Wednesday, March 7, 2012

ዘመድኩን በስም ማጥፋት ወንጀል 5 ወር ተፈረደበት - - - Read PDF

ዘመድኩን ወንጀሉ እንደ ሰማዕትነት እንዲቆጠርለት ማሰቡና ደጀሰላም ድረገጽም ይህንን ማስተጋባቱ ብዙዎችን አስገርሟል
 በመጋቤ ሐዲስ በጋሻው ላይ የስም ማጥፋት ወንጀል የፈጸመውና ጥፋተኛነቱ በፍርድ ቤት የተረጋገጠው ዘመድኩን በ5 ወር እስራት እንዲቀጣ ብይን ተሰጠ፡፡ ማህበረ ቅዱሳንን ተገን ስላደረገ ምንም እንደማይሆንና ለወንጀሉ ሃይማኖታዊ ገጽታ በማላበስ፣ በተጨብረበረ ሰነድ ፋይሉ እንዲዘጋ ሙከራ እስከ ማድረግ ሙከራ አድርጎ የነበረው ዘመድኩን የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ /ቤት አራዳ ምድብ ችሎት የካቲት 27 ቀን 2004 . በዋለው ችሎት በ5 ወር እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡
ዘመድኩንን ከኋላ ሆኖ በርታ ሲለው የነበረው አዝማቹ ማህበረ ቅዱሳን ጠበቃ አቁሞለት በአስቂኝ መከራከሪያዎች ሲሟገትለት የቆየ ቢሆንም፣ ቴፎዞዎችን በመሰብሰብና በማጫፈር ያልተደረገውን ተደረገ እያሰኘ በድረገጾቹ ሲደግፈው ቢቆይም፣ ‹‹እጄ ረጅም ነው የትም ይደርሳል›› እያለ በመመካት ምንም አይደርስብህም ቢለውም ፍርድ ቤት ግን ጥፈተኛነቱን ስላረጋገጠ ወንጀለኛ ብሎታል፡፡
ዋናው ነገር ዘመድኩን ለሰራው ወንጀል ጥፋተኛ መባሉ ሲሆን፣ የስም ማጥፋት ወንጀሉን ለወንጌል ሲል እንደተቀበለው መከራ እንዲታይለት ማሰቡና ደጀሰላም ድረገጽም ይህን ማስተጋባቱ እጅግ አስገርሟል፡፡ ዘመድኩን ‹‹ዛሬ ወደ እስር ስሄድ አባቶቼ ስለ ቤተ ክርስቲያን በተቀበሉት ፈተና ካገኙት ጸጋ በረከት እንደምሳተፍ አምናለኹ፡፡ በዚህም ደስ ይለኛል፡፡›› ማለቱ ተራ ማጭበርበሪያና ራሱን ለመሸንገል ያወራው ተራ ወሬ ካልሆነ በቀር ከእውነታው ጋር ፈጽሞ የማይገናኝ መሆኑን ከጭፍን ደጋፊዎቹ በቀር ማንም ሰው የሚያውቀው እውነት ነው፡፡ ምናልባት ‹‹አባቶቼ›› ያላቸው በሀዋርያት በሰማዕታት መንገድ የሄዱትን ሳይሆን በእርሱ መንገድ እየተጓዙ የቤተክርስቲያንን ልጆች አሳደው ሲያበቁ በክፉ ስራቸው ቅጣት ሲደርስባቸው እግዚአብሔርን እንዳገለገሉ የቆጠሩትን ነው እንጂ እውነተኞቹ አባቶች መከራ ተቀበልን ያሉት የሰው ስም አጥፍተው ሳይሆን የክርስቶስ በመሆናቸውና እርሱን በመከተላቸው ስማቸው ጠፍቶ ነው፡፡ በወንጌል ምክንያ ተሰደው እንጂ በገንዘብና በዝና ምክንያት የተጓዙበት መንገድ ወንጀል ውስጥ ከቷቸው በእውነተኛ ፍትሕ ከተፈረደባው በኋላ አይደለም፡፡
እንደዘመድኩን የሚያስበው የማህበረ ቅዱሳን ድረገጽ ደጀሰላም የጻፈውም ‹‹መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ›› አይነት ነው የሆነበት፡፡ ‹‹ቅዱሳን መላእክትን በአርያም፣ የወንጌል ገበሬዎቹን ሐዋርያትን በአጽናፈ ዓለም፣ ደጋጎቹን መነኮሳት በገዳም፣ ቆራጦቹን ሰማዕታት በደም ያጸና የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ወንድማችን / ዘመድኩን በቀለን በመከራው ሁሉ እንዲያበረታው እንለምናለን፤ ሁላችንም በጸሎታችን እንድናስበውም ደጀ ሰላም ጥሪዋን ታስተላልፋለች፡፡›› እስኪ እናስብ! ስም አጥፊውን ዘመድኩንንና በጽርሐ አርያም የጸኑትን መላእክት፣በአጽናፈ ኣለም ወንጌልን በመስበክ ስለ ክርስቶስ ስም መከራ የተቀበሉትን ሐዋርያት ምን አንድ አደረጋቸው? ቆራጦቹንና ስለ ክርስቶስ ስሙ በመመስከራቸው ደማቸውን ያፈሰሱትን ሰማዕታትና የመጋቤ ሀዲስ በጋሻውን ስም አጥፍቶ 5 ወር የተፈረደበትን ዘመድኩንን ምን አገናኛቸውና ነው ከእነርሱ ተርታ ማሰለፍ ያስፈለገው፡፡ ባይሆን በስምአ ሀሰት ጀግናቸው አድርገው ከቀደምት ጀግናቸው ከዳንኤል ክብረት ጋር (ዳንኤል የገሃነም ደጆች በሚለው ስም አጥፊ ጽሁፉ እንደ ተፈረደበት ማለት ነው) ነው መቆጠር ያለበት፡፡

