Friday, March 23, 2012

ማህበረ ቅዱሳን ጥንተ አብሶን በመታከክ በአባ ሠረቀ ላይ ዘመቻ ከፈተ - - - Read PDF

የማህበረ ቅዱሳንን ድብቅ አጀንዳ በማጋለጥና በቤተክርስቲያን ላይ የጋረጠውን አደጋ ለህዝበ ክርስቲያንና ለመንግስት አካላት በማሳየት፣ “ማንም አይደፍረኝም” ሲል የነበረውን ማህበር ከመሠረቱ ባናጉትና መያዣ መጨበጫ ባሳጡት፣ በቀድሞው የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሀላፊ በነበሩትና በአሁኑ ጊዜ ደግሞ የትምህርትና ስልጠና መምሪያ ሃላፊ በሆኑት በአባ ሰረቀ ላይ አዲስ ዘመቻ መክፈቱን እየወጡ ያሉ ጽሁፎች እያረጋገጡ ነው። ማህበሩ የሚያሳትመው ስምአ ጽድቅ የተሰኘው ጋዜጣው በየካቲት ወር እትሙ በርእሰ አንቀጹና ከአቡነ እንድርያስና ከመምህር ደጉ ዓለም ካሳ ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ፣ እንዲሁም ከዚህ ቀደም ከአባ ሠረቀ ጋር በጥንተ አብሶ ዙሪያ ውዝግብ ውስጥ የነበሩትንና “ነጭ እንቁ በአዳም ገላ” የሚል መጽሐፍ ጽፈው ማርያም ጥንተ አብሶ የለባትም ያሉትን መምህር ሀብተ ማርያም ተድላን የአብርሃም ቤት እንግዳ በተሰኘ አምዱ ላይ አቅርቦ (ስም ሳይጠሩ) በአባ ሠረቀ ላይ ያነጣጠሩ ትችቶችን እንዲሰነዝሩ አድርጓል፡፡ማህበሩ በርእሰ አንቀጹ ላይ “ማርያም ጥንተ አብሶ የለባትም” ለማለት በተደጋጋሚ ያቀረበው ምክንያት ከኒቅያ እስከ ኤፌሶን ጉባኤዎችና ከዚያም ወዲህ በተነሱ የቤተ ክርስቲያን አባቶች “ስለ እመቤታችን ጥንተ አብሶ አልተነሳም” የሚል ተልካሻ ምክንያት ነው። እንደማህበሩ ገለጻ በማርያም ላይ ጥንተ አብሶ አለባት ወይም የለባትም በሚል ከዚህ ቀደም ጉዳዩ አለመነሳቱ “ማርያም ጥንተ አብሶ የለባትም” የሚል ውሳኔ እንደሰጡ አያስቆጥርም፡፡ በቤተክርሰቲያናችን ውስጥ የምናያቸውና የምንሰማቸው አንዳንድ ትምህርቶችና ስርአቶች በጉባኤ የተወሰኑ አይደሉም። በልማድ ሲሰራባቸው የኖሩ ናቸው። ዛሬ ለውሳኔ ቀርበው ውይይት ይደረግባቸውና ውሳኔ ይሰጥ የሚል ክፍል ቢነሳ መልሱ ከቶ ምን ይሆን? አባቶቻችን በኒቅያ፣ በቁስጥንጥንያ፣ በኤፌሶንና በሌሎቹም ጉባኤዎች እንዲህ ያለ ጉዳይ አላነሱምና፣ በኖረው ልማድ ነው መቀጠል ያለብን ሊባል ነው? እንዲህ ማሰብ ያሳፍራል!!

መጽሐፍ ቅዱስም ሆነ እርሱን መሰረት አድረገው ያስተማሩ የቤተክርስቲያን አባቶች የመሰከሩት ኢየሱስ ያለ ሀጢአት ተጸንሶ ያለሀጢአት መወለዱን ነው፡፡ እውነቱም ያ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ማርያም ጥንተ አብሶ የለባትም የሚለው ትምህርት የካቶሊኮች ትምህርት እንጂ የኦርቶዶክሶች ትምህርት አይደለም። ያም ብቻ ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት የሌለውና ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ጋር የሚጣረስም ትምህርት ነው፡፡

ይሁን እንጂ ማህበሩ በሌለው የቤተ ክርስቲያን ትምህርት፣ ስልጣንና በሌለው ውክልና የእርሱ ደጋፊ የሆኑና ከአባ ሰረቀ ጋር የተጋጩ ግለሰቦችን፣ እንዲሁም የእርሱ ደጋፊዎች የሆኑ አቡነ እንድርያስና መምህር ደጉ አለም ካሳን ቃለ መጠይቅ አድርጎ ቤተክርስቲያኗ እንደ ተናገረች በማስመሰል ማርያም ጥንተ አብሶ የለባትም የሚለውን የካቶሊኮች ትምህርት በስርዋጽ ለማስገባትና የኦርቶዶክስም ትምህርት ሆኖ እንዲታይለት ጥረት አድርጓል።

መምህር ደጉ አለም ካሳ ከዚህ ቀደም ማህበሩ በተሀድሶ መናፍቃን ላይ ከፍቼዋለሁ ባለው ዘመቻ ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ወደ ጎጃም ተልከው በደብረ ማርቆስ እንዲሁም በአማኑኤል ከተሞች ለምእመናን መሪጌቶቻችሁን ጠብቁ፣ መምህራኖቻችሁን አትመኑ በማለት ህዝቡ በመሪጌቶቹና በመምህራኑ ላይ እምነት እንዳያሳድር ቅስቀሳ ሲያደርጉ ነበር። ህዝቡ መምህራኑንና መሪጌቶቹን ካልሰማ ማንን ሊሰማ ነው። ከፋም ለማም ለህዝቡ ያሉት እነርሱው ናቸው። መምህሩ ግን በቤተክርስቲያን እንጀራ እየኖሩ፣ የማህበሩ ቅጥረኛ በመሆን ህዝቡ መምህራኑን እንዳይሰማና በተዘዋዋሪ ማህበረ ቅዱሳንን ብቻ እንዲሰማ ቀስቅሰው መመለሳቸው ብዙ አስተዛዝቦ ነበር። ለመሆኑ መምህር ነኝ ከሚል አንድ ሰው ይህ የሚጠበቅ ነው? ለህዝቡ ከመምህራኑ ውጪ ማን ሊመጣ ነው? ከእነርሱስ በቀር ማንን ሊሰማ ነው? ምን ያህል ቢከፈላቸው ይሆን ይህን ያህል ወርደው የተገኙት? ፍርዱን ለአንባቢ መተው ሳይሻል አይቀርም። ዛሬ ደግሞ እንደተለመደው ማርያም ጥንተ አብሶ የለባትም ሲሉ በአድርባይነት የማህበረ ቅዱሳን ምስክር ሆነው ቀረቡ።

ማህበሩ ማርያም ጥንተ አብሶ አለባት የሚሉ የቤተክርስቲያን መጻህፍትን እየጠቀሰ፣ “አንዳንዶች እመቤታችንን ጥንተ አብሶ አለባት ለማለት የሚጠቅሷቸው እነዚህ ማስረጃዎች ናቸው ይህ ማለት ምን ማለት ነው?” የሚሉ ጥያቄዎች ለሦስቱም ተናጋሪዎች ያቀረበ ሲሆን፣ መልስ ሰጪዎቹም ግእዝን ከቋንቋነት ውጪ በማድረግና የግል ተረታቸውን ያስቀመጡበት ካዝናቸው አስመስለው በመጠቀም፣ በቋንቋው ያልተባለውን በምስጢር ስም ሌላ ፍቺ እየሰጡ የእነርሱን ሀሳብ ሲያራምዱበት ለማስተዋል ተችሏል።

