Thursday, April 12, 2012

ማህበረ ቅዱሳን በዲ/ን ያረጋል አበጋዝ ላይ የስለላ መዋቅሩን ዘረጋ - - - Read PDF

ምንጭ፡- ከዐውደ ምሕረት
“የቤተክርስቲያን አባቶች የጻፉትን መጻህፍትም ሆነ የቤተክርስቲያን አባቶችን መቶ በመቶ አንቀበልም። መቶ በመቶ የምንቀበለው መጽሐፍ ቅዱስንና ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ብቻ ነው።” ዲ/ን ያረጋል አበጋ
ማኅበረ ቅዱሳን በየወሩ በሚያካሂደው የማኅበሩ አባላት የሆኑ አገልጋዮች ውይይት  ላይ የማኅበሩ አፍ ሆኖ በተለያዩ ቦታዎች እና አዳራሾች በግንዛቤ አስጨብጣለሁ ስም፣ ያለ አንዳች ማስረጃ እውነተኛ የቤተክርስቲያን ልጆችን “ተሀድሶ - መናፍቃን ናቸው” እያለ መግለጫ ሲሰጥ የነበረው ዲ/ን ያረጋል አበጋዝ በቤተክርስቲያን ታሪክ «አውጣኪ መናፍቅ ነው» የተባለው ያለ ተጨባጭ ማስረጃ ነው ሲል ለአውጣኪ ተከላከለ።
የካቲት 29 2004 ዓ.ም. በአዲስ ቪው ሆቴል በተካሔደው በዚህ ወርሀዊ ጉባኤ ላይ ለጥናት የቀረበው ርዕስ “ቅድመ ኬልቄዶን ጉባኤ የኬልቄዶን ጉባኤ እውነታና ድኅረ ኬልቄዶን ጉባኤ” የሚል ሲሆን፣ የጽሁፉም አቅራቢ የማህበሩ ቀኝ እጅ ዲ/ን ያረጋል አበጋዝ ነው። የጥናቱ ዋና ትኩረት የአውጣኪና የፍላብያኖስን ጠብና የአውጣኪን መወገዝ የተመለከተ ነው። ያረጋል እንዳለው በዚህ ጉዳይ ዙሪያ የተቻለውን ያህል ልዩ ልዩ መዛግብትን ለማገላበጥ የሞከረ መሆኑን ጠቅሶ፣ ከዚህም በመነሳት የደረሰበት ድምዳሜ “አውጣኪ የተወገዘው መናፍቅ ሆኖ ሳይሆን በወቅቱ ስልጣን ላይ በነበሩት በነፍላብያኖስ ጥላቻ ነው” የሚል ነው። ይህም እንደ ጥናቱ ባለቤት እንደ ያረጋል አመለካከት “በወቅቱ አውጣኪ ላይ የቀረበው ክስ በእምነት ሳይሆን በጥላቻ የቀረበ ነው። ከዚህም በመነሳት ክሱ መሠረታዊውን አጀንዳ የሳተ እና በሀይማኖት ሽፋንነት የቀረበ ነው ወደሚል ድምዳሜ ያደርሰናል።” ብሏል።
ያረጋል ይህንን ሀሳቡን ሲያጠናክር በዋነኛነት እንደ ምክንያት የሚከተለውን አቅርቧል፤ “አውጣኪን መናፍቅ የሚያደርግ አንድም መረጃ አልተገኘም። አውጣኪ የተወገዘው በትክክለኛ እምነቱ ነው። በገዳሙ ውስጥ በእውነተኛ እምነቱ እና በትክክለኛ የምንኩስና ህይወቱ ይኖር የነበረ ሲሆን፣ በጉባኤው ላይ የመገኘት ፍላጎት አልነበረውም። በጉባኤው ላይ ላለመገኘትም ሕመምና የተለያዩ ምክንያቶችን አቅርቦ እንደ ነበር ያካሄድኩት ጥናት ያስረዳል። ይሁንና ያኔ ስልጣን ላይ የነበሩት አካላት በግፍ በጉባኤው ላይ እንዲቀርብና ምንም አይነት ሀሳብ ሳያቀርብ ጥያቄም ሳይጠየቅ መልስም ሳይሰጠው መናፍቅ ነው ብለው ብዙ ጫና አድርገውበታል።” ሲል ለአውጣኪ ትክክለኛ መሆኑን ለማስረዳት ሞክሯል።
