Thursday, March 29, 2012

የቀረልን ዘር - - - Read PDF

“የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘር ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ሰዶም በሆንን ገሞራንም በመሰልን ነበር” (ኢሳ. 1፥9)
ለቅድስት ድንግል ማሪያም ተሰጥተው ከተተረጎሙት የብሉይ ኪዳን ጥቅሶች መካከል ይህም ተጠቃሽ ነው፡፡
በኢየሩሳሌም የሚኖሩ የይሁዳ ሰዎች በእግዚአብሔር ላይ በማመፅ በኃጢአት ላይ ኃጢአትን እየጨመሩ እግዚአብሔርን ስላሳዘኑት ለከፋ ችግር እንደሚጋለጡ፣ አገራቸውም በጠላቶቻቸው ተቃጥላ እንደምትፈራርስ፥ ባዕዳን ሰዎችም እንደሚጠቀሙባት ሕዝቡም ለምርኮና ለብዝበዛ እንደሚሰጥ ነቢዩ ኢሳይያስ በግልጽ ተናግሯል፡፡ (ኢሳ. 1፥2-8፤ 2ነገ. 20፥17-18)።
(ቁ. 9) ላይ የተነገረው ትንቢት ለጊዜው ከባቢሎን ምርኮ ስለሚተርፉት ቅሬታዎች ሲሆን (ነህ. 1፥3) ፍጻሜው ደግሞ ክርስቶስ ወደ ወገኖቹ መጥቶ ወገኖቹ ሊቀበሉት ባለመቻላቸው ምክንያት መዳንን ለመውረስ ባይታደሉም በኋለኛው ዘመን የአሕዛብ ሙላት ሲፈጸም የእስራኤል ቅሬታዎች በክርስቶስ አምነው እንደሚድኑ ያሳያል፡፡ (ኢሳ. 10፥22-23፤ ሮሜ 11፥25-27)።ይበልጥ ደግሞ ቅ/ጳውሎስ በሮሜ 9፥29 ላይ የኢሳ. 1፥9ን ቃል ጠቅሶ በመናገሩ ትንቢቱ ከመጀመሪያው ጀምሮ የተነገረበትን ዓላማ በትክክል አስቀምጧልና ከዚህ ያለፈ ሌላ ትርጉም ሊሰጠው አይችልም፡፡

Wednesday, March 28, 2012

ብዙ ቁም ነገሮችን ያዘለው ጮራ መንፈሳዊ መጽሔት ቊጥር 42 ለንባብ በቅቷል


ከጮራ ጡመራ ላይ የተወሰደ
ርእሰ አንቀጹ፡-
እውነት ምንድር ነው? በማለት የእውነትን ፍለጋ ተከትለን እውነት ወደሆነውና ወደሚያድነው እውነት ወደ ኢየሱስ ያድርሰናል፡፡
መሠረተ እምነት
ስለ ክርስቶስ መካከለኛነት ራሱ ክርስቶስ ያስተማረውን እውነት ያብራራል፡፡ መካከለኛነቱን ለማስተባብል የሚሰነዘሩ ጕንጭ አልፋ ክርክሮችን ይሟገታል፤ ተከራክሮም በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ይረታል፡፡


ክርስቲያናዊ ምግባር
በማቴ. 5÷10 ላይ ተመሥርቶ ስለጽድቅ የሚደርሰው ስደት ለክርስቲያኖች ያለውን ጥቅም እና በአሳዳጆች ላይ የሚያስከትለውን ጕዳት ይገልጣል፡፡
የዘመን ምስክር
የቀደሙ አባቶቻችን የሠሩትን መልካም ሥራና ያሳዩትን በጎ አርኣያነት የሚዘክረው ይህ ዐምድ ለውጥ ናፋቂውን ብላቴን ጌታ ኅሩይንና መልካም ሥራዎቻቸውን ያስተዋውቃል፡፡ 
  
ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
በቊጥር 94 በስያሜ 81 እየተባለ ስለሚጠራው፣ ከሒሳብ ስሌት ውጪና ግራ አጋቢ ስለሆነው  የመጽሐፍ ቅዱስ አቈጣጠር ለቀረበ ጥያቄ፣  ምላሽ ተሰጥቷል፡፡ 
66 + 28 = 84 መጻሕፍት፡፡
ወቅታዊ ጕዳይ
ኦርቶዶክስ ማነው? በሚል ርእስ በተከታታይ በሚቀርበው በዚህ ርእስ ማኅበረ ቅዱሳን በአስተምህሮው ኦርቶዶክሳዊ መሆን አለመሆኑን ይፈትሻል፡፡ በዚህ ዕትም አንድ ቀሪ ነጥብ ቢኖርም፣ ማኅበረ ቅዱሳን ለመጽሐፍ ቅዱስ ያለው አመለካከት ተገምግሞ ኦርቶዶክሳዊ አለመሆኑ ተደርሶበታል፡፡ 
ሌሎችም ጽሑፎች ተካተዋል፡፡ በ“እውነት ምንድር ነው?” የጀመረው የዚህ መጽሔት መልእክት “እስከ ማእዜኑ” በተሰኘውና እውነትን በሚያቀነቅነው የዮናስ አድማሱ ግጥም ይደመድማል፡፡
መጽሔቱን በየመንፈሳዊ መዝሙር ቤቶች ያገኙታል፡፡

