Thursday, March 29, 2012

የቀረልን ዘር - - - Read PDF

“የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘር ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ሰዶም በሆንን ገሞራንም በመሰልን ነበር” (ኢሳ. 1፥9)
ለቅድስት ድንግል ማሪያም ተሰጥተው ከተተረጎሙት የብሉይ ኪዳን ጥቅሶች መካከል ይህም ተጠቃሽ ነው፡፡
በኢየሩሳሌም የሚኖሩ የይሁዳ ሰዎች በእግዚአብሔር ላይ በማመፅ በኃጢአት ላይ ኃጢአትን እየጨመሩ እግዚአብሔርን ስላሳዘኑት ለከፋ ችግር እንደሚጋለጡ፣ አገራቸውም በጠላቶቻቸው ተቃጥላ እንደምትፈራርስ፥ ባዕዳን ሰዎችም እንደሚጠቀሙባት ሕዝቡም ለምርኮና ለብዝበዛ እንደሚሰጥ ነቢዩ ኢሳይያስ በግልጽ ተናግሯል፡፡ (ኢሳ. 1፥2-8፤ 2ነገ. 20፥17-18)።
(ቁ. 9) ላይ የተነገረው ትንቢት ለጊዜው ከባቢሎን ምርኮ ስለሚተርፉት ቅሬታዎች ሲሆን (ነህ. 1፥3) ፍጻሜው ደግሞ ክርስቶስ ወደ ወገኖቹ መጥቶ ወገኖቹ ሊቀበሉት ባለመቻላቸው ምክንያት መዳንን ለመውረስ ባይታደሉም በኋለኛው ዘመን የአሕዛብ ሙላት ሲፈጸም የእስራኤል ቅሬታዎች በክርስቶስ አምነው እንደሚድኑ ያሳያል፡፡ (ኢሳ. 10፥22-23፤ ሮሜ 11፥25-27)።ይበልጥ ደግሞ ቅ/ጳውሎስ በሮሜ 9፥29 ላይ የኢሳ. 1፥9ን ቃል ጠቅሶ በመናገሩ ትንቢቱ ከመጀመሪያው ጀምሮ የተነገረበትን ዓላማ በትክክል አስቀምጧልና ከዚህ ያለፈ ሌላ ትርጉም ሊሰጠው አይችልም፡፡
ትንቢቱን ያለመልእክቱ ለድንግል ማርያም የሰጡት ክፍሎች “ዘር ባያስቀርልን ኖሮ” የሚለውን “አንቺን ባያስቀርልን ኖሮ” በሚለው ተክተው በድርሰታቸው ውስጥ እናነባለን፡፡ “ከመ ሰዶም እም ኮነ ወከመ ገሞራ እመሰልነ እግዚአብሔር ኪያኪ እመ ኢያትረፈ ለነ” “እግዚአብሔር አንቺን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ሶዶም በሆንን ገሞራንም በመሰልን ነበር፡፡” (ማሕሌተ ጽጌ)
በአተረጓጎማቸው ብንሄድ እንኳ የቀረልን ዘር ብለን ልንጠራው የሚገባ ከእርሷ የተወለደውን ክርስቶስን መሆን ይኖርበታል፡፡ እሱ ገና ከመጀመሪያው “የእባቡን ራስ ይቀጠቅጣል፡፡” ተብሎ ተስፋ የተጣለበት የሴቲቱ ዘር ነውና፡፡ (ዘፍ. 3፥15)።
እግዚአብሔር ዓለምን ለማዳን ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ልኮ ከድንግል ማርያም እንዲወለድ ሲያደርግ እርሷን ለዚህ ታላቅ እድል መርጦ አንጽቶ ቀድሶ አክብሯታል፡፡ ይህን ሁኔታ የምንገልጸው ግን በኢሳ. 1፥9 ሳይሆን በሉቃ. 1፥28 ነው፡፡ ኢሳ. 1፥9ን ለእርሷ የተሰጡበት ምክንያት እርሷን ከሰው ዘር የተለየች ፍጥረት አድርገው ለመመልከትና ጌታ ለእርሷ ካሣ እንዳልከፈለላት ወይም እንዳልሞተላት ለመግለጽ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ለዚህ ግን የሌላውን ምስክርነት ሳንጠቅስ በፊት ራሷ የተናገረችውን ነው የምናስቀድመው፤ “መድኃኒቴ” ብላ ለምን ጠራቸው? ጌታ ለእርሷም ጭምር እንደሞተላትና ካሣ እንደከፈለላት ለማመልከት አይደለም? (ሉቃ. 1፥47)።
ቅ/ያሬድ ይህን ሲያስረዳ፡- “. . . አስመ በእንቲአሃ ወበእንተ አዝማዲሃ ተሰቀልኩ ዲበ ዕፅ ከመ አድኅኖሙ አዳምሃ አቤልሃ፥ አብርሃምሃ፥ ይስሐቅሃ ወያዕቆብሃ፥ ወባዕዳነ ነቢያተ እለ ከማሆሙ ዐቀቡ ሕግየ ከመ በላዕሌሆሙ እሰባሕ እስከ ለዓለም ዓለም”
ትርጓሜ፡- “ስለ እርሷና (ስለማርያም) ስለወገኖቿ በዕንጨት ላይ ተሰቀልኩ፥ አዳምን አቤልን፥ አብርሃምን፥ ይስሐቅን  ያዕቆብን ሌሎችን ነቢያትንና እንደነርሱ ያሉትን ሕጌን የጠበቁትን አድናቸው ዘንድ፥ በእነርሱም እስከ ዘላለም ድረስ እመስገን ዘንድ፡፡” (የኅዳር ጽዮን ቅንዋት)።
“የኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ክ መሠረት ሃይማኖት የካህናት ተልእኮ በተሰኘው መጽሐፍ ገጽ 29 ላይ የሚከተለው ተጽፎአል፡፡” አንዳንዶች እመቤታችን አድሮ ነበረው የአዳም ጠባይ ወይም ጥንተ አብሶ እንደሌላባት ያስተምራሉ፡፡ ነገር ግን ይህ ትምህርት በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ተቀባይነት የለውም፡፡ ምክንያቱም እመቤታችን ከኢያቄምና ከሐና በሩካቤ ዘበሕግ የተገኘች ናት እንጂ ከሰማይ የወረደች የመላእክት ወገን አይደለችምና፤ ካሳ የማያስፈልጋትም ሳትሆን ክርስቶ በደሙ ከዋጃቸው ካሣም ከተከፈላላቸው ወገን ናት፡፡”
ምንጭ፡- የተቀበረ መክሊት ገጽ 120

