Sunday, April 1, 2012

በፖለቲካ ስራ የተጠመዱት የማህበረ ቅዱሳን የጡመራ መድረኮች ለ“ሰማእት” ዘመድኩን ትኩረት አልሰጡም ተባለ - - - Read PDF

ማህበረ ቅዱሳን በጀመረው ዘመቻ ተሀድሶ ዋና ተዋናይ ሆኖ ከፊት የተሰለፈውና ግንባር ለማስወጋት የተሽቀዳደመው ዘመድኩን ግንባር አስወግቶ የተከሰሰበትን ጉዳይ ከወረደበት ወኅኒ ሆኖ እየተከታተለ የነበረ ሲሆን፣ የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ /ቤት ቦሌ ምድብ ሁለተኛ ወንጀል ችሎት አቶ ዘመድኩን በቀለን ጥፋተኛ ብሎት ነበር፤ የቅጣት ማቅለያውን ለማዳመጥና የመጨረሻ ብይን ለመስጠት ለሰኞ መጋቢት 17/2004 ቀጥሮትም ነበር። በዚሀ መሰረት በእለቱ ፍርድ ቤቱ በዋለው ችሎት ተከሳሹ ዘመድኩን 6 ወር የፈረደበት ሲሆን የቅጣት ማቅለያውን እንዲያሰማ በታዘዘው መሠረት፣ እንደመጀመሪያው ብይን ምንም አልናገርም የሰራሁት ሁሉ ትክክል ነው በማለት በሀሳቡ ከመጽናትና “ሰማዕትነቱን” በማጠናከር ሌላ ስድስት ወራትን ከመታሰር ለማምለጥ ቅጣቱ እንዲቀልለት የቅጣት ማቅለያ ያለውን አቅርቧል።
በዚሁ መሰረት የማህበረ ቅዱሳኑ “ሰማዕት” ዘመድኩን “የቤተሰብ ሀላፊ ነኝ፣ ልጆች አሉኝ፣ ሁሉም በእኔ የሚረዱ ናቸው፣ አሁንም በእስር ላይ ነኝ፣ ከዚህ ቀደም ስለ በጋሻው መልካም ወንድምነት መስክሬያለሁ፤ በጋሻው የማይጠጣ የማይሰክር ጥሩ ወንድም ነው ብያለሁ” ወዘተ… በማለት ቅጣቱ እንዲቀልለት ፍርድ ቤቱን ጠይቋል። ፍርድ ቤቱም የቅጣት ማቅለያውን በመቀበል የስድስት ወሩን እስራት በ2 ዓመት ገደብና በ3 ሺህ ብር ቅጣት የለወጠለት ሲሆን፣ ለዋስትናም 5 ሺህ ብር እንዲያሲዝ አዟል።
ዘመድኩን ጥፋተኛ ከተባለና በ2 ዓመት ገደብ እንዲቀጣ ከተወሰነ እነሆ ሳምንት ሞላው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በድረገጽና በውጪው ዓለም በተለይም በሰሜን አሜሪካ በከፍተኛ የፖለቲካ ሥራ የተጠመዱትና ከዋልድባና ከዝቋላ ጉዳይ መውጣት ያልቻሉት፣ ቢዝነሱንም (በእነርሱ አገላለጽ ለዋልድባና ለዝቋላ እርዳታ) በዚያው ልክ ሞቅ ሞቅ ያደረጉት የማህበረ ቅዱሳን ድረገጾች ለ”ሰማእታቸው” ዘመድኩን በዚህኛው የፍርድ ውሳኔ ዙሪያ የሰጡት ሽፋን በጣም አነስተኛ ከመሆኑም በላይ፣ በአዳዲሶቹ ድረገጾች እየተሸፈነ የመጣው ደጀሰላም ካቀረበው ዘገባ በስተቀር ስለእርሱ የተባለ ነገር አለመኖሩን ለማረጋገጥ ችለናል። ይህም ማህበረ ቅዱሳን “ሃይማኖቴ” እያለ ከሚጠራው የላይ ልብሱ ይልቅ የውስጥ ማንነቱ የሆነው ፖለቲካ ስለሚበልጥበት ፊቱን ሙሉ በሙሉ በሚያስችል ሁኔታ ወደዚያው ስላዞረ ነው ዘመድኩንን ቸል ያለው ተብሏል፡፡  
