Thursday, March 8, 2012

መርዝ ባፉ ማህበር "ማህበረ ቅዱሳንና” ዕርቀ ሰላሙ - - - Read PDF

ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል - «ማህበረ ቅዱሳን ወይስ ማህበረ ሰይጣን» መጽሐፍ ደራሲ
ይህ ጽሑፍ፦

ራሱን ቅዱስ ብሎ በመስየም ለአመታት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሀብተ ንበረት ሲዘፍ፣ የጥንታውያን ገዳማትና አድባራት ቅርሳ ቅርስ ሲያወድምና ለውጭው ዓለም ሲቸበችብ፣ አገልጋዮችዋን ያለ ስማቸው ስም እየለጠፈና እየሰጠ ሲያሳድድና ሲያሸማቅቅ የመጣውን የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በሕግ የማታወቀው የሀገር አንድነትና ሉዓላዊነት አደጋ ላይ የሚጥል አጀንዳ አንግቦ ስለሚንቀሳቀስ ነፍሰ በላ የፖለቲካ ድርጅት “ማኅበረ ቅዱሳን” ዕርቀ ሰላሙን እውን እንዳይሆን በግላጭ ጉባኤ እየጠራ እያደረገው ስላለው አፍራሽ ዘመቻ የሚያስነብብ ነው::

ዕርቅ የተደረሰበት ዕለት እንደሆነ ይህ መናኛ ወገን (“ማኅበረ ቅዱሳን”) በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዓውደ ምህረት ላይ መታሰቢያ: ዕድል ፈንታም አይኖሮውም:: ታሪክም በማይወራለት አኵኋን ስመ ዝክሩ ያከትምለታል:: ይህንንም ጠንቅቆ ሲለሚያውቅ በቀሩለት ጥቂት ቀናቶች በውንብድና ስራ ላይ ተሰማርቶ ጉባኤ እየጠራ የምእመናንን ልብ መክፈል፤ ጥላቻን መዝራትን ስራዬ ብሎ ተያይዞታል::

በሕይወቴ ዘመኔ እጅግ ከባድ የልብ ሐዘን ከፈጠሩብኝ ሁኔታዎችና ክስተቶች መካከል በአደባባይ ለመጻፍም ሆነ ለመናገር የማያመች በ ጆርጂያ አትላንታ ከተማ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን ሁኔታ አንዱ ነው:: ነገሩም እጅግ አሳዛኝ ከመሆኑም በላይ አንገት የሚያስደፋም ነው:: እንደ ቅርጫት ስጋ ተበጣጥሳ እንደ አሜባ የተራባችውን ቤተ-ክርስቲያን ተከታዮችም አዘንኩላቸው:: "የአብያተ ክርስቲያናቱ" መጠሪያ ተቀጽላ የሰማሁትም በድንገት ነበር::

ከምሽቱ 8:00 ሰዓት (Pm) ይሆናል ከአንድ የሀገራችን የባህል ምግብ ቤት እራት ተበልቶ ወደ ቤት መነዳቱ ነው:: ታድያ በዚህ መኻል ከወደኋላ "ሄይ! ነገ’ኮ እሁድ ነው የት ነው የምንስመውሳ" ሲል ይጠይቃል:: አጠገቤ የሚገኘውን "እስቲ ነገ ደግሞ እንደው ሙሌ በዛውም አገር ታያለህ በቃ ... ያለውን የ ... ዎቹ ሂደን እንስማለን" ይላል በነገሩ ግር ያለኝ እንግዳ ደግሞ አንደኛውን "ስማ እንጂ አብያተ ክርስቲያናቱ ታቦት የላቸውም እንዴ በ ... የምትጠሯቸው" ስል እጠይቃለሁ:: ሰዎቹ ለዓመታት የሳቅ ማእቀብ ተጥሎባቸው የነበሩና ማእቀቡን የተነሳላቸው ይመስሉ ጥማታቸውን ለማርካት እስከሚያስመስላቸውና እስኪያለቅሱ ድረስም ክት ብለው ይስቃሉ:: "እንዴ! የሚያስቅ ነገር የተናገርኩ አይመስለኝም ምንድ ነው የሚያስቃችሁ" ስል እጠይቃለሁ:: ያሳቃቸውን ሳይነግሩኝ ሦስቱ በመኪናዋ ውስጥ የነበሩ በሳቅ እየተንከተከቱና እየተቀባበሉ የአብያተ ክርስቲያኖቹ ሁኔታ እንደሚከተለው ይዘረዝሩልኛል “የአማራ: የሸዋ: የጎንደር: የጎጃም” አክሎውም “የለዘብተኛና የጽንፈኛ” ሊያቆሙ ነው “የትግራይ ደግሞ ይላል አንዱ ታቦቶቹን እየጠራ የአክሱም የአድዋ ..” ሰዎቹ
ገና ዘርዝረው አልጨረሱም የገለልተኞች በማለትም ታቦቶቹን ያስቆጥረኛል:: ለእነርሱ ብቻ አልነበረም "በሉ ይብቃችሁ" ያልኩ ለራሴም እዚህ ይብቃኝና ወደ ጉዳዬ ልመለስ::

