Tuesday, April 10, 2012

ጥንተ አብሶ የጊዜው አጀንዳ - - - Read PDF

የአባ ሠረቀ መጽሐፍ ከተመረቀና በገበያ ላይ ከዋለ ወዲህ በጠቅላይ ቤተ ክህነት፣ በበርካታ አብያተ ክርስቲያናት ማህበረ ካህናት መካከልና በማህበረ ቅዱሳን መንደር አነጋጋሪ የሆነው ጉዳይ ማርያም ጥንተ አብሶ አለባት የለባትም የሚለው ጉዳይ ነው። ጉዳዩ እንደአዲስ የተነሳው ቆሞስ አባ ሠረቀ እውነትና ንጋት በተሰኘው መጽሀፋቸው ስለተወሳና በጉዳዩ ከአሜሪካ እስከ አዲስ አበባና እስከ ግብጽ፣ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ እስከ ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ፣ ከብፁዕ አቡነ ማትያስ እስከ ብጹዕ አቡነ ገብርኤል ድረስ ብዙ የተባለለትና ያነጋገረ መሆኑ የብዙዎችን ቀልብ ስቧል፡፡ በማህበረ ቅዱሳንና በመሰሎቹ ሰፈር ደግም ሃይማኖት ተጣሰ የሚል አቧራ አስነስቷል።

ጥንተ አብሶ ምንድን ነው? ጥንተ አብሶ (የውርስ ኀጢአት) የሚባለው አዳምና ሄዋን እግዚአብሔር የሰጠውን ትእዛዝ አፍርሰው የሰሩትና ወደዘራቸው የተላለፈ በዘር የሚተላለፍ ኃጢአት ነው። አዳምና ሄዋን ሰውን ሁሉ ወክለው የተቀበሉትን ትእዛዝ በመጣሳቸውና ኃጢአት በመስራታቸው በኃጢአት ሲወድቁ የወከሉትን ሰው ሁሉ ይዘው እንደወደቁና ከእነርሱ የተወለደ ሰው ሁሉ ኃጢአትን ወርሶ የሚወለድ መሆኑን ከአጠቃላዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የምንረዳው ሀቅ ነው።ከአዳምና ከሄዋን ዘር ተወልዶ በዚህ ሀጢአት ያልተያዘ፣ ይህ ሀጢአት የሌለበት የሰው ዘር የለም። አስቀድሞ በእግዚአብሄር መልክና ምሳሌ የተፈጠረው አዳም በሀጢአት ከወደቀና መንፈሳዊ መልኩ ከተበላሸ በኋላ ልጅን የወለደው በመልኩና በምሳሌው መሆኑን መጽሀፍ ቅዱስ ይመሰክራል። «አዳምም ሁለት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ልጅንም በምሳሌው እንደ መልኩ ወለደ ስሙንም ሴት ብሎ ጠራው።» (ዘፍጥረት 5፡3)። ይህም ከአዳም ከሄዋን የተወለዱ ልጆቻቸውና ከዚያም በኋላ የመጡት ዘሮቻቸው ሁሉ ሀጢአተኛ ባህርይን ወርሰው እንደሚወለዱ ያመለክታል።


ዳዊትም «እነሆ፥ በዓመፃ ተፀነስሁ፥ እናቴም በኃጢአት ወለደችኝ።» (መዝሙረ ዳዊት 50/51፡5) በማለት የተናገረው ሀጢአት በዘር የሚተላለፍ ለመሆኑ አስረጂ ነው። ከምንም በላይ ደግሞ በመጽሀፈ ኢዮብ ላይ የተጠቀሰው እውነታ የአዳምና የሄዋን ዘር ሆኖ ከሀጢአት ንጹሕ ሊሆን የሚችል የለም የሚለውን እውነት ያረጋግጣል። «ከርኩስ ነገር ንጹሕን ሊያወጣ ማን ይችላል? አንድ እንኳ የሚችል የለም።» (ኢዮብ 14፡5)። «ንጹሕ ይሆን ዘንድ ሰው ምንድር ነው? ጻድቅስ ይሆን ዘንድ ከሴት የተወለደ ምንድር ነው? እነሆ፥ በቅዱሳኑ ስንኳ አይታመንም ሰማያትም በፊቱ ንጹሐን አይደሉም። ይልቁንስ አስጸያፊና የረከሰ፥ ኃጢአትንም እንደ ውኃ የሚጠጣ ሰው ምንኛ ያንስ?» (ኢዮብ 15፡14-16)። ከተበከለ ምንጭ ንጹሕ ነገር ማግኘት አስቸጋሪ ነገር ነው። የአዳም ዘር ሆኖም ያለ ኃጢአት የተወለደ ሰውም ፈጽሞ አይገኝም፡፡

ከዚህ የተነሳ ሰው ሁሉ ሀጢአተኛ መሆኑን መጽሀፍ ቅዱስ አጽንኦት ሰጥቶ ይናገራል።
·        «ጻድቅ የለም አንድ ስንኳ፤» (ሮሜ 3፡11)።
·        «ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤» (ሮሜ 3፡23)።
·        «በምድር ላይ መልካምን የሚሠራ ኃጢአትንም የማያደርግ ጻድቅ አይገኝምና።» (መክብብ 7፡20)
·        «ልቤን አነጻሁ፥ ከኃጢአትም ጠራሁ የሚል ማን ነው?» (መጽሀፈ ምሳሌ 20፡9)፡፡
የሰውን ዘር ሁሉ ኃጢአተኛ ያደረገው ሀጢአት በአንድ ሰው በአዳም በኩል እንደገባና በኃጢአትም ምክንያት ሞት እንደነገሠ፣ ከዚህ የተነሳም ሰው ሁሉ ኃጢአትን እንደሰራም ተጽፏል፡፡ «ስለዚህ ምክንያት ኃጢአት በአንድ ሰው ወደ ዓለም ገባ በኃጢአትም ሞት፥ እንደዚሁም ሁሉ ኃጢአትን ስላደረጉ ሞት ለሰው ሁሉ ደረሰ፤» (ሮሜ 5፡12)። ስለዚህ ሞት የኃጢአት ውጤት ነው፡፡
 
የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነው (ሮሜ 6፡23)። በብሉይ ኪዳንም ኃጢአት የምትሰራ ነፍስ እንደምትሞት ተጽፏል፡፡ «ኃጢአትን የምትሠራ ነፍስ እርስዋ ትሞታለች» (ትንቢተ ሕዝቅኤል 18፡20)፡፡ ከህጻን እስከ አዋቂ፣ ከኃጢአተኛ እስከ ጻድቅ (አንጻራዊ ጻድቅ እንጂ ፍጹም ጻድቅ የለም) ሰው ሁሉ የሚሞተው ሁሉም ኃጢአተኛ ስለሆነ ነው፡፡
ይሁን እንጂ ኃጢአት በዘር አይተላለፍም ከሚለው ፔላጊዮስ፣ ከሰዎች መካከል ጥንተ አብሶ ያልነካው ሰው (ድንግል ማርያም) አለ እስከሚሉት እስከ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ድረስ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ክርክሮች አሉ። በአገራችንም አለቃ ኪዳነ ወልድ ኃጢአት በዘር አይተላለፍም የሚል አቋም አላቸው (መጽሀፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ ገጽ 25)። የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማርያም ያለኃጢአት ነው የተወለደችው የሚለውን ውሳኔ ያስተላለፈችው እ.ኤ.አ. በ1854 በፒዮስ 9ኛ አማካይነት ነው፡፡
በኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ግን እንዲህ አይታመንም፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ግን በጉዳዩ ላይ ትኩረት ተደርጎ የተካሄደ ውይይትና የተላለፈ ውሳኔ የለም፡፡ በየጊዜው በሚወጡ አንዳንድ ጽሁፎች ላይ አንዳንዱ አለባት ብሎ ሲጽፍ፣ ሌላው ግን የለባትም ብሎ ይጽፋል፡፡ የቤተክርስቲያኒቱን ዶግማና ቀኖና በተመለከተ በሊቃውንት ጉባኤና በሲኖዶስ አባላት በተሰሩ ስራዎች ላይ ማርያም ጥንተ አብሶ የለባትም ተብሎ የተጻፈበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ለዚህም ብዙዎች እየጠቀሱት ያሉት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስያን ሥርዓተ አምልኮትና የውጭ ግንኙነት የተባለውንና በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ዘመነ ፕትርክና በ1988 ዓ.ም የታተመውን መጽሀፍ ነው።
ይህን መጽሐፍ 22 የሚደርሱ ጳጳሳትና ሊቃውንት ያዘጋጁት ሲሆን፣ «አምላክን በድንግልና ጸንሳ በድንግልና የወለደችው የእመቤታችን የድንግል ማርያም ከአዳም ዘር የተላለፈ ኃጢአት (ጥንተ አብሶ) ያላገኛት መርገመ ስጋ መርገመ ነፍስ የሌለባት ገና ከመወለዷ አስቀድሞ በአምላክ ህሊና ታስባ ትኖር የነበረች » መሆኗን ይናገራል (ገጽ 49)።
ብዙዎች ይህን መጽሐፍ ማስረጃ አድርገው የሚጠቅሱባቸው በተለይ ሁለት ምክንያቶች እንዳሉ ይገመታል። አንዱ ምክንያት መጽሐፉ ቁጥራቸው 22 የሆነ ከጳጳሳትና ከሊቃውንት የተውጣጣ ቡድን ያዘጋጀው ስለሆነና የቅዱስ ሲኖዶስ አቋም ተደርጎ ስለሚወሰድና በውስጡ «ማርያም ጥንተ አብሶ የለባትም» የሚል ሀሳብ አስፍሮ ስለሚገኝ፣ የማይለወጥ የሲኖዶስ ውሳኔ ተደርጎ እንዲወሰድ፣ ከዚህ በኋላም ሲኖዶሱ በዚህ ጉዳይ ላይ ውይይት የሚባል ነገር ማድረግ የለበትም ብሎ ከወዲሁ ለማከላከል ነው።
ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ በመግቢያው ላይ የጻፉትና (በስማቸው የተጻፈም ሊሆን ይችላል) «እምነታችን፣ ስርአታችን፣ ትውፊታችን እንግዳ ደራሽ ሳይሆን ጥንታዊና ሐዋርያዊ፣ በጠንካራ አለት ላይ እንደተገነባው ቤት ጽኑ መሰረት ያለው ነው» ያሉትን መሠረት በማድረግ፣ እንዲሁም በመጽሑፉ ገጽ 49 ላይ «ማርያም ጥንተ አብሶ የለባትም» ከሚለው መሰረተቢስ አቋም ጋር በማገናዘብ፣ ድንግል ማርያም ጥንተ አብሶ አለባት የሚለው ትምህርት በኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ የሚታመን ትምህርት መሆኑን በጥናታቸው ከደረሱበት ድምዳሜ ጋር ይጋጫል በማለት ቅዱስነታቸውን ለክስ ለማመቻቸት ነው።

