Wednesday, February 1, 2012

በዲሲና በአካባቢው ሀገረ ስብከት ውንብድና እየተፈጸመ መሆኑን አቡነ ፋኑኤል ለቅዱስ ፓትርያርኩ በላኩት ደብዳቤ አስታወቁ - - - Read PDF

ማህበሩ [ማቅ] «የዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት» በሚል ስያሜ ሕገወጥ ሥራ እየሠራ ነው።
ከጀርባ እንጂ ከፊት ለፊት ምንጊዜም የማይታየው ማህበሩ [ማቅ] በአሜሪካ ከአቡነ አብርሃም ጋር በመተባበር የከፈታቸው አንዳድ አብያተ ክርስቲያናትን በማሳመጽ አቡነ ፋኑኤል እንዳይሠሩ እንቅፋት እየሆነ ነው። የውጩን ሲኖዶስ ለመኮነን እና በዚያ ውስጥ የሚገኙ ምእመናንን ለማስኮብለል ብሎም ገንዝብ ለመሰብሰብ «የሀገር ቤት ሲኖዶስና እናት ቤተ ክርስቲያን» እያለ ሲሰብክ የኖረው ማህበር አቡነ ፋኑኤልን አልታዘዝም በማለት እውነተኛ ማንነቱን አጋልጦአል። ማህበሩ የውጩን ሲኖዶስ በተሃድሶነት በመኮነን፣ ከሁለቱም አንሆንም ገልልተኛ ሆነን እንቆያለን የሚሉ አብያተ ክርስቲያናትን ደግሞ የፖለቲከኞች ምሽግ እያለ በመቃወም ሕዝብን ከከፋፈለ በኋላ የራሱን የገንዘብ ማዕከል በቤተ ክርስቲያን ስም እየከፈተ መቆየቱ ይታወቃል።
እራሱ ካቋቋማቸው አብያተ ክርስቲያናት ለገዳማት እርዳታ በሚል ሰበብ ከፍተኛ ገንዘብ ተሰብስቦ ወደ አገር ቤት ከተላከ በኋላ ካራት ኪሎ / ቤቱ ሳያልፍ በዚያው ቀልጦ ለንግድ ሥራዎች እንደሚውል ውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ። አቡነ አብርሃም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታማኝ አድርጋ ብትሾማቸውም የአንድ ቡድን ታማኝ በመሆናቸው ይህን ሁኔታ እያዩ እንዳላዩ ሆነው ትልቅ ሽፋን ሲሰጡት መቆየታቸውም ብዙዎቹን አስገርሟል። በዚህም ምክንያት በጥቅምቱ ሲኖዶስ ከሰሜን አሜሪካ ሀገረ ስብከት ተነሥተው ወደ ሀረር እንዲዞሩ ተደርጓል። በምትካቸውም ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ተተክተው እየሠሩ ይገኛሉ። ነገር ግን ማህበሩ ውስጥ ውስጡን እየቆሰቆሰ አላሰራ እንዳላቸው ይነገራል። «ማዕከላዊ አስተዳደር እፈልጋለሁ፣ ከሲኖዶስ ለሚመጣ ትእዛዝ እገዛለሁ» እያለ ራሱን ታማኝ አድርጎ ሌሎችን ሲኮንን የሚሰማው ማህበር ዛሬ ቀኑ ደርሶ «ስበዘብዝ የሚያዩኝን፣ በሥራት ሂድ የሚሉኝን ጳጳሳት ግን አልታዘዝም» ያለ ይመስላል። በመሠረቱ ማህበሩ «ማዕከላዊ አስተዳደር እፈልጋለሁ ለአገር ቤቱ ሲኖዶስ እገዛለሁ» በማለት እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን ተቆርቋሪ ለመምሰል የሚሞክረው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን እና ቤተ ክህነቱን ለማታለል እንጂ እውነተኛ ሥርዓት ፈላጊ ሆኖ እንዳይደለ ለማንም ግልጥ ነው።
ለዚህም ማስረጃችን የማህበሩ አባል ያልሆኑ ጳጳሳት የማህበሩ የቢዝነስ ማዕከላት አካባቢ ሲመደቡ አስቀድሞ «ተሃድሶ» ናቸው፣ አስተዳደር አይችሉም፣ በማለት ሕዝብን ያሳምጽባቸዋል። ለራሱ አባላት ደግሞ «የማህበሩ ጠላት ናቸው ተሃድሶን ይደግፋሉ አብራችሁ እንዳትሠሩ» በማለት ብጥብጥ ይፈጥራል። የራሱ ጥቅም ተጋሪ ለሆኑ ጳጳሳት ወደ ቢዝነስ ማዕከላቱ ተመድበው ሲመጡለት ደግሞ በከበሮና በጸናጽል በሽብሸባና በዝማሬ ይቀበላቸዋል። ወደ ሌላ ሥፍራ ሲዛወሩበት ግን በልቅሶና በዋይታ መስቀል ሸልሞ ይሸኛቸዋል ምክንያቱም የቢዝነስ ማዕከላቱ ሊጋለጡበት ነውና መራራ ለቅሶ አልቅሶ ይሸኛቸዋል ሌሎች አባቶች ወዲያው ሲመጡ ግን እንኳን ከበሮ ሊመታ በሩን ዘግቶ ባካባቢው እንኳ የሌለ እስኪመስል ድረስ እንደ ተናካሽ ውሻ ያደፍጣል። ዋሽንግተን ዲሲ ላይ በቪዲዮ ያየነው ትያትር ይኽን ነው።
