Wednesday, April 18, 2012

ከኦርቶዶክሱ ሰለፊያ - ማኅበረ ቅዱሳን ራሳችንን እንጠብቅ - - - Read PDF

ስለማኅበረ ቅዱሳን ብዙ ስንል ቆይተናል፡፡ በ09/08/04 በተደረገው የፓርላማ ስብሰባ የተሰማው የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር የማህበረ ቅዱሳንን ማንነት ያጋለጠ ነው፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ በሃይማኖት ሽፋን የሚንቀሳቀሱ በኦርቶዶክስ በኩል ማኅበረ ቅዱሳን በእስልምና በኩል ደግሞ ሰለፊያ መሆናቸውን መግለጻቸው ማኅበረ ቅዱሳን ምን እያደረገና በቤተ ክርስቲያን ብቻም ሳይሆን በአገር ላይ የደቀነው አደጋ ምን እንደሚመስል ፍንትው አድርጎ ያሳየ ነው፡፡ ይህም ማኅበሩ እያራመደ ባለው አክራሪነት ሳቢያ ከምን ጊዜውም ይልቅ በመንግስት ጥርስ ውስጥ መግባቱን ያመላክታል፡፡ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስተር « ማህበረ ቅዱሳን » ብለው የማህበሩን ስም በመጥራት አክራሪነቱን በሚዲያ ይፋ ማውጣታቸው በራሱ ትልቅ ነገር ብቻ ሳይሆን ነገሩ ተራ አለመሆኑንም የሚያመልክት ነው፡፡
እንደ ተባለውም  ማህበረ ቅዱሳን በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ የመሸገ ታሊባን እና አልካይዳ መሆኑ ሲነገር መኖሩ የሚታወቅ ቢሆንም ማኅበሩ ላይ ላዩን የሚያሳያቸውን አንዳንድ በጎ የሚመስሉ ነገሮችን ብቻ በመመልከት ያለ ማህበረ ቅዱሳን ቤተክርሰቲያኗ እንደማትኖር የሚናገሩ አንዳንድ የዋሃን የሉም ማለት አይቻልም፡፡ በብዙዎች ዘንድ ግን ማህበሩ በርካታ ድብቅ አጀንዳዎች ያሉት፣ በቤተ ክርስቲያን ከዚህ ቀደም ታይቶም ተሰምቶም የማያውቅ ከመጽሐፍ ቅዱስም ሆነ ከቤተ ክርስቲያኗ አስተምህሮት ውጪ በርካታ ኑፋቄዎችንና የስህተት ትምህርቶችን በማስፋፋት፣ ወጣቱንና የተማረውን ሀይል በጽንፈኛ ቅኝት ለሃይማኖትና ለአገር ተቆርቋሪ በማድረግ ስም አክራሪነትን ሲያስፋፋ ላለፉት 20 አመታት ቆይቷል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግን የጥምቀቱንና ማህበሩ ከኢህአዴግ ህገ መንግስት ጋር የሃይማኖት ነጻነትን በመጋፋት ኢትዮጵያ ውስጥ ከእኔ በቀር ሌላ ሃይማኖት አልመልከት ወደሚል ጽንፍ ያጋደለበትንና « አንድ ሀገር አንድ ሃይማኖት » ያለበትን የጥምቀት አጋጣሚ ብቻ ነው የጠቀሱት፡፡
ሰለፊያ የሙስሊሙ ቁጥር ከክርስቲያኑ ቁጥር ይበልጣል በሚል የተሳሳተና ኢሕገ መንግስታዊ ግንዛቤ እስላማዊ መንግስት በኢትዮጵያ ለማቋቋም ከያዘው አላማ ጋር ማህበረ ቅዱሳንም የሚመሳሰል አቋም እያራመደ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ጠቁመዋል፡፡ እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ ከሆነ አንዳንድ የሰለፊያ እምነት ከታዮች (ወሃቢ) የሚያደርጉት