Tuesday, March 27, 2012

ወደ መንግሥተ ሰማያት የይለፍ ፈቃድ - እንደ ገድለ ተክለሃይማኖት መጽሐፍ - - - Read PDF

የገድለ ተክለ ሃይማኖት ጸሐፊዎች ዋና ዓላማቸው ሕዝቡ በክርስቶስ በመድኃኒታችን አምኖ የዘላለም ሕይወት እንዲያገኝ ሳይሆን በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የሰይጣንን ፈቃድ ለማሳካት የተነሡ መሆናቸውን ጽሑፋቸው ያጋልጣቸዋል።
«መንፈቀ ሌሊት በሆነ ጊዜ ኢየሱስ ክርስቶስ ሚካኤልን በቀኙ፤ ገብርኤልን በግራው አድርጎ እናቱ ማርያምን 12ቱ ሐዋርያትን ከእርሱ ጋር ይዞ ብዙዎች የሰማይ ሠራዊትን አስከትሎ ወደ እርሱ (ተክለ ሃይማኖት) መጣ እንዲህም አለው። «በዓልህን የሚያከብር በእንጀራም ቢሆን በዕጣንም ቢሆን በመሥዋዕትም ቢሆን እስከ ጥሩ ውኃ ድረስ ስምህን የሚያስጠራ ሁሉ ባንተ ስም እንግዳ ቢቀበል በግልጽ ወደ መንግሥተ ሰማያት ይለፍ . . . ስምህ በተጠራበት በገዳምም ቢሆን በዓለምም ቢሆን እስከ ዘላለም ይቅርታና ቸርነት ከዚያ ይኑር በእውነት ያለ ሐሰት . . . » ይላል (ገድለ ተክለ ሃይማኖት ምዕ 39፥2-6)
እንደ ገድሉ ጸሐፊዎች ኃሳብ  መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሁሉ ወደ መንግሥተ ሰማያት ለመግባት በተክለ ሃይማኖት ስም እንግዳ መቀበልና እንጀራና ዕጣን መስጠት ይገባል ብሎ አስተምሯል ማለት ነው። ሆኖም ለአነዋወሩ ነቀፋ ለንግግሩ ሐሰት ለትምህርቱ ስሕተት የማይገኝበት በእኛ ሥጋ ለመዳናችን ሥራ ሲል በሥጋ የተገለጠው የእግዚአብሔር ልጅ በሰውነቱም የሰው ልጅ የተባለው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ ብሎ አስተምሯል ማለት በእርሱ ላይ ስድብ እንደመናገር ይቆጠራል።  በየትኛውም ትምህርቱ ጻድቅ እየተባሉ በተጠሩ ሰዎችና መላእክት ስም በሚደረግ ስጦታና በዓል ማክበር መንግሥተ ሰማያት ይገኛል ብሎ አላስተማረም።
እንዲያውም ጌታችን ወደ አባቱ ከማረጉ በፊት በዚህ ምድር በነበረበት ጊዜ ሲያስተምር «መንግስተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ» ብሎ (ማቴ 4፥17) መግቢያ በሩ እኔ ነኝ በእኔ የማይገባ እርሱ ሌባ ነው አለ እንጂ በተክለ ሃይማኖትና ቅዱሳን እያልን በምንጠራቸው ሰዎች ሆነ በመላዕክት ይቻላል አላለም።
ከተከታዮቹ አንዱ ፊልጶስ ወደ አብ ለመሄድ መንገዱን እንዲያሳየው በጠየቀው ጊዜ መድኃኒታችን ሲመልስ «እኔ መንገድ ነኝ . . . በእኔ ካልሆነ በስተቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም» በማለት ተናግሯል። (ዮሐ 14፥6)
ምሥጋና ገንዘቡ የሆነ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይክበር ይመስገንና ለደቀ መዛሙርቱ ሲያስተምር በሕይወተ ሥጋ ሳሉ ለወንጌል አገልግሎት ሲሄዱ ወንጌልን ሲያስተምሩ ስለሚቀበሏቸው ሰዎች የተነገረ በስሜ እናንተን የተቀበለ እኔን ይቀበላል በስሜ ጥሩ ውኃ ያጠጣ ዋጋው አይጠፋበትም አለ እንጂ (ይህም ቢሆን ደቀመዛሙርቱ በሕይወተ ሥጋ ሳሉ ለወንጌል አገልግሎትም ሲዞሩ ለሚቀበሏቸው ነው) በሰዎች ስም እንግዳ የተቀበለ ወደ መንግስተ ሰማያት ይለፍ ብሎ አልተናገረም። እንዲያውም «የምታደርጉትን ሁሉ በስሜ አድርጉት» ተብለን ሳለ «በስምህ (በተክለ ሃይማኖት) ስም ብለው በመተካት የጌታን ስም ለማስረሳት ብዙ ጥረዋልና ትምህርታቸው  እስከዛሬ ፀረ ወንጌል የሆነው ለዚህ ነው።
ጸሐፌ ገድለ ተክለ ሃይማኖት ግን ጌታችን የተክለ ሃይማኖትን በዓል የሚያክብርና በስሙ እንግዳ የሚቀበል ያለምንም ችግር ወደ መንግሥተ ሰማያት ይለፍ የሚለውን ትዕዛዝ አስፍሯል። ይህም ምን ያህል የወንጌሉ ተጻራሪ እንደሆኑ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው።
ገድል ወይስ ገደል ከተሰኘው መጽሐፍ የተወሰደ።
የወንጌል ብርሃን የበራላችሁ የቤተ ክርስቲያን መሪዎችና መምህራን። በእውነት እዳ አለባችሁ። እንደዚህ አይነቱን አሳፋሪና የቤተ ክርስቲያናችንን አንገት የሚያስደፋ እንዲሁም የምዕመናንን አእምሮ የመረዘ ኑፋቄ ተጣርቶ እንዲወጣና ምዕመናን እንዲያውቁ ብታደርጉ እንዴት ቤተ ክርስቲያናችሁን በጠቀማችሁ? የወንጌልን ሀሳብ በተረዱና እንዲሁ በጭፍን የቤተ ክርስቲያን ጠበቃዎች ነን በሚሉ የቤተ ክርስቲያን ልጆችን መካከል መለያየትን እየፈጠረ ያለው እንዲህ አይነቱ ኑፋቄ መሆኑን እያወቃችሁ ዝም አትበሉ። እግዚአብሔር ያያል።

21 comments:

 1. unless the orthodox church reject this fiction and others from the church, lord Jesus will never ever be with us.

  ReplyDelete
 2. If Lord Jesus is not with you since you accept the intercession of saints, it is your choice to ask Lucifer to pray for you because if any one hates the saints of God he/she is not from the side of God. Is there any document on the Bible which tells us to hate saints? from where did you get such knowledge.
  What is your comment about the words of God that says"BEDEKE MEZIMURE SIM KEZIKAZA WUHA YESETE WAGAW AYTEFABETIM. MATEWOS 10.? TSADIKANIN YEMITELU YITSETSETALU ON MEZIMURE DAWIT? Lib kalachihu bemetsihaf kidus temeru. Lib kelelachihum amlak endisetachihu tseliyu.

