Friday, April 6, 2012

በዋልድባው ጉዳይ ዋሽግተን ዲሲ ሰልፍ የወጡት ፖለቲከኞች መሆናቸውን የማህበረ ቅዱሳን ድረገጾች አመኑ - - - Read PDF

በዋልድባ ገዳም አካባቢ መንግስት የጀመረውን የልማት ስራ ለፖለቲካ ፍጆታ ለማዋል በሰሜን አሜሪካ በማህበረ ቅዱሳን የፖለቲካ አባቶች ወይም ስውር አመራሮች ተቀነባብሮ በማህበሩ መንደር ሲወራ፣ በማህበሩ ድረገጾችም አለቅጥ ሲናፈስና በቪኦኤም ሲራገብ በሰነበተው ሰሞነኛ የፖለቲካ ግርግር ውስጥ ፖለቲከኞች መኖራቸውን “የተዋህዶ ቤተ ሰብ ከመላው አለም” የተሰኘው http://yetbet.blogspot.com/2012/04/blog-post_5172.html  የማህበሩ ብሎግ አመነ። “የእኛ ድረገጾች” እያለ በዋናነት የማህበሩን ሀመርና የማህበሩን ይፋዊ ድረገጽ ከፊት ያሳለፈውና፣ ዜናውን በአሁኑ ወቅት የማህበሩ ዋና የወሬ መናገሻ የሆነው “አንድአድርገን” የወሬ ብሎግም አስተጋብቶታል። አባ ሰላማ የጡመራ መድረክ ከመነሻው ጀምሮ ከዚህ ጉዳይ በስተጀርባ የማህበረ ቅዱሳን አባቶች የሆኑ ፖለቲከኞች መኖራቸውንና አጀንዳቸውም ፖለቲካ እንጂ ሃይማኖት አለመሆኑን ሲዘግብ መቆየቱ ይታወሳል።
ይሁን እንጂ የማህበሩ ብሎጎች ጉዳዩን ሃይማኖታዊ ካባ አልብሰው አባሰላማ ብሎግን ሲዘልፉ መሰንበታቸውን በአንዳንዶቹ ብሎጎች ላይ ከወጡ ጽሁፎች ለመረዳት ችለናል። የማታ ማታ ግን ከእውነታው መሸሽ እንደማያዋጣ አስበው ሳይሆን፣ መንፈስ ቅዱስ ፊታቸውን ጸፍቶ አፋቸውን ከፍቶ ሳይወዱ በግድ በሰልፉ ውስጥ ፖለቲከኞች መኖራቸውን እንዲያምኑና እንዲመሰክሩ አድርጓቸዋል።
ይህ አስደናቂ ምስክርነት ከላይ ስሙ በተጠቀሰው ብሎግ ላይ ይፋ የሆነው፣ "ሰላማዊ ሰልፉ ላይ የተሳተፉት በሙሉ፥ ቤተክርስቲያንን የማይወክሉ ፖለቲከኞች ናቸው" [አሉ] አቡነ ፋኑኤል” በሚልና “ጆሮ አይሰማው ጉድ የለም!በሚል ርእስ በወጣው ማስተባበያ መሰል ጽሁፍ ውስጥ ነው።
ብሎጉ እንዳተተው እርሱና መሰሎቹ የማህበሩ ብሎጎች ሲያናፍሱት የሰነበቱት የበሬ ወለደ ወሬያቸው እንዳልያዘላቸውና በአገር ውስጥ ያለው እውነታና እነርሱ ለፖለቲካ ፍጆታቸው እያጋነኑ በየድረገጹና በውጪው ዓለም ያወሩት ወሬ ከተራ የመንደር ወሬነት እንዳላላፈ በተዘዋዋሪ በመጠቆም  “የኢትዮጵያ  ዜና  ዘገባ እና በሌላው ዓለም  የሚዘገበው  ዘገባ በጣም የተለያየ መሆኑ ብዙዎችን ዜጎች ይልቁንም ኦርቶዶክሳውያኑን ግራ ሳያጋባ የቀረ አይመስለንም። ሲል ተስፋ በቆረጠ ሁኔታ ጉዳዩን ገልጾአል።
