Thursday, March 1, 2012

አባ ሳሙኤል ይግባኝ የጠየቁበትና “አባ ሚካኤል መውለድ አይችሉም” ሲሉ በሁለት ጠበቃ የተከራከሩበት ጉዳይ ውድቅ ተደርጎ የዮሐንስን ልጅነት የሚያረጋጥ ብይን ተሰጠ - - - Read PDF

የሟቹ የብጹእ አቡነ ሚካኤል ልጅ ነኝ ብሎ የቀረበውና ወራሽነቴ ይረጋገጥልኝ ያለው ዮሐንስ ሚካኤል ከዚህ ቀደም በፍርድ ቤት ልጅነቱን አስመስክሮ ወራሽነቱን ያረጋገጠ መሆኑን ጃንዋሪ 12, 2012 መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡ ፍርድ ቤት የሰጠውን ብይን ተከትሎ በጳጳሳቶቻችን ታሪክ ታይቶም ተሰምቶም በማያውቅና ከአንድ ሊቀጳጳስ በማይጠበቅ ሁኔታ ምእመናንን መክሰስ ሥራቸው አድርገው የያዙት አባ ሳሙኤል ይግባኝ ስለጠየቁ ጉዳዩ ሲታይ ቆይቷል፡፡ ሁለት ጠበቆች አቁመው ሲከራከሩ የነበሩት አባ ሳሙኤል “አባ ሚካኤል ድንግል ናቸው፤ እንኳን ልጅ ሊወልዱ ሚስትም አላገቡም” የሚል መከራከሪያ ይዘው ልጃቸው ዮሐንስ እንዳይወርስ ሲከራከሩ የነበረ ሲሆን፤ ዮሐንስም አባ ሳሙኤል ክብራቸውን ጠብቀው ካልተቀመጡ ልጅነቴን በዲ ኤን ኤ ምርመራ ለማረጋገጥ እገደዳለሁ ማለቱን ዘግበን የነበረ መሆኑ ይታወሳል፡፡

የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዲስ ከተማ ፍትሀ ብሄር ምድብ በ21/6/2004 ዓ.ም በዋለው ችሎት የሁለቱን ወገኖች ማስረጃ ካደመጠና ከመረመረ በኋላ አባ ሳሙኤል ያቀረቡት ማስረጃ የዮሐንስን ልጅነት ማስተባበል ያልቻለ ሆኖ በመገኘቱና የዮሐንስ ማስረጃዎችና ምስክሮች የአቡነ ሚካኤል ልጅ መሆኑን ስላረጋገጡለት ፍርድ ቤቱ ዮሐንስ የአቡነ ሚካኤል ልጅ ነው ሲል በይኖለታል፡፡ ፍርድ ቤቱ አክሎም በፍርዱ ሂደት እስካሁን ዮሐንስ የከሰረውን ኪሳራ ሁሉ ከከሳሹ ከአባ ሳሙኤል መጠየቅ እንደሚችል አስታውቋል፡፡
አባ ሳሙኤል አቡነ ሚካኤል በህይወት እያሉ የወ/ሮ መሰረትን ሚስትነትም ሆነ የዮሐንስን ልጅነት የሚያውቁ ቢሆንም፣ ከሞቱ በኋላ ግን ጉዳዩን በመካድ ‹‹ወደ ፊት በእኛም ላይ ሌላ መዘዝ ይመጣል›› በሚል ስጋት ይመስላል ሁለት ጠበቆች አቁመው ሐሰት ነው በሚል ሲከራከሩ ቆይተዋል፡፡ በመካከልም አንዳንድ ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት የሌላቸውን ምክንያቶች በማቅረብ ለማደናገር የሞከሩበት አጋጣሚ እንዳለም ምንጮቻችን ጠቅሰው፣ ለምሳሌ ጉዳዩ የሃይማኖት በመሆኑ ሙስሊም ዳኛ ሊመለከተው አይገባም በሚል የዳኛ ለውጥ እንዲደረግ ጠይቀው ነበር ተብሏል፡፡ ዳኛውም ‹‹ጉዳዩን ሌላ ሰው ይመልከት ካሉ እኔ ችግር የለብኝም›› ብለው የነበረ ሲሆን አቤቱታው የቀረበላቸው የበላይ አካላትም ‹‹ጉዳዩ የሃይማኖት ቢሆን መጀመሪያውኑ ወደዚህ ባልመጣ ነበር፤ የሃይማኖት ስላልሆነም ነው መታየት የቻለው፤ ታዲያ ዳኛ ይለወጥልኝ ማለት ለምን አስፈለገ? ነው ወይስ ሙስሊም የሆነ ዳኛ ዳኝነት አያይም ማለትዎ ነው?›› በማለት ጥያቄያቸው አግባብ አለመሆኑን ገልጸው ዳኝነቱ ጉዳዩን በያዙት ዳኛ እንዲቀጥል ማድረጋቸውን ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡
ፍርዱ በተሰጠበት እለት የአባ ሳሙኤል ወገኖች የሆኑ በርካታ የአዲስ አበባ ወይዛዝርት ፍርድ ቤቱን ሞልተው የታዩ ሲሆን፣ ይህም ምናልባት በዳኛው ላይ ጫና ለማሳደር የተደረገ ነው ሲሉ አንዳንዶች ገምተዋል፡፡ ሌላው አስገራሚ ክስተት አባ ሳሙኤል አንድ ረዘም ያለ ቀይ ጢማም ጠጉረ ልውጥ ደብተራ በፍርዱ ሂደት ላይ እንዲገኝ አድርገው የነበረ መሆኑ ሲታወቅ፣ ደብተራውም እጁን እያሻሸ በለሆሳስ ሲደግም መታየቱን በፍርዱ ሂደት ላይ የነበሩ የአይን እማኞች መስክረዋል፡፡ አባ ሳሙኤል ደጋሚ ደብተራ ያቆሙት በህጋዊ መንገድ ማሸነፍ እንደማይችሉ ተገንዝበው ደብተራው በአፍዝ አደንግዝ ድግምቱ ፍርዱ እንዲለወጥ ለማድረግ አስበው ነው የሚል እምነት ያሳደረ ሲሆን፤ የእርሱን መድገም ተከትሎ ዮሐንስና ጓደኛው ይህን አጋንንታዊ አሠራር ‹‹በኢየሱስ ስም›› ብለው በጌታችን የስሙ ስልጣን ሲቃወሙ ሰውዬው አስነጠሰው ተብሏል፤ ድግምቱ በፍርዱ ላይ ያስከተለው ተጽእኖ ግን አልነበረም፡፡
በተሰጠው ብይን ዮሐንስ እጅግ መደሰቱንና አባ ሳሙኤል መናደዳቸውን ከፍርዱ ሂደት በኋላ ለማስተዋል የተቻለ ሲሆን፣ ወ/ሮ መሰረትና ወጣት ዮሐንስ ወራሽነታውን በማረጋገጣቸው አባ ሳሙኤል ለአባ ሚካኤል ዘመዶች አወርሰዋለሁ ያሉትን የአባ ሚካኤልን ገንዘብ፣ ሀብትና ንብረት እስካሁን ባለው ሂደት እንዳሰቡት ሊያደርጉ አልቻሉም ማለት ነው፡፡
  