ጉባኤው የተዘጋጀው ራሱ የቅዱሳን ማኅበር ሲል የሚጠራ በንጹሐን ደናግል እህቶች ክብረ ንጽህና መሰረት ጥሎ በምእመናን ሀብተ ንብረት የከፍተኛ ነዋይ ባለቤት የሆነው ማኅበር ነበር:: ተጋባዥ ተናጋሪውም ዶ/ር መስፍን ይባላል፥ ራሱን “ማኅበረ ቅዱሳን” ሲል የሚጠራ የህጋውያን ሸፋቱ ማኅበር አባልና አውራም ነው:: ይህ ግለሰብ ከዚህ ቀደም በአካል ባላውቀውም “ማኅበረ ቅዱሳን” ወይስ ማኅበረ ሰይጣን? በሚል ለህትመት ካበቃሁት ክፍል አንድ መጽሐፌን በአብነት ትምህርት ስም ከፍተኛ ገንዘብ ለግል ጥቅማቸው ካዋሉ በሰሜን አመሪካ ከሚገኙ የማኅበሩ አባላት መካከል በሰነድ በተደገፈ የማጭበርበር ስራውን ለንባቢ አብቅቼው ነበር:: ለመጀመሪያ ጊዜ ንግግሩም ሆነ በአካል ለማየት የቻልኩ ግን በተጠራው ጉባኤ አማካኝነት ነው::

ከዚህ ቀደም ራሱን "ማህበረ ቅዱሳን" በማለት ስለሚጠራ ማህበር ማንነት እውቀቱ ለሌላችሁ ወገኖች ከብዙ በጥቂቱ "ማህበረ ቅዱሳን" ማለት ይህን ይመስላል:

Ø ይህ ማህበር እውነተኛ መንፈሳዊ መስሎ በመታየት የራሱ አባላት በመመልመልና ጉራ በመለየት ቤተ-ክርስቲያን በጎሳ: በኑሮ ደረጃ የከፋፈለና እየከፋፈለ የሚገኝ እኩይ፤
Ø በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን ስም ቤተ-ክርስቲያኒቱ በማታውቀው ፈቃድ ጡንቻውን የሚያፈረጥምበት የንግድ ተቋማትን በመክፈትና በማደራጀት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን በአፍጢምዋ ደፍቶ ንግዱን እያጧጧፈ የሚገኝ፤
Ø ሀገርንና ቤተ-ክርስቲያንን በሚከፋፍል አጀንዳው የማይስማሙትን ነገር ግን ቤተ-ክርስቲያን ወልዳ ያሳደገቻቸውን አገልጋዮች የሚበትንና የሚያሳድድ፤
Ø የሃይማኖት አባቶችን በመከፋፈል ለቤተ ክርስቲያን ሕግ የማይገዛ፤
Ø ምእመናን ከክርስቶስ ፊታቸውን መልሰው ረብ በሌላቸው እንቶፈንቶ አስተምህሮዎች አጥምዶ በቤተ-ክርስቲያኑ አገልጋዮች ላይ ጣታቸው እንዲቀስሩ የሚያደርግና ለአመጽ የሚያነሳሳ፤
Ø በቤተ ክርስቲያን መካከል ሁከትና ብጥብጥ በማስነሳት የምእመናን መንፈሳዊ ሕይወት የሚያዳክም ግብረ እኩይ ድርጅት ነው::

ወደ ጉባኤው ልመልሳችሁ ጉባኤው ከአርብ ጀምሮ እስከ እሁድ ባሉት ቀናቶች ውስጥ በተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት የሚካሄድ ነው:: አሁን ካገኘሁት መጽሔት በሰፈረው ማስታወቂያ መሰረት በእለተ ዓርብ የሚካሄደውን የመጀመሪያውን ጉባኤ ለመከታተል ሰአቴን አክብሬ (5:00 pm) በከተማዋ መኸል ከተንጣለለው ግዙፍ እስር ቤት/ማረሚያ ቤት አከባቢ የሚገኘውን መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን (4540 Memorial Drive Suite A, Decatur, GA, 30032) በመገኘት መቀመጫ ቦታዬን ይዣለሁ:: (ሪፖርቱ: በዕለቱ ስለተካሄደው ስርዓተ ቤተ-ክርስቲያን እንዲሁም የዕለቱ ተጋባዥ ተናጋሪ የስብከት መፋለስና ህጸጽ: በተጨማሪም ማህበሩ ባሸው ሰዓት የፈለገውን ስለሚዘራባትና ስለሚፈነጭባት ቤተ-ክርስቲያን ገጽታ አያጠቃልልም)::

ተናጋሪው ወደ መድረኩ ወጥተዋል - የምንኖርባትን ዓለም የኑሮ ውጣ ውረድ: የሰው ልጆች የተመሰቃቀለ ህይወት: የምዕራቡ ዓለም የኑሮ ዘዬ (ተራ መሰረተ ቢስ ትችት) አስመልክቶ ለጥቂት ደቂቃዎች አውርቶ እንዳበቃም ወደ ርዕሱ በመመለስ የሰው ልጆች ለምን ሃይማኖት እንደሚያስፈልጋቸው በጥያቄ መልክ አንስቶም አንድና ሁለት በማለት አንደሚከተለው ለማስረዳት ይሞክራል:: የሰው ልጆች ለምን ሃይማኖት እንደሚያስፈልጋቸውም ሲዘረዝርም 1ኛ ከሞት በኋላ ያለውን ነገር ስለማያውቅና ስለሚያሰጨንቀው 2ኛ ደግሞ አቅም ማጣት ነው በማለት ራሱን ግልጽ ያደርጋል::

