Wednesday, February 15, 2012

መሪጌታ ሙሴ ከጥንቆላ ተግባሩ እና ከሰይጣን ጋር ያደረገውን ቃል ኪዳን በማፍረስ ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ መጠጋቱን አስታወቀ

መሪጌታ ሙሴ ሕያው ተስፋ ከተባለ ሬዲዮ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ «አየረ ጴጥሮስ»  ከሚባል የአጋጋንንት አለቃ ጋር ቃል ኪዳን መመስረቱን የተናገረ ሲሆን ዋናውን የኢትዮጵያን ችግር አጋልጧል። አየረ  ጴጥሮስ የኢትዮጵያ ደብተራዎች ለመዋረስ የሚመርጡት አደገኛ ነፍሰ ገዳይ ጋኔን ነው። ይህን ያልንበት ምክንያት ብዙዎች እርሱን በተዋረሱ ባጭር ጊዜ ውስጥ ትዕዛዙን ባለመፈጸማቸው አንገታቸውን ቆልምሞ ሲገድላቸው በማየታችን ነው። መርጌታ ሙሴ ከሰይጣናዊ አሠራር ነጻ መውጣቱን የገለጸ ሲሆን ከንግግሩ መረዳት እንደሚቻለው የተማረና በቆሎ /ቤት ጊዜ ያሳለፈ ይመስላል።
  (ይህን አሳዛኝ እና አስደናቂ የሆነ ቃለ መጠይቅ ከዚህ ጽሑፍ መጨረሻ ላይ ስላስቀመጥን እንዲያዳምጡ እንጋብዛለን)

መርጌታ ሙሴ ይህን የጥንቆላ ሥራ ለመማር ያነሳሳው አንደኛ የሰሎሞን ጥበብ ነው ተብሎ በመምህሮቹ ስለተነገረው፤ ሁለተኛ ኑሮውን ለማሻሻል ወይም ባቋራጭ መንገድ ለመክበር አስቦ ነው። ከልጅነቱ ጀምሮ ሳይወድ በግድ ወደ ቆሎ / ቤት የገባው መርጌታ ሙሴ አንካሳ ስለሆነሰርቶ መኖር ስለማይችል  የደጀ ስላም ፍርፋሪ እየበላ እንዲኖር ታስቦ ነበርበቄስ ትምህርቱ እስከ ቅኔ መምህርነት የደረሰ ሲሆን ጎን ለጎን ጥንቆላውንም ተምሯል። ጥንቆላውን የተማረው በመደበኛ ትምህርቱ ሳይሆን አሥራ አምስት ሺህ ብር ከፍሎ ነው። የቤተ ክርስቲያናችን ሊቃውንት ጥንቆላን በመደበኛ ትምህርት አያስተምሩም፤ ነገር ግን አንዳንዶች የሰሎሞን ጥበብ ነው ብለው ስለሚያምኑ ለሚወዱት ደቀ መዝሙራቸው በሥውር ጥንቆላና አንዳድ ድግምቶችን እንደሚያስተምሩት የታወቀ ነው።
ዛሬም አንዳንድ ቀሳውስት ለታመሙና ለተቸገሩ የንስሐ ልጆቻቸው የቡዳ ቀለበት፤ የቅዠት፣ የቁርጥማት፣ ከጠላት ለመጠበቅ እያሉ አንዳንድ ድግምቶችንና እጸዋትን፣ ቅባቶችን ጠልሰሞችን እንደሚሰጡ ብዙ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ይህም በሥውር የሚደረግ ነው። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተሐድሶ እንቅሥቃሴን የፈጠረው እንደዚህ አይነቱ የተዋረደው ከከበረው ጋር ተቀላቅሎ በመገኘቱ ነው። እንደዚህ አይነቱን ጉድ ሌሎች ወደ አደባባይ እስኪያወጡልን ከምንጠብቅ ይልቅ ራሳችን ብናስተካክለው ይበጀን ነበር። ለምን የኢየሱስን ስም ደጋግመው ይጠራሉ ብለን የቤተክርስቲያናችንን አገልጋዮች በከንቱ ከምናሳድድ ይልቅ እንደዚህ አይነቱን የጥንቆላ ስራ ብንቃወም እንዴት ቤተክርስቲያናችንን በጠቀምን!  ወደ ፊት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን በአዋጅ የሰሎሞን ጥበብ የተባለውን ባዕድ ነገር እስክታወግዝ ድረስ፤ በርካታ የጥንቆላ ምሥጢራትን ማጋለጣችንን የማናቆም መሆናችንን አስቀድመን እንገልጣለን። ጠቅላይ ቤተ ክህነት ውስጥ እና በታላላቅ አድባራት በጥንቆላ የከበሩትን አገልጋዮችንም ለማጋለጥ በዝግጅት ላይ ስንሆን  ዘንዶ የታሠረባቸው ሆቴሎችንና ንግድ ቤቶችንም ወደ እግዚአብሔር ከተመለሱ ጠንቋዮች መረጃ እየሰበስብን ነውና ይህንንም እናቀርባለን።
ለማነኛውም የመርጌታ ሙሴን ቃለ ምልልስ የሚከተሉት ላይ በመጫን ያዳምጡ እና እራስዎን ከአስማተኞች ይጠብቁ
መሪጌታ ሙሴ ከሕያው ተስፋ ሬዲዮ ጋር እያደረገ ያለው ቃለ ምልልስ አላለቀም። ቀጣዩንም ክፍል እንደየአስፈላጊነቱ እናቀርበዋለን።

36 comments:

 1. Yihew enem kezarie jemirie tinkolayen tiche getan tekebiaylehu. Geta yibarkachihu.

  ReplyDelete
 2. ድሮም ገንዘብ ነበር ፍላጎትህ አቋራጭ ገንዘብ ማግኛ ስትፈልግ መናፍቅ መሆን ደህና ጉርሻ አገኘህ፡፡

  ReplyDelete
 3. ስለ መሪጌታ ሙሴ አዲስ ሕይወትና ፈውስ ክብሩ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ይሁን!! አሜን እና አሜን::

  ይጠቀምበት የነበረው ክፉ መንፈስ እንዳይበቀለው ሙሉ የእግዚአብሔርን ጦር እቃ ግጥም አድርጎ እንዲለብስ በአጠገቡ ያላችሁ ወገኖች ተግታችሁ በቃሉ እንድታሳድጉትና በጌታ ደም ተሸፍኖ የፈጠረውን የፍቅር ጌታ በኃይልና በስልጣን እንዲያገለግል እንድታደርጉት ሁላችንንም ከጉድ ባወጣን በወደደንና በፈወሰን የፍቅር ጌታ ስም እጠይቃችኋልሁ::

  ተሀድሶ ነው:: መናፍቅ ነው:: ጴንጤ ነው:: ሃይማኖትህን ሊያረክስ ነው:: ስለዚህ በለው ውገረው አባረው እያለ የቤተ ክርስቲያኒቱን ንጹህ የወንጌል አስተማሪዎች የሚያባርረውና የሚያሳድደው የወንጌል ጠላት ይህን የመሰለ ጉዱ እንዳይወጣበት እንደሆነ እዚህ ላይ ያስተውሏል::

  መችም ይች ቤተ ክርስቲያን የተሸከመችው ጉድ ለመስማት የሚከብድና የሚዘገንን ነገር ነውና እባካችሁ አባ ሰላማዎች በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ተሰግስጎ በሕዝቡ ነፍስና ሥጋ ላይ የሚጫወተውን የክፉ መንፈስ አገልጋዮችና የእግዝአብሔር ቃል ወይም የወንጌል ጠላቶችን ሥራ በገባችሁት ቃል መሰረት በመረጃ እያቀረባችሁ ሕዝቡ እንዲያውቀው የማድረግ ሥራችሁን ብታፋጥኑት የወገናችንን ትንሳኤ ታፈጥኑታላችሁና በርቱ! በርቱ!!

