Wednesday, April 4, 2012

ከዋልድባው ጉዳይ በስተ ጀርባ የአቡነ ሳሙኤል እጅ እንዳለ እየተነገረ ነው

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዋልድባ ገዳም አካባቢ መንግስት ሊሰራ ያሰበውን የልማት ስራ መነሻ በማድረግና በሃይማኖታዊ ሽፋንነት በመጠቀም ማህበረ ቅዱሳን በውጪ ካሉ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ጋር እጅና ጓንት ሆኖ እያጋጋለ ካለው የፖለቲካ አጀንዳ ጀርባ አባ ሳሙኤል እንዳሉ እየተነገረ ነው። የቀድሞው የዋልድባ መነኩሴና የዛሬው የልማት ኮምሽን ጳጳስ አባ ሳሙኤል፣ በጉዳዩ ላይ የዋልድባን መነኮሳት በማነሳሳትና ከቪኦኤና ከሌሎችም አካላት ጋር የሚገናኙበትን ሁኔታ በማመቻቸት፣ በሰልፍ መልክ ወደጠቅላይ ቤተክህነት እንዲመጡና ተቃውሟቸውን እንዲያሰሙ በማድረግ፣ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ለጳጳሱ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ሲናገሩ ተሰምተዋል። ይህን እያደረጉ ያሉትም በአቡነ ጳውሎስ ላይ ተቃውሞ እንዲነሳ ለማድረግና ተቃውሞው ተጋግሎ ከቀጠለና እርሳቸውን በአመጽ ከመንበራቸው ማስነሳት ከተቻለ በእርሳቸው እግር እተካለሁ የሚል ቅዠት ስላላቸው ነው ይባላል፡፡ ለዚህ ደግሞ ድጋፍ እየሰጣቸው ያለው ማህበረ ቅዱሳን ነው፡፡
ማህበረ ቅዱሳንንና አባ ሳሙኤልን ያገናኛቸው አጀንዳ ተመሳሳይነት ያለው ሲሆን፣ የቤተመንግስቱንም የቤተክህነቱንም ስልጣን ጠቅልሎ መያዝ እንደሆነ የሚታወቅ ነው። አባ ሳሙኤል ከልባቸው አልወጣ ያለውን ፓትርያርክ የመሆን ቅዠት ለማሳካት እየወደቁ እየተነሱ፣ የተለያዩ ክፍተቶችን እየተጠቀሙ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ላይ መፈንቅለ ፓትርያርክ ለማካሄድ የተለያዩ ጥረቶችን ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡ ከሰሞኑ ደግሞ የዋልድባን ጉዳይ ሽፋን በማድረግ እንደተለመደው አባ ጳውሎስን መታገላቸውን ቀጥለዋል፡፡ ይሁን እንጂ ጉዳዩ ከመንግስት ጋር ሳያጋጫቸው እንደማይቀር የአንዳንዶች ግምት ነው፡፡ 
ማህበሩ በሃይማኖት ሽፋን የሚንቀሳቀስ መሆኑ ከእስከዛሬው እንቅስቃሴው በግልጽ የሚታወቅ ነው። አንጻራዊ ሰላም የሚመስል ሁኔታ በቤተክርስቲያኒቱ ሲፈጠር ትኩረቱ ሁሉ ተሀድሶ መናፍቃን የሚል ስም በሰጣቸው የቤተክርስቲያን ልጆች ላይ ይሆናል። ምክንያቱም ቤተክርስቲያኒቱ በእነርሱ አገልግሎት እየተሸፈነች ከመጣች እኔ ከጨዋታ ውጪ እሆናለሁ ብሎ ስለሚሰጋ ነው፡፡ ለፖለቲካው ምቹ የሆነ ነፋስ ሲነፍስ ደግሞ የሃይማኖት ካባን የደረበ እስከማይመስል ድረስ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት ሆኖ ያርፈዋል፡፡ ሰሞኑን እየሆነ ያለውም ይኸው ነው፡፡ ብላቴ ላይ ለወለዱት ፖለቲከኛ አባቶቹ ባመቻቸው በዚህ ትልቅ አጋጣሚ በመጠቀም፣ በውጪ የተቃውሞ ፖለቲካቸውን ለማራመድ ልዩ ልዩ ስልቶችን እየተጠቀሙ ሲሆን፣ በቅርቡ በዋሽንግተን ዲሲ ባደረጉት የተቃውሞ ሰልፍ ላይ እንኳ በሃይማኖት ሸፍነው ያሰሙት ዋና ድምጽ በሌሎች ሃይማኖት ለበስ መፈክሮች የታጀበ ይሁን እንጂ አሁን ያለው መንግስት እኛን አይወክልምና ይውረድ የሚል እንደነበር ቪኦኤ ላይ ቀርበው ከተናገሩ የሰልፉ አስተባባሪዎች ለመታዘብ ተችሏል። ይህም እነርሱን ያሳሰባቸው የገዳሙ ጉዳይ ሳይሆን ፖለቲካዊ ስልጣኑ ነው የሚል አንድምታን አሳድሯል፡፡ ገዳሙ ሽፋን ሆኖ ነው እያገለገለ ያለው፡፡ የማህበሩ ድረገጾችም ከመቼውም ጊዜ ይልቅ ሃይማኖትን እየቀባቡ ፖለቲካቸውን ማራመዳቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡ እየወጡ ያሉት ጽሁፎች፣ በወጡት ጽሁፎች ላይ እየተሰጡ ያሉ አስተያየቶችም ሁሉ ሃይማኖት ለበስ የፖለቲካ ሀሳቦች ናቸው፡፡ የሁሉም ጥያቄ ግን ማህበሩ ለምን ሚናውን አይለይም? የሚል ነው።