አንዳድ ጳጳሳት ወደ ማህበሩ የቢዝነስ ማዕከላት ሲመደቡ ዋና ጥያቄው የሚሆነው «ቢዝነስ ያሠሩኛል አያሠሩኝም» እንጂ አስተዳዳራቸውና ቡራኬያቸው ጉዳዩ አይደለም። ቢዝነስ የሚያሠሩትን ጳጳሳት «አቋም ያላቸው፣ ሊቅ፣ ችሎታ ያላቸው፣ ቅዱስ፣ ቡሩክ ዘይመጽእ.. » በሚሉ የቅኔ ቃላት ያወድሳቸዋል። በሥርዓት ተጓዝ የሚሉትን ግን ቢያንስ «ችሎታ የላቸውም» ብሎ ስማቸውን ያጠፋል።
የዲሲ ሀገረ ስብከት በብፁዕ አቡነ አብርሃም፣ በቄስ ብርሃኑ ጎበና [የማህበሩ አባል] እና በዲያቆን ዳንኤል ክብረት የተቋቋመ ነው። ችግሩ የሚጀምረው ከዚህ ላይ ነው። ሦስቱ ምሥጢረኞች በማህበሩ ከፍተኛ ወጭ ሀገረ ስብከቱን ከከፈቱ በኋላ ጸሐፊ ሥራ አስኪያጅና ሊቀ ጳጳስ ሆነው እርስ በርሳቸው ተሿሿሙበት። ይህ ሁሉ ሲሆን መንበረ ፓትርያርኩ አያውቅም ነበር። የራሳቸውን ስትራቴጂ በማህበሩ እቅድ መሠረት ከፈጸሙ በኋላ ለስሙ እውቅና ለማስገኘት ሲባል የምሥራች ብለው ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አስታወቁ። ቤተ ክህነቱ ግን የምሥራቹንና የመሥራቾቹን ማንነት ጠንቅቆ ካጠና በኋላ ትኩረቱን በዲሲ ሀገረ ስብከቱ ላይ አደረገ፣ ማህበሩ የራሱን ጳጳስና ሁለቱን አባላት ማለት .ዳንኤልን ጸሐፊ ቄስ ብርሃኑ ጎበናን ሥራ አስኪያጅ አድርጎ የራሱ ሀገረ ስብከትና የቢዝነስ ማዕከሉ ለማድረግ እንዳቀደ በስለላም ይሁን በመላ ደረሰበት። በዚህ ምክንያት ዲያቆን ኃይለ ጊዮርጊስን ከኢትዮጵያ የሀገረ ስብከቱ የበላይ ተቆጣጣሪ አድርጎ በላዩ ላይ ሾመበት። አንዳዴ ቤተ ክህነት ውስጥም ነቄዎች አይጠፉም። በዚህ ጊዜ ማህበሩ ያዙኝ ልቀቁኝ አለ «ፓትርያርኩ ተሃድሶውን ኃይለ ጊዮርጊስን በሀገረ ስብከታችን መደቡብን፣ ኃይለ ጊዮርጊስ የተመደበው ሲኖዶሱ ሳያውቅ ነው ፓትርያርኩ ያለ ሲኖዶሱ በራሳቸው ስልጣን ሥራ አስኪያጅ መመደብ አይችሉም» በማለት ደጀ ሰላም በተባለው የጠላ መጠጫው ሲኦል ውሥጥ እንደገባች እንደ ነዌ ነፍስ እሪ አለ። አቡነ አብርሃም ብርሃኑ ጎበናን ሥራ አስኪያጅ አድርገው የሾሙት በሲኖዶሱ ፈቃድ ነው? ብለን ብንጠይቀው በቀኖና ታይቶ ነው ይለን ነበር፤ ሲኖዶሱንም እባካችሁ ከዚህ እሳት አውጡኝ በኃይለ ጊዮርጊስ ነፍሴ ተቃጥላለች አለ፤ ሲኖዶሱ አቡነ ፋኑኤልን መደበ የዚህ ደባ ዋና ተዋናይ የሆኑትን ብፁዕ አቡነ አብርሃምንም አነሳ። የአቡነ አብርሃም መነሳት ለማህበሩ ከባድ የሀዘን ቀን ሆኖ ነበር የዋለው።
ማህበሩ ግን የቢዝነስ ማዕከላቴን የኔ ደጋፊ ላልሆኑ ጳጳሳት አሳልፌ አልሰጥም በማለት እስከ አሁን እየታገለ እንቅፋት ሆኖ ይገኛል። ለዚህ ማህበር የት እንሂድለት እያሉ የሚያማርሩ ኦርቶዶክሳውያን ምዕመናን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከቱ መጥተዋል፤ ጳጳሳቱ እርስ በራሳቸው ሰላም አጥተዋል፣ ሰባክያኑ ተከፋፍለዋል፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ እንደ መንግሥት አልባ ሀገር እየተበጠበጠች ነው። ማህበሩ ግን ራሱ ገንዝብ የሚያገኝበትን መንገድ ያፈላልጋል እንጂ የቤተ ክርስቲያኒቱ እንደዚህ መታወክ ጉዳዩ አይደለም።
አቡነ ፋኑኤል እንደ ወንጌላዊም እንደ ዲፕሎማትም እየሆኑ ቤተ ክርስቲያኒቱን ገለልተኞችን ጨምሮ ወደ አንደነት ለማምጣት የሚያደርጉትን ጥረት ማህበሩ ለጥቅሙ ብቻ ብሎ በሽምቅ ውጊያ ለማክሸፍ እየሞከረ ነው። በሕገ ወጥ መንገድ ያለ ሲኖዶሱ ወይም ያለ ጳጳሱ ፈቃድ «የዲሲ ሀገረ ስብከት ሥራ አስፈጻሚ ኮሜቴ» ሆኖ ራሱን በመሾም ሕገ ወጥ ሥራ እየሠራ ነው። ማህበሩ ለማን ነው የሚገዛው? ለሲኖዶሱ ወይስ ለጥቅም ተጋሪዎቹ?