  ሌሎች የቤተ ክርስቲያኒቱ እውነተኛ የወንጌል ልጆች በጌታ ፊት አብዝተን እንውደቅ
  ጌታ በምህረቱ እንደ እነመሪጌታ ሙሴ ላሉት እንዲደርስላቸውና እንዲፈውሳቸው::

  በመጀመሪያ ቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ያለው ክፉ መንፈስ ይጠረግና ይጽዳ በሚል እንጂ ሥራው በዚህ ብቻ የሚያበቃ አይመስልም:: በሁለተኛው ዙር ያገሪቱ ባለሃብቶች ላይና እንዲሁም በፓለቲካው በኢኮኖሚውና በማህበራዊ ሕይወታችን ውስጥ ያለው በጥባጭ መንፈስም አይቀርለትምና የእግዚአብሔር ልጆች ልባችሁ ይስፋ እምነታችሁም ይጠንክር:: ይህ በክርስትና ስም ወንድምን ከወንድሙ የሚያባላ ገዳይ መንፈስ አገሪቱን ለዘመናት ተቆጣጥሮ የጦርነት ባለታኮች ያደረገንን የምንበቀልበት ጊዜው አሁን ነው:: ውጊያችን ግን ከሥጋና ከደም ጋር ስላልሆነ ቅዱሱን የጌታ መንፈስ ድምጽ እየሰማንና በቃሉ እያመሳከርን በሃይልና በስልጣን የመንፈስን አንድነት ጠብቀን መሆን አለበትና እንበርታ!!!

  ቤተ ክርስቲያናችን ያጋንንት መጫዎቻነቷ ጊዜ በጌታ ጉብኝት ማብቂያው ነው!!!

  የጌታ ሰላም ለኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ!!!

  የቤተ ክርስቲያኔን ትንሳኤ ናፋቁ እህታችሁ

  ሰላም ነኝ

  ReplyDelete
  Replies
  1. wow, egziabher zemenshn ybark! We also want to see God's intervention in this demonic bandage.

   Delete
 4. እንደ ወረደ መቀበል የሚያስቸግረኝ
  መጽሐፍ ቅዱስን እንኳን እንደ ወረደ የተቀበለው ሰው አልነበረም እንኳንስ የዘመኑ ሃሳውያን የሚያቀነባብሩትን ስውር ሴራና ተንኰል ፡፡ አባ ሰላማዎች ለተነሳችሁበት ዓላማ ፣ ምክንያት ድጋፍና ማስረጃ ለማቅረብና ሰዎችን ለማሳመን እየሞከራችሁ መሰለኝ ፡፡ በእርግጥ በአገራችን እጠነቁላለሁ የሚል አፈ ጮሌ አታላይ ፣ መጽሐፍ ገላጭ የለም ብዬ አልከራከርም ፤ ዛሬ ወንድም የተባለው ግለሰብ ንግግር ግን የፈጠራ ይመስለኛል ፡፡ ከጥንቆላ ጋር የተዛመዱ ቃላቶች መኖሩ ብቻ ፣ ይህ ሥራ በአገራችን እንደነበረ በቀላሉ ያረጋግጣል ፡፡ ነገር ግን ሥራቸው እንደተባለው እውነተኛና ውጤት የሚያስገኝ ነው ብዬ በበኩሌ አላምንም ፡፡ ነገሮች በአጋጣሚ ይሆናሉ ፤ ይህን ተከትሎ ደግሞ እነሱ እንዳደረጉት ለማስመሰል የፈጠራ ወሬ ያወራሉ ያስወራሉ ፤ ከዛም ሌላውን በማታለል ይተዳደራሉ ፡፡

  ይህን መግቢያ ካስተላለፍኩ በኋላ እያንዳንዱ የተለያየ ፍተሻዎችን እንዲያደርግና ንግግሮቹን እንዲመረምር የራሴን መፈተሻ ጥያቄዎች እንደሚከተለው አቀርባለሁ ፡፡
  በ ማንነት ዙሪያ የማነሳቸው ጥያቄዎች
  - አስቀድሜ የማቀርበው ጥያቄ ምስክርነቱ ለምን በድምጽ ብቻ ቀረበ? የተሃድሶ ስውር ሴራ የሚባለውን ዘገባ ስላየሁ ተጠራጠርኩኝ፡፡
  - ገና ከቀደመ ሥራው ያልተገላገለ ይመስል የአያት ስሙስ አብሮ ለምን አልተጠቀሰም ? ሙሴ የሚለውም መጠሪያ የአማራው ፣ የመርጦ ለማርያም አካባቢ ህዝብ የስም አጠራር ባህል አይደለም ይህ የዳቦ ስም ወይም የብርዕ ስም እንደሆነ ይብራራ ፡፡
  - አድራሻውስ? የንግድ ሥራ ቦታውስ በትክክል ለምን አልተነገረም ? እንደ ጴጥሮስ ገና መጥፎ የምሽት ፈተና ላይ ሆኖ ይሆን ይህን የድብቅ መልዕክት የሚያስተላልፈው ? ወይስ ሌላ የቤት ሥራ ቀርቶት ?
  - በእውነት እምነቱን በጌታ ካስተካከለ በኋላ ለምን ራሱን መደበቅ አስፈለገው ? ማን ነው ብርሃንን ይዞ ከእንቅብ በታች የሚያኖር የሚል የመጽሐፍ ጥያቄ አቀርባለሁ?
  - የአስተማሩትንስ ሰዎች እንዲህ ከሚቀናላት ቤተ ክርስቲያን እንዲወገዱ ቢያንስ ስምና አድራሻቸውን ለምን አልዘረዘረና አላጋለጣቸውም ወይም በህዝብ መሃከል አላወገዛቸውም ? እከሌ የሚባል እዚህ ደብር ይህንን ዓይነት ትምህርት ፣ እከሌ የሚባለው ደግሞ በ---- ቤተ ክርስቲያን እንዲህ ለሚባለው ዓይነት ምትሃት ብሎ ዝርዝር አድርጐ ለምን አላቀረበም ? ወይም እንዲናገር ለምን አልተጠየቀም ?

  ሌሎቹ የመሪ ጌታ ሙሴ መንበሩ መልዕክት እርስ በርሳቸው የሚጋጩ ናቸው ለማለት የምደፍርባቸው ፣ ከትምህርትና ሥራው ጋር በተዛማጅነት የተገለጹትን ነው ፡-
  በትምህርት ላይ በነበረበት ጊዜ /በልመናና በሌላውም ዘዴ/ የሚያገኘው ለኮቾሮና ለልብስ መግዣ ያህል ገቢ እንደሆነ ተናግሯል ፤ በዛ ጊዜ መቶ ብር ማለት እጅግ ብዙ ነው ብሎም መስክሯል ፡፡ ታድያ
  - ለትምህርት አሥራ አምስት ሺህ ከፍያለሁ ሲል ዩኒቲ ኮሌጅ የገባ አስመሰለሳ ፤ ከተናገረው አቅሙና ተግባሩ /ገቢና ወጭው/ እንዴት ይጣጣማል ፡፡ ይህን ያህል ገንዘብ ከየት አምጥቶ ሊከፍል ቻለ ? ዘመኑን አስቡ ፤ ለኔ ቢያንስ ከዛሬ አስር ዓመት በፊት የተፈጠመ ተግባር ነው ፤ ምክንያቱም መቶ ብር ብዙና ፣ የወር ደሞዝ የነበረበት ወቅት ከዚያም ወዲያ ስለሚሄድብኝ ፣ እሱም ስለመሰከረው ነው ፡፡
  - ከአንድ ተማሪ ብቻ እስከ አስራ አምስት ሺህ ገቢ የሚያገኙትስ አስተማሪዎቹ ፣ የሚገፉት የደሃ ኑሮ ነው ሲባል ፣ እውነትነቱን እንዴት መቀበል ይቻላል ?
  - መስተፋቅር በዛ ጊዜ 4ዐዐ - 5ዐዐ ብር ያስከፍል ነበር ብሎናል ፡፡ በተማረበት መርጦ ለማርያም አካባቢ ይኸን ለመክፈል የሚችል ህብረተሰብስ ይገኝ ነበረ ወይ? የኀብረተሰቡ የገጠር ወርሃዊ ገቢ ያን ያህል ክፍያ የሚያስከፍል ስላልሆነልኝ ነው ፡፡
  - ንስሐ ሲገባ በዚህ ትምህርት ያሰባሰበውን የኃጢአት ገንዘብ ፣ የደም መሬት ገዛበት /እንደ ይሁዳ ለቤተ ክርስቲያን አስረከበ/ ወይስ አሁንም በዛው ንግድ ላይ እየተዳደረ ነው የሚገኘው ?
  ይቀጥላል