ይቀጥላል
ጸጋ ታደለ

18 comments:

 1. እናንተ ምአተኞች እባካችሁ አቅጣጫችሁን ለዩልን በቅዱሳን አባቶቻችን ስም እየነገዳችሁ አልፋችሁ ተርፋችሁ ደግሞ ምእመናን ለማወነባበድ ቆርጣችሁ ተነስታችኃል እኔ እኮ እሚገርመኝ ማህበረ ቅዱሳንን ካልጨመራችሁ መፃፍ አትችሉም እንደ

  ReplyDelete
 2. ከርኩስ ነገር ንጹሕን ሊያወጣ ማን ይችላል? አንድ እንኳ የሚችል የለም።» (ኢዮብ 14፡5)። «ንጹሕ ይሆን ዘንድ ሰው ምንድር ነው? ጻድቅስ ይሆን ዘንድ ከሴት የተወለደ ምንድር ነው?
  ታዲያ ከድንግል ማርያም/ከአዳም ዘር/ የተወለደው የሰው ልጅ የተባለ ኢየሱስ ክርስቶስን ምን ልትሉት ነው?ለወደፊት እርሱም ጥንተ ተሐብሶ አለበት ትሉ ይሆናል

  ReplyDelete
  Replies
  1. አንተ የጥፋት ልጅ እውነትን ለምን ታጣምማለህ? መንፈስ ቅዱስ በእመቤታችን ላይ የመጣው እኮ ቃል የሚዋሀደውን ስጋ ለማንጻት ነው። ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ ያነጻውን ስጋ ነው ጌታ የለበሰው። ሀጢአት ወደ እርሱ አልተላለፈም።

   Delete
  2. @ Apr 11, 09;40.It says" ye lioul hayil yitselilbishal" It doesn't mean like u said. It means the holly spirit will reign on you. I.e all like every body. There is no a single word in the bible that says Jesus christ is free from original seen despite he didn't do any sin through out his life on earth like what paul said.If he is human he has to inherit this original sin.

   Delete
  3. አዎን ከርኩስ ነገር ንጹህ ማውጣት አይቻልም። ነገር ግን ጌታ ኢየሱስን ከዚህ ነፃ ያደረገው መንፈስ ቅዱስ በእርሷ ላይ ሲመጣ ያን ጊዜ ኃጢአትን ከልሎ እንዲፀነስ ስላደረገ ነው። ደግሞስ ማርያም ከጥንተ አብሶ ነፃ የማትሆን ከሆነ ኢየሱስም ነፃ አይደለም ለማለት ያነሳሳህ ኢየሱስንና ማርያምን እኩል አድርገህ ስለምታያቸው ይሆን?

