Thursday, April 19, 2012

ማህበረ ቅዱሳንና ሰለፊያ!! ግልባጩ ማነው? - - - Read PDF

ከአውደ ምሕረት የተወሰደ

የማህበረ ቅዱሳን ሰለባ የሆኑ ብዙ የቤተክርስቲያን አባቶችና ልጆች ማቅን በአሸባሪነት ከፈረጁት ዓመታት የተቆጠሩ ቢሆንም፣ ማቅ ግን እንዲህ የሚሉኝ ለቤተ ክርስቲያን ጥብቅና ስለቆምኩ ነው በሚል ራሱን ሲከላከል ቆይቷል። ማህበሩ አሸባሪ የመሆኑ ጉዳይም በአንዳንዶች ዘንድ እንደ ስድበ ሲቆጠር መቆየቱ ይታወሳል። ለማኅበሩ ይህ ስም የተሰጠው በከንቱ አልነበረም። ስራው በአክራሪ ሙስሊሞች ከሚካሄደው የበለጠ እንጂ ያላነሰ ሆኖ ስለተገኘ ነበር ይህ የግብር ስም የወጣለት።
 ዕድሜ የሰጠው ሰው ብዙ ያያልና ይኸው የማህበሩ የግብር ስም ከትናንት በስቲያ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኤፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር በክቡር አቶ መለስ ዜናዊ ጸድቋል። በማኅበሩ ሲገፉና ሲነቀፉ ለኖሩ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ይህ እንደ አንድ ትልቅ ድል የሚቆጠር ነው። እንኳንም በትክክል የወጣለት የግብር ስም በማኅበሩ ዘንድ እንደ ስድብ ከመቆጠር አልፎ ትክክለኛ የማህበረ ቅዱሳንን ማንነት የሚገልጥ ስም ሆኖ ተነገረ! ይህን የተናገሩት ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትራችን መሆናቸው ትልቅ ግምት የሚሰጠው ብቻ ሳይሆን ማኅበረ ቅዱሳን ቤተክርስቲያንን ከማሸበር አልፎ አገርንም ለማተራመስ ትልቅ አላማ እንዳለው በመንግስት በኩል የተደረሰበት መሆኑን ያመለክታል።   
በአሁኑ ጊዜ ማኅበረ ቅዱሳን ማነው? ምንስ ነው የሚሰራው? አላማው ምንድነው ነው? ለሚሉት ጥያቄዎች ምላሽ የሚፈልገው የህብረተሰብ ቁጥር እየበዛ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ  ሰለፊያን አስመለክተው ሲናገሩ ሰለፊያ የማኅበረ ቅዱሳን ግልባጭ መሆኑን በግልጽ ቋንቋ እንዲህ ሲሉ ነግረውናል። “አንዳንድ የሰለፊ እምነት ተከታዮች አንዳንድ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት የሚያራምዱትን ግልባጭ ሲያራምዱ ይታያሉ።” ማኅበረ ቅዱሳን ለክፋት መምህር እንጂ ደቀመዝሙር እንደማይሆን የተረዱት ጠቅላይ ሚኒስትር ማኅበረ ቅዱሳን ስልቶቹንና አካሄዱን ለሰለፊያ ማውረሱን በማያሻማ መንገድ ገልጸዋል፡፡
መቼም ማቅ የሚሰራውን ስራ አስተውሎ ያየ ሰው በማቅና በሰለፊያ(ወሀቢያ) መካካል ያለውን የመንፈስ አንድነት በቀላሉ ይረዳል። ለማስረጃ ያህል፡-
1.      ሰለፊያ(ወሀቢያ) ሃሳቡን ለማስፈጸም እስከ መጨረሻው ጥግ ድረስ ሄዶ ሰዎችን ሊገድል ይችላል። ማቅም ከአባቱ ከዘርኣ ያዕቆብ ተምሮ በመንፈሳዊነትና በሀይማኖት ፍቅር ስም ሰዎችን ማሰቃየት መደብደብና መግረፍ ተገቢ ነው ብሎ ያምናል። እያደረገ ያለውም ይሔንን ነው። ከመቀሌ እስከ ቦረና ከሐረር አስከ ጋምቤላ ከጎንደር እስከ ሐዋሳ እንዲሁም በክብረመንግስት፣ በሻኪሶ፣ በአለታወንዶ፣ በአላባ፣ በድሬዳዋ፣ በደሴ፣ በባኮ እና በአዲስ አበባ የፈጸማቸው ድርጊቶች ለዚህ ትክክለኛ ምሳሌ ናቸው፡፡
 
2.     ሰለፊያ ትምህርቱን ለማስተላለፍ የሚጠቀምበት መንገድ የሃይማኖቱን በጎ ጎን ማሳየት አይደለም፤ የእነርሱ የሀይማኖት ማስፋፋያ መንገድ አሉታዊ ነው። ማቅም ስለቤተክርስቲያን ትምህርቶች መጽሀፍ ቅዱስን ተመርኩዞ የሚያስተምረው መሰረታዊ ነገር የለውም። የማቅ ዶግማ “መናፍቃን ተሀድሶ” የሚሉትን የስድብ ስሞች እያነሳ የቤተክርስቲያንን ልጆች ማሳደድ ብቻ ነው። በየቀኑም እንዲህ አደረጉ ይህን ፈጸሙ እያለ ሽብር በመንዛት ለኦርቶዶክሳውያን “እኔ ባልኖር ኖሮ መንፈስ ቅዱስማ ቤተ ክርስቲያንን መጠበቅ አቁሟል፤ “የጊዜው መንፈስ ቅዱስ” እኔ ነኝ፤ ትክክለኛው የቤተ ክርስቲያን ጠባቂ” በማለት በመንፈስ ቅዱስ ቦታ ራሱን አስቀምጦ እኔን ብቻ ስሙ እያለ ምእመኑ በእምነት ሳይሆን በስጋት እንዲመላለስ እያደረገ ይገኛል።

3.     ሰለፊያ የአጭር ጊዜ እቅዱ መጅሊሱን መቆጣጠር ሲሆን፣ የረጅም ጊዜ እቅዱ ደግሞ የመንግስትን ሥልጣን መያዝ ነው። ማቅ ልክ እንደ ወሀቢያ የአጭር ጊዜ እቅዱ ቤተክህነትን መቆጣጠር ሲሆን የረዥም ጊዜ እቅዱ ደግሞ የመንግስትን ስልጣን መያዝ ነው። ቤተክህነትን ለመቆጣጠር በሙሉ ሀይሉ እየሰራ ይገኛል። ጳጳሳትን በተለያዩ ስጋዊ  ጥቅሞች በመደለልና በማሳሳት፣ አልሆን ሲለው ደግሞ በነውራቸው በማስፈራራት የማህበሩ ፍላጎት አስፈጻሚ ለማድረግ እየተጋ ይገኛል። እስካሁንም በእግዚአብሔር እርዳታ የሚፈልገውን ነገር መስፈጸም አልቻለም እንጂ በተለይ በሲኖዶስ ስብሰባዎች ሁሉ ማቅ አጀንዳ በአንዳንድ የሲኖዶስ አባላት በኩል አስቅርቦ የሚፈልገውን ውሳኔ ለማስወሰን አመራሮቹ እንቅልፍ አጥተው እንደሚያድሩ ቤተ ክህነቱን በቅርብ የምናውቅ ሰዎች የምናስተውለው እውነት ነው። የመንግስትን ስልጣን በተመለከተ ያላቸው ሀሳብ ምን እንደሆነ እንኳን ማህበሩን ቀርበን አይደለም በሩቅም አይተነው የምንረዳው ሀቅ ነው። በተለያየ ጊዜ የግል ጋዜጣን ፈንድ አድርጎ ከማቋቋም ጀምሮ ክፍተት ባገኘ ቁጥር ጭንቅላቱን ለማስገባት የሚያደርገውን ጥረት ለተመለከተ ማህበሩ ፖለቲካዊ እንጂ መንፈሳዊ አቋም እንደሌለው በቀላሉ ሊረዳ ይችላል።

4.     ሰለፊያ ቀድሞ በመጮህ የሙስሊሙን ህብረተሰብ አመለካከት ለመሳብ በአህባሽ ላይ የተቀነባበረ ዘመቻ እንዳደረገ ሁሉ ማቅም እውነተኛ የቤተክርስቲያን ልጆችን ያልሆኑትን ሆኑ ያላደረጉትን አደረጉ፣ ያልረገጡትን ወረሱ እያለ በሀሰት የስም ማጥፋት ዘመቻ በማድረግ የዋሁን ሕዝባችንን በማሳሳት ላይ ይገኛል።

5.     ሰለፊያ ፍላጎቱ እስካልተሳካ ድረስ በመስጊድ አካባቢ የፈለገው ነገር ቢፈጸም ግድ የለውም። ማቅም አላማው ይሳካ እንጂ ህዝቡ የእግዚአብሔርን ቃል ቢማር ባይማር ወጣቱ ወደ ቤተክርስቲያን ቢመለስ ባይመለስ ምንም ግድ የለውም። ወጣቱ እግዚአብሔርን አውቆ የእነርሱ እጅ ያን ቤተ ክርስቲያን መቆጣጠር ከሚተው ይልቅ እነርሱ ያን ቤተ ክርስቲያን ተቆጣጥረው ወጣቱ ወደ ጫት ቤት ቢገሰግስ ይመርጣሉ። ካለፈው አንድና ሁለት ዓመት ወዲህ በስብከተ ወንጌልና በመንፈሳዊ ዝማሬዎች ወጣቱን ትውልድ ወደ ቤተ ክርስቲያን እየመለሱ ያሉትን የቤተክርስቲያን ልጆች ስም በማጥፋት ከፍተኛ ገንዘብ መድቦ በከፈተው ዘመቻ እየተገኘ ያለው ውጤትም የሚያሳየው ያንን ነው። ብዙዎች ከቤተክርስቲያን እየሸሹ ነው። ማኅበሩ ለመቆጣጠር እጁን ባስገባባቸው አንዳንድ አድባራት ውስጥ የሚታየው ነገርም እጅግ አሳሳቢ ነው። በወጣቱ ትውልድ ደምቀው ይታዩ የነበሩ የሰርክ መርሀግብሮች የመቃብር ቤት እንደሚመስሉ ዘወትር የምናየው እውነት ነው።

በአጠቃለይ ማቅንና ሰለፊያን የማያመሳስላቸው ነገር ቢኖር እቅዳቸውን የሚያስፈጽሙበት ቀዳሚው ቦታ ብቻ ነው፡፡ ሰለፊያ መጅሊሱን ሲፈልግ ማቅ ደግሞ ሲኖዶሱን መቆጣጠር ይፈልጋል፡፡ ሁለቱም ይህን እቅዳቸውን ቢያሳኩ(አያሳኩም እንጂ) ቀጣዩ ኢላማቸው ስልጣን በመሖኑ እኔ እሻል እኔ እሻል የሚለው አስተሳሰባቸው ወደ ለየለት ጦርነት ሊያመራቸው ይችላል፡፡ ሁለት የአሸባሪ ቡድኖች በአንድ ከተማ ላይ መኖር እንደማይችሉ እኔ እበልጥ በሚል ስሜት አገሪቱን ከማጥፋታቸው በፊት አንድ ሊባሉ ይገባል፡፡
 http://awdemihret.blogspot.com/ የተወሰደ

55 comments:

 1. You guys are telling us again and again about MK. We know it. We don't need your explanation... They are working hard to keep the true church. 'ye-alem aydelachihumna alem yitelachihual newu..." negeru.

  Hello - Mk, pls keep it up! so far you did a great job! We know what you have done.