  ReplyDelete
 5. እኔ በግል ለምን በእንደነዚህ ዓይነት ሰዎች ላይ ዘመታችሁ ፣ የእነዚህን ዓይነት ሰዎች ለምን ተቃወማችሁ ለማለት ፈልጌ አይደለም ፡፡ ነገር ግን አንዳንድ አታላይና አፈ ጮሌዎች የማስመሰል የልብ ወለድ ታሪክ በማውራት አዲስ የመተዳደሪያ መስክ እንዳይከፍቱባችሁ ተጠራጠሯቸው ለማለት ነው ፡፡ የቀደመ ሥራው አልሆን ሲለው በአዲሱ የመኖሪያ ስልት ለመጠቀም መጠጋቱ መስሎኛልና ወደፊትም መድረሻውን በአንክሮ ተከታተሉት ፡፡ ምክንያቱም የዚህኛው ዘመን ወጣት በጥንቆላ የሚያምን አይደለም ፤ ስለዚህም በጥንቆላ ለመተዳደር ሲያቅተው በአዲሱ ዘፈን ሊቃኝ እየሞከረ ይመስለኛል ፡፡ ስለዚህም ሌሎች ደግሞ ይህን ትያትር እንዳይደግሙ ከማስተላለፋችሁ በፊት ስለ እውነተኛነቱ በተለያየ መንገድ በመከታተል አጣሩባቸው ፡፡ ስለተናገሩ ብቻ አትመኑአቸው ፡፡ ሰው ሲጨንቀውና ሲቸግረው የማይምሰው ጉድጓድ ፣ የማይበጥሰውም ቅጠል የለም ፡፡

  ከዚህ በተጻሪራ የዚህ ምስክርነት መጥፎ ውጤት ፣ እንደ እኔ ይህን ዓይነት ሥራ የማያምነውንና የማይቀበለውን ፣ ፍጹም ውሸት ነው ብሎ የሚኖረውን ኀብረተሰብ የአጋንንትና የጥንቆላ ሥራን እውነትነትንና ተአማኒነት እንዲቀበል እያስተማራችሁት ነውና ጉዳቱ እንዳያመዝን እፈራለሁ ፡፡ ችሎታ ካለው እስቲ እኔን በምትሃቱ ይቀስፍና ይግደለኝ ፤ ይሄ ውሸታም እበላ ባይ ፣ በዛ አልሆን ሲለው በዚህ በአዲሱ ስልት መሰማራቱ ነው እንጂ ፡፡

  እንደማይሠራ ለአድባር የተጣለውን በልተን እያሳየን ፣ ደንቃራ ያሉትን እንደ ኳስ እያጓንን ያደግነውን ፣ በክንድ የተቋጠረውን እየበጠስን ምንም እንደማያደርግ እያስፈተሽን የታገልነውን ፣ ዛሬ እናንተ እውነት እንደሚሰራና ውጤት እንደነበረው እያመሳከራችሁ ነው ያላችሁት ፤ በዚህ አንጻር ካያችሁት ለክርስትናው ከማገዝ ይልቅ በክርስትና እምነት ላይ ሌላ ስልጣን ያለው አምልኮም እንዳለ እያሳያችሁን ነውና የራሳችሁን ሥራ በተለያየ መንገድ ቃኙት ፡፡ የሚያደርጉ ፣ የሚያምኑ ሰዎች የሉም አልልም ፤ ነገር ግን ለማታለልና በመታለል ካልሆነ በስተቀር የሚዋደድ ባልና ሚስት የሚያፋታ ፣ የጐረቤቱን የሥራ እንቅስቃሴ ወደ ቤቱ የሚያስገባበት ስልትና ጉልበት አለው ብዬ ለደቂቃ እንኳን አላምንም ፤ ይህ እውነት ቢሆን ኖሮ ፈረንጆቹ ከሌላው ምሁር ይልቅ እንደነዚህ ያሉ ጠቢባንን ለቃቅመው ገና ድሮ በሆነ መንገድ ያስኮበልሉዋቸው ነበረ ፡፡ ጨወታው የሳይኮሎጅ ጦርነት ነው ፡፡ ከአመንክ በወጥመዳቸው ትወድቃለህ ፤ ካላመንክ ግን ተረት ይሆንና የጻፉትም ፣ ያስነኩትም ውጤት አልባ ፣ ከንቱ ይሆናልና አትመኗቸው እላለሁ፡፡ የምታገኙዋቸውንም ብልጣ ብልጦች ደግሞ ደብቃችሁ አትቀፏቸው ፤ ጅራት ከያዙ አይለቁምና በሰንሰለት ውስጥ የተሰገሰጉትንና በህዝብ ላይ ሌላ አምልኮ የሚደርቱትን እንደነዚህ ያሉትን በሙሉ አብረን ተባብረን እንድንመነጥር ወደ አደባባይ አውጧቸው ፡፡ ቀናተኛ እየሸፋፈነ አይሠራም ፤ ሁለት ዓይነት አቋምም አይኑራችሁ ፡፡

  በተረፈ ከንግግሩ በትእዛዝ ይሁን አምኖበት የቤተ ክርስቲያኗ አስተምህሮ አይደለም ሲል ምስክርነቱን ሰጥቷልና ስለዚህ ቃሉ ብቻ አመለግነዋለሁ ፡፡ ይሁዳ ከአሥራ ሁለቱ አንዱ ሆኖ ቢቆጠርም ፣ ወደ ሌላው መንገድ እንደ ተጓዘው ሁሉ ፣ ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ካህናት መሃከልም ሰዎችን ለማታለል ፣ ከታጩበት ተግባር የተንሸራተቱ አይጠፉምና ሳትሸፋፍኑ አብረን እንመንጥራቸው ፡፡
  ክፉው መንፈስ ሥልጣን የሚኖረው በደካሞች ላይ ብቻ ስለሆነ በተባለው አትደናገሩ ፤ በንጹህ የክርስትና እምነታችሁ ቀጥሉ ፤ ሰዎች በተለያየ መንገድ ሃይማኖታችንን ይፈትኑታልና ፣ ሳትጠራጠሩ ባላችሁበት ጽናት ይኑራችሁ ፡፡

  የእግዚአብሔር በረከትና ሰላም ለሁላችሁም ይብዛላችሁ ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. የመጀመሪያውን ክፍል የት አሰቀራችሁት ፡፡ ይኸ የመደምደሚያ ሃሳቤ ነው
   ያቀረባችሁት ዘገባ ፍጹም የሃሰት ቅንብር ለመሆኑ የሚየስረዱ የመፈተኛ ጥቃቄዎቼንም አብራችሁ አቅርቡና አንባቢ ይመዝናቸው
   እንደ ተጐረደ የጽሁፉ መጀመሪያ ያስታውቃል ፡፡ ከሆነ ነገር እንደ ቀጠለ ይናገራል ፡፡ የቀሽም ሥራ አትሥሩ
   ክፉ ሃሳብ ከሆነ ህዝብ ይፍረድብኝ ፤ ህዝብ ይኰንነኝ የመጀመሪያውን ክፍል አሁንም ይኸው

   እንደ ወረደ መቀበል የሚያስቸግር
   መጽሐፍ ቅዱስን እንኳን እንደ ወረደ የተቀበለ የለም እንኳንስ የዘመኑ ሃሳውያን የሚያቀነባብሩትን ስውር ሴራና ተንኰል ይቅርና ፡፡ አባ ሰላማዎች ለተነሳችሁበት ዓላማ ፣ ምክንያት ድጋፍና ማስረጃ ለማቅረብና ሰዎችን ለማሳመን እየሞከራችሁ መሰለኝ ፡፡ በእርግጥ በአገራችን እጠነቁላለሁ የሚል አፈ ጮሌ አታላይ ፣ መጽሐፍ ገላጭ የለም ብዬ አልከራከርም ፤ ዛሬ ወንድም የተባለው ግለሰብ ንግግር ግን የፈጠራ ይመስለኛል ፡፡ ከጥንቆላ ጋር የተዛመዱ ቃላቶች መኖር ብቻ ይህ ሥራ በአገራችን እንደነበረ በቀላሉ ያረጋግጣል ፡፡ ነገር ግን ሥራው እውነት ፣ ውጤት የሚያስገኝ ነው ብዬ በበኩሌ አላምንም ፤ ነን የሚሉትንና በድግምታቸው ሊያስፈራሩን ብቅ የሚሉ ሰዎችንም አልፈራም ፡፡ ነገሮች በአጋጣሚ ይሆናሉ ፤ ይህን ተከትሎ ደግሞ እነሱ እንዳደረጉት ለማስመሰል የፈጠራ ወሬ ያወራሉ ያስወራሉ ፤ ከዛም ሌላውን በማታለል ይተዳደራሉ ፡፡

