Monday, February 13, 2012

የሁለቱ ሲኖዶሶች አባቶች የእርቅ ድርድር በሰሜን አመሪካ አሪዞና ስቴት ተጀመረ

በውጩ ሲኖዶስ በኩል ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ፣ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ፣ ሊቀ ካህናት ምሳሌ፣ መላከ ገነት ገዛኸኝ፣ የቀረቡ ሲሆን። ከሀገር ቤቱ ሲኖዶስ ደግሞ ብፁዕ አቡነ ገሪማ፣ ብፁዕ አቡነ አትናስቴዎስ፣ ንቡረ ዕድ ኤልያስ ቀርበዋል። ሁሉም አባቶች በትናንትናው ዕለት ጠቅለው ገብተው ዛሬ የሚደራደሩባቸው አጀንዳቸውን ለአስታራቂ ኮሚቴው አቅርበዋል።
 በውጩ ሲኖዶስ በኩል ከቀረቡት አጀንድዎች ውስጥ የሚከተሉት ጠንካራዎችና እርቁን የሚፈታተኑ እንደሚሆኑ ተገምቷል።


1ኛ ለቅዱስ ፓትርያርኩ መነሣት መሰደድም ምክንያት የሆነው የወያኔ መንግሥት ነው፤ መንግሥት በቤተ ክርስቲያን ነገር እንዳይገባ ገደብ እንዲደረግበትና ሁለቱም ሲኖዶሶች በዚህ ጉዳይ ላይ ጠንካራ ውሳኔ እንዲያስተላልፉ።
2ኛ የአዲስ አበባው ሲኖዶስ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን ማፍረሱን ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን መደምሰሱን ማመን አለበት፣ በጉልበትና በወታደር ኃይል ሥልጣንን ይዞ ከቤተ ክርስቲያን ራስ ላይ መቀመጥ የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ዓላማ አይደለም፤ ይኸ ታምኖበት መሻሻል፤ መታደስ አለበት፤ ወደፊትም በቤተ ክርስቲያኒቱ ታሪክ ስሕተት መሆኑ ታምኖበት ለሚቀጥለው ትውልድ መሠረታዊ መርሆ መቀመጥ አለበት።

3ኛ አጠቃላይ ብሔራዊ እርቅ ሆኖ ስደተኛው ሁሉ እንዲመለስ የታሠረው ሁሉ እንዲፈታ ካልሆነ ቤተ ክርስቲያን ልጆቿ ታስረው ተበትነው እንዴት ያለ እርቅ ልታደርግ ትስማማለች? የቤተ ክርስቲያን እርቅ ለሀገርም ሰላም የሚጠቅም እንዲሆን ይህ መደረግ አለበት።
 እነዚህ ሦስት አጀንዳዎች ከበርካታ አጀንዳዎች መካከል በውጩ ሲኖዶስ በኩል ብርቱ አቋም የተያዘባቸው ናቸው። በተለይም ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ በነዚህ ላይ ጠንካራ አቋም እንዳላቸው ታውቋል።

 በሀገር ቤቱ ሲኖዶስ በኩል የቀረቡት አጀንዳዎች
1ኛ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ሥልጣናቸውን የለቀቁት በሕመም ምክንያት በገንዛ ፈቅዳቸው መሆኑን እንዲያምኑ ለድርድር ይቀርባል።