  ReplyDelete
  Replies
  1. they already says something for ur question.plz read it again.ለደቀ መዛሙርቱ ሲያስተምር በሕይወተ ሥጋ ሳሉ ለወንጌል አገልግሎት ሲሄዱ ወንጌልን ሲያስተምሩ ስለሚቀበሏቸው ሰዎች የተነገረ በስሜ እናንተን የተቀበለ እኔን ይቀበላል በስሜ ጥሩ ውኃ ያጠጣ ዋጋው አይጠፋበትም አለ እንጂ (ይህም ቢሆን ደቀመዛሙርቱ በሕይወተ ሥጋ ሳሉ ለወንጌል አገልግሎትም ሲዞሩ ለሚቀበሏቸው ነው) በሰዎች ስም እንግዳ የተቀበለ ወደ መንግስተ ሰማያት ይለፍ ብሎ አልተናገረም። dont u understand this?GOD gives u a bright mind.(born again CHRISTIAN)

   Delete
  2. በዚህ ጉዳይ ላይ ብዝ ጥቅሶችን ጠቅሼ ልጽፍልህ/ሽ የምችል ቢሆንም አንተ/ቺ እንዳልከው/ሽው “በሕይወተ ሥጋ እያሉ መቀበል ነው::” ባልክበት/ሽበት በዚሁ በማቴዎስ 10 ላይ |”በደቀ-መዝሙሬ ስም ቀዝቃዛ ዉሀ የሰጠ ዋጋው አይጠፋበትም ይልብሃልሳ/ሻልሳ፡፡” በስማቸው መመፅወት መቼም በሕይወተ ሥጋ ዕያሉ ብቻ ነው ልትል/ይ አትችልም/ይም ምክንቱም እንኳንስ ቅዱሳንና በዚህ ምድር እንኳ መልካም ሥራ የሠራ የማንም ሰው ስም ከሞት በኋላም ቢሆን ይጠራልና፡፡ እግዚአብሔር ስለቅዱሳኑ ሲናገር “በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ለዘላለም የማይጠፋ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ” ብሎ እንደተናገረ እንኳንስ በህይወተ ስጋ እያሉ ቀርቶ በአጸደ-ሥጋ እያሉም ቃልኪዳኑ የማይታጠፍ ለመሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ምስክር ነው፡፡ እናንተ የመጽሐፉን ቃል ለራሳችሁ እንደሚመቻችሁ እያጣመማችሁ ከመተርጎም ተቆጥባችሁ በትህትና የቀደሙ አባቶቻችን ያስተማሩትን መልካሙን መንገድና እውነት ብትከተሉ መልካም ነበር፡፡ እስቲ አምላክ ልብ ይስጣችሁ አሜን!!

   Delete
 3. It is a part of mk religon not eotc. Guys undersood mk and eotc two differnet relion.

  ReplyDelete
 4. min yigermal yihenin tsega yestachew eko kiristos eyesus new "bene yemiyamin ene kemadergw belay yadergal" yihe yegeta kal bemefetsemu lemin taznalachu ebakachu yamenachu hunu.

  bekidist betekirstian lay kifu atadrigu "kifu yemiyadergu bekifu yitefalu"

  geta lib yistachu

  ReplyDelete
 5. matewos 10:40-42 kegedlu befit krestos bene sem sayl bedeqemezmer sem tterign wuha yateta mengeste semayat endemigeba tenagrual wengelu::astewul krestos bewengelu yalew beterign wuha betsadeq bedeqemzmur mestet megstesemayat endemigegn

  ReplyDelete
  Replies
  1. KA...KA...KA....KENTU TERET,JOK,KELD.YETGNAW BIBLE NEW BAKIH YANEBEBKEW?CAN U TELL ME WHERE DID U FINE IT?

   Delete
 6. look my brother with attention,Jesus Christ said that if some one gives a cup of water in the name of disciple(saints,prophets,Apostles,martyrs),he/she will get the kingdom of GOD(Matewos 10:40-42.then,what is new in the Gedle Tekle Haymanot?don't you believe in the word of Jesus who said in Mathewos 10:40-42

  ReplyDelete
 7. petros,siamrih yibaj. unknowingly you said God will never be with you.We worship our God and respect His saints!!!Ersu yakeberachewun man Yikesachewal!!!libona yistachihu!!!WEde betachihu temelesu,bebetachin honachihu yesew atkelawutu.

  ReplyDelete
 8. ማንነታችንን አስረዱኝ?

  ይህንና ይህን በመሰሉ በርካታ ጸረ ወንጌል የሰይጣን ድርሰቶች ቤተ ክርስቲያናችን ተሞልታ እያዬን አለማመናችን ታውረን ወይስ ከሰውነት ባሕሪ ውጭ ሆነን ነውን? ወይስ ዓይናችንን ግንባር ያድርገው በማለት ይባስ ብሎ ለነዚህ መጽሐፍት ጠበቃ የምንቆመው እስከመቼ ድረስ ይሆን? በአምላካችን አምሳል የተፈጠርን ስለመሆናችንና የሚያመዛዝን አእምሮ ያለን ስለመሆኑ እየተጠራጠርኩ ስለሆነ እባካችሁ ይህ ማንነታችን ከየት እንደመጣ ብታስረዱኝ??

  ፓለቲከኞቻችን ወጣ ወጣና እንደ...ተንደባለለ እንደ...ከመሆናቸው አልፎ በጥላቻና በቂም የተመሰርተ ፓለቲካ ሲሆን: ኢኮኖሚያችን በዓለም አቀፉ ማህበረስብ ፊት የድሃነት ዋና ምሳሌ ሲያስደርገን: በመካከላችን ያለው ማህበራዊው ግንኝነታችን በመንደራችን ዙሪያ ብቻ ሲያጠነጥን: የክርስትና ሃይማኖታችን ኢክርስቲያናዊ ሲሆንና የልዩ ወንጌል ባለቤቶች ሲያደርገን በማንነታችን ላይ አንድ ብቻ ሳይሆን በርካታ ጥያቄዎችን እንድናነሳ ያስገድዱናል:: ለዚህም ነው ግራ ቢገባኝ ስለማንነታችን አስረዱኝ የሚል ጥያቄ ውስጤን ያጫረው??????????????????????????????????????????????

