Thursday, April 26, 2012

ኤፍሬም እሸቴ: ብትስማማ ነው እንጂ የሚያስደምመው ባለመስማማትህ ምን ይደንቃል?

በዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤልRead in PDF
ጥብቅ ማሳሰቢያ፦ ጽሑፉ የኢትዮጵያን ጠቅላይ ሚኒስትር በመደገፍ የተጻፈ ጽሑፍ አይደለም:: ጽሑፉ ኤፍሬም እሽቴ የተባለው አንድ "የማህበረ ቅዱሳን" የስራ አመራር አባል ግለሰብ “ጠ/ሚኒስትሩ ስለ ማኅበረ ቅዱሳን በተናገሩት አልስማማም” ሲል ከግንዛቤ እጥረት የተነሳ በጻፈው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን አስተምህሮ የማይወክል ዝርው ይዘት ያለው ጥሬ ጽሑፍ አስቸኳይ እርምት እንዲደረግበትና በክርስትና ስም በአንባቢያን ላይ የፈጠረውን ብዥታ ግምት ውስጥ በማስገባት የተጣራ ምስል ለመስጠት ኩልል ቅልብጭ ባለ መልኩ የተዘጀ ጽሑፍ ነው::
"ማህበረ ቅዱሳን" የቤተ-ክርስቲያን የቆሎ ት/ቤት ያልቀመሰ፣ የዜማ፣ የቅኔ፣ የመጽህፍት ትርጓሜያት፣ የቅዳሴ፣ የአቡሻክር … ወዘተ ባህር ያልዳሰሰ የቤተ-ክርስቲያን ጥንተ ታሪክ ያልመረመረ፣ ጥምጥም ያለው ጥቁር ጎማሳ፣ ሆኖ እያለ እምነበሃን የማያውቅ ዲያቆን፣ አሀዱ አብን የማያውቅ ቄስ፣ አአትብ ገጽየን የማያውቅ ክርስቲያን፣ የሴቶችና የወንዶችን መግቢያ በር በቅጡ የማያውቅ፣ ሱቅ ከፍቶ ቄስ ቀጥሮና አቁሞ ስለ ነገደ ቄስ የሆነ የሚመስለው ጠባቂ ነኝ የሚል አጽራረ ቤተ-ክርስቲያን ጿሚ መሳይ አጋሰስ፣ የማይሰግድ አሰጋጅ፣ ለማስተማር የማይበቃ አቃቤ መቃብር ባለ ዲግሪ፣ አስራት የማይከፍል በዝባዥና አስከፋይ፣ የማይቀድስ አስቀዳሽ፣ ያልተለወጠ ለዋጭ አስመሳይ የጎበዝ ጥርቅም ማኅበር ነው ሲባልኮ ተራ ውንጀላ ወይንም ደግሞ ክስ ሳይሆን ምስክርነታችን ጭብጥ ላይ የተመሰረተ እውነት ነው::

ይህች ጦማር የቀድሞ የማህበሩ አውራ ቄስ ኤፍሬም እሸቴ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በዕለተ ማክሰኞ ሚያዚያ 9/2004 ዓ.ም በፓርላማቸው ተገኝተው ያደረጉትን ንግግር ተከክትሎ “ጠቅላይ ሚኒስትሩ እግረ መንገዳቸውን ያነሱትን እና በኢትዮጵያ ውስጥ አለውን አክራሪነትበክርስቲያኑ በኩል ይወክልልናልብለው የጠቀሱትን ማኅበረ ቅዱሳንን በተመለከተ እኔም እንደ አንድ አባል የማምንበት አቀርባለኹ። ማኅበሩ በኃላፊዎቹ በኩል የሚሰጠው መልስ እንደተጠበቀ ሆኖ ለሁለት አሥር ዓመታት አባል የሆንኩበት እና መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ አገልግሎቶችን በመስጠት በሁሉም ዘንድ የተመሰከረለት ማኅበር አክራሪአለመሆኑን በግሌ ለመመስከር እገደዳለኹ።” ሲል ባልዋለበትና ባላለፈበት የቅድሳት መጻህፍት ቃል ዓውዱን ባላገናዘበ አኳኃን ምክርን ለማጨለም ባደረገው ሙከራ የተፋለሰውን የክርስትና አስተምሮና በማን አለብኝነት መንፈስ የፈጠረውን እጅግ ግዙፍ የሆነ ስህተት ኩልል ባለ መልኩ ታስቃኛናለች:: መልካም ንባብ!

ግለሰቡ ምንም እንኳን ራሱን እንደ አንድ ተራ የማህበሩ አባል አድርጎ ለመቅረብ ቢሞክርም ለረጅም ዓመታት በማህበሩ የስራ አመራር አባል: በማህበሩ የተለያዩ የሃላፊነት ቦታችም ሲሰራ የቆየ: አሁንም ቢሆን ከቤተ-ክርስቲያን ጫንቃ ያልወረደ: በቤተ-ክርስቲያን የምጽዋት ገንዘብ ኑሮውን ያደላደለ በዋናነት ከተጣያቂነት የማያመልጡ የማህበሩ ልሂቃን መካከል ለመሆኑ የማህበሩ ስም በተነሳ ቁጥር ይህን እውነታ ሳያውቅ የሚቀር ያለ አይመስለኝም:: ግለሰቡ ወደ አሜሪካ እንዴት መጣ አሁንስ የማህበሩን ተልዕኮ ከማከናወን አንጻር ምን እየሰራ ይገኛል የሚሉትና ሌሎች ተጓዳኝ ጥያቄዎች በቅርብ በስፋት የምንመለከተው ይሆናል:: ለጊዜው ግን የተነሳንበትን ዋና ርእስ እንጠበጥባለን::

“በመጀመሪያ “አንድ ሃይማኖት” የሚለው መሠረታዊ ሐሳብ ለብዙ ውይይቶች በር የሚከፍት ትልቅ ጉዳይ ነው። ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚያስተምረን እና የጥምቀት አክባሪ ክርስቲያኖች በቲ-ሸርቶቻቸው ላይ አትመውት በፎቶግራፍ የተመለከትኩት ኃይለ ቃል ቅዱስ ጳውሎስ በኤፌሶን መልእክቱ ምዕራፍ 4 ቁጥር 5 ላይ የጻፈው “አንድ ጌታ፣ አንድ ሃይማኖት፣ አንዲት ጥምቀት” የሚለው ሐዋርያዊ ቃል ነው። ይህ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል እንጂ የጥምቀት አክባሪዎቹ የፈለሰፉት አይደለም። የትኛውም ክርስቲያን “አንድ ሃይማኖት” ቢል የሐዋርያውን ቃል መጥቀሱ እንጂ ሌላ እምነት ላላቸው ኢትዮጵያውያን ጥላቻ አለው ማለት አይደለም። የጥምቀት አክባሪ ወጣቶች ቲ-ሸርቶች ላይ የተጻፈውን የሐዋርያውን ቃል የምረዳው በዚህ መንፈስ ነው።” (ውድ አንባቢ: የዚህ ጽሐፍ ዋና ዓላማ የኤፌሶን መልዕክት መንፈሱን በሚገባ መተንተን: መመስከር ነው)::

