Friday, February 3, 2012

በዘንድሮው በዓለ ጥምቅት ላይ “አንድ አድርገን” ድረገጽ አሳፋሪ የሀሰት ወሬ አናፈሰ፤ በደብረ ማርቆስ የጥምቀት በኣል ላይ ተስፋ ፈንጣቂና አስደሳች ነገር ተሰማ - - - Read PDF

አንድ አድርገን የተባለው የማኅበረ ቅዱሳን ክንፍ የሆነው ድረገጽ በዘንድሮው የጥምቀት በዓል ለጥምቀት በአል ታቦተ ህጉ ከመንበሩ አልንቀሳቀስ አለ” በሚል ርእስ ጥቅምት 14/2004 ዓ.ም ያወጣው ዜና ለውስጥ አዋቂ ቀሳውስት ቀልድ፣ ስለታቦት መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረውን እውነት በተረዱ ምእመናን ዘንድም አጠራጣሪና ፍጹም ሐሰት መሆኑን ከስፍራው የደረሰን ዜና አመለከተ። ከቀሳውስት ወገን የሆኑቱ በተለይ “የእኛው ታቦት እንዴት እንዲህ ያደርጋል?” በማለት “እንዘ ነአምሮ ለሊነ ከመ ሊቀ ጸረብት አቡሁ” የሚለውን ሌላ ገጠመኝ አስታውሰዉበታል፤ (ይቅርታ በቅርቡ በብፁዕ አቡነ አረጋዊ አንደበት በዚህ ዓለም ትምህርት ሊቃውንት መሆናችሁ የተነገረላችሁና በቤተክርስቲያን ትምህርት ግን የላችሁበትም የተባላችሁ፣ ቀደም ሲልም በዳንኤል ክብረት እጅ እንግሊዝኛ ተናጋሪ ቤተክህነት ለመሆን የሚዳዳችሁ ተብሎ የተጻፈላችሁ የማህበረ ቅዱሳን አባላት ሆይ! ይቅርታ፣ ምስጢር ስለሆነ ነው ያልተረጎምነው)፡፡
ብዙ ያልተሰሙና ከዚህ በፊትም ያልታዩ ነገሮች ተከስተዋል፤” በማለት ሐሰተኛ ዘገባ ያቀረበው “አንድ አድርገን”፣ በአዲስ አበባ በመገናኛ አካባቢ የሚገኘው የቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን የተፈጠረው ነገር የሚገርምም የሚደንቅም ነበር ብሏል፡፡ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ በዋናነት የቅዱስ እግዚአብሔር አብ ፅላት ሲኖር በድርብነት ደግሞ የማርያም፤ የገብርኤል፤ የገብረ መንፈስ ቅዱስና፤ የመድሀኔዓለም ታቦታት እንደሚገኙ የጠቀሰው ድረገጹ፤ ከዚህ በፊት  የገብርኤል እና የማርያም ታቦታት ጥር  10 ወጥተው ጥር 11 ወደ ማደርያቸው ሲመለሱ የእግዚአብሔር አብ ታቦት ግን ጥር 12 ወጥቶ ጥር 13 ወደ መንበሩ ይመለስ ነበር ብሏል፡፡ በዘንድሮው የጥምቀት በአል ላይ ግን ቀሳውስቱ ከበአሉ ከቀናት በፊት ተሰባስበው እስከ ዛሬ ድረስ የእመቤታችን እና የቅዱስ ገብርኤልን ታቦታት ነበር የምናወጣው ዘንድሮ ለምን የመድሀኔአለምን እና የገብረመንፈስ ቅዱስን ታቦታት ቀይረን አናወጣም ተባብለው በዚሁ መሰረት ጥር 10 ቀን 2004 ዓ.ም. ለማውጣት ሲሞክሩ፣ ታቦቶቹን ለመሸከም የተመረጡት ቀሳውስት ታቦቶቹን ከመንበሩ ላይ ማንሳት እንዳቃታቸውና፤ በተደጋጋሚ ቢሞክሩም እንዳልቻሉ አትቷል፡፡ የቀሳውስት ለውጥ ቢያደርጉም አልተሳካም ያለው አንድ አድርገን፣ በመጨረሻም “ከዚህ በፊት እንደሚደረገው የእመቤታችንን ፤ የቅዱስ ገብርኤልን እና የእግዚአብሔር አብን ታቦታት በማውጣት በአሉን አክብረዋል፡፡” ሲል ተአምር ተሰራ የሚል ሀሰተኛ ዘገባ ፖስት አድርጓል፡፡
ድረገጹ የተአምርን ምንነት የተረዳ አይመስልም ያሉት ስለወሬው ያነጋገርናቸው አንዳንድ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ እውን የተባለው ይህ ድርጊት አልተፈጸምም እንጂ ተፈጽሞ ቢሆን እንኳን ተአምር ለመባል የሚያበቃ ምን ቁም ነገር ይኖረው ይሆን? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ አክለውም የመድሀኔዓለምና የገብረመንፈስ ቅዱስ ታቦቶች “እኛ ከዚህ ቀደም ወጥተን ስለማናውቅ ዘንድሮ አንወጣም፤ እንዳይቀየሙንም እንደተለመደው የማርያምና የገብርኤል ታቦቶች ይውጡ” አሉ ለማለት ነው ወይስ? … ሲሉም በሥላቅ መልክ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ ይህን ለአስተዋይ አንባቢ መተዉ ሳይሻል አይቀርም፡፡ 
በተባለው ቤተክርስቲያን ከሚያገለግሉት መካከል ስለጉዳዩ አነጋግረን ባደረግነው ማጣራት “በእለቱ በስፍራው ቤተመቅደስ ውስጥ ነበርን” ያሉት ምንጮቻችን፣ ምንም የተከሰተ ነገር እንደሌለና ዘገባው ፍጹም ሐሰት መሆኑን፣ እነርሱም ወሬውን የሰሙት ድረገጽ ላይ ወጣ ተብሎ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ ወሬውን ያቀነባበሩትም በአጥቢያው የሚገኙ የማህበረ ቅዱሳን አባላት የሆኑ ግለሰቦች ከአንዳንድ ቀሳውስት ጋር በመመሳጠር እንደሆነ እነዚሁ ምንጮች አክለው ይናገራሉ፡፡ እንዲህ አይነት ወሬዎች ከዚህ ቀደምም በተለያዩ ደብሮች መናፈሳቸው አዲስ አለመሆኑ ሲታወቅ፣ አንዳንድ ካህናት ደብራቸው ትኩረት እንዲስብና አንዳች ነገር እንዲደረግላቸው ሲፈልጉ፣ ለሃይማኖቱ ቀናኢ የሆነውን ህዝብ ስሜት ለማግኘትም ሲሉ “ታቦቱ አልንቀሳቀስ አለ” ማለታቸው የተለመደ ዘዴያቸው መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የካህናት ወገኖች ይናገራሉ። ምናልባትም በተአምር ስም ህዝቡን ለማነሳሳትና ተገቢ ባልሆነ መንገድ ገንዘብ ለመሰብሰብ የተዘየደ መላ መሆኑ በተለይ ከቤተክርስያን አገልጋዮች የተሰወረ አይደለም፡፡ ህዝቡን በተገቢው መንገድ ማስተማርና መምራት ቢቻል ለቤተክርስቲያን ተገቢውን አስተዋጽኦ እንደሚያዋጣ የታወቀ ቢሆንም፣ ወንጌል ተሰብኮ ሕዝቡ የሚጠበቅበትን እንዲያደርግ በትክክለኛው መንገድ በእግዚአብሔር ቃል ከመምራት ይልቅ፣ በጨለማ ውስጥ እየተመላለሰና አድርግ የተባለውን ሳይጠይቅና ሳይመራመር በልማድ፣ በየዋህነትና በፈሪሀ እግዚአብሔር በማድረግ የእነርሱን ጥቅም ብቻ እየጠበቀ እንዲኖር ጽኑ ፍላጎት ያላቸው አስመስሏል፡፡
ይኸው ድረገጽ አክሎ እንዳስታወሰው የዛሬ ሶስት ዓመት ቃሊቲ የሚገኝው የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለበአለ ጥምቀት የማርያምና የሚካኤልን ታቦታት ወደ ጥምቀተ ባህር ቢወጡም የሚካኤል ታቦት ሲመለስ የማርያምን ታቦት የተሸከሙት ቄስ መንቀሳቀስ እንዳልቻሉና በብዙ  ፀሎትና ምህላም አልሆን ብሎ እዚያው ድንኳን ተጥሎ በአሁኑ ሰዓት የቁስቋም ቤተክርስቲያን እንደ ተሰራ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ታቦቱ አልንቀሳቀስ አለ የተባለውም ታቦቱ እንዲህ የሚያደርግ ሆኖ አይደለም፤ ቀሳውስቱ ህንጻ ለማሰራትና ስራውን ለማፋጠን ስለፈለጉ መሆኑን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ይናገራሉ፡፡ በእርግጥም ታቦቷ አልንቀሳቀስ አለች ባይሉ ኖሮ በአጭር ጊዜ ውስጥ ህንጻ ቤተክርስቲያኑን መገንባት ባልተቻለም ነበር፡፡
ይሁን እንጂ ከዚህ ቀደም በቀልድ መልክ ሲነገር የተሰማ አንድ ወሬ በዚህ መንገድ ሁል ጊዜ ማጭበርበር እንደማይቻል ይጠቁማል፡፡ ናዝሬት ውስጥ ነው ይባላል፡፡ ታቦቱ ለጥምቀት ወጥቶ ሳለ የባቡር ሀዲዱ ላይ ሲደርስ አልንቀሳቀስ አለ ተብሎ ተወራ፡፡ ከዚያ ምን ይደረግ ሲባል ታቦቱ ደም ለምዷልና በሬ ታርዶ ደም ረግጦ መግባት አለበት የሚል ምክር ከቀሳውስቱ በኩል ተሰጠ፡፡ ታቦቱ ደም ሲረግጥ እነርሱ ደግሞ ጮማ ለመቁረጥ የዘየዱት መላ ነበር፡፡ ነገር ግን ሁኔታው በእንዲህ እንዳለ ባቡር ጡሩንባውን እያሰማ ሲመጣ፣ አልንቀሳቀስ አለ የተባለውን ታቦት የተሸከመው ቄስ እግሬ አውጪኝ ብሎ ሀዲዱን ለቀቀና የዕለቱ ድራማ እዚሁ ላይ ተቋጨ ይባላል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በደብረ ማርቆስ ከተማ በዘንድሮው የጥምቀት በዓል ላይ አስደናቂ ነገሮች መሰማታቸውን ከስፍራው የደረሰን ዜና ያመለክታል፡፡ በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች ከሁለት ዓመት ወዲህ ያለ ቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድና ዕውቅና ሃይማኖተኛ ነን በሚሉ ወጣቶች ፍላጎትና ተነሳሽነት የተጀመረው ታቦት የሚያልፍበትን መንገድ መጥረግ፣ ቄጤማ መጎዝጎዝ ከዚያም ምንጣፍ ማንጠፍ ወደሌሎች ስፍራዎችም እየተዛመተ መጥቷል፡፡ ደብረ ማርቆስም ላይ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ከማህበረ ቅዱሳን ጋር ንክኪ ያላቸው አንዳንድ ነጋዴዎች ገንዘባቸውን በማፍሰስ ከአብማ ማርያም ባህረ ጥምቀቱ እስካለበት ዉሰታ ድረስ ስጋጃ እንዲነጠፍና የጉዝጓዝ ሳር በመኪና ተጭኖ እንዲጎዘጎዝ ያደረጉ ሲሆን፣ በበኣሉ ላይ የተገኙት የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የከተራ እለት ሊስተካከሉ በሚገባቸው ልምምዶችና የተሳሳቱ ትምህርቶች ላይ እርማት እንዲደረግ አባታዊ ሀላፊነት የተሞላበት ተገቢ ትምህርት ሰጥተዋል፡፡ ብፁዕነታቸው ትምህርቱን ከመጀመራቸው በፊት በበኣሉ ላይ እዚህም እዚያም ክብ ሰርተው የሚዘፍኑ ሰዎች ነበሩና “ዘፈኑን ካላቆሙ አላስተምርም፤ ይህ መንፈሳዊ በኣል ነው፤ ዘፋኝነት ሀጢአት ነው፤ ዘፋኞችም ወደእግዚአብሔር መንግሥት አይገቡም ተብሎ ተጽፏልና መቆም አለበት” ብለው መመሪያ ይሰጣሉ፤ አባቶቹን በሚያከብረው ሕዝብ ዘንድም መመሪያቸው ተቀባይነት አግኝቶ ዘፈኑ ከቆመ በኋላ ነው ትምህርቱን መስጠት የቀጠሉት፡፡
ብፁዕነታቸው አክለውም ዘንድሮ ከሌሎች ከተሞች እየተዛመተ የመጣውንና ደብረ ማርቆስ የገባውን በየመንገዱ ቄጤማ የመጎዝጎዝና ስጋጃ የማንጠፍ አዲስ ልማድ ላይ በሰጡት ትምህርት፣ “ይህን ስጋጃ የገዛችሁት ገንዘብ ያላችሁ ነጋዴዎች ትሆናላችሁ፤ በዚህ መንግስተ ሰማያት የምትገቡ መስሏችሁ ከሆነ ተሳስታችኋል፤ እናንተ ጽድቅ ፈልጋችኋል፤ ግን ይህ የያዛችሁት የሞኝ ጽድቅ ነው፤ በዚህ ምንግስተ ሰማያት አይወረስም፤ ከእናንተ ይልቅ እኔን ያሳዘኑኝ እኒህ ስጋጃ ሲጠቀልሉ ሲዘረጉ የዋሉት ወጣቶች ናቸው” ብለዋል፡፡ በዚህ ጊዜ ገንዘቡን ያፈሰሰውና ስጋጃውን የገዛው የማህበረ ቅዱሳን ሙሌት የሆነ አንዱ ነጋዴ ሲሸማቀቅ ታይቷል ብለዋል ምንጮቻችን፡፡
ከዚህም ሌላ በበዓሉ ላይ ወጣቶች በለበሷቸው ቲሸርቶች ላይ በብዛት የተጻፈውን ምንጭ አልባውንና “ያለ ወላዲተ አምላክ አማላጅነት ዓለም አይድንም” የሚለውን ጥቅስ በተመለከተም፣ “እንደዚህ የሚል ትምህርት ከየት የመጣ ነው? ያለ ክርስቶስ ልትድኑ ትፈልጋላችሁን? አትችሉም! ምክንያቱም አልተጻፈማ! መዳን እንዲህ ከሆነ የክርስቶስ ደም ከንቱ ሊቀር ነዋ” ሲሉ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስለሃይማኖት ምንም በማያውቁና ከእኛ በላይ ላሳር በሚሉ፣ በእልህና በግልብ ስሜት የሚነዱ ክፍሎች እያሠራጩት ያለውን የስህተት ትምህርት እንዲታረም በአደባባይ አባታዊ ትምህርት ሰጥተዋል፤ የሚያድነውን ወንጌልም ሰብከዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ አንድ አድርገን ድረገጽ በቅርቡ "ያለእመቤታችን አማላጅነት አለም አይድንም" - - - ይህ ለሚያምን እንጂ ለማያምን የሚነገር አይደለም!! በሚል ርእስ ኑፋቄውን ማሰራጨቱና ከጥቂት ጊዜ በኋላ ጽሑፉን ማውረዱ ታውቋል፡፡ በዚህ ኑፋቄ ላይ ለወደፊቱ ምላሽ እናዘጋጃለን፡፡
ብፁዕነታቸው እንዲህ በማድረጋቸው በሃይማኖት ትምህርት ጉዳይ ተመሪ ሊሆን የሚገባው ሕዝብ፣ አባቶች ዝም በማለታቸውና በአግባቡ ሊመሩት ባለመቻላቸው መሪ ልሁን እያለ ያለበትን አካሄድ መስመር ማስያዝ ነውና ሌሎቹም ብፁዓን አባቶች ከቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ውጪ ልዩ ልዩ የስህተት ትምህርቶችንና ልማዶችን ወደቤተክርስቲያን ያለከልካይ እያስገቡ ያሉትን ግለሰቦች፣ ተዉ ሊሏቸውና ስርአት ሊያሲዟቸው እንደሚገባ ይታመናል፡፡ ከእስካሁኑ ልምድ መገንዘብ እንደሚቻለው፣ ከሁለት ዓመት ወዲህ እየታየ ያለው መንገድ የመጥረግ፣ ሳር የመጎዝጎዝና ምንጣፍ የማንጠፍ ልማድ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ እንደ ዶግማ ሊወሰድ እንደሚችል ጥርጥር የለውም፡፡ ምክንያቱም በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ የሚታዩ አንዳንድ ልማዶችና ስርአቶች በቅዱስ ሲኖዶስ ተፈቅደውና ተወስነው ሳይሆን አሁን እያየነው እንዳለው ልማድና በህገ ወጥ መንገድ እየገቡ ተቀባይነት አግኝተዋል፡፡ መስተካከል አለባቸው የሚሉ ወገኖች ሲነሱም እነርሱን መንካት እንደኑፋቄ ትምህርት እየተቆጠረ ውግዘት ሲያስከትሉ ኖረዋል፡፡ የክርስትና ትምህርትና ስርአት በደጋፊዎች ብዛት የሚወሰን ሳይሆን በእግዚአብሔር ቃል የሚመራ በመሆኑ፣ ቤተክርስቲያን እንዲህ ያሉት ነገሮች ከመስመር ሳይወጡ በፊት የቀደሙትንም ሆነ አሁን ለመግባት እየታገሉ ያሉትን ልማዶች መስመር ማስያዝ እንደሚገባት የብዙዎች እምነት ነው፡፡         

44 comments:

 1. Abune Markos thank you very mach Lemastemarima yichilalu zeregnet- mastemar -zemed merdat--genzeb mesebseb tewdadar yelotm degimo wetsatochin lemin letabot anetsefachihu malet jemeru? yasazinal zegebaw tikikil new Aba selama Mahibere Kidusann lemasafer yetenesa tsenkara hayil new Deje Selam yesew neger siketatel -simezegib Aba Selama wongail yizo tenesa Deje Selam Ende Ekuy Filsitsa yesewn sira yiketatelal -yimezegbal ewnetun giletsut

  ReplyDelete
 2. YALEMBETACHEN AMALAGENET ALEM AYDINEM YEMILUW MINCHU YALTAWEKE TIKEKEL YALHONE TIMHIRT NEW ..TIWOLED HULU BISET YILUGNAL..YEMILU YIBELTAL.. EBAKACHU YELELOCH HAYMANOTOCH MESAKIYA ATADREGUN..KALE HIWOT YASEMALEN ABUNE MARKOS .

  ReplyDelete
 3. ሠይፈ ገብርኤልFebruary 3, 2012 at 10:45 AM

  ጎበዝ ባላችሁበት ጸበል የለም እንዴ ወይስ ቄሱ ጸበል መርጨት አቁመዋል ? ወይስ በስልጣኔአችሁ የጸበልን ኃይል ስለማታምኑ መሄድና መፈወስ አልፈለጋችሁም?
  ይህን ያልኩበት ምክንያት በአምላክ ትእዛዝ የተመሠረተውን ፣ የታቦትን መከበር የሚቃወም መንፈሰ ከአጋንንት ብቻ ስለሆነ ነው ፡፡ ኢየሱስንም ገና በሩቅ ሲያዩ የሚለፈልፉ አጋንንት ነበሩና ፡፡ የሰናፍጭ ቅንጣት ታህል እምነት ቢኖርህ የሚለው የጌታ ቃል ፣ የእምነትን ኃይልና ጉልበት ምን ያህል እንደሆነ አያስገነዝባችሁም? ታቦት ሲከበር ለምን የጣዖት ሠርግ ይሆንባችኋል? ህዝቡ ታቦቱን ሲያጅብ ፣ ለታቦቱ ክብር ሲሰጥ በመንፈሱ ፣ በሃሳቡ ሁሉ እግዚአብሔርን ማለትም ኢየሱስን እያመስገነ ነው ብላችሁ ለምን በቀና አታዩትም? የወጣቱስ ከጫትና አረቄ ቤት ወደ ሃይማኖት መመለስስ ቢሆን እንዴት አያስደስታችሁም ?

  ታቦቱን ተሸክሞ የሚሄደው ሰው ፣ ታቦቱና ልብሱም ሁሉ የሰው የእጅ ጥበብ ያረፈበት እንደሆነ ማን መረዳት ያቅተዋል? ለስውር ተልዕኮአችሁ በዘመኑ መጨረሻ የይሁዳን - “ቁጥር 4 ከብዙ ጊዜ በፊት ለፍርድ የተጻፉ አንዳንዶች ሰዎች ሾልከው ገብተዋልና” የሚለውን እንደ ትንቢት ለመፈጸም ካልሆነ በስተቀር የግድ አምልኩ ፣ እመኑ ሳትባሉ ለምን ቤተ መቅደስ ድረስ መግባት አስፈለጋችሁ ? የራሳችሁን እምነትና ማተብ በጥሱ ፣ ስለሌላው ለምን ትገደዳላችሁ ፡፡
  ሰው በመሠረተው ላይ እሰጥ አገባ ከምትገጥሙ ፣ እንደ እምነታችሁ የራሳችሁን መቅደስ መሥርቱና እንደ ብጤዎቻችሁ ኘሮቴስታንቶች ወንጌልን ላልሰማ አሰሙ ፡፡ ብዙ የምሕረት አደባባይ መፍጠር ትችላላችሁ ፣ ሊጠፉ የተዘጋጁ ነፍሳትንም ትታደጋላችሁ ፡፡ በርትቶ ለሠራ ተከታይ አይጠፋም ፤ ምክንያቱም የዓለም ህዝብ እየጨመረ እንጅ እየቀነሰ አይደለም የሚሄደው ፡፡ መለየትም ደግሞ ኃጢአት አይደለም ፤ 2 ተሰ 3 ፡ 6 “ወንድሞች ሆይ፥ ከእኛ እንደ ተቀበለው ወግ ሳይሆን ያለ ሥርዓት ከሚሄድ ወንድም ሁሉ ትለዩ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛችኋለን።” ወንድም የሚለው ቤተ ክርስቲያንም መሆን ስለሚችል ከናንተ እምነትና ሃሳብ ካልተስተካከለላችሁ ኃጢአትን ሳታደርጉ /ሳትከራከሩ/ እንደ እምነታችሁ ተለዩ ፡፡
  አዲስ መሠረት መመሥረትም የተፈቀደ ነው ፡፡ ጴጥሮስ ባስተማረበት አውድ ጳውሎስ አልቀጠለም ፤ ምክንያት ቢባል ጴጥሮስ የተመረጠው ለአይሁድ ፣ ጳውሎስ ደግሞ ለአሕዛብ ስለነበር ነው ፡፡

  ሮሜ 15 ፡ 2ዐ በሌላው ሰው መሠረት ላይ እንዳልሠራ የክርስቶስ ስም በተጠራበት ስፍራ ሳይሆን ወንጌልን ለመስበክ ተጣጣርሁ ይላልና፡፡ አንድ ጊዜ መሠረት የተሠራበትን ደግሞ እንዳናናጋው ሲያስተምር በ 1 ቆሮ 3 ፡ 10 – 12 የእግዚአብሔር ጸጋ እንደ ተሰጠኝ መጠን እንደ ብልሃተኛ የአናጺ አለቃ መሠረትን መሠረትሁ፥ ሌላውም በላዩ ያንጻል። እያንዳንዱ ግን በእርሱ ላይ እንዴት እንዲያንጽ ይጠንቀቅ። ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት አይችልምና፥ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ማንም ግን በዚህ መሠረት ላይ በወርቅ ቢሆን በብርም በከበረ ድንጋይም በእንጨትም በሣርም ወይም በአገዳ ቢያንጽ፥ የእያንዳንዱ ሥራ ይገለጣል፤

  እምነት በሞኝነት ነው እንጅ አንቀጽ በአንቀጽ ፣ ሐረግ በሐረግ አድርጐ በመፈላሰፍና በመጠበብ አይደለም ፡፡ 1 ቆሮ 3 ፡ 19 የዚህች ዓለም ጥበብ በእግዚአብሔር ፊት ሞኝነት ነውና። ህዝቡ በየዋኀነቱ ታቦቱን ቢያከብር ልብ የሚመረምረው አምላክ ለማነ እንደተሰገደ ያውቃልና ብዙ አትጨነቁ ፡፡ ራሳችሁንም የሌላ እምነት ተከታይ አስመስላችሁ ትዝብት ላይ አትውደቁ ፡፡ እግዚአብሔር በአፍ የለፈለፍነውን ብቻ ሳይሆን በልቦናችንም ያሰብነውን ሁሉ ስለሚረዳ አምልኮአችንን ሁሉ በጐደለ አስተካክሎ ፣ የህፃንን ቋንቋ እንደ መረዳት ያህል ጸሎታችንን ሁሉ ይቀበላል ፡፡

  በተረፈ በራሳችን ዕውቀትና ብልሃት ራሳችንን ከሌሎች በላይ ማድረጉን መጽሐፍ ይቃወመዋል ፤ 1 ቆሮ 4 ፡ 6 ወንድሞች ሆይ፥ ስለ አንዱ በአንዱ ላይ አንዳችሁም እንዳይታበዩ። በቁጥር 7 ሌላውን ለመናቅ አንተ እንድትበልጥ ማን አድርጎሃል?
  ማኀበረ ቅዱሳንን እንዋጋ ብላችሁ ፣ የህዝቡን እምነትና ሃይማኖት እያንቋሸሻችሁ እንዳላችሁ ይግባችሁ ፡፡ ህዝቡ ይህን ሁሉ ዘመን እንደ ደሴት በክርስትናው የቆየው በጽኑ እምነቱ በመቆሙ ስለሆነ እንደሚቀጥል አልጠራጠርም ፡፡

  በደቡብ ክልል የ….ን ቤት እየመረጠ የሚበላውስ የእሳት ምስጢር ትንግርት ወይስ አሉባልታ ይሆን? ምንም አላላችሁምሳ ፡፡

  ስጦታ ሁሉ ከሱ ልግስና የሆነው አምላክ ልቦና ይስጥልን

  ReplyDelete
  Replies
  1. አይ ሰይፈ ገብርኤል ደህና ሰው ትመስለኝ ነበር! የኢትዮጵያ ታቦቶች እኮ በእግዚአብሔር ፈቃድ የተሰሩ አይደሉም ከእግዚአብሔር ፈቃድ ውጪ አገልግሎት ላይ የዋሉ በየትኛውም የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ የሌሉ ናቸው፤ ስለዚህ በመጽሐፍ ቅዱስ ስለብሉይ ኪዳን ታቦት የተጻፈውን ለኢትዮጵያ ታቦት እየሰጠህ ራህን አታታልል፡፡ አሁን ባሉበት ሁኔታ ጣኦት ተብለው አልቀረቡም እንጂ እየሆነ ያለውን ካየን የኢትዮጵያ ታቦቶች ከጣኦት ተለይተው አይታዩም፡፡

   Delete
  2. Eyanesena Eyanberes Musen betegedaderut gize Yasaferachew Amlake Muse Bekal kidanu Tabot Lay Yemitigedader Anteneim Yasafereh Zend Yichilal gin Mihretu ena Cherinetu Yenisiha Gize Eyeseteh mehonun lib bel. Tabote Israel Ejina Egerun Korarta Yetalechiwun Yefilistemin "daagon"asibew.nege BeEgziabhere ena Bekidusanu Bekalkidanum Lay Bemiyashofu hulu lay Yemidersew Yezih Temesasay newuna. Egnas Yeminadergewun enawukalenina anafirim .Antenina Meselochihin gin Amlak Yegestitsachihu

   Delete
 4. እረ አሁንስ ጉዳችን በዛ!!!