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በ64 አመቷ እንዳረፈች በትውፊት ይነገራል፡፡ የሀጢአት ውጤት የሆነውን ሞት የሞተችው በምን ምክንያት ነው? ቢባል መልሱ ሰው ስለሆነችና ጥንተ አብሶ ስላለባት ነው ከማለት በቀር ሌላ የሚቀርብ ምክንያት የለም። ስለዚህ የማርያም መሞት በራሱ የሚነግረን ማርያም ጥንተ አብሶ ያለባት መሆኑን ነው። እርሷ ጥንተ አብሶ የሌለባት ብትሆንማ ኖሮ ባልሞተችም ነበር። እግዚአብሔር ከሴቶች መካከል የመረጣት ብትሆንም እንደማንኛውም ሰው ስለሆነችና ጥንተ አብሶ ስላለባት የሞተች መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡

ማህበሩ ራሱን በሲኖዶስ ቦታ አስቀምጦ ጉዳዩ እንደተዘጋና ከዚህ በኋላ አባቶች ተወያይተው የሚወስኑት ነገር እንደሌለ አድርጎ የሚከተለውን አቋም ይዟል፡፡ “እነዚህ የጥፋት መልእክተኞች እንዳሰቡት በአጀንዳነት እንደ አዲስ ተነስቶ የምንነጋገርበት ጉዳይ አለመሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል” ለመሆኑ እንዲህ ለማለት እርሱ ማነው? በሃይማኖት ጉዳይ ለመነጋገር ሲኖዶስ መብት የለውም ወይ? የጥንተ አብሶ ጉዳይ የተዘጋ አጀንዳ ነው ማለትስ ምን ማለት ነው፡፡ ጥያቄው እስከ ተነሳ ድረስ መወያየትና ምላሽ መስጠት፣ ተፈራርቶ ከመቀመጥና በጓዳ ሌላ በአደባባይ ሌላ ከመናገር፣ የማያዳግም ውሳኔ ማስተላለፍም ከቅዱስ ሲኖዶስ ይጠበቃል። በውሳኔው ላይ የአኃት አብያተ ክርስቲያናት አቋም ከጥንት አስካሁን ምን እንደ ሆነ መመርመርም አለበት።

እኛም እስከዚያው መጽሀፍ ቅዱስን መሰረት ያደረገ ትምህርት አባ ሠረቀ ከጻፉት በመነሳትና ማህበረ ቅዱሳን ባናገራቸው በአቡነ እንድርያስና በመምህር ደጉ ኣለምና በመምህር ሀብተ ማርያም ተድላ ቃለ መጠይቅ ላይ በመመስረት መጽሐፍ ቅዱስን መሰረት ያደረገ ትምህርት እንደምናቀርብ ከወዲሁ ለመግለጽ እንወዳለን።

39 comments:

 1. The logic of the "mahiber" seems correct and I know Abune Endrias, He is well educated religeously. So I expect Your biblical post that can convince readers otherwise what you post today is simply opposing ideas. Opposing Ideas without convinsing postes is meaningless. I think Aba Sereke is not that much educated like Abune Endrias, so who will be correct? Anyways I expect you to come up with real evidences from bible. By the way her death couldn't indicate having "yewrse hatiat". This is a very tricky logic.

  ReplyDelete
  Replies
  1. St. Mary the mother of Christ Jesus has died. This is truth. She doesn't die since she is sinner. However; she has died since she is a humanbeing. Our Lord Jesus Christ has full human nature and full divine nature too. Evenif he has full divine nature, when he was 33 years old, he has died. Is he sinner, Glory to him, Absolutly not. He is one of the Holy Trinity. So, St. Mary has died since she is a humanbeing.

   Delete
  2. To anonymous
   you wrote
   "She doesn't die since she is sinner. However; she has died since she is a humanbeing". I don't agree


   In old days "a human being = a sinner". According to the word of God "
   For all have sinned, and come short of the glory of God" Roman 3:23
   Please note the word "all", it equals all human being. from the first man Adam to now and until the second coming. If there was at least one who doesn't come short of the glory of God, then there was no need for God to send his beloved son Jesus Christ to die for all sinners. It would have been easier to crucify the one who doesn't come short of the glory of God. And there need not be TEWAHDO HAYMANOT as well. The truth is we all were in the back of our ancestors ADAM and EVE. We all sinned when they tried and failed a coup against the kingdom of God. We were there, by blood we were part of it. All human being was part of it. There was no other human generation other than ADAM and EVE. If you believe there is please come up with some explanation. Even our lord Jesus Christ used the phrase “Son of Man" to call himself. He was proud of his humanity as well. This proves that OUR LADY ST. MARY is from ADAM AND EVE generation. ጥንተ አብሶ is hereditary. It did not remain only Adam and Eve's. As life passes from them to all of their descendants it passes as well. That is why we have corrupted, or distorted nature of a human being. We never been created like that. We sinned and we all fallen from Grace. Any way it is courageous to believe in the good and true Tewahdo teaching. It must be free of emotions and misunderstandings. By being our cuisine as human being, our lady st. Mary had ጥንተ አብሶ but free of it during BISRAT. This is how I believed and I will allways believe. I am an orthodox Tewahdo christian and other orthodox Christians (AHAT BETE CHRISTIAN) agree with me as well. Should this be a change in the country, I don't think so, it will be a disaster. But the truth has to be told in some other ways.

   by the way it is not good to compare Jesus Christ's death with his mother. His was BEFEKAD AND BEHAILU AND BESILTANU. All human beings die BEGID.

   Delete
 2. ere yiker yeblachehu emebetachen dingel mareyam besegam benfesim fitsum dingel netshu yetleyech yetemertech geta yaderebat tente habeso yelelebat selemehonu yeamelakachen sim yetemesegene yihun amenn lotu sebhat min eyalachehu new ere tewww gud endayemetabin

  ReplyDelete
 3. ስለ ጥንተ አብሶ ጉዳይ የተናገረ ሁሉ አባ ሰረቀን ለመንቀፍ ነው ነው የምትሉት:: አሁን እኮ በግምት እና በይሆናል ሳይሆን በግልጽ ኃይማኖ ታቸው እንድጣራ ውሳኔ ተላላልፎባቸዋል:: አሉባልታ ብቻ እየሆናችሁ ነው አይየተሃዲሶ ነገር:: ለምን በግልጽ አትናገሩም ተሃድሶን የተቃወመን ያለውን በማዛባት የራሳችሁን አንድምታ በመስጠት ህዝቡን አታወናብዱት በትክክል የምታምኑበትን ንገሩት እና የሚከተላችሁ ማንነታችሁን ይወቅ:: ስለቤተ ክርስቲያን የምታስቡ ከሆነ ለምንአንድም ቀን ስለአስተዳደር ብልሽቱ፡ በስልጣን ስለመባለጉ፡ በቤተ ክርስቲያንገንዘብ አላግባብ ስለመበልጸግ አታወሩም:: ገሃድ ዝርፊያ ገሃድ በደሎች ይታያሉ ምነው ዝምታችሁ ወይንስ ያም ያው ቤተ ክርስቲያንን ማዳከሚያ ስለሆነ የስትራቴጅክ አንድነት አለው::

  ReplyDelete
 4. come up with reason in the bible. otherwise shut up your mouth

  ReplyDelete
 5. አቤት ድንቁና:: በእናንተ አባባል ከሄድን ኢየሱስ በ33 ዓመቱ የሞተው ጥንተ አብሶ ስለነበረበት ነውን? እነ ኤልያስ ያልሞቱት ስለሌለባቸው ነው? እንደው ማፈሪያ የሆናችሁ ናችሁ:: በነገራችን ላይ ከጴንጤ ይልቅ ከካቶሊኮች ጋር የሚያመሳስሉን ነገሮች አሉ:: በዚህ ጉዳይ አንድ ከሆንን እሰየው::

  ReplyDelete
  Replies
  1. አቤት ድንቁና:: በእናንተ አባባል ከሄድን ኢየሱስ በ33 ዓመቱ የሞተው ጥንተ አብሶ ስለነበረበት ነውን? እነ ኤልያስ ያልሞቱት ስለሌለባቸው ነው? እንደው ማፈሪያ የሆናችሁ ናችሁ::

   Delete
  2. If you were trying to say አቤት ድንቁርና, and insulting someone just because he wrote his understanding of his belief, not only you are wrong but also you go to hell. What are you going to call yourself if you don't know MATHEW 5:22 That says,
   "But I say unto you, That whosoever is angry with his brother without a cause shall be in danger of the judgment: and whosoever shall say to his brother, Raca, shall be in danger of the council: but whosoever shall say, You fool, shall be in danger of hell fire'. I hope you will never use the word ድንቁርና.

