Monday, February 27, 2012

መርጌታ ሙሴ ከአጋንንት በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነጻ መውጣቱንና ተሐድሶዎች ባላቸው ሰዎች ጴንጤ ነህ ተብሎ መባረሩን ገለጠ።

 የመርጌታ ሙሴ ቃለ ምልልስ ክፍል ሁለት
መርጌታ ሙሴ ቀደም ሲል ባደረገው ቃለ ምልልስ እንዴት ወደ ጥንቆላ እንደገባ ከሰይጣንም ጋር ስለነበረው ቁርኝት፣ስለፈጸማቸው የኃጢአት ሥራዎች አጫውቶን ነበር። ዛሬ ደግሞ ከተወዳጀው ሰይጣን ጋር እንዴት እንደተለያየና ለመጨረሻ ጊዜ ነጻነቱን ማወጁን እና አሁን ያለውን ህይወቱን ያጫውተናል።
መርጌታ ሙሴ እንደገለጸው ከፍተኛ የአስማት ሥራ ለመማር ወደ ሱዳን በሚጓዝበት ወቅት ንብረቱንና የአስማት መጽሐፉን መዘረፉን፣ በዚያው በተዘረፈበት አካባቢ ጴንጤዎች እንግድነት ተቀብለውት ስለ እግዚአብሔር ቃል ሲነጋገርና ስለ ሃይማኖቱ ሲከራከር ማደሩን፤ ነገር ግን አንድ ወንጌላዊ የመሰከረለት ቃል እንቅልፍ ነሥቶት እንደቆየ ይናገራል።ቀጥሎ መጽሐፍ ቅዱስን በቃሉ ለማጥናት ቢሞክርም የተቆራኘው ሰይጣን ይሰውርበት እንደነበር በኋላ ግን በጸሎት ኃይል አጋንቱ ከርሱ መውጣታቸውን ተናግሯል። ሆኖም አጋንንቱ በተኛበት ሊሊት ሊገሉት መጥተው ሲይዙት ሌሊቱን ሙሉ መልካ ሚካኤል እየደገመ ሲታገል ማደሩን ነገር ግን ከአቅሙ በላይ እንደሆኑበት አውቆ፤ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሲገስጻቸው አጋንንቱ ከርሱ ሸሽተው መበታናቸውንና ከዚያንጊዜ ጀምሮ ኢየሱስን መውደዱን ይናገራል።
ጌታ በስሜ አጋንንትን ታወጣላችሁ ብሏል። ሐዋርያትም አጋንንት እንኳ በስምህ ተገዝተውልናል ሲሉ ተናግረዋል ሉቃ10 አዎ የጌታ የኢየሱስ ስም ከስም ሁሉ በላይ የሆነ ስም ስለሆነ በሰማይና በምድር ያለ ኃይል ሁሉ የሚንበረከክለት ስም ነው። ዛሬም የኢየሱስ ክርስቶስ ስም በርካታ ደብተራዎችን ነጻ እያወጣ እንደሚገኝ ብዙዎች ይመሠክራሉ። ክብር ለስሙ ይሁን አሜን!
መርጌታ ሙሴ ከደብረ ታቦር ወደ ወልድያ ሄዶ ለጥቂት ጊዜ ከቆየ በኋላ ወደ ሽዋ ሮቢት ተዛውሯል። በዚያም እንድ የሙሉ ወንጌል አገልጋይ ከቤቱ አስቀምጦ አስተምሮታል። በሽዋ ሮቢት የሚገኙ የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት በቅኔ መምህርነት ሊቀጥሩት ቢሞክሩም እኔ ለእግዚአብሔር እንጂ ለባሪያዎቹ አልቀኝም በማለት ፈቃደኛ አልሆነም። በሽዋ ሮቢት በርካታ ቀሳውስት ወንጌልን ከርሱ ተምረው እውነቱን ማወቃቸውን ይናገራል። ይህ በእዲህ እያለ ከሣቴ ብርሃን የተባለ ማህበር (መሪጌታ ሙሴ ተሀድሶዎች ናቸው ይላቸዋል) አግኝተውት ወደ አዲስ አበባ ወስደው ከነርሱ ጋር እንዲሠራ ጋብዘውት ነበር። ከጊዜ በኋላ ግን ከሣቴ ብርሃን (ሁኔታው ስላላማራቸው ይመስላል) መርጌታ ሙሴን ጴንጤ ነህ ብለው ሲያባርሩት ወደ ፕሮቴስንታት መግባቱን ተናግሯል።
መርጌታ ሙሴ እንኳን እግዚአብሔር ነጻ አወጣህ! ቤተ ክርስቲያንህን ትተህ ባትሄድ ግን መልካም ነበረ እንላለን። እግዚአብሔር ካንተ ጋር ይሁን!
ይህንን የሚያስደንቅ ቃለ ምልልስ (ካለፈው የቀጠለ ነው) ጊዜ ወድዳችሁ እንድታዳምጡ እንጋብዛለን።
የመሪጌታ ሙሴን ቃለ ምልልስ ለማዳመጥ እዚህ ላይ ይጫኑ

17 comments:

 1. ወሬኞች እናንተ እምነት አጋንንት ሲጨምር እንጂ ሲያላቅቅ አላየንም ሀሰተናው ክርስቶስ እንደሚሰራ እናውቃለን እናንተ በየጸበሉ እተመሰከረ ነው፡፡ መሪጌታ ሙሴ አትሳሳት እንደ አቡነ ያሬድ ውሸታም ትታያለህ ተዋርደህ በልመና ቅድስት ቤተክርሲቲያን በር ላይ ትጣላለህ ተርበህ ፤እነሱ እንደሆነ ጊዜያዊ ጥቅም ብቻ ነው የሚያሳዩህ ከዚያ የትም ትወድቃለህ ተጠንቀቅ ፡፡

  ReplyDelete
 2. ሰውየው አፈ ትብ ፣ ጥሩ የአማርኛ ችሎታ ያለው ፣ ፈጣን ተናጋሪና ብልጣ ብልጥ እንደ ሆነ ከመላ ታሪኩና ንግግሩ መረዳት ይቻላል ፡፡ በዚሁ ብልጠቱ ታድያ ድህነትን ለማሸነፍ ያልቆፈረው ገደልና ያልበጠሰው ቅጠል የለም ፡፡ የሰውን ስጋ በላሁ አላለም እንጅ የድመት ሥጋና ዓይን እስከ መብላት ደርሷል ፣ የጅብ አንጐልንም ፈቅዷል፡፡ ሰው የቻይናን ያወራል እዚህ አጠገቡ እያለለት ፡፡ እስከ ዛሬ አጋንንት ያዘን ብለው የሚያወሩ ሰዎች ሁሉ ዓመድ አስበላን አተላ አስጠጣን ሲሉ እንጅ እንዲህ የጅብ ሥጋና አንጐል ፣ ድመትና ውሻ ፣ አሞራ በላሁ የሚል አላውቅም ፡፡ መሰንበት ድንቅ ነውና ገና ብዙ እንሰማለን ፡፡ የቤተ ክርስቲያን ትምህርትን ተምሯል ፤ ነገር ግን ቤተ ክርስቲያን ስለ ነፍስ ሲባል የሚያገለግሉባት ሥፍራ እንጅ ስለ ሥጋ ጥቅም የሚመላለሱባት ስላልሆነች የተማረውን ለምትፈልገው ግልጋሎት አላበረከተላትም ፡፡

  ስለዚህም በመቀጠል ጠንቋይና አስማተኛ ለመሆን ሞከረ ያም ቢሆን እንደ አነጋገሩ የተሳካለት አይመስለኝም ፤ እስቲ የማይጥሙ ታሪኮቹንና ሃቆቹን እንቁጠር ፡-
  - በበፊተኛው መልእቱ በአመት በመቶ ሺህ ብር የሚቆጠር ገንዘብ አገኘሁ /በአመት ሁለትና ፣ ሦስት … ማለቱ ነው/ ብሎን ሲያበቃ ዛሬ ደግሞ ወደ ስደት ለመጓዝ እንደወሰነ ይነግረናል ፡፡ ሰዎች ስደትን እንደ መፍትሄ የሚመርጡት በአገራቸው ያለው የፖለቲካ ሥርዓት ሳይስማማቸው ሲቀር ፣ ወይም በአገራቸው የሆነ የተፈጥሮ አደጋ /ድርቅ ፣ የጐርፍ መጥለቅለቅ ፣ ሰደድ እሳት/ ፣ የእርስ በርስ ጦርነት ሲከሰት ፤ አለበለዚያም የሚኖሩበት የኤኮኖሚ ደረጃ ዝቅተኛነት ፣ ከሞት መለስ የሆነ መከራና ችግር ሲበዛባቸው ፣ እንጀራ ፍለጋ በማለት ይወጣሉ ፡፡ አንድ ከቆሎ ተማሪነት የተገላገለ ደብተራ በዓመት በመቶ ሺዎች ካገኘ ከአገሩ ለመሰደድ ወሰነ ማለት ግን ዳግም ያሞኛችሁ ማለት ይመስለኛል ፡፡

  - በደብረ ማርቆስ ከተማ በዘጠናዎቹ ውስጥ ይህን ያህል ገቢ የሚያስገባ የሱቅ መደብር ቀርቶ የረባ ትልቅ ሆቴል አልነበረም /ይህን የገቢ መጠንና የንግድ ድርጅት ለማሳመን በዛን ዘመን ቢያንስ የተገልጋዩን ኀብረተሰብ የመክፈል አቅም መፈተሽ የግድ ይላልና/፡፡ በከተማዋ ሃብታሞች ቢኖሩም ፣ በአብዛኛው ትንሽ ገንዘብ ሲይዙ የበለጠ ለማግኘት የሚኰበልሉት ወደ አዲስ አበባ ነው እንጅ ከከተማዋ ብዙ አይቆዩም ፤ የገበያ ቦታ ስላልሆነ ማለቴ ነው፡፡ ያሉትም ባለጠጐች ደግሞ በቁጥር የታወቁ ናቸው ፣ ደብተራ ሙሴ እዛ ማኀበር ውስጥ የለበትም ፡፡

  - ስቶ እንደሆነ አላውቅም ወደ ሱዳን ለመሄድ በወሰነበት ወቅት አብራኝ ትኖር የነበረች እህቴን ወደ ቤተሰብ ሸኘሁ ፣ ሱቅ ውስጥ ያለውንም ዕቃ አስረከብኩ ይለናል ፡፡ የራሱ ንብረት ከሆነ ለማን አስረከበው ? አነጋገሩ ተቀጥሮ የሠራ እንጅ የባለቤት አይመስልምና ፣ የሞከረው የጥንቆላ ሥራም ፍሬቢስ እንደ ነበረና ከሰው ቤት ተቀጥሮ እንደሠራ እገምታለሁ ፡፡ ሌላም ቦታ ላይ ስለ መተቱ ውጤታማነት ሲያስረዳ ሰው ከሚጠጣበትና ከሚበለበት እየሄደ /ሰዎች አካለ ስንኩልነቱን ሲያዩ ይመስለኛል/ እንደሚያበሉትና በቅልውጥ እንጀራ ኑሮውን እንደ ገፋ ይመስክራል ፡፡ ይህም ማለት የጥንቆላ ሥራውን ቢገባበትም የሚፈልገውን ፍሬ አላገኘበትም ፡፡ ስለዚህም ደሃነትን የማይቀበለው ሙሴ እያነከሰም ቢሆን ሱዳን ለመድረስ አሸርጦ ፣ ጐፈሬውን ለምን እንደሆነ እንጃ አበጥሮ /ወያኔን ለመምሰል ይሆን/ በአጭር ቁምጣና ካኒቴራ ሆኖ ተነሳ /የወያኔን ተዋጊዎች ስዕል ለመግለጽ መሰለኝ/፡፡

  - ሌላው ምትሃት ፡- መቸም ከኢትዮጵያ ከተሞች ሾፌር ሆቴል የሚባል የሌለበት ከጣት ቁጥር አያልፍም ፡፡ የባህር ዳሩ ሾፌሮች ሆቴል ግን ከማውቃቸው ሾፌር ሆቴሎች ለየት የሚያደርገው ለመናኸሪያው አጥር አዋሳኝ መሆኑ ነው ፡፡ ተሰርቆ ንብረትን ለማጣት ቢያንስ ከሩቅ ሥፍራ መምጣት ፣ አለበለዚያም ዘወርዋራ መንገድ ማለፍ ነበረበት ፡፡ ይህም እንደ ወሬ ሲነገር ትን ትን ብሎኛልና ውሃ ነገር ያለው ድረስልኝ እላለሁ ፡፡

  - እሺ ይሁን ይቀርድደው እንበል ፡- በወጋችንና በደንባችን ሰው ንብረቱን ሲዘረፍ ኡኡ ፣ ድረሱልኝ ፣ ያገር ያለህ ፣ ሌባ ሌባ ዘረፈኝ ብሎ ይጮሃል እንጅ ምን ቢያብድ እንደ ኮረኮሩት ከት ብሎ አይስቅም ፡፡ ይኸ ሁሉ የፌዝ ጭማቂ ነው ፡፡ የሚወድለት ካለ ሊግተው ፈልጓል ፡፡ እሺ የሰው ሁሉ ቅጽበታዊ መልስ አንድ ስለልሆነ ነው ብለን እንኳን ለማመን ብንሞክር ፣ ምትሃተኛው ከተረጋጋ በኋላ ይህን ያህል ንብረት /ብሮች ፣ ቢደገምበትም ወርቅና ብር ፣ ልብሶች ፣ የጥንቆላ መጽሃፍ/ ጠፍቶበት ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሄዶ የዕለት ሁኔታ አላስሞላም ፡፡ ይቅርታ ራሴን ሳትኩ ብሎናል ለካ ፤ በድንገት ራሱን ለሳት ሰው ደግሞ ፣ ቤተ ሰብ ያለው በዘመድ እርዳታ ፤ የኔ ብጤ ከርታታ ወገን የሌለው ከሆነ ደግሞ የቀይ መስቀል አንቡላንስ ፈለገ ህይወት ሆስፒታል ያደርሰው ነበር እንጅ ራሱን የሳተ ሰው እንደ ፊልጶስ የተነጠቀ ይመስል ደብረ ታቦር - አሞራ ገደል አረፍኩ ማለት ቧልት ይመስላል ፡፡