የአክራሪነት እንቅስቃሴ አንዳንድ የማህበረ ቅዱሳን አባላት የሚያራምዱትን ግልባጭ ይመስላል ብለዋል፡፡ አቶ መለስ በድፍኑ ይህን ይበሉ እንጂ ማህበረ ቅዱሳን ከአባይ ወዲህ ማዶ የነበረውን ዘውዳዊውን መንግስት ለመመለስና የቤተ ክህነቱንም ስልጣን በእጁ ለማስገባት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ከአመሰራረቱ ጀምሮ በቅርብ የሚያውቁት ሁሉ የሚመሰክሩት ሀቅ ነው፡፡
ማኅበሩ አክራሪነትን እያስፋፋ ያለው ብዙዎችን በማደናገር መሆኑን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትር የእርሱ ትምህርት ሰለባ የሆኑት ብዙዎች በትምህርት ሊመለሱ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ የሃይማኖት አክራሪነት በአጭሩ ሊቀጭ የሚገባው መሆኑን የጠቆሙ ሲሆን፣ ማህበረ ቅዱሳንን ከወሃቢ ጋር በማገናኘት እንዲሁም ወሀቢን (ሰለፊያን) ከአልካይዳ ጋር በማገናኘት መግለጻቸው፣ ማህበረ ቅዱሳንን የኦርቶዶክስ አልካይዳ አድርገው እንዳስቀመጡ ያሳያል። ለነገሩ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ አጸደቁት እንጂ የማህበሩን የተሳሳተ አካሄድ በመንቀፋቸው ብቻ እንደ መናፍቅ ተቆጥረው ከቤተ ክርስቲያን የተገፉ ብዙዎች ቀደም ብለው ማህበሩን በተግባሩ ታሊባን፣ አልካይዳ፣ ወዘተ ሲሉት መቆየታቸው የሚታወስ ነው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የሰጡትን ተገቢና ትክክለኛ አስተያየት የማህበረ ቅዱሳን ድረገጽ የሆነው አንድ አድርገን ሚያዚያ 10/2004ዓ.ም ባወጣው ጽሁፍ «ማህበረ ቅዱሳንን የሀይማኖት አክራሪነት የሚያራምድ ማህበር አድርገው ነው የሚያስቡት ፤ ሰው ሀይማኖቱን ሲጠብቅ እንዴት አክራሪ ይባላል? ፤ ከአባቶች የተረከቡትን እምነታቸውን ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ ስራ ቢሰሩ እንዴት የሀይማኖት አክራሪዎች ሊባሉ ይችላሉ ? » ሲል ተቃውሞውን አሰምቷል፡፡
እስካሁን ለመታዘብ እንደ ሞከርነውና በየጊዜውም ስንጽፍ እንደ ነበርነው ማኅበረ ቅዱሳን በአገሪቱ በአጠቃላይ ለማስፋፋት እየሞከረ ያለውን አክራሪነት ቀደም ብሎ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እስካሁን ያልታየ አክራሪነትን ሲያስፋፋ ነው የኖረው፡፡ ከዚህ ቀደም በቤተክርስቲያን ታሪክ ያልታወቁ ሰዎችን ቅዱስ፣ ሰማዕት እያለ ህዝቡን ከአምላኩ በማስኮብለል ሲያስት የኖረው በዋናነት ማህበረ ቅዱሳን ነው፡፡ ወጣቱ ትውልድ ማኅበሩ ከሚለው ውጪ አባቶችን፣ መምህራንን  ሰባክያንን ዘማርያንን እንዳያከብርና እንዲጠራጠር ክፉ ዘር ሲዘራ፣ ቤተክርስቲያን ውስጥ ክፍፍል እንዲስፋፋ ሲያደርግ የኖረውም ማህበረ ቅዱሳን ነው፡፡ በሌለው ስልጣንና መብት እርሱ የጠላቸውንና ክፉ ተግባሩን በማጋለጥና ለቤተ ክርስቲያናቸው ያላቸውን