Monday, March 5, 2012

አባ ገብርኤልና ማኅበረ ቅዱሳን በመመሳጠር ያዘጋጁት የሀዋሳው የ3 ቀን ጉባኤ የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔዎች በመጣስ መከናወኑ ተገለጸ - - - Read PDF

አባ ገብርኤል ከማህበረ ቅዱሳን ጋር በመመሳጠር ያዘጋጁትና ከየካቲት 23 – 25/2004 .ም ለሶስት ቀን የቆየው ጉባኤ የሲኖዶስን ውሳኔዎች የተጻረረና በደቡብ ክልል ማህበረ ቅዱሳን ከገጠመው ኪሳራ እንዲያገግም ሆነ ተብሎ የተዘጋጀ ጉባኤ መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገለጹ፤
 አባ ገብርኤል ጉባኤ ማዘጋጀታቸው ተገቢ ቢሆንም በማን አለብኝነት መምህራን ብለው የጋበዟቸው ዳንኤል ክብረት፣ ዘበነ ለማና ምህረተ አብ አሰፋ መሆናቸው ‹‹የሲኖዶስን ውሳኔ የሚጻረር ነው›› ሲሉ ማህበረ ቅዱሳንና አባ ገብርኤል ተባብረው ተሀድሶ ናቸው በሚል ሰበብ ከቤተ ክርስቲያን እንዲሰደዱ ያደረጓቸው በሀዋሳ የሚገኙ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ለጠቅላይ ቤተ ክህነት አቤት እንዲሉ አስገድዷቸው ነበር፡፡ አቤቱታቸውን ተከትሎ አጣብቂኝ ውስጥ የገቡ የመሰሉትና አቋም የለሽ መሆናቸውን በተደጋጋሚ ያስመሰከሩት አባ ገብርኤል፣ ጉባኤ ማዘጋጀታቸውንና በአስተማሪነት የጋበዟቸው ሰዎች በእነ በጋሻው ልክ የተሰፋውና ‹‹ሕገ ወጥና ፈቃድ የሌላቸው አጉራ ዘለል ሰባኪዎች በየሀገረ ስብከቱ ሄደው እንዳያስተምሩ›› የሚለው መመሪያ የሚመለከታቸው በመሆናቸው፣ ሀላፊነትን ለመውሰድ በመፍራትና ከተጠያቂነት ለመሸሽ በሚል በጉባኤው ዋዜማ ሀሙስ ዕለት /በ22/6/2004 ዓ.ም/ ከስብከተ ወንጌል መምሪያ ሁለት ሰባኪዎች እንዲላኩላቸው በጠየቁት መሰረት ሁለት ሰባኪዎች እንደተላኩላቸው ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡ በጉባኤው የመጀመሪያ ቀን ግን የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔን በመጣስና በማን አለብኝነት ከስብከተ ወንጌል መምሪያ ጋር የተስማሙበትን የጋራ አቋም ወደ ጎን በመተው ዳንኤልን በቆረጣ አስገብተው በ24/6/2004 አሰብከዋል፤ በቀጣዩ ቀንም በተለመደው የቆረጣ ስልት ዘበነ እንዲሰብክ ማድረጋቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ከሁለቱም ሲኖዶሶች የለሁበትም የሚለውና መቀመጫውን አሜሪካ ላይ አድርጎ በተወሰነ ጊዜ ብቅ እያለ በቤተክርስቲያን ሀይለኛ ቢዝነስ እየሰራ የሚገኘው ዘበነ ለማ ከሁለቱም ሲኖዶሶች ውጪ በመሆኑና ፈቃድ ስለሌለው እንደከዚህ ቀደሙ ለቢዝነሱ ጉባኤ እያዘጋጀ የሚፏልልበት መድረክ እየጠበበ ሊመጣ እንደሚችል ቢገመትም፣ አሁን በተያዘው የህገ ወጦች አሰራር ህጉ የሚከበር አይመስልም፤  ስለዚህ ቤተክርስቲያናችን የማን ናት? የሚለው ጥያቄ በብዙዎች እየተነሳ ይገኛል፤
በሲኖዶስ የሚወሰኑ ተገቢ ውሳኔዎች አንዱን ወገን ጠቅሞ ሌላውን ለመጉዳት የሚወሰኑ ባይሆኑም፣ በአንድ ውሳኔ ማህበረ ቅዱሳን ጥቅሙ የተነካ ወይም ጉዳት የሚደርስበት መስሎ ከታየው ውሳኔዎች ይተግበሩ የሚል ጩኸት በስውር በሚመራቸው ሁሉም ሚዲያዎች ማሰማቱ የተለመደ ሲሆን፣ ሲብስበት ደግሞ የሲኖዶስን ውሳኔ ሽሮ ያሻውን ከማድረግ እንደማይመለስ ከሀዋሳው ጉባኤ መገንዘብ ተችሏል፡፡