  - የዚህ ኑዛዜ ዋና መልዕክት ባለፈው ማመልከቻዬ በጥንቆላ ያገኘውን በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ገንዘብ የት አደረሰው ፣ እንደ ይሁዳ ለቤተ ክርስቲያን አስገባ ወይስ ምን ያልኩትን ባይታመንም ለሌባ እንዳስረከበ መልሷልና ጥያቄዬን ደስ እንዲለው አንስቼለታለሁ ፡፡ መጽሐፉ አምጣና ይቃጠል እንዳይባል ፣ አብሮ እንደጠፋበት ይናገራል ፡፡ ምናልባት አሁን ያለበትም ህይወት ብዙ ገቢ የማያስገኝና የማያዋጣው ከሆነ የቀድሞ ሥራውን ሊጀምር ቀብሮት መጥቶ ይሆናልና በዙሪያው ያላችሁ ክትትል አድርጉበት እላለሁ ፡፡

  የመጨረሻው ክፍል ሁለት ይቀጥላል

  ReplyDelete
 3. - በሰማንያዎቹ አካባቢ በባህር ዳር ከተማ የጴንጤዎች ሙሉ ወንጌል ቸርች የሚባል ነገር ትዝ አይለኝም ፡፡ አማኞቹ ቢኖሩም የሚሰባሰቡት ግን በግለሰብ ቤት እየተዘዋወሩ ነበር ፡፡ እንዲያውም ኀብረተሰቡ ቤት አናከራይም ስላላቸው ብዙ እንደ ተቸገሩና በአንዳንድ ያመኑ ሰዎች ቤት ጸሎትና ዝማሬ የደርጉ እንደ ነበረ እንጅ እንዲህ የሚነገርለት ምኩራብ አይታወቅም ፡፡ ኋላ ላይ አንድ ግለሰብ ለመጋዘንነት የሠራውን በደኀና ገንዘብ ተከራይተው መንቀሳቀስ እንደቻሉና ትንሽ መስፋፋት ሲጀምሩ ሃይማኖትን በተመለከተ ግጭት ተነስቶ አንድ ሰው በጥይት እስከ መሞት እንደ ደረሰ አስታውሳለሁ ፡፡ ከዛ በኋላ ግን መንግሥት ዲሞክራሲያዊ መብት መከበር አለበት በማለት ጠባቂ ፖሊስ ስላመደበላቸው በሥራዓቱ መንቀሳቀስ ችለዋል ፤ እድገትም አሳይተዋል ፡፡ ይህንንም ለማስላት ያስገደደኝ ሙሴ አበድኩ ካለበት ዘመን በፊት ቀበሌ 13 አክስቱ ጋር ሲሄድ የሙሉ ወንጌል ቸርች በማለት ስለ ጴንጤዎች ባህርይ ስላወራ ነው ፡፡ በወቅቱ የኀብረተሰቡ ጥላቻ ድንግል ማርያምን አያምኑም በማለት እንጅ በአመጋገባቸው ባህል ልዩነት አልነበረም ፡፡ በዛን ወቅት በጾም ሰዓት እስላም ምግብ ቤት ካልተገባ በስተቀር ከዓሣ በላይ የሥጋ ነገር በየትኛውም ሆቴል አይገኝም ፤ እንዲያው በጾም ሲበሉ ታዩና እንኳን ብለን አሉባልታውን እንዳንቀበል ፡፡


  - የሃገራችን ህዝብ እንደ እነ አብርሃም እንግዳ ተቀባይ ነው ቢባልም ፣ እብዱን ሁሉ ያጋፍፋል ማለት እንዳልሆነ ልብ ልንለው ይገባል ፡፡ ሰውየው እነደ አሞራ በሮ ይሁን በምን አይታወቅም ፣ አሞራ ገደል እንደ ደረሰ ይተርካል ፤ እሺ ይኸም ይሁንልህ እንበለው ፡፡ ያረፈባቸው ሰዎች ዘመዶቹ አይደሉ ፣ ወይ ከዛ በፊት ዕውቅና እንዳላቸው አይታወቅ ፣ እንደዚሁ ከአንድ ውሻቸው /የገጠር ውሻ ደግሞ እንደ አሜሪካኖች ውሻ ገራምና ሰው በቶሎ የሚለምድ አይደለም/ ጋር አኖሩኝ ማለቱ ፍጹም ቅጥፈት ይመስላል ፡፡ የቀድሞው የገጠሩ ህዝባችን እጅግ የዋህ ፣ ደግ ፣ አዛኝ ፣ ለጋስ ፣ ሃይማኖተኛ ነው ፡፡ ነገር ግን ይኸን ሁሉ ባህርዩን የሚገልጥበት የራሱ ወግ ወግ አለው ፤ ቢያንስ ሌባ እንግዳ መስሎ ገብቶ ፣ ሌሊት ከብቱን እንዳይነዳበት ሲል ይጠነቀቃል፡፡ በሌላ አንጻር ደግሞ በአገራችን ራሱን የሳተ እብድ ይፈሩታል እንጅ ስለምንም አያስጠጉትም ፡፡ ይህንን የምለውም ክርስትና ሊያስነሳው በእግዚአብሔር ከሃይማኖት ትምህርት ቤት የተላከው ልጃቸው ስለ መጽሐፍ ቅዱስ እስኪነግረው ድረስ ራሱን እንደሳተ ሲመሰክር ፣ ልጃቸው መጽሐፍ ቅዱስን ሲነግረኝ ካደረ በኋላ ራሴን አወቅሁ በማለት ስለመሰከረ ነው ፤ ማለትም እስከዛች ምሽት ድረስ ሰውየው ከህሊናው ያልነበረ ፍጹም እብድ ነበር ፡፡

  - ይህ የቀውሰ ሰው ዓለም በቃኝ ብለው በገዳም ያሉትንም አፉ አልማራቸውም ፡፡ የተረገመ እኩይ ፍጡር ስለሆነ በአምላክ እናትና በመላእክቱ ፣ በቅዱሳኑ ሁሉ ላይ ዘመተባቸው ፡፡ ከሰማንያ በላይ ለሚሆኑ መነኮሳት እንጀራ እየጋገርኩ ፣ ጠላ እየጠመቅኩ አገለግል ነበር ይላል፡፡ የቁም ቅዠት ካልያዘው በስተቀር በየትኛው ገዳም ነው እንዲህ እንደ ድግስ ቤት ምግብና ጠላ የሚሰናዳው ፡፡ ይኸማ ካለ ነገ እኔም ወጣ ብዬ የገዳምን ኑሮ እለማመዳለሁ ፤ ቀልደኛ ፤ ሥር እየማሱ ፣ ቅጠል እየቀቀሉ የሚኖሩትን ሰዎች ጠግበው የሚያድሩ ፣ ባለ ጠላና ሰካራም ማድረግ ለኛ አሁን ምን ይፈይደናል ፡፡ ያም አልበቃ ብሎት “ክርስቲያን ከሆንኩ በኋላ ….. ፣ ገዳም ስሄድ ተራራ ፣ ሸንተረሩን ኮረብታውን ፣ ድንጋዩን እንጨቱን ላወድስ አልፈለግኩም ፣ የምቀኘው ለእግዚአብሔር ብቻ ነው” በማለት ገዳም ያሉት አባቶች ወደ ጥንቱ አምልኮ ሥርዓትም የተመለሱ ፣ ለዛፍና ለተራራው የሚሰግዱ አስመስሎ ይኰንናቸዋል ፡፡ ይኸም ለእኔ የእብደቱ ትልቅ ማረጋገጫ ነው ፡፡ ፈረንጆቹ ሃሉሲኔሽን ይሉታል ይኸንን ዓይነት የቁም ቅዠት የመሰለ የጤና ችግር ፡፡ እግዚአብሔር አማኑኤል ሆስፒታል የሚያደርስ ዘመድ ይስጥህ ፤ በእውነት ሳያምህ ከሆነ እንዲህ የዘላበድከው ግን እሱ ይፍረድብህ ፤ በባሮቹ ላይ ዘምተሃልና እሱው ይምታህ ፡፡

  - ደብተራ ሙሴ ስለ ተሃድሶዎች ሴራና ህቡዕ ድርጅትነት በግልጽ ተንፍሶልናል ፤ ተሃድሶ የሚባል የለም ብለው ሊያደናቁሩንና ዓይናችንን ሊጋርዱን የሚከራከሩትን የሚያሳርፋቸው ይመስላል ፡፡ ሸዋ ሮቢት በወንጌል አገልግሎት ላይ እያለ ማርያምንና መላእክትን ሁሉ እንደማይቀበል ነገሯቸው ፣ የሚከተሉትም አንድ ዓይነት እምነት ስለሆነላቸው ለከሳቴ ብርሃን ስብከተ ወንጌል ዘኢትዮጵያ ሠራተኛነት ተቀብለውታል ፤ በዚሁም አቋሙ አብሯቸው እስከ አዲስ አበባ ድረስ ተዛውሮ እንደ ሠራ ተናግሯል ፡፡ በመሃሉ ግን አንድ ጨዋታ ለመጫወት ሞከር አድርጐላቸዋል ፤ ገድሎ ማዳን እንዲሉ የቢሮ ሥራ አይመቸኝም ስላቸው ጴንጤ ነህ ብለው ተቃወሙኝ ይላል ፤ ማለትም ተሃድሶዎች ከጴንጤ ጋር አንድ አይደሉም ፤ ጴንጤን ይቃወማሉ ለማለት ሲፈለግ ፡፡ እልፍ ሲል ደግሞ አሁንም ካህናትን እየመለመለ እንደሚያስተምር ይናገራል ፡፡ የተምታተ ነገር አለው ፣ ብቻ ዘገምተኛው እኔ ነኝ እንጅ እሱስ አስቀድሞ እብድነቱን በገሃድ ተናግሯል ፡፡ ድኀነት የማያመጣብን ፣ የማይፈጥርብን መከራ የለም ፡፡ ስለ መንፈስ ቅዱስ ስጦታ ፣ ስለ ልሳን ፣ ስለ አማላጅነት የጀማመራቸውም ጠቃሚ ርዕሶችም አሉት ፣ ነገር ግን በዚህ ወቅት አልተነተናቸውም ፡፡ ይኸን ሰው እስከ እብደት ያደረሰው ፣ ከቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓትና እምነትም ጋር የሚያጋጨው የያዘው ከርስና ችግር ነውና አትፍረዱበት ማለትን መርጫለሁ ፡፡ የተሟላ ጤንነቱን እንዲያገኝ ስለ ሙሴ ጸልዩ ፡፡

  በበኩሌ ባያምናትም ማርያም ታማልድህ ፣ ማርያም ትማርህ ብያለሁ ፡፡

  ReplyDelete
 4. ተሃድሶዎች ጴንጤ አለመሆናቸው ሲረጋገጥ!!!

  ሁለገብ ባሕሪን ተላብሶ የሚነቀሳቀሰው ማኅበረ ቅዱሳን ክስ የመሰረተባቸውና ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ጴንጤ በማለት የስም ማጥፋት ዘመቻ አዋጅ ያወጀባቸው የከሳቴ ብርሃን ስብከተ ወንጌል ዘኢትዮጵያ አገልጋዮች (የኦርቶዶክስ ቤ/ክ ተሃድሶ ልጆች)ጴንጤ አለመሆናቸው የራሳቸው አባል በነበረው አሁን ግን በተለያቸው መሪጌታ ሙሴ ተረጋገጠ::

  ሙሴ እንዳረጋገጠው በዚች ቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ያለፍን ሰዎች ሁሉ ባልግባንና እኛ ከምናምነው ውጭ ወንጌልን ብቻ የሚሰብክን ሁሉ መናፍቅና ጴንጤ በማለት ጠልተን በሌላው እንዲጠላ የምናደርግ ስለ ነበርን ከዚህ በላይ አስተያየቱን በሰጠው ሰውና(ሲራገም ቆይቶ እንጸልይለት እንዳለው) በማህበረ ቅዱሳን አባላት ላይ መፍረዱ ክርስቲያናዊነት ስላልሆነ ለሥራው ባለቤት መስጠቱ ይሻላል:: 'ቢያውቁት ኖሮ የሕይወትን ጌታ ይሰቅሉት ነበርን?' ሙሴስ ይህ ዛሬ የበራለት ወንጌል ከጅምሩ ቢበራለት ኑሮ ከነፍሰ ገዳዩ ጋር ይወዳጅ ነበረን? ለሁሉም ጊዜ አለውና በቃሉ ብርሃን እየተመራን ማድረግ የሚገባንን ድርሻ ለመወጣት ቤተ ክርስቲያናችንንና በውስጧ ያሉትን የወንጌል ጸሮች በጾም በጸሎት ሁሉን ቻይ በሆነው አምላካችን ዙፋን ስር ይዘን እንውደቅ????