  ReplyDelete
  Replies
  1. you mean he torcher the killing the unfaithfulness. evry body knows what their work is dont make ur self full. truely they are alkayeda

   Delete
  2. it is very wrong periciepion .beacouse since one body stand for his priority without touch others right it is the way of democracy.so mahibere kidusan is the protector or the solijer of our religon from other powerful inistitution which are supported by several forigne pro.

   Delete
 2. shame on you.Of all people you quot the arrogant, narrow minded,racist, selfish, killer etc etc MEles Zenawi to accuse Mehbre Kidusan.This is just an insult for all Ethiopians who are sick and tired of woyane.Your President Melese Zenawi hate the existence of Our beloved country Ethiopia and he tried very very hard to destroy it.But because of all Ethiopians( Christians and Muslims)are children of God Ethiopia still survive and will survive forever. For your information I am not Mahebere kidusan.
  You really kneel and pray.

  ReplyDelete
 3. This write show us hw much u are stupid. u praise PM Meles Zenawi and curse Emp. Zerayacob. Hw cld we trust u, one day u will curse the PM. Dont try to mix religion and politics. FYI I hate maheber at all I have only one mahiber that is EOC.

  ReplyDelete
  Replies
  1. if u know zeryazobe u didnt say these

   Delete
 4. please dont be such silly. please teach us bible and let us know the truth, then we will follow the truth. it is really boring to see peoples name again and again. by the way you are advertsing the MK in positive way. rather why dont you teach us. you raised valid discussion points like 'tinte abiso', please continue on that issue.
  thanks,

  ReplyDelete
 5. የሃይማኖት ክርክራችሁን ዘወትር እከታተል ነበር።እውነትን ለመፈለግ መትጋታችሁንም እወደው ነበር።ምንም እንኳ ማህበረ ቅዱሳንን ብትጠሉ ምንም እንኳ ትምህርታቸው ባይጥማቸሁም መለስ ዜናዊን የመሰለ አረመኔን እዚህ ውስጥ ማጣቀሻ አድርጋችሁ ማስገባት የለባችሁም።ዋነኛው ቀንደኛው ጠላታችሁ መለስ እንጂ ማህበረ ቅዱሳን አይደለም።

  ስጋ የለበሰ ሰይጣን ገላጋይ ዳኛ ሊሆን አይገባም።መለስ አረመኔ ነው።የክርስትያኑንን ደም እንዲሁ በከንቱ የሚያፈስ ነው።ይህን ሰው ከማስወገድ በቀር ለማህበረ ቅዱሳን የማይገባ ስም ስለሰጠ ብቻ እርሱን ማጣቀሻ ማድረግ የለባችሁም።

  ሞት ለመለስ ዜናዊና ለዘረኛ ቡድኑ።ኢትዮጵያና ህዝቧ ብቻ ለዘላለም ይኑሩ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. this conversation is insult or touching human rights .it self or one of the road of dissmissing our religen. because many chritian followers specially youth christians conserve their religon since the becoming of mahibere kidusan.why our leaders becoming onti once religon and pro the other?

   Delete
  2. Meles is a good leader

   Delete
 6. በጣም የሚያሳዝንና ለቤተክርስትያን ቆሜያለሁ ከሚል ሰው የማይጠበቅ እርባና ቢስ ጽሁፍ ነው።ቤተክርስትያንን ማደስ ሌላ እንዲህ ያለ ምናምንቴና የማይታመን ነገር አምጥቶ የአንባቢግ ግዜ ማጥፋት ሌላ።እርባና ቢሶች ናችሁ።

  ማህበረ ቅዱሳንን ከሰለፊዎች ጋር ማነጻጸር ነውር ነው።የልብ ድንዛዜአችሁን ከማሳየት የዘለለ የሚያስተምረው ነገር የለውም።እንኳን ማህበረ ቅዱስና ዝባዝንኬ የጻፈው እና ያስተናገደው ድህረ ገጽ ከአክራሪ ሙስሊሞች ጋር አይነጻጸሩም።ነውረኞች።

  መለስን የመሰለ አረመኔ እና የቤተክርስትያናችንን ጠላት ደግሞ እያሞካሻችሁ ማቅረባችሁ ምን ዓይነት አደርባዮች እንደሆናችሁና አርቆ ለማየት ያልታደላችሁ አህዮች መሆናችሁን ያመለክታል።
  ማህበረ ቅዱስና ችሎ ስልጣን ስልጣን ቢይዝ ምን ክፋት አለው ? መቸስ መለስ ዜናዊን ከመሰለ አረመኔ ይሻላሉ እንጂ የከፉ አይሆኑም።

  ካሁን በኋላ የምትለጥፉትን ጽሁፍ ማንስ ያምናችኋል።ዓላማችሁ ቤተክርስትያንን ማደስ ሳይሆን ማፈረስ መሆኑን ይሄው ጸረ ቤተክርስትያን አረመኔዎችን እንቱ እያላችሁ የማይገባችውን ክብር መስጠታችሁ ምስክር ነው።አሸባሪው መለስ ዜናዊ እንጂ ማህበረ ቅዱሳን አይደለም።

  ReplyDelete
  Replies
  1. እግዚአብሄር ካንተ ጋ ይሁን ወንድሜ ፣ምን ነካው የማይ ይነጻጸሩ ያነጻጽራል እንዴ ፤ምን አለበት መዋሸት ብያኩሙ?

   Delete
  2. germte new yemifetrut engeh sewech Amlak leb yestachehu

   Delete
  3. ነው እንዴ? አላወቅንም ነበር እኮ!! ይልቅ ሰለፊውን ማቅ ተነቅቶብሃል በሉት

   Delete
 7. የዛሬ ሁለት ዓመት አካባቢ ”ማኅበረ ቅዱሳን ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ግኑኝመት አለው” በማለት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ እና የዛኔው የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስተር አቶ አባይ ፀሐዬ ማስጠንቀቂያ ሰጥተውት እንደነበረ ይታወሳል:: አቶ ስብሃት ነጋ(ኦቦይ ስብሃት) እለተ አርብ ሰኔ 30፣2003 ዓ/ም ለፍትሕ ጋዜጣ በሰጡት ቃል ”ማኅበረ ቅዱሳን የቤተ ክህነት እዳ ነው:: የቤተ ክህነት አስተዳደር ለማሻሻል መጠነኛ እንቅስቃሴ ሲጀመር ገንቢ ተራ ከመጫወት አፍራሽነት ይበዛበታል፣ ብልሽት እያየ ዝምታ ያበዛል፣ ማኅበረ ቅዱሳን የፖለቲካ መድረክ ይታይበታል፣ማኅበረ ቅዱሳን በሕገ መንግሥት ክህደት ወንጀል ይጠረጠራል” በማለት ተናግረው ነበረ::

  ማክሰኞ ሚያዝያ 9፣2004 ዓ/ም ክቡር ጠቅላይ ሚኒተር መለስ ዜናዊ በፓርላማ ንግግራቸው ላይ ማኅበረ ቅዱሳንን ከዓለም አቀፍ አሸባሪ ድርጅት ከአልቃይዳ ጋር አመሳስለውታል:: ክቡርነታቸው ከምን አይነት መረጃ እና ማስረጃ ተነስተው ማኅበረ ቅዱሳን ከአሸባሪ ድርጅት ጋር እንዳመሳሰሉት ሰፋ ያለ ገለጻ አልሰጡም:: በደፈናው ግን “አልቃይዳ/ሰለፊ አንዳንድ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት የሚያራምዱት ግልባጭ ያራምዳል” አሉ::

  አልቃይዳ/ሰለፊ ባሳለፍናቸው በሃያ ዓመታት ጊዜ በሀገራችን ውስጥ ብዙ ጥፋቶችን አድርሶዋል:: ለዚህም በቂ መረጃ እና ማስረጃዎች አሉ:: ክርስቲያኖች አርደዋል፣ አብያተ ክርስቲያናት አቃጥለዋል እንዲሁም ኢትዮጵያ መተዳደር ያለባት በሸርያ ሕግ መሆን አለበት በማለት አስተምረዋል እያስተማሩም ናቸው:: ሰለፊዎች በቁጥር በዛ ብለው በሚኖሩበት ዞኖች እና ክልሎች ብቻ ገንጥለው የሸርያ ሕግ ተግባር ላይ ለማዋል እየሰሩ ናቸው:: ለምሳሌ የስልጢ ዞን እና የሐረሪ ክልል መጥቀስ ይቻላል:: ታድያ ማኅበረ ቅዱሳን የትኛው መስጅድ/መስጊድ አቃጠለ? የትኛው የፕሮቴስታን ማምለኪያ ቦታዎች አቃጠለ? ማኅበረ ቅዱሳን የትኛው ዞን ወይም ክልል በክርስትና ሕግ ይተዳደር ብሎ አስተማረ? አባላቱን ከፍለው ከአልቃይዳ ጋር እንዴት አመሳሰሏቸው? የአልቃይዳ ዓላማ ክቡር ጠቅላይ ሚኒሰተር ጠንቅቀው ያወቁት ይመስለናል:: ጠቅላይ ሚኒስተሩ የአልቃይዳ ዓላማ ጠንቅቀው ስላወቁ ይመስለናል ወታደራቸውን ወደ ሶማልያ የላኩት::


  የማኅበረ ቅዱሳን ዓላማ ሆነ ግብ ከአልቃይዳ ዓላማ እና ግብ ጋር ፈጽሞ አይገናኝም:: ሁለቱ ተቋማት ፍጹም ተቃራኒ ናቸው:: ምንም ሊያመሳስላቸው የሚችል ነገር የለም:: የእኔን ሃይማኖት ካልተቀበልክ ትታረዳለህ ብሎ የሚያስምረው አልቃይዳ እና የአባቶችን ሃይማኖት ተጠብቆ ለትውልድ ይተላለፍ ብሎ የሚስተምረው ማኅበረ ቅዱሳን ጋር እንዴት ሊመሳሰሉ ይችላሉ? ስለዚህ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር ተሳስተዋል:: ክቡርነቶ በማኅበሩ ላይ ከፍተኛ የስም ማጥፋት ወንጀል ነው የተናገሩት:: አንድ የአሸባሪ ድርጅት ለመምታት ግዴታ ሌላው አብሮ መመታት የለበትም:: በእስልምናው አልቃይዳ የአሸባሪ ድርጅት ነው ይህ ዓለም ያወቀው እውነት ነው:: የአንድ እምነት አክራሪ/አሸባሪን ለመቅጣት ግዴታ የሌላው እምነት ማኅበር መወንጀል ለምን አስፈለገ? ማስረጃ እና መረጃ ሳይኖር ዝም ብሎ በአንድ ድርጀት ወይም ግለሰብ ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ ማካሄድ ወንጀል መሆኑን ክቡርነቶ የሰሩልን ሕግጋት ይናገራሉ:: ስለስዚህ ክቡርነቶ “ሰለፊዎች(አልቃይዳዎች) አንዳንድ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት የሚያራምዱት ግልባጭ ሲያራምዱ ታይተዋል” ብለው ማኅበረ ቅዱሳንን ከአልቃይዳ ጋር ያመሳሰሉበት ንግግር ፍጹም የስም ማጥፋት ዘመቻ ነው:: ለዚህም ይቅርታ ሊጠይቁበት ይገባል::

  ክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር አንዳንድ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ያሉዋቸው እነማን ናቸው? አባ ሠረቀ ብርሃን 10% አሸባሪ ያላቸው የማኅበሩ የሥራ አመራር አባላት ይሆኑ? ወይስ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ስውር የማኅበረ ቅዱሳን አመራር ያላቸው? ማብራርያ የሚያስፈልገው ጥያቄ ነው:: የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ቅዱስ ሲኖዶስ ያጸደቀላቸው መተዳደርያ ደንብ ይዘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዶግማ እና ቀኖና ለትውልድ እዲተላለፍ የድርሻቸው እየተወጡ መሆኑን የአይን ምስክሮች ነን:: አባላቱ በሙሉ አንድ አይነት ዓላማ ይዘው እንደሚጓዙ እናውቃለን:: ነገር ግን አባ ሠረቀ እና መሰሎቻቸው አንዳንድ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሰዎች “ማኅበረ ቅዱሳን ድብቅ ዓላማ አለው” በማለት በተደጋጋሚ ሲከሱት ሰምተናል:: መንግሥት ተጨባጭ መረጃ እና ማስረጃ ሳይዝ የእነዚህን ሰዎች ውንጀላ የሚቀበል ከሆነ ክሱ መሰረተ ቢስ ይሆናል:: ክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር ይህንን የተሳሳተ የአባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል የተሳሳተ መረጃ ይዘው በአደባባይ ማኅበረ ቅዱሳን ከአልቃይዳ ጋር ማመሳሰሎ ከመስመረ የወጣ ክስ በእርሶ አገላለጽ ደግሞ የፈንጂ ወረዳ የረገጡ ይመስለናል::

  የማኅበረ ቅዱሳን አባላትን አንዳንድ፣ 10%፣ ስውር አመራር እያሉ ቢከፋፍሉዋቸውም ከእውነታ የራቀ ውንጀላ በመሆኑ የማኅበሩ አባላት ግን ፈጽሞ ሊከፋፍሉ አልቻሉም፤ አይችሉምም ምክንያቱም የማኅበሩ አባላት ያሰባሰባቸው የቤተ ክርስቲያን ዓላማ እንጂ የዓለም መንግሥት የፖለቲከኞች ዓላማ እናዳልሆነ ምስክሮች ነን:: ዓላማቸው የተሰቀለውን ክርስቶስ ለዓለም ሁሉ መስበክ እንደሆነ እኛ እንመሰክርላቸዋለን:: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት፣ ሥርዓት፣ ታሪክ፣ቅርስ ሳይፋለሱ እና ሳይበረዙ ለትውልድ እንዲተላለፍ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት በአንድነት ሆነው እንደሚሰሩ እናውቃለን::

  ከተመሠረተ ሃያ ዓመታትን ያስቆጠረው ማኅበረ ቅዱሳን በጉዞው ብዙ ፈተናዎችን እንደገጠሙት የማኅበሩ አባላት በተለያየ ጊዜ ይናገራሉ:: ማኅበሩ በእግዚአብሔር ቸርነት በቅዱሳን አበው እና እመው ጸሎት እስከ ዛሬ ድረስ ቢቆይም አሁንም እየተፈተነ መሆኑን አባላቱ ሲናገሩ ሰምተናል:: ስለዚህ አሁንም ቢሆን የማኅበረ ቅዱሳን አባላት በዚህ ሳትደነግጡ እና የተሰባሰባችሁበትን ዓላማ ሳትስቱ ሰዎችን ለማስደሰት ሳይሆን ሰለ እውነት ብላችሁ እግዚአብሔርን ለማስደሰተ ሥራችሁን ከበፊቱ ይልቅ ተግታችሁ እንድትቀጥሉ በዚሁ አጋጣሚ አሐቲ ተዋሕዶ አደራዋን ታስተላልፋለች::
  እግዚአብሔር አሐቲ ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን ይጠብቅልን!!!

  I hope you will post it.

  ReplyDelete
 8. እውነቱን እውነት ሐሰቱን ሐሰት ማለትን ብንለምድስ? በጎ ኅሊና ያለው ማንም በቀላሉ ሊረዳው እንደሚችል አባ ሰላማ የፖለቲካ ፍላጎት ወይንም የማንም የፓለቲካ ድርጅት አቀንቃኝ አይደለችምም ልትሆንም አትችልም። መቼም ስላላደለን ነው መስል የምንጠላው ሰው በጎም ሆነ መልካም ነገር ሲናገር ሁሉንም ጠቅልለን እርኩስ እናደርገዋለን። እጅግ የምንወደው ሰው ደግሞ የሚናገረው መልካምም ሆን መጥፎ እንደ መልካም ይወሰድለታል። ይሄ ጭፍንነት ነው። የክርስትናም መርሆ አይደለም። ከላይ ባሰፈርነው ጽሑፍ ግልጽ እንዳደረግነው አቶ መለስ ስለ ማህበረ ቅዱሳን የተናገሩት እውነት ነው። እንደ ክርስቲያን አቶ መለስ እውነት ሲናገሩ እውነት፤ ሐሰት ሲናገሩ ሐሰት እንላለን (ቤተ ክርስቲያንን የሚመለከት ሲሆን)። በሌላ አጋጣሚ አቶ መለስ ቤተ ክርስቲያንን የሚጎዳ ነገር ቢያደርጉ ወይንም ቢናገሩ ክፉውን ክፉ እንላለን። የፖለቲካውን ዘይቤና ፕሮፓጋንዳውን ችሎታው ላላቸው እንተወዋለን። ብሎጋችንን አየር ላይ ካዋልን ጀምሮ እንደተስተዋለው የአባ ሰላማ ዓላማ እውነቱን እውነት፤ ሐሰቱን ደግሞ ሐሰት ማለት ነው። በተለይም ደግሞ ድምጽ የተነፈጋቸውን የቤተ ክርስቲያናችንን ሰዎች ድምጽ መስጠት ነው። ወንጌል በአጉል ነገሮች ተተብትባ እንዳትቀር የሚረዱ የመወያያ ጉዳዮችን ማቅረብ እና ለቤተ ክርስቲያናችን ወይንም ለወንጌል አደጋ የሆኑ ነገሮችን (የማህበረ ቅዱሳንን እንቅስቃሴ ጨምሮ) እውነትን ይዞ መግለጥ። ቤተ ክርስቲያናችንን ወደፊት እንዳትራመድ፤ ወንጌልም ባግባቡ እንዳይሰበክ፤ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትም ያለአግባብ እንዲሳደዱ እያደረገ ስለሆን ከዚህ ድርጊቱ እስኪታረም ድረስ አባ ሰላማ በዚህም ዙሪያ እውነቱን እውነት፤ ሐሰቱን ሐሰት ማለትን ትቀጥላለች። በዚህ ዙሪያ (አስፈላጊ ከሆነ) ሰፋ ያለ ሐተታ ለአንባብያን ለማቅረብ እንሞክራለን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን። አባሰላማ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ኸረ ባክህ?
   ➠ ማንን ነው የምትፎግረው? ራስህን?
   አስመሳይ ውሸታም መናፍቅ::

   Delete
  2. Sorry, I forgot to write the source. I found it from 'Ahati-tewahido' blog and I belive it reflect my idea. By the way, Thank you for posting it.

   Delete
  3. አንተ ለመሆኑ እውነት ታቃለ?

   Delete
  4. እውነታችሁን ነው። ሀሳባችሁን እኔም እጋራለሁ

   Delete
  5. Long live aba selama. stand for truth. dont be ashemed to write the truth if u found it true and acepteble. here in Ethiopia most people have a choice becouse of you. and knows how much mk is a false organization. before aba selam we only heared everythink about our with mk blogs. and we tought they write all the truth. know after you show up we truely understand how much they are wrong in their way of doing things and informations. be stong dont go back becouse of some peoples ideas we want the other voice. that help us to find the truth. we pray for you . in every corner of ethiopia their are a lot of people we only choice aba selam for their true and reliable information. be brave.

   Delete
  6. hey please dont fear this poleticians you have to stand 4 the truth and live 4 it as you always do. melese has alot of problems but he is write in this case.

   Delete
  7. በጣም ታሳዝናላችሁ! የፖለቲካ መድረክ ሁናችኋል ማለት ነው። አቶ መለስ በምንም መልኩ እንደ እውነት ምንጭነት ሊወሰድ አይችልም። "ጠቅላይ ሚንስትራችን" እያላችሁ ያሞካሻችሁት ለምን ይሆን? በዚህ አጋጣሚ ከወያኔ ጋር ገጥማችሁ ማህበረ ቅዱሳንን ለመውጋት አስባችሁ ከሆነ ከንቱነት ነው። ለውጊያችሁ የመለስን ምስክርነት የምትሹ ከሆነ "የአይጥ ምስክሯ ድንቢጥ" ትባላላችሁ። እናንተ እውነትን በሞኖፖል እንድትይዙ ማን ነው የፈቀደላችሁ?
   "እውነቱን እውነት ሐሰቱን ሐሰት ማለትን ብንለምድስ?" ብላችሁ የምትጽፉት እናንተ የኢትዮጵያ ሕዝብ ህሊና (Conscience) ያደረጋችሁ ማነው? ህሊና መሆን ትክክልን ከመሥራት (moral authority) የሚመጣ ነው። ጸሐፊዎች ማን እንደሆናችሁ ከሞላ ጎደል እናውቃለን። እውነት ለመናገር የሚያስችል ስብእና አለን ብላችሁ ታስባላችሁ? መልሱን ለራሳችሁና ሁሉን ለሚያየው በመታገሥ ለሚያልፈው እግዚአብሔር አምላክ መልሱ።

   ለሁላችንም ብርሃንን ያብራልን!

   Delete
 9. እኔ የማይገበኝ ለምን ማህበረ ቅዱሳንን እንደዚህ ጠላችሁ ? እናነተ ቤ/ክርስትያንን ስታፈረሱ አታፈርሱ ስላለ ? ወይስ የቤ/ክርስትያንን ሀበት ለማውደም የሚፈልጉ ሰዎች በር እንድዘጋባቸው ስለጣረ ? ወይስ ሀገር ተረካቢ ዜጋ እንድፈጠር ቀን ከለሊት እየተጋ ስላሆነ? ወይስ ህዝቡን ለሴይጠንና ለስኦል ለማዘጋጀት?

  ReplyDelete
  Replies
  1. ማህበረ ቅድሳን ህዝቡን ለሰይጣንና ለመንግስቱ እያዘጋጀ ስለሆነና የሀሰተኛው ክርስቶስ እንደራሴ ስለሆነ

   Delete
 10. እንኩዋን ደስ አላችሁ ድሮም ወያኔ ፀረ ኦርቶዶክስ እንደሆነ ግልፅ ነው አጋዥ አገኛችሁ የእግዚአብሄር ፍርድ ግን መቼም ቢሆን አይቀርም አሁን ከናንተ የባሰ የጴንጤ አልቃሂዳ አለ?

  ReplyDelete
 11. እህቴ እሱ ወንድ ወኖ በእኔ ያሳብባል አለች።

  የሁሉም የባለስልጣኖቻችን አላማ በማህበረ ቅዱሳን ላይ፤ ክርስቲያኑ ሲገደልና በሃይል እንዲሰልም ሲደረግ ማህበሩ ለምን ዝም አይልም ለምን ለህዝቡ መረጃ ይሰጣል ነው ዋናው ጉዳይ፤ እንጂ ከተቃዎሚ ፖለቲካም ወነ ከሰለፊ/ከአልቃይዳ በምንም እንደማይገናኝ ያውቁታል።
  በምእራቡ አለም ያሉ ተቃዋሚዎች ማህበሩን ወያኔ፤ የወያኔ ጉዳይ አስፈጻሚ ይሉታል፤ በአገር ቤት ያሉ ባለስልጣናት ደጎሞ በዚህ ተቃራኒ ይከሱታል። እኔ የማበህበሩ አባል አይደለሁም፡ ሁሉቱም ከሳሾች ለእኔ የሚያውቁ የሚመስሉ አያላዋቂዎች ናቸው።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ስለ ማቅ ምንም ስለማታውቂ ምንም ባታወሪ ጥሩ ነው። ለምናውቀው ግን አልቃይዳነቱ እውነት ነው።

   Delete
  2. LECHIGARAM WEYANE ALCHENEKIM,LEMIN BITILU ENDENESU FERI AYDELEHUM.MUSLIMOCHIN FERTEW EKO NEW BEGNA YEMIASABIBUT.

