Wednesday, April 25, 2012

የተክለ ሃይማኖት አጥንት ባለበት ቦታ ቁርባን የተቀበለ ሁሉ ሲዖልን አያይም - ገድ/ተ/ሃይ/ ም 62 ቁ 3 (የደብረ ሊባኖስ ዶክትሪን)

ማህበረ ቅዱሳን ተከታዮችን ያፈዘዘበትና አክራሪ ወገኛ ካደረገበት የስሕተት ትምህርቶች ውስጥ አንዱ የተከለ ሃይማኖት ታሪክና የመቃብራቸው ሁኔታ ነው።
ተክለ ሃይማኖት በታሪክ ተመራማሪዎች እንደተረጋገጠው የወሎ ላስታን መንግሥት በሃይማኖት ሽፋን መገልበጣቸው ነው። ልክ ማህበረ ቅዱሳን ዛሬ እየሄደ ያለው በርሳቸው ዘዴ ነው። መንግሥቱን በስብከትም በጦርነትም ከገለበጡ በኋላ የዳዊት ዘር ነኝ ለሚለው ላክስታቸው ልጅ ለይኩኖ አምላክ ሰጥተውታል። ይኩኖ አምላክም «ኢይጠፍእ ምስፍና ወምልክና እምነ አባሉ ለይሁዳ» (መንግሥትና ገዢነት ከይሁዳ ዘር አይጠፋም) የሚለውን ለጌታ ለኢየሱስ ክርስቶስ የተነገረውን ቃል ለራሱ በማድረግ በኢትዮጵያ ላይ አወጀ። ይህንም የሃይማኖት አባቱ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አጸደቁት። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የዘር ፖለቲካው በኢትዮጵያ ሥር የሰደደ ካንሰር ሆኖ ይገኛል።
በቤተ ክህነቱ በኩል ከተመለከትነው ተክለ ሃይማኖት ሲሶ መንግሥት አግኝተዋል። ይህም የላስታን መንግሥት ለገለበጡበት የተከፈለ ዋጋ ነው። መንግሥት ከይሁዳው አንበሳ ከይኩኖ አምላክ እንዳይወጣ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እንደታወጀ ሁሉ ክህንትም ወይም እጨጌነት የአሮን ዘር ነኝ ከሚሉት ከተክለ ሃይማኖት ዘር እንዳይወጣ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ ታወጀ። ተክለ ሃይማኖት ጥንተ ዘራቸው ከሌዋውያን ወገን ኢየሩሳሌም መሆኑን ገድላቸው ይናገራል «ወኮነ ጥንተ ሙላዱ ለዝንቱ ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሀገረ ኢየሩሳሌም» (የዚህም የቅዱስ ባታችን የተክለ ሃይማኖት ጥንተ ትውልዱ ኢየሩሳሌም ነው) ገድ/ / ሃይ/ 1 41
የኢትዮጵያ ክርስቲያን ኢየሩሳሌምን እንደ ኢትዮጵያ አድርጎ ነው ሚወደው። እስራኤል የሚባለውንም ሕዝብ እንደ እግዚብሔር ቅዱስ ሕዝብ ዝቅ ብሎ ነው የሚያከብረው። የኢትዮጵያን ሕዝብ ለማታለል ቀላሉ መንገድ ከኢየሩስላሌም የመጣን ነን ማለት ነው፤ እነተክለዬ ያደረጉትም ይህንን ነው። የመንግሥትን ሥልጣን ለመውረስ የይሁዳ ዘር ነኝ አሉ፤ የክህነትን ሥልጣን ለመውረስ የአሮን ዘር ነኝ አሉ። ይህ ነው የጥንቱ የፖለቲካ ዘዴ። ከሞቱ በኋላ ሴራቸው እንዳይገለጥ በስሜ የዘከረ እስከ ሰባት ትውልድ ይድናል፤ በመቃብሬ የተቀበረ የዘላለም ሕይወት አለው፤ በኔ ስም ከተደረገው ፍርፋሪ የበላ ሥጋውና ደሙን እንደተቀበለ ነው፤ ባጥንቴ ላይ የቆረበ ሲዖልን አያይም ብለው በሃይማኖት ፍርሐት ሸፈኑት። ያገሬ ሕዝብ እንኳን የሌዊና የይሁዳ ዘር ነን ተብሎ ዛሬም ከኢየሩሳሌም የመጣ አፈር ነው፤ ከኢየሩሳሌም የመጣ ዘይት ነው ሲባል የተፈለገውን ወጪ በማውጣት በሽሚያ ሲገዛ ይታያል። አፈሩ ከዚያው ከንጦጦ አካባቢ ዘይቱ ከዚያው ከመርካቶ የመጣ መሆኑን ግን ሁላችንም የምናወቀው ጉዳይ ነው።
ተክለ ሃይማኖትና ይኩኖ አማላክም በቡልጋ አውራጃ የተወለዱ የካም ዘር ንጹሕ ኢትዮጵያዊ ሆነው እያለ የፖለቲካ ገበያ ለማግኘት ብለው እንደ እንጦጦው አፈርና እንደ መርካቶው ዘይት ከኢየሩሳሌም መጣን የሁዳና የሌዊ ዘር ነን ማለታቸው የሚደንቅ ነው። እሺ የይሁዳና የሌዊ ዘር መሆናቸውን እንቀበልና መንግሥት እና ክህነት ከኛ አይወጣም ብለው ማወጃቸውን እንዴት ልንቀበለው እንችላለን? ምክንያቱም መንግሥትም ሆነ ክህነት በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ተወርሶ በእርሱ የምናምን ሁሉ የመንግሥቱ ካህናት እንድንሆን በደሙ ቀድሶን የለምን? ራእ 5 10 ዛሬም የተክለ ሃይማኖት ሰባኪ የሆነው ማህበረ ቅዱሳን ወንጌል እንዳይሰበክ ከፍተኛ በጀት በጅቶ የሚከላከለው የይሁዳ መንግሥትና የአሮን ክህነት በክርስቶስ መንግሥት መወረሱን እኛም አማኞች የርሱ ካህናት መሆናችን እንዳይታወቅና ከይኩኖ አምላክ አገዛዝና ከተክለ ሃይማኖት የክህነት አገዛዝ  ነጻ እንዳንወጣ ለማድረግ ነው።
የኢትዮጵያ ሕዝብ የይኩኖ አምላክን (የይሁዳን መንግሥት) እንዳይነካ የተረገመበት ቃል እንዲህ ይላል «እመ ዘተሀበለ ላእለ ዝንቱ ሕግከ ወመንግሥትከ ይትዋረስ መርገመ» (ይህን መንግሥትና ሥርአትህን ደፍሮ ያፈረሰ ሰው ቢኖር መርገመ ጌባልን ይወርሳል) ገድ//ሃይ/ 26 16 ማህበረ ቅዱሳን ለአባላቱ ተግቶ የሚሰብካት ጥቅሥ ይህች ናት። አንድ የማህበረ ቅዱሳን አባል ስለኢትዮጵያ ችግር ምክንያት ስንወያይ የጠቀሰልኝ ይህችን ጥቅሥ ነው። እኔ ወንጌልን ስላልተማርን እኩልነትና ዲሞክራሲ አይገባንም ስለው እርሱ ግን የተክለ ሃይማኖትን ግዝት ስለተላለፍን ነው አለኝ። ስለዚህ ወደ ተክልዬ አዋጅ እንመለስ ነው ድምዳሜው። ይህ አስተሳሰብ እንደገና አገሪቱን ይረብሽ ካልሆልነ በቀር በዚህ ዘመን የሚሠራ አዋጅ አይደለም።
በክህነቱ በኩል ደግሞ እነጨጌ ፊልጶስ  የሚከተለውን አዋጅ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በማወጅ ለዛሬው መለያየታችን አብቅተውናል።
«ወኖላዊነ ካልእ ኢይሰየም ውስተ ኩሉ አጽናፍ በሐውርተ ሽዋ ወዳሞት ዘኢኮነ እምቤተ ተክለ ሃይማኖት ወኮነ ሥሩዓ በግዘት በመዋእለ አቡነ ፊልጶስ ሊቀ ኖሎት» (ከሽዋና ከዳሞት አውራጃ ጀምሮ በሁሉም ሀገር ከተክለ ሃይማኖት ወገን ያልሆነ አለቅነት አይሾም፤ ይህም በአባታችን በፊልጶስ ዘመን በግዝት ተወስኗል)ገድ//ሃይ/ 59 11