ይህ ሰው ሌላው ቢቀር የተጠቀሰውን ቃል ፊደላትን ከማንበብና ከማነብነብ ባልዘለለ መልእክቱን በሚገባ ለመረዳቱና አለማወቁ ብቻ ሳይሆን የፈጠረውን ስህተትና ያፋለሰውን አስተምህሮ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን ሊቃውንት ጨምሮ አባባሉን ሌሎች እንደሚጋሩት ሃፍረት ሳይሰማው እንዲህ ሲል መግለጽ ነው “በዚህ የሐዋርያው ቃል ውስጥ ያለው “አንድ ሃይማኖት” የሚለው አገላለጽ የሚናገረው ስለ ክርስትና ሃይማኖት ነው። ሌሎች እምነቶች የሉም፣ መኖርም የለባቸው የሚል የጨፍላቂነት ትምህርት አለመሆኑን ሊቃውንቱ አምልተው አስፍተው ሲያስተምሩ ኖረዋል፤ እያስተማሩም ነው። አሁን ደርሶ የሚለወጥ ነገር የለም።” እዚህ ላይ ሊቃውንት የሚላቸው በሰው እአምሮ ንብረት ስርቆት ላይ የተሰማሩ እንደነ ዳንኤል ክብረት የመሳሰሉ በጠራራ ጸሐይ ፎቶግራፍ የሚያነሱ ከሆነ እስማማለሁ::

በዚህ ሳይገታም (ጽሑፉ የሚያጠነጥነው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር እስከ ሆነ ድረስ ጠቅላይ ሚኒስትሩን መጎንተሉ ነው) በትልቁ ከቃሉ ጋር ፈጽመው የማይታወቁ ራሱ አቶ ኤፍሬም ጨምሮ ማህበሩና አባላቱ እያሉ በተጨማሪም አራት ገጽ ያስጻፈበት ምክንያት ፊደል እንደቆጠረ እንደማንኛው ሰው መልእክቱ ሲያነበው (ኤፌ. 4:5 ለማለት ነው) ነገር ቆስቋሽ ሰላም ነሺ የአመጽ ቋንቋ ሆኖም ስለተሰማው ጳውሎስ ወይንም ደግሞ እግዚአብሔርን ለማሳፈር “አንድ ሃይማኖት የሚለው አገላለጽ ከሃይማኖት ጋር በማይተዋወቁ ሰዎች ዓይን ከተመለከትነው መቻቻልን ለማስተናገድ ፈቃደኝነት የጎደለው አገላለጽ ሊመስል ይችላል።” በማለት አጉል ጥብቅና በመቆም ለመገንባትና ለማጣጣም በሚያደርገውና ባደረገው ሙከራ ቃሉን ማፋለሱ ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔርን ማሰደቡ ስመለከት አገላለጹ በቀላሉ የአብዬን ለምዬ አስብሎኛል:: ውድ አንባቢ: እንግዲህ እስከ አሁን ድረስ ያለነው መግቢያ ላይ ለመሆናችን ለመግለጽ እወዳለሁ ወደ ሚቀጥለው የጽሑፉ ዋና ክፍልና ዓላማ ስንሸጋገርም ብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ እንዳስተማረው እንዲሁ ህይወት የሆነውንና ህይወትን የሚሰጥ የመልእክቱ መንፈስ እናገኘው ዘንድ በታላቅ እርጋታና ማስተዋል ጽሑፉን እናነበው ዘንድ በድጋሜ በወንድማዊ መንፈስ በትህትና እጠይቃለሁ::

“እንግዲህ በጌታ እስር የሆንሁ እኔ በተጠራችሁበት መጠራታችሁ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እለምናችኋለሁ፤
በትሕትና ሁሉና በየዋህነት በትዕግሥትም፤ እርስ በርሳችሁ በፍቅር ታገሡ፤ በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ። በመጠራታችሁ በአንድ ተስፋ እንደ ተጠራችሁ አንድ አካልና አንድ መንፈስ አለ፤ አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤ ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ።” ኤፌ. 4: 5

ጳውሎስ እንዲህ ያለ መንፈስ ያለው የአማኞች ህብረትንና አንድነትን የሚያጠነክር መልእክት ሲጽፍ ለመጀመሪያ ጊዜው አይደለም:: የአማኞች በቁጥር መበራከትና ከተለያየ ልማድና ወግ መምጣታት ተከትሎ ይፈጥረው የነበረውን ችግር በማስመልከት ጳውሎስ በርካታ ገንቢ መልእክቶችን ጽፏል:: ለምሳሌ የተመለከትን እንደሆነ በኤፌሶን ከተማ ሳለ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች የጻፈውን አንደኛ መልእክቱ ለርእሳችን ተጠቃሽ ማጣቀሻ ነው::

የቆሮንቶስ ቤተ-ክርስቲያን ከተከሰቱ በርካታ ችግሮች መካከል ትልቁና ዋነኛ ችግር በእግዚአብሔር ቃል ካለማደግና
ካለመብሰል ቃሉንም በሚገባ ካለማጥናት የተነሳ "እኔ የጳውሎስ ነኝ" "እኔ የኬፋ ነኝ" እያሉ ለአራት ተከፍለው ጎራ ለይተው እርስ በርሳቸው መቧቀሳቸው ነበር:: ይህንን የሰማ ጳውሎስ "ነገር ግን ወንድሞች ሆይ ሁላችሁ አንድ ንግግር እንድትናገሩ በአንድ ልብና በአንድ ሃሳብም ተባብራችሁ እንድትሆኑ እንጂ መለያየት በመካከላችሁ እንዳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እለምናችሃላሁ:: ወንድሞቼ ሆይ በእናንተ ክርክር እንዳለ ስለ እናንተ የቀሎዔ ቤተ ሰቦች አስታውቀውኛል:: ይህንም እላለሁ እያንዳንዳችሁ እኔ የጳውሎስ ነኝ፥ እኔስ የአጵሎስ ነኝ፥ እኔ ግን የኬፋ ነኝ፥ እኔስ የክርስቶስ ነኝ ትላላችሁ ክርስቶስ ተከፍሎአልን? ጳውሎስስ ስለ እናንተ ተሰቀለን? ወይስ በጳውሎስ ስም ተጠመቃችሁን? …" (1ኛ ቆሮ. 1: 10) እያለ ይቀጥላል::

