Saturday, April 28, 2012

ማኅበረ ቅዱሳን እና ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልእ አይተዋወቁም

አክራሪውና ወግ አጥባቂው የሰለፊያ የግብር ወንድም ማኅበረ ቅዱሳን የተመሰረተበትን 20 ዓመት ሰባት ያህል ወራትን አሳልፎ ሚያዝያ 27 በእግር ጉዞ ሊያከብር መሆኑን ሲገልጽ የቆየ ቢሆንም፣ የተመዝጋቢ ቁጥር በማነሱና በሌላም ምክንያት መራዘሙ እየተወራ ነው። ይሁንና ማስታወቂያው ላይ በትልቁ የብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ፎቶ ተሰቅሏል። የእርሱ የጉዞ መርሀ ግብርና አቡነ ጎርጎርዮስ፣ የእርሱ 20ኛ ዓመትና አቡነ ጎርጎርዮስ ምን እንዳገናኛቸው ለጊዜው ባይታወቅም ብቻ ፎቷቸው በትልቁ የማስታወቂያው ማዳመቂያ ሆኗል።
ከ1980 ብፁዕነታቸው እስካረፉበት እስከ 82 ዓ.ም ድረስ ወደ ዝዋይ የካህናት ማሰልጠኛ ገብተው የተማሩ አንዳንድ የዩኒቨርሲቲና የኮሌጅ ተማሪዎች መካከል አንዳንዶቹ በኋላ ላይ የማኅበረ ቅዱሳን መስራቾች እንደነበሩ ይነገራል። ይህን አጋጣሚ መነሻ በማድረግ ነው ማኅበሩና የማኅበሩ ሰዎች ብፁዕነታቸውን የማኅበሩ መስራች አባት አድርገው ይቆጥራሉ።
ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስን በቅርብ የሚያውቋቸው እንደሚናገሩላቸው ግን ቤተ ክርስቲያን በለውጥ ጎዳና ላይ እንድትራመድ የሚፈልጉ ሰው ነበሩ። ይሁን እንጂ ከሕዝቡ ወግ አጥባቂነትና ንቃተ ህሊና አንጻር ለውጡ አዝጋሚ መሆን እንዳለበት ነበር የሚያምኑት ይባላል። ከላይ እንደገለጽኩት ይህ የብፁዕነታቸው ዓላማ ባይገባቸውም አንዳንድ የማኅበረ ቅዱሳን ቀደምት ሰዎች ዝዋይ ከርመው ተመልሰዋል። ምክንያቱም እነዚህ የማኅበሩ ሰዎችና ማኅበሩም እንደማኅበር ከብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ውጪ መሆናቸውን እየታዘብን ነው። ዛሬ የማህበሩ ሰዎች በስፋት የሚቃወሙት ብፁዕነታቸው በጽሁፍ ያስተላለፏቸውን ትምህርቶች ነው። የማኅበሩ መሠረት ወንጌል ሳይሆን ተረት ነውና።
ማኅበሩ በስማቸው ከሚነግድባቸው ብፁዓን አበው መካከል አንዱና ዋናው የሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልእ ናቸው። ማኅበረ ቅዱሳን በተረታዊ ትምህርቱ ባሳታቸው በብዙዎች ዘንድ አቡነ ጎርጎርዮስ የማኅበረ ቅዱሳን አባት እንደ ሆኑ ይታመናል። አቡነ ጎርጎርዮስ ሲነሱ ማኅበረ ቅዱሳን አብሮ መነሳት ያለበት እስኪመስል ድረስ ሁለቱ የተቆራኙ መስለው እንዲታዩ በማህበሩ በኩል ከፍተኛ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል። ማህበረ ቅዱሳን ስለ እርሳቸው አውርቶ የሚጠግብ አይመስልም። በየመጽሔቱና በየጋዜጣው ፎቷቸውን ያወጣል። ልዩ ልዩ ማስታወቂያ ይሠራባቸዋል። በንግዱ ዘርፍ እየተንቀሳቀሰ የከፈተውን ትምህርት ቤት በስማቸው እስከ መሰየም ደርሶ የማኅበሩ መስራች አስመስሎ ያቀርባቸዋል። በሌሎች መጽሀፍ ሻጮች ዘንድ 25 ብር የሚሸጡትን የብፁዕነታቸውን መጽሐፎች ከሚገባው ባለይ 10 ብር አትርፎ በ35 ብር ይሸጣል። ውስጥ ውስጡን ታቦት በስማቸው እንዲቀረጽና ቤተክርስቲያን እንዲታነጽ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑ ይወራል። አዲስ አበባ ውስጥ በስማቸው (?) “ፈለቀ” የተባለ ጠበል አለ፤ ነገር ግን አቡነ ጎርጎርዮስና ማኅበረ ቅዱሳን ይተዋወቃሉ ወይ? ለማለት ወደድሁ።
ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር መተዋወቅ አለመተዋወቃቸውን በዚህ ጽሁፍ ቢያንስ በሁለት ነጥቦች እንፈትሻለን።
1ኛ/ በዘመን አይገናኙም
ማኅበረ ቅዱሳን የተመሠረተው መስከረም 4 ቀን 1984 ዓ.ም ነው። ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ደግሞ ሐምሌ 22/1982 ዓ.ም ነው። ስለዚህ እኚህን አባትና ማህበሩን ዘመን አያገናኛቸውም ማለት ነው። ምናልባት ማኅበረ ቅዱሳን በፖለቲካ አባቶቹ ብላቴ ላይ ተጠንስሶ ከዚያ መልስ አንዳንድ ቀደምት አባላቱ የሆኑ የኮሌጅ ተማሪዎች ወደ ዝዋይ ሄደው የክረምት ኮርስ እንደ ወሰዱ ይታወቃል። ብፁዕነታቸው ባቀኑት የካህናት ማሰልጠኛ ውስጥ ገብተው የ3 ወራት ኮርስ መውሰዳቸውን ከእርሳቸው ጋር እንደ መተዋወቅ ከቆጠሩት ያ ሌላ ጉዳይ ነው።
ምናልባት የማህበሩ ሰዎች ብፁዕነታቸውን በአካለ ስጋ አይተዋቸው ማወቅ አይጠበቅባቸውም። ትምህርታቸውን ተቀብለው በእርሳቸው መንገድ ከተጓዙም እርሳቸውን እንዳወቁ ሊቆጠር ይገባል የሚል መከራከሪያ ሊነሳ ይችላል። ይህ ትክክል ነው። ነገር ግን በዚህም ብፁዕነታቸውና ማህበሩ ትውውቅ የላቸውም። ታዲያ ለምን በስማቸው ይነግዳል? በስማቸው መነገድ የሚያስገኝለት ኢኮኖሚያዊና ሌላም ትርፍ ስላለው ነው። ስማቸውን እየተጠቀመ የእርሳቸውን ትምህርት የተከተለ፣ በእርሳቸው አመለካከት የሚመራ መስሎ በመታየት ባላስተዋሉት ዘንድ የእርሳቸው አላማ ተከታይ መስሎ ለመቅረብ ነው። ከዚህ የተነሳም በስማቸው የሚያገኛቸውን ገቢዎች ያሳድጋል።
2ኛ/ በትምህርት አይገናኙም
በቅርቡ ነው። አንዲት እህት ወደምታውቃቸውና የማኅበሩ ወዳጅ ወደ ሆኑ አንድ ሊቀጳጳስ ትመጣና የቤተክርስቲያን ትምህርት ሊያስተምራት ከሚችል ሰው ጋር እንዲያገኛኗት ትጠይቃቸዋለች። እርሳቸውም ወደማኅበሩ ይመሯታል። ማኅበሩ የመደበላት አስተማሪ ግን ራሱን «ቢዚ» በማድረግ ሊያስተምራት አልቻለም። ስለዚህ ወደ ሊቀጳጳሱ ዳግም ትመጣና የተመደበላት ሰው ሊያስተምራት እንደልቻለ ትነግራቸዋለች። ከዚያም “ቆይ አንቺ ምን መማር ነው የፈለግሽው?” ይሏታል። እርሷም “ወንጌል” ትላቸዋለች። “እኔ እኮ ባህልና ሥርአት መማር የፈለግሽ መስሎኝ ነው እንጂ ወንጌልማ ማኅበረ ቅዱሳን ጋ አታገኚም። እዚያ የምታገኚው ባህል፣ ታሪክና የመሳሰለውን ነገር ነው። ወንጌል ከፈለግሽ ተሀድሶ እየተባሉ ወደሚታሙት ልጆቻችን ዘንድ ሂጂ” አሏት። ይህ ተረት አይደለም። እውነተኛ የቅርብ ጊዜ ገጠመኝ ነው።
ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ በቤተክርስቲያናችን ጠቃሚ የሆኑ መጻሕፍትን ከጻፉ ጥቂት ጳጳሳት መካከል አንዱና ብርቅዬው ናቸው። በተለይ “የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ” እና “የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ታሪክ” በተሰኙ በተደጋጋሚ ታትመው እየተሸጡ ባሉ መጻሕፍቶቻቸው ይታወቃሉ። ሌሎች ያልታተሙና በዝዋይ የካህናት ማሰልጠኛና በሌሎችም ማሠልጠኛዎችና በአንዳንድ አጋጣሚዎች ለቤተክርስቲያን አገልጋዮች ኮርስ የሚሰጥባቸው፣ የስብከት ዘዴ፣ ትምህርተ ኖሎትና የመሳሰሉት ሥራዎቻቸውም ተጠቃሽ ናቸው። እነዚህ መጻሕፍቶቻቸው በመጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነታ ላይ የተመሠረቱ ብቻ ሳይሆኑ፣ ከዚያ ጋር የሚቃረኑ አንዳንድ ትውፊታዊ አስተምህሮዎችንም ይዘው ለመሄድ ስለሚሞክሩ፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ጋር ተጋጭተው የሚገኙበት ሁኔታ አለ። ይህ እንግዲህ ከብፁዕነታቸው የተሰወረ ሆኖ ሳይሆን ከተለመደው ነገር በአንድ ጊዜ ወጥቶ ወደሌላ ነገር መግባት አዋጪ መንገድ እንዳልሆነ ስለሚያውቁ ነው ይላሉ ቅድመ ጵጵስና ጀምሮ በቅርብ የሚያውቋቸው። ይህ ደግሞ የብዙዎቹ ሊቃውንቶቻችን አካሄድ ነው።
በዚህ ጽሁፍ ግን ከማኅበረ ቅዱሳን ተረት የተለየውንና ማኅበሩ በገሃድ የማይቀበላቸውን፣ የማይስማማባቸውንና የሚቃወማቸውን፣ እንዲሁም አንዳንድ የቤተክርስቲያን ልጆች የብፁዕነታቸውን መጽሀፎች ጠቅሰው ስለተናገሩና ስላስተማሩ “መናፍቅ ተሀድሶ” እያለ ያወገዘባቸውን የቤተክርስቲያን ትምህርቶች ከብፁዕነታቸው መጻህፍት በጥቂቱ ልጥቀስ።
·        “በክርስትና ሃይማኖት መሠረታዊ ትምህርት የጽድቅ የሕይወት መንገድ ክርስቶስ  ብቻ ነው (ዮሐ. 14፥6፤ የሐዋ.ሥራ 4፥12)” (የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ ገጽ 58)።
ብፁዕነታቸው ይህን እውነተኛ ምስክርነት የጻፉት ግኖስቲኮችና የእነርሱ አመለካከት አቀንቃኞች ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ውጪ የሚያምኑትና የሚያስተምሩት ትምህርት ዋና ኑፋቄ ሆኖ በመገኘቱ ነው። እርሳቸውም የእነርሱን ሐሳብ እንዲህ ሲሉ ተችተውታል። “ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመግባት ብዙ መንገዶች አሉ ሁሉም ያስኬዳል እያሉ በድፍረት ሲናገሩ ይሰማሉ፡፡ ይህም ዩኒቨርሳሊዝም “UNIVERSALISM” ይባላል፡፡ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ እንዳቆየን ግን አባባሉ የቤተ ክርስቲያንን ህልውና የሚነካ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያንን ለረጅም ጊዜ የሆድ ህማም ሆኖ ሲያሰቃይ የኖረ የግኖስቲኮች እርሾ ነው፡፡”

