Saturday, February 4, 2012

ከቀድሞው የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምርያ ዋና ኃላፊ በአሁኑ ጊዜ የትምህርትና ማሠልጠኛ መምርያ ዋና ኃላፊ ከሆኑት ከቆሞስ አባ ሠረቀብርሃን ወ/ሳሙኤል ጋራ የተደረገ ቃለ መጠይቅ

ቆሞስ አባታችን ለቃለ መጠይቁ ፈቃደኛ ስለሆኑ እጅግ በጣም እናመሰግናለን

ዝግጅት ክፍሉ

እንደሚታወቀው የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያን ላለፉት 6 ዓመታት መምራትዎ ይታወቃል፡ በዚህ ጊዜ የነበሩበትን የአገልግሎት ዘመን እንዴት ነው የሚገልጹት? በመምሪያው ለዚህ ያህል ዓመት የተሠሩት ዋና ዋና ሥራዎች ምን ምን ናቸው?ሥራዎቹን ለመሥራት ያጋጠሙ ፈተናዎች እና የተሰጡ መፍትሔዎች ምን ምን ናቸው?

ቆሞስ አባ ሠረቀብርሃን

ከሁሉ አስቀድሜ ይህችን ሰዓት ባርኮ ቀድሶ ሰጥቶ ከእናንተ ከመንፈሳዊያን ወንድሞቼ ጋራ ይህንን ቃለ መጠይቅ ለመመለስ ለፈቀደልኝ ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይግባው እያልኩ እንዲሁም ደግሞ ለእናንተ ምንም እንኳ የጋራ ሥራችን ቢሆንም መልካም ሥራ መሥራት ይገባናል ብላችሁ የህን ቃለ መጠይቅ ስላደረጋችሁልኝ በእጅጉ በእግዚአብሔር ስም አመሰግናለሁ፡፡
ይህን ካልኩ ዘንድ ወደ ቀረበው ጥያቄ ልመለስና እርግጥ ነው ይህን ሁላችሁም እንደምታውቁት ለ6 ዓመታት ያህል በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጀ መምሪያ በተላላኪነት ወይም ደግሞ በሌላ አባባል በኃላፊነት በአገልግሎት ቆይቻለሁኝ፡፡ ስለዚህ በዚህ ባሳለፍናቸው 6 ዓመታት ውስጥ ሰንበት ትምህርት ቤት ማደራጃ ሥራ ላይ መቼም ከባድ ወቅት ማለት ይቻላል ፈተና የበዛበት ነበር ማለት ይቻላል፡፡ በአንጻሩ ደግሞ በርካታ ሥራዎች የተከናወኑበት ለውጥ የታየበት ወቅት ነው ማለት ይቻላል፡፡ እና በዚህ 6 ዓመት የሰንበት ት/ቤት ቆይታዬ አሁን ሆኜ ስመዝነው ያሳለፍኩትን ሁኔታ ጠቅለል አድርጌ ለመግለጽ እንደሞከርኩት ቀላል አይደለም ብዙ ፈተናዎችን አልፈናል ብዙ ሥራዎችንም ለመሥራት ችለናል፡፡ ከነዚያም መጀመሪያ እንደመጣሁኝ ከሥራ ባልደረቦቼ ጋራ በመሆን የማደራጃ መምሪያውን አቅም ለማጎልበት ማደራጃ መምሪያው የተሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ በሥርዓቱ እንዲወጣ ለማድረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ለማደራጃ መምሪያውና በማደራጃ መምሪያው ሥር ለሚንቀሳቀሱ ማንኛውም ለሁሉም ለሚመለከታቸው ማኅበራትም በተሰጣቸው ኃላፊነት ወይም ደግሞ ፈቃድ እንዲንቀሳቀሱ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል፡፡ በዚህ ሂደትም ብዙ ለውጥ አይተናል፡፡ ስለዚህ ከመጀመሪያው ይህንን ነው የማስታውሰው ማለት ነው፡፡ በሁለተኛው ስናየው ግን በዚህ በምንሠራቸው ሥራዎች ያጋጠሙ ችግሮች እና ችግሮቹን ለመፍታት የተወሰዱ መፍትሔዎች ወደሚለው እሄዳለሁ፡፡ ሰው መቼም በየትም ቦታ እስከ ሰራ ድረስ ሥራ እሰከጀመርክ ድረስ ችግር ያጋጥማል፡፡ ሰንበት ት/ቤት ማደራጃ መምሪያ እንደጥንቱ እንደፊተኛው ምንም ዓይነት ብዙ ተግባር ሳይኖር እንዲሁ በቀላሉ እያየ ብዙ ባይራመድ ኑሮ ጸጥ ብሎ ማለፍ ይቻላል፡፡ ብዙ ፈተናም አይገጥምም ነበር፡፡ ስለዚህ በዚህ ሂደታችን የገጠመን በአራት አቅጣጫ ነው ችግር ሲገጥመን የነበረ ሰዎች አብዛኛውን የሚያዩት የማኅበረ ቅዱሳንና የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ብቻ ነው የሚመስላቸው ችግራችን የነበረው ወይም ጎልቶ የታየው የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያና የማኅበረ ቅዱሳን ሲሆን ወይም ደግሞ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ኃላፊ እና የማኅበረ ቅዱሳን በሁለቱ መካከል ያለው ችግር ተብሎ ጎልቶ ይታይ ነበር፡፡ በመሠረቱ ግን ማደራጃ መምሪያ ገጥሞት የነበረው ቸግር በአራቱም አቅጣጫ ነበር፡፡ ከጠቅላይ ቤተክህነት ጀምሮ ራሱ ችግር ነበረበት፤
እራሱም ምን ማለት ነው ጠቅላይ ቤተ ክህነት የማደራጃ መምሪያው የበላይ አካል እንደመሆኑ መጠን ሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሕጉን በመከተል መሆን አለባቸው የሚላቸውንና የሚያቀርባቸውን መጠይቆች ከበጀት ጀምሮ ሌላ ሌላም ተጨምሮ በማኅበራት ዙሪያ ስለሚደረጉ ሕጎችን ተላልፈው የሚፈጸሙ ነገሮች ሥርዓት እንዲይዙ በምናደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ጠቅላይ ቤተክህነት እነዚያን ጉዳዮች በአግባቡ እንዳንሄድ እንደ አንድ ሳንካ ነበር ምን ማለት ነው ችግሮችን እንዲፈቱ በማለት በምናቀርባቸው ጊዜ ጥያቄዎች አዎንታዊ መልስ አይሰጣቸውም ነበረ:: በዚያው መጠን ደግሞ ማደራጃ መምሪያው ማወቅ ያለባቸው ችግሮች ማደራጃ መምሪያው እንዳያውቅ ተደርጎ ብዙ ነገሮች እየሾለኩ ስለሚወጡ ነገሮችን እየፈጠሩ ቆይተዋል፡፡ ሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ እና ጠቅላይ ቤተክህነቱ ራሱ እየተጻጻፈ በሥርዓት እንዳንሄድ የሚያደርግ አንዱ ችግር ነበረ፡፡ አልፎ አልፎ የሚደረግ ሕገ ወጥ የሆነ የማኅበረ ቅዱሳን ጉዳይ ብናይ በምንም ይሁን በምን በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ በኩል ማለፍ የሚገባው ወደ ሁለተኛ እና ወደ ሦስተኛ አካል ሕጉን እንደምታውቁት ወደ መምሪያዎች ወደ ጠቅላይ ቤተክህነት በሰንበት ት/ቤቶች መምሪያ በኩል ብቻ ነው ማለፍ የሚችለው፡፡ ይህንን ጠብቆ እንዲሄድ እኛ እየታገልን ጠቅላይ ቤተክህነት ግን ይህንን ጥሶ በአቋራጭ ብዙ ደብዳቤዎችን አውጥቶ ይሰጣቸዋል፡፡ ማደራጃ መምሪያው በማያውቀው መንገድ ብዙ ነገሮችን ይሠራል፡፡ ተው እንጂ ስንል ከእሱ ጋራም አንድ ትልቅ ችግር ነበረብን፡፡ እንደገና ደግሞ እስከ ሲኖዶስ ጽ/ቤትም በተለያየ ክፍልም በዲፓርትመንቶችም ራሱን የቻለ ችግር ያጋጥመን ነበር፡፡ አራተኛ ደግሞ ራሱ ማኅበሩ ሌላ ችግር ነው፡፡ የማኅበሩ ችግር ማለት አልችልም ማኅበሩ ስንል ጠቅላላ ማኅበር ማለት ነው፡፡ አሁን ለማለት የፈለኩት ግን እንደሱ አይደለም፡፡ ማኅበሩን በመምራት ላይ ያሉ አመራሮችን ማለቴ ነው፡፡ በጥቂት የአመራር አካላት የተነሳ ግን ከፍተኛ ችግር ሊገጥም ችሏል፡፡ እርሱም ምንድን ነው ሕግና ሕግን ብቻ መሠረት አድርጋችሁ ተንቀሳቀሱ እየተናበብን እንሥራ ለአንዲት ቤተ ክርስቲያን እንሥራ የተሰጣችሁ ቤተ ክርስቲያንን ለማገዝ ነው የተዋቀራችሁት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን እንድታስተምሩ ነው፡፡ ይህንን ደግሞ ከቤተ ክርስቲያን ጋር እየተናበብን እንሥራ የሚለው እንጂ ሌላ ነገረ አልነበረም፡፡ ስለዚህ እነዚህን ነገሮች በፖዘቲቭ ከማየት ይልቅ በነገቲቭ ማየት ችግሮችን ፈጥሯል፡፡ ከዚያ ባሻገር በማኅበሩ ዙሪያ አባላቶቻቸው እንዲታወቁ የንግድ ተቋማቶቻቸው እንዲታወቁ እንዲወረሱ ሳይሆን እንዲታወቁ ሁሉም ነገር የቤተ ክርስቲያን ነው እንደ ቤተክርስቲያን እንዲሄድ ብለን ጥያቄ በምናቀርብበት ወቅት ጽሑፎቹ ሳንሱር እየተደረጉ እንደ ቤተ ክርስቲያን ሕግ እንዲወጡ እነዚህን በምንላቸው ጊዜ ከፍተኛ ችግሮች ተፈጥረው ነበር፡፡ እነዚህን ችግሮች ለመፍታትም ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል ምንድ ነው የነበረው ጥረቱ በማኅበረ ቅዱሳን ያለውን ለመፍታት የአመራር አካላት ሁል ጊዜ ተገናኝተን መፍታት እንዲቻል ብዙ ጊዜ ጥረት አድርጓል እንግዲህ መዝገብ ቤቱ አለ ሁሉንም ማየት ይቻላል፡፡ ከዚያም አልፎ ከአሁን በኋላ ለመገናኘትና በጋራ መፍታት እንድንችል ብዙ ጥረት አድርገን ነበረ እንደዚያው እንደቀረ ነው፡፡ ከጠቅላይ ቤተ ክህነትም በአግባቡ መሥራት እንድንችል ውይይት አድርገናል፡፡ በየደረጃው በአራቱም አቅጣጫ በተፈጠሩት ችግሮች ብዙ ውይይት አድርገን የመፍትሔ አቅጣጫ ቀይሰናል፡፡ በመጨረሻም ስናየው ውጤታማ የሆነ ሥራ መጥቷል፡፡ ውጤታማ የሆነ ሥራ ማየት ችለናል፡፡ እርሱም ምንድን ነው ምንም እንኳ ችግር ጎልቶ የታየ ቢመስልም ለሲኖዶስ አድርሰን በሰፊው በአባቶች ማለት ይቻላል በቅዱስ ሲኖዶስ እይታም ጉዳዩ በሰፊው ታይቷል፡፡ በጠቅላይ ቤተ ክህነትም ቢሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሥርዓት እንዲሄዱ ድጋፍ እንዲሰጡ የተደረገበት ወቅት ነውና ችግሮችን ለመፍታት ይህን ያህል ተሂዷል፡፡ ያጋጠሙት ችግሮች እነዚሁ ነበሩ ልንፈታቸውም ያሰብነው እነዚህ ናቸው፡፡ አሁንም ተፈትቷዋል ማለት ይቻላል፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ በዘንድሮ ዓመት ጥቅምት ባደረገው ነገር ሰንበት ት/ቤት ማደራጃ መምሪያ ለ6 ዓመታት ሲጮህበት የነበረ እያጣረሰ ያለው ማኅበሩ ሳይሆን በተለይ ሕጎች ናቸው፡፡ በማደራጃ ሕግም ላይ በማኅበሩ ሕግም ላይ ሁለቱም እየተጣረሱ ነው ያሉት ሕጉ መሻሻል አለበት ሕጉ ከተሻሻለ ሁሉ ሠላም ይመጣል ብለን ስንጽፍ የነበረ በዘንድሮ አመት ቅዱስ ሲኖዶስ ይኼን የማኅበሩን ሕግ የማደራጃ መምሪያውን ሕግ ሌላውንም ሕግ በአዲስ መልክ እንዲታይ በአዲስ መልክ እንዲቀረጽ ሁሉም ልጆቻችን ናቸውና ወንድሞቻችን ናቸውና ማኅበሩም ዝም ብሎ ተገንጥሎ መሄድ ሳይሆን የአንዲት ቤተክርስቲያን አካል ሆኖ ሕግና ሥርዓት ተስተካክሎ ይሰጠው የሚል አንድ ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡ ይህም መፍትሔ እጅግ በጣም ጥሩ ነው፡፡ እና ይኼ አንዱ ውጤት ነው፡፡ በማደራጃ መምሪያና በማኅበረ ቅዱሳን ያለውን ጉዳይ ከዚህ በላይ ብዙ ልሄድበት አልፈልግም፡፡ ለመጀመሪያው ጥያቄ ያለኝ መልስ ይኼው ነው፡፡

