Wednesday, March 14, 2012

“ያገኙትን ቢያጡ ያጡትን ይቀላውጡ” - - - Read PDF

ይድረስ ለቆንጆ መጽሔት
“ቆንጆ” መጽሔትን “መልከ ጥፉን …” የሚለው ተረት ይገልጸዋል፡፡ የማህበረ ቅዱሳን ቅጥረኛ ሆኖ በአባ ሰላማ ድረገጽ ላይ መሰረተ ቢስ የስም ማጥፋት ዘመቻ ከከፈቱ የግል ነገር ግን የማህበረ         ቅዱሳን ተከፋይ መጽሔቶች መካከል አንዱ ቆንጆ መጽሄት ነው፡፡ መጽሄቱ ታህሳስ ወር 2004 ዓ.ም ላይ “አባ ሰላማ ድረ-ገጽ ማነው? ማህበረ ቅዱሳንስ?” በሚል ርእስ ባቀረበው ጽሑፍ በበላበት መጮሁን በሚያሳብቅበት ሁኔታ ማህበረ ቅዱሳንን እየካበ አባ ሰላማ ድረገጽን ጥላሸት እየቀባ የጋዜጠኝነት ስነምግባርን በጣሰ መንገድ እጅግ የወረደ ጽሁፍ አስነብቦ ነበር፡፡ በጊዜው አንድ የድረገጻችን ተከታታይ ቆንጆ መጽሄት አባ ሰላማ ድረገጽ ላይ የከፈተውን የስም ማጥፋት ዘመቻ በተመለከተ ምላሽ እንድንሰጥ አስተያየት ሰጥቶ ነበር፡፡ ለመጽሄቱ ጽርፈት የተሞላበት ጽሁፍ መልስ መስጠት ቢኖርብንም ለእርሱ ተራ ወሬ መልስ ከመስጠት ይልቅ በእውነተኛ መረጃ ላይ የተመሠረተና ለአንባቢዎች የሚጠቅም መረጃ በመስጠት ላይ ማተኮሩን መርጠን እስካሁን ቆይተናል፡፡
አሁን በመጽሄቱ ላይ ምላሽ ለመስጠት የተነሳነው መጽሄቱ አባ ሰላማ ድረገጽን ሲሰድብና ሲያዋርድ እንዳልነበረ፣ በቤተክርስቲያን ዙሪያ ለሚያቀርባቸው ዘገባዎች ከማህበረ ቅዱሳን ሀሰተኛ ብሎጎች እያወረደ የማህበረ ቅዱሳንን ገጽታ ሲገነባ እንዳልከረመ፣ አሁን ላይ እነዚያ ምንጮቹ የወሬ ድርቅ ስለ መታቸው ይሁን ወይም ስላልከፈሉት ባልታወቀ ምክንያት መጋቢት 2004 ዓ.ም እትሙ ላይ አለወትሮው ከአባ ሰላማ ድረገጽ ላይ ፖስት የተደረገ ጽሁፍ አትሞ አውጥቷል፡፡ ይህ በራሱ መልካም ነው፡፡ “ቆንጆ ሆይ በዚሁ ቀጥል” እንላለን፡፡ ችግሩ ግን “ዜናውን የወሰድሁት ከአባ ሰላማ ድረገጽ ነው” ብሎ ምንጩን አለመጥቀሱና ከሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ድረገጽ ላይ እንደወሰደ አድርጎ ማቅረቡ ነው፡፡ ለዚህ ነው “ያገኙትን ቢያጡ ያጡትን ይቀላውጡ”ን የተረትነው፡፡
በቅድሚያ በታህሳሱ እትሙ ላይ አባ ሰላማ ድረገጽ ላይ ያወራውን ሀሰተኛ ወሬ በተመለከተ ጥቂት ነገር አንበል፡፡ ያን በሀሰት የተሞላ ጽሁፍ ያቀረበው አንድ አስተያየት ሰጪ ቢሆን ኖሮ አንዱ የማቅ አባል ይሆናል ብለን በዚህ ጽሁፍ ላይ ሳናነሳው ባለፍን ነበር፡፡ ነገር ግን የጽሁፉ አቀናባሪ ከመጽሄቱ ከፍተኛ አዘጋጆች አንዱ የሆነው “ተስፋዬ ጥበቡ” መሆኑ ነው ለአስተያየት ያነሳሳን፡፡ አንድ ጋዜጠኛ ለዚያውም ከፍተኛ አዘጋጅ አንድን ጉዳይ በገለልተኝነት መዘገብ ሲገባው ተስፋዬ ግን ቅልጥ ያለ የማህበረ ቅዱሳን አባል