በዚህ መካከል በ1980ዎቹ ዛሬ ተሀድሶ እየተባሉ በማህበረ ቅዱሳን ከተፈረጁት ወገኖች ጋር ‹‹አይዟችሁ በርቱ ከወጣንም አብረን ነው የምንወጣው›› እያሉ ብዙዎችን ‹‹ፒስሜከር›› ሆነው ሲያበረታቱ የነበሩትና የቁርጥ ቀን ሲመጣ ቀኝ ኋላ ዙር ብለው የአቅጣጫ ለውጥ ያደረጉት አባ ገብርኤል፣ ከማህበረ ቅዱሳን ጋር በፍቅር ረጅም ወራትን ማሳለፋቸው ብዙዎችን አስገርሟል፡፡ ነገ ሌላ ቀን ነውና የአባ ገብርኤል መጨረሻ ምን እንደሚሆን ከአሁኑ መገመት እንደማይቻል ብዙዎች ይናገራሉ፡፡ ድርጊቱን በማንአለብኝነት የፈጸሙት ምናልባት ከግንቦቱ ሲኖዶስ በኋላ ከሀገረ ስብከቱ የሚነሱ ከዚያ ቀደም ብለው ለማህበረ ቅዱሳን ውለታ ለመዋልና በቁርጥ ቀን አባትነት ስማቸው በማህበሩ የክብር መዝገብ ላይ እንዲመዘገብላቸው ፈልገው ነው የሚል ግምት አለ፡፡
በዚህ ጉባኤ ላይ በሀገረ ስብከቱ በአገልግሎት እንዳይሳተፉ በቅዱስ ሲኖዶስ የታገዱትን የማህበረ ቅዱሳንና ፈቃድ የሌላቸው ሰባኪዎችን፣ ከማህበረ ቅዱሳን ዳንኤል ክብረትን ፈቃድ ከሌላቸው ሰባኪዎች ዘበነ ለማን ማሰበካቸው ተጠያቂነት እንደሚያስከትልባቸውና በቅርቡ በቋሚ ሲኖዶስ አሊያም በግንቦቱ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ሊጠየቁበት እንደሚችሉ ብዙዎች የሚጠብቁት ነው፡፡
dejeselaam-dejeselaam.blogspot.com የተባለው ብሎግ እንደዘገበውም ‹‹ክቡራን የመንግሥት ሚኒስትሮች በታዛቢነት በተገኙበት አቡነ ገብርኤል ራሳቸው የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ሆነው መስከረም 12 ቀን 2002 . በተካሄደው የሠላም ጉባዔ የወሰኑትና የፈረሙበት "ማኅበረ ቅዱሳን" በማናቸውም የቤተክርስቲያን አስተዳደራዊ መዋቅሮች ውስጥ ጣልቃ እንዳይገባ ጥቅምት 6 ቀን 2002 . በቁጥር 44/70/2002 መመሪያ ወጥቷል፡፡ የሀዋሳን ግጭት ለማብረድ በብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ የተመራው አጣሪ ቡድን ያቀረበው ሪፖርት ግጭቱ የተከሰተው ተስፋ ኪዳነ ምሕረትና ፀረ ኤች አይ ኤድስ ማኅበር እና "ማኅበረ ቅዱሳን" ባስነሱት ሁከት መሆኑን ይገልጽና ተስፋ ኪዳነ ምሕረት ማኅበርን ጨምሮ "ማኅበረ ቅዱሳን" እንደማንኛውም ተቋምና ግለሰብ አስቀድሶና ተገልግሎ ከመውጣት በስተቀር በቤተክርስቲያን አስተዳደራዊ ጉዳይ ጣልቃ እንዳይገቡና በዐውደ ምሕረት ላይ እንዳያስተምሩ፣ የካቲት 2 ቀን 2003 . በቁጥር 92/54/2003  ከቅዱስ ሲኖዶስ /ቤት መመሪያ ተላልፏል፡፡
‹‹የተሰደዱት የሀዋሳ ምዕመናን፣ ምዕመናትና የሰንበት /ቤት ወጣቶች ሥርዓተ ቤተክርስቲያን እንዲከበርና ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ለ‹ማኅበረ ቅዱሳን› ወግነው ባደረሱት የመልካም አስተዳደር በደል ሳቢያ ከሀገረ ስብከቱ እንዲነሱ ባካሄዱት የአንድ ዓመት 8 ወራት የመብት ጥያቄ እንቅስቃሴ መሠረት፣ የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልዓተ ጉባዔ ስብሰባ ተጠርቶ ጉዳዩን ከመረመረ በኋላ ሌላ አጣሪ ኮሚቴ ለአራተኛ ጊዜ ወደ ሥፍራው እንዲላክና ችግሩን አጥንቶ ለግንቦት 2004 . እንዲያቀርብ ወስኗል፡፡ እስከዚያው ድረስም ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ሁሉንም ልጆች አቅርበው አስማምተውና አቻችለው በአባትነትና በልጅነት ስሜት ሠላም እንዲያሰፍኑ ከቅዱስ ሲኖዶስ /ቤት ታህሣሥ 26 ቀን 2004 . በቁጥር //200/27/04 መመሪያ ተሰጥቷቸዋል፡፡››
አባ ገብርኤል ግን እነዚህን ሁሉ ውሳኔዎች ወደጎን ትተውና ሁሉንም የቤተ ክርስቲያን ልጅ በእኩል አይን በመመልከት የአባትነት ሀላፊነታቸውን በመወጣት ፋንታ አለአግባብ ያሳደዷቸውን የሀዋሳ ምእመናን፣ ምእመናትና የሰንበት ተማሪዎች ይበልጥ ለማናደድ በሚል የማህበረ ቅዱሳን ጭፍን ደጋፊ ሆነው ባዘጋጁት ጉባኤ የቤተ ክርስቲያን ሳይሆን የማህበረ ቅዱሳን አገልጋይነታቸውን በተግባር አሳይተዋል፡፡   

