Wednesday, March 14, 2012

የተክለ ሃይማኖት መቃብርና አጥንት ለምን ይታጠናል? - - - Read PDF

ገድለ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያናችንን፣ ሕዝባችንን ያጠፋ፣ ወንጌልን የጋረደ ግርዶሽና በበሬው ወለደ ተረት የተሞላ ሆኖ ሳለ እርሱን የጻፈ ያጻፈና የተሳለመ ስሙ በሕይወት መጽሐፍ እንደሚጻፍለት ይናገራል። በዚህ ሐሰተኛ ስብከቱ የቤተ ክርስቲያናችን ምመናን ወንጌልን ትተው እርሱን በማሰራጨት ሥጋውና ደሙን በመቀበል ፋንታ የደብረ ሊባኖስን ፍርፋሪ በመብላት፤ ንስሐ በመግባት ፈንታ በደብረ ሊባኖስ በመቀበር ለመጽደቅ ከንቱ ተስፋ ይዘው ይገኛሉ። ስለዚህ መጽሐፉ የሐሰት አባት ዲያብሎስ የሸረበው ተንኮል መሆኑን ለሕዝባችን ለማሳወቅ እንፈልጋለን። በጣም የሚያሳዝነው ግን በክርስቶስ ያመኑ ወንጌልን ተምረው ለሕዝባቸው ለማስተማር ደፋ ቀና የሚሉ መምህራን ይህን የሐሰት ድርሰት ባለመቀበላቸው በቤተ ክህነት አደገኛ ፖለቲከኞች መናፍቃን እየተባሉ መሰደዳቸው ነው። ክርስቲያን ለመባል የሚያበቃ የገድለ ተክለ ሃይማኖትን ተረት ማመን ወይስ በመጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈውን የእግዚአብሔር ቃል ማመንና በርሱ መኖር? ይህ መጽሐፍ የወንጌልን ቦታ እስኪለቅ ድረስ በውስጡ የያየዘውን ባዶ ተረት እናሳያለን።
የተክለ ሃይማኖት መቃብር በደብረ ሊባኖስ ገዳም እንደሚገኝ ሁላችንም እናውቃለን። አንጥቱ ግን ግንቦት አሥራ ሁለት ቀን ካምሳ ዓመት በኋላ ከተቀበረበት ወጥቶ አምልኮ በሚደረግበት ቤተ መቅደስ ውስጥ እንደተቀመጠ ይታወቃል። በየጊዜውም እጣን ይታጠናል።  ለምን ይሆን?  በጸሎት ብዛት ተቆረጠች የተባለችው እግር ግን የግል ቤት ተሠርቶላት በዚያ ትኖርላች ይባላል። ሌላው ታሪክ ደግሞ ክንፍ አውጥታ አርጋለች ስለሚል ከተክለ ሃይማኖት ስእል ጋር ክንፍ ያወጣች እግር አብራ ተስላ ትታያለች። ተክልዬ ክንፍ ያላወጣ አካል ያላቸው አይመስለኝም። ሆኖም የተክለ ሃይማኖት እግር አለች በሚባለው ቤት የተክለ ሃይማኖት በዓል ሲሆን በሕዝብ ተጨናንቃ በዓይናችን አይተናል፤ እግሪቱን ለማየት ሞክረን ግን ሳናያት ቀረን።
ወደ ነገራችን እንመለስና የተክለ ሃይማኖት መቃብር የሚገኘው መንግሥተ ሰማያት ባለችበት አቅጣጫ ነው ተብሏል። ታሪኩ የሚጀምረው ሃምሳ ዘጠነኛው ምራፍ ላይ ነው። አምደ መስቀል የተባለ የተክለ ሃይማኖት የእሕት ልጅ በድንገት ሞተ ይለናል። መነኮሳቱ ፍታት ፈተው ሊቀብሩት ሲሞክሩ በድኑ ተንቀሳቀሰ መነኮሳቱ ምን ሆንክ ቢሉት እንደምታዩት ሞትኩ መላእክትም ወደ ተክለ ሃይሞት ቤት ወሰዱኝ፤ በዚያ ተክለ ሃይማኖትን አየሁት አክሊሉ ከፀሐይ ሰባት እጅ ያበራል፤ ክብሩን ልናገረው አልችልም አላቸው ይላል።  ተክለ ሃይምኖትም አምደ መስቀልን ከመንግሥተ ሰማያት ወደ ደብረ ሊባኖስ እንዲመለስ አዘዘው የሚከተለውንም መልእክት ነገረው «ኤልሳ ወደኔ ይምጣ ፊልጶስ በመንበሬ ይቀመጥ.. መታሰቢያየን እንዲያደርጉ ለሚመጣው ትውልድ ንገሩ ዳግመኛም ይህ የምታየው አዳራሽ በመቃብሬ ላይ ነው፤ ጌታየ እስኪመጣ ድረስ እንዲሁ ይኖራል ይህንንም ለሚመጣው ትውልድ ነገሩ» ገድለ ሃይማኖት ምዕራፍ 59 4-6
ኤልሳእ ተክለ ሃይማኖት ሲሞቱ በርሳቸው የተተካው የገዳሙ አስተዳዳሪ ሲሆን ፊልጶስ የተባለው ደግሞ አባ ኤልሳን አስወግዶ እጨጌ የሆነው የተክለ ሃይማኖት ዘመድ ነው። የገዳም ስልጣንም አስገራሚ የፖለቲካ ድራማ ይታይባታል። ይህ አምደ መስቀል ሞቶ ተክለ ሃይማኖት ካለበት ከደረሰ በኋላ እንደገና በተክለ ሃይማኖት ታዝዞ ነው ከሞት ተነሥቶ ይህን መልክት ያደረሰው። ታሪኩን ስንመረምረው ከተክለ ሃይማኖት ጋር ሥጋዊም ሆነ ፖለቲካዊ ዝምድና ያላቸው ሰዎች ማድረግ የሚፈልጉትን ለማድረግ ተክለ ሃይማኖት ነገረን ለማለት የፈጠሩት ዘዴ እንጂ የተክለ ሃይማኖት ነፍስ ሙታንን የምታስነሳ ሆና አይደለም። በመጀምሪያ ገድሉ ተክለ ሃይማኖት 25 ኪሩብ ሆነው በጽርሃ አርያም የጌታን መንበር እያጠኑ ይኖራሉ ብሎን ነበር። አሁን ደግሞ በነፍሳቸው በመንግሥተ ሰማያት በደብረ ሊባኖስ መቃብራቸው አቅጣጫ እንደሚገኙ ይነግረናል። እኒህ ሰው በሁሉም ይገኛሉ ማለት ነው? አንድ የእግዚአብሔር ሰው «መታሰቢያየን አድርጉ ለሚመጣውም ትውልድ ንገሩ» ብሎ እንዴት ሊያስተምር ይችላል? ተክለ ሃይማኖት መታሰቢያቸው እንዲደረግላቸው ዝናቸው ለሚመጣው ትውልድ እንዲነግራላቸው የፈለጉት ለምን ይሆን? መታሰቢያቸው ቢደረግስ ለምን ይጠቅማቸዋል? መታሰቢያ ባማርኛ ሲሆን በግዝ ተዝካር ይባላል። ተዝካር ለሙታን የሚደረገው ነፍሳትን ለማጽደቅ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስና በሌሎች የቅዱሳን እውነተኛ ታሪኮች ከማናውቃቸው መታሰቢያ እንዲደርግላቸው ታሪካቸው ለትውልድ እንዲነግርላቸው ያስተማሩ ቅዱሳን የሉም። የተክለየ አዋጅ ግን ጥያቄ ያስነሳል። አጥንታቸውና መቃብራቸው የሚታጠነው በዚህ አዋጅ ምክንያት ነው ብለን እንድናስብ ያደርገናል። ከሞት ከተነሳው ካምደ መስቀል መልክት በኋላ እጨጌ ፊልጶስ ስለ ተክለ ሃይማኖት መቃብር የሚከተለውን አሳፋሪ አዋጅ አወጁ
«ወበእንተዝ ተሠራ ከመ ይጥእኑ መቃብረ አቡሆሙ በበዕብሬቶሙ ወይግበሩ ተዝካሮ በፍቅር ተጋቢኦሙ እምበሐውርቲሆሙ»
ትርጉም «ስለዚህም በየተራቸው ያባታቸውን መቃብር እንዲያጥኑ ከየሀገራቸውም ተሰብስበው በፍቅር መታሰቢያውን እንዲያደርጉ ሥራት ተሠራ» ምዕራፍ 5910 ተክለ ሃይማኖትን ማምለክ የተጀመረው ከዚህ አሳዛኝና አሳፋሪ አዋጅ ጀምሮ ነው። አምደ መስቀል መታሰቢያየን አድርጉ ብለዋል ብሎ መልክት ሲያመጣ እነጨጌ ፊልጶስ የተረዱት አምልኮን ነው። የተከለ ሃይማኖት መቃብር በመንግሥተ ሰማያት ሥር ነው የተባለውም መቃብሩን ለማስመለክ ሆን ተብሎ የተሸረበ ተንኮል ነው።
እጣን በመጽሐፍ ቅዱስ በአምልኮ ጊዜ ለእግዚአብሔር ብቻ የሚቀርብ መስዋእት ነው ዘሌ 16 13 እሥራኤላውያን የነቢያቶቻቸውን መቃብር ያስጌጡ ነበር ማቴ 2329 እጣን ለመቃብራቸው ያጥኑ እንደነበር ግን አልተጻፈም። ታዲያ የተክለ ሃይማኖት መቃብር ለምን ይታጠናል? ይህ ባዕድ አምልኮ አይደለምን? ለስእል ማጠን የተጀመረውም መቃብርን ማጠን ከተጀመረ ጀምሮ ሳይሆን አይቀርም። በቤተ መቅደሳችን ውስጥ ያሉ ስእሎች ሁሉ በቅዳሴና በኪዳን ጊዜ ይታጠናሉ። የጌታ የመቤታችን የመላእክት የተክለ ሃይማኖት የገብረ ማንፈስ ቅዱስ ሰው ከመርካቶ ገዝቶ እያመጣ ያንጠለጠለው ስእል (የሰው እጅ ሥራ) ሁሉ ይታጠናል። ስእል ለትምህርት የተሠራ እንጂ ለአምልኮ የተሠራ አይደለም ግን ለምን ይታጠናል? እጣን ማጠን አምልኮ ከሆነ ስእሎችን ስናጥንስ እያመለክን አይደለምን? የተክለ ሃይማኖት አጥንት ዛሬም በቤተ መቅደሱ ውስጥ በየጊዜው ይታጠናል። ለምን? እንዲህ ዓይነቱ ባዕድ ነገር በጌታችን በሐዋርያቱና በሊቃውንቱ ከተገለጠው እውነተኛ የክርስትና ሃይማኖት የወጣ ስለሆነ ሊወገድ ይገባዋል። የቤተ ክርስቲያናችን የሃይማኖት መሪዎችስ ስላስተዳደር ስለገንዘብ ስለ ሹመት ስለፖለቲካ በመካሰስ ጊዜያቸውን ከማባከን እንደጥንቶቹ የእሥራኤል ነገሥታት ቤተ መቅደሱን ቢያጸዱ አይሻልም? እንደዚህ ዓይነቱን ነውር ከመካከላችን ሳናስውግድ መግባባት እንችላለንን? 2 ዜና 291-24

ይድረስ ለሊቃውንት ጉባኤ

ሊቅነታችሁ ለማን ነው? ለሕዝቡ ለእግዚአብሔር ወይስ ለኑራችሁ? እኛና እናንተ ፊት ለፊት በዚህ ጉዳይ ተነጋግረናል፤ እናንተም ይህ ከዚህ በላይ ያየነው ስሕተት መሆኑን ታውቃላችሁ። ሁሉም ጳጳሳት እንዲሁም ብዙ ካህናት ገድለ ተክለ ሃይማኖት  ቤተ ክርስቲያችንን እንደበከለና ለእርምጃዋ እንቅፋት እንደሆነ ያውቃሉ። የኛ ጥያቄ ሕዝቡ በስሕተት ትምህርት እንዲህ እየተጎዳ ለምን ዝም እንላለን ነው? ለምን አይታረምም? እኛ ይህን ጉዳይ ባደባባይ በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ለመግለጥ የተገደድነው ሁላችሁም ስሕተት መሆኑን እያወቃችሁ ዝም በማለታችሁና እንዲያውም እኛን የተሳሳቱ ናቸው በማለት ክሳችሁን ባደባባይ በማቅረባችሁ ነው። እባካችሁ ወደ እውነት እንመለስ እውነቱን አስተምረን እንሰደድ ለሕዝባችን እንራራለት ምድራዊው ኑራችን የሰማይ መኖሪያችችንን የሚያዘጋጅ ነውና ለሰማዩ እንሥራ።

ተስፋ ነኝ

ከደብረ ሊባኖስ ጉብኝት በኋላ

   

45 comments:

 1. ስእል ማጠን is practiced not only in Ethiopian Orthodox church but also in the other oriental and eastern Orthodox churches. I am not sure if it is there in catholic church. You guys don't many times seem to have enough knowledge of the apostolic church because your father originated in the 16th century.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ስእል ማጠን ያለው በምስራቅ አብያተ ክርስቲያናት ብቻ አይደለም። በህንድና በታይላንድ፣ በበርማና በቻይና፣ በቲቤትና በኔፓል የቡድሃ መነኮሳት ገዳማት ሁሉ ነው። የምስራቅ አብያተክርስቲያናት ስእልን ስለማጠን በአዋጅ የጀመሩት ከ7ኛው ክ/ዘመን በኋላ ቢሆንም የቡድሃ መነኮሳት ግን ከክርስቶስ ልደት በፊት ጀምሮ ሲፈጽሙት ቆይተዋል። እንዲያውም ክርስቲያኖቹ ስእልን ማጠን፤ የምንኩስና ስርዓትንና የመነኮሳት ቢጫ መልበስን፣ መቁጠሪያ መቁጠርን የተማሩት ከቡዲሂስቶች ነው። ልዩነቱ ቡዲሂስቶች በቡድሃ ሃይማኖት ውስጥ ሲኖሩ ክርስቲያኖቹ በክርስትና ውስጥ መገኘታቸው ነው።
   የክርስትና አስተምህሮ ስለመሆኑ የምንመረምረው ብዙ የምስራቅ አብያተክርስቲያናት ስለሚፈጽሙት ሳይሆን አፈጻጸሙ የሕይወት አስተምህሮ በሆነው በወንጌልና በሐዋርያት የተሰራ ስርዓት ነው ወይ? በሚል መለኪያ ብቻ ነው። ወንጌላችን ስእል ስለማጠን ወይም እንድናጥን የሚነግረን አንድም ቃል የለውም። ሐዋርያትም ስእል ሲያጠኑ ስለመገኘታቸው የሚገልጽ አንድም ቃል ወይም አንድም አብነት የለም። ታዲያ በሌለ ነገር ላይ የሌለ ተግባር መፈጸም የለበትም ማለት ነው ስህተት ወይስ የሌለ ነገርን ሊኖር ይገባል ብሎ መከራከር?
   ስህተት ብዙ እድሜ ስላስቆጠረ ወደእውነትነት አይቀየርም። እውነትም ብዙ ዘመን ስለተሰወረ ወደውሸትነት አይለወጥም። ሃይማኖት መርምረው የሚያምኑት እንጂ ውሸት ወደእውነት ሊቀየር እንደሚችል «የኖራ ድንጋይ ወደእብነ በረድነት መቀየር» ዓይነት ምሳሌ ልትሰጥ አትችልም። ተአምረ ማርያም በመቅድሙ ከግብጽ እንደመጣ ይናገራል። መጣሁ ካለበት ጊዜ በኋላ በውግዘቱ መጽሐፍ ላይ ብዙ ኢትዮጵያዊ ታሪኮች ቆይቶ መጨመሩን ስናነበው እናገኛለን። ያ ማለት መጽሐፉ ከግብጽ አልመጣም ወይም የውግዘት መጽሐፍ አይደለም ለሚል ሰው ማስረጃ ታቀርባለህ እንጂ እድሜውን ቆጥረህ ታምናለህ ልትለው ተገቢነት የለውም። ከ15ኛው ክ/ዘመን ጀምሮ ስለነበረ ብቻ እንደእውነት ሊቆጠር አይችልም፣ የሚታየው የጽሁፉ ይዘት እንጂ እድሜውን ለእውነታው አረጋጋጭነት በ21ኛው ክ/ዘመን ጥያቄ ቢቀርብ ዛሬ ተነስተህ ስንት ዘመን የቆየውን ነገር ልትጠይቅ አትችልም ማለት አለማወቅ ነው።
   መናፍስት ጥንትም ነበሩ፣ ዛሬም አሉ። የድሮውንም ሆነ የዛሬዎቹን የምንመረምረው በመናፍስቱ እድሜ ሳይሆን በመጽሐፍ ቅዱስ ነው።

   1ኛ የዮሐንስ መልእክት4፥1
   ወዳጆች ሆይ፥ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፥ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደ ሆነ መርምሩ፤ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና።
   ይህ ከተባለ 2000 ዘመን ሆኗል። ውድ «Anonymous» ድሮ የገባ መንፈስ ዛሬ አይመረመርም?

   Delete
  2. ፍቅረ ማርያምMarch 16, 2012 at 12:40 PM

   የግንዛቤ ጉድለቶች የፈጠሩትን ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት፡
   የአቡነ ተክለ ሃይማኖት መቃብር ፣ ከመርካቶ የተገዛው ስዕል ሁሉ ዕጣን ለምን ይታጠናል ?
   የእኔ መልስ ቤተ ክርስቲያን (ቤተ መቅደስ) ውስጥ ስለሚገኙ ብቻ አብረው ይታጠናሉ የሚል ነው ፡፡ ስዕሎቹም ሆኑ የአቡኑ አጽም ከተጠቀሰው ቦታ እንዲወጡ ቢደረግ እንኳን፣ ቤተ መቅደሱ እንደተለመደው ፣ እንደ ወትሮው ሆኖ መታጠኑ አይቀርም ፡፡ ከዛ በተጨማሪ መገንዘብ ያለብን ፣ የፈቀደው ነገር ሁሉ ቢታጠንም ፣ አምልኮው ለአብ ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ መሆኑን ነው ፡፡

   ከእዚህ አንጻር ካየነው ለአንድ ነገር የታሰበው ለሌላውም ይተርፋል እንጅ በቀጥታ በጠዋት ተነስቶ የጊዮርጊስን ፣ የገብርኤልን ወይም የተክለ ሃይማኖትን ሥዕል ልጠን ብሎ ጸሎት የሚጀምር አገልጋይ የሚኖር አይመስለኝም ፡፡ ቤተ መቅደስ የሚገኙ ንዋያተ ቅድሳት ሲታጠኑ ፣ በዛ አካባቢ የተገኙ ንዋያት ፣ ስዕሎች ፣ አጣኚውም ሳይቀር አብረው ይታጠናሉ ፡፡ ይኸንኑም የምለው ከድፍረቴ የተነሳ ነው እንጅ ፣ ቤተ መቅደስ ውስጥ ገብቼ ምን ምን እንደሚያጥኑ አይቼ አይደለም ፤ ስለዚህም የንዋያቱን ልዩ ዝርዝር ማቅረብ አልችልም ፡፡

   ማስታወሻ፡-
   በዛን ሰሞን ስለ ገዳም ሲነሳ ቡድሃ ተብሎ ተጠቀሰ ፤ ዛሬ ደግሞ የእጣን ማጠን ታሪክም ወደዚያው እየተሽመደመደ ነው ፡፡ የገዳም ህይወትና የዕጣን ማጠን ሥርዓት ለክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው ፡፡ እንዲህ እየገፋን ማቆላለፍ ከፈለግን እኮ ፣ ኢየሱስም ያስተማረው ትምህርት በጐነትን ስለሚሰብክ ፣ ከቡድሃ ተምሮ አስተማረን ልንል ነው ማለት ነው ፡፡ ሰለዚህ እስከዚህ ድረስ ስለቡድሃ ሃይማኖት አስተዋጽዖ የምንቆጥረው ቢበቃን መልካም ነው እላለሁ ፡፡ ሃይማኖቱን ያንኳሰሱ እየመሰላቸው ፣ ሰዎች የክርስትና ሥርዓትንና ልማድን በሙሉ ወደ አልሆነ አቅጣጫ እየወሰዱት ነውና ፣ እኛም ተከትለን አናስተጋባው ፡፡

   መልስ ይፈልጋል ፡-
   - የአቡነ ጳውሎስ የቦሌ መድኃኒዓለም ሐውልት ስለምን ይሰገድለታል? ደሞ በሌላ እንዳይተረጐም /የቤተ ክርስቲያን አባቶችን አክብሩ ይላልና መጽሃፉ/ እስቲ ጥያቄዬን ወደ ልማድ ልቀይርልህ ፤ ፊትህን ስትታጠብ እጅህን ውሃ ለምን ይነካዋል ?

   - ቫቲካን በሐዋርያው ጴጥሮስ ላይ ቤተ ክርስቲያኗን ሰርታ ፣ እየጸለየች ፣ እየቀደሰችበትም ይገኛል ፡፡ ይኸም በእናንተ አባባል እንደ ባዕድ አምልኮ ተብሎ ይቆጠራል ወይስ አይቆጠርም ? ሐዋርያው ጴጥሮስንስ እየተደረገ ስላለው ኃላፊ አድርጐ መውቀስ ተገቢ ይሆናል ?

   አቡነ ተክለሃይማኖትን ከቅድስናቸው ባለፈ የማደንቅበት ምክንያት
   - ሳያዩት ማመናቸው ፡፡ ኢየሱስን በአካል ሳያዩት በንባብና ከቤተሰብ ባገኙት ትምህርት ብቻ አምነው ለረጅም ዓመታት ከሐዋርያቱ ባልተናነሰ ውጤት ያስገኘውን ክርስትናን ለመስበክ መትጋታቸው ፣
   - የእምነት ጽናታቸው ፡፡ እንደ ጌታ ሐዋርያት በትዕግሥትና በጽናት ቆመው ፣ እስከ መጨረሻው በእምነት መገኘታቸው ፡፡ እኛ ሁለት ሰዓት ቆመን ማስቀደስ አንችልም ፤ ወይ እንደገፋለን አለበለዚያም ማረፊያ ፈልገን እንቀመጣለን ፤ እሳቸው ግን እግራቸው መቆረጥ እስከሚደርስ ቆመው በመጸለይ ፣ የሚፈጠረውንም ህመም ተቋቁመውና ዘንግተው አምላካቸውን ለማግኘት ሲሉ እስከ ፍጻሜአቸው መበርታታቸው ፡፡ በአምላክ ጸጋና በረከት መፈጸሙን ባልዘነጋም ፣ ከሁሉ አስቀድሞ ለዚሁ ያበቃቸውን ነጻ ምርጫ ወደዚህ ማድረጋቸውም ቢሆን ማለቴ ነው
   - በትዕቢትና ትምክህት አለመወሰዳቸው ፡፡ ይህን የሚያህል መንፈሳዊና አካላዊ ተጋድሎ አድርገውም ፣ ከትህትና ውጭ ፣ ስላደረጉትና ስለፈጸሙት አንድም የትምክህት ቃል አለመናገራቸው “ከእውነተኛው ዳኛ ከጌታዬ ፊት ስቆም ምን እመልሳለሁ” የሚለው ንግግራቸው ከሐዋርያቱም በተሻለ ወንጌል የገባቸው መሆናቸውን በመንጸባረቁ

   Delete
  3. From the first centuries of Christianity, icons have been used for prayer. Orthodox Tradition tells us, for example, of the existence of an icon of the Christ during his lifetime, the Icon-Not-Made-With-Hands, and of the icons of the Theotokos immediately after him written by the All-laudable Apostle and Evangelist Luke.
   http://orthodoxwiki.org/Iconography

   Delete
 2. ፍቅረ ማርያምMarch 14, 2012 at 11:46 PM

  ይሄ እንዲህ እንዲህ የምትሉት ነገራችሁ ሲጠፋ የተዋችሁት መስሎኝ አዝኜ ነበር ፣ በእናንተ ነገር ምክንያት ለማንበብ ስለምገፋፋ ብዙ ትምህርቶችን አገኛለሁ ፡፡

  ተስፋ ነኝ የተመለከተና የዘገበልን የአቡነ ተክለሃይማኖትን ታሪክ አንዱን ገጽታ ብቻ ነው፡፡ ምልከታው የአጽም ታሪክን ብቻ ሳይሆን የህይወት ታሪክንም ያቀፈ ቢሆን ኖሮ እንደ አማኝ ሳይሆን እንደ ትስብዕት በህሊና ለመፍረድ ያመቸን ነበር ፡፡ አለመታደል ሆኖ የተለያየ ገጽታውን ማመላከት ወይም መግለጽ አንደፍርም ፣ አለመደብንምም ፡፡ የምንፈልገውን መልዕክት ብቻ በሰው አእምሮ ለመጠቅጠቅ እንታገላለን ፡፡ ያ ደግሞ የምንደብቅና የምንዋሽ ያስመስላልና ጥሩ አካሄድ አይደለም ፡፡ ገጹ ተገልብጧል ካላላችሁኝ ከዚህ በፊት ባለው ጽሁፍ ፣ ጋዜጠኛው የተወቀሰው ባለማመጣጠኑና እንደፈለገው የስሜቱን በመጻፉ ነበር ፡፡ ስለዚህ ይህን ድክመት በተቻለ እኛም ለማረም እንሞከር ፤ ሙሉ ታሪክ አቅርቡ ማለቴ ነው ፡፡ በጐ ፈቃድ ታክሎበት ቢሆን ኖሮ የህይወት ታሪካቸውን አንድ ገጽ ባልበለጠ ጨምሮ ማቅረብ ይችል ነበር ፡፡

  ስለ አቡነ ተክለሃይማኖት የማንበብ ፍላጐቱ በውስጤ አልነበረም ፡፡ ስለተወቀሱ ግን ፣ ትንሽ የተዘለለ ነገር ካለ በማለት ማግኘት በምችለው መንገድ ሌላውን ለመፈለግ ተነሳሁ ፡፡ ከዛም የጐደለውን ትልቁን የህይወት ታሪካቸውን አገኘሁ ፡፡

  እያንዳንዱም የየራሱን ግንዛቤ እንዲያገኝ ያነበብኩበት ድረ ገጽ “ http://st-takla.org/Story-index.html “ ይባላል፡፡ ከተጻፈው መሃል ለክርስትናችን ስላደረጉት አስተዋጽዖ የሚናገረውን አንድ ሁለት ለማስታወሻ ልበል

  - “The saint asked the devil to confess before all the people that he was cheating and to tell them who the real God is, so the devil confessed that Jesus Christ is the real God. The saint started preaching the people and they were all baptized. They were 111,500. They constructed a church and had their communion. As for the people who were killed by the devil; Saint Takla prayed to God to arise them from the dead. God answered his prayers. The saint baptized about 60,000 people and all "Ketana" became Christians.”
  - “He exerted a lot of effort in praying and fasting and kneeling before God. He even used to pray standing on one foot; the right one, until his leg was broken!”