33 comments:

 1. ነገሩ በጣም ያሳዝናል ነገር ግን ለውንብድናው አባ ፋኑኤልም ዋነኛው ናቸው:: በእንግሊዝኛው ማንቆሮሪያው ጀበናውን ጥቁር ብሎ ጠራው እንደሚባለው ወይንም በአማርኛችን አመድ በዱቄት ይስቃል የሚባለው አይነት ነው:: ለማንኛውም ይህ ሁሉ ነገር የሚያሳየው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እንደ አንድ የሃይማኖት ተቋም ባዶና ሊወድቅ የቀረበ ዛፍን ይመስላል:: መምሕራኖቹ መድረክ ላይ ወጥተው ስለትልቅነቷ ቢያወሩ አይሰለቻቸውም:: ነገር ግን ቢከፍቱት ተልባ እንደሚባለው ነቀዝ የበላው ዛፍ ነው::

  ReplyDelete
 2. እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ መንግሥት በሌሎች ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ዓይኑን ተክሏል። የሚያግለበልበው ትኩሳት ስላለ ያንን ለማብረድ ሲፈልግ በፍርድ ቤት፤ ሲሻም በደህንነቱ መስሪያ ቤት፣ ሲፈልግ ደግሞ በተቃዋሚው ጎራ ትንሽ በትንሹ የሚከረክመውን ጎፈሬ ከነመቀሱ ይታየናል። ከዚህ አንጻር ማኅበረ ቅዱሳን በሚያደርገው ስልታዊ ጉዞውና በማድፈጥ ባህሪው የተነሳ ከመንግሥት ጎፈሬን የመከርከም መቀስ በመትረፍ ሕይወቱን ሊያሰነብት ችሏል። ያ ማለት ግን መንግሥት ሰዶ ከማሳደድ ይልቅ ጊዜና ቦታ እየጠበቀለት ይሆን እንደሆን እንጂ የዘነጋው ሆኖ አይደለም። ማቅም እንደድመት ጸጉሩን አለስልሶ እንቅልፍ የያዘው መምሰሉ ጊዜና ቦታ እየጠበቀ እንደሆን እንጂ ለአብዮታዊ ዲሞክራሲ መርህ እጁን የሚሰጥ ሆኖ እንዳልሆነ ይታወቃል። ሁለቱም እስከሚበላሉ ቀንን የሚጠብቁ ናቸው። ይህ መሆኑ ማቅ ለመኖር እድሜን አግኝቷል። በሌላ መልኩ ለማቅ እድሜ ማግኘትና እንዳንሰራራ መቆየት ዋናው ምክንያት የኢትዮጵያ መንግሥት ትእግስት ወይም የማቅ ስውር ሴራ አለመታወቁ ሳይሆን መንግስት በጥቅሉ እንደሚለው (ቄሶቹ፣ ሲኖዶሱ ማለት ነው)ይህን ማኅበር እራሳቸው እንዳቋቋሙት እራሳቸው ያፍርሱት ወይም ከአቅማችን በላይ ሆኗል ብለው አቤቱታ ያቅርቡልኝ እንጂ ራሳቸው በጣዱት እሳት ሲቃጠሉ እኔ ጣልቃ ገብቼ ለማብረድ ስል ለምን ወደሰዶ ማሳደድ እገባለሁ ከሚል እሳቤ የተነሳ ሊሆን ይችላል። የቄሶቹ ጉባዔ(ሲኖዶስ)ደግሞ ገሚሱ በፍትፍት አፉ የተዘጋና፣ ገሚሱ ደግሞ በገመና ድራማ ታሪክ የተመዘገበ ስለሆነ በማኅበሩ ላይ ይህንን ያህል አስጊ ነገር ያመጣበታል ተብሎ አይታሰብም። ትልቁ ቄስ ብቻቸውን ቢዘሉ በውስጥ በማቅ የቄሶቹ ብድን ተቃውሞ ሲወርድባቸው በውጭ ደግሞ በሃይማኖት የለሽነት ዘመቻው የሚዲያውን አየር ይበክላል። ጥቂት ሰራተኞች ካሉ ደግሞ እነሱ ላይ በመዝመት «መጽሐፉም ዝም፣ቄሱም ዝም» እንዲሉ ለማድረግ በቤተክህነቱ አካባቢ እነአባ ሠረቀብርሃንን በመሳሰሉ፣ በመድረኩ ላይ እነበጋሻውን በመሰሉ፣ በውጪው እነ አባ ፋኑኤልን በመሰሉ ሁለገብ መንገድ ዝም ጭጭ በማድረግ የተቀናቃኝ ጎራውን ረምርሞ «ወጣ ገባነው መንገዱ፣ ወደግሸን ሲሄዱ» በሚል ዜማ በነበረት ለመቀጠል ሁሉን ዐቀፍ እርምጃውን እያሳየ ይገኛል። በጥቅሉ ለዚህ ማኅበር እስትንፋስ ተጠያቂው ሁለት ወገን ያለው ነው። 1ኛ/ በዚህ ማኅበር መንፈስ የሰከረ ደጋፊ ቡድንና 2/ ለዚህ ማኅበር መንፈስ ዘብ የቆመው የቄሶቹ(ሲኖዶስ)ቡድን ነው። በዚህ መሀከል ቤተክርስቲያን ወዲያና ወዲህ እየተናጠች ትገኛለች።
  ከዚያ በተረፈ የማቅን ስልታዊ ማፈግፈግ ሁሉ መንግስት በስልት እንደሚጠብቀው ጥርጥር የለንም። የስልቱ የአጥፊና ጠፊ ፍጻሜው መቼ ይሆን?ለሚለው ጥያቄያችን ጊዜ ይፍታው ስንል ለቄሶቹ ብድን(ሲኖዶስ) ግን አንድ ጥያቄ ለማቅረብ እንወዳለን። እውን ይህ ማኅበር «እስኪይዝ ያነክስ ከሚለው የጅቡ ምሳሌ በዘለለ የእናንተን መረማመጃነት ይፈልግ ይሆን?»ብለን እንጠይቃቸዋለን።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ደጀ ብርሃን የሚገርመዉ ፅሁፍህን ለማሳመር ብትሞክርም ማንም ኣያምንህም ማቅ ካንተ በላይ ኣባላቱ ምእመናኑ ስራዉን ያዉቁታል ይመሰክሩለታል። አረ ለመሆኑ እናንተ የፕሮቴስታንት ርዝራዦች የማትታወቁ ይመስላቹ ይሆን እንዴ መንግስትስ እናንተን እየተከታተለ ነዉ ማቅን እማ ተከታትሎ ተከታትሎ እዉነቱን ኣዉቆታል ይብላኝ ለናንተ ኣቋማቹ ግልፅ ላላደረጋችሁ ኣድር ባዩች

   Delete
  2. ፕሮቴስታንት መሆን መብት መሆኑን ስለማታውቅ በዚህ ዓለም መንፈስ እንደሚነዳው ማኅበርህ ማስፈራራትን ስራዬ ብለሃል። «ፕሮቴስታንት ማለት ተቃዋሚ ማለት ነው» እንዴት አድርገህ ይህንን እንደሰጠኸን ባይገባንም ኢ-ቅዱስ ማኅበርን መቃወም ጥፋት አለመሆኑን ግን እንነግርሃለን። ብታምንም ባታምንም ማቅ ይፈርሳል። የሚፈርሰውም ቅዱስ ያልሆነውን ቅድስና ለራሱ በመስጠት እግዚአብሔርን በማስቀናቱ ከፖለቲካው፣ ከንግዱ፣ ከሃይማኖት ብጥብጡ፣ ከአክራሪነቱ፣ ከማስመሰሉ፣ ከማጋጨቱ፣ከማሰደዱ፣ ከማለያየቱ፣ የሰውን መብት ከመንካቱና ከኋላ ሆኖ ጎጋውን(አንተን የመሰለ፣ ያዘው፣ ቹ) እያለ ከመንዳቱ የተነሳ የመጥፊያ ጽዋው ስለሞላ ነው። ልብ ብለህ አንብብ። ያኔ ሲሆን «ደጀብርሃን» ስለ ማቅ መጥፋት ጽፎ ነበር ብለህ ታስታውሳለህ! አመንክም አላመንክም፣ ማቅ በነበር የሚነገርለት ማኅበር ይሆናል!! ከእግዚአብሔር መንገድ ላይ ጠላት ያስቀመጠው ወጥመድ ይወገዳል!!
   «ዕጣህን ከእኛ ጋር ጣል ለሁላችንም አንድ ከረጢት ይሁን ቢሉ
   ልጄ ሆይ፥ ከእነርሱ ጋር በመንገድ አትሂድ፥ ከጎዳናቸውም እግርህን ፈቀቅ አድርግ
   እግሮቻቸው ወደ ክፋት ይሮጣሉና፥ ደም ለማፍሰስም ይፈጥናሉና።
   መርበብ በወፎች ዓይን ፊት በከንቱ ትተከላለችና።
   እነርሱም በደማቸው ላይ ያደባሉ፥ በነፍሳቸውም ላይ ይሸምቃሉ» ምሳሌ1፥14-18

   Delete
 3. Do not cry or talk we all eotc now to clean our church from devil mk we will pay life by taking beeter action with the leaders of mk not for naive elements.