ልባዊ ቅናት ያሳዩትን ስም ከማጥፋት እስከ መደብደብና ከቻለም እስከ መግደል ደርሶ የግብር አባቱን የዘርአ ያዕቆብን ስራ ሲሰራ የኖረው ማህበረ ቅዱሳን ነው፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆነው ለቤተ ክርስቲያን የሚበጀውን ውሳኔ እንዳያሰልፉ አባቶችን በመከፋፈልና በጥቅማ ጥቅም በመግዛት ቤተ ክርስቲያን በታሪኳ አይታው የማታውቀውን ትርምስ እየፈጠረ ያለው ማኅበረ ቅዱሳን ነው፡፡ ስለዚህ ማህበረ ቅዱሳን ለቤተ ክርስቲያን ከሰራው በጎ ይልቅ በቤተ ክርስቲያን ላይ የሰራው የተደበቀ ግን ክፉ ስራ ያመዝናል ባይ ነን፡፡ 
ዞሮ ዞሮ ከፖለቲካ መውጣት የማይሆንለት ይኸው የማህበረ ቅዱሳን ድረገጽ አንድ አድርገን በማህበረ ቅዱሳን አክራሪነት ላይ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀረቡትን አቋም ሲቃወም « የኢህአዴግ ትልቁ ችግሩ ከ1997 በኋላ ሰዎች ማህበር ሲፈጥሩ አይኑ ደም ይለብሳል ፤ ጥሩ እቅልፍ ላይ ካለም ይባንናል ፤ ፍርሀት ጥሩ ነው ፍርሀቱ ደግሞ ጠርዙን ያለፈ ይመስለናል ፤ ሰው በሀይማኖት ስም ስለ ቤተክርስትያ ብሎ ማህበር ሲመሰርት በሌላ አይን መመልከት ጤነኝነት አይመስለንም ፤ እናንተ ፖለቲካችሁ ላይ ብትበረቱ እኛ ደግሞ እምነታችን ላይ እንበረታለን ፤  » ነበር ያለው ፡፡ አሁን ይህ ንግግር ከሃይማኖታዊ ሰው ወይስ ከፖለቲካ ካድሬ አፍ የወጣ ነው ? «  ምን ያለበት ምን አይችልም » እንደሚባለው ድረገጹ በሃይማኖት ሽፋን የሚንቀሳቀስ የፖለቲካ ድርጅት መሆኑን በዚህ ንግግሩ ግልጽ አድርጓል፡፡ አንድ አድርገን የፖለቲካ ድረገጽ ባይሆን ኖሮና ለቤተክርስቲያን ተቆርቋሪ ከሆነ ኢህአዴግን ሊሟገት የሚገባው በመንፈሳዊ ጉዳይ መሆን ነበረበት፡፡ እርሱ ግን ወደሚያውቀው ፖለቲካ ነው ያመራው፡፡ የልቡን ተናግሮ ሲያበቃ ደግሞ « እናንተ ፖለቲካችሁ ላይ ብትበረቱ እኛ ደግሞ እምነታችን ላይ እንበረታለን » ማለቱ ደግሞ የሚገርም ነው፡፡
ለማንኛውም የአክራሪው ማኅበረ ቅዱሳን ትምህርትና ፕሮፓጋንዳ ሰለባ መሆን ይብቃን፣ በማህበሩ ጋዜጦችና መጽሔቶች በየድረ ገጾች ሁሉ ወደ ቤተ ክርስቲያናችን የገቡና ሕዝቡን ከወንጌል ወደ ተረት የመለሱ የስህተት ትምህርቶችን ሁሉ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ከአሁኑ እያረማችሁ የቤተ ክርስቲያንን መንፈሳዊ ውበት ለመመለስ እንድትተጉ በጌታ ፍቅር እንጠይቃችኋለን፡፡ የዚህን አሸባሪና አክራሪ ማኅበር ድብቅ አጀንዳ ባለመረዳት ለቤተ ክርስቲያን የረዳችሁ መስሏችሁ እርሱን እየደገፋችሁ ያላችሁ ኦርቶዶክሳውያን ወገኖቻችን ለቤተ ክርስቲያናችሁ ያላችሁን ቅናት እናደንቃለን፡፡ ነገር ግን ማኅበረ ቅዱሳን አልጠግብ ባይ ነጋዴ መሆኑን አውቃችሁ ድጋፋችሁን በቀጥታ ለቤተ ክርስቲያን በመስጠት ማኅበሩ ለሽፍትነት ስራ የሚያውለውን የገንዘብ አቅሙን በማዳከም ከቤተ ክርስቲያን ጎን እንድትቆሙ እናሳስባችኋለን፡፡

