Monday, April 30, 2012

የጊዮርጊስ በዓል በጦር አምላክ ምትክ የተሰራ በዓል ነው

“ ‘ኦሪስ’ ወይም ‘ማርስ’ የጦር አምላክ ተብሎ ሲመለክ የኖረ ጣኦት ነው በእርሱ ምትክ ዛሬ ቅዱስ ጊዮርጊስን የወታደሮች ጠባቂ ብለው በየአመቱ ያከብራሉ፡፡”
ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ
ገድለ ጊዮርጊስ እንደሚተርከው ጊዮርጊስ በጌታ ስም ያደረገላትን ድንቅ ነገር ተመልክታ አንዲት መበለት “አምላከ ገሊላውያን ተመሲሎ ሰብአ ወረደ እም ሰማይ ወቦአ ውስተ ቤትየ፤ ማለትም - የገሊላውያን አምላክ ሰውን መስሎ ከሰማይ ወረደ ወደ ቤቴም ገባ” በማለት ሰገደችለት። ጊዮርጊስ ግን መልሶ “ተንሥኢ ብእሲቶ አንሰ ኢኮንኩ አምላከ ገሊላውያን አላ ገብሩ ሎቱ - አንቺ ሴት ተነሺ! እኔ የገሊላውያን አምላክ አይደለሁም፤ አገልጋዩ ነኝ እንጂ” (ገድለ ጊዮርጊስ ገጽ 92)

“ይቤ ጊዮርጊስ ኀበ መኑ እኔጽር? ዘእንበለ ኀበ የዋህ ወትሑት ዘየዓቅብ ትእዛዝየ ወያከብር በዓልየ ያዕርፍ ሰላምየ ላዕሌሁ፡፡”

ትርጓሜ፡- “ጊዮርጊስ አለ ወደማን እመለከታለሁ? ሰላሜ በእርሱ ላይ ያርፍ ዘንድ በዓላቴን የሚያከብር ትእዛዜን የሚጠብቅና ትሑትና የዋህ ወደሆነው ካልሆነ በስተቀር፡፡” (የካቲትና የሚያዚያ ጊዮርጊስ ዚቅ)

Saturday, April 28, 2012

ማኅበረ ቅዱሳን እና ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልእ አይተዋወቁም

አክራሪውና ወግ አጥባቂው የሰለፊያ የግብር ወንድም ማኅበረ ቅዱሳን የተመሰረተበትን 20 ዓመት ሰባት ያህል ወራትን አሳልፎ ሚያዝያ 27 በእግር ጉዞ ሊያከብር መሆኑን ሲገልጽ የቆየ ቢሆንም፣ የተመዝጋቢ ቁጥር በማነሱና በሌላም ምክንያት መራዘሙ እየተወራ ነው። ይሁንና ማስታወቂያው ላይ በትልቁ የብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ፎቶ ተሰቅሏል። የእርሱ የጉዞ መርሀ ግብርና አቡነ ጎርጎርዮስ፣ የእርሱ 20ኛ ዓመትና አቡነ ጎርጎርዮስ ምን እንዳገናኛቸው ለጊዜው ባይታወቅም ብቻ ፎቷቸው በትልቁ የማስታወቂያው ማዳመቂያ ሆኗል።
ከ1980 ብፁዕነታቸው እስካረፉበት እስከ 82 ዓ.ም ድረስ ወደ ዝዋይ የካህናት ማሰልጠኛ ገብተው የተማሩ አንዳንድ የዩኒቨርሲቲና የኮሌጅ ተማሪዎች መካከል አንዳንዶቹ በኋላ ላይ የማኅበረ ቅዱሳን መስራቾች እንደነበሩ ይነገራል። ይህን አጋጣሚ መነሻ በማድረግ ነው ማኅበሩና የማኅበሩ ሰዎች ብፁዕነታቸውን የማኅበሩ መስራች አባት አድርገው ይቆጥራሉ።

