሌ፥ እንዲሁ ሥሩት።
  10፤ ከግራር እንጨትም ታቦትን ይሥሩ፤
  በሁሉም ለብዙ መናገሩን ተመልከቱት ፡፡ አራት መቶ ሺህ በእግዚአብሔር የሚታመን ህዝብ እንዲሠራ ተፈቅዶለታል ፤ ለእነርሱ በአንድ ስለሚኖሩ የሚያስፈልጋቸው አንድ ስለነበረ በዛ ተወስነዋል ፡፡ የህዝብ ቁጥር እየበዛ ሲሄድ ደግሞ የሚያደርጉትን መገመት አያስቸግረንም ፡፡

  ስለ ሐዋርያው ጳውሎስ እምነት ትምህርት ፡-
  የሐዋርያው መልዕክቶች የተጻፉት /በእርግጥ የሰው ደብዳቤ አንብቦ ለመረዳት አስቸጋሪ መሆኑን ብረዳም/ የተፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት ነው ፡፡ እምነት በጐደለበት እምነት እንዲጠነክር ፣ በእምነት ሰለመዳን ያስተምራል ፤ ምግባር በተበላሸበት ምግባር እንዲስተካከል ይመክራል ፤ ጸብና ክርክር ባለበት ሰላም የሚፈጠርበትን መንገድና ስልት በመለየት ያሳያል ፤ እጅግ መላ ለማያገኝለትና መቋጫ የሌለው ችግር ደግሞ ሌላ መፍትሔ ይሰጣል፡፡ በህግ መዳን አይጠቅምም ያለው አስተማሪ ለህግ ተገዥነቱን በተግባር እንደኖረው ብዙ ጊዜ መስክሯል ፡፡ ዛሬ ያ የጥንቱ ብርሃነ ዓለም ጳውሎስ ቢኖር ኖሮ ፣ እኛም እንዲህ ስንከራከር አንከርምም ነበር ብዬ እገምታለሁ፡፡ ለማንኛውም ሥራዎቹንና ህይወቱን ለመመዘን በጥቂቱ

  የሐዋርያት ሥራ
  21 ፡ 23 እንግዲህ ይህን የምንልህን አድርግ፤ ስለት ያለባቸው አራት ሰዎች በእኛ ዘንድ አሉ።
  21 ፡ 24 እነዚህንም ይዘህ ከእነርሱ ጋር ንጻ፥ ራሳቸውንም እንዲላጩ ገንዘብ ክፈልላቸው፤ ሁሉም ስለ አንተ የተማሩት ከንቱ እንደ ሆነና አንተ ራስህ ደግሞ ሕጉን እየጠበቅህ በሥርዓት እንድትመላለስ ያውቃሉ።
  24 ፡ 14 ነገር ግን ይህን እመሰክርልሃለሁ፤ በሕጉ ያለውን በነቢያትም የተጻፉትን ሁሉ አምኜ የአባቶቼን አምላክ እነርሱ ኑፋቄ ብለው እንደሚጠሩት መንገድ አመልካለሁ፤
  24 ፡ 16 ስለዚህ እኔ ደግሞ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ሁልጊዜ ነውር የሌለባት ሕሊና ትኖረኝ ዘንድ እተጋለሁ።
  24 ፡ 17 ከብዙ ዓመትም በኋላ ለሕዝቤ ምጽዋትና መሥዋዕት አደርግ ዘንድ መጣሁ፤
  24 ፡ 18 ይህንም ሳደርግ ሳለሁ ሕዝብ ሳይሰበሰብ ሁከትም ሳይሆን በመቅደስ ስነጻ አገኙኝ።
  በጳውሎስ ትምህርት መንጻት አለመንጻት ፣ በህግ መኖር አለመኖር ምን ሥፍራ አለውና በመቅደስ ሲነጻ ይገኛል ?

  ወደ ገላትያ 2 ፡ 16 – 17 ነገር ግን ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንዲጸድቅ እንጂ በሕግ ሥራ እንዳይሆን አውቀን፥ ሥጋን የለበሰ ሁሉ በሕግ ሥራ ስለማይጸድቅ፥ እኛ ራሳችን በሕግ ሥራ ሳይሆን በክርስቶስ እምነት እንጸድቅ ዘንድ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነናል። ነገር ግን በክርስቶስ ልንጸድቅ የምንፈልግ ስንሆን ራሳችን ደግሞ ኃጢአተኞች ሆነን ከተገኘን፥ እንግዲያስ ክርስቶስ የኃጢአት አገልጋይ ነዋ? አይደለም።

  ወደ ገላትያ 3 ፡ 11 – 12 ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎአልና ማንም በእግዚአብሔር ፊት በሕግ እንዳይጸድቅ ግልጥ ነው። ሕግም ከእምነት አይደለም ነገር ግን። የሚያደርገው ይኖርበታል ተብሎአል።

  ወደ ገላትያ 5 ፡ 1 – 5 በነጻነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻነት አወጣን፤ እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ እንደ ገናም በባርነት ቀንበር አትያዙ። እነሆ፥ እኔ ጳውሎስ እላችኋለሁ። ብትገረዙ ክርስቶስ ምንም አይጠቅማችሁም። ሕግንም ሁሉ እንዲፈጽም ግድ አለበት ብዬ ለሚገረዙት ሁሉ ለእያንዳንዶች ደግሜ እመሰክራለሁ። በሕግ ልትጸድቁ የምትፈልጉ ከክርስቶስ ተለይታችሁ ከጸጋው ወድቃችኋል። እኛ በመንፈስ ከእምነት የጽድቅን ተስፋ እንጠባበቃለንና።

  ለገላትያ ሰዎች ደግሞ በእምነት መጠንከር ስለሚገባቸው ፣ እንደዚሁ የተገለጸውን አስተምሯል ፡፡
  ይቀጥላል

  ReplyDelete
 8. ሠይፈ ገብርኤልFebruary 12, 2012 at 12:29 PM

  1 ቆሮንቶስ ሰዎች ፡ 9
  20 አይሁድንም እጠቅም ዘንድ ከአይሁድ ጋር እንደ አይሁዳዊ ሆንሁ፤ ከሕግ በታች ያሉትን እጠቅም ዘንድ፥ እኔ ራሴ ከሕግ በታች ሳልሆን፥ ከሕግ በታች ላሉት ከሕግ በታች እንዳለሁ ሆንሁ፤
  21 ሕግ የሌላቸውን እጠቅም ዘንድ፥ ያለ እግዚአብሔር ህግ ሳልኖር ነገር ግን በክርስቶስ ሕግ በታች ሳለሁ፥ ሕግ ለሌላቸው ሕግ እንደ ሌለኝ ሆንሁ፤
  22 ደካሞችን እጠቅም ዘንድ ለደካሞች እንደ ደካማ ሆንሁ፤ በሁሉ መንገድ አንዳንዶችን አድን ዘንድ፥ ከሁሉ ጋር በሁሉ ነገር እንደ እነርሱ ሆንሁ።
  23 በወንጌልም ማኅበረተኛ እሆን ዘንድ ስለ ወንጌል ሁሉን አደርጋለሁ።

  ለቆሮንቶስ ሰዎች ደግሞ ህግን መፈጸም ሲያስፈልግ ከህግ በታች እንደሆነ ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ሌላ ዓይነት ሰው መሆኑን እራሱ ይናገራል ፡፡ ይህን ለምን አደረገው ? እምነት ስለጐደለው አይደለም ፡፡ ነገር ግን ማስተማር ስላለበት እንዲህ ሆነ እላለሁ፡፡

  በተረፈ - ይህን የሃሳብ ልዩነት የዘራው ሰው ተልእኮውንና ሽፍን ሴራውን አላውቅም ፤ በአንድ ታቦት መኖር ከተማመንን ፣ እሱ ይበቃናልና በተስማማችሁበት አክሱም ጽዮን ስለሚገኝ እየሄዳችሁ በዛ ስገዱ ፤ ቢያንስ ከኢየሩሳሌም ይቀርበናል፡፡ አንድነትም ይኖረናል ፡፡ የተቀረው ደግሞ በሚያምንበት ባቅራቢያው ይጸልይ ፡፡

  በተሰጡት አስተያየቶች ላይ አንዳንድ ግንዛቤዎቼን ለማስረዳት ከዚህ የሚከተለውን እላለሁ ፡፡
  ስለ መጽሐፍ ለሚጠይቀን በአርአያ ስላሴ የተፈጠረ ሰው ከመጽሐፍ ለመመለስ መሞከር እንጅ ፣ ጠያቂውን ሰይጣን ተጠያቂውን ደግሞ ከኢየሱስ ጋር ማስተካከል የተዛባ ፍርድ ፣ እንዲሁም የድክመታችን ምልክት ነው ፡፡ እግዚአብሔር እንደ ፈቀደልን መጠን ለማስረዳት ፣ ለማስተማርና ለመመለስ ብንተጋ የጠፉ ነፍሳትን እናድናለን በሚል ተስፋ ይህን እናገራለሁ፡፡