   Delete
  3. NOOOOOOOOOOOO

   Delete
 12. I hope you will also post it here. I will help the readers to balance the issue and find out the truth.

  Source: http://www.adebabay.com/2012/04/blog-post_20.html

  “ጠ/ሚኒስትሩ ስለ ማኅበረ ቅዱሳን በተናገሩት አልስማማም”

  ማክሰኞ ሚያዚያ 9/2004 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ለምክር ቤቱ ሪፖርት ካቀረቡ በኋላ እንደተለመደው የምክር ቤቱ ክቡራን አባላት በንባብ ላቀረቡላቸው ጥያቄዎቻቸው መልስ ሲሰጡ ተከታትያለኹ። ከጥያቄዎቹ አንዱ ወቅታዊው የሙስሊሞች ጉዳይ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምላሻቸው “መንግሥት በሃይማኖት ውስጥ ጣልቃ አልገባም” የሚለውን በሰፊው ሲያብራሩ ቆዩ። አንዱ ማብራሪያቸው ስለ ሰላፊያዎች (አል-ሰላፊያ ወይም ወሐቢያዎች) ነው። ራሳቸውን “አል-ሰላፊዩን” የሚሉትና ትክክለኛውን የቁርዓን ትምህርት እንከተላለን የሚሉት የሙስሊም ክፍል የሆኑትና መሠረታቸውን በሳዑዲት አረቢያ ያደረጉት ጽንፈኛ ወገኖች በተቃዋሚዎቻቸው ደግሞ “ወሐቢያዎች” ይባላሉ። የዚህ ጽሑፍ ዓላማ ስለ ወሐቢያዎች እና ስለአክራሪነታቸው ማተት ስላልሆነ የዚህን ቡድን አስተምህሮ እና በኢትዮጵያ ላይ ስለ ጋረጠው ከፍ ያለ አደጋ “አክራሪ እስልምና በኢትዮጵያ” (ኤፍሬም እሸቴ፣ በ2000 ዓ.ም/ 2008 የታተመ) የሚለውን መጽሐፍ ማንበብ እንደሚቻል በመጠቆም አልፋለኹ።
  ወደ ርዕሰ ጉዳያችን ስንመለስ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ ሙስሊም አክራሪዎች ከማብራራታቸው ጎን ለጎን ደግሞ አክራሪነት በእስልምና ብቻ ያልተገታ መሆኑን ለማስረዳት በሚመስል መልኩ በክርስትናው ውስጥ በተለይም በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ያለውን በምሳሌነት ለማንሣት በጥምቀት ወቅት ወጣቶች ይዘውት ወጡ ያሉትን መፈክር ጠቅሰዋል። “ጥምቀት ላይ ከነበሩት መፈክሮች አንዱ ‘አንድ አገር - አንድ ሃይማኖት’ የሚል ነው። …. ‘አንድ አገር - አንድ ሃይማኖት’ የሚል ሕገ መንግሥት የለንም። (መፈክሩ) … የክርስቲያን መንግሥት እንዲኖር የሚፈልጉ … እንዳሉ ያሳየናል” ብለዋል - ጠ/ሚኒስትሩ። “የዚህም መነሻው የግንዛቤ ማነሥ በመሆኑ በማስተማር የሚመለሱ ናቸው” ሲሉ አክለዋል።
  ቀጥለውም ይኸው አክራሪነት በክርስትናም ውስጥ እየታየ መሆኑን ለአብነትም ጥምቀት ላይ የሚታዩ መፈክሮችን ካብራሩ በኋላ አክራሪዎቹ “አንዳንድ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት የሚያራምዱትን ግልባጭ ሲያራምዱ ታይተዋል” ሲሉ የእስልምናው “ሰለፊ” በክርስትናው በተለይም በኦርቶዶክሱ በኩል “ማኅበረ ቅዱሳን” ነው የሚል አንድምታ ያለው አጭር ነገር ግን ከባድ ኃይለ ቃል ተናግረው አልፈዋል። “አንዳንድ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት የሚያራምዱት” ያሉት ግን ምን መሆኑን በርግጥ አላብራሩም። ምናልባት ከላይ “አንድ አገር - አንድ ሃይማኖት” የሚል መፈክር ያዙ የተባሉት የጥምቀት አክባሪዎች “የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ሳይሆኑ አይቀሩም/ ናቸው” በሚል እሳቤ የተናገሩትም ይመስላል። ወደ ኋላ እንመለስበታለን።

  ReplyDelete
 13. በመጀመሪያ “አንድ ሃይማኖት” የሚለው መሠረታዊ ሐሳብ ለብዙ ውይይቶች በር የሚከፍት ትልቅ ጉዳይ ነው። ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚያስተምረን እና የጥምቀት አክባሪ ክርስቲያኖች በቲ-ሸርቶቻቸው ላይ አትመውት በፎቶግራፍ የተመለከትኩት ኃይለ ቃል ቅዱስ ጳውሎስ በኤፌሶን መልእክቱ ምዕራፍ 4 ቁጥር 5 ላይ የጻፈው “አንድ ጌታ፣ አንድ ሃይማኖት፣ አንዲት ጥምቀት” የሚለው ሐዋርያዊ ቃል ነው። ይህ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል እንጂ የጥምቀት አክባሪዎቹ የፈለሰፉት አይደለም። በዚህ የሐዋርያው ቃል ውስጥ ያለው “አንድ ሃይማኖት” የሚለው አገላለጽ የሚናገረው ስለ ክርስትና ሃይማኖት ነው። ሌሎች እምነቶች የሉም፣ መኖርም የለባቸው የሚል የጨፍላቂነት ትምህርት አለመሆኑን ሊቃውንቱ አምልተው አስፍተው ሲያስተምሩ ኖረዋል፤ እያስተማሩም ነው። አሁን ደርሶ የሚለወጥ ነገር የለም።
  በኢትዮጵያ ዐውድ ከተመለከትነው “ክርስቲያኖች ኢትዮጵያ የምትባለው አገር የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ብ….ቻ ናት፣ ያለ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሌሎቻችሁ ቦታ የላችሁም ትላላችሁ” የሚል አንድምታ እየሰጡ የሚናገሩ እና የሚጽፉ ብዙ ኢትዮጵያውያን ከመኖራቸው አንጻር “አንድ ሃይማኖት” የሚለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል አንዳንድ ሰዎች የተሳሳተ ትርጉም እንዳለው አድርገው እየተጠቀሙበት እንዳይሆን ሥጋት አለኝ።
  “አንድ ሃይማኖት” የሚለው አገላለጽ ከሃይማኖት ጋር በማይተዋወቁ ሰዎች ዓይን ከተመለከትነው መቻቻልን ለማስተናገድ ፈቃደኝነት የጎደለው አገላለጽ ሊመስል ይችላል። መቻቻል ማለት ግን መሠረታዊ የራስን ሃይማኖት አስተምህሮ መናድና መካድ ስላልሆነ መፍትሔው እርስ-በርስ መገነዛዘብና መረዳዳት ነው። የትኛውም ክርስቲያን “አንድ ሃይማኖት” ቢል የሐዋርያውን ቃል መጥቀሱ እንጂ ሌላ እምነት ላላቸው ኢትዮጵያውያን ጥላቻ አለው ማለት አይደለም። የጥምቀት አክባሪ ወጣቶች ቲ-ሸርቶች ላይ የተጻፈውን የሐዋርያውን ቃል የምረዳው በዚህ መንፈስ ነው።
  ይሁን እንጂ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጠቀሱት መፈክር “አንድ ሃይማኖት” ብቻ ብሎ ሳያበቃ “አንድ አገር” የሚለውን ጨምሮበት “አንድ አገር - አንድ ሃይማኖት” በሚል ተጽፎ ከሆነ አባባሉ ሌላ ትርጉም ማለትም “የክርስቲያን መንግሥት ለመመሥረት መሻት” የሚል አንድምታ ሊሰጠው ይችላል። ቲ-ሸርቶችን የለበሱ እና ባነሮችን የያዙ ወጣቶች በጥምቀት በዓላት አሁን ባለው መልክ በዓል ማክበር ከጀመሩ ገና ሁለት ወይም ሦስት ዓመታቸው ነው። በነዚህ ሁለት ወይም ሦስት ዓመታት የጥምቀት በዓላት ላይ የተነሱ እና ከተለያዩ ድረ ገጾችና ማኅበራዊ ገጾች የሰበሰብኳቸውን ከአንድ ሺህ አምስት መቶ በላይ ፎቶግራፎች በድጋሚ በጥንቃቄ ለመመልከት ሞክሬያለኹ። እነዚህ በተለያዩ ካሜራዎች፣ በተለያዩ አንሺዎች፣ ከተለያዩ አቅጣጫዎችና በተለያዩ ቦታዎች ከተነሡት ፎቶግራፎች ውስጥ ጠ/ሚኒስትሩ ያሉትን ዓይነት ጥቅስ ወይም ተመሳሳዩን ፈልጌ ላገኝ አልቻልኩም። በርግጥ መፈክሩ በነዚህ ፎቶዎች ውስጥ ባለመገኘቱ የተነገረው ነገር ስህተት ነው ማለት ላይሆን ይችላል። ነገር ግን ከመፈክሩ ከባድነት እና ከያዘውም ሐሳብ ጽኑዕነት አንጻር አንዱም ፎቶ አንሺ ሊያነሳው ያለመቻሉ ሁኔታ የአጋጣሚ ብቻ ነበር ለማለት አያስችልም። ስለዚህ አስቀድሞም ኅሊናዬ እንደሚነግረኝ እንዲህ የሚል ጥቅስ አልነበረምም አልተጻፈምም ለማለት እደፍራለኹ።
  “አንድ አገር” የሚለውን ነጥብም በተመለከተ ባለሙያዎች የበለጠ ሊያብራሩት እንደሚችሉ ባምንም በግሌ የሚሰማኝን ግን በአጭሩ ለመጠቆም እሞክራለኹ። እዚህ በምንኖርበት አገር በአሜሪካ Pledge of Allegiance የሚሉትና ቃል ኪዳናቸውን የሚያጸኑበት መሐላ (ማለትም "I pledge allegiance to the flag of the United States of America, and to the republic for which it stands, one nation under God, indivisible, with liberty and justice for all”) አላቸው። አሜሪካዊ የሆነ ሁሉ ከትንንሽ ተማሪዎች እስከ ምክር ቤት አባላት ድረስ ያውቁታል፣ በየአጋጣሚውም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ይሉታል። ለአገራቸው ያላቸውንም ቃል ኪዳን ይገልፁበታል።
  አንድ አገር/ one nation under God ያሉት ግን የሁሉም የሆነ አገር ማለታቸው መሆኑ ግልጽ ነው። አገር የጥቂቶች ብቻ ሳይሆን የሁሉም ዜጋ ሊሆን ይገባዋል። ኢትዮጵያን በምሳሌነት ካነሣን በአንዲቱ አገራችን ውስጥ ኢትዮጵያውያን ለብዙ ሺህ ዓመታት በሰላም እንደኖርነው ሁሉ አሁንም ክርስቲያኑም፣ ሙስሊሙም፣ የሚያምነውም የማያምነውም “አገሬ” ብሎ ሊኖርባት ይገባል እንጂ ለዚህኛው እምነት ተከታይ “አገር” ሆና ለሌላው እምነት ተከታይ ደግሞ አገር የማትሆንበት ምንም ምክንያት አይኖርም።
  “አንድ አገር” ሲባልም ሥጋት የሚገባው ዜጋ ሊኖር አይገባም። “አንዲት አገር” ዜጎቿ ተጨፍልቀው፣ ተጠፍጥፈው የምትፈጠር አይደለችም። በሌላ ጽሑፍ እንዳነሣኹት ኢትዮጵያውያን ብዙዎች ብንሆንም አንዲት አገር ናት ያለችን። አገራችን ቀለማችንና ቋንቋችን ለየቅል ቢሆንም ሁላችን በአንድነት የምንኖርባት የጋራ ቤታችን ናት። ኢትዮጵያውያንም እንደ አሜሪካኖቹ “ከፈጣሪ በታች ያለች አንዲት አገር/ one nation under God” አለችን ብንል የሚያሳፍር አይሆንም። በእርሷ ነውና እኛም “ኢትዮጵያውያን” የተባልነው። በሃይማኖትም አንጻር ካየነው ይህቺ አገራችን ቅዱሳን በኪደተ እግራቸው የባረኳት፣ አበው በደማቸው የጠበቋት፣ እምነት እና ቋንቋ ሳንለይ የምንኖርባት ቅድስት ምድር ናት።
  ጠቅላይ ሚኒስትሩ እግረ መንገዳቸውን ያነሱትን እና በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን “አክራሪነት” በክርስቲያኑ በኩል “ይወክልልናል” ብለው የጠቀሱትን ማኅበረ ቅዱሳንን በተመለከተ እኔም እንደ አንድ አባል የማምንበት አቀርባለኹ። ማኅበሩ በኃላፊዎቹ በኩል የሚሰጠው መልስ እንደተጠበቀ ሆኖ ለሁለት አሥር ዓመታት አባል የሆንኩበት እና መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ አገልግሎቶችን በመስጠት በሁሉም ዘንድ የተመሰከረለት ማኅበር “አክራሪ” አለመሆኑን በግሌ ለመመስከር እገደዳለኹ።
  ማኅበረ ቅዱሳን “እግዚአብሔር ያከበራቸው የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የጻድቃንና የሰማዕታት በአጠቃላይ የቅዱሳን ገድል፣ ትሩፋትና አማላጅነት የሚዘከበርበት” ማኅበር ሲሆን አገልግሎት መስጠት ከጀመረ እነሆ 20 ዓመት ሆነው። ማኅበሩም ያለውን ዓላማ፣ ግብና ርዕይ በመጽሔቶቹ፣ በጋዜጦቹ፣ በዐውደ ርእዮቹ፣ በኦዲዮ እና ቪዲዮ ውጤቶቹ ደጋግሞ ጽፏል፣ ተናግሯል፣ አስተምሯል። ከዚህ አንጻር ማኅበሩ አገርንም ሆነ ፖለቲካን፣ ሌሎች እምነቶችንም ሆነ ተቻችሎ መኖርን በተመለከተ ከማንም በላይ በሰፊው፣ በበሰለ እና ጤናማ በሆነ መንገድ ሐሳቡን አስተጋብቷል። ስለዚህም የማኅበረ ቅዱሳን አቋም “ጥምቀት ላይ የወጡ ጥቂት ሰዎች ይዘዋቸው ነበር” በተባሉ መፈክሮች የሚገለጽ አይደለም። በነዚህ 20 ዓመታት የተሠሩ ሥራዎቹን፣ የሕትመት ውጤቶቹን እና አባላቱ በግልጽም ሲናገሩት የኖሩትን መመርመር በርግጥም ማኅበሩ ምን ዓይነት ነጽሮተ- ዓለም (Weltanschauung) እንዳለው በቅጡ ለመረዳት ያስችላል።

