Thursday, April 5, 2012

ያለ ተክለ ሃይማኖት መቃብር የመዳን ተስፋ የላችሁም። ገድ/ ተክ/ ሃይማኖት ም 61 ቁ 10።

ግእዙ "ወአልብክሙ ተስፋ ድኂን ዘእንበለ መቃብሪሁ» አማርኛው «ያለ መቃብሩ የመዳን ተስፋ የላችሁም»
ታሪኩ እንደዚህ ነው። የተክለ ሃይማኖት ልጆች የሆኑ ሁለት መነኮሳት ኢየሩሳሌምን ለመጎብኘት ከደብረ ሊባኖስ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዱ፤ ወዲያው የእስክንድሪያውን ሊቀ ጳጳስ አግኝተው ከተባረኩ በኋላ ከወዴት እንደመጡ ሲጠይቃቸው ከኢትዮጵያ መሆናቸውን ገለጡለት። እርሱም «የእግዚአብሔርን ሰው የተክለ ሃይማኖትን መቃብር ታውቃላችሁን» አላቸው ከዚያው መጣን ብለው መለሱለት። ሊቀ ጳጳሱ ከተክለ ሃይማኖት መቃብር መጣን ባሉት ጊዜ ተነሥቶ ሰገደላቸው እግራቸውንም ሳመ ይላል ገድሉ ቁ 2
ይህ ሁሉ ውሸት የተፈለሰፈው መቃብሩን ለማስመለክ ነው። ሊቀ ጳጳሱ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ታላላቅ ታሪካዊና መንፈሳዊ ቦታዎች ይልቅ ስለ ተክለ ሃይማኖት መቃብር መጠየቁ የዚህን መቃብር ልዩነት ያመለክታል። ሰዎቹ መቃብሩን አይተናል ሲሉት ሰገደላቸው እግራቸውንም ሳመ ተብሏል። ስለዚህ ለመቃብሩ ብቻ ሳይሆን መቃብሩን ላየም ስግደት አስፈልጓል። ሊቀ ጳጳሱ መቃብሩን ላዩ መነኮሳት ከስገደ ያገሬ ሞኝ ተላላ ምእመን ወደ ደብረ ሊባኖስ ሲሮጥ ቢኖር ምን ይፈረድበታል? በውድ ልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ የደም ዋጋ የተከፈለበት ንጹሑ የድኅነት ወንጌል እንዳይሰበክ ታግዶ የተክለ ሃይማኖት መቃብር ሲሰበክለት የኖረው ወገኔ ተስፋውን በተክለ ሃይማኖት መቃብር አድርጎ መኖሩ እጅግ ያስገርመኛል።

ሊቀ ጳጳሱ ለምን መጣችሁ ብሎ ለጠየቃቸው ጥያቄ መነኮሳቱ የሰጡትን መልስና ጳጳሱ የመከረውን ምክር ከዚያው ገድሉ እንዲህ ይነበባል። «በምን ነገር ከዚህ መጣችሁ? አላቸው የነፍሳችንን ድኅነት ልንሻ አሉት ጮኸ ወይ ሰው የነፍሱን ድኅነት ሳያውቅ ለካ ይጎዳል? መድኃኒታችሁን ተዋችሁት ሕይወታችሁንም ጠላችሁት ጌታ ለተክለ ሃይማኖት በአጽምህ ቦታ የተቀበረ ዘወትርም ከሷ ዘንድ የሚኖር በሁለተኛይቱ ቀን በግልጽ ካንተ ጋራ ይለፍ ያለውን አልሰማችሁትምን አላቸው» 61 ቁ 2-3።