ሆኖ ነው የቀረበው፡፡ አባል መሆን የሚከለክለው ባይኖርም በጽሁፉ ውስጥ እኔ ገለልተኛ ሆኜ እንጂ አባል ወይም ደጋፊ አይደለሁም በማለት አስተባብሏል፡፡ አባል ሆነም አልሆነ እንደጋዜጠኛ ሲጽፍ ራሱን ከማህበሩ አባልነት አውጥቶ በጋዜጠኝነት ቦታ ላይ አስቀምጦ ነበር መጻፍ የነበረበት፡፡ የማህበረ ቅዱሳኑ ተስፋዬ ግን ከማህበረ ቅዱሳን ወንበሬ ላይ ተነስቼ ጋዜጠኛ አልሆንም ያለ ነው የሚመስለው፡፡ ይህ የእርሱ ብቻ ሳይሆን የብዙዎቹ ጋዜጠኞች ችግር እንደሆነ በተሀድሶና ማህበረ ቅዱሳን ዙሪያ በሚወጡ ዘገባዎች ላይ የምናስተውለው ሀቅ ነው፡፡ ስለዚህ ጋዜጠኞች ሆይ እባካችሁ የማቅ አባላት ወይም ደጋፊዎች ብትሆኑም እንኳን ሚዛናዊ ዘገባ ለማውጣት ሞክሩ፤ ተከፋዮች ከሆናችሁ ግን ምን ይደረጋል፤ ሚዛናዊነትን ወደጎን ብላችሁ እንደተለመደው የማቅ ፖሮፓጋንዳ ማሠራጫ መሆናችሁን ቀጥሉ፡፡ አባ ሰላማ ድረገጽ መልእክቶች ሚዛናዊ ሆነው እንዲተላለፉ በማሰብ የሁሉንም ወገን ሀሳብ በማስተናገድ ላይ ለመሆኑ በየጊዜው በሚወጡ በመረጃ በተደገፉ ጽሁፎች ላይ የሚሰጡ አስተያየቶችን ሁሉ ማስነበቡ አንድ ምስክር ነው፡፡
ተስፋዬ አባ ሰላማ ድረገጽን በመዝለፍና ማህበረ ቅዱሳንን በመካብ ካሰፈራቸው ሀሳቦች አንዳንድ ማስረጃዎችን እንጥቀስ፤
“የዚህ (ይህ) ድረገጽ በተደጋጋሚ መልስ የሚሰጠው ደጀሰላም የተባውን (ለተባለው) ድረገጽ ሲሆን ይህ ድረገጽ የማን መሆን (መሆኑ) ባይታወቅም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ማዕዛ (መዓዛ) አለበት (፡፡) ስለ ቤተክርስቲያን ጠበቃ የቆሙ እራሳቸውን ለእውነት ያቆሙ ሰዎች የሚጽፉበት ድረገጽ ነው እላለሁ፡፡ ሌላው በዚህ ድረገጽ ሰለባ ከሆነው (ከሆኑት መካከል አንዱ) ማህበር ማህበር (ማህበረ) ቅዱሳን ነው፡፡ እኔ ከእነርሱ ጋር የሚያገናኘኝ ነገር የለም(፡፡) … እውነት ነው የምለው በነብሴ (በነፍሴ) ተወራርጄ እምላለሁ (፤) በዚህ ዘመን ለቤተክርስቲያን ከማህበር (ከማህበረ) ቅዱሳን የተሻለ የለም፡፡ ሁሉም ቤተክርስቲያንን የከበባት ለኑሮ መደጎሚያው ነው፡፡” (ገጽ 22)፡፡
(ጽሁፉ በብዙ የፊደላት፣ የአረፍተ ነገር አሰካክ፣ የስርአተ ነጥብ ችግሮች የተሞላ ነው፡፡ በተጠቀሰው በዚህ ውስጥ እንኳን በቅንፍ የተቀመጡት ይህን ያሳያሉ፡፡) መቼም አባል ወይም ተከፋይ ካልሆነ በቀር ጋዜጠኛ እንዲህ ይላል የሚል ፊደል የቆጠረ ሰው ይኖራል ተብሎ አይታሰብም፡፡ ተስፋዬ ሆይ አስር ጊዜ በነብስህ (ኦንዳንተ አፃፃፍ) ብትምልም ማንም አያምንህም፡፡ አንተ ጋዜጠኛ ሳትሆን ጋዜጠኝነትን ለኑሮ መደጎሚያነት ከከበቡት ወገን ነህ፡፡ የፕሬስ ነጻነት በታወጀባት አገር ላይ ሆነህ ጋዜጠኝነትን እንዲህ እያበላሸህ ሆድ መሙያ ስታደርገው ማየት በእጅጉ ያሳዝናል፡፡