Friday, April 27, 2012

የማኅበረ ቅዱሳን ህገ ወጥ ሱቆች እየታሸጉ ነው

Read in PDF

ሊያደርግ ያቀደውን የእግር ጉዞ ለሌላ ጊዜ አስተላለፈ
በመጀመሪያ ደጀ ሰላም (dejeselaam) ከዚያም አስከትሎ ደጀ ብርሃን እንደዘገቡት ፦ አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙ የ"ማኅበረ ቅዱሳን" ሱቆች ላይ የማሸግ እርምጃ መወሰዱን የደረሱን መረጃዎች አመለከቱ፡፡ በተለይም በኡራኤልና በሜክሲኮ አካባቢ የሚገኙ የ"ማኅበረ ቅዱሳን" ሱቆች ላይ "ባልተፈቀደ የንግድ ሥራ ላይ ስለተሠማራ ሱቁ ታሽጓል" በሚል ማስታወቂያ የታሸጉት እነዚህ ሱቆች፣ "ማኅበረ ቅዱሳን" ከማንኛውም አካል የንግድ ሥራ ፈቃድ ሳይወስድ የሚሠራባቸው መደብሮች መሆናቸው ታውቋል፡፡
"ማኅበረ ቅዱሳን" በፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ እንዲሁም በቤተክርስቲያን ስም እና በራሱ ስም እያዛነቀ ሚናው ባልለየ እንቅስቃሴ ውስጥ እዚህም እዚያም የሚነከር በመሆኑ በሰሞኑ ከሕግ ጋር ለመፋጠጥ ተገዷል ተብሏል፡፡ ከንግድ ሥራ ጋር በተያያዘም ለመንግሥትም ሆነ ለቤተክርስቲያን ተገቢውን ገቢ ሳያስገባ ዝም ብሎ የሚዘርፍ ድርጅት እንደመሆኑ መጠን ሕጋዊ መሥመር እንዲይዝ ሲደረግ ጨርሶ ፈቃደኛ ሊሆን አለመቻሉ ተገልጿል፡፡

Thursday, April 26, 2012

ኤፍሬም እሸቴ: ብትስማማ ነው እንጂ የሚያስደምመው ባለመስማማትህ ምን ይደንቃል?

በዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤልRead in PDF
ጥብቅ ማሳሰቢያ፦ ጽሑፉ የኢትዮጵያን ጠቅላይ ሚኒስትር በመደገፍ የተጻፈ ጽሑፍ አይደለም:: ጽሑፉ ኤፍሬም እሽቴ የተባለው አንድ "የማህበረ ቅዱሳን" የስራ አመራር አባል ግለሰብ “ጠ/ሚኒስትሩ ስለ ማኅበረ ቅዱሳን በተናገሩት አልስማማም” ሲል ከግንዛቤ እጥረት የተነሳ በጻፈው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን አስተምህሮ የማይወክል ዝርው ይዘት ያለው ጥሬ ጽሑፍ አስቸኳይ እርምት እንዲደረግበትና በክርስትና ስም በአንባቢያን ላይ የፈጠረውን ብዥታ ግምት ውስጥ በማስገባት የተጣራ ምስል ለመስጠት ኩልል ቅልብጭ ባለ መልኩ የተዘጀ ጽሑፍ ነው::

Wednesday, April 25, 2012

የተክለ ሃይማኖት አጥንት ባለበት ቦታ ቁርባን የተቀበለ ሁሉ ሲዖልን አያይም - ገድ/ተ/ሃይ/ ም 62 ቁ 3 (የደብረ ሊባኖስ ዶክትሪን)

ማህበረ ቅዱሳን ተከታዮችን ያፈዘዘበትና አክራሪ ወገኛ ካደረገበት የስሕተት ትምህርቶች ውስጥ አንዱ የተከለ ሃይማኖት ታሪክና የመቃብራቸው ሁኔታ ነው።
ተክለ ሃይማኖት በታሪክ ተመራማሪዎች እንደተረጋገጠው የወሎ ላስታን መንግሥት በሃይማኖት ሽፋን መገልበጣቸው ነው። ልክ ማህበረ ቅዱሳን ዛሬ እየሄደ ያለው በርሳቸው ዘዴ ነው። መንግሥቱን በስብከትም በጦርነትም ከገለበጡ በኋላ የዳዊት ዘር ነኝ ለሚለው ላክስታቸው ልጅ ለይኩኖ አምላክ ሰጥተውታል። ይኩኖ አምላክም «ኢይጠፍእ ምስፍና ወምልክና እምነ አባሉ ለይሁዳ» (መንግሥትና ገዢነት ከይሁዳ ዘር አይጠፋም) የሚለውን ለጌታ ለኢየሱስ ክርስቶስ የተነገረውን ቃል ለራሱ በማድረግ በኢትዮጵያ ላይ አወጀ። ይህንም የሃይማኖት አባቱ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አጸደቁት። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የዘር ፖለቲካው በኢትዮጵያ ሥር የሰደደ ካንሰር ሆኖ ይገኛል።

«አንድ ሀገር አንድ ሃይማኖት» የሚለው አባባል “ሕገ መንግሥት” ላይ ብቻ ሳይሆን በክርስትናም ላይ የተቃጣ የጸረ- ክርስቶሱ ሃሳዌ መሲህ አጀንዳ ነው!