የዋልድባ ገዳም ይዞታና የዝቋላ ተራራ ቃጠሎን ማህበረ ቅዱሳን ለፖለቲካ ፍጆታው ቢያውላቸውም የፈለገውን ትርፍ እንዳላስገኙለት እየተነገረ ነው - - - Read PDF

በቅርቡ በዋልድባ ገዳም ዙሪያ ከገዳሙ ይዞታ ውጪ በሆነው ስፍራ ላይ በመንግስት የተጀመረውን የልማት ስራ ሌላ ትርጉም በመስጠትና መንግስትን ከገዳሙ መነኮሳትና ከኦርቶዶክሳውያን በአጠቃላይ ለማጋጨት ማህበረ ቅዱሳን አንቀላፍተው በከረሙና ፖለቲካዊ ቅስቀሳውን ተከትሎ ነቃ ነቃ ባሉ ድረገጾቹ የጀመረው ፖለቲካዊ ዘመቻ ግቡን እንዳልመታለት በአገር ውስጥ ከሚታየው የገዳሙ መነኮሳትና የህዝቡ ምላሽ ማወቅ እንደተቻለ ከተለያዩ ምንጮች ያገኘናቸው መረጃዎች እየጠቆሙ ነው። በአንድ አድርገን ድረገጽ ላይ አገር ፈረሰ፣ አገር ታረደ፣ ተነስበማለት ህዝቡን ለአመፅ ያነሳሳ ቢሆንም ሰሚም ተቀባይም እንዳላገኘ የሚታይ እውነታ ነው።

Tuesday, March 27, 2012

ወደ መንግሥተ ሰማያት የይለፍ ፈቃድ - እንደ ገድለ ተክለሃይማኖት መጽሐፍ - - - Read PDF

የገድለ ተክለ ሃይማኖት ጸሐፊዎች ዋና ዓላማቸው ሕዝቡ በክርስቶስ በመድኃኒታችን አምኖ የዘላለም ሕይወት እንዲያገኝ ሳይሆን በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የሰይጣንን ፈቃድ ለማሳካት የተነሡ መሆናቸውን ጽሑፋቸው ያጋልጣቸዋል።
«መንፈቀ ሌሊት በሆነ ጊዜ ኢየሱስ ክርስቶስ ሚካኤልን በቀኙ፤ ገብርኤልን በግራው አድርጎ እናቱ ማርያምን 12ቱ ሐዋርያትን ከእርሱ ጋር ይዞ ብዙዎች የሰማይ ሠራዊትን አስከትሎ ወደ እርሱ (ተክለ ሃይማኖት) መጣ እንዲህም አለው። «በዓልህን የሚያከብር በእንጀራም ቢሆን በዕጣንም ቢሆን በመሥዋዕትም ቢሆን እስከ ጥሩ ውኃ ድረስ ስምህን የሚያስጠራ ሁሉ ባንተ ስም እንግዳ ቢቀበል በግልጽ ወደ መንግሥተ ሰማያት ይለፍ . . . ስምህ በተጠራበት በገዳምም ቢሆን በዓለምም ቢሆን እስከ ዘላለም ይቅርታና ቸርነት ከዚያ ይኑር በእውነት ያለ ሐሰት . . . » ይላል (ገድለ ተክለ ሃይማኖት ምዕ 39፥2-6)
እንደ ገድሉ ጸሐፊዎች ኃሳብ  መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሁሉ ወደ መንግሥተ ሰማያት ለመግባት በተክለ ሃይማኖት ስም እንግዳ መቀበልና እንጀራና ዕጣን መስጠት ይገባል ብሎ አስተምሯል ማለት ነው። ሆኖም ለአነዋወሩ ነቀፋ ለንግግሩ ሐሰት ለትምህርቱ ስሕተት የማይገኝበት በእኛ ሥጋ ለመዳናችን ሥራ ሲል በሥጋ የተገለጠው የእግዚአብሔር ልጅ በሰውነቱም የሰው ልጅ የተባለው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ ብሎ አስተምሯል ማለት በእርሱ ላይ ስድብ እንደመናገር ይቆጠራል።  በየትኛውም ትምህርቱ ጻድቅ እየተባሉ በተጠሩ ሰዎችና መላእክት ስም በሚደረግ ስጦታና በዓል ማክበር መንግሥተ ሰማያት ይገኛል ብሎ አላስተማረም።