የቆሮንቶስ ሰዎች በክርስቶስ ስም በቤተ ክርስቲያን ዙሪያ መሰባሰባቸው ሲያበቁ ኑሮአቸው ግን ፈጽሞ የምስራች (ወንጌል) ካልሰሙት አህዛብ በማይተናነስ ድርጊት ተጠምደው ወደ ቀድሞ ኑሮአቸው በመመልስ/ተመልሰው ልምምዳቸውን ሲገፉበት መሆናቸው ሲሰማ የሰማውንም ሁሉ እውነት መሆኑን ሲያረጋግጥ የጻፈው መልእክት የቆሙበትን ስፍራ ለማመላከት ነበር:: ከዚህ የጳውሎስ መልእክት አንድ ትልቅ ቁምነገር ለመረዳት የሚቻለው ሰው ሲባል በእግዚአብሔር መንፈስ ካልተነካ በስተቀር በሃሳብም ሆነ በቃል አንድ ብሎ ነገር ፈጽሞ የማይታሰብ ነው የሚለውን አንድምታ እንደተጠበቀ ሆኖ የእግዚአብሔርን መንፈስ የተቀበሉ: ብዙ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች  የተገለጡባቸው: በአንድ ንግግር በአንድ ልብ በአንድ ሃሳብና ቃል ህብረታቸው ከማንም በላይ ያጠናክሩ ዘንድ የሚጠበቅባቸው የቆሮንቶስ ሰዎች በአንጻራዊ ገጽታ ሆነው ሲያገኛቸው በሌላ አነጋገር የተቀበላችሁት መንፈስ እኮ እንዲህ ለመነታረክ: ለመለያየት: ለመናቆር እርስ በርሳችሁም ለመናካስ ሳይሆን የተቀበላችሁት መንፈስ   የተበተነውን የሚሰበስብ/አንድ  የሚያደርግ: ልዩነትን በወንድማዊ ፍቅርና በመቻቻል የሚያጠብ: በጸብ ፈንታ ሰላምን ፍጹም መዋደድን የሚሰጥ: እግዚአብሔርን የሚያከብርና የሚያነግስ ነው ታድያ ይህ መንፈስ የት ገባ? ምን ዋጠው? ወይስ የተቀበላችሁትን አታውቁምን? ለመሆኑ እንዲህ ያለ ግርግርና ኢ-ክርስቲያናዊ ምግባር ከማን የተማራችሁ ነው? ይህ ሁሉ ወከባ ምን ለመሆን: የትስ ለመድረስ ይሆን? ምክንያታችሁን ማወቅ እፈልጋለሁ:: ሰው ሲያምን ከስጋ ደዌ ከመንፈስ አባዜ ይፈወሳል እንጅ እንዲህ ያለ ነገርስ ትክክል አይደለም:: አይሁድ ብንሆን የግሪክ ሰዎችም ብንሆን ባሪያዎችም ብንሆን ጨዋዎችም ብንሆን እኛ ሁላችን በአንድ መንፈስ አንድ አካል እንድንሆን  ተጠምቀናልና ሁላችንም አንዱን መንፈስ ጠጥተናል (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ 12:13) በማለት ወደ ልቦናቸው ይመለሱ ዘንድ የሚያሳስብ ነው::

አሁን በዚህ መንፈስ ወደ ኤፈሶን መልእክት ተመልሰን እንመጣለን:: የኤፌሶን መልእክት የተጻፈው በተመሳሳይ ጸሐፊ በሐዋሪያው ቅዱስ ጳውሎስ ሲሆን መልእክቱ የተጻፈበት ምክንያትም እንደ እንዳንዶቹ በሚገጥማቸው ችግሮችና መሰናክሎች የተነሳ ሳይሆን በመጽሐፉ ምዕራፍ አንድና ሁለት በተገለጸው መሰረት መልእክቱ የተጻፈበት ምክንያት በኤፌሶን የምትገኘውን ቤተ-ክርስቲያን ምእመናንና አባላት (ሌሎች) በዘመን ፍጻሜ የእግዚአብሔር ዘላለማዊ አሳብ ይረዱና ያውቁ ዘንድ: አማኞች በመንፈስ ቅዱስ ጠንክረው የክርስቶስን ፍቅር ለማስተዋልና ለማወቅ ይበረቱ ዘንድ እንዲሁም በእግዚአብሔር ጸጋ ዕለት ዕለት ወደ ምልዓት ያድጉ ዘንድ የተጻፈ መልእክት ነው::

እንግዲህ ጳውሎስ"አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት” ሲል በጌታ በማያምኑ: ሃይማኖትም በሌላቸው: በልተጠመቁ ወገኖች/አካላት ላይ ጣቱ እየቀሰረ ሳይሆን ያለው "አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት” ማለቱ የኤፌሶን ምእመናን በተጠሩበት መጠራት እንደሚገባ በሚገባ እንዲመላለሱ ቀደም ሲሉ በጌታ አምነው በእውቀት ለተጠመቁ ምእመናን በክርስቶስ የያዛችሁትን መንገዳችሁን አጽንታችሁ ያዙ: በትእግስት በየዋሃትና በፍቅርም እርስ በርሳችሁ ተጠባበቁ: ተዋደዱ ምንም የሚያጨቃጭቃችሁ: የሚያነታርካችሁና እርስ በርሳችሁ የሚያናክሳችሁ ነገር አይኑር የሁላችሁም ጌታ አንድ ጌታ ነው! ሃይማኖታችሁም እውነት መንገድም ህይወትም የሆነ ኢየሱስ አንድ ነው! ሁላችሁም የተጠመቃችሁት ጥምቀት እንዲት ጥምቀት ናት! ይኸውም:

v ግሪኩም አይሁዱም አንድ የሚያደርግ:
v ባሪያው ከጭዋው የሚያስተካክል:
v ሴቱምን ከወንዱ እኩል የሚያደርግ (በእምነት)
v ክርስቶስን የሚያለብስ:
v ከክርስቶስ ጋር ሕብረት በሚፈጥር:
v ለምስክርነት የሚያበቃ ጥምቀት ነውና እንግዲህ ይህን መንፈሳችሁን ጠብቁ! በማለት የኤፌሶን ምእመናን
ü ፍቅር አጥብቀው እንዲይዙ:
ü መቻቻል እንዲለማመዱ:
ü በሕብረት/አንድነት የሚገኘውን በረከት ተካፋዮች እንዲሆኑ :
ü ወንድማማችነት እንዲያጣጥሙ:
ü ስለ ክርስትና ህይወት ትርጉም እንዲያውቁ:
ü በጥምቀት ስለተፈጸሙት ስርዓት እንዲያስቡ:
ü ከሁሉም በላይ ደግሞ በጌታ ስም ማመን ምን ማለት እንደሆነ እንዲያውቁ ጸጥ ረጭ ባለ በዝግታ መንፈስ የሚነበብ/የሚደመጥ: ተነቦም/ተሰምቶ ወደ ልብ ስለሚወርድና በልብም ስለሚጠበቅ ከሃጢአት: ከጥፋት: ከአመጽ ስለ ሚያተርፍ የተበተነውን ስለሚሰበስብ ህያው ቃል ላከላቸው (መከራቸው) እንጂ የኤፌሶን ምእመናን "አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት!" የሚል መፎክር ይዘው በኤፌሶን ጎዳናዎች አቧራ እንዲያስነሱ አይደለም! እዚህ ላይ ልብ ሊባል የሚገባ ነጥብ ቢኖር አቶ ኤፍሬም እንዳሰበውና እንደተረጎመው "ጥምቀት! ጥምቀት!" እየተባለ የሚጮክ ዝሩው ቃል ሳይሆን ጥምቀት ተብሎ የተጠቀሰውን የውሃ ጥምቀት የሚያመላክት ለመሆኑ ሊሰመርበት ይገባል:: አንድም እንዲት ማለቱ ይህችንም ጥምቀት አንዳዶቻችሁ በውሃ ሌሎቻችሁ በወተት አልተጠመቃችሁም እንዲል ነው::

