Monday, February 20, 2012

በሁለቱ ሲኖዶሶች መካከል የተጀመረው የእርቅ ውይይት መልካም እርምጃ ነው - - - Read PDF

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ለኢትዮጵያ ያደረገችው አስተዋጽኦ ተቆጥሮ የማያልቅ ነው። ባለፉት የመከራም ሆነ የደስታ ዘመናት ለኢትዮጵያውያን ሁሉ ባለውለታ ናት። እስላሞችም ይሁኑ ፕሮቴስታንቶች ይህን እውነት የሚክዱ አይመስለንም። የኢትዮጵያን ሕዝብ ከባሕልም ሆነ ከመሬት ወራሪዎች የታደገችው ይህች ቤተ ክርስቲያን ናት። ዛሬ እነ አላሙዲ የያዙት ሰፋፊ የርሻ መሬት፣ የውጭ ወራሪዎች አስቀድመው ወስደውት ቢሆን ኖሮ እዲህ በዋዛ አይገኝም ነበር። መንግሥት ዛሬ ለሕንድና ለቻይና ባለሐብቶች እየሸጠ ወዳጅነቱን ያጠናከረበት መሬት ከጣሊያን ገበሬዎች ያመለጠ ነው።
  ሕዝቡ ምንም ዓይነት እምነት ይኑረው በራሱ ቋንቋና ባህል ለመጻፍ፣ ለማንበብ፣ ለመናገር ችሏል። ይህ ምን ቁም ነገር አለው የሚሉ ሞኞች ባይጠፉም ራስን ማወቅና በራስ መተማንን የሚመስል ጥሩ ሀብት የለም። የምዕራባውያን መንግሥታት ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ያሉት ማንኛውም በስደት የመጣ ሕዝብና ነገድ የራሱን ባሕል ቋንቋና ታሪክ እንዲጠብቅ ነው። ምክንያቱም ማንነታቸውን ያጡ ሕዝቦች ሞራል አልባ ሆነው እያስቸገሯቸው ስለሚገኙ ነው።
  ማንነትን ማጣት የሕይወት ለውጥ አይደለም። እግዚአብሔርም ሰው ማንነቱን እንዲያጣ አይወድም። ኢትዮጵያውያን ሁሉም ነገር ያላቸው ከኢኮኖሚ አቅም በቀር በራሳቸው መኖር የሚችሉ ሕዝቦች ናቸው። በዚህ ሁሉ ጌታ እግዚአብሔርን እናመሰግናለን። ዛሬ ላይ ላገኘነው መልካም ነገር ሁሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጋለች። የሕዝቡን አንድነት፣ በመጠበቅ፣ ጠላት ሲመጣ ሕዝቡን በመንፈሱ ከፍ ብሎ እንዲጋደል በማድረግ፤ መንፈሳዊ እሴቶች እንዳይሸረሸሩ በማስተማር ትልቅ ሥራ ሠርታለች። ስለዚህ የዚህች ቤተ ክርስቲያን ለሁለት መከፈልን የማንፈልገው መጥፎ ነገር ነው። ቤተ ክርስቲያናችን ከማንኛውም የውጭ ተጽእኖ ነጻ ሆና በእግዚአብሔር መንግሥትነቷ እንድትንቀሳቀስ ጥልቅ የሆነ ምኞታችን ነው።
 በእርግጥ ቤተ ክርስቲያናችን ተሀድሶ ያስፈልጋታል። የስሕተት ትምሕርቶች ለሕልውናዋ አደጋ ናቸው፣ ሙታን ሳቢ፣ አጋንንት ጠሪ፤ ድግምት ደጋሚ፣ አገልጋዮች፤ የቤተ ክርስቲያኒቱ ፈተናዎች ናቸው። በጌታ ቃል ሳይሞሉ መድረክ ላይ ወጥተው መጥፎ ዘር የሚዘሩ ሐሰተኛና አመንዝራ ሰባኪዎች፣ ለቤተ ክርስቲያኒቱ እጅግ አደገኞች ናቸው። እንደወረርሽኝ ቤተ ክርስቲያኒቱን የወረሩ ሐሰተኛ መነኮሳት ከባድ ፈተናዎች ናቸው። ፖለቲከኞች መድረኩን ቀድሞ ለመያዝ የሚያደርጉት ትግል ቤተ ክርስቲያኒቱን የሚጎዳ ነው። ችግሮች ዘርፈ ብዙና ውስብብ ያሉ ናቸው። እነዚህ ሁሉ ችግሮች ሊፈቱ የሚችሉት ግን እንደ እግዚአብሔር ቃል ተሐድሶ ስናደርግና ወደ ቀደመው የአባቶቻችን እምነት ስንመለስ ብቻ ነው።