Friday, March 23, 2012

ማህበረ ቅዱሳን ጥንተ አብሶን በመታከክ በአባ ሠረቀ ላይ ዘመቻ ከፈተ - - - Read PDF

የማህበረ ቅዱሳንን ድብቅ አጀንዳ በማጋለጥና በቤተክርስቲያን ላይ የጋረጠውን አደጋ ለህዝበ ክርስቲያንና ለመንግስት አካላት በማሳየት፣ “ማንም አይደፍረኝም” ሲል የነበረውን ማህበር ከመሠረቱ ባናጉትና መያዣ መጨበጫ ባሳጡት፣ በቀድሞው የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሀላፊ በነበሩትና በአሁኑ ጊዜ ደግሞ የትምህርትና ስልጠና መምሪያ ሃላፊ በሆኑት በአባ ሰረቀ ላይ አዲስ ዘመቻ መክፈቱን እየወጡ ያሉ ጽሁፎች እያረጋገጡ ነው። ማህበሩ የሚያሳትመው ስምአ ጽድቅ የተሰኘው ጋዜጣው በየካቲት ወር እትሙ በርእሰ አንቀጹና ከአቡነ እንድርያስና ከመምህር ደጉ ዓለም ካሳ ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ፣ እንዲሁም ከዚህ ቀደም ከአባ ሠረቀ ጋር በጥንተ አብሶ ዙሪያ ውዝግብ ውስጥ የነበሩትንና “ነጭ እንቁ በአዳም ገላ” የሚል መጽሐፍ ጽፈው ማርያም ጥንተ አብሶ የለባትም ያሉትን መምህር ሀብተ ማርያም ተድላን የአብርሃም ቤት እንግዳ በተሰኘ አምዱ ላይ አቅርቦ (ስም ሳይጠሩ) በአባ ሠረቀ ላይ ያነጣጠሩ ትችቶችን እንዲሰነዝሩ አድርጓል፡፡ማህበሩ በርእሰ አንቀጹ ላይ “ማርያም ጥንተ አብሶ የለባትም” ለማለት በተደጋጋሚ ያቀረበው ምክንያት ከኒቅያ እስከ ኤፌሶን ጉባኤዎችና ከዚያም ወዲህ በተነሱ የቤተ ክርስቲያን አባቶች “ስለ እመቤታችን ጥንተ አብሶ አልተነሳም” የሚል ተልካሻ ምክንያት ነው። እንደማህበሩ ገለጻ በማርያም ላይ ጥንተ አብሶ አለባት ወይም የለባትም በሚል ከዚህ ቀደም ጉዳዩ አለመነሳቱ “ማርያም ጥንተ አብሶ የለባትም” የሚል ውሳኔ እንደሰጡ አያስቆጥርም፡፡ በቤተክርሰቲያናችን ውስጥ የምናያቸውና የምንሰማቸው አንዳንድ ትምህርቶችና ስርአቶች በጉባኤ የተወሰኑ አይደሉም። በልማድ ሲሰራባቸው የኖሩ ናቸው። ዛሬ ለውሳኔ ቀርበው ውይይት ይደረግባቸውና ውሳኔ ይሰጥ የሚል ክፍል ቢነሳ መልሱ ከቶ ምን ይሆን? አባቶቻችን በኒቅያ፣ በቁስጥንጥንያ፣ በኤፌሶንና በሌሎቹም ጉባኤዎች እንዲህ ያለ ጉዳይ አላነሱምና፣ በኖረው ልማድ ነው መቀጠል ያለብን ሊባል ነው? እንዲህ ማሰብ ያሳፍራል!!

Tuesday, March 20, 2012

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እውነትና እውነተኞች የሚገፉባት፤ ሐሰትና ሐሰተኞች የሚነግሱባት እስከ መቼ ይሆን? - ክፍል 4 - - - Read PDF

ዘሪሁን ሙላቱ ኦርቶዶክሳዊ ወይስ ሰባልዮሳዊ ?

ኑፋቄ 3
ሐዋርያት ያጠመቁት በኢየሱስ ስም ነው

ባለፈው ጽሑፍ ላይ የተሰጡ አስተያየቶችን ለማየት ሞክሬያለሁ፡፡ እግዚአብሔር ሶስትም አንድም ነው የሚለውን ትምህርትና አገላለጽ በልዩ ልዩ መንገድ እየተማርን ያደግን በመሆናችን የምንስማማ ቢሆንም፣ ምስጢር ያደላደሉ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን አምልተውና አስፍተው ያስተማሩትን በተለይም በምስጢረ ስጋዌ ላይ ያለውን ትምህርት ቃል በተለየ አካሉ ስጋ ሆነ የሚለው የተለመደ ኦርቶዶክሳዊ አገላለጽ ለአንዳንዶች ጆሮ እንግዳ መስሎ መታየቱና ይህን ትምህርት ከማሰላሰልና ከማጤን ይልቅ ዘሪሁን ስላሴን ወልዳለች ያለውን ሃይማኖት አፍራሽ አገላለጽ ብዙም ችግር የለው ብለው መቀበላቸው አስገርሞኛል፡፡

አንዳንዶች በነገረ ክርስቶስ ላይ ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው ስለሆነው ስለአንዱ ክርስቶስ ሲናገሩ፣ በአውጣኬያዊ[1] ስልት ፍጹም ሰውነቱን ወደአምላክነቱ ያዛውራሉ። በየአውደ ምሕረቱ የሚናገሩት ስለአምላክነቱ ብቻ ነው። ለፍጹም ሰውነቱና በሰውነቱ ስለፈጸመው የቤዛነት ስራ ግን ትኩረት አይሰጡም። ይህን የሚያደርጉት በፍጹም ሰውነቱ የፈጸመውን የማዳን ስራ ዛሬ ላይ ሆኖ መናገር እርሱን ከአምላክነቱ ደረጃ ዝቅ ያደርገዋል ብለው ስለሚያስቡ ነው፡፡ በሌላም በኩል የእርሱን የመካከለኛነት ስፍራ ለፍጡራን ስለሰጡ እነርሱን የት እናድርጋቸው በሚል ጭንቀትም ነው አምላክነቱን እያጎሉ፣ ሰውነቱን እያጎደሉ እንዲለፍፉ የሚያደርጋቸው፡፡ በዚሁ ስሜት ተወጥረው ሲሮጡም ትምህርተ ስላሴን ወደሚንድና የእግዚአብሔርን ሦስትነት በአንድነቱ ወደሚያስጠቀልል የሰባልዮስ ሰፈር ማረፊያቸውን ያደርጋሉ።

