Saturday, March 17, 2012

አቶ ደስታ ጥፋተኛ ከተባለ በኋላ በ2 ዓመት ገደብ እንዲለቀቅ ብይን ተሰጠ

ማህበረ ቅዱሳን በሸጎጠለት ጠቀም ያለ የገንዘብ ጉርሻ ባልጻፈው መጽሐፈ ስድብ ላይ ስሙን ሸጦ በስም ማጥፋት ወንጀል ጥፋተኛ የተባለውና ለመጋቢት 5/2004 ዓ.ም የተቀጠረው አቶ ደስታ በ7 ወር እስራትና በ3 ሺ ብር እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡ ይሁን እንጂ ቅጣቱ እንዲቀልለት ያቀረበውን ጥያቄ ፍርድ ቤቱ ካዳመጠ በኋላ ቅጣቱን በሁለት ኣመት በመገደብና 3ሺ ብሩን እንዲከፍል በመወሰን በገደብ ለቆታል፡፡ ከገደቡ በተጨማሪ የ5 ሺህ ብር ዋስትና እንዲያቀርብም ፍርድ ቤቱ አዟል፡፡ በፍርድ ቤቱ ሲያለቃቅስ የተስተዋለው ደስታ ተገቢውን ፍትህ ማግኘቱ ለወደፊቱ ትልቅ ትምህርት እንደሚሰጠው ታምኖበታል፡፡ ማህበረ ቅዱሳን እንደሚያወራው እጀ ረጅም አለመሆኑና ተሰባሪ ሸንበቆ መሆኑ በታየበት በዚህ የፍትህ ሂደት፣ ስም አጥፊዎቹ ጥፋተኛ መባላቸውና ማህበሩ ወንጀል ሰርተው መሸሻና ማምለጫ እንደማይሆናቸው በተግባር የፈተኑበት ትልቅ አጋጣሚ ይሆናል ተብሏል፡፡

አልተሳካለትም እንጂ በህገ ወጥ መንገድ በአባ ሠረቀ ላይ ያቀረበው ክስ እንዲቋረጥ መደረጉ ስላበገነው ያን ለመበቀል፣ አባ ፊልጶስን አሳስቶ ህጋዊውን ክስ ለማቋረጥ ተንቀሳቅሶ ለቀናት የተሳካለት መስሎት ጮቤ ቢረግጥም፣ አባው የለሁበትም በማለታቸው እንደገና እንዲቀጥል በመደረጉ ጥፋተኞቹ በህግ ፊት ቀርበው ጥፋተኞች ተብለዋል። መቼም ቅጣት መማሪያ በመሆኑ ጥፋተኞቹ ከጥፋታቸው ተምረው ካሳሳታቸው ማህበር አካሄድ ራሳቸውን መጠበቅ እንደሚገባቸው እሙን ነው፡፡

ማህበሩ የብዙዎችን ስም አለአግባብ ያጠፋባቸው አጋጣሚዎች በርካታ እንደመሆናቸው፣ በየጊዜው በሌሎች ስም ብቻም ሳይሆን በስሙ በሲዲ፣ በጋዜጣና በመጽሄትና በሌሎችም ሰነዶች የከፈታቸው የስም ማጥፋት ወንጀሎች ብዙ ሊያስጠይቀው እንደሚችል የመጋቤ ሀዲስ በጋሻው ክስ ጥሩ ትምህርት ሰጥቶ አልፏል፡፡

7 comments:

 1. Kibir Le Amalkachin Letekile Haimanot Yihun. Teferedebachew Adel! Yetabatachew! MK och ende ashen bifelum bezih guday alitesakalachewum.

  ReplyDelete
 2. we all eotc members are alwayes on your side, do not affraid any thing just keep your excellent job. Mk has no way to attack our real preachers any more.If they are intersting to preache and manage our church first they will have been gone to real church school not college of engineering. That is the key objective now all of eotc aware to fight this devil invassion. Do your best abaselam we all decided to protect eotc from the devil mk. The devil they attack megabe hadis begashaow, for his great job of in eotc history that including to aba serke. All real kahenate and deacon hate mk.