17 comments:

 1. I think God is trying to tell this Zemedkun to be careful and stop persecuting his children like Begashaw falsely. If he doesn't learn from this experience and ask God for forgiveness "በ5 ወር እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል" may be changed to በእስራት እንዲቀጣ ተወስኖበታል (forever in hell).

  the funny part is
  ዘመድኩን said ‹‹ዛሬ ወደ እስር ስሄድ አባቶቼ ስለ ቤተ ክርስቲያን በተቀበሉት ፈተና ካገኙት ጸጋ በረከት እንደምሳተፍ አምናለኹ፡፡ በዚህም ደስ ይለኛል፡፡›› kkkkkkkkkkkkk

  you should be jumping for joy for getting only 5 ወር እስራት, you broke not only EPRDF law but also one of the ten commandments

  "You shall not give false testimony against your neighbor" Exodus 20:16

  And

  Jesus said, "YOU SHALL NOT BEAR FALSE WITNESS, Matthew 19:18

  If i were you i wouldn't spent time to associate myself and to compare with "አባቶቼ ስለ ቤተ ክርስቲያን በተቀበሉት ፈተና ካገኙት ጸጋ በረከት" because I know I will never be like them or tiny fraction of them, I think you know that too. Just repent and ask forgiveness from those who you hurt so much and God may forgive you.

  good luck in kality think about hell while you are there

  ReplyDelete
 2. sorry I forgot to remind you that the JUDGMENT DAY was MEDHANEALEM የካቲት 27 ቀን 2004

  ReplyDelete
 3. menydereg belachew new gizew wenbedenana yegziabhern agelglot leyeto maweq yetesanebet new i think Zemedkunem yendeze ayenet mech metot
  new yewendmun mote felgo gudgwad simes heg beqtaw endesematent sera erasun yasqoterew, lehulum Egziabher leb yesetew(yesten lehulachn).amen

  ReplyDelete
 4. would you have another story if Dn Begashaw was arrested? Come on guys.Be grown ups!

  ReplyDelete
 5. to whom should we compare you , ZEMEDKUN?
  to St.Paul, to St. Peter, ......or To Ethiopian Papas Abune Petros. As you know none of them were accused of endangering their brother's life, instead they lived and preached the goodness and love of their lord JESUS CHRIST. I am sorry brother i didn't see that in you

  ReplyDelete
  Replies
  1. 100% true. great response.