  - የኢሳይያስ ትንቢቶች የተጻፉት እስሥራኤል ከሁለት ወገን ተከፍላ በነበረበት ፣ የሰሜኑ በጣዖት የደቡቡ የይሁዳ ግዛት ደግሞ የአይሁድ ኦርቶዶክስ ተከታይ ማለትም ለእግዚአብሔር አምልኮ በሚያደርጉ በመሆኑ ፣ ኢያሱ ስለ ሰሜነኞቹ ጣዖት አምላኪዎቹ ትንቢትን ተናገረባቸው ፡፡ ያንንም ሲገልጸው በ45 ፡ 2ዐ ላይ ያድን ዘንድ ወደ ማይችል አምላክ ብሎ ይገልጸዋል ፡፡ ታቦትን ብንይዝም እኛ የምናምነው የሚያድነውን እግዚአብሔርን ነው ፤ ይህን ጥቅስ ከታቦት ጋር ለማቆላለፍ መሞከር ከእግዚአብሔር ሥራና ችሎታ ጋር የምንገዳደር ፣ አሠራሩንም ያልተቀበልነው ይመስለኛል ፡፡

  በትርጓሜ ሥራ የሰለጠንኩ አይደለሁም ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር እንድረዳው በፈቀደ መጠን የሚከተለውንም እላለሁ፡-
  ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ ማለት ኢየሱስን እንደ አዳኝ ጌታ ካመንን በኋላ ፣ በምግባራችን ፣ በኑሮአችን ፣ በንግግራችን እሱን ስለምንመስልና የቅድስና ኑሮን በመለማመድ ስንጓዝ ፣ በጽላት ላይ ተጽፈው የነበሩትን ህግጋት በተግባር ስለምንኖረው ፣ በልባችን ላይ ተጻፈ ያሰኛል እንጅ የኛ ልብ ወደ ጽላትነት ይቀየራል ማለት አይደለም ፡፡ እኛ በእምነት ልምምድ እሱን መምሰል ስንጀምር የኛን መለወጥ ማብሰሩ ነው ፡፡ የጽላቶቹ ህጐችማ አልተለወጡም ፤ ነገር ግን ምግባርን አስተካክሎ በመፈጸም ይደረግ የነበረው ፣ በኢየሱስ በማመን ብቻ በመቀየሩ ከፊተኛው የህግ ሥርዓት ተሻለ እንላለን ፡፡

  በፊደላት በድንጋዮች ላይ የተጻፈ የሞት አገልግሎት የሚባልበት ምክንያት ፣ ህጉ በተግባር ሲተረጐም ያጠፋውን ግለሰብ ከመቅጽበት እንዲቀጣ ስለሚያስገድድና ሞትን ስለሚያስከትል ነው ፤ ያመነዘረ እንደሚገደለው ማለት ፡፡ በዚህኛው የወንጌል ትምህርት ግን ህጉ ጠብቋል ፤ ያመነዘረ ብቻ አይደለም ፣ ወደ ሴት ያየና የተመኘ ሁሉ አመነዘረ ብሎ ይተረጉመዋል ፡፡ ነገር ግን ወደ ፍርድ ሂደቱ ስንሄድ ፣ ተወግሮ ይገደል አይልም ፤ በተጻራሪው የንስሃ ዘመንን ያድለዋል ፡፡ ህጉ ተሻረ ከተባለማ ሃይማኖት የለችም ፡፡ ህጉ አለ ፣ ነገር ግን እንድንድንበት ዘንድ የተሻሻለልን መንገድ በኢየሱስ ማመንን ተመደበልን እንላለን ፡፡

  ስለ ተሻረው ስለ ፊቱ ክብር የሙሴን ፊት የሚለውም ሙሴ ሲሞት ስለቀረው ያንጸባርቅ ስለነበረው ስለ ሙሴ ፊት እያስታወሰን ነው ፡፡ የኩነኔ አገልግሎት ክብር የተባለው የመስዋዕቱንና የደም መርጨቱን ሥርዓትና አገልግሎት ነው እንጅ ከታቦት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም ፡፡ የትርጓሜ ሊቃውንቱን ብንጠይቅ ብዙ ልንማር ፣ ከፈቀድነው ደግሞ ገንዘባችን ማድረግ የምንችለው ትምህርት አለ ፡፡

  ይቀጥላል

  ReplyDelete
 9. ሠይፈ ገብርኤልFebruary 12, 2012 at 12:33 PM

  መልዕክቴን የምቋጨው በጳውሎስ ወደ ሮሜ ሰዎች መልዕክት ነው ፡- ስለምግብ ቢመስለንም እንዲህ ይላል
  14 ፡ 1 – 3 በእምነት የደከመውንም ተቀበሉት፥ በአሳቡም ላይ አትፍረዱ። ሁሉን ይበላ ዘንድ እንደ ተፈቀደለት የሚያምን አለ፥ ደካማው ግን አትክልት ይበላል። የሚበላ የማይበላውን አይናቀው የማይበላውም በሚበላው አይፍረድ፥ እግዚአብሔር ተቀብሎታልና።

  14 ፡ 4 አንተ በሌላው ሎሌ የምትፈርድ ማን ነህ? እርሱ ቢቆም ወይም ቢወድቅ ለገዛ ጌታው ነው፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ሊያቆመው ይችላልና ይቆማል።
  14 ፡10 አንተም በወንድምህ ላይ ስለ ምን ትፈርዳለህ? ወይስ አንተ ደግሞ ወንድምህን ስለ ምን ትንቃለህ? ሁላችን በክርስቶስ ፍርድ ወንበር ፊት እንቆማለንና።
  14 ፡ 12 እንግዲያስ እያንዳንዳችን ስለ ራሳችን ለእግዚአብሔር መልስ እንሰጣለን።
  14 ፡ 13 እንግዲህ ከዛሬ ጀምሮ እርስ በርሳችን አንፈራረድ፤ ይልቁን ግን ለወንድም እንቅፋትን ወይም ማሰናከያን ማንም እንዳያኖርበት ይህን ቍረጡ።
  14 ፡ 22 ለአንተ ያለህ እምነት በእግዚአብሔር ፊት ለራስህ ይሁንልህ። ፈትኖ መልካም እንዲሆን በሚቈጥረው ነገር በራሱ ላይ የማይፈርድ ብፁዕ ነው።

  እኔን ተከተሉኝ ፣ እኔ የምለውንም ተቀበሉ ለማለት ቢያንስ በትንሹ እንደ ዮሐንስ መሆንን ፣ እንደጥንት አባቶቻችንም በእፍኝ ባቄላና በአንድ ኩባያ ውሃ ተመጥኖ መኖርን ፣ ከብዙው ስጋዊው ፈቃድ መወሰንን ይጠይቃል ፤ እንደ ሐዋርያቱም ሁሉ ራስን ክዶ የጌታ ገንዘብ መሆንን ይፈልጋል ማለቴም ኋላ ምን እንደሚበሉ ፣ ምን እንደሚጠጡ ፣ የት እንደሚተኙ ፣ ምን እንደሚለብሱ ፣ ምን እንደሚያተርፉ አለማሰብን ማለትም ለምድራዊው የሥጋ ፍላጎታችን አለማደርንና አለመጨነቅን ይጠይቃል ፡፡

  አንድ አባት ሲያስተምሩን አሁን እንደምለው ብዙ ደፍረን እያለፍን የሆነ ያልሆነውን በፍልስፍና ስንጠይቃቸው የሰጡን መልስ “መዳን እኛ አሁን የምንገጋረውን ሁሉ በመነጋገር /በጥበብና በዕውቀት ብዛት/ ከሆነ /ሁለት ሺህ ዓመታት ሙሉ እግዚአብሔርን በየዋኀነት ያመለኩት/ እናቶቻችንና አባቶቻችን አይድኑም ማለት ነው።” በማለት ነበር ፡፡

  ስለዚህ በጥበብና በዕውቀታችን አንመካ ፣ ሁሉን ለሚያውቅ ፣ ሁሉንም ለሚረዳ ፣ ሁሉን በፈቃዱ ለሚፈጽም ፈጣሪአችን ብንተወው እጅግ ይረዳናል እንጅ ለድክመት አይተወንም ፡፡ እሱንም በማመን እንድናለን ፡፡

  አውቀን በድፍረት ፣ ሳናስተውል በስህተት የምንበድለውን እግዚአብሔር አይቁጠርብን
  ለሁላችሁም የእግዚአብሔር በረከትና ሰላም ይብዛላችሁ

  ReplyDelete
 10. So silly. Neither Agizachew nor Abaselama understands the truth behind EOTC using Tabot. You are not so silly and don't want to know or understand why the church is using Tabot.

  We love Mihreab, Zebene, Daniel, etc who are following Christ and protect the church of God. You guys rather than showing God's way, you are always against the church and its belief.

  "AnonymousFeb 12, 2012 04:20 AM" You are very useless person. Did the church worship icons, tabot or any other thing except God? No me as an EOTC member know what we believe in and what we worship. We trust in God and His son Jesus Christ. We keep our tradition of worshiping. Please understand bible in proper way. In the mean time understand the church in proper way.


  Abaselama, if you are people who are denying the facts in the church how come we accept you to be working for the church?

  Zeegzine the Warka

  ReplyDelete
  Replies
  1. Thanks a lot and may the blessing of God pour on you. This is what we believe. They always try to hide the truth but to be the part of heaven we have to love each other.