እውነት ለመናገር ግለሰቡ ይቅር ሥነ መለኮታዊ ግንዛቤ ሊኖረው እንደ ዕድሜው ብዛት የቤተ ክርስቲያኒቱ ምእመን ለመሆኑም የሚያጠራጥር ነበር:: ይህ ሰው ያልሳተው ነገር ቢኖር ስሙና ማእረጉን (ራሱን ሲያስተዋውቅ) ብቻ እንጂ በክርስትና ስም በወጣበት መድረክ ላይ የክርስትና አስተምህሮ ተላልፎ የቅድሳት መጻሕፍት ሀቆች ለማፋለስና ለማተረማመስ ደቂቃም አልፈጀበትም:: ከመሰረታዊ ስህተቶቹም መካከል መጽሐፍ ቅዱስ የሰው ልጆች የኪሳራ ህይወትም ሆነ አመጻን ስለ ነገሰባት ምድራችን በማስመልከት በዋናነት የቀዳሚዊው አዳም በኃጢአት መውደቅ ነው ሲል ስለሚያስተምረው አንኳር የክርስትና ትምህርት ምንም ዓይነት ግንዛቤ አለመጨበጡ ብቻ ሳይሆን ከክርስትና ውጭ ለሰው ልጆች ህይወት መመሰቃቀልና መሻከር ምክንያት ናቸው ተብለው ከሚሰነዘሩና ከሚታወቁ አምስት ቲዎሪዎችም በአንዳቸውም አጠገብ አለማለፉ ነው:: በስህተት የተጀመረ ዲስኩርም በውግዘትና የአመጻ ንግግሮች ታጅቦ አንድ ሰዓት አልፎታል::

አሁን አንድ ሌላ ራሱን የቻለ ርዕስ የሌለው ስብከት ተጀምሯል:: እዚህ ላይ በተለይ በውጭው የሚገኙ የሃይማኖት መሪዎችና ግለሰቦችን አስመልክቶ ሚዛናዊነት በጎድለውና በእጅጉም ወደ አንድ ወገን ባደላ መልኩ የቀረበው የጥላቻ ቋንቋ አልነበረም:: ከበልአም ተንስቶ በአከዓብ አልፎ “ከመዋቅር ውጭ ናቸው” ሲል ከሳዖል ጋር በማመሳሰልም ፈርዶባቸዋል:: አስቀድሞ “ከመዋቅር ውጪ ናቸው” በኋም “አፈንጋጮች ናቸው” ሲል የሚከሳቸው በውጭ የሚገኙ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን የሃይማኖት መሪዎችን ማንነት በአጭር ቋንቋ ነገሩን ሲያስረዳም “ባለቤቱ ካልናቁ አጥር አይነቀንቁ” ሲል የዚህ ሁሉ ሁከትና ብጥብጥም ብቸኛ ተጠያቂዎች በማድረግ ቤተ ክርስቲያን ለራሳቸው ጥቅም መሳሪያ እያደረጓት እንደሚገኙ ያስረዳል::

ለዚህ ሁሉ ምክንያት ብሎ ከጠቀሳቸው ነጥቦች መካከልም በአሁን ሰዓት በውጭው ዓለም ራሳቸውን “ስደተኛ ሲኖዶስ” በማለት የሚጠሩ መሪዎች የእግዚአብሔር ሥርዓት ከመናቅ የተነሳ እንደሆነ አስምሮበታል:: አክሎም ቀኖና ቤተክርስቲያን ለመጣሳቸው እንደ ምሳሌ “ቅድስተ ቅዱስን ድንግል ማሪያም ጥንተ አብሶ አለባት፤ የአሳማ ስጋ ብሉ፤ በኦርጋን ዘምሩ፤ ሴቶች ከነወር አበባቸው ቤተ- ክርስቲያን ቢገቡ ችግር የለበትም” ይላሉ ሲል መረጃ አልባ ምንፍቅና የሚለውን ይዘረዝራል::

በየካቲት ወር ስለሚካሄድ የዕርቀ ሰላሙን አጀንዳ ዓላማ (ባለፈው ሳምንታት በአሪዞና ፊኒክስ ስለ ተካሄደው ድርድር ማለት ነው) አስመልክቶም የገለጸው በእንዲህ ዓይነት መልኩ ነበር “መንገዱ አቀራረቡና አመጣጡ ይለያይ እንጂ የድርድሩ ማሳረጊያ አንዲት ቤተ ክርስቲያን አንዲት መዋቅር የሚል ነው። ታድያ ከዚህ በፊት ያፈነገጡትን ወደ መስመራቸው እንዲገቡ ነው።” በማለት በሰሚዎች አእምሮ ላይ በቀላሉ የማይፋቅ የጥላቻ ዘሩን ይዘራል::

