Thursday, April 12, 2012

ሰሙነ ሕማማት የጌታ ወይስ የይሁዳ ሳምንት? - - - Read PDF

 • በሰሙነ ሕማማት የጌታን ፍቅር እንዳናስብ የሚያደርጉንንና የሚያዘናጉንን ልማዶችና ወጎች ሁሉ ልናስወግዳቸው ይገባል።
 • በጌታ ሞት የምናዝነውስ ለምን ይሆን? ለምን ሞተ ብለን ማዘናችን ኢመጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው። ከዚያ ይልቅ ስለእኛ በመሞቱ ወደር የሌለው ፍቅሩ ልባችንን ሊገዛ፣ ሊነገር በማይቻል ፍጹም ደስታ ልባችንን ሊሞላ በሰላምና በእረፍት እጦት ለሚዋትተው ሕይወታችን ሰላምና እረፍት ሊሰጣት ይገባል።
 • እባካችሁ ይህን አስደናቂውን፣ ከአእምሮ በላይ የሆነውንና የሚለውጠውን የጌታን ፍቅር ንገሩን። በሌላ በሌላው አታድክሙን። ጌታ የጠራን ከባዱን ሸክማችንን ከላያችን ጥሎ ሊያሳርፈንና የእርሱን ቀላል ሸክም ሊያሸክመን እንጂ እርሱ ያላሸከመንን ሌላ ከባድ ሸክም ተሸክመን መትከፈ ልቡናችንን (የልቡናችንን ጫንቃ) እንዲሰብር አይደለም።
ይህ የምንገኝበት ሳምንት ሰሙነ ሕማማት በመባል ይታወቃል። ሳምንቱ የተመደበው የጌታችንን ሕማማት ለማሰብ ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአይሁድ እጅ ከተያዘባት ከሐሙስ ምሽት አንስቶ በብዙ መከራ ውስጥ አልፎ እስከተሰቀለባትና እሰከ ሞተባት እስከ አርብ ድረስ የተቀበለው መከራ እጅግ አሰቃቂ ነው። ነቢዩ ኢሳይያስ በምዕራፍ 53 ስለ ክርስቶስ መከራ አስቀድሞ የተናገረው ሁሉ የጌታን ጥልቅ ፍቅር ያስረዳል። እርሱ ያንን ሁሉ መከራና ስቃይ የተቀበለው፣ ስለ እኛ ነው። የእኛን ደዌ ተቀበለ፤ ሕመማችንንም ተሸከመ። እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ። በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን። ነፍሱን የኀጢአት መሥዋዕት አድርጎ በማቅረብ ለእኛ ያደረገውን ይህን የፍቅርና የቸርነት ስራ ከማሰብ የበለጠ ነገር የለም። የመዳናችን መሠረት ይህ ነውና። ወደእርሱ የተጠራነውና የመጣነው በዚህ ሁኔታ በተገለጠ ድንቅ ፍቅሩ ነው። በምንም የማይመለሰውን የጌታን ፍቅርና ውለታ ሁልጊዜ እያስታወስን ልንደነቅና ልንገረም፤ ጌታንም በሙሉ ልባችን ልንከተል ይገባል። ሰሙነ ሕማማት ተብሎ ይህ ሳምንት የተለየውም ሁልጊዜ ልናስበው የሚገባውን ይህን የጌታን ፍቅር በተለየ መንገድ እንድናስበው ስላስፈለገ ነው እንጂ ሌላ ምክንያት አይኖረውም።
በሰሙነ ሕማማት የምናከናውናቸው ስርአቶች ሁሉ በምሳሌነት አንድ ጊዜ የተከናወነውን የክርስቶስን የማዳን ስራ የሚያስታውሱ ናቸው እንጂ ሌላ አይደሉም፤ ሊሆኑም አይገባም። ስለዚህ እነርሱ ወደሚያመለክቱን አማናዊ የክርስቶስ ፍቅር መመልከት እንጂ፣ በምሳሌዎቹ ላይ አፍጠን መቅረት የለብንም። ወደአማናዊው ነገር መድረስ ካልቻልን ከስረናል እንጂ አላተረፍንም። ለምሳሌ የመስቀል ምልክት በራሱ ምንም አይደለም፤ የእኛ ጉዳይ ከተሰቀለው እንጂ እርሱ ከተሰቀለበት ቁስ ጋር አይደለምና። ቁሱ ምን ጊዜም የሚያመለክተን የተሰቀለውንና ያዳነንን ጌታ ክርስቶስን ነው እንጂ ራሱን ወይም ሌላውን አይደለም። ለዚህ ነው ክርስቲያኖች ሁሉ መስቀልን አርማቸው ያደረጉት። ይህም አስደናቂ ነገር ነው። ለምን መስቀልን አርማቸው አደረጉት? ለምን ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት በልዩ ልዩ ጉዳዮች ሲለያዩ በአርማቸው በመስቀል ላይ ግን አልተለያዩም? የክርስትና ዋና ነገርና ማእከሉ፣ በመስቀሉ ላይ የተሰራው የማዳን ስራ ስለሆነ ነው። መስቀሉ የተሰቀለውን ስለሚጠራ ነው። በመስቀሉ ምልክትነት ወደተሰቀለው መድረስ ካልቻልንና የተመሳቀለው ዕንጨት ወይም የመስቀል ቅርጽ የተሰቀለውን ክርስቶስን ወደአእምሯችን ካላመጣው ምልክቱ ስራውን በተገቢው መንገድ አልተወጣም። ጥራ ሲባል ራሱ መጥቷልና ባየነው ዘንድ መንፈሳዊ ኪሳራ አድርሶብናል።

