Wednesday, March 28, 2012

የዋልድባ ገዳም ይዞታና የዝቋላ ተራራ ቃጠሎን ማህበረ ቅዱሳን ለፖለቲካ ፍጆታው ቢያውላቸውም የፈለገውን ትርፍ እንዳላስገኙለት እየተነገረ ነው - - - Read PDF

በቅርቡ በዋልድባ ገዳም ዙሪያ ከገዳሙ ይዞታ ውጪ በሆነው ስፍራ ላይ በመንግስት የተጀመረውን የልማት ስራ ሌላ ትርጉም በመስጠትና መንግስትን ከገዳሙ መነኮሳትና ከኦርቶዶክሳውያን በአጠቃላይ ለማጋጨት ማህበረ ቅዱሳን አንቀላፍተው በከረሙና ፖለቲካዊ ቅስቀሳውን ተከትሎ ነቃ ነቃ ባሉ ድረገጾቹ የጀመረው ፖለቲካዊ ዘመቻ ግቡን እንዳልመታለት በአገር ውስጥ ከሚታየው የገዳሙ መነኮሳትና የህዝቡ ምላሽ ማወቅ እንደተቻለ ከተለያዩ ምንጮች ያገኘናቸው መረጃዎች እየጠቆሙ ነው። በአንድ አድርገን ድረገጽ ላይ አገር ፈረሰ፣ አገር ታረደ፣ ተነስበማለት ህዝቡን ለአመፅ ያነሳሳ ቢሆንም ሰሚም ተቀባይም እንዳላገኘ የሚታይ እውነታ ነው።
የማህበሩ አላማ እንደተለመደው መንግስትን ከህዝብ፣ ቤተክህነትን ከምእመናን ማጋጨትና በሁለቱም አቅጣጫ ወደወንበሩ የሚወስደውን ጥርጊያ ጎዳና ማመቻቸት ነበር። ነገር ግን የሚሳካ አልሆነም። በመንግስት በኩል እንደተገለጸው፣ የገዳሙ መነኮሳት፣ የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ፣ ከቤተክህነት የተወከሉ ሰዎች፣ የአካባቢው ነዋሪዎችና የመንግስት አካላት በተገኙበት በተደረገው ውይይት መንግስት የገዳሙን ይዞታ እንዳልነካ ከገዳሙ በጣም ርቆ በሚገኝ ስፍራ የልማት ስራን መስራት መጀመሩን የገለጸ ሲሆን፣ የገዳሙ ሰዎችም ይህንኑ አረጋግጠዋል። ጉዳዩን የቀሰቀሱትም የዋልድባ መነኮሳት ሳይሆኑ መነኮሳት መስለው የገቡ ፖለቲከኞች መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል። ወትሮም ቢሆን ገዳም፣ ጽድቅ ገዳም በመግባት ይገኛል በሚለው ኢመጽሀፍ ቅዱሳዊ ስብከት ተደልለው ጽድቅን ፈልገው የሚመንኑ መነኮሳት መኖሪያ ብቻ ሳይሆን የብዙ ወንጀለኞች መደበቂያም እንደሆነ ይታወቃል። በዋልድባ ማህበረ ቅዱሳን ለማስነሳት የሞከረውንና ያልተሳካውን አመፅ በማቀጣጠል ታላቁን የጾም ወቅት የአመፅ ስራ መስሪያ ያደረጉትም እነዚሁ በማህበረ ቅዱሳን የሚደገፉና በገዳም የተደበቁ የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላዎች መሆናቸውም እየተነገረ ነው። ከማህበሩ ጋርም ንክኪ እንዳላቸውና ከመጀመሪያው ጀምሮ ያልሆነና ሀሰተኛ መረጃ ለማህበሩ በማቀበል፣ በድረገጾቹ እያወጣ ህዝቡን ለማሳሳት ጥረት ሲያደርግ ሰንብቷል፡፡
ይህ በእንዲህ እያለ በዝቋላ የተነሳውን የደን ቃጠሎም ማህበሩ ለተጨማሪ ፖለቲካዊ ፍጆታው ሲያውለው ተስተውሏል። ደኑ ሰው ሰራሽ በሆነ መንገድ ይቃጠል ወይም በተፈጥሯዊ መንገድ በውል ባይታወቅም፣ በአንዳንድ ሚዲያዎች እየተነገረ ያለው በበጋው ደረቅ አየር ምክንያት የተነሳ ተፈጥሯዊ ቃጠሎ ነው። ይሁን እንጂ የማህበረ ቅዱሳን ድረ ገጾች ማንንም ሊያሳምን ባይችልም፣ በቃጠሎው ውስጥ የመንግስት እጅ እንዳለበት እየተናገሩ ነው። በአገር ውስጥ ግን ሰሚ አላገኙም። ስለዚህ በውጭ በተለይም በሰሜን አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ ጣቢያ በመታገዝ የማህበሩ የሰሜን አሜሪካ አስተባባሪዎች ከፖለቲካ አባቶቻቸው ጋር በመተባበር ሰላማዊ ሰልፍ ጠርተው ሲጯጯሁ መዋላቸውን ታዝበናል። አርበኛውንና ለአገራቸው ሲሉ በፋሺስት ጣሊያን ሰማዕት የሆኑትን ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስንና በዋልድባ ገዳም ሆነ የተባለውን ጉዳይ ምን አገናኝቶት ይሆን ሰላማዊ ሰልፈኞቹ የአቡነ ጴጥሮስ ደም ይጮሃል ዋልድባን አድኑ ይላል? የሚል መፈክር ይዘው የታዩት? ሃይማኖትን ሽፋን ካላደረገ በቀር ፖለቲካውን ማራመድ እንደማይችል የተገነዘበው ማህበረ ቅዱሳን አብሮ ባይሄድም እንኳን አቡነ ጴጥሮስን ሽፋን አድርጎ በስማቸው ሊቀሰቅስ መሞከሩ ብዙዎችን አስገርሟል።
ፖለቲከኛው ብቻም ሳይሆን ነጋዴው ማህበረ ቅዱሳን በዚህ አጋጣሚ በውጭ ካሉ ኢትዮጵያውያን በተለይም ከኦርቶዶክስ ምእመናን በዋልድባና በዝቋላ ተራራ ስም ደጋፍ በማሰባሰብ ስራ መጠመዱንም ከስፍራው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ከዚህ ቀደም እንደሚያደርገው ሁሉ በስማቸው የተለመነባቸው ገዳማት ከሚሰበሰበው ገንዘብ የሚያገኙት አንዳች እንደሌለ ብዙዎች ይናገራሉ። ከዚህም በላይ እንደዚህ ባሉና በሌሎችም አጋጣሚዎች የሚያስገባውን ዳጎስ ያለ ገቢ የሚቆጣጠረው አካል ስለሌለ፣ ማህበሩ በቤተ ክርስቲያን ስም እየለመነ የራሱን ኪስ እየሞላ፣ ልዩ ልዩ የውንብድና ተግባራትን እየፈጸመ፣ ተሀድሶ ያላቸውን ወገኖች ለማስደብደብ በየደብሩ ላሰማራቸው ወሮበሎች ደመወዝ እያደረገው ነውና የሚመለከታቸው የቤተክህነትም የቤተመንግስትም አካላት ተገቢውን ቁጥጥር ሊያደርጉ ይገባል።    
የማህበረ ቅዱሳን አመራር የጾም ወቅትን እየጠበቀ ከመጾምና ከመጸለይ ይልቅ ጊዜውን ለአመጻ ተግባር የሚያውለው ከቶ ለምን ይሆን? የሚሉ ጥቂቶች አይደሉም። አላማዬ ሃይማኖት ነው የሚል ወገን በዚህ ወቅት መጾም መጸለይ፣ ወደፈጣሪ መጮህ እንጂ ፖለቲከኛ ሆኖ በሰላማዊ ሰልፍ ወደ ምድር ገዚዎች ይጮሃልን? ለነገሩ ማህበረ ቅዱሳን በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርሰቲያን መዋቅር ውስጥ ራሱን ያስጠልል እንጂ ትክክለኛ ማንነቱ ሃይማኖት ሳይሆን ሌላ ነው። መውጫው እንደደረሰ ጋኔን የጾም ወቅትን እየጠበቀ የሚያስነሳው የተለመደ አቧራም በዘንድሮው አቢይ ጾምም ከመቼውም ጊዜ ይልቅ ተባብሶ መቀጠሉ፣ ማህበሩ ድብቅ አጀንዳውን መሰወር እንዳልቻለና ፖለቲካዊ ማንነቱ ፈጥጦ የታየበት ጊዜ መሆኑን አረጋግጧል።