Monday, March 19, 2012

ዛሬም ያልተፋቱት ኢትዮጵያና ግብፅ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ግብጻውያንና የዓባይ ወንዝ፡-
ከቤተ ጳውሎስ ድረገጽ የተወሰደ - ሰኞ መጋቢት 10/2004 ዓ.ም.
ከትላንት በስቲያ በሥጋ የተለዩን የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ሀገር የሆነችው ግብጽ የረጅም ጊዜ ሥልጣኔና ታሪክ ያላት አፍሪካዊት ሀገር ናት፡፡ እጅግ የዳበረ የሥነ ሕንጻ፣ የሥነ ጽሑፍ፣ የፍልስፍና ማዕከል፣ በዓለማችን ከሚገኙት ታላላቅ ሥልጣኔዎች ተብለው ከሚጠቀሱት ከፋርስ (ፐርሺያ)፣ ከባቢሎን፣ ከአሴርያውያን፣ ከግሪክ፣ ከሮማ፣ ከቻይና፣ ከደቡብ አሜሪካዎቹ ከአዝቴክስና ከኢንካ እንዲሁም ከእኛዋ አክሱም ሥልጣኔ ጋር በግንባር ቀደምትነት የምትጠቀስ ሀገር ናት፡፡

Saturday, March 17, 2012

አቶ ደስታ ጥፋተኛ ከተባለ በኋላ በ2 ዓመት ገደብ እንዲለቀቅ ብይን ተሰጠ

ማህበረ ቅዱሳን በሸጎጠለት ጠቀም ያለ የገንዘብ ጉርሻ ባልጻፈው መጽሐፈ ስድብ ላይ ስሙን ሸጦ በስም ማጥፋት ወንጀል ጥፋተኛ የተባለውና ለመጋቢት 5/2004 ዓ.ም የተቀጠረው አቶ ደስታ በ7 ወር እስራትና በ3 ሺ ብር እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡ ይሁን እንጂ ቅጣቱ እንዲቀልለት ያቀረበውን ጥያቄ ፍርድ ቤቱ ካዳመጠ በኋላ ቅጣቱን በሁለት ኣመት በመገደብና 3ሺ ብሩን እንዲከፍል በመወሰን በገደብ ለቆታል፡፡ ከገደቡ በተጨማሪ የ5 ሺህ ብር ዋስትና እንዲያቀርብም ፍርድ ቤቱ አዟል፡፡ በፍርድ ቤቱ ሲያለቃቅስ የተስተዋለው ደስታ ተገቢውን ፍትህ ማግኘቱ ለወደፊቱ ትልቅ ትምህርት እንደሚሰጠው ታምኖበታል፡፡ ማህበረ ቅዱሳን እንደሚያወራው እጀ ረጅም አለመሆኑና ተሰባሪ ሸንበቆ መሆኑ በታየበት በዚህ የፍትህ ሂደት፣ ስም አጥፊዎቹ ጥፋተኛ መባላቸውና ማህበሩ ወንጀል ሰርተው መሸሻና ማምለጫ እንደማይሆናቸው በተግባር የፈተኑበት ትልቅ አጋጣሚ ይሆናል ተብሏል፡፡

አልተሳካለትም እንጂ በህገ ወጥ መንገድ በአባ ሠረቀ ላይ ያቀረበው ክስ እንዲቋረጥ መደረጉ ስላበገነው ያን ለመበቀል፣ አባ ፊልጶስን አሳስቶ ህጋዊውን ክስ ለማቋረጥ ተንቀሳቅሶ ለቀናት የተሳካለት መስሎት ጮቤ ቢረግጥም፣ አባው የለሁበትም በማለታቸው እንደገና እንዲቀጥል በመደረጉ ጥፋተኞቹ በህግ ፊት ቀርበው ጥፋተኞች ተብለዋል። መቼም ቅጣት መማሪያ በመሆኑ ጥፋተኞቹ ከጥፋታቸው ተምረው ካሳሳታቸው ማህበር አካሄድ ራሳቸውን መጠበቅ እንደሚገባቸው እሙን ነው፡፡

ማህበሩ የብዙዎችን ስም አለአግባብ ያጠፋባቸው አጋጣሚዎች በርካታ እንደመሆናቸው፣ በየጊዜው በሌሎች ስም ብቻም ሳይሆን በስሙ በሲዲ፣ በጋዜጣና በመጽሄትና በሌሎችም ሰነዶች የከፈታቸው የስም ማጥፋት ወንጀሎች ብዙ ሊያስጠይቀው እንደሚችል የመጋቤ ሀዲስ በጋሻው ክስ ጥሩ ትምህርት ሰጥቶ አልፏል፡፡