በቀደመው የፍርድ ውሳኔ ስም አጥፊው ዘመድኩን ወደ ወህኒ በወረደበት ጥፋት ላይ የቅጣት ማቅለያ ካለው እንዲያቀርብ ሲጠየቅ ምንም የለኝም በማለት ቅጣቱን መቀበልን መርጦ ወደ ወህኒ መውረዱ ይታወሳል። በመንፈሳዊ አውድ “ሰማዕት” ማለት ምን ማለት እንደሆነ ባላስተዋሉት የማህበረ ቅዱሳን ድረገጾች ላይም ይህ ውሳኔው ከሰማእታት ቁጥር እንደጨመረው ሲራገብ እንደነበረ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። ይህን ምርጫ የወሰደው ቅጣቱ ይቅለልልኝ ብል አምኜበትና ቤተክርስቲያኔን ከመናፍቃን ነጻ ለማውጣት የሰራሁትን “ትክክለኛ” ስራ እንደ ስሕተት መቁጠሬ ነው ብሎ ስላሰበ መሆኑንም ድረገጾቹ ተናግረው ነበር።
ሰማዕት እየበረታ እንጂ እየደከመ አይሄድም። በአቋሙ ይጸናል እንጂ አይዋዥቅም። ቀድሞም ቢሆን ዘመድኩን በእልከኝቱ መታሰሩ ያሳዝናል። በዚህኛው ወንጀል የቀረበበት ክስ ከቀደመው ጋር ተመሳሳይ እንጂ ብዙም የተለየ አይደለም። ነገር ግን ዘመድኩን በመጀመሪያው ቅጣት የተቀበለው “ሰማእትነት”፣ ሰማእት ዘበከንቱ መሆኑን ተገንዝቦ ይሁን ወይም በወህኒ ቆይታው ጠባዩ ታርሞ ምክንያቱ ለጊዜው ባይታወቅም፣ “አሁንስ ይቅርብኝ” በሚል ይመስላል ቅጣቱ ይቅለልልኝ አለ። የማህበሩ ድረገጾች ዝምታን የመረጡትና ትኩረት ያልሰጡት በ“ሰማእትነት” ቦታ ላይ አስቀምጠውት ከ“ሰማእትነቱ” ቦታ ላይ ወርዶ ስላገኙት ይሆናል የሚል ግምትም አሳድሯል፡፡ በቀጣይስ ምን ይሉ ይሆን? የሰጡትን “ሰማእትነት” ይገፉት ይሆን? ወይስ? …
የምሕረት አምላክ ለዘመድኩን ልብ ሰጥቶ ጠባዩን እንዲያርምና በቆይታውም እንዲረዳው ምኞታችንን እንገልጻለን።

5 comments:

 1. ኪኪኪኪኪ አይ ማቅ

  ReplyDelete
 2. http://awdemihret.blogspot.com/2012/04/blog-post.html

  ReplyDelete
 3. ይኸው ማስረጃ
  http://awdemihret.blogspot.com/2012/04/blog-post.html

  ReplyDelete
 4. አይ እናንተ በጣም ትገርማላችሁ!!!
  በዚህ አይነት እማ የሳችውም ጵጵስና የተወሰደውያለፈው አመት ነው በሰው ሀገረ ስብከት ክህነት ሲሰጡ
  ምነው ስንት እሳት ሲነድ ያልዘገ ባችሁ? እናንተ እራሳችሁ አንድ እሳት

  ReplyDelete
 5. betam tegermalachehu tera were becha,
  dere lay yefesesew dem be1984 ahunem yedegemal haymanotachenen beprotestant emnet atlewetum!!!!!!!!!

  ReplyDelete