ብዙ ምእመናን በዚህ ሳምንት በቤተክርስቲያን እየተገኙ ቀደምት አባቶቻችን በሠሩልንና ባቆዩልን በዚህ የሕማማት ሳምንት ሥርአት መሰረት የጌታን የመስቀል ላይ ፍቅር ያስባሉ። ከዚህ የበለጠ አምልኮትና ሰውን ከፈጣሪው ጋር የሚያገናኝ እውነተኛ መንገድ የለም። ይሁን እንጂ ምንጊዜም ሰዎች እውነቱን ወደማወቅ እንዲደርሱ የማይፈልገው ጥንተ ጠላታችን ዲያብሎስ፣ በዚህ የሕማማት ሳምንት እንኳን የጌታን ፍቅር ብቻ እያሰብን በፍቅሩ ልባችን እንዳይረካ፣ ለእርሱም ብቻ ተገዝተን በአምልኮታችን እንዳናርፍ የጌታን ፍቅር የሚሻሙብንን ሌሎች ነገሮችን ወደቤተክርስቲያን በልዩ ልዩ መንገድ በማስገባት ልባችን እንዲከፋፈል ያደረገበት ብዙ ሁኔታ አለ። አንዱ መሳሪያው የሰው ልማድና ወግ ነው። በዚህ እየተጠቀመ በተሰቀለው ጌታ እንዳናምንና አይናችንን ከተሰቀለው ጌታ ላይ እንድናነሳ ያደርጋል።
ከክርስቶስ ሞት በፊት የነበረውን ዓመተ ፍዳ ለማሰብ በሚል በተሠራው ስርአት ውስጥ ተአቅቦ የምናደርግባቸው የተለመዱ ስርአቶቻችን አንደኛዎቹ የጌታን ፍቅር እንዳናስብ የሚያዘናጉን ናቸው። ለምሳሌ በዚህ ሳምንት ይሁዳ ጌታን አሳልፎ የሰጠው በመሳም ነውና ትከሻ ለትከሻ፣ ወይም ጉንጭ ለጉንጭ መሳሳም የይሁዳ ወዳጅ መሆን እየተባለ ስለሚነገር፣ መሳሳም የተከለከለ ነው ተብሎ በልማድ ይሰራበታል። ስለዚህ ብዙው ሰው በሰላምታዊ መሳሳም እንዳይሳሳት ሲጠነቀቅ፣ ረስቶት ለመሳም የቃጣ ሲያፍርና ከአትሳመኝ ባዩ ጋር ሲወዛገብ የተለመደ ነው። እነዚህ ወጎችና ልማዶች የጌታውን ፍቅር እንዳያስብ ትልቅ ማዘናጊያ ሆኖውበታል።
ሌላው ማዘናጊያ ስለተሰቀለው ጌታ ከመናገርና የእርሱን ፍቅር በምእመናን ልብ ከመሳል ይልቅ ስለይሁዳ ክፋት፣ ጌታውን በገንዘብ እንዴት አድርጎ አሳልፎ እንደሰጠውና ስለነበረው የገንዘብ ፍቅር በዚህ የሕማማት ሳምንት አውርተውና ሰብከው የማይጠግቡ ጥቂቶች አይደሉም። ይሁዳ የሰራው ክፉ ስራ የጌታ ሕማማት አንዱ አካል ተደርጎ ሊታይ ቢችልም፣ ይሁዳን ማእከል አድርጎ ስለእርሱ ክፋትና ፍቅረንዋይ መዘርዘር ግን የክርስቶስን ፍቅር አያሳይም፤ ባይሆን የይሁዳን ክፋት ይገልጣል እንጂ። ስለዚህ ምናለበት በይሁዳ ክፋት ላይ ሳይሆን በኢየሱስ ፍቅር ላይ ብናተኩር? ያኔ በይሁዳ ልብ የገባውና ጌታን እንዲሰቀል በአይሁድ እጅ አሳልፎ የሰጠው ሰይጣን፣ ዛሬም የሰዎች ልብና አንደበት ተቆጣጥሮ በሰሙነ ሕማማት  የክርስቶስ የፍቅር ገድል ሳይሆን የይሁዳ የክፋት ገድል እንዲነገር የሚጠቀምባቸው የሉም ማለት አይቻልም። ዳንኤል ክብረት በዚህ በሰሙነ ሕማማት እንኳን ለገበያ ያቀረበው ቪሲድ ርእስ «ይሁዳ እና መግደላዊት ማርያም» ይላል። መቼ ይሆን የጌታን ፍቅር ከራሱ ከጌታ በመጀመርና በእርሱው ላይ በመደምደም የምንሰብከው። ስለጌታና ስለመስቀሉ ፍቅር ለመናገር ለምን ሌላ መደገፊያ እንፈልጋለን። ጌታ ያደረገው የፍቅር ስራ እኮ ራሱን ችሎ ሊነገር፣ ሊሰበክ የሚገባው ነው። የሁል ጊዜ ስብከታችንስ የተሰቀለው ክርስቶስ መሆን አልነበረበትምን?