  ReplyDelete
 14. ታዲያ “ማኅበረ ቅዱሳንን ከአክራሪነት ጋር ማገናኘት” ለምን አስፈለገ የሚለው ግን በደንብ መታየት አለበት። መንግሥትም የዚህን አስተሳሰብ ምንጭ መረዳት አለበት ብዬ አምናለኹ። መነሻው ቤተ ክርስቲያናችንን የእርሷ ባልሆነ ትምህርት እና እምነት ለመለወጥ የሚሞክሩ ነገር ግን “ይህንን እንዳናደርግ ማኅበረ ቅዱሳን እንቅፋት ሆኖብናል” የሚሉ አካላት (ተሐድሶዎች) ለረዥም ዘመን ሲያሰሙት የቆዩት ክስ ነው። በእነርሱ አስተያየት አንድ ሰው ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮውን አልለውጥም ካለ “አክራሪ” ይሉታል። እነርሱ “አክራሪ ነው” የሚሉትን ሰው በሙሉ ጠቅልለው በጋራ “ማኅበረ ቅዱሳን” ብለው ይጠሩታል። ሰውየው የማኅበሩ አባል ቢሆንም ባይሆንም ለቤተ ክርስቲያኑ ጥብቅና የሚቆም ከሆነ ማሸማቀቂያቸው “ማኅበረ ቅዱሳን ነህ እንዴ?” የሚል ነው።

  እንግዲህ በኦርቶዶክሳውያን እና በተሐድሶዎቹ መካከል ሲደረግ የቆየው ትግል አዲስ ምዕራፍ የሚያገኘው እነዚህ ኦርቶዶክስን ለመከለስ (ለማደስ) የሚፈልጉ ሰዎች “በፖለቲካው ጉያ ምቹ ቦታ ባገኘን” የሚለው ሙከራቸው ተሳክቶ በራሱ በመንግሥት ስም ዓላማቸውን ማራመድ ከጀመሩ ነው። ከነዚህም አብዛኞቹ የኢሕአዴግ የፖለቲካ መስመር ደጋፊዎች በመምሰል (በተለይም ከ1997 ዓመተ ምሕረቱ ምርጫ - ምርጫ ’97) እና ውዝግቡ ጀምሮ ማኅበረ ቅዱሳን ለቅንጅት ማሸነፍ ትልቅ ሚና ተጫውቷል በማለት በመንግሥት ልምጭ የራሳቸውን ዱላ ለማሳረፍ በብዙ ሲጥሩ እንደነበር ይታወቃል። በይፋም ጽፈዋል። የጠ/ሚኒስትሩ አጭርና ብዙ መልእክት የተሸከመች ዐረፍተ ነገር “እነዚያ መንግሥትን ተገን አድርገው ቤተ ክርስቲያኒቱን ፕሮቴስታንታዊ ለማድረግ የሚሞክሩ ሰዎች/ ተሐድሶዎች መንግሥትን ለዓላማቸው መጠቀሚያ ለማድረግ የሚያደርጉት ጥረት ተሳካላቸው ማለት ነው?” የሚል ስሜት ያጭራል።
  ከዚህ አንጻር ከቤተ ክርስቲያኒቱ አስተምህሮ የወጣ እምነት ይዘው ቤተ ክርስቲያኒቱን እና ትምህርቷን በመለወጥ የራሳቸው ለማድረግ የሚሞክሩ ሰዎች፣ ቡድኖች እና ድርጅቶች መኖራቸው እየታወቀ በገንዘቡ፣ በጉልበቱ እና በዕውቀቱ ለቤተ ክርስቲያኑ ብቻ ሳይሆን ለአገሩም በቅንነት የሚያገለግለውን አንድ ትውልድ ጨፍልቆ በአክራሪነት ስም መፈረጅ በቤተ ክርስቲያኒቱ ህልውና ላይ ትልቅ የሚዛን መናጋት ያስከትላል ብዬ በድፍረት መናገር እችላለኹ። ተሐድሶዎቹም ሆኑ ሌሎች የቤተ ክርስቲያኒቱ ተቀናቃኞች “ዓላማችንን ሊያውቅብን ይችላል” የሚሉትን ማኅበር ሕጋዊ አገልግሎት ያለ አግባብ ሌላ ስም መስጠት ይህንን ቃል እንደ መመሪያ ወስደው የግል ፍላጎታቸውን ለመፈጸም ለሚቋምጡ ወገኖች ትልቅ ደስታ ነው።
  የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እምነት አክራሪነትን መሸከም አይችልም። ሌላ ማንም አካል ሳያስፈልጋት ራሷ ቤተ ክርስቲያን የእርሷ ያልሆኑትን ለመለየት ችሎታ አላት። አማኞቿም ማን አክራሪ እንደሆነ ጠንቅቀው ያውቃሉ። በበግ ለምድ ተደብቀው ሌሎችን “አክራሪዎች ናቸው” በሚል ሽፋን በጎች-ምእመናንን ለመንጠቅ የሚሞክሩትንም ያውቃል። የአክራሪነትን ምንነት ለመረዳት ሰፕቴምበር 11ን፣ የሎንዶኑን የባቡር ጣቢያ ፍንዳታ፣ የጅማውን ጭፍጨፋ፣ የኒው ዴልሒን የሽብር አደጋ፣ አል-ሸባብ በየጊዜው በሶማሊያ የሚፈጽመውን መመልከት ያስፈልጋል። ትርጉሙና ምንነቱ ይህ ሆኖ ሳለ ያለቦታው ይህንን ቃል መጠቀም ሕዝቡ ቃሉ ያዘለውን ቁምነገር እንዳይረዳ ከሚያደርገው በስተቀር ውጪ ሌላ ምንም ጥቅም የለውም።
  በርግጥ ገዳማትንና አብነት ት/ቤቶችን ከጥፋት መታደግ አክራሪነት ነውን? ወጣቱ ትውልድ ሃይማኖቱን አውቆ በሥነ ምግባር ታንጾ አገሩንና ቤተ ክርስቲያኑን በቅንነት እንዲያገለግል ማድረግ አክራሪነት ነውን? በገንዘቡ፣ በዕውቀቱና በጉልበቱ በነጻ የትውልድ ኃላፊነቱን ለመወጣት የሚሞክር ትውልድ መፍጠር አክራሪነት ነውን? በጭራሽ!!! ስለዚህ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ ማኅበሩ ባሉት ሐሳብ አልስማማም።

  ከላይ በመግቢያዬ በጠቀስኹት መጽሐፍ ላይ በዝርዝር ለመቅረብ እንደሞከርኹት “አክራሪነት”ን በማይገባው ምሳሌ መግለጽ በሕዝቡ አእምሮ ውስጥ ሊፈጥረው የሚችለው ሥዕል ዞሮ ዞሮ አገሪቱ ከአክራሪዎች ሊገጥማት የሚችለውን አደጋ ይጨምረዋል ብዬ አስባለኹ። ምክንያቱም ‘አክራሪነት’ አስቀያሚ መልኩን በኒውዮርክ ፍንዳታ ፍንትው አድርጎ ስላሳየ ዛሬ ማኅበረ ቅዱሳንን በዚህ ስም መጥራት በራሳቸው በወሐቢያ አክራሪዎቹ ዘንድ ሳይቀር የማይሆን ግምት ያሰጣል።
  በአጠቃላይ ክቡር ጠ/ሚኒስትሩ የተናገሩት አጭር አስተያየት ለተለያዩ ዓይነት ትርጉሞች ክፍት ቢሆንም ይህንኑ ንግግራቸውን ከሕግ እና ከመመሪያ የሚቆጥሩ ብዙ ክፍሎች የንግግራቸውን ጫፉን ብቻ ይዘው ሙሉ መንፈሱን ሳይረዱ የመሰላቸውን አቅጣጫ እንዳይሄዱ ጥንቃቄ መደረግ አለበት። በጠቅላላውም ካየነው የማኅበረ ቅዱሳን ጉዳይ መታየት ያለበት “በቤተ ክህነቱ እና በቤተ ክህነቱ ብቻ” ነው ብዬ አምናለሁ። በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አለመግባት ማለት የቤተ ክርስቲያኒቱን ጉዳይ ለራሷ መተው ነው።
  በሌላም በኩል የሙስሊሞችን ጉዳይ ለሕዝብ ለማሳየት እና ቀሪው ሕዝበ-ሙስሊም እንዳይከፋ በሚመስል መልክ ከክርስቲያኑ ወገን ማኅበረ ቅዱሳንን በማነጻጸሪያነት መጥቀስ ተገቢ ነው ብዬ አላምንም። የሙስሊሞቹን ጉዳይ በራሳቸው ዐውድ እና በራሳቸው የእምነት ሥርዓት መፍታት እንደሚገባው ሁሉ የክርስቲያኑንም ጉዳይ በክርስትና ሃይማኖት ሕግ እና በክርስትና መነጽር ብቻ ሊታይ ይገባዋል።
  ይቆየን

