Sunday, April 22, 2012

ጥንተ አብሶ የጊዜው አጀንዳ - ክፍል 2

«የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት፥ ሥርዓተ አምልኮትና የውጭ ግንኙነት» በተሰኘውና ማኅበረ ቅዱሳን በዋናነት «ማርያም ጥንተ አብሶ የለባትም» ለማለት እየጠቀሰው ባለው መጽሐፍ ሥራ ላይ ከተሳተፉት መካከል አንዳንዶቹ ማርያም ጥንተ አብሶ አለባት የሚል አቋም ያላቸው ናቸው፡፡ ለምሳሌ መጋቤ ብሉይ ሰይፈ እና ብፁዕ አቡነ ገብርኤልም ይጠቀሳሉ፡፡
ታላቁ ሊቅ መጋቤ ብሉይ ሰይፈ ከብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ጋር በጻፉት መጽሐፍ ላይ እንዲህ ብለዋል።
አንዳንዶች እመቤታችን አድፎ የነበረው የአዳም ጠባይ ወይም ጥንተ አብሶ እንደሌለባት ያስተምራሉ። ነገር ግን ይህ ትምህርት በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ተቀባይነት የለውም። ምክንያቱም እመቤታችን ከኢያቄምና ከሐና በሩካቤ ዘበሕግ የተገኘች ናት እንጂ ከሰማይ የወረደች የመላእክት ወገን አይደለችምና፤ ካሳ የማያስፈልጋትም ሳትሆን ክርስቶስ በደሙ ከዋጃቸው ካሣም ከተከፈላላቸው ወገን ናት።» (የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መሠረት ሃይማኖት እና የካህናት ተልእኮ ገጽ 29)።
ብጹዕ አቡነ ገብርኤልም በልደታ ለማርያም የኢ.ኦ.ተ.ቤተክርስቲያን ጋዜጣ በግንቦት 1997 ዓ.ም እትም ላይ የሚከተለውን ሀሳብ አስፍረዋል።… ቅድስት ድንግል ማርያምን የወለዱ ኢያቄምና ሐና ከአዳም ሲወርድ ሲዋረድ ከመጣው አበሳ (ኃጢአተ አዳም) ንጹሐን ነበሩ ወይም ቅድስት ድንግል ማርያም ከመፀነሷ በፊት ቅዱስ ገብርኤል ወይም ራሱ መንፈስ ቅዱስ ከውርስ ኃጢአት ሐናንና ኢያቄምን አነጻቸው የሚል ቃል ከመጻሕፍተ አበው፣ ከመጻሕፍተ ሊቃውንትንና ከመጽሐፍተ ትውፊት ተፈልጎ ባለመገኘቱ እነሆ ምሁራኑ «በቅድስት ድንግል ቅድመ ብሥራት የአዳም ኃጢአት ነበረባት፤ የለም ፈጽሞ አልነበረባትም» በመባባል የጦፈ ክርክር በማድረግ ላይ ይገኛሉ። በዚህ ረገድ ከላይ የጠቀስነው  ዋቢ ቃል በመታጣቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሊቃውንትና መጻሕፍቱን የማስማማ ክፍል አልተገኘም።
ከአሥራ ስድስት ዓመት በፊት ባለው ጊዜ ጥንተ አብሶንና ቅድስት ድንግል ማርያምን በተመለከተ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰነው ተጨባጭ ውሳኔ የለም። ይህም ማለት ይህንን ዶግማ በተመለከተ ቤተክርስቲያናችን እንደ ሌሎች የኦሬንታል እና የምሥራቅ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ጥንተ አብሶ ነበረባት ግን መንፈስ ቅዱስ አነጻት። ስለዚህም አምላክ ከጥንተ አብሶ ነጻ የሆነውን ሥጋንና ነፍስን ተዋሐደ በሚል የእምነትአቋም እንደቆመች የሚታወቅ ውሳኔ የለም። ወይም ደግሞ የቤተክርስቲያኒቱ መጻሕፍት ታይተውና ተስተካክለው ሊቃውንቱም በሙሉበቅዱስ ሲኖዶስ ሥር ተሰብስበው በሰፊውና በጥልቀት ተወያይተው አበሳ አዳም (ጥንተ አብሶ) ፈጽሞ አልነካትም፣ አልነበረባትምብለው እንደሮማውያን ሊቃውንት የእማኩሌትድ ኮንሰብሽን (Immaculate conception) አስተምህሮ (ዶግማ) ዶግማችንና እምነታችን መሆኑን በሚገባ ወስኖ ለእኅት ኦሬንታል አብያተ ክርስቲያናት ማሳወቅ ነው። ነገር ግን እስካሁን እንደዚህ አልተደረገም።