   Delete
 11. እኛ ፈጣሪያችንን እንዴት እንደምናመልክ ልትነግሩን መብት የላችሁም ። እናንተ ብትፈልጉ ያለታቦት አምልኩ ፤ ነገር ግን ኦርቶዶክሳውያን ነን አትበሉ ። ይኽ አካሄዳችሁ እኮ እነዚያን የኛ ናቸው የምትሏችህውን መነኮሳት ገጽታ ያበላሽባችኋል ። እናንተንም ኪሳራ ላይ ይጥላችኋል ።
  ታቦት እኮ መጀመሪያ በአንድ አምላክ ለሚያምኑ እሥራኤላውያን ተሰጠ ፤ ከዚያ እኛም ሕገ ኦሪትን ስንቀበል አስፈለገን ፤ ከዚያም የእንስሳት የኦሪት መሥዋዕት በጌታችን ሥጋና ደም ሲለወጥ አዲሱን መሥዋዕት በታቦቱ ላይ መፈተት ያዝን ። የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን በኢየሩሳሌም በማርያም ቤት ተጀመረች ፤ ምእመናን ሲበዙ መሰብሰቢያውም እንደዚያው በዛ።
  በዚህ ዓይነትኮ መጽሐፍ ቅዱስም ከመጀመሪያው ቅጂ በላይ መባዛት የለበትም የምትሉበት ጊዜ ሊመጣ ነው ። እባካችሁን እኛን ለቀቅ አድርጉንና እናመልካለን በምትሉት መንገድ ቦታ ፈልጋችሁ አምልኩ ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. መጽሐፍ ቅዱስ ተባዝቶ እንድናነበው በየቤታችን ተገኝቷል። ጽላትም እንደዚሁ ነው ካልክ ጽላቱንም በየቤታችን አባዝተን እንደመጽሐፍ ቅዱሱ እንያዘው? የጽላቱን መባዛት በመጽሐፍ ቅዱስ መባዛት አስመስለህ መናገርህ ጽላትህን በየቤቱ እንደመጽሐፍ ቅዱስ እንዲሆን መፍቀድህ ስለሆነ አሁን ደግሞ የባሰው መጣ እንልሃለን። የዘበነ ተማሪ አይደለህ? ድሮስ ከዚህ በላይ ምን ይጠበቃል?

   Delete
 12. menafikan hulu yetesebesebebet page new endie? Egziabhe yiker yibelachihu.

  ReplyDelete
 13. የዚህ ዘመን ጽላት ጣዖት ነው የሚባልበት ነጥቦች፣
  1/ የሙሴን ጽላት የጻፈበት እግዚአብሔር በጣቶቹ ሲሆን የዚህንም ዘመን የሰዎች ጽላት የሚጽፍባቸው ማንም ደብተራ ነው!!
  2/ የሙሴ ጽላት የተጻፈባቸው ቃላት 10ቱ ትእዛዛት ብቻ ሲሆን የዚህ ዘመን የሰዎች ጽላት ሁሉን ቀይረው የሚቀረጽባቸው ስእላ ስእልና ልዩ ልዩ አስማት ነው።
  3/ የሙሴ ጽላት ከቅድስተ ቅዱሳኑ ይወጣ የነበረው በማደሪያው ታቦት ውስጥ በ4 ሰዎች ሸክም ነው። የዚህ ዘመን ሰዎች ደግሞ ታቦት የሌለውን ጽላት፣ አንዱ ደብተራ ቄስ እንደመጽሐፍ የሚሸከማት ቀላል እቃ ናት።
  4/ የሙሴ ጽላት 10ቱ ህግጋት የተጻፈበት ስለሆነ የእግዚአብሔር የሕጉ ጽላት ሲባል የዚህ ዘመን ሰዎች ጽላት ደግሞ የአቡነ ገብረ ማርያም፣ የአቡነ ኃይለ ማርያም፣ የእማሆይ ሰብለወንጌል፣ የጻድቁ ዮሐንስ፣ የአባ ዘክርስቶስ ወዘተ ጽላት ተብሎ ይጠራል።
  5/የሙሴ ጽላት በምድረ እስራኤል እግዚኣብሔር የጻፈባቸው 2ጽላቶች ብቻ ለሺህ ዘመናት ሲኖሩ በዚህ ዘመን ሰዎች ጽላት ደግሞ ሰዎች ችሎታቸውን የገለጹባቸው በሺህ ዘመናት ከ40ሺህ በላይ የልዝብ እንጨት ቅርጾች አሉ።
  6/የሙሴ ጽላትም ሆነ ማደሪያው ታቦት የሚቀረጽበት መጠንና ስፋት፣ ህግና ስርዓት በህግ የተቀመጠ ሲሆን የዚህ ዘመን ግን ይህንን ህግ ሽሮ እንዳሻው፣ እንደፈለገው፣ እንደመሰለውና ልቡ እንደተነሳሳለት መጠን፣ስፋት፣ ቅርጽና ውበት የሚሰራው ሲሆን ውበቱን ለመጠበቅ ቫርኒሽ የሚቀባ የእንጨት ዘር ነው።
  ስለዚህ በዚህ ዘመን ዓይን ያወጣ ድርቅናና ለምን ተነክተን ካልተባለ በስተቀር የሙሴ የጽላት ህግ የለም። መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትእዛዛትን የሚከተልም አይደለም። ስለዚህ በስም የሙሴ ጽላት፣ በግብር ግን በውሸት ላይ የተሰራ ሰዎች እየተደፉ የሚሰግዱለት ጣዖት ነው። ካንዱ አድራሻ ተሰርቆ ወደሌላው ተሻግሮ በመሸጥ ሊያገለግል ይችላል። እንደኪራይ ቤት ጣዖቱ በደባልነት ሊኖር ይችላል። ጣዖት ስለሆነ!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. please read from the bible in exodus 34 the whole chapter especially in the verses 27 and 28 you will get the answer,

   Delete
 14. ሠይፈ ገብርኤልFebruary 13, 2012 at 5:54 AM

  መልዕክቴን ስላላወጣችህት ፣ ስላልተረዳችሁት ስለመሰለኝ ይህን በጥቂቱ ያሻሻልኩትን ልኬአለሁ
  ስለ መጽሐፉ ፡- ጉዳያችሁን ከቀለም አዋቂዎችም ማቆራኘት የፈለጋችሁት ይመስለኛል ፤ ቢሆንም አንድ ነገር ልበል፤
  አንድ ብዙ ገጽ የያዘን ትልቅ መጽሐፍ በአንድ ገጽ ገለጻው ለመኰነንም ሆነ ጠቅላላ መልዕክት ለመረዳት ያስቸግረኛል ፡፡ ይኸ ችግር በመጽሐፍ ቅዱስ አጠቃቀም ላይ የለመድነው ይመስላል ፡፡ ከአንድ ምዕራፍ አንድ ኃይለ ቃል መዝዘን እሱን ተርጉመን ድምዳሜ ላይ የመድረስ አባዜ እንደ ሆነ ሁሉ ፤ እኔ በግል ስላጠቃላዩ ምንም ማለት አልችልም ፡፡ ከቀረበልን እንደተረዳሁት ግን ልዩነት እንዳለን አውቄአለሁ ፡፡ በእርግጥ የዲቁና ስሙ ትክክለኛ ማዕረጉ ከሆነ መጽሐፍ ቅዱስ በሚዘረዝረው ደንብ መሠረት አስቀድሞውኑ ወደ አደባባይ ይዞ መውጣት አይገባውም ነበር /1 ጢሞ 3 ፡ 8 – 11/ ፤ ግንዛቤው ጥርጣሬን ከፈጠረበት ይህን የልዩነት ጥያቄ መጠቆምና ማሳወቅ ፣ እንዲሻሻልም መጠየቅ የሚገባው ፣ እንደ አሠራር ቤተ ክርስቲያናችንን የሚመሩትን ሲኖዶሱንና ፓትሪያርኩን ነው እንጅ ምእመኑን አይደለም ፡፡ ከዚህ ሥርዓት ውጭ ፣ ደንብን ያልተከተለ አካሄድ ግን የገንዘብ መለቃቀሚያ ስልት ፣ አለበለዚያም በቤተ ክርስቲያን ላይ ሽምቅ ውጊያ መክፈት ይመስለኛል ፡፡ በተረፈ ግን ጸሃፊው የማባዛትን ሥራ ትክክል አይደለም አለን እንጅ ፣ የታቦትን ግልጋሎትና ሥርዓት እናንት እንደምትሉት አልተቃወመም ፡፡ ይኸ ጐርዶ የማውጣት ችግር ሊፈጥር የሚችለውን እንድትረዱና ለወደፊት ብታስተካክሉ የሚከተለውን አገላለጽ ተመልከቱልኝ ፡፡
  “ሮሜ 16 ፡ 22 ይህን መልእክት የጻፍሁ እኔ ጤርጥዮስ በጌታ ሰላምታ አቀርብላችኋለሁ።” እንደ እናንተ አሠራር የዚህን የሮሜ መልዕክት ባለቤት ማን ነው እንላለን ?