  'ንጉሥ ተከለሃይማኖት ዛሬ ከመቃብራቸው ቢነሱ ደ/ማርቆስ ከተማን እንዳስቀመጧት ያገኟታል' እየተባለ ስለ ኋላ ቀርነቷ በሚነገርላት ከተማ ውስጥ እንዴት ያለ ለአገር ልማት የሚያስብ ተቆርቋሪ ነጋዴ ተገኝቶ ነው እንዲህ ትንሽ ዝናብ ሲጥል አላንቀሳቅስ የሚለውን የደ/ማርቆስን ቀይ አፈር በቀይ ምንጣፍ ያሸበረቀው??? እንዴት ደስ ይላል የጦር ፊታውራሪዎችን አገር የልማት ጅግና የሆነ ነጋዴ ሲደርሳላት!!

  ምናልባት ለአገር እድገት ያስባሉ የሚባሉት እኒህ የጎረቢት ክፍለ ሀገር ተወላጅ የሆኑት አቶ አ..ን የተለመደ እጃቸውን ዘርግተው ይሆን ወይስ እሳቸውም የማህበረ ቅዱሳን አባል ሆነው ይሆን? ምነው ለተወሰነ ሰዓት ታይቶ ለሚጠቀለል ምንጣፍ ይህን ያህል ወጪ ከሚያወጡ ለከተማዋ ልማት አውለውት ስሟን ቢያስቀይሩላት አይበጅም ነበርን?? እንዲያው የልማት ባለራእይ ከምድሪቱ ጠፍቶ ነው እንደዚህ የሕዝብ ሃብት ሲባክን ዝም የተባለው?? ምነው የተማሩ የተባሉት የማህበረ ቅዱሳን አባላት የእንግሊዘኛ ቋንቋ ችሎታ ብቻ ነው እንዴ ያላቸው? እንዲያው አንድ እንኳን ኢኮኖሚስት የላቸውም ማለት ነውን??

  ያችን ጌታ ተቀምጦባት የነበረችን ውርንጭላ አስበው ይሆን እንደዚህ ያደረጉት? እስከመቼ ድረስ ነው ጎበዝ ቤተ ክርስቲያንችን የሆነውችው ኦርቶዶክስ በአሮጌ ኪዳን የምታነክሰው? በደም ከሆነው አዲስ ኪዳን ጋርስ መቼ ይሆን ተዋውቃ ይህን የዋህ ሕዝቧን የወንጌል ክርስቲያን አድርጋ ከሞት መልአክ አምልጣ የምታስመልጠው???

  አንድ ጊዜ አንድ ጋዜጠኛ ወደ አገራችን መጣ ስለተባለው ታቦት (ያውም ተሰርቆ - አስቡ ሌባ አማኝ) መረጃ ፍለጋ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር የነበሩትን ቃለመጠይቅ ሲያደርግ:

  የታቦቱ ባለቤትና ባለታሪክ እናንተ ናችሁ:: ይህ ታቦት ደግሞ የሰሎሞን የዲቃላ ልጅ እየተባለ በአፈታሪክ የሚነገርለት ቀዳማዊ ምኒሊክ ሰርቆ ወደ ኢትዮጵያ አምጥቶት አክሱም ይገኛል:: አሳዩንና አይተነው እንመን ሲባል እነሽፍንፍን ቄሶቻችን ተልካሻ ምክናያት እየሰጡ እሺ አይሉም:: ይህን ጉዳይ እርስዎ እንዴት ያዩታል? ይላቸዋል:: የተጠየቁት አምባሳደር ግን ተገቢውን መልስ ከመስጠት ይልቅ ሳቃቸውን ቂ..ቂ.. ቂ.. ቂ... በማለት አስቀድመው ጋዜጠኛውን እራሱን እንዳስደነገጡትና አይደለም እንኳን ይህ የታሪካችን ቁንጮ የሆነው ታቦታችን ይቅርና የተበተነውና ፍጹም ከአሕዛብ ጋር የተቀላቀለው ወገናችንን ሳይቀር እንስመልሳለን::(ለምሳሌ ፈላሻዎች) ይህ የሚባለው እንኳ እውነት ቢሆን አገራችሁ ባለ እዳ ሆና ከመንግሥቴ ጋር ቅራኔ ውስጥ ትገባ ነበር እንጂ እንደዚህ ያለ የዲፕሎማሲ ግንኙነት አይኖረንም ነበር ማለቱን በአንድ መንፈሳዊ መጽሔት ላይ ማንበቤ ታቦቱን ስታነሱ ትዝ አለኝ:: በዚህ ታቦት እየተባለ ከምንደናገርበት ጉዳይስ መቼ ይሆን ነጻ የምንወጣው??

  እባካችሁ ወገኖቼ!!! 'በነጻነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻነት አወጣን' (ገላ 5:1) በማለት ቃሉ እያስተማረን ለምን በእስራት ውስጥ እንድንኖር እንገደዳለን??? ስለሆነም ስለ ታቦት ቃሉ የሚለንን ለማወቅና ለመሆን ከዚህ በታች ያሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች በመንፈስ ቅዱስ ሁነን እናጥናቸው ከሌሎች ጋርም በመሆን እንወያይባቸው ቃሉ ብቻ ስለሆነ ነጻ ሊያወጣኝ የሚችል ብቸኛ መንገድ::

  1) ታቦት ማለት ከግራር እንጨት የተሠራ የሁለቱ ጽላቶች ማስቀመጫ ሳጥን ማለት ነው::
  (ዘጽ 25:10; 35:31; 37:1; 25:16)
  2) የታቦቱ ስምም 'የእግዚአብሔር ታቦት'/'የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት'በሚል በእግዚአብሔር
  ስም የሚጠራ እንጂ በመላእክት ወይም በጻድቃን ስም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድም ቦታ
  ላይ አልተጠራም:: ደግሞም አንድ ታቦት ብቻ እንጂ አርባ አራት ወይም ሺ አልነበረም::
  (2 ሳሙ 6:2 ; 1ነገ 8:1 እና 6)
  3) በተጨማሪም እስቲ በዓለም ውስጥ ያሉትን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያናትን(ራሺያና ግሪክ)እና
  የእኛይቱ ተገኘችበት የተባለችውን 'ማርቆስ አባታችን እስክንድርያ እናታችን' በማለት
  የምታዜምላትን የእስክንድርያን ወይም የግብጽን ኮብቲክ ኦርቶዶክስ የእምነት ልምምድን እናጥና

  በማጠቃለያም የማርቆሱን ጉድ በቃሉ እውነት ላይ ተመስርተው ካለምንም ፍርሃት ያጋለጡትን ጳጳስ እግዚአብሔር ከአውሬውና ከአገልጋይ ተከታዮቹ እንዲሸፍናቸውና እንዲጠብቃቸው ሁላችንም እንጸልይ ደግሞም እንደነዚህ ያሉትን ቆራጥ የቃሉ አስተማሪዎችን ለቤተ ክርስቲያናችን ትንሳኤ መፍጠን ጌታ ያብዛልን:: አሜን:: አሜን:: አሜን::

  ለደበረ ማርቆስ ሕዝብ የምህረት አምላክ ይድረስለት!!!

  ለደበረ ማርቆስ ነጋዴዎችም ብቸኛው የጽድቅ መንገድ የሆነው ክርስቶስ ያብራለቸው!!!

  በደበረ ማርቆስ ለማኅበረ ቅዱሳን ጀሌዎች ደግሞ ማስተዋል ይብዛላቸው!!!

  እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያናችንን ይፈውስ!!!!!!!!!

  የሰላም አምላክ ይባርካችሁ

  ሰላም ሁኑልኝ

  እህታችሁ

  ሰላም ነኝ

  ReplyDelete
  Replies
  1. Menew geremeh? Yehuda 30 beru ledeha biset yeshalal belo neber eko liyachebereber yeneberu...u are doing z same

   Delete
 5. ሠይፈ ገብርኤልFebruary 4, 2012 at 1:31 PM

  ውድ አናስሞስ ሆይ ደህንነት የሚለው ቃል ከምን አንጻር እንደታየና እንደተደነቀረ አልገባኝም እንጅ ፣ ጤንነትን በተመለከተ ከሆነ ኃያል የሆነው አምላካችን ይመሰገን ምንም አላጓደለብኝም ፡፡ ስለደህንነቴ የሚጨነቀው በሰላም አሳድሮ ከተኛሁበት አድሶ በማለዳ የሚያነቃኝ ፈጣሪ ብቻ ነው ብዬ ስመካ ፣ ከዚህ ምድር ፍጡርም የሚያስብልኝ ማግኘቴ ራሱ እንደ ትልቅ ጸጋ አድርጌ ቆጥሬዋለሁና ከጥርጣሬ በእምነት እንቀራረብ ፡፡

  ከዚህ በተረፈ የኔ መልዕክት የሚያምታታ አልነበረም ፤ በታቦቱም ሆነ በሌላው መንገድ ኀብረተሰቡ የፈጣሪውን ስም እየጠራና እያመሰገነ ያለው የአብ ወልድ መንፈስ ቅዱስን /ሥላሴን/ ነው ፡፡ ከዚህም የተነሳ ምእመኑ ለታቦት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ በመጥፎ አትተርጉሙት ፤ የጣዖት ሠርግ ፣ የአዶ ከብሬና የቃልቻ ጭፈራ አይሁንባችሁ ነው ያልኩት ፡፡ ወጣቱም ቢሆን ከጫት መደብ ተነስቶና ከዘማዊነት ተመልሶ መንፈሳዊ አገልግሎት ለመስጠቱ መሞከሩ ፣ ከኤድስም ሰለባነት ተርፎ ለዚሀ ጸጋ መብቃቱ በፈጣሪ እርዳታ ስለሆነ ፣ አምላካችንን ማመስገን ይገባናል እንጅ መውቀስ ማለት ወደ ቀድሞ ሥፍራህ ተመለስ ማለት ነው ባይ ነኝ ፡፡

  ጳውሎስ እግዚአብሔርን እያወቁ እንደ እግዚአብሔርነቱ መጠን አላከበሩትም /ሮሜ 1 ፡ 21/ የሚለው ይህን ዓይነት አስተሳሰብ ያለውን ሁሉ መሰለኝ ፡፡ በናንተ ልኬት /ሚዛን/ ኢየሱስ ልክ እንደ ሰው የተመጠነ አዕምሮ ያለውና የማይገባው ፣ አንዳች ነገር በራሱ የማያውቅ የተደረገ መሰለኝ ፡፡ አናስሞስ ሆይ ኢየሱስ ለራሱ የሆነውን የአምልኮ ስግደትና ለጣዖት የተመደበውን መለየት አይችልም የምትል ይመስላል ፡፡ ነገር ግን እሱ ገና በማኀፀን ሳንጸነስ መድረሻችንን የሚያውቅ አምላክ ነው ፤ እንኳንስ በእኛ ዓይን የሚታየው ግዙፉ ነገር ሊሰወረው ይቅርና ፤ ኧረ እባካችሁ እንደ አይሁዳውያን አታዋርዱት ፡፡ አምላክ ሰው ሆነ ሲባል ፣ እንደ እኛ ትንሽ ጭንቅላት ያዘ ማለት አይደለም ፡፡ ድንጋይ ቢባልም የምንረግጠውን አለት ሆነ ማለት አይደለም ፡፡ ይህን ሁሉ ችግር የሚፈጥረው እሱን ያለመረዳትና ያለማወቅ ነውና ፣ እንዲገለጽላችሁ በመንፈስ ሁኑ ፡፡ በዓላማና ዕቅድ እሱን ክደንና ገፍተን ወደ ኃጢአት መንገድ እስካልገባን ድረስ ፣ የኛ አምላክ ብንሳሳት እንኳን አቃንቶ በይቅርታ ይቀበለናል እንጅ ፣ ነጥብ እየቆጠረ ፣ ስህተት እየደመረ ለመቅጣት አይታገለንም ፤ መሃሪ አምላክ የምንለውም አውቀን በድፍረት ፣ ሳናውቅ በስህተት የምንፈጽመውን ድክመት ሁሉ እየተረዳ በፈቃዱ ስለሚሰውረው ስለሆነ ስሙን እስከጠራን ድረስ ታቦት ተከተላችኋል ብሎ ልምጭ አያነሳም ፡፡

  እናንተ ልትፈርዱ የምትፈልጉት በሥጋዊ ዓይን እየመረመራችሁ ሥጋዊውን ነገርና ሥራ ነው ፤ እግዚአብሔር ደግሞ የሚያየው የተደበቀውንና የተሰወረውን ከልብ ያለውን እምነት ነው ፤ እኔም ደግሞ የቃኘሁት በመንፈሳዊ እይታ ሰማያዊውን ፍርድ ነው ፤ ማለትም ከታቦቱ ኋላ የሚጓዘውን ህዝብ አምልኮና እምነት ማየት መመዘን ፡፡ ስጋዊ አመለካከትና መንፈሳዊው በጣም ሰፊ ልዩነት አላቸው ፤ ትክክል ብለን የምንቀበለው ዓይናችንን ያስደሰተውንና የኛን የሰዎቹን ስሜት ያረካውን ፣ የኛ አእምሮ የተቀበለውን ብቻ እንጅ ፣ ራቅ አድርገን ለአምላክ ምን እያደረጉ ነው በማለት ሰፋ አድርገን አመዛዝነን አይደለም ፡፡
  ይቀጥላል

  ReplyDelete
 6. ሠይፈ ገብርኤልFebruary 4, 2012 at 1:38 PM

  የእስራኤል ታቦት የላችሁም ስለተባለው /ጳጳሱ እንኳን ያዩት አይመስለኝም/ አናስሞስም የናዝሬቱ ኢየሱስ የለውም እላለሁ ፡፡ ምክንያት ብባል የናዝሬቱ ኢየሱስ መከፋፈልንና መለያየትን ፣ ስድብን ፣ መከራከርን ፣ ጸብን ፣ መከፋፋትን ፣ ምቀኝነትን ፣ ተንኰልን …. አላስተማረምና ፤ እሱን ካልመሰልነው ያስተማረንንም ካልተቀበልነው በስተቀር በአፋችን ስሙን ብንጠራውም ከልባችን ስለሌለ የኃጢአትን ቋንቋና ሥራ ስንሠራ እንገኛለን ፡፡

  በእግዚአብሔር የፍርድ ወንበር ለመቀመጥና በሌሎች ለመፍረድ ፣ ሌሎችንም ለመውቀስና ለመኰነን በየትኛውም የብቃት መመዘኛ ማለፍ ስለማንችል ኃጢአተኛ ነንና ማረን ብለን ሁላችን እንጸልይ ፤ ለዛሬው መዝሙር 51 /፶፩ን/ በግዝት መልክ ሶስት ጊዜ እንድትደግም አዝዤሃለሁ ፤ እኔም የይቅርታ ጸሎትን እጸልያለሁ፡፡

  ለእህታችን ሰላም ደግሞ ይሆን የመሰለኝ አጫጭር መልስ
  - የግለሰብ ንብረት የህዝብ ሃብት ተብሎ ሊቆጩለት አይገባም ፤ ግለሰቡ የፈቀደውን ፣ ቢያስፈልግ ጨረቃም መሄድ ይችልበታል ፤ መሬት ያነጠፈው ስለተረፈው ነውና አትጨነቂ
  - በአሮጌ ኪዳን አነከሳችሁ የሚለው ቃል አይስማማንምና መነጽርሽን ቀይረሽ በትክክል እንደምንራመድ ለማየት ሞክሪ ፤ ምክንያቱም አዲስ ኪዳንም ይሰበካል ፤ ዛሬ አዲስ ክርስቲያን የሆነ ሰው ግራ ይገባው ይሆናል እንጅ
  - አምባሳደር የሚሆነው ሰው የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ተወካይ አይደለም ፤ የፖለቲከኞች እንጅ ፣ ስለዚህ እስላምም መሆን ይችላልና ስለሰጡት አስተያየት ቂቂቂ ቂቂ አትበይ
  - ሌሎች እህት ቤተ ክርስቲያናት ታቦት የሌላቸው ምንም ምክንያት ስለሌላቸው ነው ፡፡ በእጅ አንድ ነገር ሳይዙ እኮ መፎከር አይቻልም ፤ ያው እንደጠቀስሽው በሌብነትም ይሁን በሌለ የእግዚአብሔርን ነገር ኦሪጅናሉ ደርሶናል ፡፡ የሌላቸው ደግሞ በታሳቢነት እንደ ታሪክ እያነበነቡ ማለፍ ይገደዳው
  - የታቦት መብዛት ምክንያቱ እንደ መጽሐፍ ቅዱሱና ቤተክርስቲያኑ ቁጥር ሰበክያን እንደሚያስረዱን ለአገልግሎት እንዲያመች የተደረገ ነው ፡፡ አለበለዚያማ እንደ ህንደኬ የሞላለት ብቻ ኢየሩሳሌም መሄድ ሊገባው ነው ፡፡ እኛ በሁሉ ቦታ የሚገኘውን ፈጣሪ ባለንበት ሆነን እናመልከዋለን ፣ እንሰግድለታለን ፣ እናከብረዋለን
  ንዴትና ቁጣ አይግባችሁ ከዲያብሎስ ነውና
  ሰላም ይግጠመን

  ReplyDelete
 7. ሠይፈ ገብርኤልFebruary 4, 2012 at 3:45 PM

  የእስራኤል ታቦት የላችሁም ስለተባለው አናስሞስም የናዝሬቱ ኢየሱስ የለውም እላለሁ ፡፡ ምክንያት ብባል የናዝሬቱ ኢየሱስ መከፋፈልንና መለያየትን ፣ ስድብን ፣ መከራከርን ፣ ጸብን ፣ መከፋፋትን ፣ ምቀኝነትን ፣ ተንኰልን …. የኃጢአትን መንገድና ሥራ አላስተማረምና ፤ እሱን ካልመሰልነው ያስተማረንንም ካልተቀበልነው በስተቀር በአፋችን ስሙን ብንጠራውም ከልባችን ከሌለን የኃጢአትን ቋንቋና ሥራ ያሠራናል ፡፡

  በእግዚአብሔር የፍርድ ወንበር ለመቀመጥና በሌሎች ለመፍረድ ፣ ሌሎችንም ለመገሰጽ ፣ ለመውቀስና ለመኰነን በየትኛውም የብቃት መመዘኛ ማለፍ ስለማንችል ኃጢአተኛ ነንና ማረን ብለን ሁላችን በአንድነት እንደ ነነዌ ሰዎች እንጸልይ ፤ ለዛሬው መዝሙር 51 /፶፩ን/ በግዝት መልክ ሶስት ጊዜ እንድትደግም አዝዤሃለሁ ፤ እኔም ይቅርታ ታገኝ እንደሁ እጸልያለሁ፡፡

  ለእህታችን ሰላም ደግሞ ይሆን የመሰለኝ አጫጭር መልስ
  - የግለሰብ ንብረት የህዝብ ሃብት ተብሎ ሊቆጩለት አይገባም ፤ ግለሰቡ የፈቀደውን ፣ ቢያስፈልግ ጨረቃም ሄዶ በድቅድቁ መዝናናት ይችልበታል
  - በአሮጌ ኪዳን አነከሳችሁ የሚለው ቃል አይስማማንምና መነጽርሽን ቀይረሽ በትክክል እንደምንራመድ ለማየት ሞክሪ ፤ ምክንያቱም አዲስ ኪዳንም ይሰበካል ፤ ዛሬ አዲስ ክርስቲያን የሆነ ሰው ግራ ይገባው ይሆናል እንጅ
  - አምባሳደር የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ተወካይ አይደለም ፤ የፖለቲከኞች እንጅ ፣ ስለዚህ እስላምም መሆን ይችላልና ስለሰጡት አስተያየት ቂቂቂ ቂቂ አትበይ
  - ሌሎች እህት ቤተ ክርስቲያናት ታቦት የሌላቸው ምንም ምክንያት ስለሌላቸው ነው ፡፡ ሊጥ ለማቡካት ምክንያት የሚሆን ትንሽ እርሾ እንኳን ያስፈልጋል ፡፡ በእጅ አንድ ነገር ሳይዙ በስሜት ብቻ መፎከር አይቻልም ፤ ያው እንደጠቀስሽው በሌብነትም ይሁን በሌላ ብልሃት የእግዚአብሔርን ነገር ኦሪጅናሉ ደርሶናል ይባላል /ጳጳሱ እንኳን አላዩትም/ አገራችን ይህን በረከት ስላገኘች ፈጣሪን ማመስገን ይገባናል ፡፡
  - የታቦት መብዛት ምክንያቱ እንደ መጽሐፍ ቅዱሱና ቤተክርስቲያኑ ቁጥር መብዛት ሁሉ ለአገልግሎት እንዲያመች የተፈጸመ ነው ፡፡ አለበለዚያማ እንደ ህንደኬ የሞላለትና ጉልበት ያለው ብቻ ኢየሩሳሌም መሄድ ይገባው ነበር ፡፡ እኛ በሁሉ ቦታ የሚገኘውን ፈጣሪ ባለንበት ሆነን እናመልከዋለን ፣ እንሰግድለታለን ፣ እናከብረዋለን
  ንዴትና ቁጣ እንዳይገባችሁ እመክራለሁ ፣ ከዲያብሎስ ነውና
  ዓላማዬ ቀናውን ነገር እንድትረዱ ለማድረግ ነው እንጅ እንድትበሳጩ አይደለም

  ሰላም ያቆየን

  ReplyDelete
  Replies
  1. berta wondemi, metseheften atawekum tebelewalena negerachew

   Delete
  2. tebarek ሠይፈ ገብርኤል kebe atetahegn!

   Delete
  3. good job Seife,i believe God will let us know who these guys are and who they are with!

   Delete
  4. Lehodachew Adrew Yemilefelifutn Menafikan, Bemastemar Bicha Atimelisachewm!!! Betsom Betselot Chimir Enji!!!

   Delete
 8. Mahberu ayankelafam bemil reis sele mahbere kidusan (MaK) tegbar

  http://dejebirhan.blogspot.com/2012/02/blog-post_7212.html#more

  Konjo tichit biyewalehu. Haimanotachinene saynquashish; meimen saisedeb sile-testafe lememar temelketut

  ReplyDelete
 9. በሥጋ ወንድሜ(በሰውነትዎ ብቻ)ሰይፈ ገብርኤል!!!!