32 comments:

 1. ቂቂቂቂ ውይ እንደው ሆዴን አቆሰላችሁት በሳቅ በስማም እንደው ደስ የምትሉ ናችሁ እኔ የማንበብ ችግር ያለባችሁ ነበረ የሚመስለኝ ለካ የመስማትም ችግር አለባችሁ፡፡

  ReplyDelete
 2. abet abet wore tegegito temotual....dedeb hulu

  ReplyDelete
 3. mk knetu derejet new. abatu yeweset abat diyabilos new. yemidekmewme yediyabilosene mengest bemedertu lay lemangese new. ayesakletem mekeneyatum ega yeyacenew getan new.

  ReplyDelete
  Replies
  1. This is a sound of pente....go hell and shout on your adarash? we are very proude of MK, they are working and working..you dogs follow them and cry. Melese Zenawi gave them recognition..he didn't undermine them as you stupid guys think.

   Delete
 4. ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተናገሩት በሰው ብዛት እንጂ በአክራሪነትና በአሸባሪነት ላይ አይደላም

  ReplyDelete
 5. ke Egziabher kehonu Yibezalu Ke Aganinit Kehonu Yitefalu....Egna gin betarikim hone bezemenachin Enideminayew Sile betekrstian bilew Genizebachewin,Gulibetachewin, Giziachewi,Nebisachewinim bihon yesetu sewoch Egziabher siakebirachew kef kef siadergachew enji yayenew siatefachew Alayenim neger gin Be anitsaru betekrstianin sikawemu ena sigefu yeneberu menigsitat Sim Aterarachew tefito siwaredu new yayenew....Wededinim telanim ke ewinet ena kebetekrstian gon yekome Ayiwedkim yihinin Demo Begilits ke Mahiber kidusan Agelgilot sifat ena Ediget Eyayenew new....Yikrta Addrgulign ena ye Tekilay minstru Geletsana Yenanite Misikrinet Anid Hagerigna Ababal Asitawesegn..."AHIYA FESA BIYE AFNCHAYEN ALYIZIM...."....Ebakachihun ena yemahibere kidusan Abal Ayidelehum yihe yegil Amelekakete new Yemahiberu Ageligilot enikuan Legna Le ETHIOPIAWYAN yikir ena le Alemu hulu Enidemiterif Gin minim tirtir yelegnim ....Huligize ke ewinet ga Komen sile ewinet meskiren Sile ewinet noren Lemalef Yabikan ....HULUM yalifal Menigstatim yalifalu Ewinet Gin Atitefam EGZIABHER AMILAK HULUN YAYAL.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Egzer yisteh wondime? Me too I am not a a member of MK but I always I appreciate them ...they stand for the church and fight those who want to reform and give it a shape of protestant. There are people who are being paid from Protestant church like this bloger admins. who attack MK. even what Prime minister said is a recognition to MK...he never said they are terrorist etc.

   Delete
 6. kendenante aynetu lbetkerstyanew ykomenew belo betkerstyanene kmiatefa mahiber ytibken belane bentselye new ymishalen dgmo mahiberu enante kalachut neger gar meanme selmayagenaghew menme ymiaschenke nger yelweme zeme belachu wera ataragbu

  ReplyDelete
 7. ጠቅላይ ሚኒሰተሩ ይህን ያሉት አንተና እንደአንተ ያሉ ውሸታሞች በሚሰጡአቸው የተሰሳተ መረጃ ነው፡፡

  ReplyDelete
 8. I agree!

  The innocent members of MK should be aware of the cult they are following and its dangers. They must distance themselves from this evil and turn to the Lord Jesus Christ our Savior.

  I pray the MK members be delivered from the darkness imposed up on them by this evil organization.

  ReplyDelete
  Replies
  1. pa pa pa sebkeh motehal...yanetn "Jesus of Martin" ezaw yazaew ...we have Jesus of st Marry. Don't pray for MK. pray for yourself to bee free from devil that involved in you on behalf of Jesus.

   Delete
 9. I really appreciate Ato Melese. He promoted MK. You see how challenging is Mk? It influences the prime minister like Alkaida does.
  From now on what ever mk exists or not it is in the heart of all sunday schools and those who are always striving to protect the mother land and the church. by no means Menafikans and pagans will not affect the church as they want. Thank God!

  ReplyDelete
  Replies
  1. Yes, thank you man. This is the exact meaning ....he prompt it.