ዝግጅት ክፍሉ

ከዚህ ጋራ ተያይዞ በማወቅም ባለማወቅም አንዳንድ ሰዎች ቆሞስ አባ ሠረቀብርሃን ወ/ሳመኤል ማኅበሩን ለማስተካከል ለማረምና ሥርዓት ወይም ሕግ ለማስያዝ ሳይሆን ማኅበሩን ለማዘጋት ነው በግልም በመምሪያም የሚንቀሳቀሱት የሚል ሰፊ አባባል አለ እና በዚህ ላይ ምን ይላሉ?

ቆሞስ አባ ሠረቀብርሃን

ለዚህ አጭር መልስ ነው ይኼ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ "እስመ ስምዕየ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ዘውስተ ልብየ" ወይም ደግሞ በአማርኛ “እንዳልዋሽ በልቤ ያለው መንፈስ ቅዱስ ምስክሬ ነው” ብሎ እንደተናገረው ይህንን በጽሑፍ ለምታወጡትም ሆነ ለማንም ከወጣ ይህ ቃለ መጠይቅ መንፈስ ቅዱስን ምስክር አድርጌ ነው የምናገረው፡፡ ከዚህ በፊትም በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ በተደጋጋሚ ተናግሬአለሁ ማኅበሩን ለመዝጋት ወይንም ለማዘጋት የሚለው ይቅርና ሀሳቡ እራሱ ሲነሳ እኔ ይቀፈኛል፡፡ ማንን አርቀን ማንን ልናቀርብ ይኼ ፈጽሞ ሽፋን የጥቂት ሰዎች ለመኖር ፈልገው የሚያቀርቡት ሽፋን ነው፡፡ ዕድሜ ለማራዘም የሚጠቀሙበት እንጂ ሠረቀብርሃን አሁንም መንፈስ ቅዱስን ምስክር አድርጌ ነው የምናገረው ይቅርና ይህ አንጋፋ የብዙ ዓመት ማኅበር ቀርቶ ሌሎች አሁንም በሀገሪቱ ያሉ ገና ወደ ሥርዓት ያልገቡ በሺ የሚቆጠሩ ከአሁን በፊት ያጠናናቸው ማኅበራት እነዚህ ሁሉ ወደ አንድ መሥመር እንዲመጡ እንጂ እንዲበተኑ የሚል ነገር የለም፡፡ ዘራውያን እኮ አይደለንም እኛ በታኞች አይደለንም እና ታዲያ አስተጋብዑ ሰብስቡ ነው የተባለ እናም ይህ ሀሰት ነው፡፡ ሊሆንም አይችልም፡፡ ይህ የጠላት ወሬ ነው፡፡ ነገ ደግሞ እያደረ ስሄድ ይታወቃልና በአጭሩ ማኅበረ ቅዱሳንን ለመዝጋትም ሆነ ለመበተን በምንም ዓይነት አልሜውም አላውቅም እንዲህ ዓይነት መንፈስም ወደ እኔ ሊመጣ ፈጽሞ አይችልም፡፡ ስለዚህ ሀሰት ነው፡፡ ይህንንም አበክረው ሰዎች እንዲረዱልኝ እፈልጋለሁ፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ እኔ አንድ ጥያቄ አለኝ፡፡ በዘንድሮ አመት በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ በኩል አንድ የተላለፈ መልዕክት ወይም ውሳኔ አለ፡፡ ያም ምንድን ነው ቆሞስ አባ ሠረቀብርሃን ወ/ሳሙል ከማደራጃ መምሪያ ተነስተው ወደ ሌላ መምሪያ መዛወር አለባቸው የሚል ውሳኔ ተላልፏል፡፡
ይኼ መደረጉ በማደራጃ መምሪያውና በማኅበረ ቅዱሳን መካከል የነበረውን ችግር ይፈታል በሚል እሳቤ የተደረገ ነውና እርሶ በዚህ ጉዳይ እውነት ችግሩን ይፈታል የእርሶ ከዚያ መነሳት እውነት ችግሩን ይፈታል የሚል አመለካከት አሎት ወይ?
ቆሞስ አባ ሠረቀብርሃን እኔ በዚህ አይደለም የተረዳሁት የሲኖዶስ ውሳኔ አሁን በጠየከኝ የግንዛቤ ዓይነት እይደለም እኔ ያየሁት፡፡ አሁን ባልከው ተወስዶ ከሆነ አባ ሠረቀብርሃን ወደ ሌላ መምሪያ ወይም ሥራ ከተዛወረ መፍትሔ ይመጣል ብሎ ከሆነ የአባቶች ሀሳብ መፍትሔ ሊሆን አይችልም፡፡ይኼ ምክንያቱም የነበረው ትግል ወይም እንቅስቃሴው የአንድ ማኅበር እና የግሌ ጉዳይ አይደለም፡፡ መሠረታዊ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ነው፡፡ ስለዚህ ሠረቀብርሃን ዛሬ ተነስቶ ችግሩና ሥርዓቱ ካልተስተካከለ ችግሩ እዚያው ነው ተደፍኖ የቀረ እንጂ ያ ነገር ነገ እንደሚነሳ እርግጠኛ ነኝ፡፡ እና በዚያ ተረድተው ከሆነ መፍትሔ አይሆንም፡፡ ሰውን በማስነሳት አይሆንም ምክንያቱም ክርክሩም ወይም ደግሞ ጉዳዩ የአንድ ግለሰብ ሥራ የአንድ ማኅበር ሥራ አይደለም መሠረታዊ የሆነ ጥያቄ ነው፡፡ ይህም የታወቀ ነው ግን እኔ የምለው አባቶች በዚያ እንዳይሆን የማደራጃ መምሪያውን ጥያቄ ተቀብለውታል፡፡ ምንድን ነው የተቀበሉት፤ ልብ ልትሉት የሚገባ ከአሁን በፊት ማደራጃ መምሪያው ሳይሆን ራሱ ማኅበሩ ችግር አለብንና ይጣራ አባ ይነሳ ካሉ በኋላ እስኪ ለመሆኑ ከመነሣት በፊት አጣሪ ኮሚቴ ይመደብ ተብሎ በሲኖዶስ ተዋቅሮ ነበር አጣሪ ኮሚቴ በሚገባ 6 ወር ማለት ይቻላል ከግንቦት እስከ ጥቅምት ባለው ጊዜ አጣርቶ ሪፖርት አድርጓል ለሲኖዶስ፡፡ ጥቅምት ላይ አጣሪ ኮሚቴ ባቀረበው ሪፖርት ግልጽ በሆነ መንገድ ችግሩን ከነመፍትሔው አስቀምጦታል፡፡ በዚያ ላይ ያስቀመጠው መፍትሔ የአንድ ግለሰብ ሳይሆን የማደራጃ መምሪያው ጉዳይ እንደሆነ በግልጽ አስቀምጦታል፡፡ የተወሰነውን ሲኖዶስም ተረድቶት የማኅበሩ ችግር የሕጉ ችግር መሆኑን አይቶት የነበረው አካሄድ አግባብ እንዳይደለ ሙሉ በሙሉ ሕጉ መቀየር እንዳለበት ተማምኗል፡፡ ይህ ውሳኔ ወደ እኛ ደርሷል ማለት ነው፡፡ ይህ በዚህ አንድ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ሲደርግ ግን የኔ ግንዛቤ ይህን ያህል አንድ ሰው እኔ ራሴ የዛሬ ሦስትና አራት ዓመት እኮ እንድነሳ ጥያቄ አቅርቢያለሁ፡፡ 6 ዓመት ለኔ ብዙ ነው፡፡ እራሱ አንደኛ የህብረተሰቡ እይታ የአንድ ግለሰብ እና የአንድ ማኅበር ጉዳይ አርጎ ይታይ ስለሆነ ይህም ራሱ የብዙ ሰዎችን አመለካከት ይቀይራል እውነት ሆኖ ከሆነ ማለቴ ነው፡፡ እና ይህ ስለሆነ በዚህ መካከል እረፍት ማግኘት የግድ ነው፡፡ ግድ ሌላ ቦታ መሥራት ስላለብኝ ወሳኝ ስለሆነ ሕጉም ስለተሻሻለ አባ ደግሞ ሌላው ደግሞ ይምጣና ያንን ሕግ ያስፈጽም በሚል መንፈስ ምክር በተሞላበት ወደዚህ እንድቀየር የተደረገ ነው ብዬ የማምነው እንጂ የችግሩ መንሥኤ አባ ሠረቀብርሃን ስለሆነ እርሱ ሲነሳ ችግሩ ይፈታል የሚል እምነት የለኝም፡፡ እርግጠኛ ነኝ የሰው መቀያየር መፍትሔ አይሆንም ወደ ፊት ግን ሁሉ ጥሩ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