   Delete
 3. አባ ሰላማዎች ታገሱ እንጂ
  ምነው አበዛችሁት እኮ

  ReplyDelete
 4. here befeterachiu hinante mindinahcu ORTODOX TEWAEDO weyes lela .bezi agenada(be DINGLE MARIAM) lay yalachu hasab mindinew. yenante ye Aba Selamawochin mels itebkalew.

  ReplyDelete
 5. እናንተ ፈረንጅ አምላኪዎች እናንተስ እውነትን ለምን ታጣምማላችሁ?በአምላክ ህሊና ታስባ የኖረችን ንጽህተ ንጹሀን እመቤታችንን በስጋ በመወለዷ ጥንተ ተሀብሶ አለባት ለማለት ያላፈራችሁ ነገ አማላጅ ያላችሁትን መድሀኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን በስጋ በመወለዱ ጥንተ ተሀብሶ የለበትም ላለማለታችሁ ምን ዋስትና ይኖራችኋል እምነታችሁ እና መጽሀፋችሁ ሁሉ እየተበረዘ መጥቷልና።
  እንዲህ ተብሎ የተጻፈውን በውኑ አላነበባችሁም?
  ልጆችህ ኪዳኔን፦
  ይህንን የማስተምራቸውን ምስክሬን ቢጠብቁ ፦
  ልጆቻቸው ደግሞ በዙፋንህ ላይ ለዘላለም ይቀመጣሉ።
  እግዚአብሔር ፅዮንን መርጧታልና፦
  ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወዷታልና፦እንዲህ ብሎ
  ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት፤
  መርጫታለሁና በዚህም አድራለሁ።
  አሮጊቶችዋን እባርካለሁ፦
  ድሆቿንም እንጀራ አንጀራ አጠግባለሁ።
  ካህናቶችዋንም ደህንነትን አለብሳቸዋለሁ፦
  ቅዱሳኖችዋም እጅግ ደስ ይላቸዋል።.....መዝሙር፻፴፩

  ReplyDelete
 6. ሰደድ እሳት በጀሪካን
  አይ ማህበረ ቅዱሳን

  ተቃጠለና አሉ የዝቋላ ጫካ
  የተቃዋሚዎች ልባቸው ተነካ

  በኢትዮጵያ ምድር መንግሥት ስለሌለ
  የአቡነ ጳውሎስም ጉዳይ ስላይደለ
  ቤተ ክህነቱም በየማኅበሩ ስለተንጓለለ

  ጎበዝ ብር አዋጡ ከቻላችሁ ዶላር
  ለጀሪካን መግዣ ለአህዮቹም ሣር
  ከንፋስና አውሎ ከሰደድ እሳት ጋር
  ተፋጠናልና አትቁሙ ከዳር

  ብለው አወጁ አሉ እነ ብር አይጠግቡ
  በጀሪካን ሰበብ ደግሞ ብር ሊያስገቡ

  ተብደል ቡድን ፈጥረው ተሐድሶ እያሉ
  ቤተ ክርስቲያንን ሊያምሱ ሲከፍሉ

  ዝም ስለተባሉ

  ታዲያ ምን አለበት ደግሞ ቀስ ብልን
  መንግሥትን ብንጀምር ብንሞክረው ደፍረን
  አደድ በጀሪካን እኛ አጠፋን ብለን

  ReplyDelete
 7. ሰደድ እሳት በጀሪካን
  አይ ማህበረ ቅዱሳን

  ተቃጠለና አሉ የዝቋላ ጫካ
  የተቃዋሚዎች ልባቸው ተነካ

  በኢትዮጵያ ምድር መንግሥት ስለሌለ
  የአቡነ ጳውሎስም ጉዳይ ስላይደለ
  ቤተ ክህነቱም በየማኅበሩ ስለተንጓለለ

  ጎበዝ ብር አዋጡ ከቻላችሁ ዶላር
  ለጀሪካን መግዣ ለአህዮቹም ሣር
  ከንፋስና አውሎ ከሰደድ እሳት ጋር
  ተፋጠናልና አትቁሙ ከዳር