Wednesday, March 14, 2012

የተክለ ሃይማኖት መቃብርና አጥንት ለምን ይታጠናል? - - - Read PDF

ገድለ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያናችንን፣ ሕዝባችንን ያጠፋ፣ ወንጌልን የጋረደ ግርዶሽና በበሬው ወለደ ተረት የተሞላ ሆኖ ሳለ እርሱን የጻፈ ያጻፈና የተሳለመ ስሙ በሕይወት መጽሐፍ እንደሚጻፍለት ይናገራል። በዚህ ሐሰተኛ ስብከቱ የቤተ ክርስቲያናችን ምመናን ወንጌልን ትተው እርሱን በማሰራጨት ሥጋውና ደሙን በመቀበል ፋንታ የደብረ ሊባኖስን ፍርፋሪ በመብላት፤ ንስሐ በመግባት ፈንታ በደብረ ሊባኖስ በመቀበር ለመጽደቅ ከንቱ ተስፋ ይዘው ይገኛሉ። ስለዚህ መጽሐፉ የሐሰት አባት ዲያብሎስ የሸረበው ተንኮል መሆኑን ለሕዝባችን ለማሳወቅ እንፈልጋለን። በጣም የሚያሳዝነው ግን በክርስቶስ ያመኑ ወንጌልን ተምረው ለሕዝባቸው ለማስተማር ደፋ ቀና የሚሉ መምህራን ይህን የሐሰት ድርሰት ባለመቀበላቸው በቤተ ክህነት አደገኛ ፖለቲከኞች መናፍቃን እየተባሉ መሰደዳቸው ነው። ክርስቲያን ለመባል የሚያበቃ የገድለ ተክለ ሃይማኖትን ተረት ማመን ወይስ በመጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈውን የእግዚአብሔር ቃል ማመንና በርሱ መኖር? ይህ መጽሐፍ የወንጌልን ቦታ እስኪለቅ ድረስ በውስጡ የያየዘውን ባዶ ተረት እናሳያለን።

“ያገኙትን ቢያጡ ያጡትን ይቀላውጡ” - - - Read PDF

ይድረስ ለቆንጆ መጽሔት
“ቆንጆ” መጽሔትን “መልከ ጥፉን …” የሚለው ተረት ይገልጸዋል፡፡ የማህበረ ቅዱሳን ቅጥረኛ ሆኖ በአባ ሰላማ ድረገጽ ላይ መሰረተ ቢስ የስም ማጥፋት ዘመቻ ከከፈቱ የግል ነገር ግን የማህበረ         ቅዱሳን ተከፋይ መጽሔቶች መካከል አንዱ ቆንጆ መጽሄት ነው፡፡ መጽሄቱ ታህሳስ ወር 2004 ዓ.ም ላይ “አባ ሰላማ ድረ-ገጽ ማነው? ማህበረ ቅዱሳንስ?” በሚል ርእስ ባቀረበው ጽሑፍ በበላበት መጮሁን በሚያሳብቅበት ሁኔታ ማህበረ ቅዱሳንን እየካበ አባ ሰላማ ድረገጽን ጥላሸት እየቀባ የጋዜጠኝነት ስነምግባርን በጣሰ መንገድ እጅግ የወረደ ጽሁፍ አስነብቦ ነበር፡፡ በጊዜው አንድ የድረገጻችን ተከታታይ ቆንጆ መጽሄት አባ ሰላማ ድረገጽ ላይ የከፈተውን የስም ማጥፋት ዘመቻ በተመለከተ ምላሽ እንድንሰጥ አስተያየት ሰጥቶ ነበር፡፡ ለመጽሄቱ ጽርፈት የተሞላበት ጽሁፍ መልስ መስጠት ቢኖርብንም ለእርሱ ተራ ወሬ መልስ ከመስጠት ይልቅ በእውነተኛ መረጃ ላይ የተመሠረተና ለአንባቢዎች የሚጠቅም መረጃ በመስጠት ላይ ማተኮሩን መርጠን እስካሁን ቆይተናል፡፡
አሁን በመጽሄቱ ላይ ምላሽ ለመስጠት የተነሳነው መጽሄቱ አባ ሰላማ ድረገጽን ሲሰድብና ሲያዋርድ እንዳልነበረ፣ በቤተክርስቲያን ዙሪያ ለሚያቀርባቸው ዘገባዎች ከማህበረ ቅዱሳን ሀሰተኛ ብሎጎች እያወረደ የማህበረ ቅዱሳንን ገጽታ ሲገነባ እንዳልከረመ፣ አሁን ላይ እነዚያ ምንጮቹ የወሬ ድርቅ ስለ መታቸው ይሁን ወይም ስላልከፈሉት ባልታወቀ ምክንያት መጋቢት 2004 ዓ.ም እትሙ ላይ አለወትሮው ከአባ ሰላማ ድረገጽ ላይ ፖስት የተደረገ ጽሁፍ አትሞ አውጥቷል፡፡ ይህ በራሱ መልካም ነው፡፡ “ቆንጆ ሆይ በዚሁ ቀጥል” እንላለን፡፡ ችግሩ ግን “ዜናውን የወሰድሁት ከአባ ሰላማ ድረገጽ ነው” ብሎ ምንጩን አለመጥቀሱና ከሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ድረገጽ ላይ እንደወሰደ አድርጎ ማቅረቡ ነው፡፡ ለዚህ ነው “ያገኙትን ቢያጡ ያጡትን ይቀላውጡ”ን የተረትነው፡፡