  ዘፀዓት 25
  8፤ በመካከላቸውም አድር ዘንድ መቅደስ ይሥሩልኝ።
  9፤ እኔ እንደማሳይህ ሁሉ፥ እንደ ማደሪያው ምሳሌ እንደ ዕቃውም ሁሉ ምሳሌ፥ እንዲሁ ሥሩት።
  10፤ ከግራር እንጨትም ታቦትን ይሥሩ፤
  በሁሉም ለብዙ መናገሩን ተመልከቱት ፡፡ አራት መቶ ሺህ በእግዚአብሔር የሚታመን ህዝብ እንዲሠራ ተፈቅዶለታል ፤ ለእነርሱ የሚያስፈልጋቸው አንድ ስለነበረ በዛ ተወስነዋል ፡፡ የህዝብ ቁጥር እየበዛ ሲሄድ ደግሞ የሚያደርጉትን መገመት አያስቸግረንም ፡፡

  ስለ ሐዋርያው ጳውሎስ እምነትና ትምህርት /የሚከተለው አርአያነቱን በመከተል መለወጥ ከቻላችሁ በማለት የተዘጋጀ ነው/ ፡-
  የሐዋርያው መልዕክቶች የተጻፉት /በእርግጥ የሰው ደብዳቤ አንብቦ ሙሉ ሃሳቡንና መልዕክቱን ለመረዳት አስቸጋሪ መሆኑን ባውቅም/ የተፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት ነው ፡፡ በብዙው መልክ ለተለያየው ወገኑ እምነት በጐደለበት በእምነት እንዲጠነክር ፣ በእምነት ስለመዳን ያስተምራል ፤ ምግባር በተበላሸበት ምግባር እንዲስተካከል ይመክራል ፤ ጸብና ክርክር ባለበት ሰላም የሚፈጠርበትን መንገድና ስልት በመለየት ያሳያል ፤ እጅግ መላ ለማያገኝለትና መቋጫ ለሌለው ችግር ደግሞ ሌላ መፍትሔ ይሰጣል፡፡ በህግ መዳን አይጠቅምም ያለው አስተማሪ ለህግ ተገዥነቱን በተግባር እንደኖረውም ብዙ ጊዜ መስክሯል ፡፡ ዛሬ ያ የጥንቱ ብርሃነ ዓለም ጳውሎስ ቢኖር ኖሮ ፣ እኛም እንዲህ ስንከራከር አንከርምም ነበር ብዬ እገምታለሁ፡፡
  ይቀጥላል

  ReplyDelete
 15. ሠይፈ ገብርኤልFebruary 13, 2012 at 5:56 AM

  ለማንኛውም ሥራዎቹንና ህይወቱን በወንጌል ከተጻፈው ለመመዘን በጥቂቱ
  የሐዋርያት ሥራ
  21 ፡ 23 እንግዲህ ይህን የምንልህን አድርግ፤ ስለት ያለባቸው አራት ሰዎች በእኛ ዘንድ አሉ።
  21 ፡ 24 እነዚህንም ይዘህ ከእነርሱ ጋር ንጻ፥ ራሳቸውንም እንዲላጩ ገንዘብ ክፈልላቸው፤ ሁሉም ስለ አንተ የተማሩት ከንቱ እንደ ሆነና አንተ ራስህ ደግሞ ሕጉን እየጠበቅህ በሥርዓት እንድትመላለስ ያውቃሉ።
  24 ፡ 14 ነገር ግን ይህን እመሰክርልሃለሁ፤ በሕጉ ያለውን በነቢያትም የተጻፉትን ሁሉ አምኜ የአባቶቼን አምላክ እነርሱ ኑፋቄ ብለው እንደሚጠሩት መንገድ አመልካለሁ፤
  24 ፡ 16 ስለዚህ እኔ ደግሞ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ሁልጊዜ ነውር የሌለባት ሕሊና ትኖረኝ ዘንድ እተጋለሁ።
  24 ፡ 17 ከብዙ ዓመትም በኋላ ለሕዝቤ ምጽዋትና መሥዋዕት አደርግ ዘንድ መጣሁ፤
  24 ፡ 18 ይህንም ሳደርግ ሳለሁ ሕዝብ ሳይሰበሰብ ሁከትም ሳይሆን በመቅደስ ስነጻ አገኙኝ።
  በጳውሎስ ትምህርት መንጻት አለመንጻት ፣ በህግ መኖር አለመኖር ምን ሥፍራ አለውና በመቅደስ ሲነጻ ይገኛል ?

  ወደ ገላትያ 2 ፡ 16 – 17 ነገር ግን ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንዲጸድቅ እንጂ በሕግ ሥራ እንዳይሆን አውቀን፥ ሥጋን የለበሰ ሁሉ በሕግ ሥራ ስለማይጸድቅ፥ እኛ ራሳችን በሕግ ሥራ ሳይሆን በክርስቶስ እምነት እንጸድቅ ዘንድ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነናል። ነገር ግን በክርስቶስ ልንጸድቅ የምንፈልግ ስንሆን ራሳችን ደግሞ ኃጢአተኞች ሆነን ከተገኘን፥ እንግዲያስ ክርስቶስ የኃጢአት አገልጋይ ነዋ? አይደለም።
  ወደ ገላትያ 3 ፡ 11 – 12 ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎአልና ማንም በእግዚአብሔር ፊት በሕግ እንዳይጸድቅ ግልጥ ነው። ሕግም ከእምነት አይደለም ነገር ግን። የሚያደርገው ይኖርበታል ተብሎአል።

  ወደ ገላትያ 5 ፡ 1 – 5 በነጻነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻነት አወጣን፤ እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ እንደ ገናም በባርነት ቀንበር አትያዙ። እነሆ፥ እኔ ጳውሎስ እላችኋለሁ። ብትገረዙ ክርስቶስ ምንም አይጠቅማችሁም። ሕግንም ሁሉ እንዲፈጽም ግድ አለበት ብዬ ለሚገረዙት ሁሉ ለእያንዳንዶች ደግሜ እመሰክራለሁ። በሕግ ልትጸድቁ የምትፈልጉ ከክርስቶስ ተለይታችሁ ከጸጋው ወድቃችኋል። እኛ በመንፈስ ከእምነት የጽድቅን ተስፋ እንጠባበቃለንና።
  ለገላትያ ሰዎች ደግሞ በእምነት መጠንከር ስለሚገባቸው ፣ እንደተጠቀሰው አስተምሯል ፡፡

  1 ቆሮንቶስ ሰዎች ፡ 9
  20 አይሁድንም እጠቅም ዘንድ ከአይሁድ ጋር እንደ አይሁዳዊ ሆንሁ፤ ከሕግ በታች ያሉትን እጠቅም ዘንድ፥ እኔ ራሴ ከሕግ በታች ሳልሆን፥ ከሕግ በታች ላሉት ከሕግ በታች እንዳለሁ ሆንሁ፤
  21 ሕግ የሌላቸውን እጠቅም ዘንድ፥ ያለ እግዚአብሔር ህግ ሳልኖር ነገር ግን በክርስቶስ ሕግ በታች ሳለሁ፥ ሕግ ለሌላቸው ሕግ እንደ ሌለኝ ሆንሁ፤
  22 ደካሞችን እጠቅም ዘንድ ለደካሞች እንደ ደካማ ሆንሁ፤ በሁሉ መንገድ አንዳንዶችን አድን ዘንድ፥ ከሁሉ ጋር በሁሉ ነገር እንደ እነርሱ ሆንሁ።
  23 በወንጌልም ማኅበረተኛ እሆን ዘንድ ስለ ወንጌል ሁሉን አደርጋለሁ።

  ይቀጥላል

  ReplyDelete
 16. ሠይፈ ገብርኤልFebruary 13, 2012 at 6:02 AM

  ለቆሮንቶስ ሰዎች ደግሞ ህግን መፈጸም ሲያስፈልግ ከህግ በታች እንደሆነ ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ሌላ ዓይነት ሰው መሆኑን እራሱ ይናገራል ፡፡ ይህን ለምን አደረገው ? እምነት ስለጐደለው አይደለም ፡፡ ነገር ግን ማስተማር ስላለበት እንዲህ ሆነ እላለሁ፡፡ ሐዋርያው ኢየሱስን አምነውለት እስከተከተሉት ድረስ በማያምንባቸው ሁኔታዎች እንኳን ምእመኑን በመከተል እንደተሳተፈ ፣ የማይቀበላቸውንም ሁሉ ችላ እንዳላቸው እንገንዘብ ፡፡ ዓላማና ፍላጐቱ የኢየሱስ ስም በሁሉም ሥፍራ ፣ በሁሉም ቦታ እንዲከብር ስለነበረ የማይስማማባቸውን እንኳን እንደ ወገኖቹ ተሳትፎባቸዋል ፤ ስለዚህም ልምዱንና ትምህርቱን እንቅሰም እላለሁ ፡፡

  በተረፈ - ይህ ዓይነቱን የሃሳብ ልዩነት የዘራ ሰው ፣ ተልእኮውንና ሽፍን ሴራውን አላውቅም ፤ በአንድ ታቦት መኖር ከተማመንን ፣ ለኔ ችግር የለውም እሱው ይበቃናልና በተስማማችሁበት አክሱም ጽዮን ስለሚገኝ እየሄዳችሁ በዛ ስገዱ ፤ ቢያንስ ከኢየሩሳሌም ይቀርባል፡፡ የእምነት አንድነትም ይኖረናል ፡፡ የተቀረው ደግሞ በሚያምንበት ባቅራቢያው ይጸልይ ፡፡