36 comments:

 1. የሲኖዶሱ ውሳኔ በእርግጥ ተጥሶ ከሆነ ደንብ መጣሱን ማሳወቃችሁ ትክክል ነው ፡፡ ነገር ግን እኛ እንድንማርበት ስለተላለፈው ወይም ሰለ ተሰጠው ትምህርት ግድፈት አንድም አላላችሁም ፡፡ መልካም ስብከት ከነበረ እግዚአብሔር ይመስገን ፤ ምእመኑ በእናንተ ሽኩቻ ምክንያት እንዳለፈ ሳያነግስ እንደተመለሰበት ፣ ዛሬም ሳይማር አለመመለሱ ጥሩ ነው ፡፡ የትምህርት ስህተት ከነበረ ግን አብራችሁ ማውጣት ይገባችሁ ነበረ ፡፡ አበበ ስለ ኢየሱስ በሥርዓቱ ካስተማረ ፣ ከበደ እኔ አላስተማርኩም በማለት ሊያኮርፍና ሊቆጭ አይገባውም ፡፡ ማለትም ዓላማችሁ አንድና አንድ እስከሆነ ድረስ ማን አስተማረ ማን ሊጨንቃችሁ አይገባም ፡፡ ወንጌልን ማስተማርና ማሠራጨት የሚለው ርዕስ የጋራ አጀንዳችሁ ከሆነ ማለቴ ነው ፡፡

  እግዚአብሔር ሰላምን ለቤተ ክርስቲያናችን ያምጣ

  ReplyDelete
  Replies
  1. dude this guys are protestants that's why they write anonymously. If they have truth,they should exposed themselves.

   Delete
 2. "እስከዚያው ድረስም ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ሁሉንም ልጆች አቅርበው አስማምተውና አቻችለው በአባትነትና በልጅነት ስሜት ሠላም እንዲያሰፍኑ ከቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ታህሣሥ 26 ቀን 2004 ዓ.ም በቁጥር ል/ጽ/200/27/04 መመሪያ ተሰጥቷቸዋል"

  "ሁሉንም ልጆች አቅርበው አስማምተውና አቻችለው በአባትነትና በልጅነት ስሜት ሠላም እንዲያሰፍኑ" is not suitable ለብፁዕ አቡነ ገብርኤል and he is not capable of doing it and he is not willing at all. As a child of the orthodox church I respect him, unfortunately, he never take side with the truth. I had a chance to meet him a couple of times and told him to side with the truth even though there is no comfort in doing that. He prefers to follow the wind and he has survived so far. There was one GUBAE which he was part of it and when MK systematically destroyed the GUBAE and kicked all member out of church, he came to those children of GOD in ELPA ADARASH and told them he can not do anything. They were begging him why they are treated as step-son and step-daughters. His final word was he does not have "THE KEY" for "BETE KEHENET ADARASH" and he also said "THE PATRIACH" does not have it either. I remember on priest asked him while he was crying about the injustice. He said to him "I tought our Lord Jesus Christ gave you the key, how can you say i Don't have it".

  The word of God states

  "To the elders among you, I appeal as a fellow elder and a witness of Christ’s sufferings who also will share in the glory to be revealed: Be shepherds of God’s flock that is under your care, watching over them—not because you must, but because you are willing, as God wants you to be; not pursuing dishonest gain, but eager to serve; not lording it over those entrusted to you, but being examples to the flock. And when the Chief Shepherd appears, you will receive the crown of glory that will never fade away"
  1 Peter 5

  please God have mercy on him

  ReplyDelete
 3. Dn. Daniel besinodos endayastemir tekelkilo neber ende? Can you tell us more about that please, thanks. This is something new for me.

  ReplyDelete
  Replies
  1. mahebere kidusan tekelkelo neber. awasa lay manew yemaheberu abal endaysebke tekelkelowal. daniel degmo yemahebeu abal silehone endesenoduse wesane mesebek aychele nebre

   Delete
 4. Why they ignored megabe hadis begashaow? Practicaly he is more qualified than all. The issue is telfo metal. Eotc erkesoal mk balubet location so all eotc do not involves any spritual activities with mk elements. Woguze yekun besem aryos. Mk please leave our church. Now day they call patriarc pulos menafek in andadregen blog. Who you are?

  ReplyDelete
 5. gubae mederegu melkam new . neger gin bizuhanu miskin tesedo eyale tikit habtamina mahiberekidusan le rejim gize yakedut gubae new. gin iko nituhanun behaset weyini keto lelaw endiseded tedergo tsedk ale? miyasazinew alamawen lemasakat yemaytaweku na ke adis abebana kelelochi ketemoche memtatachew new .ibakacihu hulachinem yeand abat lijoche nen .nege asado mesaded linor endemichil enaseb.hulachinm beamlak fit ekul nen habtam diha isu ga yelem.yemimeka beigzabeher yimeka.bizuhanu fitlafit baywetam mahberekidusan ina agarochu bemiserut sira aznwal nege gefto kemeta gin yih hizbi endeneb yiwerachihwal. AYEMSELACHEHU!!!

  ReplyDelete
 6. EWNETHINI NEW AHUN AHUN KEJERBA YALEW SEW BEZMTA MAYET YEFELEGE AYMESLM. HEDO HEDO ENDE BEREDO YEWERDBACHEWAKL. BETELEYAYU MENGEDOCH HIZBUN WEDENESU LIWESDU BIFELIGUM HIZBU KE ANGET BELAY HONOBACHEWAL. SILEZIH MAK TEGENTELO RASEN KEMESKEL NA ERASACIHUN TSADIK KEMADREG LELAWNM HATIAN KEMADREG TETEBEKU!!!!!!!!.........እግዚአብሔር ሰላምንያምጣ.

  ReplyDelete
 7. " Mk please leave our church." behasabeh alsmamam 'neseha gibuna wede hizbu temelesu' bitel yishalal......eyeseru yalew kifat ena hatiyat endihbiyasbelim.joro yalew yisma!!!

  ReplyDelete
 8. Daniel kesiret where and when he had attended church education? Please be make sure a big d/f b/n church education and scientific understanding. Daniel so far is the huge problem of our church bakhe neseha geba kureb geta bemederk aygegm. Geta be derget yelem. Yewahe hun. Wondemoch atasaded yibekah. Gojam hid.