  ከሳቴ ብርሃንም ጴንጤ አይደለንምና ወደ ጴንጤዎች ሂድ ማለታቸው ለእኔ እውነተኛ የኦርቶዶክስ ልጆች መሆናቸው ምልክትና ቋሚ ምስክር ሆኖ ነው ያገኘሁት:: ምክናያቱም በመጽሐፍቶቻቸው በመጽሔታቸውና በሬዲዮ ፕሮግራማቸው ለቤተ ክርስቲያኒቱ ምእመንና መሪዎች ባለማቋረጥ እያስተጋቡ ያሉት እኛ በህያው እግዚአብሔር ቃል ብቻ የምናምን ኦርቶዶክስ ነን:: ቤተ ክርስቲያናችን የወንጌል ጅማሬ የነበራት እና አሁን ግን ብዙ መልካም ነገሯ እንደቀድሞው ሙሴ ባሉ መናፍስት ጠሪዎች ከወንጌል ውጭ በመሆኗ ወደ ቀደመ ታሪኳ ትመለስ ወይም ትታደስ ነው እያሉ ያሉት:: በሌላ ቋንቋ ቤተ ክርስቲያናችን የክርስቶስ ወይም የወንጌል ቤተ ክርስቲያን ትሁን የወላድ መካንነቷም ያብቃና በስሯ የሚገኘውን በርካታ የዋህ ሕዝብ በወንጌል ኃይል ብቻ ከሞት ታስመልጠው በማለት ነው እየጮሁ ያሉት::

  ታዲያ እውነተኛው ማነው? ጴንጤዎች ናቸው እያለ የሚጽፈውና አስወርቶ የሚያስወራው ማህበር ቅዱሳን (ደጀ ሰላም ብሎግ) ወይስ ጴንጤ አይደለንምና አቋምህ አብሮን ሊሄድ አይችልም በማለት የመሰከረባቸውን መሴን ያባረሩት ከሳቴ ብርሃኖች (ተሃድሶዎች)?? ፍርዱን አሁንም ለአንባቢ እተወዋለሁ:: ሁሉን ፈትሹ ነውና የተባልነው በህያው ቃሉ:: እረ እስከመቼ በበሬ ወለደ እንኑር???

  ስለዚህ እባካችሁ ከቅዱሳን መላእክትና ሰዎች ባነሰ ፈጣሪውን አንዳንዴ የሚጠራውን የዋሕ ሕዝብ ራሩለትና ስታችሁ አታስቱት ገደልም አትጨምሩት? ለነገሩ እናንተም የጌታ ብርሃን እንደ ጳውሎስ የጌታን ተከታዮች ለማስገደል በራሳችሁ የደማስቆ መንገድ ላይ እስከ አልተገናኛችሁ ድረስ በጨለማ አይደል ያላችሁት:: እንደ ጊያዝ የውስጥ ዓይኖቻችሁን ያብራላችሁ:: አሜን::

  ሙሴም ቢሆን በተረዳው መረዳት ከጉድ ያወጣውን ጌታ በግልጽ ለማገልገል ጨክኖና ቆርጦ መነሳቱ ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን:: በአባታችን ቤት ያውም መከሩ ብዙ በሆነበት ምድራችን አሰራርና አገልግሎት እኔ እንዳልኩትና እንደምሠራው መሆን አለብህ አይባልም:: ጌታ እንደ ፈቃዱ በፈለገው እያንዳንዳችንን ለአንዱ መንግሥት ሥራ ቢያሠማራ አቅምና ጥበብ ይጎድለው ይሆንን?? እረ እባካችሁ እኛ ስንበላላ በአህያ ከእብደታችን እንዳይመልሰን እናስተውል????? ለነገሩ በምንም ይሁን በምን መመለሳችን ነው የሚጠቅመንና በፈለገው እንደ ወደደ ያግኘንና ለቤተ ክርስቲያንችን በጋራ ያሰልፈን:: አሜን::

  በተረፈ ለምንጽፈውና ለምንናገረው እባካችሁ እንጠንቀቅ:: በጥላቻ የእግዚአብሔር ቤት ይቅርና የራሳችን ምድራዊ ቤት እንኳ ፈጽሞ አይሠራምና ለራሳችን ስንል እናስተውል:: ለምሳሌ ከዚህ በላይ ከቀረቡት ሶስት አስተያየቶች መካከል:

  1) የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ለአንባቢህ ልታስተላልፈው የፈለከው መልእክት በእውነት
  ምንድነው? የሙሴ ምስክርነት ትክክል እንዳልሆነ ለማስረዳት ከሆነ ቦታው ላይ
  በመገኘት ወይም ሰውየውን በግንባር በማግኘት ማረጋገጥ ስለሚቻል በዚህ ማንም
  የሚታለል አይመስለኝም:: ሙሴ እየተናገረ ያለው ጠንቋይ ደብተራ ነበርኩ ጌታ
  በምህረቱ ከተያዝኩበት ልክፍት ፈውሶ ሰውን ከማታለል አዳነኝ ማለቱ ለማኝ
  ትሆናለህ ሊያሰብለው ይገባልን? የጌታ ስም ከአጋንንትስ ሊፈውስ አይችልምን?
  መችም ፈውስ በጸበል ነው የሚል በቃሉ ላይ አላየሁምና ቢጠቁሙን??
  የክርስቶስስ ተቀዋሚ/ሃሰተኛው ክርስቶስ ማነው? ከአጋንንት ጋር የተዋረሰው ወይስ
  ከስሞች ሁሉ በላይ በሆነው ስም በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንደ ሙሴ
  ያሉትን የሚያስፈታው?? እረባካችሁ ዛሬም እንደ ትናንት እየመሰላችሁ ትዝብት
  ላይ የሚጥልና በሩቁ የሚታይ ይህን የመሰለ ነጭ ውሸት ይቅርባችሁ???

  2) ሁለተኛውንና ሦስተኛውን አስተያየቶች የጻፍክ ወገኔ ሙሴ የሰጠው ምስክርነት
  ትክክል እንዳልሆነ መረጃዎችን በመዘርዘር አንባቢዎችህን አስረድተህ ለማሳመን
  ያደረከው ሙከራ የሚደነቅ ቢሆንም ዛሬ ዛሬ ጊዜ ሰው ያንድ አቅጣጫ መረጃ ላይ
  ብቻ በመርካት የሚያቆምና አሜን ብሎ የሚያቆም ነው የመሰለህ:: የነገሩን
  እውነትነት በተለያየ ስልት ተጠቅሞ በማረጋገጥ ማ? ምን? እንደሆነ አበጥሮ
  ለማወቅ የሚፈልግ ትውልድና ዘመን ላይ መሆናችንን የረሳህ ይመስለኛል::
  ስለዚህ መሪጌታውን በግንባር ሳይቀር ማግኘት የሚችልበት እድል ስላለ
  ያቀረብከው አስተያየት ግቡን የሚመታልህ አይመስለኝም:: ሌላው እርግማንና ጸሎት(ለሙሴ) አንድ
  ላይ ማድረግ አይቻልም (በረከትና መርገም ከአንድ አፍ እንዴት)???

  መሪጌታው ይልቅ ሁላችን ያለፍንበትንና ብዙዎቻችን ዛሬ ሳይሆን ድሮ የድመት ሥጋ ያበላሉ እንዲህ ያደርጉዋችኋል አትሂዱ ሰላም አትበሏቸው እንለው የነበረውን ጉዳይ በእኛው በራሳችን ውስጥ የነበረና አሁንም ያለ ጉድ ጉድ ጉድ እንደሆን አጋልጧል:: ለካ ጴንጤዎችን የሰድብንና ያዋረድን መስሎን እራሳችንን ስንሰድብና ስናዋርድ ነበረ የኖርነው:: ሁኔታችን ሁሉ ለሚያስተውል ሰው እጅግ ነው የሚያሳዝነው:: ይህም የመንፈስ ቅዱስን ወቀሳ ለሚያዳምጥ እንጂ አሁንም ቢሆን አንደበቱ ስድብ ለተሞላ እና ለታወረ ሰው ምንም አይመስለውም::

  በመጨረሻም እውነትና ንጋት እየቆየ ይጠራል እንደሚባለው ሁሉንም ሰንብተን በዓይኖቻችን ማየት እንድንችል የምህረት አምላክ ይርዳን:: ማስተዋልንም ያብዛልንና ከመቀባጠርና ስተን ከማሳት ያድነን:: አሜን እና አሜን::

  የጌታ ሰላም ለሁላችን ያለማቋረጥ ይብዛልን:: አሜን::

  ትንሳኤ ለቤተ ክርስቲያንችን ይሁን:: አሜን::

  ከፍቅር በቀር ሌላ እዳ አይኑርብን:: አሜን::

  የተጻፈን ወይም የተነገረን ሁሉ በተለያዬ መንገድ ሳናጣራና ሰናረጋግጥ (በተለይ በቃሉ)በጥሬው እንደ ወረደ አሜን ብሎ ከመቀበል ቸሩ አምላካችን ያድነን:: አሜን::

  የምወዳችሁና የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲንን እውነተኛ ትንሳኤ ቀን ከሌት የምናፍቅ እህታችሁ!!


  ሰላም ነኝ

  ሁላችሁም ሰላም ሁኑልኝ::

  ReplyDelete
  Replies
  1. enie ahun ke'anchi mikir efeligalehu.PENTIE LIHUN WOIS TEHADISO? ebakish baschekuay melishilign selamiye.
   FikireMayiyam negn.

   Delete
 5. የግለሰቡ መልዕክት ነው እንጅ እኔ በሰጠው አስተያየት የተዛባ አመለካከት እንዲኖረኝ ፈልጌ አይደለም ፡፡ ነገር ግን የናንተ አገልጋይ የነበረው ያስተላለፈውን ለማመነ ምንም የጭብጥ ነገር አላገኘሁበትም ፤ በስሌት /በሎጂክ/ ለማረጋገጥ ብሞክር እንኳን መንገድ አጣሁለት ፡፡ ጠንቋይ መሆን ይችላል ፤ አሁን ደግሞ የኢየሱስ ተከታይ ነኝም ማለት ይችላል ፤ ሊሆንም ይችላል ፡፡ እዚህ ከመድረሱ በፊት የተሰራው ቲያትር ግን ላምነው የምችል ቅንብር አይደለም ፡፡ የፈጠራ ታሪክ ይመስለኛል ፤ ስለዚህም አብጠርጥሬ ፣ ጥርጣሬ ሊፈጥሩ የሚችሉትን ነጥቦች አውጥቼአለሁ ፡፡ የተነካ ካለ ከሙሴ በላይ መጐዳት ይችላል ፡፡ ለእኔ ግን ታሪኩ የሆነ ዓላማ ያለው ድራማ ነው ፡፡ በቀላሉ ለመናገር ተሃድሶ ጴንጤ አይደለም የሚለው መልዕክት ራሱ ለናንት ነን ለምትሉት ክርስቲያኖች የሹምባሽ ሹመት ነው ፡፡

  እርግማንና ጸሎት የተደባለቁት ስለሁለት ነገሮች ነው ፡፡ ማንበብ ስለሚቻል በድጋሚ ይቃኝ እንጅ እኔም እንደ አንዳንዶች ዞሮብኝ ሳላስተውል እንደ መጣልኝ ያስቀመጥኩት አይደለም ፡፡
  - እርግማኑ የመጣው በአገራችን ገዳማት በጾምና በጸሎት ተንበርክከው የሚኖሩትን አባቶች ለመውቀስ ምላሱን ስላንቀሳቀሰ ነው ፡፡ እኒህ ያበቁ ሰዎች እንዴት እንደሚኖሩ ለመረዳት የግድ ገዳም መግባት አያስፈልግም ፡፡ በኢንተርኔት መዳሰስ ይቻላል ፡፡ ለዛ ወግ የታደለ ዘመድ ካለ ደግሞ ስለኑሮአቸው በመጠየቅ መማር ይቻላል ፡፡ ደብተራ ሙሴ እንዳለው እንደ ተስካር ድግስ የሚደገስበት ግን አይደለም ፡፡ አምልኮአቸውም ቢሆን ጥርት ያለ ወደ አንድ አምላክ ነው እንጅ ተራራና ወንዝ ፣ ዛፍና ሸንተረር አይደለም ፡፡ እንደዚህ ያለውን ልቅ ያ የሚያበሳጫችሁ ሰው ቢኖር ኖሮ እርግማን ብቻ ሳይሆን ፣ ፈረስ ይነዳበት ነበር ፡፡ የተፈጸመው እጅግ ክፉ ብልግና ነው ፤ ቤተ ክርስቲያንን መጽረፍ ፤ የደከሙ አባቶችን ያልሆነ የአምልኮ ስም መስጠት እጅግ ከሰይጣን ነው ፡፡ ለቀቀኝ ቢልም ገና አልወጣለትም ፣ ጠበል ያልሽው /አትጠራጠሪ ፊደሉን በሙሉ ካነበብሽ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል ነው/ ነገር ሳይፈውሰው አይቀርምና ወደ እዛ ተወስዶ ይሞከር ፡፡

  - ጸልዩ ማለት የመጣው እናንተ ወንድሞቼንና እህቶቼን ገድሎ የማዳን ዓይነት ሥራ ስለ ሠራና ጴንጤ አይደላችሁም ብሎ ምስክርነቱን ስለሰጠ ነው ፡፡ ቃሌም የሚለው እንጸልይለት አይደለም ፡፡ ትእዛዝ ነውና ስለ ሙሴ ጸልዩ ይላል ፡፡ ጸሎቱ ቢያንስ እኔን አይጨምርም ፡፡ የኔ የሚሆነው እርግማኑ ነው ፤ ምክንያቱም ባለፈ በአስማት ያደነዘዝኳትን ሴት እንደ ሙክት አስከትዬ ቤተ ክርስቲያን ወሰድኳት ፣ ዛሬ ደግሞ በገዳም ህይወታቸውን በሙሉ በጾምና በጸሎት የሚኖሩትን ፣ ዓለምን የናቁ ሰዎች ላይ እምነትና አምልኮአቸውን ጨምሮ ስለኰነነ ነው ፡፡ ግልጽ ካደረግሁ የተሰጠው አስተያየት ይታረምልኝ ፡፡

  ለኔም ሰላም ሁኑልኝ

  ReplyDelete
 6. ይገርማል! እውነትም ፔንጤዎች ቤ/ክርስቲያናችንን ለመውረስ እየሰሩ ናቸው፡፡ እንተ!