   ይህን መግቢያ ካስተላለፍኩ በኋላ እያንዳንዱ የተለያየ ፍተሻዎችን እንዲያደርግና ንግግሮቹን እንዲመረምር የራሴን መፈተሻ ጥያቄዎች እንደሚከተለው አቀርባለሁ ፡፡
   ስለ እራሱ ማንነት ዙሪያ የማነሳቸው ጥያቄዎች
   - አስቀድሜ የማቀርበው ጥያቄ ምስክርነቱ ለምን በድምጽ ብቻ ቀረበ? የተሃድሶ ስውር ሴራን የሚለውን ዘገባ ያየ ሰው በንጽጽር ተልእኮው ምን እንደሆነ ይገምት ፡፡
   - ገና ከቀደመ ሥራው ያልወጣ ይመስል የአያት ስሙስ አብሮ ለምን አልተጠቀሰም ?
   - አድራሻውስ? የንግድ ሥራ ቦታውስ በትክክል ለምን አልተነገረም ? እንደ ጴጥሮስ ገና መጥፎ የምሽት ፈተና ላይ ሆኖ ይሆን ይህን የድብቅ መልዕክት የሚያስተላልፈው ?
   - በእውነት እምነቱን በጌታ ካስተካከለ ለምን ራሱን መደበቅ አስፈለገው ? ማን ነው ብርሃንን ይዞ ከእንቅብ በታች የሚያኖር የሚል የመጽሐፍ ጥያቄ አቀርባለሁ?
   - የአስተማሩትንስ ሰዎች ከሚቀናላት ቤተ ክርስቲያን እንዲወገዱ ስምና አድራሻቸውን ለምን አልዘረዘረና አላጋለጣቸውም ወይም በህዝብ መሃከል አልከሰሳቸውም ?
   ሌሎቹ የመሪ ጌታ ሙሴ መንበሩ /የዳቦ ስም ፣ የብዕር ስም ፣ ትክክለኛ መጠሪያ ስም/ መልዕክት እርስ በርሳቸው የሚጋጩ ናቸው ለማለት የምደፍርባቸው ፣ ከትምህርትና ሥራው ጋር በተዛማጅነት የተገለጹትን ነው ፡-
   በትምህርት ላይ በነበረበት ጊዜ /በልመናና በሌላውም ዘዴ/ የሚያገኘው ለኮቾሮና ለልብስ መግዣ ያህል ገቢ እንደሆነ ተናግሯል ፤ በዛ ጊዜ መቶ ብር ማለት እጅግ ብዙ ነው ብሎም መስክሯል ፡፡ ታድያ
   - ለትምህርት አሥራ አምስት ሺህ ከፍያለሁ ሲል ዩኒቲ ኮሌጅ የገባ አስመሰለሳ ፤ የተናገረው አቅሙ /ገቢና ወጭው/ እንዴት ይጣጣማል ፡፡ ይህን ያህል ገንዘብ ከየት አምጥቶ ሊከፍል ቻለ ? ዘመኑን አስቡ ፤ ለኔ ቢያንስ ከዛሬ አስር ዓመት በፊት የተፈጠመ ተግባር ነው ፤ ምክንያቱም መቶ ብር ብዙና ፣ የወር ደሞዝ የነበረበት ወቅት ከዚያም ወዲያ ስለሚሄድብኝ ነው
   - ከአንድ ተማሪ ብቻ እስከ አስራ አምስት ሺህ ገቢ የሚያገኙትስ አስተማሪዎች ፣ የሚገፉት የደሃ ኑሮ ሲባል ፣ እውነትነቱን እንዴት መቀበል ይቻላል ?
   - መስተፋቅር በዛ ጊዜ 4ዐዐ - 5ዐዐ ብር ነበር ብሎናል ፡፡ በተማረበት መርጦ ለማርያም አካባቢ ይኸን ለመክፈል የሚችል ህብረተሰብስ ይገኝ ነበረ ወይ? የኀብረተሰቡ ወርሃዊ ገቢ ያን ያህል ክፍያ የሚያስከፍል ስላልሆነልኝ ነው ፡፡
   - ንስሐ ሲገባ በዚህ ትምህርት ያሰባሰበውን የኃጢአት ገንዘብ ፣ የደም መሬት ገዛበት /እንደ ይሁዳ ለቤተ ክርስቲያን አስረከበ/ ወይስ አሁንም በዛው ንግድ ላይ እየተዳደረ ነው የሚገኘው ?

   የእግዚአብሔር በረከትና ሰላም ለሁላችሁም ይብዛላችሁ

   Delete
 6. bedibik yemisera leba bicha new! ewunetin keyazachihu erasachihun giletuna sirachihun mermiren enketelachihu. yalezia atidikemu.
  yesewuyew kitifet ena yetekenebaber mehonun bandit neger bicha matarat yichalal. yihie ketema yeminor sewu endet tirie chew woim ashabo malet chew mehonun resaw jal!

  ReplyDelete
 7. Hi,
  I would love to hear if this man has any connection with MK. Because you believe ( or your spirit geared you up) that no one would read your post unless you connect it to MK. LOL!!
  Tazabiw

  ReplyDelete
 8. gojam debetra !!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!oH...........................my,,,,,,,,,,,,,,GOD TEBEKEN SEWOREN

  ReplyDelete
 9. Anonymous Feb 16, 2012 11:21 AM
  እኔ በግል ለምን በእንደነዚህ ዓይነት ሰዎች ላይ ዘመታችሁ ፣ የእነዚህን ዓይነት ሰዎች ለምን ተቃወማችሁ ለማለት ፈልጌ አይደለም ፡፡ ነገር ግን አንዳንድ አታላይና አፈ ጮሌዎች የማስመሰል የልብ ወለድ ታሪክ በማውራት አዲስ የመተዳደሪያ መስክ እንዳይከፍቱባችሁ ተጠራጠሯቸው ለማለት ነው ፡፡ የቀደመ ሥራው አልሆን ሲለው በአዲሱ የመኖሪያ ስልት ለመጠቀም መጠጋቱ መስሎኛልና ወደፊትም መድረሻውን በአንክሮ ተከታተሉት ፡፡ ምክንያቱም የዚህኛው ዘመን ወጣት በጥንቆላ የሚያምን አይደለም ፤ ስለዚህም በጥንቆላ ለመተዳደር ሲያቅተው በአዲሱ ዘፈን ሊቃኝ እየሞከረ ይመስለኛል ፡፡ ስለዚህም ሌሎች ደግሞ ይህን ትያትር እንዳይደግሙ ከማስተላለፋችሁ በፊት ስለ እውነተኛነቱ በተለያየ መንገድ በመከታተል አጣሩባቸው ፡፡ ስለተናገሩ ብቻ አትመኑአቸው ፡፡ ሰው ሲጨንቀውና ሲቸግረው የማይምሰው ጉድጓድ ፣ የማይበጥሰውም ቅጠል የለም ፡፡---------------------------
  በማለት አስተያየት የሰጠኸውን ሰው ሃሳብህን እጋራለሁ። አንዳንዶች ስም እስከነአያቱ አልተጻፈም ወይም ሊያገኝ የማይችለውን ገንዘብ ጠቅሷል፣ አለያም ጴንጤዎች ናቸው ያቀነባበሩት ሲሉ የሰጡትን ደግሞ ከእውነታ የራቀ ግምት ነው። በመጀመሪያ ልንረዳ የሚገባን ነገር፣
  1/ ጠንቋይና አስማተኛ፣መናፍስት ጠሪ ደብተራዎች በቤተክርስቲያን አሉ ወይ ብንል መልሱ አዎ አሉ ነው።
  2/ ሁሉም መናፍስትን መጥራት፣ ወይም ድግምቱን በተገቢው ሰርተው በሰይጣን አሰራር የሰለጠኑ ናቸው ብንል ጥቂቶች በጣም ጥቂቶች ይህንን ሲችሉ አብዛኛው ተራና አጭበርባሪ ደብተራ ነው።
  3/ ተራ ደብተራም ይሁን ባለሙያው መናፍስት ጠሪ በቤተክርስቲያን ውስጥ ያገለግላሉ ወይም ብለን ብንጠይቅ ጥቂቶች ወደድግምቱና ቅጠል መበጠሱ ስራ ከመሰማራታቸው በቀር ብዙዎች ቤተክርስቲያን ውስጥ ዛሬም አሉ። በተለይ ማኅሌት ቋሚ መሪጌቶች!
  4/ እውቀቱ የሌላቸው ግን ይህንን አስማት በማሰራት ራሳቸውን ለመጠበቅ ወይም ለሚፈልጉት ጉዳይ የሚይዙ ካህናት አሉ ወይ ብንል አዎ ብዙ ሺህዎች አሉ። (እኔም አንዱ ነበርኩ)
  5/ ባይገርማችሁ ከተራው አወዳሽ እስከጳጳሳት ሳይቀር ይህንን አስማት የሚጠቀሙ፣ የሚይዙ መኖራቸው ነው።(በስምና በቦታ የሚታወቁ)
  6/ ይህን የአስማትና የጥንቆላ አሰራር ወደቤተክርስቲያን ያስገባው ሰይጣን ነው። ብዙው የቤተክርስቲያኗ ሰራተኞች ለዚህ ስራ አሜን ብለው ተገዙ እንጂ ቤተክርስቲያኗ እንደአቋም በአስተምህሮዋ ይህንን ታወግዛለች። የሚሰሩትንም ትጸየፋለች።
  7/ ችግሩ ያለው ሲኖዶስ የሚባለው ማእከል ብቃት የጎደለው ሆኖ ነው እንጂ (የአስማቱ ተሳታፊዎች ስላሉበት) ይህንን ለይቶ ማውገዝ፣ መጻህፍቶችን መለየት፣ ሰዎቹን ማስወገድ፣ ምእመናኑም እንዲጠበቁ ማድረግ፣ አለመቻሉ ነው።
  8/ሳጠቃልል ከላይ የተጠቀሰው መሪጌታ ሙሴ የሚባለው ኮተቤ ኰሌጅ አካባቢ የሚኖር አንካሳ መሪጌታ ይሆናል ብዬ እገምታለሁ። ወደፕሮቴስታንት መቀላቀሉ ተሰምቷል።
  እሱ ሆኖ ከሆነ ያሳለፈውን የጥንቁልና ሕይወት ቢናገር ይህንን ያህል ውሸት ነው ላያሰኝ ይችላል። ምናልባት ከንግግሩ እንደሰማሁት የማጋነን፣ ራስን ለአዲሱ ሕይወቱ የማስተዋወቅ፣ እንደዚህ ዓይነት ችሎታ የነበረው ሰው ተለወጠ ለማሰኘት የፈለገ ይመስላል። ከተናገረው በድብትርና የአስማት ሙያ ላይ እንደነበረ ከቃለ ምልልሱ ብዙውን የምናውቀው ስለሆነ አልፎ አልፎ ማጣፈጫ ከሚጨምርበት በስተቀር እውነት ነው። ግን ስራው አትራፊ ሆኖለት ነበር?
  ባለብዙ ገንዘብ ሆኖ ነበር? አይመስለኝም። ያበደው ገንዘብ ስለጠፋበት እንጂ እውነት ስለተገለጸለት አይደለም። ዛሬስ ያለበትን እንደአማራጭ ያገኘው ሆኖ ነው ወይስ ወንጌል ስላዳነው? ከሰይጣን አሰራር መላቀቅ በራሱ መልካም ነው። ወዝ ባለው ልዝብ ቃል ራስን ማስተዋወቅ ካልሆነ እሰየው! የተናገረውን ሁሉ አምኖ መቀበል ከባድ ስለሆነ በፍሬው ይታይ!!
  በክርስትናው ውስጥ አጭበርባሪ በዝቷልና!!!