በሰላም ማሰሪያ: የሚለው ትህትና: የዋህነት: ፍቅር ሁነኛ የአንድ በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያምን ክርስቲያን  መታወቂያዎች ናቸው:: “የማህበረ ቅዱሳን” አባላት ክርስቲያን ናቸው ለማለት በራሱ ቀድሞውኑ በክርስቶስ ብቸኛ አዳኝነት ሲያምኑ አይደለም ወይ? እንዲሁም በሌላ ስፍራ ጳውሎስ “ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና” እንዲል ኢየሱስን የለበሰ ኢየሱን ይመስላል!! የሀገሬ ሰው "ከአህያ ጋር የዋለ ኰርማ ሕላ (እንደ አህያ መጮህ) ባይማር ምን ይለምዳል" እንደሚለው እንደ "ማህበረ ቅዱሳንና” አባላቶቹ ያሉት ከቃሉ ጋር ምንም ዓይነት ግኑኝነትና ሕብረት የሌለው ደግሞ ጋንጩር መምሰሉ ሊደንቀን
አይገባም::

መቼም በዚህ ሁሉ ሐተታ ጳውሎስ“አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት” በማለት የጻፈው መልእክትና "ማህበር ቅዱሳንና” አባላቱ ደግሞ በፊናቸው ባልገባቸው “አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት” ማለትና ምን እንደሆነ ግልጽ ነው ብዬ አምናለሁ የተቀረውን ደግሞ አንድ በአንድ ተለቅመው ለንባብ እስኪበቁ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ምሕረት ሰላማና ፍቅር ከሁላችን ጋር ይሁን::

/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
Email: yetdgnayalehe@gmail.com
April 26, 2012
United states of America

20 comments:

 1. ባ ሰላማ በማለት በቅዱሳን ስም እየተጠራ ቅዱሳን መላእክትን፣ እመቤታችንን እና ጻድቃንን የሚዘልፈው “አባ ሰላማ” የተሰኘው የተሐድሶ መናፍቃን ብሎግ፤ በማያፍር አንደበቱ ማኅበረ ቅዱሳንን በመሳደብ ላይ ይገኛል:: ማኅበረ ቅዱስንም “የቅዱሳኑ የስድብ በረከት ለእኔም ይድረሰኝ” በማለት ይመስለናል ለብሎጉ ምን ዓይነት መልስ ሰጥቶ አያውቅም::

  “አባ ሰላማ” ብሎግ በ1992 ዓ/ም ከቤተ ክርስቲያ ተወግዘው የተለዩት የተሐድሶ መናፍቃን በድሬዳዋዎቹ ቡድን እንደሚመራ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ::

  ይህ የመናፍቃኑ ብሎግ በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ማኅበረ ቅዱሳን ላይ በሬ ወለደ ዓይነት ወሬዎች ይዘግባል:: ሰሞኑን ከተዘገቡ የሐሰት ውንጀላዎች መካከል “ማኅበረ ቅዱሳን የግቢ ጉባኤ አባላቱን በግድ ወርሃ ጽጌ እንዲጾሙ ያዛል” የሚል ነው:: በእርግጥ ዲያቢሎስ ጾም መች ይወዳል፤ የግብር ልጆቹ ቢቃወሙም አይደንቅም:: ወርሃ ጽጌን ብዙዎች ምእመናን እና ካህናት የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስደቷን በማሰብ በፈቃድ እንደሚጾሙት የሚታወቅ ነው:: እንግዲህ አንዳንድ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎችም በፈቃድ ይጾሙታል የሚል እምነት አለን::


  በአጽዋማት ወቅት በሚሰበሰበው የቁርስ ዳቦ አማካኝነት አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን በሌለባቸው አካባቢዎች ቤተ ክርስቲያን እንደተሰሩ ሰምተናል አይተናልም:: የሰንበት ትምህርት ቤተ አዳራሽ በሌለባቸው አጥቢያዎች ደግሞ የመማርያ አዳራሾች እንደተሰሩ የአይን ምስክሮች ሲናገሩ እንሰማለን:: ታድያ ተሐድሶዎቹ ከቁርስ ዳቦ በመሸጥ የተሰበሰበው ገንዘብ “በእኛ ኪስ ለምን አልገባም” ለማለት ይመስላል “አባ ሰላማ” ብሎግ አምርሮ ተቃውሞታል::

  ለመሆኑ “አባ ሰላም” ብሎግ እና ሌሎች መሰሎቻቸው ማኅበረ ቅዱሳን ሚጠሉ ሰዎች እነ ማን ናቸው? ለምንስ ይጠሉታል? ብለን እንጠይቅ ይሆናል:: በአጠቃላይ ማኅበረ ቅዱሳንን የሚጠሉ ሰዎች በሦስት ከፍለን እንያቸው::

  ፩. ማኅበረ ቅዱሳን በዓላማ እንዲጠፋ የሚፈልጉ:: እነዚህም:-
  ተሐድሶ መናፍቃን ( ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉ)
  መናፍቃን የውጭ (“ጴንጤ”)
  አክራሪ እስላሞች
  እነዚህ ከላይ የጠቀስናቸው ቡድኖች የማኅበሩን አገግሎት በደንብ ጠንቅቀው ያውቁታል:: እንዲሁም ዓላማውም በሚገባ ተረድተውታል። አክራሪው እስላም በቤተ ክርስቲያን ላይ በተለያዩ ጊዜያት የሚያደርሱት ጥፋት እየተከታተለ መረጃ እየሰበሰበ እኩይ ተግባራቸውን እያጋለጣቸው ስለሆነ፤ የማኅበሩን መኖር የእግር ላይ እሳታቸው ነው። ወደፊትም ላቀዱት ጥፋት ይከታተለናል ብለው ስለደመደሙ ማኅበሩ እንዲጠፋ ደፋ ቀና ሲሉ ይታያሉ:: ማኅበረ ቅዱሳን “ኢትዮጵያን የማስለም ዓላማ ተግባራዊ ለማድረግ እንቅፋት ሆኖብናል” ብለው በግልፅ በተለያዩ የእስልምና ፓል ቶክ ውይይት እየሰማናቸው ነው።

  ሌሎቹ ሁለቱን የውስጥ(ተሐድሶ) እንዲሁም የውጭ መናፍቃን ግብራቸው እና ዓላማቸው ማኅበሩ በሚገባ አውቆት አጥብቆ እንደሚቃወማቸው ያውቃሉ:: ስለዚህ የተለያዩ አጋጣሚዎች በመጠቀም የማኅበረ ቅዱሳን ስም ሲያነሱት እናያቸዋለን:: ለዚሁም “አባ ሰላማ” ብሎግ ማየት በቂ ማስረጃ ነው:: ሁለቱንም የመናፍቃን ቡድን የተዋሕዶ እምነትን የማጥፋት ዘመቻቸው ማኅበረ ቅዱሳን እስካለ ድረስ ማስፈጸም አንችልም ብለው ስለወሰኑ፤ በማንኛውም መንገድ እንዲሁም ከአክራሪው እስላም ጋር በመተባበርም ቢሆን ማኅበሩን ሊያጠፉት ይፈልጋሉ።