እንዲህ ተስፋ በቆረጠ መንፈስና “አዳልጦት” ሊባል በሚችል ሁኔታ እውነቱን የመሰከረው ብሎጉ በቅርቡ በዋሽንግተን ዲሲ ቁጥራቸው 1200 የሚጠጉ ፖለቲከኞችና ጉዳዩ የሃይማኖት መስሏቸው የፖለቲከኞቹ መናጆ የሆኑ አንዳንድ ምእመናን የተሳተፉበትን ሰልፍ በተመለከተ፣ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል “ሰላማዊ ሰልፉ ላይ የተሳተፉት በሙሉ፥ ቤተክርስቲያንን የማይወክሉ ፖለቲከኞች ናቸው” አሉ መባላቸው ነው። ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊት ለፊት  ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ ሰልፍ የወጡት የቤተ ክርስቲያን ሰዎች ናቸው በማለት ለመከራከር የሞከረው ብሎጉ፣ የሰልፉ አላማ ግን ፖለቲካዊ መሆኑን በአነጋገሩ ግልጽ አድርጓል። በሃገራችን ኢትዮጵያ  ያለው  ቤተክህነት  ምንም ተስፋ የሚጣልበት እንዳልሆነ በዘገባቸው ተረድተናል፤ በስደት  የሚኖሩ  ኢትዮጵያውያን  ካህናት  አባቶች  በተለይ ህይወታቸውን በምንኵስና  የሚኖሩ  የዋልድባን  ጉዳይ  ከማናቸውም  የህብረተሰቡ  ክፍል በተለየ ይቆረቆሩለታል የሚል በተለያዩ የህብረተቡ  ክፍሎች  ታስቦ  ነበር፥  ነገር  ግን   ሊሆን ያልቻለበት  ምክንያት  ለሁላችንም  እንቆቅልሽ  ሆኖ ሰንብቷል።  ለሁሉ  በላይ  ግን  ትልቅ  የህዝብ ተቃውሞ  ያስነሳል  ብለን  የገመትነውን  ለማጣራት  በተለያዩ  መንገዶች ሞክረን፣  ሁሉም  መንገዶች ተመሳሳይ  ናቸው፥” ሲልም ለማህበሩ ፖለቲካዊ ትግል ከቤተክህነት በኩል ድጋፍ እንደተነፈገው፣ ነገሩ ሁሉ ተስፋ አስቆራጭ እንደሆነበትና ያሰበው “ትልቅ የህዝብ ተቃውሞ ይነሳል” የሚለው ቅዠቱ እንዳልተሳካለት እግረ መንገዱን መስክሯል። 
ብሎጉና መሰሎቹ በድረገጾችና እንደቪኦኤ ባሉ አንዳንድ ሚዲያዎች ያራገቡትን “ትልቅ  የህዝብ ተቃውሞ  ያስነሳል  ብለን የገመትነውን” ያሉትን ፕሮፓጋንዳቸውን በዋሽንግተን ዲሲ ከ1200 የዘለለ ሰው እንዳላጀበው ራሱ በራሱ ያረጋገጠ ሲሆን፣ በኢትዮጵያም በማህበሩ ሰፈር ካልሆነ በቀር ኦርቶዶክሳውያን ከቁብም እንዳልቆጠሩት ከሚታየው እውነታ መረዳት ይቻላል። ይሁን እንጂ ከአገሩ ርቆ ያለውንና በውጪ የሚኖረውንና ለጊዜውም የተቀበላቸው የመሰላቸውን ኢትዮጵያዊ በተሳሳተ መንገድ እየቀሰቀሱ የጀመሩት የፖለቲካ ስራ እስኪነቃባቸው ድረስ ሊቀጥል እንደሚችል ተገምቷል።
ብሎጉ በዚህ ዘገባው በዋናነት የስም ማጥፋት ዘመቻ የከፈተው በብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ላይ ሲሆን፣ በዚያ ያለውንና በቤተክርስቲያን ስም የሚካሄደውን የማህበሩን የፖለቲካና የንግድ እንቅስቃሴ በቅርበት እየተከታተሉና አንዳንድ የእርምት እርምጃዎችን እየወሰዱ መሆናቸው፣ ይልቁንም ሰሞኑን የዶ/ር መስፍንን ቅስና መግፈፋቸው ተስፋ ስላስቆረጠውና ስላናደደው መሆኑን ከወጣው ዘገባ ለመረዳት ተችሏል። ብፁዕነታቸው በዋሽንግተን  ዲሲ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጻፉት ባለው ደብዳቤ ላይ፣ በኢትዮጵያ  ኤምባሲ በር ላይ ለሰልፍ የወጣው ወገን ፖለቲካዊ እንጂ ሃይማኖታዊ አለመሆኑን መናገራቸው ትክክለኛ ምስክርነት እንጂ ሀሰት አለመሆኑን ከማንም የተሰወረ አይደለም። ከብሎጉም ጭምር። ለዚህ ነው ሳይገረፍ እንዲህ ሲል የለፈለፈው “በዚያ  ቀን  ዋሽንግተን  ዲሲ  ላይ  የተደረገው ሰላማዊ  ሰልፍ  እርግጥ  ነው  ጥቂት  የፖለቲካ  ሰዎች  ነበሩበት  ብንልም፣  ፖለቲከኞችም  እኮ  ቢሆኑ  ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን  መዘንጋት  የለብንም”። ታዲያ ብፁዕነታቸው ምን ተሳሳቱ? ብሎጉ ቁጥራቸውን አሳንሶ ማቅረቡ የሚጠበቅ ነገር ነው። ከዚያ ውጪ ሰልፉ በሃይማኖት ሽፋን የቀረበ የፖለቲካ ሰልፍ ነበረ ብሎ መደምደም ይቻላል።
የዚህን ብሎግ ዘገባ አስገራሚ የሚያደርገው ማህበሩ ያስነሳውን ፖለቲካዊ አቧራ ይበልጥ በግልጽ ለማቡነኑ መሞከሩ ነው። ለምሳሌ እንዲህ ብሏል፤  “እውን  አቡነ  ፋኑኤል  ሕዝብን  ለመንፈሳዊ አባትነት  ሊመሩ  ነው የመጡት ወይስ  የመንግስትን  አጀንዳዎች ሊያስፈጽሙ  ነው  የመጡት?” በመሰረቱ አቡነ ፋኑኤል የተሾሙት የመንግስትንም ሆነ የተቃዋሚዎችን አጀንዳ ለማስፈጸም አለመሆኑ ይታወቃል። በብሎጉ እምነት መሰረት ግን ጳጳሱ የመንግስት አጀንዳ አስፈጻሚ ተደርገዋል። ይህ ስም የተሰጣቸው በተቃውሞው ሰልፍ ላይ ስላልተገኙ ነው። ቢገኙ ኖሮ ግን ተቃዋሚ ፖለቲከኛ ሳይሆን ለቤተክርስቲያን አሳቢና ተቆርቋሪ ነበር የሚላቸው። ስለዚህ እርሳቸውን የተቃወመበት ዋና ምክንያት ከመንግስት ደጋፊነት ወደተቃዋሚ ጎራ ለምን አይገቡም የሚል ነው የሚመስለው። ይህ ግን ትክክል አይደለም። ብፁዕነታቸው ያሉት ሰልፉ የፖለቲከኞች እንጂ ቤተክርስቲያንን የሚወክል አይደለም ነው። ይህ በራሱ እንዴት የመንግስት ደጋፊ ሊያሰኛቸው ቻለ? ቢባል፣ ሰልፉ የተቃዋሚዎች ስለሆነ የሚል አንድምታ ይኖረዋል።
ቤተክርስቲያን የአማኞች ማህበር እንጂ የፖለቲካ ፓርቲዎች (የመንግስትም ሆነ የተቃዋሚዎች) መራኮቻ ልትሆን አይገባም። ብሎጉ ግን ቤተክርሰቲያን መንገድ የተቃዋሚ ፖለቲካ አቋም ማራመጃ መሆን አለባት እያለ ነው። የማህበረ ቅዱሳን ስውር አመራር ሙሉ ጊዜውን ለፖለቲካ ሰጥቶ እያለ በሃይማኖት ሽፋን ከሚያጭበረብር፣ ራሱን ግልጽ አድርጎ ለፖለቲካዊ አላማው ቢታገል የተሻለ ነው። ከዚህ በኋላ በዚህ መንገድ መጓዙ ብዙም ትርፍ የሚያስገኝለት አይሆንም።
ዋልድባን ጨምሮ በኢትዮጵያ የሚገኙ ገዳማትና አድባራት የቤተ ክርስቲያናችንን ብሎም የአገራችንን ታሪክና ቅርስ ይዘው የሚገኙ መካናት በመሆናቸው ሊጠበቁ እንደሚገባ አባ ሰላማ የጡመራ መድረክ ታምናለች። ሰለዚህ ሁሉም አካላት ቤተክህነትም ሆነ መንግስት ለገዳማትና አድባራት ተገቢውን ጥበቃ ሊያደርጉላቸው እንደሚገባ እያስገነዘበች ማህበረ ቅዱሳንም በገዳማት ስም ልዩ ልዩ ድብቅ አጀንዳዎቹን ማራመዱን ሊያቆም ይገባል ትላለች።