የደጀሰላምን ያልታረመ አንደበት ካንተባተቡት ብሎጎች አባ ሰላማ ብሎግ አንዱ ነው፡፡ ደጀሰላም የማን መሆኑን አትናገር ብለውሃል መሰል የማን መሆኑን እንደማታውቅ ሆነህ ፅፈሃል፤ ይሁን፡፡ የቤተክርስቲያናችን መዓዛ አለበት፤ ስለ ቤተክርስቲያን ጠብቅና የቆሙ እውነተኛ ሰዎች የሚጽፉበት ድረገጽ ነው እላለሁም ብለሃል፡፡ ይህ የአንተ አቋም ነውነው፡፡ በጥቅሉ ግን ቤተክርስቲያኒቱን በማህበሩ የምትለካ በመሆንህ እጅግ ተሳስተሃል ከማለት በቀር በዚህ ላይ መጨመር አያስፈልግም፡፡ ስለማህበረ ቅዱሳን በጎረስክበት እጅህ መራራውን አጣፍጠህ፣ ጥቁሩን አንጥተህ ብትጽፍ፣ ከአንተና ከመሰሎችህ በቀር ማንም አያምንህም፤ ማህበሩን እናውቀዋለንና የእርሱን ነገር ለእኛ ተውልን፡፡ በነገራችን ላይ ስለአባ ሠረቀ መጽሐፍ ፖስት ያደረግነውን ዘገባ አትመህ ያወጣኸው ስለማህበረ ቅዱሳን የነበረህንና “በነብሴ” እምላለሁ ያልከውን መሀላ አፍርሰህ ነው? ወይስ የተሻለ መንገድ ስላገኘህ በጨረታው አልገደድም ብለህ? ወይስ እንዲያ ሰማይ ላይ የሰቀልከውን የማህበሩን ጉዳይ እንደተበላ እቁብ ቆጥረኸው?
“ማህበሩ በክርስቶስ ለማፍረስ ሲዶልቱ ማህበሩ ሚስማር ሲመቱት እንደሚጠነክር ሁሉ ማህበሩም ቀን በቀን እድገት እያሳየ በስጋዊም በመንፈሳዊም እድገቱን አሳይቷል፡፡ የሰፉትም የበዙትም ጌታ ስለፈቀደ እንጂ እነተረፈ ይሁዳ ስላቀዱና ስላለሙ አይደለም፡፡ ከዚህ በኋላም እግዚአብሔር ቢፈቅድ ሙሉ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይ ሁሉ የማህበሩ አባል ይሆናል፡፡ ስለምን ቢሉ ከክፉ ጋር ከመተባበር ከደግ ጋር መተባበር ሳይሻል አይቀርም፡፡” (ገጽ 24) ተስፍሽ ፅሁፍህን ማረም እንዴት ይሰለቻል መሰለህ!
በዚህ ውስጥ የተናገርከው አንድ እውነት ያለ ይመስለናል፡፡ ማህበሩ በስጋዊ ሁኔታው አድጓል ባልከው እንስማማለን፡፡ መንፈሳዊ እድገት ያልከው ግን መንፈሳዊነትን በቅጡ ስላልተረዳህ የሰጠኸው አሳብ ነው፡፡ በመንፈሳዊነት ማደግ እኮ መገለጫው መንፈሳዊ መሆን ነው፡፡ ማህበረ ቅዱሳን እያደረገ ያለው ያደገበትን ስጋዊውን ነገር ብቻ ነው፡፡ እኔ ብቻ ነኝ ልክ ማለት ስጋዊነት ነው፤ የቤተክርስቲያን ልጆች ወንጌል ሰበኩ ብሎ ማሳደድ ስጋዊነት ነው፤ ከስርአተ ቤተክርስቲያን ውጪ በስሜት ተነሳስቶ ቤተክርስቲያን ያለወገዘቻቸውን የቤተክርስቲያን ልጆች ተሀድሶ መናፍቃን ማለት ስጋዊነት ነው፤ ለተጠሪው የመምሪያ ሃላፊ አልታዘዝ ባይነትና በህገ ወጥ መንገድ እስከ መክሰስ ድረስ ማመፅ ስጋዊነት ነው፡፡ የሰሞኑ ተግባሩ ማለትም ባልተሰጠው ስልጣንና ግልጽነት በጎደለውና ለሙስና በተጋለጠ አሰራሩ የራሱን ገቢ ለማሳደግ በገጠር አብያተ ክርስቲያናት ስም መባ መሰብሰቡ ስጋዊነት ነው፡፡ ብዙ ህጸጾቹን እየነቀሱ የማቅን ስጋዊነት ማሳየት ይቻላል፡፡