ዝግጅት ክፍሉ

እንደሚታወቀው በቅዱስ ሲኖዶስ የተወሰኑ የርሶን ጉዳይ የሚያጣሩ ማለትም የሃይማኖት ሕፀፅ አለበት በሚል ሰበብ ከሳሾችም አሉ በሚል የተዋቀረ ኮሚቴ እንዳለ ይታወቃል፡፡ ይህ ኮሚቴ ከተዋቀረ ጀምሮ የቀረበ ከሳሽ አለ ወይ? እሱስ ምን ይመስላል? የደረሶትስ ነገር አለ? ሥራውንስ ጀምረዋል ወይ ምን ደረጃ እንደደረሰ እና ምን እንደሚመስል ለሚያነቡት አንባቢዎቻችን ግልጽ ቢያደርጉላቸው፡፡

ቆሞስ አባ ሠረቀብርሃን

አመሰግናለሁ፡፡ አሁንም በዚህ ላይ ቅዱስ ሲኖዶስ ስለ አባ ሠረቀብርሃን የእምነት ችግር ጥቆማ አለና እንዲያጣራ ብሎ ለብቻ ያቋቋመው ኮሚቴ የለም፡፡ ፈጽሞ የለም፡፡ ይኼ የሰዎች አሉባልታ ወይም ወሬ እንጂ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ በእጃችን አለ በመዝገብ ቤት አለ ሁሉንም ማየት ትችላላችሁ በአጠቃላይ ስለ አባ ሠረቀብርሃን እንዲያው በዚያ ላይ አልተጠቀሰም ማኅበረ ቅዱሳንም ራሱ ወደዚያ መግባት ባልፈልግም እኔ ነኝ ከሳሽ የሚል በምንም ዓይነት የለም ምናልባት እንግዲህ እንደ ዓልዐዛር ከመቃብር ውስጥ ተነስቶ የሚመጣ ካልሆነ በስተቀር የመጣ የለም መቃብር ውስጥ ካለ ግን ተነስቶ ሲመጣ አብረን እናያለን፡፡ የከሰሰ የለም፡፡ ስለዚህ በአጭሩ ኮሚቴው የተቋቋመው ምንድን ነው ቅዱስ ሲኖዶስ ማኅበረ ቅዱሳን የተወሰኑ ድርጅቶች እና የተወሰኑ ሰዎችን ስም ጠርቶ ከ10 በላይ ሰዎች ስም ዝርዝር አለው እነዚህ ተሐድሶ አራማጆች ናቸውና እንዲመረመሩ ብሎ አንድ ሰነድ አቅርቧል፡፡ ሁለተኛ ደግሞ ለአዲስ አበባ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ህብረት የሚለው በአፄ ምኒልክ ጊዜ ከነበሩት ከነ ገብረሕይወት ባይከዳኝ ጀምሮ እስከ ትናንትናው በቤተክርስትያናችን ከፍተኛ ሥራ ሰርቶ የሄደ ታላቁ የኢትዮጵያ ሊቅ ሁላችን የምንኮራባቸው ወንድማችን ካረፉ ገና ዓመት እንኳ ያልሞላቸው የመጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ በመቃብር ያሉት ሳይቀሩ ተከሰው እንዲወገዙ የሚል በሕይወተ ሥጋ ያሉት ደግሞ አሁንም የኔም ስም በዚያ ላይ እንዳለ አይቻለሁ የሌሎችንም ሊቃውንት ስም ሁሉ ያካተተ አንድ ትልቅ ሰነድ በሰንበት ት/ቤት ወጣቶች በኩል ቀርቧል፡፡ ለሲኖዶስ እንደቀረበም ተነግሮኛል፡፡ ያን ሰነድም ስታዩት አንድም ኃላፊነት የወሰደ አካል የለም፡፡ ይገርማችኋል በዓለም ያሉ አሁን በዚህ ማንሳት ባይፈቀድም ለምሳሌ እንደ አሸባሪዎች አንድን ነገር ሲያጠቁ ሀላፊነቱን እኔ እወስዳለሁ ይላሉ፡፡ ይኼ ግን ምንም ዓይነት ኃላፊነትን የሚወስድ አካል የለውም ፊርማ ብቻ የተቀመጠበት ወደ ሲኖዶስ ቀርቧል ይኼ በአንድ ላይ ተደምሮ ማህበረ ቅዱሳን ያቀረበውን እንደገና ወጣቶች ያቀረቡትን ሰነድ የሚያጣራ ብጹዓን አባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ያሉበት የሊቃውንት ጉባኤ ያሉበት አንድ ኮሚቴ ተዋቅሯል፡፡ በእርግጥ በሀገረ ስብከት የቀረቡ ስም ዝርዝሮች አባ ሠረቀብርሃን የሚል አለበት ስለዚህ በአጠቃላይ እኔም እዚያ ውስጥ እንዳለሁ የታወቀ ነው እንጂ የአባ ሠረቀብርሃን ጉዳይ ለይቶ የሚያጣራ የሚል የለም፡፡ ይኼ በተዛባ መልኩ የመረዳት ሁኔታ አለ ማለት ነው፡፡ በአጠቃላይ ይህንን ሁሉ የሚያጣራ አንድ ኮሚቴ ተዋቅሯል፡፡ ይኼ የተቋቋመ አካል ደገሞ ሥራ ጀምሯል፡፡ ብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት መጥተው ከሊቃውንት ጉባኤ ጋር ሥራ ጀምረው ነበር፡፡ አብዛኞቹ ይህ ነውን ብለው ጥለው ሄደዋል ማለት ይህን አንከታተልም ብለው፡፡ ገና አሁንም ደግሞ ሌሎች ተመርጠዋል፡፡ በሂደት ላይ ነው ያለው እኔም ሦስት ጊዜ አራት ጊዜ ማለት ይቻላል፡፡ ይኼ የስም ማጥፋት ወንጀል ከባድ ስለሆነ በፈረንጆች አባባል "Character assesination" ስለሆነ ወይም ደግሞ የማንነት ግድያ ስለሆነ በእምነት የደረሰብኝ እንዲህ ዓይነቱ ነገር ወዲያውኑ የከሳሾቼ የክስ ቻርጅ በአስቸኳይ እንዲደርሰኝ ብዬ ከሦስት እስከ አራት ጠይቄ ከየት ይምጣ እስከ አሁኗ ሰዓት ግን ምንም ዓይነት ከሳሽም የለም እኔ አለሁ የሚልም የቀረበ ነገር የለም፡፡ ነገር ባጭሩ ከጥምቀት በኋላ አሁን ሊቃውንት እየተነጋገሩ ነው ምንም የቀረበ ነገር የለም የውሃ ሽታ የሆነ ነው፡፡ ስለዚህ ይህ ነው እንጂ በአባ ሠረቀብርሃን ብቻ የሚያጠነጥን ቅዱስ ሲኖዶስ ያቋቋመው ኮሚቴ እንደሌለ ማንም ሰው ሊረዳልኝ እፈልጋለሁ፡፡