   እነ ኤልያስ ያልሞቱት ስለሌለባቸው ነው? if you don't know he will die before the second coming being as witness for Christ, and the bible tell us "Elijah was a man with a nature like ours" James 5:17

   "በነገራችን ላይ ከጴንጤ ይልቅ ከካቶሊኮች ጋር የሚያመሳስሉን ነገሮች አሉ:: በዚህ ጉዳይ አንድ ከሆንን እሰየው" what about HULET BAHIRY ከካቶሊኮች ጋር አንድ ከሆንን እሰየው?

   Delete
  3. አንተ ሰው ምን ያለኸው አላዋቂ ነህ! ኢየሱስ የሞተው የእኛን ኃጢአት ተሸክሞና በእኛ ምትክ ሆኖ እንጂ ጥንት አብሶ ስላለበት አይደለም፡፡ ማርያም የሞተችው ግን ጥንተ አብሶ ስላለባት ነው፡፡ ሄኖክና ኤልያስም የአዳም ዘር ስለሆኑ ጥንተ አብሶ አለባቸው። አሁን ተሰውረው ቢገኙም ኋላ መጥተው እንደሚሞቱ የታወቀ ነው፡፡ ስለዚህ የሌለ "ሎጂክ" አምጥተህ አታደናግር። በዚህ ምክንያት አለቦታው ያስቀመጥከው ስድብ ወደአንተው መመለስ አለበት፡፡ ማፈሪያ ነህ።

   Delete
  4. "ስለዚህ የማርያም መሞት በራሱ የሚነግረን ማርያም ጥንተ አብሶ ያለባት መሆኑን ነው። እርሷ ጥንተ አብሶ የሌለባት ብትሆንማ ኖሮ ባልሞተችም ነበር።"

   ለካ ሎጅክ ታውቃለህ:: አላዋቂ አይደለህም ማለት ነው? ከላይ ባለው አባባል ኢየሱስ በ33 ዓመቱ የሞተው ጥንተ አብሶ ስለነበረበት ነውን? ለነገሩ አናንተ ነገ አለበተ ማለታችሁ አይቀርምና እናያችሁዋለን:: ከመናፍቅ በላይ ማፈሪያ ደሞ ከየት ይገኛል?

   በነገራችን ላይ ከጴንጤ ይልቅ ከካቶሊኮች ጋር የሚያመሳስሉን ነገሮች አሉ:: አንድ ከሆንን እሰየው" what about HULET BAHIRY ከካቶሊኮች ጋር አንድ ከሆንን እሰየው?

   አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ የሚለውን እነሱም ስለሚጠቀሙበት እንተወው እንዴ? በሁለት ባህሪማ ስለምንለያይ እኛ ተዋህዶ ተባልን:: በነገራችን ላይ 'በዚህ ጉዳይ' ማለት ጥንት አብሶ መሆኑ አልታየህም?

   Delete
  5. Please for the sake his holy name do not wrote this many times "ኢየሱስ በ33 ዓመቱ የሞተው ጥንተ አብሶ ስለነበረበት ነውን? If nobody said anything about it yet do not say it,it is a sin on you. You are invoking a holy name. the third commandment states
   "Thou shalt not take the name of the LORD thy God in vain; for the LORD will not hold him guiltless that taketh his name in vain"

   Just focus on the issue, it will help me and others understand your point.

   If you want my little understanding of the issue Our Lord Jesus Christ's death was BEFEKADU AND BEHAILU AND BESILTANU. However,all human beings including our lady st.Mary die BEGID.

   Delete
  6. @my little understanding
   seriously This is your argument?

   Delete
  7. yes, why don't you teach me then, I am ready to learn.

   Delete
 6. በጣም የሚያስገርመው ጉዳይ ይህ ማህበር ትብዬው የወንድሞች ከሳሽ የሆንው የሰይጣን የአደራ ልጆችን ከየቦታው በማሰባሰብ ህዝበ ክርስቲያኑ በሞቱ ሞትን ሽሮ ያዳነውን እየሱስን እንዳያውቅ እና እንዳያምን ምንም ከነገረ ድህነት ጋር የማይገናኝ ጉዳይ በማንሳት ድብቅ ፖልቲካዊ ዓላማውን ለማሳካት ይፍጨረጨራል::

  ርካሽ በሆነው እና በህዝቡ ዘንድ ተነባቢነቱ እየቆመ ባለው የስም ጽድቅ ጋዜጣ የክሱ ምስክር ያደረጋቸው በጥንቆላ እና አጋንንት በመሳብ ጥቅም ካገኙ ምንም ወንጀል ከመፈጸም ወደ ሓላ የማይሉትን እንደ ድጉዓለም ካሳ ዓይነት ሰዎችን ነው:: የቤተ ክርስቲያንን ህልውና የናቀው ይህ ማህበር ለድንግል ማርያም ተቆርቁሮ እንዳልሆነ ይታወቃል::

  ስለዚህም አንባቢ ሆይ የከሰረ ዓላማ ይዞ ከማስተማር ይልቅ እንደ ግብር አባቱ ሰይጣን ስም ማጥፋት;ጥል;ክርክር;አድማ.... በማሰማት የሚያውክህን የሰይጣን ማህበር አጥብቀህ ልትዋጋ ያስፈልጋል:: በገንዘብ ተገዝተው ለድብድብ እና ለፀብ የተሰለፉትን; ያልገባቸውን እና ማስረዳት የማይችሉትን ጉዳይ የሙጥኝ የሚሉትን;ሁሉ ነቅተን መጠበቅ አለብን

  ReplyDelete
 7. ምን አይነት የማይመስል አመክንዮ ነው ስጋዊ ሞት የጥንተ አብሶ ውጤት ከሆነ በጌታ በኩል የተሠራው የድህነት ስራ ሁሉ ፈረሰ ማለት ነው ገና ነገረ ድህነት አልገባህም የቀበሮ ባህታዊ በጎች መሀል ይፀልያል እንዲሉ አባ ሰረቀም ማንነታቸw tegaltoal no more confusion we know who is evry one aman aman emebetachen tente abso yelebatem!!!!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. አንተ ሰው እንዴት ነው የምታስበው? ስጋዊ ሞት የጥንተ አብሶ ውጤት አለመሆኑን ገና ከአንተ አፍ ሰማሁ፡፡ ቤተክርስቲያን እኮ ስጋዊ ሞት የጥንተ አብሶ ውጤት አይደለም አላለችም፡፡ መሆኑን ታምናለች። አንተ ግን አስተባበልክ፡፡ ጥንተ አብሶ የስጋዊ ሞት ውጤት ካልሆነ ታዲያ የጽድቅ ውጤት ሊሆን ነው? ጥንተ አብሶን የስጋ ሞት ውጤት ነው ማለት ጌታ የሰራውን የማዳን ስራ እንዴት አድርጎ ነው የሚያፈርሰው? ይህን ግልጽ ብታደርግ ጥሩ ነው፡፡ ጌታ የተፀነሰውና የተወለደው ያለ ጥንተ አብሶ ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ እመቤታችን ማርያምን የፀለላት (የጋረዳት) ጥንተ አብሶ ወደ ጌታ እንዳያልፍ ነው፡፡ ስለዚህ ያለኀጢአት ተወልዷል፡፡ የሞተው ግን እንደሌሎች ሰዎች ጥንተ አብሶም ሆነ ሌላ ኀጢአት ሰርቶ አይደለም፡፡ የሰዎችን ሀጢአት ተሸክሞ ነው። ስለዚህ በእርሱ ሞት ድኅነታችን ተከናወነ እንጂ አልፈረሰም፡፡ የእርሱ ሞትም ከጥንተ አብሶ ጋር አይገናኝምና እባክህን አስተውል!!!