23 comments:

 1. እናንተ የጳጳሱን ትገረማላችሁ ፤ ገና የሚታሙት ፓትርያርክ ሲሞቱ አንድ ሶስቱ ልጅ ነን ብለው ብቅ ይላሉ ፡፡ ይኸ በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የተለቀቀ የዘመኑ መቅሰፍት ውጤት ነው ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ኤጲስ ቆጶስ የአንዲት ሚስት ባል መሆን እንደሚገባው ይገልጻል ፡፡ ነገር ግን በኢኦተቤ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ሊቃነ ጳጳስ የሚሆን ሰው ምን እንደሚፈቀድለት አላውቅም ፡፡ ከህጉ ውጭ ተፈጽሞ ከሆነ ፣ ስለ ህጉ መከበር ሊከራከሩለት ይገባል ፡፡ ጥፋትነቱ አይታየኝም ፤ አያስወቅሳቸውምም ፤ ምክንያቱም ገንዘብ ለማግኘት የማይባል ነገር ስለማይኖር ነው ፡፡ እኔ ዳኛውን ብሆን ግን እውነትን ለማውጣት እስከ መጨረሻው የዲኤንኤ ምርመራ ድረስ እጓዝ ነበር ፡፡ ለማንኛውም ታዳጊው ዮሐንስም የሚማርበት ውርስ ቢያገኝ ለአገር ይጠቅማልና ፣ ሃብትና ንብረቱ የሚቆጩለት ፣ ወደ ውጭ የተሰደደ ገንዘብ አይደለም ፡፡

  ከዛ ውጭ የተሰጠው "የጠንቋይና የአስማተኛ የአምልኮ ትምህርታችሁ" እዚህም ጋር ተደባልቋል ፡፡ እመኑበት ለማለት ይሁን አትመኑበት ለማለት ይሁን አልገባኝም ፤ አባ ሳሙኤልም ይጠነቁላሉ ፣ ያስጠነቁላሉ ለማለት ከሆነ የእጅ አሻሻ ታሪክና አስነጠሰው ጨዋታ የልጆች የተረት ተረት ይመስላል ፡፡ በጌታ ስም አትቀልዱ ፡፡ ማስነጠሱ ምትሃቱን ገታው ለማለት ነው ወይስ የኢየሱስ ስም ሲጠራ ጉንፋን ለቀቀበት ፡፡ ብቻ የፌዝ ነገር ይታየኛል ፡፡

  በዚሁ በቃ እንዲለን ለማንኛውም ስለ ቤተ ክርስቲያናችን ድኀነት እንጸልይ

  ReplyDelete
 2. Only DNA could reveal the truth. The other is a pure hater for Aba Samuel.