  የእሰጥ አገባ ሙግት ሳይሆን እውነቱን በመረጃ አበጥረን በማዎቅ ግብስብስ የሆነውን ገለባ ከላያችን ላይ አሸንቀንጥረን በመጣል መንገድ እውነትና ሕይወት እኔ ብቻ ነኝ ያለውንና ብቸኛ አዳኝ ጌታ ዓይናችን እንዲያተኩርና አምልጠን እንድናስመልጥ እንጂ በሙግት የመሸናነፍ ጉዳይ ሳያደርጉት ሁላችንም በተረት ላይ ሙጭጭ ከማለት ቆም ብለን ሕይወታችንን በቃሉ መነጸር በማየትና በመመዘን ላይ ብናተኩር ይሻላልና 'ወንድሜ' የባጥ የቁጡን አንበል:: የሚጽፉትን ደግሞ ብዙ አዋቂወች እንደሚያዩት አውቀው በጥንቃቄ ቢያደርጉት እንጂ እንዲያው አንድም ፍሬ እንደሌለባት ጌታ እንደ ጎበኛት ባዶ ዛፍ ትርጉም የለሽ ቃላትን ብቻ አይደርድሩ(ይህን ስል እውነትን በፍቅር ለመናገር እንጂ ሞራልዎን ለመንካት እንዳልሆነ ጌታ ያውቃል)

  መጽሐፍ ቅዱስ የማንበብ ፍቅር በእውነት ካለዎት እባክዎት ሁላችንም ነጻ በሚያወጣው በዚህ ሕያው ቃል ላይ ብቻ ጊዜ ያጥፋ:: እስቲ ለዛሬ እንደርስዎ በግዝት ባላምንም እርስዎ ካመኑበትና ከተገበሩት እገዝትዎታለሁ ራእይ 11:19 ላይ ያለውን ቃል አንብበው (እንደርስዎ ይድገሙ አላልኩም)ታቦቱ ማንና አሁን የት ስፍራ እንዳለ ባጭሩ መልስ በሚቀጥለው ይስጡኝ???????

  የውስጥ ዓይንዎ እንዲበራና የሆኑትን እንዲያስተውሉ በጌታ ፊት አቀርብዎታለሁን ይስማሙ::

  የዓለም ሳይሆን የጌታ ሰላም ይብዛልዎ:: አሜን ይበሉ ግዴልዎትም::

  አክባሪ እህትዎ

  ሰላም ነኝ

  ReplyDelete
  Replies
  1. wondemi bealem eyetefah yaleh ante neh...kodachew sineta wenet new beleh yesemah...yekedus metsehab teregum eyasabah...eweket yelachehum yalewen ...zengeteh...hawariyat siyadenu kulech belo yetetsafewn yekadek....yegeziyabeher yehonuten wedegon aderegeh...endit new medan wondemi? enaneten yetekebele enin yekebelal yemilewen kedeh..endit new medan...besemay yetayechewen meleket tereh endit new medan? hulun seleamlak metwe siyaketeh...yeteweten eyetekawemek endit new medan...just collection of tekawemo...ere rasehen mermer

   Delete
 10. ሠይፈ ገብርኤልFebruary 5, 2012 at 8:14 AM

  ለሰላም ከተሰጠው አስተያየት ለአእምሮየ ምቾት ስል ለመሰወር ታግየው የነበረ ሆኖም ስለማስተማሪያነቱ የተለቀቀ፡-
  • ዲቃላ የተባልኩት እኔ እራሴ ወይም ዘመዴ ቢሆን ኖሮ እንዲህ በማለትሽ ብቻ ፍርድ ቤት እገትርሽ /እከስ/ ነበረ ፡፡ ቃሉ ጸያፍ ነው በታሪካችንም እንዲህ አልተዘገበልንም ማለቴ ነው ፡፡ የምትጸርፊው ደግሞ የንጉሥ ሰለሞንን ልጅ ነው ፤ መጽሐፍ ደግሞ ንጉሥን ማክበር ብቻ ሳይሆን ተገዙለትም ብሎ ያዛል ፡፡ ሰርቆ የሚለው አገላለጽም አጉል ምስክር ያሰኛልና የማናውቀውን የመሰለኝ ታሪክ አንፍጠር ፡፡ ክብረ ነገሥት የተባለው መጽሐፍ በኢንተርኔት በግዕዝና አማርኛ ስለሚገኝ ለመመርመር የሚፈልግ ይመልከተው ፡፡ አይ ያ የተረት መጽሐፍ ነው አንቀበልም ለሚል ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ንግሥት አዜብ ገና ለመፍረድ እንደምትነሳ መሰከረላት እንጅ ሴሰኛነቷን አላስተማረም ፡፡
  • እነ ሽፍንፍን ቄሶች ማለትም ግርድፍ ቃል ወይም አማርኛ ሶስተኛ ቋንቋው የሆነ ሰው ፣ የሚናገረው መሆን አለበት እንጅ ፣ በሥርዓቱ በክርስቲያን ቤተሰብ ውስጥ ካደገ ግለሰብ እንዲህ ዘርጣጭና የድፍረት ቃል አይወጣም ፤ ካናደዱሽ ባለጥምጥም ፣ በጣም ካበሳጩሽ ደግሞ ጉሽ የጠጣ ደብተራ ብትያቸው ይገባናል ፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ጉሽ የጠጡ የጻፉትን መጽሐፍ የቤተ ክርስቲያን ዶግማና ቀኖና አድርጋችሁ ስለምትጠቀሙ እንዲህ መባሉን የምትወጅው አይመስለኝም ፡፡ ሆኖም ግን ትክክለኛው ቃል የቤተ ክርስቲያን አባቶች የሚለው ነው ፤ ይኸ ስም ስህተት ከፈጠሩ የሚያስፈርድባቸውና የሚቀጡበት ሞገሳቸው ስለሆነ አግባብነት አለው /ያዕ 3 ፡ 1/ ፡፡ አይ ማንንም አባት አትበሉ ብሎናልና ይህንን ስም ለማንም መስጠት አይገባንም ማለት ይቻላል ፡፡ ነገር ግን ከዚህ መመሪያ ውጭ እጅግ ብዙ ብዙ የታዘዝነው አለና ሌሎቹን ካጠናቀቅን በኋላ ለዚህኛውም በቀጠሮ መመለስ እንችላለን ፡፡ ሽፍንፍን የሚለው ቃል ትክክለኛ ትርጉም ክንብንብ ፣ በዘልማድ ደግሞ በጾም የሚበላ የፍስክ ምግብ እንደሆነ ነው የማውቀው ፡፡
  • ፍጹም ከአሕዛብ ጋር የተቀላቀለው ወገናችንን ሲል ማንን አሕዛብ ያለ መስሎሽ ደስ ብሎሸ ይሆን? የገዛ ወገኖችሽንና ዘሮችሽን ሁሉ መስደቡ እንደሆነ አልገባሽም? በአይሁድ ልማድ ሸለፈቱን ያልቆረጠውን ቅዳሚ ሰንበትን እግሩን ዘርግቶ የማያከብረውንና በሙሴ ህግ የማይገዛውን ሁሉ ነው አሕዛብ እያሉ የሚጠሩት ፡፡ እንደ እነሱ መሲህን መጠበቅ ፈልጎሽ ካልሆነ በስተቀር የነሱንስ አባባል አታድንቂው ፡፡ የጥንት ኢትዮጵያውያን ወንጌልን ከአንዳንዶቹም አይሁዳውያን ቀድመው በመቀበላቸው ምክንያት አሕዛብ የሚለው ስም እኛን አይመለከተንም ፡፡ ይህ ስም እንዳይሰጠን ስትታገል የኖረችውም ደግሞ ይህችው የጦር ሜዳ ያደረግናት ቤተ ክርስቲያናችን ናትና ረጋ ብለሽ ታሪኩን አጥኚው ፤ ያኮራሻል ፡፡
  • ታቦት እየተባለ ከምንደናገርበት ጉዳይስ መቼ ይሆን ነጻ የምንወጣው ለሚለው ማመንና አለማመን የግል ምርጫ ስለሆነ ፣ አለማመንና አለመቀበልን በመረጥሽ ቅጽበት ከታቦት እሥራት የተፈታሽ ነሽና ሳትፈሪ ወስኝ ፡፡ በይሉኝታ የምታመልኪ እየመሰለኝ ይኸኛው አባባል አሳስቦኛልና ፣ ከይስሙላ እምነትስ የቀረው ይሻላል የሚል ምክር እለግስሻለሁ ፡፡ መንፈሱ ከሆነ የጠፈረሽ ውድ ልጁ እንዳትጠፊ ስለፈለገ ብቻ ነው፡፡
  • ለምን በእሥራት ውስጥ እንድንኖር እንገደዳለን የሚለው አባባል ጥርጣሬን ፈጠረብኝ ፡፡ ምናልባት አሞሽ ከነበረና ቤተሰቦችሽ በግድ አሥረው ወደ ጸበል ወስደውሽ ከሆነ ፣ የህይወት ታሪክሽን ኋላ ላይ ስትነግሪን እንረዳዋለን ፡፡ ከዛ ውጭ ግን ከመንገድ እያነቀ ፣ እንደ በሬ እየጠለፈ ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚያስገባና በግድ የሚያሳምን ጐበዝ ወይም የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ አላውቅም ፡፡ ምናልባት ይኸ መጥፎ መንፈስ የማያሳየው ነገር የለምና መንፈስሽን በኢየሱስ ስም ብለሽ ፈትሽው ፤ ይህ ስም ይፈውሳል ፤ ይህ ስም ተአምራትን ያደርጋል ፡፡ በተረፈ ግን ከአፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ የማውቀው ሃይማኖት የግለሰብ ጉዳይና ምርጫ መሆኑን እንጅ በአዋጅ ወይም በግብረ ኃይል አስገድዶ የታመነበትን መንገድ አላውቅም ፡፡ የጐረቤቶቻችንን ታሪክ ለማውሳት ከሆነ የሞከርሽው ፣ ነፍጠኞች ሰለሆኑ ዝግ ብሎ ማማት ይቻል ይመስለኛል ፡፡
  ቸር ይግጠመን

  ReplyDelete
 11. ሠይፈ ገብርኤልFebruary 5, 2012 at 6:30 PM

  ለእህት ዓለም /እታለም/ ሰላም ጥሪሽን በመቀበል ፡-
  “ብዙ አዋቂወች እንደሚያዩት አውቀው በጥንቃቄ ቢያደርጉት” ያልሽኝ ትልቅ አባባል ነው ፡፡ ስለ እውነትነቱም ሳላፍር እመሰክራለሁ ፡፡ ሊቃውንቱና ምሁራኑ ግዴታቸውን ከመወጣት ሲቦዝኑ ፣ እኔ ራሴን በራሴ ወደ እውነት ጐዳና ለመምራት የምተጋው ፣ በንባብ ያገኘሁትን የብልጭታ ዕውቀት ይዤ ብቅ ማለቴ ለሃይማኖታችን ቀናዒ ከመሆን የተነሳ ነው እንጅ ነገረ መለኮትን በሚገባ ወይም ስነ ሃይማኖትን አጥንቼ ፣ ሊቅ ሆኘበታለሁ በማለት አይደለም ፡፡ ከማይናገር ጨዋ የሚሳደብ አዝማሪን እመርጣለሁ ፤ ቢያንሰ ስድብን ያስተምረኛልና ፡፡ እነሱ በዳቦ እየተጣሉ ሥራቸውን እስከ ዘነጉት ድረስ ብዙ ባላውቅም አስተያየቴን ከመጻፍ አላቆምም ፤ ምናልባት ከጠለፋ የሚድኑ ነፍሳት ይኖሩ ይሆናልና ፤ አባ ሰላማዎች በአስተያየት ስለማልስማማቸው ምክንያት ጽሁፌን ማውጣት እስካላቆሙ ድረስ መሞከሬን አልተውም ፡፡ የምጽፈውም ለሚረዱኝና ለሚገባቸው ነው እንጅ መቀበል ለሚከብዳቸውና ለሚቸገሩ ፣ ብዙ ለሚያውቁ አይደለም ፡፡

  በተረፈ ከራዕይ መጽሐፍ እንዳነብ በታዘዝኩት መሠረት አንብቤ ፣ በጌታ ደግሞ ሌላውን ምዕራፍ ሂድ ብሎ ስለሚያዘኝ በራሴ ትንሽ ጨምሬአለሁ ፡፡ ለምስክርነትም እንዲህ ይላል
  19 ፡ 11 - “በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ ፤ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ ፤ መብረቅና ድምጽም ፣ ነጐድጓድም ፣ የምድርም መናወጥ ፣ ታላቅም በረዶ ሆነ” ፡፡
  ይህ ኃይለ ቃል ታቦቱ ከየት እንደመጣ የሚያስረዳ አይመስለኝም ፤ ከመጽሐፍም ደግሞ ታቦቱ ተነጠቀ ወይም አረገ ወይም ተወሰደ የሚል ነገር አልተነበበልንም ፤ እነ ኤልያስ ከምድር እንደ ተነጠቁ ተምረን ሳለ ፤ ኋላ ላይ ግን ጌታ በመለኮቱ ሲገለጥ አብረው ታይተዋል /ማቴ 17 ፡ 1 – 3/ ፤ ምድራዊው ታቦትም ያን ክስተት ቢያጋጥመው ኑሮ እንድንቀበል ይጻፍልን ነበር ፡፡ አንድ በሃይማኖት አሿፊ ጓደኛ ዮሐንስ ከፍጥሞ ደሴት በራዕይ የተመለከተውና የጻፈው ስለ አክሱም ጽዮን ቤተ መቅደስ ታቦት ነው በማለት ይህንኑ ጥቅስ ነበር የጠቀሰና ስለ መጽሐፍ … የተጫወተኝ ፡፡ ያም የፌዝ ይመስላልና አልተቀበልኩትም ፡፡

  - ከዚሁ ምዕራፍ ከቁጥር 15 ጀምሮ ያለውን በጥሞናና በትዕግሥት ለመረዳት - የንጉሥነቱን አዋጅ በማብሰር ይጀምርና ስለ ምጽዓት ዘመን የሚተነትን ይመስላል እንጅ ታቦት ከምድረ ገጽ እንደተሸጋገረ አይገልጽም ፡፡ ይህንኑም የሚያሰረዳው ከቁጥር 19 በፊት በቁጥር 18 … “ስምህንም ለሚፈሩት ለታናናሾችና ለታላላቆችም ዋጋቸውን ትሰጥ ዘንድ ፤ ምድርንም የማያጠፉትን ታጠፋ ዘንድ ዘመን መጣ” ስለሚል ኢየሱስ በኃጥዓንና በጻድቃን መፍረድ ሲጀምር ፣ ምድራዊው ሥርዓት ስለማያስፈልግ ስለ ሰማያዊው ቤተ መቅደስ መናገሩ ይመስለኛል ፡፡ ፍርዱ የሚጀመረው ሙታን ሁሉ ከተነሱ እኛም በህይወት ያለነው ከደረስንበት ከተነጠቅንና ምድርም ባድማ ከሆነች በኋላ ስለሆነ ማለቴ ነው ፡፡
  - በምዕራፍ 21 ቁጥር 1 ደግሞ አዲስ ሰማይንና አዲስ ምድርን አየሁ ፤ ፊተኛው ሰማይና ፊተኛይቱ ምድር አልፈዋልና … በቁጥር 5- በዙፋን የተቀመጠው እነሆ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ …በቁጥር 22 ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክና በጉ መቅደስዋ ናቸውና መቅደስ በእርስዋ ዘንድ አላየሁም ስለሚል ፣ ታቦት በደረጃው ከሰማይም የሚሰወርበት ጊዜ ወደፊት እንደሚኖር ያስረዳል ፣ ያም ደግሞ ሁሉን የዳኝነት ሥራውን ካጠናቀቀ በኋላ ፣ አዲሷን ሰማይና ምድር ካዘጋጀ በኋላ ስለሚሆን ያን ለማየት ያብቃን ማለቱን እመርጣለሁ ፡፡

  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የታቦት ሥርዓትን ብታከብርም ፣ እንደ ጥንቱ የእንስሳ መስዋዕት አታደርግም ፡፡ ይህም ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ የተደገፈ እንጅ በዘፈቀደ የተደረገ አይደለም ፡፡ በሉቃ 1 ፡ 8 – 12 እንደሚገልጸው አይሁዳውያን ታቦቱ ቢጠፋባቸውም ሥርዓቱን በአዲሱ ዘመንም እንደቀጠሉ የሚያስረዳ ምስክርነት ነው ፡፡

  ይህ ኢየሱስ ሳይወለድ የነበረና የተፈጸመ በማለት እንዳንታለልና ፣ ከኢየሱስ ትምህርት በኋላ ተሽሯል እንዳንልም ፣ የመጀመሪያዎቹ ሐዋርያት ይህንኑ ሥርዓትና ደንብ ሳያፈርሱ ወይም ሳይቃወሙ በአግባቡ እንደ ህዝቡ እንደፈጸሙትና እንደ አይሁድ ልማድም ሁሉ በሥርዓቱ እንደተጓዙ ተገልጿል /ሥራ 3 ፡ 1/ ፡፡ በዚህ ሁሉ መሃል ሁላችንንም የሚያስማማ አንድ ሃቅ ብቻ አለ ፡፡ ይኸም የአገልግሎቱ ዓይነት ፊት ከነበረው መሻሻሉ ፣ ማለትም ዕለታዊ የነበረው በዘለዓለማዊው መተካቱ ነው ፤ ፊት በእንስሳዎች ደም የነበረው ካሳ ፣ በአዲሱ ዘመን ኢየሱስ ባፈሰሰውና እርቅን ለዘለዓለም በመሠረተበት ንፁህና ክቡር ደም መሆኑ ፤ እጅን በእንስሳ ግንባር ላይ በመጫን ሳይሆን በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን መሆኑ ነው ፡፡ የኢየሱስ ደም ዘለዓለማዊውን ድኀነት ስላስገኘ የእንስሳት መሰዋትና የደም መርጨት ሥርዓት ሁሉ በቤተክርስቲያናችን ተሽሯል ፡፡ በአሁኑ ሰዓት ስጋና ደሙን ለመፈተቻ ትጠቀምበታለች ፣ እንስሳትን ለመስዋዕትነት የሚያቀርብ ካለ እንደ ጭዳ ይቆጠርለት እንደሁ እንጅ እንደ ጥንቱ ለምህረትና ለይቅርታ አይባልም፡፡ መሻሻልና መሻር ግን የትርጉም ልዩነት እንዳላቸው መዘንጋት የለብንም ፡፡
  ሐዋርያው ጳውሎስም በ2 ቆሮ 6 ፡ 16 “የእግዚአብሔርን ታቦትንስ በጣዖት ቤት ውስጥ የሚያኖር ማን ነው” ማለቱ በእጃቸው በወቅቱ ባይኖራቸውም የታቦትን ቅዱስነትና ክብር መመስከሩ ፣ ከጣዖትም እንደሚለይ ማስተማሩ ነው ፡፡ ስለሆነም ታቦት በእጅጉ ከጣዖት ይለያልና በሥርዓቱ እናክብረው /እናምልከው አላልኩም/ ፡፡

  ጽሁፌ እንዳይኰረኰም በማለት የመጽኃፍ ቅዱስ ኃይለ ቃልን ስለያዘ ፣ ፍሬ የሌለው ገለባ እንዳይባል ጥንቃቄ ይደረግ ፤ እኔ የጨመርኩት ቢነቀፍ ምንም ችግር የለውም ፤ የአምላክን ቃል አብሮ እንዳይደፈጠጥ ከወዲሁ አስገነዝባለሁ ፡፡
  ስለኮረኮርሽኝ የተዘጋ መጽሐፌን አስገለጥሽኝ ፣ አመሰግናለሁ ፡፡
  በተረፈ ሰላምና ምህረት ለሁላችንም እንዲበዛልን ጸሎቴ ነው ፡፡

  ReplyDelete
 12. ለተከበሩ ሰይፈ ገብርኤል በመልካሙ የሰላምታ ባህላችን ጤና ይስጥልኝ እንደምን ሰነበቱ?

  'ተቆጡ ኃጢአትንም አታድርጉ በቁጣችሁ ላይ ጸሐይ አይግባ ለዲያብሎስም ፈንታ አትስጡት' (ኤፌ4:26-27) በሚለው የአምላካችን ሕያው ቃል የሚመሩ ከሆነ የአንድ አፍታ ቁጣዎ ምንም አይደለም:: ግን ችግር የሚሆንብዎት በይደር ከያዙት ነውና እባክዎት በእኔ ምክናያት ከጌታ ጋር እንዳይጣሉ? ከአሰቡብኝ ፍርድ ቤት የመገተር ምኞትዎ የባሰ የሚሆንብኝ ይህ ነውና ቂም እንዳይዙብኝ በትህትና እጠይቀዎታለሁ::

  ዛሬ ግን ለመጨረሻ ጊዜ ሁለት ጥያቄዎችን እንድጠይቅዎት ይፍቀዱልኝ:

  1) ታቦቱ ተሰርቆ እንደመጣ በግልጽ ይነገራል:: ታዲያ ይህ በራሱ 'አትስረቅ' የሚለው ከ10ቱ
  ትእዛዛት ውስጥ አንዱ ሕግ አልተሻረምን? ይህንን ሌብነት እርስዎና መሰሎችዎ ንስሃ ገብታችሁበት
  ከሆነ ይንገሩን? ደግሞስ የስርቆት ሃብት ያስመካልን? ይህ ለእኔና ለእውነተኛ ኢትዮጵያውያን
  ውርደት ነው:: ሌላው ምናልባት በጨርፍታም ቢሆን አንብበውት ከሆነ በ1ሳሙ5:1-12 ላይ
  ዳጎንና ፍልስጤማውያንን ብቻውን የሰባበረና ያስጭነቀ ታቦት እንደዚሁም በ2ሳሙ 6:6-7 ላይ ኦዛን
  እጁን ዘርግቶ ታቦቱን በመያዙ የቀሰፈ ታቦት ከዝሙት የተወለደ ሰው ከእስራኤል ምድር ኢትዮጵያ
  ድረስ ሲወስደው እንዴት ዝም አለው?? ያ ታቦት እኮ ብቻውን ዳጎንን ያሰገደና የሰባበረ ነበር::
  'ተማረከ' ሳይሆን በጠላት ላይ ጸጥ ብሎ ዘመተ አያሰኝም ነገረ ሥራው? እሽ በሌባ እጅ መጣ
  እንበልና እንመን:: ታዲያ በየጊዜው መከራ ወደሚፈራረቅባት ጎስቋላ አገራችን መጥቶ አንድም ነገር ሳይሰራ ለረጅም ዓመታት በአክሱም መቀመጡ ምን ይባላል? ቱሪስት በመሳብ የውጭ ምንዛሬ ችግራችንን እንዳይቀፍ አይታይ ነገር:: ወይ እንደ እውነተኛው የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት የምድሪቷን ጠላት የሆኑትን ርሃብ ጦርነት ክፋት ድሃነት ምቀኝነት ትእቢት ጥላቻ ዘረኝነት ሌብነት(ከቀ/ምኒልክ ጀምሮ)ነፍሰ ገዳይነት.. ስንቱ?...አላስወገደ??? ታዲያ እንዲህ ነን እያልን ከማውራት ሌላ ጥቅሙ ምንድነው?? እስቲ ሌሎች ካላችሁ በዚህ ታቦት ምክናያት ዋሾ ከመሆንና ዓለም መጽሐፍ እያጻፈች ካማሳቅ ያለፍ ነገር የተጠቀምነው ምንድነው? ምንድነው? ወዳጄ ሰይፈ ገብርኤል?????

  2)አዎ ምኒልክ የሰለሞን ልጅ መሆኑ አይካድም:: የተወለደው ግን በሕጋዊ ቅዱስ ጋብቻ ሳይሆን
  እናቱ የተባለችው ለጉብኝት በሄደችበት ዝሙት አድርጎባት ነው:: ይህ አይነቱስ ዝሙት በኦርቶዶክስ
  ይፈቅዳል ወይ? ሕንደኬ የተባለችው የኢትዮጵያ ንግሥት መናገሻ ከተማዋ አክሱም ለመሆኑ ምን ማስረጃ አለ? የመኖች የእኛ ናት ሱዳኖችም የእኛ ናት እንደሚሉ አልሰሙም እንዴ ወዳጄ?? የያኔዋ ኢትዮጵያ ያዛሬዋ ስለመሆኗ ምን ማስረጃ አለን?? እንደ እኔ እምነትና ፍላጎት ታሪካችን አንድ ቦታ ላይ ተበላሽቶብናል እላለሁ:: ስለዚህ ታሪክ መፈተሽና መጠናት ይኖርበታል እላለሁ:: አዎ በትክክለኛው ታሪካችን እኔም በሴትነቴ እጅግ እኮራለሁ ግን ሺ ውሸት የወገኔን ርሀብ ቢያባብስ እንጂ መፍትሄ አላመጣምና ወደ ትክክለኛው ታሪካችን እንመለስ???

  3) ታቦቱ ወደ ኢትዮጵያ በምኒልክ መጣ የተባለበት ጊዜና የእስራኤላውያን ቤተመቅደስ ከነሙሉ ንብረቱ
  የከለዳውያን ንጉስ ያቃጠለበትና መልካሙንም እቃ ሁሉ ያጠፋበትን (2ዜና 36:17-21)ጊዜ
  እንዴት አድርገው ሊያቀራርቡልኝ ይችላሉ??

  4)እንዲያሰላስሉትና እንዲያጠኑት በሚያምኑበት ግዝት አደራ ብዬ የላኩልዎትን ራእይ 11:19 አንብበው
  ተረድተውት ከሆነ እባክዎት: ሀ) ታቦቱ ማነው? (መቼም ሰይፈ ገብራኤል ነው አይሉኝም)
  ለ) ይህ ታቦት አሁን የሚገኝበት ሥፍራ የት ነው? ይህ እንኳን መልሱ
  እዚያው መጽሀፉ ላይ 'በሰማይ ባለው ቤተ መቅደስ' ስለሚል
  ሌላ መልስ አይኖሮትም:: ታዲያ ከዚህ አሁን በአብ ቀኝ በሰማይ
  ካለ ታቦት ሌላ ከየት አምጥታ/ፈብርካ ነው ኦርቶዶክስ የዚህ ሁሉ
  ጉድ ተሻካሚዎች አድርጋ ቀና ብለን እንዳንሄድ ያጎበጠችን??