  ReplyDelete
  Replies
  1. I am addicted with his writings in his blog,he doesn't write useless things un like abaselama & other blogs. He is a very knowledgable person. I changed my social & spritual life b/c of him. U & ur brothers accused him b/c u don't compete with him.

   Delete
 9. EPRDF gov. has granted freedom and equality for all nation. The south no more say yes indirect colonization such like before. The fundemetalist play key role to be supper power by leading of eotc medric, but Ethiopian gov. offerd all nation equal. Daniel stop abusing south.

  ReplyDelete
 10. Wey Gud ahun enanete sele sinodos heg metas new yanadedachehu? ene gin ayemesegnem sele dingel mareyam, selkidusan amalajenet yebetekereseteyan sereat yetebeke temehert endemeyasetemeru enzhi memeheran yewechewem yeager westem hizibu tenkeko yawekal minalebat yehe yehonal enaneten kir yasegnew ayezoachehu enanetem yebetekereseteyann serat yetbeke temehert kastemarachehu enantem yefekedelachehual

  ReplyDelete
 11. Ante yetafek meseleh yemot. Ready to learn bible instead teret.

  ReplyDelete
 12. Yebetketstian mederk ye daniel yesegera mewotacha aydelem USA 2004

  ReplyDelete
  Replies
  1. የበጋሻው እንጂ፨

   Delete
  2. ዳንኤል ወንጌልን በማገልገል በኩል የሀጋሻውን ጸጋ ለማግኘት በትንሹ 50 ጊዜ እየተሻሻለ መፈጠር አለበት፡፡ ዳንኤል ወንጌል እንኳ ከተአምረ ማርያም ጋር ያለው ልዩነት ገና ያልገባው ሰው ነው፡፡ እርሱና ላለበት ማህበር ማኅበረ ቅዱሳን ኢየሱስ ክርስቶስ መወለዱን እንኳ የሰሙ አይመስለኝም፡፡ ስለዚህ እኛም አዳኙ ከተወለደ 2000 አመት ሞልቶታል፡፡ እንደ አይሁድ የራሳችሁን ኢየሱስ እየጠበቃችሁ በከንቱ አትድከሙ እንላቸዋለን;፡፡

   Delete
  3. Do you talk about Jesus? Poor guy! you don't know about creation. You said በትንሹ 50 ጊዜ እየተሻሻለ መፈጠር አለበት፡፡ You are making fun on the Lord creation. That shows me you are a non beliver.

   Delete
 13. daniel malet yesefer woregna mehonun silaweku new aba gebreal yeterut be colage menfesawi digry endelelew yitawekalsilezih le hawassa mie menan yemimetin menfesawi ewket yelewm hizbu betam kedmo wengel yegebaw mehonun betedegagami asaytoal melake mihretn yemeselu talak abat yewongel gebere balubet bota zebenen yemesele hod amlaku yemichurechirewn gura hzbu aysemam

  ReplyDelete
 14. business man '' zebene lema '', tertgnawo daniel and zefeagnue ye yakaw tewodros are they christians ? all are acused by adultery or zemut .

  ReplyDelete
 15. ኧረ ባክህ አማርኛ እንኳን መምረጥ አትችልም እንዴ?