«በእግዚአብሔር ጥበብ ምክንያት ዓለም እግዚአብሔርን በጥበብዋ ስላላወቀች፥ በስብከት ሞኝነት የሚያምኑትን ሊያድን የእግዚአብሔር በጎ ፈቃድ ሆኖአልና። መቼም አይሁድ ምልክትን ይለምናሉ የግሪክ ሰዎችም ጥበብን ይሻሉ፥ እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት ነው፥ ለተጠሩት ግን፥ አይሁድ ቢሆኑ የግሪክ ሰዎችም ቢሆኑ፥ የእግዚአብሔር ኃይልና የእግዚአብሔር ጥበብ የሆነው ክርስቶስ ነው።» (1ቆሮ. 1፡21-24)።
በጌታ ሞት የምናዝነውስ ለምን ይሆን? ለምን ሞተ ብለን ማዘናችን ኢመጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው። ከዚያ ይልቅ ስለእኛ በመሞቱ ወደር የሌለው ፍቅሩ ልባችንን ሊገዛ፣ ሊነገር በማይቻል ፍጹም ደስታ ልባችንን ሊሞላ በሰላምና በእረፍት እጦት ለሚዋትተው ሕይወታችን ሰላምና እረፍት ሊሰጣት ይገባል። ምክንያቱም ጌታ በይሁዳ ተላልፎ ለአይሁድ ቢሰጥም፣ አይሁድ ይሙት በቃ ፈርደውበት ሰቅለው ቢገድሉትም፣ እርሱ ግን የሞተው እኛን ያድን ዘንድ በእግዚአብሔር ዘላለማዊ እቅድና በእርሱ ቁርጥ ውሳኔ መሆኑን ፈጽሞ ልንዘነጋ አይገባንም። «እግዚአብሔርም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ» (ኢሳ. 53፡10) «እርሱንም በእግዚአብሔር በተወሰነው አሳቡና በቀደመው እውቀቱ ተሰጥቶ በዓመፀኞች እጅ ሰቅላችሁ ገደላችሁት።» (የሐዋ. 2፡23)። እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስመስጠት ደርሶ ዓለምን እንደወደደ ፈጽሞ ሊረሳ አይገባም። እኔን ሀጢአተኛውን፣ እኔን ደካማውን፣ እኔን ጠላትህን ምንኛ ወደኸኝ ነው ስለእኔ የሞትክልኝ! ብሎ በፍቅሩ መደነቅ እንጂ  «ዋ ሸሸ፥ ተበላሸ» በሚል ፈሊጥ መቆዘም፣ አይሁድ ለምን ገደሉህ ብሎ ማዘንና በእነርሱ ላይ ጥርስን መንከስ፣ የመስቀሉን ፍቅርና ክርስቶስ የሞተበትን አላማ መዘንጋት ነው የሚሆነው። እርሱ ጌታችን «አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው ሲል መጸለዩንም» አለማስተዋልና እውነተኛ ፍቅርን ከእርሱ አለመማር ነው።
በሰሙነ ሕማማት የጌታን ፍቅር እንዳናስብ የሚያደርጉንንና የሚያዘናጉንን ልማዶችና ወጎች ሁሉ ልናስወግዳቸው ይገባል። ትእምርታዊነት ያላቸውን ነገሮችም ቢሆን ከትእምርታዊነታቸው ባሻገር የያዙትን እውነት ማስተዋልና ለዚያ ራስን ማስገዛት እንጂ ትእምርቱ ላይ መቅረት፣ ሃይማኖተኛ እንጂ ክርስቲያን አያደርገንም። «እኔ የኢየሱስን ማኅተም በሥጋዬ ተሸክሜአለሁና ከእንግዲህ ወዲህ አንድ ስንኳ አያድክመኝ።» (ገላ. 6፡17) እንዳለው ቅዱስ ጳውሎስ፣ እኛም በእውነት ምንም መንፈሳዊ ትርፍ ላይኖረው እንዲያው የሚያደክመንንና ወደክርስቶስ ፍቅር የማይመራንን የሰው ወግና ልማድ አሽቀንጥረን በመጣል፣ በክርስቶስ ፍቅር ተጠምደን ወደእርሱ በእምነት መገስገስ አለብን።

