Monday, April 30, 2012

የጊዮርጊስ በዓል በጦር አምላክ ምትክ የተሰራ በዓል ነው

“ ‘ኦሪስ’ ወይም ‘ማርስ’ የጦር አምላክ ተብሎ ሲመለክ የኖረ ጣኦት ነው በእርሱ ምትክ ዛሬ ቅዱስ ጊዮርጊስን የወታደሮች ጠባቂ ብለው በየአመቱ ያከብራሉ፡፡”
ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ
ገድለ ጊዮርጊስ እንደሚተርከው ጊዮርጊስ በጌታ ስም ያደረገላትን ድንቅ ነገር ተመልክታ አንዲት መበለት “አምላከ ገሊላውያን ተመሲሎ ሰብአ ወረደ እም ሰማይ ወቦአ ውስተ ቤትየ፤ ማለትም - የገሊላውያን አምላክ ሰውን መስሎ ከሰማይ ወረደ ወደ ቤቴም ገባ” በማለት ሰገደችለት። ጊዮርጊስ ግን መልሶ “ተንሥኢ ብእሲቶ አንሰ ኢኮንኩ አምላከ ገሊላውያን አላ ገብሩ ሎቱ - አንቺ ሴት ተነሺ! እኔ የገሊላውያን አምላክ አይደለሁም፤ አገልጋዩ ነኝ እንጂ” (ገድለ ጊዮርጊስ ገጽ 92)

“ይቤ ጊዮርጊስ ኀበ መኑ እኔጽር? ዘእንበለ ኀበ የዋህ ወትሑት ዘየዓቅብ ትእዛዝየ ወያከብር በዓልየ ያዕርፍ ሰላምየ ላዕሌሁ፡፡”

ትርጓሜ፡- “ጊዮርጊስ አለ ወደማን እመለከታለሁ? ሰላሜ በእርሱ ላይ ያርፍ ዘንድ በዓላቴን የሚያከብር ትእዛዜን የሚጠብቅና ትሑትና የዋህ ወደሆነው ካልሆነ በስተቀር፡፡” (የካቲትና የሚያዚያ ጊዮርጊስ ዚቅ)
እንዲህ በእግዚአብሔር መለኮታዊ ሥልጣን ላይ የሚዘባበቱበት ሰዎች አንድ አምላክ ብቻ መኖሩን የሚቀበሉ አይመስልም፡፡ በዚህ ምዕራፍ መግቢያ ላይ ጊዮርጊስ ለመበለቲቱ “እኔ አምላክ አይደለሁም  የአምላክ ባሪያ እንጂ” ማለቱ ተጠቅሶ ነበር፡፡ እዚህ ላይ ግን ሰዎች ጊዮርጊስን በግድ አምላክ ሁን እያሉት ነው፡፡ ለመሆኑ ጊዮርጊስ እንደ አምላክ ሆኖ “ወደ ማን እመለከታለሁ” ብሎ የተናገረው በየትኛው መጽሐፍ ላይ ነው? በእውነት ይህን የተናገረ ጌታ እግዚአብሔር ነው (ኢሳ. 66፥20)።

የሰላም አለቃ ክርስቶስ የሰጠን ሰላም ዓለም ከሚሰጠው የተለየና ከእኛ የማይወሰድ እንደሚሆን ተጽፏል (ዮሐ. 14፥27)። የጊዮርጊስ የሰላም ምንጭም ክርስቶስ ነው፡፡ ነገር ግን ደራሲዎቹ በጊዮርጊስ ስም ሰላም ሊሲጡን የከጀሉት የክርስቶስ ሰላም ስለ ደፈረሰ ነውን? ወይስ ሌላ ምክንያት አላቸው?