እንደእውነቱ ከሆነ ግን ስለድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ያለን እምነትና ትምህርትን በተመለከተ ከእስክንድርያ ሥርዓተ እምነት ባንለይ እጅግ መልካም ነው።
ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ፣ መጋቤ ብሉይ ሰይፈ ስላሴ አስቀድሞ ማርያም ጥንተ አብሶ አለባት የሚል አቋም አራምደው ነበር። «የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስያን ሥርዓተ አምልኮትና የውጭ ግንኙነት» በተሰኘው መጽሀፍ ላይ ግን የአቋም ለውጥ አድርገው ይሁን፣ ወይም በሌላ ምክንያት «ማርያም ጥንተ አብሶ የለባትም» ብለዋል ተብሎ ሊወሰድ ይችላል።
ከላይ የቀረበው የብፁዕ አቡነ ገብርኤል አቋም የተንጸባረቀው ደግሞ «የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሥርዓተ አምልኮትና የውጭ ግንኙነት» ከተጻፈ ከ9 ዓመት በኋላ መሆኑ፣ ይህ መጽሐፍ ብጹዕነታቸው ከላይ እንደገለጹት የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ተደርጎ ሊወስድ የሚችል አይደለም። ምክንያቱም የጥንተ አብሶ ጉዳይ እስካሁን በሲኖዶስ ላይ ቀርቦ ውይይት ተደርጎ ውሳኔ ላይያልተደረሰበት ጉዳይ ነውና።
ብፁዕ አቡነ ገብርኤል በተጠቀሰው ጽሑፋቸው ውስጥ ያቀረቧቸው ሀሳቦች እጅግ ጠቃሚ ናቸው። የሚከተሉትንም ጭብጦች ማውጣት እነችላለን።
·        ማርያም ጥንተ አብሶ የለባትም የሚል ሐሣብ በመጽሐፍ ቅዱስ፣ በአበው ጽሑፎችና በሌሎችም ትውፊቶች አይገኝም።
·        በጉዳዩ ላይ በሊቃውንቱ መካከል በሁለት ጎራ የተከፈለና ያልተቋጨ ክርክር አለ።
·        በዚህ ጉዳይ ላይ ቤተክርስቲያናችን ውሳኔ ስላላሳለፈች አቋሟን ግልጽ በማድረግ በዚህ ረገድ የሮማ ካቶሊክን አመለካከት ተቀብያለሁ ማለትና ይህኑ ለአኃት አብያተ ክርስቲያናት ማሳወቅ አለባት።
·        በዚህ ትምህርት ዙሪያ ግን ከእስክንድርያ ቤተክርስቲያን ባትለይ (እንደ እስክንድርያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አቋም ማርያም ጥንተ አብሶ አለባት ብትል) የተሻለ ነው ብለዋል።
ብፁእነታቸው በዚህ አቋማቸው ማህበረ ቅዱሳን በስምአ ጽድቅ ካንጸባረቀው ሀሳብ ጋር ልዩነት አላቸው።
ይህን ተከትሎ በርካታ ጥያቄዎች መነሳታቸው አይቀርም፡፡ የብዙዎቹ ሊቃውንት እምነት «ማርያም ጥንተ አብሶ አለባት» የሚል ሆኖ ሳለ «ማርያም ጥንተ አብሶ የለባትም» ሲሉ ለምን ጻፉ? ይህ የቤተክርስቲያኗ አቋም ነው? አቋሟ ከሆነ መቼ እና በየትኛው ጉባኤ ነው የተወሰነው? አቋሟ ካልሆነ ለምን እንዲህ ብሎ መጻፍ አስፈለገ? በዚህ ጉዳይ ላይ ግን አቋም እንዳልተያዘ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ነግረውናል። ወደፊትስ በዚህ ጉዳይ ላይ ቅዱስ ሲኖዶስ ተወያይቶ ከሌሎች አኃት አብያተ ክርስቲያናት አቋም ጋር ይስማማል ወይስ በዚህ አቋም ከእነርሱ ተለይቶ ከካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጋር አንድ ይሆናል። ጉዳዩ በቅዱሳት መጻሕፍት እና በአበው ትምህርት ተፈትሾ ወደአንድ ውሳኔ ይደረሳል ወይስ አንዳንዶች እንደሚሉት በዚህ ጉዳይ ላይ ውይይትም ውሳኔም ሳይደረግ «ማርያም ጥንተ አብሶ የለባትም» ተብሎ በሜዳ ውሳኔ እንደጸና ይቀራል? የሚሉት ጥያቄዎች ምላሽ ይፈልጋሉ፡፡