28 comments:

 1. ye ማህበረ ቅዱሳን sera poletika mehonun be waldiba gedamna be ziquala katelo be gilts taytwal !!!.
  yibas bilo bezqwala guday በአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ ጣቢያ' < yemahbere qidusan gazetenya endezegebew > eyetebale tinitane na mabrariya mekrebu MAK be poletikaw min yahil indehede yasayal .MAK min yadirg ? betekiristiyanina hizbochiwan sibetebit, yalihone mereja balut yeteleyayu dihregetsoch(web sit) eyaserache siyateremames menigst zim ale!!!!! JORO YALEW YISMA !!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ማፈሪያዎች እስከ አሁን አንግባችሁት የምትዞሩትን ቅዱስ መፅሐፍ እንኩአን አታውቁትም
   "መለየትን የሚወድ ምኞትን ይከተላል መልካም ነገርንም ይቅወማል"የሚለውን እንኩአን አላየሄውም
   እስኪ ተቆርቁአር ከሆናችሁ ችግሯ ላይም ድረሱላት !

   Delete
 2. Ejig betam Yemigermew neger. Ye egziabher Kal Yetamene Mehonu Bezih Hulu Tegelete Kibir Letaredew Beg Yihun. Bezih Talak Tsum lay Mak Lebiso Endemetseley. Embassy Kalhedin Yilalu. Ere Lemehonu Chigir Ale Bibal Enkuan, Yebetechrstianin Situition Egziabher Yalifetawin Chigir Meles Zenawi or Girma Biru lifetaw new. NEGER GIN HULACHINIM ENDEMINAWIKEW YEMAHIBERU WANA MESIRACH ABALAT YENEBERUT / YEMAHIBERUN SECRET ALAMA YEMIAWIKUT EDIME LENE ABUNE PAULOS ENZILALINET VISA BEMASIMETAT AMERICA YEPOLITICA ASSYLM TEYIKEW BEWICH AMERICA KEMIGEGNU YESHIWA MINGIST YIMELES BAY ABYATE CHRISTIANAT GAR MENESHACHEWIN ST.MARRY CHURCH BEMADIREG YEKIDIST MARIAM DIACON KEHONEW ATO ADDISSU ABEBE (voa) ENA YE GINBOT SEBAT ABALAT GAR BEMEHON YEPOLITICA ALAMA BEMAKAHED LAY YIGEGNALU.
  NEGER GIN YIH NEGER MANINETACHEW ENDIGELET HUNUAL. bELELA MENGED MAHIBERU ERASUN LE 3 BEMEKIFEL (mk AMERICA MAEKEL, nassu, BALEWOLD) BEMALET BIZU LEMEMISEL BINKESAKESIM. YAW YAHIYA LIJ AHIYA NEW. HAHAHAHA

  aLITESAKAM, NEGER GIN MAHIBERU KE ASHEBARIWOCH GAR BEMEHON YASHEBARINET SIRA EYESERA BEMEHONU. SAYIKATEL BEKITEL EYETEBALE NEW. YIH DEGIMO YE AMLAKACHIN YEEGZIABHER SEMAYAWI WUSANE NEW.
  AYI mk BEMENFES TEJEMIROOO BESIGA MECHERES MALET YIH NEW ESHIIII. ANY WAY ENIWODACHIHUALEN ENA WODE SENBET TEMARINETACHIHU TEMELESU LELAW AYAMIRIBACHIHUM. KISINAM, DICUNAM, PAPASINETIM LETESETEW ENJI LEHULUM SENBET TEMARI AYIDELEM. LAM BALIWALEBET KUBET LEKEMA MALET YIH NEW...

  ReplyDelete
 3. Bewshet E/hern masdeset yichalal ende?