2ኛ የተሰደደ ሰው በውጭ ሀገር ሌላ ሲኖዶስ አቋቁሞ ሌሎች ጳጳሳትን መሾሙ ትክክል አይደለም በዚህ መተማመን ይገባል የሚሉት እርቁን የሚፈታተኑ አቋሞች ናቸው።
ከዚህ በተረፈ የሀገር ቤቱ ሲኖዶስ የመደራደር ሥልጣኑ አናሳ ነው ምክንያቱም እዚሁ መንበረ ፓትርያርክ ውስጥ የተወሰኑ ውሳኔዎችን የማስፈጸም እንጂ ሰጥቶ የመቀበል አቅም ይኖረዋል ተብሎ አይታመንም። ምክንያቱም ድርድሩን የሚቆጣጠር የበላይ አካል አለበትና በራስ መተማመን አይታይም። ከዚህ በፊት በተደረገው የድርድር ሙከራ ከሀገር ቤት የመጡት ተደራዳሪዎች ከሽማግሌዎች በሚቀርቡ ሐሳቦች ሁሉ ወደ አዲስ አበባ ስልክ በመደወል እሺ ወይም እምቢ እያሉ ይመልሱ ነበር በራሳቸው ተመምነው ውሳኔዎችን የማሳለፍ ብቃት ጎድሏቸው ታይቷል። የውጩ ሲኖዶስ ግን እዚያው ተነጋግሮ ሐሳቦችን የመወሰን ብቃት ያለው ነው። ዛሬም በአሪዞና የሚደረገው ውይይት ይህ ኮፊንደስ ማጣት ያሰጋዋል።

ሌላው ከዚህ በፊት የሀገር ቤቱ ሲኖዶስ ፓትርያርክ መርቆርዮስ ወደ ሀገራቸው ገብተው ጥሮታቸውን እያገኙ በአንድ ቦታ እየጸለዩ እንዲኖሩ፤ ሌሎች ሦስቱ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ፣ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ፣ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ወደ ሀገር ቤት ገብተው ሀገረ ስብከት እንዲሰጣቸውና በሥራ እንዲሠማሩ፤ አዳዲሶቹ ጳጳሳት በሀገር ቤቱ ሲኖዶስ ተቀባይነት አግኝተው ጵጵስናቸው እንዲጸድቅላቸው መወሰኑ የውጩን ሲኖዶስ አባቶች አስቆጥቷል። ውሳኔ ድርድር አይደለም እኛ ቀኖና ፈረሰ ብለን ተሰደድን እንጂ እንጀራ ሹመት ሽልማት አላገኝንም ብለን አልተሰደድንም ጥያቄያችን የፍትሕ እንጂ የእንጀራ አይደለም ብለዋል።
 ሁለቱም አባቶች አንዳድ እርምጃ ቢራመዱ እርቁ እንደሚሳካ እናምናለን ሁለቱም ማሰብ ያለባቸው የሚመጣውን ትውልድና ሀገሪቱን ቤተ ክርስቲያኒቱን እንጂ የዛሬውን ሁኔታ መሆን የለበትም እንላለን።

 ሌሎች የማህበረ ቅዱሳንና የተሀድሶዎች ግጭቶችም ወደ ፊት የቤተ ክርስቲያንን ሰላም ስለሚጎዱ አብረው ቢታዩ መልካም ነበር የሚሉ አስተያየት ሰጭዎች በርካቶች ናቸው። ሌሎችን ዜናዎች እንደደረሱን እናቀርባለን
 ቸር ወሬ ያሰማን  


26 comments:

 1. ከዚህ መለያየት ያተረፈ አንድም ወገን የለም:: እባካችሁ አባቶች ዋነኞቻችሁ የነገሯችሁን አስቡ:: በየአጥቢያ ቤተ ክርስቲያናቱ የሚታየዉ ጥል፣ክርክር እና ሽኩቻ ወደ ቤተ ክርስቲያን የምንሄድበትን ዋና ዓላማ እንድንረሳ ያደረገን ስለሆነ በቀራንዮ አደባባይ ላይ ስለተንገላታው፣ ስለቆስለው፣ እና ስለ ሞተልን አምላካችን ብላችሁ የአንድነትንና የሰላምን ወሬ አሰሙን:: እስቲ ጠላታችን ዲያቢሎስ ይፈር:: እስቲ እኛ ኢትዮጵያዉያን የምንታወቅበት አንዱ ጠባይ ልዩነታችንን በመነጋገር መፍታት ይሁን::

  የሰላም አምላክ ልዑል እግዚአብሄር የጠፋዉን ፍቅርና አንድነት ይመልስልን::

  ReplyDelete
 2. Aba selama & Deje selam eyalu metarek kbadi new were tabezalachihu yesew sim tatsefalachihu chigir tababizalachihu gebena meshefen yemibal neger atawkum yenohi lij keneann timeslalachihu Wa Wa Wa ahunim sew metarek - mesmamat yemichilew enante Good nows -melkam were menager sitjemiru new

  ReplyDelete
  Replies
  1. Egziabher Yibarkih!! Tikikl bilehal! Dejeselam & abaselama wanawochu ye-chigr minchoch nachew.