ዝግጅት ክፍሉ

አሁን የተሰጠዎት የትምህርትና ማሰልጠኛ መምሪያ በፊት የነበረው ሁለገብ የአገልግሎት ሂደት ምን ይመስላል? ለወደፊትስ ምን ዓይነት እቅድ አውጥተው ከሊቃውንቱ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መምህራን ዘንድ ለመድረስ አስቧል? እናመሰግናለን፤

ቆሞስ አባ ሠረቀብርሃን

በእጅጉ አመሰግናለሁ አጠር ባለ መልኩ ባሳለፍናቸው ዓመታት ማደራጃ መምሪያው በሚያቀርባቸውና በግሌም በተደጋጋሚ ያቀረብኳቸው አንዳንድ አባባሎች አሉ፡፡ በዓለምም ዘንድ እጅግ ተደጋግሞ የሚታወቅ እውነት አለ፡፡ እርሱም ትክክለኛ ሰው በትክክለኛ ቦታ "the right person on the right position" ማስቀመጥ መልካም ነው የሚል ነው፡፡ እኔም ገና ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ስመለስ በሕይወቴ እግዚአብሔር ቢፈቅድ እና ሥራ ብሠራ እዛ ቦታ ላይ ብመደብ ምን ያህል ሥራ በሠራሁበት ብዬ የምመኛቸው ሁለት ታላላቅ መምሪያዎች ነበሩ፡ እነዚህም አሁን ያሳለፍኩት የማደራጀ መምሪያ፣ የስብከተ ወንጌል .... አልነበረም፡፡ አንዱ ከሕይወቴ ጋራ የሚሄድ የገዳማት መምሪያን ነበር፡፡ ይኸው መምሪያ ቢሰጠኝ ምን ያህል ከመሰል ባልደረቦቼ ጋር በመሆን የተቻለኝን ያህል የተሻለ ሥራ በሠራሁ ነበር የሚል ምኞት ነበረኝ፡፡ ምክንያቱም አንደኛ የገዳማት ጉዳይ የምታውቁት ነገር ነው ሁለተኛ ከምንኩስናዬ ጋር የሚስማማ ሕይወት ስለሆነ የሚቻለኝን ሁሉ እሠራለሁ የሚል እምነት ነበረኝ፡፡ ሁለተኛ ደግሞ ስመኘው የነበረው እግዚአብሔር ባወቀ እኔ ግን ፈጽሞ በማላውቀው ሁኔታ የተሰጠኝ ይኸው የሊቃውንት መምሪያ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ፈቃድ እንደሆነ የማውቀው መጀመሪያ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ተብዬ ነበረ ከዚያ በኋላ ወደዚህ ተዛውረሃል ተብዬ መምጣቴ የዘመናት ምኞቴና ትልቅ ሥራ ከሚሠራባቸው መምሪያዎች አንዱና አንጋፋ የሆነ መምሪያ ይኸው የሊቃውንት መምሪያ ነው፡፡ በመሆኑም ወደዚህ አንጋፋ የመምህራን መምሪያ ተመድቤ መመምጣቴ እጅግ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡ ምክንያቱም ገና ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣቴ በፊትም ዓይኔ ሁለመናዬ ወደ ሊቃውንቱ ወደ አብነት ትምህርት ቤቶች ነበር ስሮጥ የነበረና ስራመድ የነበረ፡፡ ስለሆነም በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡ ከመጣሁ በኋላ ግን ይህ መምሪያ እንዴት አገኘኸው ብትሉኝ በጣም እጅግ አሳዛኝ ነው፡፡ እኔም በጣም ነው ያዘንኩት፡፡ ለምንድን ነው ብትሉ ስድስት ዓመት በአንድ ቦታ እየሠራን ስንኖር ልክ እንደውም ከሁሉም መምሪያዎች የተሻለ መስሎ ነበር የሚታየኝ የነበረው፡፡ ልክ መጀመሪያ ከአሜሪካ መጥቼ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ስጀምር ምንም ዓይነት እንዳላገኘሁ ነው፤ ቢሮውንና የቢሮውን ሥራ ሳይስተካከል እንዳገኘነው ሁሉ ይኸው መምሪያ ደግሞ ከዛ በባሰ ሁኔታ የተደራጀ የሰው ኃይል የለውም፣ መሥራትና መንቀሳቀስ የሚያስችል በጀት የለውም፤ ብቻ አንድ ኃላፊ፣ ምክትልና ጸሐፊዎች ያሉበት እንጂ ምንም ዓይነት መንቀሳቀስ የማያስችል ሁኔታ ሆኖ ነው ያገኘሁት፣ እኔ እስከ አሁን ድረስ የመምሪያው የሥራ ፍሬ ሕግና መመሪያ ምን እንደሚመስል እያጠናሁ ነው ያለሁት፡፡ ነገር ግን መምሪያዎች የሚባሉ ከመፈጠራቸው አስቅድሞ በግርማዊ ቀዳማዊ አጼ ኃ/ሥላሴ ጀምሮ በተለይ በ1940ዎቹ አከባቢ ያሉትን ታሪኮች ብታጠኑ ራሱን ችሎ በራሱ ማኅተም በራሱ ሄዲንግ ፔፐር በመንቀሳቀስ ቀዳሚ የነበረ ይኸው መምሪያ ነው፡፡ አሁን ደግሞ የመጨረሻ በሁለት ቢሮ ተቀምጦ የሚውል ይኸው መምሪያ ሆኖ ነው ያገኘሁት፡፡ በሰው ኃይልም፣ በበጀትም፣ በማቴሪያልም፣ በቢሮም .... በሁሉም የተሟላ ነገር የሌለው ትኩረት የተነፈገው መምሪያ ሆኖ ነው ያገኘሁት፡፡ ኃላፊነቱ ግን ትልቅ ነው፡፡ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የዚህ መምሪያ የልጅ ልጅ ነው፡፡ እንዳትቆጡኝ ለማለት የፈለግኩት ማደራጃ መምሪያው ለሊቃውንት መምሪያ የልጅ ልጅ ነው፡፡ ይህ ማለት ደግሞ ትምህርትና ማሠልጠኛ አጠቃላይ ትምህርትንና ስልጠናን በተመለከተ ትምህርት ምንስቴር ከመምጣቱ አስቀድሞም ጭምር በሚንስቴርነት ለዘመናት በተቋም ደረጃም ይሁን በግለ ሰብ ደረጃ የሀገሪቱ የትምህርት ሥርዓት ተስተካክሎ እንዲሰጥ ያደረገው ይኸው መምሪያ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ሊቃውንት ያሉበት ይኸው መምሪያ ነው ሊቃውንቱ ማነን ይወልዳሉ ብንል ሰባክያነ ወንጌልን ይወልዳሉ፤ ሰባክንያነ ወንጌል ማንን ይወልዳሉ ብንል ምዕመናንና የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችን ይወልዳሉ፡፡
ስለዚህ ነው ማደራጃ መምረያ የዚህ መምሪያ የልጅ ልጅ ነው ያልኩት፡፡ ይህ መምሪያ የሊቃውንት፣ የመምህራን መፍለቂያ ነው፣ ሊቃውንትን የሚመለከት መምሪያ ነው፡፡ የልጅ ልጆች የሆኑት እነ ማደራጃ መምሪያ፣ ልጆች የሆኑት እንደስብከተ ወንጌል መምሪያ፣ እንደ ካህናት አስተዳደር መምሪያ እና ሌሎች መምሪያዎች በጣም በሁሉም መስክ አድገው ስናያቸው ይሄ ሽማግሌ አንጋፋ የሊቃውንት የቤተ ክርስቲያኒቷ የጀርባ አጥንት የሆነ መምሪያ ግን እንዲሁ በጣም አነስተኛ በሆነ የሰው ኃይልና በባዶ በጀት ነው ያገኘሁት፡፡ አሁን ግን ከሥራ ባልደረባዎቼ ጋር በመሆን አዲስ እቅድ ነድፈናል፡፡ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁንና ወደፊት ብዙ ነገር ለመሥራት አስበናል ለተግባራዊነቱም እንቅስቃሴ ጀምረናል፡፡ የሥራ ዝርዝሩ አስቀድሞ መናገር ባያስፈልግም በአጭሩ ግን የአብነት ትምህርት ቤቶችን በሚመለከት ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊም ሆነ ዘመናዊ የሚመለከት እንደመሆኑ መጠን ይህንን አዲስ እቅድና በርካታ ሊቃውንቶቻችንን አሰባስበን አዲስ ምዕራፍ ከፍተን ወደ ጥንት ቦታውና ክብሩ ለመመለስ በዘመኑ አደራጅተን የተሻለ ሥራ ለመሥራት ራዕይና ፍላጎት አለን፤ የሥራ እንቅስቃሴም ጀምረናል፤ ሥራውና ዓላማው ሰፊ ነው፣ ለወደፊት እንደአስፈላጊነቱ እንገልጸዋለን፡፡