በመንፈሳዊነት አድጓል ያልከው ሃይማኖት መሰል ባህላዊ መልኩን፣ ማለትም ቅድስና ሳይኖረው ራሱን ማህበረ ቅዱሳን ብሎ መጥራቱን፣ በአባቶች እግር ስር እንደእባብ እየጠጥመለመለ መቅለስለሱን (ዘወር ብሎ የሚሰራው ሌላ ነው)፣ የተገመደ ክር አንገቱ ላይ ማሰሩን፣ ነጠላ ለባሽ መሆኑን፣ ወዘተርፈ መሰረት አድርገህ ከሆነ ተሳስተሃል፡፡ መንፈሳዊነት በኢየሱስ አዳኝነት ማመን፣ እርሱን ብቻ መስበክ፣ በእርሱ እየኖሩ እርሱን መምሰል እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ ማህበሩ ግን እንኳን ክርስቶስን ሊመስል የኢየሱስ ስም ለምን ተጠራ የሚል ፀረኢየሱስ ማህበር ነው፡፡ ጌታ ሳያውቀው የሆነ ነገር እንደሌለ ብንስማማም፤ ማህበረ ቅዱሳን በጌታ ፈቃድ ነው የተመሰረተው በሚለው ግን እንለያያለን፡፡ ከዚህ ይልቅ ማህበረ ቅዱሳንን ያስነሳው ሰይጣን ነው ቢባል ትክክል ይሆናል፡፡ ምክንያቱም ቤተክርስቲያኗ በወንጌል እውነት እንድትታደስ አይፈልግምና፣ ተሀድሶዋን ለማዘግየት ሲል ይህን እንዳደረገ ማህበሩ ከሚሰራው ስራ መረዳት ይቻላል፡፡ ለዚህም ነው ዲያቆን ሙሉጌታ ከዚህ ቀደም በማህበሩ ላይ “ማህበረ ቅዱሳን ወይስ ማህበረ ሰይጣን?” የሚል መጽሐፍ የጻፈው፡፡
ማህበሩ ሰይጣናዊ ማንነቱን ለመሸፈን ለቤተክርስቲያን ስርአት፣ ባህል፣ ወግና ልማድ መቆርቆርን መታወቂያው አድርጎ ይንቀሳቀሳል፡፡ ይህን ማድረግ በራሱ ክፋት የለውም፡፡ ነገር ግን ወንጌልን በመቃወምና እነዚህን ነገሮች ከወንጌል በማስበለጥ ከሆነ፣ ይህ ቅናት ከሰይጣን ወይም ከሰው እንጂ ከእግዚአብሔር ሊሆን አይችልም፡፡ ከእግዚአብሔር የሆነው ቅናት ቅድሚያ ለወንጌል ይሰጣል፤ ኢየሱስ ሲሰበክ ይደሰታል እንጂ አይቆጣም፤ ከላይ የተጠቀሱት ነገሮችም ከወንጌል ጋር የማይቃረኑ እስከሆኑ ድረስ ደረጃቸውን ጠብቀው አገልግሎት እንዲሰጡና ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፉ ሊደረግ ይገባል፡፡
በነገራችን ላይ አይሁድም እኮ እንዲሁ ያደርጉ ነበር፡፡ ጌታ ሃይማኖታዊ ካባቸውን ገልጦ መንፈሳዊ አቋማቸውን ሲመረምር የደረሰበት ድምዳሜ ግን አስደንጋጭ ነው፤ “እናንተ የአባታችሁን ሥራ ታደርጋላችሁ አላቸው። (እነርሱም) እኛስ ከዝሙት አልተወለድንም አንድ አባት አለን እርሱም እግዚአብሔር ነው አሉት። ኢየሱስም አላቸው። እግዚአብሔርስ አባታችሁ ከሆነ በወደዳችሁኝ ነበር፤ … እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና።” (ዮሐ.8፡41-44)፡፡ ማህበረ ቅዱሳንም እግዚአብሔር ይላል እንጂ ኢየሱስን ስለማይወድ አባቱ ሌላ መሆኑን በስራው ገልጧል፡፡ ማህበረ ቅዱሳን ማህበረ ሰይጣን ሊባል የተገባበት ምክንያትም ከዚህ የተለየ አይደለም፡፡