እንግዲህ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስን ያስገደላቸው ይህ አዋጅ ነው። እርሳቸው ከተክለ ሃይማኖት ዘር ባለመሆናቸው ከፍተኛ ስም ማጥፋት እና አድማ ሲካሄድባቸው ቆይተው በዛሬዎቹ የማህበረ ቅዱሳን ስውር አመራር አባላት ከሳሽነት ለደርግ ተላልፈው ተሰጥተው ተገደሉ። (አቡነ ቴዎፍሎስ እንዲገደሉ በሚጠይቀው ደብዳቤ ላይ በየጳጳሳቱ ቤት እየገባ በማስፈራራት ፊርማ ያሰባሰበው ሰው ዛሬ የማህበረ ቅዱሳን ሥውር አመራር አባል ነው ።የዚህን ግለሰብ ስም እና ታሪኩን ወደ ፊት እናቀርበዋለን) ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስን ከሥልጣን እንዲወርዱ ዋናውን ሚና የተጫወተው ከወያኔ ቀጥሎ ይህ የአቡነ ቴዎፍሎስ ተቃዋሚ ቡድን ነው። ወያኔም መንግሥት የኛ ነው ክህነት የናንተ ነው እያለ ሲሰብካቸው እውነት መስሏቸው መርቆርዮስን ካሳደዱ በኋላ ግን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ስለተሾሙ የወያኔ ስብከት ያለ ፍሬ ቀረ። ሥውሩ አመራርም በአቡነ ጳውሎስ ተቆጥቶ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ላይ በሰይፍ ሊያስመታቸው ሲሞክር የአቡነ ጳውሎስ ጠባቂ ቀደመና ግድያው ሳይሳካ ቀረ። ባሕታዊውም በቆፈረው ጉድጓድ እራሱ ገባ።
አሁን ይህ ሥውር አመራር በማህበረ ቅዱሳን አማካኝነት የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን ሥልጣን ለመንጠቅ እየሞከረ ነው። እስካሁን ብዙ ያልተሳኩ ሙከራዎች አድርጓል። ለምሳሌ ሕወሐትና ማህበረ ቅዱሳን በ 2001 ዓ/ም አካባቢ የተገናኙበትን ጠባብ መንገድ ማውሳት ይቻላል። ሕወሐት አቡነ ሳሙኤልን ፓትርያርክ ለማድረግ ያሰበ ይመስላል፤ ስለዚህ አቡነ ሳሙኤል ማህበረ ቅዱሳንን በመጠጋት አቡነ ጳውሎስን በሙስና ወንጅለው ከሥልጣን ለማወርድ ሞከሩ። ማህበረ ቅዱሳን ደግሞ አቡነ ሳሙኤልን ተጠቅሞ አባ ጳውሎስን ማውረድ ፈለገ። ሁለት የተላየ ፍላጎት ባንድ ዓይነት አድማ ይመራ ጀመር። ነገሩ ወደ ጫፍ ሲደርስ በአቡነ ጳውሎስ ላይ እንደራሴ መሾም ወደሚለው ድምዳሜ ተደረሰ።  በዚህ ጊዜ አቡነ ሳሙኤል እንደራሲነቱን ይወስዳሉ ብሎ ሕወሐት ሲጠብቅ ማህበረ ቅዱሳን ዋናው ጠባብ መንገድ ላይ ቀደመና እንደራሲነቱን ወስዶ ለአቡነ ቄርሎስ ሰጠ። በዚህ ጊዜ ሕወሐት በማህበረ ቅዱሳን ሥልጣኑ እንደተነጠቀ ሲረዳ በጉዳዩ ጣልቃ መግባት ጀመረ። አቡነ ሳሙኤልን ያገተ ለመምሰል በቅድስት ሥላሴ ኮሌጅ አስቀምጦ ሌሎችን ጳጳሳት የማህበረ ቅዱሳን ወኪል ሆነው እንደራሲነቱን ከአቡነ ሳሙኤል የወሰዱትን ደበደበ። ቤተ ክርስቲያናችን የፖለቲከኞች መራኮቻ ሆና ተቀምጣለች። ቤተ ክርስቲያን ከታወከች አገሪቱም ትታወካለች። ቤተ ክርስቲያን ትታደስ የምንለው ከእንደዚህ ዓይነቱም የፖለቲካ ሽኩቻ ነጻ እንድትሆን ስለምንፈልግ ነው።
እንግዲህ የቤተ ክርስቲያችንም ሆነ የሀገራችን የሁከት ምንጮች ገድለ ተክለ ሃይማኖትና የተክለ ሃይማኖትን ገድል በዘመናችን ለመድገም የሚራወጡ አድመኛና አክራሪ ብዱኖች ናቸው። እነዚህ አድመኞች የኢትዮጵያ ሕዝብ ቅዱሱን እና ንጹሑን የእግዚአብሔር ወንጌል አምኖ ወደ ሕይወት እንዳይሻገር፣ ወንጌሉን አፍነው የሚሰብኩትንም አሳደው ይህን በዘር ፖለቲካ የተቀመረውን ገድል ይሰብካሉ። ይህን የሚቃወሙትን እውነተኛ ኦርቶዶክሳውያንን ተሐድሶ መናፍቅ እያሉ ይገድላሉ ያሳድዳሉ ይደበድባሉ። በወንጌል አምኖ ንስሐ የገባ የዘላለም ሕይወት አለው የሚለውን የሐዋርያት እምነት ገልብጦ «በተክለ ሃይማኖት አጥንት ላይ ቁርባን የተቀበለ ሲዖልን አያይም» የሚለውን ባዕድ ወንጌል ይሰብካሉ። ወዴት ጠጋ ጠጋ? አንድን አማኝ ሲዖልን እንዳያይ የሚያደርገው ሥጋውና ደሙን መቀበሉ ወይስ በተክለ ሃይማኖት አጥንት ላይ መቀበሉ? የትኛው ነው እውነቱ? ደብረ ሊባኖስን የማያውቁና መሄድ የማይችሉ የጎጃም የጎንደር የወሎ የትግራይ የደቡብና የምራብ ክርስትያኖች እንዴት ሊሆኑ ነው? እነርሱ በዚያው ባካባቢያቸው ባሉ አብያተ ክርስቲያናት ቢቆርቡ ከሲኦል አይድኑምን? ገድለ ተክለ ሃይማኖት «በተክለ ሃይማኖት አጥንት ላይ የቆረበ ሲዖልን አያይም» ሲል ምን ለማለት ፈልጎ ነው። ነጹሑን ኦርቶዶክሳዊ እምነት ካጥንትና ከመቃብር ጋር ለምን ያያይዙታል? በኢትዮጵያ ከሞቱ ቅዱሳን ሁሉ የተክለ ሃይማኖት አጥንት ለመቁረቢያነት ለምን ተመረጠ? ምሥጢሩ ግን በማህበረ ቅዱሳን ለፈዘዙ ሰዎች እንጂ እግዚአብሔር እውነቱን ለገለጠልን ለኛ ግልጥ ነው። ያው የተክለ ሃይማኖትን ሥልጣነ ክህነት ለመከላከል ሲባል የተገነባ የጭንቀትና የፍርሐት አጥር ነው። ክህነት ከተክለ ሃይማኖት ወገን የሚለው ስብከት የጸና እንዲሆን የተጨማመረ ማታለያ ነው። እንግዲህ ይህ ሁሉ እንዲታረም ነው የዘወትር ጩኸታችን።
ማህበረ ቅዱሳን የተመሠረተው ቅዱሳንን ለማሰብ ነው ተብሏል። አሁን እያሰበ ያለው ግን በእምነት የተጋደሉትን የክርስቶስ ቅዱሳን ሳይሆን ለመንግሥት ሥልጣን የተጋደሉትን የይኩኖ አምላክ ቅዱሳንን ነው። የይኩኖ አምላክ ቅዱሳን ደብረ ሊባኖስ ተቀበሩ እያሉ ይሰብኩናል። የክርስቶስ ቅዱሳን ግን ንስሐ ግቡ በሃይማኖት ጽኑ እያሉ ይሰብኩናል። አሁን ማህበረ ቅዱሳን የሚሞትበት ጊዜ ደርሷል፤ ቁርባኑንም በተክለ ሃይማኖት አጥንት ተቀበሎታል። ግን የት ይቀበር ይሆን? ሲሰብክ እንደኖረው ደብረ ሊባኖስ ይቀበር ይሆን? እንደዚያ ከሆነ ሲኦልን አያይም። ወይስ አራት ኪሎ ቤተ መንግሥት ይቀበር ይሆን እንደዚህ ከሆነ ግን ኢትዮጵያን ይቀብራታል። ቀባሪዎች ሆይ! እባካችሁ መጥፎ ሽታ ሳይመጣ ቶሎ ቅበሩልን!!!
ተስፋ ነኝ