ዝግጅት ክፍሉ

ከዚህ ከምደባው ጉዳይ በተያያዘ መልኩ የሚነሳ ሐሳብ አለ፤ በተለያዩ የመገናኛ አውታሮችና ከአንዳንድ ግለሰቦች እንደሚሰማው ቆሞስ አባ ሠረቀብርሃን ከማደራጃ መምሪያ ተነስተው ወደ ትምህርትና ማሰልጠኛ ሲመደቡ አልሄድም፣ አልሠራም ብሏል፣ ይህም የሚያሳየው ማኅበረ ቅዱሳንን የሚያገኙት በማደራጃ መምሪያ ብቻ በመሆኑ ነው የሚል አባባሎች አሉና ይህንን ሐሳብ እንዴት ይገልጹታል?

ቆሞስ አባ ሠረቀብርሃን

እንግዲህ ከላይ እንደገለጽኩት አሉባልታዎችም አሉ ግን አሉባልታዎች ሲነሱ ደግሞ አንዳንድ ጊዜ መሠረት ያላቸው አስመስለው ይነሳሉ፡፡ እኔ ወደ ትምህርትና ማሰልጠኛ አልሄድም የሚለው ሐሳብ ምናልባት ከሌላ አንግል አይተውት ካልሆነ አባባሉ እንደሱ አይደለም፡፡ እኔ ከሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ስነሳ ቅዱስ ሲኖዶስም ሆነ ቅዱስ ፓትርያርኩ እንዲሁም ጠቅላይ ሥራ አስኪያጃችን በየትም ቦታ ሲኖዶስ ባይልም መቼም ቢሆን ሠረቀብርሃን ከዚህ ቦታ ተነስተህ ወደዚህ ቦታ ትሄዳለህ ከተባለ የቤተክርስቲያኗ ልጅ እንደመሆኔ መጠን አሜን ብሎ መሄድ ብቻ ነው፡፡ በዚህ ዓይነት አካሄድ አምናለሁ፡፡ እዚህ ላይ ስናይ ግን ከሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ እንደምነሳ ከተባለ በኋላ እኔ ይህን ቦታ ይሰጠኝ ብዬ ሳልጠይቅ ከዚህ በፊትም ብዬ አላውቅምና እንድነሳ ሰማሁኝ እንደተነሳሁም ወረቀት /ደብዳቤ/ ሳይደርሰኝ ሰማሁ በደስታ ተቀብልኩት ግድም ነውና፣ በዚህ መካከል እያለሁኝ ግን ጥቅምት 27 ቀን 2004ዓ.ም በቅዱስ ፓትርያርኩ የመንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሆነህ እንድትሠራ የሚል ደብዳቤ ደረሰኝ፡፡ ይህ እንደደረሰኝ ግን በተከታታይ መልኩ ደግሞ በምንም ይሁን በምን በማይታወቅ መንገድ ደግሞ ብፁዕነታቸው ወደ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ከመጣ ሥራዬን እለቃለሁ የሚል የመልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸውን ሰማሁ፡፡ ከዚህ በኋላ ይሄማ ከሆነ ለምክትል ሥራ አስኪያጅነት የማያበቃኝ ነገር ካለ ወይንም በእምነት ተጠርጥረዋል የሚል ነገር ካለና ለዚህ የማያበቃኘ ከሆነ እንደውም ምክትል ሥራ አሰኪያጅነት የቢሮ ሥራ ነው በእምነት የተጠረጠረ ሰው ከሆነ እንዴት ይህ አንጋፋ የሊቃውንት መፍለቂያ የሆነ መምሪያ ሊመራ ይችላል፣ ስለዚህ ይህ በአስቸኳይ ይጣራልኝና ከየትም ቦታ ልሠራ ዝግጁ ነኝ የሚል ጥያቄ አቅርቤአለሁ፡፡ ይህንን ጥያቄ ደግሞ ሕጋዊ ጥያቄ ነው፡፡ ሁለተኛ ያቀረብኩት ደግሞ ጉዳዩ እስኪጣራ ድረስ በዚህ ቦታ እየሠራህ እንድትቆይ የሚል ደብዳቤ ከተጻፈልኝ መሥራት እችላለሁ፡፡ እነዚህ ሁለቱ ከሌሉ ግን ወደ እኔ ሲጽፉ ጥሩ አድርገው በቅዱስ ፓትርያርኩ መልካም ፈቃድ ከሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ወደ ትምህርትና ማሰልጠኛ መምሪያ ተዛውረው በኃላፊነት እንዲሠሩ የተወሰነ መሆኑ በክብር እናስታውቃለን፡፡ በማለት ሁሉንም ነገረ ተሸፋፍኖ ስለመጣ ይሄማ አይደለም ይሄ ማዘናጋት ነው፣ ብቱቱ አልወድም ትክሻዬ እንዲህ ዓይነት ቅጥ አልባ ነገር አይሸከምም፣ በሌላ እንደፈለጉ ይበሉኝ በእምነቴ ግን አጥብቄ የምኮራ ሰው ስለሆንኩ እንደዚህ በአሉባልታ ከሳሽ በማይታወቅበት ሁኔታ አባ ሠረቀብርሃን እንዲህ ብለው ... በሚባልበት ሁኔታ ይህን ብቱቱ ኃጢአት የስም ማጥፋት ተሸክሜ አሜን አልልም መጣራት አለበት የሚል አቅርቤአለሁ እንጂ አልነሳም አልፈልግም አላልኩም፡፡ ሁለተኛ ከሰንበት ትምህረት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ አልነሳም ያለው ማኅበረ ቅዱሳን ለማግኘት ፈልጎ ነው የሚለው ግምታዊ ሐሳብ ፍጹም ተራ ስሕተት ነው፡፡ እንግድያውስ ማኅበረ ቅዱሳን ትልቅ ሥራ እየሠራበት ያለው በትምህረትና ማሰልጠኛ ነው፡፡ እንግዲያውስ ትልቅ ፕሮጀክት በመቅረጽ ከውስጥም ከውጭም የእምነት ተቋማት እንረዳለን በማለት የገቢ ማግኛ ምንጭ ያደረገው ይኸው መምሪያ ነው፡፡ ትምህርት ቤቶች እንሠራለን የአብነት ትምህር ቤቶች እንረዳለን፣ መምህራንን እንረዳለን እናሰለጥናለን ... የሚሉትን ሁሉ የሚካተተውና የሚመለከተው ይኸው የሊቃውንት መምሪያ ነው፡፡ የዚህ መምሪያ ሕግ እንደሚደነግገው ሰንበት ትምህርት ቤት፣ ስብከተ ወንጌል... እንኳ ሳይቀሩ በራሳቸው ማሰልጠን አይችሉም፡፡ ማንም ስልጠና ነክ የሆኑ ጉዳዮች በሙሉ የሚመለከተው ይኸው መምሪያ ነው፡፡ የአብነት ትምህርት ቤቶች ሁሉም የሚመለከተው ይኸው መምሪያ ነው፡፡ የመንፈሳዊም ሆነ የዓለማዊ ትምህርት ቤቶች በሚመለከትም በዋናነት የሚመለከተው ይኸው የሊቃውንት መምሪያ ነው፡፡ እንግዲያውስ አሁን ነው ማኅበረ ቅዱሳነን በተሻለ መልኩ የማገኛቸው፡፡ ግን እኔ ፈጽሞ በቀለኛ አይደለሁም፡፡ ምን አድርገውኝ ልጆቼ እኮ ናቸው፡፡ አሁንም ነገም ከነገ ወዲያም በሰላም ከእነርሱ ጋር ቤተክርስቲያንን ማገልገል የምችል ነኝ እና እንደዚህ ዓይነት የተሳሳተ ግንዛቤ ያላችሁ ሰዎች እባካችሁ ልክ አይደለም እውነታው ይኸው ነው ይህን ምንጭ አልባ የአየር ላይ ወሬ የሚያናፍሱና የሚያሰራጩ ሰዎችም እውነቱን ከሐሰት ለይተው ማወቅ እንዲችሉ ዓይነ ልቡናቸውን ያብራላቸው እያልኩ እጸልይላቸዋለው፡፡

ዝግጅት ክፍሉ

ወደ ግል ሥራዎትዎ እንመለስና አሁን "እውነትና ንጋት" የሚል አዲስ መጽሐፍ ጽፈው ለሕትመት አብቅተዋል፡፡ ከመጽሐፉ ርእስ እንጀምርና እውነትና ንጋት ነው የሚለው ምን ማለት ነው ምን ለመግለጽ ተፈልጎ ነው፡፡ ይዘቱስ ምን ይመስላል ከዚህ ጋር በተያያዘ መልኩ ሌሎች ሥራዎችንስ አዘጋጅተዋል ወይ?