ተስፋዬ ከሁሉም የሚገርመው ወደፊት ሁሉም ኦርቶዶክሳዊ የማህበሩ አባል ይሆናል ማለትህ ነው፡፡ ይህ ባለማወቅ የተባለ ነው ብለን አንወስደውም፡፡ የማህበሩ ቅዠት መሆኑን እናውቃለንና፡፡ አባላቱን ከኦርቶዶክሳውያን መካከል እየመለመለና ራሳቸውን ማህበረ ቅዱሳን ብለው እንዲገልጹ እያደረገ ነው፡፡ በሁሉም አቅጣጫ የራሱን ሲኖዶስ፣ የራሱን ዶግማ፣ የራሱን አገር ለመፍጠር የሚፍጨረጨር ፖለቲካዊ ስብስብ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በጊዜ ስለተነቃበት ግን የትም አይደርስም፡፡ አንተ ግን ትገርማለህ! እንዴት ብታስብና በምን ምክንያት ይሆን ታላቋና ጥንታዊቷ ቤተክርስቲያን በማህበረ ቅዱሳን እንድትዋጥ የፈለከው?
“ጋዜጠኛ /ከፍተኛ አዘጋጅ/” ተስፋዬ ለደጀሰላም ወግነህ አባሰላማን መኮነን ጋዜጠኝነት ነው ብለህ ታስባለህ? ፍርዱን ለህሊናህና ለአንባቢ መተው ሳይሻል አይቀርም፡፡ በአባሰላማ ብሎግ ላይ ሀሰተኛ ዘገባ ማቅረብስ ለምን አስፈለገ፡፡ እንዲህ ብለህ ስትጽፍ ስለምን አላፈርክም? እንጠቅሳለን፣ “ይህ ፅሁፍ ለህትመት እስከገባበት ድረስ በሀገራችን እጅግ ዘግናኝ ነገር ተከስቷል የግብረ ሰዶም ሀገሪቱ ላይ ተፈቅዶላቸው ሁሉም መሰብሰባቸውን ሁሉም መገናኛ ብዙኃን ሲያወግዙ ማንነቱ ያልታወቀው አባ ሰላማ ድረ-ገጽ አንድም ነገር አላለም፡፡ ቅጥረኛው አባ ሰላማ ታሪክና ሃይማኖት ሊያጠፋ የተነሳው የቤተክርስቲያኗን ብቻ ሳይሆን የሀገሪቱንም ስነምግባር ጭምር ነው አንድ ሊባል ይገባል” (ገጽ 24) ብለሃል፡፡
ይህ በመረጃ ላይ ያልተደገፈ ወይም ትክክለኛ መረጃን መሰረት ያላደረገ ዘገባ ነው፡፡ ለመሆኑ አባ ሰላማ በዚያ ወቅት ያወጣውን ዘገባ አይተኸዋል? TUESDAY, NOVEMBER 29, 2011 ፖስት የተደረገው ጽሁፍ “የሰዶምና የገሞራ ጩኸት እጅግ በዝቷል ዘፍ 18፥20” የሚል ነበር፡፡ ጽሁፉ በጊዜው ግብረሰዶማውያን በአገራችን ስብሰባ ሊያካሂዱ መሆናቸው ስለታወቀ ስብሰባውን በመቃወም የቀረበ ነው፡፡ አባ ሰላማ ድረገጽ ይህን እኩይ ምግባር ከሁሉም ቀድሞ ተቃውሟል፡፡ ታዲያ አንተ በምን ምክንያት ነው በሀሰት፣ ድረገጹ የቤተክርስቲያንን ታሪክ ብቻ ሳይሆን የአገርንም ስነምግባር ሊያጠፋ የተነሳ ነውና አንድ ሊባል ይገባል ያልከው? አጻጻፍህ ለምን በጉዳዩ ላይ አልዘገበም ከማለት ያለፈና ስብሰባውን ያዘጋጀው አባ ሰላማ ድረገጽ ነው የሚል መሰለ እኮ! ይህ በጣም የሚያሳፍርና ከአንድ ጋዜጠኛ ለዚያውም ከዋና አዘጋጅ የማይጠበቅ ዘገባ ነው፡፡