በአጠቃላይ ማኅበሩ በ ጆርጂያ አትላንታ ከተማ በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት የጠራውን ጉባኤ ዓላማና ግብ:

Ø 1ኛ በምእመናን አእምሮ ብዥታ ለመፍጠር:
Ø 2ኛ በምንም ዓይነት መልኩም ቢሆን ዕርቅ ከተፈለገ በውጭው ዓለም የሚገኙትን "ማንም ሳይሾማቸው ራሳቸው በራሳቸው የሾሙት የሃይማኖት መሪዎች" ይላቸዋል ሀገር ቤት ከሚገኘው ሲኖዶስ የሚቀርበውን የዕርቅ ሰነድ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መስማማት እንደሚጠበቅባቸው ለማሳሰብ:
Ø 3ኛ በሚቀርበው ሰነድ ሳይሳማሙ/ቅር የተሰኙ እንደሆነ ደግሞ ቅራሬ ይጣጡ በማለት ምእመናን ዕርቅ ለሚባለው ነገር ጀርባቸውን እንዲሰጡ የሚያነሳሳ: የሚያበረታታና ልባቸውን እንደ ፈርዖን ለማደንደን ሆነ ተብሎ ዕርቀ ሰላሙን ለማደናቀፍ የተዘጋጀ ጉባኤ ነበር::

ከዚህ ሁሉ ግርግር ጀርባ ያለው: የቀድሞ የውግዘት ቃለ ጉባኤ፤ የአሁንኑም የመደራደሪያ ነጥቦች/ሰነድ አርቃቂ፤ በግርግሩም የአንበሳ ድርሻ ተጠቃሚ ራሱ የቅዱሳን ማህበር ሲል የሚጠራውን የርኩሳን/የሰይጣን ማህበር "ማህበረ ቅዱሳን" መሆኑን ያልነቃ ሕዝብ ግን በዚህ ማኻል መጠቀሚያ ይሆናል ማለት ነው:: ግን እስከ መቼ? “እንግዲህ ከእነርሱ ጋር ተካፋዮች አትሁኑ፤ ቀድሞ ጨለማ ነበራችሁና፥ አሁን ግን በጌታ ብርሃን ናችሁ፤ የብርሃኑ ፍሬ በበጎነትና በጽድቅ በእውነትም ሁሉ ነውና ለጌታ ደስ የሚያሰኘውን እየመረመራችሁ፥ እንደ ብርሃን ልጆች ተመላለሱ፤ ፍሬም ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ፥ ይልቁን ግለጡት እንጂ፥ እነርሱ በስውር ስለሚያደርጉት መናገር እንኳ ነውር ነውና፤ ሁሉ ግን በብርሃን ሲገለጥ ይታያል፤ የሚታየው ሁሉ ብርሃን ነውና። ስለዚህ አንተ
የምትተኛ ንቃ ከሙታንም ተነሣ ክርስቶስም ያበራልሃል” (ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5: 7-14)::

ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
yetdgnayalehe@gmail.com
March 4, 2012
Tulsa, Ok

23 comments:

 1. እንዲህ በስምህ ዝባዝንኬህን ስትፅፍ ያምርብሀል ሙሌ እንደ ፓለቲካህ ዝባዝንኬ:: አንዴ ሰላም ፤ ተስፋ አንዴ ሉሌ ከማለት::
  አንድ ቀን ደሞ ዲ/ን የሚለውንም እንደምትጥለው ተስፋ አደርጋለሁ::

  ReplyDelete
 2. u r back mule. we expect ur no 2 book please make it fast

  ReplyDelete
 3. Minim Belu min beseferachihut kuna meseferachihu Ayikerim. Wunijelachihu kentuna Haset mehonun lemiyawuk sew min yahil tizibt lay endemitilachihu bitaweku endih ayinet neger atitsifum nebere gin min yihonal lebonachihu betilacha menifes siletemola tewu biluachihum atisemum temelesu biluachihum atimelesum Bich esu Egziabeher lib yistachihu. Yihen aynet Yetilacha menfes bewendimochachihu lay Yaderebachihu wedachihu ayidelem mikniyatun tawukutatachihu enawukewalen hizbum yawukewal Firdun leamlakachin setiten enitebikalen enji kenante ketifat lijoch gar yeminatefaw gize yelenim Kirisitina endih endinadereg alastemarechinimina. Yeamilakin sira sewun seytan malet kediabilos kalihone beker kemanim ayimetam. Egna "Mahibere kidusan" malet min malet mehonun,lemin yehe sim endetesetew sileminawuk yemitilut hulu haset endehone enawukalen.Litadenagirun atimokiru. Geta "Kesirachew tawukuwachewalachihu" endalen enantenim enesunim kesirachihu enawukachihuwalen.