ማኅበረ ቅዱሳን እንደ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ዮሐንስ 14፡6 እና የሐዋ. ስራ 4፡12ን ጠቅሶ “በክርስትና ትምህርት የጽድቅና የሕይወት መንገድ ክርስቶስ ብቻ ነው” ብሎ አያምንም። እንዲያውም እነዚህን ጥቅሶች የመናፍቃን ጥቅሶች ናቸው ብሎ ነው የሚፈርጃቸው። እርሱ የሚከተለው የግኖስቲኮችን መንገድ ነው፡፡ ለእርሱ ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሁሉም ያስኬዳል። ክርስቶስ ብቻ ሳይሆን ጻድቃን፣ ሰማእታትና መላእክት፣ የሃይማኖት ስርአት፣ ወግና ልማድ፣ ሁሉ ያድናል ብሎ ነው የሚያምነውና የሚሰብከው፡፡ ብፁዕነታቸው እንዳሉትም ይህ በመጽሀፍ ቅዱስ ላይ ያልተመሰረተ ልብወለድ ትምህርቱ የቀድሞው የሆድ ህመም ጨርሶ ሳይለቃት ላለፉት 20 ዓመታት ተባብሶ ቀጥሎ ቤተክርስቲያን በማህበረ ቅዱሳን የዩኒቨርሳሊዝም ትምህርት እየተሰቃየች ትገኛለች።
·        “ሊቃውንቱ መምህራኑ የሕዝቡን የረጅም ዘመን ፍቅር ጣዖት ለማስተው ስላቃታቸው በጣዖታቱ ተሠይሞ ይከበር የነበረው ሁሉ በቅዱሳን ስም እየለወጡ ያከብሩታል፡፡ ለምሳሌ በጣዖታዊነት በነበሩበት ጊዜ ‘ፖሲዶን’ የሚባለው ጣዖት የባሕር አምላክ ነበር፡፡ በክርስትና ዘመናቸው ግን ሊቃውንቱ ‘ኒኮላዎስ’ የሚባለውን ቅዱስ ‘የባህር ጠባቂ’ ብለው በየአመቱ ያከብሩታል፡፡ የመርከበኞች በዓል ነው፡፡ ‘ኦሪስ’ ወይም ‘ማርስ’ የጦር አምላክ ተብሎ ሲመለክ የኖረ ጣኦት ነው በእርሱ ምትክ ዛሬ ቅዱስ ጊዮርጊስን የወታደሮች ጠባቂ ብለው በየአመቱ ያከብራሉ፡፡

“በአጠቃላይ አረማውያን ለእያንዳንዱ ድርጊት (ፍጥረት) አምላክ መድበውለት ስለነበር ዛሬ በቤተ ክርስቲያናቸው የሚከበሩት ቅዱሳን መላእክት ጻድቃን ሰማዕታት ሁሉ የአንዳንድ ነገር ጠባቂዎች እየተባሉ ተሠይመዋል” (የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ታሪክ ገጽ 107)።

በዓላትን በተመለከተ ብፁእነታቸው የጻፉት ይህ እውነት የሚነግረን እኛ በልማድ የምናከብራቸው በዓላት የጣኦታት በዓላት ልዋጭ መሆናቸውን ነው። ማኅበረ ቅዱሳን ግን ይህን ሲጠቅስ አልተሰማም። የቅዱሳን የተባሉ በዓላት ከመጀመሪያው የቅዱሳኑ መታሰቢያ ሆነው እንደተመደቡ ነው የሚያምነውና የሚያስተምረው።

በሌሎቹ አገራት ያሉና ቀድሞ ጣኦት አምላኪዎች የነበሩ ወደ ክርስትና ሲመለሱ የቀደሙትን የጣኦቶቹን በዓላት በቅዱሳን በዓላት መተካታቸው ክርስትናን በሙሉ ልባቸው እንዳልተቀበሉ ያሳያል። እነዚህ የጣኦታት ፍቅር ከልባቸው ያልወጣላቸው እነዚህ “ክርስቲያን ተብዬዎች” ክርስቲያን መባላቸው ትክክለኛ አይደለም። ከጣኦታት ቅዱሳንን ወደማምለክ መሸጋገራቸው ከስም ለውጥ በቀር ምንም ምንም አዲስ ነገር አላደረጉምና ክርስቲያን ሆኑ አያሰኝም? የሚል እምነት አለኝ፡፡

ከዚሁ ጋር ተያይዞ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከጌታ በአላት ውጪ ያሉት ብዙዎቹ በዓላትና የአከባበራቸው ስርአት በህዝቡ ልማድ ላይ የተመሰረተ እንጂ በቀኖና ቤተክርስቲያን ያልተወሰነ መሆኑን ጽፈዋል (የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ 108)። ማኅበረ ቅዱሳን ግን ይህንንም ኦርቶዶክሳዊነትን መናድ አድርጎ ነው የሚመለከተው፡፡ ከብፁዕነታቸውም በተቃራኒ ነው የቆመው፡፡
·        ስለ ታቦት የብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ማህበረ ቅዱሳን ከሚያስተምረው ትምህርት ጋር ይለያያል፡፡ ብፁዕነታቸው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ታቦት ከእስራኤል ታቦት የተለየ መሆኑን እንዲህ ሲሉ ጽፈዋል፡፡ “የደብተራ ኦሪት ጽላት እግዚአብሔር በደመና ተከናንቦ ሙሴንና አሮንን የሚያነጋግርበት፣ ለእስራኤል ብቻ በረድኤት የሚገለጽበት ዙፋን ነበር። ይህ ግን የአምላክ ሥጋና ደም የሚፈተትበት ሥጋዬን የበላ ደሜን የጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው። ስጋዬን ብሉ ደሜን ጠጡ እያለ ያመኑትን ሁሉ የሚጠራበት የምሕረት ምሥዋዕ ነው።”  (የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ገጽ 94)።

ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ በሁለቱ ታቦቶች መካከል ያለውን መሰረታዊ ልዩነት አስቀምጠዋል። ማኅበረ ቅዱሳን ግን የእስራኤልን ታቦትና የእኛን ቤተክርስቲያን ታቦት አንድ አድርጎ ነው የሚመለከተው። ስለዚህ በዚህ ትምህርት ሁለቱ አይገናኙም፡፡
·        በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ካቶሊኮች “የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ኦሪታዊት እንጂ ወንጌላዊት አይደለችም በማለት አንዳንድ በህዝቡ ዘንድ የሚፈጸሙ ባህሎችን እንደ ነውር በመቁጠር ወሬውን ያናፍሱት ጀመር። በዚህ ምክንያት ንጉሡ አጼ ገላውዴዎስ የኢትዮጵያን ትክክለኛ እምነት የሚያስረዳ ጽሑፍ በወሬው ለተወናበዱት ሁሉ አስተላለፉ” (የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ገጽ 150)፡፡ በዚያ ዘመን ለተናፈሱ ወሬዎች በአጼ ገላውዴዎስ የሃይማኖት ውሳኔ በተሰጠው ምላሽ ውስጥ የምናገኛቸው አንዳንድ አቋሞች የኢትዮጵያን ትክክለኛ እምነት የሚያስረዱ መሆናቸውን ብፁዕነታቸው ገልጸዋል። ከእነዚያ ውሳኔዎች ማኅበረ ቅዱሳን የማይቀበላቸውና የሚቃወማቸው አቋሞች እንዳሉ ግልጽ ነው።
ለምሳሌ “ዐሣማንም ስለ መብላት ከመብላት የተከለከልነው፣ እንደ አይሁድ የኦሪትን ሕግ ለመጠበቅ ብለን አይደለም የሚበላውን አንጸየፈውም፤ አናረክሰውም፤ የማይበላውንም ብላ ብለን አናስገድደውም፡፡ አባታችን ጳውሎስ ለሮም እንደ ጻፈው “የሚበላ የማይበላን አይንቀፈው (አይናቀው)፤ እግዚአብሔር ሁሉንም ተቀብሏቸዋልና የእግዚአብሔር መንግሥት በመብልና በመጠጥ አይደለችም ለንጹሐን ሁሉ ንጹሕ ነው ለሰው ክፉው ከጥርጣሬ ጋር መብላት ነው።” (ሮሜ 14፡3፡17፤ ቲቶ 1፡15፤ 1ቆሮ. 8፡9-13) ወንጌላዊ ማቴዎስም “ከአፉ ከሚወጣው በቀር ሰውን የሚያረክሰው የለም፤ ወደ ሆድ የሚገባ ጥቂት ቈይቶ ይወድቃል፤ ይፈስሳል፤ ምግቦችን ሁሉ ያነጻል” አለ። (ማቴ. 15፡11፡17፤ ማር. 7፡15)፡፡ ይህ አባባሉ ከኦሪት መጽሐፍ የተማሩ የአይሁድን የስሕተት ሕንጻ ሁሉ አፈረሰው እኔና በግዛቴ ውስጥ ያሉ፣ በትእዛዜ የሚያስተምሩ ዐዋቂዎች ካህናት ሃይማኖት ይህ ነው ከወንጌል መንገድ፣ ከጳውሎስም ትምህርት ወደ ቀኝና ወደ ግራ አይሉም በኛም የታሪክ መጽሐፋችን ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ በግዛት ዘመኑ የተጠመቁትን አይሁድ ሁሉ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ዕለት የዐሣማ ሥጋ እንዲያበሏቸው አዘዘ የሚል ጽሑፍ አለ
ነገር ግን ሰው በልቡ ደስ እንዳለው የእንስሳትን ሥጋ ከመብላት ይወሰናል የዓሣ ሥጋ የሚወድ አለ፤ የዶሮ ሥጋ መብላት የሚወድ አለ፤ የበግ ሥጋ ከመብላት የሚወሰን አለ ሁሉ ለልቡ ደስ ያለውን ይከተላል የሰው ውዴታውና ፈቃዱ እንደዚህ ነው ስለ እንስሳት ሥጋ መብል በዐዲሲቱ መጽሐፍ (በዐዲስ ኪዳን) ውስጥ ቀኖናም ሥርዐትም የለም ለንጹሓን ሁሉ ንጹሕ ነው ጳውሎስም “የሚያምን ሁሉን ይብላ” አለ። (ሮሜ 14፥22-23)፡፡” (የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ታሪክ ገጽ 154-155)፡፡

በማኅበረ ቅዱሳን ዘንድ እንዲህ ያለው ትምህርት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ሳይሆን ኑፋቄ ነው፡፡ በመሆኑም ከዚህ ቀደም አባ ወልደ ትንሣኤ አያልነህ መብልን በተመለከተ ይህን ጠቅሰው ጉዳዩ ከባህል ጋር እንጂ ከእምነት ጋር እንደማይያያዝ ስለተናገሩ የማህበረ ቅዱሳን ጋዜጣና መጽሔት ተሀድሶ መናፍቀ ብሏቸዋል። በዚህ ጽንፈኛ አቋሙ ማኅበረ ቅዱሳን ከቀደመው የኦርቶዶክስ እምነት ጋር እንዳልተስማማና ከብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ጋርም በትምህርተ ሃይማኖት እንደማይገናኝ አስመስክሯል።

ጸጋ ታደለ

39 comments:

 1. የተዛባ አመለካከት አገልግሎታችንን አያደናቅፈውም
  ግንቦት 16፣2003ዓ.ም


  በእግዚአብሔር ፈቃድ በቅዱስ ሲኖዶስ ይሁንታ የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ለመደገፍና ለማጠናከር የተመሠረተው ማኅበረ ቅዱሳን ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ አያሌ ፈተናዎችን እያሳለፈ 19 ዓመታት ተጉዟል፡፡
  ማኅበረ ቅዱሳን በዓመታት ጉዞው ባከናወናቸው መልካም ተግባራት ታላላቅ የቤተክርስቲያን አባቶችን ጨምሮ እጅግ በርካታ ወዳጆችን እንዳፈራ ሁሉ ጥቂት በተቃራኒው የቆሙ ስሙን በየጊዜው በክፉ የሚያነሱ ቡድኖችም ተነሥተውበታል፡፡

  ወዳጆቹ የቤተ ክርስቲያን ወዳጆች ናቸውና በአገልግሎቱ ተማርከው በሚሠራቸው መልካም ሥራዎች ተስበው ቤተ ክርስቲያን ያለባትን የአገልግሎት ክፍተት ለመሙላት በጋራ ከማኅበሩ ጋር በመሥራት ሲተባበሩ፤ በአንጻሩ ጠላቶቹ ደግሞ የተለያዩ አጋጣሚዎችን እያስታከኩ ማኅበሩን ለመወንጀል እየተጣጣሩ ይገኛሉ፡፡

  ማኅበረ ቅዱሳን እንዴት ወዳጆች አፈራ? ጠላቶችስ ለምን ተነሡበት?