   Delete
 8. betam betam yemitasazanu miskonoch ...amilakachen kedingel mariyam sile hatiyategnoch teweled enji hatiyat yelebetm ..silehatiyategnoch mote enji tinet abso nirobet aydelem yemotew yihen sitbalu demo eyesus wend huno siletegelets wendochen aymeleketim endatelu kkkkkkkk mechem gudachuh ayalekim....enam lela beki mikneyat kalachuh ensimachuh

  ReplyDelete
 9. ቅድስት ማርያም የአዳም በደል አግኝቷታል ወይም አላገኛትም በማለት መከራከር ለእርሷ የሚጨምርላትም ሆነ የሚቀንስባት ነገር የለም። ነገር ግን እርሷን ያፈቀሩ ወይም በጣም የወደዱ በመምሰል እርሷ ያላለችውን ወይም የማትለውን ለእርሷ መናገር እብደት እንጂ ጤንነት አይደለም። የምንነጋገረው በመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃነት ከሆነ እውነቱን ማንኛውም ያለማንገራገር ሊቀበል ይገባል። የአዳም በደል የሚተላለፈው በዘር እንጂ በሰው ፈቃድ አልነበረም።
  1/ የአዳም እዳ በደል ከሰው ልጆች ላይ የወደቀው ቀራንዮ ላይ ክርስቶስ ደሙን ባፈሰሰ ጊዜ ነው አይደለም?
  ነው የምንል ከሆነ እስከሞቱ ጊዜ ድረስ የሰው ልጆች ሁሉ የአዳምን በደል በዘር መውረሱን አምነናል ማለት ነው።
  ይህንንም ወንጌል ያረጋግጥልናል።
  «ስለዚህ ምክንያት ኃጢአት በአንድ ሰው ወደ ዓለም ገባ በኃጢአትም ሞት፥ እንደዚሁም ሁሉ ኃጢአትን ስላደረጉ ሞት ለሰው ሁሉ ደረሰ» ሮሜ5፣12
  ከማርያም በስተቀር እዳ በደሉ ሁሉም ደርሷል የምንል ከሆነ ደግሞ፣
  1/ ሮሜ 5፣12 ን ክደናል ማለት ነው።
  2/ ማርያም በዘር በሩካቤ አልተወለደችም ማለት ነው። በደሉ የሚተላለፈው በዘር ስለሆነ።
  3/ ማርያም «በአምላኬና በመድኃኒቴ» ያለችው በስህተት ነው ማለት ነው። ሉቃ 1፣47
  4/ «አንጺሆ ኪያሃ፣ ቀዲሶ ሥጋሃ፣ ወኀደረ ላእሌሃ» እሷነቷን አንጽቶ፤ ሥጋዋን ቀድሶ፤በእርሷ ላይ አደረ ያለው ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ተሳስቷል ማለት ነው።
  5/ ጥንተ አብሶን በተመለከተ ኦርቶዶክስ ከካቶሊክ ጋር አንድነት አላቸው ማለት ነው።

  እውነቱ ግን ተጽፏል።«ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፣በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ» ሮሜ3፣23

  ReplyDelete
  Replies
  1. Why don't you write about the death of chirest then. You simply try to talk non related things, she is special in that she is the mathor of our savor Juses chirest. So you can't relate with other oridinary people simply by taking words like all.You fear to say Juses has the sin too but based on your logic it is true that Juses has the sin "lotu sibihat". I think some people simply take religious things as simple as common logics but certainly not. So your analogy is false by >100%. Come up with things that can differenciate death of Juses and his mother, my friends otherwise don't west your and our time.

   Delete
  2. ማርያም ኢየሱስን ስለወለደች ወደአምላክነት አልተቀየረችም። ከልደት እስከሞት ሰው ነበረች። አሁንም በሰማይ ያለችው በሰውነት ነው። ኢየሱስም ከምድራዊው ሰው ሥጋ በመልበሱ አምላክነቱ ከእሱ አልሄደም። አምላክ ሰው ሆነ ስንል ውላጤ አገኘው ማለታችን አይደለም። ማርያምን ከኢየሱስ ጋር ማመሳሰል ትልቅ ስህተት ነው። በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር በታቦቱ ላይ ሆኖ ሙሴን ያናግረው ነበር። ታቦቱ የክብሩ መገለጫ ከመሆን ውጪ እግዚአብሔር ስለተገለጠበት ብቻ ወደእግዚአብሔርነት ተቀየረ ማለት አይደለም። ወይም የተሰራበትን እብነ የእብነ በረድነት ጠባይ ቀይሮ አምላክ ሆነ ማለት አይደለም። ዛሬ በአይሁዳውያን ዘንድ ያ የቀደመው የብሉይ የታቦት ክብር አለመኖሩ የእግዚአብሔርን አለመኖር አያሳይም። እግዚአብሔር በአንድ ወቅት ለክብሩ መገለጫ ያደረገውን በሌላ ዘመን ለአምላክነቱ በሚስማማው ቀይሮት እናገኛለን። እንደዚሁ ሁሉ አምላክ በሰው ስጋ ተዋሕዶ ሰው ሆኖ ተገለጸ። ሰው ቢከብር ከአክባሪው ኃያል ክንድ የተነሳ ነው። ሰው በራሱ ምንም ነው። ማርያምን ቀደሰ፣አነጻ፣ ከስጋዋ ስጋን ነሳ ስንል የእሱን ችሎታ እንጂ ከራሷ በሆነ ችሎታ ለዚህ እንደበቃች አያሳይም። ስለዚህ ሙሴ የቀረጸው እብነ በረድ በራሱ ኃይል ያለው ሳይሆን እግዚአብሔር ቃሉን ሲጽፍበት እንደመሆኑ ሁሉ ማደሪያ ታቦት የሆነችው ማርያም ቃል ኢየሱስ በማህጸንዋ ሲጻፍ እንጂ ከዚያ በፊት የክርስቶስ እናት አልነበረችም። የኢየሱስ ኃጢአት አልቦነት ከአምላካዊ ባህርይው የሚመነጭ እንጂ ከሌላ ኃይል የሚቀበለው አይደለም። ማርያም ግን ከራሷ የሆነ አምላካዊ መንጻት የላትም። ስለዚህ ፍጡርንና ፈጣሪን አቀላቅለን ማየት አይገባም። ስለወለደችው አምላክ አልሆነችም!!!!