  ReplyDelete
 10. እንደ እኔ ይኸ ዓይነት ጥበብ እንዲያውም የለም ፡፡ ይኸ ጥበብ በእርግጠኝነት ቢኖር ኖሮ በአለም ትልቁ ሃብታም ከቢል ጌትም በላይ ኢትዮጵያዊው በሆነ ነበር ፡፡ ለእኔ አንዳንድ ብልጦች ባልተማረው ወገን ላይ የጫኑት የማታለያና የገንዘብ ማግኛ ስልት ብቻ ነው ብዬ አምናለሁ ፡፡
  አንድ የተረሳ ቀልድ ትዝ አለኝ
  አንድ ወጣት አባቴ እባክዎት አሜሪካ እንድሄድ ፎርም ሞልቻለሁና ዲቪ እንዲደርስኝ ይጸለዩልኝ ቢላቸው ፣ አይ ልጄ በኔ ጸሎት አሜሪካ መሄድ የሚቻል ቢሆን ኖሮ አስቀድሜ የምጸልየው ለራሴ ነበር አሉት ይባላል ፡፡

  አሁንም አውቃለሁ የሚለው መተተኛና ድግምተኛ ፣ ሰዎችን ሚሊየነር ለማድረግ እሱ አንድ ሺህ ብር ይቀበላል ከተባለና ከተናገረ ከሱ በላይ እናንተም እያፌዛችሁብን ነው ፡፡ ለመሆኑ እንዲህ ዓይነት ሰው የቁጥርን ትንሽና ትልቅ አያውቅ ይሆን? ችሎታ ካለው ለምን ሲባል ነው እንደ ሼክ አለ አሙዲ ቢሊዬነር እስከሚሆን ዘዴውንና ብልሃቱን ለራሱ የማይጠቀምበት? በእርግጥ የሚሠራ ከሆነ ለምን ከምስኪን ደሃ አርባና አምሳ መለቃቀም ያስፍልገዋል? ለጽድቅ ሲባል ወይስ ሌላ? ስለዚህ ጐበዝ ይህ የተሳሳተ የማጭበርበሪያ አጉለ ዘገባ ነው ፤ ከክርስትናው ውጭ አዲስ አምልኮ እንድንፈጥር የሚጋብዝ ፣ ችግረኛውን ህዝብም የእምነት መንገዱን ለማሳት የታለመ ፣ ባለቆብ አንካሳ ደብተራ ባየ ቁጥር ሲከተል እንዲውል የተፈጠረ ሴራ ነው ፡፡ ለምን ሞኝ እንሆናለን? ይኸን የመሰለ ዕውቀት እያለው እቤቱ ተዝናንቶ ማደር ሲችል ፣ ለሊቱን ሙሉ ሲቀድስ የሚያድረው ፣ ጾም እያለ በረሃብ አለንጋ የሚቀጥው ፤ እውነት ይህን የተደባለቀ እምነት ይዞ ለመጽደቅ አስቦ ነው ብላችሁ ለማሳመን እየታገላችሁ ነው? ይልቁንም ህዝብን የሚያታልሉ እንዲህ ዓይነት አፈ ጮሌዎች ስለ አሉ ተጠንቀቁ ፤ በሚነግሯችሁ እንዳትሳሳቱ ፤ ሥራቸው ለማጭበርበር ነው እንጅ ፈጽሞ እንደሚሉት አይሠራም ፡፡ የሚሠራ ቢሆን ኖሮ እነሱ ለራሳቸው ከአልጋቸው አይወርዱም ነበር ፤ የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ ባሉበት ሆነው ያግዙት ነበር ፤ ሚስት ቢባል ሚስት ፤ ንብረት ቢባል ያዩትን ንብረት እያላችሁ አስተምሩ ፡፡
  በተንኰል ወጥመድ ታስራችሁ ከሆነ እግዚአብሔር ሁሉን ይመለከታል ፡፡
  አንድ ቀንም መፍረዱ አይቀርም ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሰይጣን መኖሩን አታምንም? ሰው ለመንፈስ ቅዱስ ብቻ ሳይሆን ራሱን ለሰይጣን ማደሪያነት ራሱን ሊሰጥ ይችላል። ሴራ ሳይሆን እውነት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ይህንን ያረእጥልናል። ሲሞን መሰርይ ሰው እስኪገረም ይጠነቁል ነበር። «ከብዙ ዘመንም ጀምሮ በጥንቈላ ስላስገረማቸው ያደምጡት ነበር» የሐዋ 8፣11
   «ወደ ጸሎት ስፍራም ስንሄድ፥ የምዋርተኝነት መንፈስ የነበረባት ለጌቶችዋም እየጠነቈለች ብዙ ትርፍ ታመጣ የነበረች አንዲት ገረድ አገኘችን» የሐዋ 16፣16
   ይህች ጠንቋይ እለታዊ ትርፍ የምታስገባ እንጂ አንዴ ሁሉን ሀብት የምትሰበስብ ሁሉን አዋቂ አልነበረችም። ሰይጣን ወዳጆቹን ለማታለልና ሌላውም ያንን እያየ እንዲከተለው ልክ ህጻንን በከረሜላ እንደምናታልለው ሰውን በመናኛ ጥቅም ያታልላል። ስለዚህ አባባልህ ወደኮሙኒስታዊነት የሚጠጋ ነው። እግዚአብሔርም፣ ሰይጣንም የለም እንደሚሉት መሆኑ ነው።
   እዚህ ላይ መረዳት ያለብን ሰይጣን ሁሉን አዋቂ አይደለም። ሁሉንም ቻይ አይደለም። ለሚታዘዙለት ሁሉ የሚጠይቁትን ማሟላት አይችልም። ያም ሆኖ ተከታዩ ደብተራዎች ሁሉ ከክህደት ባሻገር ከኃጢአት በቀር የሚያገኙት ትርፍ እምብዛም ነው። ብዙዎቹ አጭበርባሪዎች ናቸው።

   Delete
  2. i believe the devil have the power to do evil things for the sake of getting follower ,,,the like of debtera, witch,,,, if you want to prove see this link

   http://www.flvmp3.org/video/8HV298zKkL0/Memehir%20Girma%20Wondimu%20:%20vcd%2015%20-%20part%20A.html

   Jesus said'' beware of the devil work,,,''

   Delete
 11. እንኳን ራስህን አጋለጥክ የተዋህዶ ራስ ምታት

  ReplyDelete
 12. Majority of mk that came from gojam rural the family members are debetera mora gelach. For this reason they fight to stop church reform. No way to serv two masters the same time. I knew one jogam debtera his name nekatebeb he just now the same life like muse. I hope if he read aba selama he may be out darkeness of hill.