13 comments:

 1. ABET WUSHET!WUSHET!WUSHET! PLEASE, GO AND READ THE ARTICLE AGAIN.

  ReplyDelete
  Replies
  1. chefen calhonke beker weset atleme

   Delete
 2. you said woshet, but I gues u have a problem to read and understand please go to school before accused such kind of intersting article.

  ReplyDelete
 3. ufffffffffff lier

  ReplyDelete
 4. አላማችሁ ምንድነው? በቅዱስ አባታችን ስም ስለምን ምንፍቅና ትሰብካላችሁ? በየ አርዕስታችሁ ማህበሩ ማህበሩ ትላላችሁ ማህበረ ቅዱሳን ምን ያድርጋችሁ? ለምን ለቤተክርስቲያን ጥቅም ቆመ ብላችሁ ነው? እርግጥ ያጣ ሌባ ተሳድቦ ከመሄድ ውጭ ምን አማራጭ አለው?!! አላዘርፍ አላስመነፍቅ አላሏችሁ:: ሴራችሁን እያጋለጡ መደበቅያ መድረሻ አሳጧችሁ:: በየ አውደምህረቱ እናንተ ያሰማራችኋቸው ዘፋኞችና ዳንሰኞች እንዳይጨፍሩ በአምላክ ቸርነት በማህበሩና በሰንበት ትምህርት ቤቶች ጥረት ተወገዱባችሁ፡፡ አንዳድርገን ብሎግ ላይ የተጻፈው እውነት ነው ፖለቲከኛ ሃይማኖት የለውም እንዴ? ፖለቲከኛ ሃገር የለውም እንዴ? እናንተ ደስ ሲላችሁ ማህበሩን የገዥው ፓርቲ መሳርያ ነው ስትሉ አልነበር ወይ? እባካችሁ እናንተ ሰዎች ለቤተክርስቲያን ቅንቅን ከመሆን እንደ ማህበሩ እውነቷን እያጎላችሁ ስርኣቷን እያስተማራችሁ እየተማራችሁ ጥንተ መሰረቷ እንዳይናጋ አድርጉ፡፡ እንጂማ የማይገናኝና የማይገጣጠም ጥቅስ እየጻፋችሁ ጥንተ አብሶ ብትሉ ተክልዬ እንዲህ ናቸው ብትሉ እውነተኞች የተዋህዶ ልጆችን የምታናውፁ አይምሰላችህ የሲዖል ደጆች አይችሏትም፡፡