  ለዚህ ሁሉ ችግራችን ምንጩ እንደነዚህ ባሉ መጽሐፍት የጽድቅ ጠላት በሆነው ሰይጣን የተሽፈነፈነውና የተበረዘው መንፈሳዊ ሕይወታችን ስለሆነ ለሁልንተናዊ መፍትሄ በሚሆነው በዚህ ዋና ችግር ላይ የመጀመሪያ እርምጃ ብንወስድ ብልህነት ነው:: ይህ ከሆነ በነጻነት የሚኖርና በአምላኩና በራሱ የሚተማመን ሕብረተስብ መፍጠርና ፓለቲካውን በትክክለኛ ቮት ኢኮኖሚውን በንጹህና ትጋት በተላበሰ እውነተኛ ሥራ ማህበራዊ ግንኙነታችንን በእውነተኛ የወንድም ፍቅር በማሳደግ አዲስና እውነተኛ ታሪክ ማስመዝገብ ከመቻላችን በላይ በዓለም ገጽታ ያለንን አሳፋሪ ስማንን ማደስ እንችላለን:: ለዚህ ዋናው መነሻ ደግሞ እያንዳንዳችን ያስተሳሰብ ለውጥ ለማስመዝግብ ከራሳችን ብንጀምርና ከዚያም ወደጓደኛና ወደሰፈር እያለ ወደማህበረሰቡ ማዝመት ይቻላል:: እንኳን መልካም ነገር ወረርሽኝ ሳይቀር ይዛመት የለ??

  እስቲ ሞኝነት በሚመስል ነገር እንዲህ በማለት እንጀምር:

  እኔ___ሌ ከዛሬ ጀምሮ ለአገሬ ለወገኔና ለቤተክርስቲያኔ እውነተኛ ለውጥ እንዲመጣ ንግግሬን አካሄዴን አስተሳሰቤን አመለካከቴንና አእምሮዬን አስፍቼ መልካምና ሁለንተናዊ ለሆነ ለውጥ እራሴን በመግዛት የበኩሌን ድርሻ ለመወጣት ቃል እገባለሁ:: ይህንንም በቤቴ በሰፈሬና በደረስኩበት ሁሉ ለማዳረስ እተጋለሁ:: ለዚህም የምህረትና የፍቅር አምላክ ይረዳኛል ብዬ አምናለሁ:: አሜን:: በማለት ከራሳችንና ሁሉን በሚያይ አምላክ ፊት ውል እንፈርም::

  እግዚአብሔር በቃሉ ኃይል ማንነታችንን ቀይሮ ያሳውቀን:: አሜን::

  ሰላም ሁኑልኝ

  እህታችሁ

  ሰላም ነኝ

  ReplyDelete
 9. selam bekrestos selam yagegnuten tsadqannm temelech;bepoltika,beikonomi,wezetz...yalshiw,esti yitaysh areboch islamoch ferenjoch endih bepoletikaw,beikonomiw yamarebachew ende wengelu,ende qalu ende krestos feqad eyehedu selehone new wey????????

  ReplyDelete
 10. ሠይፈ ገብርኤልMarch 28, 2012 at 6:50 PM

  ርዕሱን ሳየው ልክ የሉተር ጥያቄ የተነሳ መስሎኝ ነበር ፡፡ እሱም የዛሬ 5ዐዐ ዓመት ገደማ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የመንግሥተ ሰማያት መግቢያ ቁልፍና ካርድ እያለች ስትሸጥ ያንን በመቃወም ይህንን የመሰለ ጥያቄ በማቅረብ ነበር አመጽ የጀመረው ፡፡ የእናንተ ጥያቄ ግን የወንጌልን ቃል እንደራሳችሁ ትርጓሜ በመረዳት ሆኖ ነው የአገኘሁት ፡፡

  የቃላት ትርጉም ፡፡
  ጻድቅ ፡- በሕግ የጸና ፣ እንደ እግዚአብሔር ሕግ የሚኖር እውነተኛ ሰው ፡፡ አካሄዳቸውን በእግዚብሔር ፊት በማድረግ ኃጢአትን ላለመፈጸም የሚታገሉና የሚደክሙ ሰዎችን ያጠቃልላል ፡፡

  ቅዱሳን ፡- ለእግዚአብሔር የተለዩ ምርጦች ፣ ንጹሓን ፣ ብሩካን የሆኑ ፣ ከሰዎች መሃል እምነታቸውን በእግዚአብሔር አድርገው ፣ ራሳቸውን ሙሉ በሙሉ ለእርሱ ግልጋሎት አሳልፈው የሰጡ ናቸው ፡፡ ለእግዚብሔር ምርጥ ዕቃዎች በመሆን ዓላማውን ፣ ዕቅዱን እየኖሩ ወገኖችን በማስተማር ወደ እግዚአብሔር እንዲቀርቡ ያተጋሉ ፡፡ ቅዱሳን የሚመስሉት ፣ ለመሆን የሚታገሉትም ክርስቶስን ነው 1 ቆሮ 11፡1

  የመጽሃፍ ቃል ፡
  ስለተመረጡት ቅዱሳን ሲናገር ሮሜ 8፡29-30 ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤ አስቀድሞም የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ ጠራቸው፤ የጠራቸውንም እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው፤ ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞ አከበራቸው ይላል።

  የተመረጡት ሰዎች ፣ እምነታቸው በአንዱ በክርስቶስ ስለሆነ እርሱ የሚያደርገውን ብቻ ሳይሆን ከዛም የሚበልጠውን መፈጸም እንደሚችሉ መጽሐፍ ይናገራል ዮሐ 14፡2
  እምነት ላለው የሚሳነው ነገር የለም ማቴ 17፡2ዐ
  ቅዱሳንን መቀበልና ማስተናገድ ፣ በጻድቃንና በቅዱሳን ስም መዘከር ዋጋ እንደሚያሰጥ ጌታ ተናግሯል ማቴ 1ዐ፡4ዐ ፡፡ አበበ ወደ እኔ ቤት ወንጌል ሊያስተምር ቢገባ ስለአበበ እያልኩ ምሳ እንድጋብዘው ውሃም እንዳጠጣው አያዝም ፡፡ ስለጻድቃኖችና ስለቅዱሳኖች ስም በማለት ለደቀመዝሙር መልካም አድርጉ ነው የሚለን ፡፡

  እግዚአብሔር ለጻድቃኑ የቸረውን ጸጋ ፣ እንክብካቤውንም በጥበብ ለምትመረምሩ የሚከተለውን እነድትመለከቱና እነድታሰላስሉት እጠይቃለሁ ፡-
  1.እራፊ ጨርቅ ባህርይውን የሚቀይርበት ምንም ጥበብ የለም ፡፡ ታዲያ ከኤልያስ የተገፈፈው ጨርቅ ስለምን ውኃ ሊከፍል ቻለ? 2 ነገ 2፡14 ፤ የጨርቅ አምልኮ በኤልሳዕ ለመፍጠር ?
  2.የጳውሎስ ጨርስ ድውያንን ስለሚፈውስ ከልብሱ እራፊ ይወስዱ ነበር ሥራ 19፡12 ፡፡ በእራፊ ጨርቅ ኃይል ማመንስ ስለምን ከወንጌል የሚያረቅ የጣዖት አምልኮ አልተባለና አልተወገዘም ?
  3.ውሃ ውስጥ ጨው መጨመር ጣዕሙን ይቀይር እንደሁ እንጂ ሌላ የምናውቀው ነገር አይፈጥርም ፡፡ ታዲያ ኤልሳዕ ጨው ስለጨመረበት ስለምን እስከ ዛሬ ድረስ የተፈውሰ ጤናማ ውሃ ሆነ ተባለ ? 2 ነገ 2፡2ዐ-22 ፡፡ ሰው በጨው እንዲያመልክ ተፈልጐ ይሆን ?
  4.እንኳን በድን ፣ በህይወት ያለነውም ብንሆን ሙትን ማስነሳት አንችልም ፡፡ ታድያ የኤልሳዕ የገላው ፍራሽ የሆነው አጥንት ስለምን ምክንያት ሙትን አስነሳ? 2 ነገ 13፡21 ፡፡ ይኸ ታምርስ ተፈጠመ በማለት የተጻፈው በኤልሳዕ አጽም እነዲመለክበት ተፈልጐ ይሆን ?
  5.ያልሰለጠነ ቀርቶ የሰለጠነ እንስሳም ቢሆን የሰውን ቋንቋ መጠቀም አይችልም ፡፡ ታዲያ አህያዩቱ ስለምን ምክንያት ከበለዓም ጋር በስርዓቱ ውይይት ማድረግ ቻለች ዘኁ 22፡23-31 በለዓም ወደ አህያ አምልኮ እነዲገባ ታስቦ ወይስ ሌላ ?