በዲ/ ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
      የዲ/ን ሙሉጌታ ጠንካራ መልዕክት የአባ ሰላማ አዘውታሪዎች እንዳያመልጣችሁ ከ ዐውደ ምህረት እንድታነቡ እንጋብዛለን

Monday, April 23, 2012

ዲ/ን ኤፍሬም እሸቴ - ጠ/ሚኒስትሩ ፣ ስለ ማኅበረ ቅዱሳን በተናገሩት ትስማማለህ አትስማማም?

 Read in PDF
በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቻናል 3 ላይ የሚተላለፍና “እስማማለሁ፣ አልስማማም” የተሰኘ አንድ የቴሌቪዥን ፕሮግራም አለ። በዚህ ፕሮግራም ለእድለኛ ከ1 ሳንቲም ጀምሮ እስከ 15 ሺህ ብር ድረስ ሽልማት አለ። በጨዋታው ህግ መሰረት ተጋባዡ እንግዳ ሽልማቶቹ ከተቀመጡባቸው ሳጥኖች መካከል አንዱን በመጀመሪያ ይመርጥና ይቀመጣል። ከዚያ ሌሎቹን ሳጥኖች በየተራ እየጠራ በውስጣቸው ያለው የገንዘብ መጠን ተከፍቶ ይታያል። በየጣልቃው ባንከሩ (the banker) እንዲስማማ የሆነ ብር ያቅርብለታል። እንግዳው አልስማማም ካለ ጨዋታው ይቀጥላል፤ እስማማለሁ ካለ ግን ጨዋታው እዚያ ላይ ያቆምና ባንከሩ የሰጠውን ብር ይወስዳል። ኤፍሬም እሸቴ /ሚኒስትሩ ስለ ማኅበረ ቅዱሳን በተናገሩት አልስማማምሲል በድረ ገጹ ላይ ከሰሞኑ ፖስት ያደረገው ጽሑፍ ርእስ ይህን የመዝናኛ ፕሮግራም አስታወሰኛና ነው በዚህ የጀመርሁት እንጂ የዚህ ጽሁፍ አላማ ስለእስማማለሁ አልስማማም ለመናገር አይደለም። 

Sunday, April 22, 2012

ጥንተ አብሶ የጊዜው አጀንዳ - ክፍል 2

«የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት፥ ሥርዓተ አምልኮትና የውጭ ግንኙነት» በተሰኘውና ማኅበረ ቅዱሳን በዋናነት «ማርያም ጥንተ አብሶ የለባትም» ለማለት እየጠቀሰው ባለው መጽሐፍ ሥራ ላይ ከተሳተፉት መካከል አንዳንዶቹ ማርያም ጥንተ አብሶ አለባት የሚል አቋም ያላቸው ናቸው፡፡ ለምሳሌ መጋቤ ብሉይ ሰይፈ እና ብፁዕ አቡነ ገብርኤልም ይጠቀሳሉ፡፡
ታላቁ ሊቅ መጋቤ ብሉይ ሰይፈ ከብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ጋር በጻፉት መጽሐፍ ላይ እንዲህ ብለዋል።
አንዳንዶች እመቤታችን አድፎ የነበረው የአዳም ጠባይ ወይም ጥንተ አብሶ እንደሌለባት ያስተምራሉ። ነገር ግን ይህ ትምህርት በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ተቀባይነት የለውም። ምክንያቱም እመቤታችን ከኢያቄምና ከሐና በሩካቤ ዘበሕግ የተገኘች ናት እንጂ ከሰማይ የወረደች የመላእክት ወገን አይደለችምና፤ ካሳ የማያስፈልጋትም ሳትሆን ክርስቶስ በደሙ ከዋጃቸው ካሣም ከተከፈላላቸው ወገን ናት።» (የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መሠረት ሃይማኖት እና የካህናት ተልእኮ ገጽ 29)።
ብጹዕ አቡነ ገብርኤልም በልደታ ለማርያም የኢ.ኦ.ተ.ቤተክርስቲያን ጋዜጣ በግንቦት 1997 ዓ.ም እትም ላይ የሚከተለውን ሀሳብ አስፍረዋል።… ቅድስት ድንግል ማርያምን የወለዱ ኢያቄምና ሐና ከአዳም ሲወርድ ሲዋረድ ከመጣው አበሳ (ኃጢአተ አዳም) ንጹሐን ነበሩ ወይም ቅድስት ድንግል ማርያም ከመፀነሷ በፊት ቅዱስ ገብርኤል ወይም ራሱ መንፈስ ቅዱስ ከውርስ ኃጢአት ሐናንና ኢያቄምን አነጻቸው የሚል ቃል ከመጻሕፍተ አበው፣ ከመጻሕፍተ ሊቃውንትንና ከመጽሐፍተ ትውፊት ተፈልጎ ባለመገኘቱ እነሆ ምሁራኑ «በቅድስት ድንግል ቅድመ ብሥራት የአዳም ኃጢአት ነበረባት፤ የለም ፈጽሞ አልነበረባትም» በመባባል የጦፈ ክርክር በማድረግ ላይ ይገኛሉ። በዚህ ረገድ ከላይ የጠቀስነው  ዋቢ ቃል በመታጣቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሊቃውንትና መጻሕፍቱን የማስማማ ክፍል አልተገኘም።