  ReplyDelete
 13. በቤተ ጳውሎስ ብሎግ ላይ ስለ ቫለንታይን ቀን ያነበብኩት አስደስቶኛል እናንተም ለአንባቢያን እባካችሁ አቅርቡት

  ReplyDelete
 14. very bad! we need reform in our church.

  ReplyDelete
 15. yihew anbibie ende muse honikulih. des yibelih yene paster

  ReplyDelete
 16. እንደ ክርክራችን ሁለት ዓይነት ስብከትና ትምህርት ማስተላለፉ ደግሞ ግዴታ ሊሆንብን መሰለኝ ፡፡
  ሰይጣንም ሃይል ስላለው ሊያደርግ የማይችለው አንዳች የለም ፤ ስለዚህም በዚህ ጥበብ የተካኑ አዋቂዎች በቤተ ክርስቲያን ስለሚገኙ ፣ ለጸሎት ሳይሆን ጠንቋይ ደብተራ ፍለጋ ፣ ለማጠያየቅ ሥፍራው እዛ ነው ለማለት እንገደዳለን ፡፡ ይህን ሃይል የተንበረከካችሁለት ካላችሁ ክርስትናችሁን በውል መርምሩ እላለሁ ፤ እንዲህ ዓይነቱ ጥበብ ማታለያ ነው ማለትም የኮሙኒዝም ፍልስፍና ሳይሆን የክርስትና ትምህርታችንና ጸሎታችን የሚያስተላልፍልን ነው ፡፡ እከደይከ ሰይጣን ማለት ምን እንደ ሆነ ትርጉሙ ይግባን ፤ ወይስ በግዕዝ ስለሆነ ጸሎቱ ምን እንደሚል አትረዱትም ፡፡

  እኔ ደግሞ በመንፈስ ቅዱስ ሃይል ሥር እስካለሁ ድረስ የሰይጣን መንፈስ አይገዛኝም ፤ አይነግሥብኝም ፤ ኃይሉ በእኔ ዘንድ አይገለጽም ፤ ከቶ ዋጋም የለውም ፤ እንዲያው ለማጭበርበሪያ ወስላቶች የሚፈጥሩት ማታለያ ነው ፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ የሚያምን ሁሉ የዚህ ክፉ መንፈስ የበላይነትን ፣ ውጤታማነትን ፣ ፍሬአማነትን አያምንም ፤ በአእምሮው እንዳለ አድርጐ አያስበውም ፡፡

  አስማተኞችና ጠንቋዮች የሚሰለጥኑት በእምነት ደካማ በሆነ ወገን መሃል እንደ ፈርዖን ግቢ ባለው ነው እንጅ በአብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ስም ሰውነቱን ባማተበ ክርስቲያን ላይ አይደለም ፤ በወንጌልም ተጠቅሷል ፤ እነዛም ቢሆኑ ሃይል የነበራቸው በማያምኑት ላይ ነው እንጅ ፣ በኢየሱስ ዘንድ ፣ ወይም በጳውሎስ ፣ ወይም በጴጥሮስ ላይ አንዳች ሥልጣንና የበላይነት አልነበራቸውም ፡፡
  እንዳያጠቋችሁ እየፈራችሁ ፣ እየተጠራጠራችሁ እናመልካለን አትበሉና ፤ ለእኔ በእኔ ላይ ሰይጣን ሃይል የለውም ፤
  ግለሰቡን አላገኘውም እንጅ ደጋግሞ በሎሚው ቢያስነካኝና ምንም እንደማልሆን ባረጋገጥኩልህ ለተጠራጠርከው ሁሉ ደግ ይሆንልህ ነበር ፡፡ ውጤቱ ሁሉ ከእምነታችን ጋር የተቆራኘ ስለሆነ እንደ እምነታችሁ ሁኑ ፡፡እኔ ግን የምትሉትን አላምንበትም ፡፡

  አለማመኔ እንደዚህ ዓይነት ሰዎች የሉም ማለት አይደለም ፤ የህዝቡን ወዝ በየምክንያቱ ፣ በየብልሃቱ አድርገው የሚመጡ አታላይ ፣ ብልጦች አሉ ፡፡ እነዚህን ሌቦች ለማውጣት ደግሞ ሁለት አካሄድ መፍጠር ሊኖርብን ነው ፡፡ እንደ እናንተ ግለሰቡ በፈቃዱ እራሱን ሲያጋልጥልን ብቻ እየጠበቅን እልል እያልን ማስተጋባት ፣ እንደ እኔ ደግሞ ይኸ አጉል እምነት ፍጹም የማታለያ ፣ የማጭበርበሪያ ዘዴ ነው በማለት ፣ ምእመኑ እነዚህን ግለሰቦች እንዳይከተልና ራሱን በክርስትና እምነቱ እንዲያንጽ ማስተማር ፡፡ ስለዚህም ደግ የሆነላችሁን መንገድ ተከተሉ ፤ የታየኝን ጀባ ብያችኋለሁ፡፡

  ReplyDelete
 17. በጣም ደስ የሚል ነገር ነው ምክንያቱም በተለይ በገጠር ያለው ህብረተሰብ እየተጠቃ ያለው በንደዝህ ዓይነት የሰይጣን ስራ ነው በተለይ በበረዶ ጥበቃ

  ReplyDelete
 18. i dont think this man was in any of sundayschool. he is also talking about the hadis and bluey but he has never been there. what he is talking is neither dogma nor canon of EOTC. therefore this man will never represent our church.

  ReplyDelete
 19. It is really impossible to deny these problems. I can be a witness there are a lot of people doing the similar things like said in the passage.And I hate it. everybody hates it. but there are few peoples following and believing this idea.
  The worst thing is it doesn't have any relation with TEWAHEDO.
  No one can defend these, There is always one Yihuda among the twelve Apostles.So, for me this is so foolishness to correlate the so called muse with Tewahdedo. It doesn't work. No one can be cheated by these preaching. everybody is aware of it. It is too late to use such a method to fool the sheep.

  It was kind of 'Mariam atamalidim' and ' kesoch yisekiralu' earlier when protestantism trys to expand its denomination. Ethiopians never accept that except very few unfortunate ones. Now they changed the way they are trying to steal sheep. I don't think it will work.

  At the same time if Ato Muse wants to free him from that cult doing, I think he doesn't have to be a protestant. He should be in the same Tewahedo and teach the people. But he inclined to the lesser way to get secular benefit.

  Take for example the Protestant world, they give service to gay marriage in their church. It is accomplished by Pasters of the church who are appointed by the faithfuls. But, they are doing such an evil , devil spirited service. It doesn't imply that protestantism officially accepts gay marriage.
  And so, it is not possible to say that protestantism accepts it. Same thing like this there are a very few debteras in Orthodox church, but it doesn't imply the church is all accepting it.
  Generally, the passage is to abolish fame of Tewahedo, but never it will work.