በእርግጠኝነት ለመናገር ጉዳዩ ከዚህ ቀደም በቅዱስ ሲኖዶስ ተነስቶና ውይይት ተደርጎበት የተወሰነ ውሳኔ የለም፡፡ ከቤተክርስቲያን መጻህፍት ብዙዎቹ ማርያም ጥንተ አብሶ እንዳለባት የሚመሰክሩ ናቸው፡፡ ይህ የሌሎቹ አኃት ኦርቶዶክሳውያት አብያተ ክርስቲያናት አቋምም ነው።
በብዙ መልክ ከታየ እውነት ጥቂቶች ዘንድ እንጂ ብዙዎች ዘንድ የለችም፡፡ ማርያም ጥንተ አብሶ አለባት የሚለው እውነትም ብዙሃኑ ዘንድ አልደረሰም፡፡ ብዙሃኑ ዘንድ ያለው «የለባትም» የሚለው የተሳሳተ ትምህርት ነው፡፡ አንዳንድ ተምረናል የሚሉ ሰዎችም እንኳ ጉዳዩን እያወቁት ሌሎችም መርምረው አንድ ድምዳሜ ላይ ከመድረስ ይልቅ በልማድና ሲወርድ ሲዋረድ በሚለው ፈሊጥ በመወሰድ፣ ወይም ልማድን ለመተው ከመቸገር የተነሳ፣ የብዙሃኑ እምነት የለባትም የሚለው ነውና ከዚህ ውጪ መሄድ የለብንም የሚል አቋም ይዘው ይታያሉ፡፡
በግለሰቦች ደረጃ ማርያም ጥንተ አብሶ እንዳለባት ቢጻፍም፣ ቢነገርም፣ በቡድን ወይም በቤተክርስቲያን ደረጃ ግን «አለባት» በሚለው ትምህርት ዙሪያ የተባለ ነገር የለም። ይህ ማለት ግን በቤተክርስቲያኒቷ አንዳንድ ቦታዎች ጉዳዩ አላከራከረም፣ ወደአንዳች ውሳኔም አላመራም ማለት አይደለም። በዚህ በኩል የሚጠቀሰው አሜሪካ ካንሳስ ውስጥ በመልአከ ብርሃን አስተርአየ ጽጌ እና በብፁዕ አቡነ ማትያስ መካከል በ1997 ዓ.ም የተነሳውና እርስ በርስ በግል ደረጃ ሳይወሰን በዚያ ያለው ማህበረ ካህናትና ጳጳሱ ወደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስና ወደ አኃት አብያተ ክርስቲያናት ድረስ እስከ መጻጻፍ አድርሷል፡፡ በዚህ መካከል የተደረሰበት ድምዳሜ ማርያም ጥንተ አብሶ ያለባት መሆኑን ያስረዳ ነው፡፡ ስለዚህ መልአከ ብርሃን አስተርአየ ጽጌና ማህበረ ካህናቱ፣ እንዲሁም ጉዳዩ በአደባባይ መነጋገሪያ እንዲሆን ማርያም ጥንተ አብሶ የለባትም ሲሉ በመከራከር ጉዳዩ እንዲግል ያደረጉትና ጠቃሚ መረጃዎች ይፋ እንዲወጡ ሰበብ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ማትያስ፣ ይልቁንም ጉዳዩ ተዳፍኖ እንዳይቀር «እውነትና ንጋት» በተሰኘው መጽሐፋቸው ይፋ ያወጡትና ትልቅ መነጋገሪያ ያደረጉት ቆሞስ አባ ሠረቀ ብርሃን ሊመሰገኑ ይገባል፡፡[1]
ማርያም ጥንተ አብሶ አለባት የሚባለው ከምን በመነሳት ነው? አንዳንዶች እንደሚመስላቸው ፀረማርያም አቋም በማራመድ የተያዘ አቋም አይደለም፡፡ ማርያም ሰው እንጂ ከሰው የተለየች ፍጡር ስላልሆነችና ከአዳም ዘር የተገኘች በመሆኗ በዘር ከተላለፈው የውርስ ሀጢአት ነጻ አይደለችም በሚል ነው፡፡ ከጥንተ አብሶ ነጻ ስላልሆነችም ድንግል ማርያም ሞትን ቀምሳለች፡፡ ጥንተ አብሶ ባይኖርባት ኖሮ ባልሞተችም ነበር፡፡ በሌላ በኩል ጥንተ አብሶ ላይኖርባት የሚችልበት አጋጣሚ ፈጽሞ የለም እንጂ ባይኖርባት ኖሮ ለሰው ቤዛ በሆነች ነበር የሚሉም አሉ፡፡