  ReplyDelete
 3. txs God it is good news

  ReplyDelete
 4. Kirstina yihe kemeselachihu tesastachihual. BALINJERAHIN enderaseh wuded.........................yalewen kal asbut

  ReplyDelete
 5. ሠይፈ ገብርኤልMarch 18, 2012 at 9:33 PM

  ክርስትና ፡-
  ከልዩ ልዩ ዓለማዊና ሥጋዊ ነገሮች ተለይቶ በአንድ ልብ ተወስኖ ራስን ለክርስቶስ ብቻ አስገዝቶ በእርሱ ቅዱስ መንፈስ ተመርቶ ለቃሉ እየታዘዙ በመኖር በስሙ መከራውን በመታገሥ እስከ መጨረሻው በታማኘነት መጽናት ማለት ነው /ጽንሰ ሃሳቡ ከአባ አበራ በቀለ መጽሐፍ/፡፡

  የግለ ሰብ ቅደም ተከተል የውዴታ ግዴታዎች ፡- መማር ፣ ማመን ፣ መጠመቅ ፣ መመስከር ፣ በመንፈስ ቅዱስ መታተም /ለመንፈስ ቅዱስ መሰጠት ማለትም ሥጋ ወደሙን መቀበል/

  ቃለ ክርስቶስን ለማወቅ መትጋት /መጽሐፍ በማንበብ ፣ አስተማሪዎችን በማዳመጥ/
  ክርስቶስን አምኖ /ሙሉ ሰው ከሆነ/ መጠመቅ
  ትምህርተ ክርስቶስን አውቆ ለቃሉ መታዘዝ
  ትእዛዛቱን መጠበቅና በመንፈስ ቅዱስ መመራት /የተማሩትን በተግባር መኖር/
  በሕገ ወንጌሉና በፍቅሩ መኖር
  "በእርሱ /በክርስቶስ/ እኖራለሁ የሚል እርሱ እንደ ተመላለሰ ራሱ ደግሞ መመላለስ /ክርስቶስን መምሰል/ ይገባዋል" 1ዮሐ 2፡6 ።

  ሕገ ወንጌል ምንድር ነው ?
  ጌታ ታላቅ ትእዛዝ በማለት የጠቀሳቸው ሁሉንም የክርስትና ደንቦች የሚጠቀልሉት ሁለት ናቸው ፡፡
  - ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ እና ባልንጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ የምትለው ናት። /ዘዳ 6፡5 ፤ ዘሌ 19 ፡ 18 ፤ ማቴ 22 ፡ 37-4ዐ /

  - ሮሜ 13 ፡ 10 ፍቅር ለባልንጀራው ክፉ አያደርግም፤ ስለዚህ ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነው።
  - ገላ 5፡14 -15ሕግ ሁሉ በአንድ ቃል ይፈጸማልና፥ እርሱም። ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የሚል ነው። ነገር ግን እርስ በርሳችሁ ብትነካከሱ ብትበላሉ እርስ በርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ።
  - ገላ. 5፡22 የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።
  - 2 ዮሐ 5 – 6 አሁንም፥ እመቤት ሆይ፥ እርስ በርሳችን እንድንዋደድ እለምንሻለሁ፤ ይህች ከመጀመሪያ በእኛ ዘንድ የነበረች ትእዛዝ ናት እንጂ አዲስ ትእዛዝን እንደምጽፍልሽ አይደለም። እንደ ትእዛዛቱም እንሄድ ዘንድ ይህ ፍቅር ነው፤ ከመጀመሪያ እንደ ሰማችሁ፥ በእርስዋ ትሄዱ ዘንድ ትእዛዙ ይህች ናት።

  የእግዚአብሔር ልጅ የሰው ልጅ በመሆኑ ምን አስተማረን ?
  -ለማዳን መምጣቱንና እግዚአብሔርም ፍቅር መሆኑን ገልጦልናል ፡፡ ፍቅር የሆነው አምላክ ደግሞ እኛም የፍቅር ሰዎች እንድንሆን በወንጌሉ በሐዋርያቱ በኩል ያስተማረውን እንመልከተ

  -1 ዮሐ 4 ፡ 8 – 9 ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፥ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና። በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ዘንድ ተገለጠ፥ በእርሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና።

  - 1 ዮሐ 4 ፡ 10 – 12 ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም። ወዳጆች ሆይ፥ እግዚአብሔር እንዲህ አድርጎ ከወደደን እኛ ደግሞ እርስ በርሳችን ልንዋደድ ይገባናል። እግዚአብሔርን ማንም ከቶ አላየውም፤ እርስ በርሳችን ብንዋደድ እግዚአብሔር በእኛ ይኖራል ፍቅሩም በእኛ ፍጹም ሆኖአል።

  - 1 ዮሐ 4 ፡ 16 እኛም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል አምነንማል። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፥ በፍቅርም የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል።

  እግዚአብሔር ፍቅሩን ለሁላችንም ያድለን

  ReplyDelete
 6. Mk or devil is not baleinjra mk means talewo dertun wogaw belaw injeraw.

  ReplyDelete
 7. I don't see any good news from taking our case into court and accusing each other. What kind of gospel we are preaching?

  ReplyDelete