  ስለዚህ ዛሬም መጽሃፍ የሚለውን እናስተውል እላለሁ ፡፡
  1 ሳሙ 16፡7ሰው እንዲያይ እግዚአብሔር አያይምና ፤ ሰው ፊትን ያያል፥ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል አለው።

  አመሰግናለሁ

  ReplyDelete
  Replies
  1. TEKLEHAIMANOT EGZIABHERN YAMNAL ANTE GIN TEKLEHAIMANOTIN TESFA TEDERGALEH YIH NEW LIYUNETACHIHU.YEWENGELUNA YANTE MESELOCHU EMNETACHIHU.NEGE DEGMO ANTEN YEMIAMELKU LIJOCH TAFERALACHIHU.MIN ENADIRG YE'ETHIOPIA BEREKET YETEYAZEW KEWENGEL YEMIAWETU BIZU TERETOCH BEYEKENU SILEMITERETU NEW.GOD PLZ FORGIVE US?AND GIVE US THE LIGHT OF GOSPEL?IN UR BEGOTTEN AND BELOVED SON JESUS CHRIST OF NAZARETH.(BORN AGAIN CHRISTIAN)

   Delete
  2. ሠይፈ ገብርኤልMarch 29, 2012 at 9:22 AM

   ከላይ ከገድል መጽሐፍ ተገኘ ተብሎ የቀረበው ጽሁፍ የሚለው በተክለ ሃይማኖት ስም የሚሠራ ምግባር /በማቴዎስ ወንጌል የተሰጠውን ተስፋ/ የሚያስገኘውን ትሩፋት ይናገራል እንጂ በተክለሃይማኖት አምልኩ ፤ እኛም በተክለሃይማኖት እናመልካለን አላልንም ፡፡ መልካም ምግባርን በጻድቅና በቅዱሳን ፣ በደቀመዝሙር ስም ያደረገ ዋጋው አይጠፋበትም ስለተባለና በኢየሱስ ክርስቶስ ስለታወጀ ያን ለመተግበር እንታገላለን ፡፡ ማክበር ማለት ማምለክ አይደለም ፤ በስማቸው መዘከር ማለትም ማምለክ አይደለም ፡፡ ማክበር ፣ መዘከርና ማምለክ ምንም ዝምድና የላቸውም ፡፡ ያልተረዳኸኝ ስለመሰለኝ ለመግለጽ ሞከርኩ ፡፡

   ለምን ወደ መንግሥተ ሰማያት ያስገባል ተባለ የሚለው ከሆነ የሚየደናግረው ፤ ጌታ ራሱ በስማቸው ከዘከራችሁ የጻድቁን ዋጋ ፣ የደቀ መዝሙሩን ዋጋ ፣ የቅዱሳኑን ዋጋ ታገኛላችሁ ስላለንና ፣ የጻድቃን የሚገባ ስፍራቸውና ዋጋቸው ደግሞ መንግሥተ ሰማያት ስለሆነ በተክለሃይማኖት ስም የሚደረገውም ያንኑ ያልተቀናነሰ ዋጋ ያገኛል ተባለ ፡፡ ስናነበው ስህተት ቢመስልም ፣ በስሌት ስንገነዘበው ግን ትክክል ፣ ያልተጋነነ ፣ የወንጌልን ቃል ያላፈረሰ ነው ፡፡ ቅዱሳኑ በእምነታቸውና በምግባራቸው መንግሥተ ሰማያት ከገቡ ፣ እኛም በአብ ወልድና መንፈስ ቅዱስ አምነን ፣ ወንጌል ፈጽሙ ያለውን በተቻለን ከፈጸምን ፣ እንደ ተስፋ ቃሉ መንግሥተ ሰማያት እንገባለን ብለን ተስፋ እናደርጋለን ፡፡ በቅዱሳን ፣ በጻድቃን ፣ በደቀመዝሙር ስም መዘከር ማለት አምልኮ መቀየር አይደለም ፡፡

   አመሰግናለሁ

   Delete
 11. All waldeba monk better to move for hedase dam work.

  ReplyDelete
 12. ትጋትህ እጅግ ለሚያስገርመኝ ለወዳጄ ሰይፈ ገብርኤል:

  በመጀመሪያ ደረጃ በሕይዎት ጉዳይ ላይ ነጋ ጠባ መተጋተግ ከምትችል ታናሽ እህትህ ጋር አመሳስለህ እኔንም በዚያ የፍቅር ዓይን እንደምታየኝ ስለቆጥርከኝና እንደ ቤተሰብ ስላየኸኝ አንቱታውን ለመጨረሻ ረስቼ አንተ እንድልህ ልቤ በወንድምነት ፍቅር ተቀብሎ ስላጸደቀልኝ በዚህ ማእረግ እንድጠራህ ፍቅድልኝ???

  በዚህ መሰረት ውድ ወዳጄ ሁላችንም ባንሆን ብዙዎቻችን ይህን ያህል ጊዜ ወስደን የምንጽፈው እንደ እኔ እምነትና ግምት ሕዝባችን/አገራችን እና ቤተ ክርስቲያናችን ወደ አንድ ወጥ ወደ ሆነና ተወዳዳሪ ወደ ማይገኝለት የመድሃኒታችን እውነት ላይ ብቻ ደርሰው ማየት ስለምንፈልግ ይመስለኛል ደግሞም ነው::