በሰሜን አሜሪካ በሁለቱ ሲኖዶሶች መካከል የተጀመረው የእርቅ ሂደት አንዱ የተሀድሶ አካል ነው። ተሀድሶ ማለት የፈራረሰውን መጠገን፤ የተበላሸውን ማስተካከል ነውና እርቅ መጀመርም ተሐድሶ ነው። ይህ የተሃድሶ እንቅስቃሴ በፖለቲከኞች መካከልም ቢጀመር የኢትዮጵያ ተሐድሶ በቅርብ ጊዜ ይሳካል። በማሕበረ ቅዱሳን እና በተሐድሶ እንቅሥቃሴ ማህበራት መካከልም ተሐድሶ መጀመር አለበት። የጥንቶቹ ቡድኖች ለመታረቅ ተሐድሶ ሲጀምሩ ሌላ አዳዲስ የጠላትነት ቡድኖች መከሰት የለባቸውም። ተሐድሶ በያቅጣጫው ያስፈልግናል።
  በአሜሪካው የእርቅ ድርድር አባቶች በቀኖና ጉዳይ አልተግባቡም፤ ነገር ግን ከቀኖና ይልቅ ፍቅር እንደሚበልጥ መታወቅ ነበረበት። ሆኖም አብሮ መብላት ጀምረዋል፤ አብረው ዘምረዋል፣ አብረው ተጫውተዋል፣ መንፈሳዊ ሰላምታም ተለዋውጠዋል፤ የሰላሙ ውይይት ወደ ፊት እንዲቀጥል ተስማምተዋል። መልካም እርምጃ ነው፣ ተሐድሶ ማለት እንዲህ ነው። ተሐድሶ የማያስፈልገው ምንም ዓይነት ሁኔታ የለም፤ ትዳር ተሐድሶ ያስፈልገዋል፤ ወደ ቀደመው ፍቅር መመለስ ማለት ነው፤ ቤት ተሐድሶ ያስፈልገዋል ወደ ቀደመ ውበቱ መመለስ ማለት ነው፤ አእምሮ በየጊዜው ተሐድሶ ያስፈልገዋል ወደ ትክክለኛው አስተሳሰብ መመለስ ማለት ነው። መንግሥት ተሐድሶ ያስፈልገዋል፣ ሙስናን፣ ዘረኝነትን፣ ጭቆናን፣ ጥላቻን፣ ወንጀልን፣ ክፋትን፣ አመጽን፣ ከሐገሪቱ ማስወገድ ማለት ነው። ምድር እራሷ ተሐድሶ ያስፈልጋታል አስፈላጊውን ሰብል እንድትሰጥ አፈሯን በማለምለም ወደቀደመ ችሎታዋ መመለስ ማለት ነው። እባብና ንሥር በየጊዜው ይታደሳሉ፣ እህያ እንኳ ጀርባው በሚገጠብ ጊዜ በቅቤና በቂጫማ ቅጠል ይታደሳል። እንኳን በሰው የተፈጠረ በእግዚአብሔር የተፈጠረ ነገር ሁሉ ይታደሳል።
 ቤተ ክርስቲያንም ተሐድሶ ያስፈልጋታል፤ ተሐድሶ የማያስፈልገው እግዚአብሔርና በርሱ የተገለጠልን እምነት ብቻ ነው፤ እምነት አይታደስም ቤተ ክርስቲያን ግን ትታደሳለች። በውስጧ ሾልኮ የገባውን የስሕተት ትምሕርት፣ አላስመልክ ያለውን ሰው ሰራሽ ልማድ፤ በደብተራዎች አማክኝነት የሚፈጸመውን የሰይጣን ተንኮል ማስወገድ ማለት ነው። የከበረውን ከተዋረደው መለየት እንደ እግዚአብሔር ቃል የሆነውን መጠበቅና ማስተማር፤ እንደ እግዚአብሔር ቃል ያልሆነውን ማስወገድ ማለት ነው። ጥሩ መንፈሳዊ ባሕልን መጠበቅ ሃይማኖት መስሎ የተቀመጠ የክፉ መንፈስ ወግን ማስወገድ ማለት ነው። በወንድማማቾች መካከል የተፈጠረውን መለያየት ማስወገድ አንዱ የቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ ነው። ተሐድሶን የሚፈሩ የተሐድሶን ጥቅም ያላወቁና በሐሰተኛ ፕሮፓጋንዳ የተሰለቡ ብቻ ናቸው። ተሐድሶ ንስሐ ማለት ነው። ሁልጊዜ ነቢያት ያስተማሩት ሐዋርያት የመሰከሩት ስለተሐድሶ ነው። ውስጣችን መታደስ አለበት፣ አካሄዳችን መታደስ አለበት፣ አኗኗራችን መታደስ አለበት።
 በሁለቱ ሲኖዶሶች መካከል የተጀመረው የእርቅ ተሐድሶ መቀጠል አለበት፤ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶችም ይህን ዓይነቱን ተሐድሶ እንዲጀምሩ እንማጸናለን መንግሥትም ተሐድሶን እንዲደግፍ ጥሪ እናደርጋለን።
ክብር ለአምላክችን ለኢየሱስ ክርስቶስ! ተሐድሶ ለቤተ ክርስቲያን! ትንሣኤ ለኢትዮጵያ ይሁን አሜን!!!!
ኢትዮጵያዊ ነኝ
     