ይቀጥላል
ጸጋ ታደለ 


[1] በዚህ ጉዳይ ዙሪያ የነበረውን የሀሳብ ልዩነት መነሻና የክርክር ሂደት የቀረቡ ማስረጃዎችንና የአኃት አብያተ ክርስቲያናትን አቋም ለማወቅ የአባ ሠረቀን እውነትና ንጋት ከገጽ 18-80 ድረስ ያለው ሰፊ ግንዛቤ ያስጨብጣልና አንባቢ ቢመለከተው መልካም ነው፡፡

23 comments:

 1. ከጥንተ አብሶ ነጻ ስላልሆነችም ድንግል ማርያም ሞትን ቀምሳለች፡፡ ጥንተ አብሶ ባይኖርባት ኖሮ ባልሞተችም ነበር ብለሀል
  ክርስቶስም ሞትን ቀምሷል ታዲያ ከድንግል ማርያም የወረሰው/ከአዳም ዘር/ጥንተ ተሀብሶ አለበት ትሉ ይሆን? ሎቱ ስብሀት፠

  ReplyDelete
  Replies
  1. ክርስቶስማ ስለ አዳም በደል ነው የሞተው:: እንደ ኃጥያተኛ ተቆጥሮ ነው:: አዳኝ እንጅ መድኅኒት አያስፈልገውም:: እመቤታችን ግን አዳኝ መድኅኒት ያስፈልጋታል:: "ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፥ መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች" ሉቃ 1:47

   Delete
  2. ክርስቶስ በፈቃዱ እኛን ለማዳን ነው የሞተው:: እመቤታችን ግን በተፈጥሮ(ጥንተ አብሶ) እደኛ ነው የሞተችው:: ከቶ ፈጣሪ እና ፍጡር እንዴት ይወዳደራል::
   ማርያምም ፈጣሪዋን

   Delete
 2. ALEBAT WOIM YELEBATIM YEMILEW TIKIMU MINDIN NEW? ESKI GOBEZ KEHONACHIHU YIHENEN KEMETSIHAF KIDUS BEMATAKES KEDIHINET GAR MIN KURIGNIT ENDALEW BITABIRARULIGN.

  ReplyDelete
 3. betam yemigermew andin neger meliso melalso mawrat min yasfeligal? balefew bawetachihut tsihuf yetenesutin tiyakewoch lemin atmelisum? ahuniko alebat yelebatim malet sayhon lehuletum hasaboch mabrariya mestet new. ekele ale yemibalewun titachihu be felegachut wegen mabrariya situn, beteley tinte abiso yelebatim yemilut mikniat mnidinew? enantes ale yemitilubet mikniat eskahun kakerebachihut yeteleye ale?
  thanks,

  ReplyDelete
  Replies
  1. "ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፥ መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች" ሉቃ 1:47

   Delete
 4. sewe kentu.....lelas yelachehum?enanete eko gena kirstosem ጥንተ አብሶ alebete maletachu ayeqerem...demo bezihe laye yelebawen yesereqen metsehafe reference taderegalachehu..
  በዚህ ጉዳይ ዙሪያ የነበረውን የሀሳብ ልዩነት መነሻና የክርክር ሂደት የቀረቡ ማስረጃዎችንና የአኃት አብያተ ክርስቲያናትን አቋም ለማወቅ የአባ ሠረቀን እውነትና ንጋት ከገጽ 18-80 ድረስ ያለው ሰፊ ግንዛቤ ያስጨብጣልና አንባቢ ቢመለከተው መልካም ነው፡፡

  ReplyDelete
 5. You can't come up with reasonable evidences so don't wast your time. You said many likawunt but you mention only two and you interprite in a way you like. You are trying to say the church's book as simple as an individual saying. I were egure to read your post but not convincing and biased. You try to capitalize on Aba Sereke in giving high position, a man in question about his religion, and Mk(in depopularizing way) that makes you post liable to hestation. Anyways you can't make people believe in you idiology with such an argument.