  ፪. በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በተለያዩ ጥቅማ ጥቅም የተሳሰሩ ሰዎች

  ከአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን እስከ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ድረስ በጥቅማ ጥቅም የተሳሰሩ ቡድኖች ማኅበረ ቅዱሳንን ይጠሉታል የሚል እምነት አለን:: እነዚህኞቹ በጊዜአዊ ጥቅምና ሥልጣን የሰከሩ ናችው።እነ ወይዘሮ እጅጋየሁ እና ቡድኖቻቸውም እዚህ ቡድን ላይ መድበናቸዋል:: ማኅበሩን የሚጠሉበት ዓላማቸው ደግሞ ተግባራቸውን ሥለሚቃወም ነው:: እንዲሁም ደግሞ ያጋልጠናል ብለውም ይሰጋሉ:: የቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልና ይከበር የሚለው ጥብቅ አቋሙ በተቃራኒው ይህን በማይፈልጉት ጥቅመኞ ማኅበሩን እንዲጠሉ አድርጓቸዋል:: ይኸው እነዚህ “ሆዳቸው አምላክ” የሆነባቸው ወገኖች ማኅበሩን ቢችሉ ለማፍረስ ነበረ፤ ነገር ግን ስላልቻሉ ስም የማጥፋት ዘመቻ ቀጥለውበታል::

  ፫. የማኅበሩን አገልግሎትና ዓላማ ያልተረዱ ወገኖች

  እነዚህ ወገኖች ማኅበረ ቅዱሳንን በስም ብቻ ያውቁታል። የማኅበሩን ስም እንኳ የሰሙት ከተሐድሶ መናፍቃን፣ ከተለያዩ ሚድያዎች እንዲሁም ደግሞ ከአክራሪ እስላም ነው። እናም አንድ ጊዜ ብቻ የሰሙትን ወሬ ይዘው ማኅበረ ቅዱስንን ይጠሉታል። እንደው ማኅበረ ቅዱዳን ማን ነው?፤ ዓላማው ምንድ ነው? በቤተ ክርስቲያኒቱስ የትኛው መዋቅር ሥር ነው? ብሎ ለመጠየቅ ጆሮዋቸው የዘጉ አይጠፉም:: ነገር ግን ለመጠየቅ ተዘጋጅተው ምላሽ ለማግኘት አጋጣሚው ያላገኙ ወገኖች እንዳሉም እንገምታለን።

  ማኅበረ ቅዱሳን አንዳንድ ለሚነሱ የስም ማጥፋት ዘመቻዎች ምላሽ ቢሰጥ መልካም ነው እንላለን:: ሐሰት ተደጋግሞ ሲነገር እውነት ይሆናል እንደሚባለው ማኅበሩ በተመለከተ የሚወጡ የሐሰት ውንጀላዎች በተቃራኒ ማሰተባበያ ቢሰጥባቸው የሚል እምነት አለን::
  እግዚአብሔር ተዋሕዶ ሃይማኖታችን ይጠብቅልን!!! አሜን።

  ReplyDelete
 2. ሥራህን ሥራ !

  ጌታ ለእያንዳንዱ ሰው ሥራ ሰጥቶታል፡፡ ያንን መሥራት የእርሱ ፈንታ ነው፡፡ ቢቻለው እርሱን ማገድ የዲያብሎስ ሥራ ነው፡፡ በእርግጥ ሥራውን እግዚአብሔር እንደሰጠህ ያህል ሰይጣን ሊያግድህ ይጥራል፡፡ ሌላ በበለጠ ደስ የሚያሰኝ ነገር ሊያቀርብልህ ይጥራል፡፡ በዓለማዊ ተስፋዎች ያባብልሃል፡፡ የሐሜት ጎርፍ ያስወርድብሃል፡፡ ደራሲያን እንዲጠይቁህ እጅግ ስመጥር ሰዎችም በክፉ እንዲናገሩብህ ይጠቀምባቸዋል፡፡ ጲላጦስ፣ ሔሮድስ፣ ሃናንያ፣ ቀያፋ፣ ሁሉም በአንተ ላይ ያድማሉ። ይሁዳም በአጠገብህ ቁሞ በሠላሳ ብር ሊሸጥህ ይከጅላል። ይኸ ሁሉ የደረሰብህ ሰይጣን በዚህ ሰበብ ከሥራህ ሊስብህና እግዚአብሔርን ከመታዘዝ ሊያሰናክልህ መሆኑን ልትገነዘብ አትችልምን?
  ሥራህን ሥራ! አንበሳው ሲያጓራ ፍንክች አትበል፣ የሰይጣንን ውሾች ለመውገር አትቁም። ጥንቸሎችን በማባረር ጊዜህን አታጥፋ። ሥራህን ሥራ! ዋሾች ይዋሹ፣ ጠበኞች ይጣሉ፣ ማኅበሮችም ይወስኑ፣ ደራሲዎችም ይድረሱ፣ ሰይጣንም የፈለገውን ያድርግ፣ አንተ ግን ምንም ነገር እግዚአብሔር የሰጠህን ሥራ ከመፈጸም እንዳያግድህ ተጠንቀቅ።
  ሥራህን ሥራ! ገንዘብ እንድታተርፍ አልተላክህም፣ እንድትበለጽግም አልታዘዝክም፣ ለክብርህ ተከላከል ብሎ አልነገረህም፣ ሰይጣንና አገልጋዮቹ የሚነዙትን የሐሰት ወሬ እንድታስተባብል አልተጠየቅህም፣ እነኝን ሁሉ ነገሮች ብታደርግ ሌላ ሥራ ልትሠራ አትችልም፣ ይህም ብቻ ሳይሆን ለራስህ እንጅ ለጌታ አልሠራህም።
  ሥራህን ሥራ! ዓላማህ እንደ ኮከብ የፀና ይሁን፣ ተወው ዓለም እንደፈለገው ይነታረክ፣ ይጨቃጨቅ። ጥቃት ይደርስብህ፣ ትበደል፣ ትሰደብ፣ ትታማ፣ ትቆስልና ትናቅ ይሆናል። ኃይለኛ ያጎሳቁልህ፣ ወዳጆች ይተውህ፣ ሰዎችም ይንቁህ ይሆናል። አንተ ግን በፀና ውሳኔ የማያወላውል ቅናት በመጨረሻ ላይ ፀንተህ፣ የሰጠኸኝን ሥራ ፈጸምኩ፣ ሃይማኖትንም ጠበቅሁ ለማለት እስክትችል ድረስ የሕይወትህን ዓላማ እና የተፈጠርክበትን ግብ ተከተል።

  አባ ጎርጎርዮስ
  የሸዋ ሊቀ ጳጳስ
  ምንጭ፡- ሐመር መጽሔት 18ኛ ዓመት ቁጥር 1

  ReplyDelete
 3. "ማህበረቅዱሳን" ሱቅ ከፍቶ ቄስ ቀጥሮና አቁሞ ስለ ነገደ ቄስ የሆነ የሚመስለው ጠባቂ ነኝ የሚል አጽራረ ቤተ-ክርስቲያን ጿሚ መሳይ አጋሰስ፣ የማይሰግድ አሰጋጅ፣ ለማስተማር የማይበቃ አቃቤ መቃብር ባለ ዲግሪ፣ አስራት የማይከፍል በዝባዥና አስከፋይ፣ የማይቀድስ አስቀዳሽ፣ ያልተለወጠ ለዋጭ አስመሳይ የጎበዝ ጥርቅም ማኅበር ነው ሲባልኮ ተራ ውንጀላ ወይንም ደግሞ ክስ ሳይሆን ምስክርነታችን ጭብጥ ላይ የተመሰረተ እውነት ነው::

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሥራህን ሥራ !