በብሉይ ኪዳን ዘመን ለሕዝበ እስራኤል በዓላትንና ሕግን የሠራ፥ እንዲጠብቁትና እንዲያከብሯቸውም ያዘዘ እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ ሌላ ማንም የለም (ዘሌዋ. 23፥1-21፤ ዘጸ. 20፥1-17፤ ዘዳ. 5-1-21)። ታዲያ ሰማዕቱ ጊዮርጊስ አክብሩ ያለው በዓሉና ጠብቁ ያለው ትእዛዙ የትኛው ይሆን?

በብሉይ ኪዳን ይከበሩ የነበሩት በዓላት በአዲስ ኪዳን ይከበሩ የሚል ትእዛዝ የላቸውም፡፡ ስለዚህ ክርስቲያኖችን በአይሁድ ሥርዓት የሚኖር ሰው ተነሥቶ “ለምን በዓላትን አታከብሩም?” ቢል ተቀባይ እንደማይኖረው ተጽፎአል (ቆላ. 2፥16)።

የአዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች በዓል ዘወትር በየዕለቱ ክርስቶስን ማሰብና በፍቅሩ መኖር ነው፡፡ ይህን የተረዳው ደራሲ በብሉይ ኪዳን ሰዎችና በእኛ መካከል ያለውን የበዓል ቀንና ያከባበር ሁኔታውን እንዲህ በማለት ገልጿል፡- “በመንፈቀ ሳብዕ ወርኅ በዓለ መጸለት ይገብሩ ተድላ ንብረቶሙ በገዳም እስራኤል እንዘ ይዜከሩ። ንሕነሰ ክርስቶስሃ ንዜከር ለለአሚሩ”

ትርጓሜው፡- “እስራኤላውያን በሰባተኛው ወር አጋማሽ ላይ በምድር በዳ በደስታ መኖራቸውን እያሰቡ የቂጣ በዓልን ያደርጋሉ፡፡ እኛ ግን ክርስቶስን በየዕለቱ እናስባለን፡፡”(መልአክ ቁርባን)

ዛሬ በቤተ ክርስቲያን ጌታ ታላላቅ ሥራዎችን የሠራባቸው ዕለታት ለምሳሌ፡- የተወለደበት፥ የተጠመቀበት፥ የተሰቀለበት፥ የተነሣበት ... ወዘተ እንዲከብሩ የበዓላት ሥርዓት ተሰርቷል፡፡ ከዚህ ሌላ የቅዱሳን መላእክትና የቅዱሳን ሰዎች በዓላት እንዴት ማክበር እንደተጀመረ እኛን ከደሙ ንጹሕ ያስደረገ በሚመስል ሁኔታ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ መጽሐፋቸው ያስፈሩት አለ፡፡

“ሊቃውንቱ መምህራኑ (የሌሎቹ) የሕዝቡን የረጅም ዘመን ፍቅር ጣዖት ለማስተው ስላቃታቸው በጣዖታቱ ተሠይሞ ይከበር የነበረው ሁሉ በቅዱሳን ስም እየለወጡ ያከብሩታል፡፡ ለምሳሌ በጣዖታዊነት በነበሩበት ጊዜ “ፖሲዶን” የሚባለው ጣዖት የባሕር አምላክ ነበር፡፡ በክርስትና ዘመናቸው ግን ሊቃውንቱ “ኒኮላዎስ” የሚባለውን ቅዱስ “የባህር ጠባቂ” ብለው በየአመቱ ያከብሩታል፡፡ የመርከበኞች በዓል ነው፡፡ “ኦሪስ ” ወይም “ማርስ” የጦር አምላክ ተብሎ ሲመለክ የኖረ ጣኦት ነው በእርሱ ምትክ ዛሬ ቅዱስ ጊዮርጊስን የወታደሮች ጠባቂ ብለው በየአመቱ ያከብራሉ፡፡

“በአጠቃላይ አረማውያን ለእያንዳንዱ ድርጊት (ፍጥረት) አምላክ መድበውለት ስለነበር ዛሬ በቤተ ክርስቲያናቸው የሚከበሩት ቅዱሳን መላእክት ጻድቃን ሰማዕታት ሁሉ የአንዳንድ ነገር ጠባቂዎች እየተባሉ ተሠይመዋል (ገጽ 107)።