አክሎም «አውጣኪ ምንም አይነት ሃይማኖታዊ ችግር የለበትም። የሃይማኖት ችግር እንዳለበት የሚያሳይ ማስረጃ በጽሁፍም ሆነ በቃል ከአውጣኪ አፍ አልተገኘም።» ሲል አብራርቷል። በማስከተልም «በጉባኤው ላይ የሃይማኖቱን መሰረት በሚመለከት አዘጋጅቶት የነበረውን ጽሁፍ በጉባኤው ላይ ማቅረብ አልቻለም» ሲል ገልጾአል።
በአጠቃላይ አውጣኪን መናፍቅ የሚያሰኝ በቂ ማስረጃ ከጉባኤው በፊት በጉባኤው ወቅትም ሆነ ከጉባኤው በኋላ በቃልም ይሁን በጽሁፍ ያልተገኘ መሆኑን አረጋግጧል። ይህን ከዚህ ቀደም በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ተሰምቶ የማያውቅ አዲስ ምስክርነት የሰሙት የጉባኤው ተሳታፊዎች የነበሩት የማህበሩ አገልጋዮች፣ ልዩ ልዩ ጥያቄዎችን አንስተው የጦፈ ክርክር ያደረጉ ሲሆን፣ ያለምንም ስምምነትና ጉባኤው ለሁለት ተከፍሎ እንደተለያዩ ለማወቅ ተችሏል። በብስጭት በእልክና በቁጣ ከተነሱት ጥያቄዎች መካከል ጥቂቶቹ፡-
1.      በቤተ ክርስቲያናችን አውጣኪ መናፍቅ እንደሆነ ነው የሚታወቀው። አንተ ግን መናፍቅ አይደለም እያልክ ነው። ስለዚህ ቤተክርስቲያናችን ተሳስታለች ማለት ነው ወይ?
2.      በቤተክርስቲያናችን መጻህፍት አውጣኪ መናፍቅ መሆኑ በግልጽ ተቀምጧል። አንተ ግን ልክ አይደለም። መጻህፍቶቹ ተሳስተዋል እያልክ ነው ወይ?
3.      “የቤተክርስቲያን አባቶች አይሳሳቱም፤ አስተምህሮዋቸው ትክክል ነው” ስንል ነው የኖርነው። አንተ ግን ይሳሳታሉ፤ አስተምህሯቸውም ተሳስቷል እያልክ ነው?
4.      አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ “አውጣኪ መናፍቅ ነው” ብሏል። አንተ ደግሞ “የመኳንንቱ ሴራ ነው እንጂ መናፍቅ አይደለም” እያልክ ነው። ማንን እንመን? አባ ጊዮርጊስን ተሳስቷል ብለን እንመንን?
ጥያቄው የቀረበለት ዲ/ን ያረጋል ለተነሱት ጥያቄዎች መልስ ሲሰጥ በጣም በተጎዳና ሀዘን በተሞላ መንፈስ ነበር። መልሱንም ሲሰጥ በመጀመሪያ በተማጽኖ ድምጽ “እባካችሁ በዕውቀት ላይ በር አትቆልፉባት። እስከ ዛሬ ድረስ በቤተክርስቲያናችን በር የተቆለፈባት ይበቃል።” በሚል ተማጽኖ ነበር የጀመረው። በመቀጠልም “የቤተክርስቲያን አባቶች የጻፉትን መጻህፍትም ሆነ የቤተክርስቲያን አባቶችን መቶ በመቶ አንቀበልም። መቶ በመቶ የምንቀበለው መጽሐፍ ቅዱስንና ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ብቻ ነው። ስለዚህ የቤተክርስቲያን አባቶች የጻፉዋቸው መጻሕፍትና እነርሱ ራሳቸው ጥናት ያስፈልጋቸዋል። እነርሱም የማይሳሳቱበት ምክንያት የለም። እነርሱ የተጠቀሙበትን መረጃዎች ከየት እንዳገኙና ከምን ተነስተው እንደ ጻፉ መጠናት አለበት እንጂ ሁሉንም በደፈናው መቀበል ትክክል አይደለም። ለምሳሌ፣ አባ ጊዮርጊስ አውጣኪን አዎን መናፍቅ ብሏል ግን ከምን ተነስቶ? በምን አይነት ማስረጃ የሚለው ምላሽ ያስፈልገዋል። በሁለቱ መካከል የነበረው ቢያንስ የአንድ ሺህ ዓመት ልዩነት መዘንጋት የለበትም። ከዚህ በመነሳት አባ ጊዮርጊስም ቢሆን በአውጣኪ ጉዳይ ሊሳሳት የሚችልበት ክፍተት ሰፊ ነው።” ሲል ዲ/ን ያረጋል ምላሽ ሰጥቷል።
ከዚህ መልስ በመነሳት በማህበሩ አገልጋዮችና በዲ/ን ያረጋል መካከል ትልቅ ልዩነት በመፈጠሩ እነ ዲ/ን ብርሃን አድማስ ጣልቃ ገብተው ልዩነቱን ለማጥበብ ጥረት ሲያደርጉ ነበር። በዚህ አለመግባባት መሀል የጥናት ጽሁፍ አቅራቢው ዲ/ን ያረጋል እውቀትን ለማፈንና ያለበቂ ማስረጃ የሚቀርቡ ውንጀላዎችን በሚመለከት “ነፍሴ በጣም አዝናለች ከዚህ ሀዘኔ የሚያወጣኝም አካል ያለ አይመስለኝም” ሲል ሀሳቡን አጠቃሏል።
በመጨረሻም የጉባኤው ተሰብሳቢዎች በጥናታዊ ጽሁፉ ባለመስማማት ጉባኤውን በጸሎት ሳይዘጉ አንድ በአንድ እየለቀቁ የወጡ ሲሆን፣ ጉባኤውም በጥቂት ሰዎች በጸሎት መዘጋቱን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ዲ/ን ያረጋልን በቅርብ የሚያውቁት እንደሚመሰክሩት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከሰዎች ራሱን ማግለሉንና በሀሳብ ተመስጦ በትካዜ የሚቀመጥ መሆኑን ይናገራሉ። ይህ ያሳየው የባህሪ ለውጥም በማታ ክፍለ ጊዜ በሚማርበት በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በተማሪዎች ዘንድ መነጋገሪያ ሆኗል። ምናልባት እንዲህ ያደረገው ማንም በነፃነት በማይኖርበት በዚያ የብርሀን ጭላንጭል በማይታይበት የጨለምተኞች ስብስብ በሆነው ማህበረ ቅዱሳን ውስጥ ለራሱ “እውነት” የመሰለውን ሃሳብ ማንጸባረቅ መጀመሩ ያስከተለበት ነቀፋና ልወጣበት አልችልም ያለው ሀዘን ሊሆን ይችላል የሚል ጥርጣሬ አለ።