  ReplyDelete
 4. Enzeh wotemesha gormesa lemen karton aydhkemum bamerica yalsera menore brasu wongel newo. Birhanu ergetkale you think those are priest none just mafiya. We inform fbi soon how can make money with out work it is vaiolation by the law of the rule.

  ReplyDelete
 5. Ethiopian gov. has granted all citizen to practice or not any relegion , but mafya killer mk violated constitution. Please be ready to enter the kingdom of God by cleaning of trush leader of mk such like birhanu daneil gojam debters, ergetekale he not working wotemesha gormesa set yichresal idnetify the leader take action go heaven all eotc. Over over over

  ReplyDelete
 6. Aba Selama lemehonu eneman nachihu ? menafikan weys bete kihinet ?
  bewstsachihu likawint endalu yasayal mezgebachihu betsam melkam neger tasnebibalachihu- Mahibere Kidusann bemulu lemeketatel timokralachihu- merega tagegalachihu-Abune Abirhamin Tikawemalachihu- Abune Fanueiln tidegifalachihu lenegeru Abune Abirham yeneger sew Adimegana zerega nachew Abune Fanueilgitsina yewh mehonachewn Dallas TX besibseba lay temelkchalehu Ahun Abune Fanuei yetenadedu yimesilal Yemishalew Kesis Ergete kal-Kesis Birhanu Gobena -Dr Mesifin -D Efirem-Hulum Tenegagirew chigrochin meftat new digimos enesu eneman nachew ?tew belachew dinagayu yibsbachewal yitareku-yismamu kealhone yehulum maninet le hizib kirb new Abune Fanueil yenezihin siltsan meyaz alebachew Mawgezim yichilalu Papasu esachew nachew enj enersu aydelum tiegistim lik alew belachew

  ReplyDelete
 7. Dr Mesifin-Kesis Birhanu Gobena-Aba gebre wold -Kesis Ergrtr Kal -Kesis Tesheme Yohanis-Kesis fikire eyesus -hulachihum ebkachihu le betekirsityan asibu lemahiber kememot lechurch memot yishalal Astarku- Anegagiru-Aaweyayu Ahun Abune Fanueil Min bedelu? Manin neku?Manin Asadedu?sewn bemerdat yetaweku Amercan Hager yalewn Kahin hulu man sebesebew meselachihu Abune Abirham zemedochachewn new -Gojamn bicha new -Abune Markos yibisalu Ahun Aba Hiruyin wesdo ye memiriya halafi yasderege manew ?Hulachihum tawkalachuhu ke mekakelachihu Aba estsifanos DC micaeil -Aba fikre eyesus Tekel Hayimanot Leke maemiran Leyikun TX Like Kahinat Hayile Silase Denber temelket ebakachihu astewlu lechurch asbu

  ReplyDelete
  Replies
  1. ክላይ የጻፍከዉ ደካማና ጠባብ አመለካካት የለህ ነህና እባክህ/ሽ አዕምሮህን ክፍት አድርገህ/ሽ ማን ለቤተክርቲያኗ እየሰራ መሆኑን ማወቅ እንኳ ተስኖህ አፍህን ትከፍታለህ ...በጣም ያሳዝናል...ከላይ የጠቀስካቸው ሰዎች በአንተ አፍ የሚነሱ ሰዎች እንኳን አልነበሩም...አገሩ አሜሪካ ሆነና የማንም ሁሉም ክብር አጡ። ስለ አቡነ አብርሃም የምታውቅ አንዳች ነገር ያለ አይመስልኝም ትዝብት ውስጥ ከመግባት ተሰብስቦ መቀመጥ፤ አቡነ ፋኑኤል ምን አድረጉ ነው የምትለሁ? ማፈሪያ ነገር ነህ...ከዚህ በላይ ምን ያድርጉ ነው የምትለዉ? ቤተክርስቲያንን እየጎዳ ያለሁን ማን እንደሆነ ብታውቅ እንደዚህ ባልተናገርህክ ነበር... ግራ ተጋብተህ ሰውን ለማደናገር አትሞክር...