   ጌታ ለእያንዳንዱ ሰው ሥራ ሰጥቶታል፡፡ ያንን መሥራት የእርሱ ፈንታ ነው፡፡ ቢቻለው እርሱን ማገድ የዲያብሎስ ሥራ ነው፡፡ በእርግጥ ሥራውን እግዚአብሔር እንደሰጠህ ያህል ሰይጣን ሊያግድህ ይጥራል፡፡ ሌላ በበለጠ ደስ የሚያሰኝ ነገር ሊያቀርብልህ ይጥራል፡፡ በዓለማዊ ተስፋዎች ያባብልሃል፡፡ የሐሜት ጎርፍ ያስወርድብሃል፡፡ ደራሲያን እንዲጠይቁህ እጅግ ስመጥር ሰዎችም በክፉ እንዲናገሩብህ ይጠቀምባቸዋል፡፡ ጲላጦስ፣ ሔሮድስ፣ ሃናንያ፣ ቀያፋ፣ ሁሉም በአንተ ላይ ያድማሉ። ይሁዳም በአጠገብህ ቁሞ በሠላሳ ብር ሊሸጥህ ይከጅላል። ይኸ ሁሉ የደረሰብህ ሰይጣን በዚህ ሰበብ ከሥራህ ሊስብህና እግዚአብሔርን ከመታዘዝ ሊያሰናክልህ መሆኑን ልትገነዘብ አትችልምን?
   ሥራህን ሥራ! አንበሳው ሲያጓራ ፍንክች አትበል፣ የሰይጣንን ውሾች ለመውገር አትቁም። ጥንቸሎችን በማባረር ጊዜህን አታጥፋ። ሥራህን ሥራ! ዋሾች ይዋሹ፣ ጠበኞች ይጣሉ፣ ማኅበሮችም ይወስኑ፣ ደራሲዎችም ይድረሱ፣ ሰይጣንም የፈለገውን ያድርግ፣ አንተ ግን ምንም ነገር እግዚአብሔር የሰጠህን ሥራ ከመፈጸም እንዳያግድህ ተጠንቀቅ።
   ሥራህን ሥራ! ገንዘብ እንድታተርፍ አልተላክህም፣ እንድትበለጽግም አልታዘዝክም፣ ለክብርህ ተከላከል ብሎ አልነገረህም፣ ሰይጣንና አገልጋዮቹ የሚነዙትን የሐሰት ወሬ እንድታስተባብል አልተጠየቅህም፣ እነኝን ሁሉ ነገሮች ብታደርግ ሌላ ሥራ ልትሠራ አትችልም፣ ይህም ብቻ ሳይሆን ለራስህ እንጅ ለጌታ አልሠራህም።
   ሥራህን ሥራ! ዓላማህ እንደ ኮከብ የፀና ይሁን፣ ተወው ዓለም እንደፈለገው ይነታረክ፣ ይጨቃጨቅ። ጥቃት ይደርስብህ፣ ትበደል፣ ትሰደብ፣ ትታማ፣ ትቆስልና ትናቅ ይሆናል። ኃይለኛ ያጎሳቁልህ፣ ወዳጆች ይተውህ፣ ሰዎችም ይንቁህ ይሆናል። አንተ ግን በፀና ውሳኔ የማያወላውል ቅናት በመጨረሻ ላይ ፀንተህ፣ የሰጠኸኝን ሥራ ፈጸምኩ፣ ሃይማኖትንም ጠበቅሁ ለማለት እስክትችል ድረስ የሕይወትህን ዓላማ እና የተፈጠርክበትን ግብ ተከተል።

   አባ ጎርጎርዮስ
   የሸዋ ሊቀ ጳጳስ
   ምንጭ፡- ሐመር መጽሔት 18ኛ ዓመት ቁጥር 1

   Delete
 4. አንተ ማነህ ኩልል ያለ አማርኛ የምትጽፈው:: ጽሁፍህ ብዙ ጊዜ አማርኛ ይሁን ሌላ ቋንቋ አያስታውቅም ነበር:: አሁን የትኛው ትምህርት ቤት ሄደህ የአማርኛ አጻጻፍህን እንዳሻሻልክ ብናውቀው መልካም ነበር:: ዲያቆን ኤፍሬም መልስ የሰጠው ስለሚያውቀው ማኅበረ ቅዱሳን ነው:: የግንዛቤ እጥረቱ ከየት እንደመጣልህ አይገበኝም:: ስለ ማኅበረ ቅዱሳን የግንዛቤ እጥረት ያለብህ አንተ ነህ ምክንያቱም
  1/ የማኅበሩ አባል ባለመሆንህ ግንዛቤ ይጎልሃል
  2/ በጥላቻ የተመረዘ አመለካከት ስላለህ በቀናነት አስተያየት መስጠት አያስችልህም
  3/ኛው እና የመጨረሻው በግልጽ ለተጻፈው ጥቅስ የራስህን አንድምታ ስትሰጥ ከጸሃፊዎቹ ያገኘኽው ምንም መረጃ ሳይኖርህ ጥላቻህን ሊያጠናቅርልህ በሚችል መልኩ መግለጽህ ነው:: ሌላው የሐዋርያው ጳውሎስ ለአንተ ብቻ የታወቀ እና ለማኅበረ ቅዱሳን ግን የተከለከለ እስከሚመስል ድረስ በሚያሳይ መልኩ ገልጸኽዋል::
  ይልቅስ በጥላቻ ራስህን ከምትመርዝ ያመንክበትን የተሃድሶ እምነት አከናውን ማኅበረ ቅዱሳኖችም ያመኑትን ያካሂዱ ዘንድ ተዋቸው:: ያሰማራችሁ ያ ክፉ የራሳችሁን አምልኮ እንድትፈጽሙ ሳይሆን የሱ ባልሆኑት ላይ ያለእርፍት እንድትዘምቱባቸው ስለሆነ ያስታጠቃችሁ ሳያሳድድህ እንዳሳደደህ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ከመንግስት ለማጋጨት ሲገጥምላችሁ ደግሞ በመሃመዳውያኑ አሳበህ ለማጥቃት የምትሞክራቸው ሙከራዎች ማንነትህን ቁልጭ አድርገው ገልጸ ልኛል:: በቃ መባልስ ያለብህ አንተ ነህ:: ሙመ

  ReplyDelete
 5. D Mulugeta Minew ? Min Honeh New ? D Efiremin Ato- Kesis- Diyakon Maletih Mekawemina Medegef mebit bihonm Kihinetun gin menkat yelebhim
  D Efiremin Menkat Mahibere kidusann menkat new -Mahibere Kidusann Mekawem Degimo Egizabhern mekawem new metsenkek Alebihi
  Ato Meles Zenaw yetenagerutm bihon Liyaskeyim yichilal Mahibere Kidusan Akarari new Malet min malet new ? Kemusilim gar magenaget endet yichalal? Mahibere Kidusan Yadinal Eisilam degimo Yigedilal -Mahiberu Yisetsal Esilam degimo Yinetsikal -Mahiberu yiseral Esilam degimo yafersal-Mahiberu yastarkal Esilam degimo yatsalal Min Andinet alew ?

  ReplyDelete
 6. ሁሉ በፍቅር ቢሆን?