9 comments:

 1. Mechem asteyayeten yemitawotut ayimeslegnim. bihonim zim alilimina lingerachihu
  Yemin maskeyes newu enante? "Tinish kolo yizo wede asharo tega" malet yichi nat. Degmo Behaymanotachin Dogimana Kenona lay mades yasfeligal setilu kermachihu Eyesus amalaj new sitilu norachihu Kidusan ayamalidum melaekit ayradum dingil mariam amlakin alwoledechim sitilu kemachihu ahun min lemalet new yeabatochin wuyiyit ketehadisogare erikina selamin kekihdet gar yemitayayizut? Egna YeOrthodox amagnoch durom bihon Tenkuway metetegna ena muartegnan anamelkim. Yenante wegen yehonut ende debtera muse yalu legenzebina lesigachew yaderu yesytan maderiya yehonu sewoch yefelegutin genizeb kagegnu behuala zare tremelishalehu eyalu beyachiberebiru yaniniw yemifeligutin genzeb enante betezewawari keawuropa na america eyaesebesebachihu silemitisetuachew silehone anikebelachewum. Enesu kelib ketemelesu Geta yikir yibelachew enji egna dirom bihon kihdet silelelebin metades ayashanim. Enante gin yihinin materamesachihun titachihu benefisachihu metades telewotu enji lezih alem bemimech yeluter filisifina atimutu. metades yemiyasfeligachihu enante nachihuna.

  ReplyDelete
 2. unlike religious reformation, administrative reformation of the church is what every body needs!!! but the tehadiso menafkan's hidden mission is to bring tehadiso on the religion part ( dogma ) which will never, never , never be accepted.