   Delete
  2. አይ አቡነ አብርሃም ነቢዩ ነገ የሚመጣባቸውን ሳያውቁ የቀራኒዮን ቤተክርስቲያን በናሽቪል "በረት" ብለው ቤተክርስትያኗን ሲያገለግሉ የነበሩ ወጣቶችን አሰናክለው ለክርስትና እንኳን ኬንታኪ ወደሚባል ስቴት እንዲሄዱ ያደረጉ ቀትረ ቀላል ጳጳስ ናቸው። ወገኖቼ የሚያዋጣን በማህበረ ቅዱሳን እውቅና የተሰጣቸው ጳጳስን እንደ መሲህ መመልከት ወይም ማህበሩ የጠላቸውን እንደዲያብሎስ መመልከቱ አይደለም። እስኪ አቡነ አብርሃም ተብዬው ለዚህ ለናሽቪል ኪዳነምህረት የሾሙትን ዶክትር ቀሲስ መዳን በማን እንደሆነ እንጠይቀው። በፋኑኤል ወይም በአብርሃም እንዳልሆነ ይነግረናል። "መዳን ስለኃጢያታችን ስለበደላችን ስለመተላለፋችን አለምንም በደሉ ኃጥያቱ መተላለፉ በቀራኒዮ መስቀል ላይ በተሰቀለልንና ሞትን ድል አድርጎ በተነሳው በጌታችን በመድኃኒታችን በእየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ማማነ ብቻ ነው። ታዲያ እኛን ምን ያባላናል እነኚሁ ሁለት ጳጳሳትን እግዚአብሄር በኔና በናንተ ላይ ሾማቸው እስኪ እንደፈቃድህ ብለን እንቀበል። አንድ ጥያቄ አለኝ በተለይ እኔ ከምኖርበት ናሽቪል ከተማ ለዚህ ሁሉ ግርግር የተበቃው እኮ አዲሱ ቤተክርስቲያን ሲመረቅ እንዴት አቡነ ፋኑኤል አለ አጥቢያቸው መጥተው ይመርቃሉ በሚል ነበር። ፋኑኤል ናሽቪል መጥተው እኮ ባርከውን ነው የተመለሱት ያሉትም "እባካችሁ በመካከላችሁ ልዩነትን አትፍጠሩ እኛንም ጳጳሳቱን ምክንያት አታድርጉን እኛ ሲኖዶስ ላይ ተገናኝተን እንወቃቀሳለን ይህን ፍቅራችሁን ጠብቁ። እኔ ወደዚህ የመጣሁት ቤተክርስቲያን ልባርክ መስሎኝ ነበር እኔ ግን በናንተ ተብርኬአለሁ። አሉ ድንቅ አይደል በዚህ ዘመን ወደታች ዝቅ ብሎ በናንተ ተባረኩ የሚል ከየት ይገኝ ይሆ? አረ ማስተዋሉን ይስጠን። አሁን ደግሞ የኔና የናንተ መድኃኔዓለም ሥራው ድንቅ አይደል እኒህ አናጢዎቹ(ማህበረ ቅዱሳን) የናቋቸውን ድንጋይ(አቡነ ፋኑኤልን) አምላካችን የማእዘን እራስ አደረጋቸው። አምጥቶ አለአጥቢያዎት ቤተክርስቲያን ባርከዋል በሚሉአቸው ላይ አሰለጠናቸው። ታዲያስ የክርስቶስ ቤተሰቦች አሁንስ እንቀበላለን ወይስ...ኪዳነምህረት የአጥቢያውን ጳጳስ ለመጋበዝ እነ መምሬ አንዱን አያውቁ(ወረቀት እያነበቡ ሲዘምሩብን የነበሩት የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች ነን ባዮች ሽማግሌዎቹና ባልቲቶቹ) ዝግጁ ናቸሁ ወይስ አሁንም አቡነ አብርሃምን ትጠብቃላችሁ? "ያዳቆነ ሰይጣን ሳያቀሥ አይለቅም።" እንደሚባለው። በቸር ይግጠመን።

   Delete
 8. danel kisret lemen baher dar yekadkewon dikala amneh atasadgm...anten billo memeher kidase enkwan endet endmikdes atawokm..brhanu gobena too..the big enemi of our church ....geta yinlachu .. eskemeche new yemtikeldut ...be selase menor bitamnu noro yihin hulu difret baladergachu neber ..do u guys know how many ye protestant adarash endetekefete betekrstiyanwan ena agelgayochwan masaded kejemerachu bewala?????? but u dont care all u care is how to memenun mebezbez...ena kisachun memulat ..mewdkiyachu derswal..dagm latanseraru latensu tewdkalachu..yemeskel yeetcrstian yekrstos telatoch.abo yebetu kinat enket adrgo belan..amlakachn hoy ebakeh betehn asda.

  ReplyDelete
 9. Abune Fanueil HIV Yeyazew Sewna Mahibere Kidusan Yelekefew sew 1 new Arfew yikemetsu Mahibere Kidusan yasadedachewn hulu yimelket Ahunim wey Andand Kahinat nen yemiluna Amerca yalutin yifetshi -Yawgizu -Yileyachew- wey degimo yitareku-yinegageru Kahin mehonachew yetegeletsew amerka yehonu Yeyazut debr ale teblal debirun likeku belachew erso yewah yimesilugal kininet ledorom albejat yibalal Abune Abirhamm Kezi behala Yemitegu endayimesiliwot neger -adima yichilalu wede ragueilbik yibelu yehonewn hulu yayalu tetsenkeku adera

  ReplyDelete
 10. Our church not safe heaven any more for mk and gojame ergetekal gojme to he ate my son by gojame buda here in atlnta.

  ReplyDelete
 11. Who is to accept this person who bought his bishopric with money. He can not be regarded a bishop in any church.
  Our church is a laughing stock. He writes in Amharic and sign in English.

  Weyew for those who kiss his cross, who partake his KURBAN.

  Just like he was thrown out of Awasa and St Peter and Paul seminary he should be thrown out of DC. Yes he is a US citizen, we hear, and will live here but not as the spiritual father of Orthodox Ethiopians

  ReplyDelete
 12. he was not thrown out of hawassa ...exept some peopel all the hawassa crstians love him respect him for what he has done for that region churchs..late us talk we know him well. but u dont ..the good thing is u may wish to throw him out of the church or dc but u cant from heaven that is the good thing .. respect man...we know abune gebrel and what he is but we dont say bad things like some of u .. late god be the one to jud

  ReplyDelete
 13. MAHIBER KIDUSAN (YEKIDUSAN MAHIBER)smuns enkit adrigachihu yizachihutal ehhhhhh daniel know tinbit danial ante nu eniwakes yilal yesrawit gieta egziabher lemehon mekides wusit gebito mekedes yalebet min ayinet sew yiho ebakih nigern eyanim gira atagaban difret atastemire eski bahir dar yinager ????
  genzeb genzeb ...lefiteh gireh bila le americawechi yiseral yibalal simetu meten alayenim endante wunbidinawn alitemarinemin tadyia keyetiyaw campani gebith eyeserah new LOL ale yamerica sew
  BRIHANU GUBENA bileh bile degimo here tew ante wenbedie yih dibibikoshe yikrbin eskemche lenegeru frieachu merzi yetiwulid merz yihew benante yayenew MERZI dekemezumurachihu ATO ZELALEM ENDALEW bechoyache ke america eyeteleke temirew genzeban mutit adrigeo bietun gezito be ehitu sim adrigo serateya bilo kesu keketerat serateyaw welido be 15 kenu kirstina asinesto begon echoyawn alehushi eyale serg eyasenada balitasebe menged met kenante gar yetekelakel merzochi kefelk gil begilt eninegager emaillhn sity wey ethio stimeta anagrey eskemulu informationu linegerh echilalehu lineger bicha sayihon lasayih echilalehu .
  dogima kenona ferese eyalik sim sitatefa 15 ken kirstina masnesat yet new ytemarikew midre lieba

  ABA SELAMA DEGIMO ENZIHN GUDAMOCHI BE EMAILLACHUMU MULU MEREJAWN linegrachihu echilalehu ......................

  ReplyDelete
 14. ከሰሜን አሜሪካ ሀገረ ስብከት ተነሥተው ወደ ሀረር እንዲዞሩ ተደርጓል።
  that is the point. He(Abune Abrham)will uproot the source of Tehadisso(UR ORG)

  ReplyDelete
 15. DO U THINK THE PPL OF HARER WILL AXEPT ABUNE ABRHAM..yawom ye mk melktegna..... hareroch yewengel melktegna enji yebet chrstian telat mk ambassador maskemecha bota yelenm..tehadso eko mk new .i think u dont know what happen to ato epherem..