  ብለው አወጁ አሉ እነ ብር አይጠግቡ
  በጀሪካን ሰበብ ደግሞ ብር ሊያስገቡ

  ተብደል ቡድን ፈጥረው ተሐድሶ እያሉ
  ቤተ ክርስቲያንን ሊያምሱ ሲከፍሉ

  ዝም ስለተባሉ

  ታዲያ ምን አለበት ደግሞ ቀስ ብልን
  መንግሥትን ብንጀምር ብንሞክረው ደፍረን
  ሰደድ በጀሪካን እኛ አጠፋን ብለን

  ReplyDelete
 8. Immaculate conception has become a major bone of contention between Ethiopian Orthodox Tewahedo beleiever, including the clergy. Kesis Asteraye has written extensively on this subject and requested the Holy Synod to provide their verdict. When they were unable to do so, he went to the Egyptian Coptic Church. You can find this information on Kansas Medhanialem EOTC's website. Instead of becoming unruly and supporting this camp or the other, I think the best way to resolve this and many other issues affecting our church today is to demand the Holy Synod reach a conclusion on this issue and others.

  May the Peace and Love of the Lord be with you all.

  ReplyDelete
 9. The Prophet Jermias was sanctified when he was in the womb of his mother,why sait Mary?Abba Giorgis zegasecha said that the Original Sin of Adam didn't tranmit to Saint Mary,who are you?are you more holy that this saint who wrote many books in the 15th century.Saint Erélies and Saint Thedrotos said that Saint May was concieved with out sin in the womb of Saint Anne.Please attention what you are talking

  ReplyDelete
 10. Aba selama do you knew kassahun who had got big gov. Position in Ethio. Transportation through his kin Kassuilals who was one of corrupted former minister, kassahun now delivered all mk magazine in gov transportation freely.

  ReplyDelete
 11. Wise @AnonymousApr 12, 2012 08:18 AM

  ReplyDelete
 12. ለዘመናት ካራ ቅባት ሁለት ልደት ሶስት ልደት እያሉ ሲነታረኩ
  ወንጌልን መስበክ ተዉት
  አሁን ደግሞ ጥንተ አብሶ በማለት ንትርክ ተያይዘው እስላሙ አገሪቱን እየወረረ ነው
  ለጽድቅ የሚያበቃ ስራ መስራት ወንጌሉን መከተል ተናቀ
  ምነው ሐዋርያት በነዚህ ላይ ተከራከሩ ተነታረኩ የሚል አናነብም
  እነሱ በጸሎትና በማስተማር ነው ሕይወታቸውን ያሳለፉት

  ReplyDelete
 13. Hi guys!! I were expecting a good argumenent but it simply talks general thingsthat we believ in. On the first place you said the ajenda becomes issue of many stekholders like Popes, MK etc which is realy false b/c I know the reality. Second you try to say other orthodox chirstians believe in the issue without putting even a single referrence. Third you try to make the book የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስያን ሥርዓተ አምልኮትና የውጭ ግንኙነት a simple book and not the rule of the church which makes you "yechifin temuagach". Which referrence could be acceptable if not the one which is prepared by our 22 popes and approved by the patriaric. Fourth you were trying to say you have a lot of evidences but you can't write a single specific referrence about st marries share of sin (yewurs)you simply wrote what everybody knows and believes generally. So please try to be spesific, to the point and do not relat everything somebody or some organization like MK. Let's discuss on the issue and let idea win.

  ReplyDelete
 14. Abatochachin sile esua sinegirun alem kemefeteru askedimo beamilak hilina tasiba tinor neber silezih esua besigam benefim nisihit nat enante ke Abatochachin atibelitum silezih egna yesua lijoch anisemachihum minew enatachuh telachuh bemetilatachuh wagachuh mindinew bereket weyis mergemit? ahunis gorachuh leyu madenager yibika

  ReplyDelete
 15. His Holiness Pope Shenouda III has explicitly stated in his book "The Holy Virgin St. Mary" that she was conceived with the original sin (tinte abiso) like every human being. So are we following catholic dogma or orthodox dogma??? Here is the link. You can read it for yourself in page 11 of the book. Don't deny the truth, it shall set you free.
  http://tasbeha.org/content/hh_books/the_holy_virgin_st_mary/index.html

  "The sanctifying by the Holy Spirit of her depository, makes the One born of her, be conceived without the impurity of the original sin. As for The Virgin herself, her mother conceived, like all people, and so The
  Virgin said in her hymn: "my spirit has rejoiced in God my Savior" (Luke 1:47).
  That is why the Church does not agree that The Virgin was
  conceived without the impurity of the original sin, as our brothers the Catholics believe."

  ReplyDelete