  ReplyDelete
 3. ጽሁፉ ጥሩ ቢሆንም ይህንን መታደስ የሚባል ነገር ሲሰሙ የሚያንገሸግሻቸውና ዛራቸው የሚያንዘፈዝፋቸው ሰዎች አሉ። ለምሳሌም «መታደስ» የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ቢሆንም ይህንን ቃል ማኅበረ ቅዱሳን አይወደውም። «የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ» ሮሜ 12፣2 ታዲያ ለምን ይሆን ማቅ ይህንን ቃል ሲሰማ ዛሩ የሚነሳው? ሰው በንስሃ አይታደስም? ሰው በእውቀት አይታደስም? አይለወጥም? እኔ ያልገባኝ ማኅበረ ቅዱሳንን የሚያስጠላው «ተሃድሶ» የሚባለውን ቃል ነው ወይስ «ምንም የሚታደስ ነገር የለም?» በማለት ይሆን? ራሱ እተዳደርበታለሁ የሚለው መተዳደሪያ ስንቴ ተሻሻለ? ያለእድሳትና የተሻሻለ ለውጥ ስህተት ሊታረም አይችልም። ሰዎች ሊሳሳቱና ሊያሳስቱ ይችላሉ። የሚታረሙት ግን በእውነት ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ እንጂ በእልክና በኃይል አይደለም። እነአርዮስ፣ መቅደንዮስ የተለዩት በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል ነው እንጂ በዘመቻ አይደለም። ማቅ ግን ይህንን አይቀበልም። ራሱ አውግዞ ይለያል። እነምርትነሽና በጋሻውን ተሃድሶ ብሎ ሲያወግዝ ታይቷል። ምናቸው ተሃድሶ እንደሆነ፣ እንዴት እንደሆኑ፣ ለምን እንደሆኑ፣ ተሃድሶ ምን እንደሆነ ምንም እውቀት የሌለው ማቅ ራሱ የተሃድሶ ከሳሽ፣ ገምጋሚና ፈራጅ ሆኖ ይገኛል። በማን ውሳኔ? የትና መቼ? መልስ የለውም። እናም የአባቶች እርቅ መልካም ቢሆንም የእርቅ ሁሉ ጠላት የሆነው ማቅ ስፍራውን ለይተን ከወዲሁ ልናበጅለት የግድ ነው። እኛ ግን «በአእምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ» ኤፌ 4፣23 የሚለውን ቃል እንቀበላለን።