   Delete
 10. good point. please let us your view in this regard. though there are number of foreign explanation, i will hope that you will come up with EOTC explanation. if you are supporting the idea of st mary with original sin, please attend these questions;
  1. the flesh God incarnated from st mary, is it with sin?
  2. if death is your one of reason,why we see peoples not died in old testament, like henok
  3. effect of original sin was closing the gate of heaven and end of original sin is opening of the heaven returning to its original function. how do you relate this to your explanation
  i am sure i will have so many question in the future.

  one last comment is please try to be professional when you write articles, aruments should be with ideas, not to the people and asociations. otherwise it will be boring to visit your site talking and manetioning the same things forever, probably yo will loose readers.
  good luck

  ReplyDelete
  Replies
  1. አንተ ከየትኛውም አስተያየት ሰጪ የተሻለ ሃሳብ አቅርበሃል። እሱም መሰረት ያለውን ጥያቄ ማቅረብህ ነው። ለማንም መቃወም መብት ቢሆንም ለሚቃወመው ነገር የተጨበጠ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅበታል። ካላወቀ ደግሞ በማስረጃ የተደገፈ አሳማኝ መልስ መጠየቅ ደግሞ ወግ ነው። አንዳንዶች ግን ሲቃወሙም ተቃውሞአቸውን በጩኸት ለመሸፈንና መልሳቸውን በተረት ላይ አስደግፈው ለማሳመን ይፈጋሉ ወይም ነገሩ ሲከብዳቸው ብዙ ምርምር የማይጠይቀውን ስድብና ሽሙጥ ይሰነዝራሉ። እናም ያንተን ጥያቄ አድንቄ የተረዳሁትን እውነት ያህል ልመልስልህ።
   1/ የአዳም ኃጢአት የሚተላለፈው በሩካቤ ከሚከፈለው ስጋቸው እንጂ ትውልዱ ኃጢአት ስለሰራ አይደለም።
   [እስከ ሺህ ትውልድም ቸርነትን የሚጠብቅ፥ አበሳንና መተላለፍን ኃጢአትንም ይቅር የሚል፥ በደለኛውንም ከቶ የማያነጻ፥ የአባቶችንም ኃጢአት በልጆች እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድም በልጅ ልጆች የሚያመጣ አምላክ ነው ሲል አወጀ]ዘጸ 34፣7
   እንደዚሁ ሁሉ ማርያም ከኢያቄምና ከሐና በዘር የተወለደች ስለሆነ ይኼው የአዳም መተላለፍ ሊደርስ የግድ ነው። ያ ማለት ግን ማርያም በራሷ በኩል ማለትም በኀልዮ፣ በነቢብ፣ በገቢር ፍጹም ንጹሕ ነበረች። ከእናትና አባቷ የተካፈለችው ሥጋ ግን አዳማዊ ማንነት አልነበረውም ማለት አይደለም። እናትና አባቷም በኑሮአቸውና በሕይወታቸው ንጹሃንና ቅዱሳን ነበሩ። ባይሆኑማ ኖሮ ማርያምን የምትመስል ብጽእት እናት መውለድ ባልቻሉም ነበር።ያ ማለት ግን አዳማዊ ማንነታቸው ንጹህ ነበር ማለት አይደለም። ይሔው አዳማዊ ማንነት ለማርያም የተወገደላት በልዑል ኃይል ነው። መልአኩ ወንድ ልጅ ትወልጂያለሽ ስሙንም ኢየሱስ ትይዋለሽ ሲላት፣ ወንድ ሳላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል አለችው። ወንድ በማወቅ የሚገኘው ጽንስ አንድም ምድራዊ እንጂ ሰማያዊ አይደለም። አንድም የአዳም በደል በዘር የሚደርስበት ስለሆነ ንጼህ ሆኖ ሌሎችን ማዳቸው የሚችል አይሆንም። ስለዚህ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል፣ ይህም የሚሆነው መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይጸልላል አላት የሚለውን ቃል ዘወትር የምናነበው ቃል ነው። «ይጸልላል» ማለት ምን ማለት ነው። እንግሊዝኛው "Overshadowed" እብራይስጡ «בצלו » ባጻሉ ግሱ «צל » ጻል ሲል ትርጉሙ መከለል፣ መጋረድ ማለት ነው። ግሪኩ ደግሞ σκιά ሽኪያ በማለት ያስቀምጠዋል። አማርኛችን ከእብራይስጡ ጋር ካለው መቀራረብ «ይጸልላል» የሚለውን ግስ (ጸለለ)ፍቺ ስንመለከት ከአለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ገጽ 755 ላይ እንዲህ ተቀምጦ ይገኛል። «መጥራት፣ መጥለል፣ ጥሩ መሆን፣ መቅለጥ፣መንጠር ለመጥራት» ሲል ያስቀምጥዋል። ከዚህ የምንረዳው በማርያም ላይ መንፈስ ቅዱስ ላይ ሲጸልል «አጠራት፣ ወርቅ ቀልጦ እንደሚጠራ አነጻት፣ ንጹህ አደረጋት ማለት ነው። ቅዱስ ያሬድም በድጓው የተናገረው ትክክል ነው። «አንጺሆ ኪያሃ፣ ቀዲሶ ሥጋሃ፣ ወኀደረ ላእሌሃ» አንጽቶና ለይቶ በማኅጸንዋ አደረ ማለቱ ትክክል ነው። እኛም የምንለው ይህንኑ ነው። ከአዳም የዘር ውርስ ጋረዳት፤ ከለላት፣አነጻት፣ አጠራት፣ለያት፣ በማኅጸንዋ አደረ፤ ያኔም የልዑል ልጅ ተባለ እንልላለን።
   «መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፦ መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል» ሉቃ 1፣35
   በግሌ ከዚህ ውጪ ምንፍቅናና የእግዚአብሔርን አሠራር መቃወም ነው እላለሁ።
   የእኔ ማስረጃ የተጻፈውን በማቅረብ ነው። የለባትም የሚሉ ምኞታቸውን ከመግለጽ ውጪ እስኪ የለባትም የሚል ማስረጃ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተንትነው ያቅርቡ!!!!!
   2/ስላለመሞት የሄኖክን ታሪክ እዚህ ላይ ማምጣትህ ለእኔ ግልጽ አይደለም። ሄኖክ ስለተሰወረ የአዳም ዘር መሆኑ ቀርቷል አያሰኝም። ማርያም መሞቷ ይታወቃል። አርጋለች ብንልም ሳትሞት አይደለም። ካልሞተው ሄኖክ ጋር ምን ለማመሳሰል ፈለግህ? ጥያቄህ ከምን ጋር ለማያያዝ የቀረበ ነው?
   3/ የምናውቀው እውነት በቀደመው አዳም በደል ሞት ሰለጠነብን፣ በሁለተኛው አዳም ሞት ሕይወትን አገኘን። የተጻፈው ይህ ነው።
   «ነገር ግን በአዳም መተላለፍ ምሳሌ ኃጢአትን ባልሠሩት ላይ እንኳ፥ ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ ድረስ ሞት ነገሠ፤ አዳም ይመጣ ዘንድ ላለው ለእርሱ አምሳሉ ነውና፣በአንዱም በደል ሞት በአንዱ በኩል ከነገሠ፥ ይልቁን የጸጋን ብዛትና የጽድቅን ስጦታ ብዛት የሚቀበሉ በአንዱ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በሕይወት ይነግሣሉ» ሮሜ 14፣15-17
   የምናውቀው እውነት ይህ ነው። ምን ለማወቅ እንደፈለግህ ግልጽ አይደለም። ጥያቄህ ግልጽ፤ መጽሐፍ ቅዱስን መሰረት ያደረገና እውነትን ለማወቅ እንጂ ለመፈተን ያልቆመ እንዲሆን ይመከራል። እግዚአብሔር ይርዳህ።

   Delete
  2. ሠይፈ ገብርኤልMarch 27, 2012 at 8:20 AM

   የጾታ እኩልነትን አታምንበትም መሰለኝ ደጋግመህ ባልቴት የሚለውን ቃል ለማውገዣ ተጠቀምክበት ፡፡ እኔ አነበብኩት ብዬ ከጠቀስኩት አንድም በሴት የተጻፈ መጽሐፍ አልነበረም ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ኢሳያስ 1፡9 የሚለውን ጠቅሼ በማያያዝም ፣ አባቶች የጻፉትንና የሚሉትን በሎጅክም ሁላችንም መቀበል የምንችለውን አስረጅ ጠቅሻለሁ ፡፡ የእግዚአብሔርን ከሃሊነት ካልካድንና ምንም ነገር አስቀድሞ አያውቅም ካላልን በስተቀር በማለት ሁላችንም ሊያሳምን ስለሚችል በአእምሮአችን መመዘን እንድንችለው አቅርቤአለሁ ፡፡ ሌላውም መጽሐፍ የእኔ የግሌ ሳይሆን ድፍን ኢትዮጵያ የሚያነበውና የሚጠቅሰው የክብረ ነገሥት መጽሐፍ ነው ፡፡

   ራሳችንን ከሌሎች የሃይማኖት ድርጅቶች ለመለየት ሌላ አምላክ ካላመጣህልን በስተቀር የምንለያየው በጥቃቅን የትርጓሜ ልዩነቶች ነው ፡፡ ሁሎችም ክርስቶስን ያመልካሉ ፤ እና ከነሱ አምልኮ ለመለየት ክርስቶስ ያመልካሉ መባል የለበትም ማለት ፈለግህ ይሆን ? ለእኔ አይመስለኝም ፡፡

   አመሰግናለሁ

   Delete
 11. Sewo bemehona tikekel newo.