   Delete
 6. ዘመድኩን ሩጫውን ጨረሰ፤ ለቤተ ክርስቲያን ሰማዕት ሆነ፤ …. እንዴት ይባላል፤ ትላንት የበጋሻው አገልግሎት ከእርሱ የተሸለ በመኆኑ በቅናት መንፈስ መኪና የለኝም ቤት ጀምሬ ማጠናቅቅበት አጣሁ እያለ ለበጋሻው ያቀረበው ዐይን አውጣ ጥያቄ ምላሹ እምቢ ሲሆንበት፤ ለቤተ ክርስቲያን ተቆርቋሪ መስሎ እልሁን ለመወጣትና ያጣውን ገንዘብ (መኪና የለኝም ቤት ጀምሬ ማጠናቅቅበት አጣሁ) ለመሰብሰብ ያደረገው እንጂ ዘመድኩን ወሕኒ የገባበትና ራሱ ያጠመደው ወጥመድ ሩጫውን ጨረሰ፤ ለቤተ ክርስቲያን ሰማዕት ሆነ የሚባልለት አይደለም፡፡
  ኦርቶዶክሳውያን እስከ መቼ በማ/ቅ አሮጌ ስትራተጂ እንወናበዳለን፡፡ ሊቅ ሳይጠፋ ማ/ቅ እስከ ዛሬ ሊቅ ሆኖ ቤተ ክርስቲያንን በስውር ፖለቲካ ሲመራ ቆይቷል፡፡ አሁን ግን ነጋ! የወግና የባልቴቶች ተረት ተረት አሰራርና አስተዳደር ባለቤት ማ/ቅ ቦታ የለውም፡፡ ወንጌልና ወንጀልን የሚለዩ ኦርቶዶክሳውያን ማ/ቅን ከተተከለበት የትዕቢት ሥፍራ ነቅለው ከንስሐ መልስ ቦታ ሊያዘጋጁለት ይገባል፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ምን ላርግህ!! የልብ አውቃ ነህ ወንድም. ተባረክ

   Delete
 7. በጣም የሚገርመዉ ራሳቸዉን ከቅዱሳን ወይም ከሰማእታት ጋር ማወዳደራቸዉ ይገርማኛል በአንድ ወቅት በደጀሰላም ድረገፅ ስለ ዲያቆን በጋሻው በሚመለከት አቅርበዉ ዛሬ ያን ነገር እረስተዉ እሱ የታሰርዉ ለእዉነት ማለት ከእዉነተኛ ክርስትያን የሚጠበቅ እይደለም። ይህን ለማለት የፈልኩት የራሳችሁ ሰዉ ሲፈርድበት ለበረከት ነዉ ለወንጌል ብለዉ እወነቱን ሲናገሩ ተሃድሶ ናቸዉ ማለት ጥሩ እይደለም ።

  ReplyDelete
 8. በጣም የሚገርመዉ ራሳቸዉን ከቅዱሳን ወይም ከሰማእታት ጋር ማወዳደራቸዉ ይገርማኛል በአንድ ወቅት በደጀሰላም ድረገፅ ስለ ዲያቆን በጋሻው በሚመለከት አቅርበዉ ዛሬ ያን ነገር እረስተዉ እሱ የታሰርዉ ለእዉነት ማለት ከእዉነተኛ ክርስትያን የሚጠበቅ እይደለም። ይህን ለማለት የፈልኩት የራሳችሁ ሰዉ ሲፈርድበት ለበረከት ነዉ ለወንጌል ብለዉ እወነቱን ሲናገሩ ተሃድሶ ናቸዉ ማለት ጥሩ እይደለም ።

  ReplyDelete
 9. ለታሠረው እግዚአብሔር ያፅናህ ካልተባለ ላሳሰረው ምን ይባል ይሆን?????

  ReplyDelete
 10. yediyabilos yegebere lej new zemedkun.seoul megbat yisalega belo nebere misalewene eser betn agegetotal aceberbari sem silehone yigebawal

  ReplyDelete
 11. I think Mr. Zemedkun will get chance to realize where he is standing and with who he is fighting. Definitely he was creating such problem for money and judged by "GOD". Let us pray to him though he don't believe the power of the holly sprite and he fear the name of Jesus Christ as MK did..

  ReplyDelete
 12. ለዘመድኩንና በእሱ ጉዳይ ዙሪያ የሚባለውንም የማይባለውንም ለምትሉ ሁሉ!!!