ከአረማዊነት የተመለሱትን የአምልኮ ጣዖት ልማዳቸውን ለማስቀረት ባለመቻሉ በ “አልሸሹም ዘወር አሉ” መንገድ የጣዖታቱ በዓላትን በቅዱሳን ሰዎችና መላእክት እንዲተካ በቤተ ክርስቲያናቸው ሥርአት ተሠራ ተባለ፡፡ ታዲያ ወደ ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ይህ ልማድ እውነት መስሎ እንዴትና ለምን ሊገባ ቻለ? ወይስ ደግሞ ጣዖት ያመልኩ እንደነበሩት አረማውያን አልተው ያልነው ምን መጥፎ ልማድ ነበረን? ጉዳዩ በብዙ መንገድ ያጠያይቃል፡፡ ልማደ ጣዖትን ለማስቀረት ስላልተቻለ አረማውያን ለነበሩት የተሠራው ስርዓት በኛ ቤተክርስቲያን እንደ ትክክለኛ ነገር ተቆጥሮ ሕጋዊነትን ማግኘቱና አሳቡ ተስፋፍቶ የወሩ 30 ቀናት በሙሉ በዓላት ሆነውና ቀናት በ30 በመወሰናቸው ምክንያት የበዓል ቀን ያጡትን ስሞች አንዱን በአንደኛው ላይ በመደራረብ እንዲከበር መደረጉ ይገርማል፡፡

የሚያሳዝነው ግን መንፈሳዊ ቅኝ ገዥዎቻችን የነበሩት ግብጻዊያን ቤተ ክርስቲያናችንን የጉድፋቸው መጣያ ማድረጋቸው ነው፡፡

ምንጭ፦ የተቀበረ መክሊት ገጽ 86

19 comments:

 1. አሄሄ ድንቄም ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡

  ReplyDelete
 2. GORGIS KEMECHEWEDI NEWE AMELAKE YEHONEWE?HONE ENDEA?DEMO BELACHEHU BELACHU..ENANETE MENAFEQAN SILTAN SETACHEHUTE ENDEA?

  ReplyDelete
 3. አይ ቴዲ አፍሮ እንዲህ አሳረራችሁ?
  እስከ ዛሬ ያላነሳችሁትን ጊዮርጊስ አስታወሳችሁ፨
  ጌታ ይባርከው ቴዲን:: እናንተ ስትቃጠሉ ኑሩ በቅዱሳን፨

  ReplyDelete
  Replies
  1. ምነው ወንድሜ ማቅ እኮ ዘፈንን አይደግፍም። ለምን ማኅበራችንን ሰድበህ ለሰዳቢ ትጣለህ? የምትጠቅሰው አጣህና የቴዴን ዘፈን መጥቀስህ ኦርቶዶክሳዊነት አይደለም። የእኔ ስጋት ቴዲ ምናልባት ስለጊዮርጊስ ዘፍኖ ከሆነ መዝሙር ይባልልን የሚል ቅስቀሳ እንዳታኪሂድ እፈራለሁ። ደግሞም ወገኛው ማህበራችን ግጥሙን ቢወደው እንኳ ዜማው የዘፈን ነው ማለቱ አይቀርምና እዚህ ሁሉ ጣጣ ውስጥ ገብተህ ባታስገባን መልካም ነው።

   Delete
  2. ዳንኪራ ቤት ውለህ ማደርህን መግለጥህ ጥሩ ነው።ቴዲህን ከነዘፈኑ እዛው አጥብቀህ ያዘው።

   Delete
 4. you can go and ask an Italian historian about st Giorgis. He will tell you more details.
  Zendow minim biawora egnan kekidusan ayileyenim!