በሰሙነ ሕማማትም ሊዘከር የሚገባው ስለእኛ መከራ የተቀበለው ጌታ ብቻ ነው። ያልሞተልንን አንስበክ። ተነግሮና ተተርኮ የሚያልቀውን፣ ምንም ሕይወት የማይገኝበትን የይሁዳን ታሪክ ሳይሆን፣ ከመታወቅ የሚያልፈውን፣ ከቶ የማይደረስብትን፣ ጥልቅ የሆነውን ድንጋዩን ልብ የሚሰብረውንና የሚለውጠውን፣ ዓለምን የሚያስመንነውን (የሚያስንቀውን)፣ ሕይወትን እንኳ ሳይቀር እንደከንቱ ነገር የሚያስቆጥረውን፣ ብዙ የእምነት ጀግኖችን የወለደውን፣ ኀጢአተኞችን ጻድቃን፣ ከሀዲዎችን ታማኞች፣ አሳዳጆችን ተሰዳጅ ያደረገውን፣ … ብቻ ስንቱ ይነገራል? …
እባካችሁ ይህን አስደናቂውን፣ ከአእምሮ በላይ የሆነውንና የሚለውጠውን የጌታን ፍቅር ንገሩን። በሌላ በሌላው አታድክሙን። ጌታ የጠራን ከባዱን ሸክማችንን ከላያችን ጥሎ ሊያሳርፈንና የእርሱን ቀላል ሸክም ሊያሸክመን እንጂ እርሱ ያላሸከመንን ሌላ ከባድ ሸክም ተሸክመን መትከፈ ልቡናችንን (የልቡናችንን ጫንቃ) እንዲሰብር አይደለም።
«የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ፥ በዓይናችሁ ፊት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተሰቀለ ሆኖ ተሥሎ ነበር፤ ለእውነት እንዳትታዘዙ አዚም ያደረገባችሁ ማን ነው?» ገላ.3፡1
ጸጋ ታደለ