   Delete
  2. you mean he also promote Alqaeda and Selefiye, poverty and backwardness, We Apreciate our PM, he speak about our dangers

   Delete
 10. ማኅበረ ቅዱሳንን ሰይጣን እንኳን ቢቃወም ከእርሱ ጋር እንደምትቆሙ ያሳይባችኋል። የተሰጣችሁ የቤት ሥራ ቤቱን ከማፍረስ በፊት አጥሩን መንቀል ስለሆነ ቤተ ክርስቲያንን ለማጥፋት ማኅበረ ቅዱሳንን በሆነ ባልሆነ መወንጀል የአቡሃ ለሀሰት ልጆች መሆናችሁን ያሳይባችኋል።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወንድሜ! በማህበረ ቅዱሳን (የደህንነት ድርጅት) እሩቡን ያህል ገና አልተገለጸልህም። ጠቅላይ ሚኒስትሩም ለብቻቸው ሲጠቀሙበት ሰንብተው አሁን ከሌሎች ድርጅቶች ጋር መጋራት ሲጀምሩ አብረው መጋለጥ ጀመሩ። አልሰማ አላችሁ እንጂ ከዚህ በፊት ነግሪያችሁ ነበር። እንዲህ ብዬ፥ “የእባቡ (የማህበረ ቅዱሳን ድርጅት) ጂራቱ ተቆርጧል፤ ጭንቅላቱ ነው አራት ኪሎ እና ስድስት ኪሎ የመሸገው። ለእርሱም የሚመለከተው ክፍል ጸሎቱን በሱባዔ ጀምሮለታል እናም በቅርቡ ይፋ ሲሆን በራሱ አንደበት ማንነቱን ይፋ ያደርጋል።” እሄው አሁን ጀመረላችሁ በርቱና ስሙት። ማህበረ ቅዱሳን ማለት ፍቅርን የማይወድ የፍቅር ቂመኛ፣ ጳጳስን ከጳጳስ፣ ቤተክርስቲያንን ከቤተክርስቲያን፣ ቄስን ከቄስ፣ ምዕምናን ከምዕምናን፣ ወጣቱን ከወጣት፣ቤተሰብን ከዘመድ፣ ሚስትን ከባል፣ ልጆችን ከወላጅ እና ሕዝብን ከሀገር እያጋጨ የሚሳለቅ የበግ ለምድ ለባሽ የተዋጣለት እርኩስ የደህንነት ድርጅት ነው። ብጹዐን ጳጳሳት በፍጹም እንዲታረቁ እንደማይፈልግ ከአባሎቹ ፉከራ ታውቋል። ካዲያ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ምን የባህሪ ልዩነት አላቸው? እኔ ኢትዮጵያን በዘር፣ በሐይማኖትና በጎሳ አለየሁም ማህበረ ቅዱሳን (ማህበረ ዲያብሎስ) ነው እንጂ የሚሉት አያዋጣቸውም ሁለቱም ተጠያቂዎች ናቸው። አብረው አይደል እንዴ ያዋቀሩት! አመላቸው ነው አንድን ድርጅት ይጠቀሙበትና ጊዜ ሲጥለው አብረው የጥሉታል።

   Delete
 11. That is 100% true. HOW can Andadregen which is mk web called our pm melese block head. This is violation he has responsible for citizen safety to protect from terrerist action,so we all real eotc support him to save our country. The elemetnts and cells of mk terrerists are collect money here in USA, WE just inform to seceret service to control this kind of finacial transaction.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Because he's a block head! And it's true.

   Delete
 12. Very Soon Weyane will go, at that time even you will not have pace in our church to creat chaoes. God is seeing everything.... and Ehiopins also know everything....

  ReplyDelete
 13. ወገኖች!!

  አሁን መጠንቀቅ ያለብን እንደ ኢሕአፓ ወቅት ንጹሑ ወገናችን ስውር የማህበሩን ዓላማ በአገርና በባንዲራ ስም ተታሎ ሳይረዳ ሰለባ እንዳይሆን ነው መጣር ያለብን::

  መንግሥትም ቢሆን ለቤተ ክርስቲያናችን ትንሳኤ ብሎ ባይሆንም የሚወስደውን እርምጃ በጥንቃቄና አገርን በሚጠቅም መልኩ በማጣራት መሆን ይኖርበታል:: እኛም የቤተ ክርስቲያናችንን ወደ ወንጌል መመለስና ለምድራችን ሁለንተናዊ ፈውስ እንድትሠራ አጥብቀን የምንፈልግና የዚህ ማኅበር ጡጫ ያረፈብን ልጆቿ የዚህ ማህበር አባላት ወደ እውነቱ እንዲመለሱ እንጂ ክፉ ነገር ሲደርስባቸው ለማየት ጫራሽ አንፈልግምና እንጸልይ እንጸልይ:: የፍቅር ልጆች ስለሆን ከፍቅር ሌላ ምንም ዓላማ ወይም እዳ ወይም ሱስ የለብንም:: ልባችን የጌታ ልብ ነውና::

  ለሁሉም የጌታ ምህረት ለሕዛብችን ይዝነብለት!!