Sunday, March 11, 2012

ሰበር ዜና - የዘመድኩን ባልንጀራ ጨዋው ደስታም ጥፋተኛ ተባለ - - - Read PDF

የመጋቤ ሀዲስ በጋሻውን ስም በማጥፋት ክስ የተመሰረተበት አቶ ደስታ የተባለ ግለሰብ ላይ የቦሌ ምድብ ችሎት ጥፋተኛ አለው፡፡ በከሳሽና ተከሳሽ የቀረቡትን ቅጣት ማከበጃና ማቅለያ ካዳመጠ በኋላም ብይን ለመስጠትም ለመጋቢት 5 2004 ቀጥሮ መስጠቱን ምንጮቻን ገለጹ፡፡
የፊትአውራሪያቸውን የዘመድኩንን ፈለግ ተከትለው ሳሩን እንጂ ገደሉን ሳያዩ ነበር ሳህሉና ደስታ ለደረሳቸው የማህበረ ቅዱሳን ጥሪ አፋጣኝ ምላሽ የሠጡት፡፡ በንግድና በፖለቲካ እንጂ በመንፈሳዊ አገልግሎት ምእመናንን መማረክ ያልቻለውና ኪሳራ እየደረሰበት የነበረው ማህበረ ቅዱሳን በወንጌል አገልግሎትና በዝማሬዎቻቸው የብዙ ምእመናንን መንፈሳዊ ረሃብ ማስታገስ የመንፈስ ጥማቸውንም ማርካት በቻሉትና እርሱን ከገበያ ውጪ ባደረጉት በእነመጋቤ ሐዲስ በጋሻውና በእነዲያቆን ትዝታው ላይ ‹‹ከህዝብ ልብ ማስወጣት›› በሚል የሰየሙትን የስም ማጥፋት ዘመቻ መክፈታቸውን ተከትሎ ማህበረ ቅዱሳን ለዘመቻው በመደበው ገንዘብ መጽሀፍ አዘጋጅተን በስማችን በማሳተም እነበጋሻው ከህዝብ ልብ እናስወጣለን ሲሉ ትግሉን ተቀላቀሉ፡፡ የመጋቤ ሀዲስ በጋሻውን ስም የሚያጠፉ መጽሀፍትን በስማቸው አሳተሙ፡፡ መጻህፍቶቹን እነርሱ መጻፋቸውን ብዙዎቹ ይጠራጠራሉ፡፡ በተለይም ከ3ኛ ክፍል ትምህርቱን አቋርጧል የተባለውና አንዳች የቤተክርስቲያን ትምህርት የሌለው ጨዋው ደስታ ሊጽፍ እንደማይችልና፣ ልቦለዱን ጽፎ የሰጣቸው የማህበረ ቅዱሳን የስም ማጥፋት ዘመቻ ክፍል መሆኑን ብዙዎች ይስማማሉ፡፡ ጨዋው ደስታ በስሙ ስላሳተመ ደህና ገንዘብ ተከፍሎታል የሚሉት ውስጥ አዋቂዎች፣ ማህበረ ቅዱሳን ካለ ማንም አይነካኝም የሚል ጽኑ እምነት ነበረው ሲሉ ያክላሉ፡፡

Thursday, March 8, 2012

መርዝ ባፉ ማህበር "ማህበረ ቅዱሳንና” ዕርቀ ሰላሙ - - - Read PDF

ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል - «ማህበረ ቅዱሳን ወይስ ማህበረ ሰይጣን» መጽሐፍ ደራሲ
ይህ ጽሑፍ፦

ራሱን ቅዱስ ብሎ በመስየም ለአመታት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሀብተ ንበረት ሲዘፍ፣ የጥንታውያን ገዳማትና አድባራት ቅርሳ ቅርስ ሲያወድምና ለውጭው ዓለም ሲቸበችብ፣ አገልጋዮችዋን ያለ ስማቸው ስም እየለጠፈና እየሰጠ ሲያሳድድና ሲያሸማቅቅ የመጣውን የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በሕግ የማታወቀው የሀገር አንድነትና ሉዓላዊነት አደጋ ላይ የሚጥል አጀንዳ አንግቦ ስለሚንቀሳቀስ ነፍሰ በላ የፖለቲካ ድርጅት “ማኅበረ ቅዱሳን” ዕርቀ ሰላሙን እውን እንዳይሆን በግላጭ ጉባኤ እየጠራ እያደረገው ስላለው አፍራሽ ዘመቻ የሚያስነብብ ነው::