የታህሳሷ ቆንጆ መጽሄት ዘገባ ሲገርመን፣ የመጋቢት 2004 ዓ.ም ደግሞ እጅግ ከማስገረም አልፎ “ያገኙትን ቢያጡ ያጡትን ይቀላውጡ” አሰኝታናለች፡፡ ስትዘልፈውና ስትሰድበው ከነበረው አባ ሰላማ ድረገጽ ላይ Saturday, January 28/2012 የተሰቀለውንና “በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የአባ ሠረቀ ብርሃንእውነትና ንጋትመጽሐፍ ተመረቀ” የሚለውን ጽሁፍ አውርዳ በ“ሰሞነኛ ወሬ” አምዷ ላይ “አነጋጋሪው የአባ ሠረቀብርሃን መጽሐፍ እና ቃለ ምልልሳቸው” በሚል ርእስ አተመችው፡፡ በእርግጠኝነት ለመናገር ቃለ ምልልሱንም የወሰደችው ከአባ ሰላማ ድረገጽ ላይ ነው፡፡ ከሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ድረገጽ ላይ ወስደንና ምንጭ ጠቅሰን ከቀድሞው የሰንበት /ቤቶች ማደራጃ መምርያ ዋና ኃላፊ በአሁኑ ጊዜ የትምህርትና ማሠልጠኛ መምርያ ዋና ኃላፊ ከሆኑት ከቆሞስ አባ ሠረቀብርሃን /ሳሙኤል ጋራ የተደረገ ቃለ መጠይቅ” በሚል ርእስ SATURDAY, FEBRUARY 4, 2012 ቃለመጠይቃቸውን ሰቅለን ነበር፡፡ እንደስሟ ምግበሯ ያልቀናው ቆንጆ መጽሄት ግን አባ ሰላማ ድረገጽን ስትሰድብ እንዳልነበረ ስለመጽሀፉ ያወጣችውን ሰሞነኛ ወሬ ምንጭ ሳትጠቅስ የራሷ አስመስላ አወጣችው፡፡ በመጨረሻው ላይ ግን ስለ ቃለመጠይቁ በአባ ሰላማ ድረገጽ ላይ የተጠቀሰውን ምንጭ “በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ድረገጽ የተወሰደ” የሚለውን ጠቀሰች፡፡ ቆንጆ የእንግሊዝኛ አድራሻውን (eotcssd.org) ካለመጻፏ በቀር ይህንኑ ቃል ነው ያሰፈረችው፤ የፊደል ለውጥ እንኳ አላደረገችም፡፡ ለዚህ ነው ቃለ መጠይቁንም የወሰደችው ከአባሰላማ ድረገጽ ነው ያልነው፡፡ እንዲህ ያደረገችው ለአባ ሰላማ ድረገጽ እውቅና ላለመስጠት ቢሆንም፣ በገጽ 3 ላይ abaselama.org የሆነውን አድራሻ .com ብላ አንባቢን ለማደናገር መሞከሯ ሌላው ሸፍጥ ቢሆንም፣ የማደራጃ መምሪያው አድራሻ በመጨረሻ ላይ መጠቀሱ፣ የዜናው ባለቤት የማደራጃ መምሪያው ድረገጽ ይመስላልና እርሱ ያላወጣውንና ሀላፊነት የማይወስድበትን ጽሁፍ በስሙ ማውጣት ሊያስጠይቃት ይችላል፡፡ ጠያቂ ካለ፡፡ 
ሌላው አስገራሚ ነገር በዚሁ በመጋቢት እትሟ “ባህል” አምድ ላይ “ኢትዮጵያ - የቅጂ መብቶች እና የቅጂ ወንጀሎች” በሚል ርእስ ጽሁፍ ማውጣቷ ነው፡፡ ራሷ መጽሄቷ ምንጭ ባለመጥቀስና የሌላን አካል ስራ የራሷ አድርጋ በማቅረብ ወንጀል መፈጸሟን ሸፍና፣ በሌሎች ላይ ጣቷን ቀስራለች፡፡ “ቆንጆ” ሆይ አስቀድመሽ በአይንሽ ውስጥ ያለውን ግንድ አውጪ ከዚያ በሌላው አይን ያለውን ጉድፍ መመልከት ትችያለሽ፡፡ መልእክታችን ይህ ነው፡፡ በቀጣዩ እትምሽ ላይ ማስተካከያ እንደምታደርጊና ምንጩን እንደምትጠቅሽ ተስፋ በማድረግ በዚሁ እንሰናበትሽ፡፡