ቆሞስ አባ ሠረቀብርሃን

መልካም ይሄ እውነትና ንጋት የሚለው አባቶቻችን አዘውትረው የሚናገሩት ረቂቅ የሆነ አባባል ነው፡፡ እውነትና ንጋት ዳሽ ይሆናል የሚል ነገር አለ ሁሉም ሰው ሲያነብ ዳሹን መሙላት ይችላል፡፡ ግልጽና በብዙኃኑ ዘንድ የታወቀ ስለሆነ እውነትና ንጋት እያደረ ይጠራል ይላሉ አባቶች፣ ርእሱ የሚያመለክተውና ዝም ብለን ስናየው ብዙ ከባድ ምስጢር እንዳለው ማየት ይቻላል፡፡ በዚህ ላይ እውነትና ንጋት ንጋት ሁል ጊዜ ጠዋት አይታችሁ ከሆነ ድቅድቅ ጨለማ አድሮ ወደ ንጋት አካባቢ ሲደርስ የጸሐይ ብርሃን ሊወጣ ሲል ጨለማውን እየሸሸ ይሄዳል፡፡ ንጋት ማለት ይሄ ነው፡፡ እውነት ደግሞ በተፈለገ ዓይነት ዘይቤ ተራራ በሚያህል ሐሰት ከነደብዳቤም ወይም እዛ ውስጥ ብትቀበርም ቆፍረን ይህ ነው በማይባል ጥልቅ ውስጥ ብንቀብራትም እውነት ያሸንፋል እውነት እግዚአብሔር ማለትም ስለሆነ መቼም አሸናፊ ነው፡፡ ስለዚህ በተለያየ መሰናክሎች በተለያዩ የውሸት መረቦች ተተብትባ ሳንካ ቢፈጠርባትና ጊዜ ብትወስድም እውነት ሁል ጊዜ ታሸንፋለች የሚለው እውነታ የሚያመላክተው ጽሑፍ ነው፡፡ ሁለተኛ የመጽሐፉን ይዘት በተመለከተ በመረጃ የተደገፈ መጽሐፍ ነው፡፡ ትኩረት የሚሰጠው ወቅታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ነው፡፡ ወቅታዊ የምንላቸው በጠቅላላ የማደራጃ መምሪያ በነበሩ የሥራ ሂደቶች ያትታል፣ በሕይወቴና በእኔ ላይ በዘመቱ ሰዎችም ያትታል በጠቅላላ ሰፋ ያለ ሲሆን ሦስተኛው ደግሞ ለሥነ መለኮት (Theologians) ተመራማሪዎች ለምርምርም የሚጠቅም ጭምር ነው፡፡ በዚህ በነገረ ማርያም (Mariology) ትምህርት ሰፊ መረጃ የያዘ ነው፡፡ ስለዚህ ይሄ የመረጃ መጽሐፍ ስለሆነ መረጃውን አይቶ ሕብረተሰቡ ሲሰማው የነበረ በየቤቱ እየተንኳኳ የተሰጠው ሲዲ አለ፣ በየመጽሔቱ በየጋዜጣው መቼስ ጸሐፍያን ወይም የጋዜጣና መጽሔት አዘጋጆች በእውነት ጥሩ የወሬ ምርት አግኝተዋል ብዙም በእኛ የተነሳ ሽጠዋል ብዬ አምናለሁ እንግዲህ ለበረከት ከሆነላቸው፣ ብዙ ተብለናል፣ ብዙ ተሰድበናል እንግዲህ የሰው ስም አጥፍቶና አጥቁሮ ገንዘብ የሚገኘ ከሆነና ለበረከት ከሆነ ግድ የለም ይህንን በተመለከተ እውነታው ምን እንደነበረና እንደሆነ የሚያሳይ የሚያትት በመረጃ የበለጸገ፣ ሰዎች ሊያዩት የሚገባ አይተው ግንዛቤአቸውን ሊያሰፉበት የሚችሉ ምክር አዘል ማሳየት የሚችል ግልጽ አድርጎ ማሳየት የሚችል በዶክሜንት የተዘጋጀ የመረጃ መጽሐፍ ነው፡፡ ከዚህ ቀጥሎ ለወደፊት ሁለት ታላላቅ መጻሕፍቶችን ለሕትመት አዘጋጅቼአለሁ፡፡እንዲያውም ቀጥለው የሚወጡ እነዚህ መጻሕፍቶች በጣም ከባድ ርእስ ያላቸው ሥራዎች ናቸው፡፡ አንዱ "ተጠያቂ ማን ነው" በሚል ርእስ የተዘጋጀ ሲሆን ይዘቱንም ከርእሱ መረዳት ይቻላል፡፡ ይህም መጽሐፍ በከፍተኛ መረጃ የበለጸገና በመግለጫ የተዘጋጀ ጠቅላላ ምሥጢር ያዘለ በርካታ ገጾች ያሉት መጽሐፍ ነው፡፡ ይኸው አንዱ ትልቅ ጠቅላላ የቤተ ክርስቲያኗን ሕይወት የሚዳሰስ ነው፡፡ ሁለተኛ ደግሞ ቀደም ብሎ ሊታተም የነበረ ጊዜው ገና ነው ተብዬ ያስቀመጥኩት ጸሎታቸውና በረከታቸው ይድረሰኝና ብፁዕ አባታችን አቡነ መርሐ ክርስቶስ ይህ መጽሐፍ የዛሬ አራት አምስት ዓመት አካባቢ ገና በሕይወተ ሥጋ አብረን እያለን አማክሬያቸው ነበር፡፡ ልጄ ወቅቱ ገና ነው ይህንን ነገር ግንዛቤ እንድወስድ በብዙ መንገድ አመስጥረው መክረውኝ ተወው አስቀምጠው ጊዜ ይፍታው ብለው ያስቀመጥኩት መጽሐፍ ነው፡፡ ይህ መጽሐፍም ወቅቱ አሁን መስሎ ስለታየኝ አሁን ይታተማል፡፡ ይህም መጽሐፍ "መንፈሳዊ ስልጣን በቅዱስ ሲኖዶስ ሲመዘን" የሚል ርእስ ያለው መጽሐፍ ነው ይሄ በጣም አነጋጋሪና ትክክለኛ መረጃ ያለው የ2000 ሺ ዘመን ክርስትና በሙሉ አትቶ አሁን ያለንን ፍንትው አድርጎ ከሐዋርያት ጀምሮ ስለመንፈሳዊ ስልጣን ስለ ጠቅላላ ስለዲቁና ስለ ቅስና .... በአጭሩ ስለ ምንኩስና ስለ ጵጵስና ስለፕትርክና ... ሁሉ በሙሉ ያለውን እያስቃኘ የሚሄድ ትልቅ መጽሐፍ ነው፡፡ እንግዲህ እነዚህ ሁለት መጻሕፍት ናቸው ለጊዜው የተዘጋጁት እነዚህን አሳትማለሁ ብዬ ተዘጋጅቼአለሁ፡፡

ዝግጅት ክፍሉ

ቆሞስ አባታችን ውድ ጊዜዎትን ሰጥተው የማደራጃ መምሪያውን የሕትመት ክፍል ጥያቄ አክብረው የሰጡንን ሐሳብ መልስ እና ማብራሪያ በእግዚአብሔር ስም እያመሰገንን በመጨረሻ ለሚመለከተው ሁሉ የሚያስተላልፉት መልእክት ካለ እንዲያስተላልፉ ጋብዘነዎታል፤