   Delete
 3. መለያየትና መከፋፈል የሰይጣን መሣሪያ መሆን ማለት ነው ፡፡ አንድነቱ እንዲመጣ እግዚአብሔር ይርዳን እላለሁ ፤ እንኳንስ ተከፋፍለን አንድ ሆነንም ብዙ አላማረብንም ፡፡ ይኸን መከፋፈል ለግባቸው መሣካት የማይፈልጉት አይታጡም ፤ ቢሆንም የተጀመረው ሙከራ መልካም ነውና እግዚአብሔር ለሁሉም ልቡና ይስጥልን ፡፡ የእነሱ ጅምር በስምምነት የሚቋጭ ከሆነ ፣ የቡድን አባቶች ስለማይኖሩን ልጆችም ወደ አንድነት ይመጣሉ ፡፡ ቤተክርስቲያንም ባለቤት ፤ ምእመኑን ግራ ያጋባውም ስብከትና ትምህርት ሁሉ ተቆጣጣሪ ይኖረዋልና ይቆማል ፡፡ ሰይጣን ድል ሊመታ ቀኑ ቀርቧል ማለት ነው ፡፡ እልል በሉ ክርስቲያኖች ሁሉ !!!

  ReplyDelete
 4. አስተያየት ከመስጠቴ በፊት ማሳወቅ የምፈልገው በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያን በጎሳ ከፋፍሎ እየገዛ ያለው መንግሥት ደጋፊ አለመሆኔን ነው።

  ከዚህም በላይ በጎሳ በሽታ የተለከፈውና በአባ ጳውሎስ የሚመራው የወቅቱ ሲኖዶስ ለኢኦተቤ/ክ መልካም መንፈሳዊ አመራር ይሰጣታል የሚል ከንቱ እምነትጎሳ የለኝም:: "ስደተኛ ነኝ የሚለውም ሆነ ሀገር ቤት ያለው ቡደን ሁለቱም የመሪያቸውን የኢየሱስን ትዕዛዝ በግል ጥቅምና በገንዘብ የለወጡ መንፈሳዊነት የሌላቸው ቡድኖች መሆናቸውን ተረድቻለሁ::

  ከዚህ ውጭ ግን አቡነ መርቆሬዎስ ሕጋዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ናቸው ለሚለው ከሁሉ አስቀድሞ በደርግ አገዛዝ የጎንደር ክፍለ ሀገር ሊቀ ጳጳስ በነበሩበት ጊዜ እነ ሻለቃ መላኩ ተፈራ በሕዝቡ ላይ ያን መሳይ መከራ ሲያወርዱበት ምንም ሳይናገሩ በዝምታ በማሳለፋቸው ላደረጉት መልካም ትብብር የተቸራቸው ስጦታ እንጂ ለቦታው የሚመጥኑ አባት ሆነው አልነበረም። ይህንንም አሁን በሕይወት ያሉት ሊቀ ሥልጣናት አባ ሀብተ ማርያም ወርቅነህ ይመሰክራሉ።