9 comments:

 1. ሠይፈ ገብርኤልMarch 14, 2012 at 11:53 AM

  ጐበዝ ሳምንት አለፈን ፡፡
  ይኸ ተገለበጠ የምትሉትን ቃለ መጠይቅ እናንተ ሳታወጡት አስቀድሞ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲየን መንበረ ፖትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ድረ ገጽ አውጥቶት አንብቤአለሁ ፡፡ እናንተ ጋር ወጥቶ ሳየው ያነበብኩት ጉዳይ ስለነበረ ድጋሚ እንዴት እንደሆነ አላጣራሁም ፡፡ የምትወቅሱት ግለሰብ ይህን የቃለ መጠይቅ ዘገባ ከሌላም ድረ ገጽ ሊያገኘው ይችላል ለማለት ነው ፡፡ አሁንም በተጠቀሰው ድረ ገጽ ላይ ቃለ መጠይቁን ማንበብ ለሚፈልግ ሰው ይገኛል ፡፡ የተቀረው ወቀሳችሁ አግባብ ይመስለኛል ፡፡ ጋዜጠኛ ዜናን ሲዘግብ ከሁሉም አቅጣጫ የቀረቡለትን መረጃዎች አመጣጥኖ ማቅረብ ይገባው ነበር ፡፡ በተረፈ እናንተም ወንጌልን መደባለቅ ልታቆሙ ይመስላል ፤ በመወቃቀስም ይሁን የምንማማርበት ነገር መጻፍ አቁማችኋል ፡፡

  ለቤተ ጳውሎስ ድረ ገጽ ልኬው የነበረ ቃለ ወንጌል ጽንሰ ሃሳብ እንዲህ ቀርቧል

  ይፈለጋል

  ቢራቡ ያበላል ፣ ቢጠሙም ያጠጣል፤
  ቢወድቁ ያነሳል ፣ ቢደክሙም ያጸናል፤
  ድውይ ይፈውሳል ፣ ቢሞቱም ያስነሳል ፤
  እንዲህ ያለውን ሰው ፣ ቢያነግሡት ምን ይላል?

  ተኝተው እሚያበላ ፣ ሲሞቱ የሚያስነሳ
  ፈተናን አስወጋጅ ፣ መከራና አበሳ
  የሱስ ደግ ነበር ፣ ግን ከየት ይገኛል?
  የሰማሀበቱ ፣ አገሩን ማን ይሏል?

  ክፈት እያለ ነው ፣ ከደጃፍህ ያለ፣
  ነገር ግን መምጣቱን ማነው ያስተዋለ ?
  እስቲ ዛሬ ተነስ ፣ ክፈተው በርህን ፣
  ሳይፈጽም አይሄድም የተላከበትን ፤
  አንተ የፈለግከው ለስጋህ ምቾት
  የሱስ አመጣጡ ፣ ለፍትህ ምህረት
  ፍቅርን ለማስተማር ፣ ፍጹሙን እውነት
  ህይወቱን አጥፍቶ ህይወት ለመስጠት ፣ ህይወት ለመስጠት !!!

  ሠይፈ ገብርኤል

  ሃሳቡ የተመጣጠነ እንዲሆን በማለት ፡፡ በነገር ብቻ ከተወጠርን ፣ ሳናውቀው ሰይጣን በላያችን እየነገሰ ፣ ዙፋኑንም እያመቻቸ ይሄዳል ፡፡