  ReplyDelete
 3. As always ridiculous. I don't know what you are trying say. Is there any Jesus other than we know and believe in that you met and made friendship. I wish you no harm but to stop writing such a lie.

  ReplyDelete
 4. come on aba selama, you can do better than this, it just dirty story and i don't learn anything from it and i don't want to judge him as well, focus on what can build us, the rest leave it to almighty

  please don't write TERA ALUBALTA like this

  አባ ሳሙኤል ደጋሚ ደብተራ ያቆሙት በህጋዊ መንገድ ማሸነፍ እንደማይችሉ ተገንዝበው ደብተራው በአፍዝ አደንግዝ ድግምቱ ፍርዱ እንዲለወጥ ለማድረግ አስበው ነው የሚል እምነት ያሳደረ ሲሆን፤ የእርሱን መድገም ተከትሎ ዮሐንስና ጓደኛው ይህን አጋንንታዊ አሠራር ‹‹በኢየሱስ ስም›› ብለው በጌታችን የስሙ ስልጣን ሲቃወሙ ሰውዬው አስነጠሰው ተብሏል፤ ድግምቱ በፍርዱ ላይ ያስከተለው ተጽእኖ ግን አልነበረም

  ReplyDelete
 5. የጳጳሱ ልጅ ዮሀንስ ተሀድሶ ነው ማለት ነው? "በየሱስ" ስም ገሰፀ እኮ ዋው፨

  ReplyDelete
  Replies
  1. men ayente asetyayete new eysuse yemele seme yetsetew lemenafekane becha new lethadeso becha new endehe yemetasebe kehone tesasethale degmo ante tehadeso yemetelwe tehadeso yemebale ale kale asaweken eysuse yemel sem kalaweke bedenbe temare semu aganten yemeyaweta besemu dele yemenaregbete new wendema bibel temare wera kemetmare

   Delete
 6. kkkkkkk wey tata sentu yesemalll kkkkkkkkkkk yahunu yibas alech keberooo kkkkk

  ReplyDelete
 7. Abune Entsons yetebalut ( Aba Gebre Tinsae Hailu ) yeweledut lig zare Diyakon hono eyekedese new temesgen Abune Tsimotewos yederesu lijochachew hager eyetsekemu new min atsefu enersu higaw nachew bibel yifekdilachewal papas mehon yalebet 1 Mist yageba new yalageba sew mulu mehon ayichilem Abune Samueil melkam Abat neberu Ahun Min nekachew Abune Mikaeil Mewledim hone Magibat Mebtachew new yekelekelew manew ? beteley le church mastedader yalebet baletdar & ye lijoch abat yehone sew new

  ReplyDelete
 8. your lie and hate for aba samuel is clear, if the guage is muslim how come he said in the name of jesus cast out the evil spirit? or is he converted to christian rghtaway?

  ReplyDelete
 9. አቡነ ሳሙኤል ምናልባት ተሳስተው ይሆናል
  የኣባ ሰላማ ስህተት ግን የሞተን የሚዎቅስ በመሆኑ አልወደውም
  አቡነ ሚካኤል ደግሞ የዋህና ቅነ ሰው ነበሩ
  ግብዝ ሰው አይመስሉኝም
  ቢሳሳቱና ቢወልዱ አልደነቅምና በአደባባይ አልጽፈውም
  አባ ሰላማ ንስሐ ግባ

  ReplyDelete
 10. Come on guys! You can do better than this. Whatsoever they did please do not write such a shallow and merely sentimental argument like

  የእርሱን መድገም ተከትሎ ዮሐንስና ጓደኛው ይህን አጋንንታዊ አሠራር ‹‹በኢየሱስ ስም›› ብለው በጌታችን የስሙ ስልጣን ሲቃወሙ ሰውዬው አስነጠሰው ተብሏል፤ ድግምቱ በፍርዱ ላይ ያስከተለው ተጽእኖ ግን አልነበረም፡፡

  Do not equalize the name the Lord to something simple and futile. Please! Please! Please! Do not embarrass us. We have seen enough ignorance! If you want us to believe you, try to be better than this! Otherwise, what makes you better than the people you confront?