  ReplyDelete
 5. ከአረማዊነት የተመለሱትን የአምልኮ ጣዖት ልማዳቸውን ለማስቀረት ባለመቻሉ በ “አልሸሹም ዘወር አሉ” መንገድ የጣዖታቱ በዓላትን በቅዱሳን ሰዎችና መላእክት እንዲተካ በቤተ ክርስቲያናቸው ሥርአት ተሠራ ተባለ፡፡
  Shame on you. you try to compare idol wz angels and saints.
  Please read the whole Bible not only few parts like your protestant friends do and you will find it where it is mentioned why we celebrate saints and angels.
  Now you are again est this next time you are going to tell us we don't need TAbot,we dont Need bete Mekdes ,We don't need Megarega ,we don't need Etan etc etc etc
  Why you try to create confusion by writing in GEaz to look like orthodox tewahedo christian .Just rent adarash put your piano and jump as much as you can please leave us alone.Ebachachehu----------

  ReplyDelete
  Replies
  1. 1. Geez is an Ethiopian language, it is not owned by debteras.
   2. Can you pls tell us where in the Bible or in which Bible for that matter (I heareds MK is authoring its own Bible) we can get a word that mentions a worship day for Giorgis et al;

   Delete
 6. የትኛው የባሳ ይፋል????

  መንፈሳዊ ቅኝ ተገዥነት ወይስ አውሮፓውያን የድሃ አገሮችን ሃብት ለመዝረፍ ብለው ያደረጉት የጉልበት ቅኝ ተገዥነት ወረራ?

  ክብር ለነዚህ አርበኛ አባቶቻችን ይሁንና ሁለተኛው ዓይነት ቅኝ አገዛዝ በምድራችን እንዳይሰለጥን አደዋ ላይ ጉድ ተደርጓል:: የግብጻውያኑ መንፈሳዊ ቅኝ አገዛዝ ግን ጠባሳው እስከ አሁን ድረስ አልጠፋ ብሎ የመስቀሉን ቃል የማዳን ሥራ ጋርዶብን እንደነ ጊዮርጊስ እና መሰሎች ላሉ ሰዎች እንድንሰጥ ተደርገን መከራችንን እናያለን::

  እንደ እኔ ያሁኑ አመልካከት እንደነጋና ናጀሪያና ሕንድ አገሮች በሁለተኛው ዓይነት ቅኝ አገዛዝ ተገዝተን ቢሆን ኖሮ ቢያንስ ከሥጋዊ ማሕይምነት ነጻ እንወጣና
  አእምሮውን እንደሚገባ የሚጠቀም የሰለጠነ ሕዝብ በመሆን የመጣውን ሁሉ መቀበል የማያስችል ማንነት ይኖረን ነበር ብዬ አስባለሁ::

  እስከ አሁን ድረስ እስክንድርያ እናታችን ማርቆስ አባታችን የሚለው ቅዳሴያችን በደም ሥራችን ሳይቀር ገብቶ ስለተጠናውተን:

  1)ጆሮአችን ከጌታ ወንጌል ይልቅ ለነገድለ ጊዮርጊስና ግብጻዊ ነው ተብሎ ለሚገመተው አቦ (ያሁኗ የግብጽ ኮብቲክ ግን እንደዚህ ያለ ሰው አናውቅም የሚል መግለጫ እንዳወጣች ሰምቻለሁ)ክፍት ናቸው::
  2)ዓይኖቻችን በደሙ ዋጋ ወደ ገዛን ጌታ ሳይሆኑ በቅዱሳን መላእክቶችና በአጸደ ሥጋ በሌሉ ቅዱሳን ላይ ያተኮረው::
  3)ብቻውን ሁሉን ቻይ የሆነውን ጌታና አምላክ በቃሉ ላይ ተመስርተን ከማምለክ ይልቅ በአጋንንት አሰራር ጭልጥ ብለን የተውስድነው::
  4)በአጠቃላይ ካለወንጌል ክርስቲያን ሆነን በሥራ ከመባረክ ይልቅ ግብጾች ባሻከሙን የባእላት ብዛት ተታለን ሃብታችንን ሳይቀር እንደሚገባ ሳይሆን ጭራሽ እንዳንጠቀምበት በጦርነት እስከ አሁን ድረስ የሚያስፈራሩን::
  5)የእኛ ክርስትና ዓይነቱ ከየት እንደመጣና እንደተጣብቀብንና የራሳችንን የክርስትና ታሪክ ቆም በለን እንዳናይ የታወርን በመሆን አንዳንድ ወንጌል የገባቸው ብቅ ሲሉ እንደ ማህበረ ቅዱሳን የሚሳደዱት እንዲህ ባለ መንፈሳዊ ድንቁርና ነውና ቆም ብለን እናስብ!!!!