  ማኅበረ ቅዱሳን እግዚአብሔር ፈቅዶ ከተመሠረተበት ጊዜ አንሥቶ ወጣቶችን በተለይም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን በማደራጀት ከመደበኛው ትምህርታቸው ጎን ለጎን በየአካባቢው ወደሚገኙ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ሔደው መሠረታዊውን የቤተ ክርስቲያን ትምህርት እንዲማሩ በማድረግ ሃይማኖታቸውን ጠንቅቀው እንዲያውቁና ቤተ ክርስቲያናቸውን እንዲጠብቁ እንዲሁም በዕውቀታቸው፣ በገንዘባቸውና በጉልበታቸው እንዲያገለግሉ በማድረግ፤ በተጨማሪም ወጣቱ ሀገሩንና ሕዝቦቿን አክባሪ፣ በሥነ ምግባር የታነጸ እንዲሆን በማስቻሉ ብዙ ወዳጆችን አግኝቷል፡፡

  ከዚህም ሌላ የመናፍቃኑንና ቤተ ክርስቲያኒቱን እናድሳለን ብለው የተነሡትን የመናፍቃኑ ተላላኪ ቡድኖችን ሴራና የአክራሪ እስልምናውን እንቅስቃሴ በመረጃ አስደግፎ በማጋለጡ፣ ከክፉ ትምህርታቸው መመለስ ያልፈለጉ የተሐድሶ ቡድን አባላት ከቤተ ክርስቲያን እንዲወጡ ስለተወሰነባቸው እና ሌሎችንም የቤተ ክርስቲያኒቱን ችግሮች እየተከታተለ ለዕድገቷና ለብልጽግናዋ በመሥራቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የቤተ ክርስቲያን ወዳጆችን አፍርቷል፡፡

  ከዚህ በተቃራኒው የተሰለፉት ወገኖች ደግሞ ወጣቱን እንደጠፍ ከብት ወደ ማያውቀው የመናፍቃን አዳራሽ የመንዳት ልምዳቸው በመቋረጡና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በመግባት የሚያደርጉት ሥርዓቷን የማፋለስ እንቅስቃሴ፤ እንዲሁም አገልጋዮቿንና ምእመናኖቿን የማስኮብለሉ አካሔድ ማኅበሩ በክትትል በተለያዩ መረጃዎች ስለገለጠባቸው ማኅበረ ቅዱሳንን በጠላትነት በማየት ማኅበሩ እንዲፈርስ የማይቧጥጡት ዳገት የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፡፡

  እነዚህ የቤተ ክርስቲያን የውስጥ ጠላቶች ለጥቂት ጊዜ ጋብ ብለው የነበሩ ቢሆንም አሁን ባገኙት አጋጣሚ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንጀራዋን እየበሉ የሚኖሩ ወዳጆቻቸውን በማጠናከርና በማስፋፋት በሚሊዮን የሚቆጠር በጀት ከወዳጆቻቸው ተመድቦላቸው የቤተ ክርስቲያኒቱን ሥርዓት ለማዛባትና በጎቿን ለመበታተን ሌት ከቀን እየሠሩ ነው፡፡

  ይኼ ዕቅዳቸው የሚሳካው እንደ ማኅበረ ቅዱሳን ያሉ ለቤተ ክርስቲያኒቱ እምነትና ሥርዓት መጠበቅ የሚቆረቆሩ ማኅበራትን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ አጀንዳ በማድረግና እንዲበተኑ ክፉ ሥራ በመሥራት ነው፡፡ እነዚህ የቤተ ክርስቲያን ጠላቶች ይሔንን ከንቱ ቅዠታቸውን እውን ለማድረግም በቤተ ክርቲያኒቱ የተለያየ ሓላፊነት ላይ የሚገኙትን የዓላማቸው አስፈጻሚዎች ሁሉ እየተጠቀሙ እንደሚገኙም ይታወቃል፡፡

  ከዚህም ሌላ ድብቅ ዓላማቸው እንዲሳካ ተላላኪዎቻቸው በቤተ ክርስቲያኒቱ ሥር የሚሆን ነገር ግን ስውር ዓላማ ያለው ማኅበር እንዲመሠርቱና ከዚህ በፊት ከንቱ ተግባራቸው ታውቆ በቤተ ክርስቲያኒቱ ታግደው የነበሩ ማኅበራት ሁሉ ከሞቱበት እንዲቀሰቀሱ እየሠሩም እያደረጉም ይገኛሉ፡፡

  በቤተ ክርስቲያን ስም ድብቅ ዓላማቸውን ለማስፈጸም ያቋቋሟቸውና የሚያቋቁሟቸው፣ ማኅበራትንም ሕጋዊ ዕውቅና ለማሰጠት እንዲያመቻቸው ማኅበረ ቅዱሳን ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ከኔ ሌላ ሌሎች አያስፈልጉም የሚል አቋም ያለው ማኅበር እንደሆነ ያስወራሉ፡፡

  በእርግጥ ማኅበረ ቅዱሳን በትክክል የቤተ ክርስቲያኒቱን ሥርዓትና ደንብ ተከትለው በሚቋቋሙት ማኅበራት ላይ የማኅበሩ ጠላቶች ከሚያወሩትና ከሚያስወሩት አሉባልታ የተለየ አቋም አለው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርቲያን የሁለት ሺሕ ዓመታት ታሪክ ያላት ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን ትሁን እንጂ መንበሯ ከሊቀ ጵጵስና ደረጃ ወደ ፕትርክና ለማሳደግ አንድ ሺሕ ስድስት መቶ መራራ ዓመታትን አሳልፋለች፡፡ በዚህ ማለፏ ደግሞ ሌሎች አኀት አብያተ ክርስቲያናት የደረሱበት ዘመናዊ የአደረጃጀት ደረጃ ላይ ለመድረስ አልቻለችም፡፡ ልጆቿንም ጊዜው በሚጠይቀው መንገድ ለመምራት ሳትችል ስለቆየች እነዚህን ክፍተቶች የሚሞሉ አንድ አይደለም በርካታ ማኅበራት እንደሚያስፈልጓት ማኅበረ ቅዱሳን ያምናል፡፡ ነገር ግን እኩያኑ እንደሚሉት ሳይሆን እነዚህ ማኅበራት ሲቋቋሙ ለአንዲት ቤተ ክርስቲያን ዕድገትና የአገልግሎት ሥምረት የሚንቀሳቀሱ ተልእኮአቸውና ዓላማቸው ተለይቶ የሚታወቅ፣ መንፈሳዊ ተግባርን ብቻ የሚፈጽሙ፣ የሚናበቡና በስልት ለአንድ ውጤት የሚተጉ ሊሆኑ ይገባቸዋል የሚል ጽኑ አቋም አለው፡፡

  ይሔንን አቋሙን ደግሞ በርካቶች የሚደግፉት እንደሆነ ማኅበረ ቅዱሳን ያምናል፡፡ ምክንያቱም እነዚህ የመናፍቃኑ ተላላኪዎች በቤተ ክርስቲያን ስም ያቋቋሟቸው ማኅበራት ከዚህ በፊት በቤተ ክርስቲያን ላይ ጥለውት የሔዱት ጠባሳ የሚታወቅ ስለሆነ ማኅበረ ቅዱሳን በማኅበራት ላይ ግልጽ አቋም አለው፡፡ ከዚህም ሌላ እነዚህ የውስጥ ዐርበኞች ይኽ ስውር ዓላማቸው ያልታወቀባቸው ይመስል ማኅበሩን ለመወንጀል የማይለጥፉለት ታፔላ፣ የማይለፍፉት ወሬ የለም፡፡ ነገር ግን እነዚህ የቤተክርስቲያን ጠላቶች ስለማኅበሩ የሚያወሩት ሁሉ ከእውነት የራቀ እና ሁሉም የሚገነዘበው ግልጽ እውነታ መሆኑን ባለማወቃቸው እናዝናለን፡፡

  ማኅበረ ቅዱሳን ምንም ስውር ዓላማ የለውም፤ ከማንኛውም የፖለቲካ አስተሳሰብ የጸዳና በቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ በተሰጠው መተዳደሪያ ደንብና መመሪያን ሳያዛንፍ እየሠራ ያለ፤ በተሰጠውም መተዳደሪያ ደንብና ሓላፊነት መሠረት ከአባላቱና ከበጎ አድራጊ ምእመናን የሰበሰበውን ገንዘብ ገቢና ወጪ እያሰላ በውስጥ ኦዲተሮችም እያስመረመረ በመሥራት ተጨባጭ ለውጥ ያመጣ ማኅበር እንጂ በወሬ የሚኖር አይደለም፡፡ ይሔንን አሠራሩንም ቀርቦ ማየት ይቻላል፡፡ አባላቱም በገንዘባቸው፣ በዕውቀታቸው በጉልበታቸውና በመላ ሕይወታቸው ቤተ ክርስቲያንን የሚያገለግሉ እንጂ እንደ መናፍቃኑ ተላላኪዎች ለሆዳቸው ያደሩ፣ ሆዳቸው አምላካቸው የሆነባቸው እዚህም እዚያም ደሞዝ የሚቀበሉ አይደሉም፡፡

  ማንኛውም አካል እንዲያውቅልን የምንፈልገው ሐቅ ማኅበረ ቅዱሳን ቅዱስ ሲኖዶስ ለሰጠው ሓላፊነትና አባላቱም ለገቡለት ቃል ኪዳን ሃይማኖታቸው የሚፈቅደውን መስዋዕትነት ለቤተ ክርስቲያን ልዕልናና ክብር ለመክፈል የተዘጋጁ እንጂ በተዛባ አመለካከት ወደ ኋላ የሚያፈገፍጉ አለመሆናቸውን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

  ማኅበረ ቅዱሳን አገልግሎቱ የሚታይ አሠራሩም ግልጽ ነው፡፡ ስለዚህም የመናፍቃኑ ተላላኪዎች መሠረተ ቢስ ውንጀላ ከአገልግሎታችን አንዲት ጋት ወደ ኋላ እንደማይመልሰን እንዲታወቅልን እንፈልጋለን፡፡ ርእይና ተልእኮአችንን ለማሳካት ዛሬም ነገም እንሠራለን፤ ትናንትን ያሻገረን እግዚአብሔር ዛሬንም ያሳልፈናልና፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ስም ስሌለህ ስምህን ወግ ደረሰኝ ብየዋለሁ
   እስከ አሁን ድረስ ብዙ ብዙ ሲወራባችሁ
   ዛሬ ገና አንድ ብላችሁ
   ሀሁ መቁጠር ጀመራችሁ
   ቀጥሉበት እግዚአብሄር ይርዳችሁ
   እኛስ ገምተን ነበር እያላችሁ የሌላችሁ
   መንፈስ በመንፈስ የሆናችሁ ፤ ያረጋችሁ
   ህልምም መስሎን ታዘብናችሁ
   በሆነ ባልሆነው ስማችሁን እየሰማንላችሁ
   አፍረን ነበር ቆጥረን እንደሌላችሁ
   እራሳችሁን ግለጹት ፣ አትሸማቀቁ
   ለጠላትም ለወዳጅም አቋማችሁን አሳውቁ