ቆሞስ አባ ሠረቀብርሃን

እኔም ስላደረጋችሁልኝ ግብዣ ስለ ጥረታችሁ ስለ መልካም ሥራችሁ በእግዚአብሔር ስም እያመሰገንኩ እንግዲህ ይህነን በጽሑፍም ሆነ በድምጽ ስታወጡ ለሚከታተሉ በውስጥም በውጭም በየትም ዓለም የሚገኙ ወገኖቻችን ሊረዱና ሊገነዘቡ የምፈልገው እውነት ቢኖርና የማስተላልፈው መልእክት ቢኖር በተለይ ለክርስቲያኑ ምዕመናን ከሁሉ በላይ እኛ ከምድራዊ ኃላፊ ከጠፊ ዘር የተወለድን ሳይሆን እኛ ከማይጠፋ ዘር የተወለድን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፤ የእግዚአብሔር ልጆች ደግሞ ዝም ብለው በስማበለው የሚነዱ ሳይሆኑ በእርጋታ በጸጥታ በአስተዋይነት የሚንቀሳቀሱ ናቸው፡፡ በተለይ፣ ይቅርና በደል ያልበደሉት ያላጠፉትን ሰዎች መወንጀል ማማት ሌላ ቀርቶ በኃጢአት የወደቀ ሰው እንኳ ቢገኝ ክርስቲያን የሆነ ሰው ሁሉ ስለወደቀው በተሳሳተው ሊያለቅስ ሊያነሳ ኃጢአቱን እንጂ ኅጥኡን መጥላት ስለማይገባና ስለማይቻል የሃይማኖታችን መመርያም ስላልሆነ ስለተሳሳተ ሰው መጸለይ ይገባል እላለሁ፡፡ በዚሁ በዓለም ላይ በሚደረገው በሚባለው ማንኛውም ነገር ሁሉ ልበ ሰፊ በመሆን እውነትን በመፈለግ ለእግዚአብሔር ልብንና አእምሮን በመስጠት እንዲንቀሳቀሱ ከአሉባልታ ከሐሜት ከማይረቡ ነገሮች ከምድራዊ ነገሮች ርቀው ሰማያዊውን እያሰቡ በፍቅር በሰላም እንዲኖሩ እና በአጭሩ በፍጥነት እገሌ ጥፋተኛ ነው በማለት በሰው ላይ ጣትን ከመቀሰር ይልቅ ራሳቸውን እንዲመረምሩ አባቶችን እንዲያከብሩ ቤተ ክርስቲያናቸውን እንዲጠብቁ ሁላችን የአንዲት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ልጆች እንደሆንን እና አርአያና ምሳሌ እንድንሆን የጌታችንና የአባቶቻችን የሐዋርያት ፈለግ ተከትለን አገልግሎታችን የሠመረ እንዲሆንልን ከሌሎች ጋር በሰላምና በፍቅር እንድንኖር ስለምታዘዝ ይህንን ወንድሞቼንና እህቶቼ በማንኛውም መጽሐፍ የሚያነብም ሆነ ለወደፊት የሚታተሙትንም ለሚያነቡ አንብበው በረጋ መንፈስ ተገንዝበንው እውነታውን በሚገባ በሕሊናቸው መርምረው እግዚአብሔርን የሚያስደስተው ሥራ እንዲሠሩ ነው የእኔ መልእክት፡፡
እግዚአብሔር ይስጥልን
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ድረገጽ የተወሰደ (eotcssd.org)

14 comments:

 1. Abatochachen tehetenan genzeb yaderegu mehon alebachew. ~ Yemiyasadedachehun merku enji ateregemu# new zemilew metsehaf. Aba sereke gen yerasachewen netsehena lemegelethse silu rasachewen kef lemadereg metsehaf tsefewal. 1 menew egziabeher yemikeberebeten menefesawi metsehaf bitsefu 2. Metsehafes endezzihe beandena hulet were tsefo yemiderse new woy?

  ReplyDelete
 2. Some intetst group here in USA working over time to demolish the great job of patriarc paulos that he appointed abune fanuel to serve all eotc with out discrimination. Look this the point yemetelachu mereku. As this reason people such like false priest of mk spending money to campaign some zemawi monk and priest as charged to fire abune fanuel with false alegation. So any informatiom come from this group 100% not question of eotc in usa. Death to mk peace to our church. Be as eotc take action to clean up our church from devil mk.

  ReplyDelete
 3. Aba selama has being done a marvolues job to aware our real eotc members to out from confusion by providing of concise and current information. Eventhough you guys must be connect net work to investigate mk stuppid priest and deacon ethical problem. hill and death for mk mahibere kulla tebe stuppid.

  ReplyDelete
 4. Aba Sealma Thank you bet Aba Sereke bahayimanot yemtamu sew aydelum moyachewm yetenegerelet new Ahun yetsefaw tikikilega menekuse bicha new Semonun Abune Fanueil Addis Hagere Sibket Akakumewal Abune Abirham ketenesu behala leneger yakakamut komete adimawn Jemrol Abune Fanueil berkatal likawntn beye estetu medbewal zendiro gid new Mahibere Kidusanm ene yelelehubet neger aysemirm eyale new
  Papas yelelebet Yehagere Sibket gubae noth karolayina sharlet tedergal Aba Selamawoch Like Papas yelelebet Hagere Sibket yinoral wey ? mels sitsubet Digimos Abune Abirham yakakamut Mahibere Kidusann new weyis Hagere Sibiket new?

  ReplyDelete
 5. abatachen komos aba serek edemawoten yakoyelen letebeb sew and kale yebekal newena lemaheberetegnochu yemasetelalefew kal yeabaten degemea new ''EWNETENA NEGAT'' new lebona yesetachehu agelegelotachew lekesachu sayehon lenefesachu endehon amalake yerdachu.

  ReplyDelete
 6. አንዳንድ አስተያየት ሰጭዎች በማታውቁት ነገር ገብታችሁ የምትፈተፍቱ፤
  አንዳንዶቻችሁ ደግሞ በጭፍን ቲፎዞነት እንጂ ነገሩን በፅሞና ያላያችሁ፤
  አንዳዶቻችሁ ደግሞ በጭፍን ጥላቻ እንጂ ነገሩን በደንብ ሳታውቁ፤
  ሌላው ደግሞ በተለይ በተለይ ጥቅሙ የተነካበትና ከሁዋላው ጉድና ጎድጎዳ የሞላበት፤
  በመጨረሻ ደግሞ ለቤተክርስቲያን ሳይሆን ለራሱ የንግድ ድርጅትና የፖለቲካ ሥራ
  እንደበፊቱ መሥራትና ማጭበርበር ያልቻለው የማህበረ ሰይጣን ድርጅት የሚሰጠው
  የሞት የሽረት የመሰሪነትና የቅናት አስተያየቱን ነው የሚያስነብበን። የሆነው ሆኖ
  ግን ሁልጊዜ አሸናፊው የእግዚአብሔር ሃሳብ ያለው ነው። እስኪ አሁን ማ ይሙት
  በእውነት ለቤተክርስቲያን የምናስብ ከሆነና አላማችን የእግዚአብሔርን መልካም
  አገልግሎት ለማገልገል ከሆነ ምን ያጣላናል \ በእውነትስ ክርስቲያን ከሆንን
  ክርስቲያን መጣላት አለበት\ ይህንን ደግሜ እላለሁ አላማችን አንድ \ክርስትና\
  ከሆነ ምንድን ነው የሚያባላን\ በእውነት አቡነ ፋኑኤል ምን አደረጉ\ ተመድበው
  መጡ፣ ሥራቸውን መሥራት ጀመሩ የሥራ ሰው እንጅ የወሬና የአሉባልታ ካህን
  አይደሉም። ደግሞስ እኛ ማነንና ነው በስነሥርአት ሲኖዶሱ መድቡአቸው ለክርስትና
  አገልግሎት እንዳይሰጡ የምንፈራገጠው፣ አረ ተው መቼም ክርስቲያኖች እንኩአን
  አይደላችሁም ፤ ስለ እግዚአብሔር ብትባሉም አልሰማችሁምና አለቃችሁም የቀደመው
  ጠላታችን ያ ዲያብሎስ በመሆኑ ነው መሰለኝ እርሱን በማስደሰትና ቤተክርስቲያንን
  በመበጥበጥ ላይ ትገኛላችሁ። ነገር ግን እግዚአብሔር ተዋጊ ነው አታውቁም እንዴ\
  ምንም አላችሁ ምንም አሁን ጊዜው የእግዚአብሔር ሰዎች የሚፈተኑበት ጊዜ ስለሆነ
  እስከመጨረሻው የሚፀና እርሱ ይድናልና፤ አባታችን እስከመጨረሻይቱ ሰአት ድረስ እውነተኛ
  ሥራን መሰራት ብቻ ነው፣ ከእናንተ ጋር አፍ መካፈትም አያስፈልግም። ጨው ለራስህ
  ብትል ጣፍጥ ያለዚያ ድንጋይ ነው ብለው ይጥሉሃል ነውና፣ ማቅ መንፈሳዊ ድንቁርናችሁ
  የትም አያደርሳችሁም፣ ለቤተክርስቲያን ጠላት ማቅ ይገባዋል ሞት፣ ለቤተክርስቲያናችን
  ግን አንድነት፣ እድገትና ፍቅር ለዘለአለሙ ይሁን። አሜን።ሰላምንና ፍቅርን የማይወደው ማቅ
  ይግባ መቀመቅ። ባታወጡትም ካነበባችሁት ይበቃል።ሳትሰሩ የህዝቡን ገንዘብ እየበላችሁ
  አየር ላይ ለቀራችሁት ህገ ወጥ የድርጅቱ ኮሚቴ ነን ባዮች፣ እናንተ ማለት ደግሞ ማንም ናችሁና
  ካአቅማችሁ በላይ አትዘለሉ ወደ ላይ። ይቆየን።

  ReplyDelete
 7. Do not affraid this is maffiya kemagna mk.