Thursday, April 19, 2012

ማህበረ ቅዱሳንና ሰለፊያ!! ግልባጩ ማነው? - - - Read PDF

ከአውደ ምሕረት የተወሰደ

የማህበረ ቅዱሳን ሰለባ የሆኑ ብዙ የቤተክርስቲያን አባቶችና ልጆች ማቅን በአሸባሪነት ከፈረጁት ዓመታት የተቆጠሩ ቢሆንም፣ ማቅ ግን እንዲህ የሚሉኝ ለቤተ ክርስቲያን ጥብቅና ስለቆምኩ ነው በሚል ራሱን ሲከላከል ቆይቷል። ማህበሩ አሸባሪ የመሆኑ ጉዳይም በአንዳንዶች ዘንድ እንደ ስድበ ሲቆጠር መቆየቱ ይታወሳል። ለማኅበሩ ይህ ስም የተሰጠው በከንቱ አልነበረም። ስራው በአክራሪ ሙስሊሞች ከሚካሄደው የበለጠ እንጂ ያላነሰ ሆኖ ስለተገኘ ነበር ይህ የግብር ስም የወጣለት።

Wednesday, April 18, 2012

ከኦርቶዶክሱ ሰለፊያ - ማኅበረ ቅዱሳን ራሳችንን እንጠብቅ - - - Read PDF

ስለማኅበረ ቅዱሳን ብዙ ስንል ቆይተናል፡፡ በ09/08/04 በተደረገው የፓርላማ ስብሰባ የተሰማው የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር የማህበረ ቅዱሳንን ማንነት ያጋለጠ ነው፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ በሃይማኖት ሽፋን የሚንቀሳቀሱ በኦርቶዶክስ በኩል ማኅበረ ቅዱሳን በእስልምና በኩል ደግሞ ሰለፊያ መሆናቸውን መግለጻቸው ማኅበረ ቅዱሳን ምን እያደረገና በቤተ ክርስቲያን ብቻም ሳይሆን በአገር ላይ የደቀነው አደጋ ምን እንደሚመስል ፍንትው አድርጎ ያሳየ ነው፡፡ ይህም ማኅበሩ እያራመደ ባለው አክራሪነት ሳቢያ ከምን ጊዜውም ይልቅ በመንግስት ጥርስ ውስጥ መግባቱን ያመላክታል፡፡ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስተር « ማህበረ ቅዱሳን » ብለው የማህበሩን ስም በመጥራት አክራሪነቱን በሚዲያ ይፋ ማውጣታቸው በራሱ ትልቅ ነገር ብቻ ሳይሆን ነገሩ ተራ አለመሆኑንም የሚያመልክት ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ - ስለ ማህበረ ቅዱሳን፣ ሰለፊ እና አጠቃላይ የሃይማኖት አክራሪነት

ውድ የአባሰላማ ጡመራ አንባቢያን፦


በትላንትናው ዕለት አቶ መለስ ዜናዊ  አንዳንድ አክራሪ የሰለፊ የእስልምና እምነት ተከታዮችን (ወሀቢ) እና ማህበረ ቅዱሳንን ከ አልካይዳ ጋር አገናኝተው በሰጡት አስተያየት ዙሪያ ሰፋ ያለና እውነታን ያዘለ ዘገባ እንደምናጠናክር እየገለጽን እስከዚያው የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ላይ ያለውን እንዲያዳምጡ እንጋብዛለን

ለማዳመጥ እዚህ ላይ ይጫኑ

Tuesday, April 17, 2012

ዘፈንን ከማውገዝ የተሻለ ዝማሬ ማቅረብ!

ከዚህ በፊት ልዩ ልዩ ጽሑፉችን በብሎጋችን ላይ ያቀረበው ዲያቆን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል በዚህ ርዕስ ዙሪያ መጽሐፍ ቅዱስን መሰረት በማድረግ እይታውን ይለግሰናል።  ጽሑፉን ያወያየናል በሚል ለአንባብያን አቅርበነዋል።

ጽሑፉን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

Monday, April 16, 2012

ክርስቶስ ተነስቷል!