  በገለጽኩት ድረ ገጽ ካነበብኩት የተረዳሁት አቡነ ተክለሃይማኖት በብሉይ ኪዳን የተጠቀሱ ታሪኮችን የተቀራረበ የሚመስል ፣ የአምላክ ፈቃድና እርዳታን እንዳገኙ ይናገራል ፡፡ ብዙውን ገድልና ድል የፈጸሙት ፣ ወንጌልንም ለማያውቅ ኀብረተሰብ ያስተማሩና ስለክርስቶስ ለመመስከር የበቁትም ስለዚሁ የአምላክ ችሮታ መሆኑን በተለያየ ቦታ ጽሁፉ ይገልጻል ፡፡

  ጻድቁ ተክለሃይማኖት የነበሩበት ዘመን የጣዖት እምነት የነገሠበት ስለነበረ ፣ ህዝብ ከተቀበለው የተለየ የሃይማኖት ትምህርትና እምነትን ይዞ ብቅ ማለት፣ መሥዋዕት ለመሆን ቆራጥነትን የሚጠይቅ ነው ፡፡ እነዚያ “በአብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ እመኑ ፤ በኢየሱስ ክርስቶስ እመኑ ፤ ኢየሱስ ሰው የሆነ አምላካችን ነው” የሚሉ ትምህርቶች በሙሉ ፣ በጊዜው እስከ ህይወት መክፈል የሚያደርስ ዋጋን ጠይቀዋል ፡፡ እንዲህ እንደቀልድ ወንበር ላይ ቁጭ ብለን ማኪያቶ እየጠጣን እንደ ምንቀረድደው ፣ ሰደብከኝ ፣ ወቀስከኝ እንደምንባባለውም ጨዋታ ቀላል አልነበረም ፡፡ ይኸ ታሪክ አብሮ ቢቀርብ ኖሮ ለምእመኑ በቂ ምልከታ ይኖረውና አሁንም ከሃይማኖት ውጭ በሆነ መልኩ ፣ እንደ ሰውነቱ የኀሊና ፍርድ ለመስጠት ይችል ነበር እላለሁ ፡፡

  በሌላው ወገን ካየነው አሁን እየገለጽን ያለው ፣ ወደኋላ ሄደን ፣ በ 13ኛው ክፍለ ዘመን ውስጥ ሰለተፈጸመና ስለተመሠረተ ጉዳይ ነው ፡፡ የዛን ዘመን ትምህርትና እምነት በዛሬ ዕይታና ሰፈራ እየለካን ስህተት ነው በማለት ለመከራከርና ለማውገዝ እየሞከርን ስለሆነ ፣ በወቅቱ ስላልነበርን ስህተት እንዳናደርግ እንጠንቀቅ እላለሁ

  ከዚህ ውጭም ብናየው ደግሞ በወቅቱ የነበሩ ሊቃውንትና ምእመን ፣ ፈጽሞ የሰው ባህሪያቸውን በምትሃት ተገፈው ፣ ወደ አህያነት ተለውጠው ነበር ካላልን በስተቀር ፣ በሃይማኖት ውስጥ በዘፈቀደ ግድፈት ሲፈጸም ዝም ብለው ተመለከቱ ፣ ተቀበሉ ማለት አልችልም ፡፡ ስለዚህ የተሰጠውን አስተያየት መልካም ግንዛቤ ቢመስለኝም በግሌ ሙሉ በሙሉ ለመቀበል እቸገራለሁ ፡፡ ያልተፈጸመ ፣ የሃሰት ነገር ቢኖረው ኖሮ የሃይማኖት ትምህርቱና የአክብሮት ስግደቱ እስከዚህ ትውልድ አይደርስም ነበር ማለት ስለፈለግሁ ነው ፡፡

  ReplyDelete
 3. ፍቅረ ማርያምMarch 14, 2012 at 11:47 PM

  በተረፈ እንደ ግብጾች ሬሳ ማቆያ ብልሃት በአገራችንም አለ ወይስ አጽም ለማለት ፈልገህ ይሆን ? በእርግጥ የተፈጥሮ እግራቸው ያለምንም ብልሃት እንደነበረ እስከዛሬ ከቆየ እኔም ለማየት መሄዴ አይቀርም ፡፡

  በጥያቄዎች አስተያየቴን ልቋጭ ፡-
  - አንድን የእምነት መጽሐፍ የተረትና የሐሰት ድርሰት ብሎ ለመፈረጅ የሚያበቁት መስፈርቶችህ ምንድር ናቸው ? ይህን መጠየቅ የፈለግሁት ከሃይማኖት ውጭ ሆነው የሚመረምሩ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስንም ብዙ ብዙ ስለሚሉ ነውና ይህ የእምነት መጽሐፍ የተፈተሸው ከታሪክ ፣ ከፍልስፍና ፣ ከሃይማኖት …. ከምን አኳያ እንደሆነ ብትገልጸው ለማለት ነው ፡፡
  - ቢያንስ በስመ አብ ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ ተባርኮ የሚታደልን ወይም የሚከፋፈልን ቁራሽስ ስለምን ምክንያቶች ፍርፋሪ ለማለት ደፈርክ ? በመባረክ አታምንም?
  - በክርስትና እምነታችን ውስጥ የተአምር መኖርን ትቀበላለህ ወይስ አትቀበልም ?
  - ስለ መንግስተ ሰማያት ፣ ጽርሃ አርያምና እጣን ማጠን ስላልካቸው በደብረ ሊባኖስ ያገኘሃቸው አባቶች ምን አስተማሩህ ወይስ በራስህ ተርጉመህ መጣህ ?

  ይህንንም ሳልጨምር ባልፍ ዋሾ እሆናለሁ ፡፡ ተስፋ ነኝ የምትታገለው ወንጌልን ተቀብሎ በአብ ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ አምኖ የተጠመቀውን ክርስቲያን ኀብረተሰብ እምነትህን ላስተካክልልህ በማለት ነው ፡፡ በአገራችን የአብ ወልድ መንፈስ ቅዱስንና የወንጌል መኖርን የማያውቁ በአርአያ ስላሴ የተፈጠሩ ወገኖች አሉንና ፣ በእርግጥ ከልባችን ስለወገን መዳን የምንቆረቆር ከሆነ አድማሳችንን ከሸዋም ሰፋ እናድርግ ፡፡ በዜናችን ገና የሐዋርያቱ ዘመን ታሪክ የተጀመረ ይመስል አስር ሺህ ሰዎች ፣ አስራ አምስት ሺህ ሰዎች ወንጌል ተሰብኮላቸው ተጠምቀው ክርስትናን ተቀበሉ የሚለው ሰበር ዜና ብዙ ዓመታት አላስቆጠረምና ትክክለኛ የሃይማኖት ሥራ ላይ እንሠማራ ፡፡ የማይገቡ ልማዶች ካሉን በወንጌል ትምህርት በራሳቸው በሂደት ይጠፋሉ ፡፡ አክራሪ ካልሆንን በስተቀር በአንድ ለሊት ለውጥ መምጣት አለበት በማለት ከወገንና ከወንድም ጋር በእልህ ተሞልተን ቅራኔ ውስጥ መግባት አይገባንም ፡፡ በአሜሪካ በክርስትና እምነት ስም የሚጠቃለሉትን ሁሉ አንድ የሚያደርጋቸው ኢየሱስ ክርስቶስ የሚለው ስም ነው ፡፡ ከዛ ውጭ በልዩነታችን እንፋጭበት ብለው ቢነሱ ከእኛም የበለጠ የመስመር ልዩነትና ችግር አላቸው ፡፡ መቻቻልን እንልመድ ፤ መማማርን ባህል እናድርግ ፤ ይቅርታን እንወቅ ፡፡

  በተረፈ ምልከታህን እንደ ሰውነቴ አደንቃለሁ

  ReplyDelete
 4. Kibir Le Amlakachin LeTekile Hayimanot yihun.Amen
  Enantem Kibir Le Amlakachihu LeLuther Yihun.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ውድ ከዚህ በላይ አስተያየት የሰጡ እንግዳ ሆይ! ‘ክብር ለዓምላከ ተክለሃይማኖት ይሁን’። ነው የሚባለው እሺ? አይዞት አጥተውት ሳይሆን ቸኩለው ይሆናል። ማቅ የማያመጣው ጉድ የለምና በዚህ ዐምድ ደግሞ ቅዱሳን አባቶችን መዳፈር ጀመረ? “ሞት ቢዘገይ የቀረ ይመስላል፡፡” ሆኖበትና ”አይጥ ለሞቷ ሄዳ ታሸታለች የድመት አፍንጫ።” የሚለውን ለደፋሮች በዘዴ የተነገረውን ማስጠንቀቂያ ስምቶት ስለማያውቅ ነው። ስለ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት የግብጽ ኦርቶዶክሶች እያለቀሱ ሊያስረዱ ይችላሉ። በስማቸውም የተሠራውን ፊልም አውሰውት አይቶ ገድላቸውን ሊረዳ ይችላል። እኔም የሰማሁትን ሳይሆን ከልጅነቴ ጀምሮ ስለ ፃድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገድል ያየሁትንና የማውቀዉን ልነግረው እችላለሁ። እግዚአብሔር ይመስገን!!! ዳሩግን በተደፈነ ጆሮውና በደነደነው አመጸኛ ልቡ ላይ ቆሞ አይደለም፤ አምኖ እንዲገለጽለት ተማጽኖ እንጂ። አፋኙን የደህንነት ድርጅት ማህበረ ቅዱሳንን (ማህበረ ዲያብሎስን) በወንጌል ትጥቅ አቃጥሎ በፀበል እያጠመቁ በመስቀል ቀጥቅጦ ማስወጣት ነው እንጅ፣ ሉተራን ምን አደረገ? ማቅ ዲያብሎሱ በቁም ያሉትን መነኩሴዎች እንኩዋን ሙልጭ አድርጎ አይደል እንዴ የሚሳደበው። የምን ወዲህ ወዲያ መወላገድ ነው!! ኦርቶዶክስ እንደዚህ ኣይነት ውልግድግድ መንገድ የለውም። ትርጉሙም ቀጥታ ነው። ነገር ግን ኑሮው በዕምነት ጸንቶ መስዋአትነትን የመቀበል የጸጋ ውርስ ነው። እንዴት ቢሉም የጌታችን የመድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ምሳሌው እሄው ነውና። የዘመኑን ዲያብሎስ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ ብሎ ማሳደድ ነው እንጂ የምን መፍራት ነው። የሥላሴ ባርያ አይፈራም። የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ። አሜን!!!
   አንተ በለምድ የተሸፈንክ ማህበረ ቅዱሳን፣
   እውነተኛው ስምህ ‘ማህበረ ሰይጣን’ ፣
   እኛንም ጨምረህ አበዛህ መከራን ፣
   የንስሀን ጊዜም አሟጠን ጨርሰን፣
   እሄው ቁጭ ብለናል ፍርድን እየጠበቅን፣
   ምክንያት በመፈለግ እየተጠቃቀስን፣
   እየተረዳዳን ጉድጔድ እየቆፈርን፣
   ሞትን አስተናገድን ድምጻችንን ቀብረን፣
   እርቀን ሄደናል መመለሻም የለን፣
   እያልን፣
   አሁን ስንነቃ ታይቶናል ውጋገን፣
   አንተ በሄድክበት እኛም አልተከተልን፣
   እዛው በፍርድ ቀን እንናገኛለን፣
   በጻድቃኖቻችን እየተስተናገድን፣
   ተክለ ሃይማኖትን ምርኩዛችን አርገን፣
   አንተ ወዲህ ስትቀር እኛም እንገባለን፣
   መንገዱ እንዳይጠፋን በድንግል ታጅበን።

   Delete
 5. Kibir Le TEklehaimanote Amlak yihun lemalet feligeh yimeslegnale.
  Tekleye Ye'Amlakachin Agelgay nachew

  ReplyDelete
 6. ፍቅረ ማርያምMarch 15, 2012 at 12:04 PM

  ሌላም ተጨማሪ
  በ http://www.melakuezezew.info/2011/12/blog-post_30.html
  ድረ ገጽም ስለ ገድለ ተክለሃይማኖት ከተጻፈው መሃል የወሰድኩት እንዲህ ይላል ፡፡

  - “ከስምንተኛው መክዘ ጀምሮ በሃገሪቱ የመንፈስ መቀዝቀዝ ይስተዋል ነበር ፡፡ ዮዲት ጉዲት መንግሥቱን ይዛ በክርስትናው ላይ ከዘመተች በኋላ ሰሜኑ እና ደቡቡ ተቆራርጧል ፡፡ የሃሳብን ልዕልና የሚያመጣው የመንፈስ ልዕልና ተዳክሟል ፡፡ ለዚህም ኢትዮጵያን የሚዋጅ ኢትዮጵያዊ ያስፈልግ ነበር ፡፡ ይህ ነው የተክለሃይማኖት የጥሪ ምክንያት ፡፡”

  “ትሕትና በተሞላበትና በተሰበረ ልብ ወደ ፈጣሪያቸው ከለመኑ በኋላ በልዩ ልዩ የኢትዮጵያ ክፍለ ሀገራት ከኃጢአት ወደ ገቢረ ጽድቅ ፣ ከክህደት ወደ ኃይማኖት መልሰዋል፡፡ በዚህም የተነሣ ለኢትዮጵያውያን ብርሃን ፀሐይ ተብለዋል፡፡”
  አባታቸውም ሲያርፉም ጠቅላላ ሀብታቸውን ለድኾች መጽውተው አንደኛውን ለወንጌል ስብከት እንደወጡ ይናገራል፡፡

  “አቡነ ተክለ ሃይማኖት በዳሞት እና በሸዋ ካገለገሉ በኋላ መጀመርያ ደቡብ ወሎ ቦረና ወደ ነበረው ወደ ደብረ ጎል ገዳም ገብተው አሥር ዓመት በትምህርት እና በሥራ አሳልፈዋል፡፡ በዚያም ዋሻ ፈልፍለው አስደናቂ ሕንፃ ሠርተው ነበር ፡፡”

  አቡነ ተክለ ሃይማኖት ተግተው በማስተማራቸው የተኛው ሁሉ ነቃ ፤ የደከመው በረታ ፤ የጠፋውም ተገኘ ፡፡
  በሕይወታቸው የመጨረሻ ዓመታት ወደ ደብረ አሰቦ ዋሻ ገብተው በአንድ እግራቸው በጾም እና በጸሎት ተወሰኑ ፡፡ በጸሎት ብዛትም እግራቸውን በማጣታቸው ስለ ክብራቸው ከእግዚአብሔር ክንፍ ተሰጥቷቸዋል ፡፡

  ይህን ሁሉ ገድልና ትሩፋት እየፈጸሙ ዕረፍታቸውም በደረሰ ጊዜ ደቀመዝሙሮቻቸውን «ልጆቼ ሆይ ሁሉም መነኮስ መንግሥተ ሰማይ ይገባል ማለት አይደለም፤ ዓለምን በሚገባ የናቀ ብቻ ይገባል እንጂ ፣ መጀመሪያ የእግዚአብሔርን ጽድቁን ብቻ ፈልጉ፤ ጾምና ጸሎትን አዘውትሩ፤ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ፤ ትእዛዛቱንም አጥብቃችሁ ጠብቁ እያሉ ይመክሯቸው ነበር..» በኋላም «ለዓለም ጨው ለራሴ አልጫ ሆንኩ፤ ለዓለም ብርሃን ለራሴ ጨለማ ሆንኩ፣ ከእውነተኛው ዳኛ ከጌታዬ ፊት ስቆም ምን እመልሳለሁ?» እያሉ በፍጹም ትህትና እና በልዩ መንፈሳዊ ተመስጦ ይጸልዩ ነበር፡፡

  ስለዚህም በአገራችን በተለያየው አካባቢ የክርስትናን እምነት በማስተማርና በማስፋፋት ላይ ስላደረጉት አስተዋጽዖ ኢትዮጵያዊው የጌታ ሐዋርያ ብለን ልናስባቸው ይገባል ፡፡

  ከገድለ ተክለሃይማኖት መጽሐፍ መማር የሚገባን ትንሽ ጸሎት ፡-
  “አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ! የመንግሥተ ሰማያትን በር ትከፍትልኝ ዘንድ እነሆ ቤቴን እንደተከፈተ ተውኩልህ ፤ ደካማ ለሆንኩ ለእኔ ያለ አንተ የሚያፀናኝ የለም ፡፡ ለምፍገመገም ለእኔ ያለ አንተ ደጋፊ የለኝም ፡፡ ለወደቅሁ ለእኔ ያለ አንተ የሚያነሳኝ የለም ፡፡ ለአዘንኩ ለእኔ ያለ አንተ የሚያረጋጋኝ የለም ፡፡ ለድሃው ለእኔ ያለ አንተ መጠጊያ የለኝም ፡፡ ገድለ ተክለ ሃይማኖት ምዕ 28 ፡ 2-3”

  ምስጋና ለዲያቆን መላኩ አዘዘው

  ReplyDelete
 7. እኔን እስከ ዛሬ ሊገባኝ ያልቻለው
  የመንግስትን አስተዳደር ዘውድ ከጻድቆቹ
  --እስከዛሬ እኩያ የሌላቸውን ቤተ ክርስቲያን እንደ ላሊበላ ያሉትን በማነጽ
  ሕዝቡንም በጽድቅ በማስተዳደር ይመሩ ከነበሩት አታሎ ስልጣን ቀምቶ
  የሰለሞን ዘር ብለው ለሌሎች መስጠት ነው
  በክርስትና የሰለሞን የይሁዳ የሚባል ቀርቶ ኢየሱስ ክርስቶስን የተቀበለ
  የወንጌሉን ትዕዛዝ የተከተለ ብቻ ነው ዘላቂ ዘላለማዊ ስራ መስራት የሚችል

  ReplyDelete
 8. ayyiii... abaselama minew endih kemesmer wetachihu? kiristos be mhiretu yasibachihu yemtawetutin text mejemeriya mermirut alamachihu hulu yigermegnal lehamet ena lesidib berachihu betam yesela new fikirin sibeku ebakachihu. . . .