   ለሚቀበሏችሁም ለማይቀበሏችሁም የራሳችሁን እውነታና ሃቅ ማስረዳትና ማሳወቅ ጥሩ አካሄድ ነውና ቀጥሉበት ፡፡ እውነት እያደረ መጥራቱ ተረት ሳይሆን የማይሻር ሃቅ ይሆናልና ፡፡ ዝምታው ጥርጣሬንና መደናገርን ይጋብዛል ፡፡ ወዳጅንም ያሳፍራል ፡፡
   እስከዛሬ በሀሳቤ ባልደግፋችሁም ፣ ስለእናንተ የማወቅ ዕድሉን ከከፈታችሁትና አቋማችሁንና ዕቅዳችሁን ግልጽ ካደረጋችሁ ያለ ሌላ ድምር ዝም ብዬ መውደድ ፣ ማፍቀር ፣ መሸነፍ ፣ መደገፍም እችላለሁ ፡፡
   እግዚአብሔር ጽናቱን ይስጣችሁ
   ለድል ለማዕረግ ያብቃችሁ

   Delete
  2. በቅድሚያ ይህ መግለጫ መሰል አስተያየት የማኅበሩ ነው ወይስ የአስተያየት ሰጪው? ምን እያደረገ እንዳለ የሚታወቀውን ማኅበረ ቅዱሳንን እንዲህና እንዲያ ነው በማለት ስለማኅበሩ የሌለ ሥዕል ሰጥቶና ማኅበሩን በሌለበት የቅድስና ማማ ላይ ለመስቀል ይህን ያህል መዘብዘብ ራስን ትዝብት ላይ ከሚጥል ያለፈ ፋይዳ የለውም። አስተያየት ሰጪው ስለማኅበሩ መግለጫ ከመስጠት ይልቅ በተጻፈው ጽሑፍ ላይ ተመሥርቶ ማኅበሩ ከአቡነ ጎርጎርዮስ ጋር ስለመተዋወቅ አለመተዋወቁ ሊነግረን በተገባ ነበር። እርሱ ግን ይህን ጉዳይ ፈጽሞ አላነሣውም። ለእኔ ይህ የሚነግረኝ በጸጋ የተጻፈው ጽሑፍ ማኅበሩ ያልጠበቀውና ያላሰበው እንደሆነበት ነው። የተነሡት ሁለቱ ነጥቦች በቂ ናቸው። ማኅበሩና ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ በዘመንም በትምህርትም ፈጽሞ አይተዋወቁም። አስተያየት ሰጪው /ማኅበሩ(?)/ ለዚህ ምላሽ ቢኖራቸው ኖሮ ይነግሩን ነበር። ስለሌላቸው ግን በሰው ፊት ያልተገለጠውን እነርሱ ብቻ ዘወትር እንደ ዳዊት የሚደጋግሙትን የማኅበሩን ግብዝነት የተሞላ ኩሸት ይኳሻሉ።
   በአስተያዩ ውስጥ ማኅበረ ቅዱሳን ጠላት ያፈራው ተሐድሶዎች “ወጣቱን እንደጠፍ ከብት ወደ ማያውቀው የመናፍቃን አዳራሽ የመንዳት ልምዳቸው በመቋረጡና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በመግባት የሚያደርጉት ሥርዓቷን የማፋለስ እንቅስቃሴ፤ እንዲሁም አገልጋዮቿንና ምእመናኖቿን የማስኮብለሉ አካሔድ ማኅበሩ በክትትል በተለያዩ መረጃዎች ስለገለጠባቸው ማኅበረ ቅዱሳንን በጠላትነት” ይመለከቱታል ያለው አስገራሚ ነው፡፡ ለሰዎች ከቤተክርስቲያናቸው መኮብለል ዋና ተጠያቂው ተሐድሶዎች ሳይሆኑ ማኅበረ ቅዱሳን ነው። የእኔ አባል ካልሆነ ሰው በቀር ሌላ ሰው አልይ፣ ሌላ ማኅበር በተለይም ሃይማኖተ አበውን ፈጽሞ አልይ የሚል ስለሆነ ብዙዎች በሐገ ወጥ መንገድ እናት ቤተክርስቲያናቸውን ጥለው ወደ ሌላ ለመፍለስ ተገደዋል። ስለዚህ በራሳቸው መንገድ ከወጡትና ወደሌላ ከሄዱት ይልቅ “በሃይማኖት ፈረሰ” ሰበብ ማኅበረ ቅዱሳን የገፋቸውና ከእናት ቤተክርስቲያናቸው ሳይወዱ በግድ የለያቸው ጥቂቶች አይደሉም። ዛሬ የወንጌልን እውነት በመግለጥ የጎን ውጋት የሆኑበትና የጨለማ ሥራውን በወንጌል እውነት እየገለጡ ያሉት ያለስማቸው ስም ሰጥቶ ያሳደዳቸውና ስልታቸውን ቀይረው በእናት ቤተክርስቲያናቸው ውስጥ ለቤተክርስቲያኗ እውነተኛ ተሐድሶ እየተጉ ያሉ ልጆቿ ናቸው። ዛሬ ነገሩን ማኅበረ ቅዱሳን የሚቆጣጠረው አይደለም።
   ባለፈው መስከረም ግሸን ተገኝተው ስለተሐድሶ ግንዛቤ እናስጨብጣለን ያሉት የማኅበሩ ሰዎች እነ ያረጋልና ዘመድኩን “ተሐድሶ ተሐድሶ ትላላችሁ ለምን ተሐድሶ የተባሉትን አታሳዩንም?” ተብለው ሲጠየቁ፣ “እገሌና እገሌ የሚባል አይደለም የተሐድሶ መንፈስ በቀዳሾቻችን፣ በሰባኪዎቻችን፣ በመዘምራኖቻችን፣ በሰንበት ተማሪዎችችን፣ … ውስጥ ገብቷል” የሚል ምላሽ ነበር የሰጡት። በርግጥም ዛሬ በወንጌሉ እሳት የተቀጣጠሉ ከማኅበረ ቅዱሳን እይታም ሆነ ቁጥጥር ውጪ ናቸው። እንዳሉትም “መንፈሱን” በስለላም ሆነ በሌላ የተለመደ ስልታቸው ሊይዙት አይችሉም። አገልግሎቱ ወደዚህ አቅጣጫ ያደገው ግን ማኅበረ ቅዱሳን ሲያደርግ በቆየው ግፊት ነው። ዛሬ እንደ ቀድሞው ስላይደለ ማኅበረ ቅዱሳን በዚያው ስልት መዋጋት አይችልም።
   “ማኅበረ ቅዱሳን ምንም ስውር ዓላማ የለውም፤ ከማንኛውም የፖለቲካ አስተሳሰብ የጸዳና በቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ በተሰጠው መተዳደሪያ ደንብና መመሪያን ሳያዛንፍ እየሠራ ያለ፤ በተሰጠውም መተዳደሪያ ደንብና ሓላፊነት መሠረት ከአባላቱና ከበጎ አድራጊ ምእመናን የሰበሰበውን ገንዘብ ገቢና ወጪ እያሰላ በውስጥ ኦዲተሮችም እያስመረመረ በመሥራት ተጨባጭ ለውጥ ያመጣ ማኅበር እንጂ በወሬ የሚኖር አይደለም፡፡ ይሔንን አሠራሩንም ቀርቦ ማየት ይቻላል፡፡” እዚህ ውስጥ ምን እውነት አለ? ድብቅ የፖለቲካ አጀንዳ እንዳለው ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ የወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል። የሰበሰበውን ገንዘብ ገቢና ወጪውን ለማደራጃ መምሪያው ለማሳወቅ ፍላጎቱም ዝግጁነቱም እንደሌለው አስመስክሯል። ጠቅላይ ቤተክህነት የጻፈለትን ደብዳቤም ውድቅ ማድረጉና በእንቢታው መጽናቱ ከዚህ ቀደም ተገልጾአል። ስለዚህ ምናለ እውነታውን ብንነጋገር።
   በመጨረሻም በወጣው ጽሑፍ ላይ የማኅበሩ ምላሽ ምን ይሆን የሚለውን ማወቅ ከሚናፍቁት አንዱ ነኝ። እውን ማኅበሩ ከአቡነ ጎርጎርዮስ ጋር በትምህርት ይተዋወቃል ወይስ ከዚያ በተቃራኒው ነው? እስኪ የማኅበሩ ሰዎች ከመጽሐፋቸው የተወሰዱትን አስተምህሮቶች እንዴት ያዩአቸዋል? ይቀበሏቸዋል ወይስ ያወግዟቸዋል? እንዲህ ከሆነ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስም ወደፊት ተሐድሶ ናቸው ይባሉ ይሆን?

   Delete
  3. You could have atleast edit the content and change some dates. This has no relation with the issue at hand, remember the fact is you and the father you are claiming founder of your evil organization are harambana kobo.

   Delete
  4. Sorry for the editing: pls read the hereunder for the history of Mahiber Kidusan. I hope you will return to your rational thinking... pls avoid hate from your heart. The only person that will hurt is you and only you....

   Delete
  5. "በቅድሚያ ይህ መግለጫ መሰል አስተያየት የማኅበሩ ነው ወይስ የአስተያየት ሰጪው?"
   For anonymous @Apr 29, 2012 11:07 PM - Sorry for the confusion. The source of this article is:

   http://eotc-mkidusan.org/site/index.php?option=com_content&view=article&id=26:----&catid=2:-&Itemid=2

   Delete
 2. This comment has been removed by a blog administrator.

  ReplyDelete
  Replies
  1. This is talk of yegereditu(Agar) Lij. Accept Jesus Christ as your Lord and Saviour today, you will be Yechewawitu Lij, you will get eternal life, your koshasha andebet will be circamusized and you will stat speaking chewa chewa words.

   Delete
 3. በወንድሜ ጸጋ ታደለ ሃሳብ እስማማለሁ፡፡ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ‹‹ማህበረ ቅዱሳን›› ሊያቀርባቸው እንደሚሻው ሳይሆኑ በእጀጉ የተለዩ አባት እንደሆኑ እኔ ራሴ ምስክር ነኝ፡፡ ብፁዕነታቸው በሥነ-መለኮት አስተምህሮ ጠለቅ ያለ ግንዛቤ እንደ ነበራቸውና የቤተክርስቲያን አሠራርን በማሻሻልና በማዘመን ትውልዱን ለማነÒ ቆርጠው የተነሱ አባት ነበሩ፡፡ በግል ጥረታቸው ባስጀመሩት የዝዋይ ካህናት ማሠልጠኛ ገዳም ገብቼ የመማር እድሉንም ስላገኘኹ ይህንን ጉዳይ እኔው ራሴ አውቃለኹኝ፡፡ የቤተክርስቲያናችን አገልጋዮች ያላቸው የስብከተ ወንጌል አቀራረብ እንዲሻሻልና በይዘቱም መÎሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያለው እንዲሆን በብርቱ ይመክሩን ነበር፡፡ በተለይም በስብከተ ወንጌል ትምህርት ውስጥ ሁል ግዜ የስብከት አቀራረባችንን ስለ ክርስቶስና ስራው በመናገር እንድንፈÎም የሚሰጡን አÒንªትና ማሳሰቢያ የምትዘነጋ አይደለችም፡፡

  ሆኖም ግን በብፁዕነታቸው እግር ሥር ከተማሩት ውስጥ ቀላል ቁጥር የሌላቸው ካህናት/ወንድሞች ማህበረ ቅዱሳን ‹‹ተሃድሶ›› የሚል ታርጋ እያስለጠፈ ከአፀደ ቤተክርስቲያን እንዲባረሩ ምክንያት ሆኖአል፡፡ ምናልባት አንዳንዶቹ የማህበረ ቅዱሳን መሥራቾች በ ብፁዕ አባታችን ጉባኤዎች ተገኝተው ይሆናል፡፡ ይህ ብቻውን ግን እነሱን የብፁዕ አባታችን የመንፈስ እና የግብር ልጅ አያደርጋቸውም፡፡ ማህበሩ በአሁኑ ግዜ ዋና የተሃድሶ አራማጅ እያለ የሚጠቅሰው ሥዩም ያሚ የተባለው የዩኒቨርሲቲ ምሩቅ ወንድምም ከማናቸውም በላይ የሚያቀርቡትና የሚወዱት ልጃቸው እንደነበር ይታወቃል፡፡

  ስለሆነም ማህበሩ አላስፈላጊና ሕገ-ወጥ የሆነ ዝና ለማግኘትና የብጹዕ አባታችንን ታሪክ ለማበላሸት ከሚያደርገው ሩጫ እንዲገታ ልናሳስበው ይገባል፡፡ ከዚህም አኳያም ጸጋ ታደለ እንዳለው፤ በግዜም፣ በትምህርትም፣ በአላማም ከማይገናኛቸውና ከማያውቃቸው ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ላይ መለጠፉን ያቁም እጁንም ያንሳ እላለኹ!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. lememaruma yihudas ke geta sir temiro neber eko!