  ሰላም ነኝ

  ReplyDelete
  Replies
  1. እንደ እኔ ያሁኑ አመልካከት እንደነጋና ናጀሪያና ሕንድ አገሮች በሁለተኛው ዓይነት ቅኝ አገዛዝ ተገዝተን ቢሆን ኖሮ ቢያንስ ከሥጋዊ ማሕይምነት ነጻ እንወጣና አእምሮውን እንደሚገባ የሚጠቀም የሰለጠነ ሕዝብ በመሆን የመጣውን ሁሉ መቀበል የማያስችል ማንነት ይኖረን ነበር ብዬ አስባለሁ::
   ለአንድ ቀን ባሪያ ተብዬ ለሰዎች ከመገዛት እኛ በነጻነታችን የተጓዝንበት መንገድ ያኰራናል ፡፡ ነጭ እንዲያመልኩ የተደረጉ ህዝቦችን ስልጣኔ ኬንያ ወረድ ብለሽ ብታይው በራሳችን ታሪክ ትመኪ ነበር ፡፡

   Delete
  2. ሰላም

   አለማወቅሽ ነው እንጂ ክርስትና ኢትዮጵያ የገባው ገና ግብጾች ከመምጣታቸው በፊት ነው። ግብጾች ያመጡልን ጵጵስና እንጂ ወንጌል አይደለም። ታሪክ በትንሹ እንኳ እወቂ እንጂ ከመተቸትሽ በፊት።

   በአንድ ነገር ግን አድንቄሻለሁ። በመንፈስ ቅኝ በመገዛት ባልሽው። እውነት ብለሻል። አንቺና መሰሎችሽ የአመጣችሁትን የምንፍቅና ሃይማኖት መቀበል የቸላችሁት በመንፈስ ቅኝ በመገዝታችሁ ነውና ቅኝ በመገዛት ባለው እሳቤሽ የህሊና ድካምሽን ከመረዳቴም በላይ ሳታውቂው ውስጥሽኝ በመግለጥሽ ምስጋናዬ ይደረስሸ።

   በነገራችን ላይ አንድ ነገር አስታወስሺኝ። ዩኒቨርስቲ ተማሪ እያለሁ ብዙዎቹ ፕሮቴስታንቶች .ቅኝ ባለመገዛታችን ይቆቹ ነበር። አንቺም ከእነዚህ ወገን መሆንሽ ነው ይሆንን?የሚገርመው እዚህ ባለሁበት አውሮፓ በብዙ አጋጣሚ ከፕሮቴስታንት መሪዎችም ሆነ ተከታዮች ጋር የመገናኛቱ አጋጣሚ ነበረኝ። እነሱም የራሳቸውን እምነት እኔም ቤተ ክርስቲያን ያስተማረቺኝን ትምህርት አንነጋጋር ነበር። ምን እንደሚሉኝ ታውቂያለሽ? እምነት ማለት የእናንተ ነው እባካችሁ ጠብቁት ይሉኛል። ከዚህም በተጨማሪ አንዳ አንዶች እንዳውም እንደኛ ባዶ እዳትቀሩ በርቱ ይሉኛል።

   ታዲያ 'ታውረን' ላልሺው እውሩ ማነው? አንቺ በ፲፮ኛው ክፍለ ዘመን በጀርመን ሃገር የተነሳው የሃይሞኖት ንቅናቄ ተከታይ ወይስ የሐዋርያትን እምነት ለ፪ ሺ ዘመናት ይዛ የመጣቺው የኢ. ኦ. ተ. ቤ/ያን?