  የኢሕአዴግ አገዛዝ ሥልጣን እንደያዘ ምን ሊደርስባቸው እንደሚችል በመጠርጠር በነ ሊቀ ሥልጣናት አባ ሀብተ ማርያም ወርቅነህ አማካሪነት ታምሜአለሁ ብለው ከመንበረ ፕትርክና ረብሻ ሳያስነሱ ይውረዱ ተብለው በተመከሩት መሰረት ወደውና ፈቅደው ያለማንም አስገዳጅነት ለቀቁ። እውነቱ ይህ ለመሆኑ ሊቀ ሥልጣናት አባ ሀብተ ማርያም ወርቅነህ የጻፉትን መጽሐፍ ማንበብ በቂ ማስረጃ ነው። አሁን ወደ ኋላ ተመልሶ በሌለ ሥልጣን ሕጋዊው ፓትርያርክ ብሎ መጥራት የሕጻናት ጨዋታ ነው። እራሱ ሕጋዊው ፓትርያርክ የሚለው አጠራር የቀልድና የሃሰት መሆኑን ያሳያል። እውን አሁን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመን እሳቸውን ፓትርያርክ አድርጎ ይቀበላል ብሎ የሚያምን ወገን አለ? በሕልም ዓለም መኖር ይፈቀዳል። አሜሪካ ሰው ያለመውን ሊያገኝ ይችላል ቢባልም እንደዚህ ያለውን ቅዠት ግን ሕልም ልንለው አይገባም።

  ReplyDelete
  Replies
  1. your talk is not valid. you are a lier .Abune merkoriyos is been bushed by wyane to live office do you read english read the weklike info what tamrat lyneh says. Regardles of you weyane and tryant belive any think Our patriaric Abune Merkorious Will be back his home land with our stragel mke my word.
   What you saying about you do not sapport wayne lie. you are not sapporter ..you are wyane. chalenge me in any diraction all ethiopians are expecting the true patriaric of ethiopia abune Merkorioes will be back. he does not want the power but we need him to save the charch.belive me he is the firsst ethiopian hero patriaric in history of the church. in the future he will be one of kedusan that the church will mke a tabot in his name.

   Delete
  2. "he is the firsst ethiopian hero patriaric in history of the church. in the future he will be one of kedusan that the church will mke a tabot in his name."??? Really? You must be kidding me! Kidus? Hero? What did He do to be labelled as a hero? Pls open your eyes and learn the truth. Both are selfish and zeregnoch! May God give a true sheeper for EOTC.

   Delete
  3. I AGREE MY BELOVED BROTHER

   "he is the firsst ethiopian hero patriaric in history of the church. in the future he will be one of kedusan that the church will mke a tabot in his name."??? Really? You must be kidding me! Kidus? Hero? What did He do to be labelled as a hero? Pls open your eyes and learn the truth. Both are selfish and zeregnoch! May God give a true sheeper for EOTC.

   Delete
  4. በጣም እንገርማለን! አስተያየት ከመስጠቴ በፊት ያለው መንግስት ደጋፊ እንዳልሆንኩ ይታወቅልኝ ብሎ ጀምሮ የማይወዳቸውን ጳጳስ በርሱ ጅራፍ አርባ መግረፍ ያልፍርድ ምን ይባላል። ጳጳሱን ሲወነጅል የጎንደር ሃገረስብከት በነበሩበት ጊዜ ብሎ ይጀምርና ለምስክርነትም ሊቀሥልጣናት ያለውን ያስከትላል። ዘይገርም አንተና ሊቀሥልጣናትስ ምን ትሰሩ ነበር በዚያን ወቅት? ክርስቲያኖች ነን መጽሃፋችን አትፍረድ ሲለን አትፍረድ ነው እስኪ ጳጳሱ ዝም ብለዋል ብለህ በመሰከረ አፍህ አንተ በዚያን ወቅት ታደርግ የነበረውን ጻፍልን። አብዮት ጠባቂ ነበርክ ወይስ ተጋዳላይ? ውንድሜ እንዱ ያንቦቀቦቀህስ ምንድነው ስምህን ደብቀህ ፎቶህን ሳትለጥፍ ለጻፍከው በታኝ ሃሳብ እንዲ አይደለሁም ማለት ምን ይጠቅማል? እንደኔ በዚህ ወቅት ይጠቅማል የምለው እነኚህ ለስብሰባ የተቀመጡ ጳጳሳትን በእግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስ መሪነት ወደ መልካም መግባባት እንዲደርሱ በያለንበት መጸለይ ነው። ስብሰባቸው ላይ ዳመናን የሚያጠላ ወሬ ማውራቱ አስፈላኢ አይደለም። የክርስቲያን መለያው እኮ ትዕግሥት ነውና እስኪ ስብሰባው በመልካም ውጤት እስኪፈጸም ስለተሰራውም ሃውልት ሌላም ሌላም ወሬዎችን እውነት ቢሆኑም ከማውራት እንታቀብ። ካላወራን እንፈነዳ ክሆነም እራሳችንን እንፈትን። በዚህ ስብሰባ ላይ እግዚአብሄር አምላካችን አንተ የፈቀድከው ሁሉ ይከናወን።