  ReplyDelete
 9. To fekermariam do you read zmegabit tekelhimanot read it it is shameful ofcourse you mentioned some look good but this is just attracting people , but there is no way except Holy bible tekalhimanot is just one of christians member, he cannot add something on our life except Jesus christ ,
  you mentioned about monostic life, it is good but this life is copied from budhism before anthony and paule.
  feker mariam
  do you tekelhaminot had wife ?

  ReplyDelete
  Replies
  1. ዘመጋቢት ተክለሃይማኖት ጸሃፊ ማን ነው ብዬ ላንብበው ፡፡ ከቤተ ክርስቲያናችን የትምህርት ማዕከል የወጣ ትምህርት ከሆነ እቀበለዋለሁ ፡፡ መንገደኛ የሚጽፈው ከሆነ ግን አዝናለሁ ፣ ማንበብ ብችል እንኳን አላምነውም፡፡ ጥያቄው ማንበቤን ለማወቅ ከሆነ ፣ እኔ አላነበብኩም ፡፡

   ስለ ትደር የተጠየቀው ደግሞ ልጃቸው ዮሐንስ ተገኘ ብለህ ልታወራኝ ፈልገህ ይሆን ፡፡ ተራ አሉባልታ ማውራት እየተለመደ ከሆነ ዲኤንኤ አስመርምረህ አቅርብ እላለሁ ፡፡ ዳግመኛ አልሸወድም ፡፡

   Delete
  2. ፍቅረ ማርያምMarch 17, 2012 at 3:23 PM

   የተጻፈን ሁሉ ማመን ስለሚያስከትለው ችግር

   በአሁኑ ዘመን በአጠቃላይ በክርስትና ሃይማኖት ላይ ተጽዕኖ ለማሳረፍ በሚፈልጉ ወገኖች በግልጽም ሆነ በሥውርም እጅግ ብዙ ሥራ እየተሠራ ነው ፡፡ በህጻናት የቢንግ ባንግ ጽንሰ ሃሳብን ለማስረጽ እንደሚሠራው ተንቀሳቃሽ ፊልም ፣ በክርስትና እምነትም ላይ በዘመቻ መልክ ፣ ሃይማኖቱን ሊያራክሱ የሚችሉ መጽሐፍት ተጽፈዋል ፤ እውነተኛውን የመጽሐፍ ቅዱስን ታሪክ አስመስለው ፊልም ሰርተዋል ፡፡ ይኸ ዓይነቱ ቅንጅት ታድያ የሚያጠምደው እነደ እኔ ዓይነት በእምነት ደካማ የሆነውን ፣ ያነበበውን ሁሉ እውነት ነው በማለት የሚቀበለውን ወገን ፣ ያየውንም ሁሉ ሳይመረምር አሜን የሚለውን ግለሰብ ነው ፡፡

   በኢኦተቤ ላይም የሰው መስዋዕት አቀረበች ብለው አልጻፉም እንጅ ለመውቀስና ምእመኑን ለማሳሳት እጅግ ብዙ ሠርተዋል ፤ የእንደዚህ ዓይነቶቹ አገር በቀል ጸሃፊዎች ዓላማ ሌላው ጐናቸው ከታየ ደግሞ ለገቢ ምንጭነት ስለሚረዳቸው ከማስተማሪያነቱ ይልቅ ለጥቅም ሲሉ ጽፈዋል የሚል አመለካከት አለኝ ፡፡ ምክንያቱም ከቀናውና እውነትን ከማስረዳት ይልቅ ፣ የተሳሳተ የግል ግንዛቤአቸውን በወቀሳ መልክ ማስፈር ስለሚወዱ ነው ፡፡ የኢኦተቤን ትምህርትና ሥርዓት በሚቃወመው ጐራ ተቀባይነትን ስለሚያገኙም በጥፋታቸው ይተጋሉ ፡፡ ስለዚህም እንደ ወንድም የምመክረው ፣ አንድ ጉዳይ በጽሁፍ ስለቀረበ ወይም ቲያትር ስለተሰራበት ሃቅ ነው ፣ እውነት ነው ማለት ስለማይቻል ፣ በተለያየ መንገድ የገበዩትን ዕውቀት መመርመርና እውነትን ለማግኘት በግል መታገል እንደሚገባ ነው ፡፡

   በተረፈ ማንበብ እውቀት ይሰጣል እንጅ ክፋት የለውም ፡፡ እኔ ከክርስትና እምነት ጋር የሚያያዝበትንና አንድ ልንሆን የምንችልበትን ነጥቦች በመፈለግ ቁርዓንን ሳይቀር ለማንበብ ሞክሬአለሁ ፡፡ ስላነበብኩት ግን ሃይማኖቴን አልቀየርኩም ፡፡ ስለዚህ ማንበብን አላወግዝም ፤ ካነበብን በኋላ ግን ስለሚኖረን አቋምና አካሄድ መጠንቀቅ እንደሚያስፈልግ አሁንም እመክራለሁ ፡፡

   Delete
 10. ለፍቅረ ማርያም

  "በሌላው ወገን ካየነው አሁን እየገለጽን ያለው ፣ ወደኋላ ሄደን ፣ በ 13ኛው ክፍለ ዘመን ውስጥ ሰለተፈጸመና ስለተመሠረተ ጉዳይ ነው ፡፡ የዛን ዘመን ትምህርትና እምነት በዛሬ ዕይታና ሰፈራ እየለካን ስህተት ነው በማለት ለመከራከርና ለማውገዝ እየሞከርን ስለሆነ ፣ በወቅቱ ስላልነበርን ስህተት እንዳናደርግ እንጠንቀቅ እላለሁ"

  I don't understand what you wanted to say when you wrote "የዛን ዘመን ትምህርትና እምነት በዛሬ ዕይታና ሰፈራ እየለካን ስህተት ነው በማለት ለመከራከርና ለማውገዝ እየሞከርን ስለሆነ ፣ በወቅቱ ስላልነበርን ስህተት እንዳናደርግ እንጠንቀቅ እላለሁ". As you know Christianity has been for more than 2000 years and whatever was truth 2000 years ago, is true now and forever and whatever false 2000 years ago is false now and forever, let alone 13ኛው ክፍለ ዘመን ውስጥ የተፈጸመና የተመሠረተ ጉዳይ. I think we should have a courage and an obligation to declare IT AS FALSE TEACHING, any teaching which deviates from TRUE teaching of ወንጌል even if it is associated with our Lord's name, let alone ተክለ ሃይማኖት. I thought the purpose of the writing is about ገድለ ተክለ ሃይማኖት (ቤተ ክርስቲያናችንን፣ ሕዝባችንን ያጠፋ፣ ወንጌልን የጋረደ ግርዶሽና በበሬው ወለደ ተረት የተሞላ). The writer did not talk about ተክለ ሃይማኖት and never discredit him, but ገድለ ተክለ ሃይማኖት. So let us judge ገድለ ተክለ ሃይማኖት by its content based on the true Tewahdo teachings. if it doesn't pass the measure of ወንጌል. We should proudly say to ገድለ ተክለ ሃይማኖት "Mane, tekel, fares"

  ReplyDelete
  Replies
  1. ፍቅረ ማርያምMarch 16, 2012 at 10:26 AM

   - ማለት የፈለግሁት እንደ ክርስቲያን አማኝ ሆነን ከቃኘነው ፣ ቀድሞውንም ምርመራ ውስጥ መግባት አያስፈልገንም ፤ ትምህርትና ልማዱ ባለበት መቀጠል አለበት ፡፡ ሃይማኖትን በምርመራና በጥበብ ካደረግነው ግን ግድፈት ያመጣል ፤ በዚህ የተጀመረ ወደ መጽሐፍ ቅዱስም ፍተሻ ስለሚጋብዘን ማለቴ ነው ፡፡ በእምነት ከሆነ ግን የማይታመነውንም ፣ ሊሆን የማይችለውንም ሁሉ መቀበል ግድ ስለሚሆን ቀጣይ ሥራ አይኖረንም ፡፡
   - እንደ ሰው በጥበብ ከሆነ የምንቃኘው ፣ ታሪክን መፈተሽና መመርመርን ግድ ይለናል ፡፡ ያን ለማድረግ ደግሞ በቂ መረጃ ምስክርም /መጽሐፉ ውስጥ የተተረከው ታሪክ ሐሰት ነው ብሎ ተጨባጭ ማስረጃ የሚያቀርብ ማለት/ የለንምና ፣ በግምት ደፍረን ከሄድን ግን እንሳሳታለን ማለቴ ነው ፡፡ እንደ ሰው በጥበብ የመፈተሽን ጉዳት በቂ ስለሆነ አንድ ማስረጃ ላቅርብና ልቋጭ ፡-
   የመጽሐፍ ቅዱስ መርማሪዎች ሉቃስ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 9፡7-8 የገለጸው በምዕራፍ 22፡9 ከተገለጸው ተመሣሣይ ክስተት ጋር ስለማይስማማ አንድ ወጥ ጽሁፍነቱን አይቀበሉም ፡፡ አንዱ ጸሃፊ አንድን ታሪክ የተለያየ አድርጐ ስለምን ይገልጸዋል ፡፡ በዚህ ታድያ መጽሐፍ ቅዱሱን ምን ልትለው ነው ፡፡
   9፡7 ከእርሱም ጋር በመንገድ የሄዱ ሰዎች ድምፁን እየሰሙ ማንን ግን ሳያዩ እንደ ዲዳዎች ቁሙ።/ድምጽ ሰምታዋል ግን አላዩም/
   22፡9 ከእኔ ጋር የነበሩትም ብርሃኑን አይተው ፈሩ፥ የሚናገረኝን የእርሱን ድምፅ ግን አልሰሙም። /ብርሃን አይተዋል ግን አልሰሙም/

   ሌሎች ከታሪክ አኳያ የሚፈትሹ ደግሞ እጅግ ክፉ ነገር ያቀርባሉ ፡፡ እዛ ድረስ ለመሄድ ድፍረቱ የለኝም ፤ ነገር ግን የተጻፉ መጽሐፎች አሉ ፡፡ ሃይማኖታችንን ለማጥፋት ካልሆነ በስተቀር ለማጠንከር ምንም አይጠቅሙም ፡፡

   ስለዚህም ገድለ ተክለ ሃይማኖት ደስ የሚልም ፣ አእምሮአችንን የሚፈታተንም ታሪክ ይዟል ፡፡ ሁሉንም ደፍጥጦ ማውገዝ ግን ለኔ ይከብደኛል ፡፡ ባገኘው ልማርበት የምችለውን እማርበታለሁ ፤ እንደ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ጸሎት ዓይነቱ ፣ ትምክህተኛ አለመሆናቸውን የሚገልጸው አባባላቸው "ከእውነተኛው ዳኛ ፊት ስቆም ምን እመልሳለሁ" ፡፡ እምነትን ከምግባር አጣምረው ይዘው እንኳን እንደ እኛ አንድ ቀን በሙሉ አፋቸው አልፎከሩም ፡፡ ይኸን ነው የተክለ ሃይማኖት ክርስቲያንነት የሚያስተምረኝ ፡፡

   Delete
  2. If you really believe in the power of God, holy spirit will lead you to all truth. There will not be any question that will not be answered. I am appalled by you for bringing the true ወንጌል as an example when we are talking about ገድለ ተክለ ሃይማኖት. I admire and respect your individual belief as long as it remains like that. When we talk about the church, then it will be different. I think you know that there are other books like the Gospel of Thomas and the Gospel of James, but we have only four Gospels. I think you will agree that the names Apostle James and Apostle Thomas carry more weight than St. ተክለ ሃይማኖት. So it shouldn't be hard to abandon it if it is found that having it bring more questions than answers. As you said ገድለ ተክለ ሃይማኖት"አእምሮአችንን የሚፈታተንም ታሪክ ይዟል". So either it was amended by some people to add አእምሮአችንን የሚፈታተንም ታሪክ or just it is not the work of Holy Spirit. Once we finish talking about ገድለ ተክለ ሃይማኖት we can discuss your other questions.