  ReplyDelete
  Replies
  1. what do you mean? Just read and if you don't match it throw it away, your positive response is very constractive for some one who is weak in his PRN thoughts. I ask your time and please to read the following feedback. Thanks and here it is:
   የዛሬ ሃያ ሥድስት ዓመት አካባቢ አንድ የስምንት ዓምት ህፃን ልጅ በወቅቱ አርባዎች ውስጥ በሆነ ብሩክ በሚባል ሰው መጫወቻው ተይዞበት እንዲለቅለት በዙ ጊዜ እቤቱ ተመላልሶ ያጣዋል። ሌላ ሰው እንዳይሰጠው ደግሞ ብሩክ ያስቀመጠው በግራ እጁ ስለ ሆነ ማንም ዕቃውን አግኝቶ ሊሰጠው አልቻለም። ብሩክም እኔ እራሴ መክሬው ዘክሬው እሰጠዋለሁ በማለቱ፣ የልጁ ወሳጆች ደግሞ የልጃቸውን ዕቃ መመለስ በተመለከተ መሪር ለቅሶ በብሩክ ሥውር መልካምነት ጆሮ ዳባ ብለው ገና ትቀምሳታለህ ዓይነት አባሱበት፡; በዚያው ሰሞን የጌታችን ጥምቀት ስለነበረ የልጁ ወላጆች ግቢ ውስጥ ቅርጫ ታርዶ ለመከፋፈል ከታደመው ሰው መሀል የልጆች አባት ትልቁ ብሩክም ነበርና ከህፃኑ ጋር ፊት ለፊት ይተያዩ ጀመር። ታዲያ “የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳም” ሆነና ልጁ በአጋጠመው ተጠቅሞ ድምፅ ማሰማት ጀመረ፤ እንዲህ ሲል፥ አንቱ የሚለውን አንተ ብሎ “የብሩክ ስም ይቀየር” አለ። ሁሉም ጸጥ እንዳሉ ሥጋውን እኩል በማከፋፈል ያሉት በሬ አራጅ ሰው ብቻ ቢላቸውን እየሳሉ “ማን ልትለው ፈለክ ደግሞ” ብለው በመቀጠል “ልጅ ነገሮች በግልጽ ይታዩታል” አሉና ለልጁ “በል አዲሱን የብሩክ ስም ንገረን ዳቦም አያስፈልግ ጥሩ ጊዜ ነው።” ብለው ደስ የሚል እና ቅርጫ አራጅ የሚለውን ደግሞ አዲስ ስም እንዲሰይምላቸው የፈለጉ ይመስል ድምፅ እንዳይረብሸው ቢላ መሳሉን ቆም አደረጉለት፡; ህፃኑም “ለሰው ልጅ ስም መውጣት ያለበት አድጎ ተግባሩ በሚሠራው ሥራ እየታየ መሆን ነበረበት።” ብሎ በመቀጠል “ለምሳሌ እኔ እንዳልኩት ቢሆን ኖሮ የጋሼ ብሩክ ስም ጋሼ እርኩስ ይሆን ነበር።” ሲል ግማሹን አስቆ ሌላውን ደግሞ አስደንግጦ ከሁዋላው ነብር እንደተከተለው ፍየል ተፈተለከ። ስለዚህም የማህበረ ቅዱሳን ሥራ እየዋለ ሲገለጽ ትክክለኛ ስሙን ማግኘት ይገባዋል። ማህበረ ቅዱሳን ማለት ፍቅርን የማይወድ የፍቅር ቂመኛ፣ ጳጳስን ከጳጳስ፣ ቤተክርስቲያንን ከቤተክርስቲያን፣ ቄስን ከቄስ፣ ምዕምናን ከምዕምናን፣ ወጣቱን ከወጣት፣ቤተሰብን ከዘመድ፣ ሚስትን ከባል፣ ልጆችን ከወላጅ እና ሕዝብን ከሀገር እያጋጨ የሚሳለቅ የበግ ለምድ ለባሽ የተዋጣለት እርኩስ የደህንነት ድርጅት ነው። ብጹዐን ጳጳሳት በፍጹም እንዲታረቁ እንደማይፈልግ ከአባሎቹ ፉከራ ታውቋል። የእባቡ (የማህበረ ቅዱሳን ድርጅት) ጂራቱ ተቆርጧል፤ ጭንቅላቱ ነው አራት ኪሎ እና ስድስት ኪሎ የመሸገው። ለእርሱም የሚመለከተው ክፍል ጸሎቱን በሱባዔ ጀምሮለታል እናም በቅርቡ በራሱ አንደበት ማንነቱን ይፋ ሲያደርግ ተብትቦ የያዛቸውን በጎች ይለቃቸዋል። በጎቹም ሞቶ እንደተነሳ ያህል ለዓምላካቸው ይቅርታን በንሰሀ ይጠይቃሉ፤ እባቡንም ጭንቅላቱን ይቀጠቅጣሉ፤ ያን ጊዜ አባቶች በፍቅር ተሸንፈው ይታረቃሉ፤ በጎቹም (የአደራ ልጆቻቸውም) በለመለመው መስክ ምግቡና መጠጡን እንደልባቸው ያገኛሉ፡; ጊዜውም የዐብይ ጾም ወቅት ሰለሆነ እኛም በጸሎት ተግተን እናግዛለን፡; ወሥብኃት ለእግዚአብሔር።

   አንተ በለምድ የተሸፈንክ ማህበረ ቅዱሳን፣
   ወይም ልበልህ ‘አሳሳች ማህበረ ሰይጣን’ ፣
   በገዛ እጃችን ከማብዛት መከራን ፣
   ሞትን እናስተግድ ድምጻችንን ቀብረን፣
   የንስሀን ጊዜም አሟጠን ጨርሰን፣
   እሄው ቁጭ ብለናል ፍርድን እየጠበቅን፣
   አንተ በሄድክበት እኛም አልተከተልን፣
   ምክንያት በመፈለግ እየተጠቃቀስን፣
   እየተረዳዳን ጉድጔድ እየቆፈርን፣
   እርቀን ሄደናል መመለሻም የለን፣
   እዛው በፍርድ ቀን እንናገኛለን፣
   በጻድቃኖቻችን እየተስተናገድን፣
   ከናሺቭል ቴንሲ ፓስፖርታችን ይዘን፣
   አንተ ወዲህ ስትቀር እኛም እንገባለን፣
   መንገዱ እንዳይጠፋን በድንግል ታጅበን።

   Delete
 16. The south called prime minester Melese freedom father similar to Nelson Mandela who fought apartide to stop segergation. Eotc no more safe heaven for neftegna. Daniel speaker wolayta listner no way thanks to Melese we all equal.

  ReplyDelete
  Replies
  1. I thought you are smart enough who stragle to learn a new idea and rash yourself to the 22nd century thinking style, but, not yet, you are under the lid of the pot instesd. Waw,waw, wawwww. Read or ask someone read for you this tip, if it helps boost your mind:
   አላስችል ብሎህ መዘዝከው የዘር አረግህን፣
   ባንዳ መሆንህን፣
   እየጠራህ አጎትህን፣
   እያስመለስክ አብረህ የበላኸውን
   እያስታወክ ዱሮ የሰራኸውን፣
   አንተ በለምድ የተሸፈንክ ማህበረ ቅዱሳን፣
   ወይም ልበልህ ‘አሳሳች ማህበረ ሰይጣን’፣
   በገዛ እጃችን ከማብዛት መከራን ፣
   ሞትን እናስተግድ ድምጻችንን ቀብረን፣
   የንስሀን ጊዜም አሟጠን ጨርሰን፣
   እሄው ቁጭ ብለናል ፍርድን እየጠበቅን፣
   አንተ በሄድክበት እኛም አልተከተልን፣
   ምክንያት በመፈለግ እየተጠቃቀስን፣
   እየተረዳዳን ጉድጔድ እየቆፈርን፣
   እርቀን ሄደናል መመለሻም የለን፣
   እዛው በፍርድ ቀን እንናገኛለን፣
   በጻድቃኖቻችን እየተስተናገድን፣
   አንተ ወዲህ ስትቀር እኛም እንገባለን፣
   መንገዱ እንዳይጠፋን በድንግል ታጅበን።