  ReplyDelete
 4. ሠይፈ ገብርኤልMarch 28, 2012 at 7:24 PM

  አስቀድሞ ንስሃው ይቅደምልን
  “በዋልድባ ማህበረ ቅዱሳን ለማስነሳት የሞከረውንና ያልተሳካውን አመፅ በማቀጣጠል ታላቁን የጾም ወቅት የአመፅ ስራ መስሪያ ያደረጉትም እነዚሁ በማህበረ ቅዱሳን የሚደገፉና በገዳም የተደበቁ የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላዎች መሆናቸውም እየተነገረ ነው።” የዕለቱ አባባላችሁ ነው ፡፡

  http://www.abaselama.org/2012/02/read-pdf_23.html

  ከላይ በተቀመጠው አድራሻ ለአንባቢ ያስተላለፋችሁት ምን ይላልና ነው ዛሬ ታላቁ ጾም ማለት የቻላችሁት ፡፡ ለምን ዝም ብላችሁ የጾም ታላቅና ታናሽ ሳታወጡ መልዕክታችሁን አታስተላልፉም ፡፡ ይኸን የቁማር ጨዋታ የመሰለ አንድም በጨ ሌላም ጠቆረ ብየዋለሁ ፡፡ ከልባችሁ ውስጥ ያለው ሌላ ሲሆን ፣ የህዝብን አስተሳሰብ ለመንካት ፣ በቋንቋውም ለመመሳሰል መታገላችሁን ነው የተረዳሁት ፡፡ በአዋጅ ጾም አናምንም ፤ የኢኦተቤ ጾሞች በሙሉ ስህተት ናቸው ፣ የሌላ አገር ሰዎች መታሰቢያ ናቸው በማለት ዘርዝራችሁ በቀደመው ጽሁፍ አቅርባችኋልና ከዚህኛው አባባል ጋር አልተስማማልኝም ፡፡ አይ አሁን ገብቶናል ፣ ተቀብለናል የምትሉ ከሆነ ከዚህ ጽሁፍ በፊት የንስሐ ደብዳቤአችሁ መቅደም ይገባዋል ፡፡ በጾማችን እንደማታምኑ ማረጋገጫ የሚሆነኝ ጾም ከገባ እስከ ዛሬ ድረስ አንድም ነገር ስለ ጾም አለማስተማራችሁ ነው ፡፡ ጾም ስንጀምር መጾም እንደማይገባን አዋጅ ያወጃችሁትን እንደ ትምህርት እንዳትቆጥሩት አደራ ፡፡ ያ ተቃውሞ ነው የሚባለው ፡፡

  ከቀደመ ቃላችሁ ዋና ክፍል የምለውን እንድታነቡት በማለት ከዚህ በታች ለአስረጅነት አቅርቤዋለሁ ፡-
  “የጾም ነገር ሲነሣ፣ የማንን ጾም ነው የምንጾመው? የሚለው ሌላው አነጋጋሪ ጒዳይ ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን በዐዋጅ የተደነገጉትና ምእመናን በየዓመቱ እንዲጾሟቸው ከታዘዙት አጽዋማት ብዙዎቹ፣ የእኛ ሳይሆኑ ሌሎች በተለያየ ምክንያት የጾሟቸው ናቸው፡፡ በቤተ ክርስቲያን፣ በአገርና በወገን ላይ ችግር ቢደርስም ባይደርስም፣ በዓመት ውስጥ የተወሰነላቸውን ወቅት ጠብቀው የቀድሞ ታሪክን /ምናልባትም ከእኛ ጋር ትስስር የሌለውን ታሪክ ጭምር/ በማሰብ የሚጾሙት አጽዋማት ሰባት ናቸው፤ (የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከልደተ ክርስቶስ እስከ ፳፻ ዓ.ም. 2000፣ 32) እነርሱም፡- “
  ይቀጥልና ሲተነትናቸው ፡-
  “1. ጾመ ነቢያት /ነቢያት በተለያየ ጊዜ ጾሙት የሚባል/፣
  2. ጾመ ነነዌ /በትንቢተ ዮናስ እንደ ተጻፈው የነነዌ ሰዎች የጾሙት/፣
  3. ጾመ አርብዓ /ዐቢይ ጾም ወይም ጌታ የጾመው/፣
  4. ጾመ ሐዋርያት /ሐዋርያት መቼ እንደ ጾሙት ባይታወቅም ጾመውታል የሚባለው/፣
  5. ጾመ ፍልሰታ /ሐዋርያት በድንግል ማርያም ሞትና ትንሣኤ ምክንያት ጾመውታል የሚባለው/፣
  6. ጾመ ገሃድ /የክርስቶስ ልደትና ጥምቀት በዓል ረቡዕና ዐርብ ቀን የሚውል ከሆነ ለዚያ ለውጥ በዋዜማቸው የሚጾም/ እና
  7. ጾመ ድኅነት /ከበዓለ ኀምሳ በቀር ዘወትር ረቡዕና ዐርብ የሚጾመው/ ናቸው፡፡” ይላል

  አመሰግናለሁ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ያልታደለ አእምሮ ... አሉ!
   ሰይፈ ምናለበት አእምሮህን በትክክል ብታሰራው! የአንተ ጥረት ሁልጊዜ ነገሮችን በእጅ አልፋ (በጽሁፍ ስለሆነ) ክርክር የቀረቡ እውነታዎችን ከመስመር ማስወጣት ነው። አሁን ጽሁፉ የማህበረ ቅዱሳን ፖለቲካዊ ስራ የተጋለጠበት ጽሁፍ ነው። በዚህ ላይ መከራከርና ማህበሩ ፖለቲካዊ ድርጅት (ህገ ወጥ ተቃዋሚ) መሆኑን ማስተባበል አንድ ነገር ነው። ጽሁፉን በትክክል ካነበበና መልስ ካለው ሰው የሚጠበቀው ይህ ነው። አንተ ግን ለሚወጡት ጽሁፎች በቂ መልስ ስለሌለህ ወይም መልስ ብትሰጥ የሚፈርስብህ ብዙ ነገር ስላለ በጽሁፉ ጭብጥ ውስጥ ያልተወሳ ነገርን ይዘህ ጭልጥ ትላለህ። ከዚህ ቀድም ሰለጾም የቀረበው ትክክለኛ ሀሳብ ነው። በዚያ ጽሁፍ ራስህን ብትመረምርና ጾማችን እንዴት ነው ብትል ወደ እውነት ትደርሳለህ። ዛሬ ከተነጋገርን መነጋገር ያለብን ስለማህበረ ቅዱሳን ፖለቲከኛነት ነው እንጂ ስለጾም መሆን የለበትም። ስለጾም የተነሣው ወቅቱ ኦርቶዶክሳውያን በጾም ላይ መሆናቸውን ላመሳየት ይመስለኛል እንጂ ባለፈው በጾም ላይ የቀረበውን በመለወጥ አይደለም። ደግሞም አንተ የሚመችህን ብቻ ቆርጠህ አቀረብህ እንጂ በዚያ ጽሁፍ ውስጥ ከእኛ ጋር ይበልጥ ቁርኝት ያለው የጌታችን ጾም መሆኑ ተጠቅሶ የለምን? ታዲያ እርሱን ለምን አላካተትከውም? አሁን አንተ እውነተኛ ተከራካሪ ከሆንክ ማህበረ ቅዱሳን ፖለቲከኛ አይደለም በልና ተነስ። ነው ብለህ ካመንክና ያን ማጋለጥ ማህበሩን ይጎዳል ብለህ ካሰብክም ዝም ብሎ ቁምነገር የሌለውን ቀለም የሚተፋ ብእርህን ሰብስብ።