   Delete
  3. ፍቅረ ማርያምMarch 19, 2012 at 9:07 AM

   ወንድሜ በጣም ይቅርታ ፤ የምገልጸውን የማትረዳልኝ መስሎኝ በሥርዓቱ ሳላጤነው ጻፍኩት ፡፡ የማይገባ ምሳሌ የሰጠሁበት ምክንያት የእምነት መጽሐፍትን በትስብእት አእምሮና ብልሃት እንፈትሽ ካልን ፣ መጽሐፍ ቅዱሱንም ብዙ ብዙ ያወጡለት ሰዎች ስላሉ የነሱንም ሃሳብ ማስተናገድ ሊኖርብን ነው የሚለውን የማትረዳልኝ ስለመሰለኘ ነው፡፡ በህይወት የቆዩትን የቶማስና የያዕቆብ ብቻ ሳይሆን ኢየሱስ ከመሞቱ ቀን በፊት ወይም በኋላ /እርግጠኛ ዕለቱን ስለማላውቅ ነው/ የሞተውም የአስቆሮቱ ይሁዳ ወንጌል ጽፏል ተብሏል /ምን ጊዜ እንደጻፈው መልስ የለም/፡፡ ሰዎች ይተቻሉ ያልኩት የክርስትናን ዓላማና ተልዕኮ ለማርከስ ተብሎ ተጨማሪ ወንጌል ተብለው የተጻፉትን ሳይሆን ፣ በቀደምት አባቶች ጉባዔ ተቀባይነት አግኝተው አሁን የምናነበውን ስድሳ ስድስቱን መጽሐፍ ነው ፡፡ ወደፊት እንዲህ እንደ ዋዛ ያልሆነ ምሳሌ እንደማልጠቅሰ ቃል እገባልሃለሁ ፡፡ ለእንደ እኔ ዓይነት ደካማ ትልቅ እንቅፋት እንዳስቀመጥሁ አሁን ነው የተሰማኝ ፡፡

   በግሌ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስን አምላክ ፣ የሚታየውንና የማይታየውን ዓለም ፈጣሪ ፣ ኢየሱስን ደግሞ የሰው ልጅን ለማዳን ሲል በድንግል በኩል የተወለደልንና በመስቀል ላይ የሞተልን አምላካችን ፣ ሞትንም ድል አድርጐ የተነሳ ፣ ለኛም ትንሣዔን ያስገኘልንና እንዳለን ቃል የገባልን ፈጣሪያችን ነው ብሎ የሚጠቅስን መጽሐፍ ሳልመራመርI ብቀበለው በእምነቴ ላይ ብዙ ህጸጽ አያመጣም እላለሁ፡፡ ዋናው የእምነታችን መሠረቶች የተጠቀሱት ስለሆኑ ማለቴ ነው ፡፡

   እናም ስለዚህ ለእኔ ገድለ ተክለ ሃይማኖት የአንድ ቅዱስ አባት ታሪክ ስለሆነ የአክበሮት እንጅ የአምልኮ ስግደት ማድረግ አይገባንም /ፍጡር ፍጡርን ማምለክ ሰለማይገባ/ ቢባል አይረብሸኝም ፡፡ ከዛ በዘለለ ግን የዲያብሎስ ወንጌል የመሰለ ያህል አድርጐ ማወገዙ ላይ እኔ አልካፈልም ፡፡ ይህንንም የምለው ስለአክብሮት እንጅ ስለ አምልኮ ጉዳይ ብዬ አይደለም ፡፡

   እኛ ይህን ተመራምረን እንጣለው ብንል እንኳን የአምላክ ቃል የሚከተለውን ይላል፡-
   ከትንቢተ ኢሳያስ መጽሐፍ ስለ ቅዱሱኑ ተስፋ ፡
   - 57፡15፤ ለዘላለም የሚኖር ስሙም ቅዱስ የሆነ፥ ከፍ ያለው ልዑል እንዲህ ይላል። ።

   - 56፡4 - 7፤ እግዚአብሔር ሰንበቴን ስለሚጠብቁ ደስ የሚያሰኘኝንም ነገር ስለሚመርጡ ቃል ኪዳኔንም ስለሚይዙ ጃንደረቦች እንዲህ ይላልና። በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ። ፤ ቤቴ ለአሕዛብ ሁሉ የሚሆን የጸሎት ቤት ይባላልና የሚቃጠለውን መሥዋዕታቸውንና ሌላ መሥዋዕታቸውን በመሠዊያዬ ላይ እቀበላለሁ።

   - 4ዐ፡8 ሣሩ ይደርቃል አበባውም ይረግፋል፥ የአምላካችን ቃል ግን ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች።

   ታድያ ማንን ልከተል ? የማን ቃልስ ልመን ?
   ያዕ 5፡11 እነሆ፥ በትዕግሥት የጸኑትን ብፁዓን እንላቸዋለን …። የተስፋ ቃሉም ይለናልና

   Delete
  4. ፍቅረ ማርያምMarch 19, 2012 at 9:22 AM

   ይቅርታ አነደኛ መልዕክትህን ለመመለስ
   የያዕቆብና የቶማስን ወንጌል ያልተቀበሉት ምእመናን ሳይሆኑ ፣ የቤተ ክርስቲያን አባቶች በጉባኤ ተሰብስበው ነው ፡፡ አሁን እኮ መጽሐፍቱን ተሷስቷል ብለን የምናወግዝ ፣ እንደምስስ ፣ እናጥፋው የምንለው ፣ መጽሐፍ ገባን የምንለው ወጣቶች ነን እንጅ ፣ የቤተ ክርስቲያን አባቶች አይደሉም ፡፡ በሲኖዶስ አባቶች ከወሰኑማ ምኑን ይዤ እቃወመዋለሁ ፡፡ ያስተማሩን እነሱ ስለሆኑ ፣ ማንኛውንም ነገር በስህተት አስተማርናችሁ ብለው ማረምም የእነሱው የሥራ ድርሻ ነው ፡፡ እኔን አሳስተው ወደ ሌላ ከመሩኝ በሃላፊነት የሚጠየቁት እነሱ ስለሆኑ ማለት ፡፡

   Delete
  5. የተጐረደው የትንቢተ ኢሳያስ 57፡15 ቃል - "የተዋረዱትን ሰዎች መንፈስ ሕያው አደርግ ዘንድ፥ የተቀጠቀጠውንም ልብ ሕያው አደርግ ዘንድ፥ የተቀጠቀጠና የተዋረደ መንፈስ ካለው ጋር በከፍታና በተቀደሰ ስፍራ እቀመጣለሁ።"

   Delete
  6. other መጽሐፍትንና ወንጌልንም የተቀበሉት ምእመናን ሳይሆኑ ፣ የቤተ ክርስቲያን አባቶች በጉባኤ ተሰብስበው ነው but I don't know if ገድለ ተክለ ሃይማኖት is one of አባቶች በጉባኤ ተሰብስበው የተቀበሉት መጽሐፍት, if you know please let me know.

   Your argument እኛ ይህን ተመራምረን እንጣለው ብንል እንኳን የአምላክ ቃል የሚከተለውን ይላል፡ is not convincing because we are talking about one particular book that has አእምሮአችንን የሚፈታተንም ታሪክ. Unfortunately the book is about our beloved Ethiopian Saint ተክለ ሃይማኖት. Even though it is about one of the heavy weight of our church if is false Gospel it is FALSE, nothing else.

   Delete
  7. ፍቅረ ማርያምMarch 20, 2012 at 8:57 AM

   - ገድለ ተክለ ሃይማኖትን /ሌሎቹንም የገድል መጽሐፍት ማለት/ የኢትዮጵያ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ፈቅደውና አምነው ካላስገቡአቸው በስተቀር ታድያ ማን አስገባው ሊባል ነው ? መልአከ እንዳልል የማይታሰብ ነገር ነው ፡፡ እንደ ተለመደው አሠራር ከተረዳነው ግን በዘመኑ የነበሩ የቤተ ክርስቲያን አባቶችና ሊቃውንት ስለተቀበሉና ወደ ቤተ ክርስቲያን ስላስገቡ ከእኛ ደረሰ እንላለን ፡፡ የቀድሞዎቹን የቤተ ክርስቲያን መሥራች አባቶችን እንዳልልማ ዘመናቸው አይገናኝም ፡፡ እኔ አባቶች ያልኩት በወቅቱ የነበሩትን የቤተ ክርስቲያናችንን ሊቃውንት ነው ፡፡ በወቅቱ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ የለም እንዳንል ፣ እስከዚህ ዘመን ድረስም እንኳን ይኸ ስጦታ ሊኖር እንደሚችል መጽሐፍ ያስረዳል ፡፡ ስለዚህም መጽሐፉ የመንፈስ ቅዱስን ሥራ መሰከረ እንጅ ሌላ አምልኮ አልፈጠረም እላለሁ ፡፡ ሙትን አስነስቶ ስለ ኣንድ ጻድቅ የሚያስመሰክር ክፉ መንፈስ ሊሆን አይችልምና ፡፡

   - አንድን የገድል መጽሃፍ እናጥፋ ስንል በተዘዋዋሪ የጻድቁን ታሪክ እንዳይታወስ እንደምስስ ማለታችን ነው ፡፡ የትንቢተ ኢሳያስ ቃሎችን የጠቀስኩት ፣ እኛ የእነዚህን የበቁ አባቶችን ታሪክ ብንክድ እንኳን ፣ እግዚአብሔር ቃል ሰጥቶአቸዋልና አይተዋቸውም በማለት ነው ፡፡ ስለዚህም እግዚአብሔር የመረጠና ያከበራቸውን ጻድቃን ፣ የሥራቸው /ገድላቸውን/ ማስተማሪያ አሻራ እንዲጠፋ መታገል የለብንም ፡፡ በመጥፎ ተርጉሞ የሚረዳ ያለውን ያህል ፣ በተምሳሌነቱ በመጠቀም እግዚአብሔርን አምኖ የሚያመልክም ወገን አለ ፡፡ ዓላማችን ሁሉም ወደ እግዚአብሔር መንግሥት እንዲቀርብ መመኘት ከሆነ ማለቴ ነው ፡፡

   - የገድለ ተክለ ሃይማኖትን መጽሐፍ አእምሮአችንን የሚፈታተነን ታሪክ ያልኩት እንደ እናንተው በሰው ጥበብ ስቃኘው ነው እንጅ እንደ እምነት መጽሐፍትነቱ መዝኜ አይደለም ፡፡ በጥበብ መንገድ ሁሉንም እንፈትሽ ከተባለማ መጽሐፍ ቅዱስም እጅግ ብዙ አእምሮአችንን የሚፈታተን ጉዳይ አለው /ቃል ስለገባሁ አልጠቅስም/ ፡፡ አብዛኛው የክህደት ምንጭ የሆነውም ይኸው ይመስለኛል ፡፡ ነገር ግን ከእምነት መጽሐፍ ወገን አድርገን ስንረዳው ሁሉንም ሳንጠራጠር እንቀበላለን ለማለት ነው ፡፡ ስለዚህ አስቀድሜ ለማስረዳት የሞከርኩት እንደ አካሄዳችን የመጽሐፉ ግንዛቤ ሊለያይ ይችላል በማለት ነው እንጅ ፍጹም የሚፈታተን ታሪክ የሚለው የክርስቲያንነት አቋሜ አይደለም ፡፡

   አሁን የቀየርኩ እንዳይመስልህ አስቀድሜ ገልጫለሁ ፡፡ “እንደ ክርስቲያን አማኝ ሆነን ከቃኘነው ፣ ቀድሞውንም ምርመራ ውስጥ መግባት አያስፈልገንም ፤ ትምህርትና ልማዱ ባለበት መቀጠል አለበት” የሚለው ትክክለኛው የኔ የክርስቲያንነት አቋም ነው ፤ ቀጥሎም ደግሞ እንደ ሰው በጥበብ የምንቃኘው ከሆነ የሚል ከእኔ አቋም ውጭ የሆነውን አካሄድንም ለመግለጽ ሞክሬአለሁ፡፡ ነገር ግን ሰው እንደመሆኔ መጠን ፣ ከወንድሞች ስምምነት የምንፈጥርበትን መንገድ በጥበብ በኩል መሻቱ የተሻለ ነው በማለት በእናንተው አካሄድ በመቃኘት ጻፍኩት ፡፡ ነገር ግን ያ አጻጻፌ ፍጹም እምነቴ አይደለምና ተደጋግሞ አይጠቀስ ፡፡

   ልዑለ እግዚአብሔር በጥበቡ ይርዳን

   Delete
  8. ገድለ ተክለ ሃይማኖትን /ሌሎቹንም የገድል መጽሐፍት ማለት/ የኢትዮጵያ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ፈቅደውና አምነው ካላስገቡአቸው በስተቀር ታድያ ማን አስገባው ሊባል ነው ? I realy don't know. No evidence for አባቶች ፈቅደውና አምነው. Fitha Negest is silent about it as well. There are only 81 books mentioned in ANKETS 2 OF Fitha Negest. I hope someone will come up with some answer.

   I don't agree with "ትምህርትና ልማዱ ባለበት መቀጠል አለበት". Not all ትምህርትና ልማድ are good.

   Finaly, I am really disappointed by your comment. Especially "ነገር ግን ሰው እንደመሆኔ መጠን ፣ ከወንድሞች ስምምነት የምንፈጥርበትን መንገድ በጥበብ በኩል መሻቱ የተሻለ ነው በማለት በእናንተው አካሄድ በመቃኘት ጻፍኩት ፡፡ ነገር ግን ያ አጻጻፌ ፍጹም እምነቴ አይደለምና ተደጋግሞ አይጠቀስ ". What do you mean by "ከወንድሞች ስምምነት የምንፈጥርበትን መንገድ በጥበብ በኩል መሻቱ የተሻለ ነው በማለት" and "ነገር ግን ያ አጻጻፌ ፍጹም እምነቴ አይደለምና ተደጋግሞ አይጠቀስ". I thought I was communicating with a good christian who writes what he believe in. There is no compromise in religion. You are a deceptive person. Your real personality is hidden and it looks you have many layers. In the house of God, my brother, it is not good. Be yourself, be real, no matter what. Sometimes you are humble, as if you don't know anything. Other time your are like a barking dog, insulting others calling them bad names. I was struggling to know you from your postings and I wasn't sure until now. You just proved it. I really don't want to spent time with someone who has multiple personality. Again try to write ፍጹም እምነትህን.