  ታዲያ ያንተም የእህትህም የእኔና የሌሎች መሰል ወገኖቻችን ሃሳብና ዓላማ ይህ ከሆነ ልዩነታችን እንዳየሁት ዋና ባልሆኑና ለሕይወት ዋስትና ሊሰጡ(ከጌታ በቀር የለምና)በማይችሉ ነገሮች ላይ ያተኮረ ነው:: ለምሳሌ በአጸደ ሥጋ ስለማይኖሩና ሃላፊነታቸውን ተወጥተው ስላረፉት ቅዱሳን ጉዳይ ጉንጭ አልፋና የሚሰለች ክርክር ስናደርግ እንታያለን:: አዎ ሁሉን ፈትኑ የሚጠቅማችሁን ያዙ ብንባልም በማይጠቅም ነገር ላይ ጊዜ ማባከኑ ደግሞ ሞኝነት ይመስለኛል:: እስቲ ለምሳሌ እንውሰድና ቅዱሳን እንዲህ ናቸው:: የሸዋው ተክልዬ እንዲህ ነበሩ ከሚለው ታሪክ ጠንካራ ጎኑን(የታሪኩን) ወስደን ልንጽናናበትና ልንበረታ የምንችልበት ትምህርት መያዝ እንችላለን:: ነገር ግን ለመዳናችን ዋናና መተኪያ የሌለውን የመስቀሉን ሥራ ሊተካልን ፈጽሞ አይችልም:: ምናልባት ታዲያ ታሪካቸውን በታሪክነት ፈርጀን ለማያዝ ብንሞክርና የቤተ ክርስቲያን ዋና ሥራ በሆነው የማዳን ወንጌል ላይ ወይም ለዚህ ብሎ ከሰማይ ክብሩን ትቶ ለመጣውና በመስቀል ላይ ተፈጸመ በማለት ሥራችንን ሁሉ በሠራልን ብቸኛ አዳኝ ላይ ዓይናችን ቢተከል ምን አለበት እጅግ አትራፊዎች እንሆናለንና በዚህ ብንበረታ?????

  የማከብርህ ሰይፈ ገብርኤል!!! እስቲ በእውነት እንነጋገርና ከዚህ በላይ እንዳሰፈርከው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በጻድቃን ስም ማለትም ስለ ተክለሃይማኖት ስለአቡዬ ስም ብላችሁ ዘክሩ ብሎ አስተምሯል?? እስቲ በሞቴ በቃሉ የተናገረውን ከመጽሐፍ ቅዱሳችን በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ አብረን በመሆን በጥሞና እንድናየው እጠይቀሃለሁ?????

  1)"እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል......ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ
  ይወስዳል ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል::"
  (ማቴ 10:40-41) = * ይህ ማለት እኔ እንደገባኝ ለምሳሌ አንተ
  ሰይፈ ገብርኤል ነቢይ ብትሆንና(ጌታ አድሎህ ቢጠራህ)ወደ እኔ ቤት ብትመጣ የአምላክ
  መልክተኛ ነቢይ በመሆንህ ብቻ ብቀበልህ ያንተን ዋጋ ተመጣጣኝ አገኛለሁ ማለት እንጂ
  ስለ ሰይፈ ገብርኤል ብዬ እንደዘክር ማለቱ አይደለም::

  2) "ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ላንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻ በደቀ መዝሙ ስም የሚያጠጣ
  እውነት እላችኋለሁ ዋጋው አይጠፋም::" (ማቴ 10:42)
  *** ይህ ማለትም ከነዚህ ከታናናሾቹ ላንዱ(ባጠገቡ ለነበሩት)የእኔ ደቀ መዝሙር
  ስለመሆናቸው አውቆና ለይቶ የሚያስፈልጋቸውን (ለምሳሌ ውኃ) ቢሰጣቸው ዋጋው
  በእኔ ዘንድ አይጠፋም ማለቱ እንጂ በስማቸው ቢያደርግ ማለቱ ፈጽሞ አይደለም::
  ደግሞም በ10:42 ላይ የተጠቀሰ ስም የለም:: በደፈናው በደቀ መዝሙር ስም ማለትም
  ደቀ መዝሙር በመሆኑ ብቻ::

  እስቲ ለበለጠ መረዳት (ማቴ 18:5); (ማር 9:37); (ሉቃ 9:48); (ሉቃ 10:16)
  (ዮሐ 13:20); (ማቴ 25:40); (ማር 9:41) በመንፈስ ቅዱስ እርዳታና ከውድ እህትህ ጋር ሁነህ በጥሞና ተመልከታቸውና በእውነት የተረዳሃውን በፍቅር ብትገልጽልኝ??? ለሁሉም ግን የቃሉ ባለቤት ይርዳን:: አሜን::

  እኔ ግን ከመጽሐፍ ቅዱስ ትክክለኛ ትርጉም ውጭ በሆነ "በዝክር" ቤተ ሰቦቼ(የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያናችን ምእመንና የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ) እንዴት እንደደኸዬ ሳስብ እጅግ እጅግ ይቆጨኛል::

  እግዚአብሔር ማስተዋልን ይስጠን!!!

  የቃሉ ብርሃንም ሁላችንንም ያግኘን:: አሜን::

  ሰላም ሁኑልኝ

  የማከብራችሁና በጌታ የምወዳችሁ

  እህታችሁ

  ሰላም ነኝ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሠይፈ ገብርኤልMarch 31, 2012 at 8:58 AM

   እግዚአብሔር ቢጤዬን ሰጥቶ ለዚህ የቤተሰብ ምክክር ቀን ስላደረሰኝ ይክበር ፣ ይመስገን ፣ ስሙም ከፍ ከፍ ይበል እላለሁ ፡፡
   አጻጻፌ ውስጥ የማይመለከትሽን አይመለከተኝም እያልሽ እለፊው ፤ እኔ ለአንቺ ብቻ ሳይሆን ለሚያነበው ሁሉ እንዲሆን ነው ያዘጋጀሁት ፡፡

   በኢትዮጵያ ላለው የድህነት ምክንያትና ምንጭ ፣ በሥርዓቱ ታሪክን መርምሮ የሚጽፍ ወገን ካልተነሳ በስተቀር የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ደሃነትን አመጣች የሚለው አባባል ለእኔ ኢትዮጵያዊ አስተያየት አይደለም ፡፡ የአውሮፓ ሰዎች /የኘሮቴስታንት አማኞች/ ቋንቋ ነው ፡፡ ያሳለፈችውን የጦርነት ዘመን ታሪክ የሚዳስስና የሚረዳ ሰው ከተገኘ ፣ እስከ ዛሬ ስሟን ጠብቃ መገኘቷ ብቻ የእግዚአብሔር በረከት አገር እንደሆነች ያረጋግጣል ፡፡ በዓለም ታላቋና ኃብታሟ አገር ለአሥር ዓመታት ብቻ በኢራቅና በአፍጋኒስታን ጦርነት ብታካሂድ ይኸው የዓለምን ኤኮኖሚ ሳይቀር ይዛ እየናጠችውና ለራሷም እየተንገዳገደች ነው ፡፡