  ReplyDelete
 4. ታድያስ ኢትዮፕያዊ ሰላም ለአንተ ይሁን
  አዋቂነትህንንና ለቤተክርስቲያን ተቆርቃሪነትህን የቃላት አጠቃቀምህ እንዳያጠላበት ምናለ ቤተክርስቲያንንና የቤተክርስቲያንን አገልጋዮች ብትልይ
  ለምሣሌ ቤተክርስቲያን ትታደሳለች ማለት ከባድና ልክም አይመስለኝም ምክንያቱም ቤከ ማለት በውስጣ ያለው እውነት እንጂ የእኔና የአንተ የአነጋገር ዘይቤ አይደለም
  ቤተክርስቲያን የተመሰረተችው በክርስቶሰ ደም ላይ ስለሆነ የሲኦል ደጆች አይችላትም ብሎአል መስራቻ ጌታ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ቤተክርስቲያን ማለት ባንተ አባባል ህንጻ ነው እንዴ? ሰው የሌለበት ህንጻ ቤተክርስቲያን አትባልም።
   «የእግዚአብሔር እርሻ ናችሁ፤ የእግዚአብሔር ሕንፃ ናችሁ፤ ከእርሱ ጋር አብረን የምንሠራ ነንና» 1ኛ ቆሮ 3፣9
   «በእርሱም ሕንጻ ሁሉ እየተጋጠመ በጌታ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንዲሆን ያድጋል፣በእርሱም እናንተ ደግሞ ለእግዚአብሔር መኖሪያ ለመሆን በመንፈስ አብራችሁ ትሠራላችሁ» ኤፌ 2፣21-22
   ስለዚህ የክርስቶስ መኖሪያዎች እኛ ነን። ህንጻ ቤተክርስቲያን እኛ ክርስቶሳውያን የምንጸልይበት የጸሎት ቤት ነው። እኛ ኃጢአት ስንሰራ የተቀደሰውን የክርስቶስ መቅደስ ስጋችንን አረከስነው ማለት ነው።
   ምክንያቱም ይላል ጳውሎስ «ወይስ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ» 1ኛ ቆሮ6፣19-20
   መታደስ ሲባል ይህ ኃጢአት የሚስማማው ስጋችን ክርስቶስን ወደመምሰልና ከኃጢአት ሲለይ የሚመጣው መለወጥ ነው። ራስህ የክርስቶስ መቅደስ የምትሆንበት አዲስ ማንነትና የምትማረው፣ የምታስተምረውም ሕይወትንና መለወጥን የሚሰጥ የአዲሱ ወንጌል ፍሬ ሲሆን ነው ሰው ታደሰ፣ተለወጠ በንስሀ ተቀደሰ የሚባለው። በክርስቶስ መቅደስ በሆነው ሰውነታችንንና በምንጸልይበት ህንጻ ቤተክርስቲያን መካከል የቃላት ጫወታችሁን አቁሙ!!
   እኛ መቃወም ያለብን ዶግማችንን እንድንለውጥ ግድ የሚሉንን በምስጢረ ሥጋዌ ላይ ስህተትና ኑፋቄ የሚያመጡብንን እንጂ ንስሃ ስለመግባት፣ መጽሀፍ ቅዱሳዊ የሆነውን የአባቶች ትምህርት ወደጎን ትተን ወደባህልና ልምድ የሚጎትተውን እንድናስተካክል የሚፈልገውን አይደለም።ለምሳሌ ስጋዬን ያልበላ ደሜን ያልጠጣ የዘላለም ህይወት የለውም ያለውን የጌታ ቃል ወደጎን ትቶ የዘርዓ ያዕቆብ መጽሀፍ ተአምር መስማቱ ብቻውን ስጋ ወደሙ ይሆንለታል የሚለው ቃል የክርስቶስን ሞትና ትንሳዔ ዋጋ ያሳጣል ይህ ይስተካከል ቢባል ምኑ ነው ክፋቱ? እንደ እግዚአብሔር ቃል የስህተት ትምህርቶችን ማደስ ስህተት የለውም!!!!

   Delete
 5. ወንድሜ ሆይ ቤክ ማለት ዶግማዋ ቀኖናዋ ቢሆንም ቀኖና የተሰራው ዶግማውን ለማብራራት ነው
  ስለአስተዳደር ስለአፈጻጸም ልንከራከር እንችላለን
  ነገር ግን ቤክ ትታደስ የሚለው ቃል ያልተጠና ጥሬና ግርድፍ ይመስለኛል