  ReplyDelete
 6. I reaaly appreciate you if Setan also stand in your side u ll quote him like what u did b4. Your issue of immaculate conception is right in the eyes of Oriental churches but its better to wait the decission by the synod.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Aba selama is not Catholic blog. They accept Oriental church not Catholic ..

   Delete
  2. ንዌጥን በረዴተ ቅድስት ሥላሴ let me start by the name of holy trinity!! exposing the wrong teaching

   Delete
  3. this is all wrong!! i will tell u how it is so wrong

   Delete
 7. She is female and she got it.

  ReplyDelete
 8. His Holiness Pope Shenouda III has explicitly stated in his book "The Holy Virgin St. Mary" that she was conceived with the original sin (tinte abiso) like every human being. So are we following catholic dogma or orthodox dogma??? A few weeks ago, we were all praising our beloved father Pope Shenouda(as we should) but are we willing to accept his teaching (the true orthodox teaching)? hulunim neger le hilinachin etewewalew... Here is the link. You can read it for yourself in page 11 of the book.

  http://tasbeha.org/content/hh_books/the_holy_virgin_st_mary/index.html

  "The sanctifying by the Holy Spirit of her depository, makes the One born of her, be conceived without the impurity of the original sin. As for The Virgin herself, her mother conceived, like all people, and so The
  Virgin said in her hymn: "my spirit has rejoiced in God my Savior" (Luke 1:47).
  That is why the Church does not agree that The Virgin was
  conceived without the impurity of the original sin, as our brothers the Catholics believe."

  ReplyDelete
 9. re fare this web,http://medhanialemeotcks.org

  ReplyDelete
 10. SEYTAN BELBU ADRO ENDEFELEGE LLEMIYADERGEW SEW DENGAY DNGAY MEHONUN EYAWEQE DABO NEW BELO SELMIKERAKER EWNET EWENET NEW YEMNETM GUDAY NEW. SELEMEBETACHEN LEMENAGER EGNA MAN NEN MEJEMERIYA MESADEB YESEYTAN NEW SERAW YEHA SELEHONE BETAMENUM BATAMENUM EMEBETE KEHONECH AMALK KEMEJEMERIYA KENATUA MAHISEN GENA SETFETER ANSTETO QEESO MADERIYAW ENDETEHON AZEGAJETO FETROATAL. KEMEBETACHEN BEFIT EKO ENEYHONES GETAN YATEMEQU TEFETREWAL GEN BEMAHESEN EYALU SENS ALAZELELUM DENGEL MARYAM GEN NESEHETE NESUAN SELEHONECH SELAMTAWAN SISEMA YOHANES BEMAHESEN ZELELE YENHESENAWA WET NEW. BECHA BALEBETU LEBONA YEETEN.

  ReplyDelete
 11. Concerning the understanding of the Coptic Orthodox Church on the issue of the Immaculate Conception:(original sin)

  All human beings) including the Blessed.Virgin Mary) were conceived with the original sin.(psalm 51:5;Rom.5:12).

  The conception and incarnation of the only-be gotten Son of God, which was of the Holy Spirit and the Blessed Virgin Mary, is alone immaculate.(Luke 1:35; John
  8:46; Heb. 7:26-27). The Holy Spirit came upon the Blessed Virgin Mary to sanctify and purify her in order that the Incarnate Son of God may not inherit the original sin.
  The Immaculate Conception ,therefore, refers to the conception of the Incarnate Logo sin the womb of the. Blessed Virgin Mary.

  Source : http://medhanialemeotcks.org/

  ReplyDelete
  Replies
  1. this is the idea of the son of meqdenios. you don't have any thing to say beside this.