   የልቅ የመንፈስ እውርነትሽ ይገፈፍ ዘንድ የሰሊሆምን ፀበል ዝም ብለሽ ብትመኘ ይሻልሻል የማታውቂውን የተከደነብሽኝ ወንጌል ልስበክ ከምትዩ።

   Delete
 7. I dont Tewahido said Saints are God! Are you creating a lie? Is the church not remenbering the secrification of His Son daily? (With kidase,Mahelet,...) If you want to make the church wrong it will show u dont now! If u are doing this after knowing it is better for you not to be born. St George has helped we Ethiopians againest the war with Italian this is fact. What can you do? do you want to be a slave of them you can. you are shouting for protestanism! The church will be their till the end of the World and after that With its Saints. "You Saints (hawariyat) will seat at the Chair and decides on the generation" this is what Jesus said !So shall we hear you or The Almighty

  ReplyDelete
 8. Saints are people who the Christian church have recognised as a good example of how to live a holy life
  St George was a cavalry (horseback) soldier in the Roman army from the 3rd century AD - about 1,800 years ago. He probably came from Capadoccia in modern-day Turkey.
  The story says he was ordered to kill some Christians who the Romans didn't like. George refused because he was secretly a Christian himself.
  When his commander found out he was furious and had George executed. The tale of his bravery became well known and George was made an important saint.
  St George is one of the most important saints in Ethiopia. Paintings of him were taken into battle ahead of the Ethiopian army to give them victory.

  St. George In Amharic.
  http://www.youtube.com/watch?v=45aI51VO7CU&feature=related
  http://www.youtube.com/watch?v=hy-mfohChr0&feature=related

  http://www.youtube.com/watch?v=jaQMj0a8U38

  ReplyDelete
  Replies
  1. Thank you for the information. It's really a good movie. May God bless you!

   Delete
 9. ሰላም ለምትባለው አድርሱልኝ

  አለማወቅሽ ነው እንጂ ክርስትና ኢትዮጵያ የገባው ገና ግብጾች ከመምጣታቸው በፊት ነው። ግብጾች ያመጡልን ጵጵስና እንጂ ወንጌል አይደለም። ታሪክ በትንሹ እንኳ እወቂ እንጂ ከመተቸትሽ በፊት።
  በአንድ ነገር ግን አድንቄሻለሁ። በመንፈስ ቅኝ በመገዛት ባልሽው። እውነት ብለሻል። አንቺና መሰሎችሽ የአመጣችሁትን የምንፍቅና ሃይማኖት መቀበል የቸላችሁት በመንፈስ ቅኝ በመገዝታችሁ ነውና ቅኝ በመገዛት ባለው እሳቤሽ የህሊና ድካምሽን ከመረዳቴም በላይ ሳታውቂው ውስጥሽኝ በመግለጥሽ ምስጋናዬ ይደረስሸ።

  በነገራችን ላይ አንድ ነገር አስታወስሺኝ። ዩኒቨርስቲ ተማሪ እያለሁ ብዙዎቹ ፕሮቴስታንቶች .ቅኝ ባለመገዛታችን ይቆቹ ነበር። አንቺም ከእነዚህ ወገን መሆንሽ ነው ይሆንን?የሚገርመው እዚህ ባለሁበት አውሮፓ በብዙ አጋጣሚ ከፕሮቴስታንት መሪዎችም ሆነ ተከታዮች ጋር የመገናኛቱ አጋጣሚ ነበረኝ። እነሱም የራሳቸውን እምነት እኔም ቤተ ክርስቲያን ያስተማረቺኝን ትምህርት አንነጋጋር ነበር። ምን እንደሚሉኝ ታውቂያለሽ? እምነት ማለት የእናንተ ነው እባካችሁ ጠብቁት ይሉኛል። ከዚህም በተጨማሪ አንዳ አንዶች እንዳውም እንደኛ ባዶ እዳትቀሩ በርቱ ይሉኛል።