  ReplyDelete
 6. የዛሬ ሃያ ሥድስት ዓመት አካባቢ አንድ የስምንት ዓምት ህፃን ልጅ በወቅቱ አርባዎች ውስጥ በሆነ ብሩክ በሚባል ሰው መጫወቻው ተይዞበት እንዲለቅለት በዙ ጊዜ እቤቱ ተመላልሶ ያጣዋል። ሌላ ሰው እንዳይሰጠው ደግሞ ብሩክ ያስቀመጠው በግራ እጁ ስለ ሆነ ማንም ዕቃውን አግኝቶ ሊሰጠው አልቻለም። ብሩክም እኔ እራሴ መክሬው ዘክሬው እሰጠዋለሁ በማለቱ፣ የልጁ ወሳጆች ደግሞ የልጃቸውን ዕቃ መመለስ በተመለከተ መሪር ለቅሶ በብሩክ ሥውር መልካምነት ጆሮ ዳባ ብለው ገና ትቀምሳታለህ ዓይነት አባሱበት፡; በዚያው ሰሞን የጌታችን ጥምቀት ስለነበረ የልጁ ወላጆች ግቢ ውስጥ ቅርጫ ታርዶ ለመከፋፈል ከታደመው ሰው መሀል የልጆች አባት ትልቁ ብሩክም ነበርና ከህፃኑ ጋር ፊት ለፊት ይተያዩ ጀመር። ታዲያ “የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳም” ሆነና ልጁ በአጋጠመው ተጠቅሞ ድምፅ ማሰማት ጀመረ፤ እንዲህ ሲል፥ አንቱ የሚለውን አንተ ብሎ “የብሩክ ስም ይቀየር” አለ። ሁሉም ጸጥ እንዳሉ ሥጋውን እኩል በማከፋፈል ያሉት በሬ አራጅ ሰው ብቻ ቢላቸውን እየሳሉ “ማን ልትለው ፈለክ ደግሞ” ብለው በመቀጠል “ልጅ ነገሮች በግልጽ ይታዩታል” አሉና ለልጁ “በል አዲሱን የብሩክ ስም ንገረን ዳቦም አያስፈልግ ጥሩ ጊዜ ነው።” ብለው ደስ የሚል እና ቅርጫ አራጅ የሚለውን ደግሞ አዲስ ስም እንዲሰይምላቸው የፈለጉ ይመስል ድምፅ እንዳይረብሸው ቢላ መሳሉን ቆም አደረጉለት፡; ህፃኑም “ለሰው ልጅ ስም መውጣት ያለበት አድጎ ተግባሩ በሚሠራው ሥራ እየታየ መሆን ነበረበት።” ብሎ በመቀጠል “ለምሳሌ እኔ እንዳልኩት ቢሆን ኖሮ የጋሼ ብሩክ ስም ጋሼ እርኩስ ይሆን ነበር።” ሲል ግማሹን አስቆ ሌላውን ደግሞ አስደንግጦ ከሁዋላው ነብር እንደተከተለው ፍየል ተፈተለከ። ስለዚህም የማህበረ ቅዱሳን ሥራ እየዋለ ሲገለጽ ትክክለኛ ስሙን ማግኘት ይገባዋል። ማህበረ ቅዱሳን ማለት ፍቅርን የማይወድ የፍቅር ቂመኛ፣ ጳጳስን ከጳጳስ፣ ቤተክርስቲያንን ከቤተክርስቲያን፣ ቄስን ከቄስ፣ ምዕምናን ከምዕምናን፣ ወጣቱን ከወጣት፣ቤተሰብን ከዘመድ፣ ሚስትን ከባል፣ ልጆችን ከወላጅ እና ሕዝብን ከሀገር እያጋጨ የሚሳለቅ የበግ ለምድ ለባሽ የተዋጣለት እርኩስ የደህንነት ድርጅት ነው። ብጹዐን ጳጳሳት በፍጹም እንዲታረቁ እንደማይፈልግ ከአባሎቹ ፉከራ ታውቋል። የእባቡ (የማህበረ ቅዱሳን ድርጅት) ጂራቱ ተቆርጧል፤ ጭንቅላቱ ነው አራት ኪሎ እና ስድስት ኪሎ የመሸገው። ለእርሱም የሚመለከተው ክፍል ጸሎቱን በሱባዔ ጀምሮለታል እናም በቅርቡ በራሱ አንደበት ማንነቱን ይፋ ሲያደርግ ተብትቦ የያዛቸውን በጎች ይለቃቸዋል። በጎቹም ሞቶ እንደተነሳ ያህል ለዓምላካቸው ይቅርታን በንሰሀ ይጠይቃሉ፤ እባቡንም ጭንቅላቱን ይቀጠቅጣሉ፤ ያን ጊዜ አባቶች በፍቅር ተሸንፈው ይታረቃሉ፤ በጎቹም (የአደራ ልጆቻቸውም) በለመለመው መስክ ምግቡና መጠጡን እንደልባቸው ያገኛሉ፡; ጊዜውም የዐብይ ጾም ወቅት ሰለሆነ እኛም በጸሎት ተግተን እናግዛለን፡; ወሥብኃት ለእግዚአብሔር።