   Delete
  2. ሠይፈ ገብርኤልMarch 29, 2012 at 8:58 AM

   ወዳጄ አኔ ማህበረ ቅዱሳንን ለምን አጋለጡት ወይም ለምን ኰነንኩት የሚል አቋም የለኝም ፡፡ ገለጻው ውስጥ ከአባ ሰላማ አቋም ጋር የማይዛመድ አረፍተ ነገር ሳይ በመደንገጤ ጻፍኩት ፡፡ ስለ እኔ ጽሁፍ ምክንያትም መስመራችሁን አትልቀቁ ፡፡ ግን ሲጻፍ ጥንቃቄ እንዲደረግ ለማሳየት ወይም የአቋም ለውጥ ካለ ለማወቅ ብዬ ነውና በገለጻዬ አትከፋ ፡፡ የእኔ ትኩረት ሁሌም አባቶቻችን በስንት ተጋድሎ ለእኛ ካስረከቡን ሃይማኖት ጋር በተዛመደው ላይ ብቻ ነው ፡፡

   አመሰግናለሁ

   Delete
 5. ትገርማላችሁ:: ዛፍ: ደኖች ሲወድሙ, ምንም ያልገደዳችሁ:: ቆይ እስቲ ማኅበረ ቅዱሳን ዓላማ ይኑረው ይባል:: ለምን ሳቱን እያጠፋችሁ አትማገቱም:: ማፈሪያ ነገር ናችሁ:: እናንተን ብሎ ለቤተ/ያን ተቆርቃሪ::

  አምላክ ለሁላችንም የሚያስፈልገንን አስተዋይ ልቦና ይስጠን::

  ReplyDelete
 6. የብፁዕ አቡነ ኤልሳይ መግለጫ እጅግ የሚያገርምና ሊማሩበት የሚገባ ነው፡፡ ለመሆኑ ተቆርቋሪዎች ነን ባዮቹ ለባህታያን ካዘኑ ለምን በስማቸው የሚነግዱትን ባህታዊያን ተብዎች አያጋልጡም፣

  እመሰ አባ ተአምር ባቲ
  ገረገራ ዋልድባ ይእቲ

  አባ ሆይ ብታውቅበትስ
  ገረገራም ዋልድባን ናት

  ሳሙኤል አባይ

  ReplyDelete
 7. enante mechem enkuwan tegoditenilachihu litiredun kerito moatchinin yemitimegnu yebetekristiyanin mefires lemayet yemitigugwagu mehonachihun sirachihu yasayal.Ahun yegedamochachin mekatel yemayanigebegibew Ye orthodox amagn ale bilachihu new MKn yemitikesut? Yeterebarebinew eko MK silehonin sayihon ewunetegna yebetekristiyan lijoch silehonin tifatuwa tifatachin limatuwa limatachin silehone new. MK binorim bayinorim egna lebetekristiyanachin kemegaderl yeminishesh ayimiselachihu. Mahiberu belelebet sinit sira tesertuwal meselachihu. Abatochachin eko ke MK befit new EOTCn yetebekuwat. Silezih bekenitu atinchachu. gurorowachihu yisenetekal. Betekristiyan eske elete mitsiat atitefam. Mefetenuwa gin woriknetuwa yitawokina lealemu hulu yigelets Zenid new. Enante gin metsihaf endih yilachihuwal "Tifatachew ayizegeyim....." Lib Yisitachihu.

  ReplyDelete
 8. ለመሆኑ በብዙ ገዳማት ውስጥ የማኅሩን ጉዳይ ለማስፈጸም ከማህበሩ የገዳማት መርጃና ዓላማ ማስፈጸሚያ መምሪያ ወርሀዊ የደመወዝ ተከፋይ የሆኑ በየገዳሙ ብጥብጥ በመፍጠር ሥራ ብቻ የተወሰኑ በርካታ "መነኰሳት" የሚመስሉ እንዳሉ ታውቃላችሁ፡፡ የእነዚህ ሰዎች ዋና አላማም እንደአሁኑ አሳቻ ጊዜ እፈለጉ ብጥብጥ መፍጠር ነው፡፡ ምናልባት የዝቋላን እሳት ያስነሱት ማቆች ቢሆኑስ

  ReplyDelete
 9. ye ማህበረ ቅዱሳን sera poletika mehonun be waldiba gedamna be ziquala katelo be gilts taytwal !!!.
  yibas bilo bezqwala guday በአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ ጣቢያ' < yemahbere qidusan gazetenya endezegebew > eyetebale tinitane na mabrariya mekrebu MAK be poletikaw min yahil indehede yasayal .MAK min yadirg ? betekiristiyanina hizbochiwan sibetebit, yalihone mereja balut yeteleyayu dihregetsoch(web sit) eyaserache siyateremames menigst zim ale!!!!! JORO YALEW YISMA !!!
  Reply
  ABA zERA DAWITMar 28, 2012 08:45 AM

  Ejig betam Yemigermew neger. Ye egziabher Kal Yetamene Mehonu Bezih Hulu Tegelete Kibir Letaredew Beg Yihun. Bezih Talak Tsum lay Mak Lebiso Endemetseley. Embassy Kalhedin Yilalu. Ere Lemehonu Chigir Ale Bibal Enkuan, Yebetechrstianin Situition Egziabher Yalifetawin Chigir Meles Zenawi or Girma Biru lifetaw new. NEGER GIN HULACHINIM ENDEMINAWIKEW YEMAHIBERU WANA MESIRACH ABALAT YENEBERUT / YEMAHIBERUN SECRET ALAMA YEMIAWIKUT EDIME LENE ABUNE PAULOS ENZILALINET VISA BEMASIMETAT AMERICA YEPOLITICA ASSYLM TEYIKEW BEWICH AMERICA KEMIGEGNU YESHIWA MINGIST YIMELES BAY ABYATE CHRISTIANAT GAR MENESHACHEWIN ST.MARRY CHURCH BEMADIREG YEKIDIST MARIAM DIACON KEHONEW ATO ADDISSU ABEBE (voa) ENA YE GINBOT SEBAT ABALAT GAR BEMEHON YEPOLITICA ALAMA BEMAKAHED LAY YIGEGNALU.
  NEGER GIN YIH NEGER MANINETACHEW ENDIGELET HUNUAL. bELELA MENGED MAHIBERU ERASUN LE 3 BEMEKIFEL (mk AMERICA MAEKEL, nassu, BALEWOLD) BEMALET BIZU LEMEMISEL BINKESAKESIM. YAW YAHIYA LIJ AHIYA NEW. HAHAHAHA