  ፀሐፊውን ለማግኘት፦
  ephremeshete@Gmail.com
  (http://www.adebabay.com/)

  ReplyDelete
  Replies
  1. Dear Dn Ephrem, May the Grace of God and His Mother be with you always. I entirely agree with your idea. especially the last sentences"በሌላም በኩል የሙስሊሞችን ጉዳይ ለሕዝብ ለማሳየት እና ቀሪው ሕዝበ-ሙስሊም እንዳይከፋ በሚመስል መልክ ከክርስቲያኑ ወገን ማኅበረ ቅዱሳንን በማነጻጸሪያነት መጥቀስ ተገቢ ነው ብዬ አላምንም። የሙስሊሞቹን ጉዳይ በራሳቸው ዐውድ እና በራሳቸው የእምነት ሥርዓት መፍታት እንደሚገባው ሁሉ የክርስቲያኑንም ጉዳይ በክርስትና ሃይማኖት ሕግ እና በክርስትና መነጽር ብቻ ሊታይ ይገባዋል።" are worth attention. I think that Ato Melese mentioned MK just to attack the extremist Muslims. Just to compromise. But as you mentioned it is not the right way. he needed to the "extremist" extremist. Hopefully, he knows MK is not extremist.Had he believe MK is extremist "akirari" he would have automatically ban its service. He does not have any one to hinder him from doing so. Everything is in his hand. But , if the PM believes Mk is Akrari, he should be considered mindless, crazy person and he doesn't have any clue how and what extremism is. In a nut shell he is anti Orthodox. He always favors the Muslims and protestants so that he can stay on his chair long ever. Long live to Ethiopia and Tewahedo.

   Delete
 15. This is for Mk( Mahbere erkusan) becareful from mk cheating.
  ነገር ግን በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን እወቅ።
  2 ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና፥ ገንዘብን የሚወዱ፥ ትምክህተኞች፥ ትዕቢተኞች፥ ተሳዳቢዎች፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥ የማያመሰግኑ፥
  3 ቅድስና የሌላቸው፥ ፍቅር የሌላቸው፥ ዕርቅን የማይሰሙ፥ ሐሜተኞች፥ ራሳቸውን የማይገዙ፥ ጨካኞች፥ መልካም የሆነውን የማይወዱ፥
  4 ከዳተኞች፥ ችኩሎች፥ በትዕቢት የተነፉ፥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉ፤
  5 የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ።
  6-7 ወደ ቤቶች ሾልከው እየገቡ፥ ኃጢአታቸው የተከመረባቸውን በልዩ ልዩ ምኞትንም የሚወሰዱትን ሁልጊዜም እየተማሩ እውነትን ወደ ማወቅ ሊደርሱ ከቶ የማይችሉትን ሞኞችን ሴቶች የሚማርኩ፥ ከእነዚህ ዘንድ ናቸውና።
  8 ኢያኔስና ኢያንበሬስም ሙሴን እንደ ተቃወሙት፥ እንዲሁ እነዚህ ደግሞ አእምሮአቸው የጠፋባቸው ስለ እምነትም የተጣሉ ሰዎች ሆነው፥ እውነትን ይቃወማሉ።
  9 ዳሩ ግን የእነዚያ ሞኝነት ደግሞ ግልጥ እንደ ሆነ፥ ሞኝነታቸው ለሁሉ ይገለጣልና ከፊት ይልቅ አይቀናላቸውም።
  10 አንተ ግን ትምህርቴንና አካሄዴን አሳቤንም እምነቴንም ትዕግሥቴንም ፍቅሬንም መጽናቴንም ስደቴንም መከራዬንም ተከተልህ፤
  11 በአንጾኪያና በኢቆንዮን በልስጥራንም የሆነብኝን የታገሥሁትንም ስደት ታውቃለህ፤ ጌታም ከሁሉ አዳነኝ።
  12 በእውነትም በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔርን እየመሰሉ ሊኖሩ የሚወዱ ሁሉ ይሰደዳሉ።
  13 ነገር ግን ክፉዎች ሰዎችና አታላዮች፥ እያሳቱና እየሳቱ፥ በክፋት እየባሱ ይሄዳሉ።
  14 አንተ ግን በተማርህበትና በተረዳህበት ነገር ጸንተህ ኑር፥ ከማን እንደ ተማርኸው ታውቃለህና፤
  15 ከሕፃንነትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን፥ መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳን መጻሕፍትን አውቀሃል።
  16-17 የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ youth full.
  This is for mk. Please becarefull from mk(mahibere seitan)

  ReplyDelete
 16. Aba Selama you are absolutlly right about it. Please stay Bless. Good Job.

  ReplyDelete
 17. Ephrem Eshete is the falls propoganda's for mk(Mahbere seytan). Don't listen to him at all. He and his boses are liding by dable.

  ReplyDelete
 18. አፋፍ ላይ የቆመ ጎረምሳ ማህበርን ለማዳን
  by Bekeme Mihiretike

  በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ውስጥ ካሉና ለቤተክርስቲያኒቱ የራሳቸውን ድርሻ ካበረከቱ ማህበራት መካከል አንዱ ማህበረ ቅዱሳን ነው፡፡ ማህበሩ ከተመሰረተ ሁለት አስርተ አመታትን ጨርሶ እነሆ ጉርምስናውን ተያይዞታል፡፡ ይሁንና ማህበሩ በተለይ ባለፉት ጥቂት አመታት ባልሆነ መስመር ሄዶ ሄዶ ከገደል አፋፍ ላይ ተንገራግጮ ቆሟል፡፡ ወደኋላ ተመልሶ ያለበትን ችግር በጥልቀት መርምሮ የሚሄድበት መስመር ካላስተካከለና በጀመረው መንገድ ከቀጠል ባጭር ጊዜ ውስጥ ወደገደል መግባቱ አይቀሬ ይሆናል፡፡ እንደውጭ ተመልካች ገደል ሲገባ ዝም ብሎ ከማየት እንደ አንድ የቤተክርስቲያን አባል (እና የቀድሞ የማህበሩ አባል) እንዲሁም በፊት በፊት በሰራቸው መልካም ስራዎች አንጻር ችግሮቹን ፈቶ ወደ ቀደመ ክብሩ ይመለስ ዘንድ የመፍትሄ ሃሳቤን ለማቅረብ ወደድኩ፡፡ ማህበሩ የ20 አመት ልደቱን ሲያከብር አገር ሰላም ነው ብሎ ሻማ ለኩሶ ኬኩን በመቁረስ ብቻ ሳይሆን ያለበትን አደጋ አስተውሎ ራሱን ይመረምርና መስመሩን ያስተካክል ዘንድ ይጠቅመዋል፡፡ ያን ካደረገ ደሞ ገደል ከመግባት ይተርፍና ካለበት የጉርምስና ጠባይና እድሜ ተሻግሮ ወደ ጉልምስናና እርግና እንዲደርስ ይረዳዋል፡፡

  አንዳንዶች ማህበሩ በስራው የቅዱሳን ስም አርክሷል፤ ለቤተክርሰቲያኒቱ እዳ ሆኗል፤ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ በዝቷልና መዘጋት አለበት የሚል አቋም ሲያራምዱ ይስተዋላል፡፡ እኔ ግን ምንም እንኳን በጥፋት ጎዳና ቢሄድም ተስተካክሎ ለቤተክርስቲያን እንዲያገልግል መደረግ አለበት እንጂ ፈጽሞ ሊዘጋ አይገባውም የሚል አቋም አለኝ፡፡ የማህበሩ አመራር አባላትም መንግሰትና ፓትሪያርኩ ሊዘጉን ነው ሊያጠፉን ነው የሚል ፍራቻ እንዳላቸው በውስጥ አዋቂዎች ተነግሯል፡፡ ይሁንና እንዲቀጥልም ሆነ እንዲዘጋም የሚያደርገው ራሱ ማህበሩ ነው እንጂ ፓትሪያርኩ ወይም መንግሰት አይደለም፡፡ የመቀጠል ዋስትናው ደሞ ያለበትን ችግር በመፍታት የተበላሸ አካሄዱን ማስተካከል ብቻ ነው፡፡


  ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ከቆመበት የገደል አፋፍ ሊመልሱት የሚችሉ ዋና ዋና የመፍትሄ ሃሳቦች ናቸው፡፡


  1ኛ፡ ራሱን ከስውር አመራር ነጻ ማድረግ፡- ከውስጥ አዋቂዎችና የቀድሞ አመራሮች እንደተገለጸው ማህበሩ ስውር አመራር አለው፡፡ ይህ ባስቸኳይ ሊታረም የሚገባው ነው፡፡ አንድን መንፈሳዊ ማሀበር በእግዚአብሄር መንፈስ፤ በቤተክርስቲያን ሰርአትና በአባላቱ ፍላጎት እንጂ በሌላ በስውር እጅ ሊመራ አይገባውም፡፡ ማስፈጸም ያለበትም የእግዚአብሄርን፤ የቤተክርሰቲያንና የአባላቱን አላማ እንጂ የስውር አካልን ፈጽሞ ሊሆን አይገባውም፡፡ በመሆኑም በእግዚያብሄር መንፈስ ማገልገል የሚችል ጠንካራ አመራር ባስቸኳይ በመምረጥ ራሱን ማስተዳደር መጀመር ይኖርበታል፡፡


  2ኛ፡እጁን በየትኛውም ፖለቲካ ውስጥ አለማስገባት፡- በተደጋጋሚ ማህበሩ ከሚቀርብበት ክስ መሃል ከህገ ደንቡ ውጪ እጁን በፖለቲካ ማስገባቱ ነው፡፡ መንግሰት ሳይቀር ይህን በማያሻማ ሁኔታ አስቀምጦታል፡፡ አብዛኛው የማህበሩ አባላት የኢህአዴግ አባላት ናቸው የሚለው የማህበሩ አመራር መግለጫም ቢሆን ከዚህ ክስ ነጻ የሚያወጣ አይደለም፡፡ ምክንያቱም የተቃዋሚምም ሆነ የገዢ ፓርቲ አባል መሆን ያው ከፖለቲካነት የሚዘል ትርጉም የለውም፡፡ አመራሮቹም የየትኛውም ፖለቲካ ፓርቲ አባል ያለመሆናቸውን የሚያስረዳ ሰነድ ማቅረብ አለመቻላቸው አመራሩም ፖለቲካ ውስጥ እጁ የለም ለማለት የማያስደፍር ነው፡፡ በመሆኑም መንፈሳዊ ማህበር እንደመሆኑ ፈጽሞ በየትኛውም ፖለቲካ ያለመግባት የጸና አቋም ይዞ ሊተገብረው ይገባል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም እንደፖለቲካ ተቋም የስለላ ድርጅት አቋቁሞ ሰዎችን ሊሰልልም አይገባም፡፡ ብዙዎች በፖለቲካ ውስጥ ገብቷል ብለው እንዲያምኑ ያደረጋቸው ደጀ ሰላም፤አንድ አድርገን እና ገብርሄር የተባሉት ብሎጎች የሚያስተላልፉት በሃይማኖት የተሸፈነ ፖለቲካና ሃይማኖታዊ አክራሪነት ነው፡፡ እነዚህ ብሎጎች ደሞ የማህበሩ ለመሆናቸው ብዙዎች እርግጠኞች ናቸው፡፤ ማህበሩም እስካሁን የራሱ ልሳን አለመሆናቸውን በማያሻማ ሁኔታ አልገለጸም፡፡ በመሆኑም የራሱ ብሎጎች ከሆኑ ባስቸኳይ የዚህ አይነት አካሄዱን መተው፤ የራሱ ካልሆኑ ደሞ ይህን በግልጽ በማስረጃ ማሰረዳት ብሎጎቹ የሚሄዱበትን ፖለቲካና ሃይማኖት ያጣቀሰ የተበላሸ አካሄድ መኮነን ይኖርበታል፡፡