   Delete
 4. Brtalign wondimie. MKs are heresiies. Things will be disclosed in their time.

  ReplyDelete
  Replies
  1. KKKKKKKKKKKKKKK ye emyen wede adiyealu! kkkkkkkkkkkkkkkkkk

   Delete
 5. አውነትም ጸጋ!! እንዲህ በምክንያት ነገሮችን በግልጥ አሳይልን እና የእንቧይ ካባቸውን በእውነት ናደው። ዋሻ ሲዋሽ አይኑን በጨው አጥቦ እንደሆነ ከማቅ እንማራለን።

  ReplyDelete
 6. ማኅበረ ቅዱሳን ማን ነው? ምንስ እየሠራ ነው? የተዛባ አመለካከት የማይጋርደው ገሐድ እውነታ
  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሊቃውንት ብራና ዳምጠው፤ ቀለም በጥብጠው፣ ብዕር ቀርጸው በየአብያተ ክርስቲያናቱ የመቃብር ቤቶች ውስጥ በማስተማር ትውልዱ የሀገር መሪ፣ የቤተክርስቲያን አለኝታ፣ የእግዚአብሔር ቅን አገልጋይ እንዲሆን ያበረከቱት አገልግሎት ከዘመን ዘመን እየተሸጋገረ ለትውልድ ሲተላለፍ የኖረና የሚኖር ነው፡፡

  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለሀገራችን ሥልጣኔ በር ከፋች ሆና የኖረች ከመሆኗም በላይ ዛሬ ላለው ዘመናዊ ሥልጣኔም መሠረት የጣለች ባለውለታ ናት፡፡ ቀደምት የቤተክርስቲያን አበው ደከመን፣ ሰለቸን ሳይሉ ዐረፍተ ዘመን እስከገታቸው ድረስ ሲያገለግሉ ኖረው ቤተክርስቲያኒቱ አሁን ከምትገኝበት የዕድገት ደረጃ አድርሰዋታል፡፡

  በዚህ ዘመንም የሚገኙ የቤተክርስቲያኒቱ ልጆች ሁሉ ይህን ከአበው የተማሩትን ሃይማኖትና ሥርዓት ጠብቀውና አስጠብቀው ለሚመጣው ትውልድ የማቆየት ሓላፊነት ያለባቸው መሆኑ ግልጽ ነው፡፡

  በመሆኑም ይሔንን አባቶች ወዛቸውን አንጠፍጥፈው፣ ዐይናቸውን አፍዘው፣ ደማቸውን አፍስሰውና አጥንታቸውን ከስክሰው በሰማዕትነትና በተጋድሎ ያቆዩትን ሃይማኖት ለማስጠበቅና ለቀጣዩም ትውልድ በተመቻቸ ሁኔታ ለማስተላለፍ በእግዚአብሔር ፈቃድ በቅዱስ ሲኖዶስ ሙሉ ድጋፍና ዕውቅና የተመሠረተው ማኅበረ ቅዱሳን በውጪ በአጽራረ ቤተክርስቲያንና በአሕዛብ፣ በውስጥ ዓላማውን ባልተረዱ፣ ዓላማውን ተረድተው የኑፋቄ ትምህርታቸውን እንደልብ በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ ለማስረግ ሌት ተቀን በሚተጉ አንዳንድ ግለሰቦችና ቡድኖች ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ እየተከሰሰ እየተወቀሰና ያለ ስሙ ስም እየተሰጠው ይገኛል፡፡

  እነዚህ በውስጥና በውጭ የሚገኙት የቤተክርስቲያን ጠላቶች ቤተክርስቲያን ላይ በየዘመኑ በሚነሳው ፈተና እየተጠቀሙና በምክንያት እየተሳቡ ለቤተክርስቲያን ወዳጅ መስለው እየቀረቡና እያስቀረቡ ማኅበረ ቅዱሳንን ቢቻላቸው እንዲፈርስ፣ ባይቻላቸው ደግሞ የቤተክርስቲያኒቱን ሥርዓት ለማፍረስ በገንዘብ፣ በቁሳቁስ የሚያስታጥቋቸው መናፍቃን ሴራና ዓላማ እንዳይጋለጥ እና በቤተክርስቲያኒቱ ላይ እንደፈለጋቸው እንዲሆኑ ማኅበሩ አገልግሎቱ ተገድቦ እንዲዋቀር ለማስደረግና ለማድረግ የጥፋት ዘመቻዎችን በመክፈት ላይ ናቸው፡፡

  እነዚህ የቤተክርስቲያን ጠላት ወዳጆች በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ጊዜ በሰጣቸው ጊዜ ሁሉ በመጠቀም ማኅበሩን ለማሳጣትና ለማጥላላት የሚጠቀሙባቸው ስልቶች በርካቶች ናቸው፡፡

  ከብዙ በጥቂቱ ለመጥቀስ ያህል «ማኅበረ ቅዱሳን ሲኖዶስ ከሰጠው ደንብና መመሪያ ውጪ እየሠራ የሚገኝ፣ ፖለቲካዊ ዓላማ ያለውና ገቢና ወጪው የማይታወቅ ማኅብረ» እንደሆነ አድርገው» ሚያናፍሱት አሉባልታ ከብዙ በጥቂቱ የሚጠቀስ ነው፡፡

  ማኅበረ ቅዱሳን ግን ባለፉት 17 ዓመታት እነዚህ የውስጥና የውጪ የቤተክርስቲያን ጠላቶች በየጊዜው ማኅበሩ ላይ የሚያናፍሱትን ወሬ ችላ በማለት ከወሬ ሥራ ይቀድማል በማለት ከቅዱስ ሲኖዶስ የተቀበለውን ዓላማ በዓይን በሚታይ፣ በእጅ በሚዳሰስ መልኩ ሲሠራ ቆይቷል፡፡ ነገር ግን «ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል» እንዲሉ ማኅበረ ቅዱሳን ማን ነው? እንዴትስ ተመሠረተ? ዓላማውስ ምንድን ነው? ቅዱስ ሲኖዶስ የሰጠውን ሓላፊነት እንዴት እየተወጣ ነው? ለ17 ዓመታትስ ምን ሠራ? የሚሉትን ጥያቄዎት በስፋት ማቅረቡ አስፈላጊ መሆኑን ለምእመናን መግለጽ ግድ ብሎናል፡፡


  ማኅበረ ቅዱሳን ማን ነው? እንዴትስ ተመሠረተ?
  ማኅበረ ቅዱሳን ማን ነው? እንዴትስ ተመሠረተ የሚለውን ጥያቄ ከመመለሳችን በፊት አጽራረ ቤተክርስቲያንና ዓላማቸውን ለማስፈጸም የሚንቀሳቀሱት ተላላኪዎቻቸው የውስጥ ዐርበኞች ማኅበረ ቅዱሳንን በሰው ውስጥ የጥላቻ መንፈስ እንዲያድር ከሚጣጣሩበት መንገድ አንዱ ማኅበሩ የሚጠራበትን ስያሜውን በማዛባት ነው የሚጀምሩት፡፡ ከዚህ አንጻር ማኅበረ ቅዱሳን ሲባል ምን ማለት ነው? የሚለውን ነገር ማብራራት ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህ ስያሜው ላይ አጭር ትንታኔ በመስጠት ወደ ማንነቱና አመሠራረቱ እንለፍ፡፡


  የማኅበሩ ስያሜ
  አንዳንድ ሰዎች ስያሜውም ግራ ያጋባቸዋል፡፡ ከላይ እንደጠቀስነው አባላቱ ለራሳቸው ያወጡት አስመስለው የሚነግሯቸው ሰዎች አሉና የዋሀኑ ግራ ቢጋቡ አያስደንቅም፡፡ ነገር ግን የማኅበሩ ስያሜ እኩያኑ ማኅበሩን ለማጥላላት ከሚጠቀሙት ፕሮ­ጋንዳ በእጅጉ የተለየ ነው፡፡ ማኅበረ ሚካኤል «የሚካኤሎች ስብስብ»፣ ማኅበረ ማርያምም «የማርያሞች ስብስብ» ካልሆነ /እንዳልሆነ/ ማኅበረ ቅዱሳንም «የቅዱሳን ሰብስብ» አይደለም፣ ሊሆን አይችልም፤ ወይም ማኅበረ ጊዮርጊስን የመሠረቱ ሰዎች ራሳቸውን «ጊዮርጊሶች»ነን እንደማይሉት፤ እንዳልሆኑትም፣ ማኅበረ ቅዱሳንም ቅዱሳን ነን የሚሉ ሰዎች ስብስብ አይደለም፡፡ ይልቁንም ማኅበረ ማካኤል የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት፣ ተራዳኢነት የሚታሰብበት ማኅበር እንደሆነው ሁሉ ማኅበረ ቅዱሳንም የቤተክርስቲያኒቱን ትምህርተ ሃይማኖትና ሥርዐት ከመጠበቅና ከማስተማር በተጨማሪ በቤተ ክርስቲያኒቱ ትምህርተ ሃይማኖት መሠረት የቅዱሳን ጻድቃንና ሰማዕታት እንዲሁም የቅዱሳን መላእክት ክብ ራቸው፤ ገድላቸውና ትሩፋታቸው፣ አማላጅነታቸውና በረከታቸው፤ በሰፊው እንዲታወቅና ትውልዱም የዚህ ተጠቃሚ እንዲሆን ትምህርት የሚሰጡበት ማኅበር ነው፡፡ ምእመናን በነዚህ ቅዱሳን አማላጅነትና ረድኤት እየታገዙ ለመንግሥተ ሰማያት እንዲበቁ ማድረግም ቀዳሚ ተግባሩ ነው፡፡

  ከዚህ የተነሣ የእነዚያ ብዙ ማኅበራት ኅብረት የሆነው ማኅበር የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ ጻድቃን ሰማዕታትና የቅዱሳን መላእከት ሁሉ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ማኅበረ ቅዱሳን ተባለ፡፡