  ReplyDelete
  Replies
  1. አይም ነው! አፋኙን የደህንነት ድርጅት ማህበረ ቅዱሳንን (ማህበረ ዲያብሎስን) በወንጌል ትጥቅ አቃጥሎ በፀበል እያጠመቁ በመስቀል ቀጥቅጦ ማስወጣት ነው እንጅ፣ ጴንጤማ እቤቱ ነው ያለው። የምን ወዲህ ወዲያ መወላገድ ነው!! ኦርቶዶክስ እንደዚህ ኣይነት ውልግድግድ መንገድ የለውም። ትርጉሙም ቀጥታ ነው። ነገር ግን ኑሮው በዕምነት ጸንቶ መስዋአትነትን የመቀበል የጸጋ ውርስ ነው፤ እንዴት ቢሉም የጌታችን የመድሃኒታችን ምሳሌው እሄው ነውና። የዘመኑን ዲያብሎስ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ ብለሽ (ብለህ) አሳጂው (አሳድደው) እንጂ አትፍሪ (አትፍራ)። የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ። አሜን!!!

   Delete
 7. የቀደመው ስላልወጣ ይህን ትንሽ የተብራራ መግለጫዩን ይኸውላችሁ
  ችኰላዩ በፈጠረው ስህተት በማይዛመድ ዓምድ ላይ ተልኳል ፤ ብታስተካክሉት ለማለት ነው ፡፡ ድጋሚ ቃሉ ይኸ ነው ፡፡

  1. ለአስተያየት ሰጭ መልሶቼ ፡- የግለሰቡ መልዕክት ስለአነሳሳኝ ነው እንጅ ፣ እኔ ስለተሰጠው አስተያየት የተዛባ አመለካከት እንዲኖረኝ ፈልጌ አይደለም ፡፡ ነገር ግን የናንተ አገልጋይ የነበረው ያስተላለፈውን ታሪክ ለማመን የሚያስችለኝ በስሌት /በሎጂክ/ ምንም የጭብጥ ነገር አላገኘሁበትም ፤ ፣ እንዲሁም አካባቢውን ስለኖርኩበትና ስለማውቀው ከነባራዊው ሁኔታም አንጻርም ፣ ለማረጋገጥ ብሞክር እንኳን መንገድ አጣሁለት ፡፡ በአጭሩ ብዙ ታሪክና ማጣፈጫ ሳይገባለት ቀደም ደብተራና ጠንቋይ ነበርኩ ማለት ይችል ነበር ፤ አሁን ደግሞ እግዚአብሔር ስለፈቀደና ድክመቴ ስለገባኝ ከችግሬ ተፈወስኩ ፤ የኢየሱስ ተከታይም ሆኛለሁና ጌታ ይመስገን ቢለን ተደራቢ ብዙ ደባደቦ መልዕክት ስለሌለው በቀላሉ ይገባን ነበር ፡፡ ከዚህ ውጭ ለማሳመን በማለት የሆኑ ያልሆኑ ቅባቶችና ወቀሳዎች ስለታከሉበት ሆዴን ጐረባበጡኝ ፡፡ ያልተማረውን ወገን የሚያጭበረብሩ እንደ እርሱ ዓይነት የሰይጣን መልዕክተኞች ይኖራሉ ፤ እግዚአብሔር ሲያዘጋጃቸው ደግሞ በምክንያት ነጻ ይወጣሉ ፡፡

  አሁን ባለቤትና ፊትአውራሪ ለመሆን ብትፍጨረጨሩም ፣ የሙሴ መለወጥ የመጣው በናንተ ጥረት ለመሆኑ የትም ቦታ አልተገለጸም ፤ ከዜና ያለፈ አስተዋጽዖ የላችሁም ፡፡ እግዚአብሔር ስለፈቀደለት ብቻ ኘሮቴስታንት በሆነ ወንድም ምክንያት ከዛ የክፋት መንገድ መገላገል ችሏል ፡፡ እዚህ ከመድረሱ በፊት ተሰራ የተባለው መግለጫ ቲያትር ግን ላምነው የምችል ቅንብር አይደለም ፡፡ ስለሆነ ነገር በማለም የተፈጠረ ታሪክ ይመስለኛል ፤ ስለዚህም አብጠርጥሬ ፣ ጥርጣሬ ሊፈጥሩ የሚችሉትን ነጥቦች አውጥቼአለሁ ፡፡ የተነካ ካለ ከሙሴ በላይ መጐዳት ይችላል ፡፡

  ለእኔ ታሪኩ አሁንም የሆነ ዓላማና ግብ ያለው ድራማ ነው ፡፡ በቀላሉ የሚታዩ ሁለት ነገሮችን ለመግለጽ - አንድም ተሃድሶ ጴንጤ አይደለም የሚለውን ትምህርትና መልዕክት በማራገብ ፣ እናንት ነን ለምትሉት ክርስቲያኖች የሹምባሽ ሹመት ለማስገኘት ፡፡ ሁለትም ተሃድሶ ማለት እንደ እነዚህ ዓይነት ሰዎችን ለማስወገድ የሚታገል /ህቡዕና ግልጥ/ ክርስቲያናዊ ድርጅት ነው እንዲባልም ሊሆን ይችላል ፡፡ ነገር ግን በሙሴ መለወጥ ላይ እናንተ የጨመራችሁት ቅንጣት ነገር የላችሁም ፡፡ ከፊት የሞተው ተዋጊ እያለ ፣ ከኋላ እንደሚፎክረው የጦር ሜዳ አጫፋሪ ሥራ ሆኖ ነው የማየው ፡፡ ሙሴን ለዋጭ ሌላ አካል ቁጭ ብሎ ሳለ ፣ አሁን እንደ ዋና ሆናችሁ ወሬ የምታቀናብሩና የምትከራከሩ ፣ ራሳችሁን የቤተ ክርስቲያን ሞግዚት አድርጋችሁ የምትነግሩን አስመሳዮች ፣ ነገር ግን የምታሰድቧትና የምትወቅሷት ጠላቶቿ ናችሁ፡፡

  2. እርግማንና ጸሎት የተደባለቁት ስለሁለት ነገሮች ነው ፡፡ ማንበብ ስለሚቻል በድጋሚ ይቃኝ እንጅ እኔም እንደ አንዳንዶቹ ዞሮብኝ ሳላስተውል ፣ እንደ መጣልኝ ያስቀመጥኩት አይደለም ፡፡
  - እርግማኑ የመጣው በአገራችን ገዳማት በጾምና በጸሎት ተንበርክከው የሚኖሩትን አባቶች ለመውቀስ ምላሱን ስላንቀሳቀሰ ነው ፡፡ እኒህ ያበቁ ሰዎች እንዴት እንደሚኖሩ ለመረዳት የግድ ገዳም መግባት አያስፈልግም ፡፡ በኢንተርኔት መዳሰስ ይቻላል ፡፡ ለዛ ወግ የታደለ ዘመድ ያለው ደግሞ ስለኑሮአቸው በመጠየቅ መማር ይቻላል ፡፡ ደብተራ ሙሴ እንዳለው እንደ ተስካር ፣ ድግስ የሚደገስበት ሥፍራ ግን አይደለም ፡፡ አምልኮአቸውም ቢሆን ጥርት ያለ ወደ አንድ አምላክ ነው እንጅ ተራራና ወንዝ ፣ ዛፍና ሸንተረር አይደለም ፡፡ እንደዚህ ያለውን ልቅ ያ የሚያበሳጫችሁ ሰው ቢኖር ኖሮ እርግማን ብቻ ሳይሆን ፣ ዛሬም ፈረስ ይነዳበት ነበር ፡፡ የተፈጸመው እጅግ ክፉ ብልግና ነው ፤ ቤተ ክርስቲያንን መጽረፍ ፤ የደከሙ አባቶችን ያልሆነ የአምልኮ ስም መስጠት እጅግ ከሰይጣን ነው ፡፡ ለቀቀኝ ቢልም ገና አልወጣለትም ፣ ጠበል ያልሽው /አትጠራጠሪ ፊደሉን በሙሉ ካነበብሽ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል ነው/ ነገር ሳይፈውሰው አይቀርምና ወደ እዛ ተወስዶ ይሞከር ፡፡

  - ጸልዩ ማለት የመጣው እናንተ ወንድሞቼንና እህቶቼን ገድሎ የማዳን ዓይነት ሥራ ስለ ሠራና ጴንጤ አይደላችሁም ብሎ ምስክርነቱን ስለሰጠ ነው ፡፡ ቃሌም የሚለው እንጸልይለት አይደለም ፡፡ ትእዛዝ ነውና ስለ ሙሴ ጸልዩ ይላል ፡፡ ጸሎቱ ቢያንስ እኔን አይጨምርም ፡፡ የኔ የሚሆነው እርግማኑ ነው ፤ ምክንያቱም ባለፈ በአስማት ያደነዘዝኳትን ሴት እንደ ሙክት አስከትዬ ቤተ ክርስቲያን ወሰድኳት ፣ ዛሬ ደግሞ በገዳም ህይወታቸውን በሙሉ በጾምና በጸሎት የሚኖሩትን ፣ ዓለምን የናቁ ሰዎች ላይ እምነትና አምልኮአቸውን ጨምሮ ስለኰነነ ነው ፡፡ ግልጽ ካደረግሁ የተሰጠው አስተያየት ይታረምልኝ ፡፡

  ለኔም ሰላም ሁኑልኝ

  ReplyDelete
 8. It is death for us, we are behind the truth that is Jesus. Don't blame this guy, the good thing many of has Jesus, despite the elite are protecting us from knowing the son of God. Trust me , it will be soon that we are going to see our church are free from the devil work. The son of God visit our church!

  ReplyDelete
 9. ለተከበርከው ወገኔ ፍቀረማርያም!!!

  እንዳንተ ደካማ ሥጋን የለበስኩትን ሴት ከምጠይቅ ይልቅ ሁሉን ቻይ የሆነውና ጸሎትን ሰምቶ የሚመልሰውን ቸር አምላክ በንጹህ ልብህ ብትጠይቀው እጅግ እጅግ እጅግ የተሻለ መልስ ይሰጥሃልና ይህንኑ ብታደርግ ያዋጣሃል::

  አይ የለም አንች መልሽልኝ ካልከኝ ደግሞ ጴንጤም ወይም ተሃድሶ አትሁን:: ክርስቶስንና የክርስቶስ የሆነውን በቃሉ ወይም በወንጌሉ ተረድተህ ክ ር ስ ቲ ያ ን እና ክ ር ስ ቲ ያ ን ብቻ ሁን:: እግዚአብሔር ጥያቄህን የእውነትና የምር የነፍስ ጥማት አድርጎልህ የሃይማኖተኛነት ቀንበርን (ካለብህ)ከትክሻህ ላይ ጌታ በቅባቱ ኃይል ሰብሮልህ ለዘላለም ግንዘቡ ያድርግህ:: በህይወትህ ዘመን እውነትን ግዛት እንጂ አትሽጣት:: ደግሞም ጳውሎስ በቃሉ ላይ እንዳስቀመጠው 'ከእንግዲህ ሰውን ክርስቶስንም ቢሆን በሥጋ አላውቅም' እንዳለው ከስጋ ፈቃድ ውጣና ደሙን ላፈሰሰልህ ጌታ ፈቃድ እራስህን አስገዛ:: ሁላችንንም በምህረቱ ያግኘን::

  የእኔን አቋም ለማወቅ ለሚፈልግ ወገኔ ግን ላደኩባት ለኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እንደ ቃሉ የሆነ ቅናት ያለኝና ይች ለሁላችንም ወይም ለኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ ለሥጋ ወገኖቻችን ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ጭምር ባለውለታ የሆነች ቤተ ክርስቲያን እንደ ትናንቱ መሪጌታ ሙሴ ባሉ ያጋንንት አገልጋዮች መጫወቻ መሆኗ የሚያንገበግበኝና የሚያቃጥለኝ ጉዳይ ስለሆነ ለዚች ቤተ ክርስቲያን ወደ ወንጌል ብቻ መመለስ ሌት ተቀን በእንባ ለሚሰማ ጌታን ሁሉን አዋቂ አምላክ ጋር ሙግት ያለኝ ሴት ነኝ:: ከዚህ ውጭ እኔ የማመልከው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር በነበረበት ወቅት እያንዳንዳችንን በፈቃዳችን ብትወድ ተከተለኝ አለን እንጂ ኦርቶዶክስ ወይም ጴንጤ(ይህ እንኳን ጰራቅሊጦስ ስለሆነ ያስኬዳል)ወይም ካቶሊክ ወይም ተሃድሶ (ይህም ቢሆን ቤተ መቅደሱ ታድሷል ሰው ሁሉ በጌታ አዲስ ፍጥረት በመሆን ታድሷል:: ስለዚህም የተበላሸ ሁሉ መታደስና ወደ መሰረቱ ወይም ወደ ጅማሬው መምጣት ይኖርበታል)ካልሆናችሁ መንግሥተ ሰማይን አትወርሱም አላለንም:: ወይም በልጁ በጌታ በኢየሱስ ብቻ መንግሥተ ሰማይ መግባት እንደሚቻል አስተማረን እንጂ አንድም በእናቱ ወይም በአገልጋዮቹ በመላእክት ወይም በጻድቃን ወይም እንደልማዳችን በሸዋው ተክልዬ ወይም በግጻዊው አቡዬ ወይም በግሪኩ/በእንግሊዙ ፈረሰኛው ጆርጅ ወይም በቁልቢው በኩል ካልሆነ በቀር አላለምና በከንቱ ደክመን ሕዝባችንንም በየገዳሙ ባናደክመው ይሻላልና ቆም ብለን ብናስተውል ለንፍሳችን ዋስትናና እረፍት እናገኝላታለን::