ክርስቶስ ተነሥቷል ከሙታን
በታላቅ ኃይል እና ሥልጣን
ነጻ አውጥቷል አዳምን
ከዚህ በኋላ ደስታና ሰላም ይሁን።

Sunday, April 15, 2012

ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በቅርቡ እንደ አዲስ ያቋቋሙትን የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው የመንበረ ጵጵስና ሀገረ ስብከት ቅዱስ ሲኖዶሱ አጸደቀው።


ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ለአቡነ ፋኑኤል በደረሱ ሁለት ደብዳቤዎች በቅርቡ አቡነ ፋኑኤል ያከናወኗቸው የሀገረ ስብከት ማቋቋምና የስቴት ቤተ ክህነት ሊቀ ካህናት ምደባ የመንበረ ፓትርያርክ ጽ/ቤት እንዳጸደቀ እና እውቅና እንደሰጠ ገለጠ። ደብዳቤዎቹም አዲስ የተመረጡት አካላት እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ እንደ አንድ ልብ መካሪ በመሆን የሀገር ስብከቱን መዋቅር በማጠናከር እንዲሰሩ ያሳስባሉ።
የመንበረ ፓትርያርኩን ደብዳቤዎች ከዚህ በታች አስቀምጠናል።

Thursday, April 12, 2012

ማህበረ ቅዱሳን በዲ/ን ያረጋል አበጋዝ ላይ የስለላ መዋቅሩን ዘረጋ - - - Read PDF

ምንጭ፡- ከዐውደ ምሕረት
“የቤተክርስቲያን አባቶች የጻፉትን መጻህፍትም ሆነ የቤተክርስቲያን አባቶችን መቶ በመቶ አንቀበልም። መቶ በመቶ የምንቀበለው መጽሐፍ ቅዱስንና ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ብቻ ነው።” ዲ/ን ያረጋል አበጋ
ማኅበረ ቅዱሳን በየወሩ በሚያካሂደው የማኅበሩ አባላት የሆኑ አገልጋዮች ውይይት  ላይ የማኅበሩ አፍ ሆኖ በተለያዩ ቦታዎች እና አዳራሾች በግንዛቤ አስጨብጣለሁ ስም፣ ያለ አንዳች ማስረጃ እውነተኛ የቤተክርስቲያን ልጆችን “ተሀድሶ - መናፍቃን ናቸው” እያለ መግለጫ ሲሰጥ የነበረው ዲ/ን ያረጋል አበጋዝ በቤተክርስቲያን ታሪክ «አውጣኪ መናፍቅ ነው» የተባለው ያለ ተጨባጭ ማስረጃ ነው ሲል ለአውጣኪ ተከላከለ።

ሰሙነ ሕማማት የጌታ ወይስ የይሁዳ ሳምንት? - - - Read PDF

  • በሰሙነ ሕማማት የጌታን ፍቅር እንዳናስብ የሚያደርጉንንና የሚያዘናጉንን ልማዶችና ወጎች ሁሉ ልናስወግዳቸው ይገባል።
  • በጌታ ሞት የምናዝነውስ ለምን ይሆን? ለምን ሞተ ብለን ማዘናችን ኢመጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው። ከዚያ ይልቅ ስለእኛ በመሞቱ ወደር የሌለው ፍቅሩ ልባችንን ሊገዛ፣ ሊነገር በማይቻል ፍጹም ደስታ ልባችንን ሊሞላ በሰላምና በእረፍት እጦት ለሚዋትተው ሕይወታችን ሰላምና እረፍት ሊሰጣት ይገባል።
  • እባካችሁ ይህን አስደናቂውን፣ ከአእምሮ በላይ የሆነውንና የሚለውጠውን የጌታን ፍቅር ንገሩን። በሌላ በሌላው አታድክሙን። ጌታ የጠራን ከባዱን ሸክማችንን ከላያችን ጥሎ ሊያሳርፈንና የእርሱን ቀላል ሸክም ሊያሸክመን እንጂ እርሱ ያላሸከመንን ሌላ ከባድ ሸክም ተሸክመን መትከፈ ልቡናችንን (የልቡናችንን ጫንቃ) እንዲሰብር አይደለም።
ይህ የምንገኝበት ሳምንት ሰሙነ ሕማማት በመባል ይታወቃል። ሳምንቱ የተመደበው የጌታችንን ሕማማት ለማሰብ ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአይሁድ እጅ ከተያዘባት ከሐሙስ ምሽት አንስቶ በብዙ መከራ ውስጥ አልፎ እስከተሰቀለባትና እሰከ ሞተባት እስከ አርብ ድረስ የተቀበለው መከራ እጅግ አሰቃቂ ነው። ነቢዩ ኢሳይያስ በምዕራፍ 53 ስለ ክርስቶስ መከራ አስቀድሞ የተናገረው ሁሉ የጌታን ጥልቅ ፍቅር ያስረዳል። እርሱ ያንን ሁሉ መከራና ስቃይ የተቀበለው፣ ስለ እኛ ነው። የእኛን ደዌ ተቀበለ፤ ሕመማችንንም ተሸከመ። እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ። በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን። ነፍሱን የኀጢአት መሥዋዕት አድርጎ በማቅረብ ለእኛ ያደረገውን ይህን የፍቅርና የቸርነት ስራ ከማሰብ የበለጠ ነገር የለም። የመዳናችን መሠረት ይህ ነውና። ወደእርሱ የተጠራነውና የመጣነው በዚህ ሁኔታ በተገለጠ ድንቅ ፍቅሩ ነው። በምንም የማይመለሰውን የጌታን ፍቅርና ውለታ ሁልጊዜ እያስታወስን ልንደነቅና ልንገረም፤ ጌታንም በሙሉ ልባችን ልንከተል ይገባል። ሰሙነ ሕማማት ተብሎ ይህ ሳምንት የተለየውም ሁልጊዜ ልናስበው የሚገባውን ይህን የጌታን ፍቅር በተለየ መንገድ እንድናስበው ስላስፈለገ ነው እንጂ ሌላ ምክንያት አይኖረውም።