  የወገኖቻችንን ክፉና አታላይ መንፈስ ጋር መቼም ቢሆን እንደተክለሃይማኖት እርቅ የለንም::

  ለመንግሥትም ጌታ ልቦና ይስጠው!!

  ሰላም ሁኑልኝ

  ሰላም ነኝ

  ReplyDelete
 14. Is that my ear or I heard PM saying "some (Andand) members of MK" ? I think he didn't said "MK, Most MK members or the majority" So dear writer would you argue defending all members? Do you have intelligence service like him or do you have examined all the minds of the members that they have no such idea?

  I think in all religions there are people who would like to take advantage of the innocent followers who honestly seek the Kingdom of God. Religious groups or churches and mosques need to be shelters for all who would like spiritual freedom. On the contrary, members of any religion could form or join parties and promote philosophies they think will help the people to lead a better life in this world.

  Please brothers and sisters let's not mix religion with politics.That will not be useful for us and the kingdom of God too.

  ReplyDelete
 15. አባ ሰላማዎች

  ነውር አታውቁም እንዴ?

  ከዚህ በፊት ማህበረ ቅዱሳንን የምትከሱት "ከወያኔ ጋር ተለጥፎ ህዝባችንን ለጭቆና ዳረገው: አስበዘበዘው" እያላችሁ ነበር:: ዛሬ ደግሞ ጠቅላይ ሚንስትሩ ማህበረ ቅዱሳንን ሲያወግዙ: ራሳችሁን እንደመታዘብ እናንተም አብራችሁ ታወግዛላችሁ እንዴ:: እውነት ይዛችሁ የምትቃወሙ ይመስለኝ ነበር ለካስ "ለመቃወም ብቻ" ነው የምትቃወሙት::

  ReplyDelete
 16. ገና ....ማህበረ ቅዱሳን ሶማሊያ ወይም ፓኪስታን ሂዶ ቦንብ አፈነዳ የሚል ዜና እንሰማልን....አባ ሰላማ ብሎግን ያኑርልን!! እኛ እናውራ ....ማ/ቅ ስራውን ይስራ....ፈራጁ እግዚአብሔር ፊት ስንቀርብ ምን እናወራ ይሆን?
  ታዛቢው

  ReplyDelete
  Replies
  1. ጥሩ ነገር ለመናገር ምነው አፋችሁ ዘገነነው... ገፃችሁ በሙሉ እኮ ማህበረ ቅዱሳን ላይ ሆነ ምናለ ወንጌል ብቻ ብትዘሩና አንድ ወገን ላይ ትኩረት ባታደርጉ ... እያስታወቀባችሁ ነውኮ....እረ እባካችሁ በደም ግፍፊ ቃላት አታውጡ... እየተምታታባችሁ ነውና ከአንደበታችሁ ቆጠብ በሉ ...

   Delete
 17. የጅሎች ጥርቅም ናችሁ ? አቶ መለስ ምን ለማለት እንደፈለገ በራሱ በግልጽ አላስቀመጠም:: አስቀምጦ ቢሆንስ እርሳቸው ያሉት በሙሉ እውነት ነው ብላችሁ ታምናላችሁ? ወሬ ጣላን ስራና ፍቅር ይቅደም:: ማህበረ ቅዱሳን ችግሮች አሉበት እናንተ የምትሉት ግን በአብዛኛው በጥላቻ ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ተቀባይነቱ ባዶ ነው::
  ይልቅ ራሳችሁን ለውጡና ለሃገርና ለቤተ ክርስቲያን የሚጠቅም ስራ በምክክር ስሩ:: መልካም የትንሳኤ ሳምንት::