  3ኛ፡ ከራሱ ይልቅ ለቤተክርሰቲያን ቅድሚያ መስጠት፡ ማህበሩ የተቋቋመት ዋና አላማ ቤተ ክርስቲያንን ለማገለገል ነው እንጂ ራሱን ለማገልገል አይደለም፡፡ በመሆኑም ዝም ብሎ እንደስለላ ድርጅት በየቦታው መዋቅሩን ከማስፋት ይልቅ ቤተክርሰቲያንን ባሏት መዋቅር በስፋት ማገለገል አለበት፡፡ ራሱን እንደተለየ አካል ቆጥሮ ከቤተክርሰቲያን ለመጠቀም ከመሯሯጥ ይልቅ ቤተክርሰቲያኒቱን ማገልገል፤ ራሱን ከማዳን ይልቅ ቤተክርስቲያኒቱን ማዳን ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ነገር ሊሆን ይገባል፡፡


  4ኛ፡ የቤተክርሰቲያኒቱን አባቶች፤ ህግ፤ መዋቅርና አሰራር ማክበር፡ ማህበሩ ሌላ የሚከከስበት ትልቅ ቸግር የቤተክርሰትያን አባቶችን አለማክበር፤ መከፋፈልና ማጋጨት ነው፡፡ ይህ ፈጽሞ ኢ-ክርሰቲያናዊ ተግባር ብቻ ሳይሆን ሰርአት አለበኝነትም ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ለቤተክርሰቲያኒቱ ህግና መዋቅር አለመታዘዝ ሌላው የማህበሩ መገለጫ ሆኖ ቆይቷል፡፡ ለዚህም ራሱን ከሁሉም በላይ በማድረግ በቤተክርሰቲያኒቱ አመራር ራሱን በማስቀመጥ የፈለገውን ፍርድ ሲሰጥና የፈለገውን ሲሰራ መክረሙ ማሳያ ይሆናል፡፡ በመሆኑም ይህን ሰርአተ አልበኝነት በመተው አባቶቹን “ እኔ ከናንተ አልበልጥምና” ብሎ ሊያከብራቸውና ሊታዘዛቸው እንዲሁም የቤተክርስቲያቱን ህግ፤ ሰርአትና መዋቅር ያለ አንዳች ማወላወል ሊያከብር ይገባል፡፡

  ReplyDelete
 19. 5ኛ፡ ራሱን የቅዱሳንን ስም ከሚያሰድብ ነገር ማራቅ፡ማህበሩ ስማቸውን ለማስከበር ብሎ በቅዱሳን ስም ራሱን ሰይሞ የነበረ ቢሆንም ባሁኑ ወቅት በከፍተኛ ሁኔታ እያሰደባቸው ይገኛል፡፡ የሚሰሩ አንዳንድ የክፋት ስራዎች ፈጽሞ በቅዱሳን ማህበር የሚሰሩ አይደለምና፡፡ ዘረኝነት፤ ቡድንተኝነት፤ አድመኝነት፤ ሰላይነት፤ ፖለቲከኝነት፤ስም ማጥፋት፤ ሰዎችን ከቤተክርስቲያን መግፋት፤ እንደፖለቲካኞች የውስጥ ቸግር ሲፈጠር ከውጭ የማምለጫ ፍየል መፈለግ፤ አባቶችን አለማክበር ወዘተ በየትኛውም መለኪያ መንፈሳዊ ሊሆንና የቅዱሳን ባህሪ መገለጫ ሊሆን አይችልም፡፡ ቅዱሳን እንዲከበሩበትና እንዲዘከሩበት የተቋቋመ ማህበር ተሰድቦ ቅዱሳንንም ለሰዳቢዎች አሳልፎ የሚሰጥ ሊሆን አይገባውም፡፡ በመሆኑም እንደ ቅዱሳን መንፈሳዊነቱን ጠብቆ መንቀሳቀስ ያለበለዚያም ስሙን መቀየር ግድ ይሆንበታል፡፡


  6ኛ፡ ማህበሩ ስትራተጂክ እቅድ ኖሮት ለቤተክርሰቲያን ሊሰራ ይገባል፡ አንድ ማህበር የራሱን የረዥም ግዜ ራእይ፤ ተልእኮና ግብ ተልሞ ሊንቀሳቀስ ግድ ይላል፡፡ ያለበለዚያ በአውር ድንበር ከመጓዝ ባለፈ እንድም ተጨባጭ ነገር መስራት አይቻልም፡፡ በመሆኑም ማህበሩ ለቤተክርስትያን የሚያደርገውን አሰተዋጽኦ በስትራተጂክ እቅድ ሊያስቀምጥና በዛም ራሱን ሊገመግም ይገባዋል፡፡ ይሁንና በውስጥ አዋቂዎች እንደተቀመጠው ማህበሩ ተራ በሆኑ የእሳት ማጥፋት አይነት አካሄድ ላይ ራሱን ጠምዶ ነው እድሜውን ያሳለፈው፡፡


  7ኛ፡ የኔ ካልሆናችሁ ጠላቶቼ/ምንትስ ናችሁ የኔ ከሆናችሁ ግን ወዳጆቼ/ቅዱሳን ናችሁ ከሚለው የተሳሳተ አስተሳብ ነጻ መውጣት፡ ማህበሩ ብዙ ጊዜ ራሱን ብቻ እንደቤተክርሰቲያን ጠበቃ የሱ አባል ያልሆኑትን (አባቶችን ጨምሮ) በጥርጣሬ የማየት ችግር አለበት፡፡ በተለይ ሁሉም ሰዎች የኔ አባል ካልሆኑ ምንትስ ናቸው እያሉ የተለያዩ ስሞ ሰጥቶ ጠላት ከማድረግ ከተቻለ አሳምኖ አባል ማድረግ ካልሆነ ግን በጋር የሚሰሩበትን ዘዴ መቀየስ ያስፈልጋል፡፡ ወይ የኔ ሁኑ ያለበለዚያ ጠላቶቼ ናችሁ የሚለው አካሄድ ማህበሩ በራሱ ጊዜ ብዙ ጠላቶችን እንዲያፈራ አድርጎታል፡፡ ከዚህም በላይ ብዙ ምንትሶች በማህበሩ ተጠልለው ክፍ ስራ ለመስራት ዋስትና ሆኗቸዋል፡፡

  8ኛ፡ በማህበሩ ያለው ግኖስቲካዊ አመለካከት መስበር አለበት፡ ባሁኑ ወቅት ማህበሩ አገልግሎት በእውቀት ነው የሚለው አመለካከት ተንሳርፍቶበት ይገኛል፡፡ የዚህም መነሻው አባላቱ በአለማዊ ድግሪ የተንበሸበሹ በመሆናቸው ነው፡፡ በመሆኑም የሆነ አለማዊ ድግሪ ያለውና በወራት በጊቢ ጉባኤ መንፈሳዊ ኮርስ የወሰደ የማህበሩ አባል እንደሱ ባለማዊ ትምህርት ያልገፉትን አገልጋዮች በመናቅ ራሱን ሰማይ ላይ ሰቅሎ ቁጭ ይላል፡፡ ዲፕሎማና ዲግሪ የሌለው አገልጋይ ደሞ ማለት ይጀምራል፡፡ ግኖስቲክነቱ ገኖ መድረክ ላይ ይወጣል፡፡ እግዚአብሄር ጸጋ አልሰጠውምና ሰው ጀሮ ይነፍገዋል፡፡ እነዛን አልተማሩም የሚባሉትን ግን በእልልታ ይሰማል፡፡ ይሄኔ በቅናት ተነስቶ ሌላ ጦርነት ያውጃል፡፡ ከዚህ ይልቅ አገለግሎት በድግሪና በዲፕሎም ሳይሆን በእግዚአብሄር ጸጋ ነው….የቢታንያ ድንጋዮችን ያናገረ ጌታ ለሰው ልጅማ የተሸለ ሊሰጥ የታመነ ጌታ ነው፡፡

  9ኛ፡ በስጋ ሳይሆን በመንፈስ ማገልገል፡ የማህበሩ ቁልፍ ችግር በመንፈስ ሳይሆን በስጋ ማገልገሉ ነው፡፡ ምናልባትም አለማዊ ድግሪ ያላቸው አባላትና አመራሮች ስላሉት ይሆናል፡፡ ባሁን ወቅት ማህበሩ ላለበት አደገኛ ሁኔታ መሰረቱም ይሄ ነው፡፡ በጸሎት፤ በትህትና፤ በፍቅር፤ በመተሳሰብ በመሳሰሉት የመንፈስ ፍሬዎች ተደግፎ ከማገልገል ይልቅ በስለላ፤በጥላቻ፤ በትእቢት፤ ጠልፎ በመጣል በመሳሰሉት የስጋ ፍሬዎች በመነዳቱ አሁን አለበት አዘቅት ላይ ደርሶአል፡፡ በመሆኑም ባስቸኳይ ያለው በመንፈሳዊ አገልግሎት እንጂ በስጋ ስራ ላይ አለመሆኑን ተረድቶ በመንፈስ ማገልገል መጀመር የማህበሩን ህልውና የማዳን ጉዳይ ይሆናል፡፡


  Bekeme Mihiretike

  ReplyDelete
  Replies
  1. Outdated style. We know you why you are saying this... Anyway, We thank you for your comment.