  ReplyDelete
 12. ሠይፈ ገብርኤልMarch 26, 2012 at 9:34 AM

  ከተገለጸው ውስጥ በተወሰነው ላይ ያለኝ አስተያየት
  1. “ዛሬ ለውሳኔ ቀርበው ውይይት ይደረግባቸውና ውሳኔ ይሰጥ የሚል ክፍል ቢነሳ መልሱ ከቶ ምን ይሆን ?” ወገኔ
  ለጉባኤ ውይይት የሚሆን ጉዳይ መቅረብ ያለበት መጽሐፍ ተደርሶ ለገበያ ተበትኖ ሳይሆን ማስረጃና ምክንያትን የያዘውን ሰነድ ለሚመለከተው ክፍል ብቻ በማቅረብ ነው ፡፡ አባ ሠረቀ መጽሐፍ ጽፈው ለገበያ /ወደ ህዝቡ እንዲበተን/ ነው ያቀረቡት ፡፡ ይህ መጽሐፍ ለህዝብ የቀረበ አቤቱታ ነው ለማለት ደግሞ መጽሐፉን ማንበብ ያስፈልጋልና ምንም ማለት አልደፍርም ፡፡ እንደ አሠራር ግን ትክክል አይደለም ፡፡ ሰው መጽሐፍ የሚጽፈው ስለሚያምንበት ጉዳይ ሆኖ ሌላውም ወገን ቢገነዘበው ይጠቅማል በሚል ሰበብ እንደሆነ አምናለሁ ፡፡ ስለዚህም በመጽሐፋቸው ላይ አስተያየት እንዲሰጥ የተፈለገው ፣ ሕዝብ ወይስ የሲኖዶስ ሊቃውንት ? የሃይማኖትን ምሥጢር በጥልቀት ያልተማረው ህዝብ የሚያሳልፈውስ አመለካከትና ውሳኔ የሃይማኖት ቀኖና መሆን ይችል ይሆን ? እኔ አላውቅም ፡፡

  2. መጽሐፍ ቅዱስ መሰናከል ለሚፈልገውም ፣ ለቅድስና ለሚጠቀምበትም የሚያገለግል ሰፊ መጽሐፍ ነው ፡፡ መጽሐፉን እንደምንጓዝበትና እንደምንተረጉመው እውነት ሊመስለን ይችላል ፡፡ ለምሳሌ አርዮስ ኢየሱስን ፍጡር ነው ለማለት የደፈረው የመጽሐፈ ምሳሌን ምዕራፍ 8 ስለጥበብ የሚዘረዝረውን ኢየሱስ ነው በሚል ትርጓሜ ሄዶ ነው ፡፡

  ድንግል ማርያምን በተመለከተ ደግሞ ጥንተ አብሶ የለባትም የሚባለው ኢሳ 1፡9 “የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ፥ እንደ ሰዶም በሆንነ እንደ ገሞራም በመሰልነ ነበር” የሚለውን ተከትሎ ነው /ሌሎችም አስረጅዎች አሉ ፣ ነገር ግን የተሟላ የሁሉም ዝርዝር የለኝም /፡፡

  ከዚህ ከላይኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ጋር የሚዛመድ አንድ መቀበል የምችለው ስለ ድንግል ማርያም ያነበብኩት ጽሁፍም “መጀመርያና መጨረሻ የሌለው ፣ በዚህ ጊዜ ተነሣ ፣ በዚህ ጊዜ ያልፋል የማይባል ዘመን የማይቆጠርለት ቀዳማዊ ወደሐራዊ አምላክ ሁሉንም ነገር ከመሆኑ በፊት እንደሚሆን ያውቃልና አዳምና ሔዋን ትእዛዙን ከመጣሳቸው በፊት እንደሚጥሱና እንደሚፈረድባቸው ፣ ንስሐ እንደሚገቡና እንደሚመለሱም ዐውቆ ወደ ቀደመ ክብራቸው ለመመለስ መሣሪያ አድርጐ ያዘጋጀ ስለሆነ ፣ ገና በአዳም አካል ውስጥ ሳለች እንደ ነጭ ዕንቁ ታበራ ነበር ፡፡ ገና ሰማይና ምድር ሳይፈጠሩም በሕሊና አምላክ ነበረች ማለት ነው ፡፡” ይላል ፡፡ በዚህ መንገድ ከተረዳነው በእርግጥም የአምላካችን የሰውን ልጅ የማዳን ዕቅዱ አዳምን ከመፍጠሩ አስቀድሞ ስለነበር ፣ ለዚሁ የሚሆነውን ዘር አስቀርቶልናል ማለት እንችላለን ፡፡ ከሃሊነቱን የምናምን ከሆነ ይህን ለመቀበል አይከብደንም ፤ ዳዊትም ገና በማህጸን ሳለሁ ይለዋልና ፡፡

  በክብረ ነገሥት መጽሐፍም የማቴዎስ ወንጌልን የመሰለ ታሪክ ማርያም ከጥንት ጀምሮ በአዳም አካል ውስጥ እንደ ነጭ ዕንቁ ስታበራ ትኖራለች /ድኒ ዘኀደር ጽዮን/ በማለት የዘር ሃረግን ይተነትናልና ማወቅ የሚፈልግ ማንበብ ይችላል ፡፡

  3. “ማርያም ጥንተ አብሶ የለባትም የሚለውን የካቶሊኮች ትምህርት በስርዋጽ ለማስገባትና የኦርቶዶክስም ትምህርት ሆኖ እንዲታይለት ጥረት አድርጓል ፡፡” የሚለውን እንደ ሃሳብ ማለት ይቻላል ፡፡ ነገር ግን የካቶሊክ ትምህርት የሆነውን በአብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ማመንንም እንጋራለንና በቂ አሳማኝ ምክንያት ሆኖ አይታየኝም ፡፡ ትምህርቱ ሃቅ ካለበት የካቶሊክ ሆነ የኘሮቴስታንት ተብሎ ሊገፋ አይገባም ፡፡ ምክንያቱም ክርስቲያን የሆንን ሁላችንም ድኀነትን አግኝተናል በማለት የምንመሰክረው በአንዱ በኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ስለሆነ ፣ ሁላችንም በቃሉ እንመሳሰልበታለንና፡፡

  አመሰግናለሁ ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. instead of saying "እንደ ነጭ ዕንቁ ታበራ ነበር" it would have been easier if they said ማርያም ጥንተ አብሶ የለባትም. How in the world እንደ ነጭ ዕንቁ ታበራ ነበር interpreted ማርያም ጥንተ አብሶ የለባትም. it is not geez to amaharic.

   እንደ ነጭ ዕንቁ ታበራ ነበር is not even enough to describe her selection to be a mother of God out of billions of women from the beginning of time till now. She is so blessed that no word can describe it. But this does not mean that she was different human being. If we say she is, then there is no tewahdo and no salvation. We will deny our Lords humanity.