ምንም እንኳ አውጣኪ አለውም አላለው የእርሱ ትምህርት ነው ተብሎ የሚታመንበት ስህተትና እንዲወገዝ ያደረገው ትምህርት በትምህርተ ስጋዌ ላይ “መለኮት ሥጋን ውጦታል” ማለቱና “ክርስቶስን አምላክ ብቻ” በማለት ሰውነቱን መካዱ ነው። በርግጥ ይህ ትምህርት በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ አስተምህሮ ተቀባነት የሌለው ኑፋቄ መሆኑ እሙን ነው፡፡ ይሁን እንጂ ዲያቆኑ እውነትን ፍለጋ የጀመረው ጉዞ በገዛ ወንድሞቹ ሾተላያዊ ባህሪ አስወግዞ ከመስመር ካላወጣው እዛ ላሉት ወንድሞቹ የለውጥ ፊት አውራሪ ሊያደርገው ይችላል ተብሎ ይገመታል፡፡
 ይህ በእንዲህ እንዳለ ለሰው ልጅ ማሰብና የማገናዘብ ነፃነት ቅንጣት ታክል ቦታ የሌላቸው የዚህ ጨለምተኛ ድርጅት ስውር አመራሮች ከየትኛውም ነፃ አስተሳሰብ ጀርባ ሌላ ሰው ወይም የሐይማኖት ድርጅት ይኖራል በሚል የተለመደ አሰራራቸው በዚያው ሰሞን ተሰብስበው በዲ/ያ ያረጋል አበጋዝ ላይ 8 አባለት ያሉት የክትትል ቡድን እንዳሰማራ ከታመኑ ምንጮች የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፡፡
በአንድ ወቅት ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ምረቃ ላይ “እስከ ዛሬ ድረስ አራት ኪሎ ተቀምጣችሁ በየጋዜጣውና በየዌብሳይቱ በሐሜት ትወቅጡን ነበር፡፡ አሁን አውቃችሁዋል፡፡ ተመርቃችኋል፤ እንኳን ደህና መጣችሁ አብረን እንወቀጣለን፡፡” ማለታቸውን አስታወስን፡፡ ምንም የተባለው ተምረው ለተመረቁት ቢሆንም የዕውቀትን ሀሁ፣  ሀ ማለት ለጀመረው ያረጋል አበጋዝ ከእውነተኞቹ ጋር ተቆጥረህ ሰላይ ስለተመደበብህ እንኳን ለዚህ ክብር በቃህ እንለዋለን፡፡ ምንም እንኳ ሌሎቹ ወንድሞች መከራ እየተቀበሉ ያሉት እንዳንተ ለአውጣኪ ተከራክረው ባይሆንም ይህ እውነትን የሚፈልግ መንፈስህ የት እንደሚያደርስህ ባልንጀሮችህ ለማየት ያብቃቸው፡፡
ማህበረ ቅዱሳን ለቤተክርስቲያን ተስፋ የሚሆኑ ሰዎች ሲነሱ በምቀኝነት እየተመለከተ፣ «ተሀድሶ መናፍቅ» የሚል ስም በመለጠፍ የሚያደርገውን ፍረጃ ትቶ፣ በስርዓት ለእውነትና ለእውቀት በማድላት ነገሮችን በጥንቃቄ መመርመር እንዲጀምር በቁርጥ ቀን ልጁ በዲ/ን ያረጋል ምክር እንዲህ እንለዋለን። “እባካችሁ በእውቀት በር አትቆልፉባት። እስከዛሬ ድረስ በቤተክርስቲያናችን በር የተቆለፈባት ይበቃል።”
እኛ የምንለው