  ReplyDelete
 11. What a stuide report, I just wonder if the muslim Judge have said "Beyesus sim" with the so called Yohanes,we know now that Yohanis is Tehadeso, is the judge muslim? or is he also "Tehadeso"? I think you dont know what you are writting.
  Your page is full of hate and wagabis.

  ReplyDelete
 12. AS I KNOW VERY WELL AND CLOSELY ABUNA SAMUIAL IS NOT THAT KIND OF PERSON THIS IS TOTALY FABRICATION SIMPLE SLANDER HOWEVER ABBA TEKLE MICHAIL/ABBA MIKAIL/ COULD DO THAT BECAUSE HE JUST BECAME BISHOP AFTER 20 YEARS BAGING ALLMOST ALL BISSHOPS HE WAS REALY DESPRATE

  ReplyDelete
  Replies
  1. that is becouse you dont know aba samuel. we know very well what kind of person he is and what he did. one day aba selama or other website may tell us his story.

   Delete
 13. Petewo Tizeta that who have made destruction in our church in the home land of Ethiopia, now he change his gear to expaned his Tehadeso mission in michal church with his fat man false priest Girma. The mission directely assisted by aba melaku to destroyed our anncient church law. Girma appointed as priest illegaly even he not involved fastining thtough regulation of church. I assured this message not suiport your mission and you will not post it. Just read and leave for ur self.

  ReplyDelete
 14. ይገርማል
  ስርዓትና ቀኖና ባለበት ቤተ ክርስቲያን
  እንደነዚህ ያሉ ይወገዳሉ

  ReplyDelete
 15. TEZEKER MAHIBERINE ZAKIDEMIKE FETIREMarch 6, 2012 at 1:59 AM

  በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ ፊል. 4፡8 ያሳዝናል ስራችን እግዚአብሔርን ያስከብራል ተ5ላላችሁ ጌታ የቸገረው የሚኖርለት የፍቅር ሰው እንጂ አሉባልተኛ አይደለም፡፡ ይገርማል ሰይጣን የቤት ስራ ሰጥቶአችኋል ኢየሱስ የሰጣችሁን ረስታችሁታል፡፡ (ማቴ. 28፡19-20 ፣ የሐዋ. 1፡8) ሌሎች የሚሰሩትን እናንተ ከደገማችሁት መሻላችሁ ምኑ ላይ ይሆን መቼም መቼም ቢሆን ጌታ በዚህ ኤደሰትም አይከብርም አስተውሉ ፍርዱ ሲጀምር እናንተንስ የሚዘልል ይመስላችኋል

  ReplyDelete
 16. minew lela yemiwera neger tefa ende...ebakachihu lemin yesew alubalta tilekmalachihu....esti andande enquan ewnetin tsafu...hulgize whushet...
  oh...i forget yegibir abatachihu seytan leka ewnetin aywedim...enantes endet tiweduatalachihu....
  BE MARIAM EWNET YEHONENA LE BETEKRISTIAN ENA LEHAYMANOT YEMITEKIM, BETSOM GIZE YEMIWERA NEGER ENAWRA...
  I am sorry for the owners of this blog because we have reached the fourth week of this great "tsom" but the blog have never written something about tsom...only HAMET....please for God's Sake plz SEW MAMAT TIRU ENDALHONE EYAWEKACHIHU ATIMU>>>

  ReplyDelete
 17. are bakachehu post yemtareguten eko ymianebut telelek sewoch nachew endih menem yemaimesel teret atzebarku

  ReplyDelete
 18. Amlak ykrtawun ylaklachihu betkekal egziabhern tamlkalachihu
  malet new krstana aymeslengem...

  ReplyDelete
 19. ሰላምን ስበኩልን ወሬ ይብቃችሁ አደራ..

  ReplyDelete
 20. እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው፥ ሰባትንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች፤
  1. ትዕቢተኛ ዓይን፥ 2. ሐሰተኛ ምላስ፥ 3. ንጹሕን ደም የምታፈስስ እጅ፥
  4. ክፉ አሳብን የሚያበቅል ልብ፥ 5. ወደ ክፉ የምትሮጥ እግር፥
  6. በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር 7. በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ።
  መጽሐፈ ምሳሌ 6:16

  ReplyDelete
 21. እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው፥ ሰባትንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች፤
  1. ትዕቢተኛ ዓይን፥ 2. ሐሰተኛ ምላስ፥ 3. ንጹሕን ደም የምታፈስስ እጅ፥
  4. ክፉ አሳብን የሚያበቅል ልብ፥ 5. ወደ ክፉ የምትሮጥ እግር፥
  6. በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር 7. በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ።
  መጽሐፈ ምሳሌ 6:16

  ReplyDelete