  ያለመታደል ሆኖ ኢትይጵያዊነት/አበሻነት ትርጉሙ አልሸነፍነት ሆኖብናል:: ያውም ለወንድም/ለእህት መልካም ነገር እንጂ ለነጩማ ዳንኤል ክብረት 'ፕሮፌሰር ሳቤት' በሚል ርእስ ባቀረበው አስተማሪ ጽሑፉ እንደጠቀሰው አሜን አሜን ነው የምንለው

  ታዲያ 'ወንድሜ' ኤፍሬም የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ጠቅሶ በጥምቀት ላይ ስለቀረበው መፈክር ይዘት ሊያስርዳን መሞከሩ እሱ ባለው መንገድስ ቢሆን የትና መቼ ነው እውነተኛ ክርስቲያኖች ይህን መሰል መፈክር ይዘው በአደባባይ በመውጣት የፎከሩት? ክርስትና በፍቅር ፍቅር ስለሆነው ጌታ መመስከር እንጂ በመፈክር ዓለምን አላዳረሰም:: ምናልባት ኢትዮጵያ አገራችንን በዚህ አዲስ ጅማሬ አንደኛ ለማድረግና ሰይፍ ይዘው በመነሳት ከሚስፋፉት ወገኖቻችን ጋር አንድ ለመሆን ይሆንን? ወንጌል በክፉው መንፈስ ተሞልተው የሰው ሁሉ ጠላት የሆነውን ዲያብሎስን ለማገልገል የተነሱትን ሰዎች ሳይቀር እንድንወድ የሚያደርግ የፍቅር አዋጅ እንጂ ሰይፍ አይደለምና በዚህ ማህበር ውስጥ በመሰግሰግ የገዛ የሥጋ ወገኖቻችሁን የምታሳድዱ ወገኖች ልባችሁን ቆም ብላችሁ በመመርመር መልካም ወደ ሆነው የምህረት ጌታ ተመለሱ በማለት የፍቅር ጥሪ እናስተላልፍላችኋለን::

  ዲያቆን ሙሉጌታም ብትሆን ምንም እንኳን የማህበረ ቅዱሳን በትር ያረፈብህና እስከ ሞት ድረስ እርምጃ ሊወሰድብህ የነበርክ ብትሆንም ስለሞተልህ የጌታ ፍቅር ስትል እውነተኛ ይቅርታ በነዚህ ሳያውቁ ያወቁ መስሏቸው('ቢያውቁ ኖሮ የሕይወትን ጌታ ይሰቅሉት ነበርን?' በጥፋት ጎዳና ላሉ ወገኖቻችን አድርገህ ሊመለሱና እውነተኛ የሕዝብ አገልጋይ የሚሆኑበትን መንገድ የሚያመላክት ትምህርታዊ የፍቅር መልእክት ለማስተላለፍ ብትሞክር??

  ማቅንም ልብ ይስጣችሁ

  ሰላም ሁኑልኝ

  እህታችሁ

  ሰላም ነኝ

  ReplyDelete
  Replies
  1. Hu hu, what about "Eyesus Geta new", "Hale luya" yemibalu mefekiroch, beyedekikaw sil yenebere 1 hawaria bititekisulign?

   Delete
 7. Well done! Keep up.

  Ane ze-Christos,

  ReplyDelete
 8. ባ ሰላማ በማለት በቅዱሳን ስም እየተጠራ ቅዱሳን መላእክትን፣ እመቤታችንን እና ጻድቃንን የሚዘልፈው “አባ ሰላማ” የተሰኘው የተሐድሶ መናፍቃን ብሎግ፤ በማያፍር አንደበቱ ማኅበረ ቅዱሳንን በመሳደብ ላይ ይገኛል:: ማኅበረ ቅዱስንም “የቅዱሳኑ የስድብ በረከት ለእኔም ይድረሰኝ” በማለት ይመስለናል ለብሎጉ ምን ዓይነት መልስ ሰጥቶ አያውቅም::

  “አባ ሰላማ” ብሎግ በ1992 ዓ/ም ከቤተ ክርስቲያ ተወግዘው የተለዩት የተሐድሶ መናፍቃን በድሬዳዋዎቹ ቡድን እንደሚመራ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ::

  ይህ የመናፍቃኑ ብሎግ በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ማኅበረ ቅዱሳን ላይ በሬ ወለደ ዓይነት ወሬዎች ይዘግባል:: ሰሞኑን ከተዘገቡ የሐሰት ውንጀላዎች መካከል “ማኅበረ ቅዱሳን የግቢ ጉባኤ አባላቱን በግድ ወርሃ ጽጌ እንዲጾሙ ያዛል” የሚል ነው:: በእርግጥ ዲያቢሎስ ጾም መች ይወዳል፤ የግብር ልጆቹ ቢቃወሙም አይደንቅም:: ወርሃ ጽጌን ብዙዎች ምእመናን እና ካህናት የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስደቷን በማሰብ በፈቃድ እንደሚጾሙት የሚታወቅ ነው:: እንግዲህ አንዳንድ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎችም በፈቃድ ይጾሙታል የሚል እምነት አለን::


  በአጽዋማት ወቅት በሚሰበሰበው የቁርስ ዳቦ አማካኝነት አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን በሌለባቸው አካባቢዎች ቤተ ክርስቲያን እንደተሰሩ ሰምተናል አይተናልም:: የሰንበት ትምህርት ቤተ አዳራሽ በሌለባቸው አጥቢያዎች ደግሞ የመማርያ አዳራሾች እንደተሰሩ የአይን ምስክሮች ሲናገሩ እንሰማለን:: ታድያ ተሐድሶዎቹ ከቁርስ ዳቦ በመሸጥ የተሰበሰበው ገንዘብ “በእኛ ኪስ ለምን አልገባም” ለማለት ይመስላል “አባ ሰላማ” ብሎግ አምርሮ ተቃውሞታል::

  ለመሆኑ “አባ ሰላም” ብሎግ እና ሌሎች መሰሎቻቸው ማኅበረ ቅዱሳን ሚጠሉ ሰዎች እነ ማን ናቸው? ለምንስ ይጠሉታል? ብለን እንጠይቅ ይሆናል:: በአጠቃላይ ማኅበረ ቅዱሳንን የሚጠሉ ሰዎች በሦስት ከፍለን እንያቸው::

  ፩. ማኅበረ ቅዱሳን በዓላማ እንዲጠፋ የሚፈልጉ:: እነዚህም:-
  ተሐድሶ መናፍቃን ( ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉ)
  መናፍቃን የውጭ (“ጴንጤ”)
  አክራሪ እስላሞች
  እነዚህ ከላይ የጠቀስናቸው ቡድኖች የማኅበሩን አገግሎት በደንብ ጠንቅቀው ያውቁታል:: እንዲሁም ዓላማውም በሚገባ ተረድተውታል። አክራሪው እስላም በቤተ ክርስቲያን ላይ በተለያዩ ጊዜያት የሚያደርሱት ጥፋት እየተከታተለ መረጃ እየሰበሰበ እኩይ ተግባራቸውን እያጋለጣቸው ስለሆነ፤ የማኅበሩን መኖር የእግር ላይ እሳታቸው ነው። ወደፊትም ላቀዱት ጥፋት ይከታተለናል ብለው ስለደመደሙ ማኅበሩ እንዲጠፋ ደፋ ቀና ሲሉ ይታያሉ:: ማኅበረ ቅዱሳን “ኢትዮጵያን የማስለም ዓላማ ተግባራዊ ለማድረግ እንቅፋት ሆኖብናል” ብለው በግልፅ በተለያዩ የእስልምና ፓል ቶክ ውይይት እየሰማናቸው ነው።