  ከዚህ በተረፈ ነገሮችን በቅንነት ለዘላለም ሕይወት ሊሆነን በሚችል መልኩ ተመልክተን ለእኛም ለቤተ ክርስቲያናችንም ለአገራችንም ለሕዝባችንም የሚሆን በጎ ነገር በጋራ በመሆን እውነትን በፍቅር የማንነጋገርና አንዳችን ከአንዳችን የማንመማር ከሆነ ለምን ጊዜያችንን እናቃጥላለን?? የነፍስ ጉዳይ እኮ ነው እየተነጋገርን ያለነው:: ለምንድነው እንደ ልጆች ጨዋታ መያዥ መጨበጫ እንደሌለው ጉዳይ ወዲያና ወዲህ ውዣ ውዤ የምነለው? እኔ በበኩሌ እውነትን ከመናገር በቀር ለሌላ ዝባንዝኬ ጊዜ የለኝምና ዝም ብሎ አሰስ ገሰሱን ለሚሰነዝር አስተያየት ሰጪ ከእንግዲህ አፌን ላልከፍት እየወሰንኩ ነው::

  ከዚህ በተረፈ ለሁለተኛው የገዳማት ምስኪን ወገኖቻችን ተቆርቋሪ በመሆን አስተያየት ለሰጠኸው ሰው እስቲ የገዳምና የምንኩስና ሕይወት የመዳን መንገድ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረጃ ጠቅሰህ አስርዳኝ? ይህ ዓይነቱ መንገድ ከውጭ ወደ አገራችን በገቡትና በተለምዶ 9ቱ ቅዱሳን ተብለው በሚጠሩት ሰዎች አማካኝነት የተጀመረ ሰው ሰራሽ ስርአት እንደሆነ ከታሪክ መጽሐፎች ከማንበቤ በስተቀር ሁላችንም የሕይወታችን መመሪያና ምንጭ አድርገን በያዝነው መጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ ፈልጌ ስላጣሁት ብትጠቁሙኝ ባለውለታዬ ትሆናላችሁ::

  በተረፈ በአሁኑ ጊዜ እንደ ሞኝ ልቅሶ ጴንጤ መናፍቅ ፕሮቴስታንት ተሃድሶ በማለት ማደናገር የሚቻል አይደለምና እራሳችንን ትዝብት ላይ ባንጥለው ይሻላልና ብናስብበት???


  ታሪክ ያለን ሁነን ሳለ እንደሌለን መሆናችን ይሰማን ይቆጨንም!!!

  ቤተ ክርስቲያናችን በጎ ነገር ያላትን ያህል በበለጠ ሁኔታ ደግሞ ኢክርስቲያናዊ በሆኑ ነገሮች መሞላታን አምነን ወደ ቀደመ የወንጌል መሰርቷ እንድትመለስ አብረን በመሆን መሰዋእት ለመክፈል እንነሳ እንጂ በሠራተኞች ላይ የመከራ እሳት ጭሪና አንዳጆች አንሁን???

  የምድራችን እውነተኛ ታሪክ እንጂ ያልሆነው ማንነት የትም እንደማያደርሰን እንረዳ??

  ለሁላችንም ጌታ ማስተዋልን ሰጥቶን በጎ የሆነውን ለማድረግ እንነሳ???

  በክፉ የተያዙት ወገኖቻችን(ለነገሩ በጌታ ያልሆነ ሁሉ በጥቂቱም በብዙውም የተያዘ ነው)እንደ መሪጌታ ሙሴ ነጻ ወጥተው የበደሉትን ሕዝብ መልሰው እንዲያገለግሉ በንጹህ ልብ እንጸልይ???

  እስከ መቼ ድረስ ነው ቤተ ክርስቲያናችን ያሳደገቻቸውን ልጆቿን በማሳደድ የወላድ መካን የምትሆነው??

  ለምንድነው የሳተ በይቅርታ እንዲመለስ እየተደረገ ቤታችንን በተማረ የሰው ኃይል አናጠናክረውም???

  መቼ ነው እከሌ እንደዚህ ነው ያ ደግሞ እንዲህ ነው አሉ በሚሉ ወሬኞች ሊቃውንቶቻችን የምናጣው??

  እረ ወገኖች ቆም ብለን ምን እየሆነብን እንደሆን እናስተውል?? የምንቀራረብና የምንተማመን ደግሞ በቤታችን እይሆነ ያለውን ነገር እንወያይበትና መፍትሄ ለማምጣት እንጣር??

  ጉዳያችን የዘላለም ሕይወት ጉዳይ እንጂ የፓለቲካ ጉዳይ አይደለምና እንደ ውሻ አንበላላ?? ለነገሩ የሚያስተውል ሰው እንዳለ ብዬ እንጂ በክፉ የተያዙ ወገኖቼ ምክሬን ተግባራዊ ያደርጉታል ብዬ አስቤ አይደለም ይህን ሁሉ የምለው እንዲያው በውስጤ ያለውን ሸክም ላራግፍ ብዬ እንጂ:: በጠላት ጎራ የተሰለፉትንም አልፈርድባቸውም ሁላችንም የዛሬን አያድርገውና ያዙኝ ልቀቁኝ ሰውን ሁሉ እፈጃለሁ የምንል ነበርንና:: ክብር ለስሙ ይሁንና በብርሃኑ ብርሃን እንድናይ አድርጎን እንጂ::

  በሉ የምህረት አምላክ ማስተዋልንና ፍቅሩን ያልብሳችሁ:: አሜን::

  ሰላም ሁኑልኝ

  የምወዳችሁ እህታችሁ

  ሰላም ነኝ

  ReplyDelete
 10. ፍቅረ ማርያምFebruary 29, 2012 at 11:43 PM

  የገዳም ሥርዓትን የመሠረተው ጌታችንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ፡፡ ትክክለኛው መጽሐፍ ቅዱስ በእጅ ከተገኘ ከጥምቀተ ባህር ከወጣ በኋላ ፣ ሌላ ሥራውን ከመጀመሩ በፊት በቀጥታ ለመጾም የሄደው ወደ ገዳም /ምድረ በዳ/ ነው /ማር 1፡12-13 ፣ ማቴ 4፡1-2 ፣ ሉቃ 4፡1-2/ ፡፡ አይ አልሄደም ቤተ ክርስቲያን ወይም ወደ ቤቱ አለበለዚያም ካስፈለገ እንዲያመቸን ኬክ ቤት ማለት እንችላለን ፡፡ የምናነበው የመጽሐፍ ልዩነት የሚፈጥረው ችግር ሊሆን ይችላልና መጽሐፍ ቅዱሳችሁን በውል መርምሩት ፡፡

  የአምላክ እናትን ማፍቀር ጸጋ የሚሆነው ጌታ ኢየሱስ ለሚወዳቸው ብቻ ነው ፡፡ ከሥጋዋ ሥጋን የነሳውን ልጇን አመልክሃለሁ የሚል ሰው ፣ ድንግል ማርያም ስለተከበረች ሊታወክ አይገባውም ፡፡ ለኔ ሹመቴ ስለሆነ ከዛሬ ጀምሮ ቢያንስ የዳቦ ስሜን በፍቅረ ማርያም አድርጌአለሁ ፡፡
  1. መለኮትና ሥጋ ተዋሃዱ /ቃል ሥጋ ሆነ/ ሲባል የማንን ሥጋ የተዋሃደ እንደመሰላችሁ አይገባኝም ፡፡ የሷን ሥጋ ተዋህዶ ነው እኮ የአዳምን ዝርያ ያተረፈና ያከበረው ፡፡ ከመንበሩ ሥጋ ይዞ አልመጣም እኮ ፤ ከትንሣዔም በኋላ ያረገው ያን የተዋሃደውን ሥጋውን ትቶ አይደለም ፤ እናም ያ የተዋሃደው ሥጋ ዛሬ የት ሥፍራ ይገኛል ፡፡ ለፈጣሪያችን እንሰግዳለን ስንል እኮ በተዋህዶው ካመንን ፣ ባትውዷትም የእሷም ሥጋ አብሮ ይሰገድለታል ማለት ነው ፡፡ ሥጋና አጥንት መቁጠርና ማየት ከተፈለገ መነጽራችን ያንን ሁሉ ይቃኛል ፡፡ ነገር ግን ፍጡር አምላክ ሊሆን ሰለማይችል ፣ እንደ አምላክ እናትነቷ ብቻ አከብራታለሁ ፡፡ ስለዚህም ማንኛውም የተዋህዶ አማኝ ደግሞ የአክብሮት ስግደትና ጸሎት ለአምላክ እናት ስላደረገ ከመጽሃፍ ቅዱስ ውጭ ሌላ ጣዖት እንዳመለከ አድርጐ መተቸቱ ተገቢ አይደለም ፡፡ ቢያንስ ፍጥረት ሁሉ ብጽዕት ይሉኛል ብላለችና ስለ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃሏና ቅድስናዋ ባታምኗትም ማመስገን ፣ ከታደላችሁትም መስገድ ይገባችኋል ፡፡ ይኸን የእኛን ነገር እንደ ትልቅ ወሮታና ሥራ አናድርገው ፡፡
  2. ኢየሱስ ክርስቶስ እኔን ስለ ወደደኝ ሞቶልኛል ፤ በመስቀል ላይ ደሙን አፍስሶ አድኖኛል የሚል ምስክርነትን የሚሰጥም ክርስቲያን አማኝ ፣ እናቱን ቅድስት ማርያምን ሊቃወም አይገባም ፡፡ ምክንያት ቢባል እናቱን በአደራ የሰጠው ለሚወደው ሐዋርያ ስለሆነ ፤ ይወደናል የምንል ሁሉ የዛ አደራ ተካፋዮች ነንና ፡፡ ስለዚህም ቢያንስ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ብለን እንወዳታለን ፡፡ ጌታ የተጨነቀላትንና ያሰበላትን እናቱን እኛም እናፈቅራታለን ፡፡
  3. ፈጣሪያችንን ጡት አጥብታ ስላሳደገች ፣ አደጋ እንዳይደርስበት ተሰዳ ስለተንገላታች ሁሉ ማመስገን ይገባናል ፡፡ ስለዚህም የምስጋና ጸሎት እናደርሳለን ፡፡ ምድርና ሰማይ የማይበቁትን ፈጣሪዋን ስላቀፈችው ብቻ በተመስጦ ሆነን ልናከብራት ልናደንቃት ይገባል ፡፡ በእግዚአብሔር ለእናትነትም መመረጥ ራሱ እጅግ ትልቅ ሞገስና በቂዋ ነው ፡፡ የእኛ ማመስገንና ማክበር ፣ እህ ... ራሳችንን ለማነጽ ነው የሚሆነው ፡፡

  ድንግል ማርያምን የሚወድ ሁሉ በምስጋናዋ ፣ በአክብሮቷ ይከተለኝ ፡፡ ማንንም በሰይፍ ወይም በግድ እመኑ አላልኩም ፡፡ ነባሩ እምነታችን ከተባለ ግን ይሄን የሷን መከበር ሁሉ ያካትታል ፡፡ ስለሆነም በእሷ ላይ የሚሰነዘረው ዘመቻ ይቁም ፡፡

  ቤተ ክርስቲያንን እየሰደባችሁና እየዘነጠላችሁ ፣ ቅዱሳኑንና ምእመናኗን ያልሆነ ስም እየሰጣችሁ ምኑን ነው የምንወድህ የምናፈቅርህ ወገኔ የምትሉት ፡፡ ለእኔ ያ ሁሉ የማታለያ ወይም የመደለያ ቃል ነው ፡፡ ሰማይ ቤት ከፍርድ ወንበር ደርሳችሁ የተመለሳችሁ ይመስል በወገናችሁ ላይ ፣ ተሳስተሃል ብላችሁ ልትፈርዱ የምትሞክሩ ቅዱሳንና ቅዱሳት ፣ እኛ የበለጠ እናውቅልሃለን የምትሉት ሳይታወቃችሁ ትምክህተኞች ናችሁ ፡፡ ከየትም የተለቃቀመ የሃይማኖት ድሪቶ ሰባስባችሁ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ነው ፤ ከመጽሐፍ ቅዱስ ግቢ ነው ትሉናላችሁ ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን ጠንቅቆ የተረዳ ሰው ቢያንስ በቸልታ እየተከታተለ ግድፈት ሲያገኝ ሊያስተምረን ይሞክራል ፡፡ ሐዋርያቱ በቃልና በጽሁፍ እያሉ የጠቀሱት ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭም ትውፊታዊ ትምህርት እንዳስተማሩ የሚያስረዳን ነውና ፣ ተጨማሪ ትምህርት እንዳለ መገንዘብና መቀበል ግድ ይለናል፡፡ ከሁለት ሺህ ዘመንና ከዛም በላይ ታሪክ ያላት ቤተ ክርስቲያናችን ስለ ሁሉም ትምህርቶች መረጃ ይኖራታል ፤ ትናንት እንደተመሠረተች ፣ እንደ አዲስ አድርገን አንገምታት ፡፡ እጅግ ብዙ ሊቃውንትን አስተናግዳ ፣ የብዙ ምሁራንን ትምህርት ፣ ጥበብና ልምድ ጨምቃ የያዘች ናትና ስለ እግዚአብሔር ብላችሁ በደፈና አትውቀሱ ፡፡ ስለ ኢየሱስ ብላችሁ እናውቅላችኋለን አትበሉ ፡፡ መጽሐፍ ቅዱሱን የምትረዱትን ያህልና ከዛም በላይ የተረዱና የሚያውቁ ብዙ ሰዎች አሏት ፡፡ አቅሙና ዕድሉ ካለን እነሱ ሳያልፉ እንዲያስተምሩን ፣ እነሱ እውነቱን እንዲነግሩን እንጋብዝ ፤ እንዲጽፉ እንገፋፋቸው እንጂ በሆነው ባልሆነው በማናውቀው ሁሉ እኛ አንቋሰል ፡፡

  ሰላም ሁኑልኝ

  ReplyDelete
 11. ይድረስ የሕይወት ሳይሆን እንደ ጳውሎስ የሃይማኖት ቅናት ለተጠናወተህ ፍቅረማርያም!!!