  ReplyDelete
 5. Ye mk wesht yetawek new. Wesht yalut le abaselama blog kehon le baheryu aysmamawem sorry.

  ReplyDelete
 6. Before starting to write a critic, try to learn the language (Amharic) so that you can critisize the article written by other authors. I think you have problem of understang Amharic. you didn't understan the core point of the article posted on the website you mentioned. This is a good indication that you are 'yemierabawiyan buchiloch' and most likely you are not Ethiopians as most ethiopians well understand Amharic. In short, you are advised to learn Ethiopian language before trying to critisize an article written in Ethiopian language.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Thank you man!

   Delete
  2. eshi leke lekawente yemetelew attehe sile amerega kuwankuwa mastemar gemerke. maferiya

   Delete
 7. Do you think other people cannot read?????

  ReplyDelete
 8. wuahet tiru aydelem. If you have difficulty understanding, you can keep quite. why do you bother people by twisting things. Do you think you are pleasing God by doing so?
  O God please give us your peace!

  ReplyDelete
 9. min alebet knoch bthonu ena melkam zega bitaferu?

  ReplyDelete
 10. አባ ፍሬምናጦስ (የመጀመሪያው ጵጵስናን ተቀብሎ ወንጌልን የሰበከ አባት)
  አባ ቴዎፍሎስ (መስዋዕትነትን የተቀበሉ አባት)
  አባ ጎርጎሪዎስ (ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ብዙ ሥራዎችን የሰሩ፣ ካህናት ማሰልጠኛ የመሰረቱ . . .)
  አባ መርኅ ክርስቶስ (ጥርጥርን ለመጀመሪያ ያመጡ አባት፣ የጌታን አምላክነት፣ የእመቤታችንን አማላጅነት ጥርጣሬ ያመጡ፣ ከመንፈሳዊ ኮሌጅ የሚወጡትን ደቀ መዛሙርት በሙሉ የዘመኑን ተሃድሶአውያን የወለዱ አባት)
  አብ መልከፄዲቅ (በሰሜን አሜሪካ በተለይ ቀኖናን በመቀየር የታወቁ አባት፣ ቅዳሴው ረዘመ፣ ታአምረ ማርያም ምን ያረጋል፣ ገድላት አያስፈልጉንም፣ ዝማሬ በኦርጋን፣ ሴቶች ከነ ወር አባባቸው ወደ መቅደስ ቢገቡ ችግር የለውም የሚሉ የዘመኑ champion)

  እነዚህን አባቶች ምን አንድ አደረጋቸው? በስማቸው እየነገዳችሁ ነው እንዴ? ለስም አጠራራቸውም በእናንተ ስም መነሳታቸው ለእነሱ ክብር መጉደፍ ስለሚሆን ቢቻላችሁ የመጀመሪያዎቹን ሦስቱን ብትቀይሯቸው ምን ይመስላችኃል እነ ፖስተር ቶሎሳን፣ እነ ፖስተር መለሰ ወጉን ወይም ደግሞ በቅርቡ ፖስተርነትን ለመቀበል እየተዘጋጀ ያለውን የወደፊት ፖስተር በጋሻው ወይም ፖስተር ሊሆን የተዘጋጀውን ትዝታውን ማውጣት ብትችሉ የበለጠ ሊገልጿችሁ ይችላሉ ብዬ አምናለሁ።
  ልቦና ይስጣችሁ እላለሁ

  ReplyDelete