10 comments:

 1. I have a question for you: why do you change the practices of the true church (these practices were in the church since the first century) to suit to your fleshly comfort?

  ReplyDelete
 2. Abet Alemastewal...Ahun yemitech sitefa degmo bezi metachu? zemed yemotebet yezemedun photo eyetemelekete, Degnetun eyasebe, Fikirun eyastawose biyalekis "le photow new yalekeskew" yasbelewal? Endih bilo yemitechew kalem Alawaki Senef teblo mesakiya yehonal. ke Getachen mekera-meskel gar beteyayazze besemune himamat yemideregu negeroch BEMULU yemiyastawusun yegetan talak Fikir endehone nefs lawok sew hulu gilits new. LeAnte endet teseworebeh?

  ReplyDelete
  Replies
  1. Egizer yibarkeh!

   Delete
  2. Abet Alemastewal...Ahun yemitech sitefa degmo bezi metachu? zemed yemotebet yezemedun photo eyetemelekete, Degnetun eyasebe, Fikirun eyastawose biyalekis "le photow new yalekeskew" yasbelewal? Endih bilo yemitechew kalem Alawaki Senef teblo mesakiya yehonal. ke Getachen mekera-meskel gar beteyayazze besemune himamat yemideregu negeroch BEMULU yemiyastawusun yegetan talak Fikir endehone nefs lawok sew hulu gilits new. LeAnte endet teseworebeh?

   Reply

   Delete
 3. Feel free!! these days the problem is to get some one who fasts, prays and bows to God like the ancient churches do such as the Oriental and eastern Orthodoxy, and Catholics. It is easy to get people who are like protestants who don't like fasting, praying and bowing God.

  ReplyDelete
  Replies
  1. I agree with you 100 %. Tebarek! "These days the problem is to get some one who fasts, prays and bows to God like the ancient churches do such as the Oriental and eastern Orthodoxy, and Catholics."

   Despite of their church politics, centuries of hatred among their respective clergy and the laity, and superficial cultural differences these ancient churches have been preserved by the grace of God to be faithful to the apostolic traditions.

   Luther, Calvin, Zwingli, etc. missed this. Poor guys.

   Delete
 4. Dear Tsega:

  Bless you... little by little the truth and the light that is being revealed now through his trustworthy servants will no doubt change the world. No man should understimate what you are doing for Chirst. The Holy Spirit which dwells in human beings is a witness for those who oppose the truth. Eventually they come to the truth. Now they are like Nakedemus but in their heart they belive him already or, if not, their heart is divided. Surely the work God started with you will come to fruition...because it is the naked truth

  ReplyDelete
 5. who are you? i'm relly wondering why you always talk and write about an indivisual. if you are christians who preach love and truth of jusus, you should not waste your time and energy to insult diakon daniel kibret as well as mahbere kidusan and our trufats.to tell you the truth, s not proper way to teach christianity unless you are striving for achiving certain political mission. its relly shame and shaming for those who truly beleve in God.

  ReplyDelete
 6. Tsega GOD may BLESS YOU. continue it to preach about JESUS only.

  ReplyDelete
 7. You are recognizing evidentially being the blog & members are tehadso.

  ReplyDelete