  ጴንጤ ልሁን ወይስ ተሃድሶ የሚል ጥያቄህን 'ክርስቲያን' ብቻ ሁን የሚለው ንጹህ የእህትነት ምክሬ ክልብህ እንዳልገባ አሁንም ከአጸጻፍህ መረዳት ይቻላል:: ለነገሩ ማን ያውቃል በሚል ቅን አስተሳሰብ እንጂ ከጅምሩም ቢሆን የጥያቄህ መሰረቱ እውነትን ፍለጋ ሳይሆን ፈሪሳውያን ጌታን ለመፈተንና ብሎም ለማሳት ይጠይቁት እንደነበረው ዓይነት ጥያቄ እንደነበረ ተረድቻለሁ:: ቢሆንም ግን እኔ በአቅሜ ድርሻዬን ስለተወጣሁ 'ጆሮ ያለው ይስማ' ከማለትና በቅንነት ለአንተና ለመሰሎችህ ወገኖቼ ከመጸለይ በስተቀር እሰጥ አገባ ውስጥ መግባት አልፈልግም::

  እስቲ አንዳንድ ጥያቄዎችን መልስልኝ:

  1) ጌታ የገዳምን ሥርዓት ከመሰረተ ለምንድነው ከተፈተነና ፈተናውን ከአለፈ በኋላ አግለግሎቱን በሕዝብ መካከል እየዞረ ያስተማረና 12ቱን ሐዋርያት ለሥራ የመረጠው? በምድረ በዳ የገዳም ኑሮ ለመኖር ነበረን?

  2) ደቀመዛሙርቱን በማቴ28:19-20 ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ በማለት ለወንጌሉ ሥራ ሲልካቸው የመሰረተውን የገዳም ኑሮ እንደገና ሽሮት ነው ማለት ነው? ነው ወይስ በገዳም እንዲኖሩ?

  3) በአንድ በተወሰነና ሰው በማይገኝበት ቦታ የገዳምን ሕይወት የሚለማመዱ ሰዎች በጌታ ለክርስቲያኖች
  ሁሉ የተሰጠውን የወንጌል አደራ ሥራ ለማን ነው የሚያዳርሱት? ለዱር አራዊት?? ያውም የወንጌሉ
  ቃል ገብቷቸውና ክርስቶስን በዮሐ1:12 መሰረት ተቀብለውት ከሆነ አይደል?

  4) ምንኩስናና የገዳም ኑሮ በማን እንዴት መቼና ለምን የተጀመረ ይመስልዎታል?

  5) መንኩሶ ገዳም የገባ ሰው ልብና ሃሳብ ፍጹም የተለወጠ ቢሆን ለምን እርስ በርሳቸው ይጣላሉ?
  በዝሙትስ አብዛኛዎቹ ለምን ይወድቃሉ?

  6) በአገራችን አብዛኛው የገዳም ኗሪ መንኮሴ ኑሮ ሲመረው የገባና ነፍስ ሲያጥፋ የሚሸሸግበት ማምለጫ
  ቦታ እንደሆነ ከታሪካችን አላነበቡ ከሆነ የእነዘርአያእቆብን ታሪክ ቢያነቡ? እንዲያውም ኢሕአፓ እና
  ኢዲዩን የመሳሰሉት ፓለቲከኞች ገዳምን መሸሸጊያ ዋሻ አድርገው መጠቃማቸው ለምን ይሆን??

  7) ጌታ ለተከታዮቹ ሲጸልይ 'ከዓልም አውጣቸው አልልህም ነገር ግን በዓለም ሳሉ ጠብቃቸው' ሲል
  ስለገዳም ማስተማሩ ይሆን?

  8) አንድ በጌታ ቃልና በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ተከታይ ዋና ጠላቶቹ የሆኑትን
  ሀ) ዲያብሎስንና ተከታዮቹን ለ)ዓለምን እና ሐ) ሥጋን በፀጋው ጉልበት መቋቋምና ባሸናፊነት
  ህይወት መኖርና የጌታ ታማኝ ምስክር መሆን እንጂ በተሸናፊነት ከሜዳው ሸሽቶ ገዳም
  በመግባትና በመደበቅ ይመስልሃልን?

  9) ቤተ ክርስቲያን በሃዋርያትና በነቢያት መሰረት ላይ እንደ ተመሰረተች ቃሉ ሲመክረን ልክ እንደ
  እነሱ በመንፈስ ቅዱስ እየተነዱ ወንጌልን ለዓለም ማዳረስ እንጂ ጫካ መሸሸግ ይገባልን? እነዚህ
  ባላደራ ሰዎች የተባሉትን ሥራ ዓለምን እየዞሩ ባያከናውኑ ኑሮ ኢትዮጵያ ውስጥ ክርስትና ይገባ
  ነበር ብለህ ታስባለህ? ፊልጶስስ የገዳም ኗሪ ቢሆን ያንን ነፍሱ ጌታን የተጠማች የእኛውን ጃንደረባ
  ወደ ጋዛ በሚያወርደው ምድረ በዳ መንገድ በመገኘት ጌታን የማያውቅ ቤተ መቅደስ (ቤተክስያን)
  ብቻ ተሳላሚ ትሁት ኢትዮጵያዊ ያገኘው ነበርን? ምነው ዛሬ ሁላችንም የጃንደረባው የመማር ልብ
  ቢኖረን???? ገዳም, ፍቅረ ማርያም, ኪዳነምህረት, ምንኩስና ወዘተ አንልም ነበር::

  10) ቤተ ክርስቲያንን 'የገሃነም ደጆች የማይችሏት' ሲል ምን ማለቱ ነው? የገሃነም ደጆች በዓለም
  ውስጥ እንጂ በገዳም የሚገኙ ይመስልሃልን? ለነገሩ ደበተራዎች ከአጋንንት ጋር ቃል ኪዳን ሲገቡ
  ወይም መሪጌታ ሙሴ እንዳለው የሚዋረሱት በዋሻ, በጫካና ጭር ባለ ቦታ ላይ ነው ሲል አንድ
  ምናልባት እንደ እዚህ ያለ ስፍራን ለመኖሪያነት የሚጠቀሙበት ሰዎች ለምን መረጡት አያሰኝም?

  11) 'ወልድ (ቃሉ) ያለው ሕይወት አለው' 'ወልድ የሌለው ሕይወት የለውም::' እያለ አንዲት
  እንኳን የመስቀሉ ቃል የሌላቸው ሰዎች ገዳም ስለኖሩ መንግሥተ ሰማይ የሚገቡ ከሆነ
  እግዚአብሔርና ቃሉ የተለያዩና አምላካችን የሚዋሽ ነው ማለት አይመስልህም? ነው ወይስ
  እንደ የዋህ ዘመዶቻችን 'ከ150 ዳዊት የልብ የዋህነት' ትላለህ?

  12) በመጨረሻ ይች ሰውነቱ ያማረ ወፍራም ልጅ የታቀፈችና የአረብ/ግብጻውያን ሰዓሊዎች
  አሳምረው የሳሏት ሴት የጌታ እናት ትመስልሃለችን? እስቲ በዘፍ10:8 ላይ ስለሚገኘው
  'ናምሩድ' እና በሕዝ8:14 ላይ ስለሚገኘው 'ተሙዝ' እንዲሁም በኤር44:17+25
  ላይ ስላለችው 'የሰማይ ንግሥት' ማንነት እና የጌታ ልደት እየተባለ ዲሴምበር 25
  የሚከበረው በአል ታሪክን በሚገባና በቅንነት አጥናውና ካቶሊክ ያሸከመችንን ጉድ እይ?

  በመጨረሻ እዚህ መዲናችን በሆነችው ከተማችን ውስጥ የሆነውን ለትምህርታችን ላጫውትህ:

  '' አንዲት ጥሩ ኗሪ ወይዘሮ እንደዛሬው የተሃድሶ እንቅስቃሴ ጠንክሮ ባልወጣበት ወቅት ልጃቸውን ጌታ
  ልቡን ነክቶት ከጴንጤዎች ጋር ተቀላቅሎ የነፍስ ጥማቱን በማርካት ላይ እያለ ይሰሙና
  አዝነው ምነው ልጄ በማለት ንግግር ከፍተው ሲጫወቱ የገባውን ያስረዳቸዋል::እናቱም
  የገባቸውን 'እናቱም ልጇም' አንድ ናቸው እኮ ልጄ በማለት በወጣ በገባ ቁጥር ይህንኑ
  የንስሃ አባታቸው ያስተማሩአቸውን ልዩ ወንጌል በማስረዳት ላይ እንዳሉ አንድ ቀን
  ይታመማሉ ከዚያም ሃኪማቸውን እንዲጠራላቸው ይህንኑ ልጃቸውን በአስቸኳይ ሲልኩት
  ልጁ እናቱ ባስተማሩት ልዩ ወንጌል መሰረት የሃኪሙን እናት ጠርቶ ይዟቸው ከተፍ
  ይላል:: ከዚያም እናቱ ምነው ልጄ ሃኪሜን አልኩህ እንጂ እናቱን መች ወጣኝ ሲሉት
  ልጁ ከራሳቸው በተማረው መሰረት 'እናትና ልጅ አንድ ናቸው አላልሺኝም እንዴ?' በማለት
  እናት የዘሩትን የልዩ ወንጌል ትምህርት ውጤት ሳይውል ሳያድር አጨዱት ይባላል''

  'ወንድሜ' ፍቅረማርያም ይህን የጻፍኩልህ መልስ ለመስጠት ሳይሆን ምናልባት ጌታ ልብህን ወደ ማስተዋል ቢመልስልሃና ቢጠቅምህ ብዬ እንጂ ለዚህ ጽሑፌ ከአንተ ጠብቄ እንዳልሆነ ገብቶህ ዳግመኛ መልስ ለመስጠት ባትሞክር?? የማሸነፍና የመሸነፍ ጉዳይ ከሆነብህ ግዴለም እራስህን እንደ አሸናፊ አድርገህ ቁጠረውና እዚህ ላይ ብናቆም መልካም ይሆናል:: ይህን ስል ቃሉን ብቻ መሰረት አድርገው ከሚያስተምሩ ሰዎች ለመማር ፈቃደኛ አይደለሁም ማለቴ እንዳልሆነ ይመዝገብልኝ::

  ሌላው የእውነተኛ የጌታን እናት ስም የዳቦ ስም አድርጎ መጠቀምስ 'አክብሮት' ይሆንን?

  እግዚአብሔር ማስተዋልን ይስጠን አሜን::

  የጌታ ሰላም ይብዝልህ

  አክባሪ እህተህ

  ሰላም ነኝ


  10)

  ReplyDelete
 12. ፍቅረ ማርያምMarch 4, 2012 at 12:58 AM

  የተሰጡት መልሶች በጥያቄዎቹ ተራ ቁጥሮች መሠረት ስለሆኑ በማስተያየት ይነበቡ ፡፡ አመሰግናለሁ

  1. መጥምቁ ዮሐንስ አብዛኛ እድሜውን ያሳለፈው በበረሃና በተወሰነ ምግብ ነው ፡፡ ጊዜው ሲደርስ ለማስተማር ወደ ህዝቡ ቀረበ ፤ ቀሰቀሰ ጌታንም ለማጥመቅ ቻለ ፡፡ እነዚህም በገዳም ያሉ ሰዎች እግዚአብሔር ሲፈቅድላቸውና ሲችሉ ህዝብን ወንጌል ሊያስተምሩ ይችላሉ ፡፡ ከጌታ ጋር ፍጡር ሊነጻጸር ስለማይገባው ማወዳደሩ ስህተትን ይወልዳል ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ እስከ መሞት ተጉዟል ፡፡ ታድያ ለመሞተ የተዘጋጀ ክርስቲያን ነኝ የሚል ይኖር ይሆን? ስለዚህ ሰዎችን ከአምላክ ጋር አነጻጽረሽ ከሆነ ስህተት እያደረግሽ ነው ፡፡ ኢየሱስ ስለ ዮሐንስ ሲገልጽ ከሴቶች ከተወለዱት ሁሉ በላይ ብሎ ገልጾታል ፡፡ ታድያ ከተማ ስለተቀመጠ ያንን ምስክርነት አገኘ ?