   Delete
 17. ለደጀሰላም ከተላከው አስተያየት የተወሰደ-
  ለጥፋት የተዘጋጀት ከተማ ምንም ብትነገር አትሰማም እንዲሉ ሆኖ በዚሁ ብሎግ ላይ ዘመድኩን ሲዖልም የሚያወርደኝም ቢሆን አልታረቅም ብሏል ብላችሁ ዜና ስትሰሩ ተዉ! እርቅ ይሻላል፣ መታረቅ በሰውኛነት መከባበር እንጂ የሃይማኖት መለዋወጥና መጋራት አይደለም ብንል ጎበዙ፤ ደፋሩ፣ ሰማእቱ እያላችሁ ሃይማኖታዊ ሳይሆን በስሜትና በአንሸነፍም ድፍረት ለተነበያችሁት እስር ቤት አደረሳችሁት። ሊሆን ባልተገባው 5 ወራት የእስር ውሳኔ ካገኘም በኋላ ቢሆን የቅጣት ማቅለያ ሃሳብ አቅርቦ ወደ 3 ና 4 ወራት ዝቅ ቢልለት ወይም እስራቱ ወደ ገንዘብ እንዲቀየርለት መጠየቅ ሲገባው ዛሬም ሲዖልም እወርዳለሁ ባለው አቋሙ ላይ ጸንቶ፣ እናንተም ደግሞ ሰማእቱና ጀግናው ልጃችን ኦርቶዶክስን ሊያኮራ በተሰጠው ውሳኔ ጸንቶ የቅጣት ማቅለያ ሃሳብ አላቀርብም ብሎ በልበ ሙሉነት ተናግሯል ስትሉ አሞካሻችሁት። የሚያሳዝነው ደግሞ የቅጣት ማቅለያ ሃሳብ ከማቅረብ ይልቅ በይግባኝ ሙግቱን ለመቀጠል የተሻለ ነው ስትሉ ይግባኝ መጠየቅ ምንጊዜም ሁሉንም ነገር ያስቀራል ማለት ብቻ ሳይሆን የተወሰነው እንዲጸድቅ ወይም አንሷል ተብሎ ሊያስጨምር እንደሚችል ባለማሰብ የከዚህ በፊቱን ስህተት እንደገና በመድገም ሊጠናቀቅ እንደሚችል ያለማስተዋላችሁ እጅግ አስገርሞኛል። ከዚህ ሁሉ ምነው የቅጣት ማቅለያ አላቀርብም ብሏል የኛ ጀግና ከምትሉ የ5 ወራት እስራት ወደ2 እና 3 ወራት ዝቅ እንዲል ወይም ወደገንዘብ እንዲቀየር ያልመከራችሁት?
  ኩሲን መሰላችሁብኝ!!

  ReplyDelete
 18. Daniel ebakeh dan wondemeh masaded akum. Sira felege. Kese aydelehem lemen begezeh tekeledalhe. And wondeme daniel besynodos tekele woye lalekewo synodose daniel kese aydelem dacon aydelem bemenem muya selemsyawokewo askedash sifelege akabet yemegebera hone gebere bet shomotal. Legojam debetera not for awassa.

  ReplyDelete
  Replies
  1. I read so many times in this blog,the word Gojjam, Gojjam. I don't feel good. Why u don't judge persons by their deeds rather than their birth place. I was reading & trying to understand the purpose of Aba selama. But Tertir,until now other Ethiopian people said us so many many false things. Enante behageritu bitnegsu demo sayibis ayikerim. Ere Legna yemihon manew?

   Delete
 19. Zebene or zebegnawo has 18 girls with side of wife shame on him.

  ReplyDelete
 20. በጣም የሚያሳዝነው ገና የእ/ር አፈጣጠር እራሱ አልገባችሁም ቁጭ ብላችሁ ተማሩ

  ReplyDelete
  Replies
  1. አይሞኞ!! የማቅ ወንጌል ይኸው ነው፡፡ የእ/ር አፈጣጠር አልክ እግዚአብሔር ፈጣሪ እንጂ ፍጡር ዐይደለም እኮ!! ለነገሩ አይፈረድባችሁም ሰውን ከማሳደድ ውጭ ሌላ ስለማያስተምሩዋችሁ የምትናገሩትን አታውቁም፡፡

   Delete
  2. እ/ር በየት አገር ቋንቋ ሆኖ ነው እግዚአብሔር ተብሎ የተተረጐመው ፡፡ ኧረ ያልገባንን እየተጠያየቅን እንማማር ፤ ደግ አይደለም ይሄ አካሄድ ፡፡ ሁለታችሁም ጋር የቋንቋ ግድፈት አያለሁ ፡፡ እግዚአብሔር ማለቱ ከረዘመብን እግዜር የተለመደ ነው እ/ር በአጽህሮተ ጽሁፍ ህግም ቢሆን በትክክል አያሰኬድም ፡፡ መነሻና መድረሻ ፊደል እንዲህ ያገለግላል የሚል ህግ እኔ አላውቅም ፡፡ ዶክተር ከሚለው ዶ/ር ማለት ይቻላልና ከሆነ ያ እንግሊዝኛውን የተከተለ Dr የሚለውን ያገናዘበ ነው ፡፡ እንዲህ እየደከምንና እየሰለችን ፣ ትዕግሥትም እያጣን ከሄድን ኢ/ስ ማለት ኢየሱስ ነው ልንል ነውና ፣ በአምላክ ስም አጽህሮተ ቃል አንጠቀም ፡፡ የቃሉን ትርጉም ያበላሻል ፡፡ ሙሉው ቃል አድማጭ ከተገኘ የሆነ መልዕክት ያስተላልፋል ፡፡