  ReplyDelete
 8. Abune fanuel done great job , for reason he appointed very real lekawonet as leke kahinat. Others mk elememts please find job that close match to ur profile. You guys no idea about to manage and to serve thechurch just leave ourchurch now. Bc you mk come wrong, place to find job go to employment agency I hope you can be hire not in eotc.

  ReplyDelete
 9. Hello Aba Srlama

  Have you heard what' doing MK around DC?
  They decided to sen some representatives to Holy Synod in Ethiopia to complain about Abune Fanuel and they also planed to give money for Bishops who are power full to be transfer Aba Fanuel by corapying.

  ReplyDelete
 10. aba serek tihut mhonachewonma bkerb yemiyawok yawkachwal. manam aynekagem...abatoch btnikugne behaset semachun atefalehu eyale ymiyasferarawon mk bedefret ytgafetu ewonetgna menekuse... ahunme amlak yagzot kemaket beker men yibalal???

  ReplyDelete
 11. so funny haha ewinetina nigat.....
  yihe anonymous temechachihu erasachihu comment tisifalachihu meselagn mechem chinkilat yalew yihen yakil lewishet ayitebaberim lezawim orthodox kehone kemenafikan gar ayitebaberim
  lib yisten

  ReplyDelete
 12. if any thing happen to abune fanuel it should be the last age of mk to burried forever.

  ReplyDelete
 13. Leb yestem, go beg tera and buy yebeg leb. Tera mk.

  ReplyDelete
 14. « ማኅበሩ አያንቀላፋም»

  እንቅልፍ ለሰዎች የተሰጠ የሥጋ እረፍት ነው። «ቀን ለሰራዊት፣ሌሊት ለአራዊት»እንዲሉ! ዛሬ ግን ዓለማችን ቀንና ሌሊቱን አቀላቅላው ሰውም አራዊቱም ጉዞአቸው ባንድ ሆኗል። በሌሊት! ከነዚህ ቀኑንም ሌሊቱንም ከማያንቀላፋው ሀገርኛ ድርጅት አንዱ ራሱን በራሱ የቅዱሳን ማኅበር ነኝ የሚለው «ማኅበረ ቅዱሳን» በቁልምጫ ስሙ «ማቅ» የተባለው ድርጅት ነው። በቤተክርስቲያን ውስጥ ስፍራውና ድርሻው ለጊዜው ባይገባንም ረጅምና ስውር እጁ የሌለበት ቦታ የለም በሚባል ደረጃ ያለእረፍት ይንቀሳቀሳል። ለዚህም ነው የጽሁፋችንን ርእስ «ማኅበሩ አያንቀላፋም» ያልነው። አዎ! ማኅበረ ቅዱሳን አያንቀላፋም። የማያንቀላፋው ራሱን የቤተክርስቲያን ተጠሪ በማድረግና ሲኖዶሱ ባልሰጠው ውክልና በቤተክርስቲያኒቱ መዋቅር ውስጥ ስውር እጁን እንደአባጨጓሬ እያርመሰመሰ በመገኘቱ ነው። ማኅበሩ በሲኖዶስ መሃል ቁጭ ብሎ በስውር እጁ ጳጳስ ሆኖ ይወስናል፣ ያስወስናል፣ይከራከራል፣ይሞግታል። ለሲኖዶሱ አጀንዳ ይቀርጻል፣ የማይስማማውን ይጥላል፣ የፓትርያርኩ የራስ ህመም እስኪነሳ ያሳብዳል። ምክንያቱም ማኅበሩ ጳጳስ ስለሆነ አያንቀላፋም። በአምሳለ ጳጳስ «ማኅበረ ቅዱሳን ባይኖር ቤተክርስቲያን ምን ተስፋ አላት» ያሰኛል። በአድባራትና ገዳማትም መካከል ሳያንቀላፋ በአለቃነት ወይም በሀገረ ስብከት ደረጃ በሥራ አስኪያጅነት ወይም በመምሪያ ኃላፊነት ውስጥም ኅቡእ መንፈስ ሆኖ ይንቀሳቀሳል። የሰባኪዎችን፣የሰንበት ት/ቤቶችን ወይም የምእመናንን ማንነት ይቆጣጠራል፣ ይመረምራል፣ ይሰልላል። ማኅበረ ቅዱሳን አያንቀላፋምና እዚህም ቦታ አለ። ንግዱ ውስጥ! ይነግዳል፣ያስነግዳል። ግብርና ታክስ የማይከፍል የንግድ ተቋም ሆኖ በሆቴሎች፣ በሱቆች፣ በንዋያተ ቅድሳት መሸጫዎች፣በኢንኮርፖሬትድ ድርጅቶች፣ በህትመት፣ በሚዲያ ውጤቶች ውስጥ ሁሉ አለ።


  ስለማያንቀላፋ ለቤተክርስቲያኒቱ ጥናት የሚያጠናላት እሱ ነው። ማኅበሩ እንደቀንድ አውጣ ባንቀላፋ ሲኖዶስ መካከል የተገኘ ንቁ በመሆኑ ሰዶ በማሳደድ ፖሊሳዊ ሥራ ውስጥም እጁ አለ። ግለሰቦችን በግለሰቦች በኩል ሙልጭ አድርጎ ያሰድባል።(ዘመድኩንን ልብ ይሏል?) ከኋላ ሆኖ ጠበቃ ያቆማል፣ዜና ይሰራል፣ ሲሞቀው ወሬውን ያራግባል።(በደጀ ሰላም) ይመሰክራል፣ ያስመሰክራል፣ ሲጠላ ይጥላል፣ ሲወድ ደግሞ ይወዳጃል።(ዘሪሁን ሙላቱን የመሰሉ) ኃጢአት ለእርሱ ዋጋ የሚኖረው ተመንዝሮ በሚያስገኘው ውጤት እንጂ ኃጢአትን ከመጸየፍ አንጻር አይደለም። እንደቤተክርስቲያኒቱ ሕግ ነውራሞች እስከተስማሙት ድረስ ለእርሱ ቅዱሳን ናቸው፣ የማይስማሙት ደግሞ ወደሲኦል መወርወር አለባቸው ብሎ ይዋጋቸዋል፣ ያዋጋቸዋል፣ ከፊት ቀድሞ ወጥመድ ያኖርባቸዋል። ከኋላ ሆኖ ጀርባቸው ላይ ጥላት ይቀባቸዋል። (አባ ፋኑኤልን ልብ ይሏል?) ማኅበሩ እጁ የሌለበት ቦታ የለም። መንፈሱ ሁሉ ገብ ነው። ስለዚህ ማኅበረ ቅዱሳን አያንቀላፋም። ሲኖዶስ በስም ጠቅሶ እነእገሌ ተሐድሶ ስለሆኑ ቢችሉ በንስሃ እንዲመለሱ፣ ፈቃደኛ ካልሆኑ ተወግዘው እንዲለዩ ሳይል ማኅበሩ ራሱ ስም ጠርቶ ያወግዛል፣ያባርራል፣ በር ይዘጋል፣ ደብዳቤ ይጽፋል፣ ያጽፋል። ስለማያንቀላፋ ሁሉ ቦታ መንፈሱ ይሰራል። በየመድረኩ ማስተማርና መስበክ የሚችሉት ፈቃድ የተሰጣቸው ብቻ መሆን እንዳለበት ሲኖዶስ ከተናገረ እሱ ቃሉን መንዝሮና ተርጉሞ እነእገሌ ይከልከሉ፣ እነእገሌም ይሰቀሉ ሲል ኢትዮጵያዊ ኢንተርፖል ሆኖ ይቆጣጠራል፣መግለጫ ይሰጣል፣ ያሰጣል። ኦርቶዶክሳዊነታቸው ባልተገፈፈና ውግዘት ባልተሰጠበት ወገን መታገዝ በራሱ ብቻውን በቂ ባለመሆኑ የማኅበሩ ፈቃድ በየትኛውም ቦታ የግድ መሆኑን ሰውር አዋጅ ያውጃል። ያለበለዚያ ሁሉም ቦታ በሚገኘው በስውር መንፈስ እጁ ያግዳል፣ ያሳግዳል።(የልብ ህሙም የእንዳለ ገብሬን ጉዳይ ልብ ይሏል?) ሌላው ቀርቶ ማኅበሩ ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ ወይም ያለሲኖዶስ ሕጋዊ መግለጫ ራሱ መግለጫ ይሰጣል፣ ለፖሊስ፣ለደህንነት ይወነጅላል፣ያስወነጅላል። በግለሰቦች ነጻነት ውስጥ ጣልቃ ይገባል። በደብዳቤ ስም ጠርቶ መብት ይገፋል። ስም ያጠፋል። የመንቀሳቀስን መብት ለማገድ ይደክማል፣ ይወነጅላል። በሕግ ከሚያስጠይቁ የመብት ገፈፋ ተግባራቱ መካከል አንዱ አባ ድሜጥሮስ በተባለ ጳጳስ እጅ ማኅበሩ የጻፈውና ስም እየጠራ ከሀገር ያለመውጣት የውንጀላ ደብዳቤውን ከደጀሰላም ስውር አፉ አግኝተናልና ለእናንተም ሆነ መብታቸው ለተገፈፈ ወገኖች እንዲደርስ አውጥተነዋል።  The R\rest of the letter see on Dejebirhanblogspot

  ReplyDelete