   Delete
 5. anet lemene afehen zegeteh abatoche beslam enedifetut tselot ataderegem... enede anet ayenetu sera fet gena legan yeh yehonal eyalek yesewen hesabe tebetatenaleh ..
  gena lesebeseba sayeqemetu tebetenu beleh taseweraleh..

  ReplyDelete
 6. Aba Selama,

  ማህበረ ቅዱሳን\ማቅ\ማሰ\ የአባቶች መታረቅና መስማማት ለስውር አላማቸው ስለማይመቻቸው ቀን ከሌት እንዳይታረቁ ግድግዳ ሲጭሩ ነው የሚያድሩት፣ እስከ ዛሬም ቢሆን እኮ እንዳይታረቁ ከፍተኛ አሻጥር እያደረጉ የራሳቸውን ድብቅ አጀንዳ ለማራመድ የሁለቱ መጣላትን ሲያባብሱ ኖረዋል አሁንም እረፍት የላቸውም። አባ ጳውሎስን ቢያንስ ለአሥራ አምስት አመት ሲያጭበረበሩና ለቤተክርስቲያን ቆመናል በማለት ሲያታልሉአቸው፣በቤተክርስቲያን ሥም ሲነግዱና ድብቅ ፖለቲካቸውንጳጳሳትን በአንዳንድ ጥቅም በመያዝ የእነሱ ተባባሪ እያደረጉ ቤተክርስቲያናችንን እንዲህ ብጥብጥ ያደረጉአት ማቅ መሆኑን ሁሉም ያውቃል። አሁን አሁን ግን ቅዱስነታቸው የማቅ ድብቅ ደባ ስለገባቸው ቢዘገዩም እንደበፊቱ ሊያጭበረብሩአቸው አልቻሉም። በዚህ ጊዜ ማቅ ሁልጊዜም እሱን የማይደግፉ ክርስቲያኖችን ለማስጠላትና ከቤተክርስቲያን ለማስቀረት ለሌሎች የሚጠቀምበትን የስም ማጥፋት ዘመቻውን \ተሃድሶ\ መናፍቅ\ እያለ በፓትሪያሊኩ ላይ ማስወራትና ማሳደም ጀመረ።
  በፊታቸው ግን ቅዱስነትዎ እያለ የቤ\ክ ልጅ መምሰልና የሚፈልገውን ነገር ለማስፈፀም ሲል፣ በሌላ ቦታ ግን ከፍተኛ
  አድማና የሥም ማጥፋት ዘመቻቸውን እያቀጣጠሉ ነው፣ በተለይማ በውጭ የምንኖረውን ኢትዮጵያውያንን ሁሉ በማሳደምና ጥላቻ በማሳደር ረገድ የሚጫወቱሚና ቀላል አይደለም። ወደ ዋናው ነጥቤ ልመለስና ማቅ ለራሱ ድብቅ አላማ ሲል ብቻ ሁለቱ ሲኖዶሶች እንዲታረቁ በፍፁም አይፈልግም። በስደት ያሉ ሊቃውንት አባቶቻችንን እኮ ሲሳደብና ስም ሲያጠፋ ነው የኖረው። ማቅ የወንድ ወንበዴና የሴት ወንበዴ የተጠራቀመበት የወሮ በላ ድርጅት እንጂ የሐይማኖት አይደለም።
  ይህንንም ደግሞ እየዋለ እያደረ እግዚአብሔር ገለጠባቸው እንጅ እነሱማ አላማቸው ሌላ ነበር ፣ ነገር ግን ቤ\ክ የገሃነብ ደጆች እንኩአን አይችሉአትም። በአጠቃላይ ማለት የምፈልገው ለማቅ ቦታ መስጠቴ ሳይሆን፣ አንዳንድ አባቶች እንዳልኩአችሁ በተለያየ ጥቅማጥቅምና ጉዳዮች ከማቅ ጋር ለመወገን ሆዳቸው እያወቀ ለሐቅ አለመቆሙን እያወቁ ይደግፉታል፣ ብቻቸውን አግኝተህ ደግሞ ስታነጋግራቸው ማቅ ለቤተክርስቲያናችን ጠላትና ከፋፋይ እንደሆነ ይነግሩሃል፣ በአድማ ግን ከማህበሩ ጋር ሲሆኑ ይታያሉ። ስለማቅ ተንኮልና የሰይጣን ሥራ ቀንና ሌሊት ቢፃፍ አይበቃም፣ በጠቅላላ አባቶች እነዚህን ወሮበሎች በምንም ነገር ውስጥ ሳያስገቡአቸው በራሳቸው ቁዋንቁዋ ተነጋገረው በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት በፍቅር ተነጋግረው ችግራቸውን እንደሚፈቱት ተስፋ አለኝ። እግዚአብሔር ከኛ ጋር ነው። የኛ ልብ ግን ተጠራጣሪ ነው። በተረፈ እርቁ በሰላም እንዲያልቅና እንዲሳካ እንፀልይ።
  ስለ ማቅ እንደዚህ የምናገረው በደንብ የሚሠሩትን ስለማውቅ ነው እንጂ በጥላቻ እንዳይመስላችሁ። እግዚአብሔር ወደ ተቀደሰ አላማ ይመልስልን እንጂ እንዲጠፉም አንሻም።
  አባ ሰላማዎች የክርስቶስ ሰላምና ፀጋ ይብዛላችሁ፣ ሐይሉን ፣ብርታቱን፣ ፅናቱንና ፍቅሩን መንፈስ ቅዱስ ያድላችሁ።
  በርቱ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. cher yasemah tikikilneh !!!!!yihinin hulu awken agerbet yalenew makin lemetagel korten tenesstenal! በማሳደምና ጥላቻ በማሳደር ረገድ የሚጫወቱሚና ቀላል አይደለም silezi enberta.....