  ReplyDelete
 4. deacon mulugeta please stop divion and
  ' tilacha" it is to much why do not see your self as a true christian insted of beleming others try to see your misteke you can not correct this way try and show love and respect for other

  ReplyDelete
 5. Ant tera mk neh lezam y keneya sedetegna tera abyotegna yzhe poltical organaziation element simpley ur bolock head. Mk be tom yedekemu menkosat sega belto, atentachew kortemo and bedemachew yaworaredal. More over, mk not .part of eotc moraly and ethicaly which now mk has collected $40 billon dollar on behaf of eotc due to finace law that is illegal. So, they used the money to kill our church fathers and terrist activity in Ethiopia to take power from one of first democratic gov. EPRDF. This day, all eotc followers understood long and short term of mk. Finaly, mk starting armed strugle too. So, now they take 100% reponsibilty for yegodana newte.

  ReplyDelete
 6. Aba Selama Tahnk you cery mache Ahat Tewahedo Yetsebalew Blogg March 26 2012 Lewaldiba gedam selfi witsu bilo mekeskes jemroal lemehonu Yehaymanot sew Mekera & Fetena Siyagatsimew Wede Man New Yemiselefew ? Wede Egizabher weyis Wede Embbassi _wekitu Ye subae mehonun enamnalei Tadiya Besenbet sewn sebisibo Wede Bet Kersityan Bemehed egizio malet sigeb Ke Kidase Askertito Ethiopian Embassi mewsed lehager Lewgen yitekmaln ? Melyayetin Ayabezawimin SEmonun Beyesamintu Sanday Washingiton D C St . Micaeil Church Megibya lay HIzibu Kekdase siwetsa kutsirachew 10 Weyim 12 yemihonu sewoch kedej honew Abune Fanueil Yinesu -ABa Melaku Yidemsesu Yemil Mefekir yasemalu enezih sewoch kirsityanoch nachew Tilalachihu ? Hayimanotis alachew ? betalku yesubae Gize wede fetseryachew Malkesi sile rasachew Hatsiat Manbat sigebachew LeKIdase yetesebeseben HIzib mebetsmbetsi mIn yibalal ?Menafikan - esilamochi lihonu yichilalu Andandoch Poletkegoch Mehonachewn enawkalen Zerzirachu asredug
  1 Selmaw selfi Lekirsityanoch Wede Man Mehon Neberebet ?
  2 Selfun Yemiyastebabirut Hayimanot yalachew sewoch nachew ?
  3 Beyesamintu sanday St Micaeil Yemibetsebitutin Poletikegoch Min EInadrgachew ?

  4 selamaw selfu lehagerna lehizib yemtsekmew MIn yahil new ?
  5 Bezih Selamaw selfi lay yemtsekemut eneman yimeslachihal ?
  6 Melyayetu ALbezam wey ?
  7 Menafikan -POletkegoch yelbetim wey ?
  8 Abune Merkorewos Abune Pawlos Yemil Mekefafel Ayhonim wey ?
  9 Menfesaw KOlej - MAhibere KIdusan Mebabals ?
  10 Dergina weyane -Ehapana Oneg-Hamilena GInbot yelubetim wey? Behulum BEkul Yemtigodaw Haymanote ( bete Kersityane nat )mels sitsubetna lemawk endichil

  ReplyDelete
  Replies
  1. 1.selamawi self mehon yeneberebet wode hailegnaw antena meselochih dekike diablos
   2.adelum. anten sayamakiru siladeregut, degimom endante lehodachew silaladeru kiristianoch ayidelun.
   3.BeZendow sim getsisachew.
   4.ende ayitekimim. anten yemesele yediabilos sew eyale le'ante mamelket neberebachewna.
   5.Ene aba ...
   6.yeteleyayen yemimeslachew yeteleyut nachew.
   7.Alubet.
   8.Yihonal
   9.hulum wunetikin new
   10.Alubet

   Delete
  2. kikikiki.... dink melse new gin kifun bekifu atikawomu yil alneber ende bible? yeteyakiwun cheguwara satlitew atikerim