   Delete
  2. ባንተ መጽሐፈ ባልቴት ውስጥ ካልሆነ በስተቀር ማርያም በአዳም አካል ውስጥ ሆና እንደነጭ እንቁ ታበራ ነበር የሚል መጽሐፋዊ ቃል የለም። ገና ሰማይና ምድር ሳይፈጠሩ ማርያም በአምላክ ኅሊና ውስጥ ታስባ ትኖር ነበር፣ የሚልም ከዘርዓ ያዕቆብ ተረት በስተቀር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል አላነበብንም።
   አምላክ ምን እንደሚያስብ የሚያውቅ እሱ ማነው? መቼና የት አሰበ? ያሰበውን ተመራምሮ የደረሰበት እሱ አምላክ መሆን አለበት። አስቀድሞ በማሰብ ከማርያም በስተቀር ሌሎቹን የአዳምን ልጆች በግምት ወይም ሳላስባቸው ነው የፈጠርኳቸው የሚል ቃልስ አለ? እኛስ ይህንን እንመሰክራለን።
   «ዓለም ሳይፈጠር፥ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን በበጎ ፈቃዱ እንደ ወደደ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ለእርሱ ልጆች ልንሆን አስቀድሞ ወሰነን»ኤፌ1፣4-5
   ዓለም ሳይፈጠር እኛም ታስበን ነበር። እናስ? መጽሐፈ ባልቴት ስራው ምንጊዜም ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር መጋጨት ነው። እሱን ይዘህ አንተም ስትጋጭ ትኖራለህ።
   ካቶሊክ፣ በስም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በማለቷ ከኦርቶዶክስ ጋር አንድ ዓይነት እምነት አላት አይቻልም። ይህማ ከሆነ በዶግማ አልተለያዩም ማለት ነው። የኦርቶዶክስን መጽሐፍ ቅዱስ የያዙ ሁሉ ኦርቶዶክስ ናቸው ማለት አይደለም። ስም መጥራት ብቻውን አንድ ሆነን በአብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያለንን እምነት እንደምንጋራ አያሳይም። ይህም ያንተ የመጽሐፈ ባልቴት ውጤትህ ነው። ኦርቶዶክስ ሃይማኖታዊ ቃልን መማርና ማስተማር ያለባት በእጇ ካለው ከመጽሐፍ ቅዱስ እንጂ ከካቶሊክ ወይም ከፕሮቴስታንት አይደለም። ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ድኗል ማለት ስህተት ነው። ሁላችንም ድነናል ካልክ አንድ መሆን በቻልን ነበር። መዳን ማለት አንዲት ጥምቀት፣ አንድ ጌታ፣ አንዲት እምነት እንጂ ሺህ ጊዜ ሺህ ክፍፍል ያለው አይደለም። ስለዚህ ሁሉም ክርስቲያን ድኗ ማለት ስህተት ነው።የተባለው ይህ ነው።
   «አንድ ሰውም። ጌታ ሆይ፥ የሚድኑ ጥቂቶች ናቸውን? አለው። እርሱም እንዲህ አላቸው፣ በጠበበው በር ለመግባት ተጋደሉ፤ እላችኋለሁና፥ ብዙዎች ሊገቡ ይፈልጋሉ አይችሉምም» ሉቃ 13፣23
   በሌላ ቦታም እንዲህ በማለት ያረጋግጥልናል። «የተጠሩ ብዙዎች፥ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና» ማቴ22፣24
   ታምራት ገለታን ከመሰለ ከተረት ዓለም ወደ ዓይን ገላጩ ወንጌል ሕይወት ውጣ!! ምክሬ ነው።

   Delete
  3. ሠይፈ ገብርኤልMarch 27, 2012 at 10:26 AM

   የጾታ እኩልነትን አታምንበትም መሰለኝ ደጋግመህ ባልቴት የሚለውን ቃል ለማውገዣ ተጠቀምክበት ፡፡ ዘፍጥረት 3፡15 የሚለውን አንብበው ፤ ዘንዶውን ለዘለዓለም ጠላት አድርጋ የምትቃወመው ሴት እንደሆነች ይገልጻል /ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ገና ከመጀመሪያው መነገሩንም ልብ በል/ ፡፡ እኔ አነበብኩት ብዬ ከዘረዘርኩት አንድም በሴት የተጻፈ መጽሐፍ አልጠቀስኩም ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ኢሳያስ 1፡9 የሚለውን ጠቅሼ በማያያዝም ፣ አባቶች የጻፉትንና የሚሉትን በሎጅክም ሁላችንም መቀበል የምንችለውን አስረጅ ጠቅሻለሁ ፡፡ የእግዚአብሔርን ከሃሊነት ካልካድንና ምንም ነገር አስቀድሞ አያውቅም ካላልን በስተቀር በማለት ሁላችንም ሊያሳምን ስለሚችል በአእምሮአችን መመዘን እንድንችለው ም አቅርቤአለሁ ፡፡ ሌላውም መጽሐፍ የእኔ የግሌ ሳይሆን ድፍን ኢትዮጵያና የዓለም ህዝብ የሚያነበውና የሚጠቅሰው የክብረ ነገሥት መጽሐፍ ነው ፡፡

   In the tradition of Ethiopian Orthodoxy, the Kebra Nagast says:-
   He cleansed eve's body and sanctified it and made for it a dwelling in her for Adam's salvation. She [i.e., Mary] was born without blemish, for He made her pure, without pollution, and she redeemed his debt without carnal union and embrace...Through the transgression of eve we died and were buried, and by the purity of Mary we receive honour, and are exalted to the heights.

   ከዘርዓ ያዕቆብ ይልቅ የማኅሌተ ጽጌ ደራሲ እንደተቀኘው፣ ወይም ቅዱስ ያሬድ “ማርያምሰ ተኀቱ ውስተ ከርሱ ለአዳም” (ማርያም በአዳም ሆድ ውስጥ ታበራ ነበር፡፡) እንዳለ ተጽፏል ፡፡ ዘርዓ ያዕቆብ ስለዚህ ጉዳይ መጻፉን ለጊዜው እኔ አላነበብኩም ፡፡

   ስለዚህም ራሳችንን ከሌሎች የሃይማኖት ድርጅቶች ለመለየት ሌላ አምላክ ካላመጣህልን በስተቀር የምንለያየው በጥቃቅን የትርጓሜ ልዩነቶች ነው ፡፡ ሁሎችም ክርስቶስን ያመልካሉ ፤ እና ከነሱ አምልኮ ለመለየት ክርስቶስን አናመልክም መባል አለበት ማለት ፈለግህ ይሆን ? ለእኔ አይመስለኝም ፡፡

   በሮማ ካቶሊክ የሚተላለፉትን አራቱን የነገረ ማርያም ዶግማዎች እስቲ ተመልከት
   - ዘላለማዊ ድንግል ማለትም አምላኳን ከመጸነሷ በፊት ፣ በእርግዝና ወቅትና ከወለደች በኋላ እመቤታችን ድንግል ናት
   - እመ አምላክ /የአምላክ እናት ትባላለች/ - በኤፌሶን ጉባዔ 431 ዓ.ም. ውሳኔ መሠረት
   - ጥንተ አብሶ የለባትም /አቡነ ፒዮስ ዘጠነኛ በ1854 / ማለትም ከአዳም የውርስ ኃጢአት ነጻ ናት
   - ቅድስት ድንግል ማርያም ምድራዊ ህይወቷን ፈጽማ ከአረፈች በኋላ አርጋለች

   ከአራቱ ውስጥ ሶስቱ ከኢኦተቤ የሃይማኖት ትምህርት ጋር ይመሳሰላል ፡፡ ታድያ የካቶሊክ ትምህርት ስለሆነ አንቀበልም ሊባል ነው ፡፡ አራተኛውም ቢሆን ጥያቄ ሲነሳ ከቤተ ክርስቲያን አባቶች መልስ አልተሰጠም እንጅ ፣ ቤተክርስቲያናችን በትምህርቷ ፣ በቅዳሴዋ ፣ በውዳሴዋ እመ አምላክ ከኃጢአት የጸዳች እንደሆነች ሁልጊዜም ትመሠክራለች ፡፡