11 comments:

 1. እግዚአብሔር ዓለምን ለማዳን ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ልኮ ከድንግል ማርያም እንዲወለድ ሲያደርግ እርሷን ለዚህ ታላቅ እድል መርጦ አንጽቶ ቀድሶ አክብሯታል፡፡good job......

  ReplyDelete
 2. Ere befeterachu!!!

  ReplyDelete
 3. Mk meletary base found in waldeba. The tareget to kill innocent , pateriarc and gov. official. Auuu mk belan gezebachen auuuu auuuuuuuuu

  ReplyDelete
 4. Good job, keep revealing the truth.

  ReplyDelete
 5. We will be notify mk khat addicted deacon and priest false name supported by picture and video.

  ReplyDelete
 6. Mk in other word poltical party that founded by aba gebril for menkosat killer hater of lekawont.

  ReplyDelete
 7. ahunis minim tesfa yelenim.Mk eyale betekiristianin mastekakel fetsimo ayichalim.mejemria mehon yalebet mk'n matifat new.ene yemigermegn merejawun keyet endemiagegnut new. yemengist selayoch sayihonu ayikerim.

  ReplyDelete
 8. Absolutely, I agreed ur comment, but tekat megemer leke end mk yewotader hail maderaget beygubae kelebat of mk leyeto bememetat mk matfat yichalal. Programu we do not need permit to start. Just all eotc do it.

  ReplyDelete
 9. yechi yana loter kmam nat,twawkenal.kkkkkkkk

  ReplyDelete
 10. Ene lezhi yewotader adregaget metoshi estalu betkerstian lemadan mk lematfat, if you start wotaderawe tegel.

  ReplyDelete