32 comments:

 1. ተስፋ ምንሆነህ ነው ስለአንድ ሰው ስድብ ወይም ሐሜት ብቻ የቆምክ ያውም በህይወት የሌለን ሰው ተወው የአቡነ ተክለሐይማኖት ፃድቅ አባትነትም አንተ እንዳልከው ይቅርና ምነው በምድር ላይ የሌለን ሰው እያነሳሳህ ማውራት ብታቆም ፡፡ እንኳን በአይነስጋ የማታየውን በሐሜት ማንሳት ቀርቶ ከጐንህ በአካል ያለ ወንድም እህትህን /የአዳምን ዘር/ በሌሉበት ማንሳት እኮ ሐሜት ነው፡፡ ሐሜት ደግሞ ከጌታ አይደለም!!! ስለዚህ ቆም በልና ምን እየሠራሁ ነው ብለህ እስቲ እራስህን ለማየት ሞክር፡፡ እርሳቸው አንተ እንዳልከው ከተሳሳቱም እንኳ ፈራጁ ጌት እንደሥራቸው ይከፍላቸዋል አንተ ግን አሳዘንከኝ ጊዜህን የአንድን ሰው ስም በማጥፋት /ማውራት/ ሌላ ምንም ሥራ ሳትሠራ ጌታ ለሚጠራህ አሳዘንከኝ ከተጫነብህ የሐሜት እርኩስ መንፈስ ውስጥ ጌት እንዲያወጣህ የዘወትር ፀሎቴ ነው፡፡ ጌታ በቸርነቱ ወደ መልካም ሥራ ይመልስህ!!! "አሜን"

  ReplyDelete
  Replies
  1. ተናግረከረ ሞተኃል አስተውል ብዙ ሰዎችን ሲኦል እየከተተ ያለን ነገር ነው የነገረን እራስክ ተደፍኖብክ ሌላውን አትድፈን

   Delete
 2. አቤቱ ጌታ ሆይ የሚድርጉትን፣የሚናገሩትን፣የሚፅፉትን አያዉቁምና ይቅር በላቸዉ!!!


  ወንድሜ ተስፋ እግዚአብሄር ይቅር ይበልህ፤ማስተዋሉንም ይስጥህ፡፡ ለመሆኑ የእግዚብሄርን ቃል፣ቤተክርስቲያንን እና ቅዱሳኑን ማወቅ ቀርቶ እራስህንም የምታዉቅ አልመሰለኝም እራሱን ያወቀ ሰዉ እግዚአብሄርን ያዉቃል እግዚአብሄርን የሚዉቅ ሰዉ ቅዱሳንን ያዉቃል ቅዱሳንን ቅዱስ ተብለዉ እንዲጠሩ ያደረገዉ ቅዱሱ እግዚአብሄር ስለሆነ፡፡ ወንድም ተስፋ የእግዚብሄር ቃል እና የእግዚአብሄር ሰዎች መዘባበቻ አይደሉም፡፡የፖለቲካ ጥማትህን እዚያዉ በፖለቲካዉ መድረክ ተወጣ፡፡
  ማህበረ ቅዱሳንን ለመተቸት ብለህ በኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች ላይ እንደተዘባበትክ ማወቅ አለብህ፡፡ ማህበረቅዱሳን የመጣዉ ትናንት የቅዱሳን ክብር መታሰብ የጀመረዉ ጥንት እኛ ሳንሆን እራሱ ባለቤቱ ነዉ ያከበራችዉ፡፡ ባተዉቀዉ ነዉ እንጅ ብሎግህ ላይ ያስቀመጥካቸዉ ቅዱሳን አባቶች(ጳጳሳት) የአቡነ ትክለሃይማኖት እና የሌሎች ቅዱሳን አባቶች ፍሬዎች ናቸዉ፡፡ “ዋኖቻችሁን አስቡ የእምነት ፍሬያቸውንም እየተመለከታችሁ በእምነት ምሰሉአቸዉ” እንደተባለ በእምነት አቡነ ተክለሃማኖትን እና ሌሎች ቅዱሳን አበዉን መስለዉ ያለፉ ቅዱሳን ናቸዉ፡፡ ለማንኛዉም እግዚአብሄር ማስተዋሉን ያድልህ በእዉነት “ የምትናገሩትን አታዉቅምና ትስታላቸሁ” እንደተባለ የምትናገረዉንና የምትፅፈዉን አታዉቅምና አትሳት፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ተናግረከረ ሞተኃል አስተውል ብዙ ሰዎችን ሲኦል እየከተተ ያለን ነገር ነው የነገረን እራስክ ተደፍኖብክ ሌላውን አትድፈን

   Delete
 3. Are you preaching politics or religion??

  ReplyDelete
 4. “ቅዱስ ሚካኤል ስለሙሴ ሥጋ ከሰይጣን ጋር ሲከራከር እግዚአብሔር ይገስጽህ አለው እንጂ የስድብን ቃል ሊናገር አልደፈረም” ብሎ መጽሐፍ ቅዱስ እንዳስተማረን እናንተንም “እግዚአብሄር ይገስጻችሁ” ከማለት በቀር አንዳችም ክፉ ነገር ለመናገር አንሻም:: በበደላችሁት መጠን መታገሱ ትመለሱ ዘንድ የንስሀ ዕድሜ ሲሰጣችሁ እንጂ የአባታችን የተክለሃይማኖት አምላክ እናንተንና መሰሎቻችሁን ማስወገድ ተስኖት አይምሰላችሁ:: ደግሞስ በመጨረሻው የፍርድ ቀን የት ታመልጡት መሰላችሁ? አባታችንንስ ምን የምታጎድሉባቸው መሰላችሁ? በተሳደባችሁ ቁጥር ክብራቸውን ከፍከፍ ያደርግላቸዋል እንጂ ግን በኋላ ጊዜ ጸጸቱን አትችሉትምና ተመለሱ ንስሀ ግቡ ለአንደበታችሁ ለከት ይኑረው:: እንኳንስ አቡነ ተክለሃማኖትን ለመንቀፍና ራሳችሁን ማረም የማትችሉ በጨለማ የምትመላለሱ መንገድ የጠፋባችሁ መሆናችሁን አታውቁምና፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Ewunet belehal... I always think this when I see this blog.