  ReplyDelete
 20. የነዚህ ሰዎች ወንድም ፣ አስማት እንዴት እንደ ጀመረ ሲተርክ ፣ የተደረገባት ሴት ተከትላኝ ቤተ ክርስቲያን መጣች ብሏልና ሙሴ መንበሩ ቤተ ክርስቲያንን በማቆሸሹ ባላውቅበትም እንዳይረሳው ተቀኘሁለት፡-

  በእናትህ ማህጸን ፣ ጥንቱን ያወቀህ
  እንዳታመልጠው ነው ፣ ቀድሞ የመታህ

  ባለ ዘርፈ ብዙ ፣ አገልግሎትህ እየሆነ
  እውነት ነው ብሎ ፣ ቃልክን ማን አመነ

  ሚስት አስኮብላይ ፣ በጥበቡም አስማተኛ
  ከቤተክስያን ደጃፍ ፣ ለመወሰብ የተኛ ፤
  ቃሉ እርጉም ፣ እስትንፋሱም የነውረኛ
  ማን ይገኛል ከዚህ በላይ ኃጢአተኛ ፤

  ግራኝ ምን አረገን ፣ አቃጠላት እንጅ
  በክንዷ ተኛባት ፣ አታላይዋ ልጅ ፤
  ለሱ ጨዋታው ነው ፣ የግድሚያ ማውራቱ
  ስንት የደከሙላት ፣ ምነው መረሳቱ ፤

  ይኸን ጽርፈት ስላወራው አፍህ
  ከመዘከርያስ ገብርኤል ይለጉምህ

  ReplyDelete
 21. አባ ሰላማዎች ፣ ዓላማ ብላችሁ የተነሳችሁት ቤተ ክርስቲያንን ወደ ጥንት ክብሯ ለመመለስ ፣ ተበላሽቷል የምትሉትንም ለማስተካከል በሚል ተልዕኮ ነው ፤ ለሃይማኖታችን መንፈሳዊ ቅንዓት ማደሩን ብደግፈውም የምትሰሩትን ሥራ ፣ ዛሬ ላይ ሳየው ግን ፣ የተገላቢጦሽ ፣ የክፋትና የሸር ፣ የተገዛ መልዕክተኛ ዓይነት ሆነብኝ ፡፡

  ይኸ የእርግማን ልጅ የከወነው ትያትር በሙሉ ልብ ወለድ ከመሆኑም በላይ ፤ ዓይኑን ጨፍኖ ይህችን ጥንታዊትና የታሪክ አሻራችን በሆነችው ቤተ ክርስቲያናችን ላይ ፣ ላታስተውሉት ትችላለችሁ እንጅ እጅግ ጸያፍ ቃል ወርውሯል ፤ እርግጠኛ ነኝ እነኛ የኦሪት ዘመን ዳኞች ቢኖሩ ኑሮ የሚደርስበት ፍርድ ግልጽ ነበረ ፤ ይኸ የምህረት ዘመን በመሆኑ …. ፡፡

  እንደ ሽኮኮ በዱር በገደል ፣ በዋሻና በጉድባ ሆነው ዕለት ዕለት በጾምና በጸሎት ስጋቸውን የሚቀጡባት ፣ ጽድቅን ፍለጋ በሚደክሙባት አገር ፤ እንዲህ ስድ የሆነ ንግግር ለህዝብ ማስተማሪያ ብላችሁ ስለማቅረባችሁ ራሳችሁንም የግድ እንድገምት አደረገኝ ፡፡ ምናልባት አላሰተዋላችሁት እንደሁ ዛሬም እጠቅሳለሁ ፤ አመለካከቴንም ስለምትወስዱት እርምጃ አስተካክላለሁ ፡፡

  ደካማ የተጋጩት መልዕክቶቹ
  1. ከመጀመሪያው መልዕክት
  - በ27 – 28ኛው ደቂቃ ላይ የተማረውን የአስማት ብዛት ቁጥር አላውቀውም ብሎ ሲያበቃ በ29 – 3ዐኛው ደቂቃ ላይ ለትምህርቱ 15ዐዐዐ ብር እንደከፈለና ፣ ሁሎችንም መዝግቦ እንደያዘ ይተርካል
  - በቆሎ ተማሪነት ዘመኑ የሚያገኘው ለቀለብና ለልብስ ብቻ እነደሆነና ኑሮ ከባድ መሆኑን ከተናገረ በኋላ ፣ እልፍ ብሎ ደግሞ ለመማር 15ዐዐዐ ብር ከፈልኩ ይለናል
  - የተማረበት አካባቢ የገጠር መንደር /መርጦ ለማርያም/ ውስጥ እነደሆነ አስረድቶን እያለ ፣ ወደ አስማትና ጥንቆላ ሥራ ከትምህርቱ በተጓዳኝ ስሰራ የማስከፍለው ለመስተፋቅር በጣም ድሃ ከሆነ 4ዐዐ - 5ዐዐ ብር ነው ይለናል ፡፡ የገጠሩ ኀብረተሰብ ደግሞ እሱ ተማርኩና ሠራሁበት በሚለው ዓመታት ይህን ያህል ገንዘብ እንኳንስ ለማስጠንቆል ፣ ከአስከፊ ህመም ለመዳን ለህክምና እንኳን መክፈል አይችልም

  2. በሁለተኛው መልዕክት
  - ከመጀመሪያ ታሪኩን ሲዘክረን ትምህርቱን የጨረሰው በቆሎ ተማሪነት ጐጃም እንደሆነ ነግሮን ሲያበቃ፣ በዚህኛው መልዕክቱ ስለ ቅድስት ሥላሴ ኮሌጅና አብነት ትምህርት ቤት ግምገማ ያወራናል ፤ ለመማር ወይስ ለማስተማር ገብቶ ይህን ለመረዳት ቻለ ፣ ወይስ ስለቀረበለት አጥንቶ አነበነበው
  - ስለ ሥራው መስክ ምን ምን እንደሠራ ሲጠየቅ - እኔ በቀጥታ በንግድ ሥራ ላይ ነው የተሰማራሁት ፤ ለራሴ ነበር አስማት የምሰራው ፤ የማጣሪያውንም ጥያቄ እንደዚሁ በተመሳሳይ ከመለሰ በኋላ ፣ ትንሽ ቆየት ብሎ እንዲናገር የታዘዘው ትዝ ያለው ይመስል ከለማኝ እስከ ባለ ሥልጣን ፣ ጠላ ሻጯ ሳትቀር እሱ ጋር እንደሚመጡ ይመሰክራል ፡፡ ከላይ እስከ ታች ከሰጠው መልስ የት የቱን እየመረጥን እንቀበለው

  ከመልዕክቶቹ የተቀበልኳቸው
  - ይኸ ትምህርት የቤተ ክርስቲያነ አስተምህሮ አይደለም እስከሚለው ድረስ ፣ ከዚህ ቀጥሎ የሚያውራው ለመውቀስ የሚያበቃውን ምክንያቶች ይደረድራል ፣ ያ የግል አመለካከቱ ነው በሱ ላይ ችግር የለኝም
  - ህዝቡ ወደ እኛ ካልመጣ ድንጋይ ላይ አንጠነቁልም ፤ ህዝቡን ማስተማር ያለው ትልቅ መልዕክቱና እንደ መፍትሄ እናንተም ልትከተሉት የሚገባ ትምህርት ነው ፡፡ ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነውና ይኸኛው ይሰመርበት ፡፡

  የማወግዝበትና የምረግምበት ትልቅ ግድፈቱ፡-
  - የአስማት መጀመሪያ ሙከራ ያደረገው ገበያ ውስጥ ሁለት ጓደኛሞች ስም ሲጠራሩ ስለ ሰማ በስማቸው ደገመ ፤ ከዛም ውጤቱን አየ ፤ ሠርቷልና ተደሰተ፡፡ እሺ የተማረ ደንቡ ነው ፤ በውጤትም መርካትም ወግ ነው ፡፡
  - እንደገና ለማመሳከር በሁለተኛ የተጠቀመው ስሟ ባልተጠራ ወይም ባልታወቀ ሴት ላይ ነው /እላይ ለጥንቆላ ስም ሲያስፈልግ እዚህች ጋር ስም አላስፈለገውም ፤ አሠራሩን አላውቀውም ፤ ግን ልዩነት አለ/ ፡፡ እሺ ፣ አዎ ፣ በሆነው ይሁን ብለን ታሪኩን ስናዳምጥ ፣ ሴትዬዋም ላይ ንክኪቱ እንደሠራና ፣ በራስዋ ፍላጐት ተከትላው እንደሄደች ይነግረናል ፡፡ የሄደችው ደግሞ ወደ ሆቴል ወይም ወደ መኖሪያ ቤቱ አይደለም ፤ ነገር ግን ወደ ቤተ ክርስቲያን ነው ፤ ከዛም እየገለፈጠ ፈታንላት ይለናል፡፡ ህዝብ የሚሰግድበትን ቅዱስ ስፍራ ለዝሙት መደብነት ተጠቀምኩበት የሚለው ቃል በሌሎች ወንድሞች እንኳን አልተሞከረም ፡፡