  ታዲያ 'ታውረን' ላልሺው እውሩ ማነው? አንቺ በ፲፮ኛው ክፍለ ዘመን በጀርመን ሃገር የተነሳው የሃይሞኖት ንቅናቄ ተከታይ ወይስ የሐዋርያትን እምነት ለ፪ ሺ ዘመናት ይዛ የመጣቺው የኢ. ኦ. ተ. ቤ/ያን?

  የልቅ የመንፈስ እውርነትሽ ይገፈፍ ዘንድ የሰሊሆምን ፀበል ዝም ብለሽ ብትመኘ ይሻልሻል የማታውቂውን የተከደነብሽኝ ወንጌል ልስበክ ከምትዩ።

  ReplyDelete
 10. እውር ስላይደለሁ መልእክቱ ደርሶኝ አንብቤዋለሁ::

  ሰማያዊውን የእውነት ቃል በልቶና ከመንፈስ ቅዱስ ምንጭ ጠጥቶ የሚያረካ መልእክት በመረጃ አስደግፎ ለትምህርት የሚሆን እውነት ለሚያቀርቡ ወገኖች ክብር እሰጣለሁ:: ተጨባጭነት በሌለው ነገር ላይ ለሚሞነጫጭሩት ወገኖቼ ግን ብወዳቸውም ለማንበብ ጊዜ አላቃጥልም:: ስንት ቤተ ክርስቲያኒቱ ወልዳ ያሳደገቻቸው ሊቃውንት ዛሬ በጌታ የወንጌል ብርሃን ተገኝተው ፓስተር/ወንጌላዊ የሚሏቸውን ሁሉ በማስናቅ ላይ መሆናቸውን እያየን እንዴት ከገለባ ጋር እንታገል? 'ሁሉን ፈትኑ የሚጠቅማችሁን ያዙ' በማለት ቃሉ ስለሚመክረን::

  ውዽ የስድብ ሊቅ የሆነከው ወገኔ!! ክርስትናችን ከግብጾች በፊት ነው ላልከው በቂ መረጃ ቢኖርህ ደስ ይለኝ ነበር:: መቸም ያን ከተጠመቀ በኋላ የት እንደገባና ምን እንደሠራ ፍንጭ ካለ ወይም በኢትዮጵያ ምድር የት ወንጌልን እንደሰበከ ብትጠቁመን ያላወቅነውን የማሳወቅ የአዋቂዎች ሥራ ይሆንልሃል::

  ክርስትናችን ከግብጽ በፊት ነው ለሚለው በቂ መረጃ ካለ ደግሞ ምን ነክቶን ነው በግብጽ እጅ ወድቀን እስከ አሁን ድረስ ጠባሳው አልጠፋ ባለን መንፋሳዊ ተጽእኖ ውስጥ የምንዛክረው? የእኔ የአንተና የመሰሎችህ መንፈሳዊ አልመግባባት ምንጩ ይህ አይመስልህምን? ደግሞስ እስከ ዛሬ ድረስ 'እስክንድርያ እናታችን ማርቆስ አባታችን' እያልን የምናዜመው ለምንድነው?