መነኮሳቱ የነፍሳቸውን ድኅነት ለመሻት ወደ ኢየሩሳሌም መጣን ብለዋል። የነፍስ ድኅነት በጌታችን በወልደ እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንጂ ኢየሩሳሌም ድረስ በመሄድ የነፍስ ድኅነት እንደሚገኝ እንዴት አሰቡ? ለነገሩ አንድን መንፈሳዊ ቦታ በመሳለም መዳን እንደሚገኝ ሲሰበክ ከኖረ ዘመናት ተቆጥረዋል። በዚህ የስሕተት ስብከት ምክንያት የተጎዱ መነኮሳት ሳይሆኑ አይቀሩም የነፍስ ድኅነትን ፍለጋ ኢየሩሳሌም ድረስ የሄዱት። ቅዱሳት ቦታዎችን መጎብኘት ትምህርት ይሰጣሉ መንፈሳዊ ተጽእኖንም ያሳድራሉ፤ በዚህ ምንም ክርክር የለንም። የነፍስ ድኅነትን ይሰጣሉ የሚለው ግን ባዕድ ወንጌል ነው። ጌታችን ለደቀ መዛሙርቱ «ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ ያመነ የተጠመቀ ይድናል» በማለት ዓለም በዚያው ባለበት አገር ሆኖ ወንጌልን ሰምቶ ቢያምን እንደሚድን ተናግሯል። የነፍስ ድኅነት የሚገኘው ኢየሩሳሌም ድረስ በመሄድ ቢሆን ኖሮ ጌታችን «ዓለም ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ይምጣ» ብሎ ያዝዝ ነበር እንጂ ሐዋርያቱን ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ብሎ አይልክም ነበር። በጣም የሚያስቀው ግን የጳጳሱ መልስ ነው። «ወይ ሰው የነፍሱን ድኅነት ሳያውቅ ይጎዳል መድኃኒታችሁን ተዋችሁት ሕይወታችሁንም ጠላችሁት» አለ ሊቀ ጳጳሱ። መድኃኒታችሁ እና ሕይወታችሁ ሲል የተክለ ሃይማኖትን መቃብር ሰብኳል። እንደዚህ ዓይነት ስብከት የሚሰብክ ጳጳስ በክርስቶስ አምኖ ተምሮ ለሊቀ ጵጵስና የደረሰ? ወይስ ትንሽ ጠጅ ቀምሶ ሞቅ ያለው ደብተራ ይሆን? እንጃ ላንባቢ ብተወው ይሻላል። ጎበዝ! ከመቃብር ምን ዓይነት መድኃኒት ይገኛል? በመቃብርስ ምን ሕይወት አለ? ሕይወትና መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ አይደለምን? በኢትዮጵያ ካሉት የቅዱሳን መቃብር ሁሉ የተክለ ሃይማኖት መቃብር ሕይወትና መድኃኒት የሆነበት ምክንያት የደብረ ሊባኖስ ፖለቲካ አይሎ በመገኘቱ ነው እንጅ ሌላ አይመስለኝም።
ጳጳሱ የተክለ ሃይማኖት መቃብር ሕይወትና መድኃኒት የሆነበትን ምክንያት ሲናገር «ጌታ ለተክለ ሃይማኖት በአጽምህ ቦታ የተቀበረ ዘወትርም ከሷ ዘንድ የሚኖር በሁለተኛይቱ ቀን በግልጽ ካንተ ጋራ ይለፍ ብሏል» ይላል። ሁለተኛይቱ ቀን የተባለችው የጌታ የዳግም ምጻት ቀን ናት በዚህች ቀን በተከለ ሃይማኖት መቃብር የተቀበረና በዚያ የኖረ ጌታ በነጻ ይለፍ ብሏል የሚል ነው ክህደቱ። ክብር ምሥጋና ይግባውና እውነት የሆነው አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም በሚመጣበት ቀን ለሁሉም እንደ የሥራው እንደሚሰጥ ነው ያስተማረው። እያንዳዱ ሰው በቀኝ ወይም በግራ መቆሙ የማይቀር ነው። በቀኝ የቆሙት ብራብ አብልታችሁኛል ብጠማ አጠጥታችሁኛል ብታረዝ አልብሳችሁኛል .. ወዘተ ተብለው ይመሰገናሉ። በግራ ይቆሙት ብራብ አላበላችሁኝም በጥማ አላጠጣችሁኝም ብታሠር አላስፈታችሁኝም ..ወዘተ ተብለው ይወቀሳሉ እንጂ በተክለ ሃይማኖት መቃብር ከፍርድ መዳን እንደሚቻል አላስተማረም።