   ጠያቂዎች ተነስተዋል ከሆነ ጥያቄው ፣ አዎ ከጥንት ጀምሮ የነበረ ፣ አሁንም ያለ ፣ ወደፊትም የሚኖር ነው ፡፡ ጥያቄዎቹና ተቃውሞዎች ያሉት በጥንተ አብሶ ላይ ብቻ አይደለም ነገር ግን በታቦቷ ፣ በሃይማኖት ሥርዓቷ /የቅዳሴና የአገልግሎት ሰዓቷ ፣ ደንቧ/፣ በአጽዋማቷ ፣ በገዳማቷ .. ብቻ ምን ያዘረዝራል ከኘሮቴስታንትና ከካቶሊክ ሃይማኖት የምትለይበትን ርዕስ በሙሉ እያነሱ ለማስረግ ብዙ ሞክረዋል ፣ ብዙ ተከራክረዋል ፡፡ አሁን ደግሞ ጠባቂዎቿ ቸልተኞች ስለሆኑ የማይነሳ የጥያቄ ዓይነት የለምና እግዚአብሔር ለሁላችንም የሚሆን መልሱን ይስጠን ፤ ቤተ ክርስቲያናችንንም ይጠብቃት እላለሁ ፡፡

   አመሰግናለሁ

   Delete
  4. የጾታ እኩልነት እኰ እንዴት? እንደሶሻሊዝም እግዚአብሔር የለሾቹ ነው ወይስ እንደማን? ጾታ ስትል ወንድና ሴት ለማለት የፈለግህ ይመስለኛል። ሴትና ወንድ መቼም እኩል ሆነው አያውቁም።
   መጽሐፍ ቅዱስ ግን ጾታ የተለያየ እንደሆነ እንጂ እኩል እንደሆነ አይናገርም። አዳም ወንድ ነው። አዳም ያለውን ሔዋን የላትም። አዳም ቀድሞ ከምድር አፈር ተፈጠረ፤ ሔዋን ግን ከአዳም ሥጋ ተፈጠረች። የወንድ ራስ ክርስቶስ ሲሆን፣ የሴት ራስ ወንድ ነው።
   «ነገር ግን የወንድ ሁሉ ራስ ክርስቶስ፥ የሴትም ራስ ወንድ፥ የክርስቶስም ራስ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ልታውቁ እወዳለሁ» 1ኛ ቆሮ 11፣3
   ሴት ስለወንድ ተፈጠረች፣ ወንድ ግን ስለሴት አልተፈጠረም።
   «ሴት ስለ ወንድ ተፈጠረች እንጂ ወንድ ስለ ሴት አልተፈጠረምና» ሮሜ 11፣9
   እንደኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ወንድ 666 አስራው ሲኖረው ሴት ደግሞ 333 እንዳላት ይተረካል። ስለዚህ ሴት ከወንድ ጋር እኩል ሆና አታውቅም። እንደሴቶች ጉዳይ ጽ/ቤትና እንደማርች 8 ድንጋጌና እንደአንተ አባባል እኔ በመቀስቀስና ሴቶችን ዝቅ አድርጎ በማየት ሕግ እቀጣ ነበር!! ወንጌሉን ትተህ ሴቶች ቢሮ ለእኩልነት መከበር ብትሰራ ሳያዋጣህ አይቀርም።

   Delete
  5. ሠይፈ ገብርኤልMarch 27, 2012 at 4:02 PM

   የአጀንዳ ርዕስ ለማስቀየር አስበህ ከሆነ ጉዳዬን በዚሁ ቋጭቻለሁ ፡፡ ክርስቲያን የሆነ መቸም ቢሆን አዛውንት እንስት መጠሪያን ለመውቀሻ ተጠቅሞ አያውቅም ፡፡ ክርስትና ከሌሎች ሃይማኖቶች በተለየ ሁኔታ ለሴቶች ክብር ይሰጣል ፡፡ እመ አምላክ ፣ ሴት ነቢያት ፣ ሴት ቅዱሳን የሚጠቀሰው በክርስትና ብቻ ነው ፡፡ ስላለተኮርክበት ይሆናል ፡፡ አንተ ክርስትና ደስ የሚልህ ሴት ለወንድ ትገዛ በሚለው ብቻ ነው ፡፡
   መጥኔው ለሚስትህ ወይም ሚስት ለምትሆንህ ፡፡

   አመሰግናለሁ

   Delete
  6. could you please tell me when where He cleansed eve's body?
   you wrote "He cleansed eve's body and sanctified it and made for it a dwelling in her for Adam's salvation".

   Was Eve cleansed before salvation?

   thank you

   Delete
  7. I am sorry! I was not there in place when things happen to tell you the answer. I copied and paste what I read. If you want the link to read and find the answer for yourself here it is.

   http://en.wikipedia.org/wiki/Immaculate_conception

   Thank you

   Delete
  8. If there is anybody who is interested to read Kibre Negast Amharic version, the link is:-
   http://www.ethiopianorthodox.org/amharic/holybooks/kibrenegestgeezamharicc.pdf

   Delete
  9. My question was, Is it logical from NEGER HYMANOT perspective to say that "Eve was cleansed" before even the son of God was born from our Lady St. Mary. Can Kibre Negest overwrite the holy bible? Since you brought Kebre Negest, I wanted your understanding of the issue. But i agree with your answer that you were not there when things happen. But if you believe in it you should be able to explain it. Learning comes first before belief.

   Delete
 13. March 26 2012 Mahibere Kidusan & e hapa yetebalew ye poletca dirjit wede ethiopian embss selamaw self aderegu Mahibere Kidusan yepoletcca dirjit mehonun ahun geletse Abba Selama Bezih guday sefa yale Mabrariya Akirbulin Ahun Mahibere Kidusan Manew ? Menfesaw Mahiber weyis Ye Poletik Dirjt yigermal

  ReplyDelete
 14. It is 100% true.

  ReplyDelete
 15. selam abba selamawoch minew Washington DC yetederegewin yetekawimo self almezegebachihum
  1 Kirstiyan yemiselefew wede man new ?
  2 Ahun abiy tsom mehonun restew meselefachewis ?
  3 selfun yesebesebewna yekesekesew manew ?
  4 VOA Ehapa & wetsatoch ( Mahibere Kidusan )bilal?
  5 yetekawemut mann new ?
  6 yeselfu fitsames min hone ?
  7 Mahibere Kidusan Be Waldiba-be zikala - Asebot gedam sim Amercana Awropa Kefitega genzeb eisebesebe new Yemkotsatserew Manew ?

  ReplyDelete
 16. ሰዎች ለእመቤታችን ክብር ጨማሪዎችም ቀናሾም ልንሆን አንችልም፡፡ እግዚአብሄር የመረጠውን ማንም ሊከስ አይችልምና፡፡ እኔ እስከተረዳሁት ፊተኛው አዳም የተገኘው ከንጹህ ምድር ነውና ዳግማዊ አዳምም( አዳኛችን) ከንጹህ ምድር ከእመቤታችን ተገኘ፡፡ ከዛ ውጪ አባቶችን ጠይቅ ይነግሩሃል ነውና እነሱ የነገሩኝ ይበቃኛል፡፡ አባ ሰረቀም ቢሆን ኑፋቄውን በመጽሐፍ ሲያወጣ ቁርጠኛ የበ/ያን ልጆች መልስ ሰጡት እንጅ ይሄ ከምንም ጋር አይገናኝም፡፡ እናንተም ለኔ ምንም ጥርጥር የለውም በቅዱሳንና በእመቤታችን አማለጅነትና ክብር የምታምኑ አይመስለኝም፡፡ ሰው ደሞ የሚያምነውን መናገር መብቱ ነው፡፡ ለምሳሌ ብዙዎች የማያምኑ ስለ ክርስቶስ ብዙ የተሳሳተ ነገር ይላሉ፡፡ ስላሉ ብቻ ነው ማለት አይደለም፡፡ እናንተም ከአውነተኛዋ ተዋህዶ አስተምህሮ ውጪ የፈለጋችሁትን ብትሉ እንደናንተ ካለ ውጪ ማንም አይሰማችሁም፡፡

  ReplyDelete