  ReplyDelete
 7. 'ማኅበረ ቅዱሳን እንዴትስ ተመሠረተ?
  ዘ'መኑ የኮምዩኒዝም ርዕዮተ ዓለምና አስተሳሰብ የሰፈነበት፤ ስመ እግዚአብሔርን መጥራት አስቸጋሪ የሆነበትና ወ'ደ ቤተ እግዚአብሔር መሔድ እንደ ኋላቀርነት የሚቆጠርበት ዘመን ነበር 1977 ዓ.ም፡፡
  '
  በ'ተለይም በየከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ /ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች/ በሚገኙ ተማሪዎች ዘንድ ቃለ እግ'ዚአብሔርን በግልጽ መነጋገርም ሆነ መሰማት የማይታሰብበት ወቅት ነው፡፡
  '
  ቀ'ደም ባሉት ጊዜያት በተለይም በንጉሠ ነገሥት ዐፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት በዩኒቨርሲቲና ኮሌጆች እን'ዲያስተምሩ ከምዕራባውያኑ ሀገሮች መጥተው የነበሩ ሚሲዮናውያን የኑፋቄ ትምህርታቸውን ያሠራጩ የነበ'ረውም በእነዚሁ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ነው፡፡
  '
  በ'ዚህ ሁኔታ ትውልዱ በየአቅጣጫው በሚሲዮናውያኑ የኑፋቄ ትምህርት እንዲሁም በኮምዩኒዝም ርዕተ ዓለ'ምና አስተሳሰብ እየተነጠቀ ከኦርቶዶከሳዊት ተዋሕዶ እምነት የኮበለለበት ከቤተክርስቲያን የራቀበት ዘመን ነበር'፡፡
  '
  በ'ዚህ ጊዜ ነው፤ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስድስት ኪሎ ዋናው ግቢ ከፍተኛ ትምህርታቸውን ይከታተሉ የነ'በሩ አምስት ወጣቶች ፈቃደ እግዚአብሔር ሆኖ በቅዱስ ገብርኤል ስም ተሰባስበው ጽዋ መጠጣት የጀ'መሩት፡፡ ይህ መንፈሳዊ እንቅስቀሴ በዚሁ ተወስኖ አልቀረም፡፡ በየሳምንቱ እሑድ በመንበረ ­ፓትርያርክ ቅድ'ስተ ቅዱሳን ማርያም ቤተክርስቲያን ግቢ በመጠለያ ሥር እየተሰባሰቡ በተደራጀ መልክ ባይሆንም መንፈ'ሳዊ ትምህርት ይማሩ ጀመር፡፡ ከዚያም በምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ተምሮ ማስተማር ሰንበት ትምህር'ት ቤት አዳራሽ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን መንፈሳዊ ትምህርት መማር ቀጠሉ፡፡
  '
  እ'ንዲህ የተጀመረው መንፈሳዊ እንቅስቃሴ በሌሎች ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሚገኙ የቤተክርስቲያን ልጆ'ች ዘንድ የተዳረሰበት አጋጣሚና ሁኔታ የተፈጠረው ደግሞ በዚሁ በ1977 ዓ.ም ነው፡፡ በወቅቱ በነበ'ረው የመንግሥት ሠፈራ ፕሮግራም በሀገሪቱ ውስጥ ያሉት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች በሙሉ በመን'ደር ምሥረታና መልሶ ማቋቋም ዘመቻ ወደ ጋምቤላ፣ መተከል እና ፓ­ዌ እንዲዘምቱ ተደረገ፡፡ በዘመቻው ወቅት 'ከተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እየመጡ የተገናኙት የቤተክርስቲያን ልጆች ቃለ እግዚአብሔርን በመማር'፣ በማኅበር ጸሎት በማድረግ እና ስለቤተክርስቲያን ጉዳይ በመወያየት ጊዜውን ተጠቀሙበት፡፡
  '
  በ'ዚህ ዓይነት የተጀመረው እንቅስቃሴ ከዘመቻው መልስ በ1978 ዓ.ም ተጠናከረ፡፡ ውስን የነበረው የተ'ማሪዎች ቁጥርም ጨመረ፡፡ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስድስት ኪሎ፣ አምስት ኪሎ፣ አራት ኪሎ ግቢዎች እስከ አርባ የሚደርሱ ተማሪዎች በምስካዬ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ተምሮ ማስተማር ማኅበር አዳራሽ እየተገኙ ትምህርተ ወንጌል ይማሩ ነበር፡፡ የተማሪዎቹን ዓላማና ጥረት የተገነዘቡ አባቶች መምህራነ ወንጌልም በቅርብ ሆነው እየተከታተሉ ሲያስተምሯቸው ቆይተዋል፡፡

  በቀጣዩ ዓመት ከ1979 ዓ.ም እስከ 1980 ዓ.ም ድረስ ተማሪዎቹ በተምሮ ማስተማር ማኅበር አደራሽ ከሚከታተሉት መንፈሳዊ ትምህርት መርሐ ግብር ጋር ይህ መንፈሳዊ እን ቅስቃሴ ተጠናክሮ በስፋት የሚቀጥልበትን መንገድ ይወያዩ ነበር፡፡ በወቅቱ ትኩረት ተሰጥቶት ውይይት ይደረግበት የነበረው ዐቢይ ጉዳይ ከመካከላቸው ሰባኪ ወንጌል ማፍራት ነበር፡፡ ለዚህም በተለይ ወደ ዩኒቨርሲቲ ከመግባታቸው በፊት በቤተክርስቲያን አገልግሎት እየተሳተፉ በሰንበት ትምህርት ቤት ያደጉና በመጠኑም ቢሆን ልምድ ያላቸውን ተማሪዎች እንዲያስተምሩ ማድረግ አንድ መፍትሔ ነው፡፡ ለዘለቄታው ግን ከተማሪዎቹ መካከል በወቅቱ ሸዋ ሀገረ ስብከት ዝዋይ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የካህናት ማሠልጠኛ ገብተው እንዲሠለጥኑ ማድረግ የታመነበት መሠረታዊ ጉዳይ ሆነ፡፡

  ይህንኑ ሐሳብ ተግባራዊ ለማድረግ፤ አስቀድመው በዝዋይ ካህናት ማሠልጠኛ ገብተው ስለስብከተ ወንጌል ሥልጠና የወሰዱ፤ በወቅቱ የሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ የዝዋይ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም እና የካህናት ማሠልጠኛው የበላይ ጠባቂ ከነበሩት ከብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ጋር ይቀራረቡ በነበሩ ተማሪዎች አማካኝነት ግንኙነት ተደረገ፡፡

  ReplyDelete
 8. እንዲሁም በ1980 ዓ.ም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አራት ኪሎ ግቢ ትምህርታቸውን ሊከታተሉ ከገቡት መካከል እስከ ሃምሣ የሚደርሱ ተማሪዎች በመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብር ኤል ገዳም ዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት ተሰብስበው ይማሩ ጀመር፡፡ በዚሁ ዓመት በኮተቤ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ የሚማሩ ተማሪዎችም ተመሳሳይ መንፈሳዊ መርሐ ግብር ጀምረው ነበር፡፡

  በዩኒቨርሲቲ መደበኛ ትምህርታቸውን አጠናቀው በ1980 ዓ.ም ከተመረቁት ተማሪዎች ውስጥ በግቢ ቆይታቸው በቤተክርስቲያን ተሰባስበው መንፈሳዊ ትምህርት ሲማሩ የነበሩት የቤተክርስቲያን ልጆችም ለመጀመሪያ ጊዜ ተመረቁ፡፡ የምረቃው መርሐ ግብር የተካኼደው በምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ተምሮ ማስተማር ማኅበር አዳራሽ ነው፡፡ በበዓሉ ላይ ከብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮሰ ካልዕ ጋር ሌሎችም ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ተገኝተው፤ ተመራቂዎቹ ተማሪዎች ለቤተክርስቲያን አገልግሎት እንዲተጉ አስተምረው ባርከው መርቀዋል፡፡

  ከብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ጋር በተደረገው ግንኙነት መሠረት በዚሁ ዓመት ከተመረቁት መካከል ዐሥራ ሁለት ተመራቂ የቤተክርስቲያን ልጆች በዝዋይ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ካህናት ማሠልጠኛ ገብተው በክረምቱ ወራት፤ ትምህርተ ሃይማኖት፣ ሥርዓተ እምነት፣ የቤተክርስቲያን ታሪክ፣ ትውፊት እንዲሁም የስብከት ዘዴ ሲማሩ ከረሙ፡፡ ሥልጠናውን የተከታተሉት ተማሪዎች ተመርቀው ከገዳሙ ሲሔዱ፤ ብፁዕ አቡነ ጎርጎር ዮሰ ካልዕ፤ «ከዚህ ስትወጡ ተበትናችሁ እንዳትቀሩ አደራ፤ ስለ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎታችሁ እየተገናኛችሁ መወያያ ይሆናችሁ ዘንድ መሰባሰቢያ አብጁ» በማለት፤ ተመራቂዎቹ በጽዋ ማኅበር ስም በመሰባሰብ፣ በሚሔዱበት ቦታ ሁሉ ስብከተ ወንጌልን እንዲያስፋፉ፣ በየዓመቱም በዝዋይ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም እየተገናኙ ስለ ዓመቱ የአገልግሎት ቆይታቸው ሪፖርት እንዲያቀርቡና እንዲወያዩ አሳስበው አሰናበቷቸው፡፡

  ተመራቂዎቹ የቤተክርስቲያን ልጆች የብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕን አባታዊ ምክርና መመሪያ አልዘነጉም፡፡ ወደ አዲስ አበባ እንደተመለሱ «ማኅበረ ማርያም» በሚል ስያሜ የጽዋ ማኅበር መሠረቱ፡፡ በአዲስ አበባና በዙሪያው በሚገኙ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት በዓውደ ምሕረትና ሌሎች መርሐ ግብሮች ቃለ እግዚአብሔርን እያስተማሩ በየወሩ እየተገናኙ ስለአገልግሎታቸው ይወያዩ ነበር፡፡ በዓመቱ መጨረሻም በዝዋይ ተገኝተው ሪፖርት አድርገዋል፡፡ በ1981 ዓ.ም ክረምት ለሁለተኛ ዙር ሥልጠና በምስካዬ ኅዙናን መድኃኔዓለም ተምሮ ማስተማር ማኅበር እና በግቢ ገብርኤል ዓምደ ሃይማኖት አዳራሾች ይማሩ ከነበሩት መካከል ዐሥራ ሁለት ተማሪዎች ተወክለው በዝዋይ ካህናት ማሠልጠኛ በአቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ አማካኝነት ሥልጠና ተሰጠቷቸዋል፡፡

  በዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች መንፈ ሳዊ እንቅስቃሴው እየተጠናከረ ቀጥሎ በተለይም በ1982 ዓ.ም በብዙ ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች ተዳረሰ፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተለያዩ ፋኩልቲዎች፤ በጥቁር አንበሳ ሕክምና ፋኩልቲ፣ በልደታ ሕንፃ ኮሌጅ፣ በደ ብረ ዘይት እንስሳት ሕክምና ፋኩልቲ እንዲሁም በጅማ ጤና ሳይንስ፣ በዓለ ማያ ዩኒቨርሲቲ፣ በወቅቱ በአሥመራ ዩኒቨርሲቲ ወዘተ ተስፋፋ፡፡ በዓመቱ የክረምት ወራት ከየዩኒቨርሲቲ እና ኮሌጆቹ የተውጣጡ አርባ አምስት ተማሪዎች ዝዋይ ካህናት ማሠልጠኛ ገብተው ሥልጠና ወስደዋል፡፡ በሥል ጠናው በአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት ከሚገኙ ሰንበት ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ አርባ የሚደርሱ ተማሪዎችም ተሳትፈዋል፡፡ በዚህ ሥልጠና ወቅት ነበር ባልታሰበ ሁኔታ ታላቅ ኃዘን የደረሰው፤ ብፁዕ አቡነ ጎርጎር ዮስ ካልዕ በድንገተኛ የመኪና አደጋ ነዐረፉ፡፡

  በ1983 ዓ.ም በወቅቱ በነበረው መንግሥት በሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚማሩ ተማሪዎች በሙሉ ወታደራዊ ሥልጠና እንዲወስዱ ሲታዘዝ፤ በሀገሪቱ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲ፣ ኮሌጆችና ተቋማት የሚማሩ አሥራ አንድ ሺሕ ያህል ተማሪዎች በብላቴ አየር ወለድ ማሠልጠኛ እንዲገቡ ተደረገ፡፡ ፈቃደ እግዚአብሔር ሆኖ በዩኒቨርሲቲና ኮሌጆቹ ግቢዎች ተጀምሮ ቀስ በቀስ የተስፋፋው መንፈሳዊ እንቅስቃሴም የበለጠ የሰፋበትና የተጠናከረበት ጊዜ ሆነ፡፡ ተማሪዎቹ ቀን ከሚሰጣቸው ወታደራዊ ሥልጠና መልስ ማታ ማታ እየተገናኙ መንፈሳዊ ትምህርት መማር በጋራ መጸለይ ጀመሩ፡፡ መንፈሳዊ ትምህርቱና ጸሎቱ በኅብረት የሚካኼደው በወታደራዊ ማሠልጠኛ ካምፑ በሚገኝ በሌላ አገልግሎት ያልተያዘ አዳራሽ /ኬስፖን/ ውስጥ ነበር፡፡ ትም ህርቱ ከዚህ ቀደም በዝዋይ ካህናት ማሠልጠኛ ገብተው በሠለጠኑ እና ሌሎችም በቤተክርስቲያን ትምህርትና አገልግሎት በቆዩ ተማሪዎች እየተሰጠ በየቀኑ ምሽት መርሐ ግብሩ ሳይታጎል ለሁለት ወራት ቀጥሏል፡፡ በዚህ ጉባኤ እስከ አምስት መቶ የሚደርሱ ተማሪዎች ያለማቋረጥ ይከታተሉ ነበር፡፡