Tuesday, April 10, 2012

ጥንተ አብሶ የጊዜው አጀንዳ - - - Read PDF

የአባ ሠረቀ መጽሐፍ ከተመረቀና በገበያ ላይ ከዋለ ወዲህ በጠቅላይ ቤተ ክህነት፣ በበርካታ አብያተ ክርስቲያናት ማህበረ ካህናት መካከልና በማህበረ ቅዱሳን መንደር አነጋጋሪ የሆነው ጉዳይ ማርያም ጥንተ አብሶ አለባት የለባትም የሚለው ጉዳይ ነው። ጉዳዩ እንደአዲስ የተነሳው ቆሞስ አባ ሠረቀ እውነትና ንጋት በተሰኘው መጽሀፋቸው ስለተወሳና በጉዳዩ ከአሜሪካ እስከ አዲስ አበባና እስከ ግብጽ፣ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ እስከ ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ፣ ከብፁዕ አቡነ ማትያስ እስከ ብጹዕ አቡነ ገብርኤል ድረስ ብዙ የተባለለትና ያነጋገረ መሆኑ የብዙዎችን ቀልብ ስቧል፡፡ በማህበረ ቅዱሳንና በመሰሎቹ ሰፈር ደግም ሃይማኖት ተጣሰ የሚል አቧራ አስነስቷል።

ጥንተ አብሶ ምንድን ነው? ጥንተ አብሶ (የውርስ ኀጢአት) የሚባለው አዳምና ሄዋን እግዚአብሔር የሰጠውን ትእዛዝ አፍርሰው የሰሩትና ወደዘራቸው የተላለፈ በዘር የሚተላለፍ ኃጢአት ነው። አዳምና ሄዋን ሰውን ሁሉ ወክለው የተቀበሉትን ትእዛዝ በመጣሳቸውና ኃጢአት በመስራታቸው በኃጢአት ሲወድቁ የወከሉትን ሰው ሁሉ ይዘው እንደወደቁና ከእነርሱ የተወለደ ሰው ሁሉ ኃጢአትን ወርሶ የሚወለድ መሆኑን ከአጠቃላዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የምንረዳው ሀቅ ነው።ከአዳምና ከሄዋን ዘር ተወልዶ በዚህ ሀጢአት ያልተያዘ፣ ይህ ሀጢአት የሌለበት የሰው ዘር የለም። አስቀድሞ በእግዚአብሄር መልክና ምሳሌ የተፈጠረው አዳም በሀጢአት ከወደቀና መንፈሳዊ መልኩ ከተበላሸ በኋላ ልጅን የወለደው በመልኩና በምሳሌው መሆኑን መጽሀፍ ቅዱስ ይመሰክራል። «አዳምም ሁለት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ልጅንም በምሳሌው እንደ መልኩ ወለደ ስሙንም ሴት ብሎ ጠራው።» (ዘፍጥረት 5፡3)። ይህም ከአዳም ከሄዋን የተወለዱ ልጆቻቸውና ከዚያም በኋላ የመጡት ዘሮቻቸው ሁሉ ሀጢአተኛ ባህርይን ወርሰው እንደሚወለዱ ያመለክታል።