ይህንና ይህን የመሳሰለው ባዕድ ወንጌል ወገኔን ከእውነት ርቆ እንዲኖር ከፖለቲካዊ ከኢኮኖሚያዊና ከመንፈሳዊ ውድቀት እንዳይነሣ አድርጎታል። የቤተ ክርስቲያናችን መናፍቃን ደብተራዎች ያታለሉት የኢየዮጵያን ሕዝብ ብቻ አይደለም፤ ሐሰት ባንደበቱ በማይገኝበት በቅዱሱ አምላክ ላይም ዋሽተዋል። ያልተናገረውን ተናገረ ብለው በስሙ ድፍረት ተናግረዋል። እነዚያ የጥንት መናፍቃን የረጩትን ባዕድ ወንጌል ዛሬ በማህበር የተደራጁ አካላት በአዲስ መልክ እያሰራጩ መከራችንን ሲያራዝሙ ዝም ብለን ማየት የለብንም። ቅዱሱን የእግዚአብሔር ወንጌል ይዘን ልንቆም ይገባል «እግዚአብሔርን የተሳደባችሁበትና በኦርቶዶክሳውያን የቀለዳችሁበት ዘመን ይብቃ»  ልንላቸው ይገባል።
በገድሉ ላይ የሰፈረው ታሪክ እንደሚያስረዳው እነዚያ ሁለት መነኮሳት በሊቀ ጳጳሱ የወይን ቦታ በደረሱ ጊዜ ወይኑን ሲመለከቱት ወይኑ ወዲያው ደረቀ ይለናል። ይህም የሆነበት ምክንያት በተክለ ሃይማኖት መቃብር ላይ የተሾመውን አበ ምኔት ሳይሰናበቱ ስለመጡ ነው ተብሏል ቁ 8። ከዚህ በኋላ ሊቀ ጳጳሱ ለመነኮሳቱ እንዲህ በማለት ወደ ሀገራቸው መለሳቸው «መንፈስ ቅዱስ ዘወትር በተክለ ሃይማኖት መቃብር ላይ ይረባል በተክለ ሃይማኖት ወንበር ላይ የተቀመጠ እንደ ተክለ ሃይማኖት ነው .. አሁንም ወደዚያ ሂዱ ያለ መቃብሩ የመዳን ተስፋ የላችሁም» ቁ  9-10

ጉድ ነው! በሐዲስ ኪዳን መንፈስ ቅዱስ በአማኞች ልብ ውስጥ እንደሚያድር መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል ዮሐ 14፥16-17 «ወይስ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን» ተብሏል 1ቆሮ 6፥20 ታዲያ መንፈስ ቅዱስ መቃብር ላይ ዘወትር የሚረበው ለምን ይሆን? ሰው ሁሉ ተስፋውን በተክለ ሃይማኖት መቃብር ላይ እንዲያደርግ የተጠነሰሰ የክፉዎች ሴራ እንጂ ክብር ምስጋና ይግባውና መንፈስ ቅዱስ ይህን አላለም። 

ያለ መቃብሩ የመዳን ተስፋ የላችሁም ተብለዋል መነኮሳቱ። ይህን ክህደት ስላመኑ ይመስለኛል መቃብሩን እያጠኑ እንዲኖሩ የተገደዱት። የተታለለው ሕዝብም ይህን መቃብር ለመሳም ወደ ደብረ ሊባኖስ በየወሩ ይሮጣል። እግዚአብሔር ለአብርሃምና ለዘሩ የሰጠው ተስፋ ለዓለም ድኅነት የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ነው። እርሱ ሊያድነን ተሰቀለ ሞተ ተቀበረ ዳግመኛም ከሞት ሊያስነሳን ይመጣል። እርሱ ለዚህ ታላቅ መዳን ዋጋ ከፍሏል ይህን እውነት ከሕዝብ ለመሠወር «ያለ መቃብሩ የመዳን ተስፋ የላችሁም» በማለት የነፍሰ ገዳዩን ወንጀል ስንሰብክ ኖረናል። ይህ የጥንታዊት ሐዋርያዊት የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ትምህርት አይደለም። ነገር ግን ይህ ባዕድ ወንጌል በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ስም ሲሰበክ ስለኖረ የኦርቶዶክስ ነው ሊባል አይገባም። ክፉዎች በፖለቲካ የበላይነት እውነተኛ ኦርቶዶክሶችን ገድለውና አሳደው የጫኑብን ክፉ ትምህርት ነው። ዛሬም ኦርቶዶክሶች ከቤተ ክርስቲያናቸው እየተሰደዱ ስማቸውን ተቀምተው ያለ ፍርድ እየተንከራተቱ እየኖሩ ነው። እግዚአብሔር ግን እውነቱን ለኢትዮጵያውያን ሁሉ በሚገልጥበት ጊዜ ሐስተኞች ያፍራሉ እኛም ቤተ ክርስቲያናችንን እና ስማችንን የምናስመልስበት ጊዜ ሩቅ አይደለም አሜን!
ቤተ ክርስቲያናችንን በጉልበት ለቀሙን ሁሉ፦ ሐሰት በሰላማዊ ሰልፍ ወይም በድጋፍ ፊርማ እውነት አይሆንም። ወደ እውነት ተመለሱ እውነተኛውን ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን ንስሐ ግቡ፤ እምቢ ካላችሁ ግን ቤተ ክርስቲያናችንን ልቀቁ