  aLITESAKAM, NEGER GIN MAHIBERU KE ASHEBARIWOCH GAR BEMEHON YASHEBARINET SIRA EYESERA BEMEHONU. SAYIKATEL BEKITEL EYETEBALE NEW. YIH DEGIMO YE AMLAKACHIN YEEGZIABHER SEMAYAWI WUSANE NEW.
  AYI mk BEMENFES TEJEMIROOO BESIGA MECHERES MALET YIH NEW ESHIIII. ANY WAY ENIWODACHIHUALEN ENA WODE SENBET TEMARINETACHIHU TEMELESU LELAW AYAMIRIBACHIHUM. KISINAM, DICUNAM, PAPASINETIM LETESETEW ENJI LEHULUM SENBET TEMARI AYIDELEM. LAM BALIWALEBET KUBET LEKEMA MALET YIH NEW...
  Reply
  AnonymousMar 28, 2012 03:39 PM

  Bewshet E/hern masdeset yichalal ende?
  Reply
  ሠይፈ ገብርኤልMar 28, 2012 07:24 PM

  አስቀድሞ ንስሃው ይቅደምልን
  “በዋልድባ ማህበረ ቅዱሳን ለማስነሳት የሞከረውንና ያልተሳካውን አመፅ በማቀጣጠል ታላቁን የጾም ወቅት የአመፅ ስራ መስሪያ ያደረጉትም እነዚሁ በማህበረ ቅዱሳን የሚደገፉና በገዳም የተደበቁ የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላዎች መሆናቸውም እየተነገረ ነው።” የዕለቱ አባባላችሁ ነው ፡፡

  http://www.abaselama.org/2012/02/read-pdf_23.html

  ከላይ በተቀመጠው አድራሻ ለአንባቢ ያስተላለፋችሁት ምን ይላልና ነው ዛሬ ታላቁ ጾም ማለት የቻላችሁት ፡፡ ለምን ዝም ብላችሁ የጾም ታላቅና ታናሽ ሳታወጡ መልዕክታችሁን አታስተላልፉም ፡፡ ይኸን የቁማር ጨዋታ የመሰለ አንድም በጨ ሌላም ጠቆረ ብየዋለሁ ፡፡ ከልባችሁ ውስጥ ያለው ሌላ ሲሆን ፣ የህዝብን አስተሳሰብ ለመንካት ፣ በቋንቋውም ለመመሳሰል መታገላችሁን ነው የተረዳሁት ፡፡ በአዋጅ ጾም አናምንም ፤ የኢኦተቤ ጾሞች በሙሉ ስህተት ናቸው ፣ የሌላ አገር ሰዎች መታሰቢያ ናቸው በማለት ዘርዝራችሁ በቀደመው ጽሁፍ አቅርባችኋልና ከዚህኛው አባባል ጋር አልተስማማልኝም ፡፡ አይ አሁን ገብቶናል ፣ ተቀብለናል የምትሉ ከሆነ ከዚህ ጽሁፍ በፊት የንስሐ ደብዳቤአችሁ መቅደም ይገባዋል ፡፡ በጾማችን እንደማታምኑ ማረጋገጫ የሚሆነኝ ጾም ከገባ እስከ ዛሬ ድረስ አንድም ነገር ስለ ጾም አለማስተማራችሁ ነው ፡፡ ጾም ስንጀምር መጾም እንደማይገባን አዋጅ ያወጃችሁትን እንደ ትምህርት እንዳትቆጥሩት አደራ ፡፡ ያ ተቃውሞ ነው የሚባለው ፡፡

  ከቀደመ ቃላችሁ ዋና ክፍል የምለውን እንድታነቡት በማለት ከዚህ በታች ለአስረጅነት አቅርቤዋለሁ ፡-
  “የጾም ነገር ሲነሣ፣ የማንን ጾም ነው የምንጾመው? የሚለው ሌላው አነጋጋሪ ጒዳይ ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን በዐዋጅ የተደነገጉትና ምእመናን በየዓመቱ እንዲጾሟቸው ከታዘዙት አጽዋማት ብዙዎቹ፣ የእኛ ሳይሆኑ ሌሎች በተለያየ ምክንያት የጾሟቸው ናቸው፡፡ በቤተ ክርስቲያን፣ በአገርና በወገን ላይ ችግር ቢደርስም ባይደርስም፣ በዓመት ውስጥ የተወሰነላቸውን ወቅት ጠብቀው የቀድሞ ታሪክን /ምናልባትም ከእኛ ጋር ትስስር የሌለውን ታሪክ ጭምር/ በማሰብ የሚጾሙት አጽዋማት ሰባት ናቸው፤ (የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከልደተ ክርስቶስ እስከ ፳፻ ዓ.ም. 2000፣ 32) እነርሱም፡- “
  ይቀጥልና ሲተነትናቸው ፡-
  “1. ጾመ ነቢያት /ነቢያት በተለያየ ጊዜ ጾሙት የሚባል/፣
  2. ጾመ ነነዌ /በትንቢተ ዮናስ እንደ ተጻፈው የነነዌ ሰዎች የጾሙት/፣
  3. ጾመ አርብዓ /ዐቢይ ጾም ወይም ጌታ የጾመው/፣
  4. ጾመ ሐዋርያት /ሐዋርያት መቼ እንደ ጾሙት ባይታወቅም ጾመውታል የሚባለው/፣
  5. ጾመ ፍልሰታ /ሐዋርያት በድንግል ማርያም ሞትና ትንሣኤ ምክንያት ጾመውታል የሚባለው/፣
  6. ጾመ ገሃድ /የክርስቶስ ልደትና ጥምቀት በዓል ረቡዕና ዐርብ ቀን የሚውል ከሆነ ለዚያ ለውጥ በዋዜማቸው የሚጾም/ እና
  7. ጾመ ድኅነት /ከበዓለ ኀምሳ በቀር ዘወትር ረቡዕና ዐርብ የሚጾመው/ ናቸው፡፡” ይላል

  አመሰግናለሁ
  Reply

  ReplyDelete
 10. Mk ye ethiopia gemash wongel betekertstian. Not a part of eotc any more.