  ReplyDelete
 7. እናንተ ሰወች ንስሀ ግቡ !! ለምን ተዋህዶ ነን እያላችሁ ያላችሁን የንስሀ ዘመን እንዲሁ ታሳልፉታላችሁ ኦርቶዶክሳዊነት እኮ ኢትዮጵያዊነት ነው እንዲሁ በእርዳታ ዱቄት እና ዘይት ከፈረንጂ የወረስነው አይደለም ::
  እናንተ ተሰድሶ የሚባል ሀይማኖትን የማስካድና/የማስለውጥ ስራ ወይንም አባዜ ይዟችኌል እኛ ደግሞ ተሀድሶ የሚባለውን መንፈስ በድርሳነ ሚካኤል እናባርረዋለን:: ተሀድሶ ድርሳነ ሚካኤል ገና ስሙ ሲጠራ 40.000 ክንድ ይርቃል ሲደገምበት ደግሞ ይቃጠላል::እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተሀድሶ መዳህኒት ናት ስሟ በተጠራበት ቦታ መድረስ አትችሉምና ::እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የጌታችን እናት በመሆኗ ክብር ይገባታል። ከዚህ ውጭ ግን የእግዚአብሔርን ፈቃድ በምንወዳት በድንግል ማርያም ስም ማጣመም ተገቢ አይደለም።

  ”ወቅድመ ሥእላ ስግዱ ዘኢሰገደ ላቲ ይደምሰስ እምቅዋሙ ወኢይት አወቅ ዝክረ ስሙ” ትርጉም፥ “በሥእሏ ፊት ስገዱ ለሥእሏ ያልሰገደ ከቆመበት ቦታ ይጥፋ ስም አጠራሩም አይታወቅ” የዘውትር መቅድም ም 1 ቁ 35።
  ንስሀ ገብታችሁ ወደ እናት ቤተክርስቲያን ተመለሱ ማምታታቱ ይብቃ !!!!

  ReplyDelete
 8. I don't think the very headache for the Church is preaching the preachers or lack of Tahadso or simply Dogma and Qenona . The very serious and notorious challenge is when it comes to the question of honesty,morality, interest and courage to have a genuine and whole-hearted engagement from both of the parties/groups in conflict. And it is when the directly concerned parties/groups have the courage and willingness to get themselves out from the their respective small and undesirable world that it will be a very great opportunity to resolve the unncessary and ugly conflict . I do not think a kind of superficial engagement will result in a desirable ,healthy and sustainable outcome.

  Yes, it is well and good to see those religious leaders getting together and agree to disagree , and agree to meet again within the next five months. But I do not think seeing each other after two decades and ending their meeting with out any substantial start is something to be taken as a big deal leave alone a success. Although it may not sound good to call it a failure, it seems disappointing to hear the news heralding," It is great to see you,and see you next time!" Mind you folks, hundreds and millions of followers had experienced a very terrible situation for 17 years (1974-1991)and have gone through not only religious dilemma (the divided synods) but sadly enough very ugly religious and political mix for the last two decades . What really has gone terribly wrong and who has been at the very top of all this mess back home is an open secret . And that is the very head of the synod/the Church and close supporters of that head have done huge mess by using the religion/the Church as kind of soft weapon ( preaching with out practice) and politics ( the ruling elites ) as a hard weapon . I do not want to enumerate spesific crimes committed under the cover of religion as they have been crystal clear. I strongly believe that the people deserve a genuine and deep self-evaluation and self-reconcliation ,and subsequently heart-felt aopolgy fronm those top religious leaders and then get together and confess their wrong doings ,and make sincere reconcliation between the two parteis(synods) . Believe or not, if this is not the way to bring about true and realistic resolution and genuine reunion, things will fall apart again even if there may be "agreement."
  I am not merely speculating or optimistically predicting. I am just expressing my impression about the very disingenous start of the reconcliation process which is not able even to start the talks about talks.

  I strongly argue that the very intelligence of the people (followers)should not be undermined . To tell them that what happened in Arizona was a "great success " is nothing but a kind of insult to the intelligence of the people. They desrve to be told the truth and the challenges so that they can contribute to the scuccess of the effort and enjoy the good result they are greatly aspiring. Is it not very minimal attempt to those top religious leaders to see each other after two decades?? I do not think unnecessa mystification,especially to those leaders is a good thing.

  May God help us all in this effort!!

  ReplyDelete