   sorry I had to say it

   Delete
  9. ገድል በክርስቶስ ኢየሱስ ክርስቲያን የተባሉ ቅዱሳን የሰሩትን ሥራ የሚተርክ መጽሐፍ ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደሚገኘው የሐዋርያት ሥራ እንደ ማለት ነው፡፡ ገድሎች በአብዛኛው የተጻፉት ቅዱሳኑ ከሞቱ በኋላ ነው፡፡ ገድልን እንደ ትምህርት፣ ቅዱሳኖቹ ስለክርስቶስ የከፈሉትን ዋጋ ለማክበር እኛም የእነሱን አርዓያ ለመከተል በመጽሀፍ ቅዱስ ቃል እየመዘንን እስካነበብነው ድረስ ችግር የለውም፡፡
   በቤተክርስቲያናችን የሚነበቡት ገድሎች ገድሉ ላይ በተጻፉት የተስፋ ቃሎች አብዛኛው ምዕመን እግዚአብሔር ያዘጋጀልንን የጽድቅ መንገድ በመተው የራሱ የሆነ የጽድቅ መንገድ እንዲያቆም አስተዋጽኦ እያደረጉ ነው፡፡ ብዙዎቻችን ቅዱሳን ማለት ቅድስናን በግል ጥረት ወይም ብቃት እንደተገኘ አድርገን እናምናለን፡፡ ይህ ግን ስህተት ነው፡፡ ያለ አንዳች ልዩነት በክርስቶስ አምነው ዳግመኛ የተወለዱ ሁሉ ቅዱሳን ናቸው፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ በመልእክቱ ወስጥ ክርስቲያኖችን ቅዱሳን እያለ ይጠራቸዋል፡፡ በእርግጥም ቅድስና ክርስቶስን በማመንና በመታዘዝ የሚገኝ እግዚአብሔር የሚደሰትበት ከእርሱ፣ በእርሱና ለእርሱ የሆነ መልካም ኑሮ ነው፡፡ የቀደሙትና አሁን በህይወተ ሥጋ የሌሉት ቅዱሳንም ቢሆኑ ከዚህ ውጪ በሌላ መንገድ ቅድስናን አላገኙም፡፡ ‹‹ብቃታችን ከእግዚአብሔር ነው እንጂ በገዛ እጃችን እንደሚሆን አንዳቸን እንካ ልናስብ ራሳችን የበቃን አይደለንም፡፡›› 2ቆሮ 3፡5
   በአብዛኛው ገድሎች ውስጥ የተሰገሰጉትን ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የሚጋጩትን ትምህርቶች ሊቃውንቶች አሳምረው የሚያውቁት ቢሆንም ለማስተካከል የሚያደርጉት ጥረት እጅግ አናሳ ነው፡፡ ለዚህም የተለያዩ ምክንያቶች ይኖbቸዋል፡፡ ከነዚህም ውስጥ ለማስተካከል እንነሳ ብንል ስህተቶች ዘመናትን ያስቆጠሩና ሥር የሰደዱ በሕዝብም ልብ ውስጥ የእውነትን ያህል የሚታዩ በመሆናቸው ሰሚ አናገኝም፣ እውነትን በሚቃወሙ ክፍሎች ‹‹መናፍቅ›› የሚል ስም ተሰጥቶን እንደተሰደዱት ወንድሞቻችን መሰደድ፣ ከእንጀራችን መፈናቀል ሌላም ሌላም መከራ ይገጥመናል የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ እውነትን የሚያወግዙ መናፍቃን የመብዛታቸውን ያህል ውሸትን በብዕራቸው ጫፍ እንካ ለመንካት የሚደፍሩ እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን አባቶች መታጣታቸው ያሳዝናል፡፡
   ስለዚህ ከዚህ ጥፋት ለመዳን የሰው የሆኑትን ነገሮች ከትክክለኛው የቤተ ክርስቲያን የሃይማኖት ውሳኔና ዶግማ አንጻር መመርመርና መልካሙን ሁሉ ይዞ በሃይማኖት ጸንቶ መኖር የእያንዳንዱ ኦርቶዶክሳዊ ወገን ኃላፊነት ነው፡፡

   Delete
  10. ፍቅረ ማርያምMarch 21, 2012 at 9:49 AM

   -“ራሳችንን እንደ ምእመን ከቆጠርን መጽሐፍን መመርመር ውስጥ የሚያስገባን ጉዳይ አይኖርም” ፡፡ በጽሁፍና በቃል የተሰጠውን ትምህርት ሳንጠራጠር መቀበል ይገባናል ፡፡ ፍልስፍናና ጥበብ ሃይማኖት ውስጥ ገብተው ከተቀላቀሉ የሚያሰተካክሉልንን ያህል እጅግ አስቀያሚ ውጤት አላቸው ፡፡ ሰው በአእምሮ በመሆን ክፉና ደጉን እንዲረዳ ተፈጥሯል ፣ ሃይማኖትንም አንድ ጊዜ ተሰጥቷል ፡፡ ነገር ግን ይኸ ዕውቀቱ በሃይማኖት ምርምር ውስጥ ከተደነቀረ ፣ የማይጐትተው ነገር ስለማይኖር አይጠቅምም ፤ ወደ ክህደት ያመራል ፤ ወንጌልንም ያጐድፋታል ፡፡ አሁንም ምእመን ነን ብለን ካመንን ፣ ለሃይማኖት መመሪያ ማውጣት የኛ ሥልጣንና ሥራ አይሆንምና ትምህርቱ ባለበት መቀጠል አለበት የሚለውን አሁንም አምንበታለሁ ፡፡ አባቶች ጉድለቱንና ስህተቱን ካጤኑና አሻሽለው ካስተማሩኝ እቀበላለሁ ፤ በራሴ ግን የቤተ ክርስቲያናችንን ትምህርት በየትኛውም ሥፍራ አላወግዝም፡፡ ዝግጅቷና አገዛዟ ለምድራዊ ስላልሆነ ሃይማኖትም በህዝብ ድምጽ ብልጫ አትቀየርም ፡፡

   - በአጻጻፌ ውስጥ በአብዛኛው ከመንፈሳዊ አመለካከት ውጭ ያሉትን በሰው ጥበብ መሆኑን ለመግለጽ እንደ ሰውነቴ /ሥጋዊ/ በማለት አስቀምጫቸው ነበር ፤ የቋንቋ ልዩነት አለን እንዳልል የምጽፈውን የተገነዘብክልኝ መስሎኛል ፡፡ የተጠራጠርካቸው እምነቴና ስብዕናዬ ለእኔም ሆነ በአካበቢዬ ለሚኖሩ ምንም ዓይነት ችግር አላስከተሉም ፤ በእምነቴ የኢኦተቤ ትምህርተ ሃይማኖትን ሳላጐድልና ሳልጨምር እቀበላለሁ ፤ የምታስተምረውንም በሙሉ በተቻለኝ ለማወቅ እየጣርኩ እገኛለሁ ፡፡ እስከ ዛሬም ብዙ ትኩረት የማላደርግባቸውን ርዕሶችና ትምህርቶች እንዳነብ ያደረገኝ በዚሁ ድረ ገጽ የተጻፉት አሉታዊ መግለጫዎች ናቸው ፡፡ በስብዕናዬ ደግሞ ፍቅርን የተጠማሁ ስለሆነ ከወንድሞች አንድነትንና ፍቅርን ለመፍጠር ብዙ እጓዛለሁ ፡፡ የወንጌል ተቀዳሚ መልዕክትም ከእምነት ቀጥሎ ፍቅርን /ለምግባር መገለጫ ትሆን ዘንድ/ ይሰብካል ፡፡ ኢየሱስ ስለ እኛ ፍቅር በመስቀል ላይ ደሙን ሲያፈስና ሲሞትልን ፣ እኔ ደግሞ በአቅሜ በትእዛዙ መሠረት ስለአንተ ፍቅር ቃልህን ብጋራልህና በአንድ አምልኮ ብንስማማ ምንም ችግር አልነበረውም ፡፡ እንደምኞቴ ቢሆን ክርስቲያን ነኝ የሚለውን ወገንን ብቻ ሳይሆን፣ ከዛም ውጭ /ከአብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አምላክነት ውጭ የሚያምነውን/ በሌላ እምነት ያለውን ኀብረተሰብም ቢሆን ፣ የዚህን ዓለም ፈጣሪ በአንድ ቃል ሆነን የምናከብርበትንና የምንዘክርበትን ቋንቋ ባገኝና አንድ ብንሆን እጅግ ደስ ይለኝ ነበር ፡፡

   ከገለጻዬ የተከፋሁ እንዳይመስልህ ፤ እኔ ሃሳብና ዓላማህ ገብቶኛል ፤ እኔን ለመርዳት ብዙ እንደ ደከምክም አውቃለሁ ፡፡ ስለሁሉም ውለታህ አመሰግንሃለሁ ፡፡ እንደ ሰው የሽርደዳ እንዳይመስልህ ፣ በዛሬው ሃሳብ ባንስማማም ባለፈው ያስተማርከኝን አልዘነጋውም በማለት ነው ፡፡


   -“ገድል በክርስቶስ ኢየሱስ ክርስቲያን የተባሉ ቅዱሳን የሰሩትን ሥራ የሚተርክ መጽሐፍ ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደሚገኘው የሐዋርያት ሥራ እንደ ማለት ነው፡፡ ገድሎች በአብዛኛው የተጻፉት ቅዱሳኑ ከሞቱ በኋላ ነው፡፡ ገድልን እንደ ትምህርት፣ ቅዱሳኖቹ ስለክርስቶስ የከፈሉትን ዋጋ ለማክበር እኛም የእነሱን አርዓያ ለመከተል በመጽሀፍ ቅዱስ ቃል እየመዘንን እስካነበብነው ድረስ ችግር የለውም፡፡ “ ድንቀ አድርገህ አሰቀምጠኸዋል ፡፡ ከዚሀ ቀጥሎ ያለውን አባቶችን የሚመለከት ስለሆነ ትቼዋለሁ ፡፡ አባት ተብለው ለልጆቻቸው የማያምኑበትን የሃሰት ትምህርት ፣ ላልተማረው ወገን ካስተማሩ ከፍርድ አያመልጡምና ሁሉን ለፈጣሪ እተወዋለሁ ፡፡

   ንጹህ ህሊናዬ በራሳችን አባቶችን አልፈን እንድንሄድ አይፈቀድልኝም ፡፡ ስለዚህ አቤቱታው ከምእመን ይልቅ ለአባቶች በምስጢር ቢደረግና እነርሱ እርምት አድርገው ቢያወጡልን ደግ ይሆን ነበር ፡፡ ግን ይኸው ሌላው ቀርቴ እኛ ስንገነጣጠልና ስንከራከር ሊገላግል አንድ አባት እንኳን መች ብቅ ብሎ ሃቁን አስረዳ ፡፡ መች አካሄዳችሁ ለቤተ ክርስቲያን ደግ አይደለምና ኑ ተቀመጡ ብሎ ለመገላገል ተነሳ ፤ ማነው የተሳሳተውንና ጥፋተኛውን በግልጽ ተመለስ ብሎ ያገደ ፣ ያወገዘ ፤ ለሁሉም መጸለይ ደግ ይሆናልና ፣ በጸሎት እናግዛቸው ፡፡ ከቁም እንቅልፍ ውስጥ ሆነውም ከሆነ መንፈስ ቅዱስ እንዲረዳቸውና ቤተ ክርስቲያናችን ያለችበትን ፈተና እንዲገንዘቡ እጸልያለሁ ፡፡

   ሃሳባችሁንና አመለካከታችሁን ያካፈላችሁኝን ከልብ አመሰግናለሁ

   Delete
  11. ክርስቲያን የሆነ ሲኖር በዓለም
   መመርመር ነው እንጂ ክፉና መልካም
   እውነት እስኪገለጽ አጥብቆ መድከም

   አለቃ ታየ ገብረ ማርያም በእሥር ቤት በነበሩ ጊዜ ከገጠሙት የወሰድኩት ነው፡፡ እውነት ነው ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ክፉና መልካሙን መመርመር ግድ ነው፡፡ ለዘመናት እውነት ተቀብሮ ልዩ ልዩ አንግዳ ትምህረቶች እና የፈጠራ ድርሰቶች በነገሱበት በዚህ ዘመን በሐዋርያት ወንበር ላይ ተቀምጠናል የሚሉት አበው ገለባና ፍሬውን እየለዩ ለምዕመናን ማቅረብ ይገባቸው ነበር፡፡ ነገር ግን እነሱ ዝም ቢሉም ዘመናችን የብዙ መልካም እድሎች ተጠቃሚዎች አድርጎናል፡፡ ዛሬ የምናነበውን ሁሉ ከንፈር በመምጠጥና በማድነቅ አናልፈውም አናስተጋባውም፡፡ እንዴት ለምን ማን ወዘተ በሚሉ መጠይቆች በመጽሀፍ ቅዱስ ቃል እየመረመርን እናጣራዋለን ይህንንም ለማድረግ ኀሊናችን ያስገድደናል፡፡

   Delete
  12. ‹‹ሰው በአእምሮ በመሆን ክፉና ደጉን እንዲረዳ ተፈጥሯል ››፣
   ታዲያ ገድሎች ላይ የተጻፈውን ጉድ ማየት እንዴት ተሳነህ
   ‹‹ሃይማኖትንም አንድ ጊዜ ተሰጥቷል›› - ሃይማኖትማ በልዩ ሶስትነት የሚመለክ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ፣ ቅዱስ እግዚአብሔር ወልድ፣ ቅዱስ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ
   እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም ያለውን ኢየሱስ ክርስቶስን (እግዚአብሔር ወልድ) ፍጹም አምላክ ፣ ፍጹም ሰው ብሎ ማመን ነው፡፡
   ከዚህ ውጪ ሌላ በክርስትና እምነት ውስጥ ምን ዓይነት ሃይማኖት አለ

   Delete
 11. ቅዱስ ጳውሎስ በ1ቆሮ.1፡30-31 ቅዱሳን የምንላቸው ምእመናን የዳኑት ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብ ጽድቅ ቅድስና ቤዛ በሆነላቸው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ ያሳስባል፡፡ በራሳችንማ እነርሱም ‹‹እኛም የቁጣ ልጆች ነበርን›› ይላል፡፡ ኤፌ2፡3

  ቅዱስ ጴጥሮስም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኃጢአታችንን ተሸክሞ በመስቀል ላይ ስለ እኛ መከራ በመቀበሉና በመሞቱ መዳናችንን ይናገራል፡፡ (1 ጴጥ.2፡24) ቅዱሳን የራሳቸው ያልሆነ የእግዚአብሔር የሆነ ጽድቅ ተቆጥሮላቸው በተጣበበ ሁኔታ በጭንቅ ስለሚድኑ (1 ጴጥ 4፡17-18) ሌላውን ኀጢአተኛ ማዳን የሚችል ተዛውሮ ለኀጢአተኛ እንዲመዘገብ የሚደረግ ተራፊ ጽድቅ የላቸውም፡፡

  ከዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ በኢትዮጵያ እያደገ የመጣውንና መላእክትና ያንቀላፉ ቅዱሳን ሰውን ለማዳን በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ በቃል ኪዳን የተሰጠ ታላቅ ድርሻ እንዳላቸው ተደርጎ በገድል፣ በድርሳን፣ በተአምርና በተለያዩ የሰላምታ ድርስቶች ተስፋፍቶ የሚነገረውን ሁሉ ሊቁ አባ ስብሐት ለአብ በመልክአ ሥላሴ እንዲህ በማለት ይቃወሙታል፡፡

  ሰላምታ አቀርባለሁ
  የደም እንባ መጠጥ ለማያሻው ጉረሮአችሁ
  ባለጸጋዎች ሥላሴ አይለፈኝ ሞገሳችሁ
  ከተዋችሁኝማ በችግሬ እንዳለሁ
  ወደ ሚካኤል አልሄድ ሥጋዬን እንዳልፈጠረ አውቃለሁ
  ወደ ገብርኤልም አልሄድ ነፍስ እንዳልሰጠኝ እረዳለሁ