Monday, April 9, 2012

በስደት ላይ የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ በዋልድባና በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ አወጣ

በማያወላውል አቋማቸው የሚታወቁት ብፁዕ አቡነ መልከ ጼጼቅ  የፈረሙበትና ጠንከር ያለ መልዕክት ያለው መግለጫ ደርሶናል። በዚህ አጋጣሚ ሳንጠቁም የማናልፈው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከተነሱና በአቋማቸው፣ በዓላማቸው እና በጥንካሬአቸው ጽኑ ከሆኑ አባቶች መካከል አንዱ የሆኑት ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ የ 88 ዓመት ሽማግሌ አባት ሲሆኑ አስተሳሰባቸው፣ እውቀታቸውና፣ ጥንካሬአቸው ምንም እንዳልተለወጠ በቅርብ ከሚያውቋቸው ሰዎች ተረድተናል።  የቅዱስ ሲኖዶሱን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ።

Sunday, April 8, 2012

በብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የሚመራው የዋሽንግተን ዲሲና ካሊፎርኒያ አህጉረ ስብከት ጽህፈት ቤት በምዕራብ አሜሪካ ካሊፎርኒያና አካባቢው የተቋቋመውን የስቴት ቤተ ክህነት ሊቃነ ካህናቱን አስታወቀ

የሹመት ደብዳቤዎችን ለማየት እዚህ ላይ ይጫኑ 
በብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የሚመራው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዋሽንግተን ዲሲና ካሊፎርኒያ አህጉረ ስብከት ጽህፈት ቤት በምዕራብ አሜሪካ ካሊፎርኒያና አካባቢው የተቋቋመውን የስቴት ቤተ ክህነት ሊቃነ ካህናቱን አስታወቀ።

ከዚህም በተጨማሪ በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው የመንበረ ጵጵስና ሀገረ ስብከት መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ አባላትንም አሳውቋል።

Friday, April 6, 2012

በዋልድባው ጉዳይ ዋሽግተን ዲሲ ሰልፍ የወጡት ፖለቲከኞች መሆናቸውን የማህበረ ቅዱሳን ድረገጾች አመኑ - - - Read PDF

በዋልድባ ገዳም አካባቢ መንግስት የጀመረውን የልማት ስራ ለፖለቲካ ፍጆታ ለማዋል በሰሜን አሜሪካ በማህበረ ቅዱሳን የፖለቲካ አባቶች ወይም ስውር አመራሮች ተቀነባብሮ በማህበሩ መንደር ሲወራ፣ በማህበሩ ድረገጾችም አለቅጥ ሲናፈስና በቪኦኤም ሲራገብ በሰነበተው ሰሞነኛ የፖለቲካ ግርግር ውስጥ ፖለቲከኞች መኖራቸውን “የተዋህዶ ቤተ ሰብ ከመላው አለም” የተሰኘው http://yetbet.blogspot.com/2012/04/blog-post_5172.html  የማህበሩ ብሎግ አመነ። “የእኛ ድረገጾች” እያለ በዋናነት የማህበሩን ሀመርና የማህበሩን ይፋዊ ድረገጽ ከፊት ያሳለፈውና፣ ዜናውን በአሁኑ ወቅት የማህበሩ ዋና የወሬ መናገሻ የሆነው “አንድአድርገን” የወሬ ብሎግም አስተጋብቶታል። አባ ሰላማ የጡመራ መድረክ ከመነሻው ጀምሮ ከዚህ ጉዳይ በስተጀርባ የማህበረ ቅዱሳን አባቶች የሆኑ ፖለቲከኞች መኖራቸውንና አጀንዳቸውም ፖለቲካ እንጂ ሃይማኖት አለመሆኑን ሲዘግብ መቆየቱ ይታወሳል።

Thursday, April 5, 2012

ያለ ተክለ ሃይማኖት መቃብር የመዳን ተስፋ የላችሁም። ገድ/ ተክ/ ሃይማኖት ም 61 ቁ 10።

ግእዙ "ወአልብክሙ ተስፋ ድኂን ዘእንበለ መቃብሪሁ» አማርኛው «ያለ መቃብሩ የመዳን ተስፋ የላችሁም»
ታሪኩ እንደዚህ ነው። የተክለ ሃይማኖት ልጆች የሆኑ ሁለት መነኮሳት ኢየሩሳሌምን ለመጎብኘት ከደብረ ሊባኖስ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዱ፤ ወዲያው የእስክንድሪያውን ሊቀ ጳጳስ አግኝተው ከተባረኩ በኋላ ከወዴት እንደመጡ ሲጠይቃቸው ከኢትዮጵያ መሆናቸውን ገለጡለት። እርሱም «የእግዚአብሔርን ሰው የተክለ ሃይማኖትን መቃብር ታውቃላችሁን» አላቸው ከዚያው መጣን ብለው መለሱለት። ሊቀ ጳጳሱ ከተክለ ሃይማኖት መቃብር መጣን ባሉት ጊዜ ተነሥቶ ሰገደላቸው እግራቸውንም ሳመ ይላል ገድሉ ቁ 2