  2. የገዳም ህይወትና የደቀ መዛሙርትነት ሥራ የተለየየ ነው ፡፡ ሁሉ ሰው ገበሬ ሊሆን አይችልም ፡፡ አንዱ ገበሬ ከሆነ ሌላው ነጋዴ ፣ ሌላው ደግሞ መምህር እንደ እኔና እንደ አንቺ አይነቱ ደግሞ የጌታ ተከታይ ይሆናል ፡፡ የእነዚህ ሰዎች ገዳም መግባት መጀመሪያውኑ የሚያነጣጥረው ራሳቸውነ ማጽዳትና ማትረፍ ላይ ነው ፤ ከዛ ባለፈ በጸሎታቸው ስለ አገር ፣ ስለ ህዝብ ፣ ስለ መንግሥት … ይጸልያሉ ፡፡


  3. የሶስተኛውም መልስ ከላይኛው ጋር ተጠቃልሏል

  4. ታሪክ ተመራማሪዎች ከቡድሃ ሃይማኖት ጋር ያዛምዱታል ፡፡ እኔ ግን የቡድሃ ሃይማኖተ ተከታይ ስላልሆንኩ ከመጽሃፍ ቅዱስ አኳያ ያለውን እውነታ እመሰክራለሁ ፡፡ ሌላው እንደ ጥበቡና ችሎታው ማያያዝና መተርጐም ይችላል ፡፡ የገዳም ትርጉሙ ዓለምን የናቁ መናኞች ፣ ባሕታውናንና መነኮሳት መኖሪያ ፤ ዓለማዊ /ምግባር/ የሌለበት ስፍራ ፣ ዱር ፣ በረሐ ፣ ደን ፤ መማጠኛ ስፍራ ማለት ነው ፡፡ ከዓለማዊ ፍላጐት የሚለዩበት ፣ ዓለማዊ ህይወትን ክደው የሚኖሩበት ሥፍራ ነው ፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ቃሉ በቀጥታ ገዳም ባይባልም ፣ ሙሴ አርባ ቀንና ለሊት ያለ እህልና ውሃ የከረመበት ተራራ ሁሉ ለኔ የገዳም ልምምድ ያህል ነው ፡፡


  5. መጣላትና በሥጋ ፍላጐት መድከም የተፈጥሮአችን ጉዳይ ነው ፤ ተረስቶሽ ካልሆነ በስተቀር አንድ ሰው እንኳን ቅዱስ የለም ይላል መጽሐፉ ፡፡ እግዚአብሔር ሲፈቅድልሽ ጽናቱን ያድልሻል ፤ እንደ እኔ ዓይነቱ ደካማና ሰነፍ ደግሞ ሰላሳ አርባ ጊዜ ይወድቃል ፤ ያ ግን የብዙሃኑን ህይወት አይወክልም ፡፡ ይኸው ሰሞኑን እንኳን አባ ማናቸው ልጅ ወለዱ ፣ አይወልዱም በመባባል አደባባይ ወጡ አይደል ፡፡ እንግዲህ በሊቀ ጳጳስ ደረጃ ያለ ሰው በድንግልና ይኖራል ፤ ሲሞትም ንብረትና ሃብቱን ለቤተ ክርስቲያን ያወርሳል የሚል ወግ ነበር የምናውቀው ፤ ታድያ በሳቸው ሰበብ ሁሉ አባት ሊወቀስ ነው ፡፡ የትስብዕት ባህርይ ስለሆነ ከአግባቡ ውጭ መሆን ልማድ ነው ፡፡ እንደዛ ሲሆን ማዘን አለብን

  6. እናት ዓለም ሃይማኖትንና ሌላውን አጀንዳ /ፖለቲካን/ አብረን እያደባለቅን ከሄድን የበለጠውን የተሳሳተ አመለካከት ይኖረናልና ፣ ሌባ ከቤትሽ ሮጦ ቢሸሸግ አንቺን ሌባ ማለት እንደማልችል ያህል ማለቴ ነው ፡፡ ወንጀል ከሠሩ በኋላ ስለሃይማኖት ከሆነ የገቡት ፣ የገዳም ትርጉም ከላይ ገልጨዋለሁ ፣ ያስኬዳቸዋል ፡፡ የንስሐና የመጸጸቻ ሥፍራ አድርገው ስለሚጠቀሙበት ፣ በዓለማዊ ነገር ስለማይጠመዱ ድንቅ ቦታ ነው ፡፡ መንፈሳቸውን ወደ ፈጣሪ ብቻ ያደርጋሉ ፤ ይጾማሉ ፤ ይጸልያሉ ፤ ይሰግዳሉ … የሃይማኖትን ነገር ይለማመዳሉ ፡፡


  7. አንዲት ነፍስ ብትተርፍ በሰማይ ምን ይሆናል? ስለዚህ ገዳም የገቡ ሰዎች ችለው ለህዝብ ቢደርሱ እጅግ መልካም ይሆን ነበር ፡፡ ያ ሳይሆን ቀርቶ ፣ ጌታን አውቀው ራሳቸውን ማትረፍ ከቻሉ በሰማይ ከበሮ ተይዞ ይጨፈርላቸዋል ይላልና አንዘን ፡፡ ሁሉም ዘማች ሊሆን አልተፈጠረም ፡፡ ሁላችንም ራሳችንን ለማትረፍ ነው የመጀመሪያ ሩጫችን ፡፡ እሳት ቢነሳ ለማምለጥ እንደምንሽቀዳደመው ማለት ያህል ፡፡

  8. ይኸ እንደ ጽናታችንና እንደ ብቃታችን አለ ፡፡ ወደ ፈተና አታግባን ብላችሁ ጸልዩ ብሎ ያስተማረው ጌታችን ይኸን የዓለም ፈተና ስለተረዳው ነው ፡፡ ዓለም ውስጥ ሆኖ ዓይኑን ፣ ምላሱን ፣ እጁን መቆጣጠር የማይችል ከሆነ ትክክለኛው ቦታ በፈቃዱ ከመረጠው ገዳም ነው ፡፡ ቢያንስ ብዙ ዓለማዊ ፈተና አይገጥመውም ፡፡ ድንግል ማርያም ጌታን ይዛ የተሰደደችው የጌታ ህይወቱን ለማትረፍ ነው ፤ መጋፈጥ ትችል ነበር ፡ ነገር ግን ልጅዋ እንደሚገደል ስላወቀች ሸሸች ፡፡ እነዚህም ሰዎች ደግሞ በዓለም ቢሰነብቱ የሚገጥማቸውን ፈተና መቋቋምና ማሸነፈ ስለማይችሉ ወደ ተሻለ ስፍራ መሄዳቸው መልካም ነው
  ይቀጥላል

  ReplyDelete
 13. ፍቅረ ማርያምMarch 4, 2012 at 1:14 AM

  9. ገዳም የገባው የህዝብ ቁጥር ይህን ያህል የራስ ምታት የሚሆንብን አይደለም ፡፡ ከተሳካልንና ፈቃዱ ካለን ከገዳም ውጭ በዓለም ያለነው ሰዎች እንኳንስ በምድር ፣ ጨረቃም ሰው ከተገኘ እዛም ድረስ ሄደን ለማስተማር አናንስም /ቁጥራችንን ለማለት ነው/ ፡፡ ሌላ በአእምሮአችን ውስጥ የሚብላላ የሚያመን ስውር ነገር ከሌለ የእነዚህ ሰዎች ራሳቸውን ለማትረፍ መትጋት ርዕስ ሊሆን አይገባም ፡፡ መጀመሪያ እኔና አንቺ መጽሐፉን የምናውቀው መች ከአገር አገር ተንቀሳቀስንና ሌሎችን አልሠሩም ብለን እንወቅሳለን ፡፡ ሁላችንም ማስተማር የምንፈልገው እኮ ከተማ ከተማውን ፣ ቴሌቪዥንና ኢንተርኔት ባለበት ቦታ ነው ፡፡ በማስተማር የምናምነው እኛ ፤ ችሎታ አለን ፣ አደራ አለብን ብለን የምናምነው እኛ ፤ ስለዚህ መጀመሪያ እኛ እንዝመት ፤ ከዛም የእኛ ቁጥር ካነሰ እነሱን እንቀሰቅሳለን ፡፡ የሚያስማማን ይመስለኛል ፡፡

  10. ወቀሳውን ተቀብያለሁ ካገኘሁዋቸው ሃሜታውን ጭምር አስተላልፋለሁ

  11. ጌታ ይባርክሽ ፡፡ አላስተማሩም ስትይ የከረምሽው የጌታ ቃል የሌላቸውን የኔ ብጤዎችን ነው እንዴ? በይ ከዚህ በላይ ያለውን ጥያቄዎችሽን በሙሉ ሠርዥልኝ ፡፡ ጥያቄ ፈጥረሽ መልስ ሳታገኝ አፈረስሽው ፡፡ እንዲያው በቀና ካየሽው በዓለም ሆነው በብዙ ዓለማዊ ነገር ተጠምደው ምንም ሳያውቁ ከገቡት እንኳን ቀስ በቀስ በጸሎቱ ፣ በንባቡ ፣ ከሌሎቹም ወገኖች ስለሚማማሩ የተሻለ ክርስትናውን የመማር እድል አላቸው ፡፡ ከዚህ በላይ ተሻግረን የጌታ ቃል ይጐድላቸዋል የምንል ካለን አሁንም እኛ እነሱን ለመገምገም ጌታን ሆነናል ማለት ነውና ቀስ በቀስ እንደግ ፡፡ ስለ ሰው ብቃትና ጽድቅ ማውራት አቁሙ ፡፡ እንኳንስ ሰለ ሰው ፣ እኔ ስለ ራሴም መናገር ያዳግተኛል ፡፡ መጥፎ ልማድ ነው ፡፡ ወንድም ወንድሙን በደካማነት በደንቆሮነት አይወቅሰውም ፡፡ ስላልተማሩ እንደኔና እንዳንቺ ኃይለ ቃል ላይመዙ ይችላሉ ፡፡ ነገር ግን እምነታቸውን የሚፈልግ ፣ የሚቃኝ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ይቀበላቸዋል ፤ የጐደላቸውን እሱ ራሱ ሰው ሆኖ ድክመታችንን ስላየልን በእርግጠኛነት እነግርሻለሁ ፣ እንደእኔና እንደ አንቺ አይፈርድባቸውም ፡፡ ቢያንስ እሱን ፍለጋ ቤት ንብረት ትተው ሄደዋልና ፡፡

  12. የማትወቅሽው የእምነት ድርጅት የናንተን ብቻ ነው ፡፡ ይኸ ደግሞ ሌላው መጥፎ ዓመል ነው ፤ ስለሌሎች የሃይማኖት ድርጅቶች አንነጋገር ፡፡ ስለ ሌሎች ሰዎች እምነት አንከራከር ፡፡ ከቻልን ማስተማርና መግለጽ ነው እንጅ መተቸቱ ቅራኔንና ክርክርን ነው የሚወልደው ፡፡ የሥዕል ነገር የተጀመረው በካቶሊኮች አይደለም ፡፡ ኢስተርን ኦርቶዶክስ በማለት ረሺያና ግሪክ የተገነጠሉት አንደኛው የልዩነት ምክንያት ስዕልን በተመለከተ የተነሳው ጥያቄ ነበር ፡፡ ስዕል መጠቀም የተጀመረው ለማስተማር በማለት ፣በምድር ውስጥ ባሉ ዋሻዎች እየሠሩ በመሄድ ፣ ዋሻ የሄደ ሰው ስለሚያየቸው ፣ ማንበብ መጻፍ በማይችል ህብረተሰብ ውስጥ ሃይማኖቱን ለማስተማሪያነት በስፋት ስለተገለገሉበት ነው ፡፡ ኋላም በየቤተክርስቲያን ግድግዳ ላይ እየሳለ ህዝቡ ወንጌልን በአይኑ ጭምር እየቃኘ እንዲረዳ መገልገል ጀመሩ ፡፡ የአምላክ ፎት ይኸ የምናየው ይሁን ማረጋገጥ አይቻልም ፡፡ ቢያንስ የዚህ የኛ ዘመን ቴክኖሎጅ ስለሌለ የተዋጣ ነገር ላይኖራቸው ይችላል ብዬ እገምታለሁ ፡፡ ያም ቢሆን ግን ከፎቶ የተሻለው የሚስሉ ሰዓሊዎች /ሌዎናርዶ ዳቪንቺና ሌሎቹ/ ካገኙት ስዕልና ጽሁፍ በመነሳት ጥሩ ጥሩ ምስል ሠርተዋል ፡፡

  *****አንቺ ብለሽ ብለሽ ማዝናናትም ጀመርሽ ፤ ድንቅ ትምህርተ ሰጭ ነው ፡፡ የኔንም ተመልከቺው

  በግ ገዥ ስለ ሻጭ ያወራል ፤ በግ ሻጭ ደግሞ ስለ በግ ይመልሳል ፤ ሁለቱም የሚያግባባቸውን ቋንቋ ከመናገር ይልቅ ፣ ለየቅል በየራሳቸው መንገድ በመጠቀማቸው ትርፉ … ሆነባቸው ፡፡ ቁልቁል ብታነቢው የሚሉት ፈጠን ብሎ ይገባ