  ReplyDelete
 11. ወዳጄ ሰይፈ ገብርኤል አንድ ጭብጥ ካለው ዜና ውስጥ በጾም ጉዳይ ላይ የተጻፈ ይመስል ያን መዘህ ማውጣትና ነገሩን ከዋልድባ ወደ ጾም መመለስ ምን ይባላል? ይህን አካሄድህን ማረም የሚገባህ መስለኛል። አስተያየት መስጠት ካለብህም በተባለው ጉዳይ ነው እንጂ ያን ትተህ ያልተባለና በእግረ መንገድ የተጠቀሰን ነገር፣ ዋና ጉዳይ አድርገህ አስተያየት መስጠት በዋናው ጉዳይ ላይ ሀሳብ ለመስጠት አለመፈለግህንና እርሱን መቃረንህን ነው የሚያሳየው።
  አባ ሰላማ እስካሁን እያስነበበን ያለው ቤተክርስቲያናችን መጽሐፍ ቅዱስ በሚለው መሠረት ትመራ፤ ከመጽሀፍ ቅዱስ የሚቃረን ሀሳብ አታስተናግድ፤ ታስተካክል የሚል ነው። እኔ እንደመሰለኝ የዐቢይ ጾም ጉዳይ መነሳቱም ኦርቶዶክሳውያን ሁሉ የሚጾሙት ጾም መሆኑን ለማመልከት እንጂ ሌላ አይደለም። ደግሞም በኦርቶዶክሳውያን ዘንድ ጾሙ ታላቅ መሆኑ ይታወቃል። አባ ሰላማ አደረገ ያልከው የአቋም ለውጥ ታዲያ ምንድነው? ጊዜውን መጥቀስ አይቻልም ልትል ነው? አሁንም ራስህን ብትመረምር የተሻለ ነው። ብዙዎቹ እንደ አንተ ያሉ የማቅ ሰዎች አስተያየት ሲሰጡ በጉዳዩ ላይ ምንም ማለት ሲያቅታቸውና ውስጣቸው ሲቆጣ ከዚህ ቀደም እንዲህ ተባለ አሁን ደግም እንዲያ ተባለ ማለት ይቀናችኋል። አሁንም አስተያየት ካለህ በዋልድባው ጉዳይ ላይ አስተያየት መስጠት የሚገባህ እላለሁ።
  ሰላም

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሠይፈ ገብርኤልMarch 31, 2012 at 9:43 AM

   ከላይ ለሁሉም መልስ ይሆን ዘንድ ይህን ጽፌ ነበር ፡፡ "ወዳጄ አኔ ማህበረ ቅዱሳንን ለምን አጋለጡት ወይም ለምን ኰነኑት የሚል አቋም የለኝም ፡፡ ገለጻው ውስጥ ከአባ ሰላማ አቋም ጋር የማይዛመድ አረፍተ ነገር ሳይ በመደንገጤ ጻፍኩት ፡፡ ስለ እኔ ጽሁፍ ምክንያትም መስመራችሁን አትልቀቁ ፡፡ ግን ሲጻፍ ጥንቃቄ እንዲደረግ ለማሳየት ወይም የአቋም ለውጥ ካለ ለማወቅ ብዬ ነውና በገለጻዬ አትከፋ ፡፡ የእኔ ትኩረት ሁሌም አባቶቻችን በስንት ተጋድሎ ለእኛ ካስረከቡን ሃይማኖት ጋር በተዛመደው ላይ ብቻ ነው ፡፡"

   እዚህ ጋር ደግሞ የማኀበረ ቅዱሳን አባል እንደሆንኩ ተደርጐ ቀርቧል ፡፡ አዝናለሁ እኔ የክርስቶስ ወገን እንጅ የማንኛቸውም የእበላ ባይ ድርጅቶች አባል አይደለሁም ፡፡ ስለ ገዳማትና ስለ ቤተ ክርስቲያናችን መቆርቆሩ ፣ በእውነት ስለ እውነት ከልብ በናንተም ዘንድ ቢኖር ኖሮ ፣ በደቡብ ክልልና በጐንደር ቤተ ክርስቲያናት ፣ የአሰቦት ፣ የዝቋላና ሌሎችም ገዳማት ሲቃጠሉ ባይታዘን እንኳን እንደ ዜና መተንፈስ ይገባችሁ ነበር ፡፡ የአንድ ግለሰብ እስር ቤት መግባትን ዜና ያደረገ የቤተ ክርስቲያናችን ተቆርቋሪ ድረ ገጽ ፣ ቤተ ክርስቲያን ተቃጠለች ሲባል ውይ ያላለ ምን ስለሆነ ነው ይባል?

   በሥርዓቱ በእርጋታ አልተነበበ እንደሁ እንጅ በጽሁፉ የተባለውን ነገር በቅንፍ አስቀምጨ አቅርቤአለሁ ፡፡ ለማጋነን በማለት ያልተባለ አንድም ቃል አልጨመርኩም ፤ ያጐደልኩትን ለማየት እንዲቻልም ለአንባቢ የማግኛ አድራሻውን “http://www.abaselama.org/2012/02/read-pdf_23.html” በማለት አስቀምጫለሁ፡፡ ማኀበረ ቅዱሳንን ለመክሰስና ለመውቀስ ሲባል ብቻ ታላቅ ጾም የሚል ቃል መጠቀማችሁ አግባብ አይደለም ፣ ደበሎ ለብሶ ለማደናገርና በጾም የምታምኑ ለማስመሰል ይመስላል የሚል ጽሁፍ አቅርቤአለሁ ፡፡ የፊት ያስነበባችሁት ይህን ይላል ፤ የአቋምና የአመለካከት ለውጥ አድርጋችሁ እንደሁ አስቀድማችሁ አሳውቁን በማለት ለማወቅ በመጓጓት ጻፍኩ ፡፡ የሰጠሁት ርዕስ ራሱ ይህንን ነው የሚለፍፈው ፡፡

   ከዚህ በተረፈ በአንድ አንባቢ ወዳጅ ርዕስና ጭብጥ እያስቀየርክ ስለተባልኩና ስለተወቀስኩ እሺ ሁኑበት ብዬ ለወዳጄ መርቄ ተለይቼ ነበር ፡፡ አሁንም ከዛ የተለየ አቋምና እምነት የለኝም ፡፡ እግዚአብሔር ይርዳችሁ ፡፡ እኔን ግን በይሆናል አትቀቢኝ ፤ ተለጣፊ ስም መስጠት መጥፎ የፖለቲካ ባህላችን ቅሪት ነው ፡፡ ብሆን አላፍርበትም ፤ ሽንጤን ገትሬ ለማምንበት መከራከር እወድ ነበር ፤ ያልሆንኩትን ግን ነኝ ብዬ ለመሟገት አልችልም ፡፡ ምንም በግሌ የማውቀው መረጃ የለኝም ፡፡ በስማ በለው የሚባለውን ደግሞ የመቀበል ልምድ እኔ በተፈጥሮዬ የለኝም ፡፡ ድክመታቸውን በራሴ በግልጽ ባውቅ ግን ለመኰነን አላፍርም ነበር ፡፡

   መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ

   Delete
  2. ሠይፈ ገብርኤልApril 1, 2012 at 9:53 AM

   የቀደመውን የጽሁፍ አስተያየቴን ስላላወጣችሁት ይህን ሻል ያለውን በድጋሚ ጽፌአለሁ፤

   ሰላም ፣ ከላይ ለሁሉም አንባቢ ይሆን ዘንድ በማለት ይህን ጽፌ ነበር ፡፡ "ወዳጄ እኔ ማህበረ ቅዱሳንን ለምን አጋለጡት ወይም ለምን ኰነኑት የሚል አቋም የለኝም ፡፡ ገለጻው ውስጥ ከአባ ሰላማ /አቅራቢዎች/ አቋም ጋር የማይዛመድ አረፍተ ነገር ሳይ በመደንገጤ ጻፍኩት ፡፡ ስለ እኔ ጽሁፍ ምክንያትም መስመራችሁን አትልቀቁ ፡፡ ግን ሲጻፍ ጥንቃቄ እንዲደረግ ለማሳየት ወይም የአቋም ለውጥ ካለ ለማወቅ ብዬ ነውና በገለጻዬ አትከፋ ፡፡ የእኔ ትኩረት ሁሌም አባቶቻችን በስንት ተጋድሎ ለእኛ ካስረከቡን ሃይማኖት ጋር በተዛመደው ላይ ብቻ ነው "፡፡

   ታድያ ድጋሚ ተመሳሳይ አቤቱታ የተጻፈው ምን ለማለት ታስቦ ነው?

   አዎ እዚህ ጋር ደግሞ የማኀበረ ቅዱሳን አባል እንደሆንኩ ተደርጐ ቀርቧል ፡፡ አዝናለሁ እኔ የክርስቶስ ወገን እንጅ የማንኛቸውም የእበላ ባይ ድርጅቶች አባል አይደለሁም ፡፡ ስለ ገዳማትና ስለ ቤተ ክርስቲያናችን መቆርቆሩ ፣ በእውነት ስለ እውነት ከልብ በናንተም ዘንድ ቢኖር ኖሮ ፣ በደቡብ ክልልና በጐንደር ቤተ ክርስቲያናት ፣ የአሰቦት ፣ የዝቋላና ሌሎችም ገዳማት ሲቃጠሉ ባይታዘን እንኳን እንደ ዜና መተንፈስ ይገባችሁ ነበር ፡፡ የአንድ ግለሰብን እስር ቤት መግባት ዜና ያበሰረ የቤተ ክርስቲያናችን ተቆርቋሪ ፣ ቤተ ክርስቲያን ተቃጠለች ሲባል ውይ ያላለና ያላስተላለፈልን እንግዲህ ምን ስለሆነ ነው ይባላል?

   አሁንም ጽሁፌ በሥርዓቱ በእርጋታ አልተነበበ እንደሁ እንጅ ፣ በጽሁፉ የተባለውን ነገር እንዳለ በቅንፍ አስቀምጨ አቅርቤአለሁ ፡፡ ለማጋነን በማለት ያልተባለ አንድም ቃል አልጨመርኩም ፤ ያጐደልኩትን ለማየት እንዲቻልም ለአንባቢ የማግኛ አድራሻውን “http://www.abaselama.org/2012/02/read-pdf_23.html” በማለት አስቀምጫለሁ፡፡ ማኀበረ ቅዱሳንን ለመክሰስና ለመውቀስ ሲባል ብቻ ታላቅ ጾም የሚል ቃል መጠቀማችሁ አግባብ አይደለም ፣ ደበሎ ለብሶ ለማደናገርና በጾም የምታምኑ ለማስመሰል ይመስላል የሚል ስሜቴን በጽሁፍ ገልጫለሁ ፡፡ የፊት ያስነበባችሁት ይህን ይላል ፤ የአቋምና የአመለካከት ለውጥ አድርጋችሁ እንደሁ አስቀድማችሁ አሳውቁን በማለት ለማወቅ ያለኝን ፍላጐት ጻፍኩ ፡፡ የሰጠሁት ርዕስ ራሱ ይህንን ነው የሚለፍፈው ፡፡

   ከዚህ በተረፈ አስቀድሞ በአንድ አንባቢ ወዳጅ ርዕስና ጭብጥ እያስቀየርክ ስለተባልኩና ስለተወቀስኩ እሺ ሁኑበት ብዬ ወዳጄን መርቄ ተለይቼ ነበር ፡፡ አሁንም ከዛ የተለየ አቋምና እምነት የለኝም ፡፡ እግዚአብሔር ይርዳችሁ ፡፡ እኔን ግን በይሆናል አትቀቢኝ ፤ ተለጣፊ ስም መስጠት መጥፎ የፖለቲካ ባህላችን ቅሪት ነው ፤ ሁሉ ባለ አንድ መሆን አይችልም ፤ የተለየ ኃሳብ ያለው በተለየበት ሃሳቡ ላይ አስተያየት መጻፍ እንጅ ዝርያ መስጠቱ ስህተት ነው ፡፡ እኔ ከዚህ በፊት ስም ስታወጭልኝ አንቺንም የክርስትና ስም ለጥፌልሽ ነበር ፡፡ ስም መሰጣጠት ያንን ዓይነት ችግር ነው የሚያስከትለው ፡፡ አባል ብሆን አላፍርበትም ነበር ፤ ሽንጤን ገትሬ ለማምንበት መከራከር እወድ ነበር ፤ ያልሆንኩትን ግን ነኝ ብዬ ለመሟገት አልችልም ፡፡ ምንም በግሌ የማውቀው መረጃ የለም ፡፡ እንደ እናንተው በ http://eotc-mkidusan.org/ ድረ ገጽ የሚጽፉትን አነባለሁ ፤ በ http://tewahedomedia.org/ ደግሞ መዝሙርና ስብከት አደምጣለሁ ፡፡ የእናንተን ያህል የክስና የአቤቱታ መልዕክት ግን አንብቤበት አላውቅም፡፡ በስማ በለው የሚባለውን ደግሞ የመቀበል ልምድ እኔ በተፈጥሮዬ የለም ፡፡ የእናንተን እውነት አድርጌ የእነሱን ሃሰት የምልበት ፣ በሌላው ደግሞ የናንተን ሃሰት ብዬ የእነርሱን እውነት የምልበት ምንም የማውቀው ተጨባጭ ምክንያት የለኝም ፡፡ ድክመታቸውን በግልጽ በራሴ የማወቅ ዕድሉ ቢያጋጥመኝ ግን ለመኰነን አላፍርም ነበር ፡፡