   ዛሬ ተረት እየመሰለ ሄደ እንጅ ክምሩን ከምሮ በጥይት እየመታ ፣ ጥይት አሳልፏል አላሰለፈም እያለ የምርቱን ብዛትና መጠን የሚለካ ጸጋ የተትረፈረፈበት አገር እንደነበር እናውቃለን ፡፡ ገለባው እንኳን ለከብቶቹ ለዓመት የሚበቃ እራት ነበር ፡፡ ህዝቡም ደግሞ ለቸርነቱ ወደር እንዳልነበረው የቅርብ ዘመን ትዝታችን ነው ፡፡ የከተማ ልጆች ላታውቁት ትችሉ ይሆናል እንጅ ፣ የኔ ብጤ ሲመጣ የሚሰጠው ቁራሽ ሳይሆን ሙሉ እንጀራ ታጥፎ ከነማባያው ፣ ለጊዜው ካልተቻለ ደግሞ ካለው ያድርስህ ይላል ፤ እህል ውቂያ ላይ ከደረሰ ደግሞ ቢያንስ አንድ ቀርበቦ ወይም ቁና /አንድ አስራ አምስት ኪሎ የሚሆን/ ንጹህ እህል ሲቸር በእኔ ዕድሜ በአይኔ አይቻለሁ ፡፡ ጊዜው ተበለሻሽቶ ፣ ሥርዓቱም ተቀያይሮ ፣ እግዚአብሔርን መካድ ሲመጣና ፣ አገሪቱ የጦር አውድማ ስትሆን ፣ አምራች ያልሆነ በምላሱ አዳሪ ሲባዛ ፣ ፈሪሃ እግዚአብሔር መሆን ቀርቶ አላግባብ በአቋራጭ መክበር ባህል ሲሆን ፣ የህዝብ ቁጥርም እጅግ ሲጨምር ፣ የነበረው ሁሉ መልኩን ቀየረ እንጅ ፣ አልፎ አልፎ ከሚነሳው ተፈጥሮን ተከትሎ ከሚከሰት ጊዜያዊ ችግር በስተቀር ፣ እንዲህ ድሃነትና ረሃብን ለማስረዳት ለምሳሌ የምትጠራ አገር ፣ ሁለት አስራ አንድ የተባለ የአመጋገብ ሥርዓትና ፣ የጉርሻ ቤት የሚባል ነገር በታሪካችን አይታወቅም ነበር ፡፡

   በሃይማኖት ቋንቋ ብቻ እንነጋገር ከተባለ ፣ ክርስትናችን የምታስተምረውና የምታዘጋጀው ለሰማያዊ መንግሥት ነው እንጅ ለምድራዊ ብልጽግና አይደለም ፡፡ ምድር ገነት ትሆናለች ፣ ለመኖሪያነት ትመቻቻለች የሚለው የይሆዋ ምስክሮች ትምህርት ነው ፡፡ ስለዚህ እንደ ክርስቲያንነታችን መነጋገር ከቻልን መደህየትና መበልጸግ የእምነት መለኪያዎቻችን ሊሆኑ አይችሉም ፡፡ አባቶቻችን ምድራዊ ብልጽግናን ከሃይማኖት ቢያስበልጡ ኖሮ ከሺህ ዓመት በላይ ቋንቋችንን የማይናገርና የማያስተምረንን አባት በዝሆን ጥርስ ፣ በወርቅ ፣ በብር … እየለወጡ ባላስመጡልን ነበር ፡፡ በአሁኑ ጊዜ በድካማችንና በድህነታችን ርዕስ ተንተርሰው ክርስትናን ሊያስተምሩንና ሊስፋፉ የሚሞክሩት የመንገድ ላይ ጠላፊዎች /ትራክት አዳዮች/ ናቸው ፡፡ የፈዘዘና የተጨነቀ ሲያገኙ ሠርጋቸው ይሆንና ፣ በደከመ መንፈሱ በኩል በመቃኘትና በማሳመን ሥራቸውን ይሰራሉ ፡፡

   እስቲ ተመልከቺው ፤ ለእግዚአብሔር የተመረጡ ህዝቦች ተብለው የሚጠሩት እሥራኤላውያን 4ዐዐ መቶ ዘመን በግብጻውያን ባርነት ቀንበር ሥር ማቀዋል ፤ 4ዐ ዓመታት ሙሉ ዕለት ተዕለት በበረሃ ተንከራተዋል ፤ በመቀጠልም በአሶራውያን ፣ ባቢሎናውያን ፣ ፋርስ ፣ ግሪካውያንና በሮማውያን በተከታታይ መከራና ፍዳቸውን አይተዋል ፡፡ አሁንም ቢሆን ፍጹም የሆነ ሰላም የላቸውም ፡፡ ሌሎች ከክርስትና እምነት ውጭ ያሉ ደግሞ ከአልጋ ሳይወርዱ ያህል ፣ ነጫጭ ለብሰው ፣ በጥላ ተቀምጠው በአሽከርና ገረድ እየኖሩ እንደሆነ እናውቃለን ፡፡ ይባስ ብሎ ጭራሹን አምላከ የለሾች /ኤቲይስት/ የሆኑት ደግሞ ፣ እግዚአብሔር የሚባል ፈጣሪ የለም ብለው ቢክዱም እጅግ የተማሩና ዘመናዊው የምድር ጸጋም የበዛላቸው ፣ ከማንኛችንም የተሻለውን ኑሮ የሚኖሩ ቡድኖች ናቸው ፡፡ ስለዚህ በተደጋጋሚ የደሃነት ምክንያት ሃይማኖታችንና ቤተ ክርስቲያናችን ናት የሚለው ከግንዛቤ ጉድለት ነው ፤ ሃብታምነትና ብልጽግናም የቅድስና ምልክት አለመሆኑ ታውቆ ለወደፊቱ ይታረም ፡፡

   ሁሉንም የቤተ ክርስቲያናችንን ታሪክና ችግር በስፋት መቃኘቱ አሁን የምንገኝበትን ደረጃ ምክንያት በአግባቡ ለመረዳት በጣም ይረዳን ነበር ፤ ሆኖም ያለንበት ሁኔታ ስለማይፈቅድ የመጀመሪያ የክርስትና እምነት ተቀባይ ብንሆንም ሃይማኖታችን ዕድገት አሳይቶ ድንበር ዘለል ያልሆነበትን ጥቂቶቹን ታሪካዊ ምክንያቶች ብቻ ላመላክት ፡፡

   - በ7ኛው ምዕተ ዓመት የእስልምና በቀይ ባህር አካባቢ አገሮች መስፋፋትን ተከትሎ /ከግብጽና ከሌሎች ክርስቲያን አገሮች ጋር የነበረው ግንኙነት መተጓጐሉ/
   - በ9ኛው ምዕተ ዓመት የፈላሻዋ ዩዲት ጉዲት መነሳት ያስከተለው የቤተ ክርስቲያን ውድመት
   - ከ1ዐ - 12ኛው ምዕተ ዓመት የእስልምና ወደ ኢትዮጵያ መሃል አካባቢዎች መስፋፋት
   - በ15ኛው ምዕተ ዓመት የአህመድ ኢብን ኢብራሂም አል ጋዚ /ግራኝ/ ወረራ የፈጠረው ግድያና ጥፋት
   - በ18ኛው ምዕተ ዓመተ የመሳፍንቱን አገዛዝ መፈጠርና የሚሲዮናውያንን መግባት ተንተርሶ በክርስቲያን ኢትዮጵያውያኖች መሃከል ክፍፍል መፈጠሩ
   - በ19ኛው ምዕተ ዓመት ሶሻሊዝም የሃገሪቱ መመሪያ ሆኖ መታወጁን ተከትሎ እስከ አሁን ድረስ በተከታታይ የሚታዩት ችግሮች ፡፡
   - የአጎራባች አገሮች እምነት የተለየ መሆኑና የቋንቋ አንድነት አለመኖሩ ሁሉ ዋና ምክንያቶች ናቸው