  ሌሎቹ ሁለቱን የውስጥ(ተሐድሶ) እንዲሁም የውጭ መናፍቃን ግብራቸው እና ዓላማቸው ማኅበሩ በሚገባ አውቆት አጥብቆ እንደሚቃወማቸው ያውቃሉ:: ስለዚህ የተለያዩ አጋጣሚዎች በመጠቀም የማኅበረ ቅዱሳን ስም ሲያነሱት እናያቸዋለን:: ለዚሁም “አባ ሰላማ” ብሎግ ማየት በቂ ማስረጃ ነው:: ሁለቱንም የመናፍቃን ቡድን የተዋሕዶ እምነትን የማጥፋት ዘመቻቸው ማኅበረ ቅዱሳን እስካለ ድረስ ማስፈጸም አንችልም ብለው ስለወሰኑ፤ በማንኛውም መንገድ እንዲሁም ከአክራሪው እስላም ጋር በመተባበርም ቢሆን ማኅበሩን ሊያጠፉት ይፈልጋሉ።

  ፪. በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በተለያዩ ጥቅማ ጥቅም የተሳሰሩ ሰዎች

  ከአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን እስከ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ድረስ በጥቅማ ጥቅም የተሳሰሩ ቡድኖች ማኅበረ ቅዱሳንን ይጠሉታል የሚል እምነት አለን:: እነዚህኞቹ በጊዜአዊ ጥቅምና ሥልጣን የሰከሩ ናችው።እነ ወይዘሮ እጅጋየሁ እና ቡድኖቻቸውም እዚህ ቡድን ላይ መድበናቸዋል:: ማኅበሩን የሚጠሉበት ዓላማቸው ደግሞ ተግባራቸውን ሥለሚቃወም ነው:: እንዲሁም ደግሞ ያጋልጠናል ብለውም ይሰጋሉ:: የቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልና ይከበር የሚለው ጥብቅ አቋሙ በተቃራኒው ይህን በማይፈልጉት ጥቅመኞ ማኅበሩን እንዲጠሉ አድርጓቸዋል:: ይኸው እነዚህ “ሆዳቸው አምላክ” የሆነባቸው ወገኖች ማኅበሩን ቢችሉ ለማፍረስ ነበረ፤ ነገር ግን ስላልቻሉ ስም የማጥፋት ዘመቻ ቀጥለውበታል::

  ፫. የማኅበሩን አገልግሎትና ዓላማ ያልተረዱ ወገኖች

  እነዚህ ወገኖች ማኅበረ ቅዱሳንን በስም ብቻ ያውቁታል። የማኅበሩን ስም እንኳ የሰሙት ከተሐድሶ መናፍቃን፣ ከተለያዩ ሚድያዎች እንዲሁም ደግሞ ከአክራሪ እስላም ነው። እናም አንድ ጊዜ ብቻ የሰሙትን ወሬ ይዘው ማኅበረ ቅዱስንን ይጠሉታል። እንደው ማኅበረ ቅዱዳን ማን ነው?፤ ዓላማው ምንድ ነው? በቤተ ክርስቲያኒቱስ የትኛው መዋቅር ሥር ነው? ብሎ ለመጠየቅ ጆሮዋቸው የዘጉ አይጠፉም:: ነገር ግን ለመጠየቅ ተዘጋጅተው ምላሽ ለማግኘት አጋጣሚው ያላገኙ ወገኖች እንዳሉም እንገምታለን።

  እግዚአብሔር ተዋሕዶ ሃይማኖታችን ይጠብቅልን!!! አሜን።

  ReplyDelete
 9. ማኅበረ ቅዱሳን የአቋቋም ምስክር ትምህርት ቤትን በ4.6 ሚሊዮን ብር ለመገንባት ውል መፈረሙን ገለጸ
  ሙሉ ዘገባውን የወሰድነው ከማኅበረ ቅዱሳን ድረ ገጽ ላይ ነው::

  ReplyDelete
 10. የብሎጋችሁን ስም አባ ሰላቢ ወይም ሰዳቢ ብትሉት ይሻላል ከመሳደብ እና ከመተቸት ዉጭ ምንም ቁም ነገር የሌለዉ መንፈሳዊ ይዘት የማይተይበት የጨዋዎች መደረክ ነዉ ስለዚህ የሰላቢዉ የዲያቢሎስ የግብር ልጆች ስለሆናችሁ ብሎጋችሁን አባ ሰላቢ ብትሉ ከግብራችሁ ጋር ይስማማል፡፡

  ReplyDelete
 11. Elias, what I have to beg you is that please follow what divisive policy Diakon Mulugeta is following like woyanne hodames. I swear to God, Diakon Mulugeta has some secret plan. Any one living in Ethiopia can understand who is learning Geez and Kidase even while attending higher education in Ethiopia? Diakon, are you crazy? If you are okay, please take time and consider what Mahibere Kidusan is. One thing I don’t agree with mahibere kidusan is only its submission to the cruel politician and dictator Paulos to secure its existence and avoid removal by mad Zenawi. Had the legitimate Synod been in Ethiopia, I would say Mahibere Kidusan Could have done alot. One thing I have to say here is that even though Diakon Mulugeta’s Biblical explanations are right and don’t have substantive contradiction with what has been written by members of mahibere kidusan except manipulation of words in bad faith, there is something we have to smell beyond that. He has taken some position in advance and I am reading many totally fabricated accusations which we can’t expect from spiritual persons like him.

  So, I am compelled to beg everyone to dig deep what this diakon is for our religion and beloved country Ethiopia. We have to interpret his attitude and know on whose side he stands. If he stands with crazy Zenawi and the evil patriarch, then we have to stand against him. If he stands for our religion and Ethiopia truly then his position against Mahibere Kidusan is not a big problem as at the end of the day they will have similar goal.

  God bless Ethiopia and its people….death for dictatorship

  ReplyDelete
 12. kkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkk
  kkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkk
  kkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkk

  I just wonder if people can be chited with your nonsence words. It is not about Eferem or MK,
  you are trying to poisen the Orthodox Church blives and Dogmas, you are not from Orthodox why doe u worry? why don’t you write about TEHADESO, directly?

  Insulting poeple or some one is none sence.

  ReplyDelete
 13. Diakon hono negerochn lemasredat sewechn mezilef, menak yelebetm new yager betun bahl restehewal diakon…

  ReplyDelete
 14. Muluget …poor… I think you are getting mad about MK. Let me advise you…just forget MK and restore your health. Really you are sick about it. Your bitter but trash words are telling how you are sick about MK. Otherwise, you will go soon to the street. May God help you.
  TW.

  ReplyDelete
 15. Mulgata

  Why you want to write all this lie sitting in USA? Why not you go to school and change your life. I think most of Ethiopia know what is good and what is bad at this time. Any way let God forgive for all your sin.

  ReplyDelete
 16. min alik an dekike nistros!!!!!!!!! egiziabher yigesitsih ante yenat tut nekash

  ReplyDelete