   Delete
  2. dear Moderator pls post my replies to the above comment.I know U don't want truth to be told

   Delete
 7. ማህበረ ቅዱሳን\ማቅ\ማሰ\ የአባቶች መታረቅና መስማማት ለስውር አላማቸው ስለማይመቻቸው ቀን ከሌት እንዳይታረቁ ግድግዳ ሲጭሩ ነው የሚያድሩት፣ እስከ ዛሬም ቢሆን እኮ እንዳይታረቁ ከፍተኛ አሻጥር እያደረጉ የራሳቸውን ድብቅ አጀንዳ ለማራመድ የሁለቱ መጣላትን ሲያባብሱ ኖረዋል አሁንም እረፍት የላቸውም። አባ ጳውሎስን ቢያንስ ለአሥራ አምስት አመት ሲያጭበረበሩና ለቤተክርስቲያን ቆመናል በማለት ሲያታልሉአቸው፣ በቤተክርስቲያን ሥም ሲነግዱና ድብቅ ፖለቲካቸውን ጳጳሳትን በአንዳንድ ጥቅም በመያዝ የእነሱ ተባባሪ እያደረጉ ቤተክርስቲያናችንን እንዲህ ብጥብጥ ያደረጉአት ማቅ መሆኑን ሁሉም ያውቃል። አሁን አሁን ግን ቅዱስነታቸው የማቅ ድብቅ ደባ ስለገባቸው ቢዘገዩም እንደበፊቱ ሊያጭበረብሩአቸው አልቻሉም። በዚህ ጊዜ ማቅ ሁልጊዜም እሱን የማይደግፉ ክርስቲያኖችን ለማስጠላትና ከቤተክርስቲያን ለማስቀረት ለሌሎች የሚጠቀምበትን የስም ማጥፋት ዘመቻውን \ተሃድሶ\ መናፍቅ\ እያለ በፓትሪያሊኩ ላይ ማስወራትና ማሳደም ጀመረ።
  በፊታቸው ግን ቅዱስነትዎ እያለ የቤ\ክ ልጅ መምሰልና የሚፈልገውን ነገር ለማስፈፀም ሲል፣ በሌላ ቦታ ግን ከፍተኛ
  አድማና የሥም ማጥፋት ዘመቻቸውን እያቀጣጠሉ ነው፣ በተለይማ በውጭ የምንኖረውን ኢትዮጵያውያንን ሁሉ በማሳደምና ጥላቻ በማሳደር ረገድ የሚጫወቱሚና ቀላል አይደለም። ወደ ዋናው ነጥቤ ልመለስና ማቅ ለራሱ ድብቅ አላማ ሲል ብቻ ሁለቱ ሲኖዶሶች እንዲታረቁ በፍፁም አይፈልግም። በስደት ያሉ ሊቃውንት አባቶቻችንን እኮ ሲሳደብና ስም ሲያጠፋ ነው የኖረው። ማቅ የወንድ ወንበዴና የሴት ወንበዴ የተጠራቀመበት የወሮ በላ ድርጅት እንጂ የሐይማኖት አይደለም።
  ይህንንም ደግሞ እየዋለ እያደረ እግዚአብሔር ገለጠባቸው እንጅ እነሱማ አላማቸው ሌላ ነበር ፣ ነገር ግን ቤ\ክ የገሃነብ ደጆች እንኩአን አይችሉአትም። በአጠቃላይ ማለት የምፈልገው ለማቅ ቦታ መስጠቴ ሳይሆን፣ አንዳንድ አባቶች እንዳልኩአችሁ በተለያየ ጥቅማጥቅምና ጉዳዮች ከማቅ ጋር ለመወገን ሆዳቸው እያወቀ ለሐቅ አለመቆሙን እያወቁ ይደግፉታል፣ ብቻቸውን