  እባክዎት! እባክዎት! እባክዎት! መጠሪያ አድርገው በሚጠቀሙበት (እውነተኛው ብስራተ ገብራኤል ባይሆንም)በአስመሳዩ የቁልቢው ገብራኤል ይዤዎታለሁ ከቻሉ መረጃ(በዋናነት መጽሐፍ ቅዱስን)ጠቅሰው ካልቻሉ ደግሞ የሚችሉትን ጠይቀው ተገቢ መልስ ይስጡኝና እኔን ነፍጠኛዋን (ኢሕአዴግን መሰሉኝ እኔን ሴቷን ነፍጠኛ ሲሉኝ)ከእንደዚህ ያለ ዘላባጅ አፈ ታሪክ ያሳርፉኝ:: ለነገሩ ያላረፈ እንዴት ሊያሳርፍ ይችላል????? የሚሻለው ግን እርስዎም እኔም ሁላችንም በሚያሳርፈው የምድርና የሰማይ ጌታ ኢየሱስ ላይ ተዘልልን ማረፉ ነውና ያስቡበት::

  ከ 'ገብርኤል ሰይፍ' የበለጠ እጅግ የሚሻለውና ሁለት አፍ ካለው ሰይፍ ይልቅ የተሳለውን እውነተኛና ፈዋሽ ሰይፍ (እብራውያን 4:12) እንደ ነፍጠኞች ጀንበርና ዝናር ሸንከፍ ሳይሆን ጠበቅ አድርገው ቢታጠቁት እንኳን ስድብና ጥላቻ ይቅርና የነዚህ ምንጭ/አባት የሆነው ዲያብሎስ ሳይቀር ባጠገብዎ ድርሽ አይልምና ይበርቱና እለት እለት ይታጠቁት:: ወንድ አይደሉም እንዴ? ያውም ቆፍጣና ኢትዮጵያዊ!

  እኔ ሴቷ እንኳ አንዳንዴ ጀግና ሲጠፋ (የወንጌል ጀግና ማለቴ ነው::የወንጀል አላልኩም) እንደ እብድ ያደርገኛል (እንደ ሐዋርያው ጳውሎስ ማለቴ ነው) ቅንፍ ያበዛሁት የለመዱትን አንድምታ ተጠቅመው ወደ ልዩ ትርጉም እንዳይገቡና አበሳ እንዳያበዙ ብዬ ነውና ይቅርታ::

  የሚያስተምረው የቸሩ ጌታ መንፈስ ይብዛልዎት!!

  ኦሮቶዶክስ ቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ካለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጥበበኞች ነን የሚሉትን ደንቆሮዎች (ሮሜ 1:22)(እኔ አይደለሁም ቃሉ ነው ያላቸው)እግዚአብሔር በብርሃኑ ይድረስላቸው!!!

  ሰላም ይሁኑልኝ

  አክባሪ እህትዎ

  ሰላም ነኝ

  ReplyDelete
 13. አባ ሰላማዎች፡- ጽሑፋችሁን አነበብኩት፡፡ በዚህም ጽሁፍ ላይ የተሰነዘሩትን አስተያየቶች አነበብካEቸው፡፡ አንድ ጥያቄ ለማቅረብ ፈለኩኝ፡፡ በአዲስ ኪዳን የታቦቱ ጥቅም ምንድነው; የቡሉይ ኪዳን መታሰቢያ እንዲሆን ነው; ወይስ አሁንም የእግዚአብሔር ማደሪያው ነው; ታቦቱን ይዘን የምናመልከው እግዚአብሔርን ነው፡፡ እግዚአብሔር ልባችንን ይመረምራል ተብላEል፡፡ በተመሳሳይም የዘመን መለወጫ ጊዜ ቢሾፍቱ ሃይቅ ላይ የሚደረገው የአምልኮ ስርዓትም በዓድ አምልኮ ነው ተብሎ ሲነገር የበዓሉ አክባሪዎች አይ እኛ የምናመልከው እግዚአብሔርን ነው እዚህ ቦታ የመጣነውም በፍጥረት ውስጥ ፈጣሪን ለማምለክ ነው ተብሎ አንብቤያለሁ፡፡ እዚህ ላይ አንድ ጥያቄ ሳላነሳ አላልፍም፡፡ እግዚአብሔር የሚመለከው እኛ በምንፈልገው መንገድ ነው ወይስ እሱ ባዘዘን መንገድ; በብሉይ ዘመን እንዴት ማምለክ እንዳለባቸው እግዚአብሔር ገልጾቸዋል፡፡ በአዲስ ኪዳን እንዴት ነው እግዚአብሔርን ማምለክ ያለብን; መጽሐፍ ቅዱስን መሰረት አድርጎ መልስ የሚሰጠኝን እፈልጋለሁ፡፡ አመሰግናለሁ፡፡

  ReplyDelete
 14. ሰይፍ ገብርኤል እንደዚህ የእግዚአብሔርን ቃል መሰረት አድርገን የምንነጋገር ከሆነ ውይይቱ ጠቃሚ ይሆናልና ያሁኑ አጻጻፍዎ ቃሉ በተጻፈበት መንፈስ መረዳትና ማስረዳት ቢታከልበት እጅግ እጅግ ይሻላል::

  እስቲ እርስዎ ወደ ጠቀሱት ወደ 2ኛ ቆሮ 6:16 አንዴ ልውሰድዎት ይፍቀዱልኝ? ጥቅሱ የተወሰደው ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተብሎ ከታተመው ከ81ዱ(ባሁኑ ጊዜ ግን ቁጥሩ 85 ከደረሰውና ዳንኤል በጉድጓድ ውስጥ ለ7 ቀናት ቆየ የሚለውን ተረፈ ዳንኤል 13:30 እና በትንቢተ ዳንኤል 6:19 ላይ በነጋውም ንጉሡ... የሚሉ ሁለት ተቃራኒ ሃሳቦችን የያዘና እግዚአብሔር ይዋሽ ዘንድ ሰው አይድለም በማለት ቃሉ የሚያረጋግጥልንን አምላክ ዋሾ ያደረገ መጽሐፍ ከዓለም በብቸኝነት የምትጠቀምና ለራሷ ብቻ መጽሐፍ ቅዱስ ብላ ያሳተመች ብቸኛ ቤ/ክ)መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ነው:: እሺ ይህንኑ የጠቀሱትን ጥቅስ ወስደን ስናዬው ደግሞ እዚያው ላይ 'እኛ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነን' የሚለውን እውነት ከተቀበሉ (እኔ ስለምቀበል አይስጉ)እርስዎ በጌታ በኢየሱስ ደም ታጥበው ከነጹ ቤተ መቅደስ ነዎት ማለት ነው:: ታዲያ በእርስዎ (እንደቃሉ በሚኖሩ ቅዱሳን ሁሉ)ውስጥ የሚኖረው ታቦት ማነው? መቼም በሁለቱ መሎጊያዎች 4 ሰዎች ይሸከሙት የነበረው ከግራር እንጨት የተሠራ የእግዚአብሔር ታቦት (ዛሬ የእኛ አጭበርባሪዎች በአንድ ሰው አሸክመው እንደሚያስጨፍሩንና ሥጋ ሲያምራቸው በሬ ካላረዳችሁልኝ ታቦቱ አልንቀሳቀስም አለ እንደሚሉት)ነው እንደማይሉኝ አምናለሁ:: በሰው ውስጥ ጌታ ብቻ በመንፈሱ የሚኖር ካልሆነ እንዴት ሆኖ ይህን ያህል የእንጨት ሳጥን በሰው ውስጥ ይኖራል? 1ቆሮ 3:16 እና 17ን ሮሜ 8:9-10ን ያንብቡ እስቲ?
  በተጨማሪም እግዚአብሔር ለሙሴ እንዲታዘዙትና እንዲኖሩበት የሰጠው ዋናው ነገር 10ቱ ትእዛዛት (ቃሉ)እንጂ ታቦቱ(ሳጥኑ)አለመሆኑን ብናስተውል እንጠቀማለን እንጂ አንጎዳምና እስቲ ኤር 31:33ን 2ቆሮ 3:3ን ያንብቡና የአዲስ ኪዳን ዘመንን ጽላትና ታቦት በጥንቃቄ ተረድተው የሰላምና የፍቅር ሕይወት እንዲኖሩና የመንግሥተ ሰማይ ዋና ወራሽ እንዲሆኑ ግብዝነት በሌለው በክርስቶስ ፍቅር እጠይቀዎታለሁ:: በመንግሥተ ሰማይ ኦርቶዶክስን ወይም ካቶሊክን ወይም ፕሮቴስታንትን ወይም ኢትዮጵያን ወይም እስራኤል ዘሥጋን ፈጽመው እንደማያገኙ ይወቁ:: በእምነታቸው እንደቃሉ የጸኑትን እንደ እነጳውሎስን የጌታን እናት ማርያምን ሐዋርያትን እነኢትዮጵያዊው እስጢፋኖስን ያገኟቸው ይሆናል:: ምናልባት ጌታ በመንፈሱ ከረዳን እኔና እስዎም እንገናኝ ይሆናል:: በእውነት ያድርግልን:: አሜን:: ግዴለዎትም እርስዎም አሜን ይበሉ:: ማን ያቃል ድንገት መንፈሱ ቢወርድብዎትና አሮጌውን ማንነትዎን/አዳማዊነት አስወልቆ አዲሱን ልብስ ክርስቶስን ቢያከናንብዎና ከሞተ/ከኩነኔ አገልግሎት(2ቆሮ3:9 ወይም ከ7-18) ሊያላቅቅዎት ጌታዬ ይቻለዋልና ቃሉን ይራቡ መንፈሱንም ይጠሙ::

  አጻጻፍዎ ትንሽ ትንሽ እየተስማማኝ (ቃል በመጥቀስዎ)መጥቷልና ይቀጥሉበትና እንማማር?

  በዚች ቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ሆኖ በመንፈሱም በሥጋውም የተጎሳቆለውን ወገናችንን እግዚአብሔር በምህረቱ ይድረስለት:: አሜን::

  ሰላም ሁኑልኝ

  አክባሪ እህትዎ

  ሰላም ነኝ

  ReplyDelete
 15. ሠይፈ ገብርኤልFebruary 6, 2012 at 1:04 PM

  እታለም ሰላም እኔ አልተቆጣሁም ፤ ነገር ግን የጽሁፌ መንፈስ የቁጣ ከመሰለ የኔ ሃሳብና ምኞት ስላልሆነ ይቅርታ ፡፡ ቀልድ ማጫወት አላውቅበት ብዬ እንጅ ፈገግ እንድትሉ ያቅሜን ሞክሬ ነበር ፡፡ በተረፈ ወደ ተረት ተረት ጨዋታ ገባህ ካላላችሁኝ የታሪክ መረጃ ለመስጠት ያህል የጠየቅሻቸውን ጥያቄዎች ከሞላ ጐደል ለመመለስ እሞክራለሁ ፡፡

  1. ስለታቦቱ መሰረቅ ታሪክ በአጭሩ ፡
  አንድ ምሳሌ ላስቀድም፡- አንቺ መርካቶ ዕቃ ለመግዛት ወጥተሽ ሳለ ፣ አንድ ሞጭላፋ የሰረቀውን ወርቅ ከቦርሳሽ ቢከተውና ፣ ከነማስረጃው ተይዘሽ ፍርድ ቤት ብትቀርቢ አዎ ሌባ ነኝ ቅጣት ይገባኛል ነው ወይስ አይ አልሰረቅሁም ብለሽ ነጻ መሆንሽን ለማስረዳት ትከራከሪያለሽ ?
  ከዚሁ ጋር በተመሳሰለ መልኩ ንጉሥ ዳዊት ወይም ምኒልክ /የንጉስ ሰሎሞንና የንግስት አዜብ ልጅ/ አባቱን ጐብኝቶ ወደ ሃገሩ ለመመለስ ሲነሳ የእስራኤል መኳንንት በኩር ልጆች አብረው አጅበውት እንዲሄዱ ተወስኖ ነበረ ፡፡ እነዚህ ሰዎች ደግሞ በታቦተ ፅዮን ትምህርት ያደጉና በረከቷንም የቀመሱ ስለነበሩ መለየት የማይሆንላቸው መሆኑን ስለተረዱ ንጉሥ ዳዊት ባልመከረበትና ባላወቀበት ሰርቀው ሄዱ ፤ ግማሽ መንገድም ከተጓዙ በኋላ ጋዛ ከሚገኘው የንግስቷ ርስት ሲደርሱ አስታወቁት ፡፡ እንዲቀበላቸው ለማሳመን ከተናገሩት ቅንጫቢ ተመልከቺ -

  “ፀሃይ ከሰማይ ወረደች ፡፡ በሲናም ለእስራኤል ተሰጠች ፡፡ ከሙሴ እስከ እሴይ ዘር ድረስ ለአዳም ዘር ሁሉ መድሃኒት ሆነች ፡፡ እነሆ በእግዚአብሄር ፈቃድ በአንተ ዘንድ ናት ፡፡ ይህም በእግዚአብሄር ፈቃድ እንጂ ከእኛ የተደረገ አይደለም ፡፡ እኛ ፈቀድን ፡፡ እግዚአብሄር ፈጸመ ፡፡ እኛ ተስማማን እግዚአብሄር አሳመረልን ፡፡ እኛ ተናገርን ፡፡ እግዚአብሄር ሰራ ፡፡ እኛ አሰብን ፡፡ እግዚአብሄር መከረ ፡፡ እኛ አልን ፡፡ እግዚአብሄር ወደደ ፡፡ እኛ አመለከትነ ፡፡ እግዚአብሄር አቀናው ፡፡ እኛ አሰብን እግዚአብሄር ግን እውነት አደረገው ፡፡ እነሆ ዛሬም እግዚአብሄር አንተን መረጠ ፡፡ አገርህንም ወደደ ፡፡ ይሄውም ለእግዚአብሄር ታቦተ ሕግ ለቅድስቲቱና ለሰማያዊቷ ፅዮን አገልጋይ ትሆን ዘንድ ነው ፡፡”

  ይህ ሰው ደግሞ ገና ሃይማኖቱን በሥርዓቱ ከአይሁዳውያን ተምሮ ፣ በተግባርም ሁሉን በማየቱ ከልብ ተለውጦ መመለሱ ነው ፡፡ እግዚአብሔር አንተን መረጠ ፣ ለአንተ ፈቀደ ስለዚህም ያሰብነውን ያለእንቅፋት ፈጸመ ሲሉት ፣ ስለጻድቃን ይሁንባችሁና ከእግዚአብሔር ጋር መታገል ይገባው ይሆን ? እኔ መልስ የለኝም ፡፡ በተረፈ የታቦቱ መምጣት የፀሃይን አምልኮ ፣ የዛፍና የድንጋይን አምልኮ አስቀርቶልናልና በናንተ ሃሌ ሉያ በእኛ ደግሞ ስብሐት ለአብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ እንበል ፡፡

  2. ስለ እናቱ ዘማዊነት ባህርይ የተባለውን በአጭሩ
  አሁንም እንዲገባን እንደ ጌታዬ አንድ ሌላ ምሳሌ፡- አንቺ አንድ መናፈሻ ጫካ ለመዝናናትና ተፈጥሮን ለመቃኘት ሄደሻል እንበል ፡፡ ከዛም አንድ ወጠምሻ ጐረምሳ በተክለ ሰውነትሽ ተማርኮ ፣ በሰይጣን ተገፋፍቶ ቢደፍርሽና ፍሬ ብታገኝ በዘማዊነት ተሰማርቼ ይህን ልጅ ወለድኩ ብለሽ ንስሐ ትገቢያለሽ ወይስ ያለፍላጐቴ ተደፍሬ ጸነስኩ በማለት ራስሽን ከህሊና ፍርድ ለመታደግ ትከራከሪያለሽ ? አትፍረድ ፣ ይፈረድበሃልና ፤
  ንግሥት አዜብ በስጋዋ ድንግል ፣ የጥበብ ፍቅር እጅግ የሚያሸንፋት ፣ የፀሐይ አምልኮ ያላት ሴት ነበረች ፡፡ የሰሎሞንን ጥበብ በነጋዴዋ ታምሪን ምክንያት ስለሰማች ፤ እግዚአብሔር የሚባልም የዚህ የሚታየውንና የማይታየውን የፈጠረ አምላክ መኖሩንና እንደሚያመልኩም ስለተነገራት ፣ ለማወቅና ለማረጋገጥ ፣ የሰሎሞንን ጥበብንም ለማየት በመጓጓት ተጓዘች ፡፡ አሁንም የተለወጠ ቅንጫቢ

  “.. የራት ግብዣ ሲያደርግላት ሆን ብሎ ትንሽ ምላስ የሚይዝ /ጨው የበዛው/ ምግብ ጋበዛት ፤ በአንድ ጣራ ስር አብረው ሲያድሩ አንዱ የአንዱ ንብረት እንዳይነካ /እንዳይሰራረቁ ፣ እንዳይደፋፈሩ/ መሃላ አደረጉ ቅንጫቢውን በሥርዓቱ አቀርባለሁ ፡፡
  ንግስት አዜብ - “ትንሿን የሰው ህግ ብሳሳት በመንገድ ላይ ወደ ድካም ፣ ህማምና ችግር ውስጥ እገባለሁና እንዳትደፈረኝ በአምላክህ በእስራኤል አምላክ ማልልኝ አለችው /አርግዠ ጉዞ ሳደርግ ችግር ውስጥ ስለምገባ በሰው ልማድ አትቅረበኝ በማለት ምሃላ አስቀድማ መጠየቋን ተገንዘቢልኝ/፡፡
  ንጉስ ሰሎሞንም - በጥበቡና በሰራው ተንኰል ስለሚተማመን አንቺም በቤቴ ውስጥ ያለውን ሁሉ እንዳትደፍሪ ማይልኝ አላትና በመሃላው ተስማሙ ፡፡
  ትንሽ ቆይቶ ግን ውሃ ስለጠማት ሳታስፈቅድ ለመጠጣት ስትል ያዛት ፤ መሃላዋንም እንዳፈረሰች ነገራት ፡፡ እሷም “ውሃን መጠጣት ማሃላን መተላለፍ ነውን ስትል መለሰች
  ሰለሞንም ጥበበኛ ስለሆነ “ከሰማይ በታች ከውሃ የሚሻል አይተሻልን” አላት
  እሷም “ራሴ በድያለሁ ፡፡ አንተ ግን ከመሃላህ ንፁህ ነህ ፡፡ ይሁንና ለጥማቴ ውሃን እጠጣ ዘንድ ተወኘ” አለችው ፡፡ እሱም “ እነሆ ካማልሽኝ መሃላ ንፁዓ ነኝ” አላት ፡፡
  ንግስቲቱም “ከመሃላህ ንፁህ ሁን፡፡ ነገር ግን ከውሃው እንድጠጣ ተወኝ” አለችው ፡፡ ውሃም ትጠጣ ዘንድ ተዋትና መሃላቸውን በጋራ አፈረሱት ፡፡ በዚህም ምክንያት ጸነሰች ፤ ህጻንም ተወለደ ፤ ስሙንም በይነ ልሀለም አለችው

  ንጉሥ ዳዊት ሰሎሞንንም የወለደው ከህጋዊ ሚስቱ አይደለም ፤ ነገር ግን የእግዚአብሔርን ማደሪያ እንዲገነባ ከንጉስ ዳዊት ይልቅ ተመርጧል ፡፡ ይህን ስል ግን ሥራቸውን ደግፌና ትክክል ነው በማለት አይደለም ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረንን ታሪክ እንድናስታውስ ለማለት ብቻ ነው ፡፡
  ይቀጥላል

  ReplyDelete
 16. ሠይፈ ገብርኤልFebruary 6, 2012 at 1:17 PM

  3. ታቦት እንዴት ይሰረቃል
  የቀደም ታሪኩን ከተከታተልሽ አሕዛብ የእስራኤልን ታቦት እንደወሰዱት ይናገራልና እንመርምር ፡፡ ከላይ በተራ ቁጥር 2 የተገለጸው እግዚአብሄር … እግዚአብሄር የሚለው ምናልባት ማመን ከቻልን ከሌብነቱ ባሻገር ፣የአምላክ ፈቃዱ ስለሆነ ወደ አገራችንም መምጣት ችሏል ፡፡ ያነበብኩት መጽሃፍም የሚደረድረው ምክንያት ይህንኑ የኢትዮጵያን በእግዚአብሔር መመረጥ ነው ፡፡
  በተረፈ ተአምር ማድረጉ ለምን ቀረ ለሚለው ለማያምኑ ይሆናል እንጅ የቀረው ለሚያምኑትማ ብዙ ተአምር እየፈጸመ ነው ፡፡ አንድ የንግስ ቀን አንድ ቤተክርስቲያን /እንዲያውም የምታውቂውን የቁልቢ ገብርኤልን/ ለትዝብት ያህል እንኳን ብትቆሚና የሚገባውን የስእለት ምክንያት ብታዳምጭ ፣ የራስሽን በዚህ ምድር ላይ መኖር ትጠራጠሪያለሽ ፡፡ በእርግጥም ላመኑበት እጅግ ብዙ ተአምራትን አድርጓል ፣ ያደርጋልም ፡፡

  ጸቡ ሊኖር የሚችለው አንድ ወጥ አገር አቀፍ አለመሆኑና እንደ ፍላጐታችን አለመፈጸሙ ነው ፡፡ ለዛም ምክንያቴ እንደኔ ዓይነት ኃጢአተኛ ፣ በሃይማኖት የተከፋፈለ ኀብረተሰብ በተሰገሰገበት አገር ለሁሉም የሚሆን በረከት አልጠብቅም ፤ እስቲ ለሰባት ቀን ብቻ አንድ ሆነን ፣ አንድ ቃል ተናግረን ፈጣሪን በጾምና በጸሎት እንለምነውና አይፈጽም እንደሁ እንይ ፤ መንገድ የዘጋው የኛ ችግር /በሃይማኖትና አምልኮ መለያየታችን/ ይመስለኛል ፡፡ በሌላ አንጻር ካየነው ደግሞ ተአምር የሚያስፈልገው ለማያምኑ ነው እንጅ ለሚያምኑ አይደለም ይላል መጽሐፍ ፤ ለዚህም ተጨማሪ የሚደረገው እግዚአብሔር ያስፈልጋል ብሎ የፈቀደው ብቻ ነው እንጅ እኛ የተመኘነው ሁሉ አይደለም ፡፡

  4. ታቦቱ አይታይ ነገር ስትይኝ እግዚአብሔር የሚመራቸው ሰዎች ሥራ ውስጥ እንዳልገባ ፈራሁ ፡፡ ፈረንጆቹ ይህን ምስጢር ለማወቅ ቄሰ ሆነው ፣ ወታደር ሆነው ፣ ቱሪስት ፣ ጋዜጠኛ ሆነው … ብቻ ዓይነቱን ምን ልበልሽ ያልመጡበት መንገድ ፣ ያልፈተሹት የሰው ጥበብና ስልት የለም ፡፡ ያ ሁሉ ከሺህ ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ትግል ፣ ፍሬ አልባ ሲሆንባቸው ፣ አሁን ደግሞ አይ ታቦቱ የላችሁም እንበላቸው ፣ ቢኖርም ጥቅም የለውም እንበላቸውና እራሳቸው ያውጡና ያሳዩን ያሉ ይመስል በታቦት ላይ ጦርነት ያልከፈተ መጽሐፍ ገላጭ ፣ ያልጻፈ ደራሲ ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ተንታኝ ፣ እንዲያም ሲል ታሪክ ተመራማሪ የለም ፡፡
  በተረፈ ይህችን የማስቀምጣትን አስተያየት እንደፈለግሽው - ጥንቆላ ፣ መላ ምት ወይም ትንቢት ብለሽ ተመልከችልኝ ፤ ታቦቱ በገሃድ የሚታይና በቀላሉ እንደተፈለገ የሚገኝ ቢሆን ኖሮ የሚያጋጥሙን ፡-
  ሀ. የኢትዮጵያ መካ መዲና ይፈጠርና በቱሪስትና በአማኝ ጐርፍ በመጥለቅለቅ ፣ ዜጎቿ ሳንቀር በእያንዳንዳንዷ ሜትር የኮቴ ግብር እንጠየቅ ነበር ፤ የቀብር ቦታ የሚባልማ ጨርሶውንም አይታሰብም ፣ ያው እንዳመጣብን በወፍጮ እንፈጨው ነበር እንጅ
  ለ. ኢአማንያን የሆኑት ደግሞ ሃይማኖቱን ከገጸ ምድር ለማጥፋት ሰለሚፈልጉ እንደ ሂሮሺማ በኑክሊየር ሳይቀር እኛን ጭምር አብረው ከመደምሰስ አይመለሱም ነበር ፤
  ሐ. የኛ ነው ባይዎቹም በጉልበት ለመንጠቅ እስከ ዛሬ በታሪክ ያልታየ እልህ አስጨራሽና ዘመን ያስቆጠረ ጦርነት ይከፍቱብን ነበረ ፡፡ በራሱ ባለመታየቱ ግን ለሁላችንም መልካም ሆነልን ፤ ይህንንም ያደረገው አምላክ በጥበቡ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ለምናምነው ወገኖች ሳናይ በማመናችን ብፁዕ እንባልበታለን ፤ ለማያምነው ወገን ደግሞ ቢያንስ ጦርነት የሌለበትን ሰላማዊ ምድርን ፣ የሚቀበርበትን ሰፈር አግኝቷል ፡፡ ስብሐት ለእግዚአብሔር