ዕርቅ የተደረሰበት ዕለት እንደሆነ ይህ መናኛ ወገን (“ማኅበረ ቅዱሳን”) በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዓውደ ምህረት ላይ መታሰቢያ: ዕድል ፈንታም አይኖሮውም:: ታሪክም በማይወራለት አኵኋን ስመ ዝክሩ ያከትምለታል:: ይህንንም ጠንቅቆ ሲለሚያውቅ በቀሩለት ጥቂት ቀናቶች በውንብድና ስራ ላይ ተሰማርቶ ጉባኤ እየጠራ የምእመናንን ልብ መክፈል፤ ጥላቻን መዝራትን ስራዬ ብሎ ተያይዞታል::

በሕይወቴ ዘመኔ እጅግ ከባድ የልብ ሐዘን ከፈጠሩብኝ ሁኔታዎችና ክስተቶች መካከል በአደባባይ ለመጻፍም ሆነ ለመናገር የማያመች በ ጆርጂያ አትላንታ ከተማ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን ሁኔታ አንዱ ነው:: ነገሩም እጅግ አሳዛኝ ከመሆኑም በላይ አንገት የሚያስደፋም ነው:: እንደ ቅርጫት ስጋ ተበጣጥሳ እንደ አሜባ የተራባችውን ቤተ-ክርስቲያን ተከታዮችም አዘንኩላቸው:: "የአብያተ ክርስቲያናቱ" መጠሪያ ተቀጽላ የሰማሁትም በድንገት ነበር::

Wednesday, March 7, 2012

ዘመድኩን በስም ማጥፋት ወንጀል 5 ወር ተፈረደበት - - - Read PDF

ዘመድኩን ወንጀሉ እንደ ሰማዕትነት እንዲቆጠርለት ማሰቡና ደጀሰላም ድረገጽም ይህንን ማስተጋባቱ ብዙዎችን አስገርሟል
 በመጋቤ ሐዲስ በጋሻው ላይ የስም ማጥፋት ወንጀል የፈጸመውና ጥፋተኛነቱ በፍርድ ቤት የተረጋገጠው ዘመድኩን በ5 ወር እስራት እንዲቀጣ ብይን ተሰጠ፡፡ ማህበረ ቅዱሳንን ተገን ስላደረገ ምንም እንደማይሆንና ለወንጀሉ ሃይማኖታዊ ገጽታ በማላበስ፣ በተጨብረበረ ሰነድ ፋይሉ እንዲዘጋ ሙከራ እስከ ማድረግ ሙከራ አድርጎ የነበረው ዘመድኩን የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ /ቤት አራዳ ምድብ ችሎት የካቲት 27 ቀን 2004 . በዋለው ችሎት በ5 ወር እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡
ዘመድኩንን ከኋላ ሆኖ በርታ ሲለው የነበረው አዝማቹ ማህበረ ቅዱሳን ጠበቃ አቁሞለት በአስቂኝ መከራከሪያዎች ሲሟገትለት የቆየ ቢሆንም፣ ቴፎዞዎችን በመሰብሰብና በማጫፈር ያልተደረገውን ተደረገ እያሰኘ በድረገጾቹ ሲደግፈው ቢቆይም፣ ‹‹እጄ ረጅም ነው የትም ይደርሳል›› እያለ በመመካት ምንም አይደርስብህም ቢለውም ፍርድ ቤት ግን ጥፈተኛነቱን ስላረጋገጠ ወንጀለኛ ብሎታል፡፡

Monday, March 5, 2012

አባ ገብርኤልና ማኅበረ ቅዱሳን በመመሳጠር ያዘጋጁት የሀዋሳው የ3 ቀን ጉባኤ የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔዎች በመጣስ መከናወኑ ተገለጸ - - - Read PDF

አባ ገብርኤል ከማህበረ ቅዱሳን ጋር በመመሳጠር ያዘጋጁትና ከየካቲት 23 – 25/2004 .ም ለሶስት ቀን የቆየው ጉባኤ የሲኖዶስን ውሳኔዎች የተጻረረና በደቡብ ክልል ማህበረ ቅዱሳን ከገጠመው ኪሳራ እንዲያገግም ሆነ ተብሎ የተዘጋጀ ጉባኤ መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገለጹ፤
 አባ ገብርኤል ጉባኤ ማዘጋጀታቸው ተገቢ ቢሆንም በማን አለብኝነት መምህራን ብለው የጋበዟቸው ዳንኤል ክብረት፣ ዘበነ ለማና ምህረተ አብ አሰፋ መሆናቸው ‹‹የሲኖዶስን ውሳኔ የሚጻረር ነው›› ሲሉ ማህበረ ቅዱሳንና አባ ገብርኤል ተባብረው ተሀድሶ ናቸው በሚል ሰበብ ከቤተ ክርስቲያን እንዲሰደዱ ያደረጓቸው በሀዋሳ የሚገኙ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ለጠቅላይ ቤተ ክህነት አቤት እንዲሉ አስገድዷቸው ነበር፡፡ አቤቱታቸውን ተከትሎ አጣብቂኝ ውስጥ የገቡ የመሰሉትና አቋም የለሽ መሆናቸውን በተደጋጋሚ ያስመሰከሩት አባ ገብርኤል፣ ጉባኤ ማዘጋጀታቸውንና በአስተማሪነት የጋበዟቸው ሰዎች በእነ በጋሻው ልክ የተሰፋውና ‹‹ሕገ ወጥና ፈቃድ የሌላቸው አጉራ ዘለል ሰባኪዎች በየሀገረ ስብከቱ ሄደው እንዳያስተምሩ›› የሚለው መመሪያ የሚመለከታቸው በመሆናቸው፣ ሀላፊነትን ለመውሰድ በመፍራትና ከተጠያቂነት ለመሸሽ በሚል በጉባኤው ዋዜማ ሀሙስ ዕለት /በ22/6/2004 ዓ.ም/ ከስብከተ ወንጌል መምሪያ ሁለት ሰባኪዎች እንዲላኩላቸው በጠየቁት መሰረት ሁለት ሰባኪዎች እንደተላኩላቸው ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡ በጉባኤው የመጀመሪያ ቀን ግን የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔን በመጣስና በማን አለብኝነት ከስብከተ ወንጌል መምሪያ ጋር የተስማሙበትን የጋራ አቋም ወደ ጎን በመተው ዳንኤልን በቆረጣ አስገብተው በ24/6/2004 አሰብከዋል፤ በቀጣዩ ቀንም በተለመደው የቆረጣ ስልት ዘበነ እንዲሰብክ ማድረጋቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