   Delete
  3. ስላመ ክርስቶስ ይብዛላችሁ! እግዚአብሔር ወይም እ/ር በሚለውን ስለ አምላክ ላይ ስለተባለው ጥቂት ለማለት ስለፈለግኩ ነውና ታገሱኝ። የጥንቶቹ የእምነት ሰዎች ወይም አባቶች እንዲህ እንደ ዛሬው ዘመን አንደበታቸውን በከንቱ የማይላቅቁ፤ አእምሯቸው ያፈለቀውን ወደ እጃቸው አዝልቀው እንዳገኙ የማይከትቡ፥ ግን ለሚያደርጉትና ለሚናገሩት ማንኛውም ነገር ሁሉ ተጠንቅቀውና በማሰብ አጢነው የሚከውኑ ነበሩ። ክርስትናቸው የሰጣቸውን መብትና ግዴታም ጠንቅቀው የሚያውቁና የገባቸው ነበሩ። የዛሬው ዘመን ግን እውቀቱ ሳይኖረው ግን ያለው መስሎ በመቅረብ፥ በጥራዝ ነጠቅ ምላስ፥ በመንገድ ትምሕርት አባቱን ሲሰድብ፥ እናቱን ሲራገም የሚሰማና የሚታይ ለመሆኑ ይህ ከላይ የተጻፈው ጽሁፍ ዋና ምስክር ሊሆነን ይችላል። ኧረ ለመሆኑ መቼ ይሆን ለአባቶች ክብር የምንሰጠው? እውቀቱም ሥልጣኑም ችሎታውንም የሌለው ሁሉ በክምፒውተር ጥላ ተጠልሎ ያሰኘውን በጥላቻ፥ በቂም፥ በቅናት ፈረስ ሌጣውን እየጋለበ ጦሩን የሚሰብቅ ከሆነ ክርስትናችንን ልንመረምር ይገባል። ክርስቶስ ለአንተና ለመሳይዎችህ፥ ለአንቺና ለመሳይዎቻችሁ ብቻ አልተሰቀለም። ክርስቶስ ለስታሊን፥ ለሂትለር፥ ለቻርለስ ቴለርም ተሰቅሏል። ብጹ ጊዜ ጽሁፎቻችሁን እንዳነበብኩት ከሆነ፥ ሆድ የሚያባብስ፥ እሳት የሚጭር፥ ሰላም ፈጽሞ ወደ ኢትዮጵያውያን በተለይ ወደ ቤተክርስቲያን እንዳይገባ የሰይጣን መልእክተኛ የሆኑ ጽሁፎችን ነው የምታቀርቡት። እባካችሁ ልባችሁ የይቅርታ ይሁን! እናንተን ሁሉን የምታውቁና ለእውነት ታጋይ ያደረጋችሁ ማን ነው? ለመሆኑ የራሳችሁ ማንነትት፥ ማለቴ ክርስትናችሁን ለመመርመር ጊዜ ወስዳችሁ ታውቃላችሁ? እግዚአብሔር ይቅር ይበለን ሁላችንንም።….. ስለ እ/ር የተሰጠው ትርጉምና ምሥጢር ማመሳጠር ከአላዋቂዎች ጎራ የተባለ ስለሆነ ከላይ እንዳልኩት ጥቂት ልበል። የጥንት የእምነት ሰዎች የሚያደርጉትን የሚያውቁ ናቸው። እ/ር ብለው የእግዚአብሔርን ስም ሲያሳጥሩ ፈጣሪ ኵሉ-ዓለም ከማክበርና በፍርሃት ከመንቀጥቀጥ የተነሳ ነው። አይሁዳውያን YHVH (ዮድሄዋሄ) የሚለውን ፈጣሪ ልጠራበት ብሎ ለነቢይ ሙሴ የተሰጠውን ስም በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ያም በፋሲካው በዓል ጊዜ ብቻ በታላቅ ፍርሃት ለመሥዋዕት ማቅረቢያ ይጠቀሙበት ነበር። ከዚህም የተነሳ YHVH ተብሎ የተጻፈውን አዶናይ እያሉ ያነባሉ። ይህም በመሆኑ አበው የእምነት አባቶቻችን የፈጣሪን ስም ከማክበራቸውና ከመፍራታቸው የተንሳ ኃያልና ታላቅ ስሙን ሙሉ ለሙሉ ለመጥራት ከመፍራታቸው የተነሳ እ/ር ብለው አስቀምጠውታል። በእንግሊዝኛውም G-D ብለው እንደሚጠሩት ማለት ነው። ስለዚህ ወገኖቼ ስለምናውቀው፥ ጠልቀን ስለተረዳነው ነገር እንበል፥ እንጻፍ። የኢንተርኔት ምሁር ሆነን ያሰኘንን፥ የመሰለንን በስሜትና በግልብ እውቀት እየተመራን የወንድማችንን ልብ አናሳዝን። የስማችንንም እንኑር። ክርስቲያን ነን በግብርና በእምነትም ሆነን እንገኝ። ክርስቶስን እንምሰል። ደጀ ሰላም ነን እያልን ቅኔ ማኅሌታችን የአምባጓሮ፥ የክርክር፥ የመለያያ ወረብ የሚወረብበት፥ መቋሚያ የሚሰበቅበት አይሁን። ሁላችንንም እግዚአብሔር ይሁነን። አሜን!