  ስለ ተሰጡት አስተያየቶች አንዳንድ ግንዛቤዎቼን ለማስረዳት ከዚህ የሚከተለውን እላለሁ ፡፡
  ስለ መጽሐፍ ለሚጠይቀን በአርአያ ስላሴ የተፈጠረ ሰው ፣ ከመጽሐፍ ለመመለስ መሞከር እንጅ ፣ ጠያቂውን ሰይጣን ተጠያቂውን ደግሞ ከኢየሱስ ጋር ማስተካከል የተዛባ ፍርድ ፣ እንዲሁም የድክመታችን ምልክት ነው /መጽሐፍ በማቴዎስ ወንጌል ወንድምህ ቢደክምብህ እንኳን ምከረው ይላል እንጅ አሳልፈህ ለዲያብሎስ ስጥ አይልም/፡፡ እግዚአብሔር እንደ ፈቀደልን መጠን ለማስረዳት ፣ ለማስተማርና ለመመለስ ብንተጋ የጠፉ ነፍሳትን እናድናለን ፣ የደከመውን እናጽናናለን በሚል ተስፋ ይህን እናገራለሁ፡፡

  - የኢሳይያስ ትንቢቶች የተጻፉት እሥራኤል ከሁለት ወገን ተከፍላ በነበረበት ፣ የሰሜኑ በጣዖት ፣ የደቡቡ የይሁዳ ግዛት ደግሞ የአይሁድ ኦርቶዶክስ ተከታይ ማለትም የእግዚአብሔርን አምልኮ በሚያደርጉ በመሆኑ ፣ ኢሳይያስ ስለ ሰሜነኞቹ ጣዖት አምላኪዎቹ ትንቢትን ተናገረባቸው ፡፡ ያንንም ሲገልጸው በ45 ፡ 2ዐ ላይ ያድን ዘንድ ወደ ማይችል አምላክ ብሎ ይገልጸዋል ፡፡ ታቦትን ብንይዝም እኛ የምናምነው የሚያድነውን እግዚአብሔርን ነው ፤ ይህን ጥቅስ ከታቦት ጋር ለማቆላለፍ መሞከር ከእግዚአብሔር ሥራና ችሎታ ጋር የምንገዳደር ፣ አሠራሩንም ያልተቀበልነው ይመስለኛል ፤ የተቀሩትም ትንቢቶቹ ደግሞ እሥራኤላውያን በአሶራውያን ፣ ሌላም ጊዜ በባቢሎናውያን ሥር በመውደቃቸው ምክንያት የተነገሩ ናቸው እንጅ በታቦት ይገለገል የነበረ ወገን መልሶ ጣዖት አለው ብለን ራሳችንን አንሸንግለው ፡፡

  በትርጓሜ ሥራ የሰለጠንኩ አይደለሁም ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር እንድረዳው በፈቀደ መጠን የሚከተለውንም እላለሁ፡-
  ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ ማለት ኢየሱስን እንደ አዳኝ ጌታ ተቀብለን ካመንን በኋላ ፣ በምግባራችን ፣ በኑሮአችን ፣ በንግግራችን እሱን ስለምንመስልና የቅድስና ኑሮን በመለማመድ ስለምንጓዝ ፣ በጽላት ላይ ተጽፈው የነበሩትን ህግጋትም በተግባር ስለምንኖራቸው ፣ በልባችን ላይ ተጻፈ ያሰኛል እንጅ የኛ ልብ ወደ ጽላትነት ይቀየራል ማለት አይደለም ፡፡ እኛ በእምነት ልምምድ እሱን መምሰል ስንጀምር የኛን መለወጥ ማብሰሩ ነው ፡፡ የጽላቶቹ ህጐችማ አልተለወጡም ፤ ነገር ግን ምግባርን አስተካክሎ በመፈጸም ይደረግ የነበረው ፣ በኢየሱስ በማመን ብቻ በመቀየሩ ከፊተኛው የህግ ሥርዓት ተሻለ እንላለን ፡፡

  በፊደላት በድንጋዮች ላይ የተጻፈ የሞት አገልግሎት የሚባልበት ምክንያት ፣ ህጉ በተግባር ሲተረጐም ያጠፋውን ግለሰብ ከመቅጽበት እንዲቀጣ ስለሚያስገድድና ሞትን ስለሚያስከትል ነው ፤ ያመነዘረ እንደሚገደለው ማለት ፡፡ በዚህኛው የወንጌል ትምህርት ግን ህጉ ጠብቋል ፤ ያመነዘረ ብቻ አይደለም ፣ ወደ ሴት ያየና የተመኘ ሁሉ አመነዘረ ብሎ ይተረጉመዋል ፡፡ ነገር ግን ወደ ፍርድ ሂደቱ ስንገባ ፣ ተወግሮ ይገደል አይልም ፤ በተጻራሪው የንስሃ ዘመንን ያድለዋል ፡፡ ህጉ ተሻረ ከተባለማ ሃይማኖት የለችም ፡፡ ህጉ አለ ፣ ነገር ግን እንድንድንበት ዘንድ የተሻሻለልን መንገድ በኢየሱስ ማመንን ተመደበልን እንላለን ፡፡

  ይቀጥላል

  ReplyDelete
 17. ሠይፈ ገብርኤልFebruary 13, 2012 at 6:16 AM

  ስለ ተሻረው ስለ ፊቱ ክብር የሙሴን ፊት የሚለውም ሙሴ እንደማንኛችንም ሲሞትና ሲቀበር ስለቀረው ፣ ያንጸባርቅ ስለነበረው ስለ ሙሴ ፊት እያስታወሰን ነው ፡፡ የኩነኔ አገልግሎት ክብር የተባለው የመስዋዕቱንና የደም መርጨቱን ሥርዓትና አገልግሎት ፣ በኃጢአት ምክንያት የፍርድ በትር የሚያመጣውን አገልግሎት ማለቱ ነው እንጅ ከታቦት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም ፡፡ የትርጓሜ ሊቃውንቱን ብንጠይቅ ብዙ ልንማር ፣ ከፈቀድነው ደግሞ ገንዘባችን ማድረግ የምንችለው ትምህርት አለ ፡፡

  ወደ ኢየሱስ መንበር ሄዶ የተመለሰ ዘመድ ስለሌለን ፣ መልዕክቴን የምቋጨው በጳውሎስ ወደ ሮሜ ሰዎች መልዕክት ነው ፡- ስለምግብ ቢመስለንም እንዲህ ይነበባልና ከልብ ሆነን እንመልከት
  14 ፡ 1 – 3 በእምነት የደከመውንም ተቀበሉት፥ በአሳቡም ላይ አትፍረዱ። ሁሉን ይበላ ዘንድ እንደ ተፈቀደለት የሚያምን አለ፥ ደካማው ግን አትክልት ይበላል። የሚበላ የማይበላውን አይናቀው የማይበላውም በሚበላው አይፍረድ፥ እግዚአብሔር ተቀብሎታልና።
  14 ፡ 4 አንተ በሌላው ሎሌ የምትፈርድ ማን ነህ? እርሱ ቢቆም ወይም ቢወድቅ ለገዛ ጌታው ነው፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ሊያቆመው ይችላልና ይቆማል።
  14 ፡10 አንተም በወንድምህ ላይ ስለ ምን ትፈርዳለህ? ወይስ አንተ ደግሞ ወንድምህን ስለ ምን ትንቃለህ? ሁላችን በክርስቶስ ፍርድ ወንበር ፊት እንቆማለንና።
  14 ፡ 12 እንግዲያስ እያንዳንዳችን ስለ ራሳችን ለእግዚአብሔር መልስ እንሰጣለን።
  14 ፡ 13 እንግዲህ ከዛሬ ጀምሮ እርስ በርሳችን አንፈራረድ፤ ይልቁን ግን ለወንድም እንቅፋትን ወይም ማሰናከያን ማንም እንዳያኖርበት ይህን ቍረጡ።
  14 ፡ 22 ለአንተ ያለህ እምነት በእግዚአብሔር ፊት ለራስህ ይሁንልህ። ፈትኖ መልካም እንዲሆን በሚቈጥረው ነገር በራሱ ላይ የማይፈርድ ብፁዕ ነው።

  ስለ ምግብ የተነገረውን ስለ ታቦት አድርጋችሁ ብትመለከቱት ለማለት ፈልጌ ነው ፡፡ በተረፈ እየወቀሰን እኔን ተከተለኝ ፣ እኔ የምለውንም ተቀበል ለማለት የሚደፍር ግለሰብ ቢያንስ በትንሹ እንደ መጥምቁ ዮሐንስ መሆንን ፣ እንደጥንት አባቶቻችንም በእፍኝ ባቄላና በአንድ ኩባያ ውሃ ተመጥኖ መኖርን ፣ ከብዙው ስጋዊው ፈቃድና ልማድ መወሰንን ይጠይቃል ፤ እንደ ሐዋርያቱም ሁሉ ራስን ክዶ የጌታ ገንዘብ መሆንን ይፈልጋል ማለቴም ኋላ ምን እንደሚበሉ ፣ ምን እንደሚጠጡ ፣ የት እንደሚተኙ ፣ ምን እንደሚለብሱ ፣ ምን እንደሚያተርፉና በምን እንደሚከስሩ አለማሰብን ማለትም ለምድራዊው ፍላጎታችን አለማደርንና አለመጨነቅን ይጠይቃል ፡፡