Friday, March 2, 2012

ድል የእግዚአብሔር ነው! - - - Read PDF

‹‹ጎልያድም ዳዊትን፡- በትር ይዘህ የምትመጣብኝ እኔ ውሻ ነኝን አለው? …. ዳዊትም እኔ ግን ዛሬ በተገዳደርኸው በእስራኤል ጭፍሮች አምላክ ስም በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ስም እመጣብሃለሁ አለው››   ፩ ሳሙ ፲፯፣፵፫-፵፭፡፡

የአድዋው ጦርነት ለብዙ አውሮፓውያን የጦርነቱ ታዛቢዎችና ለጦርነቱ ተሳታፊዎች ለኢጣሊያውያንም ጦርነቱ ‹‹የጎልያድንና የዳዊትን ጦርነት›› ታሪክን ከቅዱስ መጽሐፍ ዞር ብለው እንዲያስታውሱ የተገደዱበትን ሁኔታ የፈጠረ ነበር፡፡ እጅግ ዘመናዊ በሆነ ጦር ተደራጅቶ የመጣውን የኢጣሊያን ጦር ለመመከት ከመላው ሀገሪቱ የተሰባበሰበው የኢትዮጵያ ጦር ምንም ዓይነት ዘመናዊ የጦርነት ሥልጠና ያልወሰደና በእጁ የነበረውም መሣሪያ ጦርና ጎራዴ ቢሆንም፣ ከሁሉም በላይ በኢትዮጵያውያን በልባቸውና በደማቸው ውስጥ ግን ለዳዊት ድልን ያጎናጸፈውና ያን ግዙፍና በጦረኝነቱ መላው ፍልስጤም የሚርድለትን፣ የእስራኤልን ሠራዊት ለ40 ቀናት የተገዳደረውን ጎልያድን በአንዲት ጠጠር ድል ያደረገው የዳዊት አምላክ ኃያሉ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ነበር፡፡ የድሉ ምንጭም የእግዚአብሔር ኃይል፣ ኢትዮጵያውን ለሃይማኖታቸውና ለነጻነታቸው የነበራቸው ቀናዒነት እንጂ ሌላ ምን ሊሆን ይችላል?

Thursday, March 1, 2012

አባ ሳሙኤል ይግባኝ የጠየቁበትና “አባ ሚካኤል መውለድ አይችሉም” ሲሉ በሁለት ጠበቃ የተከራከሩበት ጉዳይ ውድቅ ተደርጎ የዮሐንስን ልጅነት የሚያረጋጥ ብይን ተሰጠ - - - Read PDF

የሟቹ የብጹእ አቡነ ሚካኤል ልጅ ነኝ ብሎ የቀረበውና ወራሽነቴ ይረጋገጥልኝ ያለው ዮሐንስ ሚካኤል ከዚህ ቀደም በፍርድ ቤት ልጅነቱን አስመስክሮ ወራሽነቱን ያረጋገጠ መሆኑን ጃንዋሪ 12, 2012 መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡ ፍርድ ቤት የሰጠውን ብይን ተከትሎ በጳጳሳቶቻችን ታሪክ ታይቶም ተሰምቶም በማያውቅና ከአንድ ሊቀጳጳስ በማይጠበቅ ሁኔታ ምእመናንን መክሰስ ሥራቸው አድርገው የያዙት አባ ሳሙኤል ይግባኝ ስለጠየቁ ጉዳዩ ሲታይ ቆይቷል፡፡ ሁለት ጠበቆች አቁመው ሲከራከሩ የነበሩት አባ ሳሙኤል “አባ ሚካኤል ድንግል ናቸው፤ እንኳን ልጅ ሊወልዱ ሚስትም አላገቡም” የሚል መከራከሪያ ይዘው ልጃቸው ዮሐንስ እንዳይወርስ ሲከራከሩ የነበረ ሲሆን፤ ዮሐንስም አባ ሳሙኤል ክብራቸውን ጠብቀው ካልተቀመጡ ልጅነቴን በዲ ኤን ኤ ምርመራ ለማረጋገጥ እገደዳለሁ ማለቱን ዘግበን የነበረ መሆኑ ይታወሳል፡፡