·        /ን ያረጋል ዛሬ ገና ትልቅ እውነት ተናገርክ! እኛም እንኳን ደኅና መጣህብለናል። ትልቁ እውነተኛ ምስክርነትህ “የቤተክርስቲያን አባቶች የጻፉትን መጻህፍትም ሆነ የቤተክርስቲያን አባቶችን መቶ በመቶ አንቀበልም። መቶ በመቶ የምንቀበለው መጽሐፍ ቅዱስንና ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ብቻ ነው። ስለዚህ የቤተክርስቲያን አባቶች የጻፉዋቸው መጻሕፍትና እነርሱ ራሳቸው ጥናት ያስፈልጋቸዋል። እነርሱም የማይሳሳቱበት ምክንያት የለም።» የሚለው ነው። እባክህን የማህበርህ ሰዎች ብንነግራቸው አልሰሙንምና ይህንኑ እውነት አስጨብጥልን።
·        ዲ/ን ያረጋል ማህበሩን በመወከል የቤተክርስቲያንን ልጆች “የቤተክርስቲያን አባቶችንንና መጻህፍትን አይቀበሉም። ተሀድሶዎች ናቸው። መጻህፍቱ ስህተት አለባቸው እያሉ ስለሚያስተምሩ ከቤተክርስቲያን ይውጡ፣ ይጥፉ ይወገዙ” እያለ የቤተክርስቲያናችንን ልጆች እንዲባረሩ ከፍተኛ ቅስቀሳ ያደርግ የነበረ መሆኑ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው። አሁን ግን ሲቃወማቸው የነበሩትን ሀሳቦች ማለትም ከቤተክርስቲያን መጻህፍት ችግር ያለባቸው አሉ እና የቤተክርስቲያን አባቶች ሊሳሳቱ ይችላሉ በማለት ማንጸባረቅ መጀመሩ ለማኅበሩ አገልጋዮች ዱብዕዳ ቢሆንም፣ ለአስተዋዮች ግን ግለሰቡ የወንጌልን ጎዳና መጀመሩ ነው ተብሎለታል። እርሱ ሲያሳድደው የነበረውን እውነት ለመስበክ መነሳቱ እውነት ምን ያህል ሀይል እንዳላት ትልቅ ማሳያ ሆኗል። እውነትን ማፈን የትም እንደማያደርስና እንደ ያረጋል ነፍስን ትልቅ ሀዘን ላይ የሚጥል ክፉ መንፈሳዊ ደዌ መሆኑን መረዳት ይቻላል። ከአንድ አመት በፊት ያለምንም ማስረጃ የከሰሳቸውን የቤተክርስቲያን ልጆችን በተመለከተ ትልቅ ሀዘንና ጸጸት እንደተሰማው በዚህ ንግግሩ ውስጥ የገለጸ ይመስላል። ከዚህ ቀደም በግንዛቤ ማስጨበጥ ስም እውነትን ለማፈን በማኅበሩ ስም በወሰዳቸው እርምጃዎች ላይ አሁን ምን አይነት አቋም ይኖረው ይሆን?
·        ዲ/ን ያረጋል ስለአውጣኪ ሲከራከር ከዚህ በፊት በእርሱ አነጋገር ልክ እንደአውጣኪ ተጠርተው ሳይጠየቁና ስለሚያምኑት ነገር ቃላቸው ሳይሰማ «የአይነህ ቀለም አላማረኝም» በሚል ተልካሻ ሰበብና ሃይማኖታዊ ባልሆነ ነገር ግን ሃይማኖታዊ ሽፋን በተሰጠው የማህበረ ቅዱሳን ውንጀላ ከቤተክርስቲያን ስለተባረሩና ዛሬም እንዲባረሩ ማህበሩ ስለከሰሳቸው ሰዎች ምን ይል ይሆን?