ተስፋ ነኝ

ከሰላ ድንጋይ ጉብኝት በኋላ
በተክለ ሃይማኖት አጥንት ቦታ ቁርባን የተቀበለ ሁሉ ሲኦልን አያይም ገ/ተ/ሃይማኖት ም 62፥3 ይቀጥላል  

ጻድቃኔ ማርያምና ሰላድንጋይ ውስጥ አንድ ወታደር የፈለፈለውን ዋሻ ስጎበኝ የገጠመኝን በሚቀጥለው አጫውታችኋለሁ።

   

9 comments:

 1. Good job my brother tesfa thank you my Lord this is a day That I wish .

  ReplyDelete
 2. le awiraew kidusanin yemisebidibet afi tesetew

  ReplyDelete
  Replies
  1. ayawkumena yesetalu,says holy Bible ,H/Bible the only
   word of God ,any saint has to be measured by the bible , may God give us the wisdom

   Delete
 3. ESEY!!! ENKUWAN TEBALU!!! ENKUWANIS YETEKILIYEN MEKABIRNA YEREGETUTIN HAGERNA MIDIR YEREGETE MIHIRET YAGEGNAL WANAW NEGER BEKAlkidanachew betihitina yemamenina yalemamen guday new. Metsihaf kidusim "bebetena bekitire wusit yemayitefa simina metasebiya esetachewalehu" bilowalina. LENANTE MECHE YIGEBACHIHUWAL. LIBONACHIHU BESEYTAN TAWURO KIDUSANIN YASEDIBACHIHUWAL ENJI. BETEGAGERACHIHUWAT NEGER HULU BEFIRID KEN MILASH TATALACHIHU. KIDUSANIS ENANTE SILESEDEBACHIHUWACHEW AYIWAREDUM "ESU YAKEBERACHEWUN MAN YAWARIDACHEWAL?" YEMIL TEKALU MISIKIRINET ALLACHEWUNNA.

  ReplyDelete
 4. ጥሩ ነው ነገር ግን ይህን ስትቃወሙ ዶግማውን እንዳታፋልሱ ምሰሌ በጌታ ያመነ ይድናል ብለችሁ በፃፋችሁት ላይ ያመነ ብቻ ሳይሆን የተጠመቀም ጨምሩበት ምክንያቱም ጥምቀት አያስፈልግም ከሚሉት ወገን ይመስላል አፃፃፋችሁ

  ReplyDelete
 5. GOD bless you. please forward to reflect the truth.

  ReplyDelete
 6. ኢየሱስ ክርስቶስን በእነ አቡነ ተክለሃይማኖት አወቅነው።ጌታችንም የአሁኑ ትውልድ ወረቀት አምላኪ (እምነት የለሽ) መሆኑን አዉቆ ለቅዱሱ ቃል ኪዳን ሰጠው።ያመንን ጥቂቶቻችን እንድንበት ዘንድ ብዙ ቸርነትን አደርገልን። ለዚህ ሁሉ ርህራሄው ምን እንላለን፧ እኔ ሆዳሙ ወረቀት ኣምላኪው ምን እላለሁ፧

  ReplyDelete
 7. mastewalun yadlachiw

  ReplyDelete
 8. May God bless you!!

  ReplyDelete