  5. ስለማነበው መጽሐፍ ቅዱስ ዓይነት
  - በብዛት አጼ ኃይለ ሥላሴ ያሳተሙትን 66 መጽሃፍት ነው ፡፡ ይመቸኛል
  - ሰማንያ አሐዱም ከላይ ከተጠቀሰው የሚለየው ትንሽ መጽሐፍት ስለታከሉበት ነው ፤ ይኸ ደግሞ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳይሆን ከቀደምት ቤተ ክርስቲያን መስራቾች አንዱ የሆነው የካቶሊክ መጽሐፍም አለው ፡፡ በመጽሐፍቱ መሃከል ግን ትንሽ ልዩነት አላቸው ፡፡ የቀደም ኘሮቴስታንት መጽሐፍትንም ማግኘት ብትችይ እንደ ኢንዴክስ አድርገው ይጽፋቸው ነበር ፡፡ ኋላ ላይ ግን ያው መገንጠልና መለየት ስለሚገባ ልዩነትን ለማሳየትና ለመፍጠር ምልክት ሲባል አጉድለው መጻፍ ጀመሩ /የ19ንኛው መቶ ችግር ነው/፡፡ በተረፈ የማረጋግጥልሽ ግን ይህን መጽሐፍ በእጅሽም እንኳን አልነካሽውም ፤ እንዲያው ባሉ ብቻ ተቸሽው ወይም ጠላሽው፡፡ የአዲስ ኪዳኑ ወንጌልና የብሉይ ኪዳን መጽሐፍት ከየትኛውም መጽሐፍ ቅዱስ ልዩነት የላቸውም ፤ የሚለዩት 2ኛ የቀኖና መጽሐፍት ወይም አፖክሪፋ በተባሉት 18 መጽሐፍት ነው ፡፡ ከነዚህ ውስጥ ደግሞ አሁን ዓለም ሁሉ ተቀብሎ እየገለበጠ ያለው የሄኖከ መጽሐፍ ይገኝበታል ፡፡ እናንተ ሰፈር አልደረሰ እንደሁ እኔ አላውቅም ፡፡
  - በተጨማሪ የቀደመው ክፍለ ዘመን የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስም አለኝ ፤ ከአይሁዳውያን መጽሃፍ ጋር በብዙ ይዛመዳል ፡፡ ማርቲን ፍላድ የወንጌል መልዕክተኛ የሚል ወንጌሉ ርዕስ መጀመሪያ ላይ አለው ነው ፡፡ አማርኛው ግን ለመረዳት እጅግ ያስቸግራል ፡፡ /ሽፋኑና የመጀመሪያ ገጾቹ ስለሌሉት መግለጽ አልችልም
  - e-Sword software ይኸኛው ከሃምሳ በላይ የመጽሐፍ ቅዱስን ዓይነት የያዘ ኘሮግራም ነው ፡፡ የካቶሊኩ ፣ የኘሮቴስታንቱ ፣የወንጌላውያኑ ፣ የይሆዋ ምስክሮቹ ፣ ብቻ ሁሉንም በሃይማኖት ዝርያ ከፋፍዬ መጥራት አልችልም እንጅ ሁሉም የጻፉት ድግን መትረየሶች ይዟል ፡፡ በቀረች ዘመኔ ሁሉ እሱን እያነበብኩ ብኖርም አላዳርሰውም ፡፡ ነገር ግን በተራ ቁጥር 1 የተመለከተውን አንብቤ ትንሽ ግር ካለኝ ለማነጻጸሪያ ከአንዱ ወደ አንዱ ለመሸጋገር ቀላል ስለሆነ በተለያየ መልክ የተጻፉትን ለመረዳት ያህል አስተያያለሁ
  - በተረፈ የመጽሐፍ ቅዱስ ማጥኛ የሚሆኑ መጽሐፍ ቅዱስን የሚተነትኑ ፣ የሚያስረዱ አንድ አራት መጽሐፍትን አገኛለሁ ፡፡ በጣም የማዝነው ግዕዝን አውቄ በምስጢሩ ሁሉ እንደ ሊቃውንቱ ባለመፈንጨቴ ብቻ ነው ፡፡ በግዕዝ የተጻፈ ነገር ሳይ ዓይነ ስውር ነኝ ፡፡ ብቻ ማነው ያልሻቸው እነዚያ “እነሽፍንፍን ቄሶቻችን” የምትያቸው ሰዎች ግዕዙንም አውቀው ጥምጥሙንም አድርገው በሁለት ቢለዋ እያፈራረቁ እየበሉ እንደሆነ በቅርቡ ሰምቻለሁ ፡፡ ግዕዝ ማወቁም ምስጢርን ለመረዳት የሚሆነው እግዚአብሔር ሲፈቅድና ሲያድል ብቻ ነው ፡፡
  ይቀጥላል

  ReplyDelete
 17. ሠይፈ ገብርኤልFebruary 6, 2012 at 1:30 PM

  የተረት ጽሁፌ ማስከበሪያ እንዲሆን ከዚህ በታች ያለውን በተነሳሽነት ጨምሬዋለሁ
  - በራዕይ 11 ፡ 19 ላይ ያለውን ከማንበብሽ በፊት በራዕይ 1ዐ ፡ 7 የተጻፈውን አንብበሽ ካቆራኘሽው የሚናገሩት ሰለ ምጽዓት እንደሆነ በግልጽ ያስረዳል ፡፡ “ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን ለባሪያዎቹ ፣ ለነቢያት የምስራች እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል” ይለናል ፡፡ ይህ ለነቢያት የተገባ ቃል ኪዳን ፣ በኃጥአንና በጻድቃን ላይ የሚካሄደውን የፍርድ ጉዳይ የሚመለከት ስለሆነ የሚፈጸመው ሁሉን አደራጅቶ በፈጸመ ጊዜ በምጽዓት ዋዜማ ወደ ፍርድ ሥራው ሲገባ ነው እንጅ ዛሬ አይደለም

  - ጳውሎስ የእኛን አካል መቅደስ እንደሚለው አልጠፋኝም ፤ ነገር ግን የኔን ዓይነቱን ገላ ወይም አካል ከጣዖት ጋር አነጻጸረው ማለቱ አይደለም ፡፡ እግዚአብሔር ለማደሪያው እንድትሆን የመሰረታትን ታቦተ ጽዮንን እንጅ ፡፡ ታቦተ ጽዮንን ከጣኦት ጋር በልዩነት ካስቀመጠ በኋላ የኛን ሰውነት በእምነት ክርስቶስን ከተቀበልን መቅደስ /ቅዱስ ሰውነት/ መሆኑን ያስረዳናል ፡፡ ይህ ማለቱ ከእምነት በኋላ ሰውነታችሁ በሙሉ ጥፍርና ፀጉር ሳይቀር ፣ የቅዱሱ የእግዚአብሔር ማደሪያ ሰለሆነና ፣ የተባረከም ስለሆነ የኃጢአት መሣሪያ አድርጋችሁ አትገልገሉበት ማለቱ ነው እንጅ ከታቦተ ጽዮን ጋር መላተሙ አይደለም ፡፡

  እንዳዘዝሽኝ ወደ 1 ቆሮ 6 ፡ 19 ላይ ከመዝለላችን በፊት ስለምን እንደሚተነትን ከቁጥር 9 ጀምሮ ያለውን እንመልከት እንዲህ ይነበባል -
  9 ወይስ ዓመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዳይወርሱ አታውቁምን? አትሳቱ፤ ሴሰኞች ቢሆን ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ ወይም አመንዝሮች ወይም ቀላጮች ወይም ከወንድ ጋር ዝሙት የሚሠሩ
  10 ወይም ሌቦች ወይም ገንዘብን የሚመኙ ወይም ሰካሮች ወይም ተሳዳቢዎች ወይም ነጣቂዎች የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።
  13 መብል ለሆድ ነው፥ ሆድም ለመብል ነው፤ እግዚአብሔር ግን ይህንም ያንም ያጠፋቸዋል። ሥጋ ግን ለጌታ ነው እንጂ ለዝሙት አይደለም፤ ጌታም ለሥጋ ነው፤
  14 እግዚአብሔርም ጌታንም አስነሣ እኛንም በኃይሉ ያስነሣናል።
  15 ሥጋችሁ የክርስቶስ ብልቶች እንደ ሆነ አታውቁምን? እንግዲህ የክርስቶስን ብልቶች ወስጄ የጋለሞታ ብልቶች ላድርጋቸውን? አይገባም።
  16 ወይስ ከጋለሞታ ጋር የሚተባበር አንድ ሥጋ እንዲሆን አታውቁምን? ሁለቱ አንድ ሥጋ ይሆናሉ ተብሎአልና።
  17 ከጌታ ጋር የሚተባበር ግን አንድ መንፈስ ነው።
  18 ከዝሙት ሽሹ። ሰው የሚያደርገው ኃጢአት ሁሉ ከሥጋ ውጭ ነው፤ ዝሙትን የሚሠራ ግን በገዛ ሥጋው ላይ ኃጢአትን ይሠራል። ከዚህ በኋላ አንቺ የፈለግሽውን ቁጥር 19 መቀጠል ይቻላል

  በተረፈ እንዚህንም ተመልከቺልኝ “2 ጴጥ 3 ፡ 15 – 16 የጌታችንም ትዕግሥት መዳናችሁ እንደ ሆነ ቍጠሩ። እንዲህም የተወደደው ወንድማችን ጳውሎስ ደግሞ እንደ ተሰጠው ጥበብ መጠን ጻፈላችሁ፥ በመልእክቱም ሁሉ ደግሞ እንደ ነገረ ስለዚህ ነገር ተናገረ። በእነዚያ ዘንድ ለማስተዋል የሚያስቸግር ነገር አለ፥ ያልተማሩትና የማይጸኑትም ሰዎች ሌሎችን መጻሕፍት እንደሚያጣምሙ እነዚህን ደግሞ ለገዛ ጥፋታቸው ያጣምማሉ።” ጴጥሮስ አለው እንጅ እኔ አላልኩትም
  ያወቁትንና ትንሽ የቃሉን ፍሬ ቀምሰው የካዱትን በንስሐ መመለስ እንደማይቻል መጽሐፍ ያስገነዝባልና ብዙ አንከራከርበት ዕብ 6 ፡ 4 – 6 ፡፡ እጅግ የተደሰትኩበት በሰበቡ ማንበብ መቻሌን ነውና እግዚአብሔር ይባርክሽ ፡፡ ወደፊት በሌላ ርዕስ ደግሞ እንደ እግዚአብሔረ ፈቃድ ሃሳብ በመለዋወጥ መጽሐፉን ለመመርመር ያብቃን

  በግሌ ጥሩ የአነባበብ ስልት ይሆናል ብዬ የምገምተው አንድ ኃይለ ቃልን ብቻ ነጥሎ ሳይሆን ሙሉ ምዕራፉን ማንበብ ፤ ከተቻለም መልሶ መድገም ፤ ቀጥሎ ደግሞ ከሌላው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ጋር መስማማቱን ለማየት ማገናዘብ ስለሆነ እስቲ ሞክሪው ፡፡

  ሰላምና የእግዚአብሔር በረከት ለምታነቡ ሁሉ ይብዛላችሁ

  ReplyDelete
 18. ሰይፈ ገብርኤል ከተረት ሰፈር የማትወጣው እስከ መቼ ነው? አሁን ማን ይሙት የኢትዮጵያን ታቦቶች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ለማድረግ መታገልህ ምን ይባላል? እስኪ ‹‹አልተሳሳትንምን?›› በሚል ርእስ በዲ/ን አግዛቸው የተጻፈውን እንዳንተ ሲያደናቁረን ለነበረው ምሕረተ አብ አሰፋ የተሰጠውን ምላሽ አንብብና ከዚያ በኋላ አንተ እስካሁን የዘበዘብከውን መልሰህ የምትዘበዝብ ከሆነ እንይ፡፡ ለሁሉም የሰማይ አምላክ ልቡናህን ያብራልህ! እውነቱን እንዳታውቅ የጋረደብህን ግርዶሽ ያንሳልህ! ከሳውል አይን እንደወደቀው ቅርፊት ወደአዳኙ ኢየሱስ ብቻ እንዳትመለከት ያደረገህን ነገር ከአይነ ልቡናህ ላይ ይጣልልህ!

  ReplyDelete
 19. ለሰይፈ ገብርኤልና ለሰላም ምክር፡-
  ውድ እህቴ ሰላምና ወንድሜ ሰይፈ ገብርኤል፡፡ ጽሑፎቻችሁን ተከታትያለሁ፡፡ ነገር ግን ሁለታችሁም በክርስቶስ ኢየሱስ አምላክነትና አዳኝነት የምታምኑ ከሆነ በማይጠቅም ጉዳይ ላይ ለምን ይህንን ያህል ጊዜ ታጠፋላችሁ፡፡ የክርስትና ዋና ዓላማ ክርስትያን የተሰኘንበትን የክርስቶስ ኢየሱስ አዳኝነት ማመን ላይ ስለሆነ ሁለታችሁንም ይህ ካግባባችሁ የምትግባቡበትን ጉዳይ ማጠንከር የሚሻል ይመስለኛል፡፡ እውነትን ለመመስከር ግብ ግብ መግጠም ጥሩ አካሄድ አይመስለኝም፡፡ ለብዙ ዓመታት በሰዎች ልብ ገብቶ ስፍራ የያዘውን ውሸት ለማስወጣት የጋራ በሆነ ጥቂት እውነት ላይ መወያየት መልካም ነው፡፡ በዚህ አካሄድ ሰሚው ሳይታወቀው ውሸት የሆነውን ሁሉ ከውስጡ ተንኖ ያገኘዋል፡፡ እውነት ቦታውን ታስለቅቀዋለች፡፡ አለበለዚያ ጭቅጭና ንትርክ ወደ እውነቱ የሚያደርስ አካሄድ አይደለም፡፡

  ReplyDelete
 20. የተከበሩ ሰይፈ ገብርኤል ስለመልስዎ አመሰግናልሁ::

  1)እንደ አባባልዎ እግዚአብሔር በስርቆቱ ተስማምቷል ካሉኝ 'አትስረቅ'ያለውን ትእዛዝ ስለሻረው 'ይዋሽ ዘንድ ሰው አይደለም' የሚለውን ጥሶ እግዚአብሔር ዋሽቷል ማለትዎ ነው?

  2) ይህ ታቦት በክብሩ ሳይሆን ተደብቆ እንዲኖርባት ነው አገራችንን እግዚአብሔር የመረጣት? ከሱዳን ከግብጽ ከሱማሊያ ወዘተ ጋር አብረን አሕዛብ መባላችንን ለምን ይረሱታል? ደግሞስ የተመረጠችበትን ዓላማ መፈጸም አቅቷት የሕይወትን ጌታ ሳያውቁት ሰቅለው ገደለው ደሙ በላያችን ላይ ይሁን በማለት አመጹ እንጂ እስራኤልን የመረጠ ቅዱሱ እግዚአብሔር የምርጫ ቃሉን እስከ ዓለም ፍጻሜ መቼ ይሽርና ነው ሌላ አሕዛብ አገር ታቦቱን ለመደበቅ የሚመርጥ? እረ እባክዎት አሁንም ለዚህ ሁሉ በሁሉ የሆነውንና ቃሉ የማይሻረውን አምላክ ያለውን ወይም ሃሳቡን እንደተመቸው እንደሚለዋውጥ ሰው አይቁጠሩት?

  አልፈርድብዎትም - ምክናያቱም:
  - እየሰረቅን እየተጋደልን አጋንንት እየሳብን ወዘተ 'የክርስቲያን ደሴት'
  - በድህነት አሮንቃ ተዘፍቀንና መጠሪያ ስማችን ሆኖ ሳለ 'ለምለሚቷ አገሬ'
  - ፈሪዎች ተለማማጭና ለመጣው ሁሉ ተግዢ ሆነን ሳለ 'ጀግኖች'
  - በዋናነት በግብጾችና በነዘርአ ያእቆብ ታሪካችን ተበላሽቶ ሳለ 'ታሪካዊ አገራችን'
  - እረ ስንቱ ስንቱ ተቆጥሮ ያልቃል ወዳጄ?

  በሚል ዘራፍነትና አጉል ጀብደኝነት በተካነ ሕብረተሰብ መካከል ተወልደን አብረን እንደ ሙሾ ስንዘምረው ስላደግን አሁንም 'ኢትዮጵያ' የምትባል አገር ከምንም ከማንም በላይና እንዲያውም አንዳንድ ወገኖቼማ ከእስራኤል የበለጠ የመረጣት 'ምድረ ገነት' ናት ማለት እየዳዳቸው ነው::

  ሰይፈ ገብርኤል እግዚአብሔር አይዘበትበትምና እንዲያው እውነተኛ ታሪካችን ላይ ብናተኩርና የሆነውን ሆነን ለበለጠ መሻሻል እጅ ለእጅ ተያይዘን በጌታ ፍርሃትና ፍቅር ብንነሳ ይሻላልና እኔ ዝም ማለቱንና ወደ ጌታ ማንባቴን መርጫለሁ::

  ደግሞም ታቦቱ የእግዚአብሔር ማደሪያ ነው ካልንና እግዚአብሔር በዚህ ታቦት ላይ በምድራችን ካለ ለምድነው ድህነታች/ርሃባችን ቅጥ ያጣውና ስንዴ ለማኞች የሆነው? 'ጻድቅ ሲራብ ልጁም እህል ሲለምን አላየሁም' እያለ ሕያው ቃሉ? እስቲ የግብጽ ተሿሚ ጳጳሳት በቤተ ክርስቲያናችን ላይ ያጣበቀችብንና ቤ/ክቱም ለቃሉ ሳይሆን ለነሱ ጉዳይ አስፈጻሚ በመሆን እስከ አሁን ድረስ ሰርተን እንዳያልፍልን ያሸከመችንን የባእላትና በሌለ አቅም የዝክርና የተስካር ደጋሺዎች ያደረገችበት ታሪክ ይጠና? ደግሞም እነግራኝ ሙሐመድ ዮዲት ጉዲትና እነዘራአ ያእቆብ ያሸከሙንን ተቅጥላ ባእድ ነገሮች እስቲ እናጥናና እንማማር:: ይህን ያህል ጉድ ተሸክመን እንዲህ ነን እንዲያ ነን እያልን በውሸት አንኮፈስ:: ካልረባባ ግልድም ሙልጭ ያለ ቂ?(አንባቢ ለራሱ ፊደሏን ይጨምር)

  በአጠቃላይ ታቦቱ/እግዚአብሔር ባለበት በረከት እንጂ ለመናገር የሚዘገንን ጉስቁልናና ክፋት ሊኖር አይገባም ነው እያልኩ ያለሁት:: ደግሞስ እስዎ እንዳሉት ከተመረጥን ለድህነትና ለጉስቁልና የዓለም ምሳሌ እንድንሆን ነው እንዴ የመረጠን?? እረ እናስተውል??

  ሌላው ጌታ በኤርሚያስ 3:16 ላይ 'በዚያ ዘመን የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት በለው ከእንግዲህ ወዲህ አይጠሩም ልብ አያደርጉትም አያስቡትምም አይሱትምም ከእንግዲህ ወዲህም አይደረግም::' የሚለውን በመንፈስ ሁነው ቢያጠኑት ይጠቃማሉ::

  ታቦቱ በግልጥ መኖሩ ቢታወቅና ቢታይ እንዲህ ያደርጉናል ይሆንብናል ብለን ነው የደበቅነው የሚለውን መላምት የሚያሳፍርና ለእስዎ ያለኝን ግምት ስለሚያቀልብኝ ወዲያ ይጣሉት:: ደግሞም የራሳችንን ችግር አናሳይም ስንላቸው ነጮች የፈጠሩብን ነው በማለት በጽሑፍዎ ላይ ያደባለቁት አጉልና ተልካሻ ምክናያት ወንዝ አያሻግርዎትምና ይህንንም ይተውትና ወደራሳችን እንመለስ::

  ለማጠቃለል ያህል 1) በሚኖሩበት አካባቢ እስራኤላውያን የሚኖሩ ከሆነ ያታቦቱን ታሪክ ጠይቀው ቢረዱ
  2) ቤተ መቅደስ ማለት ቅዱሱ እግዚአብሔር በታቦቱ በኩል የሚገለጥበት/የሚያድርበት ስለሆነ እንዳልክዎት ጌታን በዮሐ 1:12 መሰረት በግልዎ በእምነት ተቀብለውት ከሆነ ያለጥርጥር እርስዎ መሆንዎን ቃሉ በ 1ቆሮ 3:16-17 ላይ 'የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና ያውም እናንተ ናችሁ'' ስለሚልና ደግሞም በትንቢት ላይ 'ከእንግዲህ የሰው እጅ በሰራው አልኖርም' ስለሚል ውብ አድርጎ በፈጠረው በሰው ውስጥ እንደሚኖር እንድጂ የጥበብ መንፈስ በተቀበለው ባስልኤል ከግራር እንጨት በተሠራ ሳጥን ውስጥ እኔ የማመልከው እግዚአብሔር አምላክ አይኖርምና ቆም ብለው ቃሉን ያሰላስሉት::

  በተረፈ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ያለኝ ፍቅር ከእርስዎ ቢያይል እንድጂ እንደማያንስ ላረጋግጥልዎት እውዳለሁ:: ይህን ስል ለመወዳደርና ለፍከራ ሳይሆን የእኔንም ቀናተኛነት እንዲያውቁት ብዬ ነው(ለአእምሮዎ) የእኔ ቅናት ከእርስዎ ዓይነት ቅናት የሚለየው:-
  *ቤተ ክርስቲያኒቱ የሁላችንም ባለውለታ እንደሆነች አምናለሁ
  *የቤተ ክርስቲያኒቱ መሰረት ወንጌል ብቻ እንደነበረ አምናለሁ
  *ቤተ ክርስቲያኒቱ በታሪክ ውስጥ በርካታ ችግሮች እንደተፈራረቁባት አምናለሁ
  *ቤት ክርስቲያኒቱ የበርካታ ሊቃውንት መፍለቂያ እንደሆነች አምናለሁ
  *ቤተ ክርስቲያኒቱ ደካምም ጠንካራም ጎኖች እንዳሏት አምናለሁ
  *ቤተ ክርስትያኒቱ ለምድራችን ሁለንተናዊ ጉስቁልና ተጠያቁ እንደሆነች አምናለሁ::

  *** ስለዚህ እውነትን በፍቅር እየተናገርንን ስህተቱ በእግዚአብሔር ቃል እየመዘን ወደ ወንጌል ብቻ እንመለስ ነው የእኔ ጽኑ አቋም:: ይህን ከተረዱና ካመኑበት አንድ ነን ባንድነት እንሠራለን::

  ለዚህ ሳይማር ላስተማረን የዋህ ሕዝባችን/አገራችን ዘርፈ ብዙ ችግር መንስኤው ከፓለቲከኞቻችን ሳይሆን ከላይ ከሰማይ በወንጌል ስብከት ብቻ የአምላክን ክንድ በምድራችን ላይ በማንቀሳቀስ እንደሚሆን አምናለሁ::

  ሰላም ይሁኑልኝ

  በእውነት በጌታ ፍቅር እወድዎታለሁ

  አክባሪ እህትዎ

  ሰላም ነኝ

  -

  ReplyDelete
 21. ሠይፈ ገብርኤለFebruary 7, 2012 at 2:33 PM

  ጉዳዬን የጨረስኩ መስሎኝ ተሰናብቼ ነበር ፡፡ ሆኖም ደንበኞቼ መምጣታቸውን ስላላቋረጡ እንደገና ሃሳቤን ለማቅረብ ተገደድኩ ፡፡

  ለቀዳማይ አናስሞስ
  - ስምህ ማነው ተብሎ ለሚጠየቅ ሰው ስሙን መናገር ያባት ወግ መሰለኝ ፡፡ እኔ ወደ ተረት በስሜቴ ተገፋፍቼ አልገባሁም ፡፡ እህቴ ሰላም የታሪካችን ውዥንብር ስለነበረባት በጠየቀችኝ መሠረት በፍርሃት ሆኜ የማውቀውን ቁንጽል ዕውቀት ለማካፈል ጫጫርኩ ፡፡
  - ዲያቆን አግዛቸው የጻፈው በእጄ ስላልገባ አላነበብኩም እንጅ ባነብና ትንሽ ዕውቀት ባገኝ እጅግ ደስ ይለኝ ነበረ ፤ ሌላ አይደለም የማንበብ ሱሰኛ ስለሆንኩ ነው ፣ ከቀረበልኝና ከተረዳሁት የማላነበው የለም ፡፡ ልብ ማለት ስላለብህ ግን ይህን ለማለት እገደዳለሁ ፡፡ የዘመኑ የዲያቆንነት ሹመት መጽሐፍ ቅዱስ በሚሰጠው መመሪያ መሠረት የሚሄድ ስላልሆነ ፣ መተማመኛ ሹመት ወይም የኢየሱስ አገልጋይነት መገለጫ አድርገህ በመቁጠር እንደማይሳሳቱ እንዳትገምት ነው፡፡ ሰዎች ዲያቆንም ሆነው አንዳንድ ጊዜ የራሳቸውን ስሜት ሲያንጸባርቁና ፣ ለምድራዊው ምቾት ሲጋደሉና ሲታገሉ /ጸብን ማለቴ ነው/ ሊታዩ ይችላሉና ፡፡
  የግርዶሽ መነሳትን ምኞት ለእኔ ብቻ ሳይሆን ቀናውን ላለማየት ለጨፈኑ ሁሉ እንዲሆን የኔም ጸሎቴ ነውና ሰዓታችንን ብናስማማ ባለሁበት እንበረከካለሁ ፡፡

  ለዳግማዊ አናስሞስ
  ወጣት ከሆንክ የልጅ ሽማግሌ ፣ እንደ እኔ ዕድሜ የጠገብክ ከሆንክ ደግሞ የወግ የባህል ደንቡን ያከበርክ ስለሆነ ምክርህን ተቀብየዋለሁ ፡፡ ታቦቱም በስፍራው በክብሩ ይቀጥል ፤ ዕጣኑም ይጨሰ በተጓዳኝ ግን ኢየሱስ እንዲከብር የምናውቀውን እናስተምር በሚለው ሃሳብ ፍጹም እስማማለሁ ፡፡

  ለእታለም ሰላም
  እኔ መጽሐፍ ቅዱስ ሃሰት አለው አላልኩም ፤ ላሻሻሽለውም ምኞት የለኝም ፤ አጻጻፉ ከምን እንደሆነ በደንብ ጠንቅቄ ተረድቻለሁ ፤ በእግዚአብሔርም ለመዘበት ህልሙም ፣ ችሎታውም የለኝም ፤ ስለሆነም በተጻፈው በሙሉ ፣ ሳይቀነስ ሳይጐድል አምናለሁ ፡፡ እግዚአብሔርም ለቃሉ ታማኝ እንደሆነ አውቃለሁ ፡፡

  ኃጢአት አታስገቢኝ እንጅ በመጽሐፍ ቅዱስ አትግደል የሚለው ህግ ተጽፎ እያለ በሺ የሚቆጠር ህዝብ በጦርነት እንዳለቀ ተዘክሮ ተጠቅሷል ፡፡ ታድያ ይህን በምን ትገልጭዋለሽ ? የገዳዮች ተባባሪ ስለሆነ ነው? አይመስለኝም ፡፡ አታመንዝር ያለው ህግ የሚያስከትለው ተወግሮ የመገደል ህግ በዳዊት ላይ ለምን አልተፈጸመም ፡፡ ሰሎሞን የሚባለውም መንገሥ አይችልም ነበረ እኮ ታድያ እግዚአብሔር ምን አደረገ እንበል? የኃጢአት ተባባሪ ወይስ እቅድ ስላለው?