   Delete
  2. one more stupid

   Delete
 5. የጻፍከው እውነት ቢሆንም በውሸት ጠጅ የሰከሩ ሲያነቡት ይንገዳገዳሉ!!!!!

  ReplyDelete
 6. Semonun Degimo Abune Abirhamin Or Abune Samueiln Patiryark Lemasdereg eyetedekeme new Mahibere Kidusan Ahun meregagat yinorbetal Abune Pawlos Bemot Melyetachew Aykerm Simotu Yidersal Le Ginbot Sibseba yemyakerbewn Hulu Neger AStekaklowal Abba G wold-Kesis Teshome -Abba Zelibanos yetebalutim Abune Abirham Menfesaw Naachew Abune Fanueil Sigaw Nachew lemalet Ke America yimetsalu tebilo eyetetsebeke new Mahibere Kidusann Yedegefe Menfesaw Yetekawme Sigaw new Ahun Arfew Kaltekemetsu ABune Abirham Ethiopa honew Yeserut America Yaderegut Hulu tezerziro yiwetsal Temedibew yemimetut Lieukanm Mannetachew yitawekal Sew Menfesaw Yemibalew Mahibere Kidusan Hono New Or Besira new Kebad Neger Ale

  ReplyDelete
 7. Weyi - Enante. Defaroch nachihu...

  If you don't know abount abatachin...
  http://st-takla.org/Story-3.html

  Ayne-berhanun yigletelachu... Yihuda ye-mimeles leb baynorequm.

  ReplyDelete
 8. EGEZHABEHER AMELAKE YKER YEBALKE!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 9. Similarly, the Jews accused our Lord in politics (the Jewish leaders accused Jesus of claiming to be the king of the Jews, an accusation claimed to attract the interest the Roman Empire), in religion (the Jews said Jesus had to die because of his claim to the sonship of God) and economic issue (the Jews said that Jesus had forbidden them of paying taxes for the Roman Empire).
  The Jews said “We found this man subverting our nation, forbidding us to pay the tribute tax to Caesar and claiming that he himself is Christ, a king.” (Luke 23:2)
  In the same way and identical matters, 'abaselam and the writer' accuse the holly man chosen by God himself. This was the word our Lord said when he was in the holy cross:

  "Father, forgive them, for they do not know what they do." (Luke 23:34)

  'abaselam or the writer' you see who you are! And you see who Abune Teklehaimanot is? Abune Teklehaimanot not only resembled Jesus Christ in miracles and holy deeds but also of with false accusations against him'.

  While his people accused Jesus and handed over him to death , the Genitals came to redeemed by blood of Jesus. Similarly, while you, people of Abune Teklehaimanot accuse him, the Egyptians embrace him as their own holy man and get the holy blessings from him.

  http://st-takla.org/index.html
  or
  http://st-takla.org/Story-index.html

  Geta hoy yemeyadirgutin ayawikumin; Yikir belachew‼! Libachiwin seyitan yizot newina; kezi kifu menifes alakih bezih yesidib afachew lay kidus kalihin anureh lememsiker abkachew!‼ Amen∷

  ReplyDelete
 10. Gedle teklehymanotn yetsafew MK new ende??

  ReplyDelete
 11. የዚች በራሷ ልጆች ታሪኳ የተበላሸባት ኢትዮጵያ ተቆርቋሪ ወገኖቼ!!!

  እስከ መቼ ድርስ ነው????

  'ግእዝ ተናጋሪ ሁሉ የቤት ክርስቲያን አዋቂ'

  'እንግሊዘኛ ተናጋሪ ሁሉ የተማረ'

  'የጠመጠመና መስቀል የያዘ ሁሉ ቄስ'

  'መልካም ስም የያዘ ሁሉ ደግ'

  'አገሬ ቤተ ክርስቲያኔ ባንዲራዬ ያለ ሁሉ እውነተኛ የሕዝብ ተቆርቋሪ'

  'ፎካሪና ያዙኝ ልቀቁኝ ያለ ሁሉ ጀግና'

  'ሰው ሁሉ ሰው'

  'ተናጋሪ ሁሉ ፓለቲከኛ'

  'ሱሪ የታጠቀ ሁሉ ወንድ'

  'ቀለሙ የነጣ ሁሉ አዋቂ ፈረንጅ'

  'በስመ አብ ያለ ሁሉ ጸሎተኛ'

  'በብራና የተጻፈ የቤተ ክርስቲያናችን ድኩስ ሁሉ እውነትን የያዘ መጽሃፍ'

  ወዘተ......እየመሰለን እየመሰለን እየመሰለን....

  እድሜ ልካችንን ስንታለል የምንኖረው???????

  እረ የታዬና የተገኘ ሁሉ አይበላምና ቆም ብለን እናስተውልና ለራሳችንም ለአገራችንም የሚረባንን እናድርግ:: እስቲ ይታያችሁ በመንግሥት ሥራ ውስጥ እንደዚህ ያለ መፈንቅለ አገዛዝን ከአንዱ ወደ ሌላው ያስተላለፉ ጀግና ፓለቲከኛ ተክለሃይማኖትን የመንግሥተ ሰማይ ባለሟል አድርጎ በማቅረብ ሕዝብን ማታለል ምን ይባላል??? ርግማን ወይስ መንፈሳዊ ድንቁርና?? አሁንስ ለኢትዮጵያዊ ማንነት ትርጉም እያጣሁለት ነው:: ይልቅስ 'የታወቀው ፓለቲከኛ ጳጳስ' በሚለው እውነተኛ ማንነታቸውና በሰሩት ሥራ እንዲዘከሩ ቢደረግ ሁላችንም በባእሉ ላይ ተገኘተን እናከብር ነበርና ቢታሰብበት????

  ከገድለ ተክለሃይማኖት መጽሐፍ ይልቅ ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ብንመለስ እጅግ የተሻለ ይሆናልና ትኩረታችን በዚሁ ቢሆን???

  ሰላም ሁኑልኝ

  እህታችሁ

  ሰላም ነኝ

  ReplyDelete
 12. እግዝአብሔር ይባርክ በርቱ እውነቱን ግለጡ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. እውርን እውር አይዞህ ቢለው ምንድን ነው ጥቅሙ?

   Delete
 13. በርቱ በርቱ በርቱ ቀጥሉ ምስጥሩ ይታወቅ እውነቱ ይገለጽ

  ReplyDelete
 14. በርቱ!!!!!!ተባረኩ

  ReplyDelete
 15. በርቱ!!!!!!ተባረኩ

  ReplyDelete
 16. 666 dardaritaw kidusanin mesideb new!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ይሔ ብቻ አይድለም የቤተክስቲያንን አስተምህሮ የሚንቅፍ ነገር ግን የማርቴል ሉተርን የሙት ፍልስፍና የሚያመልክ ዳቢሎስ ወይም የሰይጣን ባሪያ ማንን ለማታለል መሆኑንም ማወቅ አለብህ

   Delete
 17. ማኅበረ ቅዱሳን የአቋቋም ምስክር ትምህርት ቤትን በ4.6 ሚሊዮን ብር ለመገንባት ውል መፈረሙን ገለጸ
  ሙሉ ዘገባውን የወሰድነው ከማኅበረ ቅዱሳን ድረ ገጽ ላይ ነው::

  ReplyDelete
 18. አቡነ ተክለ ሃይማኖት ማናቸው? በዲያቆን ዳንኤል ክብረት

  አቡነ ተክለ ሃይማኖት በ1186 ዓም በሰሜን ሸዋ ቡልጋ ጽላልሽ ተወለዱ፡፡ አባታቸው የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ሲያስተምሯቸው አካባበቢያቸው ደግሞ በዘመኑ የነበሩ ልጆች ይማሩ የነበረውን ፈረስ መጋለብን፣ ቀስት መወርወርን፣ እርሻን እና አደንን አስተምረዋቸዋል፡፡