  የአምላካችን ማስተዋል ለሁላችንም ይብዛልን እያልኩ እንዲህ ልበል ለጥቅማችን:-

  እንደ እኔ መረዳት ይህ ሰው ምንም ዓይነት የተረጋገጠ መጥፎ ሥራ ቢሠራም እንኳ በዚህ ዓለም ፍርድ ቤት ተፈርዶበት ወህኒ መግባቱን አልደግፍም:: ይልቁንም ሰው የመሰከረበትን ሥራውን ከማንም በላይ የልብ አምላክ ስለሚያውቀው ንስሃ ገብቶ ከፍርዱ ነጻ ቢለቀቅ ደስተኛ እሆናለሁ:: ምክናያቱም ይህን ቢያደርግ ከሰው ጋር ብቻ ሳይሆን ከእግዚአብሔር ጋር ጭምር ይታረቅና ከዘላለም ፍዳ ሁሉ ነጻ ይወጣልና ነው:: ስለዚህ የሚገደን የሰማዩ ጉዳይ ቢሆን እጅግ ይበጀናልና በዚህ ላይ እናተኩር ለዚህ ሰውም ጌታ በፍቅሩ እንዲገናኘው እንጸልይለት::

  አንድ ወቅት በቢቢሲ ዜና ላይ አንዲት በለንደን ከተማ የምትኖር ጥቁር ክርስቲያን ልጇን የገደላባት ሰው ፍርድ ቤት ቀርቦ በፍርድ ሂደት ላይ ሳለ በጋዜጠኞች አስተያየትና ስላደረባት ስሜት ተጠይቃ የሰጠችው መልስ ''እኔ በፈጠረኝ አምላኬ ኃጢአቴ በክርስቶስ ሞት በኩል ይቅር የተባልኩ የይቅርታ ሰው
  ነኝና ይህ የልጄ ገዳይ በነጻ ቢለቀቅ ደስታዬ እጥፍ ድርብ ይሆናል ልጄም አሁን የት እንዳለ
  አውቃለሁ'' በማለት የተናገረችው ትዝ ይለኛል::

  ታዲያ እኛ ዛሬ የት ላይ ነው ያለነው? ሳያውቁ ያወቁ እየመሰላቸው የክርስቶስ ወንጌል ባላደራወችን በገቡበት እየገቡ የሚያሳድዱትን ክፉ ነገር ሲደርስባቸው ደስ የሚለን ከሆነ ጥያቄ አለኝ ፍቅር የሆነው ጌታ በእኛ ውስጥ ስለመኖሩ? ሁላችንም እራሳችንን እንጠይቅ? እኔ መችም ዘመድኩንም ይሁን የማህበረ ቅዱሳን አባላት በሙሉ ከክፉ ሥራቸውና የወንጌል ጠላትነት ወደ ፍቅር አገልግሎት ተመልሰው አብረን በመሆን ቤተ ክርስቲያናችንን በወንጌል ስብከት ጎልብታ ለሌሎች የአፍሪካ አገሮች ሳይቀር ብርሃን በመሆን ስትተርፍ ማየት ብቻ ነው የምናፍቀውና እባካችሁ ለዚህ ሰማያዊ ዓላማ ብቻ በጌታ ፍቅር በጾም በጸሎት አብረን እንትጋ?? ጌታም ክንዱን የሚገልጠው በፍቅርና በፍቅር ብቻ ነውና ይኸው በመካከላችን ይብዛልን አሜን እና አሜን::

  የጌታ ሰላም ለቤተ ክርስቲያናችን ይሁን

  ለዘመድኩንም እውነተኛው የመንፈስ ቅዱስ መጽናናት ይምጣለት!!!

  ከክፉው በስተቀር ሁላችሁንም የምወዳችሁ
  እ ህ ታ ች ሁ

  ሰላም ነኝ

  ReplyDelete
  Replies
  1. St. Paul said "the metalworker did me a great deal of harm. The Lord will repay him for what he has done" 2 Timothy 4:14

   I think Dn Begashw can say same thing by substituting "the metalworker" by -NEGADEW- OR ZEMEDKU

   Delete
 13. THIS JUDMENT FROM THE COURT IS A GOOD TEACHING THOSE WHO DEFAME PEOPLE . ZEMEDEKUN SHOULD BE PUNISHED .

  ReplyDelete
 14. leba mechem sikafel enji siserk aytalam yetebalew derese huletum beyefinachew memenanenen sibotebutu noruna zare semaet megabe hadis menamen yebabalalu wonbede hula aba selamawoch demo yetelate telat wodaje bemalet begashaw yemibalewen seweye agul atkoleluben yelek kemetemtem memar yekdem belut wengel tehetenan enji tesadabineten alstemarechenem selegeta sem enji selerasachen sem edansera new yetenegeren tadia seme tebelashe eyale yemikases sew beyet alfo new megabe hadis yemibalew are nuroachen hulu segawi becha hone meche yehon getan yemnmeslew wegen

  ReplyDelete