9 comments:

 1. አቡነ ሳሙኤል ችግር ያለባቸው ሰው ቢሆንም በዋልድባ ጉዳይ እጃቸው አለበት የሚለውን ነገር አላምነውም። ምናልባት የእነአባ ጳውሎስ ወገኖች ሰውዬውን ለማስመታትና ብቀላቸው መስመር እንዲይዝላቸው የጎነጎኑት ነገር ይሆናል ብዬ እገምታለሁ። ከዚያ ባሻገር አባ ሳሙኤል ራሳቸው የሽሬ ሰውና የህወሐት አባል ሆነው ህወሐትን ይቃወማሉ ማለት ጅልነት ነው። አባ ጳውሎስን ይቃወማሉ ወይም ማኅበረ ቅዱስና ከኋላቸው አለ ማለት የትግራይን ዓላማ ያደናቅፋሉ የሚለውን ሊጂክ አሳማኝ አያደርገውም። ይህ ጽሁፍም በይሆናል ላይ የተመሰረተ እንጂ አንድም አሳማኝ ማስረጃ የሌለው ተረት ታሪክ ከመሆን አይዘልም። ይልቅስ ከዚህ ዙሪያ የማኅበረ ቅዱሳን እጅ እንዳለበት ስለምንጠረጥር በዚያ ዙሪያ መረጃ ካለ አድርሱን። ከተረት መሰል ነገር ወጣ በሉ!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ይህ ዘረኛና ጠባብ አመለካከት ነው። ሰው ለአላማው ሲል ከዚህ የበለጠም ያደርጋል። ስለዚህ ከዘረኛነት አስተሳሰብ መውጣት አንዱ የክርስቲያን ጠባይ ነውና ከዘረኛ አስተሳሰብ መውጣት ያስፈልጋል። አቡነ ሳሙኤል ለአላማቸው የማያደርጉት ነገር የለም።

   Delete
 2. በተገኘው አጋጣሚ ማኅበረ ቅዱሳንና የምትጠሉትን ከሌላ ጋ ወስዳችሁ ማላተም ለምንድነው የምትፈልጉት? የናንተ ሃሳብ በገዳማቱ ቃጠሎ ዙሪያ እና በዋልድባ አካባቢ ልማት ምንድነው? እርግጥ ከአሁን በፊት ምንኩስናን እንደማትደግፉ ጽፋችኋል እና በአንድም በሌላም የገዳማቱ መጥፋት ጥሩ ነው የምትሉት ማለት ነው? እስኪ ማሳበቁን ተውትና ሃሳባችሁን እንስማው::

  ReplyDelete
 3. mk setenesese bepoletika newe dike dike yalewe pepoletika new. ahunew yemiyaramediw poletika new. yidefachew abo
  ke harer

  ReplyDelete
 4. በመጀመሪያ የምትናገሩትን አስተውላችሁ ብትመለከቱት አቡነ ሳሙኤል እንዲህ እያደረጉ ነው ብላችሁ አትጽፉም ነበር ፡ ምክንያቱም አቡነ ሳሙኤል በፓትርያርኩ ላይ ያደረጉትን ከባድ ተቃውሞ ሌላ ከአማራ ወገን የሆነ ጳጳስ ቢያደርገው ኖሮ እስከ አሁን በህይወት እንደ ማይገኝ የተረጋገጠ ነው ፡፡ስለዚህ አቡነ ሳሙኤል ዋና የመንግሥት አካል መሆናቸው ጥርጥር የለውም "ጠባቂ ያላት በግ ላቷ ከውጭ ያድራል"ይላል አማራ ሲተርት ለዚህ ነው በሰላም የሚኖሩት እንጅ ፓትርያርኩ እስከ አሁን እነያሬድን መላክ አቅቷቸው አይደለም ወደዋቸውም አይደለም ጠባቂ አላቸው ፡ስለዚህ አቡነ ሳሙኤል ከመንግሥት ጋር የተቃረነ ሐሳብ የላቸውም ብየ አምናለሁ፡

  ReplyDelete
 5. Kalubetim Eseyew. Mechem ayadergutim enji biyaderigutima beman edilachil ande papas agegnen malet neber gin negeru wushet silehone enazinalen. Enante gin yemayihon wore atawuru. "Ahiya Lahiya Biraget Tiris ayisebirim" endetebalew YeAbune Paulosina YeAba Samuel erese beris regica endihu new GHuletum ande alama yalachew silehonu. silezih egnan atatalu. bekachihu.