  በሰባት ዓመታቸው ከግብፃዊው አቡነ ቄርሎስ ዲቁናን ከተቀበሉ በኋላ እግዚአብሔር በክህነት ሕዝቡን እንዲያገለግሉ መረጣቸው፡፡ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ለክህነት መጠራት በዚህ ዓለም ትዳር መሥርቶ፣ የዓለሙንም ሥራ ሠርቶ መኖር አያስፈልግም ከሚል ፍልስፍና የመነጨ አይደለም፡፡ ከ8ኛው መክዘ ጀምሮ በሀገሪቱ የመንፈስ መቀዛቀዝ ይስተዋል ነበር፡፡ ዮዲት ጉዲት መንግሥቱን ይዛ በክርስትናው ላይ ከዘመተች በኋላ ሰሜኑ እና ደቡቡ ተቆራርጧል፡፡ የሃሳብን ልዕልና የሚያመጣው የመንፈስ ልዕልና ተዳክሟል፡፡ ለዚህም ኢትዮጵያን የሚዋጅ ኢትዮጵያዊ ያስፈልግ ነበር፡፡ ይህ ነው የተክለ ሃይማኖት የጥሪ ምክንያት፡፡

  አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከአባታቸው ዕረፍት በኋላ ቅስናን ከአቡነ ቄርሎስ ተቀብለው በጽላልሽ አካባቢ በክህነት ከአባታቸው ጋር አገልግለዋል፡፡ አባታቸው ሲያርፉ በወንጌሉ ማንም ሊከተለኝ የሚወድድ ቢኖር ያለውን ሁሉ ትቶ መስቀሉን ተሸክሞ ይከተለኝ ያለውን በመከተል ሀብታቸውን ለድኾች መጽውተው ለወንጌል ስብከት ወጡ፡፡ የዋልድባው ገድለ ተክለ ሃይማኖት ወደ አቡነ ኢየሱስ ሞዓ ከመሄዳቸው በፊት ቅስናን ተቀብለው በሸዋ እና በዳሞት ማገልገላቸውን ይገልጣል፡፡
  አቡነ ተክለ ሃይማኖት በዳሞት እና በሸዋ ካገለገሉ በኋላ መጀመርያ ደቡብ ወሎ ቦረና ወደ ነበረው ወደ ደብረ ጎል ገዳም ገብተው አሥር ዓመት(12 የሚልም አለ) በትምህርት እና በሥራ አሳልፈዋል፡፡ በዚያም ዋሻ ፈልፍለው አስደናቂ ሕንፃ ሠርተው ነበር፡፡
  ገድለ አቡነ ኢየሱስ ሞዓ እንደሚለው አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወደ ሐይቅ የገቡት በሠላሳ ዓመታቸው ነው፡፡ ይህም የሚያሳየን በሸዋ እና በወላይታ ያገለገሉት ገና በወጣትነታቸው ጊዜ መሆኑን ነው፡፡ በ1216 ዓም አካባቢ ወደ ሐይቅ የገቡት አቡነ ተክለ ሃይማኖት በሐይቅ ከመመንኮሳቸው በፊት ሰባት ዓመት ከመነኮሱም በኋላ ሦስት ዓመት በትም ህርት ፣ በሥራ እና በአገልግሎት ቆይተዋል፡፡
  ሐይቅ እስጢፋኖስ በዚያ ዘመን እንደ አዳሪ ትምህርት ቤት ያለ ዩኒቨርሲቲ ነበረ፡፡ ወደዚያ የሚገባ ሁሉ ሦስት ነገሮችን ይማራል፡፡ ትምህርት፣ የጥበበ እድ ሥራ እና ሥርዓተ ምንኩስና፡፡ ትምህርቱ የቤተ ክርስቲያኒቱን መላ ትምሀርት ያካትታል፡፡ የሞያ ትምህርቱም መጻፍ፣ መደጎስ፣ ሕንፃ ማነጽ፣ ልብስ መሥራት፣ እርሻ፣ የከብት ርባታ እና የሥዕል ሥራን ይመለከታል፡፡ ከእነዚህ ጎን ለጎን ደግሞ ጽሙድ እንደ ገበሬ ቅኑት እንደ በሬ እንዲሆኑ ሥርዓተ ምንኩስናን ይማራሉ፡፡
  በእነዚህ ትምህርቶች የታነፁት መነኮሳት ከገዳሙ ሲወጡ ዛሬ የፒኤች ዲ ተማሪ ዴዘርቴሽን እንደሚያቀርበው የተማ ሩትን ጽፈው አንድ የብራና መጽሐፍ አዘጋጅተው ይወጣሉ፡፡ በዚህም ምክንያት ሐይቅ ከስምንት መቶ መነኮሳት በላይ በአንድ ጊዜ የሚማሩባት በመጻሕፍትም የበለጸገች ዩኒቨርሲቲ ነበረች፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖት እዚህ ነው አሥር ዓመታትን ያሳለፉት፡፡
  ከሐይቅ ወጥተው በዘመኑ በሥርዓተ ምንኩስና እና በትምህርት ብሎም በጥበበ እድ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ወደ ነበረው ወደ ደብረ ዳሞ ሄዱ፡፡ በዚያም ከአቡነ ዮሐኒ ዘንድ መንፈሳዊ ትምህርት፣ ሥርዓተ ምንኩስና እና ጥበበ እድ ሲማሩ ሰባት ዓመት አሳለፉ፡፡ ያነጹት ፍልፍል ድንጋይ ዋሻ፣ መጻሕፍት ሲጽፉ ቀለማቸውን ያስቀምጡባቸው የነበሩትን ሽንቁሮች ዛሬም በደብረ ዳሞ ማየት ይቻላል፡፡
  ቀሪዎቹን አምስት ዓመታት ሌሎችን የትግራይ ገዳማት እየተዘዋወሩ ሲመለከቱ ቆይተው ከሸዋ በወጡ በሃያ ሁለት ዓመት እድሜያቸው ሃምሳ ሁለት ሲሆን ለበለጠው ክብር እና ርእይ በግብጽ በኩል ወደ ኢየሩሳሌም ተሻገሩ፡፡ ከኢየሩሳሌም ሲመለሱ በሐይቅ በኩል አድርገው ደብረ ጎልን ተሳልመው በሚዳ እና በመርሐ ቤቴ በኩል ወደ ሸዋ በመምጣት ከዮዲት ዘመን በኋላ በመንፈሳዊ ሕይወት የተጎዳውን ሸዋን እና ደቡብ ኢትዮጵያን በመዘዋወር ለአሥር ዓመታት ያህል አስተምረዋል፡፡
  አቡነ ተክለ ሃይማኖት ተግተው በማስተማራቸው የተኛው ሁሉ ነቃ፣ የደከመው በረታ፣ የጠፋውም ተገኘ፡፡ በስብከታቸው እንደገና ለነቃው ለመካከለኛው እና ለደቡብ ኢትዮጵያ ሐዋርያትን ለማፍራት እንዲችሉ አንድ ገዳም ለመመሥረትና ደቀ መዛሙርትን ለማስተማር አሰቡ፡፡ እናም ወደ ደብረ አስቦ ገዳም ገቡ፡፡ ቦታውን አስተካክለው እና ከደብረ ዳሞ እና ከሐይቅ የተከተሏቸውን ጥቂት ደቀ መዛሙርት ይዘው በደብረ ሊባኖስ ገዳም ልክ እንደ ሐይቅ እስጢፋኖስ ሁሉ ሦስቱን ነገሮች ያካተተ አገልግሎት ጀመሩ፡፡ ምንኩስና፣ ትምህርት እና ሥራ፡፡ መነኮሳቱ መንፈሳዊ ትምህርት ይማራሉ፤ በሕገ ገዳም ይመራሉ፤ ለራሳቸው እና ለአካባቢው ሕዝብ ርዳታ የሚሆን እርሻ ያርሳሉ፡፡
  ደቀ መዛሙርትን አፍርተው፣ ገዳማቸውን አደራጅተው፣ ስብከተ ወንጌልንም አስፍተው አስፍተው ሰያደ ላድሉ በሕይወታቸው የመጨረሻ ዓመታት ወደ ደብረ አስቦ ዋሻ ገብተው በአንድ እግራቸው በጾም እና በጸሎት ተወሰኑ፡፡ በጸሎት ብዛትም እግራቸውን በማጣታቸው ስለ ክብራቸው ከእግዚአብሔር ክንፍ ተሰጥቷቸዋል፡፡
  አቡነ ተክለ ሃይማኖት አገልግሎታቸውን ፈጽመው ነሐሴ ሃያ አራት ቀን 1287 ዓም በ99 ዓመታቸው ዐረፉ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. tewew yihe kifu menfes yetetsenawetew yihuda new