  በወቅቱ በብላቴ አየር ወለድ ማሠልጠኛ ካምፕ ለወታደራዊ ሥልጠና የገቡት ተማሪዎች ማታ ማታ እየተ ሰበሰቡ በአንድነት ከሚያደርጉት ጸሎት እና ከሚማሩት የቤተክርስቲያን ትምህርት በተጨማሪ፤ በአካባቢው ወደሚገኘው ብላቴ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን እየተደበቁም እያስፈቀዱም በመሔድ ምስጢራተ ቤተክርስቲያንን ይሳተፉ ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታ ከተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተሰባሰቡት ተማሪዎች ኅብ ረት እየጠነከረ መንፈሳዊ እንቅስቃሴው እየሰፋ መጣ፡፡ እነዚህ የቤተክርስቲያን ልጆች በወታደራዊ ማሠልጠኛ ካምፕ በነበሩበት ጊዜ የ1983 ዓ.ም የእመቤታችንን የልደት በዓል /ግንቦት ልደታ/ ለጸሎትና ለመንፈሳዊው ትምህርት በሚሰበሰቡበት አዳራሽ በደመቀ ሁኔታ አክብረዋል፡፡

  በብላቴ አየር ወለድ ማሠልጠኛ ካምፕ የነበረው የተማሪዎቹ ወታደራዊ ሥልጠና የሁለት ወር ቆይታ በመን ግሥት ለውጥ ምክንያት ሊበተን ግድ ሲሆን፤ ተማሪዎቹ በወታደራዊ ካምፑ ቆይታቸው የነበረው መንፈሳዊ እንቅስቃሴና ኅብረታቸው ዕጣ ፈንታ አሳሰባቸው፡፡ ይህ መንፈሳዊ አንድነት እንዴት መቀጠል እንዳለበት ተነጋገሩ፡፡ ከብዙ ውይይት በኋላም ፈቃደ እግዚአብሔር ሆኖ በየዩኒቨርሲቲና ኮሌጆቻቸው ሲመለሱ በቅዱስ ሚካኤል ስም ተሰባስበው ቤተክርስቲያንን ለማገልገል በመስማማት ቃል ገብተው ተለያዩ፡፡

  በዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ዕረፍት ዓመታዊ መታሰቢያ ላይ የተገኙ ደቀመዛሙርትና መምህራን ነሐምሌ 22 ቀን 1983 ዓ.ም፤ በወቅቱ የሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ፣ የገዳሙና የካህናት ማሠልጠኛው የበላይ ጠባቂ በነበሩበት በብፁዕ ዶ/ር አቡነ ገብርኤል ሰብሳቢነት ጉባኤ ተደርጎ ነበር፡፡ በጉባኤው ላይ «በብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ተምራችሁ በማኅበረ ማርያም የታቀፋችሁ፣ በየቦታው ያላችሁ፣ በገዳሙም የምትኖሩ መነኮሳት እንዳትበታተኑ በአባታችን ስም ማኅበር አቋቁሙ» በማለት ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ሐሳብ አቀረቡ፡፡ በሐሳቡ ላይ ውይይት ከተደረገ በኋላ ለጊዜው «የዝዋይ ደቀመዛሙርትና መምህራን ማኅበር» በሚል ስያሜ እንዲጠራ ተወስኖ ማኅበር ተመሠረተ፡፡

  ReplyDelete
 9. ከዚህ ቀደም በ1981 ዓ.ም በምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም በተምሮ ማስተማር ማኅበር እና በመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት የሚማሩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተማሪዎች ጉባኤ አንድነት በመፍጠር የተጠናከረ እንቅስቃሴ ባያደርግም «ማኅበረ እስጢፋኖስ» የሚባል ማኅበር መሥርተው ነበር፡፡ ከዚያ በኋላም ቢሆን እንቅስቃሴአቸው የተጠናከረ ባይሆንም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሕክምና ፋኩልቲ ተማሪዎች «ማኅበረ ሥላሴ» በሚል ስያሜ፤ በሌሎችም ፋኩልቲዎችና ኮሌጆች ግቢዎች የሚገኙ ተማሪዎች በተለያዩ ቅዱሳን ስም በሰየሟቸው ጽዋ ማኅበራት ተሰባስበው ነበር፡፡

  በጥር ወር 1984 ዓ.ም በመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት አዳራሽ የመጀመሪያውንም የመጨረሻውንም ጠቅላላ ጉባኤውን ያደረገው «ማኅበረ ሚካኤል» የማኅበሩን መተዳደሪያ ደንብ አጽድቆ አመራሩንም መርጧል፡፡ ሆኖም በቅዱሳኑ ስም ማኅበር መሥርተው የተሰባሰቡት አባላት፤ «ዓላማቸው፣ አገልግሎታቸውም ሆነ ታሪካቸው አንድ ነው፡፡ ለምን አንድ ስያሜ ይዘው በአንድነት አይንቀሳቀሱም?» የሚል ሐሳብ በውስጣቸው እየተነሣ በተለያዩ አጋጣሚዎች በጉዳዩ ሲወያዩበት ቆይቷል፡፡

  በዝዋይ ለተመሠረተው ማኅበር ስያሜ ለመስጠት አዲስ አበባ በብፁዕ አቡነ ገብርኤል ቤት በዚሁ ዓመት በየካቲትና መጋቢት ወራት በተካኼደው ስብሰባ ላይ ሐሳቡ ቀርቦ ውይይት ተደረገበት፡፡ በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ ገብርኤል «ሁላችሁም የያዛችሁት አገልግሎት የቅዱሳን ክብር የሚገለጽበት ነው፡፡ ስለዚህ የማኅበራችሁም ስም 'ማኅበረ ቅዱሳን' ይባል፡፡» በማለት ባቀረቡት ሐሳብ መሠረት፤ የ«ማኅበረ ማርያም»፣ «ማኅበረ ሚካኤል» እና «የዝዋይ ደቀመዛሙርትና መምህራን ማኅበር» ተዋሕደው የሁሉም ማኅበራት የጋራ የሆነው ማኅበረ ቅዱሳን ተመሠረተ፡፡

  አባላቱም መንፈሳዊ አገልግሎታቸው የቅድስት ቤተክርስቲያንን ሥርዓትና መዋቅር ጠብቆ በቤተክርስቲያን አስተዳደር ዕውቅና ማግኘት እንዳለበት አምነው፤ «በጠቅላይ ቤትክህነት በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር ሆነን እናገልግል» በማለት መተዳደሪያ ደንባቸውን ይዘው ወደ መምሪያው ጽ/ቤት ቀረቡ፡፡ በዚህ ዓይነት ማኅበረ ቅዱሳን ለመጀመሪያ ጊዜ በቤተክርስቲያኒቷ መዋቅር ዕውቅና አግኝቶ ግንቦት 2 ቀን 1982 ዓ.ም በጠቅላይ ቤተክህነት በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር መደራጀቱ ይፋ ሆነ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Source: http://eotc-mkidusan.org/site/index.php?option=com_content&view=article&id=47:-----&catid=2:-&Itemid=2

   Delete
 10. lemehonu Aba Selama fotachewen Kelay Yeletefachew abatoche gar Beteleyem Ke Aba Selama Ke Aba Gorgorios Gar Mine Yagenagnewal? weye Lerase sekoresu .... Bewenu Abune Gorgorios Sele Kedusan Atenageru Belew Yehon? Tadia Lemen YebetekerestiaYan Tarik Tsafu? (Why you focuse on MK ? If you are to teach Bible can you see the percentage you give to that. When you repetedly say about MK I visited their Web site it is concerned only on the teaching .So why you focuse on Mk? Is there no good things about them ?

  ReplyDelete
 11. ማቅ ምን ነካው የተባለው ማቅና አቡነ ጎርጎርዮስ አይተዋወቁም ነው። እርሱ ግን እንደፈሪሳዊው (ሉቃ. 18፡11} የራሱን "ጽድቅ" ያወራል። የሚተዋወቁ ከሆነ ሊያስረዳ ይሞክር አሊያ በብፁዕ አባታችን መነገዱን ያቁም። በተለይ በመጽሐፎቻቸው የተገለጠው ትምህርት በማቅ እይታ ምን ይመስላል? ይቀበለዋል ወይስ አይቀበለውም? መነጋገር ካለብን በዚህ ላይ ነው እንጂ፣ እኔ እንዲህ ያለሁ ጻድቅ ነኝ ማለቱ በዚህ ሰዓት ቀልድ ነው። ስለዚህ ማቆች ሆይ አቋማችሁን ግለጡ፤ ወደሌላ አትሽሹ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. I thkink you are not reading the following paragraphs:

   ከብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ጋር በተደረገው ግንኙነት መሠረት በዚሁ ዓመት ከተመረቁት መካከል ዐሥራ ሁለት ተመራቂ የቤተክርስቲያን ልጆች በዝዋይ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ካህናት ማሠልጠኛ ገብተው በክረምቱ ወራት፤ ትምህርተ ሃይማኖት፣ ሥርዓተ እምነት፣ የቤተክርስቲያን ታሪክ፣ ትውፊት እንዲሁም የስብከት ዘዴ ሲማሩ ከረሙ፡፡ ሥልጠናውን የተከታተሉት ተማሪዎች ተመርቀው ከገዳሙ ሲሔዱ፤ ብፁዕ አቡነ ጎርጎር ዮሰ ካልዕ፤ «ከዚህ ስትወጡ ተበትናችሁ እንዳትቀሩ አደራ፤ ስለ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎታችሁ እየተገናኛችሁ መወያያ ይሆናችሁ ዘንድ መሰባሰቢያ አብጁ» በማለት፤ ተመራቂዎቹ በጽዋ ማኅበር ስም በመሰባሰብ፣ በሚሔዱበት ቦታ ሁሉ ስብከተ ወንጌልን እንዲያስፋፉ፣ በየዓመቱም በዝዋይ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም እየተገናኙ ስለ ዓመቱ የአገልግሎት ቆይታቸው ሪፖርት እንዲያቀርቡና እንዲወያዩ አሳስበው አሰናበቷቸው፡፡

   ተመራቂዎቹ የቤተክርስቲያን ልጆች የብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕን አባታዊ ምክርና መመሪያ አልዘነጉም፡፡ ወደ አዲስ አበባ እንደተመለሱ «ማኅበረ ማርያም» በሚል ስያሜ የጽዋ ማኅበር መሠረቱ፡፡ በአዲስ አበባና በዙሪያው በሚገኙ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት በዓውደ ምሕረትና ሌሎች መርሐ ግብሮች ቃለ እግዚአብሔርን እያስተማሩ በየወሩ እየተገናኙ ስለአገልግሎታቸው ይወያዩ ነበር፡፡ በዓመቱ መጨረሻም በዝዋይ ተገኝተው ሪፖርት አድርገዋል፡፡ በ1981 ዓ.ም ክረምት ለሁለተኛ ዙር ሥልጠና በምስካዬ ኅዙናን መድኃኔዓለም ተምሮ ማስተማር ማኅበር እና በግቢ ገብርኤል ዓምደ ሃይማኖት አዳራሾች ይማሩ ከነበሩት መካከል ዐሥራ ሁለት ተማሪዎች ተወክለው በዝዋይ ካህናት ማሠልጠኛ በአቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ አማካኝነት ሥልጠና ተሰጠቷቸዋል፡፡

   በዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች መንፈ ሳዊ እንቅስቃሴው እየተጠናከረ ቀጥሎ በተለይም በ1982 ዓ.ም በብዙ ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች ተዳረሰ፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተለያዩ ፋኩልቲዎች፤ በጥቁር አንበሳ ሕክምና ፋኩልቲ፣ በልደታ ሕንፃ ኮሌጅ፣ በደ ብረ ዘይት እንስሳት ሕክምና ፋኩልቲ እንዲሁም በጅማ ጤና ሳይንስ፣ በዓለ ማያ ዩኒቨርሲቲ፣ በወቅቱ በአሥመራ ዩኒቨርሲቲ ወዘተ ተስፋፋ፡፡ በዓመቱ የክረምት ወራት ከየዩኒቨርሲቲ እና ኮሌጆቹ የተውጣጡ አርባ አምስት ተማሪዎች ዝዋይ ካህናት ማሠልጠኛ ገብተው ሥልጠና ወስደዋል፡፡ በሥል ጠናው በአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት ከሚገኙ ሰንበት ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ አርባ የሚደርሱ ተማሪዎችም ተሳትፈዋል፡፡ በዚህ ሥልጠና ወቅት ነበር ባልታሰበ ሁኔታ ታላቅ ኃዘን የደረሰው፤ ብፁዕ አቡነ ጎርጎር ዮስ ካልዕ በድንገተኛ የመኪና አደጋ ዐረፉ፡፡

   +++++...