  ReplyDelete
 16. kikikikikiki zelalem endalew yetekula liji tekula daniel enqan dess aleh yewngilu sir kumarteya metaleh rizrazih ayi anba selama ebakachihu kechalachihu wedegondar zor belulin bizu hodachin bisot aswetulin
  ZELALEM ENDALEW (TINSHU DANIEL )belski antem america gebah kikikikik weyi america bagoreshe ejishen tenekeshe ale yagerie sew liela belateya metalishi
  zelalemn yemawukew addiss abeba kasanchis hotel teketro sisera new wedage edil kento ke mahiber seyitan gar tekelakelen yegenzeb wengil yegemerew yanie new america bemitnor echoyaw eyeterda enien yale bit gezito nurssing memarunim awukalehu mechem diha sigey ayawkibet kirstnaw wengilum wede zimut tekeyro yihew wendilijun yizo aleyi bila wedmitebikew echoyaw hidelata kikikikik zelalem sintewawek antelalek zarie ageligayn ney bileh medirek tikom yihon abun biet gebrhil gonder unversty gibi ageliglot lemin tebarerik astenatalehu ealik ebith sitasmeshat yeneberchi abitam muslims manechi ihihihihihhiih zelalem antem america wodi yifgew.......................

  ReplyDelete
 17. Mk leaders have stolen$28,000,000.000 dollar from the church and depsite at western bank in difernt family members. We Eotc now go head take action any where and time then go to heaven. Specially danel kisret took the lion share of the money because he helpe his three children that born out side marriage.

  ReplyDelete
 18. በሁለት ሰዎች አዝናለሁ፡ አንደኛ አቡነ ፋኑኤል ተብዬው እንደዚህ አይነት ደረጃውን ያልጠበቃና አባትነታቸውን በሚያጎድፍ የሀሰት ወሬ ተጠምደው የሀሰት ፕሮፓጋንዳ በማስወራታቸው በጣም አዘንኩ። ስለሀገረ ስብከቱ ካለወቁ መጠየቅ አያስነውርም; ክፉ ነገር ተናግረው ብዙሃኑን ከሚያሳዝኑ። ሀሰትን ተናግረው ምን አይነት አንድነት ሊያመጡ ነው ቤተክርስቲያን ላይ ክብሪት እየጫሩ ስለሰላም ማውራት ከንቱ ነው። ስለዚህ "አባታችንን" እንዳልሎት የአባትነት ፍቅርና ተግባር አላሳዩን፤ የምንናፍቃትን የቤተክርስቲያን አንድነት እያናጉ አባታችን ቢሎትም አዕምሮዬም አይፈቅድልኝም፤ እንደብዙሃኑ መመሳሰል አንገሽግሾኛል ስለዚህ በበኩሌ የቁማር ጨዋታው ይብቃ ባይ ነኝ። የአባቶቻችን አምላክ ልቦናዎትን መልሶሎት "አባታችን" ለማለት ያብቃኝ። እርሶ ፈቃደኛ ከሆኑ ብዙም አይከብዶትምና ይሞክሩት ባይ ነኝ። ቅን ልቦና ይኑሮዎት። የያዙት ስልጣን ብዙ ያስጠይቆታልና መንጋውን ለመጠበቅ መጀመሪያ እርሶ ግዴታዎትን ይወጡ ; ያ ሲሆን እግዚአብሔርም ይታረቀናል; መንጋውም ሰላም ያገኛል ጠላትም ያርፋል፡፡ መቼም ያነባሉ ብዬ ነው።
  ሁለተኛው ይህ ድህረ ገጽ ይህን የሀሳት ወሬ ፖስት ማድረጉ ያሳዝናል ;; ጋዘጠኝነት ይውነት መገለጨ ነው እንጂ የሀሰት ማስፋፊያ መድረክ አይደለም። ሞያው ብቻ ያስገድዳል። በርግጥ የቤተክርስቲያን ልሳን ባለመሆኑ ብዙም አይደንቀኝም።
  በመጨረሻ እኔ ሀሳቤን የገለጽኩትን ስለቤተክርሰቲያን ቅናትና ስለእውነት ብዬ እንጂ ሌላ ችግር ኖሮኛ አይደለም። ሰለዚህ ወደሌላ ሳትወስዱንኝ በቅን ልቦና ውሰዱት። ሌሎቻችንም በስሜት ብቻ ተነሳስተን ሰዎችን ሊያሰናክል የሚችል አስተያያት ባንሰጥ ይመረጣል። ይህ የቤተክርስቲያን ጉዳይ ነው እንጂ የግለሰቦች ጉዳይ አይደለም፡፡ ማንም ስለቤተክርስቲያን ብሎ ሃሳቡን ይግለጽ እንጂ ለሌሎች መሰናክል አንሁን።

  ReplyDelete
 19. ‹‹እኔን ለምን ትወቅሱኛላችሁ››
  ጥቅምት 21/2004 ዓ.ም ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤው ባካሄደው ዐሥረኛ ቀን ስብሰባው አቡነ ፋኑኤል በሌላው አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ገብተው ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በመጣስ በፈጸሙት ተግባር በግልጽ ገሥጧቸዋል፡፡ በተለይም ብፁዕ አቡነ ማርቆስ፣ ‹‹ገለልተኛ ቤተ ክርስቲያን በሚባሉት ተገኝተው የሚባርኩት፣ ሥልጣነ ክህነት የሚሰጡት ማን ፈቅዶሎት ነው? በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት የሾሟቸው ‹ካህናት› ክህነት ወድቅ እንደሚደረግ አያውቁም? እርስዎ ባቋቋሙት ቤተ ክርስቲያን የቅዱስነታቸው ስም ይጠራበታል? የሚጠራበት የእርስዎ ስም ነው፤ ይህ ሕገ ወጥነት ነው፤ ተገቢም አይደለም!!›› በማለት በከፍተኛ ኀይለ ቃል ገሥጸዋቸዋል፡፡ አቡነ ፋኑኤልም ‹‹እኔን ለምን ትወቅሱኛላችሁ፤ አቡነ አብርሃም ገለልተኛ ቤተ ክርስቲያን ሄደው አይባርኩም፤ ሄደህ አገልግል ብለው ፓትርያርኩ ስላዘዙኝ ነው፤›› በማለት ችግሩ ከወደላይ መሆኑን አጋልጠዋል፡፡ አቡነ ፋኑኤል ይህን ጉድ ሲገልጡት ርእሰ መንበር ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ አንገታቸው ዘልሰው አንዳችም ቃል አለመናገራቸው ምልአተ ጉባኤውን ማስገረሙን ያዩ ተናግረዋል፡፡