  ReplyDelete
 6. ይድረስ ለሁሉም!!!

  ለእውነተኛ የምድራችን/የሕዝባችን ለውጥ (ፓለቲካዊም ይሁን ሃይማኖታዊ)የሚደረገውን እንቅስቃሴ መደገፉ ለችግራችን መፍትሄ የሚሆን ይመስለኛል:: ነገር ግን የማህበረ ቅዱሳንም ሆነ የተሃድሶ እንቅስቃሴ ለዚች ታሪኳ ለተበላሸባት ቤተክርስቲያን ይበጃል ወይ? የእነዚህ ማህበራት መሰረታዊ ዋና ዓላማ ምንድነው? ነው ቁም ነገሩ:: እውነተኛው ማነው? የሚለው ጥያቄ ነው በመጀመሪያ መመለስ ያለበት:: እውነተኛ የሕዝብ ልጅ የሚያደርገው ሁሉ ለአገርና ለሕዝብ ጥቅም ስለሚሆን ፓለቲካም በሉት ሃይማኖት የተመሰረተበት እውነት ስለሚመራው ችግር ባለበት ቦታ ሁሉ ቢሰለፍም ያው ለተነሳበት እውነት ስለሆነ ያስኬደዋል ባይ ነኝ:: በእርግጥ አንዳንድ የክርስትና ሁለንተናዊነት ያልገባቸው ሰዎች ፓለቲካው አያገባንም እንደሚሉ እገነዘባለሁ:: ይህን ባዮችን ግን ፈጽሞ የሚቀበልበት አእምሮ የለኝም:: የቄሳርን ለቄሳር የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር በሚለው ቃል መሰረት አንድ መንግሥት ሲያጠፋ የማይገስጽ የሃይማኖት አስተማሪ እንዲኖር ቃሉ አይደግፈንም:: አጥብቄ የማምንበትና ቤተ ክርስቲያናችን ጎደላት የምለው እነዚህን የመሰሉ ለእውነት የቆሙና ሕዝቡን በወንጌልና በወንጌል ብቻ እያስታጠቁ የስልጣን ባለቤት መሆኑን አውቆ መልካም አስተዳደር ሲያጣ የሚቆጣና የወከለውን መሪ በተገቢው መልክ የሚያስተካክል/የሚያወርድ ሕዝብ የሚያፈሩ የእምነት አርበኞች ነው ያጣነው::

  ስለዚህ ማቅ መንግሥት ያስተዳደር ስህተት አለበት ብሎ እስካመነ ድረስ(እኔም በዘር ላይ ያተኮረን አመራር አልቀበልም--ምሳሌ ሰሞኑን ከደቡብ ኢትዮጵያ የተባረረው ያማራ ሕዝብ) መቃወም ይችላል:: ዋናው ቁም ነገር የዚህ ማህበር ዋና ዓላማ በእውነት ምንድነው? አዎ የፓለቲከኞቻችን ታሪክ የሚፈልጉት ደረጃ ላይ ለመድረስና ዋና ዓላማቸውን ለማሳካት ሲሉ የማያነሱት የማያደርጉና ለጊዜውም ቢሆን ከማይግባባቸው ጋር ሁሉ ሲዋዋሉ አይተናል እያየንም ነው:: በዚህ መሰረት ማቅ ሰልፍ ወጥቶ መንግሥት ይውረድ የሚለው ሳይሆን ይዞት የተነሳው ድብቅ ዓላማው(አሁን ግን እየተገለጠ ነው)እውነትነት አለው ወይ???? ይህ ነው መፈተሽ ያለበት::

  ከዚህ በተረፈ ጠላትንም ቢሆን በተገቢው መልክና በዋና ማንነቱና ጥፋቱ ላይ ተመሥርተን መቃወም እንጂ አንዳንድ ተሳስቶም ቢሆን በሚያደርጋቸው መልካም በሚመስሉ ነገሮች ላይ ሁሉ ማውገዝ የሚኖርብን አይመስለኝምና ብናስተውል???

  ሰላም ሁኑልኝ

  ሰላም ነኝ

  ReplyDelete
 7. Weriegna dihregetsi newu. Werie yemizegib hayimanotin yastakeke ye weyane seleda!

  ReplyDelete
 8. Weyane made freedom and democracy. What about you?

  ReplyDelete