·        ዲ/ን ያረጋል አውጣኪን ደግፎ መነሣቱና እርሱን ያወገዙት አባቶች ትክክል አይደሉም በማለት ሀሳቡን በነጻነት መግለጽ መጀመሩ በራሱ ትልቅ ነገር ነው። ሆኖም አውጣኪ እንዲወገዝ ያደረገው በትምህርተ ስጋዌ ላይ መለኮት ሥጋን ውጦታል ማለቱና ክርስቶስን አምላክ ብቻ በማለት ሰውነቱን መካዱ ነው። ይህ ኑፋቄ በቤተ ክርስቲያን የተወገዘ መሆኑ ዘወትር ቢነገርም፣ በተግባር ግን ቤተክርስቲያን ትምህርቱን ተቀብላለች የሚያሰኝ ምልክት ይታያል። ምክንያቱም ዘወትር እየተሰበከ ያለው የክርስቶስ አምላክነት ጎልቶ ሰውነቱ ደብዝዞ ነው። ከዚህ አንጻር አውጣኪ በአፍ ቢወገዝም በተግባር እየተሰበከ ያለው ግን የእርሱ እምነት ነው ማለት ይቻላል። እምነታችን ክርስቶስ ወልድ ዋሕድ፣ ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው የሚል እንጂ አምላክ ብቻ ወይም ሰው ብቻ የሚል አይደለም። በሰውነቱ ቤዛ የሆነልን በአምላክነቱ ያዳነን የክርስቶስ ኢየሱስ አምላክነቱ ተለይቶ ለብቻው ሊሰበክ አይገባም፤ ሰውነቱም ከቤዛነቱ ጋር ተያይዞ ሊሰበክ ይገባል። ስለዚህ ያረጋል አውጣኪ አለአግባብ ተወገዘ ማለት ብቻ ሳይሆን የተወገዘበትን ትምህርት ትክክለኛነት እና ስሕተት በሚገባ ማሳየት አለበት።
·        ዲ/ን ያረጋል «እባካችሁ በዕውቀት ላይ በር አትቆልፉባት። እስከ ዛሬ ድረስ በቤተ ክርስቲያናችን በር የተቆለፈባት ይበቃል።» በማለቱ ሌላ ትልቅ ነገር ተናግሯል። ለአውጣኪና ለትምህርቱ በመከራከር ዋጋ ሊከፍል መዘጋጀቱ ግን ከወንጌል አንጻር ዋጋ ቢስ ነው። እርሱ መከራ መቀበል ካለበት ስለአውጣኪ በመከራከር ሳይሆን ስለክርስቶስ ብቸኛ አዳኝነት መስክሮ ነው መከራ ሊቀበል የሚገባው። ሐዋርያትና ሰማዕታት መከራ የተቀበሉት ስለክርስቶስ ስም ነው እንጂ በሌላ ምክንያት አይደለም። ስለዚህ ያረጋል ሆይ! እባክህን ዋጋ መክፈል ካለብህ በአውጣኪ ስም ሳይሆን በክርስቶስ ስም መከራ ለመቀበል ራስህን አዘጋጅ። የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ይልሃል፤ «ወዳጆች ሆይ፥ በእናንተ መካከል እንደ እሳት ሊፈትናችሁ ስለሚሆነው መከራ ድንቅ ነገር እንደ መጣባችሁ አትደነቁ፤ ነገር ግን ክብሩ ሲገለጥ ደግሞ ሐሤት እያደረጋችሁ ደስ እንዲላችሁ፥ በክርስቶስ መከራ በምትካፈሉበት ልክ ደስ ይበላችሁ። ስለ ክርስቶስ ስም ብትነቀፉ የክብር መንፈስ የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ላይ ያርፋልና ብፁዓን ናችሁ። ከእናንተ ማንም ነፍሰ ገዳይ ወይም ሌባ ወይም ክፉ አድራጊ እንደሚሆን ወይም በሌሎች ጒዳይ እንደሚገባ ሆኖ መከራን አይቀበል፤ ክርስቲያን እንደሚሆን ግን መከራን ቢቀበል ስለዚህ ስም እግዚአብሔርን ያመስግን እንጂ አይፈር።» (1ጴጥ. 4፥12-16)።
http://awdemihret.blogspot.com/