  አወዛጋቢው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፋኑኤል በፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ትእዛዝ በመፈጸሙት ኢ-ቀኖናዊ ተግባር የሹመት ሽልማቱን በዚህ መልክ ያግኙ እንጂ በአህጉረ ስብከቱ ግን ጠንካራ ተቃውሞና ተቀባይነት ማጣት እንደሚጠብቃቸው ግልጽ ነበር ፡፡ የምልአተ ጉባኤውን ውሳኔ አቡነ ፋኑኤል በሰሜን አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ከፈጸሙት ኢ-ቀኖናዊ ድርጊት በተቃራኒ እዚያው እንዲሾሙና ምፀታዊ በሆነ መልኩ አቤቱታ አቅራቢዎቹ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት እንዲነሡ መወሰኑ ተከታዩን ችግር አርቆ አለማየትን.ያመለክታል።

  ቅዱስ ሲኖዶስ ለወሰነው ውሳኔ ተገዥዎች ነን። ሆኖም ግን በሰሜን አሜሪካ ያለን ምእመናን ለመናፍቃን አሳልፎ የሚሰጠን ሳይሆን ከጠላት የሚታደገን ኖላዌ ትጉህ ያስፈልገናልና ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔውን ደግሞ እንዲመረምር ማድረግ ይጠበቅበታል ምክንያቱም የችግሩን ስፋት ከቅዱስ ሲኖዶስ በላይ ሊያውቀው የሚችል የለምና።

  ለመሆኑ አቡነ ፋኑኤል ለየትኛው አገረ ስብከት እንደተላኩ ያውቃሉን?
  የሚከሱትስ ለየትኛው አገረ ስብከት ነው? ሴኖዶስን ነው ወይስ እራሳቸው?
  “ከሳሽ የተክሳሽን ልብ ቢያውቅ ኖሮ ከቤቱም ባልወጣ ነበር” እነደሚባለው ብጹነታቸው እየከሰሱ ያሉ እራሳቸውን ነው።

  ReplyDelete
  Replies
  1. አስባችሁ ነበር ጠንካራ ተቃውሞ ለማስነሳት መድሃኔዓለም የት ሄዶ "እባብ ልቡን አይቶ እግር ነሳው።" አይደለም እንዴ ተረቱ እግር ነሳችሁ እንጂ አስባችሁ ነበር። ቸር ይግጠመን።

   Delete
 20. አንዳንድ አስተያየት ሰጭዎች በማታውቁት ነገር ገብታችሁ የምትፈተፍቱ፤
  አንዳንዶቻችሁ ደግሞ በጭፍን ቲፎዞነት እንጂ ነገሩን በፅሞና ያላያችሁ፤
  አንዳዶቻችሁ ደግሞ በጭፍን ጥላቻ እንጂ ነገሩን በደንብ ሳታውቁ፤
  ሌላው ደግሞ በተለይ በተለይ ጥቅሙ የተነካበትና ከሁዋላው ጉድና ጎድጎዳ የሞላበት፤
  በመጨረሻ ደግሞ ለቤተክርስቲያን ሳይሆን ለራሱ የንግድ ድርጅትና የፖለቲካ ሥራ
  እንደበፊቱ መሥራትና ማጭበርበር ያልቻለው የማህበረ ሰይጣን ድርጅት የሚሰጠው
  የሞት የሽረት የመሰሪነትና የቅናት አስተያየቱን ነው የሚያስነብበን። የሆነው ሆኖ
  ግን ሁልጊዜ አሸናፊው የእግዚአብሔር ሃሳብ ያለው ነው። እስኪ አሁን ማ ይሙት
  በእውነት ለቤተክርስቲያን የምናስብ ከሆነና አላማችን የእግዚአብሔርን መልካም
  አገልግሎት ለማገልገል ከሆነ ምን ያጣላናል \ በእውነትስ ክርስቲያን ከሆንን
  ክርስቲያን መጣላት አለበት\ ይህንን ደግሜ እላለሁ አላማችን አንድ \ክርስትና\
  ከሆነ ምንድን ነው የሚያባላን\ በእውነት አቡነ ፋኑኤል ምን አደረጉ\ ተመድበው
  መጡ፣ ሥራቸውን መሥራት ጀመሩ የሥራ ሰው እንጅ የወሬና የአሉባልታ ካህን
  አይደሉም። ደግሞስ እኛ ማነንና ነው በስነሥርአት ሲኖዶሱ መድቡአቸው ለክርስትና
  አገልግሎት እንዳይሰጡ የምንፈራገጠው፣ አረ ተው መቼም ክርስቲያኖች እንኩአን
  አይደላችሁም ፤ ስለ እግዚአብሔር ብትባሉም አልሰማችሁምና አለቃችሁም የቀደመው
  ጠላታችን ያ ዲያብሎስ በመሆኑ ነው መሰለኝ እርሱን በማስደሰትና ቤተክርስቲያንን
  በመበጥበጥ ላይ ትገኛላችሁ። ነገር ግን እግዚአብሔር ተዋጊ ነው አታውቁም እንዴ\
  ምንም አላችሁ ምንም አሁን ጊዜው የእግዚአብሔር ሰዎች የሚፈተኑበት ጊዜ ስለሆነ
  እስከመጨረሻው የሚፀና እርሱ ይድናልና፤ አባታችን እስከመጨረሻይቱ ሰአት ድረስ እውነተኛ
  ሥራን መሰራት ብቻ ነው፣ ከእናንተ ጋር አፍ መካፈትም አያስፈልግም። ጨው ለራስህ
  ብትል ጣፍጥ ያለዚያ ድንጋይ ነው ብለው ይጥሉሃል ነውና፣ ማቅ መንፈሳዊ ድንቁርናችሁ
  የትም አያደርሳችሁም፣ ለቤተክርስቲያን ጠላት ማቅ ይገባዋል ሞት፣ ለቤተክርስቲያናችን
  ግን አንድነት፣ እድገትና ፍቅር ለዘለአለሙ ይሁን። አሜን።ሰላምንና ፍቅርን የማይወደው ማቅ
  ይግባ መቀመቅ። ባታወጡትም ካነበባችሁት ይበቃል።ሳትሰሩ የህዝቡን ገንዘብ እየበላችሁ
  አየር ላይ ለቀራችሁት ህገ ወጥ የድርጅቱ ኮሚቴ ነን ባዮች፣ እናንተ ማለት ደግሞ ማንም ናችሁና
  ካአቅማችሁ በላይ አትዘለሉ ወደ ላይ። ይቆየን።