  ReplyDelete
 18. Good Job, Mr. Melese

  ReplyDelete
 19. ወንድሜ! በማህበረ ቅዱሳን (የደህንነት ድርጅት) እሩቡን ያህል ገና አልተገለጸልህም። ጠቅላይ ሚኒስትሩም ለብቻቸው ሲጠቀሙበት ሰንብተው አሁን ከሌሎች ድርጅቶች ጋር መጋራት ሲጀምሩ አብረው መጋለጥ ጀመሩ። አልሰማ አላችሁ እንጂ ከዚህ በፊት ነግሪያችሁ ነበር። እንዲህ ብዬ፥ “የእባቡ (የማህበረ ቅዱሳን ድርጅት) ጂራቱ ተቆርጧል፤ ጭንቅላቱ ነው አራት ኪሎ እና ስድስት ኪሎ የመሸገው። ለእርሱም የሚመለከተው ክፍል ጸሎቱን በሱባዔ ጀምሮለታል እናም በቅርቡ ይፋ ሲሆን በራሱ አንደበት ማንነቱን ይፋ ያደርጋል።” እሄው አሁን ጀመረላችሁ በርቱና ስሙት። ማህበረ ቅዱሳን ማለት ፍቅርን የማይወድ የፍቅር ቂመኛ፣ ጳጳስን ከጳጳስ፣ ቤተክርስቲያንን ከቤተክርስቲያን፣ ቄስን ከቄስ፣ ምዕምናን ከምዕምናን፣ ወጣቱን ከወጣት፣ቤተሰብን ከዘመድ፣ ሚስትን ከባል፣ ልጆችን ከወላጅ እና ሕዝብን ከሀገር እያጋጨ የሚሳለቅ የበግ ለምድ ለባሽ የተዋጣለት እርኩስ የደህንነት ድርጅት ነው። ብጹዐን ጳጳሳት በፍጹም እንዲታረቁ እንደማይፈልግ ከአባሎቹ ፉከራ ታውቋል። ካዲያ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ምን የባህሪ ልዩነት አላቸው? እኔ ኢትዮጵያን በዘር፣ በሐይማኖትና በጎሳ አለየሁም ማህበረ ቅዱሳን (ማህበረ ዲያብሎስ) ነው እንጂ የሚሉት አያዋጣቸውም ሁለቱም ተጠያቂዎች ናቸው። አብረው አይደል እንዴ ያዋቀሩት! አመላቸው ነው አንድን ድርጅት ይጠቀሙበትና ጊዜ ሲጥለው አብረው የጥሉታል።

  ReplyDelete
 20. በትክክል የመስማት ችግር አለባችሁ፡፡ የኢትዮጵያን ህዝብ ቁጥር አስመልክቶ ጠቅላይ ሚንስትሩ በሰጡት አስተያየት ላይ ሰለፊ የሙስሊሙ ቁጥር ይበልጣል ብሎ እንደሚከራከር በግልባጩ ደግሞ ማህበረ ቅዱሳን አይደለም የክርስትያኑ ይበልጣል ብሎ አቋም መያዙን ከመጥቀስ ዉጪ እንዴት አድርጋችሁ ከአልቃይዳ ጋር ለማያያዝ እንደሞከራችሁ ገርሞኛል፡፡ ቁርጣችሁን እወቁ! የክርስቲያኑ ቁጥር ይበልጣል ብቻ ሳይሆን የበለጠ እንዲጨምር የበለጠ ጠንክሮ ይሰራል ተብሎ ይታመናል፡፡ ይህ ካልተዋጠላችሁ...አልቃየይዳና ሰለፊ እናንተ ናችሁ፡፡

  ReplyDelete
 21. ገና ....ማህበረ ቅዱሳን ሶማሊያ ወይም ፓኪስታን ሂዶ ቦንብ አፈነዳ የሚል ዜና እንሰማልን....አባ ሰላማ ብሎግን ያኑርልን!! እኛ እናውራ ....ማ/ቅ ስራውን ይስራ....ፈራጁ እግዚአብሔር ፊት ስንቀርብ ምን እናወራ ይሆን?
  ታዛቢው

  ReplyDelete
  Replies
  1. they have already bombed Hawasa and USA

   Delete
 22. Egziabher yesteh wedaje. Eine tazebhuacheh men ainet thadeso endehonachehu. Ewnet Ewnet newew. Egiziabehere ewnet new. MK degemo ewnetegna yebetekristian tkorkuari ena lewnet ykome begziabher agzinet yemeramedu ewnetega krstianoch nache. Enante gen bewnet weshetamoch nachehu. Ahunma weshetachehu betame bhizbu zende eyetawkebachehu newena erefu. Egiziabhere bewnet lefered yemetal.

  ReplyDelete