አግኝተህ ደግሞ ስታነጋግራቸው ማቅ ለቤተክርስቲያናችን ጠላትና ከፋፋይ እንደሆነ ይነግሩሃል፣ በአድማ ግን ከማህበሩ ጋር ሲሆኑ ይታያሉ። ስለማቅ ተንኮልና የሰይጣን ሥራ ቀንና ሌሊት ቢፃፍ አይበቃም፣ በጠቅላላ አባቶች እነዚህን ወሮበሎች በምንም ነገር ውስጥ ሳያስገቡአቸው በራሳቸው ቁዋንቁዋ ተነጋገረው በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት በፍቅር ተነጋግረው ችግራቸውን እንደሚፈቱት ተስፋ አለኝ። እግዚአብሔር ከኛ ጋር ነው። የኛ ልብ ግን ተጠራጣሪ ነው። በተረፈ እርቁ በሰላም እንዲያልቅና እንዲሳካ እንፀልይ።

  ስለ ማቅ እንደዚህ የምናገረው በደንብ የሚሠሩትን ስለማውቅ ነው እንጂ በጥላቻ እንዳይመስላችሁ። እግዚአብሔር ወደ ተቀደሰ አላማ ይመልስልን እንጂ እንዲጠፉም አንሻም።

  አባ ሰላማዎች የክርስቶስ ሰላምና ፀጋ ይብዛላችሁ፣ ሐይሉን ፣ብርታቱን፣ ፅናቱንና ፍቅሩን መንፈስ ቅዱስ ያድላችሁ።
  በርቱ።

  ReplyDelete
 8. for the sake of TEWAHDO AND her groom LORD JESUS CHRIST, our fathers please lower your ego, open your eyes and your heart, remember the one who forgave you and us in his last moment in the cross, a king of kings who was born in manger, who washed his disciples feet at the last supper. Don't you have fear of God, what are you going to answer when you are called by him, it is clear that none of have left a decade, please do not destroy his bride, orthodox TEWAHDO, keep her as ONE AND FOREVER

  ReplyDelete
  Replies
  1. thanks whoever wrote the above comment that wha everybody should need to say and pray...thanks

   Delete
 9. betam yigermal...minale sile kirstos bilew bitarequ..yihe hulu ye weyane sera new.