Wednesday, April 4, 2012

ከዋልድባው ጉዳይ በስተ ጀርባ የአቡነ ሳሙኤል እጅ እንዳለ እየተነገረ ነው

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዋልድባ ገዳም አካባቢ መንግስት ሊሰራ ያሰበውን የልማት ስራ መነሻ በማድረግና በሃይማኖታዊ ሽፋንነት በመጠቀም ማህበረ ቅዱሳን በውጪ ካሉ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ጋር እጅና ጓንት ሆኖ እያጋጋለ ካለው የፖለቲካ አጀንዳ ጀርባ አባ ሳሙኤል እንዳሉ እየተነገረ ነው። የቀድሞው የዋልድባ መነኩሴና የዛሬው የልማት ኮምሽን ጳጳስ አባ ሳሙኤል፣ በጉዳዩ ላይ የዋልድባን መነኮሳት በማነሳሳትና ከቪኦኤና ከሌሎችም አካላት ጋር የሚገናኙበትን ሁኔታ በማመቻቸት፣ በሰልፍ መልክ ወደጠቅላይ ቤተክህነት እንዲመጡና ተቃውሟቸውን እንዲያሰሙ በማድረግ፣ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ለጳጳሱ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ሲናገሩ ተሰምተዋል። ይህን እያደረጉ ያሉትም በአቡነ ጳውሎስ ላይ ተቃውሞ እንዲነሳ ለማድረግና ተቃውሞው ተጋግሎ ከቀጠለና እርሳቸውን በአመጽ ከመንበራቸው ማስነሳት ከተቻለ በእርሳቸው እግር እተካለሁ የሚል ቅዠት ስላላቸው ነው ይባላል፡፡ ለዚህ ደግሞ ድጋፍ እየሰጣቸው ያለው ማህበረ ቅዱሳን ነው፡፡

Monday, April 2, 2012

የዶክተር መስፍን የቅስና ማዕረግ ተገፈፈ

ራሳቸውን ዲያቆን መምህርና ቄስ እያደረጉ ቤተ ክርስቲያንን ከሚበጠብጡ የማህበረ ቅዱሳን አባላት መካከል አንዱ / መስፍን ነው። ሰውዬው በዘመናዊ ትምህርቱ ውጤታማ እና እስከ ዶክትሬት ድረስ በመድረሱ አገሪቱን ሊጠቅም የሚችል ዜጋ መሆኑ አይካድም።  የማህበሩ ቄሳውስት በሃይማኖት በኩል በማይገባቸው ነገር ከመፈትፈት በቀር ምንም የሚያቁት ነገር የለም። ለዚህም ምልክቱ ጳጳሳትን ወይም በሃይማኖት ምሥጢር ከነርሱ የተሻሉ መንፈሳዊ እውቀትናና ልምድ ያላቸውን አባቶች ለማክበር ፈቃደኛ አለመሆናቸው ነው። ዲያቆን ሙሉጌታ በጻፈው የአትላንታው ጉባኤ ላይ የአባቶችን እርቅ ለማደናቀፍ ደፋ ቀና ሲሉ ታይተዋል። አቡነ ፋኑኤልንም ለመታዘዝ ፈቃደኛ አይደሉም። በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትን እያሳመጹ የሚገኙትም እነርሱ ናቸው። ከዚህ በከፋ ደግም ያልተማሩትን የሃይማኖት ትምህርት እስተምራለሁ እያሉ የስህተት ትምህርታቸውን ቀጥለውበታል።ይህ በንዲህ እንዳለ ከሥርዓት የወጣ አካሄዱን እንዲያቆም በተደጋጋሚ በአባቶች ሲመከር ቢቆይም አሻፈረኝ አልታዘዝም ያለው / መስፍን ከማን እንደተቀበለው የማይታወቀው ክህነቱ እንደታገደ በደብዳቤ ተገልጾለታል። በቀጣዩም ሌሎች የማህበሩ ቄሶች ከክህነታቸው ሊታገዱ መሆኑን ውስጠ አዋቂ ምንጮች ይጠቁማሉ።