   Delete
 19. ስለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የሚነሡ ጥያቄዎች
  አቡነ ተክለ ሃይማኖት እና የመንግሥት ለውጥ
  አንዳንዶች «ከዛግዌ ሥርወ መንግሥት ወደ ሰሎሞናዊ ሥርወ መንግሥት የተደረገውን ሽግግር ያከናወኑት አቡነ ተክለ ሃይማኖት ናቸው፡፡ ይህንንም ያደረጉት ይኩኖ አምላክ የሸዋ ሰው ስለሆነ ለዘራቸው አድልተው ነው» ይላሉ፡፡
  በሸዋው ይኩኖ አምላክ እና በዛግዌ ሥርወ መንግሥት ወራሹ በነአኩቶ ለአብ መካከል መቀናቀን የተጀመረው አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሐይቅ በትምህርት ላይ በነበሩበት ጊዜ ነበር፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሕፃን በነበሩበት ጊዜ ከዳሞት የሚመጣው የሞተለሚያውያን ኃይል ሸዋን ደጋግሞ በመውረር አብያተ ክርስቲያናትን ዘርፏል ሕዝቡንም ማርኳል፡፡ ይህ ጉዳይ የሸዋን ሕዝብ ማስቆጨቱ እና ማነሣሣቱ የማይቀር ነው፡፡
  በተለይም ከአኩስም የተሰደደው የሰሎሞናዊው ሥርወ መንግሥት ዘር ሸዋ መንዝ ነው የገባው ተብሎ በሚታመንበት ሁኔታ ሸዋዎች ራሳቸውን ለመከላከል መደራጀት ጀምረዋል፡፡ ደቡቡ ኢትዮጵያ ከማዕከላዊው መንግሥት መቀመጫ ከሮሐ እየራቀ ሄዶ ስለነበር ለይኩኖ አምላክ ጥሩ መደላድል ሆኖታል፡፡
  ገድለ ኢየሱስ ሞዓ እንደሚተርከው የመንግሥትን ነገር ከይኩኖ አምላክ ጋር የተነጋገሩት አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሳይሆኑ አቡነ ኢየሱስ ሞዓ ናቸው፡፡ ያን ጊዜ ደግሞ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በተማሪነት ሐይቅ ገዳም ውስጥ ነበሩ፡፡
  አቡነ ኢየሱስ ሞዓ እና ይኩኖ አምላክ በመንግሥት ጉዳይ ላይ ለመነጋገር የበቁት ይኩኖ አምላክ በሸዋ ላይ ይደርስ ከነበረው የሞተለሚ ጥቃት ሸሽቶ በሐይቅ እስጢፋኖስ ትምህርት ቤት ወጣትነቱን ያሳለፈ በመሆኑ ነበር፡፡
  ሁለቱ ባደረጉት ስምምነት
  የዐቃቤ ሰዓትነትን መዓርግ ለሐይቅ ገዳም መምህር እንዲሆን ተደርጓል፡፡ ይህም ማለት የንጉሡ ገሐዳዊ ግንኙነቶች በዐቃቤ ሰዓቱ በኩል እንዲፈጸሙ ማለት ነው፡፡
  የንጉሡ ደብዳቤ ወደ ሐይቅ ገዳም ሲላክ መነኮሳቱ ተቀምጠው እንዲሰሙ
  ለገዳሙ የተሰጠውን መሬት የመኳንንቱም ሆነ የነገሥታት ልጆች እንዳይነኩ
  ነፍስ የገደለ፣ ንብረት የሰረቀ፣ እግረ ሙቁን ሰብሮ እዚህ ገዳም ገብቶ ቢደውል ከሞት ፍርድ እንዲድን
  ለገዳሙ የተሰጠው ርስት ለአገልጋዮች ብቻ ስለሆነ ዘር ቆጥሮ ማንም ተወላጅ እንዳይወርስ
  የገዳሙ ርስት መነኩሴ ላልሆነ ጥቁር ርስት እንዳይሰጥ
  የሚሉት ታወጁ፡፡ ይህ ሁሉ ሲከናወን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሐይቅ ትምህርት ላይ ነበሩ፡፡
  በኋላ ዘመን ይኩኖ አምላክ ኃይሉ እየበረታ ነአኩቶ ለአብም ግዛቱ እየጠበበ እና ኃይሉ እየደከመ ሲሄድ ከወሎ በታች ያለውን ሀገር የያዘው ይኩኖ አምላክ እና ላስታን እና ሰሜኑን የያዘው ይኩኖ አምላክ ለጦር ይፈላለጉ ጀመር፡፡ በዚህ ዘመን ነበር አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከኢየሩሳሌም የተመለሱት፡፡
  አቡነ ተክለ ሃይማኖት ያደረጉት ነገር ቢኖር ኃይሉ እየገነነ የመጣውን ይኩኖ አምላክን እና የወቅቱን ንጉሥ ነአኩቶ ለአብን ማደራደር ነበር፡፡ ይኩኖ አምላክ ለመንገሥ ከቅብዐት በቀር የቀረው ኃይል አልነበረም፡፡ የነአኩቶ ለአብ ኃይል ደግሞ ቢዳከምም አልሞተም፡፡ ሁኔታው ወደ እርስ በርስ ጦርነት እንዳይሄድ ያሰጋቸው አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሁለቱን በማደራደር ከአንድ ስምምነት ላይ አደረሷቸው፡፡
  ይኩኖ አምላክ ምንም ኃይል ቢኖረው ነአኩቶ ለአብ እስኪያርፍ ድረስ ንግሥናውን እንዳያውጅ
  ከነአኩቶ ለአብም በኋላ የዛግዌ ዘር የላስታን አውራጃ እንዲገዛ
  የላስታው ገዥ በፕሮቶኮል ከንጉሡ ቀጥሎ እንዲሆን
  ይህ ስምምነት ባይኖር ኖሮ ጦር በሰበሰበው በይኩኖ አምላክ እና ሥልጣን ላይ በነበረው በነአኩቶ ለአብ መካከል በሚፈጠረው ጦርነት የሀገሪቱ ልጆች ባለቁ ነበር፡፡ ዛሬ ቢሆን ይሄ ተግባር የኖቬል ሽልማት የሚያሸልም ነበር፡፡ ይህ ስምምነት በኋላ በዐፄ ይትባረክ ዘመን በመፍረስ የተከሰተውን ጦርነት ያየ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን ያደንቃል እንጂ አይተችም፡፡
  ሲሦ መንግሥት
  አንዳንዶች «አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሰሎሞናዊ ሥርወ መንግሥት በዋሉት ውለታ ለቤተ ክርስቲያን ሲሦ መንግሥት ተሰጠ» ይላሉ ይኩኖ አምላክ ሲነግሥ በኢትዮጵያ ውስጥ ጳጳስ አልነበረም፡፡ ከአቡነ ጌርሎስ ሞት በኋላ ከግብፅ የመጣ ጳጳስ አልነበረም፡፡ ይህ ሁኔታ በመንፈሳዊ ትንሣኤ ላይ ለነበረችው ኢትዮጵያ የአገልጋዮች እጥረት አስከተለ፡፡ በዚህ ጊዜ የተሰባሰቡት የኢትዮጵያ ሊቃውንት በትምህርትም በአገልግሎትም የበረቱትን አቡነ ተክለ ሃይማኖትን መረጡ፡፡ የሚሾም ሲኖዶስ አልነበረምና እግዚአብሔር «ሐዋርያትን በሾምኩበት ሥልጣን ሾምኩህ» አላቸው፡፡
  ይኩኖ አምላክ ምንም እንኳን በንግሥናው ቢገዛ እንደ ወጉ ሥርዓተ መንግሥት አልተፈጸመለትም ነበር፡፡ በመሆኑም በዘመኑ የነበሩት አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሥርዓተ መንግሥቱን ፈጸሙለት፡፡ እርሱም ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ርስት ሰጠ፡፡
  ለቤተ ክርስቲያን ርስት መስጠት በይኩኖ አምላክ የተጀመረ አይደለም፡፡ እንዲያውም ቅዱስ ላሊበላ ለአኩስም፣ ለላሊበላ፣ ለመርጡለ ማርያም እና ለተድባበ ማርያም የሰጠው ርስት ይበልጣል፡፡ በወቅቱ ለሐዋርያዊ አገልግሎት እና ለተማሪዎች ድርጎ ለቤተ ክርስቲያን ጥሪት ያስፈልጋት ስለነበር ይኩኖ አምላክ ርስት ሰጥቷል፡፡ ይህ ግን ከመንግሥት ዝውውር ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም፡፡ ዛሬም ቢሆን እኮ አንዳንድ የአውሮፓ ሀገሮች ለቤተ ክርስቲያን የተለየ በጀት ይሰጣሉ፡፡
  እጨጌ የሚለውን ስም ከርስት አስተዳዳሪነት ጋር የሚያገናኙት ሰዎች አሉ፡፡ እጨጌ የሚለውን ስም ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት የሰጣቸው መንግሥት ሳይሆን የወላይታ ሕዝብ ነው፡፡ በወላይተኛ «ጨጌ» ማለት «ሽማግሌ፣ ታላቅ፣ አባት» ማለት ነው፡፡ ወደ አማርኛ ሲመጣ «እጨጌ» ተባለ፡፡ የአቡነ ተክለ ሃይማኖትን አገልግሎት አይቶ ይህንን የሰጣቸው ሕዝቡ ነው፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሥልጣን ወዳድ አለመሆናቸውን በግልጽ አሳይተዋል፡፡ ከብዙ ዘመናት በኋላ አቡነ ዮሐንስ 5ኛ ከግብጽ መጥተው አቡነ ተክለ ሃይማኖትን በግማሽ ኢትዮጵያ በመንበረ ጵጵስና እንዲያገለግሉ ለምነዋቸው ነበር፡፡ እርሳቸው ግን ለሥልጣን ፍላጎት እንደሌላቸው ገልጸው እንዲያ ሕዝብ ሲወዳቸው እና ሲፈልጋቸው ወደ በኣታቸው ነው የተመለሱት፡፡