  አንድ አባት ሲያስተምሩን አሁን በዚህ ገጽ እንደምንለው በመተረጓጐም ብዙ ደፍረን እያለፍን የሆነ ያልሆነውን በፍልስፍና ስንጠይቃቸው የሰጡን መልስ “መዳን እኛ አሁን የምንነጋገረውን ሁሉ በመነጋገር /በጥበብና በዕውቀት ብዛት/ ከሆነ /ሁለት ሺህ ዓመታት ሙሉ እግዚአብሔርን በየዋኀነት ያመለኩት/ እናቶቻችንና አባቶቻችን አይድኑም ማለት ነው።” የሚል ነበር ፡፡

  ስለዚህ በጥበብና በዕውቀታችን አንመካ ፣ ሁሉን ለሚያውቅ ፣ ሁሉንም ለሚረዳ ፣ ሁሉን በፈቃዱ ለሚፈጽምና በሁሉ ለሚፈርድ ፈጣሪአችን ብንተወው እጅግ ይረዳናል እንጅ ለድክመት አይተወንም ፡፡ እሱንም በማመን እንድናለን ፡፡

  አውቀን በድፍረት ሳናስተውል በስህተት የምንበድለውን ሁሉ እግዚአብሔር አይቁጠርብን
  ለሁላችሁም የእግዚአብሔር በረከትና ሰላም ይብዛላችሁ

  አባ ሰላማዎች የሌለ ልማድ አታምጡ ፣ መልዕክቴ ለመማማር ነው እንጅ በክርስቶስ ስም ፣ ሞትና ትንሣዔ የሚያምን ወገኔን ለማስከፋትና ለመቃወም አይደለም ፡፡ ሁላችንም ልዩነቶችን ከመፈለግ ይልቅ ወንጌሉን ብቻ እናስተምር ፤ ወቀሳ ይወገድ ፤ ስህተት እናርም ማለት ከመሃላችን ይጥፋ ፤ ማንም ንጹህ አይደለም ፤ አንዱ ቅዱስ አንዱን ባለበደል አናድርገው ፤ መጽሐፍ የሰው ዘር በሙሉ ኃጢአተኛ ነው ብሎ ይመሰክራልና ፡፡ ካስተላለፋችሁልኝ አመሰግናችኋለሁ ፡፡

  ReplyDelete
 18. የዚህ ዘመን ጽላት ጣዖት ነው የሚባልበት ነጥቦች፣
  1/ የሙሴን ጽላት የጻፈበት እግዚአብሔር በጣቶቹ ሲሆን የዚህንም ዘመን የሰዎች ጽላት የሚጽፍባቸው ማንም ደብተራ ነው!!
  2/ የሙሴ ጽላት የተጻፈባቸው ቃላት 10ቱ ትእዛዛት ብቻ ሲሆን የዚህ ዘመን የሰዎች ጽላት ሁሉን ቀይረው የሚቀረጽባቸው ስእላ ስእልና ልዩ ልዩ አስማት ነው።
  3/ የሙሴ ጽላት ከቅድስተ ቅዱሳኑ ይወጣ የነበረው በማደሪያው ታቦት ውስጥ በ4 ሰዎች ሸክም ነው። የዚህ ዘመን ሰዎች ደግሞ ታቦት የሌለውን ጽላት፣ አንዱ ደብተራ ቄስ እንደመጽሐፍ የሚሸከማት ቀላል እቃ ናት።
  4/ የሙሴ ጽላት 10ቱ ህግጋት የተጻፈበት ስለሆነ የእግዚአብሔር የሕጉ ጽላት ሲባል የዚህ ዘመን ሰዎች ጽላት ደግሞ የአቡነ ገብረ ማርያም፣ የአቡነ ኃይለ ማርያም፣ የእማሆይ ሰብለወንጌል፣ የጻድቁ ዮሐንስ፣ የአባ ዘክርስቶስ ወዘተ ጽላት ተብሎ ይጠራል።
  5/የሙሴ ጽላት በምድረ እስራኤል እግዚኣብሔር የጻፈባቸው 2ጽላቶች ብቻ ለሺህ ዘመናት ሲኖሩ በዚህ ዘመን ሰዎች ጽላት ደግሞ ሰዎች ችሎታቸውን የገለጹባቸው በሺህ ዘመናት ከ40ሺህ በላይ የልዝብ እንጨት ቅርጾች አሉ።
  6/የሙሴ ጽላትም ሆነ ማደሪያው ታቦት የሚቀረጽበት መጠንና ስፋት፣ ህግና ስርዓት በህግ የተቀመጠ ሲሆን የዚህ ዘመን ግን ይህንን ህግ ሽሮ እንዳሻው፣ እንደፈለገው፣ እንደመሰለውና ልቡ እንደተነሳሳለት መጠን፣ስፋት፣ ቅርጽና ውበት የሚሰራው ሲሆን ውበቱን ለመጠበቅ ቫርኒሽ የሚቀባ የእንጨት ዘር ነው።
  ስለዚህ በዚህ ዘመን ዓይን ያወጣ ድርቅናና ለምን ተነክተን ካልተባለ በስተቀር የሙሴ የጽላት ህግ የለም። መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትእዛዛትን የሚከተልም አይደለም። ስለዚህ በስም የሙሴ ጽላት፣ በግብር ግን በውሸት ላይ የተሰራ ሰዎች እየተደፉ የሚሰግዱለት ጣዖት ነው። ካንዱ አድራሻ ተሰርቆ ወደሌላው ተሻግሮ በመሸጥ ሊያገለግል ይችላል። እንደኪራይ ቤት ጣዖቱ በደባልነት ሊኖር ይችላል። ምክንያቱም ጣዖት ስለሆነ!!

  ReplyDelete
 19. Am happy to learn that YEDEBTERNA ENA YETINKOLA era is coming to an end.you,the rest it is up to you to open your eyes begin readingthe Bible .BETERETERETNA ENA ENDEKURA BEMECHOH YEMIHON NEGER YELEM .Long live Aba Selama!Tank you LORD FOR OPINING OUR EYES!

  ReplyDelete
 20. በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ፥ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ::የዮሐንስ ራእይ 11:19
  ኢያሱም ካህናቱን የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸክማችሁ በሕዝቡ ፊት እለፉ ብሎ ተናገራቸው፤ የቃል ኪዳኑንም ታቦት ተሸክመው በሕዝቡ ፊት አለፉ።መጽሐፈ ኢያሱ 3:6

  ReplyDelete
 21. ወገኖች!!!ወገኖቼ!!!ወገኖቼ!!!

  እስቲ ቆም ብለን እናስተውል??????

  የእኛ ማንነት ለመደማመጥና የሚጠቅመንን ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር አመሳክረን የራሳችን ለማድረግ ሳይሆን እሰጥ አገባ ሙግት ውስጥ መግባት እንወዳለን:: የሚገርመው ደግሞ በእጅጉ የታዘብኩት አበሻ አበሻን ከመስማትና ከማክበር ይልቅ ቀለሙ ነጣ ያለውን ማመን ይቀናናል:: ለዚህ ይመስለኛል በፓለቲካው ቢሆን በኢኮኖሚው ቢሆን በማህበራዊ ሕይወት ቢሆን ተሰባስበው ትንሽ ሳይቆዩ እንዳልሆኑ የሚሆኑትና የሚፈራርሱት:: እኔ መችም ተመካክረን ወይም ተማምረን አንድ ቁም ነገር ያለው ሥራ ላለመስራት በመካከላችን የተጋረጠ ክፉ መንፈስ በሉት ወይም ያልሽነፍ ባይነት ትእቢት ያለማስተዋልና እኔን ብቻ ስሙኝ መንፈስ ተጠናውቶናልና በእውነት ከመንፈሱ ለመማር በመጀመሪያ በማንነታችን ላይ ሰማያዊ ፈውስ የሚያስፈልገን ይመስለኛልና ለዚህ ጉዳይ ቅድሚያ ሰጠተን በቸሩ አምልካችን እግር ስር በጾም በጸሎት ብንቀርብ??? አለበለዚያ መደነቋቆር ብቻ ነው የሚሆነው::

  ከዚህ በተረፈ ወገኖቼ ማንኛችንም በተናገርነው/በጻፍነው ጉዳይ ላይ የሚጠይቅ ጻድቅ ጌታ መኖሩን ባንዘነጋ መልካም ይመስለኛል እንዲያው እከሌ እንዲህ አለ ለመባልና ከበሬታን ከሰዎች እሱማ/እሷማ ለሃይማኖቱ/ቷ በሚል ምድራዊ ብድራትን/መደነቅን ለማግኘት ባይሆንና እውነትን/ቃሉን ብቻ በፍቅር እየተነጋገርን ብንማማር ሁላችንም እጅግ እንጠቀማለን:: እባካችሁ ለመማር ጭምር እንጂ ለማስተማር ብቻ አንጻፍ???? አንደበት ከስድብ ሳይጠራ እንዴት አድርጌ ነው የምማረው???