  ReplyDelete
 2. ሰይፈ ምን ነካህ? በቅድሚያ ሀሳቡን ተረዳ እንጂ፡፡ ቃለመጠይቁን በመጀመሪያ ያወጣው አባ ሰላማ ነው አልተባለም እኮ፡፡ የተባለው አባ ሰላማ ከሰንበት ትምህርት ቤቶች ድረገጽ ላይ ወስዶ ፖስት ያደረገውን ነው ቆኖጆ ተብዬዋ መጽሄት ያወጣችው፡፡ ለዚህም ማስረጃ በመጨረሻው ላይ የተጠቀሰው አድራሻ ከአባ ሰላማ ላይ እንደተወሰደ አመላካች ነው የሚል ነው፡፡ ስለዚህ ደካማ ጎንን ስንተችም በማስረጃ ላይ ተደግፈን ቢሆን ይመረጣል፡፡ በተረፈ አስተያየትህ መልካም ነው፡፡ ወቅታዊ ጉዳዮችን መስማታችን ጠቃሚ ነው፡፡ የዚያኑ ያህልም ሕይወትን የሚያነጹና የሚያነጋግሩ ጽሑፎችም ቢወጡ ለአይነት መልካም ነው እላለሁ፡፡

  ReplyDelete
 3. Keep the good work. Bravo Aba selama

  ReplyDelete
 4. Ahun yihe hulu weree yemitsaf neger tefo new? Whether they copy and Paste it or not what is the difference? Yenanten dereja yaworidal?Enesunis yasikebirachewal? Woyes Yehe yeaba sereke kalemeteyik enante copy paste endaderegachihut eyawokachihu lelawun mekawomachihu Yemirimir sira seritachihuna yetezerefachihu meselachihu?
  sile mahiberekidusan banesachihut lay gin"መንፈሳዊነት በኢየሱስ አዳኝነት ማመን፣ እርሱን ብቻ መስበክ፣ በእርሱ እየኖሩ እርሱን መምሰል እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ ማህበሩ ግን እንኳን ክርስቶስን ሊመስል የኢየሱስ ስም ለምን ተጠራ የሚል ፀረኢየሱስ ማህበር ነው፡፡" bilachihuwal. Lemehonu Tsere eyesus malet min malet new? Yeyesus telatochis megelechachew mindinnew? Yesun amlakinet yemikidu ayidelumin? Amilakinetun beamalajinet yemilewutu kehadiwoch eneman nachew?MK woyes Tehadisowochina meselochachew Lutherawiyan? Dingil mariam amilakin sayihon sew new yewoledechiwe yemiluna Adagnu gena wedefit endemimeta yemiyasimesilu eneman nachew? Enante yemitachafiruwachew menafikanina tehadisowoch ayidelumin?
  Getachin gin silenezehina meselochachew"Gata Hoy Gata Hoy Yemilegn hulu mengiste semayat yemigeba ayidelem" biluwalna ayidenikegnim. betechemarim "Besime yimetalu bizuwochinim yasasitalu" endalew besimu sewochin lemot yemitazegaju enaniten meselochachihu bemitiserutna bemitaworut alidenekim mininetachihun kemiyasayegn beker.
  Mahiberu rasun "Kidus" yaderigal maletachihus ahun yesimun tirgum satawuku kertachihu new? bemiyawotachew hitimetoch lay hule megiletsun atawukumen? joroachihun definachihu alawukim maletachihuna lela tirigum mesitetachihu maninetachihun yasayal enji lenanite min waga yasigegnlachihuwal?
  "Eyesusin mesibek" sitilus endeenanite Yegetan kalkidan mekad kidusanin mawaredna kibirachewun makalel lemalet feligachihu kalihone beker MK silegeta ayisebikum beadagninetum ayaminim litilu newun? Yihenin erasu azimachchihu Satinael kesema anegetachihun kolimimo yigedilachihuwal tetenikeku weyolachihu.Enanite kale wunijellana hasetegna kis beker kumneger endelelachihu kesirachihu teredichalhuna Libona yistachihu kemalet beker minim malet alichilim.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Diablose ktefat ena melkam siran kemoqesheshe wechi min sera alwe belhe new wendeme, ensu eqo yetquaquamute lezhe new!! betsolatachin enashenfachewalen!! eyteshenfum new!! yawequtal

   Delete
 5. aba selama ye tehadeso mefencha

  ReplyDelete
 6. ምን አይነቶቹ ናችሁ ብቻ እግዚአብሔር ይድረስልን እንጂ ልታጠፉን ነው??????

  ReplyDelete
 7. yetesfaye hasab lik eko new yegna betekrstiyan be eyesus adegninet bekidusan amalajinet yemitamin nat letintawitwa betekrestiyan enanten endet enisemalen

  ReplyDelete