   Delete
  4. እ/ር የሚለው አጽህሮተ ቃል እንደ እግዚአብሔር የተተረጐመበት መጽሐፍ ካለህ ብታሳውቀን ደግ ነው ፡፡ እኛ በአይሁድ እምነት ውስጥ አይደለንም ፡፡ አምላካችንን እስከ ዛሬ ድረስ ለመጥራት ተሸማቀን አናውቅም ፡፡ አይሁዶች ስለ አምላክ ስም አጠራርና አጻጻፍ እጅግ ብዙ ስለሚጨነቁ ፣ በመጽሐፍ አተረጓጐማቸውም ስለ አምላክ ስም የሚያስጠነቅቀውን በራሳቸው ስልት ስለሚያዩት ያስኬዳቸዋል ፡፡ እስከዛሬ ድረስ በኢትዮጵያ ቋንቋ ጽሁፍ ውስጥ እንዲህ የሁለት ፊደል አጠራር አላየሁም ፡፡ ለወደፊቱ እንዳንደክም ማስረጃህን ጨምረህ ብትጠቁመን ለእኛ ለችኩሎቹ ትምህርት ይሆነናል ፡፡

   Delete
 21. Please do not tell us that the main point is the content of the lesson ,not whether it is delivered by Daniel, Begashaw or Zebene . I strongly argue that the question of who is who? who does what? Why and how he or she does it matters a lot. An arguement that separetes the doer of the action (he or she) from the very suject to be acted on does neither hold water nor make any sense at all. This is very true when it comes especially to the Great Book (the Bible) which has deeb meaning and/or contniued to be very suceptible to very wide and different interpretations . I strongly believe that unless we have a rational and fairly good infomation and obsevation or knowledge for that matter about the preachers , there is no doubt we will be lost in a situation that is controlled by kind of misleading and disingenous teachers or preachers. And this is a very harmful practice not only to our religious/spritual lives but also to our day- to- day earthly lives. I do not know how the arguement that the teachings delivered by some very "smart" preachers like Zebene Lemma are OK as long as they are in line with the basic teaching of the Book even using the very emotinally charged rehetorics. I often hear from almost all followers of the Church and clergymen saying a kind of very absurd advices like," Do not follow what I am doing but give attention to what I am saying or preaching." Yes,as a general principle, we must not undermine our beliefs for the simple reason a clergyman does violate what he preaches. However, as a matter of practical aspect of our religious practice , this arguement sounds so clumsy and misleading. How innocent followers are expected to accept and respect a lesson delived by a preacher who claims to be the messanger between God and His peaple does practice contrary to what he preaches about? I am afraid that this kind of very common and disingenous way of thinking and practice is highly harmful to the very essence of faith itselsf. Should the followers of the Church be blamed or condemned if they question the credibilty of their faith which is being violated by a religious leader or any other clergyman ? I do not think so.

  Although I have no investigative and objective information , I do not think it would be sinful to say that preachers - very good orators like Zebene Lemma are desperately using religion as a very fantastic source or means of a very good standard of living . I am sure most people who are genuinely concerned about their faith share this kind of very unfortunate trend of religious mentality - changing the very purpose of religious teaching into just like any other way of doing business without worrying about cost-benefit analysis. This comment of mine sounds harsh or even rude or impolite or immoral/unethical to some of innocent believers . Unfortunately that is the way it is!! There is no any other way to tell about it.

  Believe or not , like it or not, unless the innocent followers of the Church get out of the undesirable tradition of " we have nothing to do, and we do not worry about anythingelse,but just going to church at least every sunday and attend the mass service, pray and listen what the preachers want to say" ,the mischievous practices by those who are using the church as a good source of business will continue . I do not know if Juses Christ thaught that those clergymen should not be responsible to the people and accountable to their terrible wrong doings. I have an impression that many of our religious leaders and other clerymen want to convince us that they are responsible and accountable to the judgement after death, not to the people they serve right here on earth.To this end, they use the merciful Father as scary as possible.

  May God give us the true hearts and minds so that we would be people of love and peace on earth and people of His ever lasting world !!

  ReplyDelete
 22. ማር ቆራጭ ፣ ማር ሲቆርጥ መላሱ አይቀርም ፡፡ የሚያርስ በሬን አፉን አትሰር ተብሏልና ፣ በሚሰሩበት መስክ መጠቀማቸው ባልከፋ ፡፡ ነገር ግን ለምእመን የተረፈው ዕዳ የእኔን አዳምጥ ጦርነቱ ዳፋ ነው ፡፡ ይኸ ደግሞ ከየት መጣ ቢባል ከጥቅም ግጭት እንጅ መቶ በመቶ በሃይማኖት ዶግማና ቀኖና ልዩነት ላይ ያተኮረ አይደለም ፡፡ እሥራኤላውያን ከፋርስ አገዛዝ ነጻ ሲወጡ ፣ ከሁለት ተከፍለው እስከ መጋደል ደርሰው ነበር ፡፡ እኛም ቤት የዛ ዓይነት ትግል እየተካሄደ ይመስላል ፡፡ ከሶሻሊዝም ውድቀት በኋላ መብቶች ተረጋግጧል ሲባል የነጻነት ምልክቱ በሃይማኖት ጉዳይ መባላትም አንዱ ሆኗል ፡፡ ከነበጋሻው ብትሄድ ማኀበረ ቅዱሳን አውጋዥ ነው ከሌሎቹ ደግሞ ብትሰለፍ ተሃድሶ ነኝ የሚለው ወቃሽ ነው ፡፡ በዚህም ምእመን ሳይወቀስ የሚያመልክበት ሥፍራ እያጣ ነውና ሁሉም ራሱን መርምሮ ለሰላም መፈጠር ትንሽ አስተዋጽኦ ቢያደርግ መልካም ነው ፡፡

  ReplyDelete
 23. what happen? why? U are post our comment b/c you are not understand what you are doing. pleas brothers do not talk about others see your self.

  ReplyDelete