   Delete
 7. Feri neh below mk atfera

  ReplyDelete
 8. የዛሬ ሃያ ሥድስት ዓመት አካባቢ አንድ የስምንት ዓምት ህፃን ልጅ በወቅቱ አርባዎች ውስጥ በሆነ ብሩክ በሚባል ሰው መጫወቻው ተይዞበት እንዲለቅለት በዙ ጊዜ እቤቱ ተመላልሶ ያጣዋል። ሌላ ሰው እንዳይሰጠው ደግሞ ብሩክ ያስቀመጠው በግራ እጁ ስለ ሆነ ማንም ዕቃውን አግኝቶ ሊሰጠው አልቻለም። ብሩክም እኔ እራሴ መክሬው ዘክሬው እሰጠዋለሁ በማለቱ፣ የልጁ ወሳጆች ደግሞ የልጃቸውን ዕቃ መመለስ በተመለከተ መሪር ለቅሶ በብሩክ ሥውር መልካምነት ጆሮ ዳባ ብለው ገና ትቀምሳታለህ ዓይነት አባሱበት፡; በዚያው ሰሞን የጌታችን ጥምቀት ስለነበረ የልጁ ወላጆች ግቢ ውስጥ ቅርጫ ታርዶ ለመከፋፈል ከታደመው ሰው መሀል የልጆች አባት ትልቁ ብሩክም ነበርና ከህፃኑ ጋር ፊት ለፊት ይተያዩ ጀመር። ታዲያ “የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳም” ሆነና ልጁ በአጋጠመው ተጠቅሞ ድምፅ ማሰማት ጀመረ፤ እንዲህ ሲል፥ አንቱ የሚለውን አንተ ብሎ “የብሩክ ስም ይቀየር” አለ። ሁሉም ጸጥ እንዳሉ ሥጋውን እኩል በማከፋፈል ያሉት በሬ አራጅ ሰው ብቻ ቢላቸውን እየሳሉ “ማን ልትለው ፈለክ ደግሞ” ብለው በመቀጠል “ልጅ ነገሮች በግልጽ ይታዩታል” አሉና ለልጁ “በል አዲሱን የብሩክ ስም ንገረን ዳቦም አያስፈልግ ጥሩ ጊዜ ነው።” ብለው ደስ የሚል እና ቅርጫ አራጅ የሚለውን ደግሞ አዲስ ስም እንዲሰይምላቸው የፈለጉ ይመስል ድምፅ እንዳይረብሸው ቢላ መሳሉን ቆም አደረጉለት፡; ህፃኑም “ለሰው ልጅ ስም መውጣት ያለበት አድጎ ተግባሩ በሚሠራው ሥራ እየታየ መሆን ነበረበት።” ብሎ በመቀጠል “ለምሳሌ እኔ እንዳልኩት ቢሆን ኖሮ የጋሼ ብሩክ ስም ጋሼ እርኩስ ይሆን ነበር።” ሲል ግማሹን አስቆ ሌላውን ደግሞ አስደንግጦ ከሁዋላው ነብር እንደተከተለው ፍየል ተፈተለከ። ስለዚህም የማህበረ ቅዱሳን ሥራ እየዋለ ሲገለጽ ትክክለኛ ስሙን ማግኘት ይገባዋል። ማህበረ ቅዱሳን ማለት ፍቅርን የማይወድ የፍቅር ቂመኛ፣ ጳጳስን ከጳጳስ፣ ቤተክርስቲያንን ከቤተክርስቲያን፣ ቄስን ከቄስ፣ ምዕምናን ከምዕምናን፣ ወጣቱን ከወጣት፣ቤተሰብን ከዘመድ፣ ሚስትን ከባል፣ ልጆችን ከወላጅ እና ሕዝብን ከሀገር እያጋጨ የሚሳለቅ የበግ ለምድ ለባሽ የተዋጣለት እርኩስ የደህንነት ድርጅት ነው። ብጹዐን ጳጳሳት በፍጹም እንዲታረቁ እንደማይፈልግ ከአባሎቹ ፉከራ ታውቋል። የእባቡ (የማህበረ ቅዱሳን ድርጅት) ጂራቱ ተቆርጧል፤ ጭንቅላቱ ነው አራት ኪሎ እና ስድስት ኪሎ የመሸገው። ለእርሱም የሚመለከተው ክፍል ጸሎቱን በሱባዔ ጀምሮለታል እናም በቅርቡ በራሱ አንደበት ማንነቱን ይፋ ሲያደርግ ተብትቦ የያዛቸውን በጎች ይለቃቸዋል። በጎቹም ሞቶ እንደተነሳ ያህል ለዓምላካቸው ይቅርታን በንሰሀ ይጠይቃሉ፤ እባቡንም ጭንቅላቱን ይቀጠቅጣሉ፤ ያን ጊዜ አባቶች በፍቅር ተሸንፈው ይታረቃሉ፤ በጎቹም (የአደራ ልጆቻቸውም) በለመለመው መስክ ምግቡና መጠጡን እንደልባቸው ያገኛሉ፡; ጊዜውም የዐብይ ጾም ወቅት ሰለሆነ እኛም በጸሎት ተግተን እናግዛለን፡; ወሥብኃት ለእግዚአብሔር።

  አንተ በለምድ የተሸፈንክ ማህበረ ቅዱሳን፣
  ወይም ልበልህ ‘አሳሳች ማህበረ ሰይጣን’ ፣
  በገዛ እጃችን ከማብዛት መከራን ፣
  ሞትን እናስተግድ ድምጻችንን ቀብረን፣
  የንስሀን ጊዜም አሟጠን ጨርሰን፣
  እሄው ቁጭ ብለናል ፍርድን እየጠበቅን፣
  አንተ በሄድክበት እኛም አልተከተልን፣
  ምክንያት በመፈለግ እየተጠቃቀስን፣
  እየተረዳዳን ጉድጔድ እየቆፈርን፣
  እርቀን ሄደናል መመለሻም የለን፣
  እዛው በፍርድ ቀን እንናገኛለን፣
  በጻድቃኖቻችን እየተስተናገድን፣
  ከናሺቭል ቴንሲ ፓስፖርታችን ይዘን፣
  አንተ ወዲህ ስትቀር እኛም እንገባለን፣
  መንገዱ እንዳይጠፋን በድንግል ታጅበን።