  ሰውየው በቅኔ የሰለጠነ ምሩቅ ስለሆነ መፍታት የሚለውን ቃል መተርጐም እንገደዳለን
  መፍታት የሚለው ቃል በመዝገበ ቃላት
  - ከኃጢአት ነጻ ማድረግ ፣ ግዝትን ማስወገድ ፤ ከትዳር ጓደኛ መለየት ፤
  - መተረተር ፣ ማውለቅ ፣ መክፈት /መቀነት መፍታት/ ፣ መልቀቅ ፣ መስደድ ፣ ማብረር ፣ መተው

  ፈታ -አጠፋ ፣ አፈረሰ ፣ ሻረ ፣ በተነ
  - አሸነፈ ፣ ድል አደረገ ፤ ለሞተ ሰው ጸለየ ፤ አዘዘ ፣ ፈቀደ
  - ገለጠ ፣ ተረጐመ ፤ ፈረደ ፣ ዐደለ ፣ በየነ

  ስለነዚህ ስህተቶች ይህን ቃለ መጠይቅ አውርዳችሁ ፣ በዚሁ ርዕስ ወቀሳም ይሁን ሌላ ትምህርት ብታስተላልፉ ፣ አብሬ ገንቢ አስተያየቶችን መስጠት እችላለሁ ፡፡ ቤተ ክርስቲያንን የአመንዝራ ሥፍራ ፣ የወሲብ መቀጣጠሪያ አድርጐ ከሚቆጥራት ጋር ግን ምን ጊዜም አንድነት አይኖረኝም ፡፡ ስድቡን የተገነዘብኩት ሁለተኛ ሳዳምጠው ነው ፤ ስለሆነው ሁሉ በጣም አዝናለሁ ፡፡ እናንተም እንዳላስተዋላችሁት እገምታለሁ ፡፡
  ሰላም ሁኑልኝ

  ReplyDelete
 22. Actually almost what he said above are aweful truth , most of Debteras are orginated from our churches, however we have also a true Meri getoch who represent our church. So if we are a true orthodox we have to fight this kind of trend and stand only for bible truth. Finally we have to differenciate those books whether 100% align Holy Bible or not. we should have to ask & must get the answer of these question . who wrote those books ? and does they have a bible truth ? if they dont have, we must vanished from our churches. We Orthodxian have to Reform our church from this kind of unworthy trend. God bless our church !!

  ReplyDelete
 23. Actually almost what he said above are aweful truth , most of Debteras are orginated from our churches, however we have also a true Meri getoch who represent our church. So if we are a true orthodox we have to fight this kind of trend and stand only for bible truth. Finally we have to differenciate those books whether 100% align Holy Bible or not. we should have to ask & must get the answer of these question . who wrote those books ? and does they have a bible truth ? if they dont have, we must vanished from our churches. We Orthodxian have to Reform our church from this kind of unworthy trend. God bless our church !!

  ReplyDelete
 24. This comment has been removed by a blog administrator.

  ReplyDelete
 25. እንደ እኔ ይኸ ዓይነት ጥበብ እንዲያውም የለም ፡፡ ይኸ ጥበብ በእርግጠኝነት ቢኖር ኖሮ በአለም ትልቁ ሃብታም ከቢል ጌትም በላይ ኢትዮጵያዊው በሆነ ነበር ፡፡ ለእኔ አንዳንድ ብልጦች ባልተማረው ወገን ላይ የጫኑት የማታለያና የገንዘብ ማግኛ ስልት ብቻ ነው ብዬ አምናለሁ ፡፡
  አንድ የተረሳ ቀልድ ትዝ አለኝ
  አንድ ወጣት አባቴ እባክዎት አሜሪካ እንድሄድ ፎርም ሞልቻለሁና ዲቪ እንዲደርስኝ ይጸለዩልኝ ቢላቸው ፣ አይ ልጄ በኔ ጸሎት አሜሪካ መሄድ የሚቻል ቢሆን ኖሮ አስቀድሜ የምጸልየው ለራሴ ነበር አሉት ይባላል ፡፡

  አሁንም አውቃለሁ የሚለው መተተኛና ድግምተኛ ፣ ሰዎችን ሚሊየነር ለማድረግ እሱ አንድ ሺህ ብር ይቀበላል ከተባለና ከተናገረ ከሱ በላይ እናንተም እያፌዛችሁብን ነው ፡፡ ለመሆኑ እንዲህ ዓይነት ሰው የቁጥርን ትንሽና ትልቅ አያውቅ ይሆን? ችሎታ ካለው ለምን ሲባል ነው እንደ ሼክ አለ አሙዲ ቢሊዬነር እስከሚሆን ዘዴውንና ብልሃቱን ለራሱ የማይጠቀምበት? በእርግጥ የሚሠራ ከሆነ ለምን ከምስኪን ደሃ አርባና አምሳ መለቃቀም ያስፍልገዋል? ለጽድቅ ሲባል ወይስ ሌላ? ስለዚህ ጐበዝ ይህ የተሳሳተ የማጭበርበሪያ አጉለ ዘገባ ነው ፤ ከክርስትናው ውጭ አዲስ አምልኮ እንድንፈጥር የሚጋብዝ ፣ ችግረኛውን ህዝብም የእምነት መንገዱን ለማሳት የታለመ ፣ ባለቆብ አንካሳ ደብተራ ባየ ቁጥር ሲከተል እንዲውል የተፈጠረ ሴራ ነው ፡፡ ለምን ሞኝ እንሆናለን? ይኸን የመሰለ ዕውቀት እያለው እቤቱ ተዝናንቶ ማደር ሲችል ፣ ለሊቱን ሙሉ ሲቀድስ የሚያድረው ፣ ጾም እያለ በረሃብ አለንጋ የሚቀጥው ፤ እውነት ይህን የተደባለቀ እምነት ይዞ ለመጽደቅ አስቦ ነው ብላችሁ ለማሳመን እየታገላችሁ ነው? ይልቁንም ህዝብን የሚያታልሉ እንዲህ ዓይነት አፈ ጮሌዎች ስለ አሉ ተጠንቀቁ ፤ በሚነግሯችሁ እንዳትሳሳቱ ፤ ሥራቸው ለማጭበርበር ነው እንጅ ፈጽሞ እንደሚሉት አይሠራም ፡፡ የሚሠራ ቢሆን ኖሮ እነሱ ለራሳቸው ከአልጋቸው አይወርዱም ነበር ፤ የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ ባሉበት ሆነው ያግዙት ነበር ፤ ሚስት ቢባል ሚስት ፤ ንብረት ቢባል ያዩትን ንብረት እያላችሁ አስተምሩ ፡፡
  በተንኰል ወጥመድ ታስራችሁ ከሆነ እግዚአብሔር ሁሉን ይመለከታል ፡፡

  ReplyDelete
 26. endezih aynet yehizb dem yemitetu sewoch meweged alebet. kersu tejemirowal. lelochim yiketelutal. we need pure orthod church, not including people like him. that is good to say goodbye. goodbye musse??????????????kkkk???????

  ReplyDelete
 27. look for your foolish followers...let God turn your mind to think well about eotc.

  ReplyDelete
 28. "ከልጅነቱ ጀምሮ ሳይወድ በግድ ወደ ቆሎ ት/ ቤት የገባው መርጌታ ሙሴ አንካሳ ስለሆነና ሰርቶ መኖር ስለማይችል የደጀ ስላም ፍርፋሪ እየበላ እንዲኖር ታስቦ ነበር።"
  በእውነት ደጀ ሰላም የፍርፋሪ መብያ ስለሆነች ይሆን ለ ብሎጋችሁ መጠሪያ ያደረጋችኋት? አንድ ነገር ልጠይቃችሁ… ዛሬ ላይ ሁኖ ወደ አብነት ት/ቤት የገባሁት ሳልወድ በግድ ነው ያለው ነገ ደግሞ ወደ እናንተ የመጣሁት ኑሮ ከብዶብኝ አማራጭ ስላጣሁኝና መጠጊያ ትሆኑኝ ዘንድ ነበር ብሎ ወደ ሙሰሊሞች ወይም ወደሌላ የ እምነት ድርጅት ትቷችኁ ላለመሄዱ ዋስትናችሁ ምንድነው?

  ReplyDelete
 29. Jesus Christ died on the Cross for the whole world not only for Ethiopian's Orthodox please. JOhn 3:16 For God so loved the world that he gave his only son, so that everyone who believe in him may not perish but may have eternal life. I think Ethiopia Orthodox is just mixed up with the ethiopian's culture.

  ReplyDelete
 30. የሰይጣን ባለሙዋሎች ቀስ በቀስ ለጌታ እጃቸዉን ይሰጣሉ

  ReplyDelete
 31. Those are responsible for all backwardness of Ethiopian!!

  ReplyDelete