   እነዚህን ሁሉ መከራዎች አሳልፋ ዛሬም ክርስቲያን ነኝ የሚልና የሚመሰክር ምእመንን ይዛ መገኘቷ ፣ ስለትርፍና ምድራዊ ጥቅም ሳይሆን ለሃይማኖቱ ቀናዒ የሆነ ፣ መከራና ችግር የማይበግሩት ፣ ሰማያዊውን ብቻ በተስፋ የሚጠባበቅ ህዝብ ያላት መሆኑን የሚያስረዳ በቂ ማረጋገጫ ነው ፡፡ በዚሁ በደሃነታችን ውስጥ ሆነን የምናመልከው ፣ አንድም ቀን ያልካድነው የፍጥረት ሁሉ ንጉሥ ኃያል ነውና ፣ ይኸን የምድር ሰቆቃ በራሱ ብልሃትና ጊዜ ያሰወግደዋል ፤ ለአገራችንም ሰላምና ብልጽግናን ያጐናጽፋል የሚል እምነትና ተስፋ አለኝ ፡፡

   በተረፈ እንደ አንዳንድ መረጃዎች ከሆነ በኢትዮጵያ የክርስቲያኑ ቁጥር 5ዐ-6ዐ ከመቶ ነው ፡፡ አሁን ዳግም ክርስቲያን እናድርግህ የሚባለውም ይኸው በመከራ ተፈትኖ ነጥሮ የወጣውና የተጠቀሰውን ወገን ብቻ ነው ፡፡ የተቀረው 4ዐ-5ዐ ከመቶ ያለው ወገን በሁሉም ወገን የተዘነጋ ይመስላል ፡፡ አቅምና ችሎታው ከተገኘ መዳን የሚያስፈልገው እጅግ ብዙ ህዝብ ፣ ብዙም የሚሠራ ሥራ አለና ትኩረት በየአቅጣጫው ይደረግ የሚል መልዕክት አለኝ፡፡

   Delete
  2. ሠይፈ ገብርኤልMarch 31, 2012 at 8:59 AM

   በወንጌል ትርጓሜ ላይ ለተነሱት ጉዳዮችም አንዳንድ ነገር ልበል
   “በአጸደ ሥጋ ስለማይኖሩና ሃላፊነታቸውን ተወጥተው ስላረፉት ቅዱሳን”
   መጽሐፍን በሥርዓቱ ካነበብሽው እግዚአብሔር እኔ የህያዋን አምላክ ነኝ ነው የሚለው ፡፡ ሥጋና ነፍሳቸው ቢለያይም እንኳን ፣ ሙሉ ለሙሉ እነደ እንስሳ በሰበሱ ፣ ፈረሱ አይባልም ፡፡ ድኀነት ከመገኘቱ በፊት እንኳን ነፍሳት በሲዖል ይጠበቁ ነበረ እንጅ ነፍሳቸው አትጠፋም ፡፡ አሁን ደግሞ በኢየሱስ ክርስቶስ መስዋዕትነት ከእሥራቱ ነጻ ወጥተዋል /1ጴጥ 3፡18-19/፤ አሁን አምኖ የተጠመቀ ወገን ሁሉ ነፍሱ እንደ ቀድሞው በሲዖል አትጠበቅም ፡፡ እኔ የአብርሃም ፣ የይስሃቅ ፣ የያዕቆብም አምላክ ነኝ በማለት ራሱን ለሙሴ የገለጸው ህያው መሆኑን መመሰከሩ ነው ፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲያውም ሞትን ሲንቀው እንደ እንቅልፍ ያህል አድርጐ ነው የሚተረጉመው /1 ተሰ 4፡ 13-18 ፤ 1 ቆሮ 15፡51-54 ፤ ሌላም ቦታ ሥጋን ይበሰብሳል ይላል እንጅ ነፍስ ከአፈጣጠሯም ህያው መሆኗን ይገልጻል /ዘፍ 2፡7 ፤ ያዕ 2፡26/ ፡፡ በዮሐንስ ራዕይም አልፎ አልፎ በአጸደ ነፍስ የሚገኙት ቅዱሳንና ቅዱሳት ምን እየሠሩ እንደሆነ ይናገራልና በእርጋታ ማንበብ ደግ ነው /ለምሳሌ ራዕ 6፡9-11/፡፡

   ኢየሱስ ክርስቶስ በታቦር ተራራ ክብረ መለኮቱን አዕማድ ለሚባሉት ሐዋርያት ሲገልጥ ከሙታን ሙሴ ፣ በህይወት ከተነጠቁት ደግሞ ኤልያሰ በመንፈስ ቀርበው ለእነ ጴጥሮስ ከጌታ ሲነጋገሩ ታይተዋል ማቴ 17፡3 ፤ ሉቃ 9፡3ዐ
   የጌታ ዓይኖች ወደ ጻድቃን ናቸው ፣ ጆሮዎቹም ለጸሎታቸው ተከፍተዋል 1ጴጥ 3፡12

   ስለነዚህ ምክንያቶችና ማስረጃዎች ቅዱሳን ቀርቶ ፣ አምነን ከተጠመቅን እኛም ስንሞት ፣ ስጋና ነፍሳችን ስትለይ ፍጹም ሙታን አንባልም ፡፡ እግዚአብሔር የህያዋን እንጅ የሙታን አምላክ አይደለምና ፡፡ ስለዚህም ጻድቃንና ቅዱሳን እንደ ወንጌል ቃል መስተናገድ ይገባቸዋል እንጅ ፣ ስለሞቱ በማለት እንደ ዮሐንስ ፣ ቴዎድሮስና ምኒልክ ወይም አፄ ኃይለ ሥላሴ በታሪክ ብለን መዝገባቸውን የምንዘጋው ጉዳይ አይደለም ፡፡

   - እንደዚህም ያለውን አንድ ሕፃን በስሜ የሚቀበል ሁሉ እኔን ይቀበላል ፤ እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል ማለት ፣ ሐዋርያቱን እንዲያስተምሩ ሲልካቸው ፣ የሚያስተምሩት የጌታ ወንጌልን ስለሆነ ፣ እናንተን የሚቀበል ቤተሰብ የወንጌል ቃልን ያምናል ፣ በእኔ አምላክነትና መሲህነት ያምናል ለማለት ነው እንጅ ፣ ሐዋርያቱ ወደ ፈጣሪያቸው ባህርይ ወደ ተመላኪነት ይቀየራሉ ማለት አይደለም ፡፡