  ReplyDelete
 9. ዲ/ን ሙሉጌታ፦ በሕይወት ዘመንህ እጅግ ከባድ የልብ ሐዘን የፈጠረው ጉዳይ በብዙዎቻችን ላይ ያለ ጭንቀት ንው። ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ ቤት ሆና እያለች ብዙ የጎሳ ስም ሲሰጣት መስማታችን መንፈስን እጅግ ይረብሻል። ስለዚህ ጉዳይ መጸለይ ከሁላችንም ይጠበቃል፤ የስድብ ጋጋታውን ትተን ወደ እግዚአብሔር እናልቅስ።
  ጽሑፍህን ሳልዎድ በግዴ አንብቤ እንድጨርሰው ህሌናየ ገፍቶኛል። ገና ከመንደርደሪያው አንባቢን የማይስብ ሆኖ ነው ያገኘሁት። አይ አባ ሰላማ፤ ምነው ጽሁፎችን ለአንባቢ የሚመቹ እንዲሆኑ ጥረት ብታድርጉ። ይህ ጽሁፍ ገና ከእርእሱ አንባቢን ይዘጋል። ተጀምሮ እስኪያልቅ በጥላቻ መንፈስ የተሞላ ነው። አሁን ስለ እውነት አንድን የመንፈሳዊ ድርጅት “ነፍሰ በላ የፖለቲካ ድርጅት“ ብሎ መጥራት ከዲያቆን ይጠበቃል? እኔ የማኅበረ ቅዱሳን አባል አይደለሁም ሆኖም ግን ይህ ማህበር ከሚያሳትማቸው መጽሄቶችና ጋዜጦች በጣም ብዙ የኦርቶዶክስ ሃይማኖቴን የሚያለመልሙና መንፈሰ ጠንካራ የሚያደርጉ እውቀቶችን ገብይቻለሁ። ስለዚህ ዲያዎን እራስክን አስተቸህ።
  በሌላ በኩል ደግሞ ዶ/ር መስፍን ብለህ ስለጠቀስካቸው አባት ስንመጣ አሁንም ቁልጭ ያለ ቅራኔ በሳቸው ላይ እንዳለህ ነው የሚታይ፤ ወይም እሳቸውን ከማይወዱ ጋር በመሆን እነሱን ለማስደሰትና ትቂት የዶላር ኮቸሮ ለመለቃቀም ካልሆን በቀር ስለ ቀሲስ ዶክተር መስፍን እውቀት ምንም አታወጣላቸውም። ቀሲስ ዶክተር መስፍን በብዙ ቦታዎች ሲያስተምሩ እድሉ አጋጥሞኝ ማንነታቸውን ጠንቅቅቄ ተረድቻልሁ። በአንዲት ኦርቶዶህሳዊ ሃይማኖት የሚያምኑና በተቻላቸው መጠን ለአንድነት ከሚጥሩት አባቶች አንዱ አባት ናቸው ብል ማጋነን አይሆንም። በመሆናቸውም በውጭው አለም ላሉት “ተገንጣዮች“ ስለማይመቹ የተለያዩ ስሞች ይሰጡዋቸዋል። እውንቱ ግን እያደር ይጠራል።
  “ያልነቃ ሕዝብ ግን በዚህ ማኻል መጠቀሚያ ይሆናል ማለት ነው፥ ግን እስከ መቼ ?“ ብለህ ላልከው ጥያቄ መልሱን አንተ ታውቀዋለህ፥ አንተ መልሱን ብትመልስ ከስድብ ይልቅ እራስክን ለእግዚአብሔር አገልጋይ ለማድረግ ትጥር ነበር።
  በስብሰባው ላይ የሰማከውን ስትጠቅስ “ቅድስተ ቅዱስን ድንግል ማሪያም ጥንተ አብሶ አለባት፤ የአሳማ ስጋ ብሉ፤ በኦርጋን ዘምሩ፤ ሴቶች ከነወር አበባቸው ቤተ፡ ክርስቲያን ቢገቡ ችግር የለበትም” ይላሉ ሲል መረጃ አልባ ምንፍቅና የሚለውን ይዘረዝራል።“ ብለሃል። መረጃ ካስፈለገኽ አቡነ መልከ ጸዲቅን ወደ ኒውዮርክ ጎራ ብለህ አነጋር ከትምህረታዊ መረጃ ጋር ሊያስረዱህ ይችላሉ፥ አለዚያም ወደ ዩቲዩብ ድህረ ገጽ ጎራ ብል። መቸም አባታችን ቆመው ለሕዝብ ያስተማሩትን ላንተ አይከለክሉህም።
  ስለ እርቅ ጉዳይ ደግሞ፦
  ሀ. ለእርቅ ማን ከማን ነው ይቅርታ ሚጥይቀው?
  ለ. የትኛው አባት ናቸው ጥፋተኛ የሚባሉ? በማን?
  ሐ. ጥፋት ካለ ጠፋቱ የእኔ ነው ብሎ የሚቀበሉ የትኛው አባት ናችው?
  መ. ወደ ገዳም ከመግባትና በጸሎት መታገል ይልቅ ከእምነቱ ማዕከል ወጥቶ አሜሪካ መሄዱ ለምን አስፈለገ አሜሪካ ገዳም ነው?
  ሠ. ህዝብን ከማታለል በቀር ኣሁን የትኛው ኣባት ናችው ለእግዚአብሔር ተገዝተው ስልጣን ቁመው የሚለቁ?
  ረ. ሴኖዶስ ጉልበት ስለሌለው አይደለም ወይ ሐውልቱ እስከ ዛሬ የተገተረው?
  ሰ. ምእመን ጉልበት አጥቶ አይደል ፓትርያርኩ አሜሪካ በአሥራዎቹ የሚቆጠሩ አመታት ያሳለፉ?
  ሸ. የጥቅም ጉዳይ ሆኖ ነው እንጅ ለእግዚአብሔር የሚመቸውን ከቤተ ክርስቲያን በላይ የተቀመጡት ሳያውቁ ቀርተው ነው ሕዝበ ክርቲያን የሚተራመሰው?
  የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን አጣች እንዳይሆን እምነታችንን እንጠብቅ።