   Delete
  2. To the last anonymous; Your pettiness can be seen even by a blind man. What does meqdonios has anything to do with "tinte abiso"?.. How dare you say the true orthodox teaching is an idea derived from meqdonios? How dare you say Pope Shenouda has the idea meqdonious? Egziabehare yeker yebelot.. We don't want menafik in our orthodox tewahedo church. Please you are more than welcome to join the Catholic Church.

   Delete
 12. ሠይፈ ገብርኤልApril 26, 2012 at 2:17 PM

  እናንተ የእፉኝት ልጆች፦

  በማኅበረ ቅዱሳን እያሳበባችሁ ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያምን እና ቅዱሳንን ለመሳደብ አፋችሁን መክፈታችሁ ገሀድ እየወጣ ነው:: የኦርቶዶክስ ተዋህዶን ካባ የለበሳችሁ መስሏችሁ (ለብሳችኋል አላልኩም) ድብቅ አላማችሁን ለማሳካት እየተንፈራገጣችሁ ያላችሁ መስሏችሁ ከሆነ ተሳስታችኋል፤ ከፍሬያቸው ታውቋችኋላችሁ ተብሎ ተጽፏልና:: የለየላችሁ መናፍቃን መሆናችሁ እሳት ከሞቀው ውሎ አድሯል እኮ:: ይልቁንስ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ስም መነገዳችሁን አቁማችሁ ማንነታችሁን እና እምነታችሁን በግልጽ ብታስተምሩ አይሻልም? የሚከተላችሁ ካገኛችሁ::

  ከብዙ በጥቂቱ፦

  የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች የምናምነውና የምንከተለው አምላክ የሆነውን መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስን ነው:: አማላጅ የሆነውን ኢየሱስ አናውቀውም እኮ:: ስለዚህ ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያምን “ጸጋንም የተመላሽ ሆይ፥ ደስ ይበልሽ፤ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነው፤ ከሴቶች ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽ” (ሉቃስ ፩፥ ፳፰ - ፳፱) ብሎ ቅዱስ ገብርኤል እንዳመሰገናት እኛም እሱን አብነት አድርገን ዘወትር እናመሰግናታለን:: ይህንን የቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ ላስተዋለው አስቀድሞ ለነበረ ሁኔታ የተነገረ እንጂ ለወደፊት ብቻ የተነገረ እንዳልሆነ ልብ ይሏል:: እግዚአብሔር ከእርሷ ጋር መሆኑን ቅዱስ ገብርኤል እየነገረን ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም ጥንተ አብሶ ነበረባት ማለት የእግዚአብሔርን የማዳን ኃይልና ጥበብ ካለመረዳት ወይም ካለማመን የሚመነጭ እንጂ ሌላ ምን ሊሆን ይችላል:: በነገራችን ላይ ጥንተ አብሶ አልነበረባትም ስንል እንደ ልጇ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተጸነሰች ማለታችን ሳይሆን እግዚአብሔር ከአዳም ኃጢያት ጠበቃት ማለታችን ነው:: እዚህ ላይ ነው እንግዲህ ከካቶሊኮችም የምንለየው:: ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለ? እንግዲህ ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያምን በተመለከተ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አስተምህሮ እንደዚህ ነው:: የእናንተ ደግሞ ከሌላ ነውና መቼም ቢሆን በዚህ ጉዳይ ልንስማማ ስለማንችል እረፉት::

  እግዚአብሔር ማስተዋሉን ያድላችሁ::

  ReplyDelete
  Replies
  1. "በነገራችን ላይ ጥንተ አብሶ አልነበረባትም ስንል እንደ ልጇ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተጸነሰች ማለታችን ሳይሆን እግዚአብሔር ከአዳም ኃጢያት ጠበቃት ማለታችን ነው:: እዚህ ላይ ነው እንግዲህ ከካቶሊኮችም የምንለየው::"

   You claim that the Catholic Church teaches the Virgin Mary was conceived by the holy spirit like her son Lord Jesus. Where is your evidence? You are misrepresenting the Catholic Church to come to your skewed conclusion. Catholics don't believe St. Mary was conceived by the Holy Spirit. You are wrong.

   This is the true orthodox teaching, link is below.

   Peace and blessings

   (Read page 11) http://tasbeha.org/content/hh_books/the_holy_virgin_st_mary/index.html

   (Read 9d)
   http://oakleighcopts.org/copticorthodox.html

   Delete