  ReplyDelete
 10. በጣም ያሳዝናል ምናለ ፊታቸው የተሰቀለውን ክርስቶስን ቢያስቡ ይህ ሁሉ እራስን አለመካድ ነው፡፡ ስለሰላም ይሰብኩልናል እነሱ ግን ሰላም የላቸውም፣ስለፍቅር ይሰብኩልናል እነሱ ግን ፍቅር የላቸውም ለሁለቱም ልብ ይስጣቸው ፡፡ መሰረታቸውን እረስተዋል፡፡ የመንፈስ ውጊያ ሳይሆን የሥጋ ውጊያ ላይ ናቸው፡፡ ሁሉም ያልፋል የማያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር ሚያስተምሩና ቢማሩ ይጠቅማል፡፡

  ReplyDelete
 11. yemnidenwo bekristos amlakachen kedengle mariyam bensaw sigga ena demu new enji beabunoe pole or merkoriyos aydelem ayniachenen keswoch lay enansa yetesekelwon amlak enmelket ,,lebona endisetachew yemeder seltan halafi ena yemayreba mengestachenm besmay endehone yigleslachewo ..tebaltewo aleku ahunes astelugne yet heden eneref bebete crstiyanchen kalasarefun?????????...kaltesmamu terargo yemibejenen yishumelen,

  ReplyDelete
 12. We now fire all of them and replace them by mk.

  ReplyDelete
 13. we, all know who aba selama is. you have no courage and rite to talk about this issue!!!we are 100% sure that the issue will be resolved one day, the day determined by God. that day will be the day those heretics like aba selama will get their destination!

  ReplyDelete
 14. እውነተኛ ክርስቲያን አባቶች ነን ካሉ
  ሁለቱም ፓትርያርኮች ከፓትርያርክነቱ ወርደው በገዳም ተወስነው
  በጸሎት ይቀመጡ
  በቅድስናቸው በመንፈሳዊነታቸው በብቆታቸው ከታመኑት 3 አባቶች
  - በአባ ጳውሎስ በወገን እና ገንዘብ የተሾሙት ከዚህ ይገለሉ--
  አንዱን የቤተ ክርስቲያን አባቶች እና እናቶች ወርቅና ገንዘብ የማይሹ
  የቤተክርስቲያን አባቶች ይምረጡ
  የሚመረጠውም ቤተ ክርስቲያንን ከወንድሞቹ አባቶች ጋር ሊመራ
  እንጂ ሊገዛ እንዳልተመረጠ ይወቅ
  ይህ ሲሆን ቤተ ክርስትያን የወንጌል ማስተማር ተልኮዋን የክርስቶስ መንግስትን መስበክን
  ለድሆች መቆምን ሐዋርያዊ ተግባርን ትቀጥላለች

  ReplyDelete
 15. Menaw Qalate eyemeretachehu betetsifu. lemen ereqe sibal torenet taweralathihu. Egziabheare naw dagnaw.

  For many shall come in my name, saying, I am Christ; and shall deceive many. And ye shall hear of wars and rumours of wars: see that ye be not troubled: for all [these things] must come to pass, but the end is not yet. For nation shall rise against nation, and kingdom against kingdom: and there shall be famines, and pestilences, and earthquakes, in divers places. All these [are] the beginning of sorrows.

  Matthew 24:5-8

  ReplyDelete
 16. fire them all and replace them with mk?????do u mean destroy mk and ever thing will be back to normal?

  ReplyDelete
 17. pls pray insted of play to wast your time by saying bad word the holy bible says do not say hard word at all (Eytsae abiy nger emafukmu)

  ReplyDelete