   Delete
 20. “እኛ «አክራሪ» የሚለውን ቃል በጥንቃቄ ነው የምንመረምረው” የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ
  READ IN PDF
  የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም በአጠቃላይ የማኅበረ ቅዱሳን አገልግሎት አስመልክቶ ከዚህ በፊት ከስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ ጋር ቃለ ምልልስ አድረገው ነበረ:: በዚህ ቃለ ምልልሳቸው አክራሪነትን እና የማኅበሩ የፖለቲካ ተሳትፎ በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ የማኅበሩን አቋም በመንተራስ ምላሽ ሰጥተው ነበረ:: ይህ አስቀድሞ ምላሽ የተሰጠበት አሁን ወቅታዊ ሆኖ ስላገኘነው ከቃለ ምልልሱ ቀንጨብ አድርገን በአክራሪነት እና የፓለቲካ ጉዳይ የሰጡት ቃል እንደሚከተለው አቅርበነዋል:: ሙሉ ቃለ ምልልሱን የወሰድነው ከማኅበረ ቅዱሳን ድረ ገጽ ላይ ነው::

  ስምዐ ጽድቅ፡- ማኅበሩ አክራሪ ነው ስለሚባለውስ?
  ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ፡- እኛ «አክራሪ» የሚለውን ቃል በጥንቃቄ ነው የምንመረምረው:: አክራሪ ማለት የሃይማኖቱን ሕግ አክብሮ የሚኖር ተግቶ የሚጾም፣ የሚጸልይ በሃይማኖቱ ላይ ለሚነሡ ጥያቄዎች መልስ የሚሰጥ፣ ታሪኩን፣ ቤተክርስቲያኑን የሚወድ፣ ለሃይማኖቱ የሚቀና የማይዋሽ ወይም ወደ ከፍተኛ ሥነ ምግባራዊ ሕይወት ራሱንም የሃይማኖት ወገኑን ሁሉ ለማድረስ የሚተጋ ከሆነ የማኅበራችንን አባላት ሊገልጽ ይችላል፡፡ ሰዎች ምናልባት በልማድ በዚህ ብያኔ ለመጥራት ፈልገው ከሆነ ችግር ላይኖረው ይችላል፡፡ ነገር ግን በዚህ ሁኔታ የሚመላለሱትን ክርስቲያኖች «አክራሪ» ተብለው ከሚጠሩ አጥባቂ፣ ዐቃቤ ሃይማኖት ቢባሉ የተሻለ ነው፡፡


  በሌላ በኩል ግን «አክራሪ» የሚለው የሚያሰቃይ፣ የሚገድል፣ የሚያስገድድ፣ የሚሳደብ፣ የሌላውን ሳይነኩ የራሳቸውን አምልኮ እየፈጸሙ ያሉትን የሚረብሸ፣.. ወዘተ ለማለት የተቀመጠ ብያኔ ከሆነ በወንጌል የሚያምኑ፤ አምነውም የሚያስተምሩ ክርስቲያኖች ሊያደርጉት አይችሉም፡፡ ምክንያቱም ከላዩ የተጠቀሱት ተግባራት ከክርስትና ሃይማኖት አስተምህሮ ጋር ተጣጥመው አይሔዱም፡፡ ማኅበራችንም ስብከተ ወጌልን በመላው ሀገሪቱ እና ዓለማት የማስፋፋት ዓላማ ይዞ የሚሠራ በመሆኑ ለፍቅርና ለመከባበር ትልቅ ቦታ አለው፡፡

  ምናልባት በማስጨነቅ ወይም በማስገደድ ሃይማኖታችንን ለማስጣል የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ሲኖሩ ቅሬታችንን መግለጻችንና በሃይማኖታችን ላይ በኅትመት ወይም በኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ አማካኝነት የሚሰጡ አስተያየትና ጥያቄዎች ሲኖሩ መልስና የአጸፋ አስተያየቶችን መስጠታችን በዚህ ደረጃ አስ ፈርጆን ከሆነ ሚዛናዊ ነው የሚል እምነት የለኝም፡፡ እነዚህን የምናደርገው በሃይማኖታችን ላይ ጥያቄ ያነሣውን ወይም አስተያየት የሰጠውን አካል ለመተቸት ወይም ለመሳደብ ተፈልጐ ሳይሆን እነዚህ አካላት ካሠራጯቸው መልእክቶች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናንን ሐሳብ እንዳይበረዝ፣ ሃይማኖታችን መልስና አስተያየት የሌለው መስሎ ለምእመናን እንዳይታሰብ ለመጠበቅ የሚደረጉና ለጠየቁን መልስ እንድንሰጥ በሃይማኖታችንም የታዘዘውን መንፈሳዊ ተግባር ለመፈጸም ነው፡፡

  መከራ የደረሰባቸውና የሚደርስባቸው ክርስቲያኖች ሲኖሩ ቅሬታችንን መግለጻችን ተገቢ ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም ለሀገር ሰላምም የሚበጀው ችግሮች መኖራቸውን ጠቁሞ ሕዝብም መንግሥትም መፍትሔ እየሰጣቸው ሲሔዱ ነው፡፡ ከዚህ ባለፈ ግን ስሜታዊ በሆነ መልክና ከጀርባው ሌላ ዓላማ ያለው እንቅስቃሴን በክርስቲያኖች ስም ማካሔድን በጽኑ የምንቃወመው ነው፡፡ በአንጻሩ ደግሞ ማኅበረ ቅዱሳን ለቤተክርስቲያን ያለውን ተቆርቋሪነት ከግምት አስገብቶ የተለያዩ አካላት በስሜት የሚያካሒዷቸው ግልጽና ሥውር እንቅስቃሴዎችን ሁሉ ማኅበረ ቅዱሳን ሳይሆን አይቀርም የሚሉ አካላት እንደሚኖሩ እናምናለን፡፡ ሌላው ቀርቶ በዓውደ ምሕረት ቆሞ ያለ ሕግና ሥርዓት የሚያስተ ምሩ መምህራንን ሁሉ የማኅበረ ቅዱሳን መምህራን ናቸው የሚሉም እንዳሉ እናውቃለን፡፡ ነገር ግን በጭፍን የሚሰጡ እነዚህን የሚመስሉ አስተያየቶች ተገቢ አይደሉም፡፡ ምክንያቱም እነዚህ አካላት ማኅበሩ ያሰማራቸው መሆን አለመሆኑን ማጣራትም ወይም ሆኖም ከተገኘ ማኅበሩ ባለው አሠራር ርምጃ እንዲወስድ ማሳሰብ የተሻለ መንገድ ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ ዓይነት አቋም ላይ ያለን ማኅበር አክራሪ የሚሉት አካላት ካሉ ያን ለማለት መነሻ ያደረጓቸውን ጭብጦች ማጤን ይኖርባቸዋል እላለሁ፡፡

  ReplyDelete
 21. መለስ፡ቀበጡ፡ወጥ፡ረገጡ፡
  ለይቅርታ፡ይምጡ፡
  ተራ፡ወሬ፡አይምሮዋቸው፡ለይ፡አያስቀምጡ
  በራሳቸው፡ላይ፡ጉድ፡እንዳያመጡ

  ReplyDelete
 22. መቼም የማቅን ማንንነት የምናውቅ እናውቀዋለን ቢሆንም ግን አንድ ኤቲስት የሆነ አምባገነን እድሜውን ለማራዘም ማቅ ላይ ሲነሳ እሰይ አበጀ የምንልበት ጊዜ ላይ አይደለንም። ማቅ ከዜናዊ 100% ሊትዮጵያ አኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ይሻላል። ማስተዋሉን ስጠን እንበል። መለስ ማን ነው ብለን እንጠይቅ? በቤተክርስቲያናችን ላይ በገዳሞቻችን ላይ እኮ መለስ ያነጣጠረው የሚጠላት ኢትዮጵያ ታኢኳ ሁሉ በገዳሞቻችንና በቤተክርስቲያኖቻችን ስላሉ ነው። ስለዚህ የመለስን "የጣር ጩኸት" አናዳምጥ እልቁኑስ ወደመቃብሩ የሚወርድበትን ጉድጓድ መማስ ጀምሮአልና ከዃላው ሆነን ተባብረን እንግፋው አምባገነኖች በጥር ጩኸታቸው ጊዜ ነው ብዙ ጥፋት የሚያጠፉትና ማቅን አስበላን ስንል ገዳሞቻችንን እያጣን ነውና በሕብረት ብንንነሳ መልካም ነው። ዝንጀሮ እኮ መጀመሪያ የመቀመጪያዬን ያለችው እኛም ከመለስና ከማቅ የትኛውን ቀድመን እንድናጠፋ ነው። ስለዚህ ለዚህ ሃይማኖት የለሽ መሪ ትብዬ መጥፊያ ቅድሚያውን ሰጥተን እናጥፋው። ማቅን መለስ እኮ ነ በፓትርያሪኩ ቡራኬ ያቋቋመው እኛን እንዲያዘናጉለት ብርግጥ ከፋፍሎናል አሁን ማቆች በገንዘብም በጣም ስለተደራጁ መለስና ጳውሎስ ፈሩአቸው ነገ መሪዎቻቸውን በአሸባሪነት ፈርጆ ወደ ከርቸሌ እንደሚልካቸው ለማወቅ ነቢይ መሆን አያስፈልገውም ቢሆንም እባካችሁ ተባብረን እህን የሰው ልጅ ደም እንደ ትዃን የጠማውን መለስ ተባብረን እናስወግድ። ስብሃት ለእግዚአብሄር።

  ReplyDelete
 23. ወገኑን በድንጋይ ደብዳቢ፣
  እውር ፈረስ ጋላቢ፣
  ትልቅ ትንሹን ተሳዳቢ፣
  የዳቢሎስ አጃቢ፣
  ማቅ ማጂራት መችው ሰድቦ ለሰዳቢ፣
  ባለ ውቃቢ ነው ድቤ ደብዳቢ።
  ስድ አደግ የእናቱን ቀሚስ ገላቢ፣

  ReplyDelete
  Replies
  1. write you are dear brother.God bless Ethiopia and it's people.

   Delete
 24. ከሳሾች ለእኔ የሚያውቁ የሚመስሉ አያላዋቂዎች ናቸው

  ReplyDelete
 25. ይሄ ነው እንግድህ የመናፍቅ ስራ
  ስለ ማህበረ ቅዱሳን የሚታውቀው አንዳች ነገር የለም ።

  ReplyDelete
 26. አቤት ያንተ ያለህ! ወሀቢያ እና ማቅ ምን ልዩነት አላቸው የቄሣር አንድ ሣንቲም ናቸው ዕኮ፤
  የሰውን ሕይወት ግራ በማጋባትና በማደናገር አንድ ከመሆናቸውም ባሻገር ተራውን ቀርቶ ዋናውን ያልተማረው ይቅርና የተማረውን ሀገር ቤትስ ይሁንና ከተሜውን እያደናበሩ ይገኛሉ፤
  እናም እነዚህኞቹ ዘረዐ ያዕቆብን እነዚያኞቹ ግራኝን ለመመስ ሲጣጣሩ ይታያሉ፤
  ያም ሆነ ይህ ከዝንጀሮ ቆንጆ ምን ይመራርጣሉ፤

  ReplyDelete
  Replies
  1. If you prick us do we not bleed? If you tickle us do we not laugh? If you poison us do we not die? And if you wrong us shall we not revenge?
   If you look into your own heart, and you find nothing wrong there, what is there to worry about? What is there to fear?

   Delete
 27. mk is wehabiya. 100% true

  ReplyDelete
 28. በጣም አሳፋሪ ጽሁፍ ነው በእርግጥ ማቅ ለቤተከርስቲያን መልካም ስራ የተቋቋመ መሆኑን ባምንም አሁን ግን እጅግ የሚያሳዝን ነገር እሰማለሁ ብዙ ስውር ተግባር አስፈጻሚ አካላት ከመንግስትም ይሁን ከሌላ ቡድን መርዝ የሚረጭ ተኩላ ቁልፍ ቦታውን በመያዝ ትክክለኛ አገልጋዮችን በየጊዜው ያወናብዷቸዋል፡፡እናንተ ደግሞ ከጫካ የመጣ አውሬ ስልጣኑ ገነቱ ያደረገ ሰው መግለጫ ሰጠ ስትሉ እርሱ ምንድነው ሰው እኮ ነው መላዕክ ምስክር የሰጣችሁ ይመስል በምክር ቤቱ መግለጫ ሰጠ አታፍሩም፡፡ ደግሞ እናንተ እንደምትፈልጉት አላለም እንጂ የተጠቀመበት ቃል ‹……….የማቅ አባላትን ግልባጭ …..›ነው ያለው ትርጉሙ አማርኛ ከብዷችሁ ከሆነ ሲተረጎም የማቅ ስራ እንሰራለን በማለት በእነሱ ስም የሚንቀሳቀሱ አሉ አለ እንጂ አንተ እንዳልከው አይደለም፡፡ይህን ጽሁፍ አቶ መለስ ቢያዩ ያዝናሉ ያላሉትን መዝለፍ ስለምትፈልግ ብቻ ነው እኔ እግዚአብሔር አንድ ቀን እውነቱን ይገልጻል፡፡ ማንን እንደምናምን ግራ ብንጋባም የፈጣሪ እናት አትለየን!!!

  ReplyDelete