23 comments:

 1. oooooooooooowwwwwwwwwwwwwwwwweeeeeeeeeeeee
  yidenkal

  ReplyDelete
 2. ምንም እንኳ አውጣኪ አለውም አላለው የእርሱ ትምህርት ነው ተብሎ የሚታመንበት ስህተትና እንዲወገዝ ያደረገው ትምህርት በትምህርተ ስጋዌ ላይ “መለኮት ሥጋን ውጦታል” ማለቱና “ክርስቶስን አምላክ ብቻ” በማለት ሰውነቱን መካዱ ነው። በርግጥ ይህ ትምህርት በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ አስተምህሮ ተቀባነት የሌለው ኑፋቄ መሆኑ እሙን ነው፡፡
  ቁምነገሩ የትምህርቱ ምንፍቅና እንጂ የአውጣኪ እምነት አይደለም።ምንፍቅናውን አለመቀበሉን መናገር የሚከለክለው ጠብመንጃ የነበረ አይመስለኝም ስላመነበት ዝምታን መረጠ ስለዚህም ተወገዘ።የምን ያለፈ ታሪክ አምጥቶ ማራገብ ነው?

  ReplyDelete
  Replies
  1. ይህን ከያረጋል ጋር ተነጋገርበት ያለፈ ታሪክ አምጥቶ ያራገበ እርሱ ነው። አባ ሰላማማ ማቅ ያለበትን ውዥንብር ነው ያሳየችን

   Delete
 3. There is no hard evidence to convict Eutychus of the monophysite heresy that the Chalcedonian invented as a counter attack to what is a very weak position of the council.

  ReplyDelete
 4. kesis gregory the nyssaApril 13, 2012 at 11:48 PM

  I graduated in Holy Trinity Theological college . I want tell you WHO Euthychus is , he is just a believer has no profound( enough) knowledge. He said I am a very weak person how God is incaranted from my flesh no no I am a sinner , he said this to respect the highest most God . He didnot deny the incarnation during that time ome priests and bishops confused and they concluded he deny incarnation . He never said my Lord didn't take flesh. There is no evidence . The egytians are hate this guy , so they called him hersey , and then the Ethiopia orthodox church is daughter of alexanderia church condemn him . So there is no evidence , nothing . Aba selama this is untrue so he isnot deny incarnation. So, dn yargel keep it up next read and study hebrew, galatians, and Romans epistles , near you become a true chrisian . God bless you

  ReplyDelete
  Replies
  1. what if, if he read the Gospel of Mathieu specially ye "teraraw sibket" & the James epistle?

   Delete
 5. u said that"እምነታችን ክርስቶስ ወልድ ዋሕድ፣ ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው የሚል እንጂ አምላክ ብቻ ወይም ሰው ብቻ የሚል አይደለም" tadya temelsachu "ዲ/ን ያረጋል ዛሬ ገና ትልቅ እውነት ተናገርክ! እኛም “እንኳን ደኅና መጣህ” ብለናል።" ymtlut lmeindnew? new weys yetelate telat wedaje huno new? ersu baydersibetim abatoch dersewbet awgizewutal!! manim yhun manim nufaqe bizera menafik baybal enkuwan ensu menafik newna!! lemin leand alama atkomum? lemin haymanot atatsenum?

  ReplyDelete
  Replies
  1. enkuwan dehena metahe Yetebalew ewneten fielega megemeru new engi arewosen mewededu aydelem. Yeariyos temiheretma tenekfowal eko besehufu

   Delete
 6. all mk will come to our merdet thank you Jesus christ

  ReplyDelete
 7. ok it is good. tell to those mk people to think about truth and kmowledge.

  ReplyDelete
 8. Aye Yaregal are bekerestos mekera tekbel mindinew awetaki minamin malet. Ye mk sewoche behulu neger new yemiyatmmemachu.

  ReplyDelete
 9. Elelelelelelelele erifiw mk. taotese teferekakese

  ReplyDelete
 10. You are trying to spoil yaregal's goodwill. But we know him well, he is a highly devoted orthox. While u are all tehadso we know. We are watching out all what u doing. But God MK and its members.

  ReplyDelete
 11. kesis gregory the nyssa: You missed very big idea. It is not copts/egyptian fathers who condemned Awutaki, rather it is flabianos who was the arch bishop of constantinople at that time.

  Awutaki is considered as heretic not only by Tewahedo church but both the easter orthodox and catholics consider him as heretic.

  Awutaki did not want to explain his belief in front of the scholars rather he denied his heresy when he went to scholars and he tough heresy when he is in front of laity.

  I don't agree with Yaregal's argument. He cannot have enough resource on Awutaki to deafened Awutaki's teachings.

  I am surprised by Aba selamawoch as they are "Wore aragabi" and MK if they want to spy Yaregal.

  Abaselam and his team usually invite tewahedo's to read some part of bible. Do you think that orthodox preachers don't know/read/understand Hebrew, roman and some other epistles of Paul? Don't be mistaken we read and understand all the bible not partial as your master protestants do.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Thank you. You look logical.... I think they thought that they know a lot about the bible... though they know nothing.