  የኢዮብስ ፈተና ለምን ሲባል መጣ? እግዚአብሔርን ስለበደለና ስለ ኃጢአቱ ይሆን ይሆን? ታድያ ይኸ ስለምን ምክንያት ሊሆን ቻለ? አንዳንዴ ችግርና መከራን ከአምላክ ፍርድና ሃይማኖት ጋር አቆራኝተን መተርጐሙ ወደ ስህተት ያመራናል ፤ እንድናማርረው ስለሚያደርገን ፡፡ በምድራዊ በረከትም መትረፍረፍ የሚታወቁት አገሮችና መንግሥታት በሙሉ በኢየሱስ የሚያምኑ ክርስቲያኖች ብቻ አይደሉም /ከዚህ ቀደምም ይህን ሃሳብ በሌላ ቦታ ጠቅሼዋለሁ/፡፡ እግዚአብሔር የሚያሰናዳን ፍጹም ለሆነ ለዚህ ዓለም ተድላ አይደለም ፤ በረከቱ ግን የሚደርሳቸው የመረጣቸው ሰዎች እንዳሉ አውቃለሁ ፤ ነገር ግን መለኪያ መሆን የለበትም ፡፡ እንደዛ ካደረግን እንሳሳታለን ፡፡ እኛ የምንለምነው ለዚህ ጊዜያዊ ቤታችን ከዕለት እንጀራ ያለፈ አይደለም ፤ ነገር ግን እሱ ሁሉን ስለሚያውቅ አትረፍርፎ ይሰጠናል እንጅ ፡፡

  በተረፈ እግዚአብሔር በፈቃዱ የሚያደርግውን ራሱ ነው የሚወስነው እንጅ እኛ በምንቀይሰው ፣ እኛም በምንፈልገው አይደለም ፡፡ ሮሜ 9 ላይ ሙሉ ምዕራፉን ተመልከችልኝ ፤ ሐዋርያው ጳውሎስ የሚመሰክረውንና የሚያስተምረውን በጥሞና ተረጋግተን እናንብበው ፤ ሁሉን ይመልሳል ፡፡
  እኔም ከልብ እወድሻለሁ

  ሁላችሁም ሰላምና የእግዚአብሔር በረከት አይለያችሁ

  ReplyDelete
 22. ሠይፈ ገብርኤልFebruary 7, 2012 at 7:52 PM

  ለእታለም ሰላም ትንሽ ተጨማሪ አስተያየት

  በዓለማዊ ተድላ መሟላትና መጓደል ሃይማኖታችንን ከመዘንነው ፣ ኢየሱስን ከድተን ቡድሃ ፣ ዊካ ፣ ሺንቶንና አላህን ለማምለክ እንገደዳለን ፡፡ የእኔ አዕምሮ የማይቀበለው ፣ ሃይማኖትን በኤኮኖሚ ዕድገት የመለካቱን ዘይቤ ነው ፤ ምክንያቱም የአዳም ልጅ በሙሉ ጥረህ ግረህ ብላ ስለተባለ ፣ ተግቶ እየሠራ የተሻለ ደረጃ ላይ ደርሷል ፤ እንደኛ ደግሞ እርስ በእርሱ ሲላተምና ሲቆራቆስ የኖረው ስልቻ ይዞ ሲለምን ይኖራል ፡፡ በዚሁ ከቀጠልን ገና የባሰ ይመጣል ፤ ምንም አታስቢ ፡፡

  ስለዚህም የድኀነታችን ምንጩ መለያየታችን እንጅ አምላክ ታቦት ስለያዝን ተቆጥቶ አይደለም እላለሁ ፡፡ ታሪካችንን ከዳሰስሽው ከሺህ ዓመት በላይ ያስቆጠረ የጦርነት ታሪክ አለው ፡፡ ይህን ርዕስ አዲስ አድርጌ አልከፍትም ፤ ሌሎች የድንበር ጥያቄ የጠቃቀስሻቸው ፣ የግብጾችና የሌሎቹም ቤተ ክርስቲያናት ተጽእኖ ሁሉ ከመጽሃፍ ቅዱስ የወጣ ታሪክ ስለሚሆንና መጽሃፍ ደግሞ ወደ አሮጊቶች … አትግባ ስለሚል እጅግ እፈራለሁ ፤ ቀዳማዊ አናስሞስም እንደማይወድ አስታውቆኛል ፡፡

  የምንመራበት የፖለቲካ ስልትም እንዲሁ በእምነታችን ላይ የራሱ ተጽእኖ አለው ፡፡ መች ነው ፣ ገና በደንብ ሳንተዋወቅ የሰውየውን ገንዝብ ፣ የህዝብ ሃብት ያልሽው ዓይነት የሶሻሊዝም ቋንቋ ፣ ገባሽ ምን ያህል ሳይታወቅ በደማችን እንደሚሰርጽ?

  አሁንም ይኸ የሚያከራክረን ሌላ ይመስልሻል? አይደለም ፤ ዋና ምክንያቱ ዴሞክራሲ የሚባለው ፍልስፍና ገና ስላልተዋሃደንና የግለሰብ መብትን ማክበር ስላለመድነው ነው ፡፡ በግድ የእኔን አመለካከትና እምነት ተቀበል ፤ የአንተ የተሳሳተ ፣ ያረጀና ያፈጀ በማለት የምንከራከር ፣ የግለሰቦችን መብት ደፍጥጠን ፣ የብዙሃኑን ጥቅም እያስከበርን ነው በማለት ራሳችንን የምናታልል ነን ፡፡ ሁሎችም ደግሞ በዚሁ ዓይነት ፈተናና መከራ ውስጥ አልፈው ነው አሁን የዓለም የዴሞክራሲ ጠበቃ ለመሆን የበቁት ፡፡ እናም አንድ ቀን ሃይማኖተህ ፣ ሃይማኖትሽ ተባብለን የማንወቃቀስበት ዘመን ይመጣል ፡፡ አውሮፓውያንን እያቸው ፣ አሜሪካኖችንም ታዘቢያቸው ፡፡ ሌላውን እስካላወክሽ ድረስ የግል እምነትሽን ህግና ደንብ በሚፈቅደው መሠረት ታንቀሳቅሻለሽ ፡፡ እኛ ቤት ግን ጽናጽልና መቋሚያው ቀርቷል ፣ ታቦቱ ተሽሯል ፣ ዕጣኑም ተረት ሆኗልና አስወጣ አላስወጣም እየተባባልን እንታገላለን ፡፡ ከሁሉ የሚያስቀው ዴሞክራሲ ንጉሥ በሆነበት አገር ፣ አሜሪካ ድረስ ተሻግረው ይዋጋሉ ፤ ይኸ የበሽታ ወይስ የጤንነተ ይባላል ? ሆኖም ግን ሁሉም በሂደትና በዕድገት ይስተካከላል የሚል እምነትና ተስፋ አለኝ ፤ አምላክም ደግሞ እንዲሁ ሜዳ ላይ ፣ ጠባቂ እንደሌለው አይተወንም ፡፡

  እስከዛው ግን ድሃም ብንሆን በአብ ወልድና መንፈሰ ቅዱስን እያመንን ፣ ታቦታችንንም በአግባቡ እያከበርን እንቀጥላለን ፤ ይኸ እኛን የሚማርከን ያይን አበባ በሙሉ ከንቱና ውሸት ፣ የጠዋት ጤዛ ፣ የበጋ አበባ ፣ የክረምት ጐርፍ ነው፡፡ ምድራዊውን ብልጽግና የእምነታችን ጥራትና ብቃት መለኪያ አናድርግ ፤ ሁሉ ይጠፋል ፤ ሁሉም ያልፋል ፡፡
  ማን ያውቃል ይኸ የኛ መከራ እንደ ኢዮብ የጽናታችን መለኪያና መፈተሻ እንደሆነ ፤ ማንስ ደፍሮ ይናገራል የፍቅሩ መገለጫው ይኸ እንዳልሆነ ፤ ኧረ ማን
  ኧረ ጐራው ልታስብይኝ ነው የጥንቱን ፣ የጠዋቱን የተረሳውን ፉከራና ቀረርቶ ብለሽ ጽፈሽ

  ስለዚህም እንደ ክርስቲያን ወንድም ካያችሁኝ የምሰጠው ምክር እንደ ዳግማዊ አናስሞስ ፣ የህዝቡን ሃይማኖትንና እምነት ሳትቃወሙ ወንጌሉን ብቻ አስተምሩት፤ በራሱ መሳሳቱን ከተረዳ እራሱን እንዲያስተካክልም ነጻነት ስጡት ፤ ምን ጊዜም በተጽዕኖና በማዋከብ የሚጫንብን ሃይማኖት ከውስጣችን አይገባም ፤ ካቶሊኮችም መጥተው እኮ እንዲሁ እናንተ አሁን እንደምታደርጉት ሲታገሉት ነው ኧረ ጽድቅ መጥታለች ያለው ፡፡ መጋረጃህን ቅደድ ፣ ከበሮህም ይወገድ … ይኸኛው ያኛው እያልን አናዋክበው ፡፡ የማመን ነጻነቱን አትጋፉ ፤ አሁን ባለው አምልኮ ጀርባ ምንጊዜም አብ ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ መጠራታቸውን አስቡ ፡፡ እዛ መሃል እናቴም አለች ፤ እኔ መጽሐፍን በመረዳት እበልጣት እንደሁ እንጅ ከልብ በሚደረገው እምነት አጠገቧ አልደርስም ፤ የእኔ በእውቀትና በድፍረት ነው ፤ ልጅ በአባቱ ላይ እንደሚሞላቀቀው ፣ የእሷ ደግሞ የፍርሃት ፣ የጌታና የገረድ ነው ፡፡ ታድያ የኔ የጀግናው እምነት ነው ወይስ የሷ ልክ የሚባለው? እኔ አምኛለሁና ድኛለሁ ብዬ በእርግጠኝነት የምፎልለው ነው ወይስ የሷ አምላኬ ይቅር በለኝ እያለች ዘወትር ምህረትን የምትጠይቀው ልክ? እስቲ ማን ነው ትክክለኛ ዳኛ የሚሆነንና የሚፈርድ?

  ለመሰናባበቻየ ንባብ እንዲሆነንና መጽሐፍ ቅዱስ ፈጽሞ ሃሰት እንደሌለው ፣ እግዚአብሔርም አሠራሩ እንደማይመረመር ለማረጋገጥ እነዚህን ሁለቱን አንብቡልኝ ፤ የሰው ሥራና ብልሃት ቢሆን እንዲህ አይጻፍም ፤ ሌላ ታሪክ ይሞሸርልን ነበር ፡፡
  ዘፍጥረት 22 ፡ 9 – 13 ፤ መጽሐፈ መሳፍንት 11 ፡ 29 - 39
  ያቆየን

  ReplyDelete
 23. ከሁሉ በፊት ይህ ምላሽ ቢዘገይም ከጎንደር ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም መምሪያ የተሰጠ መሆኑን ልንገልጽ እንወዳለን፡፡
  በቅድሚያ አንድ አድርገን በድህረ ገጹ ህዝብን ለከፋ አመጽ የሚያነሳሳ ክርስትና ከሚከተለው አስተምህሮት የወጣ በፈጠራ ወሬ ሊያውም እራሱ በሚፈበርካቸው ወሬዎች ሃገር አንድ እንዳትሆን ሃይማኖታዊ ፖለቲካ የሚከተል በመሆኑ ስለአሰራጨው አሉባልታ ላንገረም እንችል ይሆናል እውነታው ግን ከዚህ የተለየ ነበር፡፡
  የጎንደር ከተማ አስተዳደር በየዓመቱ ከጥር 9-13 የሚያዘጋጀው ኢትዮጵያን በጎንደር በዋናነት ጎንደር ያላትን ባህላዊና ታሪካዊ መስህቦች የውጪ ጎብኚዎችን በተሸለ ሁኔታ ስበው የጎብኚውን ቆይታ በማራዘም ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ታስቦ የተወጠነ ዝግጅት ነው፡፡ ይህን ዝግጅት ለማዘጋጅት በመላው ዓለም ከፍተኛ ትኩረት እያገኘ በመጣው ጎንደር ጥምቀት በሚከበርበት ሰዓት እንዲዘጋጅ የተመረጠውም ጎንደር በዚህ ወቅት ያላት ድባብ ከመቼውም ግዜ የበለጠ ደማቅ ስለሆነ ነው፡፡ በሌላ ቋንቋ መንግስት የጥምቀት በዓልን የሚያዘጋጅበት አግባብ የለም ይሁን እንጂ ጥምቀት ለሃገራችን ቱሪዝም ልማት እንዲሁም ለመልካም ገጽታ ግንባታችን ያለው ፋይዳ ከፍተኛ በመሆኑ በተሳካ ሁኔታ እንዲከናወን ከመንግስት የሚፈለገውን ድጋፍ መንግስት ያደርጋል፡፡
  አንድ አድርገን መንግስት ታቦታቱ ከጥር 4 ጀምሮ እስከ ጥር 10 ቀስ በቀስ እንዲወጡ የሚል መመሪያ አስተላልፎ በአባቶች ጽናት ሊቀለበስ ችሏል በሚል መንግስት በእምነት ጉዳይ ጣልቃ ገብቶ ቀኖና ለማስጣስ እንደሞከረ የተላለፈው መረጃ ለብዙ መረጃው ለሌላቸው ምእመናን እውነት መስሎ ሊሰማቸው ቢችልም መረጃው ግን ጭፍን ፖለቲካን በኃይማኖት ሽፋን ለማራገብ የተደረገ መሰሪ ተግባር መሆኑን ልንገልፅ እንወዳለን፡፡
  መንግስት ይህን በዓል አስታኮ ተጨማሪ ቱሪዝም ምርት ሲፈጥር መርሁ ለህብረተሰቡ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ነው፡፡ ሆኖም በዓሉ የጥምቀትን ድባብ እንዳይነካ በሚል እስቤ ከጥር 10 ከተራ እስከ ጥር 12 የቃና ዘገሊላ የሚካኤል ታቦት እስኪገባ ተጨማሪ ዝግጅት እንዳይኖር በማድረግ መርሃ ግብር ነድፏል፡፡ በዚህ ሁሉ እንቅስቃሴ ውስጥ ደግሞ ቤተ-ክህነት የአዘጋጅ ኮሚቴው አብይ ኮሚቴ አባል በመሆን ከጅምሩ ጀምሮ እኩል ባለድርሻ ሆና የተካፈለችበት ዝግጅት ነው፡፡ እውነታው ይሄ ሆኖ ሳለ አንድ አድርገን ከስሙ በማይገጥም ተግባር ተሰማርቶ ይህንን መረጃ በማስተላለፍ የተሰማንን ቅሬታ እየገለጽን ልናርመው ተገደናል፡፡ ጉዳዩን በሚመለከት የሚመለከታቸው የቤተክርስቲያን አባቶች ተጨማሪ ምላሽ እንደሚሰጡ ልንገልጽ እንወዳለን፡፡
  የጎንደር ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም መምሪያ

  ReplyDelete
 24. የተከበሩ ሰይፈ ገብርኤል????

  ዳግማዊ አናስሞስ እንዳሉት ክርስትና የሕይወት/የመዳን ጉዳይ እንጂ የታቦት ወይም የኢትዮጵያ ታሪክ ጉዳይ ስላልሆነ በክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ ወይም በመስቀሉ ቃል ላይ ብቻ ብናተኩር ተጠቅመን እንጠቅማለንና በዚህ ብንስማማ እጅግ ይሻለናል::

  በዚህ ከተስማሙ ቤተሰብ ነና ለዛሬ ያለኝን እንሆ:

  'በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ' (ፊልጵ 2:12)

  ቃሉ ስለሚል በመጀመሪያ መዳናችንን በሚከተለው መንገድ ማረጋገጥ ይኖርብናል:

  1) ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል' (ሮሜ 3:23)
  ስለሚል ሁላችንም የአዳም የዘር ኃጢአት እንዳለብን ማመን ይኖርብናል::

  2) ኃጢአት ቅጣት እንዳለው ማወቅ 'የኃጢአት ደሞዝ ሞት ነውና' (ሮሜ 6:23)
  መረዳት ይኖርብናል::

  3)የአዳምን ዘር በሙሉ ከዚህ ሞት የሚያድን ንጹህ/ቅዱስ ደም መፍሰስ ስላለበት ጌታ ሰው ሆኖ
  የሁላችንን ኃጢአት በመስቀል ሞት ተሸክሞ ከሞት አዳነን ወይም ከገነት የወጣውን ያዳም ዘር ወደ
  መጀመሪያ ቦታው መጋረጃውን ቀዶ በጸጋው እንዲገባ መንገድ ሆነለት::

  'መዳንም በሌላ በማንም የለም እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች
  ሌላ የለምና::' (የሐዋ/ሥራ 4:12) ስለሚል

  'እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ' (ማቴ1:21)

  'በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር
  አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና::' (ዮሐ3:16)

  'ልጁ ያለው ሕይወት አለው የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም::'
  (1ዮሐ5:12)

  በእነዚህ ጥቅሶች መሰረት ማንነታችንን በማውቀና ንስሃ በመገባት ጌታን የህይወታችን ጌታና ንጉስ አድርገን ወደ ልባችን በሥራ ሳይሆን በእምነት ብንቀበለው/ብንጋብዘው (ዮሐ1:12) የእግዚአብሔር የልጅነት ስልጣን በዳግም መወለድ (ዮሐ3:3-5)እናገኛለንና በዚህ ጉዳይ ላይ ብናተኩር ይሻላል::

  .......ወዘተ.......

  የሕይወት ጉዳይ የሆነውን ዋና ነገር ትተን በማይጠቅምና ሕይወት ሊሰጥ በማይችል ርእሰ ጉዳይ ላይ ላጠፋነው ከንቱ ጊዜ ጌታ ሁለታችንንም ይቅር ይበለን:: አሜን::

  ሰላም ይሁኑልኝ

  ሰላም ነኝ

  ReplyDelete
 25. ሠይፈ ገብርኤልFebruary 8, 2012 at 5:20 PM

  ክርስቶስን በማመን እህቴ ለሆንሽ ሰላም
  ያሳለፍነው ጊዜና ሰዓት ሁሉ ከንቱ አልነበረምና አትጸጸቺ ፤ አንቺ እኔን ፣ እኔ ደግሞ አንቺን ለማሳመን ባደረግነው የሃሳብ ልውውጥ ብዙ ስላነበብኩ ፣ በግሌ እጅግ ብዙ ተምሬበታለሁ ፡፡ ኢየሱስን በማመን ከዕድሜዬ አንጻር እቀድም ይመስለኛል ፤ በስሙ በማመን በኩል ደግሞ የሚፈጠረውን ልዩነት ባላውቅም ፣ ለጊዜው ሁለታችንም የኢየሱስ ተከታይ ባሮች ነንና ልዩነት አናድርግ ፡፡ በተረፈ ግልጽ እንዲሆኑ በማለት አንቺ ከወንጌል እንደጠቀስሽልኝ ሁሉ እኔም ከወንጌል ለማሳወቅ የታገልኩትን ለማስነበብ አዘጋጅቼአለሁ ፡፡

  ታቦት ምን ማለት ነው?
  ታቦት = ዐሠርቱ ቃላት የተጻፉባቸው ኹለት ጽላቶች በውስጧ ያሉባት ከዕንጨት የተሰራና በወርቅ የተለበጠ ሣጥን ነው ፡፡
  የአምላክ ስምና የቅዱሳን ስም በላዩ ይጻፍበታል ፡፡ ማንም በየሜዳው ሳጥን እየሰራ ታቦት እንዳይል ፣ ታቦትን ታቦት የሚያሰኘው ከአምላክ ስም በተጨማሪ ፣ እግዚአብሔር የፈቀደላቸውና የመረጣቸው ፣ እሱንም ለማገልገል ራሳቸውን የካዱና የተሾሙ አባቶች በጾምና በጸሎት ታቅበው እየኖሩ በአብ ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ ስም መባረካቸው ነው ፡፡ ታቦት የሚለው ቃል የግዕዝ መሠረቱ ቤተ ሃደረ የሚለው ሲሆን ትርጓሜውም የእግዚአብሔር ማደሪያ ማለት ነው ፡፡
  ታቦተ ጽዮን = በዳዊት ዐምባ የነበረው ታቦት ሲሆን ኋላ ላይ ግን በሰሎሞን ልጅ አማካኝነት ወደ ኢትዮጵያ መጥታለች ተብሎ በክብረ ነገሥት መጽሐፍ ተመዝግቧል

  ታቦት ምን ጥቅም አለው?
  - በኦሪት ዘመን እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ወይም ለመኖሩ ምልክት ፣ ለሙሴ ደግሞ ከፈጣሪው ጋር መገናኛውና መነጋገሪያው መንገድ ነው ዘጸ 25 ፡ 22
  - በአዲስ ኪዳን ደግሞ ሥጋና ደሙን ለመፈተት /ለመቁረስ/ ፣ የሥጋ ወደሙ መቀመጫ ፣ መከበሪያ ፣ ዙፋኑ ነው ፡፡ ሥጋወ ደሙ የኢየሱስ ተአማኒ ስጋና ደም ፣ ህይወትም የሚሰጠን ነው ብለን ስለምናምን በሻይ ጠረጴዛ እንደ ቁርስ አይቀርብም ፣ እንደ ፋሲካ ቂጣም ሁሉም እንደፈቀደ አይቧጨቀውም ፤ ሥርዓትና ክብር ባለው መልኩ ፣ ሃይማኖታዊ ከበሬታው እንደተጠበቀ ቤተ ክርስቲያናችን ለሚያምኑና ለተዘጋጁ ሁሉ ታቀብላለች ፡፡

  ታቦትን ለምን ጣዖት ማለት አንችልም?
  ታቦትንና ሥርዓቱን የጀመረና የፈቀደ እግዚአብሔር በመሆኑ ነው ፡፡ እግዚአብሔር የምናመልክበት ጣዖት ሰጠን አንልም ፡፡
  - ዘጸ 31 ፡ 2 – 3 ባስልኤል የተባለውን ሰው ታቦት እንዲሰራ እንደመረጠው ፣ ጥበብንና ማስተዋልን ሁሉ እንደሰጠው መንፈሱንም እንደሞላበት ይመሰክራል ፡፡
  - ዘጸ 31 ፡ 18 እግዚአብሔር ከሙሴ ጋር የተናገረው በፈጸመ ጊዜ በእግዚአብሔር ጣት የተጻፈባቸውን ጽላቶች ሰጠው
  - 32 ፡ 16 ጽላቶቹም የእግዚአብሔር ሥራዎች ነበሩ እያለ በተደጋጋሚ የእሱ ፍሬ እንደሆኑ ይናገራል ፡፡ ስለዚህም ብርሃንና ጨለማ እንደማይዛመዱ ፣ ታቦትና ጣዖትም ስምምነት የላቸውም /ጰውሎስ የተናገረውን ሳልጨምር/ ፡፡