  ለንዋየ ውስጥ ምህረታችሁ ሰላም እላለሁኝ
  ምልአት ናችሁና ሥላሴ ትርፋማ አገልጋይ አድርጉኝ
  የሰውን ገድልማ ልሳተፍ ብፈልግ አጣሁኝ
  ከደሙ ጠብታ ጊዮርጊስም አልሰጠኝ
  ከአጽሙ ስባሪም ተክልዬ ነፈገኝ

  ReplyDelete
 12. ወንድሜ ፍቅረማርያም

  ከዚህ በላይ በአንድ ጉዳይ ላይ ሦስት ጊዜ አስተያየት ስትጽፍ (አንቱታው የማይገባህ ስለሆነ ትቸዋለሁ) የመልእክቶችህ ይዘት ትክክለኛ ስምህ ''የምድራችን አፈ ታሪክ ሊቅ'' መሆን እንዳለበት ስላሳሰቡኝ ዳቦ ባንቆርስም ከዛሬ ጀምሮ ይህ ስም ከሌሎች በበለጠ ማንነትህን ስለሚገልጽህ በዚህ ብትጠራ በመሰሎችህ ዙሪያ ከበሬታን ታገኛለህ:: የምትፈልገውም ይህን መሰለኝ:: አይዞህ በፊውዳሉ ዘመን በግራ ያላችሁት ግራዝማች በቀኝ ያላችሁት ደግሞ ቀኛዝማች ብያችኋለሁ እንድሚባለው ዓይነት አይደለምና አታመሳስለው በእውነተኛ ማንነትህ ላይ ያነጣጠረ ገላጭ ስም ነውና አሜን ብለህ ተቀበለው:: ወደ እውነተኛው ታሪክ ስትመጣ ደግሞ እጅግ የተሻል ስም ይሰጥሃልና የተክለሃይማኖትን ታሪክ ከአዳኛችን ጌታ ኢየሱስ ይልቅ በማጉላትና አዳኝነቱን ከመስቀሉ ሥራ ጀምሮ ለተክልዬ በመስጠት በርታ የሚያዋጣህ ከሆነ:: እጅግ የሚያሳዝነው ግን ትንሽ እንኳ መንፈስህን የሚወቅስ ነገር የማያሰማህ መሆንህና ብዙ ዝባዝንኬ ለመጻፍ የማትታክት ለከንቱ ነገር ብርቱ መሆንህ ይገርመኛል::

  ምናልባት የወንጌል ብርሃን እንዳይበራላቸው የዚህ ዓለም አምላክ ዓይኖቻቸውን ካሳወራቸው ሰዎች መካከል ትሆን እንደሆነ ማን ያውቃል?? ግን የምህረት አምላክ ቸርነቱን እንዲያሳይህ ንስሃ ብትገባ ይምርሃልና ብታስተውል????????????

  እግዚአብሔር ማስተዋልን ይስጥህ

  እውነቱን ስለነገርኩህ አካኪ ዘራፍ እንደምትልና የስድብ ናዳ እንደምታወርድብኝ ይገባኛል::

  የተክለሃይማኖት(ስለሌላቸው) ሳይሆን የጌታ ኢየሱስ ሰላም ይብዛልህ!!!!

  ሰላም ነኝ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ፍቅረ ማርያምMarch 16, 2012 at 10:29 AM

   ለእህቴ ወለተ ሉተር
   - የመጀመሪያው ሁለቱ ተከታታይና አንድ መልዕክት የሚናገሩ ናቸው ፡፡ ያገኘሁት ከአንድ ድረ ገጽ ሆኖ የምፈልገውን ሃሳብ ወስጄ በራሴ ግንዛቤ አደራጀሁት ፤ ሶስተኛ ያልሽው ከሌላ ድኀረ ገጽ ዘግይቼ ስላገኘሁት ፣ ሃሳቡ የተዛመደ ስለሆነ አብሮ እንዲነበብ አቀረብሁት ፡፡ ለአንቺ ሶስተኛ ለእኔ ሁለተኛ የሆነው 98 በመቶው ቃል ከድረ ገጹ ጽሁፍ እንዳለ የተወሰደ ነው እንጅ እኔ ዋጋ ያለው ነገር አልጨመርኩም ፡፡ ስለዚህም አንባቢ የሚሰጠውም ምስጋና ለሚገባው እንዲሆን በማለት ስም አስቀምጫለሁ ፡፡ በተላለፈው ከተስማማሽ አሁንም ልታቀርቢለት ይገባል ፡፡
   - የስም ነገር ያነሳሽው አንቺ ባወጣሽልኝ መጠራቴን አልቃወምም ፤ አንድ ለአንድ እንድንሆን ግን እኔ ያወጣሁልሽም ከጽሁፍሽና ከአገላለጽሽ ስለሚስማማ ሳታፍሪ ተቀበይኝ ፡፡
   - እውነትን ሸፍኖ የሐሰት ጭንብል ሊያጠልቅና ሊያሳስት የሚሞክረውን በምችለው ሁሉ እቃወማለሁ ፡፡ ዘገባው ከገድለ ሃይማኖት መጽሐፍ ምንም ጥሩ ነገር ጠቅሶ ስላልጻፈ ፣ ከሐዋርያቱ ያልተናነሰ ተጋድሎን ያደረጉትን አባትም በማይገባ አኳኋን ስለገለጸ ፣ የዛን ታሪክ ገጽታ ሚዛን ለመጠበቅ ስል ያገኘሁትን አቅርቤዋለሁ ፡፡ አቡነ ተክለሃይማኖት በእምነታቸው ጸንተው የሞቱት የክርስቶስን ቃል ስለሚያምኑ ነው ፡፡ ያስተማሩትም ደግሞ ወንጌልን ነው እንጅ ሌላ የባዕድ አምልኮ ትምህርት አይደለም ፡፡ ስለዚህም ትምህርታቸውን አንቺም ክርስቲያን ነኝ ካልሽ ልትቃወሚ አይገባም ፡፡ ክርስትናውን ማመንና መቀበል ብቻ ሳይሆን ለመኖርም ብለው የወረሱትን ንብረት ሳይቀር ለድሃ አከፋፍለው ጌታን ለመከተል ፣ ወንጌልንም ለማስተማር በማያውቀበት አካባቢ ሁሉ ተሰደዋል ፡፡ እንዲህ ዓይነት ሰው ጣዖት በሚያመልክ ኀብረተሰብ መሃል መውጣቱ ደስ አይልም ፡፡ ሙሉ መረጃ ለማግኘት ገድለ ተክለሃይማኖትን አንብቢ ፡፡

   እግዚአብሔር ለሁላችንም ማስተዋልን ይስጥ

   Delete
 13. Oh.christians whats this all.teklehaimanot is one of z ethiopian saints.i dont think that teklehaimanot is a bad person.teklehaimanot are our father who connect us 2 jesus christ.i am very fair by who doesnt like teklehahaimanot.any way GOD gives us his forgiveness.

  ReplyDelete
 14. TO SELAM (actually u r not selam u r . . .) please give a valuf for KIDUSAN otherwise. . . enesu yekefelutin waga atarkshi eshi lenegeru alferdibishim yeseytan andebetu neshina tegbarishin atreshim adamin yasatew man honena new.

  ReplyDelete
 15. god job selam jeus is great

  ReplyDelete
 16. ውድ ከዚህ በላይ አስተያየት የሰጡ እንግዳ ሆይ! ‘ክብር ለዓምላከ ተክለሃይማኖት ይሁን’። ነው የሚባለው እሺ? አይዞት አጥተውት ሳይሆን ቸኩለው ይሆናል። ማቅ የማያመጣው ጉድ የለምና በዚህ ዐምድ ደግሞ ቅዱሳን አባቶችን መዳፈር ጀመረ? “ሞት ቢዘገይ የቀረ ይመስላል፡፡” ሆኖበትና ”አይጥ ለሞቷ ሄዳ ታሸታለች የድመት አፍንጫ።” የሚለውን ለደፋሮች በዘዴ የተነገረውን ማስጠንቀቂያ ስምቶት ስለማያውቅ ነው። ስለ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት የግብጽ ኦርቶዶክሶች እያለቀሱ ሊያስረዱ ይችላሉ። በስማቸውም የተሠራውን ፊልም አውሰውት አይቶ ገድላቸውን ሊረዳ ይችላል። እኔም የሰማሁትን ሳይሆን ከልጅነቴ ጀምሮ ስለ ፃድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገድል ያየሁትንና የማውቀዉን ልነግረው እችላለሁ። እግዚአብሔር ይመስገን!!! ዳሩግን በተደፈነ ጆሮውና በደነደነው አመጸኛ ልቡ ላይ ቆሞ አይደለም፤ አምኖ እንዲገለጽለት ተማጽኖ እንጂ። አፋኙን የደህንነት ድርጅት ማህበረ ቅዱሳንን (ማህበረ ዲያብሎስን) በወንጌል ትጥቅ አቃጥሎ በፀበል እያጠመቁ በመስቀል ቀጥቅጦ ማስወጣት ነው እንጅ፣ ሉተራን ምን አደረገ? ማቅ ዲያብሎሱ በቁም ያሉትን መነኩሴዎች እንኩዋን ሙልጭ አድርጎ አይደል እንዴ የሚሳደበው። የምን ወዲህ ወዲያ መወላገድ ነው!! ኦርቶዶክስ እንደዚህ ኣይነት ውልግድግድ መንገድ የለውም። ትርጉሙም ቀጥታ ነው። ነገር ግን ኑሮው በዕምነት ጸንቶ መስዋአትነትን የመቀበል የጸጋ ውርስ ነው። እንዴት ቢሉም የጌታችን የመድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ምሳሌው እሄው ነውና። የዘመኑን ዲያብሎስ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ ብሎ ማሳደድ ነው እንጂ የምን መፍራት ነው። የሥላሴ ባርያ አይፈራም። የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ። አሜን!!!
  አንተ በለምድ የተሸፈንክ ማህበረ ቅዱሳን፣
  እውነተኛው ስምህ ‘ማህበረ ሰይጣን’ ፣
  እኛንም ጨምረህ አበዛህ መከራን ፣
  የንስሀን ጊዜም አሟጠን ጨርሰን፣
  እሄው ቁጭ ብለናል ፍርድን እየጠበቅን፣
  ምክንያት በመፈለግ እየተጠቃቀስን፣
  እየተረዳዳን ጉድጔድ እየቆፈርን፣
  ሞትን አስተናገድን ድምጻችንን ቀብረን፣
  እርቀን ሄደናል መመለሻም የለን፣
  እያልን፣
  አሁን ስንነቃ ታይቶናል ውጋገን፣
  አንተ በሄድክበት እኛም አልተከተልን፣
  እዛው በፍርድ ቀን እንናገኛለን፣
  በጻድቃኖቻችን እየተስተናገድን፣
  ተክለ ሃይማኖትን ምርኩዛችን አርገን፣
  አንተ ወዲህ ስትቀር እኛም እንገባለን፣
  መንገዱ እንዳይጠፋን በድንግል ታጅበን።

  ReplyDelete
  Replies
  1. Ende Metsihaf kidus kehone Amlakachim Tekile Haimanot new. Metsihaf Kidus Bedenib anibib. Eski Ahun Bemetsihaf Kidus Ketekilehaimanot Lela Amlak Menoron asredagn?

   Delete
  2. Tsihufochen endematawotachew aukalehu. gin abizagnawochun comments antew endemititsifachew silemawuki melikitie betikikil endederese ergitegna negn.

   Delete
 17. ለውድ እህቴ ሰላም
  ብዙ ጊዜ አስተያየቶችሽን ተከታትያቼዋለሁ፡፡ ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት የምትቆረቆሪና ሁሉም አማኝ ትክክለኛውን እውነት እንዲቀበሉ የምታደርጊውንም ጥረት አደንቃለሁ፡፡ ይህንን ለመግለጽ የተጠቀምሽበትን መንገድ ግን አልደግፈውም፡፡ ሁሉም ሰዎች እንደኔ ካላሰቡ የሚል ግትር አቀም አለሽ፡፡ በእኔ እምነት ግን ለአንቺ የተገለጸው እውነት በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ እንጂ በአንቺ ጥረት እንዳልሆነና አንቺም አሁን ለያዝሽው እምነት ብዙዎች አምጠውልሽ ለዚህ መድረስሽን መርሳት የለብሽም፡፡ ማንም ያለ ምጥ አልተወለደምና፡፡ ሐዋርያውም በሮሜ መልእክቱ ም. 14፡1 ላይ ‹‹በእናንተ መካከል በእምነቱ ያልጸና ደካማ ሰው ቢኖር በፍቅር ተቀበሉት እንጂ በአስተሳሰቡ አትፍረዱበት›› ይላል፡፡
  ብዙዎቻችን አባቶቻችን ያቀረቡልንን ያጎረሱንን ሁሉ የሚበላ መሆን አለመሆኑን አንካን ሳናውቅ ሳናጣጥም የዋጥነውን ለመትፋት ቀላል አይደለም፡፡ በጾምና በጸሎት የእግዚአብሔርን እርዳታ ካላገኘን ለዓመታት የተገነባው ልማድ አይፈርስም፡፡ ከዚህ በፊትም አስተያየት ለመስጠት እንደሞከርኩት በሰዎች ልብ አስቀድሞ ገብቶ ስፍራ ያያዘውን ውሸት ለማስወጣት ግብ ግብ መፍጠር ጥቅም የለውም፡፡ ምስክርነታችንን የጋራ በሆነ ጥቂት እውነት ላይ በመወያየት ብንጀምር የተሻለ ይመስለኛል፡፡ አሁን በአገራችን የሚታየው በክርስቲያኖች መካከል ያለው መገፋፋት ከዚህ ችግር የመነጨ ይመስለኛል፡፡ አብዛኛዎቹ ወንጌላውያን ቤተክርስቲያኖች ምስክርነታቸውን የሚጀምሩት አንድ ከሚያደርገን ነገር ሳይሆን ከልዩነታችን ነው፡፡ ይህ ደግሞ ብዙዎችን የሚያስቆጣና ወደ አክራሪነት የሚወስድ መንገድ ነው፡፡ ከራሴም ምስክርነት ብነሳ ወደ እውነቱ የመጣሁት በብዙ ጭንቅና ምጥ መሆኑን አስታውሳለሁ፡፡ እውነቱን ለሚመሰክርልኝ ወንድም ብዙ ጥያቄዎችን ይዤለት ብሄድም ጥያቄዎቼን ወደፊት እንደምንወያይበት ነግሮኝ መጀመሪያ በፍቅርና በለመድኩት ተወዳጅ በሆኑ የቤተክርስቲያን ቃላት የጽድቅን መንገድ አስረዳኝ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ አጋዥነትም ወደ እውነቱ ደረስኩ፡፡ ልጠይቃቸው የነበሩትም ጥያቄዎች አነሱብኝ፡፡ ለጥያቄዎቼ ሁሉ ክርስቶስ ኢየሱስ መልስ ሆነኝ፡፡ ስለዚህ እህቴ ወደ እውነቱ ብዙ ወገኖቻችን እንዲደርሱ በጾምና በጸሎት ስለእነሱ ማማጥ አለብን፡፡ ልናስቆጣቸው ግን አልተፈቀደልንም፡፡ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ፍቅረ ማርያምMarch 17, 2012 at 2:48 PM