   Pls also read MK bylaw if you want to know the mission and objectives of Mahiber kidusan. It's on thier website. MK has a big impact for the life of our young generation... We always remember those MK preachers how they helps us to known our church teaching. We remember how they life in christianity and deducation for spreading the God's word.

   Anyways, pls stop and think what you are doing... Life short and we should us it properly.

   Delete
 12. Mk is an enemy of Ethiopia and eotc most elements are came from gojam debtera and very rural side of Ethiopia. I am sure if abune Gorgorios in live should be called him Tehadeso. This mafiya killer playing game for on behalf of eotc let start action to attack them we can identified them set mesay netela lebash uniform.

  ReplyDelete
  Replies
  1. I like that. That is true, most of them are
   pretainding to christian by netela. Beteley
   wondoch yemibezut benetela yteshefenu setaset
   negeroch nachew. Also thair act is like a womon (The way they talk, the way they act, and
   look like gay people( gibresedomawiyan). Let God expose them, before poisond inocent people.

   Womens of mk also Galemota, and bale yatu yemender set tirikim engi menem selekrestna yemiyawqut neger yelem. Egziabehere betun yatra. Amen, Amen, Amen.

   Delete
 13. ወንድሜ ዲያቆን ሙሉጌታ ወልደ ገብርኤል፤ እንዳንተ ያሉ ክርስትና የገባቸውና እግዚአብሔር የባረካቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስቲያኖች አንድ አሥር ወገኖች ቢኖሩ እኮ ቤተክርስቲያናችንና እምነታችን እንዴት በምህረት እንደምትጎበኝ እጅግ እምነቴ ፅኑ ነው። መቼም እንዴት አድርጌ ላንተ ያለኝን አድናቆት ለመግለፅ ቃላቶች ያጥሩኛል።
  እንደው ግን በጥቅሉ እግዚአብሔር እስከ መጨረሻው የፀና የክርስቶስ አገልጋይ ያደርግህ ዘንድ የዘወትር ፀሎቴ ነው።

  አላዋቂዎችና ግብዞች ፈሪሳዊያን \ማቅ\ በክርስቲያንና በክርስትና ላይ የሚሠሩትን ተንኮል ከማጋለጥ አትቆጠብ። የሚፈልጉትን ሁሉ በአንተ ላይና አንተን በመሰሉ የተዋህዶ ልጆች ላይ ቢናገሩ ምንም አይሰማህ፣ ያመንከውን እውነትና የቆምክበትን አለት መሠረቱ ፅኑ መሆኑን ታውቃለህና። እንኩአን እኛን ደካማዎችንና ታናናሾችን ይቅርና፤ ለአምላካችን ለጌታችን ለመድሐኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ እንኩአን ያላረፉ የእፉኝት ልጆች ናቸውና።

  አንተ ግን ወንድሜ አይዞህ እግዚአብሔርን ይዘሃልና ፈፅሞ ብርታቱን ይሰጥሃል። እግዚአብሔር ተዋጊ ነው። የምትፅፋቸው ፅሁፎች ሁሉ እጅግ በጣም ጠቃሚና አስተማሪዎች ናቸው። ነቀፋና ስድብ ቢመጣም እንኩአን ከጥፋት ልጆች ከማቅ መሆኑን እወቅ። አሁን አሁንማ ማንነታቸው ስለተነቃባቸው እኔ ወይም እኛ የማህበሩ አይደለንም ግን እንደግፋቸዋለን የሚል ራስን የደበቀ አንጋገር ተጀምሮአል። ገና ገና እንደ ጴጥሮስ ይህ የምትሉትን ማህበር አላውቀውም የሚሉበት ጊዜ ይመጣል። የተመሠረተው፣ የኖረው በክፋት፣ በአመፅ፣ በስውር ሴራ ነውና ለሰይጣንና ለሠራዊቱ በተዘጋጀው እሳት ውስጥ መጣላቸው አይቀርም። ማቅ የአውሬው ምልክት ማህበር በመሆኑ ለክርስቲያኖች ፈተና መሆኑ ግልፅ ነው። ላላወቁትና በጭፍን ለሚከተሉት ማሳወቅና መገለፅ ያስፈልጋል። ሌባን ሌባ ካላሉት ከመስረቁ አያርፍምና።
  በተረፈ ዲ\ሙሉጌታ እግዚአብሔር ዘወትር ከሰይጣን ፈተና ይጠብቅህ ትላለች በክርስቶስ እህትህ።

  ወስብሐት ለእግዚአብሔር።

  ReplyDelete
  Replies
  1. selam menefikua: ye ayit misikir dibit!

   Delete
 14. ክርስቲያን ወንድሙ ሲወድቅ ያዝንል አንጂ አይሳለቅም ዝም ብሎ ወሬ አያራግብም ይጸልያል ስለዚህ ክርስቲያን ከሆናችሁ ጸልዩ ከጸሎት እንጂ ከወሬ ምንም አይገኝም ማ/ቅ መቼም አይወድቅም አትድከሙ

  ReplyDelete
 15. EGEZEABHER YESTEEH WENDEME


  ABASELAMWECH EYLEKESACHU NURU ENGE MEHABERKEDUSANEN YEKIDUS AMELAKACHEN FEKADEEE NWE.

  ReplyDelete
 16. By the MK has no time to respond to your all baseless accusition. Rather it wants to make use to this golden time to do activities that builds the christianity in Ethiopia. And responding to your baseless accussition does not only take precious time unnecessary but also fool's duty. I'm really sorry that you don't who MK is all about. Of course those who wants the truth can follows its works and activities and also its official website: www.eotcmk.org and other sites. And of course those who has doubt can also directly ask the legally placed leaders or any member. The above mentioned article just baseless as usual. It does not give clear truth. shame on you!

  ReplyDelete
 17. Dearest Dn Mulugeta H/Gebriel , editors of Abba Selama Website,
  Greetings to you. I am really proud of your spritual strength and I am wondering which gospel are you reading to get such a wierd spirit of insult and negative energy. Why not you use it to save lives and to serve the church ? I wish you all the best in your spiritual services in the peaceful and free world of truth and democracy. I am saying this , because I can't really capture your theme and intentions. Are you telling us to refute our beliefs thought by the holly father himself ? word by words not by your wierd interpretation ?

  I have no clue of the Mahibere Kidusan or its detais, for that matter you can Go and cook your Mahibere Kidusan and its details add the Pork and fried snake and Frog Pizza you are striving but keep the teaching of the church as it is.

  Regarding the peaceful and holly father Gorgoriyos,
  Better to tell the truth, humbly speaking - the guy who tried to disconnect the ambitions and dreams of this holly father from the activities of Mahibere Kidusan --- please Go and wash your mouth !!! before you talk of sprituality at the first place.

  I wish you all the best - and spirit of unity and purity as per the true teachings of the church.

  See you soon.

  ReplyDelete
  Replies
  1. your essay writing got C-, can you please tell us the essence of your essay? and then rate you again.

   Delete
 18. መቼ ነዉ ከማህበረ ቅዱሳን አራስ የምትወርዱት?እግዚአብሄር ልቦና ይስጣችሁ;ይቅርም ይበላችሁ

  ReplyDelete
 19. የመውጊያውን በትር ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል፣ የገሃነም ደጆች/ ፣ ተሃድሶና መናፍቃን የጻጻሳትን ፎቶ መጠቀም ለምን/ ታምራት ገለታም የቅዱሳንን ስዕላት ለማታላያነት ይጠቀም ነበር፡፡

  ReplyDelete
 20. አቡነ ጎርጎሪዮስን በቅርብ እሚያውቋቸው ነገር ግን እንደ ይሁዳ የቅርብ ሩቅ የሆኑ ሞልተዋል ስዚህ አታስብ
  ዛሬ ብዙ ሊወራ ይችላል ማህበሩ ግን አንተ በማታምንባቸው በቅዱሳኑ ጸሎት ይጠበቃል በርታና ጻፍ አንድ ቀን ግን የምትጽፍበት ይቆማልና ከመ ቆሙ በፊት እራስህን ተመልከት

  ReplyDelete
 21. የተገነዘብኩት

  1 ትልቅ የሃይማኖት ልዩነት በጻድቃን በሰማዕታትና ባማላጅነት ማመንና ያለማመን
  2. አንዳንዴ ደግሞ ይህን ልዩ ነት እንደሌለ በማስመሰል የኢኮኖሚና ያስተዳደር ወይም የፖለቲካ ግጭት ማስመሰል
  3. እንዴ እንዴት ተሃድሶ ያስፈልጋል አንድ ነገር ነው አያስፈልግም ሌላ ነገር ነው፣ግን ችግሩ ግጭት የተፈተረው ሁላችንም ተሃድሶአዊያን እንሁን ሲባል ነው::
  4.የናንተ ከ ፕሮቴስታንት በምን ይለያል?
  5. ብሎጉን በነጻነት ያለ ተጽእኖ ሳነብ እውነት እየመሰለኝ መጥቶ ግን ከማህበረ ቅድሳን ጋር ብቻ ሳይሆን ጸባችሁ የቅድሳንን ምልጃ ከምታስተምር ቤ/ቲያን ጋር ነው

  ReplyDelete
 22. ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ያልሆነ ትምህርት እያስተማራች
  ማኅበረ ቅዱሳን በመኮነን ልትሸፍኑት አትችሉም ኅበረ ቅዱሳን በሚሰሩት ቢገመገሙ ምን አይደለም ነገር ግን የምታስተመሩት ትምህርት ግን ምንም ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ምንም አይወክልም

  ReplyDelete
 23. ክርስቲያን ወንድሙ ሲወድቅ ያዝንል አንጂ አይሳለቅም ዝም ብሎ ወሬ አያራግብም ይጸልያል ስለዚህ ክርስቲያን ከሆናችሁ ጸልዩ ከጸሎት እንጂ ከወሬ ምንም አይገኝም ማ/ቅ መቼም አይወድቅም አትድከሙ

  ReplyDelete
 24. አምላካችን ሲመጣ የትኛችሁን የሚቀበል ይመስላችኋል? ማናችሁንም አባካችሁን ፍቅር ከሁሉም የይበልጣል ፍቅር የለሌለው እግዚአብሔርን አያውቀውም፡፡ 1ኛ ዮሐ 4፡8 ደግሞም ታሪካዊቷን ቤ/ክ የሚጠብቅ ማሕበር ሳይሆን ሙሽራዋ ክርስቶስ ነው፡፡

  ReplyDelete