  ስለሆነም እኔ እንደሚገባኝ ሁላችንም አገሬ? ወገኔ? ሃይማኖቴ? ቤተ ክርስቲያኔ? በማለት ይህን ሁሉ የምናደርገው በመቆርቆር/በቅናት እንደሆነ አምናለሁ:: ይህ ማለትም በሮሜ 10:2 በእውቀት አይቅኑ እንጂ ለእግዚአብሔር እንዲቀኑ እመሰክርላቸዋለሁና:: እንደተባለው መሆኑ ነውና ቅናታችን ከንቱ እንዳይሆን እናስተውል???????? መችም ሁላችን ብንሆን እየተሽከረከርን ያለነው በመስቀሉ ቃል ዙሪያ እንጂ በዚህ አጋጣሚ ተጠቅመው ሊያሰ..ሙን ከፍተኛ ሙከራ በማድረግ ላይ እንደ አሉት ጎረቢት አገሮችና አብረውን ተወልደው አብረውን በፍቅር እንዳደጉት ተከታዮቻቸው እጅግ የተራራቀ ልዩነት የለንምና ውሻ በቀደደው ጅብ እንዳንጋብዝበት መጠንቀቁና ማስተዋሉ ይበጀናል:: ለነገሩማ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ቃሉ የሌለው ሁሉ በአንድ ወገን ያለውና የሕይወቱ ጌታ በማድረግ ያነገሠው ደግሞ ሌላው ወገን በመሆን ሁለት ወገን ብቻ ነው ያለውና እያንዳንዳችን በትንሹም ቢሆን ወገንነታችን ከየቱ እንደሆነ ብንረዳ መልካም ነውና ይህም ቢታሰብበት????

  በመጨርሻም እባካችሁ አንድ ነገር ላይ እንስማማ? እሱም በታቦቱ የሚያምን ቢኖር የራሱ ምርጫ ነውና የቃሉ ብርሃን እስኪበራለት ድረስ ተውት:: ጌታም ቢሆን እሺ ብትሉ...እንደቃሌ ብትኖሩ...ወዘተ በማለት እንጂ የማስገደድ ሥራ አልሠራምና አንዳንዶቻችሁ የጉልበት ሥራችሁን አምጻችሁ የዋሁን ወገን ማሳመጻችሁን ብታቆሙ ትጠቀማላችሁ ከቁጣውም ትተርፋላችሁና ብታስተውሉ???

  በማለት እንሆ የጊዜው ቃል:

  1) ከተጻፈው አትለፍ (1ቆሮ4:6)

  2) በአንዳች ነገርም ልዩ ሃሳብ ቢኖራችሁ እግዚአብሔር ይህን ደግሞ ይገልጥላችኋል (ፊልጵ3:15)

  3) ሆኖም በደረስንበት በዚያ እንመላለስ (ፊልጵ3:16)

  4) የላከኝ አብ ከሳበው በቀር ወደ እኔ ሊመጣ የሚችል የለም (ዮሐ6:44)

  5) በእነዚያ ዘንድ ለማስተዋል የሚያስቸግር ነገር አለ (2ጴጥ3:16)

  የሚሉት ጥቅሶች ምናልባት እየሆነ ያለብንን ነገር እንድናስተውልና ወደ ሥራው ባለቤት ጌታ ፊታችንን እንድንመልስ ይጠቅሙን ይሆናልና በጸሎት በመሆን ብናጠናቸው????

  እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያናችንን ከሙግት መድረክነት አላቆ
  የወንጌል አርበኞች መድረክ ያድርጋት:: አሜን::

  ሰላም ለሁላችሁ ይሁን!!!

  እህታችሁ

  ሰላም ነኝ

  ReplyDelete
 22. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ዶግማውም ሆነ ቀኖናዋ ውስጥ ታቦት እንደ ኦሪቱ ዘመን የእግዚአብሔር የክብሩ ዙፋን ወይም ማደሪያው ነው ብላ አታስተምርም፡፡ ቤተክርስቲያናችን ለምዕመኖቸE ግልጽ አድርጋ ባታስቀምጠውም ታቦት በቀኖና ተደንግጎ እንደ አንድ የቤተክርስቲያን ንዋየተ ቅዱሳት ማለትም እንደ ከበሮው፣ ጽናጽኑ ወዘተ…. በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚገኝ ነው፡፡ ከሌሎቹ ንዋየተ ቅዱሳት ለየት የሚያደርገው ለስጋ ወደሙ መፈተቻ አገልግሎት እንዲውል በዚሁ በቀኖና ቤተክርስቲያን ተደንግጎ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም ታቦት በሌለበት ቤተክርስቲያን ስጋ ወደሙ በዮሐንስ ወንጌል ላይ እንዲፈተት በቤተክርስቲያናችን ቀኖና ተደንግገEል፡፡ አሁን በቤተክርስቲያን ያለው ታቦት ሁለት ገጽ ያለው ዝርግ ሰሌዳ እንደ መሆኑ በፊትና በጀርባው የተለያዩ ነገሮች ይቀረጹበታል፣ ይጻፉበታል፡፡ ሥእላት፣ የእግዚአብሔር ሚስጢራዊ ስሞች (አልፋ፣ ኦሜጋ ወዘተ…) በጊዜው የነበሩ የንጉሱ፣ የጳጳሱ ስሞች ወዘተ እንጂ አስርቱ ቃላት አይቀረጹም፡፡ በአሁን ጊዜ ግን በቤተ ክርስቲያናችን ስለ ታቦት የሚነገረውና የሚታመነው ሁሉ በየትኛው የቤተ ክርስቲያን ጉባኤ እንደ ተወሰነ ግልጽ አይደለም፡፡ ቤተክርስቲያናችን የቃል ኪዳን ታቦት ጥላና ምሳሌ እንደ መሆኑ በዐዲስ ኪዳን እርሱን የተካው አካሉና አማናዊው ታቦት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ሆነ ታምናለች፡፡ በውዳሴ ማርያም ዘእሁድ ላይ ‹‹ከማይነቅዝ እንጨት ተሰርቶ ሁለንተናው በወርቅ የተለበጠው ታቦት ያለ መለያየትና ያለ መለወጥ ሰው የሆነውን የእግዚአብሔር ቃል (ኢየሱስ ክርስቶስን) ይመስልልናል›› ይላል፡፡ ከዚህ የምንረዳው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከእግዚአብሔር ጋር የምንገናኝበት ዐዲስ መንገድ ተጠርጎልናል ማለት ነው፡፡ የቀድሞው የታቦት አገልግሎት አብቅተEል፡፡ ዛሬ በክርስቶስ በኩል እግዚአብሔርን ማግኘትና ማነጋገር እንጂ እግዚአብሔርን ለማነጋገር ወደ ታቦት መሄድ አያስፈልግም፡፡ ይህንን የቤተክርስቲያናችንን እምነት ግን ማንም ደፍሮ ለምዕመኑ ግልጽ አድርጎ የሚያስተምር ወይም የሚያስረዳ የለም፡፡ ስለዚህ አብዛኛው ሕዝባችን በተሳሳተ መንገድ ወደ ታቦት አምልኮ ፊቱን አዙbል፡፤ የሚካኤል ታቦት ወይም የማርያም ታቦት ሲባል ልክ ታቦቱ ላይ ሚካኤል ወይም እመቤታችን እንዳደረች አድርጎ ታቦቱን በመከተል አምልኮ ይፈጽማል፡፡ ይህም ከትምሀርት ማጣት የተነሳ የመጣ ችግር ነው፡፡ በእኔ አስተያየት ታቦት ይዘን መገኘታችን ሳይሆን ችግሩ አገልግሎቱን በግልጽ የቤተክርስቲያን አባቶች ለምዕመኑ አለማስተማራቸው ነው፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. የሰው ልጅ በባህሪው ያልተፈቀደን ነገር ለማየት ይፈቅዳል። ልክ እንደአዳምና ሚስቱ!ሙሴ ኮሬብ ሄዶ ቢዘገይ ባህረ ኤርትራን ከከፈለው አምላክ ይልቅ የጥጃ ጌታ አማራቸው። የሙሴም ሥጋ እስከዛሬ የተቀበረበት አለመታወቁ መቃብሩ ለአይሁዳውያን ፈቃድ ምክንያት እንዳይሆን ነው። ኢታምልክን የሰጠው የሰውን የባእድ አምልኮ ፍላጎት ለማስጠንቀቅ ነው። ኢየሱስ ያደረጋቸውን ሁሉ ለመጻፍ ዓለም ራሱ ባልበቃ ነበር ማለቱ(ዮሐ21፣25)ሰው ባለው ከመጽናት ይልቅ ብዙ መዘዝ እንዳያመጣ ነው። እንኳን ዓለም በሚያክል ተጽፎ ዕቅርና ያለውን ቃል እንኳን መንዝሮ ልዩነቱ ሰፍቷል። ሰው ማለት እንደዚያ ነው።
   ስለሆነም ጽላቱን የእግዚአብሔር ሕግ ነው ብሎ ላመነ ስግደትና አምልኮ የግዱ ነው። አሮጌውን አቁማዳ ይዞ ወደአዲሱ ወይን ጠጅ እንዴት? የወንድምህን ሚስት ልታገባ አልተፈቀደልህም ብሎ እንደዮሐንስ መናገር አንገት ሊያስቆርጥ ይችላል፣ ግን አንገት እንዳይቆረጥ እንደዮሐንስ ከመናገር መከልከል ግን እውነቱን ለመሸፈን መሞከር ነው።አሁን ያለው ጽላት ለምን አገልግሎት ሊውል ይችላል፣ ማለት የሚመጣው ጽላት ምንድነው? በሚለው ላይ ስንግባባ ነው። ከሰው ልብ አልወጣ ያለው ጽላቱ የሚሰጠው አገልግሎት ሳይሆን ጽላቱ የተቀመጠበት ልብ ነው። እናም አንገትም የሚያስቆርጥ ቢሆን ልባችሁን ለሌለ የጽላት ጣዖት ማደሪያ አታድርጉ ብለን በግልጽ ልንናገር ይገባል። ሰው እምነቱን በማሳደግ ወይም ክርስትናን በመኖር ላይ ድካም ሊታይበት ይችላል። ይህንን በየዋህነት መንፈስ ማቅናት ተገቢ ነው። ግን አምልኮውን በሌላ ነገር ላይ ካሳረፈ ያለምንም ማቅማማት መናገር ተገቢ ነው። ጳውሎስ አምልኮን በተመለከተ መቼም ተለሳልሶ አያውቅም። ለማይታወቅ አምላክ ይሰግዱ ለነበሩ አቴናውያን «የምታመልኩትን እየተመለከትሁ ሳልፍ። ለማይታወቅ አምላክ የሚል ጽሕፈት ያለበትን መሠዊያ ደግሞ አግኝቼአለሁና። እንግዲህ ይህን ሳታውቁ የምታመልኩትን እኔ እነግራችኋለሁ፣ዓለሙንና በእርሱ ያለውን ሁሉ የፈጠረ አምላክ እርሱ የሰማይና የምድር ጌታ ነውና እጅ በሠራው መቅደስ አይኖርም» የሐዋ17፣23-24
   በማለት ያለምንም ሽፍንፍን ተናግሯል። ዛሬም ጽላት የሚባል የአምላክ ክብር መገለጫ የሕግ ሰሌዳ የለም ብለን በግልጽ እንናገራለን። ለጽላት የሚሰግዱ ሁሉ ለማይታወቅ አምላክ የሚሰግዱ ናቸው እንላለን። አንተ ያወቅኸው የተሸፈነውን በግልጽ ካልተናገርከው በቀር የገንዘብ ምንጭ አድርገው ከሚጠቀሙበት ደብተራዎች በኩል ምንም አትጠብቅ!