   የእህታችን ፍላጐት
   1. በተደጋጋሚ ለክፋት ነገር የምትጋብዘኝ እሷን በመስደብ እኔ ወደ ሲዖል እንድሄድና ፣ እሷ ደግሞ በዚህ ምክንያት የማይገባትን ወንበር ልትይዝ በመመኘት ይመስለኛል ፡፡ እኔ ግን ለማንም የመጽድቅ ምክንያት ልሆን አልችልም ፡፡
   2. በወገኖቿና በጓደኞቿ ስለ ኢየሱስ ይህን ተባልኩ በማለትም የራሷን የሐዋርያነት መጽሐፍ ልትደርስ በመፈለግም ዘወትር አንድ ነገር እንድትባል የምትፈልግም ይመስለኛል ፡፡ ስለ ግል የኑሮ ሁኔታዬ ምንም መረጃ ሳይኖራት በተደጋጋሚ በመሰሎችህ መሞገስን ስለምትፈልግ ይህን ጻፍክ በማለቷ ስም እስከመቀየር ድረስ ተጓዝኩላት ፡፡ አሁን ላይ ስገምተው ግን ፣ ይህ የሷ አባባል በግልባጩ ከልቧ ውስጥ ተቀብሮ ያለውን የራሷን ሥራ ፣ ምኞትና ፍላጐቷን ሳታስበው እያስተጋባችው ያለ ይመስለኛል ፡፡ የቱንም ያህል ክርስትናውን ያወቅን ብንሆን ፣ አንዳንዴ ሳናስበው የአስተዳደጋችን ጉድለትና የግል ፍላጐታችን ፣ በእምነታችን ውስጥ ልንፈተንበት ጣልቃ እየገባ ይደነቀራል ፤ ይንጸባረቃልም ፡፡

   አቋሜ
   ግራህን ለሚልህ ቀኝህን አዙርለት የሚለውን በምችለው እንድትመለከተው በማለት እንደፍላጐቷ አንድም ቀን በዕውቀት የጽርፈት ቃል በጽሁፌ ውስጥ አላስገባሁም /ኃጢአት መሆኑን ስለማውቅ/ ፤ የማልቀበለውን ሃሳብ ግን በተቻለኝ ምክንያቶቼን እየሰጠሁ ለማስረዳት ሞክሬአለሁ ፡፡ የሚያሰተምረኝ የገባው ሰው ሳገኝ ደግሞ ያለ ንቀት እማራለሁ ፡፡ በሌላ ጐኑ ደግሞ የእምነታችንና የጽናታችን መፈተሻ ስለሚሆን ባመነችበት ጉዳይ ላይ መከራከሯን ደስ ይለኛል ፤ ነገር ግን “ያዕቆብ 5 ፡ 9 ወንድሞች ሆይ እንዳይፈረድባችሁ እርስ በርሳችሁ አታጉረምርሙ” የሚለውም ሳይዘነጋ ማለቴ ነው፡፡ ከዚህ በተረፈ ግን እኔም እንደ አለቃዬ ሱሬ አውልቅ እስካላሉኝ ድረስ የምል ሰው ነኝና ውጤት ስለማይኖረው ብዙ ትንኰሳ አይጠቅምም፡፡ ይህንን ትዕግስት ደግሞ ያስተማረኝ የወለድኩት ትንሹ ልጄ ነው ፡፡

   ቅሬታዬ
   አንድ ትልቅ የሚያሳዝነኝ ድክመት ፡- ወንጌልን አውቄዋለሁ ብሎ የክርስቲያንነት ምስክርነትን ከሚሰጥ ወገን ፣ ኑና የእኔን ቃልም ስሙና ተቀበሉ ከሚል ግለሰብ የዚህ ዓይነቱ ባህርይ በአጋጣሚ ሳይሆን በተደጋጋሚ መገለጹ ብቻ ነው ፡፡


   ምክሬ
   ኃይለ ቃልን ማነብነብ ብቻ ሳይሆን ፣ ያነበብነውን ወደ ተግባር መንዝረን መኖር ስንጀምርና ስንታወቅበት ፣ ሌሎችም አርአያ ስለሚያደርጉን እግዚአብሔርን እንዲያከብሩ ምክንያቶች እንሆናለንና የምናደርገውን እናስተውል /ማቴ 5 ፡ 16 ፤ 1 ጴጥ 2 ፡ 12/፡፡

   ይቅርታዬ
   በተረፈ ለእህቴ አጻጻፍ መነሾ ምክንያቱ እኔው ራሴ መሆኔን ሰለምገነዘብ ፣ ስሜቷንና ብሶቷን ስለገለጸች አልከፋም ፤ አሁንም ገና ታዳጊ ክርስቲያን ስለሆነች በግሌ አልኮንናትም ፡፡ እሷም የኔን ኢየሱስ ትለኛለች ፣ እኔም ደግሞ ስንት ያደረገልኝን የእኔን ኢየሱስም አልከዳውም ይልቅ አንቺም እንደ እኔው ተቀበይው ብዬ እከራከራለሁ ፡፡ ድንቅ አይደለም ለየራሳችን የሚሆን ሁለት ዓይነት ኢየሱስ ክርስቶስ ፈጥረን መወዛገባችን ???

   Delete
 18. አኖኒመስ (ከዚህ በላይ በማርች 17 ሁለተኛ ተራ ቁጥር ላይ አስተያየት የሰጠህ/ሺ)

  እውነት ነው! ወንጌል/ክርስትና ፍቅር እንጂ ጥላቻ አይደለም:: እኔም በፍቅረማርያም ላይ የሰነዘርኩት አስተያየት ልክ እንዳልሆነ አምኜ በጌታ ፊት ንስሃ ገብቻለሁ/ መንፈስ ቅዱስም ወዲያው እንዳስተላለፍኩት ወቅሶኛል:: ስለዚህ የቀረበውን ማረሚያ አሜን ብዬ በመቀበል:

  1)ያሳዘንኩትን ጌታ ምህረት እንደሚገባ በመጠየቅ በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ለጠላት ሁለተኛ ላልገኝ ቃል
  በመግባት እተጋለሁ

  2) ፍቅረማርያምም ሥጋ ለባሽ እንጂ የመላእክት ዝርያ እንደሌለኝ አውቀህ ይቅር እንድትለኝ በጌታ
  ፍቅር ከልቤ እጠይቅሃለሁና እባክህ በእውነት ይቅር በለኝ??????????

  3) ከዚህ በላይ ይህን የሚያንጽና እውነተኛ ክርስቲያናዊ የሆነ ምክር የሰጠኽኝ/ሺኝ ወንድም/እህት
  ደግሞ በእውነት እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክህ እያልኩ ለቤተ ክርስቲያናችን እውነተኛ ፈውስ
  እንደዚህ ያሉት አስተዋዮች ይብዙልን:: ለዚህ ዓይነት ሕይዎትም በግሌ የምጸልይ መሆነን
  ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ::

  እያንዳንዳችን ስህተት ልንሠራ እንችላለን ነገር ግን ስህተትን መንፈስ ቅዱስ በራሱ ወይም በሰው ሲነግረን እንደዳዊት በአምላካችን ዙፋን ስር መንበርከክ ለሁላችንም የሚያስፈልገን ይመስለኛልና በዚሁ ብንበረታ??

  ወንድሜ ፍቅረማርያም ይህን ጥያቄዬን በይቅርታ ልብ የተቀበልከኝ መሆንህን/አልመቀበልህን ብታረጋግጥልኝ እጅግ ደስ ይለኛል:: ጌታ ሁላችንንም በመንፈሱና በቃሉ ይርዳን ይደግፈን አሜን::

  ሁላችሁንም በጌታ ፍቅር እወዳችኋለሁ

  ሰላም ሁኑልኝ

  ሰላም ነኝ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ፍቅረ ማርያምMarch 17, 2012 at 3:18 PM

   ውድ እህቴ
   የሰው ይቅርታ ብዙ ዋጋ ስለማይኖረው ፣ እግዚአብሔር ይቅር ይበልሽ ፤
   እኔ በግሌ እንደ አንድ የቤተሰቤ አካል አድርጌ ስለማይሽ ወይም እንደ ትንሽ እህቴ ስለምቆጥረሽ የምትይውን በሙሉ ብዙ ተበሳጭቼበት አላውቅም ፡፡ በባህላችን በቤተሰብ ውስጥ መተማመኑ ስላለ ብዙ ብዙ መባባል አለና /እህት ወንድሙን ፣ እህት እህቷን …/፡፡ የጋራ ወንድማችን የሆነው ሰው ተሰምቶት ስለጻፈው ብቻ አስተያየቴን ለሱም ሰጥቼ ነበር ፡፡ በእውነት የምመሰክረው እንደ አንቺው ዓይነት አመለካከት ያላት እህት ስላለችኝም አንዳንዴ ከእሷው ጋር በስውር የምንተጋተግ ይመስለኝ ነበር ፡፡ በአእምሮዬ የቤተሰብ አካል እንጅ የማይተዋወቅ የሩቅ ሰው አድርጌሽ አላውቅም ማለቴ ነው ፡፡

   ለሱም እንደገለጽኩት ፣ ከምድር ተነስተሽ ስሜን ፈልገሽ እንዳልጻፍሽ ስለምረዳ ፣ የጽሁፍሽ ሁሉ መነሻ ምክንያት ፣ ማለቴም ኃጢአት ሆኖም ከተቆጠረብሽ ፣ የኃጢአትና የድክመትሽ ምክንያት እኔ ስለሆንኩ ለእኔም ከልብ ይቅርታ እንድታደርጊልኝ በወንድምነት እጠይቅሻለሁ ፡፡ እኔ በደልኩሽ እንጅ አንቺ አልበደልሽኝም ፡፡ ስለዚህ አሁንምም አስቀይሜና አስቆጥቼሽ ከሆነ ይቅርታ አድርጊልኝ ፡፡

   የእግዚአብሔር ፍቅር ይብዛልን

   Delete
 19. ወለተ ጊዮርጊ
  ተስፋ ነኝ ከምትባል ተስፋ ቢስ ብትባል ይሻላል, ለከንቱ ነገር ብርቱ ነህና
  አንተን ብሎ ተስፋ, አንዴ;-በጸሎት ብዛት ተቆረጠች የተባለችው እግር ግን የግል ቤት ተሠርቶላት በዚያ ትኖርላች ይባላል ትላለህ እንደ ቱሪስት::
  አንዴ:-እኛና እናንተ ፊት ለፊት በዚህ ጉዳይ ተነጋግረናል ትላለህ ኦርቶዶክስ ለመባል :: ያንተ ችግር ባጠፋኽው ጥፋት ባደባባይ መከሰስህ ነው እንጅ, ለሃይማኖት የምትቆረቆር አይደለህም::ሃይማኖትም የለህም ::ሃይማኖት በህዝብ ድምጽ ብልጫ አትቀየርም ፡፡::አንተው ራስህን በማጋለጥ እንዲህ ብለሃል:-
  እኛ ይህን ጉዳይ ባደባባይ በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ለመግለጥ የተገደድነው ሁላችሁም እንዲያውም እኛን የተሳሳቱ ናቸው በማለት ክሳችሁን ባደባባይ በማቅረባችሁ ነው ብለሃልና, አንተው ራስህን በማጋለጥ:: ትንኰሳ አይጠቅምም እባክህ ::ይህን አንብብ
  በሮሜ ም. 14፡1 ላይ ‹‹በእናንተ መካከል በእምነቱ ያልጸና ደካማ ሰው ቢኖር በፍቅር ተቀበሉት እንጂ በአስተሳሰቡ አትፍረዱበት›› ይላልና እንታገሳለን ፡፡
  የኤልሳዕ የገላው ፍራሽ የሆነው አጥንት ስለምን ምክንያት ሙትን አስነሳ? 2 ነገ 13፡21 ፡፡ ይኸ ተአምርስ ተፈጸመ በማለት የተጻፈው በኤልሳዕ አጽም እነዲመለክበት ተፈልጐ ይሆን ? እኔ እንደገባኝ ከገድል መጽሐፍ ተገኘ ተብሎ የቀረበው ጽሁፍ የሚለው በተክለ ሃይማኖት ስም የሚሠራ ምግባር /በማቴዎስ ወንጌል የተሰጠውን ተስፋ/ የሚያስገኘውን ትሩፋት ይናገራል እንጂ በተክለሃይማኖት አምልኩ ፤ እኛም በተክለሃይማኖት እናመልካለን አላልንም ፡፡ መልካም ምግባርን በጻድቅና በቅዱሳን ፣ በደቀመዝሙር ስም ያደረገ ዋጋው አይጠፋበትም ስለተባለና በኢየሱስ ክርስቶስ ስለታወጀ ያን ለመተግበር እንታገላለን ፡፡ ማክበር ማለት ማምለክ አይደለም ፤ በስማቸው መዘከር ማለትም ማምለክ አይደለም ፡፡ ማክበር፣ መዘከርና ማምለክ ምንም ዝምድና የላቸውም ፡፡
  1. የጌታ ዓይኖች ወደ ጻድቃን ናቸው ፣
  ጆሮዎቹም ለጸሎታቸው ተከፍተዋል 1ጴጥ 3፡12
  <>

  ReplyDelete
 20. አንተ ደፋር እምንት የጎደለህ አለማመንህ ሳያንስህ እኔ እና መሰል ታናናሾችን ለማሳት አትሞክር!!! ልቁንስ በሃይማኖት ብትኖሩ ራስህን መርምር!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. አንድ ጥያቄ ሐዋርያት የሰበኩት ስለኢየሱስ ብቻ ነው።የዛሬ ድርሣናት እና ገድላት ማንን ነው የሚሰብኩት

   Delete
  2. ቤተክርስቲያናችን የአጋንንት ትምህርት በያዙ ገድላት ተበርዛለች ። እባካችሁ እናስወግዳቸው?

   Delete