  የታቦት ሃይማኖታዊ ምሳሌነቱ /አንደምታ/ ምንድር ነው?
  - በዘጸአት 32 ፡ 15 ሙሴ እግዚአብሔር የሰጠውን የምስክር ጽላቶች ይዞ ከተራራው /ከከፍተኛው ሥፍራ/ ወረደ ፡፡ ይላል
  በቁጥር19 - 20 ደግሞ ሙሴ ወደ ሰፈሩ ሲቀርብ ጥጃና /ጣዖቱን/ ዘፈኑንም አየ ፤ ሙሴ በዚህም በመቆጣቱ ጽላቶቹን ጥሎ ሰበራቸው። የሠሩትንም ጥጃ ወስዶ በእሳት አቀለጠው፥ እንደ ትቢያም እስኪሆን ድረስ ፈጨው፥ በውኃውም ላይ በተነው ፡፡ ይኸን የሙሴን ታሪክ ፣ ኦሪቱ በአዲስ ኪዳን ለሚፈጸመው ትምህርት ወይም ጥላነቱን ሲያስረዳን ነው ብለው ሊቃውንቱ ይተረጉሙታል
  1. የታቦቱ ከተራራ መውረድ የኢየሱስ ከሰማየ ሰማያት የመውረዱ ተምሳሌት ነው
  2. የታቦቱ በጣዖቱ ላይ ወድቆ መሰበሩ ደግሞ ኢየሱስ ኃጢአታችንን ለመደምሰስ እንደሚሞትልን ማስረዳቱ ነው
  3. የጣዖቱ መሰበር ደግሞ የሰይጣን መደምሰስ የማብሰር ምሳሌ ነው

  ይቀጥላል

  ReplyDelete
 26. ሠይፈ ገብርኤልFebruary 8, 2012 at 5:24 PM

  የተሰጠው ታቦት አንድ ሆኖ ሳለ ለምን እየሠራን እናባዛዋለን
  - ዘጸ 34 ፡ 1 – 7 ሙሴን እንደፊተኞቹ አድርጐ እንዲቀርጽ ስላዘዘው ፤
  ዘጸ 36 እና 37 ለመቅደስም ማገልገያ ሥራ ሁሉ ያደርጉ ዘንድ እንዲያውቁ እግዚአብሔር ጥበብንና ማስተዋልን ሰጣቸው ። ከዚህም በመነሳት ጥበቡንና ማስተዋሉን እግዚአብሔር ስለሰጠ ፣ ይኸን በመከተል ለስሙ ክብር የሚሆነውን እንሠራለን፡፡ ጥበብና ማስተዋልን መስጠት ኮፒ ራትይ ፈቃድን ማንሳት ነውና እሱን ለማገልገያ ይሆን ዘንድ መሥራት ይቻላል ፡፡ ቁጥሩን ማብዛት የተፈለገውም ለአገልግሎት እንዲያመች ታስቦ ነው ፡፡ የቀደመው የተሰራው ከአንድ ሚሊዮን ለማይበልጥ ህዝብ ነበር ፤ አሁን የህዝብ ቁጥሩ እጅግ ብዙ ነው ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ለአገልግሎት ሲባል በየቋንቋው በብዛት እንደተሚዘጋጀው ለማለት ነው ፡፡
  - ኤር 23 ፡ 23 የቅርብ አምላክ ነኝ እንጂ የሩቅ አምላክ አይደለሁም ይላልና አገልግሎቱ ኀብረተሰቡ በሚገኝበት አካባቢ አምልኮውን እንዲያካሂድና ለማመቻቸት ፣ ልቦናውን ወደ ሃያሉ እግዚአብሔር እንዲያደርግ ለማገዝ በየአጥቢያው ታቦትና ቤተ ክርስቲያን ይታነጻል ፡፡ ይህ ባይደረግማ ኖሮ ኢየሩሳሌም መጓዝ ግድ ይሆን ነበር /ስለ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ሥራ 8 ፡ 27 – 38/ ይተርካል ፡፡
  - በሚልከ 1 ፡ 11 “ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፤ በየስፍራውም ለስሜ ዕጣን ያጥናሉ፥ ንጹሕም ቍርባን ያቀርባሉ፤ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር” በማለት በየሥፍራው እሱን ማመስገኛ እንደሚኖር በትንቢቱ ቃኝቶታል ፡፡ የጌታ ሥጋና ደም የሚጠበቀው ወይም የሚቀርበው በመቅደሰ ነው ፡፡ መቅደሱ ባለበት ደግሞ ስሙን የያዘው ታቦት አለ ፤ ስለዚህም ስለስሙ ዕጣን በየሥፍራው ይታጠናል እንላለን፡፡

  ኢትዮጵያ የሚለውን አገር እግረ መንገዴን ከማውቀው ለመተንፈስ ፤ በመጽሐፍ ቅዱስ የተጠቀሰውን ለማብራራት ከግሪክ ቃል ትርጓሜ በመነሳት ለማካላል ተሞክሯል ፤ በአብዛኛው የሚስማሙበት ግን ከግብጽ በታች በአባይ ዙሪያ ያለውን ምድር ሁሉ ነው ፤ እስከ የት እንደሚደርስ ማወቅ አልቻልኩም ፡፡ ከዚህ ወጣ በማድረግ እንደ አንዳንዶች ግምት ቀይ ባህርን አሻግረን የአረብ መሬትን ሁሉ ኢትዮጵያ ነው ብለን ለመጥራት ብንሞክር እንኳን /እንደዛ መሆኑን ባላምንም/ ፣ ከክርስትና እምነት ጋር የተቆራኘ ታሪክና አሻራ ያላት ይህችው የኛዋ የደጋ መሬት ብቻ ናት ፡፡ የመንና ሳዑዲ አረቢያ ብንገባ የዚህ እምነት ምልክቱም የላቸውም ፤ ከእኛ በታች ብንሄድም እንደዚሁ ለፍተን እንመለሳለን ፡፡ ኢትዮጵያ ይህች ለመሆኗ በሃይማኖት በጣም የሚቃረኑን እንኳን ይመሰክራሉና ሌላ ኢትዮጵያ የሚል ዓለም አንፈልግ ፡፡ ስማችን በመጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ቦታ ያለሰዎች ፈቃድ ስለገባ የሚገርማቸውና የሚቆጠቁጣቸው ሰዎች ጥርጣሬ የሚፈጥረው ጥያቄ ይመስለኛል ፡፡

  ታቦት ለምን በጻድቃንና በመልአክ ስም ይሰየማል
  ኢሳ 56 ፡ 4 - 5 “እግዚአብሔር ሰንበቴን ስለሚጠብቁ ደስ የሚያሰኘኝንም ነገር ስለሚመርጡ ቃል ኪዳኔንም ስለሚይዙ ጃንደረቦች እንዲህ ይላል ፤ በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ።”
  በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ማለቱ ስሙን የያዘው ታቦቱ የሚገኝበትን ቤተ መቅደስ ሲነግረን ነው ፡፡ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ ማለቱም የሰው ልጆች ስም ከአንድ ሰባት ትውልድ በኋላ መጥፋቱ ስለማይቀር ፣ ለአገልጋዮቹ የሚሰጣቸው ስም ግን ትውልድ ቢጠፋና ትውልድ ቢቀየርም የዘላለም ስም መሆኑን በመግለጹ ምክንያት ለመታሰቢያ እንዲሆን በስማቸው ይደረጋል ፡፡ እኛ በዚህ ለነሱ መታሰቢያ የምንሰይመው ብቻ ሳይሆን ጌታችንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስማቸው በሰማያት ባለው መዝገብም እንደሰፈረ ተናግሯል ሉቃ 1ዐ ፡ 2ዐ ይመልከቱ፡፡

  ከታቦት አገልግሎት ተሻረ የሚባለው ምኑ ነው?
  - እንስሳትን ለድኀነት መሰዋትና የደም መርጨት ስርዓት ተሽሮ ፣ እውነተኛ መዳንን በሚያስገኘው በዘላለማዊው የኢየሱስ መስዋዕትነትና ደም ተተክቷል
  - የቤተ መቅደስ አገልግሎት በሌዋውያን ዘር ብቻ የሚለው ከማንኛውም ወገን ካህናት ሊሆን መቻሉ ነው ፡፡ ከዚህ በተረፈ ግን ማቴ 5 ፡ 17 እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም ይላልና የተሻረና ያልተሻረውን ከአባቶች ጠይቀን ለመረዳት እንበርታ፡፡
  - ራዕ 11 ፡ 19 “በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ተከፈተ ፤” እዚህ ላይ በሰማይም ብሎ ሲናገር ከሰማይ ውጭ ሌላ ሥፍራ ቤተ መቅደስ አለ ማለት በመሆኑ ምድራዊ ቤተ መቅደስ መኖሩን ያረጋግጣል ፡፡

  ይቀጥላል

  ReplyDelete
 27. ሠይፈ ገብርኤልFebruary 8, 2012 at 5:32 PM

  የዘመኑ ታቦት እንደጥንቱ ኃይለኛና ቁጡ ያልሆነበት ምክንያት ምንድር ነው ? ምንም ሲያደርግ አይታይም?
  ታቦትንም እንደማንኛውም ንብረት ይሰረቃል ፤ ለምን?
  መጽሐፍ ቅዱስም እንደሚሠረቅ ይናገራል/1 ሳሙ 5 ፡ 1/
  - የኦሪቱ ዘመን ፣ ዘመነ ፍዳ ወይም ዓመተ ኩነኔ ስለነበር ቅጣቱ ከመቅጽበት ይፈጸም ነበር ፤ ሰዎችን በለምጽ ፣ በቁስል ፣ ብቻ በተለያየ መንገድ ይቀስፋቸው ነበር ፤ ወንጀለኛም ሲገኝ ህብረተሰቡ ሁሉ በራሱ ምህረት የለሽ ነበር ፣ ምንም ይቅርታ የለውም ፤ ልጅ ፣ ሚስት ፣ አባት ወይም እናት አይባልም ፡፡ ኃጢአት ሞትን ይወልዳልና ፡፡
  - ስሙን በኃጢአተኛ አፋችን እንደፈቀደን እንድንጠራው ያሳወቀንና የፈቀደልን አምላክ ይመስገንና ይኸ የኛ ዘመን ግን ፣ ዘመነ ምህረት ስለሚባል የንስሃ ጊዜን ይሰጠናል ፤ ኃጢአትን ከሠራን በመጸጸት ንስሃ እንድንገባ ያስታምመናል ፤ ስለዚህም ታግሶናል ይባላል እንጅ ሰንፏል ወይም ድል ሆኗል ፤ አቅሙን አጥቷል አይባልም፡፡ የጡንቻ ማነስና ማደግ ጉዳይ አይደለም ፤ ኢየሱስ በፈቃዱ እጁን ሰጠ እንጅ ችሎታ ጐድሎት አልተማረከም ማቴ 5 ፡ 26 ፤ ኃይለኛ ሲታገሰን ያሸነፍነው የሚመስለን እኛን ደካሞቹን ነውና ፡፡

  ለሰራችሁት ታቦት ስለምን ትሰግዳላችሁ?
  - እያሱ 24 ፡ 15 እኔና ቤቴ እግዚአብሔርን እናመልካለን እናንተ የምታመልኩትን ምረጡ በማለት መስክሯል ፤
  - እያሱ 7 ፡ 6 ኢያሱም ልብሱን ቀደደ፥ እርሱና የእስራኤልም ሽማግሌዎች በእግዚአብሔር ታቦት ፊት እስከ ማታ ድረስ በግምባራቸው ተደፉ፤ በራሳቸውም ላይ ትቢያ ነሰነሱ። ከላይ እግዚአብሔርን ብቻ እንደሚያመልክ ለታቦት ሲሰግድ መዋሉን ልብ በሉት ፡፡ ለታቦት መስገድ ፣ በታቦቱ ላይ ስላለው ቅዱስ ስም መስገድ ነው ፤ የአክብሮት ነው፡፡
  - በወንጌልም በዕብ 13 ፡ 7 የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው በማለት ያዘናልና እንደ ኢያሱ ሁሉ እኛም በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ለአክብሮቱ እንሰግዳለን ፡፡ እንዲሁም በፊሊጵ 2 ፡ 10 ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ /እግዚአብሔር/ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥ በማለቱ ስሙ ባለበት ታቦት ፊት እንሰግዳለን

  ኢሳ 66 ፡ 1 ሰማይ ዙፋኔ ምድርም ደግሞ የእግሬ መርገጫ ነች ያለን አምላክ ስለፈቀደ ብቻ በድንግል ማርያም ፣ ትንሽ ማህጸን ለመወሰን ቻለ ፤ ስለፈቀደ ከሰው ባነሰ እንስሳ በውርንጫ አህያ ተቀመጠ ፤ ስለፈቀደም ክብሩን በታቦት ላይ አኖረ ፤ ስለዚህ ስለዘረዘርኩት ሁሉ በፈቀደውና በጀመረው ታቦትም ምክንያት አመልከዋለሁ ፡፡ ትምህርቱ ፍጹም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው ፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስ ያፈነገጠ አንድ ልማድና ሥርዓት እንኳን አልጠቀስኩም ፡፡

  በተረፈ በምትችይው ሁሉ ኢየሱስ የሚባል አምላክ መኖሩን ለማያውቁ ፣ ኢየሱስ እግዚአብሔር መሆኑን ለማያምኑ ፣ ሞትና ትንሳዔውን ለሚክዱ ፣ ስሙንና አምላክነቱን ግለጭላቸው ፡፡ ይኸ እኔም በአቅሜ በአጋጠመኝ ሁሉ የምዳክርበት ግዴታዬ ነውና የእሱ ፈቃድና ችሮታ በያለንበት ከሁላችንም አይለየን

  አመሰግናለሁ
  ለስሙ የምትታገሉትን ሁሉ እግዚአብሔር ጉልበት ይሁናችሁ

  ReplyDelete
 28. 'ወንድሜ' ሰይፈ ገብርኤል!

  በዚህ ጉዳይ ላይ የሥራው ባለቤት የሆነው የምህረት አምላክ እግዚአብሔር በማይለወጥ ቃሉ:

  1)ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር (1ጴጥ 4:11)ስለሚል በዚህ ብንመራ?

  2)እኔ ያዘዝኋችሁን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ትጠብቃላችሁ እንጂ ባዘዝኋችሁ ቃል ላይ
  አትጨምሩም ከእርሱም አታጎድሉም (ዘዳ 4:2)ስለሚል በዚሁ ብንመራ?

  3)እኛ ከጨለማ የተነሳ በሥርዓት መናገር አንችልምና
  የምንለውን አስታውቀን (ኢዮብ 37:19) ብለን ወደ ራሱ ብንጮህ?

  4)መጻሕፍትን ያስተውሉ ዘንድ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው (ሉቃ24:45)

  5)በእርግጥ ከእግዚአብሔር ጋር ስትጣሉ ምናልባት እንዳትገኙ (ሐዋ 5:39)

  በማለት ስለሚመክረንና ስለሚያስጠነቅቀን ሁላችንም እንኳን ያለተጻፈውን ጨምረንበት ይቅርና በተጻፈልንም መኖር አቅቶናልና ብናስተውል መልካም መልካም ነው::

  ስለዚህ በጽሑፎዎ ላይ:
  *ሙሴ ከተራራው ይዞት የወረደውና የተሰበረው ሁለቱ ጽላቶች እንጂ ታቦቱ አይደለም::
  *ታቦቱ በፍልስጥኤማውያን ተማረከች (1ሳሙ4:11) ያለው ለእኔ የጠላቶቹ ጣትኦት የሆነውን ዳጎንን ብቻዎን ሊያደቅና ሊሰብር ዘመተ እንጂ ተሠረቀ ማለት አይደለም:: ማለት እርስዎ እንደሚሉት
  'እንደእኛዎቹ' ጎዶች እየተቸበቸቡ የሌቦች ማክበሪያ በመሆን አውሮፓ ሄደው ሙዚየም ተቀምጦ አልፍቀረም::
  *በኅጢአት ምክናያት እግዚአብሔር በታቦቱ በኩል ብቻ ለሕዝቡ ይገለጥ ስለነበር ኢያሱ የሰገደው በዚህ መልኩ እንደነበር ያስተውሏል
  *በአዲስ ኪዳን ግን አማኑኤል ስለሆነልን እኔ የማመልከው አምላክ በታቦት በኩል መገለጥ አያስፈልገውም በቅዱስ መንፈሱ በኩል እንጂ::

  እንግዲህ የሕይወት ጉዳይ በክርክር ማሳመንና ማመን ፈጽሞ ስለማይሆን ነጻ ሊያወጣ በሚችለው ሕያው የአምላካችን ቃል ላይ ብቻ ሁላችንም ትኩረት ብናደርግ ተርፈን እናተርፋለንና ይህንኑ ብናደርግ????

  እንደ እኔ ቤተ ክርስቲያናችን የታቦት ፋብሪካ ስፍራ ከመሆኗ ይልቅ ለሚከተላት ሕዝብ ቃሉ ላይ ብቻ ትኩረት አድርጋ ብታስተምር ኖሮ ይህ እኔና እርስዎ የምንከራከርበት መድረክና ሌሎችም ባልተፈጠሩ ነበር::

  ወደድንም ጠላንም ምድራችን የታቦትና የበርካታ በሬ ወለደ ውሸት ፋብሪካ ሆና በሁለንተናዊ መልኳ መሳቂያ ሆና አሁን ባለችበት ሁኔታ እንድትገኝ ያደረገችው (ምንም እንኳ ብዙ መልካም ጎን ቢኖራትም)ይች ዋሽታ (ከተመሰረተችበት የወንጌል መሰረት ውጭ)ዋሾ ያደረግችንና እንዲሁም የአስማተኞች የጠንቋዮች የአጋንንት ሳቢ ደብተራዎች የደጋሚዎች የነጋዴዎች የክፉዎች ወዘተ መጨዋቻ ያደረገችን ይች ቤተ ክርስቲያን ነች:: ለዚህ ደግሞ ፍቅር ብቻ ሳይሆን የሚባላ እሳት ጭምር የሆነው ጌታ የጽድቅ ፍርዱን በአጭር ጊዜ እንደሚፈርድና ወደ ትክክለኛ ክርስትና በልቅሶ የምንመለስበት ቀን ሩቅ አይሆንም:: እድሜ ብቻ ይለምኑ አብሮ ለመፈወስና የጌታን ክብር ብምድራችን ለማየት:: እንዲህ ያጋንንት መፈንጫ ሆነን እንደማንቀርና ፈጽሞ እንደማይተወን ጌታዬን አምነዋለሁ:: እባክዎት እስዎ የሚልኩልኝን ጥቅሶች እኔ እንደማነባቸውና እንደማመዛዝነው እስዎም የምልክልዎትን የጌታ ቃል ደጋግመው ያንብቧችው ያጥኗቸውም የሚያነቧቸው ስላልመሰለኝ ነውና ይቅርታ???

  የእኛዋ ጉድ ጉዳይ:
  ከአታላይቱ ከይሁዳ ይልቅ ከዳተኛይቱ እስራኤል ጸደቀች::(ኤር 3:11) ነው የሆነብን

  ምክናያቱም የአታላይ ሕይወት የማስመሰል ሕይወት(የብርሃን መልአክ በመምሰል እንደሚያታልለው) ነውና እኛም ያለወንጌል ትምህርት(በገድሎችና በድርሳናት ብቻ)ክርስቲያን ነን እያልን እራሳችንን የምናታልል አሳዛኝ ሕዝቦች!!! መችም በዚህ ጉዳይ ላይ እጅግ ነው የማዝነውና የሚቆጨኝ:: ታሪካችን የተበላሸብን የማስመሰልና በውሽት ታሪክ የከበርን-- በባዶ ጩኸት ወይኔ!!! ወዮ!! ወዮ!! ልበል እንጂ ሌላ ምን እላለሁ:: ይህ ብሶቴ ደግሞ ሴት ስለሆሆንኩ የመጣብኝ አይምሰልዎት(ነፍጠኛ እንዳሉኝ)ያገሬ ወይም የወገኔ ጉስቁልና ልቤ ውስጥ እንደ ብርድ ገብቶ ስላንዘፈዘፈኝ ብቻ እንጂ::

  በዚህ ጉዳይ ላይ

  እግዚአብሔር ጋር ሙግት አለኝና!!! በራሱ ሰምቶ ይመልስልኛል ብዬ አምናለሁ::

  የቤተ ክርስቲያናችንን ዓይኖች ጌታ ያብራ!! አሜን

  የጌታ ሰላም ለቤተ ክርስቲያናችን/ለየዋሁ ሕዝባችን ይፍጠንለት::

  አክባሪዎ

  ሰላም ነኝ

  ReplyDelete
 29. ሠይፈ ገብርኤልFebruary 9, 2012 at 7:34 PM

  1. እታለም ሰላም የተጻፈው ትንሽ ስላስደነገጠኝ አምልኮና እምነቴን እዚህ ጋ ለማወጅ ተገደድኩ፡፡ ምክንያት ቢባል ጥንቆላንና አጋንንት መሳብን እንደ ተዋህዶ ክርስቲያን መለያ ባህርይ አድርጐ ማቅረብ የግንዛቤ ጉድለት ፣ አለያም የተሳሳተ አመለካከት ሰለመሰለኝ ነውና በትዕግሰት አንቢብልኝ ፡፡
  - ይህን የሚታየውንና የማይታየውን ዓለም ያስገኘና የፈጠረ አንድ አምላክ ፣ እግዚአብሔር እንደ አለ አምናለሁ ፡፡
  - እግዚአብሔር በመለኮቱ አንድ ሲሆን ፣ የአካል ሦስትነት አለው ፤ በስምም አብ ፣ ወልድ ፣ መንፈስ ቅዱስ እላለሁ ፤
  - አብ እግዚአብሔር ነው ፤ ወልድም እግዚአብሔር ነው ፤ መንፈስ ቅዱስም እግዚአብሔር ነው ፡፡ በግብር ደግሞ አብ ወላዲ ፣ ወልድ ተወላዲ ፣ መንፈስ ቅዱስን ሠራፂ ብዬ አምናለሁ ፡፡
  - የሦስቱም አካላት መለኮት አንድ ብቻ ስለሆነ ፣ አንድ እግዚአብሔር እላለሁ እንጅ ሦስት አማልክት /እግዚአብሔሮች/ አልልም ፡፡ በስም ፣ በግብርና በአካል ሦስት ቢሆኑም አንዱ ከአንዱ አይበልጥም ፤ አንዱ ከአንዱ አይቀድምም ብዬም አምናለሁ ፡፡
  - ከሦስቱ አካላት የእግዚአብሔር ቃል የሆነው ወልድ ፣ መወለድ የግብር ባህርዩ ስለሆነ ፣ ከትስብዕት ልማድ ውጭ በድንግልና በመጸነስ ፣ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከስጋዋ ሥጋ ፣ ከነፍሷ ነፍስን ነስቶ ፣ ኃጢአታችንን ደምስሶ ከራሱ ጋር ለማስታረቅ ሲል በተዋህዶ ሰው ሆነልን ፤ በመስቀልም ላይ ስለ እኛ ኃጢአት ሞተ ፤ በሶስተኛው ቀን መቃብር ክፈቱልኝ ፣ መግነዝ ጨርቁንም ፍቱልኝ ሳይል ሞትን ድል አድርጐ ተነሣ ፤ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ ፤ በመጨረሻው ዘመን ደግሞ ለመፍረድና ለሁሉም እንደ ሥራው ለመስጠት ተመልሶ ይመጣል ብዬ አምናለሁ ፡፡
  - በስሙም ለሚያምኑት ሁሉ የእግዚአብሔር ልጅነትን ፣ ድኀነትንና የዘላለም ሕይወትን ይሰጣቸዋል ብዬ ስለቃል ኪዳኑ አምናለሁ ፡፡

  ከዚህ ውጭ የሸማ አለባበስ በየፈርጁ እንደሚሆን ሁሉ በአምልኮ ሥርዓት መለያየት የምንችል ይመስለኛልና ጥንቆላንና አጋንንት መሳብን አውርጃቸው ፤ ለአእምሮየ አይመቹኝም ፡፡ ሰዎች ቢኖሩ እንኳን የቤተ ክርስቲያን ዶግማና ቀኖና ስለማይሆኑ እንደ ቤተ ክርስቲያኗ ሥርዓት ቆጥረን በጅምላ አንውቀስባቸው ፡፡ የአሁኑ ዘመን ሰዎች ገንዘብ ለማግኘት ብለው የጎጃሙን ዘፈን መዝሙር እንደሚሉን የብልጣ ብልጥ ጨዋታና ሰዎችን ማታለያ ፣ በግለሰቦች ልናይ እንችል ይሆናል እንጂ ከቤተ ክርስቲያን የሃይማኖት ትምህርት ዘርፍ የሚቆጠር ተግባር ነው ማለት አንችልም ፡፡ ለዚህ የሚቆሙና የሚከራከሩ ካሉ ከመስመር የወጡና ያፈነገጡ ስለሚሆኑ እኔም አብሬሽ እቃወማቸዋለሁ ፡፡ ሌላው ምናልባት የቤተ ክርስቲያኗን ስም አጥፍተው ማስጠፋት እንጀራና ዳቦ የሆናቸው ፣ በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ስም እያሉ ሊያምታቱ ይችሉ ይሆናል ፡፡ ይህንንም ለመገመት የተገደድኩት አስመሳይና ሰርጐ ገቦች ፣ ሆዳምና የቀን ጅቦችን በተለያየ መልክና ስልት ማየቱ በዘመናችን እየተለመደ በመምጣቱ ምክንያት ብቻ ነው ፡፡