   Delete
 23. tsilat and bicha mehon alebet bilachihu yemitikerakeru tsilatin inde taot yemitayu nachihu,enya gin endeza aydelenm tsilat bizatu minim yahil bihon igziabiher aydelem maderyaw new inji.indet yadrbetal bibal inya anawkim irsu befelegew yifesemal .teseri seriwun lemin indih aderek yih yante sirat aydelem bilo likeraker aychilm yetebalewun inji.inyam igziabiher indih new yememelekew bilo bemeliktenyochu ketenagere mekebel new yaa new imnet.baygermachihu semayawiyan inkwan betabotu zuriya new inji igziabihern bemulu haylu liyayut aychilum yih beraiye yohannis miraf 11:19tetsifo inagenyalen

  ReplyDelete
 24. ታቦትን "ከሌሎቹ ንዋየተ ቅዱሳት ለየት የሚያደርገው ለስጋ ወደሙ መፈተቻ አገልግሎት እንዲውል በዚሁ በቀኖና ቤተክርስቲያን ተደንግጎ ይገኛል፡፡"
  የሚያውቅ ሰው ይህን ያህል ምስክርነቱን ከሰጠ ይበቃናል ፤ የእኛም ክርክር የክቡር ስጋና ደሙ መቁረሻ ስለሆነ መከበር አለበት የሚል ነው፡፡ የሬሳ ሣጥን ላይ አይደለም አማናዊው ስጋና ደም የሚቆረሰው ፤ አንዳንዶች ስጋና ደሙን ለተምሳሌትና ለትዝታ የሚሉ ወገኖች የት እንደሚፈትቱ ፣ እንዴትም እንደሚያከፋፍሉ እናውቃለን ፡፡ የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ግን ገብቷትም ሆነ በእግዚአብሔር ፈቃድ ፣ ኢየሱስ እንካችሁ ሥጋዬን ብሉ፣ ይኸውላችሁ ደሜንም ጠጡ ብሎ እንድንድንበትና ህይወትን እንድናገኝበተ የሰጠንን የመስዋዕትነቱ ስንቅ እግዚአብሔር እራሱ ባጸደቀው ክቡር ንዋየ ቅድሳት ላይ ትፈትታለች ፡፡ በዚህም ኀብረተሰቡ ሲወርድ ሲዋረድ በመጣው ሃይማኖቱ ተንተርሶ ታቦትን ያከብረዋል ፣ ይሰግድለታልም ፡፡ በመጽሃፍ ቅዱስ እያሳበብን የኢየሱስ መከበርን አንቃወም ፣ መጽሐፍ ቅዱስ የትም ቦታ ታቦትን አይቃወምም ፤ እንዲያውም ቅዱስነቱን ይመሰክራል እንጅ፡፡ የታቦት ክብር የሚባለው ይኸው ነው ምስጢሩ ፡፡ ይኸን ምስጢር አዋቂ ብቅ በማለቱ እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ ፡፡ እውነትን የሚያውቁ ተሸፍነው እኛ የማናውቀው በመሰለኝ እንጮሃለን ፡፡

  ReplyDelete
 25. አባ ሰላማዎች እጀግ አመሰግናችኋለሁ ፡፡ በናንተ ሰበብ የምህረተ አብን የክርክር ነጥቦች ለማዳመጥ ቻልኩ ፡፡ ሌሎችም እንዲህ ትጉህ መምህራን የሆኑ ወጣቶችን የስም ዝርዝር ብታስተዋውቁን ይበልጥ እወዳችኋለሁ ፡፡ ምንም አይገኝበትም ከሚባልም ቦታ በስልት ከተፈለገ ፣ ከውጭው ይልቅ እጅግ ብዙ ጠቃሚ ነገሮችን ማግኘት ይቻላል ፡፡ እኔ ከንምንከራከረው ሳላስበው ብዙ እውቀትን አግኝቼአለሁ ፡፡ በሌሎች ዘንድ ትምህርቱ ይተላለፋል ፤ ብዙ የሚያከራክር ርዕስ ስለማያነሱ ፣ አንብበን ዞር ነው ፡፡ እዚህኛው ጋር ግን እሳቱ ይለኮሳለ ፤ ሁሉም መጫጫር ይጀምራል ፡፡ በዚህም ወንጌል በሥርዓቱ ይመረመራል ፤ አንድ ቀንም ሁላችን በአንድ ቃል ብቻ እንነጋገር ይሆናልና ብስጭት ሳይኖር ፣ ቁጣና ንዴትም ሳይገባችሁ መልዕክታችሁን አስተላልፉልን ፡፡ ደስ ብሎን እናነባለን ፡፡
  የምንጠቀምበት መጽሐፍ ቅዱስ ልዩነት እንዳይሆን የሚያለያየን ይህን እስቲ ተጠቀሙበት ፣ ንጹህ የ66ቱ መጽሐፍት ወንጌል ነው ፡፡

  http://bible.org/sites/default/resources/foreign/amharic/

  ReplyDelete
 26. ega ortodocsoch taboten enakeberalen enge anamlkem yemnamelkaw 1 amlaken naw

  ReplyDelete
 27. beandand bete chrstinachen wost 3 tabot yikemtal..i think in every church 1 yibekal .but can some body tell me why they keep 3 or 4 tabotin the same church???

  ReplyDelete
 28. The writer first told us that there is no order given by God to multiply the 'Tabot'. However, he said it is written in the 'Fitiha Negest' by our fathers.He concluded that having the 'tabot' has no problem, but it's not important to lie.

  On the other hand, some commenter assumed that people in EOC are worshiping the 'Tabot'. Is that the truth? Is there a teaching in EOC that orders to worship 'Tabot'? I don't think so.Let me ask some of you a question if you go to some recently established protestant churches you will see different sermons like - in marriage, baptism, holly dinner ...etc. Is every thing what they are doing and saying written in the bible? Are all the materials used there are ordered by God?

  Recently, what I'm realizing is that most of us do not know EOC and even those who say we are the "only" do not know well. So before any critics better to learn and know EOC.The fathers of EOC are fathers who learn from The Holly Spirit not from theology seminaries. That doesn't mean they are all perfect but more glories. So those of you from Seminaries please sit and learn from holly fathers who committed their personal life to learn from the Holly Spirit and spend most of their life in fasting and praying.But I don't mean don't learn in seminaries, but the fruits of seminaries should be measured by the fruits of spirit we bear.

  Kind regards,

  ReplyDelete
 29. እግዚአብሄር እውነቱን ያስመልክታችሁ።

  ReplyDelete
 30. የበግ ለመድ በመልበስ በግ መሆን አይቻልም የአባቶቻችንን ፎቶ፣ ስም በመጠቀም ኦርቶኮሣዊ መሆን አይቻልም ማን እንደሆናችሁ ግልፅ ነው የፕሮቴስታንት ቃል አቀባዮች ጉዳይ ፈፃሚዎች

  ReplyDelete
 31. be sime Aba selama yemitinegedew denkoro menafik zetseat 34:1 bedenbe anbibew mihereteab fetro aydelem yemisebkew bible ke zeftiret eske yohannes rayi dires anbibo new please lekek argun lemin egizeabheren kale anbibachehu atamelkum lenegeru endet yigebachehual yeyazachihut menged minfikina sile hone kalu aygebachihum gin egnan lekek argun EOTB ke oriet eske Addis kidane asamira astemira lezare yadereseche nate degmo enante min yizachehu new ye western ye protestant erdata birr new yategebachehu please le le midirawe tikime bilachehu semayawi hiwot endatatu any way esu libona yistachehu ena wede enat betekirstiyani yimelisachehu

  ReplyDelete