  ስለዚህ በመረጃ ያለው የክርስትና ጅማሬያችን በመጀመሪያው የቤ/ክ ጳጳስ በነበሩት አባ ሰላማ ነው በሚለው ላይ በቂ መረጃ ስላለ እሱን ተቀብዬ ስለሆነ አስተያየቴን የሰነዘርኩት በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ነው የምትለኝ ከሆነ:

  1)የንግሥቲቷ መናገሻ ከተማ የት እንደነበረ?
  2)ጃንደረባው ወደ ኢየሩሳሌም ጉዞውን የጀመረው ከየት ከተማ እንደነበረ?
  3)ጃንደረባው ከኢየሩሳሌም መልስ በኢትዮጵያ ውስጥ የትኛው ስፍራ ላይ እንደነበረ?
  4)ጃንደረባው በኢትዮጵያ ውስጥ ወንጌልን እንዴትና የት ስፍራ እንዳዳረሰ?
  5)ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የሚለው ስያሜ መቼ? በማን? እና እንዴት እንደ
  ተጀመረ መርጃ ካለህ ብታስረዳኝ? ደስ ይለኛል

  ከዚህ በተረፈ በውጭ ያላችሁት ወገኖቻችን ቤተ ክርስቲያናችን አሁን ያለችበትን ሁኔታ በውስጧ ሁነን ሁሉን ወደ ሚችለው አምላክ እንባችንን እንደምናፈሰው ያህል ስለማታውቁ (አሉ ከሚል ወሬ በስተቀር) አንተም ጎራ ብለህ ብታይ የተሻለ ይሆናል:: ሌላው በትናንትናው እለት በቤ/ክ ዙሪያ የገጠመኝን ላጫውትህ:

  'ከአንድ ብዙ ጊዜ በሩቁ ሰላም ከሚለኝና እስላም ከሚመስለኝ ወገኔ ጋር መርካቶ ሱቅ ውስጥ ፊት ለፊት ተገናኝተን የሩቁን ሰላምታ ቅርብ ለቅርብ ተገናኝተን ስንጨዋወት ሳለ በእጁ ላይ በያዘው የቁልፍ መያዣ ላይ ድንገት ዓይኖቼ ሲያርፉ ያንዲት ግብጾች አሳምረው የሳሏት ስእል (አንዳንዶቻችን ሰመርናሚስ የምናላት) ልጅ ታቅፋ ተመለከትኩ:: ከዚያም እኔም ድሮ ከእውቀት ማጣት የተነሳ አደርገው የነበረ በመሆኑ ገባኝና እንዴ? ክርስቲያን ነኽ እንዴ የሚል የደስታ/የመገረም አይሉት ጥያቄ ጠይኩት:: አይ! አይደለሁም: ሲለኝ ታዲያ ምንድነህ? ይህ ምንድነው? ስለው እኔ ኦርቶዶክስ እንጂ ክርስቲያን አይደለሁም ሲለኝ ወዲያውኑ ወደ ውስጤ የመጣልኝ መልእክት 'እውነትን በማያውቁ ሰዎች እውነት ሲነገር' የሚል ነበር:: አንተ በዚህ ገጠመኝ ምን ትማርበታለህ?? (ገታን በተሰቀለበ ወቅት የነበረው ንጉሥ 'ያአይሁድ ንጉሥ' ብሎ እንደጻፈው ማለት ነው ነገሩ)

  ለማንኛውም የምህረት አምላክ በቃሉ እውነት ሁላችንንም ያግኘን አሜን::

  ሰላም ሁኑልኝ

  ሰላም ነኝ

  ReplyDelete
 11. Abet kehedet degmo bezih metachehu Egziabehere yeqer yebelachehu selemecheresha zemenachehu ferahulachehu zarew beneseha temelesu.

  ReplyDelete
 12. I have a message for Selam!
  You sound like pure "tehadiso" but unkwongly.. ! I can feel ur humble way of stating ur qns...
  If you put ur qns here... Why don't u go to church n ask our fathers..
  They'll get u as money books as possible! Don't blame Ethiopia Orthodox church..of being slave for Coptics.. After all we r z same.
  If you take me, i would rather say am Coptic Orthodox than Ethiopia!
  I love their Bible commentaries... It is purely based on Holly Bible! They know history of the Bible in detail.. So what is wrong with u girl?

  ReplyDelete
 13. keep it up selam!

  ReplyDelete