   ለእናንተ መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ
   ለሁላችንም እግዚአብሔር ሰላምና ፍቅሩን ያድለን

   Delete
  3. "ስለ ገዳማትና ስለ ቤተ ክርስቲያናችን መቆርቆሩ ፣ በእውነት ስለ እውነት ከልብ በናንተም ዘንድ ቢኖር ኖሮ ፣ በደቡብ ክልልና በጐንደር ቤተ ክርስቲያናት ፣ የአሰቦት ፣ የዝቋላና ሌሎችም ገዳማት ሲቃጠሉ ባይታዘን እንኳን እንደ ዜና መተንፈስ ይገባችሁ ነበር ፡፡ የአንድ ግለሰብን እስር ቤት መግባት ዜና ያበሰረ የቤተ ክርስቲያናችን ተቆርቋሪ ፣ ቤተ ክርስቲያን ተቃጠለች ሲባል ውይ ያላለና ያላስተላለፈልን እንግዲህ ምን ስለሆነ ነው ይባላል?" ውንድሜ የዋህ ነህና እስካሁን ማንነታቸውን አላወቅህም አንዴ??! እነሱ የገዳመቶቻችን መቃጠል እልል ያስብላቸዋል እንጂ እንዴት ያቆረቁራቸዋል??! ቢሆን አጋጣሚውን ቢያገኙ ቤንዚን ያርከፈክፋሉ (ለቃጠሎው መንስኤ እጃቸው ከሌለበት ማለት ነው ግን እጠራጠራለሁ) ግን ያሰቡት አልሆነም እና ኩም አሉ እርር ድብን አሉ አሁን ደሞ ዋልድባ እንዲፈርስላቸው ደፋ ቀና እያሉ ነው ግን ምንግዜም እግዚያብሄር ከኛ ጋ ነው እና ምንም እንደማይመጣ እናውቃለን ማህበረ ቅዱሳንንም ለምን እንደጠሉት ማንም ማሰቢያ አይምሮ ያለው ሰው ይገነዘበዋል እና ወንድሜ የዋህነትህን ትተህ ማንነታቸውን በደንብ ለይተህ እወቅ!! (መቼም ይሄ መልዕክት ለሰይፈ ጋብርኤል እንደማይደርሰው አውቃለሁ ግን የውስጤን ተንፍሻለሁ

   Delete
 12. You only want to acuse mk but you never write on what should be done for waldiba and ziquala# lairs

  ReplyDelete
  Replies
  1. ትገርማላችሁ:: ዛፍ: ደኖች ሲወድሙ, ምንም ያልገደዳችሁ:: ቆይ እስቲ ማኅበረ ቅዱሳን ዓላማ ይኑረው ይባል:: ለምን ሳቱን እያጠፋችሁ አትማገቱም:: ማፈሪያ ነገር ናችሁ:: እናንተን ብሎ ለቤተ/ያን ተቆርቃሪ::

   Delete
 13. betam tasazenalachu ebakachehu fetaren feru lesmu yednbune lebse lebsachu hayemanotachnen yemyasafer negr eyaregachu ategudune ebakachu fetare yehunen

  ReplyDelete
 14. አይ አዛኝ ቅቤ አንጓች ሆናችሁ
  እናንተስ ቦለቲካ አይደል ያወራችሁት ስለጾም ተቆርቋሪ ነን እያላችሁ

  ReplyDelete
 15. EGZIABHER NEGESEA AHIZABEM DENEGETU , , , , , ,

  YESTERDAY, TODAY & TOMORROW MK is striving for the development and progress of Christians and international community's spirituality as well.

  YEMENEDGIFEWUN ,,,,YEMENEKAWOMEWUN LEYITEN ENWOK !!!!!!!

  ReplyDelete
 16. ወትሮም ቢሆን ገዳም፣ “ጽድቅ ገዳም በመግባት ይገኛል” በሚለው ኢመጽሀፍ ቅዱሳዊ ስብከት ተደልለው ጽድቅን ፈልገው የሚመንኑ መነኮሳት መኖሪያ ብቻ ሳይሆን የብዙ ወንጀለኞች መደበቂያም እንደሆነ ይታወቃል።
  WHAT DO YOU MEAN WHEN YOU SAY E-MESEHAF KIDUSAWI SIBKET TEDELELEW?

  ReplyDelete
 17. enante were were were were .....nachihu.....egziabher lib yistachihuna ketifat menged yimelsachihu...mahibere kidusan yeserawun esti eyuna enantem siran askedimu. kewere yilik tegbar yinurachihu.

  ReplyDelete
 18. አረ ለመሆኑ ከርስቶስ በገዳመ ቆሮንቶስ መፆሙ ተረስቶ ነው በገዳም መፆም መፀለይ ኢ-ምፀሃፋው የሆነው? ትንሽ አታፍሩም?

  ReplyDelete
 19. lehulum gizew ahun new tsom mefetegna new. sira yefera tegnto yahelmal. wore atimajoch mahiberu yeserawn kemekonen nuna temaru. metsaf kidus tirasachihu engi ere lemehonu sletsom kibir ena tsega andimita yet tawkaleh...


  tadele asm

  ReplyDelete
 20. yeketema menagnoch enanten baiktachehu mahiberun poletica gar malatemu yekibachihu negeru keemnetum kepoleticawm mehon yakatachihu erasachihun maskemecha yatachihu nachihu. lemehonu silemahiberu tiru alemehon betsom wokit lantes tegebi new tsomin yawoke gedam yikemetal eng serategnan aykoninm

  tade

  ReplyDelete
 21. aba selama man endehone,sele mahibere kidusan yemitsifew entewew ena, sele betekirstiyan gin minim aykorekorim,be betekirstiyan yalew neger yemitay gilts silehone ke aba selama merega ayasfelgenim.manim rasun kebetekirstiyan yemiley rasun yileyal engi betekirstiyan ayleyim. sele waldba,sele zikuala... wezete lemechenek,lemaseb ethiopiawi mehone bicha yibeka neber...

  ReplyDelete