  ReplyDelete
 20. «ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሌላ ናቸው »
  አንዳንዶች «በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ከ8 እስከ 13ኛው መክዘ ባለው ጊዜ የኖሩ ሌላ ተክለ ሃይማኖት የሚባሉ ጻድቅ ነበሩ፡፡ የርሳቸው ታሪክ ከሌላ ተክለ ሃይማኖት ታሪክ ጋር ተዳብሎ አሁን ያለWን ገድለ ተክለ ሃይማኖት አስገኘ፡፡ እናም ጻድቁ ተክለ ሃይማኖት ዘደብረ ሊባኖስ አይደሉም » ይላሉ
  እስካሁን ድረስ ይህንን አባባል የሚጠቅሱ ሰዎች ያቀረቡት ማስረጃ የላቸውም፡፡ እገሌ አይቶት ነበር፡፡ እዚህ ገዳም ነበር ከማለት ውጭ፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ለሌለ ማስረጃ ሲባል ያለ ማስረጃ አይሰረዝም፡፡
  አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዘደብረ ሊባኖስን በተመለከተ ያሉት ማስረጃዎች አራት ዓይነት ናቸው፡፡
  ገድላቸው
  የሌሎች ቅዱሳን ገድሎች
  ዜና መዋዕሎች እና
  የግብፅ ቤተ ክርስቲያን መረጃዎች
  ገድለ ተክለ ሃይማኖት
  እኔ ለማየት የቻልኩት የደብረ ሊባኖስ፣ የሐይቅ እስጢፋኖስ፣ የዋልድባ፣ የጉንዳንዳጉንዲ እንዲሁም ዐፄ ምኒሊክ ወላይታን ሲወጉ ያገኙት የወላይታ ገድለ ተክለ ሃይማኖት ቅጂዎች አልፎ አልፎ ከሚያሳዩት መለያየት በስተቀር የሚተርኩት በ13ኛው መክዘ ስለነበሩት ተክለ ሃይማኖት ነው፡፡ እኒህ ተክለ ሃይማኖት ጽላልሽ ተወልደው፣ በኢትዮጵያ ገዳማት ተምረው፣ በመላ ሀገሪቱ ሰብከው፣ ግብጽ እና ኢየሩሳሌም ተሻግረው፣ ደብረ ሊባኖስን መሥርተው ያገለገሉትን ተክለ ሃይማኖት ነው የሚናገሩት፡፡
  ሌላው ቀርቶ ወሎ ጉባ ላፍቶ፣ ጎንደር አዞዞ ተክለ ሃይማኖት የተገኙት ገድላትም ተመሳሳይ ታሪክ ነው የሚተርኩት፡፡ እስካሁን ከኒህኛው ተክለ ሃይማኖት ውጭ ስላሉ ሌላ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የሚተርክ ገድል አልተገኘም፡፡ አለ ከመባል በቀር፡፡
  የኢትዮጵያ የብራና መጻሕፍትም ሆኑ በአካል ያልተገኙት ማይክሮ ፊልሞቻቸው በተከማቹባቸው በብሔራዊ ቤተ መጻሕፍት ወመዛግብት፣ በመንበረ ፓትርያርክ ሙዝየም እና ቤተ መጻሕፍት፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናት ቤተ መጻሕፍት፣ በብሪቲሽ ሙዝየም እና ቤተ መጻሕፍት፣ በቫቲካን ቤተ መዛግብት እና ቤተ መጻሕፍት፣ አሜሪካ ኮሌጅቪል በሚገኘው ቅዱስ ዮሐንስ ኮሌጅ ያሉትን ማይክሮ ፊልሞች እና የብራና መጻሕፍት ዝርዝሮችን ብናይ ስለ ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዘደብረ ሊባኖስ እንጂ ስለ ሌላ ተክለ ሃይማኖት የተጻፈ ገድል የለም፡፡ (የዚህን ዝርዝር የጥናት ውጤት በቅርብ ለኅትመት አበቃዋለሁ፡፡)
  ሌሎች ገድሎች

  ReplyDelete
 21. አበው ይናገሩ


  እስኪ ቀስቅሷቸው አበው ይናገሩ
  የምንኩስና ግብር ምን ነበር ምሥጢሩ
  የክርስትና ሕይወት ምን ነበር ተግባሩ
  መቃብሩን ክፈቱና አበው ይመስክሩ፡፡

  እኔስ ሰው አማረኝ የሃይማኖት ጀግና
  ወልድ ዋሕድ ብሎ በእምነቱ የፀና
  ጀግና ሰው አማረኝ ጠላት አሳፋሪ
  ንጽህት ድንግል ብሎ እምነቱን መስካሪ፡፡