   - “በ10:42 ላይ የተጠቀሰ ስም የለም:: በደፈናው በደቀ መዝሙር ስም ማለትም ደቀ መዝሙር በመሆኑ ብቻ::” - ይኸኛው የተወሰነ ስም ሳይጠቀስ በክፍተት የተተወው የኢየሱስ ደቀ መዝሙር አንድ ብቻ ሊሆን ሰለማይችል ነው ፡፡ ትውልድ አልፎ ትውልድ ሲተካ ደቀ መዛሙርቱ ግልጋሎታቸውን በጽናት ፈጽመው ያልፋሉ ፤ በእነርሱ ምትክ ደግሞ ሊያገለግሉ የሚነሱ አዲሶች ይመጣሉ ፡፡ የአደግንበት ቤተሰብ ወይም አካባቢ ይወስነዋል እንጅ ፣ አንድ ዝክር ያዘጋጀ ቤተሰብ ጋር በእንግድነት ብትጠሪ የተባረከውን ቁራሽ ሲያድሉ የገብርኤል ከሆን ስለ ገብርኤል በማለት ፣ የሚካኤል ከሆነ ደግሞ ስለሚካኤል ብለው ያስይዙሻል ፡፡ ይኸ ነው እኔ የምረዳው በቅዱሳንና በጻድቃን ስም የሚባለው ዝክር፡፡ ዝክር ማለትም ትርጉሙም ማስታወሻ ፣ መታሰቢያ ማለት ነው ፡፡ መታሰቢያ ደግሞ በህይወት በአጠገባችን እየተንጓለለ ለማንም አይደረግም ፤ ካስፈለገ ልደቱን አብረን እያሸበሸብን ልናከብርለት እንችላለን ፡፡

   - ክርክርን የሚጀመረው የሚቀርቡት ጽሁፎች በቀጥታ በልዩነት ላይ ብቻ ያተኮሩ መሆናቸውና ውግዘትና ኩነኔን ስለሚናገሩ ነው እንጅ በራሴ ፈልጌው አይደለም ፡፡ በማይስማሙበትና በልዩነቶቻችን ላይ ከሚነጣጠር ፣ ሁላችንን የሚያስማማንንና አንድ ቋንቋ የሚያናግረንን የወንጌል ትምህርት ላይ ቢተኰር ምንም ተቃውሞና ክርክር አይነሳም ነበር እላለሁ ፡፡ ክርስቲያን የሚታወቀው ደግሞ ራሱን ዝቅ አድርጎ ፣ አዋርዶ ሲያይና ለሌሎች አርአያ ሲሆን እንጅ ፣ እኔ የምለውን አድምጥ ፣ እኔ ነኝ የማውቅልህ በማለት በበላይነት የሚያቅራራ ፣ የራሱንም አምልኮ በግድ ለመጫን የሚታገል ከሆነ ክርስቲያን ነኝ ቢለኝ እንኳን አላምነውም ፡፡ የክርስትናችን ዋና መገለጫ ምግባራችን ፣ የዋህነት ፣ እርስ በርሳችን መፈቃቀራችን ፣ አንድነትን ለመፍጠር መታገላችን ነው ፡፡

   እኔ በበኩሌ አምልኮዬን በማንም ላይ በግድ ለመጫን አልፈልግም ፤ ምኞቴም አይደለም ፡፡ መከባበሩ በመሃላችን ካለ የማንንም እምነት አላወግዝም ፡፡ መማርና መረዳት ፈልጐ ለሚጠይቀኝ ደግሞ የማውቀውንና የምችለውን ያህል ለማስረዳት እደክማለሁ ፡፡ በአጋጣሚ በአንድ ጣራ ሥር ሆነን ሲላቀሱና ሲጸልዩ ፣ ጣሊያንኛ በመሰለም ቋንቋ ሲናገሩ እየሰማሁ በትዕግስት ነው የምመለከተው እንጅ ለምን ሆነ ብዬ በሰዎች ላይ ተነስቼ ፣ ተከራክሬም አላውቅም ፡፡ እምነቴንና አምልኮዬን የሚተናኮል ሲያጋጥመኝ ግን መጓዝ የሚገባኝን ያህል ሁሉ እሄዳለሁ ፡፡ በዚህም ምክንያት እህት ካልኩሽ ጋር በመከባበር ፣ ማንም የማንን ሳያንቋሽሽ ለየግላችን በየእምነታችን እንተጋለን እንጅ የአተረጓጐምና የግንዛቤ ልዩነትስላለን የወንጌል ጥናት ባልደረባ መሆን አልቻልንም ፡፡

   ከአነበብኩት ውስጥ - የሃይማኖት መጽሐፍትን ለመመረመር ይረዳል ብሎ ከተጻፈው ቃል ማስተወሉ ከተገኘ ላስነብብ እዚህ አክየዋለሁ ፡፡ “Holy Scripture must be understood within the Tradition of the Church, which is the experience of the Church, and this experience is handed down to us through the writings of the Fathers.”

   በተረፈ ይህም የዘመናችን የቤተ ክርስቲያናችን ፈተና ሆኖ ሊመዘገብ ስለቀረበልን ይመስለኛል ፣ ልጆቿ ከመደማመጥ ይልቅ እኔ የምለው ትክክል ነው ፣ የእኔ መቀበል አለብህ/ሽ በመባባል እየተወዛወዝን እንገኛለንና እግዚአብሔር እሱ በብልሃቱ መፍትሄውን እንዲሰጠን የሚል ጸሎት አለኝ ፡፡

   ሰላም ይብዛላችሁ
   እግዚአብሔር ሁላችሁንም ይባርክ

   Delete
 13. Welete Giyorgis NA.
  ሠይፈ ገብርኤል ቃለ ህይወት ያሰማልን:- እግዚአብሔር የህያዋን እንጅ የሙታን አምላክ አይደለምና እዚነህን እምነት የለሾች ማስተዋልንይስጥልን:: ምክንያቱም እምነት ቢኖራቸው ኖሮ አንተ የመረጥካቸውን ጥቅሶች
  1.ታድያ የኤልሳዕ የገላው ፍራሽ የሆነው አጥንት ስለምን ምክንያት ሙትን አስነሳ? 2 ነገ 13፡21 ፡፡ ይኸ ታምርስ ተፈጠመ በማለት የተጻፈው በኤልሳዕ አጽም እነዲመለክበት ተፈልጐ ይሆን ?
  2.በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ለዘላለም የማይጠፋ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ”
  3.ስለተመረጡት ቅዱሳን ሲናገር ሮሜ 8፡29-30 ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤ አስቀድሞም የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ ጠራቸው፤ የጠራቸውም እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው፤ ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞ አከበራቸው የሚለውን ቃል በእርጋታ ማንበብ በቂ ማረጋገጫ ነበር :፡
  እኔ ደግሞ ትንሽ ልበል,
  1.ለቅኖች ብርሃን በጭለማ ወጣ መዝ 101:4

  2.እግዚአብሔር ከመረጠና ጸጋውን ከሰጠ በኋላ
  ባደረገው ነገር አይጸጸትም:: ሮሜ 11:29 እንበላቸው
  <>

  ReplyDelete
 14. Ytsadkanene kebere Mayet Ytsanacehu wegenocacen Fetari lebonacehune Yaberalacehu Amen.

  ReplyDelete