  ReplyDelete
  Replies
  1. አጻጻፍዎ ብዙ ፍሬ ሀሳቦችን ይዞ የአቋም ባለቤትነትን አጥቷል።
   በከፊል መንፈሳዊ ሲሆን በከፊል በስድብ የተሞላ ነው። በከፊል ቅዱስ ሴኖዶስን ሲያከብር ቅዱስ ሴኖዶስ የሚያውቃቸውን አብያተ ክርስቲያን ባዶ ያስቀራል። አቡነ ፋኑኤል የተላኩት በቅዱስ ሴኖዶስ መሆኑን ሁሉም ይስማማሉ። ቅዱስ ሴኖዶስም የላካቸው አቡነ አበርሃምን ለመተካት ነው። በዚህ እንስማማለን።
   ቅዱስ ሴኖዶስ ደግሞ በአቡነ አብረሃም አባታዊ መሪነት የተመሰረተ አገረ ስብከት እንዳለ ጠንቅቆ ያውቃል።
   ታዲያ ብጹዕነታቸው አቡነ ፋኑኤል ጽፈት ቤቱን እንደመጡ መረከብ የለባቸውም? ነገር ግን ሃገረ ስበከት የለም ብለው ነው በቪኦኤ የዘገቡት። ለምንድንስ አቡነ አበረሃምን አላነጋገሩም? እነዚህ አባቶች ሁለቱም የቅዱስ ሴኖዶስ አካል ሲሆኑ ለምን አንዱን አስተዳደር አንዱ ይበትናል። እንደኔ አስተያየት ችግሩን እያባባሰው ያለ ምዕመናኑ ነው። አንተ ምእመን ከሆንክ ነቃ በል አስተውል በእምነትህ ጽና አንዲት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ እምነትን ጠብቅ።
   ካህንም ከሆኑ ይንቁ ችግሩ ከእርዎ የበላይ እነደሆነ ይረዱ በማስተዋልና በጸና እምነት ሆነው አንዲት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ እምነትን ይጠብቁ በጎችንም በጥሩ መስክ ያሰማሩ።

   Delete
 21. bedaneal kebert be gobena and aba abrham yetemesertwon hager sibket new ende????sinodos yemayawokewon abatochen yemaysemawon erseh danel kalohnek manm yinen asteyayet lisef ayichelm .. kidase telemamed befit .. are u realiy dicon???i dont think so ...

  ReplyDelete
 22. The time will come when the Truth will be revealed and the darkness we are in will disappear. This article mixes truth with COMPLETELY made up fiction, when this happens our fathers will call this a false document because there are many elements of falsehood in it, that is why they said, a drop of poison in clean milk, spoils the whole milk. I am not here to defend any maheber, or Bishop or Kesis or Deacon, if they are in the wrong they will pay for it, if they are in the right then they will get the reward. I will tell you however from direct personal experience that Mahiber Kidusan is not the founder of the Washington DC Diocese, they contributed as they should as its their duty, just like every other mehaber who have the organization and ability, like bale wold. Many many individuals who have no associations with any mahiber supported the DC diocese under Abune Abraham much more than any mahiber put together, they did it again for duty and reward from God and not for personal gain or control. I served in the committee when the Washington DC Diocese under Abune Abraham was created I served with Kesis Berhanu and D Daniel, I do not belong to any mahiber, and I am here to tell you that there was no conspiracy theory behind the creation of the Washington DC diocese under Abune Abraham. It was God's will, have we forgotten that? I think we have. The diocese house belongs to the EOTC meaning all members of the EOTC from clergy to laity. The reason the diocese house loan is under an individuals name is because the EOTC Diocese did not have sufficient credit to get the loan so there needed to be some one to serve as a guarntor for the loan...is that a bad thing? to sacrifice ones own financial situation for the sake of the church? this individual did not seek to control anything, Abune Abraham who is also part of the loan did not seek anything, infact how the house was bought and under whos name it is was reported by Abune Abraham at a comprehesive meeting before the synod meeting where the patriarach and bishops including abune fanuel was present. fathers mothers brothers sisters, let us hear the true word of God, the true word of the church, and pray for unity. blaming each other does not teach or preach Christianity, it teaches the religion of sin. blaming does not rid us of our sin. so we should just stop speaking about things we know little or nothing about and start searching with in to find the little devils who seek to completely devour us...are we paying attention to them or are we too busy "trying to get the splinter out of our brothers eye?...joro yaley mesmatin yesma..." Tsleyu, mejemeria erasachinn enadin...lets not worry about mahibers, bishops, priests, etc...at the end of it all they are only the vehicles through which the Holy Spirit or evil spirit operates. Before we judge the evil in them, the Gospel teaches to clear our selves of evil first. Can any one say they are 100 percent clean from the evil spirit? i think not even Saints never admitted this!! So in short, work our your own salvation, God will take care of His Church, have bego hasab, pray, fast, hold to the traditions of the fathers, pray to the holy mother just as they did, and guess what, you will pass through this valley, this trail, unharmed and entacted through the mercy of God...pray.

  ReplyDelete
 23. PLZ KISSES BERHAN GOBENA STOP MESSING OUR CHURCH FOR YOUR OWN GOOD . WE ALL KNOW KNOW HOWYOU BECAME KISS , WE KNOW YOU NAVER BEEN DEAKON BUT NOW YOU ACTING YOU CAN BRAKE AN DMAKE THINK AROUND USA . PLEASE BE GOOD LEADER AND STOP DIVIDING US , WE ARE AWARE OF WHAT YOU ARE DOING AROUN SMALL TOWN LANCASTER,PA . YOU YOURSELF KNOW HOW YOU ARE DIVINGING THOSE PEOLA EBY ETHIIC AND MAHIBER. OANCE AGAINE PLEASE RESPEACT THE WHO ARE THRER TO WORSHIP THE TRUE GOD .

  ReplyDelete
 24. When I read the statement I really feel shame. Are you really worried for orthodox church or for your personal interest? If you were good christian, you would not accuse others. As chiristian do not blame others. Try to see yourself first. I think religion is not like politics where someone plan to get benefit(position). If somebody made mistake,tell him the way to solve it. An

  ReplyDelete
 25. rasun kefkef madereg ena swochine mwenjel melkam aydelem. yelkunes bgara bmhone yeweset tkulawocen lmesale tehadiso ymsaslutene bgara btselot xenewagacwe

  ReplyDelete
 26. Together with which experts state nachos is just bread
  dough, gravy, parmesan cheese, and additionally toppings.
  The kind of garment recommended nicely sum of material made there is essential, since they are this particular characteristic
  as well as placement for these particular coverings in regards to the hoop on top of that boulders.
  You certainly will pre-taste the mixture is perfectly to change the
  flavor or inclination internet site your decision.


  My web blog :: good toaster brands india (toasterovensplus.com)

  ReplyDelete