   Delete
 12. “እስከ ዛሬ ድረስ አራት ኪሎ ተቀምጣችሁ በየጋዜጣውና በየዌብሳይቱ በሐሜት ትወቅጡን ነበር፡፡ አሁን አውቃችሁዋል፡፡ ተመርቃችኋል፤ እንኳን ደህና መጣችሁ አብረን እንወቀጣለን፡፡”

  ReplyDelete
 13. every thing u say is true zeegzine! mk don't depend on one person . if he is mistaken, it only his belief or idea not mk ,not our church .but we 'orthodoxawyan' will pray for him so that he come back to the truth.

  ReplyDelete
 14. ወንድወሰን ሶርሳMay 30, 2012 at 5:02 AM

  እኔ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮልጅ ምሩቅ እና ከሀገር ዉጭ ትምህርት በመከታተል ላይ እገኛለሁ፡፡ እንደኔ እንደኔ ስለአንድ ነገር ጫፍ ይዞ ማውራት ጥሩ አይደለም፡፡ የሰው ውግዘትንም መናፈቅም ጥሩ አይደለም፡፡ የአውጣኬ ውግዘት ብዙ ማንበብ ይጠይቃል፡፡ ዛሬ የሚበጀን ከመወጋገዝ ይልቅ መነጋገር ነው፡፡ "የእውነት ምንጭ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው" ሌሎች ነገሮች ሁሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ይመዘናሉ፡፡ ካልተስማሙ ቴቄል ይባላሉ!

  ReplyDelete
 15. enanten man mezagn ena asteyayet sechi aderegachuh?????????

  ReplyDelete
 16. ከሀረርና ድሬደዋ እንዲሁም ከአሜሪካ የተሰባሰባችሁ ፕሮቴስታንት መሆናችሁን እኮ ማኅበረ ቅዱሳን አጋልጧችኋል ስለዚህ ‹‹አባ ሰላም››የተሀድሶ ቡድን ስብስብ ግሎግ መሆኑ ኦርቶዶክሳዊ ምዕመን ሁሉ የሚረዳው ሀቅ ነው፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. የኦርቶዶክስ ቤ/ክርስትያን ብርቅዬ ልጆች እባካችሁ እኛ የቤተክርስቲያናችን ጉዳይ ስለሚመለከተን አስተያየት እንዳንሰጥ አትከልክሉን

   - የእናንተ አባል ካልሆነ የተሃድሶ አባል
   - በናንተ ሳንሱር ካላደረገ የተሃድሶ መዝሙር
   - ›› ›› ›› ›› መጽሃፍ
   - እንደናንተ ካልዘመረ ›› ዘማሪ
   - ›› ካልሰበከ ›› ሰባኪ

   Delete
 17. ስትፈልጉ Published አታድርጉት ማንነታችሁ የተጋለጠ ስለሆነ ተዉት፡፡

  ReplyDelete
 18. 1ኛ ብርሃናተ ዓለም ፓውሎስ ነገርን ሁሉ መርምሩ ብሎናል ያረጋልም
  በአንድ ወቅት በቤተ ክርስትያናችን ውስጥ የተከሰተውን ኩነት ነው የመረመረው ( ያጠናው )፣
  2 ኛ ከጥናቱም በኋላ የደረሰበትን ድምዳሜ ገለጸ ድምዳሜው ስህተት ከሆነ በሌላ ጥናት ማሳመን ሲገባ ቀድሞ የተጻፈውን ለምን ነካህ ብሎ ጉባዓ ለቆ መውጣት አግባብ አይደለም፣
  3ኛ ከያረጋል ድምዳሜ አንጻር ሲታይ ካለ በቂ ፍተሸ እና ጥናት አገልጋዮችን ማውገዝ ለታሪክ ወቀሳ እንደሚዳርግና ቤ/ክርስቲያናችንን ያለ ሰው ያስቀራታልና እባካችሁ በየትኛውም ቡድን ውስጥ ያላችሁ ወንድሞቼ ሊፈታ በሚችል ጥላቻ አትወጋገዙ፡፡

  ReplyDelete