  2 - የሊቃውንቱን ትርጓሜና ትምህርት ፣ ሃይማኖቱን እስካላፋለሰ ድረስ መቀበሉ መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳት ይጠቅማል እንጅ አይጐዳንም ፡፡ ዓይናችንን ጨፍነን ድንጋይ የሆነውን ሃሳብ አንወርውር ፡፡ ጢሞ 3 ፡16-17 የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል ይላልና ፣ መንፈሳቸውን አስቀድመን እንመረምር ፡፡ የትርጓሜ መጽሐፍት አለመገኘታቸው ነው እንጅ ፣ ሁሎችም ቢገኙ የመጽሐፍ ቅዱስን እውነታነት ለማረጋገጥ ያግዛሉ እንጅ ወደተለየ ባዕድ አምልኮ አይወስዱንም ፡፡
  ሐዋርያት ከጻፉት መልዕክታት ውጭ “በአፍም እንዳስተማርናችሁ” የሚል ቃል መናገራቸው በጽሁፍ ካሰፈሩት ውጭ ተጨማሪ በቃል ያስተላለፉት ትምህርትም እንደነበረ ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ሳይጻፍ አስቀድሞ የሚያጠኗቸው መጽሐፍት እንደነበሯቸው ከጳውሎስ “የብራና መጽሐፎቼን ይዘህልኝ ና” ትእዛዝ መገመት እንችላለን ፡፡ ዮሐንስም በወንጌሉ ኢየሱስ አምላክ እንደሆነ ለማሳመን የሚያስችለውን መርጦ እንደጻፈ ገለጸ እንጅ በጠቅላላው የሃይማኖትን ነገር ለመጻፍ ቢሞከር … አይበቃውም ነበር ነው ያለን ፡፡ ነገር ግን እነዚያን የተተውት ትምህርቶችና ያጠኗቸው የነበሩ መጽሐፍት የትኞቹ እንደሆኑ ከማሰብ በስተቀር ፣ መገመቱ ወይም ማግኘቱ እንደ ራዕይ የራቀ ይመስለኛል ፡፡

  እስቲ አንቺ በምትረጂው ስልት ከዚህ በታች የሚገኙትን አምስት ጥያቄዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ አንድም መስመር ሳትወጭ ለመመለስ ሞክሪ ፤ እንዲህ ዓይነት መቶ ጥያቄዎችን ማቅረብ እችላለሁ ፤ ነገር ግን ከጥቅማቸው ጉዳታቸው ያመዝንብኛልና ተጨማሪ አንጠያየቅ ፤
  1 - ኢየሱስ ምድራዊ አባት እንደሌለው እየታወቀ በማቴዎስና በሉቃስ ወንጌል የዮሴፍ የዘር ሃረግ ስለምን ይቆጠራል?
  2 - በመጽሐፈ ኢዩብ 1፡2 ሰባት ወንዶች ፣ ሦስትም ሴቶች ልጆች ተወልደውለት ነበር ፡፡ እነዚህም ደግሞ በኢዩብ ፈተና ወቅት በሙሉ ሞተዋል ፡፡ የፈተና ጊዜውን በጽናት በማሳለፉ እግዚአብሔር በነበረው ፋንታ ሁለት እጥፍ አድርጎ ለኢዮብ ሰጠው /42 ፡ 11/ ይለናል ፣ ዝርዝር ቁጥራቸውን ሲያሰፍር ግን እንደ ቀድሞው ሰባት ወንዶችና ሦስት ሴቶች ልጆች ሆኑለት ይላል በ42 ፡ 13 ፤ ታድያ እንደ ቃሉ የተጠበቁት ተጨማሪ ሰባት ወንዶችና ሦስት ሴቶች ልጆች የት ሄዱ?
  3 - በይሁዳ 14 – 15 የተጠቀሰው የማገናዘቢያ የትንቢት መጽሐፍ የት ነው የሚገኘው
  4 - የአዳም ልጆች የታወቁና ስማቸውም የተጠቀሱ ሆኖ ሳለ የቃየል ሚስት ከየት ዓለም መጣች /እንደ ሔዋን ተፈጥራ ይሆን/
  5 - በዘሌ 2ዐ፡1ዐ ማናቸውም ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ወይም ከባልንጀራው ሚስት ጋር ቢያመነዝር ሁለቱም ፈጽመው ይገደሉ ይላል፡፡ በዮሐ 8፡3 - 5 በምንዝር የተያዘች ሴት ለኢየሱስ አመጡለትና ምን ትላለህ ብለው ጠየቁት ይላል፡፡ ወንድየው አመንዝራ የት ገባ? ለምንስ ለኢየሱስ የፍርድ መመዘኛ አብሮ አልቀረበም?
  ይቀጥላል

  ReplyDelete
 30. ሠይፈ ገብርኤልFebruary 9, 2012 at 7:40 PM

  በተረፈ እኛ በለስላሳ ወንበር ላይ ተቀምጠን ይቆረቁረናል ፤ ቁርስ በልተን ለምሳ እስከምንደርስ እንቸገራለን ፤ አንድ ኪሎ ሜተር እንኳን ያለለስላሳ ጫማ መሄድ አይሆንልንም ፤ የምንተኛበት የጠፈር ሰዎች ፍርናሽ የመሰለውም አንዳንድ ቀን አይመቸንም ፤ በአዳሪ ትምህርት ቤት ነገረ ሃይማኖትን ለመማር የገቡት ሳይቀሩ ስለሚጐድሏቸው ነገሮች ብዙ ይጨነቃሉ ፡፡ ይህችን ቤተ ክርስቲያንና ይህችን ሃይማኖት የተማሩዋትና ያቆዩዋት አባቶች ግን ….. መንፈሳቸው ይግለጽልሽ እንጅ መዘርዘር አልሞክርም፡፡ እነሱ ያዩና ይጓዙ የነበረው እንደ እስጢፋኖስ የሰማዩን ጽድቅ እንጅ ምድራዊውን ተድላ ጐምጅተው ፣ ሹመትና ዝናን እናገኝ ብለው አልነበረም ፤ እግዚአብሔር ስለፈቀደው እኒያ የተንከራተቱላት ፣ የተንገላቱላት እምነት ፣ ዛሬ በጥቂት ሆድ አምላኪዎች ሰበብ መወገዝና መወቀስን ልማድ አደረገች ፤ እንደ እኔ ዓይነቱም ያለ አዋቂ በየሥፍራው ሊጫወትባትና ሊቀልድባት ቻለ ፡፡ አንድ ወንድም የዛሬዎቹን ደራሲዎች መጽሐፉን ከመጻፍ በፊት የሚጨነቁት ስለሚያስተላልፉት ትምህርትና የነፍስ ማዳን ሥራ ሳይሆን ፣ ስለ ትርፍና ኪሣራቸው ነው ፤ ሰባኪው የራሱን የሥራ ብቃትና ጥራት የሚለካው በተሰበሰበለት አድማጭ ቁጥር እንጅ ስንት ሰው ትምህርቱ ገብቶት ዳነ በሚለው አይደለም ብሎ ነበር፤ ይህን ያለው ያለ ምክንያት አይምሰልሽ የካሴት ትምህርት የወጣ እንደሁ የገዥውን ብዛት የሚያሰላው በአድማጩና በተከታይ ቁጥር ስለሆነ ነው ፡፡ ይኸ ደግሞ ውድድርንና መመቀኛኘትን በመውለዱ ጉዞአቸው ወደመጠፋፋት ፣ እኛንም ደግሞ የሚከፋፍል ሆነ ፡፡

  ምናልባት በመሃከላችን የልሳን መለያየት እንዳይኖር በመጠራጠሬና ሳንረዳው እንዳናልፍ በማለት ይህን ታላቅ ትዕዛዝ እንዲገባን በተለያየው ሞክሬአለሁ ፡፡
  ማቴ 7 ፡ 1 – 5 “እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ፤ በምትፈርዱበት ፍርድ ይፈረድባችኋልና፥ በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ ይሰፈርባችኋል። በወንድምህም ዓይን ያለውን ጉድፍ ስለምን ታያለህ፥ በዓይንህ ግን ያለውን ምሰሶ ስለ ምን አትመለከትም? ወይም ወንድምህን። ከዓይንህ ጉድፍ ላውጣ ፍቀድልኝ እንዴትስ ትለዋለህ? እነሆም፥ በዓይንህ ምሰሶ አለ። አንተ ግብዝ፥ አስቀድመህ ከዓይንህ ምሰሶውን አውጣ፥ ከዚያም በኋላ ከወንድምህ ዓይን ጉድፉን ታወጣ ዘንድ አጥርተህ ታያለህ።”

  ትርጉም “ኢትኰንኑ ከመ ኢትትኰነኑ ፤ እስመ በኵነኔ ዘኰነንክሙ ትትኴነኑ አንትሙ ወበ መስፈርት ዘሰፈርክሙ ይሰፍሩ ለክሙ ፤ ለምንተ ትሬኢ ሐሠረ ዘውስተ ዐይነ እኁከ ወኢትሬኢ ሠርዌ ዘውስተ ዐይንከ ኢታቤይንኑ ፤ ወእፎ ትብሎ ለእኁከ ኀድገኒ አውፅእ ኃሠረ እም ውስተ ዓይንከ ወናሁ ሠርዌ ውስተ ዓይንከ ፤ አመደልው አውፅእ ቅድመ ሠርዌ እምውስተ ዐይነ እኁከ ፡፡”

  ትርጉም “ብዝፈረድኩምዎ ፍርዲ ኺፍረደኩም ብዝሰፈርኩምሉ መስፈሪውን ኪስፈረልኩም እዩ እሞ ከይፍረደኩም ኣይትፍረዱ ፡፡ ኣብ ዓይንኻ ዘሎ ጒንዲ ዘይፈለጥካስ ንምንታይከ ኣብ ዓይኒ ሓውካ ዘሎ በሰር እትርኢ ፣ ወይስ ከመይ ጌርካ ንሓውካ ካብ ዓይንኻ በሰር ከውጽ ኣልካስ ሕደገኑ ትብሎ ፣ እንሆ ጒንዲ ኣብ ዓይንካ ኣሎ ፡፡ ኣታ ግብዝ ቅድም ካብ ዓይንኻ ጒንዲ ኣውጽእ ፡፡ ሽዑ ኻብ ዓይኒ ሓውካ በሰር ንምውጻእ ኣጸቢቕካ ትርኢ ፡፡”

  - ከዚህ በተረፈ እንደ መልካም አካሄድ የምቆጥረው ፣ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርትና ሃይማኖት የተሳሳተ የመሰለው ማንኛውም ሰው ፣ ቄስና ዲያቆኑ ብቻ አይደለም ፣ ሌሎቹም ቢሆኑ እንደዛ ከተሰማቸው ፣ በመለየት ወደሚያምኑበት ወገን መጠጋት ይገባቸዋል እንጅ ፣ የግድ እኔን ተከተሉኝ ፣ እንደ ኢየሱስ የሆኑ ያህል እኔ ዕውነትም መንገድም ነኝ በማለት ልምራችሁ ብሎ ምእመንን ማወክ አግባብ አይደለም ፡፡ ምናልባት አንዳንዶች ዛሬ የተረዱትን ስህተት ፣ ወደፊት እኛም በደረጃችን እየተገለጸልን ከመጣ ፣ በራሳችን ፍላጐት ሳይቀሰቅሱን ወደሄዱበት እንከተላቸዋለን ፡፡

  - ያዩትንና ያገኙትን ድክመት ማሳወቅ ፣ ከዶግማና ቀኖናችን ውጭ የሆነውን አሠራርና ልማድ እንዲስተካከል የቤተ ክርስቲያናችን ደንብና ህግ በሚፈቅደው መሠረት በአግባቡ መጠየቅ ፣ ጥልቅ የሆነውን የሃይማኖት ዕውቀት የደረሱበት ሊቃውንትና ጠቢባን ብቻ አይደለም ፤ የማነኛችንም ክርስቲያን ነን የምንል ሁሉ ግዴታ ነው ብዬ አምናለሁ ፡፡ ከዚህ በዘለለ ግን እኔን አስገድዶ በማሳመን ፣ በእኔ ለመጽደቅ የሚመኝና የሚሞክር ካለ የክርስትና እምነታችን አካሄድ አይደለምና ቁም እላለሁ ፡፡ የኢየሱስ ሐዋርያት እንደ ትእዛዙ በፍቅር አስተማሩ እንጅ ጦርነት አልከፈቱም ፤ አንፈልጋችሁም ሲባሉ ፣ እንደ ጌታ ፈቃድ የእግራቸውን ትቢያ እያራገፉ ወደ ሌላው ተሰደዱ እንጅ ተመልሰው ድንጋይ አልወረወሩም ፤ ችግራቸውን ለመፍታት ወደ አባቶችና ሽማግሎች አቤት አሉ እንጅ ፣ የሚዋጉበት ግንባር አልፈጠሩም /ማቴ 1ዐ፡ 7 – 14/፡፡
  ይቀጥላል

  ReplyDelete
 31. ሠይፈ ገብርኤልFebruary 9, 2012 at 7:46 PM

  ታድያ እኛ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚታየው ችግር ፣ ከየትኛው ሃይማኖት መሠረት ላይ የወጣ ቅጥል ልማድ ነው እንበል? መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል ወይስ ሌላው መንፈስ? መልሱን ለየግላችሁ አድርጉት ፡፡ እኔ በፍላጐቴ አምኘበት ወደ ሰይጣን ጐራ ለመግባት ወስኜ ከተነሳሁ ፣ አበበ ወይም ከበደ ለኔ ከኔ በላይ በመሆን ፣ አውቅልሃለሁ እንዲለኝና እንዲታገለኝ አልፈልግም ፤ የአዛኝ ቅቤ አንጓች ታሪክ ነው የሚሆንብኝ ፡፡

  የደከመውን ማበርታት ፣ ማሰተማር እንጅ ፣ በክርስቲያን ዘንድ ነቀፋ እንዳይኖር ሐዋርያው ጳውሎስ በተለያየ ወቅት አበክሮ ተናግሯል ፡፡ ምክንያት ቢሉ ግጭትና ክርክር የሥጋዊ ስሜት መገለጫዎች ናቸው እንጅ የክርስቲያን መንፈሳዊ ባህርያት አይደሉምና ፡፡ ሁሉም የሚታገለው ለአንድ አምላክ አገልግሎት እስከ ሆነ ድረስ ፣ እያንዳንዱ እንደታደለው መጠን ተግቶ ይሥራ ይለናል ፤ ስለተሰጠው ግልጋሎት ደግሞ ሁል ጊዜም ታማኝ ይሁን ፡፡ ከምላሳችንና ከጽሁፋችን ጀርባ አዝለን የምንዞረው የእኔ እበልጥና የትምክህት ችግር ፣ በመሃከላችን ሊነግስ የሚታገል መጥፎ መንፈስ ሁሉ በኢየሱስ ስም ይወገድ !!!

  አንዳንዶችን ተመልከቷቸው ፤ የእምነት ምስጢሩ በተለየ ሁኔታ የገባቸው ፣ ካልተስማሙበት በመለየት ፣ ከጦር አውድማውም ራቅ ብለው የደረሱበትንና የቃኙትን የጥበብ ፍሬና እውነታ ለህዝብ በመጣጥፋቸው በማቅረብ ፣ በቻሉት ሁሉ በማስተማር ገድል እየሠሩ እናያለን፡፡ ሌላውም ያልተስማማውና መንፈሱ ያልፈቀደለት የእነሱን አርዓያነት ቢከተል ወገንን የሚጠቅም ሥራ መሥራት ይችላል እላለሁ ፤ በአሁኑ አካሄድ ከቀጠልን ግን እኛም ሳንሠራ ፣ ሌላውም እንዳይሠራ እያወክን እምነት የለሹን እያበዛን ነው የምንሄደው ፡፡ ይህን መድረክ ስጀምርም እኔ እንደ ምእመን ትክክል አይደለም ብዬ የኰነንኩት በቤተ ክርስቲያን አውድ ላይ ጥቅስ የሚመዙት በአሽሙር ሌላው ወንድማቸውን ለመውጋትና ለማድማት የሚያልሙትን ፣ ሃይማኖቱን ከማስተማር ይልቅ የህዝቡን የቆየ የአምልኮ ሥርዓት እያንቋሸሹ ፣ እምነቱን እንደ ጣዖት የሚኮንኑትንና አዛውንቱን በአልተገራ ቋንቋ የሚተቹትን ፣ እኛ እናውቅልሃለን ባዮች ነው ፡፡

  1 ቆሮ 14 ፡ 33 እግዚአብሔርስ የሰላም አምላክ ነው እንጂ የሁከት አምላክ አይደለምና፤ በቅዱሳንም አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እንዲህ ነው።
  ይህን እምነት ካልተቀበልነው ሌላውን ምርጫ እንዲህ ይለዋል ፡፡
  ቲቶ 3፡10-11 መለያየትን የሚያነሣ ሰው ጠማማ እንዲሆን በራሱም ላይ ፈርዶ ኃጢአትን እንዲያደርግ አውቀህ፥ አንድ ጊዜ ሁለት ጊዜም ከገሠጽኸው በኋላ እንዲህ ከሚመስል ሰው ራቅ።

  በተረፈ መጽሐፍ ቅዱስን ለማገላበጥ የሚቸገር ሰው ስለማይጠፋ ይህኛው ለአፈላለግና ለማንበብ ቀላል ስለሆነ ከጠቀመ ተመልከቱት

  http://bible.org/sites/default/resources/foreign/amharic/


  አባ ሰላማዎችም ስላሰጣችሁኝ ግልጋሎት አመሰግናችኋለሁ
  ሰላምና የእግዚአብሔር በረከት ለሁላችሁም እንዲሆን ጸሎቴ ነው

  ያቆየን

  ReplyDelete
 32. If i ever get the chance, I will blow you inside your car for my unique Religion. you are one of the most hated pishop in Ethiopia!!!! SO, stop acting like you are doing well. The people here in USA are well informed in every direction about their Religion. So, once again, STOP!!!!!!

  ReplyDelete
 33. We got you will be arres soon. This not ethiopia how you blow up him, are you taliban mk ?

  ReplyDelete
 34. manen new degmo yemtafendawo..?wey medahniyalem..blachu blachu degmo alkayid honachu?.belu erfu.

  ReplyDelete
 35. የተከበሩ ሰይፈ ገብርኤል

  በመዘግዬቴ ይቅርታ እየጠየቅሁ ለጠየቁኝ ጥያቄዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ መረጃ እስከሌላቸው ድረስ አፌን ልከፍት አልፈቅድም:: ነገር ግን አንዲት ጥያቄ እንድጠይቅ ከፈቀዱልኝ እንድንኖርበት የተጻፈልንን መቼ ኖርንበትና ነው ባልተጻፈና ግምት በወለደው ነገር ላይ የምንጨነቀው? ደግሞስ ሁላችን እየተነጋገርን ያለነው ታቦት ተብሎ በተጻፈልን ጉዳይ ላይ እንጂ ባልተጻፈ ላይ አልነበረም/አይደለም::

  ለማንኛውም በአብዛኛው አባባልዎ ላይ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረጃ ስላላቸው እስማማለሁ:: የማልስማማበት ነገር ቢኖር 'ታቦቱ ወደ አገራችን መጥቶ ይገኛል' 'በርካታ ታቦታት ያሉን ሰው በአካባቢው እንዲያመልክ ነው/ከቦታ ቦታ እንዳይከራተት' 'ቤተ ክርስቲያናችን አሁን ስህተት የለባትም' 'የምትሰብከው ወንጌል ብቻ ነው' ወዘተ በማለት በሚሞግቱና የቃሉ ድጋፍ በማያቀርቡ ወገኖቼ ሃሳብ ላይ ብቻ ነውና የእኔም ሃሳብ እንደ እርስዎ ሁሉ በፍቅር እንጂ በጥልና አንዳችን በአንዳችን በመፈራረጅ አይሁን ነው እያልኩ ያለሁትና ይረዱኝ:: ከእርስዎ ጋርም ያደረግነው የሃሳብ ልውውጥ በቃሉ ላይ ብቻ እንመስረት እንጂ የጠብ እንዳልሆነ የልብ አምላክ ያውቃል:: መችም ሁላችንም የተዘጋጀልንን ሰማያዊ እርስት አብረን ብንወርስ በማለት እንጂ ሌላ ምናልባት ያልተረዳነው ድብቅ አጀንዳ እንኳ ድንገት ቢኖር የሥራው ባለቤት የሆነው ቸር አምላክ ይርዳን:: አሜን::

  በተረፍ ለጠየቁኝ ጥያቄዎች ከዚህ በላይ ያልኩት ነገር እንደተጠበቀ ሆኖ
  1) ስለ ኢዮብ ልጆች ጉዳይ የተጻፈው በኢዮብ መጨርሻው ምእራፍ ላይ እንደሰፈረው የልጆቹ
  ቁጥር ባርኮት ብዛታቸው መጀመሪያ እንደነበረው ሲሆን ሌላው ሃብት ብቻ በእጥፍ
  መሰጠቱን ከመግለጽ በስተቀር ሌላ አልተገለጸም:: እጥፍ እስከ አለ ድረስ ልጆችን
  ለምን እንደቃሉ አላደረገም የሚለው ጥያቄ ቢያስኬድም ለእኔ ግን አዳምን ክፉውንና
  መልካሙን ከምታሳውቀው ዛፍ አትብሉ አለ? ዓይናቸው እንዳይከፈት? ብሎ እንደመጠየቅ
  ነውና ከተጻፈው ባናልፍ???

  2)የሄኖክን ትቢት ጉዳይም ቢሆን እንኳን መጽሐፉ እርሱ እራሱ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ስላደረገ
  አልተገኘም እያለን ለምንድነው ከራሱ የህይወት አካሄድ ያልተማርን እንደዚህ ካለ የሞኝ ጥያቄ
  ከሚመስል ጋር ሙጭጭ እንበል? እንዲያውም እንደ እኔ መረዳት እስከ 6ኛው ትውልድ ድረስ ኖረ
  ሞተ...ኖረ ሞተ የሚለው የተለመደ አካሄድ ሞትን ሳያይ ተወሰደ በማለት የተነገረን ቃል እርስዎ
  ከሚሉት መጽሐፍ የበለጠ የሥጋን ሞት ቅስም የሠበር ትልቅ ቮሊዩም ካለው መጽሐፍ አይሻልም?

  3) ሴት ብቻዋን የዝሙት ሥራ እንደማትሠራ እየታወቀ ወንዶን ሳያመጡ ሴቷን ብቻ ይዘው
  መምጣታቸው ምናልባት አንዳንዶች እንደሚሉት ባህሉ ከወንድ ይልቅ ለሴት የሚሰጠውን
  ስፍራ የሚያመላክት ነው ቢሉም እንደ እኔ ግን የሰውን ሁለንተናዊ ድካም የሚያሳይ ምልክት
  ነው ብዬ ነው የማስበው:: የሚገርመው ግን ይህ ዓይነቱ ጥያቄ ሁሉ የማይጠቅም መሆኑን
  የተረዳው ጌታ ከሳሾችን የጠየቃቸው 'ከእናንተ ውስጥ ሐጢአት የሌለበት አለን?' የሚለው
  መሆኑ እኛን ደካሞችን ሊያስተምረን ያለው ጉዳይ ያለ ይመስለኛል:: በሕይወት ጉዳይ ላይና
  በሚጠቅመን ነገር ላይ ብቻ እንድናተኩር? አይመስልዎትም? ወንዱ አብሮ ቢጠየቅ ኑሮ
  ለእኔና ለእርስዎ ሕይዎት ልዩነት ያመጣ ነበርን?

  4) የኢየሱስ የሥጋ አባት ጉዳይም እንደላይኛው ነው:: ማርያም እራሷ አባትህና እኔ አጥተንህ
  ስንጨነቅ ብላ የተናገረችው የሥጋ አባቱ አለመሆኑን እረስታው ይመስልዎታልን? ለዚህ ሁሉ
  እኔ በበኩሌ የምልዎት ቢኖረኝ የሚከተለውን ሕያው የእግዚአብሔር ቃል ብቻ ይሆናል:-

  ''ምሥጢሩ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ነው
  የተገለጠው ግን የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ
  እናደርግ ዘንድ ለእኛ ለዘላለምም ለልጆቻችን ነው::''
  (ዘዳ 29:29)

  ደግሞም ቃሉ(የተጻፈልን) ይፈርድባችኋል ተባልን እንጂ ያለተፃፈው እንኳን ሊጠቀመን አይፈርድብንምና ሰይፈ ገብርኤል የማያሳስብ ነገር ላይ አይጨነቁ ይልቁንስ እንደ ገባኝ በተጻፈው ላይ ብዙ እውቀት ያለዎት ስለመሰለኝ (እንዳጠቃቀስዎ) በዚህ ቢያተኩሩ ተጠቅመው ይጠቅሙናልና በዚሁ ቢበረቱ??????

  ሰላም ይሁኑልኝ

  በጌታ እህትዎ

  ሰላም ነኝ

  ReplyDelete
 36. Gondar lay ketejemere hulet amet honew.geta yigesitsewna.

  ReplyDelete