  ነብያት በመጋዝ የተሰነጠቁት
  ሐዋርያት ቁልቁል የተዘቀዘቁት
  ሰማዕታት በእሳት የተለበለቡት
  ቅዱሳን በገዳም ደርቀው የተገኙት
  ምሥጢሩ ምን ነበር? አበው ይናገሩት፡፡

  ይናገር ዝቋላ ግሸን ላሊበላ
  የቅዱሳንን ዐፅም ለምን እንዳልበላ፡፡
  ዋልድባ ይናገር ዜጋመልም ሳይቀር
  እንባቸው መፍሰሱ ለምን እንደነበር፡፡
  ነበር ወይ ፈልገው ሹመት ሽልማት?
  ወይስ ሀብት ንብረት የተሟላ ቤት?
  ወይስ አምሯቸው ነው ፈልገው መሞት?
  እናንተ ገዳማት ምሥጢሩን አውሩት፡፡

  ጐበዝ ሰው አማረኝ በእምነቱ የፀና
  ምግባር ሃይማኖቱ በእጅጉ የቀና፡፡
  እንጦንስ የወለደው በምግባር በእምነት
  ተምሮ ያደገ ከተክለሃይማኖት፡፡
  የጊዮርጊስ ወገን የት ነው የማገኘው?
  በመሀል ከተማ በአራዳ ውስጥ ነው?
  ወይስ በዝቋላ በደብረ ሊባኖስ በደብረ ዳሞ ነው?

  ወገን ሰው ናፈቀኝ ዐይኔን ሰው አማረው
  የሃይማኖት ጀግና የትነው የማገኘው?
  ልግባ ወይ ዋልድባ ጫካ ካለበት
  ማኅበረ ሥላሴ ከቅዱሳን ቤት?
  አክሱም ግሸን ማርያም ከቃል ኪዳን ቦታ
  ይገኛል ወይ ጀግና ጠላት የሚረታ?
  ፈሪሐ እግዚአብሔር በልቡ ያደረ
  ቤተ ክርስቲያንን ያልተደፋፈረ፡፡

  የት ነው የማገኘው ለሃይማኖቱ ሟች
  ለተዋሕዶ እምነት ጠበቃ ተሟጋች፡፡
  የወገን መመኪያ የከሀዲ መቅሰፍት
  ማነው እሱ ጀግና ተኝቶ እንደሆነ ይነሣ ቀስቅሱት፡፡
  እስኪ ቀስቅሷቸው አበው ይናገሩ
  የምንኩስና ግብ ምን ነበር ምሥጢሩ?
  የክርስቲያን ሕይወት ምን ነበር ተግባሩ?
  መቃብሩን ክፈቱት አበው ይመስክሩ፡፡

  ወገን ሰው ናፈቀኝ ዐይኔን ጀግና አማረው
  በእምነቱ የፀና የትነው የማገኘው?
  ብቅ ይበል እንየው እሱ ማነው ጀግና?

  በጐችን ከተኩላ ነቅቶ የሚጠብቅ
  መከራ ቢከበው ከቶ የማይሰቀቅ
  የሃይማኖት ጀግና ቆራጥ ሰው ገበሬ
  እንደዚያ እንደ ጥንቱ ይገኛል ወይ ዛሬ?
  የወገን የዘመድ ጥቅም ያላወረው
  የመናፍቆች እጅ ኪሱን ያልዳበሰው
  የዓለም አሸክላ ልቡን ያልማረከው
  የክርስቶስ ወዳጅ እሱ ጀግና ማነው?
  ምሥጢርን ከምሥጢሩ አንድ አድርጐ ቀምሮ
  ወልድ ዋሕድ ብሎ ሃይማኖት መስክሮ
  እንጦንስን መቃርስን በልቡ ያኖረ
  ከአትናቴዎስ ከቄርሎስ ጥበብ የተማረ፡፡

  ድንግል እመቤቴ ብሎ የሚመሰክር
  መሆኗን የሚያምን ማኅደረ እግዚአብሔር
  ቋቅ እንትፍ ብሎ የጠላ ክህደትን
  ትንታግ ምላስም ጭንግፍግፉን
  ልሳነ ጤዛ መናፍቅን
  ወልደ አርዮስ ዲቃላውን፡፡
  በሰይፈ ሥላሴ የሚቀላ
  ጀግና ማነው ዝቅ ይበላ፡፡

  ነበር ወይ ያን ጊዜ ለሹመት መጓጓት
  እስኪ ጎርጎርዮሰ ይምጣና ጠይቁት
  ፍቅርንም ይጠየቅ አባ ሕርያቆስ
  ምሥጢርን ጠባቂ ወይም አባ መቃርስ፡፡

  የክርስቶስ ባርያ የአጋንንት መቅሰፍት
  ወንጌል አስተማሪ የሃይማኖት አባት
  ይህንን ጉድ እንዲያይ ይምጣ ተክለሃይማኖት
  የጸሎት ገበሬ ገብረ መንፈስ ቅዱስንም ይነሣ ቀስቅሱት
  ይነሣ ጊዮርጊስ ይመስክር ምሥጢር
  የሃይማኖት ፍቅር ምን እንደነበር፡፡

  ከእናቶቻችንም አሉ ለፍጥረት ያዘኑ
  ዲያብሎስ እንዲማር ጌታን የለመኑ፡፡
  ስንቱን ልዘርዝረው የአባቶችን ሙያ
  መር ብለው የወጡት ከሥጋ ገበያ
  ጾም ጸሎት ነበረ የሃይማኖት ጋሻ
  መልከስከስ ምንድነው እንደ አበደ ውሻ፡፡

  እንደ መስኖ ውሃ ከነዱት መነዳት
  ዓላማው ምንድነው የዘመኑ ወጣት፡፡

  እኔስ ሰው አማረኝ የሃይማኖት ጀግና
  ወልድ ዋሕድ ብሎ በእምነቱ የፀና
  ዐይኔን ሰው አማረው ጀግና ሰው ገበሬ
  ሃይማኖት መስካሪ እንደ ጥንቱ ዛሬ፡፡

  MK is Following the footstep of Our Fathers (Abune Teklehaymanot and all Other Church Holy Fathers! Not Poleticians like abune Paulos,aba sereke and other existing dead fathers!!!!!!!!!! they are striving to keeep their Dignity while they are dead All Young Ethiopians are Following MK B/c They love their Religion and You Aba Selam Blog writters all of you are yeTehadiso rizirazoch!!!!!!!!! there for don't try to bias with the photo of Our Fathers and with the name of our true fathere "Aba Selama" please try to confess and Follw Christianity than Following money like aba sereqe aba sereqe his name is also named by the Angels of God! He is a theif he has a building in axum with the name of Dikuman he is a trader of Ethiopianism and Orthodox! Since he is dead any ways it is not necessary to blame the dead person while he is dead. He is the dead not alive!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. you are well enough to understand the truth unless you choose being religious blindly! what you write might be direct those religious people to continue their wrong way. you will be punished with your own wrong way. wake up the truth let you free not talking about thrush stupid histories.

   Delete
 22. በስሙ ሃውልት አሰርቶ ምስሉን በቤተክርስትያናት ሁሉ እንዲሰቀል ያዘዘውን አባ ገብረመድህን (አቡነ ጳውሎስን) ብጹ ወቅዱስ ብለህ ከሸንከው:: KKKKKK በጣም ቅሌታም ሰው ነህ:: ጽሁፍህ ፖለቲካ አዘልና የብሄር ጦርነት ነው መንፈሱ:: ትግሬውን እያሞካሸህ አማራውን ማጥቆር :: የሚያሳዝነው ቅዱስ ወንጌልን እየጠቀስክ የዘረኝነት አመለካከትህን ማራባትህ ነው:: ክፉ የሰይጣን መልእክተኛ ነህ:: እንዴት እዚህ ገጽ እንደደረስኩ አላውቅም ግን እንዳንተም አይነት የረከስ ርካሽ ሰው አለ::

  ReplyDelete