  ገዥ - በያዘው ዘንግ በጉን እየወጋጋ ፣ ባለ በግ
  ነጋዴ - አይሸጥም ለዘንግ
  ገዥ - ምን ይላል ይሄ !!
  ነጋዴ - ከጠሩት ባ ይላል
  ገዥ - ምን የሚያራ ነው !!
  ነጋዴ - ምን ቢበላ በጠጥ
  ገዥ - የት ያደገ ነው !!
  ነጋዴ - ከጋጥ
  ገዥ - ሽመሉን ጥሎ ጩቤውን ከማኀደሩ ላጥ አደረገው
  ነጋዴ - አይተንልሃል ፣ ሁለት ጨው ያወጣል ፤ ይሸጥ እንደሁ ወዲህ በለው

  ሰላም ሁኑልኝ

  ReplyDelete
 14. ፍቅረ ማርያምMarch 4, 2012 at 9:25 AM

  በተራ ቁጥር 1ዐ ለተጠቀሰው ጥያቄ መልስ ይሆን ስለመሰለኝ እላለሁ - ቢሳካልኝ እኔም ለራሴ የገሃነም ደጃፍን ማየት አልመኝም ፤ ያ እነሱ የመረጡት በእርግጥ ይኸን የገሃነም ደጃፍ የማያሳይ ከሆነ የኔም ጸሎቴ እሱው ነው ፡፡ ጀግና የሆነ ወታደር በደረት ገብቶ መዋጋት ይችላል ፣ የኔ ብጤ ፈሪና ደካማ ደግሞ እየተሰወረ ላለመፈተን ፣ ላለመጋፈጥ ይሞክራል ፡፡ ውሳኔው እንደየሰውነታችንና እንደየባህሪያችን ሊለያይ ይችላል ፡፡ ጀግንነት የሚስማማው ሰው ያለውን ያህል ፣ ፈሪ የናቱ ልጅ የሆነም አለና ፣ ያለፍላጐቱ የግድ በተጽእኖ የባህርይ ለውጥ አምጣ ለማለት ይከብዳል ፡፡

  ሌላው ሳልጠቅስ የማላልፈው አሁን አሁን በእምነት የናንተ ደጋፊ መሆን ያልቻለውን ሁሉ ደብተራ ፣ ጠንቋይና አስማተኛ የማለት አባዜ እየለመደባችሁ የመጣ ይመስላል ፡፡ በአለፈው አባ ሳሙኤልን ምን ለማለትና ምን ለመቀባት እንደሞከራችሁ የታዘብኩት ከአእምሮዬ ሳይጠፋ አሁን ደግሞ በገዳም ራሳቸውን ያገለሉ መነኰሳትን ይኸው ስም ሊለጠፍላቸው የሚሞከር ይመስላል ፡፡ እነሱ እንኳንስ በአሉባልታ ሊፈቱ ብንገድላቸው እንኳን እንደ እስጢፋኖስ “የሚሠሩትን አያውቁምና ጌታ ሆይ አትመልከታቸው” ይሉና ይጸልዩልን እንደሆነ እንጅ ለእኛ አሉባልታ መልስ አይሰጡም ፡፡ የቅድስና ማረጋገጫው እንደ ጥንቷ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እናንተ ምኩራብ ውስጥ ሊሰጥ ወይም ሊሸጥ የታቀደ ይመስላልና ስህተትን ደግማችሁ አትፈጽሙ ፤ ይህ ዓይነቱ አቋም የትምክህት መገለጫ ነው ፡፡ መንገዳችሁ ጥሩ አይደለም ፤ አባባላችሁ ከማስተማር ይልቅ ወደ መውቀስ ያዘነብላል ፡፡

  ከተራ ቁጥር 12 ጥያቄዎች ውስጥ ለተዘለለው መልስና ትምህርት እንዲሆነን በማለት
  የክርስትና ሃይማኖትን ጉዞና የዕድገት ታሪክ ስንመለከት ፣ የሮም መንግሥት በንጉስ ቆስጠንጢኖስ አማካኝነት ያደረገችውን አስተዋጽዖ መካድ አንችልም ፡፡ ክርስትና እንደ ሃይማኖት ዕውቅና ያገኘና ፣ የአደባባይ እምነት ለመሆን የበቃው በዚሁ መሪያቸው ውሳኔ ነው ፡፡ ከዛ በፊት የነበረው የክርስትና ህይወት በሙሉ እንዲህ በአደባባይ ሆነው የሚተርኩት ፣ የሚመሰክሩለትና የሚያስተምሩት ሳይሆን የሚወገሩበትና የሚታረዱበት ፣ የሚጋዙበትና የሚቃጠሉበት ፣ ለአውሬ የሚሰጡበትና የሚሰደዱበት ነበር ፡፡ በዘመኑ የጣዖት ፣ የፀሃይና የጨረቃ ባዕድ አምልኮዎች በሰዎች ዘንድ በእጅጉ የሠለጠኑ ስለነበሩ ፣ ክርስትናን የሚቀበል ግለሰብን ማግኘት የተአምር ነው እንጅ የዕለት ተዕለት ገጠመኝ አይደለም ፡፡ ንጉሡ በእርግጥ ኋላ ላይ አምኖ መጠመቁ ባይካድም ይህን ጣምራ እምነት የፈቀደው የክርስትናው እምነት ገብቶትና ተቀብሎት አልነበረም ፤ ነገር ግን አገሩን በሰላም ለማስተዳደር እንዲያመቸው ፣ ሁሉንም ወገኖች ያቀፈ ሥርዓት ለመዘርጋት በመፈለግ ነበር እንጂ ፡፡ ኋላም የነበረውን የኀብረተሰብ እምነት በአንድ ጊዜ መቀየር ስለማይቻል ፣ ንጉሡ የወሰነው የባዕድ አምልኮውና የክርስትናው እምነት ጐን ለጐን ፣ በጣምራ ፣ በእኩልነት በአገሪቱ ውስጥ መተግበር እንደሚቻል ማወጁ ነበር ፡፡ በአገራችን ክርስትናና የእስልምናው ወይም የኘሮቴስታንቱ እምነት በጣምራ ነጻነት እንደሚንቀሳቀሱት ማለት ነው ፡፡ ይኸ ለክርስትና ሃይማኖት ዕድገት እጅግ ትልቅ እመርታ ወይም የድል ምልክት ነበር ፡፡

  አብረው ይተገበሩ በነበሩበት ወቅት አብዛኛው ህዝብ የባዕድ አምልኮ ተከታይ በመሆኑ ክርስትናውን ለማስፋፋት ሲባል አንዳንድ የባዕድ አምልኮ በዓሎችን የክርስትናው እምነት በዓል ማድረግ ተጀመረ ፤ በዚህም የዲሴምበር 25 በዓል በወንጌል ብዙም በውል የማይታወቀው የጌታ ልደት ዕለት ፣ በዓል እንዲሆን ተወሰነ ፡፡ ይህም በዘፈቀደ አይደለም ነገር ግን በሉቃስ ወንጌል 2 ፡ 8 ከተጠቀሰው የእረኞች ታሪክ በመነሳት ፣ እረኞች በሜዳ ሲጠብቁ የሚያድሩበትን ወቅትና ወራት በማስላት የተወሰነ ነው ፡፡ ከዚሁ በተጨማሪም በዚሁ ዕለትም አያሌ ክርስቲያን ወገኖችና አባቶች አስቀድመው በመስዋዕትነት ተገድለውበት ስለነበር ፣ የነሱንም የፈሰሰ ደም ተረግጦ እንዳይቀር ፣ ጉዳያቸውን ለማንሳት በማሰብ ጭምር የተደነገገ ነው ፤ በአንድ ደንጊያ ሁለት ወፍ እነዲሉ ማለት ነው ፡፡ የሰማዕታቱን ዕለት ብቻ መታሰቢያ ላድርግ ቢል ኖሮ ለክርስትና እምነት አደላህ የሚሉ ተቀናቃኞች ይነሱበት ነበር፡፡ ይህን የባዕድ አምልኮ በዓል ቀን ክርስትናው ባይቀበልና የራሱን ርዕስ ሰጥቶ ማክበር ባይጀምር ኖሮ ፣ ባዕድ አምልኮው በክርስትና እምነት ተውጦ የመጥፋቱ ነገር ዘበትና የማይታሰብ ይሆን ነበር ፡፡ ስለዚህም ዲሴምበር 25 የጌታ ልደት መከበር ለክርስትናው መስፋፋት ትልቅ አስተዋጽዖ አድርጓል እላለሁ ፡፡ ዛሬ ያለነበትና ይኸ ታሪክ የተፈጸመበትን ዘመን ማወዳደርና መተቸት ለእኔ በክርስትናው ታሪክ ላይ ወንጀል እንደመሥራት ያህል ነው ፡፡

  የካቶሊክ እምነት በኢትዮጵያ ላይ ያደረሰው የገነነ የሃይማኖት መወራረስ ጉዳይን በንባብ አላገኘሁም ፡፡ በእኛ የክርስትና ሃይማኖት ላይ ትልቅ አስተዋጽዖና ተጽዕኖ የነበራቸው ግብጾች ፣ ግሪኮችና አገራችን የገቡ አይሁዶች ናቸው ፡፡ የቀን አቆጣጠራችንም በራሳችን የስሌትና የአተረጓጐም የተፈጠረ ነው እንጅ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የለጠፈችልን አይደለም ፡፡ የማይታለፍ ጉዳታቸው ከአፄ ገላውዴዎስ እስከ አፄ ሱስንዮስ እስከ ልጁም ፋሲለደስ ዘመን ድረስ ወደ አገራችን የመጡት የፖርቱጊዝ የካቶሊክ መነኰሳት ቤተ ክርስቲያንን ሁለት ዓይነት ትምህርት አስተምረው በመውጣታቸው ፣ ክርስቲያን የሆነው ወገን በግፍ ፣ በማያውቀው ሴራና ተንኮል ተጠምዶ እርስ በርሱ ጸጋ ፣ ካራና ቅባት በመባባል ሲተራረድ ቆይቷል ፡፡ በዚህም ምክንያት በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ክርስቲያኖችና አያሌ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ተገድለዋል ፡፡ ለወደቁ አባቶች መቆርቆሩ ባህልና ወግ ያለን ፣ በቤተ ክርስቲያናችን ታሪክ ላይም ትልቅ ቁስልና ጠባሳ የፈጠሩትን እክሎች የምንፈትሽ ቢሆን ኑሮ የእነዚህም ደመ ከልብ ወገኖች ጉዳይ ለትምህርት እንዲሆነን መነሳት ፣ መመርመርና መታወቅ የሚገባው ነበር ፡፡

  የግብጾችንም ተንኰል የተሞላ ተጽእኖ በቅንጫቢ ከወሰድኩት የመጽሐፍ ቃል ተመልከቱት ፡፡ ኢትዮጵያዊ ሲባል ፍጹም አማኝ ፣ መታለልንና ማታለልን የማያውቅ ፣ ቅዱስ ህዝብ ፣ የተነገረውን በሙሉ እውነት ነው በማለት በእምነት የሚቀበል መሆኑን የተረዱት ግብጾች ትልቅ የተጽእኖ ትምህርታቸው እንዲህ ይነበባል ፡- “ጳጳስ የሚኾነውን ሰው ጥንቱን ሲፀነስ በናቱ ራስ ላይ ኋላም ሲወለድ በሕፃኑ ላይ ነጭ ርግብ ከሰማይ ወርዶ ያርፍበታል ፡፡ ይህ ምልክት ያልታየበት ሰው እንኳንስ ጥቁሩ ኢትዮጵያዊ ቀዩ ግብጽም ቢኾን ጰጳስ ለመሆን አይበቃም” ፡፡

  ከዚሁ የተንኰል ትምህርት የተነሳም እስከ ቅርብ ዘመን ድረስ አገራችን ጳጳስ የተባለውን በወርቅና በብር ለውጥ እየለመነች ታስመጣ ነበር ፡፡ ይኸ የሃይማኖት ንግድ የቀረው በአያሌ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ያላቋረጠ ትግል ቢሆንም ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ስለፍጻሜው ምስጋና ይገባቸዋል ፡፡

  ጸሃፊው በመቀጠልም የታዘቡትን ሌላ የተፈጠረ ጉዳት አክለውም እንዲህ ጽፈውታል “አላስተርጓሚ የማይሰሙትን ፣ የማይሰማ ቋንቋና መልኩ የተለየ ፣ የውጭ አገር ጳጳስ ፣ አባ ቀዮ በመጣ ቁጥር ፣ በሃይማኖት ነገር ጢስ እንደ ገባው ንብ ሲታወኩና ሲታመሱ ሲተራመሱ ፣ ሲሟገቱና ሲፋለሱ ፣ ሲካሰሱ ይኖራሉ፡፡”

  ለዚህች ቤተ ክርስቲያናችን ሰለቸኝ ደከመኝ ሳይሉ የታገሉላትን ሁሉ እግዚአብሔር ያስብ

  ReplyDelete
 15. "Merigeta" Musse, if you deny your holy believe, please leave the title to where you get it from. In addition, please stop using our holy language Geez. All the words that you are using to prove that you know the almighty GOD (JESUS) is since you met the protestant world. Meanwhile, you are using the Ethiopian Orthodox true teaching that you learned in the holy places of Ethiopian Orthodox Church. I just want to remind you that you know that the Ethiopian Orthodox Church knows JESUS CHRIST before the protestant, and you learned about His love, forgiveness, and that he is alpha and omega. May God bring you up to where you were from your current degrade .

  ReplyDelete