  ወስብሐት ለእግዚአብሔር

  ReplyDelete
  Replies
  1. take care brotheres from your normal way

   Delete
 10. ሰለአም አባ ሰላማዎች

  ReplyDelete
 11. Miskin Mulugeta,....I can see how you are crazy about MK achievements. Keep on writing fictitious MK's 'Gebena' as MK has been doing its job. One day you both of you will be asked what you have done by the Almight. Lerasih Ewoqbet, make sure that you have good job to answer in front of HIm. May God bless you to do better and may God bless MK to keep on doing its good jobs.
  tazabiw

  ReplyDelete
 12. አቡነ ተክለሃይማኖት ሰይጣንን እንዳመለኮሱት ገድሉ ይናገራል!!!!!!!!!!! ምናልባት ያ የመለኮሰው ሰይጣን ማህበረቅዱሳን የሚባለው ይሆን? ነው ወይስ ሰይጣን አቡነ ተክለሃይማኖትን ገዳም አስገብቶ አመለኮሳቸው? እርግጠኛ ነኝ ከሁለቱ አንዱ መሆን አለበት። ለነገሩ ሁለቱም ትክክል ነው ብትሉኝም ልክ ናችሁ

  ReplyDelete
 13. Ato Mulugeta (u don deserve respected "Dn."), Didn't we read ur "professional" article stating that two Synods should not agree? What happened now? Why u always zip out ur mouth when u hear/see MK? For that matter, u have identified urself now by posting ur poison on 'Devil House-Aba Selama blog' Enkuan ante weregnaw ena confused diaspora MK endehone Egziabher yemeseretew mahiber silehone ye Ghanem Dejoch aychlutim!Antena leloch Ekuayane Megbare Senay, wulude menafst erkusan gena Kidis Betekrstianin Dem Enba Taslekisalachihu! Gin Betekrstian atitefam, yeKirstos Bet yetsenach nech! Enantem enqura eyechehochihu kene ekuy migbarachihu meqabir tiwerdalachihu! Ayin aleh atayim, Jorom aleh kifu enji bego neger atisemabetim, Eji aleh tilachana hamet enji selamna fikir tsifo ayawkim. Enant yehiwot wulu yetefabachihu confused diasporas, lemin hagerachinina Betekrstianachinin letenegnaw atitewm? Edime likachihun siletilacha, silemekefafel temirachihu astemarachihu, ahuns aybekam? Hilina yemibal neger alfeterebihm, Mr. W/Gebrial? Eski mot saykedimih, and ken tesasteh enkuan bego neger asibeh mut. Egziabher endante yalu yetwulid atelawochin yastagisilin!

  ReplyDelete
 14. Ere Bakachihu bilachihu bilachihu Mqahber Kidusanin (MK) ke betekirstian gar mawedader jemerachihu ? ye Gehanem dej aychiluatim yetebalew be Nitsuh be Eyesus kirstos dem yetanetsechiwin betchirstian new enji le 1 mahber aydelem . yeh tilik alemawek bicha sayhon difret new. Ebakachihu sininager bemastewal yihun , sew hulugize le ewinet yikum ,MK band weket melkam yenebere mahber endenebere awkalew , ahun gin ende 1 Kirstosin yemiyawik mahber sayhon , ende tera mangnawim mahber besiga ena bedem bicha yemyadergewin erucha alwededkutim , lezim new sewin hulugize mekses , yesew sim matfat , abatochin menkef yehuligize sirachu yehonew . yihinin sil gin mahberu (MK)diro yemiyadergewin bego neger bicha eskahun bemaseb negerochin saymeremiru ahunim endediro mesluachew beyewahinet yemidegfu bizu abalat alu. Eg/r endiyastewluna le Mahber sayhon le ewinetegnawa betechirstian enditkomu esu yirdachihu !! sew be 1 mahber sir teketarim bihon or beteleyaye mikiniyat ke mahberu gar gingnunet noren beminiseraw sira yemnagegnew tikim binor enkuan , lik yalhone neger mahberu sisera eyayen bechifin kemedegef ewinet kehonew ke Eg/r komen , Bilishu yehonewin astedader mastekakel yishalal . Eg/r Abatachinin be Ewineteina be Menfes endinagelegilew yirdan !!

  ReplyDelete
 15. ወንድሜ ውሸት በእግዚአብሔር ዘንድ እንደማይወደድ አታውቅምን? ፈጣሪ አርቆ ማሰቢያ አእምሮ ይስጥህ፡፡

  ReplyDelete